natnaelmekonnen21 | Unsorted

Telegram-канал natnaelmekonnen21 - Natnael Mekonnen

169400

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7 Facebook.com/natnaelmekonnen.et Instagram.com/natnaelmekonnen21

Subscribe to a channel

Natnael Mekonnen

" አሳድ የሩስያን ድጋፍ በማጣታቸው ሶሪያን ለቀው ሸሽተዋል " - ትራምፕ

ተመራጩ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ የሶሪያው ፕሬዜዳንት በሽር አላሳድ የሩስያን ድጋፍ በማጣታቸው ሀገራቸውን ጥለው መሸሻቸውን ገለጹ።

ይህን ያሉት ' ትሩዝ ' በሚሰኘው ማህበራዊ ሚዲያቸው ላይ ነው።

" አሳድ ሄዷል " ያሉት ትራምፕ " ጠባቂው በቭላድሚር ፑቲን የሚመራው ሩስያ፣ ሩስያ፣ ሩስያ ! ከዚህ በላይ እሱን (አሳድን) ለመጠበቅ ፍላጎት አልነበረውም " ሲሉ ገልጸዋል።

የትራምፕ ሀገር አሜሪካ በርካቶች ባለቁበት የባለፉት 13 ዓመታት የሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት ሶሪያ ውስጥ ናት።

ሀገሪቱ ዋና አላማ ብላ የገባችው ' ISIS 'ን ለማፅዳት ቢሆንም በቀድሞ ፕሬዜዳንት ኦባማ ሰዓት " አሳድ መሄድ አለበት / ከአገዛዙ መወገድ አለበት " የሚል አቋም በይፋ ይንፀባረቅ ነበር።

እኤአ በ2013 ኦባማ እስራኤልን ሲጎበኙ ከቤኒያሚን ኔታንያሁ ጋር ሆነው " አሳድ መሄድ አለበት አገዛዙ ማብቃት አለበት " ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህም ባለፈ ፤ የአሳድን ተቃዋሚዎች በቁሳቁስ እና በስልጠና ድጋፍ ታደርግላቸው ነበር።

የፑቱን ሀገር ሩስያ የአላሳድን መንግሥት የምትደግፍ ሲሆን የአገዛዙ ጠላቶች ላይ እርምጃዎችን ስትወስድ ነበር።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽንን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማና አጠቃላይ የተቋሙን የሥራ እንቅስቃሴ ግምገማ አካሄደ

ቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ በተከበሩ ፕሮፌሰር መሀመድ አብዶ እየተመራ የቀረበለትን ሪፖርትን መሠረት አድርጎ የአፈፃፀም ግምገማ አድርጓል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል ለተከበሩ የቋሚ ኮሚቴ አባለት ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል።

በመድረኩ ለክትትልና ድጋፍ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ስለተቋሙ የውስጥ አሰራር እና የሕግ ማዕቀፍ በተመለከተም የሥልጠና መድረክ ለቋሚ ኮሚቴው ተዘጋጅቶ በቂ ማብራሪያ እና ገለፃ ተሰጥቷል።

ለቋሚ ኮሜቴው ከተላከው ሪፖርት በላይ ኮርፖሬሽኑ በሩብ ዓመቱ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን በግምገማ ማረጋገጡን ነው ቋሚ ኮሜቴው የገለፀው::

ቋሚ ኮሚቴው የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ሠራተኞች አሁንም እንደ አገር ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት ያላቸውን ቁርጠኝት በለቀ ሁኔታ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ሲሉም አሳሰበዋል።

ኮርፖሬሽኑ የወቅቱ ዋነኛ ችግር የሆነውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመፍታት የሚያድርገውን ጥረት ለማገዝ ቋሚ ኮሜቴው እንዲሚሠራም አሰታውቋል።

ኮርፖሬሽኑ መመሪያዎችን መሠረት አድርጎ የቤት አሰተዳደር ሥራዎችን እያከነወነ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው ገልጿል ::

በቅድሚያ የሰራተኛው አመለካከት እንዲቀየር እና የተቋሙ የሪፎም መሠረት በሠራተኛውና በአመራሩ መካከል ያለው የተግባርና የአመለካከት አንድነት እንዲሆን ማስቻሉ ቀጣይነት ያለው ውጤት እንዲያስመዘግብ እንዳደረገው ነው የቋሚ ኮሚቴው አባላት የተናገሩት ።

ይኸው ተምክሮም በመንግሥት ተቋማት እንዲሰፉ ቋሚ ኮሚቴው ጠይቋል።

ከሕግ ማዕቀፍ እና የፖሊሲ ጉዳዮች ማሻሻያዎች እንዲደረጉና በመንግሥት የተጣለበትን ኃላፊነት ኮርፖሬሽኑ በላቀ ሁኔታ እንዲወጣ ለማስቻል ቋሚ ኮሚቴው በቀጣይ ድንጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በመላው ሀገሪቱ የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ ነው - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።

የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቆ፤ ያሉትን መረጃዎች በፍጥነት የሚያሳውቅ መሆኑንም ገልጿል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የአሜሪካ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ቲክቶክ እንዲሸጥ የሚያስገድደውን ውሳኔ አጸደቀ

የዜጎችን ግላዊ መረጃዎች ለቻይና መንግስት አሳልፎ ይሰጣል በሚል በአሜሪካ የተከሰሰው ቲክቶክ ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደርጓል።
https://bit.ly/4inEzp2

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

Must Listen : ማሪያማዊት እግዜር ይስጣት እኛ ለዘመናት የተናገርነውን ነገር በገዛ ሚዲያዋ አረጋግጣልናለች።

ድሮ ፌስቡክ ላይ የአማራና የኦሮሞን ህዝብ ወደግጭት በሚወስድ እኩይ ንግግሩ የምናውቀው የህውሀቱ አክቲቪስት ልፍሀተይ ተስፋ (ብርሀነ) ለዘመናት የጮህንለትን ነገር አረጋግጦልናል።

ብርሀነ ወለጋ ተወልዶ ማደጉንና ኦሮሚኛ ቋንቋ አቀላጥፎ እንደሚናገር ገልፆ ወለጋ ላይ እዛው ያደጉ ብዙ የትግራይ ልጆች መኖራቸውንና የሸኔ ጦርን መቀላቀላቸውን ከዚያም በላይ የሸኔ ጦር ውስጥ የአመራር ቦታ ላይ ያሉ የትግራይ ልጆች መኖራቸውን ገልፆልናል። ይህ እንግዲ ወለጋ አካባቢ ላለፉት ስድስት አመታት ሲሰራ የነበረው ቁማርና ጥፋት ከየት እንደሚመነጭ ለሁላችንም በግልፅ የሚያሳይ ይመስለኛል።

ሴራው ፀሀይ ላይ እየወጣ ነው። በኦሮሚያ በተለይም በወለጋ ንፁሀን ላይ ጥቃት በማድረስ በአማራና በኦሮሞ መሀከል የነበረን የዘመናት ፍቅርና አንድነት ማፍረስ፥ ሁለቱ ትልልቅ ህዝቦች መሀል እሳት መጫር በነብርሀነና መሰሎቹ ለሁለቱ ህዝቦች የተዘጋጀ ወጥመድ ነበር። ይሄ የሚፈፀመው ደግሞ እነብርሀነ እንደነገሩን በሸኔ ውስጥ አስርገው ባስገቧቸው ኦሮሚኛ ተናጋሪ ህውሀቶች ነበር። በኢትዮጵያና በንፁሀን ላይ የቆመሩ ገና ይለፈልፋሉ።

ህዝብ ይንቃ። በነፃ አውጪ ስም የተፈለፈለ ሁሉ ነፃ አውጪ አይደለም። ኦሮሚኛ ያወራ ሁሉ ኦሮሞ አይደለም። በአማርኛ የዘበዘበ ሁሉ አማራ አይደለም። “እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል” እንደሚባል በብዙ ንፁሀን ደም እጁ የጨቀየው ብርሀነ “ቁርጣችሁን እወቁ ሸኔ ማለት እኛ ነን” ብሎናል። እናመሰግናለን ወንድማችን። እኛ ስንናገር አንሰማ ብለውን ነበር። እንዲህ እራሳችሁ ንገሯቸው።

ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

"ጽንፈኛው ቡድን በፈረስ ቤት 37 ወገኖችን በግፍ ጨፍጭፏል" አቶ ደሳለኝ ጣሰው

በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ጉዳዮች አስተባባሪ እና የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰው በወቅታዊ የሰላም እና የጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም የክልሉ የሰላም እና የጸጥታ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ተናግረዋል። ማኅበረሰቡ ለሰላም ያለው ግንዛቤ ትልቅ ነው ያሉት ኀላፊው ለሰላም የሚከፍለው ዋጋ ከፍ ያለ መኾኑንም ገልጸዋል።

ከሕግ ማስከበር ጎን ለጎን ለሰላም የሚዘጋ በር የለም በሚል ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎች ሲቀርቡ መቆየታቸውንም አመላክተዋል። መንግሥት በድርድሩ ብቻ ውጤት ይገኛል ብሎ ባይቀመጥም የሰላም አማራጮች ግን አሁንም ዝጎች አይደሉም ነው ያሉት። ማኅበረሰቡ መንግሥት ለሰላም ለሰጠው አማራጭ ድጋፍ ማድረጉንም ተናግረዋል።

ነፍጥ ባነሳ ኃይል ላይ ሕግ ማስከበር ግድ መኾኑንም ገልጸዋል። እስካሁን በተሠራው ሥራ 2 ሺህ 594 ታጣቂዎች ሲያደርጉት የነበረው ድርጊት ተገቢ አለመኾኑን ተረድተው ለሰላም መግባታቸውን ተናግረዋል። በየቀኑ ለሰላም የሚገቡ ታጣቂዎች መኖራቸውንም አስታውቀዋል።

ጽንፈኛው ቡድን በምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ሚካኤል በሚባል ሥፍራ የሕዝብ እና የመንግሥት አገልግሎት የሚሰጡ 97 የኅብረተሰብ ክፍሎችን ከመስከረም 29/2017 ዓ.ም ጀምሮ አሥሮ መቆየቱን ጠቁመዋል። ከቤተሰቦቻቸው ከመቶ ሺህ እስከ 1 ሚሊዮን ብር ድረስ እየተቀበለ ቆይቶ ዛሬ ኅዳር 27/2017 ዓ.ም 37 ወገኖችን በግፍ ጨፍጭፏል ነው ያሉት።

ጽንፈኛው ቡድን የፈጸመው ድርጊት አሳዛኝ እና ዘግናኝ መኾኑንም ተናግረዋል። ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው እንኳን ወገናቸውን ሀገራቸውን ሊደፍር የመጣን ጠላት እንኳን ሲማርኩ ተንከባክበው፣ ድርጊቱ ልክ እንዳልኾነ አስተምረው የሚልኩ ናቸው ያሉት ኀላፊው ጽንፈኛው ቡድን ግን ከኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ስብዕና ባፈነገጠ መልኩ የራሱን ወገኖች በግፍ ይገድላል ነው ያሉት።

ጽንፈኞች የያዛዟቸውን ወገኖች እጅ እና እግራቸውን እያሠሩ ሁለት ወራት ካቆዩ በኋላ በግፍ መግደላቸውን ነው የተናገሩት። የቀሩት ወገኖችንም በግፍ ሊገድሏቸው እንደሚችሉም ገልጸዋል። ከዚህ በፊትም በተናጠል የሚረሽኗቸው ወገኖች በርካቶች መኾናቸውን ተናግረዋል።

ሕዝቡ በጽንፈኞች ምክንያት በራሱ ከተማ፣ ክልል እና ሀገር እንዳያለማ፣ እንዳይነግድ እና እንዳይኖር ኾኗል ነው ያሉት። ሕዝቡን ከግፍ ቀንበር ለማውጣት እየተወሰደው ያለውን እርምጃ ሕዝቡ እንዲደግፍም ጥሪ አቅርበዋል።

በፈረስ ቤት ሚካኤል በጽንፈኛው ቡድን በተፈጸመው አሰቃቂ ግፍ የክልሉ መንግሥት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ይገልጻል ነው ያሉት። የተፈጸመው ድርጊት ከአማራ ሕዝብ ታሪክ ያፈነገጠ እና ነውር መኾኑንም ነው የተናገሩት። መንግሥት ይህን ድርጊት በፈጸመው የጽንፈኛ ቡድን ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመላክተዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

https://vm.tiktok.com/ZNeTdRWjk/

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት እና የሀብት አስተዳደር ሥርዓቱን ለማዘመን ከደቡብ አፍሪካ ኩባንያ ጋር ስምምነት ፈጸመ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና መቀመጫውን ደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ካደረገው ሎህባወር አሶሴት ጋር በዘመናዊ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አስተዳደር እንዲሁም በሀብት አስተዳደር ዙሪያ ዓለምዓቀፋዊ ልምዶችን ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነት ደርሰዋል፡፡

ስምምነቱን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል እና የአማካሪ ድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስተር ሬን ሆርድ ፈርመዋል፡፡

በከፍተኛ ሁኔታ እያደገና እየሰፋ ያለውን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የቤት ግንባታ መርሀ ግብር ዓለምዓቀፋዊ የፕሮጀክትና የሀብት አስተዳደር ልምዶችን በመቀመር ረገድ ስምምነቱ አገራዊ ፋይዳ ይኖረዋልም ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በቴክኖሎጂ ፣ እውቀት ሽግግር እና በኮንስትራክሽን እንዲሁም በቤት አስተዳደር ሥራዎች ዘመናዊ የአሰራር ስርዓቶች ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ነው፡፡

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር ኮርፖሬሽኑ በፕሮጀክት አስተዳደር ረገድ በሞዴልት የሚጠቀስ ስርዓት መዘርጋት የቻለ ተቋም እንደሆነ አስታውሰው በአሁኑ ሰዓት የኮርፖሬሽኑ የግንባታ ፕሮጀክቶች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ በመሆኑ የተቋሙን የፕሮጀክትና የሀበት አስተዳደር አቅምን በማሳደግና የአሰራር ሥርዓት በማሻሻል የኮርፖሬሽኑን ትርፋማነትና ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥራ ከወዲሁ መሥራት አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ከሎህባወር አሶሴት ኩባንያ ጋር በመሆን ዓለምዓቀፋዊ ልምዶችን ተግባራዊ ለማድረግ ኮርፖሬሽኑ እንደሚሰራ ክቡር አቶ ረሻድ ተናግረዋል፡፡

የሎህባወር አሶሴት ዋና ሥራ አስፈጻሚ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት በከፍተኛ ለውጥ ላይ ካለው ከፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ ለመስራት እድል በማግኘታቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸው በዘርፉ ለ28 ዓመታት ያዳበሩትን የማማከር አገልግሎት ልምድ ለኮርፖሬሽኑ ለማከፈል እንደሚሰሩም ተናግረዋል፡፡

በስምምነቱ ወቅትም የዓለምቀፉ የሙያ ደህንነትና የጤና ፕሬዜደንት የኢንተርናሽል የሲቪል መሀንዲስ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር ካርል ሀይንስ ተገኝተዋል፡፡

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ልዩ መረጃ መቀሌ‼️

ህወሓቶች በጠላቶቻችን ተከበናል (ክባን ዕፅዋን) እያሉ ሲንጫጩ እንዳልነበር ዛሬ እርስበርስ ሲካበቡ ዋሉ! ህወሓት ድሮም ለትግራይ ህዝብ አልቆመም ለስልጣን እና ለዘረፋ እንጂ‼️

ለሁለት የተከፈለው ህወሓት ዛሬ ሁለቱም ከንቲባዎች ( የደብረፂዮኑ ሹመኛና የጌታቸው ሹመኛ ) ቢሮ ሳይገቡ ነው የዋሉት። የመቀሌው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር አንድነት ከፖሊሶች ጋር በመሆን የደብረፂዮኑ ሹመኛ ዶ/ር ረዳኢ ወደ አስተዳደር ፅ/ቤቱ ቢሮ እንዳይገባ ለመከላከልና ለመግባት ከሞከረም በቁጥጥር ስር ለማዋል ፅ/ቤቱን በመክበብ ጥበቃ ሲያደርግ ውሏል።

ታደሰ ወረደ ደግሞ ፅ/ቤቱን የከበቡትን እነ ኮማንደር አንድነትን በወታደሮቹ (የTDF አባላት) አስከብቦ ውሏል !! ይሄንን የተረዱት ከንቲባዎች ዛሬ ቢሮ ባለመግባት ሁለቱም በፎርፌ ነጥብ ጥለዋል

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ትናንት የሩሲያ ፕሬዘዳንት ፑቲን በሩሲያ የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ በኢትዮጵያ እየተከሰተ ያለውን የልማት ተአምር እና የሚደነቅ እንቅስቃሴዎች ሲመሰክሩ ነበር።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ወደ ሰላም አልመጣም ካለ ይደምሰስ!!

በአማራ ክልል ጎጃም እና አካባቢው የሚገኙ 8 የገጠር መንደሮች በየ ቤተክርስቲያን እና ገበሬ ቤት ተደብቆ የነበረው ጽንፈኛ ቡድን ዛሬ አይቀጡ ቅጣት እየተቀጣ ተደምስሶ እግሬ አውጪ በማለት ፈርጧል:: ፅንፈኛዉ ጀግና ተዋጊ ነን የሚሉትና በየሚዲያቸው ፕሮፓጋንዳ የሚሰሩላቸው ሚዲያዎቻቸው እነዴት ንብረቱ እያ ጠበጠበ እግሬ አዉጭኝ እያለ ሲፈረጥጥ ባዩት:: ቪዲዮና ተጨማሪ መረጃዎችን ይዤ እመለሳለሁ::

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነግ ሸኔ) ትጥቃቸውን ለመንግስት በማስረከብ ወደ ታህድሶ ካምፕ መግባት ጀምረዋል። ሁሉም አካላት ለህዝብና ሀገር ሰላም ቅድሚያ ሊሰጡ ይገባል።

ሰላም ለኢትዮጵያና ህዝቦቿ!

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (ኦነግ ሸኔ) ተዋጊዎች ወደ ሰላም መመለሳቸው አርዓያነት ያለው ተግባር ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የሰላም መንገድ አማራጭ የሌለውና ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ መንገድ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (ኦነግ ሸኔ) ከፍተኛ አመራር በሆኑት ጃል ሰኚ ነጋሳ የተመራ የሠራዊቱ አመራሮች የዓድዋ ድል መታሰቢያን እና ሌሎች የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ከጎበኙ በኋላ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንኳን ወደ ሰላም መንገድ መጣችሁ ብለው ተቀብለዋቸዋል::

በዚሁ ወቅት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ የሰላም መንገድ አማራጭ የሌለው እና ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ መንገድ መሆኑን በመረዳት መንግስት ላደረገው ጥሪ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አባላት የሰጡት ምላሽ የሚያስመሰግን መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ስምምነቱ የፖለቲካ እና የሃሳብ ልዩነቶችን ዘመናዊ በሆነ መንገድ በውይይትና በሰላም መፍታት ለሌሎችም አርአያ የሚሆን ተግባር መሆኑን ገልጸዋል::

የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር ጃል ሰኚ ነጋሳ በበኩላቸው፤ ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው፤ የሰላም ጥሪውን የተቀበሉት የህዝብን ጉዳት ለመቀነስ እና የሰላም አማራጭን መቀበል ብልህነትና አዋቂነት መሆኑን በመረዳታቸው እንደሆነ ተናግረዋል::

በኦሮሚያ ክልል መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች መካከል የሰላም ስምምነት መፈራረሙን ተከትሎ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያን፣ አንድነት ፓርክን እንዲሁም በአዲስ አበባ የተገነቡ ሌሎች ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን የከንቲባ ፅ/ቤት መረጃ ያመለክታል::

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

Good morning #Ethiopiaዬ

በጠዋቱ እየገቡ ነው‼️

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

🔶️ ውሳኔዎን የሚያደንቁበት ትርፋማ ኢንቨስትመንት  ከአሚባራ ፕሮፐርቲ ! 🔶️

➣ ለ50 ቤቶች ብቻ የተዘጋጀ
ታላቅ ቅናሽ!

➣ ሸራተን ሆቴል አጠገብ
ወዳጅነት ፓርክ ፊትለፊት
ቅንጡ አፓርትመንቶች
ከ852,000 ብር ቅድመ ክፍያ
ጀምሮ

➣ ሁለት የመዋኛ ገንዳ,
የልጆች የእግር ኳስ ሜዳ,
የቅርጫት ኳስ ሜዳ
እንዲሁም የቤት ውስጥ
የበረዶ መንሸራተቻ

➣ ከባለ አንድ እስከ ባለ አራት
የመኝታ ቤት አማራጮች

➣ በ10% ቅድመ ክፍያ
በኢትዮጵያ ብር የሚዋዋሉት

➣ እስከ 25% የሚደርስ
ታላቅ ቅናሽ

ለበለጠ መረጃ
0979804444
በቀጥታ ወይንም በዋትሳፕ
ይደውሉ

አሚባራ ፕሮፐርቲ
ለዘመናዊ ኑሮ ታስቦ የተገነባ

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ኃይል ወደነበረበት እየተመለሰ መሆኑን የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከልን ጠቅሶ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማዕከሉን ጠቅሶ እንዳለው፥ የሲስተሙን ቮልቴጅ በማረጋጋት የተቋረጠውን ኃይል ደረጃ በደረጃ ለመመለስ የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ ነው።

በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች እንዲሁም በክልል ከተሞች የተቋረጠው ኃይል ወደነበረበት መመለሰ መጀመሩንም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በማኅበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።

የተፈጠረው ችግር ሙሉ በሙሉ እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጠይቋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች እና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች “አገራዊ መግባባት ለኅብረብሔራዊ አንድነት” በሚል ለ19 ጊዜ ለሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አርባምንጭ ከተማ የገቡ ሲሆን በከተማው ሲደርሱም በእንግዳ ተቀባይነት የሚታወቀው ፍቅር ሰባኪው ሰላም ወዳዱ የጋሞ ህዝብ በነቂስ በመውጣት ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

🔶️ ውሳኔዎን የሚያደንቁበት ትርፋማ ኢንቨስትመንት  ከአሚባራ ፕሮፐርቲ ! 🔶️

➣ ለ50 ቤቶች ብቻ የተዘጋጀ
ታላቅ ቅናሽ!

➣ ሸራተን ሆቴል አጠገብ
ወዳጅነት ፓርክ ፊትለፊት
ቅንጡ አፓርትመንቶች
ከ852,000 ብር ቅድመ ክፍያ
ጀምሮ

➣ ሁለት የመዋኛ ገንዳ,
የልጆች የእግር ኳስ ሜዳ,
የቅርጫት ኳስ ሜዳ
እንዲሁም የቤት ውስጥ
የበረዶ መንሸራተቻ

➣ ከባለ አንድ እስከ ባለ አራት
የመኝታ ቤት አማራጮች

➣ በ10% ቅድመ ክፍያ
በኢትዮጵያ ብር የሚዋዋሉት

➣ እስከ 25% የሚደርስ
ታላቅ ቅናሽ

ለበለጠ መረጃ
0979804444
በቀጥታ ወይንም በዋትሳፕ
ይደውሉ

አሚባራ ፕሮፐርቲ
ለዘመናዊ ኑሮ ታስቦ የተገነባ

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

#WBO ጉዞ ወደ ሰላም

ሰላም ከሁሉም በላይ ነው!

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ደጋዳሞት ወረዳ የደረሰው ክስተት እጅግ ልብ የሚሰብር ቢሆንም የጽንፈኛውን የሽንፈት መጨረሻ የሚያሳይ ነው።

ከመከላክያ ጋር መዋጋት ያቃተው ጽንፈኛው ድቡድን ደጋዳሞት የረሸናቸው ቁጥር 34 ደርሷል። ከእነዚህ መካከል (ከወረዳ አመራሮች በተጨማሪ ፣ የፖሊስ እና የሚሊሻ አመራርና አባላት እንዲሁም የዕድር ሃላፊዎችና የመንግስት ሰራተኞች ይገኙበታል

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ልዩ መረጃ‼️

የነ ደብረፅዮን ቡድን ያቀረቡትን ፥የፕሬዝዳንትነት እጩ ፕሮፖዛል ውድቅ ሆነ‼️

የነ ደብረፅዮን ቡድን ይዘውት ያቀረቡትን ፥የፕሬዝዳንትነት እጩ ፕሮፖዛል ዛሬም በፌደራል መንግስት ውድቅ መደረጉ ታውቋል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት የመሾም ወይም የፕሬዝደንትነት ፕሮፖዛል የማቅረብ ስልጣን ህወሓት እንደሌለው እንደተነገራቸው ታውቋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ለሁለት የተከፈለው የህወሓት አመራሮች አቶ ጌታቸው ረዳና ቡድናቸው ዶር ደብረጺዮንና ቡድናቸው አዲስ አበባ ናቸው::

በአዲስ አበባ የሁለት ቀን ቆይታቸው እስካሁን ከየትኛው የፌደራል መንግስት አመራሮች ጋር እንደተግናኙ የታወቀ ነገር የለም::

የመቀሌው ከንቲባ ቢሮ ለተሾሙት ሁለቱም ከንቲባዎች ወደ ቢሮ እንዳይገቡ በመቀሌ ፖሊስና በ TDF ሃሎች የከንቲባው ቢሮ ዝግ ተደርጏል::

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በደብረጺዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን በመቀሌ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ

ህወሃት ህዳር 29 የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ጥያቄ አቀረበ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ_ህወሃት በመጪው ህዳር 29 በመቀሌ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ይፈቀድልኝ ሲል ደብዳቤ ጻፈ።

ለመቀሌ ከተማ አስተዳደር በተጻፈው ደብዳቤ እንደተገለጸው፤ ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም፤ በትጥቅ የተደገፈ የአስተዳደር ፈረሳ በመከናወኑ ይህን ለመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ እናደርጋለን ብሏል።

ለዘመናት መስዋዕት ከፍለን የመሰረትናቸው ምክር ቤቶች በግለሰቦች ሲፈርሱ አንታገስም በሚል ምክንያት፤ ከህዝባችንና አባላቶቻችን በተደጋጋሚ ጥሪ እየቀረበልን በመሆኑ ህዳር 29 በመቀሌ ከተማ  ሰልፍ ለማድረግ አቅደናል ብሏል።

ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ 6:30 ሰልፉን ለማድረግ ተዘጋጅተናል ያለው ፓርቲው፤ የጸጥታ ኃይል ጥምር ኮሚቴ እንዲፈቅድልንና ከለላ እንዲያደርግልን እንጠይቃለንን ሲል በመቀሌ የህወሃት ጽህፈት ቤት በደብዳቤ ጠይቋል።

በመቀሌ ከተማ ምክር ቤት አማካኝነት የተመረጠውን አስተዳደር፤ በጌታቸው ረዳ የሚመራው ቡድን በኃይል አፍርሶታል ሲል፤ ደብረጺዮን ገብረሚካኤል(ዶ/ር) የሚመራው የህወሃት ክንፍ ከሰሞኑ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የኦነግ/ሸሼ መሪ ጃአል ሳኒ ናጋሳአን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በሸገር ከተማ ያለውን የልማት እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

ከሰሞኑ የሰላም ስምምነት በኋላ በሸገር ከተማ ፉሪ ወረዳ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ፣ፍርድ ቤትን እና የእንስሳት ሀብት ልማት ክላስተርን ጎብኝተዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የአቶ ጌታቸው ረዳን የፕሬዚዳንትነት ውክልና አንስቻለሁ’’ በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ትላንት ምሽት ባወጣዉ መግለጫ ለአቶ ጌታቸው ረዳ ሰጥቷቸው የነበረውን የፕሬዚዳንትነት ውክልና ማንሳቱን ገልጿል፡፡ በመሆኑም በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት እንዴት እና በማን እንደሚተኩ ከፌደራል መንግስት ጋር እየተወያየበት እንደሚገኝ አስታዉቋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ለፅንፈኛው ቡድን ሊደርስ የነበረ 12,300 የሽጉጥ ጥይት በባህርዳር ከተማ ተያዘ።

መነሻውን ምዕራብ ጎንደር ቋራ መዳረሻውን ባህርዳር ከተማ በማድረግ ሲጓጓዝ የተያዘው 12,300 የሽጉጥ ጥይት በፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ክትትል ሲደረግበት ቆይቶ ከማሽላ ጋር በማመሳሰል ተጭኖ ለፅንፈኛው ቡድን ሳይደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉን በኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ የክፍለጦር ምክትል አዛዡ ሌተናል ኮሎኔል አየልኝ አስናቀ ተናግረዋል።

ህገ ወጥ ጥይቱን ለፅንፈኛው ቡድን ለማድረስ ሲሉ በቁጥጥር ስር የዋሉት ጥላሁን ገነቱና ስማቸው ወንድ ይፍራው የተባሉ ግለሰቦች በባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ ጥይቱን ጭነው ለፅንፈኛው ቡድን ለማድረስ ሲሉ በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ11 በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን ነው ሌተናል ኮሎኔል አየልኝ አስናቀ የገለፁት።


የባህርዳር ከተማን ሠላምና ፀጥታ ለማወክ የሚንቀሳቀሱ የፅንፈኛው ኃይሎችን የማደንና በቁጥጥር ስር የማዋል ተግባሩ ተጠናክሮ ቀጥሏል ያሉት የክፍለጦር ምክትል አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል አየልኝ አስናቀ የፅንፈኛው ቡድን በአሁኑ ወቅት በተለያዩ አቅጣጫዎች እጅ በመስጠት ላይም ይገኛል ብለዋል።

ህብረተሰቡ ሠላም እንዲሰፍን  በቁርጠኝነት አየሰራ ይገኛል ያሉት ሌተናል ኮሎኔል አየልኝ አስናቀ የፅንፈኛውን ቡድን ርዝራዦች ለማደን በሚደረገው ዘመቻ ጥቆማና መረጃ በመስጠት እያደረገ ያለውን ትብብር የበለጠ አጠናክሮ እንዲቀጥልም  ጠይቀዋል። ዘገባው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ነው።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ሰበር መረጃ ጎጃም‼️

በጎጃምና አካባቢው በርካታ የገጠር መንደሮችን የመከላክያ ሰራዊት ጽንፈኛውን እየደመሰሰ እያስለቀቀ ነው በተለይ ጭንባ ጎልጎሉማ ኢሎማ ሙጋር ነጭ ድንጊያ የመሣሠሉትን የገጠር መንደሮች በአሰሳ እያስለቀቀ መሆኑም ከስፍራው የደረሰኝ መረጃ ያመልክታል::

ዘመነ ካሴና ቡድኑ ሁለት ምርጫ አላቸው:: 1 እጅ መስጠት 2 ወደ ሰላም መምጣት:: አለዚያ ለወሬ ነጋሪ እንዳይሆኑ ሆኖ ሙሉ በሙሉ መደምሰስ! በታሪክ ዘመነ ካሴ እጄን አልሰጥም ብሎ እራሱን እንደማያጠፋ 100% እርግጠኛ ነኝ ወኔ የለውም:: ምናልባት አስረስ ዳምጤና ለግዜው ሙሉ ስማቸውን የረሳሁት የቀድሞ ግ7 አባሎች እጅ ከመስጠት እራሳቸውን ሊያጠፉ ይችላሉ ብዬ እገምታለሁ እንጂ ዘመነ (ዘመነች) በምን ወኔና ድፍረቷ እላይዋ ላይ ቃታ ትስባለች? በፍጹም እንተዋወቃለን እኮ ከኤርትራ በርሃ እስከ አማራ ክልል!

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በምዕራብ ሸዋ ዞን የሰላም አማራጭ የተቀበሉ የሸኔ አመራርና ታጣቂዎች ወደ ሠላም ተመልሰዋል።

በምዕራብ ሸዋ ዞን ጅባት ወረዳ ፅናት ክፍለ ጦር በሠራዊቱ አመራሮችና ኦነግ ሸኔ ታጣቂ መካከል ውይይት የተካሄደ ሲሆን የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ የቀረበላቸውን የሰላም አማራጭ ተቀብለው ወደ ሠላም መመለሳቸውን በማዕከላዊ ዕዝ የፅናት ክፍለ ጦር አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል አማረ ሰጥአርገው ገልፀዋል።

ለሀገር የሚጠቅመውን ለህዝቡ የሚበጀውን አማራጭ በሰውኛ አስተሳሰብ በመመልከት እስካሁን የነበረው ችግር ሊቆም እንደሚገባ በውይይቱ ላይ መነሳቱን አዛዡ ተናግረዋል።

ከቡድኑ አመራሮች መካከል የጊዱ ገሌሳ አመራር ከቤ ጋድሳ በጫካ ስሙ (ኢራንጎሬ) በስሩ ከሚገኙ አመራሮች እና አባላት ጋር በመሆን መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ በመቀበል በርካታ ታጣቂዎች ወደ ህብረተሰቡ መቀላቀላቸውን የገለፁት ሌተናል ኮሎኔል አማረ ሰጥአርገው በቀጠናው አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን የተደረገው ጥረት ውጤታማ ነበር ብለዋል።

ውይይቱ የክፍለ ጦሩ የሠራዊት አመራሮች የወረዳ የስራ ሀላፊዎች የሀይማኖት አባቶች እና አባ ገዳዎች የተሳተፉበት ሲሆን በአካባቢው ባህልና ወግ መሰረት እርቀ ሰላም አውርደዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

https://youtu.be/GXTvI8sgmw8?si=tKWL6vNtJGO-gjGn

Читать полностью…
Subscribe to a channel