natnaelmekonnen21 | Unsorted

Telegram-канал natnaelmekonnen21 - Natnael Mekonnen

169400

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7 Facebook.com/natnaelmekonnen.et Instagram.com/natnaelmekonnen21

Subscribe to a channel

Natnael Mekonnen

መከላከያ በሮቹን ከፍቶ ሲያስገባቸው፦ ለምን በሩ ተከፈተ ብለዉ የማያስቡ ከፉከራ ዉጪ ቅንጣት የወታደራዊ ጥበብ የሌላቸው የጫካ ታጣቂዎች ናቸው ያሉት። ወታደሩ ወደኋላ የተሳበው መከላከያን በግንባር ሰለማይገጥሙት ወደፊት ለፊት እንዲመጡ የተጠቀመባቸዉ ወታደራዊ ጥበብ ነው። Finally፦ ድል አብሳሪዎቹ ወደ መርዶ ነጋሪነት ተቀይረዋል። ;)

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) በአደረባቸው ህመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ጳጉሜን 4 ቀን 2012 ዓ.ም የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሹመው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት በፖለቲካ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ከቆዩ አንጋፋ ሰዎች መካከል አንዱ መሆናቸው የሚነገርላቸው በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር)÷ የተፎካካሪ ፓርቲው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀ-መንበር ሆነው ማገልገላቸው ይታወቃል፡፡
የተለያዩ ፓርቲዎችን በአባልነት የያዘውን የመድረክ ፓርቲንም በሊቀ-መንበርነት የመሩ ሲሆን÷ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም በመምህርነት እንዲሁም በትምህርት ሚኒስትር ዴዔታነት ማገልገላቸው የሚታወስ ነው፡፡

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

“ከጦርነቱ በኃላ የህወሓት ደጋፊነቴን ትቻለሁ “ አሉላ ሰለሞን

“ጦርነት ባህላዊ ጨዋታችን ነው” አሉላ ሰለሞን ከጦርነቱ በፊት

እርግጥ ነው በትግራይ ጆኖሳይድ አለመጸሙን እኛ ከተናገርነው በላይ የህወሓቱ ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል ከማራማዊት ጋር ባደረገው ቆይታ ግልጽ አድርጎልናል:: እንደው በትግራይ ጆኖሳይድ ተፈጽሟል እንኳን ቢባል ፈጻሚውና ሃላፊነቱን የሚወስደው እንደነ አሉላ ሰለሞን የመሰሉ በሎም እያሉ ውጪ ተቀምጠው ወጣቱን ያስፈጁት ስለመሆናቸው መናገር ተመራማሪና ፖለቲካ አዋቂ መሆን አያስፈልግም::

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በ5 ሺህ የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት በቤልጂየም ብራሰልስ በተካሄደው የ2024 ዳያመንድ ሊግ 5 ሺህ የወንዶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ በመያዝ ተከታትለው ገብተዋል።

በውድድሩ አትሌት በሪሁ አረጋዊ 12:43.66 በሆነ ሰዓት በመግባት በውድድሩ ቀዳሚ ሆኖ አጠናቋል።

አትሌት በሪሁ አረጋዊን በመከተል ሀጎስ ገብረህይወት 12:44.25 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ እንዲሁም ጥላሁን በቀለ 12:45.63 በሆነ ሰዓት በመግባት ሶስተኛ ደረጃ ይዘው በመግባት ውድድሩ ላይ ደምቀው ታይተዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች

ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተ‍እ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበ‍ኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።

ሚለየን ምንድነው?

የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ

🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።

🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።

🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።

🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።

🪄We Care

አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ

📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69

www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ያለፈው አመት እንደ አየር ሃይል በርካታ ሥራዎች በስኬት ተከናውነዋል።

የአየር ኃይል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ያሳለፍነው ዓመት እንደ ሀገር ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገብንበት ከነዚህም የታላቁ ህዳሴ ግድባችን ወደ ተሟላ የኃይል ማመንጨት ብስራት በአረንጓዴ አሻራ ልማት በምግብ ራስን የመቻል ስኬትን ጨምሮ በማክሮ ኢኮኖሚ ፓሊሲ ወደ አለም የፋይናንስ ስርዓት የገባንበት ልዩ ዓመት ነው ሲሉ ገልፀዋል።

በሰው ኃይል ግንባታ በስልጠና አቅም በዘመናዊ የአቭዬሽን ትጥቆች እና ከሀገር ውስጥም አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃም አድናቆትን ያተረፈው የምስረታ በአላችን በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ አየር ኃይል የድል አመት መሆኑንም ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ተናግረዋል።

በአዲሱም ዓመት የኢትዮጵያ አየር ኃይል በላቀ የወትሮ ዝግጁነት አቅም ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የጠቆሙት ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ የሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም ለመጉዳት የሚንቀሳቀሱ ታሪካዊ ጠላቶቻችንና ተባባሪ የውስጥ ባንዳዎች ፍላጎታቸው መቼም እንደማይሳካ ተረድተው ከድርጊታቸው እንዲታቀቡም አሳስበዋል።

በዕለቱ ለሚዲያ ሙያተኞች እንዲሁም ለኤር ፖሊስ የጥበቃ አባላት ፈጣን የማዕረግ ዕድገት በሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ አማካኝነት ሽልማት የተሰጠ ሲሆን ምክትል አዛዥ ለአየር ኃይል አካዳሚም አነስተኛ ገቢ ለሚያገኙ አቅመ ደካሞች ልዩ የበዓል ስጦታ አበርክቷል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች

ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተ‍እ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበ‍ኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።

ሚለየን ምንድነው?

የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ

🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።

🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።

🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።

🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።

🪄We Care

አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ

📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69

www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

Breaking : Ethiopian Army Chief of Staff declares Egypt a historical enemy of Ethiopia.

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የሉዓላዊነት ቀን በኮምቦልቻ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው

ሰላም ለሕዝባችን!
ትልማ ኢትዮጵያችን!

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የኦቪድ ግሩፕ ስራ አስፈፃሚ አቶ ዮናስ ታደሰ ለአዋሬ መንደር በአይን የሚታይ አስደናቂ ለዉጥ አሻራህን አኖረሃልና ምስጋና እውቅና ይገባሃል::

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች

ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተ‍እ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበ‍ኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።

ሚለየን ምንድነው?

የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ

🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።

🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።

🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።

🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።

🪄We Care

አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ

📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69

www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ከዚህ ቀደም ብየዋለሁ አሁንም ልድገመው::

የፖለቲካ ጫማዬን የምሰቅለው ቀይ ባህር ላይ ነው‼️

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

እንደ ትላንቱ ዛሬም የሀገራችን ዳር ድንበር እንዳይደፈር ከጀግናው ሠራዊታችን ጋር ሆነን የሚጠበቅብንን ሁሉ እናደርጋለን ፦አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ

"ከራስ በፊት ለሀገርና ለህዝብ" በሚል እሴቱ በሚታወቀው ሰራዊታችን እንኮራለን ሲሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ሙሁመድ ተናግረዋል።

ርዕሰ-መስተዳድሩ በጅግጅጋ ከተማ እየተከበረ በሚገኘው የምስራቅ ዕዝ 47ተኛ የምስረታ በዓል ላይ ተገኝተው እንዳሉት፦

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል አጋጥሞ በነበረ ግጭት ምቹ አጋጣሚ የተፈጠረለት የመሰለው አልሸባብ ጀምሮት የነበረውን ጥቃት ከህዝብ ወጥቶ ለህዝብ ሰላም ከቆመው ሰራዊት ጋር በመሆን ማምከን ተችሏል።

የምስራቅ ዕዝ ለክልላችን ሰላም የተጫወተው ሚና የሚዘነጋ አይደለም ያሉት ሙስጠፋ ሙሁመድ የሶማሌ ክልል ህዝብ እንደ ትላንቱ ሁሉ ዛሬም ከጀግናው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጎን እንደሚቆም አረጋግጣለሁ ብለዋል።

ከፖለቲካ ወገንተኝነት የጸዳ፣የማድረግ አቅሙ ከፍ ያለ ፕሮፌሽናል ሰራዊት እየተገነባ በመሆኑ ለዚህ አድናቆት እንዳላቸውም ርዕሰ-መስተዳድሩ ተናግረዋል።

በጅግጅጋ እየተከናወነ የሚገኘው የምስራቅ ዕዝ 47ኛ ዓመት ክብረበዓል በዛሬው ዕለት የሚጠናቀቅ ሲሆን አከባበሩ በሀረር ከተማ እንደሚቀጥልም ታውቋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የኢትዮጵያ አየር ሀይል የምስራቁን የአየር ክልል በንቃት እየጠበቀ እንደሚገኝ አስታወቀ።

- የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ደግሞ የምስራቅ ዕዝ በተሟላ ወታደራዊ ዝግጁነት ላይ ይገኛል ብሏል።

ከሰሞኑ ግብፅ እና ሶማልያ በቀጠናው እያረጉት ያለውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር ሀይል የምስራቁን የአየር ክልል በንቃት እየጠበቀ እንደሚገኝ አስታውቋል።

በኢትዮጵያ አየር ሃይል የ3ኛው አየር ምድብ የተሰጠውን ሃገራዊ ግዳጅና ተልዕኮ ለመወጣት በላቀ የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የአየር ምድቡ አዛዥ ኮሎኔል ደረጀ ቡሽሬ ገልፀዋል፡፡

አዛዡ የ3ኛው አየር ምድብ የሃገራችንን ብሎም የምስራቁን የአየር ክልል በንቃት እየጠበቀ የሚገኝ የሃገር መከታና መመኪያ የሆነ ምድብ ነው ያሉ ሲሆን "ወደፊትም ኢትዮጵያን ከውስጥም ይሁን ከውጭ ፀረ ሰላም ኃይሎች ለመጠበቅ በላቀ የዝግጁት ደረጃ ላይ ይገኛል" ብለዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የምስራቅ ዕዝ በተሟላ ወታደራዊ ዝግጁነት ላይ ይገኛል ብሏል።

"በተለያዩ ዘመናት ሀገራችንን ለመውረርና የሽብር ጥቃት ለመፈፀም የሚሞክሩ ሀይሎችን በመከላከል በመስዋዕትነት የተረከቡትን አደራ ለማስቀጠል እስከ ህይወት መስዋዕትነት ለመክፈል በተሟላ የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛሉ" ሲል መከላከያ አሳውቋል።
መረጃው ከሀገር መከላከያ ገፅ የተገኘ ነው

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ጀኔራል አበባው ታደሰ 47ኛውን የምስራቅ ዕዝ በዓል ለመታደም ጅጅጋ ገቡ።

የጦር ሀይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ 47ኛውን የምስራቅ ዕዝ የምስረታ ክብረ በዓል ለመታደም ጅግጅጋ ገብተዋል።

በአቀባበል ስነ-ስርዓቱ ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር ሙስጠፌ መሀመድን ጨምሮ ከፍተኛ የሠራዊቱና የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል።

በዕዙ 47ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓል ላይ ለመታደም ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል አመራሮች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ከሀሰተኛ መረጃው ጀርባ….!

የሶማሊ ማህበረሰብ ኃይማኖቱን አክባሪ፣ ለሀገር ሽማግሌ፤ ለጋራድ፣ ሱልጣን እና ኡጋዝ እሺ ብሎ መታዘዝን የሚያውቅ፣ከባህላዊ ጎሳ መሪ የሚሰጥ ትዕዛዝን በመቀበል በጋራ እና በአንድነት መኖር ትልቅ ዕሴቱ ነው፡፡

በመሬት ወሰን የተጋጨም ሆነ በድንገተኛ ጸብ የተጣላ ፣ በጎሳ የመሬት አከላለም ሆነ በግጦሽ መሬት ነፍስ የተጣፋ፣ በድንገተኛ ጸብም ይሁን ሆን ብሎ አደጋ ያደረሰ፣ እንዲሁም ለኒካህ (ጋብቻ) የሚሰጥ ጥሎሽን በተመለከተ በጎሳ መሪ፣ በሀገር ሽማግሌ የተወሰነን የሚያከብር ለቃላቸውም የሚገዛ ማህበረሰብ እንደሆነም ይታወቃል፡፡

በትላንትናው ዕለትም የሀገር ሽማግሌዎች፣ ገራዶች፣ ሱልጣኖች በጋራ ስብሰባ በማካሄድ በሶስት ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ የውይይታቸው ሶስት ዋና ነጥቦች፡-

1.የኒካህ (ጋብቻ) ጥሎሽ መቀነስን በተመለከተ፤ ልጆቻችን ለጥሎሽ የሚጠየቁት ዋጋ ከፍተኛ መሆን ወዳልተገባና አላህ ወደ ማይወደው የዝሙት ሊያመራ ስለሚችል ለኒካህ(ጋብቻ) የሚሰጥ ክፍያን መወሰን፤

2.የሰው ህይወት በድንገተኛ ሁኔታ ( በመኪና አደጋና በመሳሰሉት) ያጠፋ ሰው ለቀብር ተብሎ የሚጠየቀው ክፍያን በተመለከተ ገደብ ማስቀመጥ፤

3.በጎሳዎች መካካል በሚፈጠሩ ግጭቶች የሚከሰቱ ጉዳቶች የካሳ አከፋፋል ምን መሆን አለበት በሚሉ ነጥቦች ላይ በመምከር ውሳኔዎችን አሳልፈዋል፡፡

ነገር ግን ይህን እውነታ ሽምጥጥ አድርጎ በመካድ ጦርነት፣ እልቂት፣ ድርቅና ችግር መርዶ እንጂ የሰላም ዜና የሚያሳምማቸው አንዳንድ ትላንትን ናፋቂ የሆኑ የማህበራዊ ሚዲያዎች “በሶማሊ ክልል አንድ ዞን በሼሪአ እንዲተዳደር ተደረገ” በሚል በማህበራዊ ሚዲያ ሀሰተኛ መረጃ ሲያሰራጩ ለመመልከት ተችሏል፡፡

ከለውጡ በኋላ ባሉ ዓመታት እስካሁን ድረስ በክልሉ ላይ ሆን ተብሎ የህዝቡን አንድነትና እድገቱን ለማሰናከል ያልተፈነቀለ ድንጋይ፣ ያልተሞከረ ሴራ፣ ያልታቀደ ተንኮል ባይኖርም ዛሬም በከፍታ እንደምትታይና ለአካባቢ ሁሉ ብርሃን እንደምትሰጥ ኮከብ ይበልጥ ማንጸባረቅና ማብራቱን የቀጠለው የሶማሌ ህዝብ ይህንንም እንደሌሎቹ ታዝቧል፡፡

በዛሬው ዕለትም “ሼሪዓ መንግስት ተመሰረተ” በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛና በሬ ወለደ ብቻ ሳይሆን ኢስላም ጠል አላማ ያነገበ ለዘመናት በሶማሊ ማህበረሰብ ላይ ሲሰራጭ የነበረው ትርክት አንድ ማሳያ ብቻ ሳይሆን ከሀሰተኛ መረጃው ጀርባ ያለውን ግብም ያመላከተ ነው፡፡

ትላንት የሶማሊ ህዝብ ሲገድልና ሲጨፈጭፍ ከነበረ ሃይል ጎን ተሰልፈው የነበሩ እነኚህ አካላት በህዝቡ ሞትና እልቂት ከማዘን ይልቅ ለፍርፋሪ ብለው ህዝቡን ‘አሸባሪና ተገንጣይ’ ሲሉ ስም እንደሰጡት ሁሉ ዛሬ ባይሳካላቸውም በተደጋጋሚ ከሚነዙት ሽብር በተጨማሪ ‘ሸሪዓ ተመሰረተ’ የሚል ካባ ለብሰው መምጣታቸው ዓላማቸውን ይበልጥ ግልፅ ያደረገ ነው፡፡

የሶማሊ ክልል ህዝብን ከሌላው ክልል ህዝብ ጋር የመነጠል ግብን በመያዝ በተከታታይ የሀሰት መረጃዎችን ከሚያሰራጩ ጭር ሲል አልወድም የሆኑ የማህበራዊ ሚዲያዎች መካከል ይህ ዓይነቱን አጀንዳ ተቀብለው የሶማሌ ክልል ማህበረሰብ ትልቅ እሴት የሆነውን የሀገር ሽማግሌና የጎሳ መሪዎችን በመንካትና ያልተባለ በማራገብ መርዛቸውን ሲረጩ ተስተውሏል፡፡

በዚህ አጋጣሚ የሀገር ሽማግሌዎቹና የጎሳ መሪዎቹ የውይይት ዓለማ ህዝብን በሚጠቅሙ ከላይ በተነሱ ባህላዊ የእርቅ መፍቻ መንገዶች ላይ ያተኮሩ ሲሆን ይህን በካደ መልኩ ያልተባለ ተባለ በሚል በሀሰት የሚነዛው ፍጹም ሀሰት ብቻም ሳይሆን ይህ አይነቱ ሴራ ያገኘውንና ያተረፈውን ጠንቅቆ የሚያውቀው የሶማሊ ህዝብን፣የሚከበሩ የጎሳ መሪዎቹንም ሆነ የሀገር ሽማግሌዎቹን የማይወከል መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የሶማሊ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች መጋዣ ሁኖ የሚያገለግለዉ ጽንፈኛ ቡድን መጨረሻዉ የደረሰ ይመስላል፤

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው ፅንፈኛ፣ ዘራፊና የውጭ ታሪካዊ ጠላቶቻችን መጋዣ በመሆን የሚያገለግለዉ ቅጥረኛ ቡድን እስከዛሬ ድረስ ወደ ሠላማዊ መንገድ ይመለሳል ተብሎ በሠላም ጥሪና በሽምግልናም ሆነ በድርድር ጥረት ቢደረግም ውስጣዊና ውጫዊ ጠላቶቻችንን በመተማመን ወደ ሠላም መንገድ መምጣት አልቻለም።

የሠላም በሮችን ዘግቶ ህዝባችን እያሰቃየ ህሙማን ወደ ሆስፒታል እንዳይሄዱ፣ ነጋዴው ተንቀሳቅሶና ነግዶ እንዳያተርፍ በማድረግ ነዋሪዎች በኑሮ ውድነት እንዲሰቃዩ፣ ተማሪዎች ትምህርት ቤት እንዳይገቡ፣ ማዳበሪያ ለአርሶአደር እንዳይደርስ በማድረግ የአማራ ህዝብ ላይ ጥቁር መጋረጃ ከልሎበት አንድ አመት አሳልፏል። በዚህ እኩይ ተግባር የተሰቃየዉ ህዝብም የመንግስትን እርምጃ እየተጠባበቀ እና እየጠየቀ ይገኛል።

መንግስትም ለሰላም ካለዉ ቁርጨኝነት የመነጨ ከዛሬ ነገ በሠላማዊ መንገድ ይፈታል ብሎ በአነስተኛ ቁጥር ባለው የሠራዊት ኃይል በማጥቃት በሙሉ አቅሙ ወደ ኦፕሬሽን ሳይገባ ቆይቷል።

ፅንፈኛ፣ ዘራፊውና የታሪካዊ ጠላታችን ተላላኪው ቡድን ግን በባንዳነቱ ቀጥሎ ክልሉን እየጎዳ በመሆኑ የማያዳግም እርምጃ በጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን ሊወሰድበት እንደሆነ መረጃዎች ደርሰውናል።

አንበሳው የመከላከያ ሠራዊታችን በተለመደው ባንዳንና ተላላኪን የመጥረግ ልምዱ እርምጃ ሲወስድ ተባባሪ የሚሆኑ፣ መረጃ የሚያሾልኩ፣ ግብአትና ቁሳቁስ የሚሠጡ ወዘተ. ኃይሎች ከፅንፈኛውና ዘራፊ ቡድኑ ተለይተው እንደማይታዩና እርምጃ እንደሚወሰድባቸው መረጃው ደርሶናል። መጠንቀቅ ይበጃል ለባንዳና ተላላኪ መወገን እርምጃው ከባድ ነው።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በትግራይ #ሽሬ የነበረው ስብሰባ ተቋረጠ‼️

ለዛሬ ቀጠሮ ተይዞ የነበረው የሽሬ  መድረክ  ተበተነ‼️ ጄኔራል ፃድቃን ወደ አዳራሹ ከገቡ በኋላ የአዳራሹ ድባብ ጥሩ መስሎ ያልታያቸቸው ጀጀራል ፃድቃን አዳራሹን ለቀው የወጡት ከሌሎቹ ግዚያዊ አስተዳደሮች ቀደም ብሎ እንደሆነ ተነግሯል።

ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር  አዳራሹ ውስጥ የቆዩት ሹማምንት ስብሰባውን መቀጠል እንደማይችሉ ተረድተው ለሌላ ቀን ቀጠሮ በመያዝ አዳራሹን ለቀው እንዲወጡ የተገደዱት ከተሰብሳቢዎቹ መካከል አንዲት ሴትዎ ወንበር አንስታ እነሱ ወደ ተቀመጡበት አቅጣጫ ለመወርወር ስትገለገል ታይታለች::

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ዶ/ር አሸብርን ጨምሮ የ #ኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮች በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ክስ ተመሰረተባቸው

የ #ኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ አራት አመራሮች በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ሌሎች ተያያዝ ጉዳዮች ክስ ተመሰረተባቸው።

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፤ ዐቃቤ ነዋይዋ ዶ/ር ኤደን አሸናፊ፣ ዋና ፀሐፊ አቶ ዳዊት አስፋው እና ምክትል ፀሐፊ አቶ ገዛኸኝ ወልዴም ከተከሳሾቹ መካከል ነው።

ክሱን የመሰረቱት ሻለቃ አትሌት #ኃይሌ_ገብረሥላሴ፣ አትሌት #ገዛኸኝ_አበራ፣ የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ ቴኒስ ፌዴሬሽን ናቸው።

በከሳሾቹ ጠበቆች በኩል ክሱ የቀረበለት የፌደራል አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት አራድ ምድብ ችሎት ኮሚቴው፤ ግንቦት 5 እና ሰኔ 4፤ 2016 ዓ.ም. ያካሄዳቸው ጠቅላላ ጉባኤዎች እና ውሳኔዎች እንዲታገዱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

የከሳሽ ጠበቃ የሆኑት አቶ አያሌው ቢታኔ “ከፓሪስ ኦሊምፒክ ጋር በተያያዘ [ተከሳሾቹ] ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ ተሰማርተዋል ብለን እንጠረጥራለን። የወንጀል ተጠያቂነቱ እንዳለ ሆኖ ሥልጣናቸውን ያለ አግባብ በመጠቀም ኦሊምፒክ ኮሚቴውን [በዝብዘዋል]” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ጠበቃው አክለው “ደብዳቤ ስለተጻፈ ብቻ የማይመለከተው ሰው [ወደ ፓሪስ] ይሄድ ነበር” ብለዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ወደቅኩኝ አትበል ምንድነው መውደቅ
ተነሳ እንደገና ደጋግመህ ዉደቅ
ዛሬ ላይ ነው እንጂ የሚጨንቅህ
እመነኝ ነገማ ድል አለልህ
አይችልም ይሉሃል ያጣጥሉሃል
ሞራልህን ሰብረው ታች ይጥሉሃል
ጠንክረህ በርትተህ ስታሳያቸው
ሰማይ ይሰቅሉሃል ሰላም በላቸው
አንተ ልዩ ሰው አይዞህ አንተ የኔ ጀግና አይዞህ
ዛሬን እለፈው አይዞህ በርታ በልና አይዞህ
መውደቅ መሸነፍ አይዞህ ያለነውና አይዞህ
አልፈህ አሳየኝ አይዞህ ይሄን ፈተና አይዞህ
አይዞህ አይዞህ አይዞህ
አይዞህ አይዞህ አይዞህ

አብዱ ኪያር (ABD) 🙌 @abdukiarofficial

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ሉዓላዊነቷን የተዳፈሩትን አሳፍራ መልሳለች፤ ትመልሳለችም!

“ኢትዮጵያ የሚለው ስም ከጥንት እስከዛሬ ከክብር ፣ ልቆ ከመገኘት እና ከነጻነት ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው። ኢትዮጵያ ለዘመናት ሉዓላዊነትቷን ጠብቃ ከመቆየት ባሻገር በየትኛውንም ሀገር ወረራ ፈጽማ አታውቅም። ነገር ግን ሉዓላዊነቷን የተዳፈሩትን አሳፍራ መልሳለች፤ ትመልሳለችም። ይህም በልጆቿ የጋራ ጥረት የጸና ነው።”

ጠቅላይ ሚንስትር Abiy Ahmed Ali ( ዶ/ር )

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ተጀምሯል
እልል ያለ እንቁጣጣሽ ለመላዉ ቤተሰቦቻችሁ
የበዓል ማድመቂያ ስጦታ ምን ይፈልጋሉ?
ለመጪው የትንሳኤ በዓል! ከአውዳ'መት ሸመታ
ግልግል የሚያሰኝ የበዓል ማድመቂያ ስጥታ
ከሐበሻ ዴሊቨሪ እንምርጫዎ ቀረበልዎ!።
ለወዳጅ የበዓል ማድመቂያ ስጦታ...
+251-929908906 / 0946700505 ከወዲሁ ይደውሉ!

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የቻይና የሕዝብ ደኅንነት ሚኒስቴር ለክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የGreat Wall Commemorative Gold Medal Award አበረከተ

የቻይና የሕዝብ ደኅንነት ሚኒስቴር ለክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የ Great Wall Commemorative Gold Medal Award አበረከተ፡፡

የተበረከተላቸው የወርቅ ሜዳሊያ ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል የሁለቱን ሀገራት ፖሊስ ለፖሊስ ግንኙነት በማጠናከር በተለይ በቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ የፀጥታ ትብብር ስራዎች፣ የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅትንና የቀጠናውን ትብብር ከቻይና ፖሊስ ጋር በማስተሳሰር ላበረከቱት ሚና እንዲሁም አሁን ላይ የዓለም አቀፍ የሕዝብ ደኅንነት ትብብር ፎረም የቦርድ አባል ሆነው ለዜጎች ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ እየተጫወቱ ላሉት ክፍተኛ አስተዋዕፆ ሲሆን በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የወርቅ ሜዳሊያ Great Wall Commemorative Gold Medal Award ከቻይና የህዝብ ደኅንነት ሚኒስትር ክቡር ዋንግ ዣዎሆንግ እጅ ተበርክቶላቸዋል፡፡

በሥነ-ሥርዓቱም ላይ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ክቡር አቶ ተፈራ ደርበው፣ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ክቡር ቼን ሃይ፣ የቻይና የህዝብ ደኅንነት ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትሮችና እና የፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል ፡፡

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ሀገራችንን ለመውረር ግፊት ሲያደርጉና ግጭት ሲያባብሱ የነበሩ የሀገራችን ታሪካዊ ጠላቶች አብረው የቆሙ ቢመስሉም በሽንፈት ጊዜ እንደማይገናኙ ከታሪክ መማር ይገባል !!

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በ47ኛው የምስራቅ ዕዝ ምስረታ በዓል ላይ ያስተላለፉት መልዕክት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 30 ቀን 2016 ዓ.ም

👉 የምስራቅ ዕዝ 47ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ከሰላም ወዳዱ የሱማሌ ህዝብና ከጀግናው የዕዙ አመራርና አባላት ጋር ለማክበር በመቻሌ ደስታ ተሰምቶኛል፤

👉 ዕዙ አንደኛ አብዮታዊ በሚል ስያሜ የዛሬ 47 ዓመት መመስረቱና ከምስረታው ማግስት ጀምሮ ተስፋፊውን የዚያድ ባሬ ጦር ጨምሮ የተለያዩ የሽብር ሀይሎችን በመከላከልና በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተሰጠውን ግዳጅ በጀግንነት ሲመክት የቆየ አንጋፋና ጀግና ዕዝ መሆኑን፤

👉 ዕዙ ተስፋፊውን የዚያድ ባሬ ጦር ወደ መሀል ሀገር ያደረገውን ወረራ መስዋዕትነት በመክፈል ጭምር የሀገሩን ዳር ድንበር ማስከበር መቻሉን፤

👉 በክልሉ ለታየው ሰላምና እየተመዘገበ ላለው ሁለገብ እድገት የተረጋገጠው ሰላም ወሳኝ በመሆኑ ክልሉ ለልማትና ለኑሮ ተመራጭ እየሆነ መምጣቱን፤

👉 ዕዙ የሀገራችን ሰላም ሉአላዊነትና አንድነትን በማስጠበቅ ከፍተኛ ዋጋ መክፈሉና የሰራዊቱ መመኪያ የሆነ ዕዝ መሆኑን፤

👉 ክልሉ በፀጥታ ችግር ምክንያት ከልማት ርቆ መቆየቱና ዕዙ መንግስትና ህዝቡ ባስመዘገቡት ሰላም በፈጣን ሁኔታ ዕድገቱ እያደገ መምጣቱን፤

👉 ተስፋፊነት የጦርነት ነጋሪት መሆኑንና ሠራዊታችን ሀገራችንን ለመውረር የሞከሩ ሀይሎች ለመመከት የሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝ፤

👉 ሀገራችንን ለመውረር ግፊት ሲያደርጉና ግጭት ሲያባብሱ የነበሩ የሀገራችን ታሪካዊ ጠላቶች አብረው የቆሙ ቢመስሉም በሽንፈት ጊዜ እንደማይገኙ ከታሪክ መማር እንደሚገባ፤

👉 ሠራዊቱ በቀጠናው ያለውን የተስፋፊዎች የጦርነት ነጋሪት ጉሸማ ለመመከት የሚያስችል የተሟላ ወታደራዊ ቁመና ላይ እንደሚገኝና ህዝባችን ላይ ስጋት ለመፍጠር የሚሞክሩ ተላላኪዎችን መስማት እንደሌለበት፤

👉 ውስጣዊ ችግሮች ቢኖሩም ሀገርን ከጥቃት ለመከላከል ብቻ ሳይሆን ከሞከሩ ዳግመኛ እንዳያስቡት አድርጎ ለመመከት የሚያስችል ዝግጁነት መኖሩን የተናገሩት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ፤

የሀገራችንን ነፃነት አስከብረን እንኳን አሁን በጦርና በጋሻ ታንክ በመመከት በነፃነት የቆየን የጀግኖች መገኛ መሆናችንን የምስራቁ የሀገራችንን ድንበር ለመመከት ለዕዙ የሚደረግ ማንኛውንም ድጋፍ መከላከያ እንደሚያደርግ መላው የሀገራችንና የክልሉ ማህበረሰብ ለዕዙና ለሰራዊታችን የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

የምስራቅ ዕዝ 47ኛ ዓመት በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩን ቀጥሏል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የሶማሌ ክልል ርዕስ መስተዳደር ክብር ሙሰጠፌ ሙሁመድ ዑመር በምስራቅ ዕዝ የተገነባውን የገርብ-አሴ አምፊ ቴአትር መርቀው ከፈቱ

የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በምስራቅ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል የተገነባውን የገርባሳ አምፊ ቴአትር መርቀው ከፍተዋል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ 47ኛውን የምስራቅ ዕዝ የምስረታ ክብረ በዓልን ለመታደም በዛሬው ዕለት ጅግጅጋ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

በዝግጅቱ የተለያዩ ወታደራዊ ትዕይንቶችን ጨምሮ ምስራቅ ዕዝን የሚዘክሩና ቀጣይ አቅጣጫን የሚጠቁሙ መልዕክቶች ይተላለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል::

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ 47ኛውን የምስራቅ ዕዝ የምስረታ ክብረ በዓል ላይ ለመታደም ጅግጅጋ ገቡ።

የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ 47ኛውን የምስራቅ ዕዝ የምስረታ ክብረ በዓልን ለመታደም ጅግጅጋ ገብተዋል።

በአቀባበል ስነ ስርዓት ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር ሙስጠፌ መሀመድ ጨምሮ የሠራዊቱና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

47ኛው የምስራቅ ዕዝ የምስረታ ክብረ በዓል በተለያዩ ሁነቶች እስከ ጳጉሜ 02 ቀን እየተከበረ ይቆያል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561

Читать полностью…
Subscribe to a channel