በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7 Facebook.com/natnaelmekonnen.et Instagram.com/natnaelmekonnen21
ዛሬን ጨምሮ ለ5 ቀናት ብቻ የሚቆየው የኦቪድ የ6 ሺህ 124 ቤቶች ሽያጭ በአድዋ ዜሮዜሮ ሙዚየም እየተከናወነ ነው
ቀድመው ለሚገዙ 1000 ሰዎች ከ 415 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ የቤት ባለቤት ይሆናሉም ተብሏል፡፡ በርካታ የቤት ገዥዎችም በአድዋ ሙዚየም እየተካሄደ ባለዉ ታላቅ የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ላይ ተገኝተው ምዝገባ እያከናወኑ መሆኑ ታወቋል። ግንባታን በአጭር ጊዜ እና በጥራት በመገንባት ከፍተኛ ስምና ዝና ያተረፈው ኦቪድ ግሩፕ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ኦቪድ ገላን ጉራ የተሰኘ መለሰተኛ ከተማን በሦስት ዓመታት ዉስጥ ገንብቶ ለማጠናቀቅ በቅርቡ ግንባታ አስጀምሯል፡፡
ኦቪድ በ18 ወራት ግዙፍ የመኖሪያ መንደር፣ በ69 ቀናት 11 ወለል ሕንጻ እንዲሁም በ8 ወራት ግዙፍ የገበያ ማዕከል ገንብቶ ማጠናቀቅ የቻለ ተቋም ነው፡፡ በኦቪድ ግሩፕ ቦሌ ቡልቡላ አከባቢ በሚገነባው የኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ መለስተኛ ከተማ ውስጥ 6 ሺ124 ቤቶችን ለአንድ ሳምንት ብቻ የሚቆይ በታላቅ ቅናሽ የሽያጭ አውደርይ ነው ዛሬ ያስጀመረው ። የኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ ከቦሌ አየርመንገድ በ8 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ግንባታው ተጀምሯል፡፡
ከሚያዝያ 16 – 20/2016 ዓ.ም ለ 5 ቀናት ብቻ በአድዋ ሙዚየም ብቻ የሚቆው ይህ አውደርይ ለመግዛት ተገኝቶ ቀድሞ መመዝገብ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።
የመመዝገቢያ ሊንክ: https://bit.ly/ovid2024
ለበለጠ መረጃ በ 9727 ይደውሉ!
ኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ የነገ መኖርያዎ!!!
የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ይሄንን ነባር ልማድ ቀይሮታል። ጦርነትን በፖለቲካዊ መፍትሔ የመቋጨት ባህል አምጥቷል። ይሄ የሰላም ስምምነት ለትውልድ የአሸናፊ ተሸናፊ ትርክትን ከቂም ጋር ላለማውረስ የተደረገ በሳልና ቆራጥ ውሳኔ ነው። ይሄንን አማራጭ ተከትለን፣ ደም መፋሰስ እና ግጭትን ማቆም ችለናል። በአማራ፣ በአፋርና በትግራይ ክልሎች የመልሶ ግንባታ እና የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች ተጀምረዋል። ሰብአዊ ድጋፍም ያለመሰናከል ወደ ትግራይ መድረስ የሚችልበትን ዐውድ ፈጥረናል። የሰላም ስምምነቱ በተፈረመ ማግሥት መንግሥት በሰላም ስምምነቱ ከገባው ግዴታ ያለፈ፣ መተማመን ለመፍጠር እና ሰላምን ለማጽናት አስፈላጊ ናቸው ያላቸውን ርምጃዎች በተከታታይ ወስዷል። በሰላም ስምምነቱ እስካሁን የተገኘው ውጤት እና እፎይታ እንደተጠበቀ ሆኖ ቀሪ ሥራዎችም አሉ። በተለይ በስምምነቱ መሠረት የሕወሐት ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው። የማንነት እና የአስተዳደር ወሰን ጥያቄ ያለባቸውን አካባቢዎች ጉዳይ እልባት ለመስጠት እንዲቻል የተቀመጠው አቅጣጫ ተግባራዊ መደረግ አለበት። በጦርነቱ የተፈናቀሉትን ለመመለስና ለማቋቋም የተጀመረው ሥራ እልባት ማግኘት አለበት። ካለፈ ስሕተተ አለመማር የመጀመሪያውን ስሕተት ከመሥራት የባሰ ነው። ካለፈው ስሕተታቸው ሳይማሩ ዛሬም ተመሳሳይ ችግር ለመፍጠር የሚከጅሉትን ሁላችንም ተባብረን አደብ ማስገዛት ይኖርብናል። ከትዕግሥት በኋላ የሚከሠት ሕግ የማስከበር ሥራ የሚኖረውን አስከፊ ውጤት ከቅርቡ ታሪካችን ልንማር ይገባልና።
መንግሥት የተቋረጡ መሠረት ልማቶችን እና አገልግሎቶችን ለመጠገን እና መልሶ ለማስጀመር ወገቡን አሥሮ እየሠራ ነው። የፋይናንስ እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን በትግራይ ክልል ለማሣለጥ እጅግ ከፍተኛ ወጪ አውጥቷል። የሰላም የትርፍ ድርሻው ታላቅ በመሆኑ መንግሥት ከሚጠበቅበትም አልፎ ቁስልን ለመሻር የሚያስችል ሥራ እየሠራ ነው። ይሄ ግን መንግሥታዊ ኃላፊነት እንጂ ፍርሃት ተደርጎ መወሰድ የለበትም።
በፕሪቶሪያ ስምምነት እንደተገለጸው፣ በሕገ መንግሥታችንም እንደተደነገገው፣ እንደ ሀገር የሚኖረን አንድ የመከላከያ ሠራዊት ብቻ ነው። ክልሎች በክልል ደረጃ ሕግ ለማስከበር ከሚያስፈልጋቸው ፖሊስ እና ሚሊሺያ ያለፈ የታጠቀ እና የተደራጀ ሠራዊት ሊኖራቸው አይችልም፤ አይገባምም። በዚህ መሠረት ትጥቅ መፍታት እና ተያያዥ ሂደቶች በተሐድሶ ኮሚሽኑ ዕቅድ መሠረት በፍጥነት ሊተገበሩ ይገባል።
ወንድሞቻችን/እኅቶቻችን በተለይም ወጣቶች በተለያዩ ምክንያቶች ተገፋፍተው በጽንፈኞች እና በግጭት ጠማቂዎች ወደ ጦር ዐውድማ የሚማገዱበት አጋጣሚ አለ። መንግሥት ይሄንን ሁኔታ ከአንድ አቅጣጫ ብቻ አያየውም። እንቅስቃሴያቸው ሕገ ወጥ ስለሆነ ብቻ ጉዳዩን በጉልበት ብቻ ይፈታ ማለት እንደሌለበት ይገነዘባል። ስለዚህ ከጥፋት መንገድ ለመመለስ እና ማኅበረሰቡን ተቀላቅለው ሰላማዊ ሕይወት ለመኖር ፍላጎት ያላቸውን ታጣቂዎች ሁሉ፣ በተዘረጋ እጅ ለመቀበል መንግሥት ፈቃደኛ ነው። ይሄንን ፈቃደኝነቱን እና ፍላጎቱን በተግባር በተለያዩ ክልሎች አሳይቷል። በቤነሻንጉል ጉሙዝ፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች በዐሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጥተዋል። እነዚህም የተሐድሶ ሥልጠና ወስደው፣ ከማኅበረሰቡ ጋር እንዲቀላቀሉ ተደርጓል። ይሄንንም በተሐድሶ ኮሚሽን በኩል ከክልሎች ጋር በመቀናጀት አጠናክረን እንቀጥላለን። ጥረቱን የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች እንዲደግፉ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪ እናደርጋለን።
እነዚህን ዘላቂ መፍትሔ አምጪ ሥራዎች በአንድ በኩል እያከናወንን የሕዝቡን ሰላምና ደኅንነት የሚያስከብሩ አሁናዊ ተግባራትንም ማከናወናችንን እንቀጥላለን። ጽንፈኛ የፖለቲካ አመለካከቶች እንዲሁም የተደራጁ የወንጀል እና የዘረፋ ፍላጎቶች በአንዳንድ አካባቢዎች እየታዩ ናቸው። እነዚህን በገጠርም ሆነ በከተማ የሕዝብን ሰላም የሚያውኩ እንቅስቃሴዎች ለመቆጣጠር መንግሥት ሰፊ ሥራ እየሠራ ነው። የዚህ ሥራ አንዱ አካል፣ የሕግ አስከባሪ ተቋማትን እያሻሻሉ ፤ ቅንጅታቸውን እና ከሕዝብ ጋር ያላቸውን ትሥሥር እያጠናከሩ እንዲሄዱ ማድረግ ነው። በገጠር ቀበሌዎች እና መንደሮች፣ የየአካባቢው ነዋሪ በአግባቡ ሠልጥኖ አካባቢያዊ ሰላሙን ለማስከበር እንዲችል ይደረጋል። በዚህ ረገድ በአንዳንድ ክልሎች በጎ ጅምር አለ። እንደ ኢትዮጵያ ላለ እጅግ ሰፊ እና ብዙ ሕዝብ ላለበት ሀገር፣ የአካባቢ ሚሊሽያ እና ሌሎች አጋዥ ሰላም አስከባሪ አደረጃጀቶች አካባቢያዊ ሰላም እና ጸጥታን ለማስከበር ትልቅ ሚና አላቸው።
ከዚያ በተጨማሪ፣ የክልል ፖሊስ ኃይሎችን መልሶ በማደራጀት እና በሁለንተናዊ መልኩ በማጠናከር፣ ሕገ መንግሥታዊ ተልዕኳችውን በአግባቡ እንዲወጡ እየተደረገ ነው። በየአካባቢው ካሉት ሚሊሺያዎች እና የክልል ፖሊሶች ጋር በመቀናጀት፣ የፌደራል ፖሊስ የሀገር ውስጥ ሰላም እና ሕግ የማስከበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ ቀጣይነት ያለው ተቋም ግንባታ እና ማሻሻያ እየተካሄደ ነው። ከእነዚህ ሕግ አስከባሪ ተቋማት ያለፈ ሥጋት ካጋጠመ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰላም የማስጠበቅ እና ሕግ የማስከበር ተግባሩን እየተወጣ ይገኛል።
ይሄንን ዓይነት የጸጥታ አካላትና የሕዝብ ቅንጅት በመኖሩ፣ በአማራ ክልል የክልሉን መንግሥት አፍርሶ በኃይል ሥልጣን ለመያዝ ያሰበው ኃይል ፍላጎቱን ለማሳካት እንዳይችል ተደርጓል። በተሠራው የሕግ ማስከበር ሥራ፣ የክልሉን መንግሥት እና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመታደግ ተችሏል። በኦሮሚያ ክልልም በአንዳንድ የክልሉ ዞኖች የነበረው የታጣቂ ኃይሎች ሰፊ እንቅስቃሴ እና አንዳንድ ወረዳዎችን የመቆጣጠር አዝማሚያ ተቀልብሷል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልም የጸጥታና የደኅንነት ሁኔታው በእጅጉ ተሻሽሏል። በአዲስ አበባ እና በሌሎችም የሀገሪቱ ትላልቅ ከተማዎች የተለያዩ የሽብር ጥቃቶችን ለመፈጸም አቅደው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን ዕቅድ ለማክሸፍም ተችሏል።
የተሠራው ሥራ ወሳኝ ቢሆንም በቂ ግን አይደለም። ፖለቲካ ቅብ የሆኑ የተደራጁ የዝርፊያ እና የወንጀል ቡድኖችን በሚገባ መቆጣጠር ይገባናል። ይሄንን ለማድረግም ጠንካራ እና ውጤታማ ሕግ አስከባሪ እና የጸጥታ መዋቅር እንዲኖረን የተጀመረው ሥራ ይቀጥላል። በዚህ ረገድ የሕዝብ ተሳትፎ እና እገዛ ወሳኝ ነው። እየዘረፈ፣ እየነጠቀ እና እያገተ ያለን ቡድን በተለያየ ሰበብ መሸከም እና ማባባል ማብቃት አለበት። በድኻ ገንዘብ የተሠሩ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማትን የሚያወድም ቡድን የማንንም ፍላጎት አያስከብርም። ሕዝቡ ከሕግ አስከባሪ አካላት ጋር በመተባበር የሕግ የበላይነትን ማስከበር ይገባዋል። በየአካባቢው የሚገኙ የፖለቲካ እና የአስተዳደር መዋቅሮችም፣ ሌላ አካል መጠበቅ ሳይሆን፣ ሕግን ማስከበር ቀዳሚ ኃላፊነታቸው እንደሆነ ተገንዝበው ሊንቀሳቀሱ ይገባል።
"የሚሊሻ አባላትን ትጥቅ ማስፈታት" አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገፆች እየተላለፈ ያለው መልዕክት ሀሰተኛ ነው" :- የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት አወጣ ተብሎ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲተላለፍ የነበረው "የሚሊሻ አባላትን ትጥቅ ማስፈታት" የተመለከተ ደብዳቤ በሐሰት የተቀናበረ መሆኑን የአማራ ክልል አስታውቋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ደሳለኝ ከኢቢሲ ሳይበር ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ተጻፈ የተባለው ደብዳቤ ከመስሪያ ቤታቸው የወጣ አለመሆኑን እና የተቀነባበረ መሆኑን ገልጸዋል።
ክልሉ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የሚሊሻ ኃይሉን የማጠናከር ስራን እየሰራ ይገኛል ያሉት ሃላፊው፤ የርዕሰ መስተዳድሩን ጽ/ቤት የደብዳቤው ይዘትም ሆነ ቅርጽ ሀሰተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።
የጎጃም ኮማንድፖስት መረጃ ባደረገው ክትትል ለጽንፈኛው ሊደርስ የነበረ 2 ሺ 500 ጥይት በቁጥጥር ስር አውሏል ።
ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 13 በተደረገው ክትትል 2 ሺ 500 የኤ ኬ ኤም ጥይት በቁጥጥር ስር ሲውል ከዚህ በተጨማሪ ዘጠኝ ካዝና ፣ የመሳሪያ መጠገኛ እና ሌሎች መሰል ቁሳቁሶች ለጽንፈኛው ሲጓጓዙ በቁጥጥር ስር ውለዋል ።
የጎጃም ኮማንድፖስት መረጃ ከዚህ ቀደምም የሕብረተሰቡን ሰላም ለማናጋት ሲጓጓዙ የነበሩ 5 ሺ ጥይት ፣ 32 ቦምብ እና ሌሎች ለሽብር ስራ የሚውሉ ቁሳቁሶች ለጽንፈኛው ከመድረሳቸው በፊት የማክሸፍ ግዳጆችን ሲወጣ ቆይቷል ።
ጽንፈኛው በከተማ የሽብር ስራዎችን ለመፈጸም ቦምቦችን እና ጥይቶችን ከያለበት እያፈላለገ እንደሚገኝ ስለታወቀ ይህንን የሚያመክን የክትትል እና የአሰሳ ግዳጆች ወደፊትም አጠናክሮ በመቀጠል የሕዝብ ደህንነት የመጠበቅ ተልዕኮው ይቀጥላል ።
ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች
ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተእ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።
ሚለየን ምንድነው?
የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ
🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።
🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።
🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።
🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።
🪄We Care
አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ
📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69
www.elegas.com.tr
Email:- ethiopia@elegas.com.tr
ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል:: ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት
አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
Tel: 0913858561
የኮሪደር ልማት ተነሺዎች እውነታ!
ይኖር የነበረበትን የሚያውቅ እንዲህ አምላኩን ያመሰግናል::
እንግሊዝ በሀገሯ የሚገኙ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለማዘዋወር የነደፈችው ረቂቅ ሕግ ፀደቀ
*************
እንግሊዝ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለማዘዋወር የነደፈችው እና ከፍ ያለ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የታመነው ረቂቅ ሕግ በሃገሪቱ ፓርላማ መጽደቁ ተሰምቷል።
ለሁለት ዓመታት ክርክር ሲደረግበት የቆየው ይህ ውሳኔ በእንግሊዝ ጠቅላይ ሚስቴር ሪሺ ሱናክ እና በሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ መካከል የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ የተደረሰ መሆኑ መዘገቡ ይታወሳል፡፡
ውሳኔው የተወሰኑ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ከእንግሊዝ ወደ ሩዋንዳ የሚያዘዋውር ሲሆን ስደተኞቹም የጥገኝነት ጥያቄያቸው እስከሚጠናቀቅ ድረስ በሩዋንዳ እንደሚቆዩ ነው የተጠቀሰው።
ለሚቀጥሉት 664 ቀናት ስደተኞችን የያዙ አውሮፕላኖች ወደ ሩዋንዳ መብረር እንደሚጀምሩ የተገለፀ ሲሆን፤ በእቅዱ መሰረት 52 ሺህ የሚደርሱ ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ሩዋንዳ እንደሚዘዋወሩ ተጠቅሷል፡፡
"የሩዋንዳ ዕቅድ" የሚል ቅጽል ስም የተሰጠው ይህ ረቂቅ ህግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ ከእንግሊዝ ፓርላማ አባላት እና ከሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተቃውሞ ቢገጥመውም፤ የሃገሪቱ ፓርላማ እቅዱን ማፅደቁን ተከትሎ ህግ ሆኖ ሊወጣ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
የዕቅዱ ተቃዋሚዎች ስደተኞቹን በኃይል ከአገር የማስወጣቱን ውጥን ማገድ የሚችል አዲስ የሕግ መቋቋሚያ ለማበጀት የሚያደረጉትን ጥረት አሁንም እንደሚቀጥሉ መግለጻቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው።
#Humanity ❤️
ይህ የሆነው በአሜሪካ ሀገር ሚኒሶታ ነው።
በሚኒሶታ በሚገኝ #ፈጣን_መንገድ ላይ አንድ አሽከርካሪ መንገድ ስቶ ወጥቶ ከመብራት ፖል ጋር ተጋጭቶ እዛው መኪና ውስጥ እያለ መኪናው በከፍተኛ እሳት መያያዝና መንደድ ይጀምራል።
በመንገዱ ሲጓዙ የነበሩ አሽከርካሪዎች ይህን አይተው አላለፉም።
መኪናቸውን አቁመው ከሚነደው መኪና ውስጥ አሽከርካሪውን ለማውጣትና ለማዳን ርብርብ ጀመሩ።
ከእሳት ነበልባል ጋር #እየታገሉ ፤ በሹፌሩ በር በኩል ያለውን መስታወት ሰብረው ከብዙ እልህ አስጨራሽ ትግል በኃላ አሽከርካሪውን በእሳት ተያይዞ ከሚነደው መኪና ውስጥ በህይወት አወጡት።
በኃላም ወደ ሆስፒታል እንዲወሰድ አደረጉ።
አሽከርካሪው ላይ ምንም አይነት የከፋ ጉዳት አልደረሰበትም ተብሏል።
ከከፍተኛ እሳት ጋር ተጋፍጠው የሰው ህይወት ለማትረፍ ርብርብ ሲያደርጉ ከነበሩት አንዱ ከድር ቶላ ይባላል። (ጥቁር ጁንስ ሱሪ በነጭ ጫማ ያደረገው)
ወደ ስራ እየሄደ በነበረበት ሰዓት ነው ይህ ክስተት ያጋጠመው።
ከድር የነፍስ አድን ስራውን ፥ " በህይወቴ እጅግ በጣም አስፈሪው ቅጽበት ነበር። ይህንን መቼም ቢሆን አልረሳውም ሁሌም ቢሆን አስታውሰዋለሁ " ሲል አስረድቷል።
አሽከርካሪው በህይወት እንዲተርፍ ቦታው ላይ የነበሩ ሁሉም ሰዎች ላደረጉት ፍጹም #ሰብዓዊ ተግባርና ርብርብ ፈጣሪን አመስግኗል።
የነበረውን የህይወት አድን ርብርብ የሚያሳይ ቪድዮ ከድር ቶላ መኪና ላይ በነበረ የዳሽቦርድ ካሜራ የተቀረጸ ነው።
Video Credit : Kadir Tolla / ከድር ቶላ
ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል:: ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት
አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
Tel: 0913858561
ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች
ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተእ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።
ሚለየን ምንድነው?
የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ
🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።
🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።
🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።
🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።
🪄We Care
አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ
📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69
www.elegas.com.tr
Email:- ethiopia@elegas.com.tr
የጎጃም ኮማንድፖስት ባደረገው ክትትል የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ እያገኙ መሆኑን የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር አርሶ አደሮች ተናገሩ።
ኮሩ በተሰማራበት ዞን ስር የሚገኙ ቲሊሊ ፣ እንጂባራ ፣ አዲስ ቅዳም ፣ ዳንግላ እና ሌሎች ወረዳዎች ስርጭቱ በተገቢው መንገድ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
አርሶ አደሮቹ በሰጡት አስተያየት ፣ የዘንድሮ የአፈር ማዳበሪያ ግብዓት ስርጭት አምና ከነበረው አንፃር ስንመለከት ዋጋው ተመጣጣኝ ሲሆን ወቅቱን ጠብቆ በመምጣቱ ለስራችን ምቹ ሆኔታን ይፈጥራል ብለዋል፡፡
ሰራዊቱ ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር እያደረገልን ሁሉም አርሶ አደር ድርሻውን በአግባቡ እየወሰደ ይገኛል ያሉት አርሶ አደሮቹ ፣ የጥፋት ቡድኑ የማዳበሪያ ግብዓቱን እንዳንወስድ በርካታ የሀሰት ወሬዎችን ቢነዛም አልተቀበልነውም ብለዋል፡፡
ከመንግስት ገንዘብ ከፍላችሁ አትውሰዱ እኛ በነፃ እንመጣለን ፣ በቅርቡ የማዳበሪያ ፋብሪካ እንገነባለን እያለ የበሬ ወለደ ወሬዎችን ቢያናፍስም አርሶ አደሩ ሀሰት መሆኑን ተገንዝቦ የቀረበለትን ማዳበሪያ ተገቢውን ክፍያ ለመንግስት በመክፈል እየወሰደ እንደሚገኝ አረጋገጠዋል ፡፡
የኮሩ ምክትል አዛዥ ኮሎኔል መንገሻ ሞላ ፣ የአፈር ማዳበሪያ ስርጭቱ ለአርሶ አደሩ አማካኝ በሆኑ ቦታዎች ላይ እንዲከማች በማድረግ እየተሰራጨ እንደሚገኝ እና ሰራዊቱ ግብዓቱን አጅቦ በማምጣት የእደላ ስራውን በቅርበትና በትኩረት እየተከታተለ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡
ሰራዊቱ ከሁሉም የሀገራችን ክፍሎች የተወጣጣ የህዝብ ልጅ በመሆኑ ማንኛውም ፈተና ሳይበግረው ለህዝባችን ሰላምና ልማት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ግዳጁ የሚጠይቀውን ሁሉ ዋጋ በመክፈል የህዝባችንን ሰላምና ልማት የማረጋገጥ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኮሩ ምክትል አዛዥ ኮሎሬል መንገሻ ሞላ አረጋግጠዋል፡፡
ኤልናፍ ትሬዲንግ ኋ.የተ.የግ.ማህበር
ELNAF TRADING PLC
የቱርክ ብሎኬት ማምረቻ
ድርጅታችን በኢትዮጵያ ተመዝግቦ የሚገኝና በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን በአሁን ስዓትም በለገጣፎ አካባቢ በ15,000 ካ.ሜ ላይ በቀን ከ40,000 በላይ ብሎኬቶችን ማምረት የሚያስችል የቱርክ ማሽኖችን ተክሎ ወደስራ የገባ ሲሆን በዚህም ለ150 ሰዎች የስራ ዕድል የፈጠረ ና በኮንስትራክሽን ዘርፉም የራሱን ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛል።
ለየት የሚያደርገን
⨳ በቱርክ ማሽኖች ማምረታችን
⨳ የራሳችንን የከርሰ ምድር ውሃ አውጥተን መጠቀማችን
⨳ በሰዓቱ ምርት ማቅረባችን
⨳ ያሉበት ድረስ በራሳችን ተሽከርካሪዎች ማድረሳችን
⨳ በሚፈልጉት size እናመርታለን
ባለ 10 cm
ባለ 15 cm
ባለ 20 cm
ባለ 24 cm (ሪብድ)
ይምጡ ይጎብኙን በምርታችንና ዘመናዊነትን በተከተለ አሰራራችን ይረካሉ።
ቤትና ህንፃዎችዎን በኤልናፍ ብሎኬት ይገንቡ ያትርፉ
አድራሻችን ቁ.1 ለገጣፎ አባ ኪሮስ ቤ/ያን እንዳለፉ
+251993999999
https://maps.app.goo.gl/kQ884KEndxzVxezaA
ቁ.2 ጀሞ 3 ሰይድ ያሲን አደባባይ አከባቢ
+251985888899
https://maps.app.goo.gl/djEzNajMtsvVA9JY9
የአማራ ክልል ክፍተኛ አመራሮች የልዑካን ቡድን በሰሜን አሜሪካ በኒውዮርክ ከተማ ከኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር ውይይትና ምክክር አደረገ።
በአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ የሚመራው የልዑክ ቡድን ኒውዮርክ ከተማ የሥራ ጉብኝት ቀጥሎ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ሚሲዮን ጽሕፈት ቤት አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ ኢትዮጵታዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ተወካዮች ጋር በሀገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርጓል።
የልዑክ ቡድኑ በሀገር ደረጃ እና ክልላዊ የልውጥ ጉዞ፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና የመፍትሔ መንገዶች ላይ ውይይት ያደረገ ሲሆን በውይይቱም ክልሉን ወደ ተሟላ ሰላም ለማምጣት መንግሥት እያደረገ ስላለው ጥረትና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እየተደረገ ስላለው ጥረት ውይይት ተደርጓል። ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ሚና በተመለከተ ውይይት ተደርጓል።
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለክልሉ እና ለሀገራቸው ሰላም በጎ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ በሥራ እድል ፈጠራ እና ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሰማሩ ያሉ አማራጮችን በልዑክ ቡድኑ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች ስለክልሉ የሰላም ሁኔታ፣ የልማት ሥራዎችና ድህነት ቅነሳ፣ ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ የማድረግ ሥራን፣ የሀገራዊ አካታች የምክክር መድረክ ላይ የአማራ ክልል ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ እየተከናወነ ያለውን ሥራ እና ለሥራ እድል ፈጠራ ያለውን ምቹ ሁኔታ በተመለከተ ጥያቄዎችን አንስተዋል።
የልዑክ ቡድኑ አባላት በክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የሕግ ማስከበር ሥራው ያለበት ደረጃና ለሰላም እየተደረገ ያለውን ጥረት፣ የተጀማመሩ የልማት ሥራዎችን በተመለከተ፣ ተፈናቃዮችን ለመመለስ የተጀመረውን ሥራ እና እየገጠመ ያለውን ፈተና፣ የምክክር መደረኩን የሕዝባችንን ጥያቄዎች ለማስመለስ እየተሠራ ያለውን ሥራና ያለውን ተስፋ ለማስፋት ከግጭት አባባሽ ተግባራት ሁሉም ርቆ ወደ ተሟላና ክልሉን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ተግባራት ዙሪያ ለተሳታፊዎች አሥረድተዋል።
የልዑክ ቡድኑ የሥራ ጉዞ እንደቀጠለ ነው።
ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል:: ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት
አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
Tel: 0913858561
በአንድ በኩል ሕግ የማስከበርና ሰላምና ደኅንነትን የማጽናት ሥራ እያከናወንን፤ በሌላ በኩል ደግሞ የተፈናቀሉ ሰዎችን የመመለስ ተግባር መከናወን አለበት። ሰላምና ጸጥታ ሕዝብ ሲረጋጋ የሚፈጠሩ ሥርዓቶች በመሆናቸው። በሀገራችን በተለያዩ ምክንያቶች፣ ሰዎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተፈናቅለዋል። እነዚህ ዜጎች ከመጠለያ ካምፖች ወጥተው ወደቀያቸው መመለስ ይኖርባቸዋል። በዘላቂነት ተረጋግተው ወደ መደበኛ ኑሮ መግባት አለባቸው። ይሄንን እውን ለማድረግ መንግሥት ሲተጋ ቆይቷል፣ አሁንም ሰፊ ሥራ እየሠራ ይገኛል። ለምሳሌ በሶማሌ እና ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች፣ እንዲሁም በጌዴኦ አካባቢ ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ እና ዘላቂ መኖሪያ እንዲያገኙ ለማድረግ ተችሏል።
በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ባጋጠመው ግጭት፤ እንዲሁም በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ባጋጠሙ የጸጥታ ችግሮች የተነሣ የተፈናቀሉ ዜጎች አሉ። እነዚህ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ እየሠራን ነው። የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል አመራሮች በጋራ ሠርተው ብዙዎችን ከመጠለያ ጣቢያ ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ አድርገዋል። በዚህ ሂደት በማኅበረሰቡ ዘንድ ወትሮም የነበረውን መተሳሰብ እና ጥብቅ ትሥሥር ለማየት ተችሏል። የተፈናቀሉ ጎረቤቶቻቸው እንዲመለሱ በየአካባቢው ከፍተኛ ፍላጎት አለ። ለሚመለሱት ተፈናቃዮች የየአካባቢው ማኅበረሰብ የሚያደርገው አቀባበል ልብ የሚጠግን ነው። በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ለምሳሌ በራያ እና አላማጣ አካባቢ ከተፈናቀሉ ዜጎች መንግሥትን ሳይጠብቁ በማኅበረሰባዊ መተሳሰብ ብቻ በርካታዎች ወደ ቤታቸው ገብተዋል።
በዚህ ሂደት የተፈናቃዮችን ጉዳይ እንደ ፖለቲካ አጀንዳ አድርገው ሊጠቀሙ የሚፈልጉ አካላት መኖራቸው ታይቷል። ተፈናቃዮች ከተመለሱ የልመናና፣ የተቃውሞ አጀንዳችን ይከስራል ብለው ይፈራሉ። እነዚህ ኃይሎች ተፈናቃዮቹ ወደ ቤታቸው እንዳይመለሱ ፕሮፖጋንዳ እና ማስፈራሪያ ይደረድራሉ። አንዳንዴም በኃይል ጭምር የተፈናቃዮችን መመለስ ለማሰናከል ይቃጣቸዋል። መንግሥት ካለበት የሞራል እና የሕግ ኃላፊነት የተነሣ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቤታቸውና ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ማድረጉን ይቀጥላል። ከክልሎች ጋር የተጀመረው ሥራም ይጠናከራል።
ሰላምና ጸጥታን ለማደፍረስ፣ የተፈናቀሉ ወገኖች እንዳይመለሱ ለማድረግና የልማት ተግባራትን ለማሰናከል አንዱ የመዋጊያ መሣሪያ የተዛባ፣ የተሳሳተና የተመረዘ መረጃን ማሠራጨት ነው። እንደሚታወቀው የመገናኛ ቴክኖሎጂ ዕድገት ዕድልም፣ አደጋም ይዞ መጥቷል። በዚህ ዘመነ መረብ ሽኩቻ እና ፉክክር ይበዛል። ነባር ተቋማት እና ሥርዓቶች በእጅጉ ፈተና ላይ ይወድቃሉ። በዚህ ዐውድ ውስጥ ሀገራት ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለማስከበር ያለ ይሉኝታ እና ያለ ብዙ ልጓም የቻሉትን ሁሉ ያደርጋሉ።
በዚህ ወቅት ሁኔታውን በአግባቡ በመረዳት፣ ይሄንን ማዕበል እና ወጀብ እንዴት ማለፍ አለብን የሚለውን በጥንቃቄ ተልመን ካልተንቀሳቀስን አደጋው ከባድ ነው። በዚህ ረገድ ውጤታማ ለመሆን የውስጥ አንድነት እጅግ ወሳኝ ነው። እንደ ኢትዮጵያ ያለ ትልቅ ሀገር የውስጥ አንድነት ካለው ነጥሮ ይወጣል። እንደ ሀገር እና እንደ ሕዝብ ለአንድ ዓላማ በጋራ ከተሰለፍን ወቅቱ ሀገራችንን ከፍ ለማድረግ የራሱን በጎ አጋጣሚዎች ይዞ ይመጣል። ከተከፋፈልን ደግሞ የሀገር ህልውና አደጋ ላይ ይወድቃል። ስለዚህም የሚመጡ መረጃዎችን መምረጥ፣ መመዘንና ማንጠር አስፈላጊ ነው። በምድር ያሸነፍናቸው ጠላቶቻችን በአየር እንዲመጡ መፍቀድ የለብንም።
እነዚህን ሁሉ የምናከናውነው መጀመሪያ ዘላቂ ሰላም፤ በዘላቂ ሰላም በኩልም ዘላቂ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ነው። እንደ መንግሥት ግባችን በአቋራጭ መንገድ፣ ከላይ ከላይ በሆነ እድሳት የሚመጣ ጊዜያዊ ጸጥታ አይደለም። ዘላቂ ሰላም ነው። ዘላቂ ሰላም የጦርነት አለመኖር ብቻ አይደለም። በመርሕ እና በሥርዓት ላይ የተመሠረተ፣ በቀላሉ የማይናወጥ ሰላም ነው። ግጭትን፣ እና አለመግባባትን በሰላማዊ እና በሕጋዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ዐቅም እና ሥርዓት መኖር ነው። በመሠረታዊ ጉዳዮች ላይ በመግባባት፣ ያለፈን ቁርሾ እና የታሪክ ጠባሳን አልፎ ወደፊት ለመሄድ መቻል ነው።
ይሄንን ዘላቂ ሰላምና ዘላቂ ብልጽግና ለማምጣት አዲስ የፖለቲካ ባህል የግድ ነው። ሁሉን አካታች ሀገራዊ ምክክር፣ የሽግግር ፍትሕ እና የተሐድሶ ተግባራት የዚህ ማከናወኛ ዋነኞቹ መሣሪያዎች ናቸው። ማንም እንደሚያውቀው አካታች የሆነ መንግሥታዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት ፈር ቀዳጅ እየሆንን ነው። ይህ ጥረት ውጤታማ እንዲሆን ግን የመንግሥት ተግባር ብቻውን በቂ አይሆንም። ገዢው ፓርቲ አዲስ የፖለቲካ ባህል ለማስተዋወቅ - አብረን እንሥራ፣ እንምከር፣ በጋራ ለሀገራችን ጉዳዮች መፍትሔ እንፈልግ እያለ ነው። አንዳንዶች ደግሞ በድሮ በሬ እያረሱ በጉልበት፣ በኃይልና በጠመንጃ መንግሥትን ጥለን ሥልጣን ጠቅልለን ካልወሰድን እያሉ ናቸው። እንደዚህ በተቃራኒ መንገዶች ተጉዘን የተጀመሩት ጥረቶቻችን ሊሳኩ አይችሉም። የ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ባህልን ይዞ በ22ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መሄድ ርግማን እንጂ ለውጥ አያመጣም።
ጦርነት ሁላችንንም ያከስራል። ሰላም ሁላችንንም አትራፊ ያደርጋል። እኛ ከአባቶቻችን ስለጦርነት እየሰማን አደግን፤ ይበቃናል። በእኛ ትውልድ እንኳን ሁለትና ሦስት ከባድ ጦርነቶች አለፉ። ለቀጣይ ትውልድ ግን ብልጽግናን እንጂ ቁስልን ማውረስ የለብንም። የኢትዮጵያን ዘመናዊ የፖለቲካ ቅኝት ለሃምሳ ዓመት የበየነው የ1966ቱ አብዮት ከተከሠተ ግማሽ ምእተ ዓመት ሆኖታል። አዙሪቱ ያልለቀቃቸው ግን አሁንም አሉ። ካለፈው ተምረን፣ የራሳችንን እና የዘመናችንን ዐውድ ተገንዝበን፣ በራሳችን ቅኝት እና አጀንዳ ወደፊት ልንራመድ ይገባል። የዚህ ትውልድ የሃምሳ ዓመት አጀንዳ ዘላቂ ሰላም እና ሁለንተናዊ ብልጽግና ነውና።
የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት
ሚያዚያ 16፣ 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ
በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ ከብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ
የተከበራችሁ የሀገራችን ሕዝቦች፣
ኢትዮጵያ በረጅም ዘመን የሀገረ መንግሥትነት ታሪኳ፣ የፖለቲካ ልዩነቶችን፣ አለመግባባቶችን እና ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ፣ በንግግር፣ በውይይት እና በሕጋዊ አግባብ የመፍታት ልምምድ የላትም። እንደ አለመታደል ሆኖ ፖለቲካችን የዜሮ ድምር ፖለቲካ ነው። በሀገራችን የተለመደው በጉልበት አሸንፎ ሥልጣን የያዘ ኃይል፣ በጉልበት ተሸንፎ ሥልጣን እስኪለቅ ድረስ ሁሉንም ጠቅልሎ የሚቆጣጠርበት እና የፈቀደውን የሚያደርግበት የፖለቲካ ባህል ነው።
የለውጡ መንግሥት ወደ ሥልጣን የመጣው በጉልበት አይደለም። ይሄም አዲስ የፖለቲካ ባህል ነው። ይሄን አዲስ የፖለቲካ ምእራፍ የሚያጸና ሌላ ሰላማዊ የፖለቲካ ባህል ደግሞ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የሕዝብ ይሁንታ አግኝቶ መንግሥት በመመሥረት አሳይቷል። ከዚህም በመሻገር ልዩ ልዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላትን በመንግሥት ኃላፊነት በመመደብ፣ ኢትዮጵያ የጋራ ቤት መሆንዋን አስመስክሯል።
ሰላማዊ የፖለቲካ ሽግግር ብቻውን ግብ አይደለም። ሌሎች ግቦችን ለማሳካት መሣሪያ እንጂ። የኢትዮጵያ ችግር የአሁኑን አካሄድ በማስተካከል ብቻ አይፈታም። በታሪክ ውስጥ የወረስናቸውን ስብራቶች መጠገንም የግድ ይለናል። እነዚህን የታሪክ ስብራቶች ለመጠገን ሦስት ዓይነት መፍትሔዎች ተቀምጠዋል። ነባሩን ፖለቲካዊ ችግር በሀገራዊ ምክክር መፍታት፤ የቅርብ ዘመናችንን የፖለቲካ ችግር ደግሞ በሽግግር ፍትሕ እና በተሐድሶ ማረም።
በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አንድ መንግሥት በምርጫ አሸንፎ ሥልጣን ቢይዝም እንኳን ብቻውን ሊወስናቸው የማይገቡ፣ ሀገራዊ እና አካታች ምክክር የሚፈልጉ ጉዳዮች አሉ። ይሄ ድምጽ መሰማት ከጀመረ ግማሽ ምእተ ዓመት እየዘለቀው ነው። የለውጡ መንግሥት እስከመጣበት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ግን ሰሚ አላገኘም ነበር። የለውጡ መንግሥት ሐሳቡን መቀበል ብቻ ሳይሆን ይሄንን የሚያሣልጥ ገለልተኛ ተቋምም አቋቁሟል።
በዚህ ተቋም ውስጥ በኃላፊነት የተሰየሙት ክፍተኛ ልምድ እና ብቃት ያላቸው ገለልተኛ ኮሚሽነሮች ናቸው። እነዚህ ኮሚሽነሮች አካታች ሀገራዊ ምክክሩን የማከናወን ሰፊ ሥልጣን በሕግ ተሰጥቷቸዋል። በዚሁ መሠረት ባለ ድርሻ አካላትን በማማከር ሂደቱ ምን መምሰል አለበት የሚለውን ዝርዝር አካሄድ እና አሠራሩን ነድፈዋል። በአሁኑ ወቅት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በነደፈው አካሄድ መሠረት በ10 ክልሎች እና በሁለት የከተማ አስተዳደሮች ከየወረዳው በምክክሩ ሂደት የሚሳተፉ ተሳታፊዎችን የመለየት ሥራ አጠናቋል። በእያንዳንዱ ክልል እጅግ ጥብቅ እና አድካሚ የሆነ ሥራ ተከናውኗል። ማኅበረሰቡን ከታችኛው የአስተዳደር መዋቅር ጀምሮ አሳትፏል። በዚህም በምክክሩ አካሄድ የሚሳተፉ ዜጎች ተለይተዋል። ከ679 ወረዳዎች፣ እስካሁን 12,294 ተሳታፊዎች ተለይተዋል።
ይሄ አካሄድ የጉዳዩ ባለቤት የሆነውን ሕዝብ ማዕከል ያደረገ ነው። አጀንዳዎች እና የመፍትሔ ሐሳቦች ከላይ ወደ ታች ብቻ ሳይሆን ከማኅበረሰቡም ፈልቀው፣ በውይይት ዳብረው ወደ መሐል የሚመጡበት አካሄድ ነው። በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ኮሚሽኑ በክልል ደረጃ የሚደረጉ የምክክር መድረኮችን ማካሄድ እንደሚጀምር ይጠበቃል። እንዲሁም የተሳታፊ ልየታ ባልተደረገባቸው ሁለት ክልሎች ላይ የተሳታፊዎች ልየታ በቅርቡ ይጠናቀቃል። በጉጉት የሚጠበቀው አካታች ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚካሄድ ተስፋ ይደረጋል።
ይሄንን በትውልድ መካከል አንዴ የሚገኝ ዕድል ሳናባክን፤ እያቃናንና እየደገፍን፣ ለኢትዮጵያ ነባር ችግሮች መፍትሔ አዋላጅ እንዲሆን፣ ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባናል። ዕድሎችን በሰበብ አስባቡ እያባከንን፣ ራሳችንን በችግር አዙሪት የማክረም አካሄድ ማብቃት አለበት።
ሁለተኛው የሽግግር ፍትሕ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች በደል፣ ግፍ እና መሠረታዊ የመብት ጥሰቶች ተከሥተዋል። ይህ በሌሎች ሀገራት ታሪክም የሚታይ ክሥተት ነው። እስከዛሬ ባለው አካሄዳችን በጉልበት አሸናፊ ሆኖ ሥልጣን የያዘው አካል፣ ሌሎችን በዳይ እና አጥፊ አድርጎ ይኮንናል፤ ይቀጣል። ይህ አካሄድ ግን ፍትሕን አያሰፍንም። እልህን፣ ቁጭትን እና የበቀል ጥማትን ያገነግናል እንጂ። የቁርሾ እና የቂም በቀል አዙሪት፣ የተበዳይነት እና የብሶት ትርክት በሀገራችን ዋነኛው የፖለቲካ ማጠንጠኛ የሆነበት አንዱ ምክንያትም ይሄው ነው። ይሄንን የበዳይ ተበዳይ አዙሪት ለመስበር የሽግግር ፍትሕ አንዱ ተመራጭ ስልት ነው። ስለዚህም የሽግግር ፍትሕ ሂደት የሚመራበት የፖሊሲ ማሕቀፍ ጸድቋል።
የፖሊሲው ዝግጅት የሚመለከታቸውን አካላት ያሳተፈ፣ ዓለም አቀፍ ልምድን መሠረት ያደረገ ነው። በቅድመ ፖሊሲ ማርቀቅ ሂደቱ ብቻ 60 የክልል እና 20 ሀገራዊ የግብአት ማሰባሰቢያ መድረኮች ተካሂደውበታል። የፖሊሲው ዓላማ የሽግግር ፍትሕ ሂደት የሚመራበት እና የሚተገበርበትን ሥርዓት በመዘርጋት ዘላቂ ሰላምን፣ ዕርቅን፣ የሕግ የበላይነትን፣ ፍትሕን እና ዴሞክራሲን ማረጋገጥ ነው። ይሄንን ዓላማ ለማሳካት እንደ አግባብነቱ የወንጀል ምርመራ እና ክስ፣ እውነት ማፈላለግ፣ ዕርቅ፣ በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ምሕረት፣ ማካካሻ እና ተቋማዊ ማሻሻያ እንደ ሽግግር ፍትሕ ስልቶች በሀገራችን ተግባራዊ ይደረጋሉ።
እንደሚታወቀው በሀገራችን ከመንግሥት ውጭ የሚኖር የታጠቀን ኃይል ሕገ መንግሥታችን አይፈቅድም። የመንግሥትም አንዱ መብት በብቸኝነት ኃይልን መጠቀም ነው። ነገር ግን በሀገራችን በወረስነው የፖለቲካ ስብራት የተነሣ የታጠቁ ኃይሎች ተፈጥረዋል። ሰላማችንን የጸና ለማድረግ፣ እነዚህ የታጠቁ ኃይሎች ትጥቅ ፈትተው፣ የተሐድሶ ሂደት ውስጥ መቀላቀል አለባቸው። የፖለቲካ ጥያቄዎቻቸውንም በሀገራዊ ምክክር ሂደት በመሳተፍ መፍታት ይችላሉ። ለዚህ የሚሆን የተሐድሶ ኮሚሽን ተቋቁሟል። ዓላማውም መሣሪያ ማስፈታት፣ የትጥቅ ቡድኖችን ሰላማዊ ማድረግና ከማኅበረሰቡ ጋር መቀላቀል ናቸው። ይሄንን የተሐድሶ ሥራ በማሳካት ፖለቲካችን ከግንባር ወደ ጠረጴዛ፣ ከጫካ ወደ አዳራሽ እንዲመለስ ማድረግ አለብን። እነዚህን ስልቶች በሚገባ ተግባራዊ በማድረግ፣ ከበዳይ ተበዳይ አዙሪት ልንወጣ ያስፈልጋል። በምሕረት፣ በይቅርታ፣ በካሣና፣ በፍትሕ ታክመን ወደፊት መጓዝ መቻል አለብን። ለዚህ ስኬትም ኢትዮጵያውያን ሁሉ በንቃትና በብቃት ልንሳተፍ ይገባናል። መንግሥትም የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አተገባበርን ከሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ጋር የተናበበ እና የሚመጋገብ እንዲሆን በማድረግ ኃላፊነቱን ይወጣል።
ነባር ሀገራዊ ችግሮቻችንን በሀገራዊ ምክከር እና በሽግግር ፍትሕ እያረምን የገጠሙን የግጭትና የጦርነት ፈተናዎች ለመሻገር ደግሞ ሰላማዊ የፖለቲካ አካሄዶችን ተመራጭ ማድረግ አለብን። ለሁለት ዓመታት የዘለቀውን የሰሜኑን ጦርነት በሰላም ስምምነት ለመፍታት የተፈለገውም ለዚህ ዓላማ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ በተለያዩ ወቅቶች የእርስ በርስ ግጭቶች እና ጦርነቶች በተደጋጋሚ ተከሥተዋል። በእነዚህ ጦርነቶች እንደ ሀገር ከባድ ኪሣራ ደርሶብናል። የዚህም ምክንያቱ ግጭቶችን በንግግር እና በስምምነት የመፍታት የፖለቲካ ልምምድ ብዙም ስለሌለን ነው። የለመድነው በጠላታችን መቃብር ላይ ሐውልት መገንባት ነው።
ትክክለኛ እርምጃ‼️
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሁሉንም ሃይማኖቶች በእኩልነት ያከብራል
ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ ፖሊስ ከየትኛውም ሃይማኖት፣ ብሄር እና ፖለቲካ ወገንተኝነት የፀዳ እና ብዛህነትን እሴቱ ያደረገ ሕዝባዊ ተቋም መሆኑን ገልጿል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሃይማኖቶች ብዛህነትን የሚያከብርና የሚያስከብር በእኩልነት ለሁሉም ሙያዊ አገልግሎት የእየሰጠ ያለ ተቋም ሆኖ ሳለ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ አዲስ የፖሊስ አባላትን ለመመልመል ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ የተላከ የፖሊስ አባል ምክትል ሳጂን ታመነ ዱባለ ጥር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ኬቾ ወዜ ቅዱስ ባለወልድ ቤተክርስቲያን በመገኘት የደንብ ልብሱን እንደለበሰ ሃይማኖታዊ መዝሙር በመዘመር እና በሕዝብ ፊት ጥይት እየተኮሰ በማህበራዊ ሚዲያ ሰሞኑን የሚሰራጨው ቪዲዮ ከተቋሙ መተዳደሪያ ህግና አሠራር ውጭ እንደሆነ መግለጫው አረጋግጧል።
አባሉም ይህንን ተግባር እንደፈፀመ ወዲያውኑ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎት የፈፀመው ድርጊት በተቋሙ ሕገ ደንብ መሠረት በሕግ አግባብ እያጣራ እንደሚገኝ መግለጫው አመላክቷል።
ፖሊስ የሁሉም አገልጋይ ሆኖ ሳላ አባሉ እምነቱን በግል መከተል እየቻለ ነገር ግን መንግስት ፀጥታ እንዲያስከብር ያስታጠቀውን የጦር መሣሪያ ከፍተኛ ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ፍፁም የፖሊስን ዲሲፕሊን በጣሰ መልኩ የፈፀመው ተግባር በሕግ የሚያስጠይቅ ስለሆነ ተቋሙ ሕግ ፊት እንደሚያቀርበው በመግለጫው ገልጿል።
አባሉ የፈፀመው ተግባር እውነታው ይሄ ሆኖ ሳለ ከዚህ ውጭ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚራገቡ የተሳሰቱ መረጃዎችን ኅብረተሰቡ እንዳይከተል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ አሳስቧል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ
ኤልናፍ ትሬዲንግ ኋ.የተ.የግ.ማህበር
ELNAF TRADING PLC
የቱርክ ብሎኬት ማምረቻ
ድርጅታችን በኢትዮጵያ ተመዝግቦ የሚገኝና በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን በአሁን ስዓትም በለገጣፎ አካባቢ በ15,000 ካ.ሜ ላይ በቀን ከ40,000 በላይ ብሎኬቶችን ማምረት የሚያስችል የቱርክ ማሽኖችን ተክሎ ወደስራ የገባ ሲሆን በዚህም ለ150 ሰዎች የስራ ዕድል የፈጠረ ና በኮንስትራክሽን ዘርፉም የራሱን ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛል።
ለየት የሚያደርገን
⨳ በቱርክ ማሽኖች ማምረታችን
⨳ የራሳችንን የከርሰ ምድር ውሃ አውጥተን መጠቀማችን
⨳ በሰዓቱ ምርት ማቅረባችን
⨳ ያሉበት ድረስ በራሳችን ተሽከርካሪዎች ማድረሳችን
⨳ በሚፈልጉት size እናመርታለን
ባለ 10 cm
ባለ 15 cm
ባለ 20 cm
ባለ 24 cm (ሪብድ)
ይምጡ ይጎብኙን በምርታችንና ዘመናዊነትን በተከተለ አሰራራችን ይረካሉ።
ቤትና ህንፃዎችዎን በኤልናፍ ብሎኬት ይገንቡ ያትርፉ
አድራሻችን ቁ.1 ለገጣፎ አባ ኪሮስ ቤ/ያን እንዳለፉ
+251993999999
https://maps.app.goo.gl/kQ884KEndxzVxezaA
ቁ.2 ጀሞ 3 ሰይድ ያሲን አደባባይ አከባቢ
+251985888899
https://maps.app.goo.gl/djEzNajMtsvVA9JY9
Must Watch : ስድብ የለ:: የጥላቻ ንግግር የለ:: አንድን ዘር (ብሔር) ለይቶ ማንቋሸሽ ማብጠልጠል የለ:: ጤናማ ለሃገር የሚጠቅም በጎ ውይይት:: https://youtu.be/VJe3i4h-Z4k?si=it_keaaIpNhNU0RD
Читать полностью…🔷 የአያትን አክሲዮን የገዛ ሁሌም ትርፋማ
በ 2015 ዓ.ም 51% ትርፍ /Dividend/ ለባለክሲዮኖች አከፋፍለናል
በቀላል አማርኛ የ 1 ሚሊዮን ብር አክሲዮን የነበራቸው ባለአክሲዮኖች 510 ሺ ብር ትርፍ /Dividend/ አግኝተዋል
የ 5 ሚሊዮን ብር የገዙ 2.5 ሚሊዮን ብር አትርፈዋል
የአንድ አክሲዮን ዋጋ 100 ብር ነው
ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የአክሲዮን መጠን 2500 ነው
ዝቅተኛ የአክሲዮን ዋጋ 262,500 ብር ፣ 5% የአገልግሎት ክፍያን ጨምሮ
ከፍተኛ የአክሲዮን መጠን ገደብ የለውም
40% ከፍለው ቀሪውን በሶስት ዓመት መጨረስ ይችላሉ
አክሲዮኑን ከገዙ ከአንደኛው ወር ጀምሮ የትርፍ ተካፋይ መሆን ይጀምራሉ
ለበለጠ መረጃ: በ 0948888672/ 0935407638 ይደውሉ
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የቤት ልማት ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት በማጠናቀቅ ረገድ የታዩ ልምዶች ይበልጥ መጎልበት እንዳለባቸው የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን አስታወቀ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የበጀት ዓመቱን የመንግሥት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሲገመግሙ የፌዴራል ሱፐርቪዥን ቡድን ተቋቁሞ ትኩረት በተሰጣቸው ዘርፎች ላይ የመስክ ምልከታ እንዲያደርጉ አቅጣጫ ማስቀመጣቸው ይታወሳል።
በዚህም የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የሚያስተባብረው የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን የኮርፖሬሽኑን ዋና መሥሪያ ቤት፣ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችና የቤቶች ልማት ፕሮጀክቶችን የሥራ እንቅስቃሴ ተመልክቷል፡፡
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል፤ ኮርፖሬሽኑ ግንባታዎች በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቁበት የፕሮጀክት አስተዳደር ሥርዓት በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ረዥም ዕድሜ ያስቆጠረ አንጋፋ የመንግሥት ተቋም ቢሆንም ለውጡ እስከመጣበት 2010 ዓ.ም ድረስ ዕድሜውን በማይመጥን ችግር ውስጥ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
ከለውጡ ማግስት በተደረገው ተቋማዊ ሪፎርም ለ42 ዓመታት ከቆየበት ችግር በማውጣት ትርፋማና ተወዳዳሪ ተቋም ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡
በሪፎርሙ ጠንካራ አደረጃጀት በመፍጠር፣ ተወዳዳሪ የሰው ኃይል በማፍራት፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት የኮርፖሬሽኑን የማስፈፀም አቅም ማሳደግ መቻሉን ገልፀዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ የቤቶችን የይዞታ ካርታ በማዘጋጀት፣ ለቤቶች መለያ ምልክት በመለጠፍ፣ ጂ.ፒ.ኤስ እና ወደ ጎግል ካርታ በማስገባት የኮርፖሬሽኑን የቤት አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻል መቻላቸውን ጠቁመዋል፡፡
ተቋሙ የንግድ ቤቶችን ኪራይ በማሻሻል የገቢ አማራጮችን እያሰፋ መሆኑን ገልጸው፤ በ2010 ዓ.ም.የተቋሙ ገቢ ከነበረበት 308 ሚሊየን ብር በ2015 ዓ.ም. ወደ 2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ማሳደግ ተችሏል ብለዋል፡፡
ለ28 ዓመታት ተቋርጦ የነበረውን የቤቶች ግንባታ ከማስጀመርም ባለፈ፤ የጥራት፣ ጊዜና የግንባታ ዋጋ ማሻሻል ተችሏል ነው ያሉት፡፡
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ነመራ ገበየሁ፤ የኮርፖሬሽኑ ተቋማዊ አመራር ከዋና መሥሪያ ቤት እስከ ቅርንጫፍ ወጥነት ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ የቤት አስተዳደር ሥርዓት ለማሻሻል የተጀመረው የቤቶች የመረጃ አያያዝ ሥርዓት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ጠቁመዋል።
ፕሮጀክቶችን በአግባቡ በመከታተል በተያዘላቸው ጊዜ፣ ጥራት እና ዋጋ እንዲጠናቀቁ እየተደረገ ያለው ተግባር ለሌሎች አርዓያ እንደሚሆንም ተናግረዋል፡፡
ከቤቶች ልማት ጎን ለጎን በቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገነባው የብሎኬት እና የኮንክሪት ማምረቻ ፋብሪካ የዘርፉን ችግር ከመፍታት ባለፈ ለኢንዱስትሪው ተሞክሮ የሚሆን ነው ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ታምራት ሙሉ፤ የኮርፖሬሽኑ የቤቶች ግንባታ እንደ ሀገር ተሞክሮ የሚወሰድበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በግንባታ ሂደት የሚሳተፉ ባለቤቶች፣ አማካሪዎችና ተቋራጮች ጥምረት ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል በበኩላቸው፤ የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን የመስክ ምልከታ የበለጠ ለመሥራት የሚያበረታታ ነው ብለዋል።
የተሰጠውን አስተያየት በመቀበል ተቋሙ አሁን ካለበት በተሻለ መልኩ ለመሥራት እንደሚያነሳሳም አቶ ረሻድ ተናግረዋል።
የሱፐርቪዥን ቡድኑ በተመረጡና ትኩረት በተሰጣቸው ዘርፎች የሚያደርገው የመስክ ምልከታ እስከ ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ደርምኔት የተመረጡ 3 የህፃናት የቆዳ በሽታዎችን ፎቶ በማንሳት ብቻ የሚለይ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የበለፀገ መተግበሪያ ነው፡፡ ስለመተግበሪያው አጠቃቀም እና አስፈላጊነት በዚህ ጥንቅር ልናስቃኛችሁ ወደናል ተጋበዙልን፡፡
ከኢትዮጵያ አርቴፍሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ፌስቡክ ገጽ የተወሰደ
🔷 የአያትን አክሲዮን የገዛ ሁሌም ትርፋማ
በ 2015 ዓ.ም 51% ትርፍ /Dividend/ ለባለክሲዮኖች አከፋፍለናል
በቀላል አማርኛ የ 1 ሚሊዮን ብር አክሲዮን የነበራቸው ባለአክሲዮኖች 510 ሺ ብር ትርፍ /Dividend/ አግኝተዋል
የ 5 ሚሊዮን ብር የገዙ 2.5 ሚሊዮን ብር አትርፈዋል
የአንድ አክሲዮን ዋጋ 100 ብር ነው
ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የአክሲዮን መጠን 2500 ነው
ዝቅተኛ የአክሲዮን ዋጋ 262,500 ብር ፣ 5% የአገልግሎት ክፍያን ጨምሮ
ከፍተኛ የአክሲዮን መጠን ገደብ የለውም
40% ከፍለው ቀሪውን በሶስት ዓመት መጨረስ ይችላሉ
አክሲዮኑን ከገዙ ከአንደኛው ወር ጀምሮ የትርፍ ተካፋይ መሆን ይጀምራሉ
ለበለጠ መረጃ: በ 0948888672/ 0935407638 ይደውሉ
በአቡዳቢና ዱባይ አከባቢ እየተሰጠ ባለው የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎቶች ከዚህ ቀደም የሚነሱ ቅሬታዎችን እየተፈቱ መሆኑ ተገለፀ
በአቡዳቢ እና ዱባይ አከባቢ ለሚገኙ ዜጎች እየተሰጠ ያለው የኢግሬሽን ዜግነት አገልግሎት ከዚህ ቀደም የሚነሱ ቅሬታዎችን እየፈታ መሆኑንን የኮሚኒቲ አባላት ተወካዮችና አመራሮች ተናግረዋል።
በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የተመራ ልዑክ በአቡዳቢና ዱባይ ሚሲዮኖች እየተሰጡ ያሉ የዜግነት አገልግሎቶችን ያሉበትን ሁኔታ በመመልከት በጉዳዩ ዙርያ ከሚሲዮን መሪዎችና ኮሙኒቲ ተወካዮች ጋር ውይይት አካሂዷል። በውይይቱም በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የታዩ በጎ ስራዎችና ውስንነቶች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።
በዚህም በሁለቱም ሚሲዮኖች ከፓስፖርት እድሳትና ተያያዥ አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ ዜጎች ላቀረቡት ጥያቄ ተቋሙ የሰጠው ምላሽ የሚደነቅ ነው በማላት የኮሙኒቲ አመራሩ ምስጋናውን አቅርቧል። ሆኖም ከጉዞ ሰነድና ቪዛ ጋር ተያይዞ ሊፈቱ የሚገባቸው ችግሮች መቀረፍ እንዳለባቸው ጠይቀዋል።ከዚህ ባሻገር የመረጃ ልውውጥ ክፍተት፣ ፎርጅድ ማስረጃ፣ የጉዞ ሰነድ(ሊሴ ፓሴ) ፣ የበየነ- መረብ አጭበርባሪዎች መበራከት፣እንዲሁም ከዜግነት አገልግሎት ጋር ያሉ ክፍተቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
ውይይቱን የመሩት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ተቋሙ 11 የሪፎርም አጀንዳዎችን በመቅረፅ ወደ ስራ መግባቱን በማስታወስ ከዜጎች አገልግሎት ጋር በተያያዘ እየታዩ ያሉ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴዎች የዛ ውጤት መሆኑን ጠቁመዋል።የሪፎርሙ ስራ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ በዘርፉ የተስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ትልቅ እድል የሚሰጥ መሆኑን አክለው ገልፀዋል።
በተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች በነበረው ውይይትና የስራ ጉብኝት አገልግሎቱን በዘመነና በተቀላጠፈ መልኩ ከመስጠት አኳያ የዱባይ ሚሲዮን ቴክኖሎጂን በመጠቀም ረገድ የሚከተለው አሰራር የሚደነቅና በሌሎችም ቦታዎችም እንደተሞክሮ ሊወሰድ የሚገባ መሆኑን ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።ከሰነድ አልባና ከዜግነት አገልግሎት ጋር ያሉ ስራዎች ከአገር ደህንነት ጋር በጥብቅ የተቆራኘ መሆኑን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሯ ይህም በመሆኑ ዜግነትን የማረጋገጥ ስራ በጥንቃቄና በህግ አግባብ ብቻ መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል።
በዋና ዳይሬክተሯ የተመራው ልዑክ በጂቡቲ፣ጂዳና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ከሰነድ አልባ ዜጎችና ዜግነት አገልግሎት ጋር በተያያዘ ከሚሲዮን መሪዎች፣የኮሙኒቲ ተወካዮችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር በዘርፉ በሚስተዋሉ ችግሮችና መፍትሄዎች ላይ ተከታታይ ምክክር ማድረግ ችሏል።
ኤልናፍ ትሬዲንግ ኋ.የተ.የግ.ማህበር
ELNAF TRADING PLC
የቱርክ ብሎኬት ማምረቻ
ድርጅታችን በኢትዮጵያ ተመዝግቦ የሚገኝና በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን በአሁን ስዓትም በለገጣፎ አካባቢ በ15,000 ካ.ሜ ላይ በቀን ከ40,000 በላይ ብሎኬቶችን ማምረት የሚያስችል የቱርክ ማሽኖችን ተክሎ ወደስራ የገባ ሲሆን በዚህም ለ150 ሰዎች የስራ ዕድል የፈጠረ ና በኮንስትራክሽን ዘርፉም የራሱን ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛል።
ለየት የሚያደርገን
⨳ በቱርክ ማሽኖች ማምረታችን
⨳ የራሳችንን የከርሰ ምድር ውሃ አውጥተን መጠቀማችን
⨳ በሰዓቱ ምርት ማቅረባችን
⨳ ያሉበት ድረስ በራሳችን ተሽከርካሪዎች ማድረሳችን
⨳ በሚፈልጉት size እናመርታለን
ባለ 10 cm
ባለ 15 cm
ባለ 20 cm
ባለ 24 cm (ሪብድ)
ይምጡ ይጎብኙን በምርታችንና ዘመናዊነትን በተከተለ አሰራራችን ይረካሉ።
ቤትና ህንፃዎችዎን በኤልናፍ ብሎኬት ይገንቡ ያትርፉ
አድራሻችን ቁ.1 ለገጣፎ አባ ኪሮስ ቤ/ያን እንዳለፉ
+251993999999
https://maps.app.goo.gl/kQ884KEndxzVxezaA
ቁ.2 ጀሞ 3 ሰይድ ያሲን አደባባይ አከባቢ
+251985888899
https://maps.app.goo.gl/djEzNajMtsvVA9JY9
ምዕራባውያን መጨረሻው አስከፊ ወደሆነው የኑክሌር ጦርነት እየተንደረደሩ ነው ስትል አስጠነቀቀች
የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ለዩክሬን የ61 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ አጽድቋል።
https://bit.ly/449eWBv
ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች
ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተእ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።
ሚለየን ምንድነው?
የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ
🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።
🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።
🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።
🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።
🪄We Care
አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ
📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69
www.elegas.com.tr
Email:- ethiopia@elegas.com.tr
የአሜሪካ እርዳታ ዩክሬን የበለጠ እንድትፈራርስ የሚያደርግ ነው-ክሬሚሊን
የአሜሪካ የተወካዮች ምክርቤት ለዩክሬን፣ ለእስራኤል እና በኢንዶ ፓሲፊክ ለሚገኙ የአሜሪካ አጋሮች የሚወል የ95 ቢሊዮን ዶላር ወታደራዊ እርዳታ አጽድቋል።
https://bit.ly/3Qbr6Er
🔷 የአያትን አክሲዮን የገዛ ሁሌም ትርፋማ
በ 2015 ዓ.ም 51% ትርፍ /Dividend/ ለባለክሲዮኖች አከፋፍለናል
በቀላል አማርኛ የ 1 ሚሊዮን ብር አክሲዮን የነበራቸው ባለአክሲዮኖች 510 ሺ ብር ትርፍ /Dividend/ አግኝተዋል
የ 5 ሚሊዮን ብር የገዙ 2.5 ሚሊዮን ብር አትርፈዋል
የአንድ አክሲዮን ዋጋ 100 ብር ነው
ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የአክሲዮን መጠን 2500 ነው
ዝቅተኛ የአክሲዮን ዋጋ 262,500 ብር ፣ 5% የአገልግሎት ክፍያን ጨምሮ
ከፍተኛ የአክሲዮን መጠን ገደብ የለውም
40% ከፍለው ቀሪውን በሶስት ዓመት መጨረስ ይችላሉ
አክሲዮኑን ከገዙ ከአንደኛው ወር ጀምሮ የትርፍ ተካፋይ መሆን ይጀምራሉ
ለበለጠ መረጃ: በ 0948888672/ 0935407638 ይደውሉ