natnaelmekonnen21 | Unsorted

Telegram-канал natnaelmekonnen21 - Natnael Mekonnen

169400

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7 Facebook.com/natnaelmekonnen.et Instagram.com/natnaelmekonnen21

Subscribe to a channel

Natnael Mekonnen

ሰበር ዜና!!

ህወሃት…… ፍርክስክሱ አየወጣ ነዉ ፡፡ ሁለተኛ ቀኑን በያዘዉ የህወሃት ምሉእነት የጎደለው እንዲሁም ተሳታፊዎቹ በዉል የማይታወቁት የህወሃት የጨረባ ጉባዔ አዲስ ነገር እያስመለከተ ይገኛል ፡፡ ጠዋት የመወያያ ነጥብ በነበረዉ ጉዳይ ላይ ሶስት ከፍተኛ የድርጅቱ አመራሮች የተቃዉሞ ሃሳብ በማንሳት ድምፃቸዉን ለማሰማት የሞከሩ ቢሆንም አንባ ገነኑ የደብረፂሆን ቡድን በይፋ በማስፈራራት ጭምር ጫና ያደረሰባቸዉ ሲሆን 3ቱም አመራሮች ጉባዔዉን አቋርጠዉ ወጥተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ከሰመዓዕታት አዳራሽ እንደወጡ የነጄኔራል ታደሰ ወረደ ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር አዉለዋቸዋል፡፡

በመቀሌ ያለዉ ዉጥረት እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ከስፍራዉ ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል፡፡

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች

ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተ‍እ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበ‍ኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።

ሚለየን ምንድነው?

የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ

🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።

🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።

🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።

🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።

🪄We Care

አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ

📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69

www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

“በህወሓት እና ጊዜያዊ አስተዳደሩ መካከል ያሉ ቁርሾዎች በክልሉ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል” - ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) በህወሓት እና በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መካከል “አሉ” ያላቸው ቁርሾዎች በክልሉ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ስጋት መደቀናቸውን አስታወቀ። ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ የፌደራል መንግስት እና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የዜጎችን ሰላም እና ደህንነትን ከምንም ጉዳይ በፊት ትኩረት እንዲሰጡ አሳስቧል።

ኢዜማ በዚህ መግለጫው “በአንድ የፖለቲካ ፓርቲ የውስጥ አሰራር እና ሒደት ላይ አሰተያየት መስጠት” ፍላጎቱ አለመሆኑን ጠቅሶ፣ ነገር ግን “እብሪተኛ” ሲል በሚነቅፈው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ምክንያት በትግራይ ክልል እና አጎራባች ክልሎች ውስጥ በሚገኙ ንፁሐን ዜጎች ላይ ይዞ ሊመጣ የሚችለው አደጋ ቀላል አለመሆኑን ገልጿል። አክሎም፣ ህወሓት እንደፓርቲ ሕልውናውን ለማስቀጠል እያደረገው “ነው” ባለው ሂደት ሳቢያ፣ እንዲሁም የፓርቲው አመራሮች የእርስ በእርስ ሽኩቻ፤ በህወሓት እና ጊዜያዊ አስተዳደሩ መካከል “አሉ” ባላቸው ቁርሾዎች የተነሳ በክልሉ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ስጋት “ደቅኗል” ሲል ኢዜማ በመግለጫው አትቷል።

“የፕሪቶሪያው ሰምምነት በአግባቡ አለመከበሩ በክልሉ ለሚስተዋለው ስር የሰደደ ስጋት፣ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት መጥፋት ዋነኛ መንስኤ መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም” ያለው ኢዜማ፣ “የፕሪቶሪያው ስምምነት በተያዘው ዝርዝር ዕቅድ መሰረት አለመፈጸሙን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ የመሣሪያ አይነት እና ቁጥር በፖለቲካ ኃይሎች እጅ ባለበት ሁኔታ፣ የሃሳብ ልዩነትን ሰላማዊ በሆነ መንገድ በውይይት መፍታት በማይታወቅበት፣ ብሎም መንግስት እና ፓርቲ የመለየት ምንም የረባ ልምድ በሌለው ፖለቲካችን ውስጥ ሕዝብ የሚያስተዳድር ፓርቲ በውስጡ ያሉ መካረሮች ዳፋው ለሰፊው ሕዝብ እንደሚተርፍ ትናንታችንን ዞር ብሎ ማየት በቂ ነው፡፡” ብሏል።

ኢዜማ የትኛውንም ዓይነት ልዩነት በውይይት እና ሕጋዊ መንገድ ከመፍታት ውጪ ያለው አማራጭ ሁሉ ውጤቱ የዜሮ ድምር መሆኑን በመጠቆም፣ አሁንም ቢሆን በጥይትና ጠመንጃ ማሰብ ጊዜው ያለፈበት ያረጀ ያፈጀ መንገድ መሆኑን አውስቷል፡፡ እንዲሁም “እኔ ያልኩት ብቻ ‘ካልሆነ’ የሚል ግትር መንገድን መከተል ጦረኝነት፣ ግጭት መጥመቅ እና እልቂት መጋበዝ መሆኑን በመረዳት በሰከነ መንገድ ማሰቡ ይሻላል እንላለን” በማለት ጥሪውን አቅርቧል።

“አለ” ያለውን ችግር የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደርም ሆነ የፌደራል መንግስት ትኩረት ሰጥተው በመመልከት የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ከምንም ጉዳይ በፊት ቅድሚያ እንዲሰጡ በአንክሮ ጠይቋል፣ ኢዜማ በመግለጫው

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

#NewsAlert🚨

" ቀድሞ የገባውን ግዴታ ሲሸራርፍ የመጣው ህወሓት ዛሬ በተጨባጭ ተግባር  ደምስሶታል። ... ይህ ድርጊቱም የትግራይ ህዝብ ያገኘውን አንጻራዊ ሰላም እንደመንጠቅ ይቆጠራል !! " - ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

በሊቀ መንበሩ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ቡድን ጉባኤውን መጀመሩ ይፋ በተደረገበት በዚህ ሰዓት ላይ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) አጭር ግን ጠንካራ መልእክት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አሰራጭተዋል።

በዚህም " በየትኛውም የዓለም ጥግ ያለ  አገር የሚመራው በህግና በስርዓት ነው " ብለዋል።

" ህግና ስርዓት ከማንኛውም ሰው፣ ተቋም፣ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ፣ ቡድን፣ ስብስብ በላይ ነው። " ያሉት ለገሰ (ዶ/ር) " እነዚህ ሁሉ ከህግ እና ስርአት በታች ናቸው፤ ህግና ስርዓትን አክብሮ  የማይንቀሳቀስ የትኛውም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ የመጨረሻ ግቡ ጥፋት ነው " ሲሉ አስገንዝበዋል።

ለገሰ (ዶ/ር) ፥ " የህወሓት ያለፉት ዓመታት የግትርነት ባህሪም የዚሁ ምሳሌ ነው " ያሉ ሲሆን " ህወሓት ደጋግሞ  እንደመሸሸጊያ የሚያነሳው የፕሪቶሪያ ስምምነት የፌደራል ተቋማትን አሰራሮች፣ ህጎችና አካሄዶች በጥብቅ ሊያከብር ግዴታ ጥሎበታል " ብለዋል።

" ቀድሞ የገባውን ግዴታ ሲሸራርፍ የመጣው ህወሓት ዛሬ በተጨባጭ ተግባር  ደምስሶታል፡፡ " ሲሉ አሳውቀዋል።

" ድርጊቱ  የትግራይ ህዝብ ያገኘውን አንጻራዊ ሰላም እንደመንጠቅ ይቆጠራል፡፡ " ያሉት ለገሰ (ዶ/ር) " አንዴ፡ ሁለቴ፡ መሳሳት ያለንና  የነበረ ነው፡፡ በተመሳሳይ መንገድ ተመሳሳይ ስህተት ሶስቴ መፈጸም  ግን የመጨረሻው የጥፋት መንገድ ነው " ሲሉ አስንገብለዋል።

" ለዚህ ደግሞ ብቻኛ ተጠያቂ እራሱ (ህወሓት) ይሆናል " በማለት ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች

ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተ‍እ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበ‍ኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።

ሚለየን ምንድነው?

የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ

🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።

🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።

🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።

🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።

🪄We Care

አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ

📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69

www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

“ ዶ/ር አሸብር ህዝብን ካከበሩ ኃላፊነታቸውን ያስረክቡ “ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ

ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የኢትዮጵያን ህዝብ ካከበሩ ሀላፊነታቸውን እንዲያስረክቡ ጠይቋል።

“ በኦሎምፒክ ከአለም አርባ ሰባተኛ ደረጃን ይዘን አጠናቀን አነገታችንን ቀና ማድረግ አንችልም “ ያለው ኃይሌ “ በኬንያ እና በእኛ መሀል የበርካታ ሀገራት ልዩነት ነው ያለው “ ሲል ገልጿል።

አትሌት ሲሳይ ለማ ታምራት ቶላ እንዲወዳደር በመጠየቁ ትልቅ ክብር እንዳለው የገለፀው ኃይሌ ገ/ስላሴ “ እሱም ወርቅ ነው ያመጣው “ ሲል አክብሮቱን ገልፆለታል።

ሌሎች አትሌቶች እና ሀላፊዎችም ከአትሌት ሲሳይ ለማ መማር እንዳለባቸው እና ሀገርን ማስቀደም እንዳለባቸውም አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ አሳስቧል።

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር “ እንደሚናገሩት ለኢትዮጰያ ህዝብ ክብር ካላቸው ኃላፊነታቸውን ያስረክቡ “ ሲልም ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ ጠይቋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ሳር ቤት ላይ ባለ 3 መኝታ በ8.9 ሚሊዮን ብር ብቻ

156 ካሬ

በካሬ 57,000 ብር

ለ 10 ቀን ብቻ የሚቆይ

ድጋሚ የማያገኙት ዕድል!

ለበለጠ መረጃ፦ በ 0983638578 ይደውሉ

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች

ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተ‍እ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበ‍ኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።

ሚለየን ምንድነው?

የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ

🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።

🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።

🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።

🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።

🪄We Care

አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ

📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69

www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተፈናቀሉ ዜጎች የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በጎፋ ዞን በድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ የሚውል የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በዛሬው እለት አሰረክቧል፡፡

የገንዘብ ድጋፉን የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኃይለብርሀን ዜና በቦታው በመገኘት አስረክበዋል፡፡ አቶ ኃይለብሀን ዜና በወገኖቻችን ላይ በደረሰው ድንገተኛ አደጋ የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ሠራተኞችን ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በመላ አገሪቱ የሚከሰቱ ሰው ሠራሽ እና ተፍጥሯዊ አደጋዎች ምክንያት ጉዳት ለደረሰባው ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ ሲያደርግ መቆቱን አስተውሰው በ6 ዓመታት ብቻ ኮርፖሬሽኑ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ታሳቢ በማድረግ ያደረገው ድጋፍ ግማሽ ቢሊየን ብር መሻገሩን ተናግረዋል፡፡

በጎፋ ዞን በድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተፈናቀሉ ዜጎች መልሶ ለማቋቋም እየተደረገ ያለውን አንቅስቃሴ መደገፉን አጠናክሮ ይቀጥላልም ነው ያሉት አቶ ኃለብርኃን ዜና ፡፡

የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ በበኩላቸው ከፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለተደረገው የገንዘብ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው ፣ ድጋፉ በአደጋው ለተጎዱ እና የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በአደጋው ለተጎዱና ለተፈናቀሉ ወገኖች ተገቢው የሆነ ሰብዓዊ ድጋፍ እየተደረገ እንደሆነ ጠቁመው ተፈናቃዮችን ከአደጋ ስጋት ነጻ ወደ ሆነ ቦታ የማስፈር ሥራ እየተሰራ እንደሆም ገልጸዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ያደረገው የገንዘብ ድጋፍም ለመልሶ ማቋቋም ሥራው ትልቅ አጋዥ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

አዲስ አበባ

ጉዳዩ፦በቅርቡ የተሰጠ የህወሓት ምዝገባ በማስመልከት ያለን ቅሬታ ማቅረብን ይመለከታል

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነሐሴ 03 ቀን 2016ዓ.ም ለህወሓት በልዩ ሁኔታ የምዝገባና የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መስጠቱን ይታወቃል።

ቦርዱ ይህንን በማስመልከት በተመሳሳይ ቀን በሰጠው መግለጫ በተራ ቁጥር 2 ደግሞ ህወሓት የፓርትው ኃላፊዎች ስምና ፊርማ የያዘ ሰነድ ማቅረቡን ይፋ አድርጓል።ይሁንና ይህ የምዝገባ ጥያቄ ህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ የማያውቀው እና እኛ ደግሞ ለዚሁ ምዝገባ ብለን የፈረምነው ምንም ዓይነት ሰነድ ሳይኖር ግለሰዎች ብቡድን ተደራጅተው ከድርጅቱ አሰራር ውጭ የፈፀሙት ያልተገባ ተግባር መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን።

በመሆኑም ይህ ድርጊት እኛ የማናውቀው መሆኑን እየገለፅን በድርጅቱ ስም ምዝገባ የጠየቁ ግለሰዎችም እኛን ሳያስፈቅዱ የፈፀሙት መሆኑን እየገለፅን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለነዝህ ግለሰዎች የሰጠው ምዝገባ በተጭበረበረ ማስረጃ መሰረት የተሰጠ በመሆኑ መልሶ እንዲመረምረው እንጠይቃለን።

የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ስም ዝርዝር እና ፊርማ ቀጥለን የምናቀርብ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ከሰላምታ ጋር

ጌታቸው ረዳ

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

አዲስ አየር ማረፊያ ከሚገነባበት በቢሾፍቱ አቅራቢያ ከሚገኝ ቦታ፤ 2,500 አባወራዎች እንደሚነሱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በስድስት ቢሊዮን ዶላር አዲስ አየር ማረፊያ ከሚያስገነባበት ቦታ፤ 2,500 አባወራዎች እንደሚነሱ ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው ተናገሩ።

አየር መንገዱ ተነሺዎችን በሚያሰፍርበት ምትክ ቦታ ላይ፤ የመኖሪያ ቤት እና ለነዋሪዎቹ የሚያስፈልጓቸው “ፋሲሊቲዎች” እንደሚገነቡላቸውም ገልጸዋል።

አቶ መስፍን ይህን የገለጹት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ አዲስ የሚያስገነባውን የአየር ማረፊያ ንድፍ ለማሰራት፤ መቀመጫውን በዱባይ ካደረገ አማካሪ ኩባንያ ጋር ስምምነት በተፈራረመበት ወቅት ነው።

ስምምነቱን ዛሬ አርብ ነሐሴ 3፤ 2016 በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል የተፈራረሙት፤ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን እና የዳር አል-ሃንዳሳህ ኩባንያ የኦፕሬሽን ዳይሬክተር ታሪቅ ናጂ አል-ቃኒ ናቸው።

በቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ “አቡሴራ” በተባለ ቦታ የሚገነባው አዲስ አየር ማረፊያ፤ 100 ሚሊዮን መንገደኞች የማስተናገድ አቅም እንደሚኖረው አቶ መስፍን በዛሬው የፊርማ ስነ ስርዓት ላይ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት በዋነኛ ማዕከልነት እየተገለገለበት የሚገኘው የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት፤ በዓመት 25 ሚሊዮን መንገደኞችን ወደ ማስተናገድ በቅርቡ እንደሚሸጋገርም ዋና ስራ አስፈጻሚው ጠቁመዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ላይ ውይይት አደረጉ።

በጠንካራ የኢኮኖሚ መሰረት ላይ የተገነባች ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ በሚያስችል መልኩ በመንግስት ቁርጠኛ ውሳኔ ሙሉ በሙሉ መተግበር የተጀመረውን አገራዊ የማይክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም አስመልክቶ የገንዘብ ሚኒስቴር ሀላፊዎች ከመከላከያ ሠራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በመንግስት ይፋ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ለአገራችን ሁሉ ዓቀፍ ተሰሚነትና ዲፕሎማሲ ትልቅ ድል ያመጣ ስለሆነ ለተግባራዊነቱ ሰራዊቱ የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚያበረክት አስታውቀዋል።

ሰራዊቱ እንደሀገር ሰላምና ፀጥታን ከማስከበር ጀምሮ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር የሚጠበቅበትን ሁሉ ያደርጋል ያሉት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ እንደ ተቋም ለማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ትግበራ በሙሉ አቅም እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ በበኩላቸው ማሻሻያው የአገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርም አካል ሆኖ የኢኮኖሚ ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ብልፅግናን በማረጋገጥ እንደ አገር ውስጣዊ አቅምን በማጎልበት በቀጠናዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ሚናችን እንዲጨምር የሚያደርግ ነው ብለዋል።

የአገር እድገትን እና የህዝብ ጥቅም የሚረጋገጠው አገራዊ ሰላም ሲሰፍን ፣ ህግና ስርዓት ሲከበር ነው ያሉት የገንዘብ ሚንስትሩ አህመድ ሽዴ የተገባበትን ሪፎርም ለመተግበርም የጋራ ሀላፊነትን የሚጠይቅ ነውና መከላከያ እንደተቋም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙን አበይት ፋይዳዎች እና ተያያዥ ነጥቦች ያብራሩ ሲሆኑ ማሻሻያው ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በምዕራፍ ተከፍሎ ሲተገበር እንደቆየና አሁን ላይ ደግሞ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር የአገራችንን ብሄራዊ ጥቅም የሚያስከብሩ ድርድሮችንና ምክክሮችን በማድረግ በሙሉ አቅም ለመተግበር የተሳካ የትብብር ማዕቀፍ እንደተመሰረተ ተናግረዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙን በሙሉ አቅም መተግበር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ባለፉት ሳምንታት የሚያበረታታ ጅማሮ ላይ መሆኑን በማሳያዎች ያመላከቱት ዶክተር እዮብ ተካልኝ በቀጣይም የውጭ ምንዛሬ ፖሊሲን በማስተካከልና በገበያ የሚመራ አስተዳደር በመመስረት እና በመዘርጋት ብሎም የብሄራዊ ባንክን የመቆጣጠርና የማስፈፀም አቅምን በማጎልበት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

በውይይቱ ላይ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሀመድ ፣ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰን ጨምሮ መላው የመከላከያ ከፍተኛ ወታደራዊ መሪዎች የተሳተፉ ሲሆን የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ወቅታዊና ተቀባይነት ያለው በመሆኑ ለተግባራዊነቱ ሁሉም የመከላከያ ሰራዊት የበኩሉን እንደሚወጣ አረጋግጠዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

News Alert ‼️

ከእነ ደብረፅዮን ቡድን ጀርባ ማን አለ?

በእነ ዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው ቡድን የተምቤን፣ አድዋ እና ሀውዜን አካባቢ ተወላጆች የሆኑ እና 15 ሽህ የሚሆን ታጣቂ ኃይሎችን በማሰባሰብ ተንቤን እና ሀውዜን መካከል አስፍሯል። የእነ ደብረፅዮን ቡድን የእንደርታ፣ ጨርጨር፣ መሆኒ፣ ራያ አላማጣ እና ደቡባዊ ትግራይ ተወላጆች የእነ አቶ ጌታቸው ረዳ ደጋፊዎች ናቸው በሚል ቀኑ ባልተገለፀ ምሽት ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመፈፀም ሊጨርሳቸው መሆኑ ታውቋል። የእነ ደብረፅዮን ቡድን በዚህ ዙር በማዕከላዊ እና ደቡባዊ ትግራይ ተወላጆችን ኢላማ በማድረግ ድንገተኛ ጥቃት ለመፈፀም ዝግጅቱን በመጨረሱ ጠቅላላ ጉባኤውን በድፍረት ማድረጉ ከውስጥ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

special news

#TPLF : የህወሓት ጉባኤ የተመለከተ አሁናዊ መረጃ፦

ደብረፅዮን እና ጢቂት ቡድኖች የሚሄዱት አካሄድ ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠመው ቢሆንም ለግል ስልጣን ጥማት ሲሉ የትግራይን ህዝብ ዳግም ወደአላስፈላጊ መንገድ እየወሰዱት ነው። መንግስትን እየተፈታተኑት ይገኛሉ። ይዋጣልን እያሉ ነው። ይህን የአጥፊውን ቡድን አካሄድ የተረዱ አካላት አቋማቸውን እያንፀባረቁ ነው።
1) በርካታ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በግልፅ ጉባኤው መካሄድ እንደሌለበት አቋማቸቅን አንፀባርቀዋል።

2) የድርጅቱ ማእከላዊ ቁጥጥር ኮሚሽን በይፋ ከሂደቱ እራሱን አግልሏል።

3) በርካታ ከፍተኛ፣ መካከለኛና ዝቅተኛ አመራር እራሳቸውን ከጉባኤው አግልለዋል።

4) ነባር እና ተተኪ የማእከላዊ ኮሚቴ ካውንስል በግልፅ ተቃውመዋል።

5) ደቡባዊ ዞን ሙሉ በሙሉ፣ ደቡብ ምስራቅ 12 ወረዳዎች ፣መቀሌ ከተማ አስተዳደር 5 ክፍለ ከተሞች እንዲሁም በሌሎች ዞኖች የሚገኙ አንዳንድ ወረዳዎችና ቀበሌዎች አልተወከሉም።

6) በጉባኤ ለመሳተፍ የተመረጡ የተለያዩ ከተሞችና ወረዳዎች ተወካዮች አንሳተፍም በማለት ቀርተዋል።

7) ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያልተገኘበትና እውቅና የለውም ብሎ መግለጫ አውጥቷል።

8) ህወሓት ህገመንግስቱና ህገመንግስታዊ ስርአቱ፣ የፌዴራል ተቋማት እንዲሁም የፕሪቶርያው ስምምነት እንዲያከብር በፌዴራል መንግስት ጥሪ አስተላልፏል። ይህ የማይሆን ከሆነ ተገዶ ወደ ማይፈልገው እርምጃ ሊገባ እንደሚችል ከዚህ ቀደምም አመላክቷል።

8) በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የስቪክ፣ የሃይማኖትና የቢዝነስ ተቋማት ያላቸውን ተቃውሞ በግልፅ አመላክተዋል።

9) በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የትግራይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ትክክል አለመሆኑን እየገለፁ ነው።

10) በውጭ ሀገራት የሚንቀሳቀሱ ስቪክ ማህበራት ማሳሰቢያ ሰጥተዋል። በአጠቃላይ የተለያዩ የትግራይ ማህረሰብ አካላት ምክረ-ሐሳብ የሰጡበት ሲሆን በጎሳ እና በትውልድ አካባቢ የተቧደነው የነ ዶ/ር ደብረፅዮን ቡድን ይህን ሁሉ የትግራይ ህዝብ ተቃውሞ ችላ በማለት እንዋጣልን እያለ ነው። መላው የትግራይ ህዝብ ይህን ሊያውቅ ይገባል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

አወዛጋቢው የህውሓት ድርጅታዊ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ ፡፡

በአወዛጋቢ ሂደቶች የተሞላው የህወሃት ድርጅታዊ ጉባኤ በመቀሌ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በሊቀመንበሩ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል(ዶ/ር) የሚመራው ቡድንም ጉባኤውን በመቀሌ ሰማእታት የሃወልት አዳራሽ „ ጉባኤ ድሕነት  የመዳን ጉባኤ „ በሚል መሪ ቃል መክፈቻውን እያካሄደ ይገኛል፡፡

ጉባኤው ከዚህ ቀደም በወጣለት መርሀ ግብር መሰረት ከነሀሴ 7 – 12 2016 ዓ.ም እንደሚቆይ ነው የተነገረው።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ እና ሌሎች በርካታ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በተለያዩ ምክንያቶች ከጉባኤው እራሳቸውን ማግለላቸው  ይታወሳል፡፡

የጉባኤውን መከናወን ሲያወግዙ የቆዩት  አቶ ጌታቸው ረዳ ከደቂቃዎች በፊት ባወጡት መግለጫ ጉባኤው „ በችኮላና የጋራ መግባባት ሳይደረስበት ፤ በማደናገርና በአቋም አልባነት አሰባስበናቸዋል በሚሉት ኔትወርክ  ‚ ይቃወሙናል ‚ የሚሉዋቸው የተወሰኑ አመራሮች ለማስወገድ በማለም የሚካሄድ ጉባኤ ነው „ ብለውታል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለህውሀት በጻፈው ደብዳቤ በፓርቲው መተግበር ካለባቸው ተግባራት መካከል ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ከማድረጉ ከ21 ቀን በፊት ለቦርዱ ማሳወቅና ፖርቲው በሚያደርገው ጠቅላላ ጉባኤ የቦርዱ ታዛቢዎች መገኘት በዋናነት የተገለፁ ግዴታዎች አለሟሟላቱን ተከትሎ ለጉባኤው እውቅና እንደማይሰጥ አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከሳምንታት በፊት ህወሃት ከምርጫ ቦርድ እውቅና ሳያገኝ ጉባኤው የሚያከናውን ከሆነ  ክልሉን ወደ አላስፈላጊ ግጭት ዳግም ይከተዋል ሲሉ ማሳሰባቸው አይዘነጋም፡፡

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በአንካራ በሶማሊያ እና ኢትዮጵያ መካከል በመካሄድ ላይ ያለው ቀጥታዊ ያልሆነ ውይይት ዛሬም መቀጠሉ ተገለጸ!

በአንካራ በሶማሊያ እና ኢትዮጵያ መካከል በመካሄድ ላይ ያለው ውይይት ዛሬ ነሃሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም እንደቀጠለ መሆኑ ተገለጸ፣ የሁለቱም ሀገራት ተወካዮች ፊት ለፊት ተገናኝተው አለምምከራቸውም ተጠቁሟል።በትላንትናው ዕለት ነሃሴ 6 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሁለቱ ሃገራት መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ለመፍታት ያለመ ሁለተኛ ዙር ንግግር በቱርክዬ አንካራ መጀመራቸው ይታወቃል።

የሁለቱም ሀገራት ተወካዮች ፊት ለፊት ሳይገናኙ በቱርክዬ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን አስተባባሪነት ውይይታቸውን እያካሄዱ እንደሚገኙ የቱርክ የዜና ወኪል አናዶሉ በዘገባው አስታውቋል።

የቱርኩ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሁለቱንም ተደራዳሪዎች በተናጠል በማወያየት ልዩነቶቻቸውን እንዲያጠቡ ጥረት እያደረጉ ነው ሲል ዘገባው ጠቁሟል፤ ትላንት ነሃሴ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ሃካን ፊዳን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታየ አቅፀስላሴ እና ከሶማሊያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አህመድ ሞአሊም ፈቂ ጋር መምከራቸውን ዘገባው አመላክቷል።ከሩሲያ ቱዴይ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ነብዩ ተድላ ውይይቱ መልካም ነገር ይዞ ይመጣል ብለው እንደሚጠብቁ ገልጸዋል፤ ቱርክየ እየተጫወተች ያለው ዲፕሎማሲያዊ ሚናን አወድሰዋል።

የቱርክዬ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶሃን ከኢትዮጵያ ጨ/ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) እና ከሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሸክ ጋር በስልክ መወያየታቸው መዘገቡ ይታወሳል።የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን ነሐሴ 4 ቀን ከጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አህመድ (ዶ.ር) ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ቀጣናዊ ትብብርን ለማጠናከር እና ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር የገባችበትን ውዝግብ በሰለማዊ መንገድ ለመፍታት መምከራቸው ተገልጿል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ሳር ቤት ላይ ባለ 3 መኝታ በ8.9 ሚሊዮን ብር ብቻ

156 ካሬ

በካሬ 57,000 ብር

ለ 10 ቀን ብቻ የሚቆይ

ድጋሚ የማያገኙት ዕድል!

ለበለጠ መረጃ፦ በ 0983638578 ይደውሉ

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

#TPLF : የህወሓት የፅህፈት ቤት ሃላፊና የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ብሔር  የህወሓት ማእከላዊ  የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት በጉባኤ እንዲሳተፉ በፃፉት ደብዳቤ “ 14ኛው የህወሓት ጉባኤ ነሃሴ 7/2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 3:00  ጀምሮ በመቐለ የሰማእታት ሓወልት አዳራሽ ይካሄዳል “ ይላል።

ይሁን እንጂ የደርጅቱ ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ከ2 ሳምንት በፊት ከሚካሄደው ጉባኤ ራሱ ማግለሉ ይታወሳል።

የህወሓት ምክትል ሊቀ-መንበርና የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 14 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት “ ማንአለበኝነት የተጠናወተው ጠባብ ቡድን “ ያሉት አካል “ ጉባኤ ንድሕነት ! “  በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው ጉባኤ እንደማይሳተፉ አስታወቀዋል።

“ ጉባኤውን ተከትሎ ለሚመጣ ነገር እኛ የለንበትም “ ብለዋል።

አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣  ምክትል ሊቀ-መንበሩ የሚገኙባቸው 14 ፒቲሽን የፈረሙ የማእከላይ ኮሚቴ አባላት ጨምሮ በመስዋእት ፣ ከደርጅቱ በመልቀቅ ፣ በህመም እና በሌሎችም ምክንያቶች ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ጉባኤ በርካታ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት አይሳተፉም።

በርካታ የማእከላዊ ኮሚቴ ማለትም ከ50 በመቶ በላይ አለመሳተፍ ደግሞ የደርጅቱ ህልውና እጅጉ የሚጎዳ የሚሉ በርካታ አስተያየቶች በመንሸራሸር ላይ ናቸው።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

​የጄሲ ኦውንስ ታሪክ የሃገሩ አሜሪካን የዘረኝነት መንፈስ ቅጥ ያጣ እንደነበር በማጋለጥ ወሳኝ ሚና መጫወቱን ታሪክ ይነግረናል፡፡ እሱና ሌሎች አፍሪካ አሜሪካውያን ከኦሎምፒክ መልስ ወደሃገራቸው ሲመለሱ በቆዳ ቀለማቸው ምክንያት ብዙ መከራ ደርሶባቸዋል፡፡ ኦውንስ አራት የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያዎች አምጥቶ እንኳን በአውቶብስ ተሳፍሮ እንዳይሄድ ክልከላ ይደረግበት ነበር፡፡ ጥቁሩ ፈርጥ ከፍተኛ የገንዘብ ችግር ውስጥ በመውደቁም መረራር ህይወትን ለመግፋት ተገዷል፡፡ ከውድድር ፈረሶች ጋር የመፎካከር፣ የጋዝ ቀጂነት እና የውድድር ስፍራዎች የፅዳት ሰራተኝነት አይነት ሙያዎች ውስጥ ለመግባትም ተገዷል፡፡ ቀጣዩን የዩትዩብ ሊንክ ስትከፍቱም የናዚ ሰዎችን ከአሜሪካ ጋር ስላፋለመው ጥቁር አሜሪካዊ አሳዛኝ መጨረሻ ብዙ ሚስጥራትን ታደምጣላችሁ። እግረ መንገዳችሁን ቪዲዮውን ላይክ፣ ቻናሉን ሰብስክራይብ እንድታደርጉም በማክበር ተጋብዛችኋል፡፡
https://youtu.be/13TD3igQWRE?si=kW2rkvvZarZJn-KR

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የሲዳማ ክልል ፋይናንስ ቢሮ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማህበረሰብ ጋር በመተባበር ለውጥ ተኮር ስራዎችንን እየሰራ መሆኑ ተገለፀ።

በሲዳማ ክልል ከሚገኙ በርካታ የሲቪል ማህበረሰብ ጋር በመተባበር በክልል ማዕቀፍ በርካታ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን በዚህም ህዝቡን ተቃሚነትን የሚያረጋግጡ በርካታ ፕሮጀክቶች መሰራታቸውም ተገለፆል።

የሲዳማ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር አራርሶ ገረመው እንደገለፁት በቀድሞ ሲዳማ ዞን በነበረበት ወቅት የዞኑ በጀት 7.1 ቢሊዮን ዓመታዊ በጀት ያለው ሲሆን አሁን ግን ክልል ስንሆን ወደ 23 ቢሊዮን ከፍ አድርገን በርካታ ልማታዊ ስራዎች ላይ እየተሳተፍን እንገኛለን ሲሉ አሳውቀዋል።

በዚህ አመት ከዩኒሴፍ 1.2 ሚሊዮን ዶላር ወይንም 96 ሚሊዮን በ18 ወራት ተገንብቶ የሚያልቅ የሀዋሳ ከተማን እና 3 ወረዳዎችንን ተጠቃሚ የሚያደርግ ድጋፍ ያገኘን ሲሆን በዚህም የሀብት ምንጮችንን በልዩ ትኩረት በመፈለግ ብሎም በመጠቀም ክልላችንን ማልማትና የብልፅግና ጉዞ ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑንም ዶ/ር አራርሶ ገለፀዋል።

ዶ/ር አራርሶ አክለውም Sustainabel Development Goals (SDG) ከዚህ የሲቪል ተቋም ጋር አነስተኛ፣ መካከለኛ፣ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ ወደ 22 ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ወደ ስራ የገቡ ሲሆን ለህዝብም አገልግሎት እየሰጡ ነው ያሉት ሃላፊው በተጨማሪም ከSDG ቻናል 1, 2, 3, የሚገኘው ዓመታዊ የክልሉ በጀት 4 ቢሊዮን ሚጠጋ ሆኗል ብለዋል።

በቀጣይነትም ከGo-CSOs፣ ከUN OCHA፣ ከUNICEF፣ SDG ብለውም ከሌሎች ሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ጋር በመስራት የህዝባችንን የመልማት ፍላጎት ብቻ ሳይሆን “ውስን ሀብትን በጥበብና በእውቀት በመምራት ታሪካዊ አደራችንን መወጣት አለብንም ተብሏል”.

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

BREAKING NEWS : “ ህወሓትን ለማፍረስ አልሞ በሚካሄደው ጉባኤ አንሳተፍም “ ያሉት ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 14 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት “ ጉባኤውን ተከትሎ ለሚመጣው ነገር እኛ የለንበትም “ ብለዋል።

ጉባኤው “ በጥቂት ቡድኖች ማን አለበኝነት “ የተዘጋጀ ፦
- የጉባኤው ከፍተኛ ስልጣን ያለው የማእከላዊ ኮሚቴ አመራር ያልወሰነው
- የድርጅቱ የማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ውድቅ ያደረገው
- ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ መግባባት ያልተደረሰበትና
- ትግራይ ከጫፍ አስከ ጫፍ ያልተወከለበት፤ ነጻ ያልወጡ አካባቢዎች ባሉበት ነው ብለዋል።

“ ጉባኤው የጠባብ ቡድን ጥቅም ለማስከበር ብቻ ያለመ ነው ፤ እኛ ደግሞ በዚህ ላይ አንሳተፍም “ ሲሉ ገልጸዋል።

“ ህወሓትን እና የትግራይ ህዝብ ወደ ከፋ አደጋ የሚያጋልጥ ያልተረጋጋ ጉባኤ ማካሄድ የጠባብ ቡድኑ ጥቅምን ከማረጋገጥ ያለፈ እርባና የለውም “ ሲሉም ገልጸዋል።

14ቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት “ ህወሓትን እና የትግራይ ህዝብ ወደ ሌላ የተወሳሰበ ቀውስ በሚከት በጠባብ ቡድን የተዘጋጀው ጉባኤ አንሳተም “ ብለው “ ጉባኤውን ተከትሎ ለሚፈጠረው ማንኛውም ነገር ተጠያቂው ይኸው ቡድን መሆኑ እናስታውቃለን “ ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ያሉበት 14 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት “ ጠባብ ቡድን “ እያሉ የገለጻቸውን ጥቂት ቡድኖች በስም አልገለጿቸውም።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

መግለጫ

በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ የሐዋሳ ቅርንጫፍ በመደበኛው የፓይለት ስልጠና ልምምድ ላይ የነበረ ቀላል የተማሪዎች መለማመጃ አውሮፕላን (Dimond DA40NG) አየር ላይ ሳለ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ምክንያት አርሲ ነጌሌ አካባቢ ለማረፍ ተገድዷል። ይህንን ተከትሎ በመደበኛ ስልጠናው ላይ የነበሩት አስተማሪውና ተማሪው የመለማመጃ አውሮፕላኑ ሕብረተሰቡ ላይ አደጋ በማያደርስ ሁኔታ ለማሳረፍ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ ቢሆንም ለማረፍ በተደረገው ጥረት መሬት ላይ በነበረች አንዲት ታዳጊ ላይ ጉዳት ደርሷል።ለተፈጠረው ሁሉ እያዘንን ለታዳጊዋ ቤተሰቦች ፍፁም መፅናናትን እንመኛለን።

የአደጋው መንስኤ በሚመለከታቸው አካላት በመጣራት ላይ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርስቲ

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በ33ኛው የፓሪስ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች።

ዛሬ በተካሄደው የወንዶች የማራቶን ውድድር አትሌት ታምራት ቶላ 1ኛ በመውጣት ለሀገሩ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል።

ከ2 ዓመታት በፊት በአሜሪካ ኢዩጂን በተደረገው የዓለም ሻምፒዮና የርቀቱ አሸናፊ የነበረው ታምራት፤ ከ21 ኪሎ ሜትር ጀምሮ ውድድሩን በልዩነት እየመራ በማጠናቀቅ ነው የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት የሆነው።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች

ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተ‍እ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበ‍ኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።

ሚለየን ምንድነው?

የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ

🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።

🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።

🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።

🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።

🪄We Care

አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ

📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69

www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

"ስማችን እውነት ነው,ስራችንም የእውነት ነው"

❇️ከዚህ በፊት የተመረጡ ቦታዎች ላይ ጥንቅቅ አድርገን እንዳስረከብናቸው አሁንም እጅግ ውብ ለኑሮ መቹ በከተማችን የተመረጡ ቦታዎች

❇️በሳርቤት እና በ ቦሌ ቅድመ ክፋያ 770 ( ሰባትመቶ ሰባ ) ሽህ ጀምሮ በመሸጥ እንገኛለን

✅ 65.7 , 86 , 90 ካሬ ባለ 1 መኝታ
✅ 98 , 100 , 114 ካሬ ባለ 2 መኝታ
✅ 140 , 152 , 212 ካሬ ባለ 3 መኝታ

❇️የቤት ባለቤት ከመሆን ባለፈ፣በመሀል አዲስ አበባ የምንገነባቸው ቅነጡ ቤቶቻችን ኢንቨስተር ያደርጉታል !
✅ምስክሮቻችን ከዚህ በፊት ሰርተን ያስርከብናቸው ደንበኞቻችን::

❇️ወለል ውፍረት 25ሲ.ሜ ኮንክሪት አስላብ።
✅ከወለል ወለል እርዝማኔ 3.2 ሜትር
❇️የውጭ በሮቻችን 100ኪሎ የሚመዝኑ፣ከኮንክሪት እና ከብርት የሚስሩ፣ድመፁ የማያስተላልፍ ፣6 የተለያዩ ቦታዎች የሚቆልፍ።


✅Reality real estate✅
🚧 3B+G+17 አፓርታማ
🚘 sufficient parking space
🏋️gymnasium and spa
👉🏻17 th floor club house
👉🏻under ground water and backup generator

💰 10% ቅድመ ክፍያ

What makes Reality real estate different
- Affordable price
- Easy payment schedule
- Prime Location
- Reputed company
- Early Delivery
የድርጅቱ የሽያጭ አማካሪ
☎️0976 20 68 68
0951 69 14 66

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) የሕግ ሰውነት ጉዳይን

በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. በቁጥር 3944/ማኮ1/644 በተጻፈ ደብዳቤ የፓርቲው ሕጋዊ ሰውነት ወደነበረበት እንዲመለስ ጥያቄ አቅርቧል፡፡ ቦርዱም የቀረበለትን ጥያቄ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና ይህንኑ ዐዋጅ ከአሻሻለው ዐዋጅ ቁጥር 1332/2016 አንጻር መርምሮ የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥቷል፡፡

1. ፖርቲው ያቀረበውን የሕጋዊ ሰውነት ወደነበረበት የመመለስ ጥያቄን በተመለከተ ይኸው ጥያቄ ከዚሀ ቀደም ሚያዝያ 13 ቀን 2015 ዓ.ም. እና ሚያዝያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ለቦርድ ቀርቦ ቦርዱም ጥያቄውን መርምሮ በዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሠረት የቀድሞውን የፓርቲውን ሕልውና መመለስ የሚያስችል የሕግ ድንጋጌ የለም በማለት ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ.ም. ወሥኗል። ውሣኔውንም በወቅቱ አሳውቋል፡፡ በሌላ በኩል ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011ን ያሻሻለው ዐዋጅ ቁጥር 1332/2016 በዓመፅ ተግባር ተሠማርቶ ለተሠረዘ ፖርቲ የቀድሞውን ኅልውና መልሶ የሚሰጥ የሕግ ድንጋጌ ያልያዘ በመሆኑ ቦርዱ በድጋሚ የቀረበለትን ሕጋዊ ሰውነት ወደ'ነበረበት እንዲመለስ የሚለውን ጥያቄ አልተቀበለውም፡፡

2. በዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 ማሻሻያ ዐዋጅ ቁጥር 1332/2016 አንቀጽ 2 (1) አንድ የፖለቲካ ቡድን ኃይልን መሠረት ያደረገ የአመፅ ተግባር ላይ የተሣተፈ እንደሆነ እና ይህንን ተግባር ማቆሙን እና ሕገ-መንግሥታዊ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን አክብሮ ለመንቀሳቀስ መስማማቱን በሚመለከተው የመንግሥት አካል ከተረጋገጠ በልዩ ሁኔታ እንደ ፖለቲካ ፖርቲ ሊመዘገብ እንደሚችል ተደንግጓል፡፡ በዚሁ መሠረት የፍትሕ ሚኒስቴር በማሻሻያ ዐዋጅ ቁጥር 1332/2016 አንቀጽ 2 (1) መሠረት ሰኔ 17/2016 በቁጥር ፍሚ1/1345 ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጻፈው ደብዳቤ ሀ.ወ.ሓ.ት ኃይልን መሠረት ያደረገ የዐመፅ ተግባሩን በማቆም ሕገ-መንግሥታዊ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን አክብሮ ለመንቀሳቀስ የተስማማ መሆኑን በመጥቀስ በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፖርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ማሻሻያ ዐዋጅ ቁጥር 1332/2016 አንቀፅ 2 (1) መሠረት በልዩ ሁኔታ እንደ ፖለቲካ ፖርቲ እንዲመዘገብ ማረጋገጫ ለቦርዱ ሰጥቷል፡፡ በተጨማሪ ሀ.ወ.ሓ.ት ካቀረበው ማመልከቻ ጋር በተሻሻለው ዐዋጅ ቁጥር 1332/2016 አንቀፅ 2 (2) ላይ የተዘረዘሩት የፖለቲካ ፓርቲ ፕሮግራም፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ የፓርቲ ኃላፊዎች ስምና ፊርማ የያዘ ሠነድ አቅርቧል፡፡ በመሆኑም የፍትሕ ሚኒስቴር የሰጠውን ማረጋገጫ እና ሀ.ወ.ሓ.ት ያቀረባቸውን ከላይ የተገለጹትን ሠነዶች መሠረት በማድረግ ህ.ወ.ሓ.ት በልዩ ሁኔታ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ እንዲመዘገብ ቦርዱ ወሥኗል፡፡ የሚሰጠውም የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ በዐዋጅ ቁጥር 1332/2016 ላይ በተደነገገው መሠረት በልዩ ሁኔታ የሚል ቃል ያለበት ሆኖ እንዲዘጋጅ ቦርዱ ወሥኗል፡፡

3. ቦርዱም በዐዋጅ ቁጥር 1332/2016 አንቀጽ ሦስት መሠረት ይህ በልዩ ሁኔታ የመመዝገብ ውሣኔን የያዘው ደብዳቤ ለፓርቲው ከደረሰው ቀን ጀምሮ ባሉት ስድስት ወራቶች ውስጥ ፓርቲው የቦርዱ ታዛቢዎች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባዔ እንዲያደርግ፤ በዚህ ጉባዔም መተዳደሪያ ደንቡን እንዲያፀድቅ፣ አመራሮቹን እንዲያስመርጥ ቦርዱ ወሥኗል፡፡ የቅድመ ጉባዔ ዝግጅት የተመለከቱ ሥራዎችን ቦርዱ መከታተል እንዲችል ፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔ ከማድረጉ 21 ቀናት በፊት የጠቅላላ ጉባዔ የሚያደርግበትን ቀን ለቦርዱ ማሳወቅ አለበት፡፡

4. ጠቅላላ ጉባዔው በቦርዱ ከፀደቀ በኋላ ባሉት የአንድ ዓመት ከስድስት ወራት ውስጥ ፖርቲው ሰላማዊ እንቅስቃሴ እያደረገ ስለመሆን አለመሆኑ በዐዋጅ ቁጥር 1332/2016 አንቀጽ 3 መሠረት ክትትል የሚያደርግ መሆኑ ቦርዱ ወሥኗል፡፡

5. በመጨረሻም ቦርዱ የሰጠውን ውሣኔ የሚገልፅ ሁለት ገጽ በቀን ነሐሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. በቁጥር አ1162/11/15180 የተጻፈ ደብዳቤና በልዩ ሁኔታ እንደ ፖለቲካ ፖርቲ ስለመመዝገቡ የተሰጠው የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ለህ.ወ.ሓ.ት እንዲደርሰው ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

አዲስ አበባ

ነሐሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም.

Читать полностью…
Subscribe to a channel