negere_evangelical | Unsorted

Telegram-канал negere_evangelical - ነገረ ወንጌላውያን

2910

በወንጌላውያን አማኞች ዘንድ የሚፃፉ ፅሁፎች፣ ዘገባዎችና ዜናዎች ይቀርባሉ! ትምህርቶች፣ መረጃዎችና ምካቴ እምነቶች በዚህ ቻናል ይስተናገዳሉ! በተለያዮ ሶሻል ሚዲያዎች የሚገኙ ፀሐፊያን የሚፅፉቸው ፅሁፎችን እናጋራለን።

Subscribe to a channel

ነገረ ወንጌላውያን

ዘረኝነት ኀጢአት ነው፤ ኑፋቄም ነው።

“እርሱ አካሉ የሆነችው የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፤ በሁሉ ነገር የበላይነት ይኖረው ዘንድ እርሱ የመጀመሪያ፣ ከሙታን መካከልም በኵር ነው። እግዚአብሔርም ሙላቱ [πλήρωμα - ፕሌሮማ፤ ምሉዕ የሚያደርግ ሙሉነት] ሁሉ በእርሱ ይሆን ዘንድ ወዶአልና፤ በመስቀሉ ላይ በፈሰሰው ደሙ ሰላምን በማድረግ በምድርም ሆነ በሰማይ ያለውን ነገር ሁሉ በእርሱ በኩል ከራሱ ጋር አስታረቀ።” (ቈላ. 1÷18-20)

“ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለ መከፋፈል በሥላሴ ክብር ላይ የተሰነዘረ ዐመፅ ነው . . . ቤተ ክርስቲያን ይህን ስታደርግ፣ የራሷን ውበት ትገፋለችል፤ የጥንት ክብሯንም ታቃልላለች።"*

የእግዚአብሔር በፈጣሪነት የራስ ግላጭ (self-disclosure) ወሳኝ ተልእኮአዊ እንድምታዎች አሉት። “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ” (ዘፍ. 1፥1። እግዚአብሔር ዘላለማዊ ነው! ይህ ዘላለማዊ አምላክ፣ የፍጠረት መገኛ ነው። ሰውን ጨምሮ የመንፈሳዊ፣ በዐይን የሚታየውና የማይታየው ገሃዱ ዓለም መገኛ እርሱ ራሱ እግዚአብሔር ነው። እርሱ ለዘላለማዊ ህልውናው ሰበብ የለሽ ነው። ጅማሬም ፍጻሜም የለውም - ስሙም "ያለና የሚኖር" ነው። የሚልቀው፣ አቻ የሆነው ወይም የሚያንሰው አምላክ የለውም። በእርሱና በፍጥረት መካከል ትልቅ የማንነትና የባሕርይ ልዩነት አለ። ፍጥረት፣ ሰውን ጨምሮ፣ የእርሱ ተቀጥያ አይደለም። ፍጥረት ሁሉ ተደግፎ የተያዘው በእርሱ ብቸኛ ፈጣሪነትና ሉዓላዊነት ነው። የፍጥረት ዋጋ፣ ትርጕምና ዐላማ ምንጩ እራሱ እግዚአብሔር ነው።

እግዚአብሔር ሰውን ፈጠረ። “ስለዚህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሰውን በራሱ መልክ ፈጠረው፤ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም) መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጐ ፈጠራቸው። እግዚአብሔርም (ኤሎሂም)፣ ‘ብዙ ተባዙ፤ ምድርን ሙሏት፤ ግዟትም፤ የባሕርን ዓሦች፣ የሰማይን ወፎች፣ እንዲሁም በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሕያዋን ፍጡራንን ሁሉ ግዟቸው’ ብሎ ባረካቸው።” (ዘፍ 1፥27-28)።

ከዚህ እውነት የሚመነጩ ዘጠኝ ጊዜ የማይሽራቸው ተልእኮአዊ ፋይዳዎች አሉ፦

1) የእግዚአብሔርን ፈጣሪነት- የፈጣሪና የተፈጣሪ ኑባሬአዊና የዐይነት ልዮነት (ontological and categorical difference)

2) ሰው በእግዚአብሔር፣ ለእግዚአብሔር ክብር የተፈጠረው ነው፤ ስለዚህ የሰው ባለቤት ራሱ ልዑል እግዚአብሔር ነው።

3) እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው በራሱ አምሳያ ነው፤ ስለዚህ የሰው ኑባሬአዊ ዋጋ (ontological value)፣ የሕይወት ክቡርነት (dignity) ወይም ንጽሐ-ሕይወት (sanctity) በእግዚአብሔር አምሳያ መፈጠሩ ነው።

4) “ወንድና ሴት አድርጐ ፈጠራቸው”- ወንድ እና ሴት እኩል ናቸው፤ አንድ ዐይነት ግን አይደሉም። በኑባሬ እኩል፣ በተፈጥሮ ተደጋጋፊ የድርሻ ልዩነት አላቸው

5) የማኅበረ ሰብ መሠረት ቤተ ሰብ ነው፤ የቤተ ሰብ መሠረት “የወንድ እና የሴት” እኩልነት፣ ጾታዊና የድርሻ ልዩነት ነው። በአጭሩ - ወንድ ባልና አባት ሲሆን፤ ሴት ሚስትና እናት ናት።

6) ሰው ከነጻ ፈቃድ ጋር ነው የተፈጠረው፤ ከዚህ አንጻር ከእግዚአብሔር ጋር፣ እርስ በእርስ እንዲሁም ከፍጥረት ጋር ባለው መስተጋብር በእግዚአብሔር ዘንድ ተጠያቂ የሆነ ሞራላዊ ፍጡር (moral being) ነው።

7) ሰው የፍጥረት ባለቤት ሳይሆን፣ የእግዚአብሔር ፍጥረት እንደ ራሴ በመሆን ጠባቂ ነው።

8 ሰው ሁሉ የፍጥረት በረከት እኩል ተካፋይ ነው።

9) ፍጥረት ግንኙነታዊ ነው። ሰው የተፈጠረው ከእግዚአብሔር ጋር፣ እርስ በእርስ እንዲሁም ከተፈጥሮ ጋር በኅብረት፣ በስምረት፣ በፍቅርና በሰላም ለእግዚአብሔር ክብር እንዲኖር ነው።

እነዚህ ፋይዳዎች፣ በተለይም ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ ሰውና ስለ ፍጥረት ማንነት፣ እንዲሁም በመካከላቸውም ሊኖረው የሚገባውን ግንኙነት አስመልክቶ ትልቅ ተልእኮአዊ እንድምታ አላቸው። ሰው የእግዚአብሔር አምሳያ ነው። በዚሁ ዘመን በማይሽረው ኑባሬአዊ እውነት መሠረት፣ የሰው የክቡርነት ዋጋ ማኅበራዊ፣ ጐሣሳዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሥሪት በፈጠረው እሴት በፍጹም ሊለካ አይችልም። ማንንም ሰው ከትውልድ አገሩ፣ ከቈዳው ቀለም፣ ከብሔሩና ከጐሣው፣ ከቋንቋውና ከባህሉ የተነሣ አናሳና ገሚሰ ሰው አድርጐ መቊጠር፣ ማግለል፣ መበደል፣ ፍትሕ መንፈግና ከምድር በረከት ማጕደል፣ ከእግዚአብሔር ፈጣሪነት ጋር ቀጥታ ግጭት ነው። ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ለማድረግ፣ እርሱን ለማምለክና ለማክበር መፈጠሩ፣ እንዲሁም የሰው ሁሉ የፍጥረት በረከት ባለዐደራነትና እኩል ተካፋይነት መሠረቱ፣ የእግዚአብሔር ብቸኛ የፈጣሪነት የራስ ግላጫ ነው።

ዘረኝነት የማኅበራዊ ትስስርን መሠረት ከሥሩ ያናጋል። ፓለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶችን የበለጠ ያብሳል። ከዚህ ባለፈ መልኩ ግን፣ በእግዚአብሔር ፈጣሪነትና መግቦት ላይ ቀጥታ የተሰነዘረ ዐመፅ ነው። ለአገራችን ፈረጅ ብዙ ስብራቶች ምክንያቶች ከዋነኛቹ አንደኛው ነው። ማኅበራዊ ችግር ብቻ ሳይሆን፣ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ተግዳሮት ነው።

የክርስቶስ አማራጭ ማኅበረ ሰብ ዘረኝነት የሚቃወምበት ምክንያቶች፡-

1) ኑፋቄ ስለሆነ! ክርስቶስ በመስቀል ሞቱ ያሰገኘውን ቤዛዊ ዕርቅ (ከእግዚአብሔር ጋር፣ እርስ በእርስ እና ከተፈጥሮ ጋር) አፍራሽ ስለሆነ።

2) ከአዲሱ የክርስቶስ ቤተ ሰብ ማንነት ጋር ቀጠተኛ ተቃርኖ ስላለው። (ገላ 3፥28፤ 5፥9–10፤ ራእ 7፥9–12፤ 22፥1–5)።

3) ጌታችን ወደ መስቀል ሞት ከመሄዱ በፊት ስለ አማኞች አንድነት ከጸለየው ጸሎት ጋር በጠላትነት ስሊሚቆም። (ዮሐ 17)

4) የራስን ዘር ዋጋ (self-worth) ወደ ምልኩነት (divinity) የማላቅ ኀጢአት ስለሆን። ሰው ሁሉ የእግዚአብሔር ክብር የጐደለው ኀጢአተኛ ነው። በበደሉና በኀጢአቱም ምክንያት በእግዚአብሔር የቁጣ ፍርድ ሥር ያለ ሙት ነው፤ ሕይወት የሚያገኘውም በክርስቶስ ብቻ ነው። ሰው ሁሉ የሚፈረጀው ወይ በመጀመሪያው አዳም ወይም በሁለተኛው አዳም በክርስቶስ ነው። ከዘሩ የተነሣ፣ “ንጹሕና ምርጥ” የሚባል፣ ወይም ከማንነቱ የተነሣ "የተለየ ስፍራ" የተሰጠው ሕዝብ የለም (ሮሜ 3፥10–20፤ 5÷12–21)።

5) የራስን ማንነት፣ እንደ ክብርና እንደ ጽድቅ በመቁጠር፣ የክርስቶስን ቤዛዊ ሥራ ስለሚያቃልልና የክርስቶስን ማኅበረ ሰብ አማራጭነት ስለሚያፈርስ።

6) አንድን ሕዝብ በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ፣ ከሰው ሁሉ የተለየና የበላይ ክብርና ስፍራ እንዳለው እንዲያስብ ስለሚያደርግ።

7) ከእግዚአብሔር ለሰው ሁሉ በተለይም ከማንነታችው የተነሣ ለሚገፉና ለድኾች ካለው ፍቅር፣ ርኅራኄና ፍትሕ ጋር ቀጥታ ስለሚጋጭ።

8. ዘረኝነት ጨቋኝ፣ ግፈኛና አግላይ ብቻ ሳይሆን፣ የሌሎች ሕዝቦችን መልክ፣ ባህልና ቋንቋ በመናቅ በሰው ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን አምሳያ ስለሚገፍፍ። ዘረኝነት ጥላቻ ነው፤ ክርስቶስ ጥላቻን፣ ከነፍሰ ገዳይነት ጋር አቈራኝቶታል። (ማቴ 5፥20–21፤ 1ዮሐ 3፥15–17)። በከፋም መልኩ ዘረኝነት ከዐመፅ ጋር ሲጋባ፣ የንጹሐን ደም ስለሚያፈስስ የዲያብሎስ እኩይ መገለጫና የእግዚአብሔር ጠላት ነው።

9) ሌላውን ሕዝብ ከምድር ትሩፋት እኩል ተጠቃሚ እንዳይሆን ስለሚያገልልና ስለሚበድል።

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

"መንፈስን አታዳፍኑ"
***
ከጠፊው ዓለም የተጠሩት የእግዚአብሔር ኅሩያን (ምርጦች) የእምነት ተጓዦች ናቸው። አዎ አማኞች ወደ ቤታችን በመኼድ ላይ ያለን የእምነት ተጓዦች ነን። ወደ ዘላለም ቤታችን በመኼድ ላይ ነን። ቲም ፌሎስ አንድ አገላለጽ አለው፤ “ዘላን ቤት የለውም፤ ሽፍታ ከቤቱ የሸሸ ነው፤ እንግዳ ከቤቱ የራቀ ሲኾን፥ የእምነት ተጓዥ ግን ወደ ቤቱ የሚኼድ ነው።” አዎ፥ ተጓዦች ነን። https://youtu.be/1isHkE-ZfU8
.
በእምነት በምንጓዝበት ጊዜ ታዲያ ብቻችንን አይደለንም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው። የዚህ ዐብሮነቱ ማረጋገጫው ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ማደሩ ነው። አዎ፥ ጌታ እንደ ተስፋ ቃሉ “ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንኾን፥ በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው” (ቲቶ 3፥6-7)። ...
.
ከማንኛውም ክፉ ትምህርትና ተመክሮ ለመራቅ መፍትሔው እውነተኛውን አሠራር ማዳፈን አለመኾኑን መረዳት የተገባ ነው (1ቆሮ. 14፥39-40)። በመንፈስ ነጻነትና በድንጋጌ ሥርዐት መካከል ተገቢ ሚዛን መጠበቅ ያስፈልጋል። ትእዛዙም “መንፈስን አታጥፉ፤ ትንቢትን አትናቁ፤ ኹሉን ፈትኑ፤ መልካሙንም ያዙ፤ ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ” (1ተሰ. 5፥20) የሚል ነውና። ..
.
... ሙሉውን መልእክት ለማግኘት፦ https://youtu.be/1isHkE-ZfU8

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የመጽሐፍ ምረቃ
የወንድም ጆንሰን እጅጉ ሁለተኛ መጽሐፍ የሆነው የመለኪያ ያለህ የፊታችን እሁድ መጋቢት 3 ይመረቃል። ምርቃቱ በሳር ቤት ሙሉ ወንጌል ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ይከናወናል።

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

https://www.bbc.com/amharic/articles/czq0xq7zzv9o?at_link_origin=BBC_News_Amharic&at_bbc_team=editorial&at_link_id=77021998-B65C-11ED-A7B5-A7353AE5AB7B&at_campaign=Social_Flow&at_format=link&at_link_type=web_link&at_medium=social&at_campaign_type=owned&at_ptr_name=facebook_page

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የመጽሐፍ ምረቃ!

በወንድም ዲያቆን አግዛቸው ተፈራ የተጻፈው "ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ እና አባ እስጢፋኖስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ" የተሰኘው መጽሐፍ የፊታችን እሑድ የካቲት 19 ከ8:30 ሰዓት ጀምሮ ይመረቃል። ቦታው አራት ኪሎ ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ላይ ቤል ኤር አካባቢ በሚገኘው አቤንኤዘር ግቢ ውስጥ ይሆናል። ትታደሙ ዘንድ ተጋብዛችኋል።

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

አገር አቀፍ የምልጃና የንስሓ የጸሎት ጥሪ
መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

አቤቱ ፊትህን አብራልን!

ጌታችን በመስቀል ቤዛዊ ሞቱ፣ በእግዚአብሔርና በሰው እንዲሁም በሰው መካከል ያለውን የጥልን ግድግዳ ለአንዴና ለዘላላም በማፍረስ አንድ አዲስ ሰው ፈጥሯል። “. . . ሁለቱን አንድ ያደረገ፣ የሚለያየውንም የጥል ግድግዳ ያፈረሰ ሰላማችን እርሱ ራሱ ነውና” (ኤፌ. 2፥14-15)። አይሁድ፣ አሕዛብ፣ ወንድና ሴት፣ ባርያና ጨዋ አንድ ሆነዋል። ከዚህ ዘላለማዊ እውነት የተነሣ፣ የክርስቶስ ማኅበረ ሰብ መታወቂያውም ሆነ ውቅሩ ዘር፣ ቋንቋ፣ ባህል፣ መደብ ወይም ፖለቲካዊ ርእዮተ ዓለም አይደለም። እነዚህ ሁሉ ማንነቶች አንጻራዊ ሆነዋል። የዚህን ማኅበረ ሰብ የእርስ በእርስም ሆነ ከሌሎች ጋር ያለውን መስተጋብር የሚገዛው ዕሴት በክርስቶስ ያገኘው አዲሱ ማንነት ነው። ክርስቶስ በመስቀሉ ያፈረሰውን ግድግዳ መልሰን የምናቆም ከሆነ፣ ምን ተስፋ አለን?

በምድር ላይ ካሉ ማኅበረሰቦች ሁሉ፣ የክርስቶስን ማኅበረሰብ ልዩ የሚያደርገው ይኸው በመስቀሉ ሥራ ብቻ የተገኘው ማንነት፣ ሰላምና አንድነት ነው። ዘላለማዊ የእግዚአብሔር ቤተሰብ ሆኗል! “ከቅዱሳን ጋር የአንድ አገር ዜጋ፣ የእግዚአብሔርም ቤተሰብ አባል” (ኤፌ 2፥19) የሆነው በክርስቶስ መስቀል ቤዛዊ ሥራ ነው። ይህ እግዚአብሔራዊ ቤተ ሰብነት፣ በየትኛውም ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ዐውድ የማይገረሰስ ነው። ቤተ ክርስቲያን የፓለቲካ ሥርዓት በተለወጠ ቁጥር አትለወጥም፤ አትከፈልም፤ ማንነቷና መልእክቷም አይቀየሩም። ለሕልውናዋም ሆነ ለመልእክቷ የምትደገፈው በእግዚአብሔር ላይ ብቻ ነው። ለዘላለም የክርስቶስ ናትና!

በበዓለ አምሳ ቀን የወረደው መንፈስ ቅዱስ ነበር፣ ከልዩ ልዩ ባህል፣ ነገድና ቋንቋ የተሰበሰበውን ሕዝብ አንድ ያደረገው። ይህን ዓይነት አንድነት ቀደም ሲል፣ የሮም ፓለቲካዊ ርእዮተ ዓለም ወይም ይሁዲነትን ጨምሮ በወቅቱ የነበሩ ሃይማኖቶች ሊሰጡ አልቻሉም ነበር። አሁን ግን ከሰሙትና ከተቀሉት ወንጌል የተነሣ፣ በክርስቶስ አንድ መሆናቸውን ተረድተዋል። ይህ አንድነት ቅዱስና ዘላለማዊ ነው። ስለዚህ የክርስቶስ ማኅበረሰብ ውበቱ ልዩነቱ ነው። ለእግዚአብሔር ለራሱ የተለየ ቅዱስ ሕዝብ በሆነበት መጠን ያህል ብቻ ነው ለሌላው ሕዝብ የዕርቅ፣ የሰላምና የአንድነት አማራጭ የሚሆነው። በርግጥ ልዩ የእግዚአብሔር ሕዝብ ከሆንን፣ የሚገዛንም ዋናው ፋይዳ ደግሞ ከሕዝብ፣ ከነገድና ከቋንቋ የተዋጀንበት ማንነት ከሆነ፣ እርስ በእርስም ሆነ ሌሎችን በብሔርተኝነት መነጽር ልንመለከት አንችልም (ራእ 5፥ 8-10)።

የብዙዎቻችን መገኛ የሆችውን የተከበረችው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እንዲሁም የወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያንን ስብራቶች እግዚአብሔር ይጠግን፤ ወደራሱ ይመልሰን፤ እንደ ቅዱስ ቃሉም እውነት ብቻ መልሶ ያድሰንም። "እረኛ እንደሌላቸው በጐች ስለ ነበሩ አዘነላቸው" (ማር. 6፥4) ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ ታላቁ የበጐች እረኛ የሆነው ክርስቶስ፣ ወሰን በሌለው ቸርነቱና ርኅርኄው ይጠብቀን። በተለይም በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ለኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰላም ይሁን።

አቤቱ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ፤ "መልሰን፤ እንድንም ዘንድ፣ ፊትህን አብራልን።" (መዝሙር 80፥3)

አሜን!

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ሃገራዊ ቤተ ክርስቲያኖች (National Churches)

እንዲህ እንደዛሬው Free Churches (ነጻውያን) ከመብዛታቸው በፊት ሃገርን የሚወክሉና በሃገርም የሚወከሉ ቤተ ክርስቲያናት ብዙ ነበሩ። እንደ ምሳሌ የጀርመኗ ሉተራውያን፣ የእንግሊዟ አንገሊካን፣ የራሺያዋ ኦርቶዶክስ፣ የኢትዮጵያዋ ኦርቶዶክስ ... ወዘተረፈ ይዬኹሉ መጥቀስ ይቻላል። እነዚህን ሁሉ ለመዘርዘር አይደለም የዚህ ልጥፍ ዓላማ።

የሃገራዊ ቤተ ክርስቲያን ባሕርይ እና በመቦዳደስ የተከፈቱ (የተተከሉ አልልም መቼም) ጠባይ ለየቅል ነው። የ free churchesም ባሕርይ ይለያል፤ በተለይ አሁን አሁን ሃገራችንን ከወረሩት Customers Oriented Churches በጣም ይለያል። እነዚሁ Customers Oriented Churches ደግሞ ሃገራዊ ቅኝትና ሃገራዊ ይዘት ያላቸውን 'ሲዘልፉ'ና ንግርት ሲያወጡባቸው (ያው ትንቢት ነው የሚሉት እነሱ) የባሰ ግራ ያጋባል።

መጀመሪያ ቤተ ክርስቲያን ሁኑ! ምክሬ ነው። What makes the church - church? የሚለውን ጥያቄ አስቀድማችሁ መልሱ። ዘመንና የሚለዋወጥ ጊዜ ቤተክርስቲያንን ቤተክርስቲያን አያደርጋትም። መንግሥታዊ ድጋፍም ይሁን ፈቃድ ቤተክርስቲያንን ቤተክርስቲያን አያደርጋትም። እሳት የላሰ ጮሌ ተናጋሪም (አንዳንዶች እንዲህ ዓይነቱን 'የተቀባ' ይላሉ) ስላለን ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን አትሆንም። የእግዚአብሔር በመካከሏ መኖር ነው ቤተክርስቲያንን ቤተክርስቲያን የሚያደርጋት።

እናም እግዚአብሔር በመካከላችን አለ ወይ ብለን እንጠይቃለን። ስሜታችንንና ግላዊ መረዳታችንን ለመልስነት ከማቅረባችን በፊት በመካከላችን ሊኖር የወደደው አምላክ የሁሉ አምላክ እንጂ በአምሳላች እንደ ምሳሌያችን የፈጠርነውና ለስሜታችን ቅርብ የሆነ 'አምላክ' አለመሆኑን እናረጋግጥ (የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን ያንብቡ)።

እና ምንድነው? ሃገራዊ አብያተክርስቲያናትን ስትናገሩ ባሕርያቸውን አብራችሁ ብታውቁ ጥሩ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የገጠማትን ችግር ተናግሬ ነበር ብሎ ልከኝነትን ለማግኘት መጣጣር እብደት ነው። የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ኅብረትም እንዲህ ዓይነት ንግርተኞችን አደብ ቢያስገዛ ነው (ነግ በ'ኔ ነውና)።

ሰላም ኹኑ

ተገኝ ሙሉጌታ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሰን!

ጥምቀት በዓለም ዐቀፍ ቋሚ ቅርስነት በዩኔስኮ የመተዘገበ በዓል መሆኑ የሁላችንም ክብር ነው። የመድኀኒችንና የጌታችን የኢይሱስ ክርስቶስ በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ መጠመቁ፣ ቋንቋንና ባሕልን ባለፈ መልኩ የክርስትና እምነትን ተከታዮችን ካስተሳሰሩን የእምነት የጋራ መገለጫዎች መካከል አንደኛው ነው። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከዚህ ባለፈ መልኩ ዕለቱ የሚያስተላልፈውን ትልቅ መንፈሳዊ መልእክት አጽንዖት በመስጥት ልብ ልንለው ይገባል። በተለይም፡- “ከእኔ ይልቃል’ ብዬ የመሰከርሁለት እርሱ ነው" በማለት በዮሐንስ 1፥15 ላይ መጥምቁ ስለ ክርስቶስ የሰጠው ምስክርነት የበዓሉ መካከለኛ መልእክት ነው።

መጥምቁ ዮሐንስ ከብሉይ ኪዳን ወደ አዲስ ኪዳን የመሸጋገሪያ ድልድይ እንዲሁም የአዳኛችን የክርስቶስ አገልግሎት መንገድ ጠራጊ እንዲሆን ከእግዚአብሔር የተላከ መልእክተኛ ነበር። “እነሆ፤ በፊቴ መንገድ እንዲያዘጋጅ መልእክተኛዬን እልካለሁ” (ሚልክያስ 3፥1)። እውነተኛ ብርሃን ስለሆነው ስለ ክርስቶስ ምስክር ለመሆን አስቀድሞ እግዚአብሔር የላከው ታላቅ አገልጋይ ነበር። ስብከቱም፦“መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሓ ግቡ” የሚለው ዐዋጅ ነበር። (ማቴ. 3፥2)። ልክ እንደ ዱላ ቅብብሎሽ ጌታችንም ይህንን ስብከተ ወንጌል ከመጥምቁ ዮሐንስ እጅ ተረክቦ ቀጥሏል።

መጥምቁ ዮሐንስ ያለምንም ፍርሃት፣ ግብዝ ለነበሩት የሃይማኖት መሪዎች፣ ለኀይላትና ለሥልጣናትና ለሕዝብ ሁሉ የሚሆን የንስሓ ጥሪ ነበረው። ይኸው ሥር-ነቀል የሆነ የጽድቅ ዐዋጅ ከጨካኙ ሄሮድስ ጋር አጋጭቶት አሰይፎታል። ሕይወቱን አሳልፎ እስከመስጠት ታማኝና ለጽድቅ የጨከነ ምስክር ነበር። ዮሐንስ እንደ ተጻፈለት፣ በርግጥ “ስለ ብርሃን ምስክር ሆኖ ለመቆም መጣ።” (ዮሐ. 1፥7)።

አገልግሎቱን የፈጸመው በትልቅ ትሕትና ሲሆን፣ ፈጽሞውኑ ወደ ራሱ አላመለከተም። ይልቁንም ወደ ክርስቶስ እንጂ! ዮሐንስ የሰጠው ምስክርነት ይኽ ነበር፦

▶ “እኔ ክርስቶስ አይደለሁም” - ብቸኛ መድኅን ክርስቶስ ብቻ ነው! “አንተ ክርስቶስ ነህን?” የሚል ጥያቄ የቀረበለት ዋነኛ ምክንያት የአገልግሎቱ ተጽእኖ ያስገኘለት ክብርና ዝና ነበር። ስም፣ ስኬትና ዝና ለብዙ መሪዎች ፈተና እንደሆነ በታሪክም ሆነ በእኛም ዘመን ግልጽ ነው። እግዚአብሔር እንዲሁ ከታላቅ ምሕረቱ፣ ደግነቱና ሉዓላዊነቱ የተነሣ ብቻ የቱንም ያህል ክብሩን በእኛ ቢገልጥንም፣ በየትኛውም መልኩ የክርስቶስ ምትክ ልንሆን አንችልም። እኛ እንዲሁ በጸጋ ብቻ ድነት ያገኘን ኀጢአተኞች ነን! ምንጊዜም የምናገልገልውም በማያልቀው ምሕረቱ ተደግፈን እንጂ ብቁ ስለሆንን አይደለም። ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሚለው፣ "ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፣ በራሳችን ብቃት ከእኛ ነው የምንለው አንዳች ነገር የለንም።" (2 ቆሮ. 3፥5)። መሲሕ ግን ከዘላለም እስከ ለዘላለም ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ፤ የስላሴ አካል ነው!

▶ “ኤልያስ አይደለሁም” - ኤልያስ ታላቅ የእግዚአብሔር ነቢይ ነበር። ክርስቶስ በመስቀል ሞቱ ስለሚፈጽመው የቤዝዎት ሥራ ለመነጋገር፣ ክርስቶስ በአስፈሪ ግርማ በተለወጠበት ተራራ ላይ ከሙሴ ጋር አብሮ ተገኝቷል። “በክብርም ተገልጠው፣ በኢየሩሳሌም ይፈጸም ዘንድ ስላለው ከዚህ ዓለም ስለ መለየቱ ይናገሩ ነበር።” (ሉቃስ 9፥31)። ሙሴ የሕግ መጻሕፍት ወኪል በመሆን እንደተገኘ ሁሉ፣ ኤልያስም የነቢያት ወኪል በመሆን፣ ክርስቶስ የድነት ታሪክ ፍጹም ፍጻሜ መሆኑን ለመመስከር በዚያ የመለወጥ ተራራ ላይ ተገኝተዋል። የሙሴ ሕግ፣ ነቢያትና መዝሙራት ሁሉ መልእክታቸው ስለሚመጣው መሲሕ ነበር፤ መልእክታቸውም በክርስቶስ ፍጻሜ አግኝተዋል። (ሉቃ. 24:44)። መጥምቁ ዮሐንስ በኤልያስ መንፈስ ከክርስቶስ አስቀድሞ የተላከ ነቢይ ነበር። ሆኖም ከዝናው የተነሣ "ኤልያስ ሳይሆን አይቀረም" የሚለው የወቅቱ ግምት ፈተና አልሆነበትም። ምላሹ፣ "አይደለሁም!" ነበር።

▶ “ነቢዩም አይደለሁም” - ይኽ ነቢይ በዘዳግም 18፥15 “አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ከገዛ ወንድሞችህ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል፤ እርሱን አድምጥ።” ተብሎ የተተነበየለት ነው። በአይሁድ አረዳድ ይህ ነቢይ ዳግማዊ ሙሴ፣ ኤርምያስ ወይም ከታላላቅ ነቢያት መካከል አንዱ ነው። በወቅቱ ክርስቶስን ራሱን፦ “ኤልያስ፣ ኤርምያስ ወይም በዘዳግሙ ተስፋ የተገባለት ነቢይ" ሳይሆን አይቀርም ብለው የሚገምቱም ነበሩ። “አንዳንዶቹ [ኢየሱስን] መጥምቁ ዮሐንስ፣ ሌሎች ኤልያስ፣ ሌሎች ደግሞ ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ።” (ማቴ. 16፥14)። ሆኖም ይህም የዝና ፈተና ለመጥምቁ ዮሐንስ ማንቆ አልሆነበትም። ይልቁንም፣ "ነቢዩም አይደለሁም!" ለማለት አልተቸገረም።

“እንግዲያስ ማን ነህ . . . ስለ ራስህ ምን ትላለህ?” አሉት፤ በትሕትናው ግራ በመጋባት።
እኛስ እንደግል አማኝ፣ ደግሞም እንደ ክርስቲያን ማኅበረሰብ ስለራሳችንና ስለ ክርስቶስ የምንሰጠው ምስክርነት ምን ይሆን?

መጥምቁ ዮሐንስ ስለራሱም ስለክርስቶስም እንዲህ ሲል መሰከረ፡-

▶ “በነቢዩ በኢሳይያስ እንደ ተነገረው፣ ‘ለጌታ መንገድ አቅኑለት’ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ድምፅ እኔ ነኝ።’” (ዮሐ. 1፥23)። ዮሐንስ ይኽን ሲመስክር፣ እኔ የእግዚአብሔር መልከት ሰበር ዜና አብሳሪ ድምጽ ነኝ ማለቱ ነበር። ክርስቶስ የእግዚአብሔር መንግሥት ዐቢይ አጀንዳ መሆኑን የሚናገር ድምፅ፤ የዚህ የምሥራች አንባቢ ነኝ ማለቱ ነበር። ክርስቶስ በቤዛዊ ሞት ዓለምን ከኀጢአት ባርነት ነጻ ለማውጣት የተላከ የእግዚአብሔር ልጅ መሆንን በአጽንዖት መስክሯል። ዐዋጁም ክርስቶስ ካህንም የኀጢአት ስርየት መስዋዕት ለመሆን ስለመምጣቱ ነበር። በጨለማ ለሄደ ሕዝብ ብርሃን የመውጣቱ፤ ለተጠማው ምድረ በዳ፣ የሕይወት ውሃ ምንጭ መፈለቁን የሚያበስር ዐዋጅ ነጋሪ! እኛም ለእግዚአብሔር እንዲሁ እንሁንለት፤ የድነትና የተስፋ ዐዋጅ ነጋሪዎች! መልእክታችኝ ስለክርስቶስ እንጂ ስለ እኛ አይሁን! ጌታ ኢየሱስ ኀጢአታችንን ተሸክሞ በመስቀል ላይ ሞተ (ማቴ. 27፥35፤ 1ጴጥ. 2፥24) ። መምትካችን በመሞት፣ ቅጣታችንን ተቀበለ (ኢሳ. 53፥5-6)። ጻድቅና ልዑል እግዚአብሔር በልጁ ሞት ምክንያት የእያንዳንዳችንን ሞትና እርግማን አስወግዷል (ኢሳ. 53፥4፤ ገላ. 3፥13)። ከዚህ ውጭ ያሉ ድርብ፣ ባዕድና ተጻራሪ ትምሕርቶች ሁሉ ከቤተ ክርስቲያን ተጠራርገው ሊወጡ ይገባል። ክርስቶስ ብቻ!

▶ እኔ “የጫማውን ማሰሪያ ለመፍታት እንኳ የማልበቃ” (ዮሐ. 1፥27፣ ማቴ. 3፥11)። ሆኖም፣ የከበረውን የእግዚአብሔርን ልጅ ክርስቶስን የማሳይ ነኝ። በአጭሩ፣ እኔ መሲሑ፣ ኤልያስ ወይም ነቢዩ አይደለሁም፤ ይልቁንም ያልኋችሁ “እነሆ! የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” (ዮሐ. 1፥29)። ከእኔ በኋላ የሚመጣው በባሕርይ፣ በክብርም ከእኔ የላቀ፣ ፊተኛና ኋለኛ፣ "ያልሁት እርሱ ነው!"(ዮሐ. 1፥30)።

▶ የመጣኹበት፣ የሕይወቴና የአገልግሎቴ ሁሉ ግብ “[እርሱ - የእግዚአብሔር በግ ክርስቶስ] በእስራኤል ዘንድ እንዲገለጥ ነው።” (ዮሐ. 1፥31)። አባቱም "የምወደው ልጄ" በማለት ከሰማያት ሲያውጅለት ሰምቻለሁ። " . . . በውሃ እንዳጠምቅ የላከኝም፣ ‘በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቀው፣ መንፈስ ሲወርድና በርሱ ላይ ሲያርፍ የምታየው እርሱ ነው’ ብሎ እስከ ነገረኝ ድረስ እኔም አላወቅሁትም ነበር፤ አይቻለሁ፣ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ እመሰክራለሁ።” (ዮሐ.

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ክርስቶስ ከቅፍርናሆም በግምት የሁለት ቀን መንገድ ተጉዞ ወደ ናይን ከተማ የሄደው ርኅራኄና ፍቅር ግድ ብሎት ነበር። የናይን ከተማ ሕዝብ የአንድን ወጣት ሞት፣ ሞቱ አድርጐ፤ የመበሊት እናቱን ሐዘን፣ ሐዘኑ አድርጐ ለቀብር በነቂስ ከተማ እየወጣ መተላለፊያ መንገድ ላይ ከክርቶስ ጋር የተገናኘ ልቡ የተሰበረበት ሕዝብ ነበር።

በዚህ መንገድ ላይ ሁሉት ዓይነት ሕዝብ ተገናኙ። አንደኛው፣ ሕይወት ሰጪውን ክርስቶስን ተከትሎ ይተም የነበረ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በደን በቃሬዛ ተሸክሞ ወደ ቀብር ሲሄድ የነበረ ነው። ሕይወትና ሞት፤ የተስፋ ብርሃንና ጽልመት፤ ተገናኙ። ለሁለቱም ሕዝብ መገናኘት ምክንያት የሆነው ክርስቶስ ነበር። ይህ መገጣጠም፣ በጐበዙ ከሞት መነሣት ደስታ ሲደመደም፣ ሁለቱም ሕዝብ በአንድ ላይ “እግዚአብሔርም ሕዝቡን ጐብኝቶአል” በማለት እግዚአብሔርን አመስግኗል።

ሁለቱን ሕዝብ ተመሳሳይ የሚያደርጋቸው የነበራቸው አንድነት ነበር። ከቅፍርናሆም የመጣው ሕዝብ፣ ላለበት ችግር ሁሉ በመፍትሔነት ክርስቶስን በአንድ ላይ የተከተለ ሲሆን፣ “የከተማውም ሕዝብ ከእርሷ ጋር ነበረ” በማለት ሉቃስ የዘገበለት የናይን ሕዝብ ደግሞ በአንድ ልብ በርኅራኄ የመበለቲቱን የልብ ስብራት በመጋራት ወደ ቀብር ይሄድ ነበር።

ሕይወትን እንመረጥ፤ በርኀራኄ የአንድን ሰው ሐዘን የራሳችን እናድርግ። አገራችን ባለችበት በዚህ የጨለማ ወቅት፣ ክርስቶስን እንደ ተከተለው ሕዝብ ሕይወትን መከተል፤ የመበለቲቷን ሐዘንና ስብራት የራሱ ሐዘንና ስብራት እንዳደረገው ሕዝብ ደግሞ፣ የአንድም ሰው ሞት ቢሆን እንኳን፣ ከፓለቲካና ከዘር ባለፈ ሰብአዊነት በአንድ ልብ በርኅራኄ ልንቆም ይገባናል። ላለንበት ፈርጀ ብዙ ቀውሶና ስብራቶች፣ በመጨረሻ መፈትሔነት ልንከተለው የሚገባው የርኅርኄ ሁሉ አምላክ የሆነውን ክርስቶስን ብቻ ሊሆን ይገባል።

እርሱን መከተል ሕይወት ነው! ከምንጊዜው በላይ ሕይወትንና ሰላምን ልንከተል፤ የግፉዓንን ሞት፣ ስብራትና ሐዘን የራሳችን አድርገን፣ አንደ አንድ ሕዝብ፣ በአንድ ልብ ልንያያዝ የሚገባበት ፈታችን ወቅት ላይ ደርሰናል። በክርስቶስ ርኅራኄ፣ የአንዱን ሰቆቃና ሞት የራሳችን እስካላደረግን ድረስ ሁላችንም በሞት ጥላ ውስጥ ያለን በደለኞች ነን። ከከበበን የጥፋት ጽልመት የምንወጣው፣ የዘር ግድዳን ጨምሮ፣ ከማንኛውም ሰው ሠራሽ ክልል በላይ ከፍ ብለን የሰውን ሁሉ አምሳለ መልኮት ተሸካሚነት ስንቀበል ብቻ ነው። የሰው ሕይወት ንጽሕናና ክብሩነት፣ "በፓለቲካዊ አሰላለፍ፣ በጐሳዊ ማንነትና ማኅበራዊ ውቅሮች” ዋጋ እንድንለካ ካዳረገን አዘቅት ውስጥ ፈጥነን ልንወጣ ይገባናል። በተለይም በመስቀል ላይ በፈሰሰው ክብሩ ቤዛዊ የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጀ የእግዚአብሔር ማኅረ ሰብ! መስቀሉ ያፈረሰውን የመለያያት ግድግዳ መለሰን የምናቆም ከሆን፣ ምን ተሰፋ አለን?

ይህቺ መበለት ሦስት ዓይነት ስብራቶች ውስጥ ነበረች።

አንደኛው ባሏን፣ ምናልባትም በወጣትነቷ፣ አጥታለች። በወቅቱ በነበረው ማኅበራዊ አተያይ እንደ "ባል ገፊ" ተቈጥራ ሥነልቡናዊ መገለል የደረሰባት ነበረች። “ሁሉን የሚችል አምላክ ሕይወቴን እጅግ መራራ አድርጐታልና ማራ በሉኝ” በማለት እንደ ተመረረችው ኑኃሚን፣ ይህቺም መበለት ከእግዚአብሔር ጋር የግል ሙግት የነበራት ይመስለኛል።

ሁለተኛው፣ አንድ የተስፋ ልጇን ሞት ድንገት መጥቶ ነጥቈባታል። መከራዋን የበለጠ የሚያከብድና ዐጥንት የዘለቀ መሪር ሐዘን ውስጥ ከቷታል።

በመጨረሻም፣ የሚቤዣት ባል የማግኘት ተስፋዋ እጅግ የተሟጠጠ ነበር። እነዚህ ስብራቶች፣ በሰው ኀይል የሚጠገኑ አልነበሩም።

ትጓዝ በነበረበት ተስፋ ሁሉ በተሟጠጠበት የጨለማ መንገድ ላይ፣ ርኅራኄና ፍቅር ግድ ያለው ክርስቶስ አገኛት! ያም ታሪኳን ቀየረ። ለእኛም እንደ ግለሰብም ሆነ እንደ አገር እንዲሁ ይሁንልን። ባሳልፈነው ጦርነት እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ከሚፈጸሙ ግፎች የተነሣ የመበለቶችና የድኻ አደጐች ቁጥር በጨመረባት አገራችን የእግዚአብሔር የምሕረት ይድረስልን። ጌታም ባያት ጊዜ፦

• ራራላት
• “አይዞሽ፤ አታልቅሺ” አላት
• ቀረብ ብሎም ቃሬዛውን ነካ
• ቃሬዛውን የተሸከሙትም ሰዎች ቀጥ ብለው ቆሙ
• ኢየሱስም፣ “አንተ ጐበዝ፤ ተነሥ እልሃለሁ” አለው
• የሞተውም ሰው ቀና ብሎ ተቀመጠ፤ መናገርም ጀመረ
• ኢየሱስም ወስዶ ለእናቱ ሰጣት።

እንደ ግለሰብ፤ እንደ ቤተ ሰብ፤ እንደ ቤተ ክርስቲያን፤ እንደ አገር፤ ብዙ ነገሮች ለሞቱብን ለእኛም፣ እንዲሁ ትንሣኤ ይሁንልን! እናም በዚህ ጉብኝት፣ “የኢየሱስ ዝና በመላው ይሁዳና በአካባቢው ባለው አገር ሁሉ” እንደ ወጣ፣ ለእኛም ለእውነትኛ ጉብኝት ወደ ክርስቶስ መመለስ ይሁንልን!

"አቤቱ አባት ሆይ፤ አሰበን፤ አድሰንም።”

አሜን!

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ። (21-22)" ይላል።

እነሆ አነቃቂዎቹ ደጋግመው የሚጠሩት እግዚአብሔር እና የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር ግና ፈጽሞ አይገናኙም። ሃሳባቸውን የሚደግፍላቸውን ቃል ከመጽሐፉ ቢጠቅሱም ከጥቅስ ያለፈ ስለ ህልውናው ዓይነተኝነት የሚናገሩት የላቸውም። ብዙዎቹ ጥቅስ ጠቃሾች በክርስትና ሃይማኖት ውስጥ ያደጉ ስለሆኑ ያንን ያደርጋሉ እንጂ የኤርክሃ ቶሌ ደቀ መዛሙርት እስከሆኑ ድረስ መጽሐፍ ቅዱስን ብቸኛ መለኮታዊ ቃልና ሥልጣን ያለው መጽሐፍ አድርገው አይቆጥሩም። ክርስቶስንም ከሌሎች የሃይማኖት ጉሩዎች በተናጠል ብቸኛ የሕይወት ጌታና መንገድ ነው ብለው አያምኑም።

ዳግማዊት ክፍሌ ለወጣቷ ልጅ ያቀረበችው ሌላው ጥያቄ ደግሞ ስለ "ጆርላኒንግ" ( ማስታወሻ የመጻፍ) ልምምዷ ነው። የወጣቷ ምላሽ አሁንም ውስጣዊ ፍላጎትን ዕለት ዕለት በምንጠቀምባቸው ቁሶች፣ ለምሳሌ የኮምፒውተር ዋልፐር ላይ ያሰብነውን ነገር በጽሁፍ በማስፈር ያንን ያሰብነው ነገር በማውጠንጠን እንደሚሳካ ለአእምሮ የመንገር ብልሃት ነው።

ወጣቷ ፌቨን መላኩ ስለዚህ ነገር ስትገልጽ፦ "በጆርናሊንግ አንዳንዶች ስለ ግራቲቲዩድ (አመስጋኝነት)፣ አንዳንዶች ስለ አፈርሜሽን ይጽፋሉ። አፈርሜሽን አንቺ ዴቨሎፕ ልታደርጊው የምትፈልጊው ካራክተር ካለ፣ ያንን እኔ እንደዚህ ነኝ ብለሽ ትጽፊውና የጻፍሺውን በየቀኑ መድገም ነው። 'ልበ ሙሉ ነኝ'፣ 'ስኬታማ ነኝ'፣ 'መሆን የሻትኩትን መሆን እችላለሁ'፣ እያልሽ ደጋግመሽ ትጽፊያለሽ። ያኔም ኮንፊደንስ ያድጋል። የጻፍሻቸውን ነገሮች በየቀኑ ደጋግመሽ ስታያቸው ሳይታወቅሽ አእምሮሽ ቪዥን እየሠራ ነው። ለምሳሌ እኔ መቶ ሺህ ፎሎወር ይኖረኛል ቤዬ ከጻፍኩ ቆይቻለሁ። ያ እንደሆነ የነገረኝ አንድ ሰው ነው። " ብላለች።

ባጭሩ አዲሱ ሃይማኖት ራስን የሁሉ ነገር ፈጣሪና አድራጊ አድርጎ መቁጠር ነው። "እችላለሁ! በራሴ ብቁ ነኝ!" የማለትን ስሜት የማዳበር ሃይማኖት ነው። ለአዳምን የብርሃን መልአክ መስሎ ያሳታቸው ክፉ ዛሬም በሌላ መንገድ ዘመኑን መስሎ መምጣቱን እያየን ነው። ሰው ነንና ፈተና በገጠመን ሰዓት መፍትሔ ለመሻት በምንሄድበት መንገድ እንዲህ ዓይነቱ አባባይ ቃል ቢገጥመን ጭራሹን ተሰነካክለን እንዳንቀር አእምሯችንን ከአዲሱ ሃይማኖት እሳቤዎች እንጠብቅ።

መልካም የጌታ ልደት በዓል ይሁንልን!

©ሽመልስ ይፍሩ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

በወንጌላውያን ዘንድ በተለያዮ ርእሶች የተጻፉ በርካታ መጽሐፉች ቢኖሩንም ነገረ ቤተክርስቲያን ላይ ግን የተጻፉትን ለማግኘት አድካሚ ይሆናል። በጣም ጥቂት (በጣት የሚቆጠሩ) መጽሐፍት ብቻ ናቸው በቤተክርስቲያን ዙሪያ የተጻፉልን። ይህም አንድም ቤተክርስቲያንን የምንመለከትበትን ዛቢያ ሲያፋልስ ሁለትም ደግሞ የቤተክርስቲያንን ምንነት እኛ ሚና እስካለን ድረስ ብቻ እንድንረዳ አድርጎናል። «በሃገራችንም ... ለቤተክርስቲያን ሕብረቶቻችን የምንሰጠው ግምት አንድ አማኝ ከግል እምነቱ ያነሰ ነው። ቤተክርስቲያን አስፈላጊነቷ እስከጠቀመችን ወይም በኅብረት ውስጥ የእኛ መኖር ዋጋ እስከተሰጠው ድረስ ብቻ እንደሆነ የሚያሳብቁ ብዙ ምልልሶች አሉን።» ይላል።

ስለዚህም በዚህ መጽሐፍ ተጉ የነገረ ቤተክርስቲያንን አስተንትኖት ለወንጌላውያን ግድ ካደረጉት ነገሮች አንዱ የሚከተለው ነው፦

«ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ማደሪያ የቅዱስ ሥርዓቱም መገኛ ናትና ለራሷም ይሁን ለሌላው ብርሃን ትሆን ዘንድ ራስ ከሆናት ጌታ ሥርዓቶችና ምስጢራቶች ተደንግገውላታል። ሆኖም እነዚህ ሥርዓቶችና ምስጢራቶች ትክክለኛ ነገረ መለኮትና ትክክለኛ ልምምድ ከሌላቸው የቤተክርስቲያንን ቤተክርስቲያንነት ይፈታተናሉ። በተለይ የሃገራችን የ‘ፕሮቴስታንት’ አማኞች አብያተክርስቲያናት ለቅዱስ ቁርባንና ለጥምቀት እንዲሁም ቤተክርስቲያን ሥርዓት አድርጋ ከቅዱስ ቃሉ በመነሣት የደነገገችውን የጸጋ መሣሪያዎች [Means of Grace] የሚሰጡት ነገረመለኮታዊ ትንተና ደካማ መሆኑ የነገረ ቤተክርስቲያንን ድጋሚ አስተንትኖት አስፈላጊነት ያጎላዋል። ‘በግል ጌታን ማወቅ ትችላለህ’ የሚለው ክርስትናዊ ስብከቶቻችንና አካሄዶቻችን በቤተክርስቲያን እንደ ጸጋ መሣሪያ የተደነገጉትን መንፈሳዊ ሥርዓቶች ችላ እንዲባሉ አስተዋጽዖ አድርገዋል።»

ቤተክርስቲያን ለምትኖርበት ማኅበረሰቡ ፈያጅ መሆኗንና ለልምምድና አስተምህሯ ጥንቁቅ መሆን እንዳለባት፤ ቅዱሳት መጽሐፍት ያሏትን ሆና መገኘት እንዳለበት የሚሞግት መጽሐፍ ነው።

ዛሬ ከሰዓት 9:00 ሰዓት ላይ በሃያ ሁለት ሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን ይመረቃል። በኋላ እንገናኝና ይህንን ድንቅ መጽሐፍ ገዝተን እናንብብ እናስነብብ!

አማኑኤል አሰግድ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ሐቅ ነው ማለት አይደለም፡፡ ይህን ቊጥር ያደላደለው “ሥነ ዕውቀታዊ አጽድቆት” (Epistemic Justification) እንደ ሆነ ልብ ይሏል፡፡

“ሥነ ዕውቀታዊ አጽድቆት” ፋይዳው አነስተኛ በሆነበት ጊዜ እንዲሁም “ገቢራዊ አጽድቆት” (Prudential Justification) በብርቱ በሚፈለግበት ጊዜ ምን ማድረግ አለብን? በሕይወት ለመኖር ለሚፈልግ ሰው፣ አለመሞት ገቢራዊ ፋይዳው ነው፡፡ ከሞት ምን ይገኛል? (ጳውሎስ ብቻ ነው፣ “ልሄድ ከክርስቶስ ጋር ልኖር እናፍቃለሁ” ብሎ ሲጣደፍ የምናየው)፡፡

4. የውይይቱ ጭብጥ

​መሰንበቻውን ዮናታን አክሊሉ ዐቃቤ እምነት ሆኖ ተከሥቶአል፡፡ ለንጹሕ ወንጌል ቀናዪ ነኝ እየለ ነው፡፡ የኢትዮጵየያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በገድላት ላይ ያላትን ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ እንከን በቀጥታ በመጥቀስ፣ የገድላቱ ትምህርት የክርስቶስ ወንጌልን እንደሚያቅፋፋ ሞግቶአል፡፡

​አንዳንዶች አንተ ራስህ ከኑፋቄ መቼ ተለይተህ ስለ ኑፋቄ ታወራለህ የሚል ዐሳብ ሰንዝረዋል፡፡ አንደንዶች ደግሞ፣ ዮናታን ትላንት የተሳሳተ ትምህርት ማስተማሩ፣ ዛሬ ንጹሑን ወንጌል እንዳይናገር እክል አይፈጥርበትም፡፡ ስሕተት በይርጋ አልታገደም፡፡ የወደቀ ይነሣል የሚል አጸፋ ሰጥተዋል፡፡ ትምህርቱ እውነትን መሠረት እስካደረገ ድረስ፣ የዮናታን ዕቅበተ እምነታዊ ዲስኲር ይበል የሚባል ነው ባይ ናቸው፡፡

​አንዳንዶች ታሪክን በማጣቀስ የቤተ ክርስቲያኒቱን ታላቅነት በማድመቅ፣ የዮናታንን ትንሽነት በተለይ ደግሞ፣ በተለያዩ ጊዜያት ያስተማራቸውን ዝርክርክ ትምህቶች በእማኝነት በማቅረብ፣ ዮናታን ለዕቅበተ እምነታዊው ሥራ እንደማይመጥን ገልጸዋል፡፡

​ሌሎች ደግሞ ቤተ ክርስቲያኒቱ ታላቅ የሆነችበት አግባብ እንደ ተጠበቀ ሆኖ፣ በገድላት፣ በተኣምረት፣ በፍካርያት፣ በድርሳናት ወዘተ ላይ መሠረት ያደረጉት ትምህርቶችዋ፣ ከብሉያትና ከሐዲሳት ቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርት ጋር በቀጥታ የሚቃረኑ እስከ ሆነ ድረስ፣ ዮናታን ዕቅበተ እምነታዊ ትምህርት አግባብነት አለው ይላሉ፡፡

​አንዳንዶች፣ “የጠቢብ ዐይኖች በራሱ ላይ” ናቸውና፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለቀቅ በማድረግ በራስህ ብቻ ላይ አተኲር የሚል ምክር ለግሰዋል፡፡ ሁሉም በራሱ ላይ፣ “ብቻ” ማተኰር ካለበት፣ እነርሱስ በምን አግባብ በዮናታን ላይ አስተያየት ሊሰጡ ይችላሉ? የነገሩን መርሖ በእነርሱ ላይ ለምን አይሠራም? በዐጭሩ በራስ ላይ ማተኰር፣ በሌለው ላይ አስተያየት መስጠትን አይከለክልም፡፡

5. “ያለምንም ደም እንከኗ ይውደም!”

​ዮናታንን በመደገፍም ሆነ በመቃወም የተሰጡ አስተያየቶች በአብዛኛው ሥነ ዕውቀታዊ አጽድቆትን (Epistemic Justification) መሠረት ያደረጉ ናቸው፡፡ ሚዛናችን ሥነ ዕውቀታዊ አጽድቆት ብቻ ከሆነ፣ ዮናታን አንዳችም ስሕተት የፈጸመ አይመስለኝም፡፡

ዮናታን ትልቅ ስሕተት ተሳስቶአል እንድንል የሚያደርገኝ፣ ገቢራዊ አጽድቆትን (Prudential Justification) በማገናዘቢያነት ካቀረብሁ ብቻ ነው፡፡

​ዮናታን ትልቅ ስሕተት ፈጽሞአል፡፡ የዮናታንን ትምህርት ተከትለው አስተያየት የሰጡ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስትና ሊቃውንት፣ “ዐንገታችንን ለካራ ሰጥተን፣ ዐንገት እንቀነጥሳለን” ብለዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ በትምህርት ልዕልና ብቻ ሳይሆን፣ በሰይፍም መጠበቅ እንዳለባት የሚያምኑ ብዙዎች ናቸው፡፡ በዚህ አግባብ ሲታይ፣ ዮናታን ብዙዎች በአደጋ ቀጠና ውስጥ እንዲገቡ አድርጓል፡፡ ዮናታንን በአዋሳና በዐዲስ አበባ መንግሥት ጥበቃ ሊያቆምለት ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን መንግሥት በሁሉ ቦታ ለሚገኙ፣ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት አማኞች ዘብ ሊቆም አይችልም፡፡ በዮናታን ዳፋ ብዙዎች ሊደፉ ይችላሉ፡፡ ስብከተ ወንጌል ትልቅ ጥበብ የሚፈልግ ጠንቃቃ ሙያ ነው፡፡ ለረጅም ዓመት የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ይህን አካሄድ ነው የተከተሉት፡፡

​ዮናታን ገድላቱን በተመለከተ የነገረን ነገር ዐዲስ አይደለም፡፡ ብዙዎች የሚያውቁት፣ የኦርቶዶክስ ምሁራን ጭምር ቢታረም የሚል ለቤተ ክህነት አስተያየት ያቀረቡበት ጒዳይ እንደ ሆነ ይታወቃል፡፡ ከሃያ ዓመት በፊት የተጻፈው፣ “ገድል ወይስ ገደል?” መጽሐፍ ይህን ችግር በጨዋ መንገድ የሚሞግት ምሁራዊ ሥራ ነው፡፡ ዕቅበተ እምነት ጨዋነትንና ጥበብን በብርቱ ይፈልጋል፡፡ ወንጌልን መስበክ ያለብን፣ ዐብረነው የምንኖረውን ሕዝብ ሳናስቈጣ መሆን አለበት፡፡ ዕቅበተ እምነት ጥንቃቄ የሚፈልግ ሥልጠና የሚሻ ሙያ ነው የምንለው ይህ ዐላማ ከዳር እንዲደርስ ነው፡፡ በተለይ አገሪቱ በዘርና በሃይማኖት ክፉኛ በምትታመስበት ጊዜ፣ ዮናታን ሌላ የራስ ምታት ሊፈጥርብን አይገባም ነበር፡፡

6. ዮናታን አክሊሉ ተሳስተሃል!

​ የእኔ አስተያየትና ምክር የሚከተለው ነው፡፡ ዮናታን አክሊሉ ስሕተት ፈጽመሃል፡፡ ስሕተትህ ብዙዎች እንዳሉት ሥነ ዕውቀታዊ እውነታ (Epistemic truth) ላይ ነው ብዬ አላስብም፡፡ ዐዋጃዊ እውነታ (Propositional truth) ላይ የተፈጸመ አንዳችም ስሕተት ያለ አይመስለኝም፡፡ ወንጌል የሚለውን እንዳጸናህ ከሙሉ ልብ እቀበላለሁ፡፡

​ይህ እንዳለ ሆኖ፣ ትልቅ የሆነ የጥበብ ጒድለት ታይቶብሃል፡፡ ገቢራዊ እውነታን (Prudential truth) አዛብተሃል፤ አፋልሰሃል፡፡ በዚህ ምክንያት የሰዎች በሰላም ዐብሮ የመኖር እሴታቸው ተናግቶአል፡፡ ምናልባትም የብዙዎች በፍርሓት እንዲወጡና በሰቀቀን እንዲገቡ ምክንያት ሆነሃል፡፡ ለዘመናት የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያና ይከተሉት የነበረውን የጥበብ አካሄድ ክፉኛ አበላሽተሃል፡፡ ከዚህ የከፋ ችግር ሳይከተል፣ ዶፉ ሳይዘንብ፣ በይፋ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ይቅርታ መጠየቅ ያለብህ ይመስለኛል፡፡

“አቀራረቤ ስሕተት ነበር! ይቅር በሉኝ!” ብትል ችግሩ ሊለዝብ የሚችል ይሆናል፡፡ እኛንም ጦር ቀጠና ውስጥ ስለከተትኸን ይቅርታ ልትጠይቅልን ይገባል፡፡ አንተ መንግሥት ይደርስልህ ይሆናል! በተለይ በሰሜን የአገሪቱ ክፍል የሚኖረው የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት አማኝ መድኀኔዓለም እስኪደርስለት ድረስ ባንተ ዳፋ ለምን ይደፋ?

​ወገን፣ የአስተምህሮ ንጽሕና ብቻ ሳይሆን፣ ገቢራዊ ፋይዳን ተከትሎ ወንጌልን መስበክ፣ ዘመኑ በብርቱ የሚፈልገው ሰማያዊ ጥበብ ነው!

ተስፋዬ ሮበሌ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ዮናታንም "ወንጀለኛ" ነው!

“ሁሉም እውነት የእግዚአብሔር እውነት ነው” (All truth is God’s truth) የሚል አባባል አለ። አንድን “እውነት” ማንም ሰው ይናገረው እውነት ከሆነ እውነት ነው ለማለት ነው (በእርግጥ በዚህ ላይ ክርክር የሚያነሱ ባይጠፉም)። ለምሳሌ “ይጠብቁህ ዘንድ ስለ አንተ መላዕክቱን ያዛል ተብሎ ተፅፏል” ብሎ በምድረ በዳ ፈተናው ወቅት ሰይጣን ለኢየሱስ የተናገረው አውነቱን ነበር። ሰይጣንም “እውነት” ሊናገር ይችላል ማለት ነው። “የልዑል ለጅ ሆይ ልታሰቃየን መጣህን” ብለው አጋንንቶችም ሲናገሩ እውነታቸውን ነበር። ነገር ግን ሰይጣይን “እውነት” ስለተናገረ ብቻ ሰይጣንነቱን አይተውም። ማንነቱ ነውና። “እውነትንም” ሲናገር “አሳች” ለሆነው አላማው እንደሚናገርም እሙን ነው።

ስለዚህ ሰይጣን “እውነት” ሲናገር እንደ ትልቅ ነገር እንደማንቆጥረው ሁሉ፤ አንድ ከሃሰተኛ መምህራን ዋና የሆነ ሰው “አውነት” ተናገረ ብለን በአንድ ጀምበር ከጎኑ ተሰልፈን አብረነው ወንጌል ካልሰበክን አንልም። እግዚአብሄር በሉዓላዊ አሰራሩ ዓላማውን ለመፈፀም ሁሉንም አካል እና ሁኔታ ይጠቀማልና። አጋንንቶች “የልዑል ልጅ” ብለው ስለ ኢየሱስ “እውነቱን” መናገራቸውን ኢየሱስ እንደ ግበዓት ሳይጠቀም ማንነቱን በራሱ መንገድ ለዓለም ገለጠ።

እኛም ወንጌል የምንሰብክበት የራሳችን መንገድ አለን። ለኦርቶዶክሳዊያንም ሆነ ለሌሎች። ነገር ግን አንድ ሃሳዌ “ወንጌሌን” ሰብኮልኛልና ከጎኑ ቆሜ “አግዘዋለሁ” ዓይነት አካሄድ አንከተልም። በተለይ ሃሳዊያንን በመቃወም እና ለርቱዕ አስተምህሮ ቆሜያለሁ በምንል ዘንድ ደግሞ እንዲህ ያለ ግብታዊነት ማየት ደስ አይልም። "በአንድም በሌላም ወንጌል ይሰበካል" በማለት የማርያም መንገድ ለሃሳዊያን ለመክፈት መሞከርም በኋላ አደጋው የከፋ ነው።

ከሰሞኑ የናታን አክሊሉ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ገድላትን ጠቅሶ “ይህ በወንጌል ላይ የተፈፀመ ወንጀል ነው። ክህደት ነው” ማለቱ በራሱ እውነት ነው። ይህን ማለቱ ግን እርሱን እውነተኛ አያደርገውም። ከጎንህ ተሰልፌ “አብሬህ ወንጌል እሰብካለሁም" አያሰኝም። ሃሰተኛ ነውና። ሃሰተኛ ደግሞ “እውነትን” ቢናገርም “የብረሃን መልዓክ ለመምሰል እና በጎችን የበለጠ ለማደናገር ስለሚጠቅመው እንጂ ለእግዚአብሔር ክብር ወይም ሰዎች እንዲድኑ አይደለም።

እንዲያማ አስቦ ቢሆን ቀድሞውኑ የራሱን ሃሰተኛ ትምህርቶች አርሞ ከሃሳዊያን ጋር ያለውንም ቁርኝት በጥሶ ይመጣ ነበር። ይህ ሰው ግን ተገማች የሃሳዊያንን ስልት ነው የተጠቀመው። የታዘብሁት ግን አንዳንዶቻችሁ ነገ እነሃይሉና እነጃፒ የዮናታን ዓይነት ዘዴ ተጠቅመው ቢመጡ በራችሁን ከፍታችሁ ለመቀበል እንደተዘጋጃችሁ ነው። አሳችነቱን እንደማትደግፉ በአንክሮ የገለፃችሁትን ግን አይጨምርም።

ለማንኛውም በሃሳዊው ዮናታን የሚሰበክ እና እኔ የምደግፈው የወንጌል እገልግሎት የለም። “ችግሩ የአቀራረብ ነው እንጂ የተናገረው እውነት ነው” ብዬ በማሽሞንሞን እንደ አንድ የወንጌል አገልጋይ አልቆጥረውም። እግዚአብሔር ሉዓላዊ አምላክ ስለሆነ ሰይጣንን ጨምሮ በፈለገው አካል የወደደውን እንደሚሰራው በዮናታንም ተናገረ። በቃ ይኸው ነው። ሰይጣን አውነትን ተናገረ ብዬ አነጋገሩን እያረምኩለት ከጎኑ እንደማልቆምና የእርሱን እውነት በማጣቀሻነት እንደማልጠቀም እንዲሁ ከዚህም ሰው ንግግር ጎን አልቆምም።

እርሱ (ዮናታን) አንድም የወንጌል "ተጋዳላይ" መስሎ በመቅረብ እና የአማኙን ስስ ብልት በመንካት ከነ ስህተቱ ቅቡልነት ለማግኘት፤ ሁለትም ከነምህረተአብ ጋር ላለው ግብ ግብ የመልስ ምት ለመስጠት ወይም ሌላ ዓላማ ሊኖረው ይችላልና። ስለዚህ አማኞች በተለይ ለርቱዕ አስተምህሮ ቆመናል የምንል ወገኖች ከንፋሱ ጋር አብረን ባንነፍስ ጥሩ ነው እላለሁ። በትህትና!

በመጨረሻም፦ለዮናታን ያለኝ መልዕክት

አንተም በድፍረት በእግዚአብሔር ስም ከምትናገረው ያልተፈፀመ ትንቢትህ በላይ ፍጡር የሆነውን ሰው ከፈጣሪ እኩል አድርገህ “አማኝ የሚፈልገውን ነገር መፍጠር ይችላል……አማኝ የፈለገውን ነገር (ቁሳዊ ነገር) መጥራት ይችላል” ወዘተ በማለት ጥንቆላዊ ልምምድ ያለውን የቃል እምነት ስሁት ትምህረቶችን ማስተማርህ በወንጌል ላይ የተፈፀመ ወንጀል ነው! በወንጌል ላይ የተፈፀመ ክህደት ነው። የሃሳዊያንን ወዳጆችህንም እጅ ለማበርታት ላይ ታች የምትለውም በወንጌል ላይ የሚፈፀም አመፃ ነው! ስለዚህ ተመለስ! ንሰሓም ግባ። የሚል ነው።

ቴዎድሮስ ተጫን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

“ተቋርጧላዊ” (Cessationist) ያልሆንኩበት ዋና ምክንያት በሚል ርእስ በዛዲግ ብርሃኑ የተጻፈውን ጽሑፍ ይህንን ሊንክ shorturl.at/fpLZ7 በመጫን በPDF ማግኘት ይችላሉ::

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ሐዋሳ የምትገኙ ወገኖች ከቻላችሁ እንድትታደሙ ትጋበዛላችሁ!

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሮሜ. 10፥9

ይህ ጌታን ተቀብዬ ድኜ መጀመሪያ በቃሌ የያዝኩት ጥቅስ ነው። አብሮኝ አለ።

አንድ ቀን ደግሞ ይመጣል መላስ ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ተንበርክኮ የሚመሰክርበት።

መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው። ፊል. 2፥11

አንዲት ሙስሊም ተማሪ ወድቃ፥ 'ኢየሱስ ጌታ ነው!' ማለቷ የሀላባዋን ታዳጊ ተማሪ ሊድያን ወደ እስራት ሊያስገባት መቻሉ የሚያሳዝን ነው። ሙስሊሞች በበዙባቸው የአገራችን ጥቂት ኪስ ቦታዎች ኢፍትሐዊነት የሚታይበት ሁኔታ እየቀጠለም ይገኛል።

አምና ሀላባ ነበርኩ። እዚያ ሳለን ከሰማነው ብዙ ምስክርነቶች አንድ ሁለቱን በአጭሩ ላካፍል።

ሀላባ አጠገብ በምትገኝ ትንሽ መንደር አከል ከተማ የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ከመተከሏ በፊት ጌታን ያገኘውን ሰው እርሻ የአካባቢው ወጣቶች አወደሙበት። ሄዶ የቀረውን ቃርሚያ ሰብስቦ ወደ ጎታው አስገባ። ለዓመቱ የሚሆን ቀለብ ለቤተ ሰቡ አልነበረውም። ይህ ቃርሚያ ግን የሚቀጥለው ዓመት ሰብል እስኪሰበሰብ ድረስ አላለቀም። የኤልያስንና የኤልሳዕን ታሪክ ሲያውቅ ይህ ሰው ለእርሱ የተደረገለትም ያ እንደሆነ ተረዳ።

በአካባቢው ሊያገለግል ወንድማችን ዶ/ር ደስታ ላንገና ሄዶ በነበረበት ቀን (እነዚህን ምስክርነቶች በሰማሁበት ቀንም አብረን እዚያው ነበርን) እርሱንና አብረውት የሄዱትን አገልጋዮች ሊያንገላቱ የሞከሩ ሌሎች ወጣቶች መካከል አንዱ፥ በዚያ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ተተክላ፥ አገልጋይም ነበረና ወደ አገልጋዩ መጥቶ፥ 'ያ ሰውዬ ይቅር እንዲለኝና እንዲጸልይልኝ እፈልጋለሁና አስጠራልኝ።' ይለዋል። ምክንያቱንም ይነግረዋል። ለደስታ ይነገረዋል። ደስታ ለመሄድ ባይችልም ባለበት ሆኖ ጸለየለት፣ ይቅርታም ቀድሞውኑም እንዳደረገለት ተነገረው። ሰውየው፥ 'ከዚያ በኋላ ሚስት ማግባትና ልጅ መውለድ ችያለሁ።' ብሎ መሰከረ።

ሌላ አንድ ልጨምር። ከላይ ያልኳት ከተማ ውስጥ የምትገኝ አንዲት ጠንቋይ አለች። በአካባቢው ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ የሚመሰክሩ ሰዎች በመብዛታቸው ጥንቆላዋ እየከሳ ሄደ። አምና እዚያ ሳለን ከነገሩን ነገሮች መካከል አንዱ ግቢዋንና ቤቷን ለአማኞች መሸጥ እንደምትፈልግ ነው። መሬቷን አማኞች ብቻ ሳይሆን እሷንም የናዝሬቱ ኢየሱስ በደሙ ይግዛት።

ኢየሱስ ጌታ መሆኑ በሀላባና በዙሪያዋ ብቻ ሳይሆን በዓለምም ሁሉ ከሐዋርያቱ ዘመን ጀምሮ እየተነገረ ነው።

እኔም ከዚያች መሬት ላይ ወድቃ፥ 'ኢየሱስ ጌታ ነው!' ካለችው ተማሪ ጋር እላለሁ።

ኢየሱስ ጌታ ነው።

ዘላለም መንግስቱ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

#የጸሎት_ጥሪ

ቅዳሜ እለት የጾምና የምልጃ ጸሎት ፕሮግራም ለማድረግ የወንጌላውያን ተሃድሶ እንቅስቃሴ አዘጋጅቷል። ይህንን ዝግጅት ለሁለት ጉዳይ አስፈላጊ ነውና እንድንገኝ የወንድምነቴን እመክራለሁ።

አንደኛው እንደ ሃገርም ይሁን እንደ ማኅበረሰብ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል እርሱም የሕያው እግዚአብሔር እጅ እንዲረዳን የሚያስፈልግበት ጊዜ ስለሆነ ነው። በብዙ ነገር የሞከርናቸውና መንፈሳዊ ስያሜ የሰጠናቸው ወይም በአመክንዮአዊ አካሄድ ልከኝነትን ለመያዝ የተካረርንባቸው ነገሮች፣ የሆነብንን ወይም የደረሰብንን ነገር አጠበቁብን እንጂ መፍትሄ አልሰጡንም። በተለይ እንደ እግዚአብሔር ማኅበር የእርሱ የሕያው እግዚአብሔር መገኛ መሆን አልቻልንም። ስለዚህም በደረሰብን ነገር ሁሉ ጻዲቅ የሆነው እርሱ የሚራራልንና የሚለመነን ነውና እንዲረዳን መጸለይ አለብን።

ሁለተኛው እንዲህ ዓይነት የጸሎት ፕሮግራሞች ሲዘጋጁ ጸሎትን መማሪያ ስፍራችንም ናቸውና በእጅጉ እንጠቀማለን። ከመማር ያልጀመርናቸው፣ ከፉክክርና ከኩረጃ የቀዳናቸው ጸሎቶች አልረቡንም። ከእግዚአብሔር አሠራር ጋር አላዋደዱንም። ደቀመዛሙርቱ ሲከተሉት ቆይተው የሚነግራቸው ይዋኻዳቸው ዘንድ፣ የአምላክን መንገድ ይለምዱት ዘንድ፣ ከሕያው አምላክ ጋር ረዥም መንገድ ይሄዱ ዘንድ ጸሎትን ከጌታ ሊማሩ ወደዱና “ጸሎትን አስተምረን” ብለው ለመኑ። አሁንስ ማን ያስተምረን ዘንድ እንለምን? ወይስ እውነተኛውን የጸሎት ጭብጥና ልማድን ከማን እንማር? ያላችሁ እንደሆን የቅዱሳን ኅብረት ጥሩ ስፍራችን ነው። ጸሎት ጮሆ መመለስ፣ ተናግሮ መተንፈስ ብቻ የሚመስለው ትውልድ እየበዛ ነውና እስቲ ይህቺን የጸሎት ፕሮግራም ስለ ጸሎት ምንታረቅበት፣ ልባችንን ጭምር ምናበረክክበት፣ ለአምላክ እጅ የምንሰጥበት እንዲሆንልን እንጠቀምበት።

“ከከበረው ዕንቁ ሰው ከሚሻበት
ለኔስ ትህትና ባ’ገኝ በዚ’ች ‘ለት
ጥማቴም ጸሎቴም ዝቅ ዝቅ ማለት ....”

ቅዳሜ በጸሎት መርሃ ግብሩ እንድትገኙ እለምናችኋለሁ። እግዚአብሔር በገዛ ደሙ የዋጀውን ሕዝቡን ይርዳ - አሜን!! እግዚአብሔር ይህ ቀኝና ግራውን የማይለየውን ማኅበረሰባችንን ይርዳ - አሜን!!!

ተገኝ ሙሉጌታ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

"የጾምና የምልጃ ጸሎት” ፕሮግራም
ቀን፡- የካቲት 25 - 2015 ዓ.ም. (ቅዳሜ)
ሰዓት፡- ከቀኑ 3፡00-11:00 ሰዓት
ቦታ፡- ካዛንቺስ ኡራኤል መካነ ኢየሱስ ማህበረ ምዕመናን

በሚታየው ፖለቲካዊ ፣ ማኅበራዊና ኅይማኖታዊ አለመረጋጋትና
ምስቅልቅሎሽ ውስጥ እግዚአብሔር ጣልቃ እንዲገባና ጥላቻንና ጠብን አርቆ ለአገሪቱና ለሕዝቧ ምህረት እንዲያደርግ የምንጸለይበት መርኅ ግብር ነው።

አብረውን እንዲጸልዩ ተጋብዘዋል!

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

"የእኛ አባት፥ ስምህ ይቀደስ"
***

እውነተኛው አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔር (ዮሐ. 17፥3)፣ እጅግ የገነነ ብቻ ሳይኾን ባሕርይውንና ማንነቱን የሚገልጥ ስም አለው። ስሙ ራሱን፣ እሱነቱን ይወክላል። የእግዚአብሔር ስም የአስተርእዮው (የመገለጡ) ነጸብራቅ ነው (ዘፀ. 3፥14-15፤ ሆሴ. 12፥6)። ግልጠተ መለኮት ከስሙ ጋር የተቈራኘ ብቻ ሳይኾን፥" እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚችልበት ብቸኛው መንገድም ነው። ኤሚል ብረነር ከግማሽ ምእት ዓመት በፊት በታተመው መጽሐፉ እንዲህ ብሏል፦
.

"እግዚአብሔር የሚታወቀው ስሙን በገለጠበት ቦታና ኹኔታ ብቻ ነው፤ ከዚህ ራሱን የመግለጥ ኺደት ውጪ አይታወቅም፤ ከእኛ የእይታ አቅጣጫ የራቀና ሊደረስበት የማይችል ምጡቅና ኢውሱን ነውና። እርሱን ከማንኛውም ሌላ ነገር መካከል ልዩት (unique) ያደረገው፥ ልዩ የኾነው ‘ስሙ’ ነው፤ እግዚአብሔርን በሌላ ማንኛውም ዐይነት ጥቅል ግንዛቤ ልንረዳው አይቻለንም፤ የትኛውም የሰው ልጅ ዕውቀት ሊደርስበት ከሚችለው ኹሉ በላይ ይልቃል፤ ይረቅቃል፤ ይመጥቃል። በራሳችን አመክንዮኣዊ ግንዛቤ ላይ በተደገፈ ተመክሮ ልንደርስበትም አይቻለንም። ይልቁንም፣ ይኽ ዕውቀት በእግዚአብሔር ስጦታ ብቻ የሚገኝ መገለጣዊ ማስተዋል ነው።"*
.

በመጽሐፍ ቅዱሳዊ መገለጦች ማዕከላዊ ስፍራ ላይ የቆመው የእግዚአብሔር ስም መገለጥ ነው (ዘፀ. 6፥3)። የመገለጡ ዐቢይ ከፍታ እግዚአብሔር ራሱን በልጁ መግለጡ ነው። “ከቶውንም እግዚአብሔርን ያየ ማንም የለም፤ ነገር ግን በአብ ዕቅፍ ያለው አንድያ ልጁ የኾነው አምላክ እርሱ ገለጠው” (ዮሐ. 1፥18 አመት)። ኢየሱስ ይኽን “አብን የመግለጥ” ተልዕኮውን አስመልክቶ ሲናገር “ስሙን ከማስታወቅ” ጋር ማቈራኘቱን በይፋ አሳይቷል፤ “ከዓለም ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገለጥሁላቸው። የአንተ ነበሩ፤ ለእኔም ሰጠሃቸው፤ … እኔንም የወደድህባት ፍቅር በእነርሱ እንድትኾን እኔም በእነርሱ፥ ስምህን አስታወቅኋቸው፤ አስታውቃቸውማለሁ” (ዮሐ. 17፥6፡26) ብሏል። እኛም እንዲህ ስንል እንጮኻለን፤ አባታችን ሆይ፥ ስምህ ይቀደስ።

https://youtu.be/mR0C2WUppoM
______
*Emil Brunner, The Christian Doctrine of God: Dogmatics I (Cambridge: James Clarke & Co., 1949), 120.

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ተአምራቱ ቀጥሏል ¡

"መንፈስ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ እንጂ ስለራሱ አይናገርም!"

ዛሬ ደግሞ ነቢይ በላይ ሽፈራው ስለ መንፈስ ቅዱስ ማንነት፣ ስለ አምላካዊ ትህትናውና ኢየሱስን ስለሚያከብርበት ዓይነተኛ ጠባዩ እያወራ ደረስኩ። በቴሌቪዥን ማለቴ ነው። የሰዎቹ አያያዝ ለየት እያለብኝ ነው። ከዚህ ቀደም በትምህርታቸው የሰውን ልብና አእምሮ የነዋይ ፍቅር በተጠናወተው የብልጽግና ወንጌል መበከላቸውን እንደዋዛ ገሸሽ አድርገው፣ "አሜን ብለህ ቅለበው፣ ያዘው፣ ጨብጠው..." እያሉ ጉባኤ የሚያጯጩሁትን ዲስኩር ዘንግተው አሊያም ለጊዜው ቆም አድረገው የወንጌል ዋና መልዕክት ወደሆኑት ትምህርቶች ፊታቸውን ያዞሩ ይመስላል።

መድኮቹ ሁሉ ነቢያቱ ከራሳቸው ስለራሳቸው የሚያወሩበት ሆኖ ሳለ "መንፈስ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ እንጂ ከራሱ፣ ስለራሱ አይናገርም!" የሚለውን ስብከት ሞቅ አድርጎ ሲሰብከው ሰምቼም ነው "የተአምራቱ መቀጠል" የገረመኝ። ነቢይ በላይ ሽፈራው ስለ መንፈስ ቅዱስ ሲሰብክ እርሱ ስለ ኢየሱስ እንጂ ከራሱ፤ ስለ ራሱ ምንም እንደማይናገር ፤ አምላክ ሆኖ ሳለ ከኢየሱስ የሆነውን እንጂ ራሱን እንደማይሰብክ የሚተርክበት መንገድ አፍ ያስከፍታል።

በተገኘበት መድረክ ሁሉ ስለ $ብርርርር ሳያወራ፣ "ሚሊዬነር" የሚል ቃል ሳይጠቅስ የማይወርደው ሰውዬ ቃል በቃል፦ "መንፈስ ቅዱስ ሰውን ወደ ክርስቶስ እንጂ ወደ ገንዘብ አይመራም!" ሲል ብሰማውም ነው "ተአምራቱ ቀጥሏል¡" ያልኩት። ለተአምሩ ዓይነት የተጠቀምኩት ምልክት "ትምህርተ ስላቅ" (¡) መሆኑን ልብ ይሏል። ተሳላቂውም የስላቁ ባለቤት እንጂ እኔ አይደለሁም።

በየሠፈሩ የተንጣለለ አዳራሽ ቀልሰው ሕዝብ እየሰበሰቡ፣ በ24 ሰዓት የቴሌቪዥን ፕሮግራሞቻቸው ሰማይና ምድሩን ተቆጣጥረው የሚገኙቴ ባልንጀሮቹ በጣቢያቸው አየር ላይ ነግሰው ዘጠና አምስት እጅ የሚሆነው መርሀ ግብራቸው አምልኮተ ሰብዕን በሚያበረታታ፣ አለኝ የሚሉትን የፈውስ ኃይልና ምስጢርን የመግለጽ ጸጋ ራሳቸው ከራሳቸው የሚያመነጩት አድረገው እስኪመስል ማቅረባቸውም በአለም አደባባይ የወጣ ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው።

ወንጌል በጸጋ ስጦታነታቸው የሚዘረዝራቸው የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ኢየሱስ የሚከብርበት መሆኑ ከቀረም ሰነባብቷል። የየነቢያቱ አገልግሎት ተቋዳሾች ፊታቸው ላይ ካሜራ ተደቅኖባቸው እንዲመሰክሩ የሚገፋፉት ስለ ገስት ሀውሳቸው ቅዱስ ቦታነት፣ ስለ ነቢዩ አስገራሚ ጸጋ እንጂ ስለ ኢየሱስ አይደለም።

መስካሪዎቹ፦ "ነቢዩ መጣና እጁን ሲጭንብኝ...፣ በዘይት ሲጸልይልኝ...ውሃ ሲያጠጣኝ... ላቡን የጠረገበትን ሶፍት በውሃ በጥብጬ ስጠጣ... ወዘተ ተፈወስኩ" እንዲሉ እንጂ የኢየሱስ ፈወሰኝ ብለው ስሙን እንዲጠሩ ግድ አይባሉም። "መንፈስ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ እንጂ ከራሱ፣ ስለራሱ ምንም አይናገርም!" ከሚለው ከነቢይ በላይ ሽፈራው የአሁኑ ጤናማ የወንጌል ቃል አንጻር ስቃኘውም ኢየሱስ በነቢያት ተብዬዎቹ ቤተ መቅደስ ውስጥ እንኳን ሊከብር ቀርቶ የክብራቸው ተጋሪ እንኳ እንዳይሆን ውሽልሽል ያለ ሸፍጥ እየፈጸሙበት ነው። ይኼ ደግሞ እነዚህ ሰዎች ስተው እያሳቱ ያሉት እውነቱ ጠፍቷቸው ሳይሆን በምርጫቸው እንደሆነ ጥቁምታን ይሰጣል።

አንዳንድ ወገኖች እንዲህ ዓይነት ሂስ ሲሰነዘር ከጥላቻና ከቅናት ጋር ቢያያይዙትም እውነታው ግን የግድ መነገር አለበት። የዕለቱ መልዕክቴም እናንተ ሆይ እባካችሁ ከአስመሳይነት ውጡና፣ መንፈስ ቅዱስ ብቻውን ከፍ ከፍ ይል ዘንድ የሚሻውን ኢየሱስን ብቻ አክብሩ። ራሳችሁንም ሆነ የሚከተላችሁን ሕዝብም ከእኔነት እሥራት፣ አፍቅሮተ ንዋይና ካልተገባ ክብር ፍለጋ አድኑ። ነቢይ በላይ ሽፈራው እንዳለው በእርሱም ሆነ በእናንተ ውስጥ አድሮ እየሠራ ያለው በእርግጥ መንፈስ ቅዱስ ከሆነ ከራሳችሁ፣ ስለ ራሳችሁ መስበክ አቁሙና እንታረቃችሁ። "ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደ ሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክምና፥ ስለ ኢየሱስም ራሳችንን ለእናንተ ባሪያዎች እናደርጋለን።" (2ኛ ቆሮ.4÷5) ተብሎ በተጻፈው ቃል ፈትነን እንደ ወንድሞች እንቀበላችሁ።

©ሽመልስ ይፍሩ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የኢኦተቤ/ክ ባትከፈል ደስታዬ ነው። መከፈሏን አልመኝም። መታደስና ወደ ቃሉ እውነት መምጣት እንዳለባት ከሚያምኑት ግን ነኝ።

ከዐፄ ቴድሮስ ዘመንና ከዚያም በፊት፥ ከነፒተር ሃይሊንግ ጀምሮና ከዚያም በኋላ የመጀመሪያዎቹ ወንጌላውያን ሚስዮናውያን ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ አንግበው የመጡት ዓላማ ቤተ ክርስቲያን መኖሯን ተቀብለው መታደስ ግን አለባቸው ያሏቸውን የሰሜን አፍሪቃና መካከለኛው ምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናትን ወደ ቃሉ እውነት በመመለስ ለማደስ ነበር። በተለይ ኢትዮጵያ ላይ ያተኮሩት ይህች ቤተ ክርስቲያን (የኢኦተቤክ) ታድሳ ወንጌልን ብትዘራ ለአፍሪቃም የሚበቃ ጉልበት አላት በማለት ነበር። ይህ እንደማይሆን ሲረጋገጥ ነው ከመሐሉ አገር ተገፍተው ወንጌልን ወደ ዳር ድንበሩ ብቻ እንዲሰብኩ የተደረጉት። ያውም መጀመሪያ ከመሐል አገር ከፈላሻና ከአረማውያን መካከል ያመኑ ከኖሩ በኦርቶዶክስ ቤ/ክ ሥርዓት እንዲጠመቁ ግድ ተብለው ነበር።

ባለፉት ብዙ አሠርታት በቤተ ክርስቲያኒቱ ተሐድሶዎች ሲኖሩ የሁሌም ምኞቴ ተባርረው እንዲወጡ ሳይሆን እዚያው ኖረው እንዲያገለግሉ ነበር። መጀመሪያ ያየሁት የተሐድሶ እንቅስቃሴ አሥመራ ነበር። ወጣቶቹ ከአጥቢያቸው አይወጡም፤ እዚያው ሆነው በጥርጥር እየታዩም፥ እየተሰደዱም የወንጌልን እውነት ይሰብካሉ። ሲያቅታቸው ብቻ ይወጣሉ፤ ወጥተውም ወደ ነባሮቹ ወንጌላውያን አማኞች ይደባለቃሉ። የኔ ምኞት ያ ባይሆን ነበር። ያኔም ቅርጻቸው ሳይለወጥ ይዘታቸው ብቻ ታድሶ ለብቻቸው እንዲቆዩ ነበር። አልሆነም። አንድ ረዘም ላለ ጊዜ የቆየ ተሐድሶ ያየሁት እንዳ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብቻ ነበረ። ያም የኋላ ዕጣ ፈንታው ምን መሆኑን አላወቅሁም።

ከአሥመራ ወደ መሐል አገር ስመለስ የአማኑኤል ቤተ ክርስቲያን የሆነው እንቅስቃሴ ሲጀመር አሁንም ምኞቴ አሥመራ ሳለሁ እንደተመኘሁት ያለው ነበር። አልሆነም። አገልግሎቴ ደብረ ዘይት ነበረና እዚያ ካለችው አጥቢያ ጋር በኛ ቤ/ክ መጽሐፍ ቅዱስ ት/ቤት ምክንያት በጥቂት እገናኝ ነበር። ሳየው ሳየው አማኑኤል ላትመለስ ወጥታለች። መውጣት ብቻ ሳይሆን ከፔንቲኮስታሎቹም ብሳለች። በቁጥር ሲሰሉ ጥቂት ቢባሉም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ሳይወጡ ያልተበረዘውንና ያልቀጠነውን ወንጌል የሚሰብኩ እንዳሉ የታወቀ ነው። ደግሞም እጅግ ብዙ ሺህዎች በክርስቶስ ብቻ አዳኝነት አምነው የሚያገለግሉ እንዳሉም አውቃለሁ። የክርስቶስ አዳኝነት ስል ለአንዳንዶች የማይዋጥ መሆኑን እቀበላለሁ። ቢሆንም ተግባራዊና ግንዛቤያዊ እውነቱን ስናጤነው ነገሩ እውነት ነው። ከሦስት ዓመት በፊት ለወንጌል ሥራ አገር ቤት ሳለሁ ሥልጠና ከሰጠናቸው ቀሳውስት መካከል ተገኝቼ ይህን አይቻለሁ። እነዚህ ሰዎች የማይወጡና ሌላ ማኅበር የማይመሠርቱ ሰዎች ናቸው። ምኞቴን መሬት ላይ ስላየሁት ደስተኛ ሆኜ ነበር በዚያ ጉዞ ከሰሜን የተመለስኩት።

በቃሉ የምናውቀው እግዚአብሔር ቤቱን የማደስ እንጂ ቤተ እምነት የመክፈል አጀንዳ የለውም። አሁን በኢኦተቤ/ክ የተከሰተው ነገር ዮናታን የተነበየው ትንበያ ነው ብዬ አላምንም። ‘በወደፊታዊ ትንበያ ስጦታነት አላምንም’ ብዬ ከዚህ በፊት ገልጫለሁ። አሁንም በወደፊታዊ ትንበያ ስጦታነት አላምንም። ወደፊት የሚፈጸም አንድ ግልጽ ትንቢት የክርስቶስ ዳግም መምጣትና ከመምጣቱ በፊት በዓለማችን የሚከሰቱ ነገሮች ናቸው። ሌሎቹ ነገሮች ሁሉ፥ በነሲብ ተነግረው የሚፈጸሙትም ጭምር፥ ተናጋሪዎቹን (ተንባዮቹን) ተጠያቂ ለማድረግ ኤግዚቢት መሆን ይችላሉ። የተነገረው እኔ የሰማሁት ብቻ ከሆነ፥ ዮናታን ተናገረ የተባለው ትንበያ ስለ ኢኦተቤ/ክ መሆኑም ግልጽ አይደለም። የሴራ ፖለቲካ ሊኖር እንደሚችል ባውቅም፥ በዮናታንና በመንግሥት፥ በመንግሥትና በኦርቶዶክስ ካህናት፥ በኦርቶዶክስ ካህናትና በዘር ፖለቲካ አራማጆች መካከል የተሸረበ ሴራ አለ ብዬ አላምንም። ሁለቱን የተለያዩ ሲኖዶሶች አንድ ያደረገ መንግሥት እንደገና ይፈነክታታል ማለት ተአማኒነት ለማግኘት ብዙ መልፋት ያለበት ቂሪላ ነው።

በቤተ ክርስቲያን መከፈል ብዙ ልምድ ያለን እኛ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ነን። የኛው ክፍፍል በአንድ በኩል የነጻነታችንና በአንድ ሰው የአለመመራታችንና በአንድና አንድ ብቻ መዋቅር ስር የአለመሆናችን በረከት ቢሆንም ብዙ ስጋዊና ጥቅማዊ የሆኑ ኢመንፈሳዊ ጉዳዮች እንዳሉበትም የታወቀ ነው። የቤተ ክርስቲያን ፖለቲካም ራሱን የቻለ ጉዳይ ነው። የኢኦተቤ/ክ በአገራችን ፖለቲካ ውስጥም በተለይ ከ13ኛው ምዕት ዓመት ጀምሮ (ገድለ ተክሌን አዚህ ላይ አለማስታወስ አይቻልም) ትልቅ ሚናና ድርሻ ቢኖራትም፥ ይህ ምድራዊ ጥቅምና መብትና ሥልጣን አጎናጸፋት እንጂ ከቃሉ የምናነብበውን የወንጌል አደራ እንደ ወንጌል አደራነቱ እንድታቀላጥፈው ረድቷታል ብዬ ለመቀበል እቸገራለሁ። ምድራዊ ሥልጣን ባለበት ደግሞ ብዙ ሽኩቻዎች አሉ። አሁን በአገራችን እንዳለው የመሰለ የዘር ፖለቲካ እስሌቱ ውስጥ ሲገባ ደግሞ በአሳት ላይ ነዳጅ መጨመር ነው። ቤተ ክርስቲያን ከዘረኝነት የጸዳች ልትሆን የተገባት ቢሆንም ያልጸዳችባቸው ታሪኮች አሏት። በቅርብ እንኳ የትግራይ ሲኖዶስ ተገነጠልኩ ብሎ ነበር፤ ወይም እንዲል ተገድዶ ነበር። እንዲህ ያለው ችግር ከኖረ በጉባኤው እንደሚፈታና ለዘለቄታም እንደማይደገም አስባለሁ እመኛለሁም።

በጀመርኩበት ቃል ልጨርስ። የኢኦተቤ/ክ ባትከፈል ደስታዬ ነው። መከፈሏን አልመኝም። መታደስና ወደ ቃሉ እውነት መምጣት እንዳለባት ከሚያምኑት ግን ነኝ።

ዘላለም ነኝ።

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

1፥ 32-34)።

ዮሐንስ ከመታሰሩ በፊት የመጨረሻ ምስክርነት ይሰጣል . . .

▶ እኔ ሚዜ ነኝ - የእኔ ሕይወት ስለ ሙሽራው ነው። የሰርግ መርሐ-ግብር ድምቀት ሙሽራው እንደሆነ ሁሉ፣ እኔም የመጣኹት በእግዚአብሔር የድነት መርሐ-ግብር ውስጥ መካከላኛ የሆነውን ክርስቶስ ለማድመቅ ነው! እርሱ የአብ የክብር ነጸብራቅ ነው፤ የእኔም ሥራ ሙሽራውን ማድመቅ ነው። የደስታዬ ምክንያት ክርስቶስ ሲደምቅ ነው። “ሙሽራዪቱ የሙሽራው ነች፤ ድምፁን ለመስማት በአጠገቡ የሚቆመው ሚዜ ግን፣ የሙሽራውን ድምፅ ሲሰማ እጅግ ደስ ይለዋል፤ ያ ደስታ የእኔ ነው፤ እርሱም አሁን ተፈጽሞአል።" (ዮሐ. 3፥29)። ወገኖቼ፣ ለእኛም ክርስቶስን ማግነን፤ ማድመቅ፤ ማሳየት፤ ይሁንል! አሜን!

▶ እርሱ ከሁሉ እንደሚበለጥ እመሰክራለሁ - ከአብርሃም፣ ከሙሴ፣ ከአሮን፣ ከነቢያት፣ ከእኔም ከመጥምቁ ዮሐንስ ይበልጣል! እኛ ሁላችን ጫማውን እንኳን ለመሸከም የማይገባን አገልጋዩቹ ነን። እርሱ ጌታችን፣ አብን የገለጠ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ልጅ ነው። አብ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” በማለት የመሰከረለት እርሱ ክርስቶስ ከሁሉ ይልቃል! ስለዚህ፣ "እርሱ ሊልቅ፣ እኔ ግን ላንስ ይገባል . . . ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሆነው የምድር ነው፤ የምድሩንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው. . .” (ዮሐ. 1፥30-31)።

የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት መልእክት ያድሰን፤ እርሱ በሁሉ ነገር በቤተ ክርስቲያን ልቆ ይታይ፤ መልእክታችንም እርሱ ብቻ ይሁንልን!

አሜን!

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

Book Recommendation!

A New Apostolic Reformation? A Biblical Response to a Worldwide Movement

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

“ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም፣ ሰላምም እርሱ ለሚወድዳቸው ሰዎች በምድር ይሁን!”
(ሉቃስ 2 : 14 )

ሰው በኀጢአት ምክንያት ለገባበት ቀውስ በመጨረሻና በብቸኛ መድኀኒትነት እግዚአብሔር ራሱን በአንድያ ልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ገልጧል። አምላክ ሥጋ ኾነ! በድነት የታሪክ ውቅር ውስጥ ይህ ዘመን የማይሽረው ወሳኝ እውነት ነው። “ነገር ግን የተወሰነው ዘመን በደረሰ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን፣ ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ” (ገላትያ 4:4)። የጊዜ ፈጣሪ የኾነው ዘላለማዊ አምላክ፣ እርሱ ራሱ በልዕልናው በወሰነው ሰዓት ሥጋ ኾነ። እርሱ ብቸኛ መድኅን ነው። እኩያ፣ ደባል፣ ተፎካካሪ ወይም የበላይ የለውም። የቤተ ክርስቲያን ማንነትና ተልክእኮ መሉ ለሙሉ ያረፈው በዚህ እውነት ብቻ ላይ ነው። ይህ ዐርነት የሚሰጥ ብቸኛ እውነት ያድሰን። ከኀጢአትና ጦሱ ነጻ ሊያወጣን፣ አምላክ ሥጋ ኾነ፤ በእኛም መካከል ዐደረ!

በድጋሚ፣ ቅዱስ አውግስጢኖስ እንዳለው፦

"ጊዜን ሁሉ የፈጠረበት የአብ ቃል ሥጋ ኾነ፤ በጊዜም ውስጥ ለእኛ ተወለደልን። የየትኛውም ቀን ክንውን ያለ እርሱ መለኮታዊ ፈቃድ የማይጠናቀቅ ሆነ ሳለ፣ ሰው ኾኖ የሚወለድበት ቀን እንዲለይ ፈለገ። የዓመታት ዑደት ሳይፈጠሩ በፊት እርሱ በአባቱ ዕቅፍ ነበር፤ ከምድራዊም እናት በመወለድ በዓመታት ሂደት መካከል በዚህ ቀን ተገለጠ።
ከእናቱ ጡት ይጠባ ዘንድ፣ የከዋክብት ገዢ የሆነው የሰው ፈጣሪ ሰው ኾነ።
እንጀራ የኾነው፣ ይራብ ዘንድ
ምንጭ የኾነው፣ ይጠማ ዘንድ
ብርሃን የኾነው፣ ያነቀላፋ ዘንድ
መንገድ የኾነው፣ በጉዞ ይዝል ዘንድ
እውነት የኾነው፣ በሐሰት ይከሰስ ዘንድ
በሕያዋንና በሙታን ላይ የሚፈርደው፣ በመዋቲ ዳኛ ፊት ለችሎት ይቀርብ ዘንድ
ፍትሕ የሆነው፣ በኢፍትሐውያን ይኮነን ዘንድ
[በጽድቅ] የሚገሥጸው፣ በጅራፍ ይገረፍ ዘንድ
የሁሉ ነገር መሠረት የኾነው፣ በመስቀል ላይ ይንጠለጠል ዘንድ
ብርቱው የሆነው፣ ደካማ ይኾን ዘንድ
ፈዋሹ፣ ይቈስል ዘንድ
ሕያው የሆነው፣ ይሞት ዘንድ - ሰው ኾነ
ከነቱ የሆነውን እኛ ፍጥረቱን ነጻ ሊያወጣ፣ እነዚህንና የመሳሰሉ ውርደቶችን በጽኑ ታገሠ። ከዘመናት በፊት፣ ያለጅማሬ ለዘላለም የእግዚአብሔር ሕያው ልጅ ሆኖ የኖረው፣ የሰው ልጅ ለመሆን በዘመናት መካከል ራሱን ዝቅ አደረገ። ይህን ሁሉ ያደረገውና ለታታላቅ ክፋቶች ራሱን ያስገዛው ስለ እኛ ሲል እንጂ ፈጽሞውኑ ክፋት አድርጐ አይደለም፤ ይልቁንም የተትረፈረፈ መልካምነትን ከእጁ የተቀበልነው እኛ፣ ቸርነቱን ለመቀበል የሚያስችል ምንም በጐነት የለንም።"

ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለዘላለም ክብር ይሁን!

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በዓል አደረሳችሁ።

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

አእምሯችንን ከ"አዲሱ ሃይማኖት" እሳቤዎች እንጠብቅ!

የአኗኗር ብልሃት አሰልጣኝ ወይም "ላይፍ ኮች" ነን የሚሉቱ ዘመነኞቹ የአነቃቂ ንግግር (ሞቲቬሽናል ስፒች) ባለሙያዎች ወይም በተገቢው ስማቸው የአዲሱ ሃይማኖት ሰባኪያን "የእኛ የሰው ልጆች ትልቁ ችግር የአምስቱ የስሜት ህዋሳታችን ጫጫታ ነው።" ይላሉ። ጫጫታውና ረብሻው ከዚህ ዓለም ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ካለውና በጊዜና በቦታ ከተወሰነው ንቁው የአእምሯችን ክፍል ጋር የተያያዘ ሰለሆነ እርሱን ችላ ብለን በከፊል ብቻ ንቁ በሆነው የአእምሯችን ክፍል ላይ ብናተኩር፣ ወደዚያ ጠልቀን ብንገባ ከግርግሩ መደበቂያ የሚሆን አንዳች ጉድባ፣ ፍሰሃ የሞላበት አንዳች ሰርጥ እናገኛለን ይላሉ። እውነተኛው ማንነታችን ተሸጉጦ የሚገኘው በፍዙ የአእምሯችን ክፍል ውስጥ እንደሆነ ይሰብካሉ። ፍለጋውን "ሰልፍ ሪያላዜሽን" ይሉታል።

በእነዚህ ሰዎች አስተምህሮ ስሙ በጣም ጎልቶ የሚጠቀስ ኤክሃርት ቶሌ የሚባል ጉሩ (መንፈሳዊ መምህር) አለ። የሰውዬው ትምህርት ፍልስፍናዊ ወይም ሳይንሳዊ ሳይሆን ሃይማኖታዊ ነው። በኢቢ ኤስ ቴሌቪዥን የዳጊ ሾው መርሃ ግብር ሆስት የሆነችው እንስት አብዛኛው እሳቦቶች የተቀዱት ከዚህ ሰው እንደሆነ በሰይፉ ፋንታሁን ሾው ላይ ቀርባ የተናገረችውም በቅርቡ ነው። አብዛኞቹ እንግዶቿ የዚህ ነገር ዝንባሌ ያላቸው መሆኑን ግን ቀድሞውንም ይታወቃል። ልጅት የኤክሃርት ቶሌ ደቀ መዝሙር መሆኗን በይፋ ሳትናገር ነው ቀስ በቀስ ዙሩን እያከረረች የመጣችው። መጻሕፍቶቹን ማንበብ፣ ትምህርቶቹን ማድመጥ ብቻ ሳይሆን ቡራኬውን ለመቀበል ጭምር ወዳለበት ሀገር ተጉዛለች።

በዳዊት ድሪምስ መድረክ ላይ ራሷን ስትሟሟቅ የሰነበተችው ዳግማዊት ክፍሌ በቅርቡ ደግሞ የኗኗር ብልሃት አሠልጣኝነትን (ላይፍ ኮች) ካባ ደርባ በግሏ ሥልጠና ለመስጠት መስታወቂያ ባወጣችበት ጥቂት ቀናት ውስጥ ሦስት ሺህ ተመዝጋቢዎችን አግኝታለች። ሰይፉ ፋንታሁንም ይኼንኑ በግርምት ሲያነሳው ነበር። እርሱም ሆነ ብሎ ትቶት እንጂ በዚህ ሥልጠና አላባውያን ላይ ሊነሱ የሚገቡ ጥያቄዎች መኖራቸው አይጠፋውም ነበር። ዳግማዊት የኤርክሃ ቶሌን መንፈሳዊ አስተማሪነት እየነገረችው እንኳ በዚያ ላይ ምንም ማለት አልፈለገም።

ዛሬ ላይ የትኛውም አነቃቂ ንግግር አድራጊ የኤክሃርት ቶሌን "ዘ ፓወር ኦፍ ናው" እና የሮንዳ ባይርንን "ዘ ሴክሪት" የተሰኙ መጻሕፍት ባለውለታነት ሳይጠቅስ አያልፍም። የሕይወት መመሪያቸው ራሱ በአብዛኛው የተቀዳው ከነዚሁ መጻሕፍት ነው። ለአብነት ያህል የኤክሃርት ቶሌ ደቀ መዛሙርት ስለ "አሁን ኃይል" ሲናገሩ፦ "የአሁን ኃይል (ዚ ፓወር ኦፍ ናው) ከጊዜ ሃሳብ ወጥተን እውነተኛ ማንነታችንን እንድናውቅ፣ ከመንፈሳዊ ህመማችን ተፈውሰን ጥልቅ ውሳጣዊ ሰላም እንድናገኝ የሚረዳን መንፈሳዊ የራስ አገዝ መመሪያ ነው" ይላሉ።

"በአሁን ጠንካራ ሁኔታ ውስጥ ስንገኝ፣ ከጥልቁ ንቃተ ህሊና ምላሽ እናገኛለን፣ በህይወት የደስታ ባህር ውስጥ እንሳፈፋለን" ሲሉም በግኝታቸው ይጓደዳሉ። ካሻቸው፦ "ኢየሱስ 'በእኔ የሚያምን የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል' እንዳለው አይነት ነው" ብለው ሊጠቅሱም ይችላሉ። እውነቱ ግና ወደ እግዚአብሔር ደስታ የሚያደርስ እግዚአብሔር መኖሩ ከቁብ የሚገባ አለመሆኑ ነው። የዚህ ሃይማኖት ማዕከሉ ሰው ነው። ሁሉን አቃፊ ሃይማኖትም ነው። የሃይማኖቱ ቄስ፣ ኤክሃርት ቶሌም ከየትኛውም ሀይማኖት ይበጀኛል የሚለውን ሃሳብ መዥረጥ አድርጎ እንደሚወስድ፣ የዜን ቡዲዝምንና የሱፊዝም ትምህርቶች እንደሚጠቀም፣ ከሂንዱይዝምና ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች እንደሚጠቅስ ይታወቃል።

የዳጊ ሾው አዘጋጅና አቅራቢ ዳግማዊት ክፍሌ በዚሁ ሳምንት እንግዳዋ ከነበረችው ወጣት ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ያደመጠ ሰው አዲሱ ሃይማኖት ምንኛ በደጃችን እያደባ እንዳለ ጥቁምታ ይሰጣል። በእሳቦትቱና በባህርይው ከቃል እምነት አስተምህሮ ጋር ኩታ ገጠም እንደሆነም ይገነዘባል። አዲሱ ሃይማኖት እንደ ቃል እምነት (ዎርድ ኦፍ ፌዝ) እንቅስቃሴ ሁሉ የሃሳቡ ቀደምት አመንጪዎችና አዳባሪዎች እንጂ እገሌ የሚባል መሪ የለውም። ለሰዎች ሌላ ሃይማኖት እንደሆነ የማይረዱትም ለዛ ነው።

ዳግማዊት ክፍሌ እና ታዳጊዋ ወጣት ካደረጉት ቃለ ምልልስ ጥቂቱን ልጥቀስ። ወጣቷ፦ "ሎው ኦፍ አትራክሽን ላንቺ ምንድነው? ተብላ ስትጠየቅ፦ "ሎው ኦፍ አትራክሽን አንድን ነገር በአእምሯችን ደጋግሞ በማሰብ ወደ እውኑ ዓለም የምንለውጥበት ኃይል ነው።" በማለት ስትመልስ፤ ጠያቂዋ፦"እስቲ ስለ ማኒፌስቴሽን ደግሞ ንገሪኝ" ባለቻት ጊዜ ደግሞ የታዳጊ ወጣቷ ፌቨን መኮንን ምላሽ፦"ለእኔ ማኒፌስቴሽን ማለት አንድ እንዲሆንልኝ የምፈልገውን ነገር አጠንክሬ ካሰብኩት ፈጣሪ ይሰጠኛል፣ ያሳካልኛል ማለት ነው። ወይም እንደዛ ብዬ ነው የማምነው። ማኒፌስቴሽን የምለው ያንን ነው። ስለ ማንፌስቴሽን ያወቅሁት በዚያ ላይ የተጻፈ መጽሐፍ አንብቤ ነው።" የሚል ነው። ማኒፌስቴሽን ራሱን የቻለ ትምህርት እንዳለው ልብ ይሏል።

በዳግማዊት ክፍሌ ቀጣዩ ጥያቄም ውስጥ ጭብጡ ተቀምጧል። "እንግዲህ ስለመጠየቅ፤ ከዚያ ደግሞ ስለማመን፤ ከዚያ ያመነውን ነገር ስለመቀበል እያወራን ነው። 'ዘ ሴክሪትን' እና 'ዘ ሎው ኦፍ ዘ ዩኒቨርስን' እንዳነበብሽም ነግረሺኛል። ከዚያ ስላገኘሽው ውጤት እንደምሳሌ የምታነሺው ምንድነው?" ስትል ዳግማዊት ላቀረበችው ጥያቄ ፌቨን መኮንን በሰጠችው ምላሽ፤ የትምህርት ቤት ጓደኞቿ ውጤት ለማምጣት ሲፈጉ፣ ፈተና ለማለፍ የመማሪያ መጽሕፍቱን ሁሉ በማንበብ ጊዜ ሲያጠፉ፣ መሉ ሰሚስተሩን ሲያጠኑ እርሷና የእርሷ ዓይነት እምነት ያላቸው ልጆች ግና በጥቂት ንባብ ውጤት ማምጣት እንደቻሉ፣ የሚፈልጉትን ነገረ የመጠየቅ፣ የማመንና በቀላሉ የመቀበል መርህ እንደሰራላቸው ገልጻለች። ይኼ ደግሞ ጃፒ በቤተ እምነቱ መድረክ ላይ እየተወራጨ ከሚሰብከው ስብከት የተለየ አይደለም።

በነገራችን ላይ የ"ዘ ሎው ኦፍ ዘ ዩኒቨርስ" ዋና ሃሳብ የአጽናፈ ዓለሙን ህግ የመለኮታዊ አንድነት ህግ ብሎ የማመን ጉዳይ ነው። ይህ ህግ ሁሉም ነገር እርስ በእርሱ የተገናኘ ስለመሆኑና ምንም ነገር ከሌላው የተነጠለ እንዳልሆነ የሚብራራበት የአዲሱ ሃይማኖት አስተምህሮ አንዱ ክፍል ነው። በዚህ ዓለም ላይ ምንም አይነት ሁኔታ ቢፈጠር የሰው ልጆች መንፈሳዊ ደረጃ ምንም ሳይቀንስ ከመለኮት ጋር እርስ በእርስ የተጋመደ መሆኑም ይታመናል። እዚህ ውስጥ የአዳም፣ ውድቀት፣ የእግዚአብሔር ቁጣና ምህረት ወ.ዘ.ተ ብሎ ነገር የለም። እንከን ቢገኝ ለመንጻት የክርስቶስ ደም ብቸኛው መድኅን አይደለም። የዚህ ሃይማኖት የመንጻት ሥርዓት አሉታዊ አስተሳሰብን ማስወገድ፣ ከትናንት ጸጸት፣ ከነገ ፍርሃት ሸሽቶ አሁንን የመኖር ሰዋዊ ብልሃት ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ግና ስለ ፈጣሪያችንና አዳኛችን ሲናገር፦" እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን። እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው። የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። እርሱም ከሁሉ በፊት ነው ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል። (ቆላ.15-17) እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ፥ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠላቶች

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የጳውሎስ ወንጌል ሌላ፤ የነጩፋ የነዮናታን ሌላ!

'ኢየሱስም ጳውሎስም እየገሰጹ እየተቆጡም ወንጌል ሰብከዋል፣ የሰበኩትም ሰውን አስቆጥቷል። ታዲያ እነ ዮናታን ያጠፉት ምንድነው' መሰል ክርክር ምን የሚሉት ነው? የማይሆን ንጽጽር! የቅዱሳት መጻሕፍት ሰባኪዎች ፍቅርንና እና ለሌላው መትረፍ፣ ሌላውን ለማዳን ማገልገል የአገልግሎታቸው መነሻ መሆኑን ማጽናት ተገቢ ነው። በእርግጥም መነሻቸው ፍቅር፥ ግባቸው የሰው መዳን ነው። ለዚህኛውስ ወንጌል ለሚሰጠው ማንኛውም ምላሽ 'አዎ ልክ ነው' ይባላል፣ ከመጣም ዋጋ ይከፈላል! ይህኛው ሌላ፤ የሐሰት አስተማሪ 'ወንጌል' ተብዬ ድስኩር፤ ከጨካኝ ልባቸው የሚወጣ ገደብ የለሽ የጭከና መንፈስ ጩኸት ልፍለፋ፤ ግን ሌላ!

ዛሬ ዛሬ ሰዎቹ ከዬትኛው መንፈስ እንደሆኑ ብቻ አይደለም ያለን ጥያቄ፤ የአንዳንዶች የ'ወንጌል' ሰባኪና 'ወንጌል ጠባቂ' የልብ አዕምሮ ሁኔታም ነው የሚያሳስበን!

ለዓመታት በተግሳጽ 'ሲኦል ተዘጋጅቶላችኋል፣አሁኑኑ ንሥሐ ግቡ' የሚለውን የሜክሲኮ-ስታዲዬም ተወዋዋሪ የጎዳና ወንጌል ሰባኪ ባለፈው ሳየው ገረመኝ። ከገጽታውም በላይ፤ መጽሐፍ ቅዱሱ ወይቧል፣ የማስታወሻ ወረቀቶቹ በዝተዋል፣ ተጨራምተው ቆሽሸዋል። አሁን ደግሞ አዳዲስ የንቀት ስድብንም ለአላፊ-አግዳሚው በየልክ እየሰፋ መወርወርን ጨመርመር አድርጎበታል። ተላላ 'ወንጌሉ በእንዲህም መንገድ ይሰበካል' ሊል ይችል ይሆናል። ሰውዬው ግን የአዕምሮ ታማሚነቱ፥ እንደባሰበትም ለማወቅ ሐኪም መሆን አይጠይቅም !

ባለፈው አንድ ጎምቱ ጸሐፊ የፓይለቶች በየስድስት ወሩ የአዕምሮ ጤንነት ምርመራ እንደሚያደርጉ ግዴታ እንዳለባቸው የተናረው ልብ ማለት ተገቢ መሆኑን አምኛለሁ። የዛሬዎቹን አገልጋዮች የስራቸውን ጫና ብዛት፣ ሰዎቹ ወደ ቤተክርስቲያን የመጡበት ልዩ ልዩ መንገድ ካየን፤ ቢሆንማ 'ያ እና ይህ' ሳይባል ለሰባኪ፥ ለቤተክርስቲያን መሪ አገልጋዮች፥
ለእግዚአብሔር መንግሥት ቀኚ የግራ የቀኙ 'የወንጌል ጤንነት' ተከላካዮች፣ ቢያንስ በየስድስ ሳምንቱ 'የአዕምሮ ጤንነት' ምርመራ ሳያስልገን አልቀረም። ግድ የላችሁም ይጠቅመናል!

የመናፍስቱና የአዕምሮ በሽተኞች በየፊናም ሆኖ ተናቦ መስራት ወንጌላዊውን እምነት ዋጋ እንዳያሳጣው ያሰጋል። አሁን አሁን በግራ-ቀኙ የሚታዬው ከልክ ያለፈ በ'ወንጌል ጠባቂነት' ስም እውቅና የበላይነት ፍለጋ ሩጫ የአዕምሮ በሽታ ምልክት ካልሆነ ይገርመኛል (ባለሙያዎች ያን ሲሉም ሰምቻለሁ)፤ ከራስ ክብር መውደድ ልክፍት የመነጨው የነ ጩፋ የጭከና ነበልባላዊ 'ወንጌል' ስብከት ልቡም፥ መንፈሱም ምድቡም ከበሽተኞች እንጂ የነጳውሎስ ሊሆን እንዴትም ሊሆን አይችልም፤ ጥርት ብሎም ሊታየን የግድ ነው!

አፈወርቅ ኃይሉ (ዶ/ር)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ሞትን አፈራለሁ፣ ሳሳለሁ ለነፍሴ
ከተስፋዬ ሮበሌ

​የ“ነገር በምሳሌ፣ ጠጅ በብርሌ” ብሂል ደጋፊ ነኝ፡፡ “ብርሌውንና ጠጁን” ጥለን፣ “ነገሩንና ምሳሌውን” አንጠልጥለን እንጓዝ፡፡ የፍልስፍና ምሁራን፣ “thought experiment” የሚሉት ነገር አለ፡፡ መላምት ላይ የተመሠረቱ ልብ ወለድ ዐሳቦችን በማቅረብ፣ መላምቱ የተመሠረተበት ቀመር ነባራዊ መሠረት ይመረምራሉ፡፡ “thought experiment” “የዐሳብ ቤተ ሙከራ” ያልሁት፣ በዚህ አግባብ ነው፡፡ የሳይንስ ምሁራን፣ ቊሳዊ ቤተ ሙከራ አላቸው፡፡ ኬሚካልን ከኬሚካል ጋር ያጋጩበታል፡፡ ግኝት ይመዘግቡበታል ወዘተ፡፡ የፍልስፍና ሊቃውንት፣ በዐሳብ ቤተ ሙከራ ውስጥ ዐሳብን ከዐሳብ ጋር ያፋጫሉ (ያላጋሉ)፡፡ በዚህ መንገድ ነባቤ ቃል ይወለዳል፤ መላምት ወይ ይመክናል ወይ ቀመር ሆኖ ይወጣል፡፡ ሁለት ልብ ወለድ የዐሳብ ቤተ ሙከራዎችን አከታትዬ በማቅረብ፣ በማኅበራዊ መገናኛዎች ላይ የወር ተረኛ ሆኖ በቀረበው ጭቅጭቅ ላይ አስተያየት እሰጠለሁ፡፡ ሰሚ ከተገኘ ምክሬን አለግሳለሁ፡፡

1. የዐሳብ ቤተ ሙከራ አንድ

​ዮሐንስ የሚባል አንድ ክርስቲያን ወንድም አለ እንበል፡፡ አራተኛ ደረጃ የተሰፈረ የጣፊያ ነቀርሳ እንደያዘው፣ ሐኪም ነገረው እንበል፡፡ ከተያዘበት በሽታ የመዳን ዕድሉ 95 በመቶ የተሟጠጠ ነው፡፡ “ሐዋርያው” ጃፒ ዘንድ ሄዶ ግን፣ “ፈውስ የልጆች እንጀራ ነች!”፣ “ድኛለሁ!” የሚል አዎንታዊ እምነት በማመንጨት፣ አዎንታዊ ዐዋጅ ቢያውጅ፣ 5 በመቶ የሚደርስ የመዳን ዕድል እንዳለው ሐኪሙ፣ ከአስደንጋጩ ዜና ጋር አያይዞ፣ ይህን የምሥራች አበሠረው፡፡ ዮሐንስ 95 በሞቶ የተሰላውን፣ “ሐቅ” ክዶ፣ ጭል ጭል የምትለውን የ5 ከሞቶ፣ “ሐቅ” ይቀበልን? (ዐደራ ለዮሐንስ ሞትም ሆነ መዳን ምክንያት ናቸው የተባሉት ነገሮች፣ ሳይንሳዊ ሐቅ ናቸው ብለን ማሰብ ይኖርብናል)፡፡ “ለእውነት እሞታለሁ፣ አልሳሳም ለነፍሴ” የምትሉ ወገኖች፣ በሞትና በሕይወት መኻል ላለው ወንድማችሁ ዮሐንስ ምን ትመክሩታላችሁ? ዮሐንስ ሊከተለው የሚገባው ትክክለኛው የአማራጭ ጐዳና የቱ ነው?

​“ዮሐንስ የአዎንታዊ ዐዋጅ አስተምህሮን ቢቀበል፣ ዘላለማዊ ድነቱን ያጣል” የሚል ዐቃቤ እምነት ወይም የነገረ መለኮት ምሁር ያለ አይመስለኝም፡፡ ዮሐንስ ጓዘ ብዙውን የእምነት እንቅስቃሴ አስተምህሮ ሳይቀበል፣ “አዎንታዊ ዐዋጅ” የተባለውን የእምነት እንቅስቃሴ ዶክትሪን ብቻ መቀበሉ፣ ከዘላለማዊ ሕይወት ያጐድለዋል የሚባል አይመስለኝም፡፡

​ስለዚህ በዚህ ቅድመ ሁኔታ ብቻ ዮሐንስ፣ “ሐዋርያው” ጃፒ ዘንድ መሄዱ ዘላለማዊ ድነቱን ሊያሳጣው አይችልም፡፡ በዚህ ቅድመ ሁኔታ የምንስማማ ከሆነ፣ “ዮሐንስ እሞታለሁ ከሚለው 95 ከመቶ ዐሳብ ጋር መስማማት የለበትም”፡፡ ዮሐንስ፣ “ሐዋርያው” ጃፒ ዘንድ ሄዶ፣ “ፈውስ የልጆች እንጀራ ነች” እያለ አዎንታዊ ዐዋጅ እንዲያውጅ፣ ሁለችንም እንስማማለን ማለት ነው፡፡

ዮሐንስ ይህን ማድረጉ፣ 5 ከመቶ ከገቢራዊ ፋይዳ አለውና፡፡ ማናችንም ብንሆን፣ ከ95 ከመቶው ሐቅ ጋር ሳይሆን፣ ከ5 ከመቶው ሐቅ ጋር እንስማማለን ማለት ነው፡፡

​[በነገራችን ላይ፣ “ፈውስ የልጆች እንጀራ ነች” የምትባለዋ ንግግር፣ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አትገኝም፡፡ ነገር ግን፣ “ሐዋርያት” የዕለት እንጀራችንን ሊሰጡን ሲከጅሉ፣ ከእንጀራው በፊት ደጋግመው የሚያሳስቡን ተወዳጅ “ጥቅስ ነች”፡፡ “ከሐዋርያቱ” በቀር ምንጯን የሚያውቅ የለም]፡፡

2. የዐሳብ ቤተ ሙከራ ሁለት

​ከሞት ጋር የተያያዘ ሌላ ታሪክ ልጨምር፡፡ እንደ እናቴ፣ “አሟሟቴን አሳምርልኝ” ከማለት ውጪ፣ ስለ ሞት ማሰብ በጭራሽ አልፈልግም፡፡ ሲመጣ ያጠናቅቀኝ እንጂ፣ ለቅጽበትም ቢሆን የሞት ጽልመት ውስጥ ገብቼ አይቀሬውንና አስፈሪውን ሐቅ መመርመር (ስለ እርሱ ማሰብ) አልሻም፤ ከጭንቀት በቀር ገቢራዊ ፋይዳ የለውምና ሁሌም ገለል አደርገዋለሁ፡፡

ብዙ ጊዜ በአውሮፕላን ስጓዝ፣ አውሮፕላኑ ተከስክሶ ተሳፋሪው እምሽክ ሲል፣ እኔ በአምላክ ኪነ ጥበብ ስተርፍ ይታየኛል፡፡ የአገር ጋዜጠኛ ተሰብስቦ፣ “በምን ተኣምር ተረፍህ?”፣ “በክንፉና በአክናፉ የታደገህ ማነው?” ብሎ በአግራሞት ተውጦ የመዳኔን ምስጢር ሲመረምር እኔም፣ “ከእኔ የሆነ አንዳች ነገር የለም” እያልሁ፣ የጌታን አዳኝነት ጅንን ብዬ ሳበሥር፣ የእግዜርን ታላቅነት ሳውጅ ይታየኛል፡፡

​ጒዳዩ እውን ቢሆን፣ የጋዜጠኞቹ ጥያቄ፣ “እንዴት ተረፍህ?” የሚለው ነው፡፡ መላምታዊ ሆኖ ሲቀርብ ግን የእናንተ ጥያቄ፣ “ቈይ ቈይ፣ ለመሆኑ ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኝህ የተቀበልኸው፣ ከአውሮፕላን አደጋ ለመትረፍ ነው እንዴ?”፣ “ክርስቶስን ማመንህ ከአውሮፕላን አደጋ የመትረፍ ዋስትና ይሰጥሃል እንዴ?”፣ “ይህ ቅዠት ነው!” እንደምትሉኝ አይጠፋኝም፡፡

እውነት ነው! ቅዥት ነው! ክርስትና ከአውሮፕላን አደጋ ለማምለጥ፣ አንዳችም ዋስትና አይሰጥም፡፡ ክርስቶስ ኢየሱስን ያመንሁት፣ እንደ ጀምስ ቦንድ ከገባሁበት ሁሉ በድል ለመውጣት አይደለም፡፡ በጌታ ማመኔም ሆነ፣ ሞትን አምርሬ መጥላቴ፣ ከንፍሮ መኻል እንደሚገኝ ጥሬ፣ ትንግርት ሆኜ በምድር እንድቀር ዋስትና አይሰጠኝም፡፡
​ነባራዊው ሐቅ፣ “ተስፋዬ ይሞታል!”፤ “የትንሣኤው ጌታ እስኪ መጣ ድረስ፣ ተስፋዬን ብል ይበላዋል!”፡፡ ሞት እስኪ ሞት ድረስ፣ እያንዳንድሽ ዐፈር መሆንሽ ክርስቲያናዊ ሐቅ ነው! አሜን ነው? ይህ መቶ ከመቶ እውነት ቢሆንም፣ ስለሞትም ሆነ ስለ አመሟሟት ማሰብ ያስፈልጋል ማለት አይደለም፡፡ እሞታለሁ ከሚለው የዐሳብ ጭንቀት በቀር፣ ከሞት ገቢራዊ ፋይዳ የለምና፡፡

3. ነባቤ ቃል

​በእነዚህ ሁለት ልብ ወለድ ታሪኮች ውስጥ ከአንዱ አካሄድ ይልቅ ሌላኛውን አካሄድ የተመረጠበት ምክንያት ምንድን ነው? ዮሐንስ እሞታለሁ የሚለውን ጒዳይ እንዳያምን፣ ይልቁንም ድናለሁ በሚለው አዎንታዊ ዐስተሳሰብ እንዲጥለቀለቅ ፈቅደናል፡፡ ግን በምን አግባብ?

ሰው ሁሉ ከሞት ያለማምለጡ፣ “ዘግናኝ ሐቅ” ቢሆንም፣ “ብል ይበለኛል”፣ “ዐፈር እሆናለሁ” ወዘተ በሚለው አስቀያሚ ሐቅ ውስጥ መዋል ማደር እንደሌለብን ያስማማናል፡፡ ግን ለስምምነታችን መሠረቱ ምንድን ነው? ከአካላዊ ሞት ይልቅ፣ በሕይወት መኖር ገቢራዊ ፋይዳው የተሻለ ነው፡፡ ቢያንስ ይህ አካሄድ በአብዛኞቻችን ዘንድ ቅቡል ነው፡፡

​በእነዚህ ሁለት የዐሳብ ቤተ ሙከራዎች ውስጥ፣ “የትኛውን አካሄድ እንከተል” የሚለውን ጒዳይ ለመወሰን ምክንያት ያደረግነው (በማውቅም ሆነ ባለማወቅ) ምርሕ ምንድን ነው? የአንድን ነገር እውነተኝነት፣ “የምናጸድቀው” (jutifiability) ቢያንስ በሁለት መንገድ ነው፡፡ አንደኛው፣ “ሥነ ዕውቀታዊ አጽድቆት” (Epistemic Justification) የሚባለው ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ፣ “ገቢራዊ አጽድቆት” (Prudential Justification) ይባላል፡፡

​ሥነ ዕውቀታዊ አጽድቆት መሠረቱ፣ እውነትና እውነት ብቻ ነው፡፡ ገቢራዊ አጽድቆት ግን “ፋይዳው ምንድን ነው?” የሚለውን ጒዳይ መሠረት ያደርጋል፡፡ ዮሐንስ በአራተኛ ደረጃ የጣፊያ ነቀርሳ የለብኝም ብሎ እንዲያምን፣ ጃፒ ዘንድም እንድሄድ ያበረታታነው፣ ገቢራዊ ፋይዳውን መሠረት አድርገን ነው፡፡ ገቢራዊ ፋይዳው ማለትም ዮሐንስ በሕይወት የመኖር ዕድል እንዲያገኝ፣ ከበሽታው ነጻ እንዲሆን ስለምንፈልግ ነው፡፡ ዮሐንስ የመዳን ዕድሉ 5 ከመቶ ብቻ ነው ማለት፣ በሕይወት መኖሩ አይፈለግም ማለት አይደለም፡፡ በዚህ አግባብ፣ 95 ከመቶው ሐቅ ተፈላጊ እንዲሁም 5 በሞተው ተፈለጊ ያልሆነ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ተቋርጧል? ወይስ የለም? የሁለቱ ቪድዮዎች አሳብ በአጭሩ።

ባለፉት ሁለት ቪድዮዎች ስለ ሴሴሽኒዝም ጉዳይ ባልታሰበ መንገድ ተጀምሮ ብዙ አወዛገበ። የኔ የመጀመሪያ ልጣፍ November 22 የለጠፍኩት ወደፊታዊ ትንበያን ብቻ የተመለከተ ነበር። ኋላ፥ የጸጋ ስጦታዎች ቀርተዋል የምል አድርገው አንድ ሁለት ሰዎች በርዘው አቀረቡትና ጉዳዩ ወደ ‘ተቋርጧል? አልተቋረጠም?’ ንትርክ አመራ። ንትርክ ትክክለኛ ቃል ይመስለኛል። ነገሩ ተባብሶ ጥቂት ነገሮችን ጨምሬ እንድጽፍና ሁለት ቪድዮዎችን እንድሠራ ሆነ።

በመጀመሪያ አሳቤን በጽሑፍ ብቻ ለማካፈል ነበር አሳቤ። ብዙ ጊዜ ስለሚወስድና ከሥራ ጋር ስለማይመቸኝ አቆየሁት።ቪድዮው ተጨማሪ ሰዎችን ስለሚደርስ በማለት በቪድዮ አደረግሁት። ስለ ‘ተቋርጧል? አልተቋረጠም?’ ጉዳይ የሁለቱ ቪድዮዎች ዋና አሳብና የመጨረሻ ማጠቃለያዬ በጣም አጭር በሆነ ጽሑፍ ይህ ነው። ቪድዮው ወደ ጽሑፍ እየተቀየረ ነው፤ ሲያልቅ በቴሌግራም ገጼ አስቀምጠዋለሁ።

ተቋርጠዋል የተባሉት አራት ተአምራውያን ስጦታዎች፥ #ፈውስ፥ #ልሳን፥ የልሳን #ትርጉም፥ እና #ትንቢት ናቸው። የተቋርጧላውያን መነሻዎች አራት መሆናቸውንና፥ አራቱ መነሻዎች፥ ስጦታዎቹ አሉታዊና አፍራሽ ሚና መጫወታቸው፥ ቃሉ ሙሉና በቂ መሆኑ፥ ምልክቶች ከሐዋርያት ጋር መቅረታቸው፥ እና ቃሉ ይቀራሉ ይሻራሉ ማለቱ ናቸው። አራቱም ሕጋውያን መነሻዎች ቢሆኑም አራቱም መቋረጣቸውን አረጋጋጭ አለመሆናቸውን አብራርቻለሁ። ይሁን እንጂ ቃሉ ጥቂቱን፥ ‘ይሻራሉ ይቀራሉ’ ስለሚል፥ ‘ተሽረዋል እና ቀርተዋል’ የሚሉ ክርስቲያኖች ከቃሉ ስለሚንደረደሩ የሳቱ ወይም የተሳሳቱ አይደሉም። በሁሉ ነገር እገሌ እኔን መምሰል የለበትም። እኔም እርሱን መምሰል የለብኝም።

ወደ ስጦታዎቹ በመግባት አራቱንም ስጦታዎች በዝርዝር ተመልክቼአቸዋለሁ።

1. ፈውስ ቀርቷል? ተቋርጧል? አልቀረም፤ አልተቋረጠም። ነገር ግን ፈውስ እንደ ጌታ ፈቃድ የሚሆን እንጂ ሰዎች ብልጭ ድርግም የሚያደርጉት ነገር አይደለም። ደግሞም ፈውስ ሲኖር የሚታይና የሚታወቅ ክስተት ነው። የውሸት ፈውሶች ቢኖሩም፥ በፈውስ ስም ብዙ ማጭበርበሮች ቢደረጉም፥ ፈውስ አልተቋረጠም።

2 እና 3. ልሳንና ትርጉም ተቋርጠዋል? ቀርተዋል? አልቀሩም፤ አልተቋረጡም። ተለማምደውና አለማምደው የሚናገሩት ልሳን እርሱ ጸጋ አይደለም። እውነተኛው ልሳን እንደ ሐዋ. 2 ያለው ተናጋሪዎች የማያውቁት፥ ሰሚዎች የሚያውቁት ቋንቋ ነው። እውነተኛው የጉባኤ ልሳንና ትርጉም ደግሞ በ1ቆሮ. 14 እንደተጻፈው ያለው ነው። በተጻፈበት መልኩ ከተደረገ ይህ ዛሬም ያለ ጸጋ ነው። ልሳን የመንፈስ ጥምቀት ወይም ሙላት ምልክት ተብሎ ጉባኤ ሁሉ የሚናገርበት ጫጫታ፥ ጳውሎስ እብደት ያለው ልምምድ ነው። ይህ የሰው ሥራ ነው። እውነተኛው ልሳንና ትርጉም ግን አልቀረም፤ አልተቋረጠም።

4. ትንቢት ቀርቷል? ተቋርጧል? አልቀረም፤ አልተቋረጠም። ትንቢት ያለንበትን ዘመንና ሁኔታ መናገር ነው። ትንቢት ቅዱስ ቃሉን መግለጥ ነው። ትንቢት እንደ ጸጋ፥ ነቢያትም እንደ ስጦታ ለቤተ ክርስቲያን እነጻ ተሰጥተዋል። ትንቢት ወደፊት ስለሚሆኑ ነገሮችም የተነገረበት መሆኑ በታሪኮች ውስጥ ተጽፎአል። በታሪኮች ውስጥ የተጻፉ ነገሮች ሁሉ ትእዛዛት አይደሉምና አይደጋገሙም። በትንቢት ጸጋ ስም ስለ ወደፊቱ መጻኢ ዘመን መናገር እንደ ጸጋ ስጦታ በቃሉ ውስጥ አልተጻፈም። ነቢያትና ትንቢቶች በአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያናት ውስጥ ምን እንዳደረጉ ስንመረምር በቀጣይ ዓመታት የሚሆኑትን ክስተቶች ሳይሆን መምከር፥ ማጽናት፥ መላክ፥ ቅዱሳንን ማነጽ እና የመሳሰሉትን ተግባራት ሲፈጽሙ እንጂ ወደፊታዊ ትንበያዎችን ከመንፈሳዊ ዓለም እየተቀበሉ ሲያድሉና ሲነሰንሱ አይታዩም። ትንቢት ቀርቷል? ተቋርጧል? አልቀረም፤ አልተቋረጠም። ወደፊታዊ ትንበያ ግን ሲጀመርም የጸጋ ስጦታ አይደለም። ደግሜ እላለሁ፤ አይደለም። እኛ ስለ ነገ እንድናውቅ ወይም እንድንጨነቅ ሳይሆን ስለ ነገ በጌታ እንድንታመን ነው የተነገረን።

ይህ ስለ ነገ ማወቅ የሚባለው ነገር ጸጋ እንዳልሆነ ሲነገር እጅግ የሚያስጨንቃቸውና የሚረብሻቸው ሰዎች አሉ። እነማን ናቸው? ቢባል፥

ሀ) ዋናዎቹ ስለ ነገ ከመንፈስ ዓለም እየቀዱ የመናገር ስጦታ ያላቸው የሚያስመስሉ እየጠነቆሉ ገንዘብና ዝና የሚሠሩ ‘ነቢያት ነን’ የሚሉ ነጋዴዎች እና ጋሻ ጃግሬዎቻቸው ናቸው። ወደፊታዊ ትንበያን በትንቢት ስም ስለሚነግዱበት።

ለ) ነገን አስይዘው ቁማር መጫወት የሚወዱ፥ ከተበሉ (ሁሌም የተበሉ ሰዎች ናቸው) ‘ወየሁ ከሰርኩ!’ የሚሉ እያስጠነቆሉ በአቋራጭ መበልጸግ የሚወድዱ ሰዎች፤

ሐ) ቃሉን በማንበብና ደቀ መዝሙር በመሆን ፈንታ ዋጋ ባለመክፈል መጓዝ እና ያደጉ ለመምሰል የሚፍጨረጨሩ እየተማሩ እውነትን ለማወቅ ያልወደዱ ሰዎች ናቸው።

እነዚህ ስጦታዎች ባይቋረጡም በአካሉ ውስጥ ጉዳት ፈጣሪዎች በመሆናቸው፥ ስጦታዎቹንም ቀውሶቹንም ከመንፈስ ቅዱስና ካሪዝማዊ ቀውሶች መጽሐፌ ጀምሮ ቀደም ባሉት በርካታ ዓመታት በብዙ መጣጥፎችና ትምህርቶች ዳስሻቸዋለሁ። እዚህም ያንኑ አድርጌአለሁ። የለወጥኩት ምንም ነገር የለም። ብለውጥ፥ ‘ለወጥኩ’ ለማለት ወይም ብሳሳት፥ ‘ተሳስቼ ነበር’ ለማለት አልፈራም፤ አላፍርምም። ተቋርጧላዊ ብሆን፥ ‘ነኝ’ ለማለትም ምንም አይከለክለኝም። ብዙዎች በአንዳንድ ጉዳዮች ደፍረው መጻፍ ባይሆንላቸውም አይገርመኝም። አንዱ ለስሕተት አሠራር ከሌላው ይበልጥ የተጋለጠ ቢሆንም ቅሉ፥ ሁለቱም ወገኖች (ተቋርጧላውያንም፥ ቀጥሏላውያንም) ክርስቲያኖች መሆናቸውን አልጠረጥርም።

እንደገና ስደመድም፥ አራቱም ስጦታዎች ቀርተዋል? ተቋርጠዋል? አልቀሩም፤ አልተቋረጡም። የተቋረጠ ጸጋ የለም። በአንዳንዶች ዘንድ እንዳለ የሚቆጠርና የሌለ ወደፊታዊ ትንበያን መከተል ግን ላም ባዋለበት ኩበት ለቀማ ነው። ይህንን ጉዳይ አንጠፍጥፌ ጨርሻለሁ።

ዘላለም ነኝ።

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የውበት አደገኛነት የት እንደሚደርስ በሌላ ምሳሌ እንይ ...በኢትዮጵያ ስነፅሁፍ ከጥንት ጀምሮ የቆዳ ንጣት/ቅላት ሰልካካ አፍንጫ መካከለኛ ከንፈር ዞማ ፀጉር እንደቁንጅና ሚዛን ሲሳል ነው የኖረው፤ ጥቁረት ፣ ከርዳዳ ፀጉር ትልቅ ከንፈር ሰፊ አፍንጫ ፣ትንንሽ አይኖች ወዘተ መልከ ጥፉነት ጎዶለት የተናቀ ማንነት መግለጫ ...ሲቆይ ይሄ ነገር ያመጣብን ጦስ ሚሊየኖችን በሰውነታቸው እንዲሳቀቁ ፣ እንዲያፍሩ ከአገር ጥቅም እንዲገፉ ወዘተ አደረጋቸው ...አሁን በተራቸው ቤተ አምልኮዎች በአፋቸው ስለሰው ልጅ እኩለነት እየሰበኩ የሐብትና ውበት "ክላስ" ምስባካቸው ላይ እያስቀመጡ ነው! የውበት "ስታንዳርድ" እየፈጠሩ ነው! በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ብዙዎችን እየገፉ ነው! ይሄ የአለባበስ እና የአዋዋብ ስርዓት ጉዳይ አይደለም! መመለስ ሲያቅተን የሚያባንነን በሽታ ነው! ይሄ የውበት አምልኮ ከቃሉ በላይ ገዝፏልና መናገር የቸርቹ ምሰሶ የሆኑ "ቱባ አማኞችን" ማሳዘን ነው! ስለዚህ የሚተነፍሰሰ የለም!

እንግዲህ በሊሊ ታካችሁ ውበትን እናመልክ ዘንድ መንፈሳዊ ስጦታ ነው እያላችሁ ለሰበካችሁን ፣ በሊሊ ታከን ያመንበትን እውነት መስክረናል! ለማንኛውም አይናችሁን ከዘማሪዋ ውበት ላይ አንሱና ስለአገልግሎቷ ፣ስለዝማሬዋ ምሳሌ የሚሆን ህይወት ካላትም ስለዛ የምትሉትን በሉ! ስለውበቷ መናገር ከፈለጋችሁ ግን ሳታመናፍሱት በግልፅ ቆንጆ ነሽ ፣የበለጠ ይመርብሽ ፣ ልብስሽን የት ገዛሽው እኛም እንልበሰው፣ ፀጉርሽን የት ተሰራሽው እኛም እንሰራ ...ሚስቶቻችን እንዳንች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ምከሪልን ብትሉም ይቻላልኮ!

ሰፊው ጌታን ወዳድ ምዕመን ግን ይህን ቀድማችሁ ብታውቁ መልካም ነው ፣ ጌታ ለእናተ ካለው ልዩ ፍቅርና ርህራሄ የተነሳ በቤቱ ስትኖሩ የተረገጠ ጣሳ አልያም የተላጠ ብርቱካን ሊያስመስላችሁ ይችላልና ክርስትና የአካላዊ ውበት ዋስትና እንደማይሰጥ አውቃችሁ ግቡበት! የሰማዮን እያሰባችሁ በደስታ ኑሩ! ጌታ ነው ያዘነጠኝ ከሚል የመድረክ ላይ ውበት ሰባኪ በመንፈስ ሽሹ ! ለእናተ ስሪ ፒስና ብራንድ ቀሚስ የተሰቀለ ጌታ በዚህ የለም! በኑሮ መቸገርም ሆነ መባረክ መንፈሳዊ ሚዛን አይሁኑባችሁ! አዳምን ቅጠል አስጥሎ ሌዘር ስለሰጠው እናተን እጀ ጠባብ አስጥሎ ጅንስ ለማልበስ ልጁን አላከም! የዚህ ፅሁፍ ሐሳብ ላልገባችሁ በጌታ ፍቅር የራሳችሁ ጉዳይ😀

Читать полностью…
Subscribe to a channel