የቀድሞ የሶሪያ አማጺዎች ተዋህደው በመከላከያ ሚኒስቴር ስር ለመሆን መስማማታቸው ተገለጸ
የበሽር አላሳድን የ 24 አመት ስልጣን በገረሰሰው የትጥቅ ትግል ውስጥ ወሳኝ ሚና የነበረው ሙርሃፍ አቡ ቋስራ የመከላከያ ሚኒስትር ሆኖ ተሾሟል
https://bit.ly/3VUemEY
በTiktok እና በተለያዩ የ ሶሻል ሚዲያ ላይ ጥሩ ጥሩ የስፖርት ቪዲዮዎችን እና ማነቃቂያዎችን በማጋራት የሚታወቀው የስፖርት አሰልጣኝ ሄኖክ ገብሬ (Coach Henny) የዚህ አመት የ Tiktok creative award ላይ በምርጥ የስፖርት ኮንተንት እጩ ሆኗል።
ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ለሰዎች ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን በየቀኑ በመልቀቅ የሚለፋ ሲሆን ይህንን ሽልማት እንዲያሸንፍ ድምጽ እንሁነው። በ Tiktok creative award ድህረ ገጽ ውስጥ በመግባት ድምፃችሁን ስጡ
ኢትዮጵያ የሶማሊያ መንግስት በኢትዮጵያ ጦር ላይ ያቀረበው ክስ አሳዝኖኛል አለች
የሶማሊያ የጉዳይ ሚኒስቴር በትናንትናው እለት ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ኃይሎች ከአንድ ቀን በፊት በጊዶ ግዛት የምትገኘውን ዶሎ ከተማ አጥቅተዋል ሲል ከሶ ነበር።
ኢትዮጵያ ይህን ያለችው በአንካራ የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ በአዲስ አበባ ከሶማሊያ ልኡካን ጋር እየመከረች ባለችበት ወቅት ነው።
https://bit.ly/3BMgw2D
የዉጪ ጉዳይ ሚኒስትሯን ግብፅ ፤ ሚኒስቴር ድኤታዋን ደግሞ ኢትዮጵያ የላከችዉ ሶማሊያ ከአዲስአበባ ጋር ባላት ግንኙነት ዙሪያ ዉይይት አደረገች
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ሞሃመድ ኦማር ጋር መወያየታቸው ተነግሯል።
በዉይይቱ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር እና የአንካራውን ስምምነት መተግበር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ አተኩረዉ ነበር ተብሏል፡፡
ሶማሊያ ከኢትዮጵያ እና ከግብፅ ጋር በተመሳሳይ ቀን ዉይይት ላይ ተቀምጣ የነበረ ሲሆን የዉጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ አህመድ ሙአሊም ካይሮ በሀገራቸዉ የሰላም ማስከበር ላይ እንደምትሳተፍ እና ጦሯን ሶማሊያ እንደምታስገባ ተናግረዋል።
በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች እና በልዩ ልዩ የፓርቲ አጀንዳዎች ላይ ለመወያየት፣ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ጠዋት ስብሰባ ጀምረናል።
This morning we have began Prosperity Party’s Executive Committee meeting to discuss key national as well as party agenda items.
በሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተመራ ልዑክ ወደ አትዮጵያ እንደሚመጣ ተሰማ
በውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር አሊ ኦማር የተመራ የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት የልዑካን ቡድን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ እንደሚገባ የሶማሊያ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።
ይህ ጉብኝት ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ሲሆን ይህም በሁለቱም ሀገራት መሪዎች በተፈጠረው የአንካራ መግለጫ ላይ ተገልጿል።
የልዑካን ቡድኑ በጋራ በመከባበር፣ በጋራ ጥቅም እና በትብብር ላይ የተመሰረተ አጋርነት ለመፍጠር የለውጥ ዕድሎችን በማሰስ ላይ ያተኩራል።
ቅዳሜ'ለት በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ ኢትዮጵያ የዕዳ ሽግሽግ እንዲደረግላትና ይህም በቀጣይ ሳምንታት መፍትሄ ሊያገኝ እንደሚገባ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።
ፕሬዝዳንት ማክሮን፣ ኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በማድረጓ፣ አበዳሪዎች የአገሪቱን የሦስት ቢሊዮን ዩሮ ብድር የማሸጋሸግ ሂደት "በቀጣይ ሳምንታት" ውስጥ የማጠናቀቅ ሃሳብ እንዳላቸው ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ጋር እያካሄደች ያለችውን ንግግር ፈረንሳይ እንደምትደግፍም ፕሬዝዳንት ማክሮን አስታውቀዋል
🔶️ ውሳኔዎን የሚያደንቁበት ትርፋማ ኢንቨስትመንት ከአሚባራ ፕሮፐርቲ ! 🔶️
➣ ለ50 ቤቶች ብቻ የተዘጋጀ
ታላቅ ቅናሽ!
➣ ሸራተን ሆቴል አጠገብ
ወዳጅነት ፓርክ ፊትለፊት
ቅንጡ አፓርትመንቶች
ከ852,000 ብር ቅድመ ክፍያ
ጀምሮ
➣ ሁለት የመዋኛ ገንዳ,
የልጆች የእግር ኳስ ሜዳ,
የቅርጫት ኳስ ሜዳ
እንዲሁም የቤት ውስጥ
የበረዶ መንሸራተቻ
➣ ከባለ አንድ እስከ ባለ አራት
የመኝታ ቤት አማራጮች
➣ በ10% ቅድመ ክፍያ
በኢትዮጵያ ብር የሚዋዋሉት
➣ እስከ 25% የሚደርስ
ታላቅ ቅናሽ
ለበለጠ መረጃ
በ 0979804444
በቀጥታ ወይንም በዋትሳፕ
ይደውሉ
አሚባራ ፕሮፐርቲ
ለዘመናዊ ኑሮ ታስቦ የተገነባ
የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በአዲስ አበባ የነበራቸው ቆይታ ከአጼ ሚኒሊክ ጀምሮ አጼ ሃይለስላሴ ኮሎኔል መግስቱ ሃይለማሪያም እና አቶ መለስ ዜናዊ በቤተ መንግስት ይጠቀሙብቸው የነበሩ መኪኖችና ቁሳቁሶች የተተያዩ የአለም መንግስታት ለነገስታቱ የሸለሟቸውን ሽልማቶችና ሎችም ጥንታዊና ታሪካዊ ነገሮችን ብክብር ተቀምጠው ጎብኝተዋል::
Читать полностью…መረጃ‼️
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዲስ ፕሬዝዳንት ሾመ !
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ትላንት እና ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል አካሄዷል።
በጉባኤው ከሚጠበቁ ሁነቶች መካከል አንዱ የሆነው ቀጣዩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ምርጫ በዛሬው ዕለት ሲካሄድ ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በአብላጫ ድምፅ አሸንፏል።
ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በምርጫው 1️⃣1️⃣ ድምፆችን በማግኘት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በመሆን ማሸነፉ ታውቋል።
ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን በመተካት በሚቀጥሉት አራት አመታት ፌዴሬሽኑን በፕሬዝዳንትነት የሚመራ ይሆናል።
ዓለም ባንክ፣ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለማጠናከር የሚውል የ700 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጽድቋል።
ከብድሩ 90 በመቶው የንግድ ባንክን ሒሳብ ለማስተካከልና ባንኩን መልሶ ለማዋቀር እንደሚውል ዓለም ባንክ ገልጧል።
ከፊሉ ብድር ለብሄራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ማጠናከሪያና መዋቅራዊ ማሻሻያ እንደሚሰጥ ባንኩ ጠቅሷል።
ብድሩ በአራት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የሚለቀቀው፣ የባንኮቹ አፈጻጸም፣ የደንቦችና የመዋቅሮች ማሻሻያ ሂደት እየታየ የሚለቀቅ ነው። የብድሩ ዓላማ፣ የአገሪቱን የፋይናንስ ዘርፍ ጠንካራና አስተማማኝ ለማድረግና ተደራሽነቱን ለማስፋት ያለመ እንደኾነም ባንኩ ባሠራጨው አጭር መግለጫ አንስቷል።
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር ) በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ወንድሜ እና የኢትዮጵያ የልብ ወዳጅ የፈረንሳይ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ባለፉት ስድስት አመታት ለሁለተኛ ጊዜ ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ እላለሁ ብለዋል።
በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለው ግንኙነት የበለጠ በመጠናከር ላይ ይገኛል። ክቡር ፕሬዚዳንት በሚኖራቸው ቆይታ ፍሬያማ ውይይት እንደሚኖረን እምነቴ ፅኑ ነውም ሲሉ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልእክታቸውን ያሰፈሩት።
#attention #ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ #ከቴምር ሪልስቴት ላመለጣችሁ በድጋሜ አዲስ ሱቅ ሽያጭ አውጥተናል
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ በኩል
0939770177/0996856273
/channel/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
ከየመን የተተኮሰ ሚሳኤል በቴል አቪቭ 14 ሰዎችን አቆሰለ
የእስራኤል ጦር የአየር መቃወሚያ ስርአቱ ሚሳኤሉን መትቶ መጣል እንዳልቻለ ገልጿል።
ዝርዝሩን ያንብቡ፦ https://bit.ly/3Bv0ASp
ኢትዮጵያ ባለፋት አራት ወራት ከቡና የውጪ ንግድ ከ674 ሚሊዮን በላይ የአሜሪካን ዶላር ገቢ አገኘች
ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ አራት ወራት ውስጥ 98 ሺህ 999.38 ቶን ቡና ለውጪ ገበያ በመላክ ከ674 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል።
የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነትና የኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳህለ ማርያም ገብረ መድህን ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በዚህ ጊዜ ውስጥ ለሽያጭ ካቀረበችው የቡና ምርት 5 መቶ 31ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዳ ነበር።አያይዘውም ከእቅድ በላይ 150 ሺህ 3 መቶ 46ነጥብ 57 ቶን ቡናን ለገበያ ማቅረብ ችላለች ያሉት አቶ ሳህለ ማርያም በምላሹ 674 ነጥብ 55 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ አግኝታለች።
በዚህም ከታቀደዉ አንፃር 127 በመቶኛ ብልጫ ያለው ገቢ ተገኝቷል ሲሉ ተናግረዋል። አፈጻጸሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በመጠን 62 ሺህ 5መቶ 87 ነጥብ 58 ቶን እና በገቢ ደግሞ 2መቶ 26 ነጥብ 89 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይም 51 በመቶ ጭማሪ ተመዝግቧል።በ2017 በጀት ዓመት አራት ወራት የተላከዉ ቡና ከመዳረሻ ሀገራት አኳያ ሲታይ ጀርመን ቀዳሚዋ የኢትዮጵያ ቡና ገዢ ሀገር መሆኗ ተመላክቷል።
ወደዚህችዉ ሀገር 32 ሺህ 6 መቶ 66.48 ቶን ቡናን መላክ እንደተቻለ የተገለፀ ሲሆን 132ነጥብ 40 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል። በሌላ በኩል ወደ ሳዑድ አረቢያ 26ሺህ 579ነጥብ49 ቶን ቡና ለሽያጭ ቀርቦ 113 ነጥብ 83 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።እንዲሁም ባለፋት አራት ወራት 15 ሺህ 325 ነጥብ 9 ቶን ቡናን ለቤልጅየም በመላክ 71ነጥብ 59 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘት እንደተቻለ ሲገለፅ ይህን አፈፃፀም በማስመዝገብ እነዚህ ሀገራት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡
በገቢ ቅደም ተከተል የተቀሩት የገበያ መዳረሻ ሀገራት 4ኛ አሜሪካ፣ 5ኛ ደቡብ ኮሪያ ፣ 6ኛ ጃፓን፣ 7ኛ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ 8ኛ ዮርዳኖስ፣ 9ኛ ጣልያን እና 10ኛ አዉስትራሊያ በመሆን የኢትዮጵያ ዋንኛ የቡና ምርት መዳረሼ ናቸው። ከ1ኛ እስከ 10ኛ ደረጃን የያዙት ሀገራት በአጠቃላይ በመጠን 77 በመቶ እና በገቢ ደረጃ ደግሞ 78 በመቶ የዉጪ ምንዛሪ ግኝት ይሸፍናሉ፡፡ በጥቅሉ የእነዚህ ዋና 10 መዳረሻ ሀገራት ከ2016 አፈፃፀም ጋር ሲወዳደር በመጠን 84 በመቶ እና በገቢ ሲታይ የ60 በመቶ ጭማሪ አለው ሲል ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡
🔶️ ውሳኔዎን የሚያደንቁበት ትርፋማ ኢንቨስትመንት ከአሚባራ ፕሮፐርቲ ! 🔶️
➣ ለ50 ቤቶች ብቻ የተዘጋጀ
ታላቅ ቅናሽ!
➣ ሸራተን ሆቴል አጠገብ
ወዳጅነት ፓርክ ፊትለፊት
ቅንጡ አፓርትመንቶች
ከ852,000 ብር ቅድመ ክፍያ
ጀምሮ
➣ ሁለት የመዋኛ ገንዳ,
የልጆች የእግር ኳስ ሜዳ,
የቅርጫት ኳስ ሜዳ
እንዲሁም የቤት ውስጥ
የበረዶ መንሸራተቻ
➣ ከባለ አንድ እስከ ባለ አራት
የመኝታ ቤት አማራጮች
➣ በ10% ቅድመ ክፍያ
በኢትዮጵያ ብር የሚዋዋሉት
➣ እስከ 25% የሚደርስ
ታላቅ ቅናሽ
ለበለጠ መረጃ
በ 0979804444
በቀጥታ ወይንም በዋትሳፕ
ይደውሉ
አሚባራ ፕሮፐርቲ
ለዘመናዊ ኑሮ ታስቦ የተገነባ
ኢትዮጵያ በሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣው መግለጫ መሰረተ ቢስ መሆኑን ገለጸች
የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ዶሎ በተባለ ከተማ በተፈጠረው ክስተት የኢትዮጵያ ኃይሎችን መክሰሱ ኢትዮጵያን ማስቆጣቱን እና ክሱም ሀሰተኛ መሆኑን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ሀሰተኛ ውንጀላው በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማስተካከል የተጀመረውን ጥረት ለማስተጓጎል የታለመ ነው ብሏል።ይህም የአፍሪካ ቀንድን ሰላም ለመበጥበጥ የሚፈልጉ እና በቀጣናው ሁልጊዜም ሰላም እንዳይኖር የሚሰሩ የሶስተኛ ወገን አካላት ተግባር መሆኑን መግለጫው አትቷል።
በአንካራው ስምምነት ላይ እንደተገለጸው ሁለቱ ሀገራት ለሰላም የሚያደርጉት ቁርጠኝነት እንዳይደናቀፍ ክፍተት መፍጠር የለባቸውም ሲል ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።የኢትዮጵያ መንግስት ተመሳሳይ አደጋዎችን ለመከላከል ከሶማሊያ ፌዴራል መንግስት የሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር መስራት እንደሚቀጥልም መግለጫው አካቷል።
ኢትዮጵያ በአንካራ ስምምነት መሰረት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማደስ እና ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት አጠናክራ ትቀጥላለችም ተብሏል።
የሀገራቱ መሪዎች ለሰላም ያላቸው ቁርጠኝነት የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ቀጣናዊ ትብብርን እንደሚያጠናክርም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ አስታውቋል።
#TemerRealEstate በቴምር ሪልስቴት ለሽያጭ የወጡ 3 ሳይቶች
👉7ሳይቶችን ሰርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ካወጣናቸው 3 ሳይቶች
🎯1,ፒያሳ (ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት) ጀርባ
👉1መኝታ 46ካሬ =Soldout
👉2መኝታ 71ካሬ=
10%ቅድመ ክፍያ 745,000ብር
ሙሉ ክፍያ 7,455,000ብር
👉2መኝታ 93ካሬ=
10% ቅድመ ክፍያ 1,044,000ብር
ሙሉ ክፍያ 10,044,000ብር
👉3መኝታ 130ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,365,000ብር
ሙሉ ክፍያ 13,650,000ብር
👉3መኝታ 142ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,533,600ብር
ሙሉ ክፍያ 15,336,000ብር
👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው የሚጨርሱት
💥30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
0939770177/0996856273
/channel/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከሶማሊያ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከሶማሊያ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ ዳይሬክተር አብዱላሂ መሐመድ አሊ ጋር ተወያዩ።
🔶️ ውሳኔዎን የሚያደንቁበት ትርፋማ ኢንቨስትመንት ከአሚባራ ፕሮፐርቲ ! 🔶️
➣ ለ50 ቤቶች ብቻ የተዘጋጀ
ታላቅ ቅናሽ!
➣ ሸራተን ሆቴል አጠገብ
ወዳጅነት ፓርክ ፊትለፊት
ቅንጡ አፓርትመንቶች
ከ852,000 ብር ቅድመ ክፍያ
ጀምሮ
➣ ሁለት የመዋኛ ገንዳ,
የልጆች የእግር ኳስ ሜዳ,
የቅርጫት ኳስ ሜዳ
እንዲሁም የቤት ውስጥ
የበረዶ መንሸራተቻ
➣ ከባለ አንድ እስከ ባለ አራት
የመኝታ ቤት አማራጮች
➣ በ10% ቅድመ ክፍያ
በኢትዮጵያ ብር የሚዋዋሉት
➣ እስከ 25% የሚደርስ
ታላቅ ቅናሽ
ለበለጠ መረጃ
በ 0979804444
በቀጥታ ወይንም በዋትሳፕ
ይደውሉ
አሚባራ ፕሮፐርቲ
ለዘመናዊ ኑሮ ታስቦ የተገነባ
#attention #ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ #ከቴምር ሪልስቴት ላመለጣችሁ በድጋሜ አዲስ ሱቅ ሽያጭ አውጥተናል
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ በኩል
0939770177/0996856273
/channel/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
ዲጄ ኪን ታሟል
#Ethiopia | በመድረክ ስሙ ዲጄ ኪን በመባል ይታወቃል፣ መጠሪያ ስሙ ደግሞ ትርፌ ማንያህልUል ይባላል። ውልደቱና እድገቱ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ነው። ለሙዚቃና ለፋሽን ልዩ ፍቅር የነበረዉ ዲጄ ኪን፣ ገና ከልጅነቱ ጀምሮ የእንግሊዝኛ ሙዚቃዎችን እየሰማ ማደጉ እና በሳንፎርድ የእንግሊዝ ትምህርት ቤት ውስጥ መማሩ፣ ወደ ዲጄነት ሞያ እንዲገባ እንዳደረገው ይነገራል ። ዲጄ ኪን ለፋሽንና ለሞዴሊንግ ስራም ልዩ ፍቅር ስለ ነበረው ከታዋቂዋ ሞዴል ሊያ ከበደ ጋር በሞዴልነት አብሮ ይሰራ ነበር። ዲጄ ኪንን ከሁላችን ጋር እንዲተዋወቅ ያደረገው ግን FM አዲስ 98.5 ሬዲዮ ጣቢያ ዉስጥ በሙዚቃ ፕሮግራም አቅራቢነትና በዲጄነት ከዛሬ 25 ዓመት በፊት ይሰራ በነበረበት ወቅት ነው። በወቅቱ ደጄ ኪን ዝነኛ ዲጄ እና ዘናጭ ነበር። ዲጄ ኪን የሙዚቃ ስራዎቹን በዲጄነት በኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ውጭ አቅርቧል።
ዲጄ ኪን በ1990ዎቹ የተዋጣለት የሙዚቃ ባለሞያ ነበር ፣ በሽራተን አዲስ ውስጥ በጊዜው ቋሚ ዲጄ ሆኖ ያገለግል ነበር። አዲስ አበባ ዉስጥ አባ ጉበን የተባለ ሬስቶራንት ከፍቶ የነበረ ሲሆን በተለይ በውጭ ሀገር ሰዎች ተመራጭ ስፍራ ሆኖ ነበር።
እጅግ ፈጣንና ብሩህ አዕምሮ የነበረው ዲጄ ኪን ፣ ከ15 ዓመት በፊት ጀምሮ መፅሐፍ ቅዱስን በማንበብ አካሄዴ የተሳሳተ ነው፣ ሰው በጉብዝናው ወራት ፈጣሪውን ሊያስብ ይገባዋል ብሎ በማመን ዲጄነቱን ሙሉ ለሙሉ ትቶ ወደ መንፈሳዊው ዓለም ገባ፣ አዘውትሮ ወደ ገዳማት ይሔድ የነበረዉ ዲጄ ኪን፣ ወደ መንፈሳዊው ዓለም በመግባቱ ዘላለማዊ ደስታ እንደገፕ ይናገር ነበር። ወጣቶች በእግዚአብሔር ቤት እንዲመላለሱ የተለያዩ ፅሁፎችን በመፃፍና ሲዲ በማሳተም በአብያተ ክርስቲያናት ያከፋፍል ነበር። ዲጄኪን ታዋቂ የነበረውን አባ ጉበን የተባለውን ሬስቶራንቱንም ሙሉ ለሙሉ በመዝጋት የሙሉ ጊዜ የእግዚአብሔር አገልጋይ በመሆን ጊዜውን ለእግዚአብሔር የሰጠ ወጣት ነበር።
ቤተሰቡን እጅግ የሚወደውና የሚያከብረው ዲጄኪን ሁለት ታናናሽ ወንድሞቹን የሚረዳቸው እና የሚደግፋቸውእርሱ ነው።
ይህ ወጣት የእግዚአብሔር አገልጋይ ፣ ዛሬ ላይ የጤና እክል አጋጥሞታል ፣ ለ ለሰዎች ልዩ ፍቅር የነበረዉ ጠንካራው ዲጄ ኪን ዛሬ የእኛን እርዳታ ያስፈልገዋል፡ ዲጄ ኪን ኩላሊቶቹ መስራት በማቆማቸው ዲያሌሲስ ያደርጋል፣ የስኳር በሽተኛ መሆኑ ነገሮችን ውስብስብ ያደረገበት ሲሆን፣ አይኑን ስለጋረደውና ፣ አይኖቹ የማየት አቅማቸው ስለቀነስ አስቸኳይ የአይን ቀዶ ህክምና እንደሚያስፈልገው ዶክተሮች ገልጸውለታል።
በበሽታው ምክንያት የእግር ህመም ስላለበትም እንደፈለገው እንዳይንቀሳቀስ ገድቦታል። በፍጥነትም ወደ ዉጭ ሀገር ሄዶ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ እንደሚገባው የህክምና ባለሞያዎች ገልጸውለታል።
ዲጄ ኪንን ለመርዳት በተከፈተው የጎ ፈንድሚ ገፅ ገብተው የሚችሉትን አስተዋፅዖ እንዲያበረከቱ እየጠየቅን ፣ ለሌሎችም መልዕክቱ እንዲደርስ ይህንን እንዲያ ጋሩልን በአክብሮት እንጠይቃለን ። እግዚአብሔር ለዲጄ ኪን ጤንነቱን መልሶ እንዲሰጠው ምኞታችንና ፀሎታችን ነው።
የጎ ፈንድሚ ሊንክ
https://gofund.me/bcb24849
የዲጄ ኪንን አጭር ታሪክ በቪዲዮ ለመመልከት ከዚህ በታች ያለዉን ሊንክ ተጭነው ይመልከቱ::
https://youtu.be/dWRBsArurU8?si=bzzfW4zWm0DtUrnM
መዝናኛ ሚዲያ፣ ዳንኤል ገብረማርያም፣ ከአሜሪካ
የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በአዲስ አበባ የነበራቸው ቆይታ ከአጼ ሚኒሊክ ጀምሮ አጼ ሃይለስላሴ ኮሎኔል መግስቱ ሃይለማሪያም እና አቶ መለስ ዜናዊ በቤተ መንግስት ይጠቀሙብቸው የነበሩ መኪኖችና ቁሳቁሶች የተተያዩ የአለም መንግስታት ለነገስታቱ የሸለሟቸውን ሽልማቶችና ሎችም ጥንታዊና ታሪካዊ ነገሮችን ብክብር ተቀምጠው ጎብኝተዋል::
Читать полностью…#TemerRealEstate በቴምር ሪልስቴት ለሽያጭ የወጡ 3 ሳይቶች
👉7ሳይቶችን ሰርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ካወጣናቸው 3 ሳይቶች
🎯1,ፒያሳ (ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት) ጀርባ
👉1መኝታ 46ካሬ =Soldout
👉2መኝታ 71ካሬ=
10%ቅድመ ክፍያ 745,000ብር
ሙሉ ክፍያ 7,455,000ብር
👉2መኝታ 93ካሬ=
10% ቅድመ ክፍያ 1,044,000ብር
ሙሉ ክፍያ 10,044,000ብር
👉3መኝታ 130ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,365,000ብር
ሙሉ ክፍያ 13,650,000ብር
👉3መኝታ 142ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,533,600ብር
ሙሉ ክፍያ 15,336,000ብር
👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው የሚጨርሱት
💥30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
0939770177/0996856273
/channel/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
🔶️ ውሳኔዎን የሚያደንቁበት ትርፋማ ኢንቨስትመንት ከአሚባራ ፕሮፐርቲ ! 🔶️
➣ ለ50 ቤቶች ብቻ የተዘጋጀ
ታላቅ ቅናሽ!
➣ ሸራተን ሆቴል አጠገብ
ወዳጅነት ፓርክ ፊትለፊት
ቅንጡ አፓርትመንቶች
ከ852,000 ብር ቅድመ ክፍያ
ጀምሮ
➣ ሁለት የመዋኛ ገንዳ,
የልጆች የእግር ኳስ ሜዳ,
የቅርጫት ኳስ ሜዳ
እንዲሁም የቤት ውስጥ
የበረዶ መንሸራተቻ
➣ ከባለ አንድ እስከ ባለ አራት
የመኝታ ቤት አማራጮች
➣ በ10% ቅድመ ክፍያ
በኢትዮጵያ ብር የሚዋዋሉት
➣ እስከ 25% የሚደርስ
ታላቅ ቅናሽ
ለበለጠ መረጃ
በ 0979804444
በቀጥታ ወይንም በዋትሳፕ
ይደውሉ
አሚባራ ፕሮፐርቲ
ለዘመናዊ ኑሮ ታስቦ የተገነባ
ከፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በብሔራዊ ቤተመንግሥት በነበረን የሁለትዮሽ ውይይት ሰፋ ያለ መጠነርዕይ ባላቸው የሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል። ጠሚ አቢይ አህመድ
ክቡር ፕሬዚዳንት እና የፈረንሳይ መንግሥት በብሔራዊ ቤተመንግስት እና በመካሄድ ላይ ባለው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እድሳት ሥራዎች ላደረጉት አስተዋፅዖ ምስጋናዬን አቅርቤያለሁ። በውይይታችን በተለያዩ ዘርፎች የሚኖሩ ትብብሮችን የፈተሽን ሲሆን የፈረንሳይን ኢንቨስትመንት መጨመርን አስመልክቶ ብሎም በትምህርት እና ባሕል ዘርፎች ያለንን ግንኙነት በማጠናከር ጉዳዮች ላይ ተነጋግረናል። ታሪካዊ ትስስራችንን ይበልጥ የመገንባትን አስፈላጊነትንም በውይይታችን አፅንዖት ሰጥቼ አንስቻለሁ።
አሜሪካ አዲሱን የሶሪያ መሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል አውጥታው የነበረውን የእስር ማዘዣ ሰረዘች
በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተመራ ልዑክ ከአህመድ አልሻራ ጋር ውይይት አድርጓል።
https://bit.ly/41NfXAk
በስነ ምግባር ጉደለት ከሚሰራበት ተቋም የተሰናበተው ግለሰብ የመስሪያ ቤቱን ስም በመጠቀም የተቋሙ ሰራተኛ መስሎ የማታለል ወንጀል ሲፈፅም በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን ፖሊስ ገለፀ።
***
ከዚህ ቀደም የፌዴራል ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሰራተኛ የነበረ እና በተለያየ የስነ ምግባር ጉደለት ከተቋሙ የተሰናበተ ታረቀኝ ክፍሌ የተባለ ተጠርጣሪ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኛ እንደሆነ በማስመሰል የተለያዩ ግለሰቦች ያሉበት የመንግስት የኪራይ ቤቶች ላይ እየተዘዋወረ የኪራይ ቤቶቹ ታፔላ ወደ ዲጂታል እየተቀየሩ ነው በማለት በተቋሙ ስም የተዘጋጁ ቅፆች የያዘ በማስመሰል እና ሀሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም ታፔላውን ወደ ዲጂታል ማስቀየር አለባችሁ በማለት ከሁለት የግል ተበዳዮች ከእያንዳንዳቸው 1ሺህ 7መቶ ብር የተቀበለ ሲሆን በግል ተበዳዮች ጥቆማ ሰጭነት በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
የማታለል ወንጀሉ የተፈፀመው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ጎጃም በረንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኙ የመንግስት ኪራይ ቤቶች ውስጥ ባሉ ነጋዴዎች ላይ ነው።
አንዳንድ የሥነ ምግባር ጉድለት ያለባቸው ግለሰቦች የግል ጥቅማቸውን በማሰብ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የተለያዩ ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ሊኖሩ እንደሚችሉ በመገንዘብ ለመሰል የወንጀል ድርጊት ህብረተሰቡ እንዳይዳረግ በማንኛውም ጉዳይ ለሚጠይቀውና ለሚጠየቀው አገልግሎት ህጋዊነቱን ከማረጋገጥ ባሻገር አስፈላጊውን መረጃና ማስረጃ መጠየቅ እንደሚያስፈልግ ፖሊስ አሳሰቧል ።
*
🔶️ ውሳኔዎን የሚያደንቁበት ትርፋማ ኢንቨስትመንት ከአሚባራ ፕሮፐርቲ ! 🔶️
➣ ለ50 ቤቶች ብቻ የተዘጋጀ
ታላቅ ቅናሽ!
➣ ሸራተን ሆቴል አጠገብ
ወዳጅነት ፓርክ ፊትለፊት
ቅንጡ አፓርትመንቶች
ከ852,000 ብር ቅድመ ክፍያ
ጀምሮ
➣ ሁለት የመዋኛ ገንዳ,
የልጆች የእግር ኳስ ሜዳ,
የቅርጫት ኳስ ሜዳ
እንዲሁም የቤት ውስጥ
የበረዶ መንሸራተቻ
➣ ከባለ አንድ እስከ ባለ አራት
የመኝታ ቤት አማራጮች
➣ በ10% ቅድመ ክፍያ
በኢትዮጵያ ብር የሚዋዋሉት
➣ እስከ 25% የሚደርስ
ታላቅ ቅናሽ
ለበለጠ መረጃ
በ 0979804444
በቀጥታ ወይንም በዋትሳፕ
ይደውሉ
አሚባራ ፕሮፐርቲ
ለዘመናዊ ኑሮ ታስቦ የተገነባ
"አዲስ የትግል አቅጣጫ እንከተላለን" ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል
በህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ቡድን "የእምቢታ ዘመቻ" በሚል ከትናንት ጀምሮ በመቀሌ ከተማ ስብሰባ እያካሄደ ይገኛል፡፡
በዚሁ ስብሰባም የህወሓት ቡድን በቀጣይ አዲስ የትግል ስልት እንደሚከተል እና አጠቃላይ አባላቶቹ በመጠቀም "የእምቢተኝነት ዘመቻ" ያለው እንቅስቃሴ ለማድረግ ያቀደ ሲሆን ለዚህ ዘመቻ "እምቢ ለብሔራዊ ክህደት፣ ለአገዛዝ እና ብተና" የሚል መፈክር እንደተሰጠው አስታውቋል፡፡