የአሜሪካ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ቲክቶክ እንዲሸጥ የሚያስገድደውን ውሳኔ አጸደቀ
የዜጎችን ግላዊ መረጃዎች ለቻይና መንግስት አሳልፎ ይሰጣል በሚል በአሜሪካ የተከሰሰው ቲክቶክ ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደርጓል።
https://bit.ly/4inEzp2
Must Listen : ማሪያማዊት እግዜር ይስጣት እኛ ለዘመናት የተናገርነውን ነገር በገዛ ሚዲያዋ አረጋግጣልናለች።
ድሮ ፌስቡክ ላይ የአማራና የኦሮሞን ህዝብ ወደግጭት በሚወስድ እኩይ ንግግሩ የምናውቀው የህውሀቱ አክቲቪስት ልፍሀተይ ተስፋ (ብርሀነ) ለዘመናት የጮህንለትን ነገር አረጋግጦልናል።
ብርሀነ ወለጋ ተወልዶ ማደጉንና ኦሮሚኛ ቋንቋ አቀላጥፎ እንደሚናገር ገልፆ ወለጋ ላይ እዛው ያደጉ ብዙ የትግራይ ልጆች መኖራቸውንና የሸኔ ጦርን መቀላቀላቸውን ከዚያም በላይ የሸኔ ጦር ውስጥ የአመራር ቦታ ላይ ያሉ የትግራይ ልጆች መኖራቸውን ገልፆልናል። ይህ እንግዲ ወለጋ አካባቢ ላለፉት ስድስት አመታት ሲሰራ የነበረው ቁማርና ጥፋት ከየት እንደሚመነጭ ለሁላችንም በግልፅ የሚያሳይ ይመስለኛል።
ሴራው ፀሀይ ላይ እየወጣ ነው። በኦሮሚያ በተለይም በወለጋ ንፁሀን ላይ ጥቃት በማድረስ በአማራና በኦሮሞ መሀከል የነበረን የዘመናት ፍቅርና አንድነት ማፍረስ፥ ሁለቱ ትልልቅ ህዝቦች መሀል እሳት መጫር በነብርሀነና መሰሎቹ ለሁለቱ ህዝቦች የተዘጋጀ ወጥመድ ነበር። ይሄ የሚፈፀመው ደግሞ እነብርሀነ እንደነገሩን በሸኔ ውስጥ አስርገው ባስገቧቸው ኦሮሚኛ ተናጋሪ ህውሀቶች ነበር። በኢትዮጵያና በንፁሀን ላይ የቆመሩ ገና ይለፈልፋሉ።
ህዝብ ይንቃ። በነፃ አውጪ ስም የተፈለፈለ ሁሉ ነፃ አውጪ አይደለም። ኦሮሚኛ ያወራ ሁሉ ኦሮሞ አይደለም። በአማርኛ የዘበዘበ ሁሉ አማራ አይደለም። “እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል” እንደሚባል በብዙ ንፁሀን ደም እጁ የጨቀየው ብርሀነ “ቁርጣችሁን እወቁ ሸኔ ማለት እኛ ነን” ብሎናል። እናመሰግናለን ወንድማችን። እኛ ስንናገር አንሰማ ብለውን ነበር። እንዲህ እራሳችሁ ንገሯቸው።
ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር።
"ጽንፈኛው ቡድን በፈረስ ቤት 37 ወገኖችን በግፍ ጨፍጭፏል" አቶ ደሳለኝ ጣሰው
በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ጉዳዮች አስተባባሪ እና የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰው በወቅታዊ የሰላም እና የጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም የክልሉ የሰላም እና የጸጥታ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ተናግረዋል። ማኅበረሰቡ ለሰላም ያለው ግንዛቤ ትልቅ ነው ያሉት ኀላፊው ለሰላም የሚከፍለው ዋጋ ከፍ ያለ መኾኑንም ገልጸዋል።
ከሕግ ማስከበር ጎን ለጎን ለሰላም የሚዘጋ በር የለም በሚል ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎች ሲቀርቡ መቆየታቸውንም አመላክተዋል። መንግሥት በድርድሩ ብቻ ውጤት ይገኛል ብሎ ባይቀመጥም የሰላም አማራጮች ግን አሁንም ዝጎች አይደሉም ነው ያሉት። ማኅበረሰቡ መንግሥት ለሰላም ለሰጠው አማራጭ ድጋፍ ማድረጉንም ተናግረዋል።
ነፍጥ ባነሳ ኃይል ላይ ሕግ ማስከበር ግድ መኾኑንም ገልጸዋል። እስካሁን በተሠራው ሥራ 2 ሺህ 594 ታጣቂዎች ሲያደርጉት የነበረው ድርጊት ተገቢ አለመኾኑን ተረድተው ለሰላም መግባታቸውን ተናግረዋል። በየቀኑ ለሰላም የሚገቡ ታጣቂዎች መኖራቸውንም አስታውቀዋል።
ጽንፈኛው ቡድን በምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ሚካኤል በሚባል ሥፍራ የሕዝብ እና የመንግሥት አገልግሎት የሚሰጡ 97 የኅብረተሰብ ክፍሎችን ከመስከረም 29/2017 ዓ.ም ጀምሮ አሥሮ መቆየቱን ጠቁመዋል። ከቤተሰቦቻቸው ከመቶ ሺህ እስከ 1 ሚሊዮን ብር ድረስ እየተቀበለ ቆይቶ ዛሬ ኅዳር 27/2017 ዓ.ም 37 ወገኖችን በግፍ ጨፍጭፏል ነው ያሉት።
ጽንፈኛው ቡድን የፈጸመው ድርጊት አሳዛኝ እና ዘግናኝ መኾኑንም ተናግረዋል። ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው እንኳን ወገናቸውን ሀገራቸውን ሊደፍር የመጣን ጠላት እንኳን ሲማርኩ ተንከባክበው፣ ድርጊቱ ልክ እንዳልኾነ አስተምረው የሚልኩ ናቸው ያሉት ኀላፊው ጽንፈኛው ቡድን ግን ከኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ስብዕና ባፈነገጠ መልኩ የራሱን ወገኖች በግፍ ይገድላል ነው ያሉት።
ጽንፈኞች የያዛዟቸውን ወገኖች እጅ እና እግራቸውን እያሠሩ ሁለት ወራት ካቆዩ በኋላ በግፍ መግደላቸውን ነው የተናገሩት። የቀሩት ወገኖችንም በግፍ ሊገድሏቸው እንደሚችሉም ገልጸዋል። ከዚህ በፊትም በተናጠል የሚረሽኗቸው ወገኖች በርካቶች መኾናቸውን ተናግረዋል።
ሕዝቡ በጽንፈኞች ምክንያት በራሱ ከተማ፣ ክልል እና ሀገር እንዳያለማ፣ እንዳይነግድ እና እንዳይኖር ኾኗል ነው ያሉት። ሕዝቡን ከግፍ ቀንበር ለማውጣት እየተወሰደው ያለውን እርምጃ ሕዝቡ እንዲደግፍም ጥሪ አቅርበዋል።
በፈረስ ቤት ሚካኤል በጽንፈኛው ቡድን በተፈጸመው አሰቃቂ ግፍ የክልሉ መንግሥት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ይገልጻል ነው ያሉት። የተፈጸመው ድርጊት ከአማራ ሕዝብ ታሪክ ያፈነገጠ እና ነውር መኾኑንም ነው የተናገሩት። መንግሥት ይህን ድርጊት በፈጸመው የጽንፈኛ ቡድን ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመላክተዋል።
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት እና የሀብት አስተዳደር ሥርዓቱን ለማዘመን ከደቡብ አፍሪካ ኩባንያ ጋር ስምምነት ፈጸመ
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና መቀመጫውን ደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ካደረገው ሎህባወር አሶሴት ጋር በዘመናዊ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አስተዳደር እንዲሁም በሀብት አስተዳደር ዙሪያ ዓለምዓቀፋዊ ልምዶችን ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነት ደርሰዋል፡፡
ስምምነቱን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል እና የአማካሪ ድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስተር ሬን ሆርድ ፈርመዋል፡፡
በከፍተኛ ሁኔታ እያደገና እየሰፋ ያለውን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የቤት ግንባታ መርሀ ግብር ዓለምዓቀፋዊ የፕሮጀክትና የሀብት አስተዳደር ልምዶችን በመቀመር ረገድ ስምምነቱ አገራዊ ፋይዳ ይኖረዋልም ተብሏል፡፡
በተጨማሪም በቴክኖሎጂ ፣ እውቀት ሽግግር እና በኮንስትራክሽን እንዲሁም በቤት አስተዳደር ሥራዎች ዘመናዊ የአሰራር ስርዓቶች ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ነው፡፡
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር ኮርፖሬሽኑ በፕሮጀክት አስተዳደር ረገድ በሞዴልት የሚጠቀስ ስርዓት መዘርጋት የቻለ ተቋም እንደሆነ አስታውሰው በአሁኑ ሰዓት የኮርፖሬሽኑ የግንባታ ፕሮጀክቶች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ በመሆኑ የተቋሙን የፕሮጀክትና የሀበት አስተዳደር አቅምን በማሳደግና የአሰራር ሥርዓት በማሻሻል የኮርፖሬሽኑን ትርፋማነትና ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥራ ከወዲሁ መሥራት አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ከሎህባወር አሶሴት ኩባንያ ጋር በመሆን ዓለምዓቀፋዊ ልምዶችን ተግባራዊ ለማድረግ ኮርፖሬሽኑ እንደሚሰራ ክቡር አቶ ረሻድ ተናግረዋል፡፡
የሎህባወር አሶሴት ዋና ሥራ አስፈጻሚ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት በከፍተኛ ለውጥ ላይ ካለው ከፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ ለመስራት እድል በማግኘታቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸው በዘርፉ ለ28 ዓመታት ያዳበሩትን የማማከር አገልግሎት ልምድ ለኮርፖሬሽኑ ለማከፈል እንደሚሰሩም ተናግረዋል፡፡
በስምምነቱ ወቅትም የዓለምቀፉ የሙያ ደህንነትና የጤና ፕሬዜደንት የኢንተርናሽል የሲቪል መሀንዲስ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር ካርል ሀይንስ ተገኝተዋል፡፡
ልዩ መረጃ መቀሌ‼️
ህወሓቶች በጠላቶቻችን ተከበናል (ክባን ዕፅዋን) እያሉ ሲንጫጩ እንዳልነበር ዛሬ እርስበርስ ሲካበቡ ዋሉ! ህወሓት ድሮም ለትግራይ ህዝብ አልቆመም ለስልጣን እና ለዘረፋ እንጂ‼️
ለሁለት የተከፈለው ህወሓት ዛሬ ሁለቱም ከንቲባዎች ( የደብረፂዮኑ ሹመኛና የጌታቸው ሹመኛ ) ቢሮ ሳይገቡ ነው የዋሉት። የመቀሌው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር አንድነት ከፖሊሶች ጋር በመሆን የደብረፂዮኑ ሹመኛ ዶ/ር ረዳኢ ወደ አስተዳደር ፅ/ቤቱ ቢሮ እንዳይገባ ለመከላከልና ለመግባት ከሞከረም በቁጥጥር ስር ለማዋል ፅ/ቤቱን በመክበብ ጥበቃ ሲያደርግ ውሏል።
ታደሰ ወረደ ደግሞ ፅ/ቤቱን የከበቡትን እነ ኮማንደር አንድነትን በወታደሮቹ (የTDF አባላት) አስከብቦ ውሏል !! ይሄንን የተረዱት ከንቲባዎች ዛሬ ቢሮ ባለመግባት ሁለቱም በፎርፌ ነጥብ ጥለዋል
ትናንት የሩሲያ ፕሬዘዳንት ፑቲን በሩሲያ የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ በኢትዮጵያ እየተከሰተ ያለውን የልማት ተአምር እና የሚደነቅ እንቅስቃሴዎች ሲመሰክሩ ነበር።
Читать полностью…ወደ ሰላም አልመጣም ካለ ይደምሰስ!!
በአማራ ክልል ጎጃም እና አካባቢው የሚገኙ 8 የገጠር መንደሮች በየ ቤተክርስቲያን እና ገበሬ ቤት ተደብቆ የነበረው ጽንፈኛ ቡድን ዛሬ አይቀጡ ቅጣት እየተቀጣ ተደምስሶ እግሬ አውጪ በማለት ፈርጧል:: ፅንፈኛዉ ጀግና ተዋጊ ነን የሚሉትና በየሚዲያቸው ፕሮፓጋንዳ የሚሰሩላቸው ሚዲያዎቻቸው እነዴት ንብረቱ እያ ጠበጠበ እግሬ አዉጭኝ እያለ ሲፈረጥጥ ባዩት:: ቪዲዮና ተጨማሪ መረጃዎችን ይዤ እመለሳለሁ::
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነግ ሸኔ) ትጥቃቸውን ለመንግስት በማስረከብ ወደ ታህድሶ ካምፕ መግባት ጀምረዋል። ሁሉም አካላት ለህዝብና ሀገር ሰላም ቅድሚያ ሊሰጡ ይገባል።
ሰላም ለኢትዮጵያና ህዝቦቿ!
የሰላም መንገድ አማራጭ የሌለውና ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ መንገድ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (ኦነግ ሸኔ) ከፍተኛ አመራር በሆኑት ጃል ሰኚ ነጋሳ የተመራ የሠራዊቱ አመራሮች የዓድዋ ድል መታሰቢያን እና ሌሎች የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ከጎበኙ በኋላ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንኳን ወደ ሰላም መንገድ መጣችሁ ብለው ተቀብለዋቸዋል::
በዚሁ ወቅት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ የሰላም መንገድ አማራጭ የሌለው እና ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ መንገድ መሆኑን በመረዳት መንግስት ላደረገው ጥሪ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አባላት የሰጡት ምላሽ የሚያስመሰግን መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ስምምነቱ የፖለቲካ እና የሃሳብ ልዩነቶችን ዘመናዊ በሆነ መንገድ በውይይትና በሰላም መፍታት ለሌሎችም አርአያ የሚሆን ተግባር መሆኑን ገልጸዋል::
የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር ጃል ሰኚ ነጋሳ በበኩላቸው፤ ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው፤ የሰላም ጥሪውን የተቀበሉት የህዝብን ጉዳት ለመቀነስ እና የሰላም አማራጭን መቀበል ብልህነትና አዋቂነት መሆኑን በመረዳታቸው እንደሆነ ተናግረዋል::
በኦሮሚያ ክልል መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች መካከል የሰላም ስምምነት መፈራረሙን ተከትሎ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያን፣ አንድነት ፓርክን እንዲሁም በአዲስ አበባ የተገነቡ ሌሎች ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን የከንቲባ ፅ/ቤት መረጃ ያመለክታል::
የሰላም ወሬ መስማት እንዴት ደስ ያሰኛል‼️
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነግ ሸኔ) አመራሮች የደረሱትን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት ወደ ካምፕ ሲገቡ ውለዋል:: የተቀሩት ታጣቂዎች ነገና ከነገ ወዲያ ሙሉ በሙሉ ካሉበት አካባቢ በመነሳ ወደ ተዘጋጀላቸው ካምፕ ይገባሉ::
Good News : በምዕራብ ሸዋ ጮቢ ወረዳ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አመራር ጃል ሰኚ እና ኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተከትሎ የትጥቅ ትግሉን በመተው በዛሬው እለት ወደ ሰላማዊ ትግል የገቡ ታጣቂዎች።
ሰላም ለሀገራችን❗️
ሰላም ለህዝባችን❗️
"ባለፉት የለውጥ አመታት በሶማሌ ክልል የተረጋገጠው ሰላም እና ልማት የየበኩላችንን በመውሰድ እናስቀጥላለን"፦ በአውሮፓ የሚኖሩ የዲያስፖራው ማህበረሰብ
ባለፉት የለውጥ አመታት በሶማሌ ክልል የተረጋገጠው ሰላም እና ልማት የበኩላችንን ወስደን ለማስቀጠል ቃል እንገባለን ሲሉ ኑሮዋቸውን በአውሮፓ በተለይ በስካንዴኔቭያን ሀገራት ያደረጉ የሶማሌ ክልል ተወላጆችና የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላት ገለፁ።
የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ከአውሮፓ ሀገራት የተውጣጡ የክልሉ ተወላጆች እና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ጋር በስዊድን ስቶኾልም ከተማ ተወያዩ።
በውይይቱም ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል አመስግነው፣ በኢትዮጵያ በተለይ በሶማሌ ክልል የሰፈነው ለውጥ ያስገኛቸው ፍሬዎች እና ድሎል እንዲሁም ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ገለፃ አድርገዋል።
ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ በገለፃቸው፤ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ መሪነት በፖለቲካው ዘርፍ በተደረገው ሪፎርም ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሆና ዜጎች በሀገራቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተረጋግጧል ብለው፣ ለዚህም ላለፉት ስድስት አመታት በሶማሌ ክልል የሰፈነው ሰላም፣ ልማትና የክልሉ ህዝብ በሀገር ጉዳይ ላይ ከተመልካችነት ወደ ውሳኔ ሰጪነት የመጣበት ሁኔታ ማሳያ ነው ብለዋል።
በተለይም ባለፉት ስድስት አመታት በኢትዮጵያ በተፈጠረው ለውጥ አማካኝነት በሶማሌ ክልል የሀይማኖት ነፃነት፣ ሰበዓዊ መብት መጠበቅ፣ ፖለቲካ ምህዳር መስፋትና ማንም በፖለቲካ አመለካከቱ በሀሳቡ እንደማይታሰር እና የህዝቡን ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ መልስ መስጠት መቻሉን ገልጸዋል።
አቶ ሙስጠፋ ባለፉት አመታት እንደ ጤና፣ መንገድ፣ ትምህርት፣ ከተማ ልማት፣ ግብርና፣ የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ ሃይልና የስራ እድል ፈጠራ፣ የኢኮኖሚ ሪፎርም፣ያሉ አንኳር የልማት ሥራዎችን መሰራታቸውን አንስተዋል።
በሶማሌ ክልል የፌዴራል እና የክልሉ መንግሥት ከሰላሙ ባሻገር ለ50 አመታት ያልተሰሩ የልማት ሥራዎች ባለፉት ስድስት አመታት ብቻ መሰራታቸውን ጠቁመው፣ በተለይ በጤናው መስክ ከስድስት አመታት በፊት በክልሉ 9 ሆስፒታሎች ብቻ እንደነበሩና፣ ለውጡ ማግስት 9 አዳዲስ ሆስፒታሎች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ እንሆነና በአሁኑ ወቅትም 15 ሆስፒታሎች በግንባታ ሂደት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።
በሌላ በኩል በክልሉ የመንገድ አውታሮች ማስፋፋት መቻሉንና የፌደራሉ መንግሥት ከ2 ሺህኪ.ሜ በላይ የአስፓልት መንገድ በክልሉ መገንባቱንና ሌሎች በርካታ መነረገዶችም በግንባታ ላይ ናቸው ብለው፣ ከኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ጋር በተያያዘም ባለፉት ስድስት አመታት በክልሉ 80 የሚሆኑ ከተሞች ወረዳዎች እና በቀበሌ ደረጃ ያሉ የ24 ሰዓት ኤሌክትሪክ ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን በውይይት መድረኩ ላይ ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም መንግሥት ለዲያስፖራው ምቹ ሁኔታዎችን ማመቻነቱንና፣ በውጭ ሀገራት የቀሰሙትን እውቀትና ያፈሩትን ሀብት ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ኢንቨስት በማድረግ እራሳቸውንም ሆነ ዜጎችን እንዲጠቅሙ ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ጥሪ አቅርበዋል።
በበኩላቸው በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላት በተወካዮቻቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክት፤ በተደረገላቸው ገለፃ በኢትዮጵያ በተለይ በሶማሌ ክልል ያለውን ሁኔታ ጥሩ ግንዛቤ ማግኘት መቻላቸውን ገልፀው፣ የተረጋገጠው ሰላም እና ልማት ለማስቀጠል የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ዲያስፖራው ሀገር ቤት ከተለያዩ ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት በሚሄዱበት ጊዜ መጉላላት እንዳለ ጠቁመው፣ ይህም እንዲስተካከል ጠይቀዋል።
በመጨረሻም የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ዲያስፖራው ለክልሉ ልማትና ለዜጎች ኑሮ መሻሻል እያደረገ ያለውን የተያየ ድጋፍና እገዛ አመስግነው፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የተነሱት ጥያቄዎች እንደሚታረሙ ተናግረዋል።
በመድረኩ ላይ በስካንዲናቪያን ሀገራት ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ምህረተአብ ሙሉጌታን ጨምሮ የሶማሌ ክልል አመራሮች እንዲሁም የስቶኾልም ከተማ ምክትል ከንቲባ ተገኝተዋል።
🔶️ ውሳኔዎን የሚያደንቁበት ትርፋማ ኢንቨስትመንት ከአሚባራ ፕሮፐርቲ ! 🔶️
➣ ለ50 ቤቶች ብቻ የተዘጋጀ
ታላቅ ቅናሽ!
➣ ሸራተን ሆቴል አጠገብ
ወዳጅነት ፓርክ ፊትለፊት
ቅንጡ አፓርትመንቶች
ከ852,000 ብር ቅድመ ክፍያ
ጀምሮ
➣ ሁለት የመዋኛ ገንዳ,
የልጆች የእግር ኳስ ሜዳ,
የቅርጫት ኳስ ሜዳ
እንዲሁም የቤት ውስጥ
የበረዶ መንሸራተቻ
➣ ከባለ አንድ እስከ ባለ አራት
የመኝታ ቤት አማራጮች
➣ በ10% ቅድመ ክፍያ
በኢትዮጵያ ብር የሚዋዋሉት
➣ እስከ 25% የሚደርስ
ታላቅ ቅናሽ
ለበለጠ መረጃ
በ 0979804444
በቀጥታ ወይንም በዋትሳፕ
ይደውሉ
አሚባራ ፕሮፐርቲ
ለዘመናዊ ኑሮ ታስቦ የተገነባ
ደጋዳሞት ወረዳ የደረሰው ክስተት እጅግ ልብ የሚሰብር ቢሆንም የጽንፈኛውን የሽንፈት መጨረሻ የሚያሳይ ነው።
ከመከላክያ ጋር መዋጋት ያቃተው ጽንፈኛው ድቡድን ደጋዳሞት የረሸናቸው ቁጥር 34 ደርሷል። ከእነዚህ መካከል (ከወረዳ አመራሮች በተጨማሪ ፣ የፖሊስ እና የሚሊሻ አመራርና አባላት እንዲሁም የዕድር ሃላፊዎችና የመንግስት ሰራተኞች ይገኙበታል
ልዩ መረጃ‼️
የነ ደብረፅዮን ቡድን ያቀረቡትን ፥የፕሬዝዳንትነት እጩ ፕሮፖዛል ውድቅ ሆነ‼️
የነ ደብረፅዮን ቡድን ይዘውት ያቀረቡትን ፥የፕሬዝዳንትነት እጩ ፕሮፖዛል ዛሬም በፌደራል መንግስት ውድቅ መደረጉ ታውቋል።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት የመሾም ወይም የፕሬዝደንትነት ፕሮፖዛል የማቅረብ ስልጣን ህወሓት እንደሌለው እንደተነገራቸው ታውቋል።
ለሁለት የተከፈለው የህወሓት አመራሮች አቶ ጌታቸው ረዳና ቡድናቸው ዶር ደብረጺዮንና ቡድናቸው አዲስ አበባ ናቸው::
በአዲስ አበባ የሁለት ቀን ቆይታቸው እስካሁን ከየትኛው የፌደራል መንግስት አመራሮች ጋር እንደተግናኙ የታወቀ ነገር የለም::
የመቀሌው ከንቲባ ቢሮ ለተሾሙት ሁለቱም ከንቲባዎች ወደ ቢሮ እንዳይገቡ በመቀሌ ፖሊስና በ TDF ሃሎች የከንቲባው ቢሮ ዝግ ተደርጏል::
በደብረጺዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን በመቀሌ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ
ህወሃት ህዳር 29 የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ጥያቄ አቀረበ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ_ህወሃት በመጪው ህዳር 29 በመቀሌ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ይፈቀድልኝ ሲል ደብዳቤ ጻፈ።
ለመቀሌ ከተማ አስተዳደር በተጻፈው ደብዳቤ እንደተገለጸው፤ ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም፤ በትጥቅ የተደገፈ የአስተዳደር ፈረሳ በመከናወኑ ይህን ለመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ እናደርጋለን ብሏል።
ለዘመናት መስዋዕት ከፍለን የመሰረትናቸው ምክር ቤቶች በግለሰቦች ሲፈርሱ አንታገስም በሚል ምክንያት፤ ከህዝባችንና አባላቶቻችን በተደጋጋሚ ጥሪ እየቀረበልን በመሆኑ ህዳር 29 በመቀሌ ከተማ ሰልፍ ለማድረግ አቅደናል ብሏል።
ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ 6:30 ሰልፉን ለማድረግ ተዘጋጅተናል ያለው ፓርቲው፤ የጸጥታ ኃይል ጥምር ኮሚቴ እንዲፈቅድልንና ከለላ እንዲያደርግልን እንጠይቃለንን ሲል በመቀሌ የህወሃት ጽህፈት ቤት በደብዳቤ ጠይቋል።
በመቀሌ ከተማ ምክር ቤት አማካኝነት የተመረጠውን አስተዳደር፤ በጌታቸው ረዳ የሚመራው ቡድን በኃይል አፍርሶታል ሲል፤ ደብረጺዮን ገብረሚካኤል(ዶ/ር) የሚመራው የህወሃት ክንፍ ከሰሞኑ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።
የኦነግ/ሸሼ መሪ ጃአል ሳኒ ናጋሳአን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በሸገር ከተማ ያለውን የልማት እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።
ከሰሞኑ የሰላም ስምምነት በኋላ በሸገር ከተማ ፉሪ ወረዳ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ፣ፍርድ ቤትን እና የእንስሳት ሀብት ልማት ክላስተርን ጎብኝተዋል።
የአቶ ጌታቸው ረዳን የፕሬዚዳንትነት ውክልና አንስቻለሁ’’ በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት
በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ትላንት ምሽት ባወጣዉ መግለጫ ለአቶ ጌታቸው ረዳ ሰጥቷቸው የነበረውን የፕሬዚዳንትነት ውክልና ማንሳቱን ገልጿል፡፡ በመሆኑም በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት እንዴት እና በማን እንደሚተኩ ከፌደራል መንግስት ጋር እየተወያየበት እንደሚገኝ አስታዉቋል።
ለፅንፈኛው ቡድን ሊደርስ የነበረ 12,300 የሽጉጥ ጥይት በባህርዳር ከተማ ተያዘ።
መነሻውን ምዕራብ ጎንደር ቋራ መዳረሻውን ባህርዳር ከተማ በማድረግ ሲጓጓዝ የተያዘው 12,300 የሽጉጥ ጥይት በፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ክትትል ሲደረግበት ቆይቶ ከማሽላ ጋር በማመሳሰል ተጭኖ ለፅንፈኛው ቡድን ሳይደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉን በኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ የክፍለጦር ምክትል አዛዡ ሌተናል ኮሎኔል አየልኝ አስናቀ ተናግረዋል።
ህገ ወጥ ጥይቱን ለፅንፈኛው ቡድን ለማድረስ ሲሉ በቁጥጥር ስር የዋሉት ጥላሁን ገነቱና ስማቸው ወንድ ይፍራው የተባሉ ግለሰቦች በባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ ጥይቱን ጭነው ለፅንፈኛው ቡድን ለማድረስ ሲሉ በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ11 በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን ነው ሌተናል ኮሎኔል አየልኝ አስናቀ የገለፁት።
የባህርዳር ከተማን ሠላምና ፀጥታ ለማወክ የሚንቀሳቀሱ የፅንፈኛው ኃይሎችን የማደንና በቁጥጥር ስር የማዋል ተግባሩ ተጠናክሮ ቀጥሏል ያሉት የክፍለጦር ምክትል አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል አየልኝ አስናቀ የፅንፈኛው ቡድን በአሁኑ ወቅት በተለያዩ አቅጣጫዎች እጅ በመስጠት ላይም ይገኛል ብለዋል።
ህብረተሰቡ ሠላም እንዲሰፍን በቁርጠኝነት አየሰራ ይገኛል ያሉት ሌተናል ኮሎኔል አየልኝ አስናቀ የፅንፈኛውን ቡድን ርዝራዦች ለማደን በሚደረገው ዘመቻ ጥቆማና መረጃ በመስጠት እያደረገ ያለውን ትብብር የበለጠ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል። ዘገባው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ነው።
ሰበር መረጃ ጎጃም‼️
በጎጃምና አካባቢው በርካታ የገጠር መንደሮችን የመከላክያ ሰራዊት ጽንፈኛውን እየደመሰሰ እያስለቀቀ ነው በተለይ ጭንባ ጎልጎሉማ ኢሎማ ሙጋር ነጭ ድንጊያ የመሣሠሉትን የገጠር መንደሮች በአሰሳ እያስለቀቀ መሆኑም ከስፍራው የደረሰኝ መረጃ ያመልክታል::
ዘመነ ካሴና ቡድኑ ሁለት ምርጫ አላቸው:: 1 እጅ መስጠት 2 ወደ ሰላም መምጣት:: አለዚያ ለወሬ ነጋሪ እንዳይሆኑ ሆኖ ሙሉ በሙሉ መደምሰስ! በታሪክ ዘመነ ካሴ እጄን አልሰጥም ብሎ እራሱን እንደማያጠፋ 100% እርግጠኛ ነኝ ወኔ የለውም:: ምናልባት አስረስ ዳምጤና ለግዜው ሙሉ ስማቸውን የረሳሁት የቀድሞ ግ7 አባሎች እጅ ከመስጠት እራሳቸውን ሊያጠፉ ይችላሉ ብዬ እገምታለሁ እንጂ ዘመነ (ዘመነች) በምን ወኔና ድፍረቷ እላይዋ ላይ ቃታ ትስባለች? በፍጹም እንተዋወቃለን እኮ ከኤርትራ በርሃ እስከ አማራ ክልል!
በምዕራብ ሸዋ ዞን የሰላም አማራጭ የተቀበሉ የሸኔ አመራርና ታጣቂዎች ወደ ሠላም ተመልሰዋል።
በምዕራብ ሸዋ ዞን ጅባት ወረዳ ፅናት ክፍለ ጦር በሠራዊቱ አመራሮችና ኦነግ ሸኔ ታጣቂ መካከል ውይይት የተካሄደ ሲሆን የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ የቀረበላቸውን የሰላም አማራጭ ተቀብለው ወደ ሠላም መመለሳቸውን በማዕከላዊ ዕዝ የፅናት ክፍለ ጦር አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል አማረ ሰጥአርገው ገልፀዋል።
ለሀገር የሚጠቅመውን ለህዝቡ የሚበጀውን አማራጭ በሰውኛ አስተሳሰብ በመመልከት እስካሁን የነበረው ችግር ሊቆም እንደሚገባ በውይይቱ ላይ መነሳቱን አዛዡ ተናግረዋል።
ከቡድኑ አመራሮች መካከል የጊዱ ገሌሳ አመራር ከቤ ጋድሳ በጫካ ስሙ (ኢራንጎሬ) በስሩ ከሚገኙ አመራሮች እና አባላት ጋር በመሆን መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ በመቀበል በርካታ ታጣቂዎች ወደ ህብረተሰቡ መቀላቀላቸውን የገለፁት ሌተናል ኮሎኔል አማረ ሰጥአርገው በቀጠናው አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን የተደረገው ጥረት ውጤታማ ነበር ብለዋል።
ውይይቱ የክፍለ ጦሩ የሠራዊት አመራሮች የወረዳ የስራ ሀላፊዎች የሀይማኖት አባቶች እና አባ ገዳዎች የተሳተፉበት ሲሆን በአካባቢው ባህልና ወግ መሰረት እርቀ ሰላም አውርደዋል።
ነፍጥ ማንሳት በቃኝ:: በጦርነት የሚመጣ ለውጥ የለም ያለው የጃል ሰኚ የሚመራው ጦር ከሰዓታት በፊት በአምቦ በኩል መሳሪያውን እያስቀመጠ እየገባ ነው::
ሰላም ለሃገራችን
ሰላም ለህዝባችን
አንድ ወስላታ በሚዲያ ቀርቦ እኔን “የቀድሞው ፕሬዚዳንት” እያለ ሲጠራኝ ነበር አሉ።እሱ ችግር የለውም።ፖሊስ ጋ ቀርቦ መልስ ይሰጥበታል።የእነዚህ ሰዎች ችግር ስራ አለመስራታቸው ብቻ አይደለም።ከበፊት ጀምሮ የወንጀልና የሌብነት ኔትወርካቸው እንደሚጋለጥና እንደሚጠይቁ ስለሚያውቁ የትግራይ ፖለቲካ እንዲስተካከል አለመፈለጋቸው ነው።በዘረፋ የተሰማሩባቸው የወርቅና የመዳብ ማዕድናቱ ከእጃቸው እንዲወጣ አይፈልጉም።የትግራይ ፖለቲካ ተበላሽቶ የቀረው በነዚህ ሰዎች ምክንያት ነው
ጌታቸው ረዳ
በቡሄ ግዜ የደነቆረው ስታሊን
ስታሊን ገብረስላሴ "ጃል ሰኚ የወቦን ትግል ከዳ" ብሎ በሀዘን ስሜት የፃፈውን አየሁትና አሳቀኝ። የኦሮሞ ልጆች "መገዳደል ይብቃ" ብለው እርቀሰላም ስለፈፀሙ የአንደኛው የህውሀት ክንፍ ደጋፊዎች ድንኳን ጥለው ለቅሶ ሲቀመጡ እንደማየት የሚገርም ነገር ነው 😁
የነ ስታሊን ካምፕ ህውሀት ፕሪቶሪያ ላይ እርቅ ስትፈራረም አጨብጭበው ሰላም ከሰፈነ በኋላ፥ አማራና ኦሮሚያ ክልል ግን በጦርነት ውስጥ እንዲከርሙ ሲቀሰቅሱ ይውላሉ። ምክኒያቱም ለትግራይ ማህበራዊ እረፍት የሰጠ የሰላም አየር በኦሮሚያና በአማራ ክልል ውስጥ እንዲነፍስ አይፈልጉም። በዚህ ሰአት እንደዚህ አይነት ተራ ብልጣብልጥነት የማይገባው ኢትዮጵያዊ አለመኖሩን የተረዱት አይመስሉም።
"በቡሄ ግዜ የደነቆረ ሁልጊዜ ሆሆሆ ይላል" አሉ። ወንድሜ በድሮ በሬ ያረሰ የለም። እራስህ በጀመርከው ቁማር ጆከር ተጥሎብህ ከተሸነፍክ በኋላ "እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል" እንዳለችው አህያ በሰገሌ ግዜ የቀረ ተንኮል አራምዳለሁ ካልክ የአዲሱ ትውልድ መሳለቂያ ትሆናለህ እንጂ የምታገኘው አንዳች የፖለቲካ ትርፍ የለም።
ቢያንስ ግዜውም ትውልዱም መለወጡትን አይተህ እውቀትህን ባታሳድግና ከትናንት ስህተትህ መማር ባትችል እንኳን የተሻለ ተንኮል ይዘህ ገበያ እንዳጣ ግሮሰሪ የቀዘቀዘ ዩቲዩብህን ብትሸቅል የሚል ወንድማዊ ምክር አለኝ። move on my brother.