negere_evangelical | Unsorted

Telegram-канал negere_evangelical - ነገረ ወንጌላውያን

2910

በወንጌላውያን አማኞች ዘንድ የሚፃፉ ፅሁፎች፣ ዘገባዎችና ዜናዎች ይቀርባሉ! ትምህርቶች፣ መረጃዎችና ምካቴ እምነቶች በዚህ ቻናል ይስተናገዳሉ! በተለያዮ ሶሻል ሚዲያዎች የሚገኙ ፀሐፊያን የሚፅፉቸው ፅሁፎችን እናጋራለን።

Subscribe to a channel

ነገረ ወንጌላውያን

*** እናቶች ቡሩክ ኹኑ!

እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለውን ፍቅርና ርኅራኄ፣ በእናት ፍቅር ገልጿል። እናት ሆደ ሰፈ፣ ታጋሽ፣ ሩኅሩኅ፣ ለልጆቿ ሟች፣ በሥራዋ ደግሞ ባተሌና ትጉ ናት። በዐመፃቸውና ኀጢአታቸው ምክንያት በግዞት ምድር ተበትነው ለነበሩት እስራኤላውያን እግዚአብሔር የነበረውን ፍቅር የገለጸው፣ እናት ለልጇ ባላት የማይቀየር ፍቅር ነበር። ሰማይንና ምድርን የፈጠረ፣ ሁሉን ቻይና ታላቅ የሆነ አምላክ፣ በስደት በስብራት ውስጥ ለነበረው ሕዝቡ፣ ራሱን በድጋሚ የገለጠው በቁጣ ሳይሆን፣ በጥፋቱ የሚገባውን ቅጣት የተቀበለ ልጇን መልሳ በዕቅፏ በመያዝ እንደምታባብል እናት ነበር። ከግብፅ የባርነት እቶን እሳት የታደጋቸውንና ለድነት ዓላማ ብሔራዊ ሉዓላዊነት የሰጣቸውን አምላክ የተውት፤ ኪዳናቸውን በተደጋጋሚ ያፈረሱት፤ ፍቅሩና ምሕረቱን ረግጠው የሄዱት፤ እውነትኛ ወዳጃችውን በባዕድ አማልክት የቀየሩት እነርሱ ነበሩ። (ኤር 2:4-6)

ይሁን እንጂ፣ እግዚአብሔር ኪዳኑን የሚያድስበትንና ደጋሚ ብሔራዊ ትድግና የሚሰጠበትን የማለወጥ ፍቅር ሲገልጥ እንዲህ ነበር ያለው፦

“የጽዮን ልጅ ሆይ፤ ዘምሪ፤ እስራኤል ሆይ፤ እልል በዪ፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፤ በፍጹም ልብሽ ደስ ይበልሽ፤ ሐሤትም አድርጊ . . . የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው፤ ከእንግዲህ ወዲያ አንዳች ክፉ ነገር አትፈሪም። በዚያን ጊዜ እሰበስባችኋለሁ፤ ያን ጊዜ ወደ አገራችሁ እመልሳችኋለሁ፤ ዐይናችሁ እያየ፣ ምርኳችሁን በምመልስበት ጊዜ፣ መከበርንና መወደስን፣ በምድር ሕዝብ ሁሉ መካከል እሰጣችኋለሁ”፤ ይላል እግዚአብሔር።” (ሶፎንያስ 3 : 14 - 15 , 20)

ያን የቀድሞ፣ የማለዳ፣ የጥንቱን ፍቅር ለማደስ፣ እግዚአብሔር ከዳተኛዪቱን እስራኤልን ለግዞት አሳልፎ ሰጥቶአታል። ይኽ የግዞት ዘመን የምድረ በዳ ኑሮ ነበር። ልክ እንደ መጀመሪያው ዘፀአት፣ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከፍቅር የተነሣ ታድጓል። በጥፋቱ የሚያለቀስ ወይም የተከፋ ልጇን አባብላ መስመር እንደምታስይዝ ሩኅሩኅ እናት፣ እግዚአብሔር ለእስራእል ራሱን ድጋሚ ይገልጣል። በእሳት ዓምድ፣ በነጎድጓድና አስፈሪ ድምፅ ሳይሆን፣ በእናትነት የፍቅር “እሹሩሩ”! ክብር ለስሙ ይኹን። ፍቅሩ ወሰን የለውም!

“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ሰላምን እንደ ወንዝ ውሃ አፈስስላታለሁ . . . በዕቅፏም ትያዛላችሁ፤ በጭኖቿም ላይ ትፈነድቃላችሁ። እናት ልጇን እሹሩሩ እንደምትል፣ እኔም እናንተን እሹሩሩ እላችኋለሁ፤ በኢየሩሳሌምም ትጽናናላችሁ።” (ኢሳይያስ 66 : 12 - 13 )

እናቶች፣ እግዚአብሔር ይባርካችሁ . . . በተለይም፣

እግዚአብሔርን መፍራት ያስተማራችሁ
የራሳችሁን ያለስስት ለልጆቻችሁ የሰጣችሁ
ሳትማሩ ትውልድ ያስተማራችሁ
በጉዲፈቻ የእግዚአብሔርን ፍቅር የምትሰጡ
ባሎቻችሁ ሞተውባችሁ፣ ወይም በግፍ ትተዋችሁ ሄደው፣ በብዙ መከራ ልጆቻችሁን ለቁም ነገር ያበቃችሁ፤ ወይም አሁንም የምትታገሉ
አስቸጋሪ ባሎችንና ልጆችን በተስፋ የምትታገሡ
በአድካሚ ሥራ ቤታችሁን የምትደገፉ፤ በየፋብሪካው የምትደክሙ፣ በየገጠሩ በበዕርሻ ሥራ በውሃ እንሥራ፣ በማገዶ እንጨትና የገበያ ሸክም ወገባችሁ የዛለ
በሴትነታችሁ ስትገፉም፣ በልበ ስፋትና ጽናት ለልጆቻሁ የነገ የተሻለ ተስፋ ያምትተጉ
በጦርነትና በዐመፅ የደረሰባችሁን ብርቱ ሐዘን በመቻል፣ አሁንም ለአገር ፈውስና ሰላም የምትቃትቱ
ለቤተ ክርስቲያንና ለትውልድ መታደስ የምታነቡ
መድረክና ሚዲያ ያማያውቃችሁ፣ ዐጥንተ ብርቱ፣ ጠባየ ሸጋና ደጋግ ውድ እናቶች- የሦስት ልጆቻን እናት ገኒን ጨምሮ፦

ተባረኩ - “የሚገባትን ሽልማት ስጧት፤ ሥራዋም በየአደባባዩ ያስመስግናት።” (ምሳሌ 31:31)።

ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው፤ ክብረት ይስጥልን፤ ኑሩልን፤ እግዚአብሔርም ይባርካችሁ!

አሜን!

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ቅይጣዊነት #5
(የሃሳዊያኑ ፍኖተ ካርታ)

ይህ ልጥፍ የመጨረሻው ክፍል ነው። በዋናነት የሃሳዊያኑን ፍኖተ ካርታ ለመመልከት እንሞክራለን። የሃሳዊያኑ ፍኖተ ካርታ አራት ደረጃዎች አሉት። በአሁን ወቅት በሀገራችን የሚገኙ ሀሳዊያን ወደ ሁለተኛው ደረጃ ተሸጋግረዋል።
...........................

አንድ አስተሳሰብ (ሰናይ ቢሆን እኩይ) በማህበረሰብ መካከል ሰርፆ ገዢ ሃሳብ ሆኖ ለመውጣት ፍኖተ ካርታ (Road Map) ያስፈልገዋል። የጠራ ግብ (መዳረሻ)፣ ስልት፣ በየደረጃው የሚጠበቅ ውጤት እና የታሰበባቸው እርምጃዎችን ያላካተተ ማንኛውም "ሃሳብ" የትም አይደርስምና።

ስለ ሃሳዊያን ያለን ምልከታ በልካቸው መሆን አለበት። አቅልለንም አግዝፈንም ማሰብ አደጋ አለውና። አንዳንዶቻችን እንደምናስበው ሃሳዊያኑ ሞኛሞኝ አይደሉም። ቤትና መኪና መግዛት ላይ የተንጠለጠለ ብቻም አይደለም ዕቅዳቸው። አውቀው ገብተውበትም ይሁን ተታለው የሃሳዊያን ዓላማ የሰይጣን ዓላማ ነው። የሰይጣን ዓላማ ደግሞ ግልፅ ነው። ወንጌልን መሸቀጥ፣ ክርስቶስን መጋረድ፣ ቤተክርስቲያንን ማዳከም፣ ሰውን ወደ ገሃነብ መስደድ፣ የእግዚአብሔርን ክብር ማጉደል ነው። ይኸው ነው። እኒህ ሃሳዊያን ይህንን ዓላማቸውን ለመፈፀም ፍኖተ ካርታ (Road Map) አላቸው። ይህም ፍኖተ ካርታቸው አራት ደረጃዎች አሉት።

የመጀመሪያው ደረጃ

በሃሰዊያኑ ፍኖተ ካርታ መሠረት የመጀመሪያው ደረጃ ስሁት አስተምህሯቸውንና ስሁት ልምምዳቸውን በተለያዩ መንገዶች ወደ አማኙ ማህበረሰብ ማስረፅ ነበር። ይህንን ለማሳካት አሳች እየተባሉም ቢሆን ብዙ ጥረት አድርገዋል። ጥቂት የማይባልም ቁጥር ያለው "አማኝ" ለማጥመድ ችለዋል። ሃሳዊያኑ በዚህ በመጀመሪያው ደረጃ በአብዛኛው መከላከል ላይ የተመሰረተ ስትራተጂ ተጠቅመው ነበር።

ሁለተኛው ደረጃ

በአሁኑ ወቅት (በእኔ እምነት) ሃሳዊያኑ ሁለተኛው ደረጃ ላይ ናቸው። ይህ ሁለተኛ ደረጃ ራሳቸውን ከእውነተኞች ጋር ለመቀየጥ የሚጥሩበት ደረጃ ነው። የ"ቅይጣዊነት" ደረጃ ማለት ነው። ይህ እንግዲህ "የማጥቃት ስትራተጂ" መሆኑ ነው። ንፁሁን ወንጌል በሃሳዊ ትምህርታቸው በከፍተኛ ሁኔታ እየበከሉት ይገኛሉና። ባለፉት ተከታታይ ልጥፎች "ቅይጣዊነት" ምን እንደሆነ በእነማን እንደሚከወን እንዲሁም በወንጌላዊያን መካከል ያነበረውን አደጋ ተመልክተናል።

ሶስተኛው ደረጃ

ሶስተኛው ደረጃ ደግሞ ወንጌላዊው ክርስትና ሙሉ ለሙሉ በእነርሱ ትምህርት የሚወከልበትን ክበብ መፍጠር ነው። ይህኛው ደግሞ የመቆጣጠር ደረጃ ነው። በዚህ ወቅት ዋነኛ ትኩረታቸው እንደ ካውንስሉ ያሉ ተቋማትን መቆጣጠር ህብረቱንም ጥርስ የሌለው አንበሳ እንዲሆን እንዲሁም በራሳቸው ልክ ሰፍተው ያዘጋጇቸውን ማህበሮች "ተፅዕኖ ፈጣሪ" ወደሚሆኑበት ደረጃ ማሳደግ ነው። ይህ አሁንም በጥቂቱ የሚታይ ቢሆንም በአብዛኛው ግን ወደፊታዊ ነው። ይህም የ"መቀየጥ" ሩጫቸውን ሲጨርሱ የሚገቡበት ይሆናል።

አራተኛው ደረጃ

አራተኛው ደረጃ የከፋው ደረጃ ነው። ሃሳዊያኑ ሙሉ በሙሉ ካውንስሉን እና መሰል ተቋማትን እንዲሁም በቀደሙ "አባቶቾ" ተይዘው የነበሩትን የተሰሚነት መድረኮች መቆጣጠር የሚችሉበት ነው። ይህም ጊዜ እውነተኛውን ወንጌል በሙሉ ሀይላቸው ማሳደድ የሚጀምሩበት ጊዜ ነው። ይህ ፍፁማዊ የበላይነትን የማረጋገጥ ደረጃ ነውና። በዚህ ወቅት ሃሳዊያኑ ዛሬ ላይ ለ"ቅይጣዊነት" የሚጠቀሙባቸውን "መሀል ሰፋሪዎችን" ጨምሮ ወደ ማሳደድ ሊሸጋገሩም ይችላሉ (ለእነርሱም አይመለሱምና)።

ጊዜው አሁን ነው!

አንዳንድ ወገኖች "ሃሳዊያኑ የትም አይደርሱም.... የሆነ ወቅት መጥፋታቸው አይቀርም.... ገንዘብ ሲጠግቡ መቆማቸው አይቀርም....መንግስት አንድ ነገር ማድረጉ አይቀርም...ወዘተ.ሲሉ ይደመጣል። አንዳንዶችም በሰሜን አሜሪካ ያለውን ተሞክሮ እያጣቀሱ "በአሜሪካን እኮ ዛሬም ድረስ በሃሳዊያኑ ያልተደፈሩ በርካታ ቤተ እምነቶች አሉ" የሚል ማስረጃ በማቅረብ ሃሳዊያኑ በሀገራችን የሚኖራቸው ተፅዕኖ ያንን ያህል አስጊ እንዳልሆነ ለማስረዳት ይሞክራሉ።

ነገር ግን ይህንን የሚሉ ወገኖች የሀገራችን ነባራዊ የወንጌላዊያን ሁኔታ ከምዕራቡ ዓለም ፈፅሞ የተለየ መሆኑን አላስተዋሉም። ምክንያቱም በእኛ ሀገር የሚገኙ የወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት መካከል እንደ ሰሜን አሜሪካዊያኑ ቀድሞውኑ የተሰመረ የልዩነት መስመር አለመኖሩን አላወቁምና። በሀገራችን ቤተ ዕምነቶች መካከል ያለው የስምና የዲኖሚኔሽን እንጂ አስተምህሮና የልምምድ አይደለምና። ይህም ሁኔታ ሃሳዊያኑ ምንም ሳይገድባቸው በስህተት እርሿቸው ሁሉንም ቤተ-ዕምነቶች ለማብኳት ሰፊ ዕድል ፈጥሮላቸዋል።

ስለዚህ

በተከታታይ አራት ልጥፎች ለመጠቆም እንደሞከርሁት "ቅይጣዊነት" ከቃል እምነት ስሁት ትምህርቶች ባልተናነሰ አሁናዊ የወንጌላዊያን አደጋ ነው። ይህ "ቅይጣዊነት" ደግሞ በሃሳዊያኑ ፍኖተ ካርታ መሠረት ሁለተኛው ደረጃ ነው። ሃሳዊያኑ ይህንን ደረጃ ካለፉ ቀሪዎቹ ሁለቱ ደረጃዎች ብዙም ከባድ አይሆኑም። የሀገራችንም አብያተ ክርስቲያናት ተቆላልፈው የሚኖሩና በመካከላቸው ምንም አጥር የሌለ መሆኑ ለሃሳዊያኑ ምቹ መደላድል ፈጥሮላቸዋል።

በመሆኑም "ያገባናል!" የምንል ሁሉ የፍፃሜው ጦርነት መሆኑን አስተውለን ለሰበብ የሚተርፍም ጊዜ ስለማይኖረን ባለን ሃይል ሁሉ ስህተትን እና ሃሳዊያንን ለማጋለጥ፣ ንፁህ የሆነውን ወንጌል ለማስተማር እና ለመጠበቅ፣ ለትውልድም ለማሻገር እንትጋ የሚል ሃሳብ በታላቅ ትህትና አቀርባለሁ።

ቴዎድሮስ ተጫን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ቅይጣዊነት #3

ቀደም ባሉት ልጥፎች "ቅይጣዊነት" ከቃል እምነት ስሁት ትምህርቶች ጎን ተሰልፎ የሚዋጋን ወቅታዊው የወንጌላዊያን አደጋ እንደሆነ ለማየት ሞክረናል። ቅይጣዊነት ክፉ ነው። ሃሳዊውን ነጥለህ በእውነትህ እንዳትመታው መደበቂያ ጫካ ሆኖ ያገለግላልና። ሃሳዊያኑ ጮሌ ስለሆኑ ከሆነ ከምታከብረው ሰው ጀርባ ሄደው ይደበቁብሃል። አንተም "ይህንን የተከበረ አገልጋይ አልፌ እንዴት እናገራለሁ" ብለህ ስታመነታ እነርሱ በአጭር ጊዜ እንደ አረም ተንሰራፍተው ይጠብቁሃል።

አስበው እስኪ ሃሳዊ ያልኸው ጃፒ ለዘማሪ ተከስተ ሲፀልይለት እና ተከስተ "ተነክቶ" መሬት ላይ ሲወድቅ፤ ከዚያ ደግሞ ተከስተን ሙሉ ወንጌል ጋብዘህ፣ አብረኸው ስትዘምር፣ ከዚያ ደግሞ ዞረህ ጃፒ ሃሳዌ መምህር ነው! ልትል ስትነሳ። አሰብኸው?...ተዘራ የስህተት መምህር ነው ብለህ ስታበቃ እና "ዘማሪ እንዳለ ከተዘራ ጋር ኮንፈረንስ አዘጋጁ" የሚል ፖስተር ስትመለከት፤ በዚህ ተደንቀህ ሳታባራ ዘማሪ እንዳለን ሀዋሳ ላይ ከፓስተር ጌቱ ጀርባ ለአገልግሎት ተሰይሞ ስታገኘው። አስብኸው? ደህና፤ ይህንን እያሰላሰልክ የቀያጮቹን ሎጂክ ወደ መመርመር እንለፍ

ቀያጮቹ

መቼም "በቅይጣዊነት" ሂደት የ"ቀያጮቹ" ሚና ቀላል አይደለም። ለነገሩ "ቅይጣዊነት" ካለ "ቀያጭ" መኖሩ የግድ ነው። አሊያማ ተቀያጭ ያለ ቀያጭ እንዴት ሊቀየጥ ይችላል? አሁን ጥያቄው ቀያጮቹ እነማን ናቸው...!? የሚል ነው። ቀያጮቹ? ቀያጮቹማ ሁለት ዓይነት ናቸው። የመጀመሪያዎቹ በርቱዕ አስተምህሮና መዝሙራቸው የማንጠረጥራቸው ነገር ግን በሃሳዊያኑ ወይም በሃሳዊያን አሳላጮች (መሃል ሰፋሪዎቹ) መድረክ የሚመላለሱ "የምንወዳቸው አገልጋዮች" ናቸው። እነዚህ አገልጋዮች ህዘበ-ክርስቲያኑ በሃሳዊያኑ ስሁት አስተምህሮ እና ሌብነት ላይ እንዳይነቃ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሃሳዊያኑ መጠቀማያ የሆኑ ናቸው። በአማኞችም ላይ አዚም (በስህተት ላይ ድንዛዜ) እንዲፈጠር ያላቸው አስተዋፅዖ ቀላል አይደለም። ቀያጮቹ!!

ታዲያ ቀያጮቹ የዋዛ እንዳይመስሉህ፤ ይህን እንደ ወንጌል እውነት ያልሆነ ግብዝ አካሄዳቸውን ለማፅደቅ የተመናፈሰ ሎጂክ (አመክንዮ) ቀምረውልሃል። ሃሳዊያኑ መድረክ ላይ መቆማቸውን አይቶ ልክ አይደላችሁም ለሚላቸው ሁሉ "ማምለጫ" (ሎጂክ) አዘጋጅተዋል። ይህም ሎጂካቸው ቅቡልነት (ገዢ) እንዲያገኝ ደግሞ በተለያየ መንገድ ሎቢ ያደርጋሉ።

የቀያጭቹ ሎጂክ

ለርቱዕ አስተምህሮ "የቀኑ" ነገር ግን ከሃሳዊያኑ ወይም ከአሳላጮቻቸው ሰፈር የማይጠፉትን አገልጋዮች ጠጋ ብለህ ለምንድነው የሃሳዊያኑ ወይም የአሳላጮቻቸው መድረክ ላይ የምትገኙት? ብለህ ስትጠይቃቸው እንዲህ ብለው ሎጂካቸውን ይጀምራሉ።

"እኔ የተጠራሁት በተከፈተልኝ መድረክ ሁሉ የጌታን እውነት እንዳገለግል ነው። ስለዚህ ምንም እንኳን ሃሳዊያን ወይም የሃሳዊያኑ አሳላጮች ቢሆኑ እነርሱ ጋር እሄዳለሁ...." ይሉሃል። ትንሽ ቆፍጠን ብለውም "ማንም ጋር ይሁን እሄዳለሁ! ዋናው እውነቴ ነውና!! ወንጌሉን ሄጄ እናገራለሁ!....ከዚያ ምርጫው የሰሚዎቹ ነው...." ይሉህና ጨመር አድርገው ለማግባባት በሚሞክር ድምፀት "እነኚህ ሰዎች'ኮ (ሃሳዊያኑን ማለታቸው ነው) ሊለወጡ ይችሉ ይሆናል....እኛ ካልሄድን ማን ይንገራቸው ታዲያ?...ዕድል ልንሰጣቸው'ኮ ይገባል....የስነ-መለኮት ትምህርት ዝግጅት የላቸውም....ጥቂት ብንረዳቸው ምናልባት ሊለወጡ ይችሉ ይሆናል....ምን ይታወቃል...አንዳንዶቹን ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ አይደል እንዴ የሚለው ቃሉ" ይሉሃል።

ወዲያው ደግሞ እንደ ማስፈራራት ሲያደርጉት "ወጣቱንም እኮ ይዘውታል...ብሩም ቢሆን በእጃቸው ነው ሚዲያውንስ ብትል.....እኛ ጋር አለ የምንለውም ህዝብ እኮ በልቡ ኮብልሏል...ዘመኑ እኮ ከፍቷል!..... ካውንስሉም ቢሆን በግልፅ ይደግፋቸዋል...ህብረቱስ ቢሆን በጓሮ በር ከጎናቸው አይደል....ብቻዬን ተቃውሜ ምን አመጣለሁ....የሚሻለው ወደ እነርሱ ጠጋ ብሎ ለመለወጥ መጣር ነው.....አሊያ እዚህ ሆነን ዝም ብለን ብንጮህ ሰንበት ብሎ የሚለወጥ ሳይሆን የሚሰማንም እኮ ልናጣ እንችላለን" ይሉሃል።

የሎጂኩ ክሽፈት

ከላይ የተዘረዘረው "ሎጂክ" ክሽፈቱ የሚጀምረው መነሻውን በቃሉ ላይ ሳይሆን በሁኔታዎች ላይ ከማድረጉ ነው። በእርግጥ ሁኔታዎችን ተመልክቶ ለአንዳንዱ ነገር አመክንዮ መገንባት ተገቢ ሊሆን ይችላል። በዚያ ጉዳይ መፅሐፍ ቅዱስ ግልፅ መመሪያ ከሌለው። ነገር ግን ከሃሳዊያን ጋር ሊኖረን ስለሚገባው ግንኙነት ቃለ እግዚአብሔር ግልፅና የማያሻማ መርህ እንዲህ ሲል አስቀምጧል:-

"በክርስቶስ ትምህርት የማይኖርና ከትምህርቱ የሚወጣ ሁሉ አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት የሚኖር ግን አብም ወልድም አለው።
ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ፣ ይህንንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት፤ ሰላምም አትበሉት፤ የሚቀበለው ሰው፣ የክፉ ሥራው ተባባሪ ይሆናልና" (2ዮሐ 9-11አ.መ.ት)

ልብ በሉ የፍቅር ሐዋርያ የሆነውና ስለ ፍቅር አብዝቶ የነገርን፤ "ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው!" ብሎ ከወንድሞች ጋር ነፍስን እስከ መስጠት በደረሰ ፍቅር መኖር እንደሚገባን ያስተማረን ዮሐንስ "በክርስቶስ ትምህርት የማይኖረውን ሃሰተኛ ሰላም አትበለው...ሰላም ካልኸው የክፉ ስራው ተባባሪ ትሆናለህ" በማለት ከሃሳዊያን ጋር "በትብብር በጋራ በመቀበልና በመቀባበል ወይም በሰጥቶ መቀበል" መርኸ የምንሰራው ምንም ዓይነት ነገር እንደሌለ ቁርጥ አድርጎ ነግሮናል።

ቀያጮቹ ግን ከዮሐንስ በላይ "አፍቃሪ" ሆነው በክርስቶስ ሳምራ መንፈስ "ከሃሳዊያን ጋር በመተባበር እነርሱን መርዳት ያስፈልጋል" በሚል በቃሉ እውነት ላይ ታብየው ከላይ የተዘረዘረውን የከሸፈ ሎጂካቸውን ይደረድራሉ። አንዱ ይሄ ነው።

ሁለተኛው ደግሞ ይህ ሎጂክ የሰህተት ትምህርትን ዓይነተኛ ባህሪ እና የአሳቾችን ማንነትና ዓላማ ከግንዛቤ ያስገባ አለመሆኑ ነው። ምክንያቱም ጌታችን ስለ ፈሪሳዊያን ስሁት ትምህርት ሲናገር "እርሾ" የሚል ቃል ተጠቅሟልና። "ከፈሪሳዊያን እርሾ ተጠበቁ" ብሎም አዟልና። መቼም ብዙ ሊጥ ለማቡካት የሚያስፈልገው ጥቂት እርሾ ነው። ሃሰትም እንደዚያው ነው። ብዙሃኑን ለማሳት ጥቂት ይበቃል። እኒህ ጤነኛ የምንላቸው አገልጋዮች (ቀያጮቹ) ግን ይህንን አያስተውሉም። ሃሳዊያኑ በእነርሱ ተከልለውና ተንጠላጥለው የስህተት እርሿቸውን አማኙ ላይ "ብን" እያደረጉ ወንጌላዊውን ክርስትና በስሁት ትምህርታቸውና ልምምዳቸው እያቦኩት እንደሆነ አያስተውሉም።

ስለዚህ ከቃሉ መርኸ ያፈነገጠ፣ "እንዲህ ካሉት ራቅ" የሚለውን ሐዋርያዊ ትዕዛዝ ያላከበረ፣ ዐቃቢያንን እንደ ፈራጅ ቆጥሮ ለሃሳዊያን ከመጠን በላይ የሚራራ ዕቡይ ስለሆነ፣ ወንጌልና ወንጌላዊያንን ከመጥቀም ይልቅ ለሃሳዊያኑ መስፋፋት ዓይነተኛ መሳሪያ መሆኑ በፍሬው ስለታየ፣ ሃሳዊያኑ ሲብስባቸው እንጂ ሲመለሱ ስላላየን፣ ይህ ከላይ የተዘረዘረው ሎጂክ ቅይጣዊነትን ከማስፋፋቱ ባሻገር ለወንጌልም ሆነ ለወንጌላዊያን የማይፈይድ ከመነሻው የከሸፈ ነው። ስለዚህ ከቅይጣዊነት አደጋ እንጠበቅ!!!

ቅይጣዊነትን እንፀየፋት!

ቴዎድሮስ ተጫን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ቅይጣዊነት #2

በቀዳሚው ልጥፍ ላይ ጠቆም እንዳደረግሁት "ቅይጣዊነት" አፋጣኝ መፍትሔ የሚሻ አሁናዊ ችግራችን ነው። አደጋው ለትውልድ ነውና። ምክንያቱም ሃሳዊያኑ ከነባሩ ክርሰትና ጋር ራሳቸውን መቀየጣቸው በእምነታቸው ደካማ የሆኑ ክርስቲያኖችና መጪው ትውልድ በተነፃፃሪም ቢሆን "ንፁህ" የነበረውን ወንጌላዊ ክርስትና አጥርቶ እንዳይመለከተው ብርቱ እንቅፋት ያኖራልና።

እኒህ ሃሳዊያን ስልተ ብዙ ሆነው ራሳቸውን ከነባሩ ክርስትና ጋር "ለመቀየጥ" በአጋንንታዊው "ጥበብ" እና በከፍተኛ ባጀት እየሰሩ ነው። የ"ቅየጣ" ዓላማቸውንም ለማሳካት የማይፈነቅሉት ድንጋይና ከሰማይ በታችም የማይጠቀሙት ዘዴ የለም።

በአባቶች መደበቅ

ሃሳዊያኑ ለቅየጣ ዓላማቸው በቀዳሚነት የሚጠቀመት አባቶችን ነው። በተለይ ተደማጭ የነበሩ አባቶችን። ለዚህ ጥሩ ማሳያ የሚሆኑን ጋሽ በቄ ናቸው። ያው ቄስ በሊና በህይወት የሉምና ምን እንላለን? እንተወው እንጂ ሃሳዊያኑ እርሳቸውን ተከልለው ስለሰሩት ተንኮል ብዙ ማለት ይቻል ነበር። ወደ ጋሽ በቄ እንመለስ። ጋሽ በቄ ታምራት ታረቀኝ ቲቪ (cj tv) ላይ ከቀረቡበት ቀን ጀምሮ የሃሳዊያኑ የመድረክ ማድመቂያ እና ለተኩላዎቹ መደበቂያ በመሆን በብዙ አገልግለዋል። እነኚህ ተኩላዎች አደገኛ ናቸው። በሆነ ወቅት ቅቡል የነበሩ አባቶችን በተለያየ ዘዴ አጥምደው በግ ለመምሰል እንደ ለምድ ይጠቀሙባቸዋል። በዚህም በበርካታ የዋህ አማኞች ልብ ውስጥ ብዥታን በመፍጠር ሰዎች ስለእነርሱ ያላቸው እይታ የተጥበረበረ እንዲሆን ይጥራሉ።

እዚህ ላይ ጃፒ በቄስ ቶሎሳ ሲደበቅ (ያው እርሳቸውም ከቃል እምነት ስህተት ባያመልጡም)። ዮናታን ደግሞ በተወደደው ዘማሪ ፓስተር ታምራት ሃይሌ እና በፓስተር ፃድቁ ለመደበቅ ሲሞክር፤ ዘላለም ጌታቸው የቄስ በሊናን ፎቶ (ከሞታቸወ በፊት) በትልቁ በየፖስተሩ እየለጠፈ እርሱ ከኋላ ሲደበቅ ነበር። አሁን ደግሞ በቃለ ህይወትና በመካነ ኢየሱስ መሪዎች ጀርባ ተደብቆ እውነተኛ መስሎ ለመታየት ይጥራል።

ሃሳዊያኑ ብዙሃኑ እውነትን ከሃሰት የሚለየው በቃሉ ማንፀሪያ ሳይሆን እነ ማን የት ጉባኤ ተገኙ በሚለው እንደሆነ በሚገባ ያውቃሉ። "እገሌ ካለ ያ "ቸርች" ወይም "አገልጋይ" ትክክለኛ ነው ማለት ነው ብሎ "ልክን" በ"እገሌ" የሚለካ" ትውልድ እንዳለ ያውቃሉ። ስለዚህ "ተሰሚ" የባለ "አባት" ፍለጋ በደረቅ እና በባህር ይሮጣሉ።

መድረኮችን "መግዛት"

ሃሳዊያኑ "ጤነኛ" የተባሉ መድረኮችን ክፉኛ ይፈልጓቸዋል። ባጀት መድበውም ይገዛሉ። የገዟቸው መድረኮች ላይ መቆምና ራሳቸውን መቀየጥ አይነተኛ መንገዳቸው ነውና። እንደ ምሳሌም ከአስር ወር በፊት በቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ሊደረግ ታቅዶ የነበረውንና ኋላ በኤፍ ቢ አይ አዳራሽ የተደረገውን የዘርፌን የመዝሙር ኮንሰርት ማንሳት እንችላለን።

ልብ በሉ ዘርፌ ከወዲያኛው ሰፍር ወደ ጴንጤው ከመጣች በኋላ ሰፋ ያለው ግንኙነትዋ ከሃሳዊያኑ ጋር ነው። ለኮንሰርቷም የእነጩፋን አዳራሽ በቀነሰ ዋጋ ማግኘት ትችላለች። ሃሳዊያኑ ግን ምን አደረጉ? ብዙ ብር መድበው ቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌልን መድረክ ለመግዛት ተጋደሉ። በመቶ ሺዎችም ከፈሉ (በወቅቱ ብሩን የመደቡት ሃሳዊያ እንደነበሩም ጭምጭምታዎች ተሰምተዋል)

ምን ነበር ዓላማቸው? ኮንሰርቱን ቀጠና ሁለት አዘጋጅተው የሙሉ ወንጌል አባላት "በቸርቻችን የተዘጋጀ ነው" ብለው ሲመጡ ሌሎችም "ጤነኛ" ከተባሉት አብያተክርስቲያናት ዘንድ "ሙሉ ወንጌል ነው'ኮ የተዘጋጀው" በሚል ቅን ልብ ሲመጡ ሃሳዊያኑ ከያሉበት ተጠራርተው ራሳቸውን ከሙሉ ወንጌል ጋር ለማመሳሰልና "ሃሳዊያን እንባላለን እንጂ አንድ ነን!" የሚል መልዕክት በማስተላለፍ ራሳቸውን ለመቀየጥ ነዋ። በብልጠት ነው እኮ የተራመዱት። በእርግጥ በማህበራዊ ሚዲያ በተደረገው ርብርብና የሙሉ ወንጌልም መሪዎች በወሰዱት እርምጃ (የዘገየም ቢሆን) ኮንሰርቱ ተሰረዘ እና ዓላማቸው ከሸፈ እንጂ።

እነኚህ ሰዎች ገንዘብ በመክፈል (ለአገልጋይ ጋባዦች) እና በነባር ቸርቾች በመጋበዝ በመድረኩም ላይ ቆመው ሲሰብኩ ፎቶ ተነስቶ በመለጠፍ "እዚህም መድረክ ላይ አለን" የሚል መልዕክት በማስተላለፍ የብዙዎችን የዋህ ልብ አታለዋል።

"አቃቢያኑን" መሸንገል

ሃሳዊያኑ ራሳቸውን ከበጎች ጋር አመሳስለው ለማቅረብ (ለመቀየጥ) ሁሉንም መንገድ ይጠቀማሉ ብለናል። አንዳንድ አቃቢያንንም ጭምሮ። "ኑና አሰልጥኑን እኛ እኮ ስነ መለኮት አልተማርንም....ችግራችን እውቀት ነው..." ወዘተ ይሉት ማታለያም ያቀርባሉ። ራሳቸውንም ለእውነተኛው ወንጌል ፍላጎት ያላቸው እና "ስልጠና" የሚሹ ለማስመሰል እስስታዊ ባህሪያቸውን ይጠቀማሉ።

ታዲያ አንዳንድ አቃብያን ይህን አታላይ ባህሪያቸውን ባለማስተዋል (ወይም ሆነ ብለው በራሳቸው ምክንያት) "እናሰልጥናችሁ" ብለው ወደ ረከሰ ሰፈራቸው ሲሄዱላቸው አብረዋቸው ፎቶ ተነስተው "እገሌ የተባለው ያ የምትወዱት እና የምታደንቁት ለእውነት ይቆረቆራል ያላችሁት ሰው መጥቶ አሰለጠነን እኮ....ከእኛ ጋር ነው'ኮ" የሚል መልዕክት ባላቸው ሚዲያ ሁሉ አጮጩኸው ያስተላልፋሉ። የተወሰነውን አማኝ ደግሞ በዚህ ያደናግራሉ። "ኮንቪንስ" ወይም "ኮንፊውዝ" ማድረግ ነዋ ዓላማቸው።

ከዚያስ? ከዚያማ በስልጠናው ማግስት "ዲስኮኔክት አደርጋችኋለሁ" ወደሚለው ስሁት ትምህርታቸው ያለ ይሉኝታ ይመለሳሉ። "ያሰለጠኗቸውንም" አቃብያን ከዚያ ወዲያ ዞር ብለውም አያዩዋቸው። አላማቸው ከነባሩ "ክርስቲያናዊ ህብረት" ጋር ራሳቸውን መቀየጥ ብቻ ነውና። ወዲያው ደግሞ ሌላውን ነሆለል "አቃቤ" በሌላ ስልት ለማጥመድ መኳተናቸውን ይቀጥላሉ። የወንጌልን እውነት ለጊዜያዊ ጥቅማቸው ሲሉ ከመሸቀጥ መቼ ይቦዝናሉ....

ቅይጣዊነት ፅዩፍ ናት!

ቴዎድሮስ ተጫን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

“መንገድና - መዳረሻ”

ስቅለትና ትንሣኤ የአንድ ሰሞን የወረት ዜና አይደሉም (ሊሆኑ አይገባም!)። ይልቊንስ የአማኞች የኑሮ ዘይቤና የሚጠብቊት የዐዲስ ፍጥረት ተስፋ እውነታ ናቸው ። በሌላ አገላለጽ የክርስትና ጉዞ ፍኖተ ካርታ ናቸው። የጉዞውን መንገድ መስቀል ብንለው መዳረሻውን ደግሞ ትንሣኤ ማለት እንችላለን። እንዴት? የሚለውን በቀላሉ እንመልከት፤

• መስቀሉ

መስቀል፣ ክርስትና ያለአጃቢ በጠባቧ መንገድ የራሳችንን ሸክም ተሸክመን የምንጓዘው ሕይወት እንደሆነ ያሳስበናል። በወደቀው ዓለም ስንኖር ከአሮጌው ሰዋችንና ከዐመጻ ጋር ዘወትር እየታገልን፣ ስለ ወንጌል እየተገፋን እንደምናምጥ አስረጂ ነው። ለዚህች ዓለም ሥርዓት እንግዳና መጻተኛ፣ ለምትመጣው መንግሥት ደግሞ ዜጋና መናኝ እንደሆንን ያስተምረናል።

አሮጌውን ሰው እንድናሸንፍ ለሥጋ ምኞትና ለፈቃዱ በየቀኑ እየሞትን በዐዲሱ ሰው ዕሴቶች እንድንመራ ይጠቊመናል! በመስጠት ማግኘት የሚቻልበት ፣ ከሁሉ ኋላ በመሆን ፊተኛ የሚኮንበት፣ በድካም ብርታት የሚታፈስበት፣ በውርደት ክብር የሚለበስበት አያዎ (paradoxical) መንገድ እንደሆነም ያስረዳናል።

መስቀሉን ስናስብ አሁን ለከበበን ውጫዊ ምስቅልቅልና ዕኲይ ቀላልና ግዴለሽ መልስ (quick fix) ከመስጠት እንታቀባለን። ነገር ግን መስቀል፥ አምላክ የአዳምን ልጆ ሥቃይ በፈቃዱ የተካፈለበት ምስጢር በመሆኑ አብሮ እየቃተተ ፍጥረቱን የሚያድን ታዳጊ እንደሆነ እናስተውላለን። ምስኪን መስሎ ሽንፈት በሚመስል መንገድ የሞትን መውጊያ እንደሰበረ ሁሉ፥ አንድ ቀን ሐዘንና ልቅሶን፥ ሥቃይንና ርግማንን ሙሉ በሙሉ እንደሚሽር ስለምናምን በመንገዱ እንጸናለን!

• ትንሣኤው

“እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፣ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ በተቀመጠበት በላይ ያሉ ነገሮችን እሹ” (ቈላ.3፥1) ተብሎ እንደተጻፈው ትንሣኤውና ኅይሉ ሲገባን ዳፍንታሙ ዕይታችን ይስተካከላል። እውነት የሆነውን፣ ክቡር የሆነውን፣ ትክክል የሆነውን፣ ንጹሕ የሆነውን፣ ተወዳጅ የሆነውን፣ መልካም የሆነውን ሁሉ፣ በጎነትና ምስጋናን እናስባለን።

ትንሣኤ እውነት ስለሆነ መሲሁ ዳግም በክብር ሲገለጥ እንዳናፍር በመክሊታችን ተግተን እናተርፋለን። አሮጌውን እርሾ እያስወገድን አስቀድሞ ያዘጋጀልንን መልካሙን ሥራ እንፈጽማለን። ጽድቅና ሰላም በመንፈስም የሆነ ፍስሃ የሞላባትን የንጉሡን ከተማ እንናፍቃለን።

እግዚአብሔር በዓለም ላይ በጽድቅ የሚፈርድበትን ቀን መወሰኑን በልጁ ትንሣኤ ስላረጋገጠልን ሰዎች ሁሉ ንስሓ እንዲገቡና ከዚህ ጠማማ ትውልድ ራሳቸውን እንዲያስመልጡ እንመክራለን! እንድንበት ዘንድ ለሰዎች የተሰጠ ከዚህ ስም በስተቀር ሌላ ስም ከሰማይ በታች እንደሌለ በድፍረት እንመሰክራለን! ኢየሱስ እርሱ "ጌታም ክርስቶስም" እንደሆነ በኑሮም በቃልም እንናገራለን!

መስቀሉ የመዳናችን ጥበብና መንገዳችን — ትንሣኤውም የእምነታችን ኅይልና መዳረሻችን ነው! የትንሣኤውን ጌታና ኅይሉን ይበልጥ እንድናውቅ እርሱ ይርዳን!

መልካም የትንሣኤ መታሰቢያ!

ፍጹማን ግርማ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ሊያድነን የሞተው ሊጌተይ ተነስቷል!
1ቆሮንቶስ 15፡1 - 58

ለመላ ዓለሙ ብቸኛ ተስፋ እንደሆነ አምነን የምንሰብከው የሙታን ትንሣኤ፣ የወንጌል ማእከላዊ መልእክት (15:2-4)፣ እስትንፋሰ መለኮት የሆኑ የመጻሕፍት/ትንቢት/ ቃል ፍጻሜ (15፡3-4) የሆነና፣ በበርካታ ተአማኒ የዐይን ምስክሮች የተደገፈ ነው፡፡ አስቀድሞ ሶስት ሴቶች፣ ሐዋርያው ጰጥሮስ፣ በኋላም አስራ ሁለቱ ሐዋርያት፣ ከአምስት መቶ በላይ የሚሆኑ ደቀ መዛሙርት፣ የጌታ ወንድም የሆነው ያዕቆብ፣ በኋላም ሐዋርያው ጳውሎስ (15:5-8) ሞቶ የተነሳው የአይሁድ መሲህ ቸሩ መድኃኒዓለም በከበረ ሥጋ ትንሣኤ ቁልጭ ብሎ እንዳዩት መስክረዋል፡፡

ይህ ታሪካዊ እውነት፣ ከክርስትና አገልግሎታዊ ህይወት ለአፍታ ያህል ልናሰልሰው አይገባንም፡፡ የኃጢአታችን ስርየት የተረጋገጠበት፣ በክርስቶስ ያንቀላፉት የሚነሱበት፣ ወንጌልም “የምሥራች” ተብሎ የሚሰበክበት (15፡14)፣ በህይወት ያሉትም ከሞት ባሻገር ላለው ዐለም ተስፋ የሚያደርጉበት ሰለሆነ በክርስቲያናዊ አገልግሎት ትምህርተ ትንሣኤን ችላ ማለት ሰይፍ የሌለው ሰገባን እንደመታጠቅ ይቆጠራል፡፡ ዓመታዊ ከበራ ብቻ ሳይሆን እለታዊ ኑሮ ካላደረግነው፣ የምናገለግላቸው ሰዎች “ብላና ጠጣ ነገ መሞትህ አይቀርም!” የሚል ፋታሊስት ኑሮ የሚኖሩ ይሆናሉ፣ አገልግሎታችንም የምስኪኖች፣ አስቀድሞ ስለ ትንሣኤው የነገሩንን ሰዎችም ውሸታም የሚያደርግ (15፡15)፣ ንስሐ የገቡትንም ኃይላቸውን የሚያደክም ይሆናል፡፡ ስለዚህ የትንሣኤው ታሪካዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት የማያቋርጥ ስብከትና ትምህርታችን ነው፡፡ ትንሣኤው የክርስትና አዋጅ ምክንያትም፣ የክርስትና ሕይወት ኃይልም፣ የመጪው ዓለም ተስፋም ነው (15፡12 19)፡፡

የትንሣኤው አካል ሙሉ በሙሉ የተለወጠ፣ ዳግም በሞት ኃይል ላይበሰብስ በክብር የተነሳ 15፡43) ነው፡፡ ይህ አካል በኃይልና በመንፈሳዊ ማንነት የተነሳ ዘላለማዊና ኢሟቲ (የማይሞት) የሆነና የፍጻሜ ታሪኩም በድል ዋስትናና በአካል ክብረት የሚደመደም ቋሚ አካል ነው 15:50-58፡፡ ባጭሩ፣ ተስፋችን ተፈጽሞ የእግዚአብሔርን መንግስት በቋሚነት በምንወርስበት ጊዜ በአካላችን ላይ ታላቅ ለውጥ ይካሔዳል (15፡ 50-53)

በፍጻሚው ድል፣ ሕይወት ከማይመስል ነገር ውስጥ በውበቱና በስሪቱ ወደር የሌለው አዲስ ማንነት እንለብሳለን፣ ቢራቢሮዋ አባ ጨጓሬ ውስጥ እንዳለች ሁሉ፣ ጎተራዎችን ሁሉ የሚሞላው ምርት ያለው ስንዴዋ ውስጥ እንደሆነ ሁሉ፣ ነፍስም መንፈስም ያሉት ሥጋ ውስጥ እንደሆነ ሁሉ፣ እኛም አሁን ያላየነው፣ ነገር ግን በጌታ በኩር ትንሣኤ የታየውን ሁለእንተናዊ ለውጥ ተለውጠን ክቡር ሥጋውን እንመስላለን (ሉቃ 24:39... የፍጻሜው ምስጢር፣ የሞት ድል መነሳትና የአዲሱ ማንነታችን መገለጥ ዋናው ትኩረት ናቸው፡፡ “ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሊለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሊለብስ ይገባዋልና።” (15፡53-54) “ይገባዋልና” የሚለው ቃል ይሄ አውልቆ ማጥለቅ የማይቀር የትንሣኤ ፕሮቶኮል እንደሆነ ያሳየናል፡፡ ድንኳን ፈርሶ በቋሚ ቤት ይቀየራል ቁ52 ላይ ብቻ ሁለት ጊዜ “እንለወጣለን” ይላል - ሞት የተባለ ዋጠው ሰልቅጠው ራሱ ይሞታል- ሆሴዕ 13:14 “...ከሲኦል እጅ እታደጋቸዋለሁ፥ ከሞትም እቤዣቸዋለሁ፤ ሞት ሆይ፥ ቸነፈርህ ወዴት አለ? ሲኦል ሆይ፥ ማጥፋትህ ወዴት አለ?...።” ሞት ሲሸነፍ ኃጢአትም ተሸነፈ ማለት ነው፡፡

እንግዲህ የትንሣኤ እምነታችን የደኅንነታችንን ሙላት የምንቀበልበት ብቻ ሳይሆን፣ የጌታን ሥራ ለመስራት የሚያነሳሳን ተስፋችንም ነው 15:57፡፡ ስለዚህ ለግዚአብሔር ምስጋናን እየሰጠን በዚህ በሚሞተው ስጋ ሳናቋርጥ የጌታን ስራ እንስራ (15፡58) “ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ድካማችሁ በጌታ ከንቱ እንዳይሆን አውቃችኋልና የምትደላደሉ፥ የማትነቃነቁም፥ የጌታም ሥራ ሁልጊዜ የሚበዛላችሁ ሁኑ።

ውድ ወገኖች እንግዲህ “ክርስቶስ ከሞት ተነስቷል” የሚለው መልእክት ከወንጌል አንደኛው መልእክት ሳይሆን ወንጌል ራሱ እንደሆነ አውቀን ዓለማዊ ለሆነ ለሚሞተው ለአንዳች ነገር እንዳንሞት፣ ለሚጠፋውም እንዳንጠፋ እንጠንቀቅ፡፡ “ክርስቶስ ኢየሱስ በሥጋ ከሞት ተነስቷል” የሚለው እምነት ላይ የሚኖር ማንኛውም ልዩነት ክርስቲያን መሆንና አለመሆን እንደሆነም እንገንዘብ፣ በተለያዩ ምክንያቶች ሞት በግልና በማኅበር ቢያስፈራራን እንኳ የሚነገረን የትንሣኤ ህይወትንን ቅርበት እንደሆነ እንወቅ፡፡

በአጸደ ሥጋ ሕይወት እያለን እንኳ ለድል አድራጊ የክርስትና ሕይወት ምንጩ የክርስቶስ ትንሣኤ ነው፡፡

በመጨረሻውም ዘመን የዓለሙ ሁሉ መፋረጃ ይህ የትንሣኤው ጌታ ክርስቶስ ነው! እንኳን ደስ አላችሁ፣ ሊያድነን የሞተው ሊጌተይ ተነስቷል!

መጋቢ ሰለሞን ጥላሁን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የጴጥሮስ ጌታ ዛሬም ይራራል! (ማር. 14፥66-72)


ቅዱስ ማርቆስ፣ ወንጌሉን ሲጽፍ በቅዱስ ጴጥሮስ ላይ ያተኵራል፤ ነገር ግን ከኢየሱስ በላይ አያልቀውም ወይም ከፍ ከፍ አያደርገውም። ኢየሱስ በተያዘበት ሌሊት ስለ ነበረው ኹኔታ ሲናገር፣ “ጴጥሮስንም፦ ስምዖን ሆይ፥ ተኝተሃልን? አንዲት ሰዓት ስንኳ ልትተጋ አልቻልህምን?” (ማር. 14፥37) ሲል፣ ሌሎቹ ወንጌላት ግን ኢየሱስ ይህን ጥያቄ ያቀረበው ለኹሉም ደቀ መዛሙርት እንደ ነበር ይናገራሉ (ማቴ. 26፥40፤ ሉቃ. 22፥46)።

በተመሳሳይ መንገድ ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ፣ ደቀ መዛሙርቱን በገሊላ እንዲጠብቃቸው መልእክት ሲናገር፣ ማርቆስ አኹንም በተመሳሳይ መንገድ ከሌሎቹ ወንጌላውያን በተለየ ኹኔታ፣ “ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ለጴጥሮስም፦ ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል፤ እንደ ነገራችሁ በዚያ ታዩታላችሁ ብላችሁ ንገሩአቸው አላቸው።” (ማር. 16፥7) በማለት ትኵረት ሲያደርግ እንመለከተዋለን።

ቅዱስ ጴጥሮስ፣ ኢየሱስ ሲገረፍ አይቶታል፤ እንዲሁም የኢየሱስ ተከታይ መኾኑ በብዙዎች ዘንድ ታውቆአል፤ በሌላ መልኩ ደግሞ ስምዖን ጴጥሮስ፣ እንደሚክደው ጌታችን ኢየሱስ በተደጋጋሚ ትንቢት ተናግሮ ነበር። ጴጥሮስ ምንም እንኳ ኢየሱስን እስከ መጨረሻው ግቢ “የተከተለውም ቢኾን እንኳ”፣ ነገር ግን መንገዶቹ ኹሉ በቅጥፈት፣ በውሸትና ስለ ኢየሱስ “ይህን የምትሉትን ሰው አላውቀውም በማለት በመራገምና በመማል” (ማር. 14፥71) በክህደት የተሞላ ነበር።

ስምዖን ጴጥሮስ፣ እንደ ጌታችን ኢየሱስ ትንቢት በአደባባይ በሴቶችና በተወሰኑ ሰዎች ፊት ክዶአል፤ ልክ እንደ ካደ ግን፣ ኢየሱስ “ትክደኛለህ ያለው ቃል ትዝ ሲለው፤ ነገሩንም አስቦ አለቀሰ።” (14፥72)። ይህ እጅግ አስደናቂ ተግባር ነው፤ የሠራውን ኀጢአት ሊናዘዝበትና አልቅሶ ሊመለስ መውደዱ ለእኛ የሚያስተምር ብርቱ መልእክት አለው።

ብዙዎቻችን ኀጢአት ሠርተን ከመናዘዝና ለመተው ከመጨከን ይልቅ ለመደበቅ እንሞክራለን። ምናልባት ብዙዎቻችን እንደ ጴጥሮስ፣ በጌታ ዘመን ኖረን ልክ ጴጥሮስ ኢየሱስ ሲገረፍ እንዳየው እኛም ተመልክተን ቢኾን፣ ኢየሱስን ደጋግመን ልንክደው እንችላለን። ነገር ግን ማርቆስ እንደሚነግረን ኢየሱስ ጴጥሮስን በልዩ ፍቅር ወደደው፤ ይቅርም አለው፤ ራራለትና ወዶ ተቀበለው።

ይልቁን የክርስቶስን ወንጌልና ክርስቶስ ስለ እኛ የከፈለውን ታላቅ የመስቀል ሥራ በሥራ ቦታ፣ በትምህርት ገበታ፣ በታክሲ ስፍራ፣ በቤተሰብ መካከል፣ በባልንጀሮቻችን ፊት ለመመስከር ብዙ ጊዜ የምናፍርና የምንክድ ነን። የምንፈራውና የምንክድበት ምክንያታችንም ብዙ ነው፣ አንዳንዶቻችን አፍረን፣ ሌሎቻችን ፈርተን፣ ሌሎቻችን ደግሞ ሰዎች እንዳይሳለቁብንና እንዳያሸማቅቁን ብለን የትንሣኤውን ወንጌል ከመመስከር ቸል ያልንባቸው ጊዜያት ብዙ ናቸው።

በዚህ ረገድ ኹላችንም በካድንባቸው፣ በበደልንባቸው፣ በክርስቶስ ባፈርንባቸው፣ ችላ ባልንባቸው ጊዜያት ኹሉ ኢየሱስ የማይለወጥ ታማኝ ወዳጅና አባት ነው፤ እስክንመለስ የሚጠብቅ እረኛም ነው፤ መካዳችንን ረስቶ በፍቅር ሊቀበለንና ሊምረን የታመነ ሊቀ ካህናት ነው። ስለዚህም እንደ ጴጥሮስ በኀጢአታችን ልንናዘዝና ይቅርታ ልንለምን ይገባናል እንጂ መሸፋፈንና መደበቅ አይገባንም። ጴጥሮስን ይቅር ያለው ጌታ ዛሬም መሐሪ ነው!

ቅዱስ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበለ በኋላ፣ በሙሉ ድፍረት በሕዝብ ኹሉ ፊት መሰከረለት። እናንተም፣ ያላፈረባችሁን አትፈሩበት፤ በአደባባይ ለክብራችሁ የተዋረደውን እርሱን በሰዎች ኹሉ ፊት ስሙን በመመስከር ፍቅራችሁን ግለጡለት።

“በማያቋርጥ ፍቅር ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለሚወዱ ሁሉ ጸጋ ይሁንላቸው።” (ኤፌ. 6፥24)

አቤኔዘር ተክሉ (ዲያቆን)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የእግዚአብሔር የመስቀል ማሕተም!

ሐዋርያው ዮሐንስ የፍቅር እርግጠኝነትን የሚያስረዳው ፍቅር በእኔ መውደድ ሳይሆን በእግዚአብሔር መውደድ እንደሆነ በማሳየት ነው (1ዮሐ 4፥10)። የእግዚአብሔር መውደድ ደግሞ ልጁን የኅጢአት ማስተሰረያ ይሆን ዘንድ በመስቀል ላይ በሚኖር መከራ አዋለው።

መቼም ለፍቅር መስቀልን መምረጥ ከሚከስተው መጥፎ ምስል አንጻር ትክክል አይመስልም። ሮማውያን በመስቀል መሰቀልን በራሳቸው ዜጎች ላይ እንዳይፈጸም በህግ ከልከለዋል። ከዜጎቻቸው ሕሊና ምስሉን ለማራቅም ይተጉ ነበር። መስቀል በጣም ዘግናኝ የመግደያ መንገድ ነው። የሚፈጥረው ስቃይና ጣር ከፍተኛ ነው። ጣሩ ብቻ ሳይሆን መሰቀያ ቦታው ራሱ የሞት ድባብ የሚያደባበት ነበር።

እግዚአብሔር ፍቅሩን በዚህ መንገድ ገለጸ። «መድቀቁና መሠቃየቱ ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር፤ እግዚአብሔር ነፍሱን የኀጢአት መሥዋዕት ቢያደርገውም እንኳ» (ኢሳይያስ 53:10)። ልጁን አሳልፎ ለመስቀል ሞት ሰጠው። በዘመኑ በነበረው የመጨረሻው የጭካኔ ግድያ ክርስቶስ ኢየሱስ ተላልፎ ተሰጠ። በኢየሱስ ስቃይና ጣሩ ውስጥ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አሳየ። አለም ደካማ ባለችው መንገድ እግዚአብሔር ፍቅሩንም ጽድቁንም እውን አደረገ።

የእግዚአብሔር ትድግና አንድያ ልጁን በመስቀል በመስጠት ተገለጠ። ትድግናውን በአጀብ ሳይሆን በውርደት መስቀል ላይ ፈጸመ። በኅጢአቱ አመጽ የተመታው አለም አመጹን በሙሉ ክርስቶስ ላይ በማኖር የማስተሰርያ መስዋእት አድርጎ አቅርቦታል (ሮሜ 3፥25)። በደካማው መንገድ ብርቱው ጠላት ተረታ፥ ድነትና ትድግናም ተበሰረ።

በመስቀሉ ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር ታረቅን፣ ቀረብን፣ ተቀባይ ሆንን። ፍቅሩንም ጽድቁንም እግዚአብሔር ገለጠልን! እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ላይ በሰራው ስራ ርቀን የነበርነውን ታርቆናል!

በክርስቶስ ኢየሱስ፣ አምላክ-ሰው ስቃይና ህማም በኩል የጸጋውን ባለጠግነት ተገልጧል። ለእኛ ለምናምን መስቀሉ የእግዚአብሔር መውደድ ማህተም ነው!

አማኑኤል አሰግድ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

<<ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን?>> ዩሐ. 13፥ 12

~~~~
[ትህትና ሊያስተምረኝ ወዶ
እግር አጠበ ባሪያውን ወርዶ
እራሱን አዋርዶ]
~~~

በአቧራማዋ እስራኤል በነጠላ ጫማ (Sandals) መንቀሳቀስ የተለመደ ነበር። በአቧራው ምክንያት እግር የሰፈሩን አዳፋ ይሰበስባል። የእግሩን አቧራ ሰው ወደ ቤት ሲገባ ማጽዳት የተለመደ ተግባር ነበር። ጠረጴዛው ዝቅ ያለ (low table) ስለሆነ ምግብ ከመቅረቡ በፊት ደግሞ ሰው እግሩን ታጥቦ ነው የሚቀመጠው፣ እጅ መታጠብ በኛ ዘንድ እንደተለመደው።

ኢየሱስ ተነስቶ እግራቸውን ሲያጥብ የመጨረሻው ተራ ሎሌ ባሪያ የሚያደርገውን እየከወነ ነበር። ደቀመዛሙርቱም ራሱን 'በማዋረዱ' ሳይገረሙ አይቀሩም። ለዚህ ነው ጴጥሮስ ራሱ ሊያደርገው የማይደፍረውን የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ብሎ የመሰከረለት መሲህ (ማቴ. 16:16) የተራ ባሪያን ድርጊት ሲከውን በተቃውሞ የቆመው። የነፍሳችን ጌታና መሲህ ሲሉት የከረሙት ሰዎች እግሩን ማጠብ ሲጠበቅባቸው እሱ ቀድሞ እግራቸውን ለማጠብ ማበሻ ማንሳቱ አስደናቂ ነውና። ምንም እንኳን እንደ ምድራዊ ንጉስና ነፃ አውጪ ሳይሆን እንደ ስቅዩ-ሎሌ (suffering Servant) ቢመጣም። (ኢሳ. 53)

~~~~~~~
[ደቀመዛሙርቱ እግራቸው ቆሸሸ
አደፈ ጎደፈ ፍጹም ተበላሸ
ሁሉን የፈጠረ ሰውን የወደደ
ጭቃውን ሊያስወግድ ወደ ታች ወረደ]
~~~~~~

ሁሉን የሚገዛና ሁሉ በሁሉ የሆነ አምላክ እግር ሊያጥብ ዝቅ አለ፣ ከአቧራማ እግሮች ስር ተገኘ። በላይኛው ክፍል ቆሻሻቸው ሊያፀዳ፣ አደፋቸውን ሊያጠራ ብቻ ግን አይመስልም። እንዲያ ቢሆን ኖሮ "ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን?" ብሎ ባልጠየቀ።

~~~
[እሱ ያላጠበው ከእርሱ ጋር አይኖርም
አይቆርስም ከአምላክ ጋር አንድነት የለውም
ጴጥሮስ ይህን አይቶ ሰውነቴን ደሞ
እጠበኝ ጌታ ሆይ አለውም ተማጽኖ]
~~~~~

ኢየሱስ ያደረገው ስለራሱ በማቴ. 20፥28 እንዳለው "ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።" ራሱን ዝቅ አድርጎ ሌሎችን ሊያገለግል ነው የመጣው። ከማገልገሉም ባሻገር ሕይወቱ እንደሚነግረን በትህትና መሞላቱን ነው። ከአመጣጡ እስከ አሟሟቱ ድረስ ድንቅ በሆነ ትህትና የተሞላ ነው። በህማም የተሰበረ፣ ለመወደድ ደም ግባት የሌለው አይነት ሰው ነው።

~~~~
[በሚደነቅ ብርሃን የሚኖር ፈጣሪ
አልፋና ኦሜጋ የፍጥታት ሰሪ
ማበሻ ጨርቅ ወስዶ እግር ሊያጥብ ወረደ
ዝቅ አ'ረገ ራሱን ለሰው ተዋረደ]
~~~~

የኢየሱስ ዝቅ ብሎ እግር ማጠቡ ደረጄ ከበደ እንዳለው "ትህትናን ሊያስተምረኝ ወዶ" ነው። ያደረገልን ራሳችንን በትህትና ዝቅ አድርገን የባልንጀራችንን እግር እንደድናጥብ ነው። የባልጀራችን እግር ጉድፍ ሲያነሳ እንድንጠርገው በዚያም ትህትናችን እንዲታይ ተጠርተናል።

~~~~~~~
[የሁሉ ማሰሪያ አላማ ያለው ነው
ጌታ ይህን አድርጎል እኔስ እንደምን ነው?
የወንድሜን እግር እስካጥብ ዝቅ ካልኩ
እውነትም 'የሱስን በእርግጥ ተከተልኩ]
~~~~~

ኢየሱስ የደቀመዛሙርቱን እግር አጥቦ ሲጨርስ "እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና" ብሏቸዋል። እንደተከታይ እሱን ልንመስል ይገባልና፣ ትሁት መሆን አለብን። የጌታ ተከታይ ልዮ ምልክቱ እንደ ጌታው ዝቅ ማለቱ ነው። ራሱን ስለሌሎች አሳልፎ መስጠቱ ነው። የዝቅታን መንፈስ ይስጠን!

~~~~~~~
[ባሪያ ከሚያኖረው አይበልጥም አላቸው
መልክተኛም አይበልጥ ይልቁን ከላከው
እንግዲህ ጌታችሁ እኔ ይህን ስፈጽም
አድርጉት ለሁሉም ዛሬ ሁኑ እናንተም]
~~~~~~

Every good thing in the Christian life grows in the soil of humility. Without humility, every virtue and every grace withers. That's why Calvin said humility is first, second, and third in the Christian faith.
John Piper

ጌታችን አዳፋማ እግር በማጠቡ ውስጥ ትህትናን የምንማረውን ያህል ጌታን ማገልገልንም እንማራለን። ለጌታ ልንሰጠው የምችለው ምንም ነገር አለመኖሩና ልንሰጠው የምንከጅለው ራሱ የራሱ እንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል።

አማኑኤል አሰግድ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ቦታዬ እንዳልሆነ አውቃለሁ! ልብን መመርመር፥ ኩላሊትንም ማወቅ ለቸሩ ብቻ የተገባ ነው። አይደለም የሌሎችን የራሴን የልብ ማዘንበል እንኳ መርምርልኝ፥ ፈትንልኝ ከማለት በቀር ማድረግ ምችለው የለም። ልቤ አሳች መሆኗ መች ጠፍቶኝ! ቀጥሎ የማነሳቸው ሃሳቦች "የይመስለኛል" አተያዮች ናቸው። በአንድዬ ዙፋን ላይ ራሴን አልሰይምም። የልባቸውንም ኾነ የልቤን ሊዳኝ የበቃ እሱ ብቻ ነው። እኔ ከተገለጠ የኑሮ ዘይቤ ተነስቼ ነው የይመስለኛል ዳሰሳዬን ምሰራው።

መዝሙር ገበያ ተኮር ከኾነ ከረመ። አትራፊ የመሰለ ሃሳብ ይዘመርበታል። ህልውናህ እና መገኘትህ የሚሉ ዝማሬዎች መበራከት ገበያው ላይ ከመፈለጋቸው የመነጨ ይመስለኛል። በስንኞቻችን እንደ ምንለው እንቅልፋችን እስኪ ተንን፥ አይኖቻችንም እስኪ ደነግዙ ልኡሉን ፈልገነው ከኾነ እሰየው። ቃሎቻችን ግን የደፈሩ ናቸው። "ኢየሱስን" መዘመር የሚያዋጣ የመሰለ ሰሞን ዘማሪዎቻችን የአልበማቸውንም የነጠላቸውንም መጠሪያ ኢየሱስ አድርገዋል። በአንድ ዝማሬ ውስጥ ስሙን አብዝቶ መጥራትም ስለ ኢየሱስ ከመዘመር ጋር አቻ ተደርጎ ተወስዷል።

ዘማሪዎቻችን የዜማ መልእክቶቻቸውን እንደ ሚቆሙበት መድረክ አድርገው ሲያበጃጁም አስተውያለው። የእምነት ቃል እንቅስቃሴ በግልጽ የሚሰበክባቸው ጉባኤዎች ላይ ቆየት ያሉ ዝማሬዎች ሳይቀር እርምት ተደርጎባቸው ነው ሚዘመሩት። አንድ ምሳሌ ብቻ ላንሳ። "የሚመጣ የሚከብር" የሚለው የደረጀ ከበደ ቆየት ያለ መዝሙር New creation ሲዘመር "ብንወድም ባንወድም ኢየሱስ ይነግሳል" በሚለው የስንኝ አንጓ ፈንታ "እኛ እንወዳለን ኢየሱስ ይነግሳል" ተደርጎ ሲዘመር ሰምቻለሁ።

ከዘመናችን እንቁዎች መኻል አንዱ በረከት ተስፋዬ ነው። ከምደነቅባቸው ዘማሪያን ተርታ ነው። የተዋጣለት vocalist ደግሞም composer ነው። ዝማሬዎቹን በብዙ ደስታ አደምጣለሁ። ዳሩ ግን ከላይ ባነሳሁት የገበያ ጥናት የተጠቃ ሰውም ይመስለኛል። የብሔር ማንነት ጥያቄ ሰቅዞ ባስጨነቀን ወቅት "ሰው ነኝ" የሚል የፖለቲካ ርእዮት ተቀስቅሶ ነበር። ይኼ አተያይ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘ በመሰለበት ጊዜ በረከት "ክርስቲያን ነኝ ብሄር የለኝ" ብሎ አቀነቀነ። በወቅቱም እዚኛው ዝማሬው ላይ ልክ አይደሉም ብዬ ባሰብኳቸው ጉዳዮች ላይ መጻፌን አስታውሳለሁ። አዲሱን አልበሙን ለማስተዋወቅ የመረጠው መዝሙርም ገበያ መር መስሎኛል። ሙግቴን እንደሚከተለው አቀርባለሁ። በወንጌላዊያንና ኦርቶዶክሳዊያን መሃል ከባድ መካረር ደግሞም ብሽሽቅ አለ። በሁለቱም ወገን ለአንደበታቸው ከልካይ የሌላቸው ጠባጫሪዎች እንደ አሸን ፈልተዋል። የጋራ አካፋይ የሌላቸው ይመስል ወንጌላዊያኑ ኦርቶዶክሳዊያን ላይ ኦርቶዶክሳዊያኑም ወንጌላዊያን ላይ ይዘባበታሉ። ጉንተላም እንደ ዕቅበተ እምነት መወሰድ ከጀመረ ሰነበተ። የቲክቶኩ መቋጫ የሌለው ንትርክ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው። በግሌ ቲክቶክ ላይ ያለው ንትርክ ራሱ እርባና ቢስ ኾኖ ይታየኛል። ባስ ሲልም መቃቃርን የሚፈጥር ለወንጌልም እንቅፋት የሚኾን ሁሉ ይመስለኛል። ወንጌላዊ አማኝ ስለሆንኩ እኛ ወንጌላዊያኑ ላይ ላተኩር። የወንጌል ስርጭታችን ራሱ ኦርቶዶክሳዊ ልምምዶችን ማጥቃትን ማእከሉ ያደረገ ይመስላል። በዚህ መሻከር መኻል ነው በረከት "አማላጄ" የሚለውን ዝማሬ የአልበሙ ማስተዋወቂያ አድርጎ ያቀረበው። ብዙ ወንጌላዊያን ይኼን ዝማሬውን በከፍተኛ ፍጥነት እንደ ሚቀባበሉት ጥርጥር የለኝም። በመጨረሻም ሃሳዊያንን በሞገተበት ዝማሬው መገረሜ አልቀረም። ሁሉም ሃሳዊያን ጋር ለማለት በሚያስደፍር መልኩ በረከት ያልቆመበት መድረክ የለም። አሁን በአባልነት ያለበት አጥቢያ ራሱ ለኔ ጤናማ የወንጌል ቃል ከማይሰበክባቸው ማህበራት መኻል ነው። እስራኤል ዳንሳን መቃወሙን ዘንግቼ አይደለም። እስራኤል ዳንሳ ላይ ዘማሪው ያነሳው ጠንካራ ሂስ ራሱ የወደቀ ዛፍ ምሳር ይበዛበታል አይነት መስሎ ስለ ሚታየኝ ነው ብዙም ስፍራ ያልሰጠሁት። ይኼ ሁሉ የግል አተያይ መኾኑን በድጋሚ ላስታውስ እወዳለሁ።

ኢብሳ ቡርቃ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ወንጌላችን "ክርስቶስ" እንጂ "ቁስ" አይደለም!

በተለምዶ "የብልፅግና ወንጌል" ተብሎ በሚጠራው "የስግብግቦች" ትምህርት ውስጥ አንደ ዋና ትምህርት የሚወሰደው "እግዚአብሔር ሁሉም አማኞች እንዲበለፅጉ ይፈልጋል" የሚለው ሰው ወለድ አስተሳሰብ ነው። ይህም ክፉ ትምህርት ምንም መለያ ሳያስቀምጥ "ድህነትን" በጥቅሉ ከአጋንንት እንደሆነ አድርጎም ይሰብካል። ነገር ግን ክርስትና ክርስቶስን እየመሰሉ መኖር እንጂ ደሃም ባለጠጋም የመሆን ጉዳይ አይደለም። የመፅሐፍ ቅዱስ ማዕከላዊ መልዕክት ክርስቶስ ነውና።

በዚህ ከመሰረቱ በተዛነፈ አመለካከት የተነሳ የትምህርቱ መምህራን ለተከታዮቻቸው አብዝተው ምድራዊና ሃላፊ የሆነውን ስኬት፣ ከፍታና ድል ይሰብካሉ። በዚህ አትሮኑሳቸውን በሞላው የተጣመመ "ወንጌል" ምክንያትም "በድህነት" የሚኖሩ አማኞች ተሳቀው እንዲኖሩ አሊያም ከጉባኤያቸው እንዲርቁ ያስገድዷቸዋል። ስለወንጌል እውነት "ደሃ" የሆኑትንም ጭምር የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጓቸዋል።

እነዚህ "ሃሳዌ መምህራን" ኢየሱስ በድህነት የኖረው "መደኸየትም" የእግዚአብሔር ፈቃድ አካል ከመሆኑ የተነሳ እንደሆነ ይዘነጋሉ። ጳውሎስም ያንኑ ፈለግ የተከተለውና በድህነቱ ሳያፍር "ድሆች ስንሆን" ብሎ የተናገረው፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ "በቁስ" ከመበልጠግ ጋር አያይዞ ስለማይመለከተው እንደሆነም አያስተውሉም። ጴጥሮስ "ፍለጋውን ተከተሉ" ብሎ የፃፈልን "ድህነትንም" ሊጨምር እንደሚችል ማሰብ አይፈልጉም።

ሙሴ የፈርኦንን "ብዙ ገንዘብ" ጥሎለት ወደ "ድህነት" መንደር የኮበለለው "መደህየትም" ሆነ "መበልጠግ" በአምላካችን ዘንድ የተፈቀደ መሆኑን ስለተረዳ እንደሆነ ስንቶች ይሆን የሚገነዘቡት። ቆይ፤ አንድ አማኝ በእውነት ክርስቶስን እየመሰለ ሊኖር ወዶ በድህነት ውስጥ ቢያልፍ እንዴት ነው እንደ ተረገመ እና በአጋንንት ቁጥጥር ስር እንደሆነ የምንቆጥረው? እኛ እየመረጥን የማንበብ ፍላጎታችን ስለሚጫነን ነው እንጂ እኮ፤ "ሁሉን እያጡ መከራ እየተቀበሉ በተራራና በሸለቆ ዞሩ ዓለም አልተገባቸውምና" እያለ "ምሳሌነታቸውን" እንድንከትል የሚወተውት መፅሐፍ ነው በእጃችን ያለው።

በድህነት የኖረውን ሁሉ አጋንንት እንደቆጣጠረው ካሰብን፤ ሐዋርያው ጳውሎስን አጋንንት ሲጫወትበት ነበር ማለት ነው? ኢየሱስም በድህነት ኖሯልና አጋንንት ተቆጣጥረውት ነበር እያልን ይሆን? ቆይ ይህ "ድህነት ከአጋንንት ነው" ይሉት ጭፍን ፈሊጥ ምን ማለት ይሆን? ደግሞስ "ደሃ ከአጋንንት አይደለም ድህነት ከአጋንንት ነው" ማለት ምን ይሉት ማጭበርበር ነው? "ደሃው" ላይ ድህነት ካለ፤ "ድህነቱ" ላይ ደግሞ "አጋንንት" ካለ "ድህነቱ ላይ ያለው አጋንንት ደሃው ላይ ሆነ ማለትም አይደል? ስለዚህ ደሃው በአጋንንት ቁጥጥር ስር ወደቀ ማለታችን አይደል? ስለዚህ በዚህ አካሄድ ካየነው "ደሃ ከአጋንንት ነው" ሆነ ማለት እኮ ነው።

ለማንኛውም፤ ዋናው ነገር ምንድነው? ዋናው፤ ክርስቶስን ማወቅና መከተል ነው። እርሱን ስንከተል በወደደው መስክ ያሰማራናል። ለዘለዓለም ፍሬ በምናፈራበት መንገድ ይመራናል። ዘለዓለማዊ ፈቃዱን ይገልጥልናል። ያንጊዜ ህይወት ማግኘትና ማጣት ሳይሆን የእግዚአብሔርን አጀንዳ አገልግሎ ማለፍ እንደሆነ ፍንትው ይልልናል። የእኛም አላማ እርሱን ማስደሰትና ማክበር ብቻ ይሆናል። እርሱ ሰላማችን ነውና። ይሄኔ ብልጥግናና ድህነት፣ ማግኘትና ማጣት፣ ከፍታና ዝቅታ፣ ውርደትና ክብር የሰርክ ህይወታችን ክፍል ይሆናሉ። እግዚአብሔርም ይከብራል!!

መቼም:~ የተሰደበ፣ የተዋረደ፣ በድህነት የኖረ ጌታ እየተከተልን፤ የተከበረ፣ የሚጨበጨብለት፣ በቁስ የተንቆጠቆጠ "ክርስቲያን" ለመሆን እንደመሻት ያለ "እብደት" አይኖርም።

በበኩሌ "መበልጠግን" በጥቅሉ ከጌታ "መደኸየትን" በጥቅሉ ከአጋንንት አድርጎ ማሰብ በራሱ ከአጋንንት ነው ብዬ ነው የማምነው። እኛ "ድህነትንም ብልጥግናንም" ለመስበክ አልተጠራንም መልዕክታችን የተሰቀለው "ክርስቶስ" ነውና።

“እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን” (1ኛ ቆሮ 1፥23)

ቴዎድሮስ ተጫን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

Gold Mafia 1
https://www.youtube.com/watch?v=evWEuVR1XIs

Gold Mafia 2
https://www.youtube.com/watch?v=HYIcCoYt9YE

Gold Mafia 3
https://www.youtube.com/watch?v=xP_rhbJHokw

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

“ይቅር በለን፤ ... ይቅር እንደምንል” https://youtu.be/Y-k8mZ8h1WY
.
ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ኅብረት ኀጢአት ያበላሸዋል። ኹላችንም በደለኞች ነን። እግዚአብሔር ምሕረት ካላደረገለት በስተቀር ወደ እርሱ መቅረብ የሚችል ማንም የለም። “ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል? በቅድስናውስ ስፍራ ማን ይቆማል?” (መዝ. 24፥3)፤ እንዲሁም፥ ከመዓርግ መዝሙራት መካከል በአንዱ እንዲህ እናነባለን፤ “አቤቱ፥ ኀጢአትንስ ብትጠባበቅ፥ አቤቱ፥ ማን ይቆማል? ይቅርታ ከአንተ ዘንድ ነውና” (130፥3-4)።
.
ይቅር ማለትና ይቅርታ መለመን የዕለት እንጀራችንን ያህል ለመኖር የሚያስፈልገን ነገር ነው። ሰው በበደሉ የታሰረ ባለ ዕዳ ፍጡር ነው። ዕዳውን ልክፈለው ቢል፥ ሕይወቱም አይበቃው፤ የኀጢአት ደመወዝ ሞት ነውና። ሰው ምሕረት ያስፈልገዋል። እግዚአብሔርም፥ ወደ እርሱ በንስሓ ለሚመለሱ ምሕረት አድራጊ ነው። “በደላችንን ይቅር በለን” ብለን የምንጸልየው ለዚያ ነው።
.
ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረት ስንጠይቅ ታዲያ እኛም ሌሎችን ይቅር በማለት እንዲኾን የጌታችን ጸሎት ቀጣይ ክፍል ይህን አጽንዖት ይሰጣል። ተማጽኖው እንዲህ ነው የሚለው፤ “እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል፥ በደላችንን ይቅር በለን” …

.
ምሕረት በዋናነት አጽንዖት ሰጥቶ የሚያውጀው የእኛን የተቀባይነት ዋጋ ሳይኾን የክርስቶስ ኢየሱስን ግርማዊ ክብር ዋጋ ነው። እግዚአብሔር ኀጢአተኛውን በምሕረቱ ይቅር በሚልበት ጊዜ፥ የክርስቶስን የመልካም ሥራ ትሩፋት በሰማያት ሰሌዳ ላይ ይጽፈዋል እንደ ማለት ነው። እኛንም ከአሸናፊው የእግዚአብሔር በግ ጀርባ አሰልፎ በድል ነሺነት ይመራናል። … (ሙሉውን ለማዳመጥ https://youtu.be/Y-k8mZ8h1WY

ሰሎሞን አበበ ገብረ መድኅን (መጋቢ)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የእኔነት አባዜ፣ የግለኝነት ስካር!

የዚህ ዘመን የቤተክርስቲያን አንዱ ምናልባትም ዋነኛው ተግዳሮት እኔነት ሳይሆን አይቀርም፡፡ እጅ ለእጅ ተያይዞ ማገልገል፣ ተከባብሮ መንግሥቱን ማስፋት፣ አንተ ትብስ የሚል መንፈስ ጨርሶ እየጠፋ ይመስላል፡፡ ባመዛኙ በቤተክረስቲያን መካከል ያለ ክፍፍልም ምንጩ ይኸው ነው፡፡ እኔነት አዙሪቱ ከባድ ነው፡፡ እኔነት ራስን የማንገሥ ሩጫ ነው፡፡ እኔነት ዙሩ ሲከርር “ከእኔ በቀር!” ያሰኛል፤ ይህ ደግሞ አንጋጦ ከመትፋት አይተናነስም፡፡ “ከእኔ በቀር” ሊል የተገባው አንዱ አንድዬ ብቻ ነውና፡፡

ለእኛ “እኔነት” ከፍጥረታችንም ጋር እንኳ አይገጥምም፡፡ ስሪታችን በእኔነት ክንፍ ለብቻ ለመክነፍ የሚያበቃ አይደለም፡፡ አንዳችን ያለሌላችን ምንም ነን፡፡ የቤተክርስቲያን ክብር ደግሞ በአብሮነት ውስጥ የሚገለጥ ልምላሜ ነው፡፡ ማንም ብንሆን ለብቻችን ምንም ነን፡፡ ለዚህ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ምንነታችንን በአካል መስሎ የሚያስተምረን፡፡ ከአካል ክፍሎች አንዱ የጎደለ እንደሁ፣ በሙሉነት መድመቅ አይቻልም፡፡ ያው “ጎዶሎ” የሚል ተቀጥላ ያስከትላል፡፡

ብቻ የመድመቅ አባዜ የሉሲፈር መንገድ ነው፡፡ የገነነ እኔነት ውስጥ ትእቢት አሸምቆ አለ፡፡ ዶ/ር ኃይሉ ቸርነት በአንድ ወቅት “ትእቢት በእኔነት ጢም ብሎ መሞላት ነው” ሲል ሰምቼዋለሁ፡፡ እውነት ነው፤ የገነነ እኔነት መጨረሻን ያከፋል፡፡ አብሮት በሚያገለግለው ወንድም ምክንያት በቂ ከበሬታ ያጣ የመሰለው ወንድም፣ “ሁለት ፀሐይ በአንድ ሰማይ ላይ አይደምቅም” በሚል አመክንዮ ከወንድሙ ተለይቶ ብቻውን የሚደምቅበትን የገዛ ቸርቹን ከፍቷል፡፡ (በነገራችን ላይ የአገልግሎት ጥሪ ግብ ራስን ማድመቅ ሳይሆን፣ ራስን መደበቅ ነው፡፡) እዩኝ እዩኝ ማለት የልከኛ መንፈሳዊነት መገለጫ አይደለም፡፡ የአገልግሎቱ እና የጸጋው አሠራር ግብ እርሱን እዩልኝ የማለት ነው፡፡

የዚህ ዘመን የአገልግሎት ዝንባሌ ግን ባመዛኙ ሐዲዱን የሳተ ይመስላል፡፡ የአዲስ ኪዳን ጸሐፍት አብሮነትን በእጅጉ ያበረታታሉ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ በአብዛኞቹ መልእክቶቹ ውስጥ እኔ በማለት ፈንታ “እኔና…” ሲል እናነባለን፡፡ ሰላምታ እንኳ ሲያቀርብ “እኔና አብረውኝ…” ይላል፤ ምን ጸጋ የበዛለት ቢሆን፣ ብቻውን እንዳልቆመ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡

አሁን የእኔነት አባዜ በእጅጉ ገንኖ ይታያል፡፡ እኔነት በአልባሌ ጭብጨባ ይፋፋል፤ ያልተካደ እኔነት የመስቀሉ ጠላት አድርጎ ያቆማል፡፡ የደረስንበት ጥግ እኔነትን የሁሉ መፍትሔ እና መላ አድርጎ እስከማቅረብ የተለጠጠ ነው፡፡ “እኔ እንደሌላው አይነት አይደለሁም” እስከማለት ደፍረናል፡፡

በየግል ቤተክርስቲያኖቻችን እንደነገሥን ለማሳየት በየደጆቻችንን ደማቅ ፎቶዎቻችንን በየአቅጣጫው ሰቅለናል፡፡ በየመርሐግብሮቻችን “ዋነኛው እኔ ነኝ!” ለማለት፣ ከጋበዝናቸው ሰዎች አናት ላይ ደማቅ ፎቶዎቻችንን እናኖራለን፡፡ በአዳራሹ መካከል የተለየ የከበሬታ ወንበር አሰናድተን በእርሱ ላይ እንሰየማለን፤ በሌለን ጊዜ እንኳ ሌላ አይቀመጥበትም፡፡ ክርስቶስ ራስ በሆነለት አካል ውስጥ፣ ከአካሉ ብልቶች መካከል እንደ አንዱ በመሆን ፈንታ፣ ከ“ራሱ” በላይ ጠቃሚ መሆናችንን ለፍፈን በሕዝቡ ላይ ሰልጠነናል፡፡ የመለኮት ሙላት ሁሉ ተጠቅልሎ እጃችን እንደገባ አምነን በእኔነታችን ሰክረናል፡፡ ክርስቶስ በእኛነታችን እንዳይገለጥ እኔነት ትልቁ መጋራጃ ነው፤ ቢያምም የእኔነትን መጋረጃ ገፍፎ መጣል የተገባ ነገር ነው፡፡

ይኸው ሩጫችን ደግሞ መጨረሻ ያለው አይመስልም፡ በየዕለቱም በእኔነት የፋፉ ሰዎች ብቅ ብቅ እያሉ ነው፡፡ በዘመን እላቂ እንደመኖራችን ብዙ ተስፋ ማድረግ ላይኖርብን ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን ደግሞ ልኩ ይኸው መስሏቸው በቅንነት እና ባለማወቅ በዚህ መንገድ የተጠመዱትን ማዳን ይቻል እንደሆን እውነትን እንናገራለን፡፡ ከገነነ እኔነት መዳን ከብዙ ነገር መዳን ነው፡፡ የእኔነት ስካር ወስዶ ወስዶ የት እንደሚደፋ አይታወቅም፡፡ ከእኔነት መዳን ሌለውን በልኩ ለማየት እና ንጉሡን በእውነት ለማላቅ ዕድል ይሰጣል፡፡

ሕዝብ ሁሉ ግርርርር ብሎ ይከተለው የነበረው መጥምቁ ዮሐንስ በጮክታ “እኔ አይደለሁም!” ብሎ ወደ መሲሁ እጁን ጠቁሟል፡፡ ይህ አይነተኛው ማምለጫ ነው፡፡

“እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል።” ዮሐ 3፡30

ስንታየሁ በቀለ (መጋቢ)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

"የዕለት አንጀራችንን ዛሬ ስጠን"
https://youtu.be/onMHZmJTRpk
.
ለምን የዕለት እንጀራ ኾነ? በሌላ አባባል ለምን የዕለት ብቻ? ለዕድሜ ዘመናችንን የሚበቃውን ኹሉ አንዴ ቢዘረግፍልን ምናለበት? ወይም ለምን የ10 ዓመት ዕቅዳችንን የሚሸፍን እንጀራ አንጠይቅም? የ50 ዓመቱን ብንለምነውስ? የሰማኒያውንስ ቢኾን? እርሱ እንደ ኾነ ኹሉ የተረፈው ነው፤ ምን አለበት የዳቦ ተራራ ቢሰጠን?

የዕለት እንጀራችንን እንዲሰጠን እግዚአብሔርን መለመን ያለብን ለምንድን ነው? እኛ የሕይወታችን ባለቤት አይደለንም። የህልውናችን ምንጭ እግዚአብሔር ስለ ኾነ ራሳችንን አላስገኘንም። ሕይወት የእግዚአብሔር ስጦታ ናት፤ የግል ርስታችን አይደለችም። “የሕያዋን ኹሉ ነፍስ፥ የሰውም ኹሉ መንፈስ በእጁ ናት[ና]” (ኢዮ 12፥10)፥ ለመገኘታችን ሌላ ሰበብ አልነበረም፤ የለምም። ከእርሱና በእርሱ ተገኝተናል፤ ወደ እርሱም እንመለሳለን። በፍጥረትም ኾነ በድኅነት የተቀበልነው ሕይወት ምንጭ ሕያው አምላክ ነው።

ሕይወታችን የምታሣሣ ችግኝ ነች። እግዚአብሔር ራሱ ከሕይወት ውሃ ካላጠጣን ለዘላለሙ ደርቀናል። እርሱ ጥላ ከለላ ካልኾነልን ላለመለምለም ጠውልገናል። እርሱ ካላቆመን ላለመነሣት ወድቀናል። እርሱ ካልሰበሰበን ለዘላለሙ ተበትነናል። …

የዘላለም ሕይወት የሰጠን አምላክ ምድራዊ እንጀራም ይሰጠናል። በሰብአዊ ኀይል፥ በቍሳቍስና በምድራዊ ባለጠግነት ሕይወታችንን አናጸናውም። ዕውቀትና ጥበባችን አልፈጠረንምና ገንዘባችን ሕይወት አልሰጠንምና የራሳችን አይደለንም። የሕይወታችን ባለቤት የፈጠረን አምላክ ነው። የሕይወታችን ባለቤትና ጌታ እግዚአብሔር ራሱ ነው። ያስብልናል። …

እግዚአብሔር የሕይወታችን ባለቤት ብቻም ሳይኾን መጋቢና ጠባቂዋ ነው። አንጡራ ሀብታችን፥ ገንዘባችንና ቍሳቍሳችን አሳዳሪዎቻችን አይደሉም። በዘላለም ሕይወት ዋስትናም አያኖሩንም። ዋስትናችን መግቦቱ ነው።

እውነተኛ አማኝነት በእግዚአብሔር ላይ የተደገፈ ሕይወት ነው። ከገበታችን ላይ በቀረበልን የዕለት ምግባችን ጀርባ የተወሳሰበ ምጋቤ ሀብታዊ የምግብ ሰንሰለት አለ። ከመጨነቅ ይልቅ በእግዚአብሔር ላይ ያለ ቋሚ መታመን ዋስትና ያስገኝልናል። ዲትሪክ ቦኖፈር “ክርስትያን መጨነቅ እንደማይችል እና እንደማይደፍር ብቻ ሳይኾን መጨነቅ እንደማያስፈልገውም ያውቃል። የዕለት እንጀራውን የሚያገኘው በመጨነቁ ወይም በመሥራቱ አይደለም፤ ምክንያቱም እንጀራ የአባት ስጦታ ነውና።” …
.
ሙሉውን ለማግኘት፦ https://youtu.be/onMHZmJTRpk

ሰሎሞን አበበ ገብረ መድኅን (መጋቢ)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የምትችሉ ወገኖች እንድትታደሙ ትጋበዛላችሁ!

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ቅይጣዊነት #4

"ቅይጣዊነት" በሚለው መሪ ርዕስ ስር ከማቀርበው ተከታታይ ልጥፍ መካከል አንድ የመጨረሻ ልጥፍ ይቀረናል። እንዳላሰለቸኋችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። ዓላማዬ "ቅይጣዊነት" የደቀነብንን አደጋ በጥቂቱም ቢሆን ለማመላከት፤ ለመፍትሄውም "ስለ ወንጌል ያገባኛል!" የምንል ሁሉ በጋራ እንድንቆም እንደ ታናሽ ወንድም ጥሪ ለማቅረብ ነው።

ወገኖች "ቅይጣዊነት" የወንጌላዊያኑ አሁናዊ አደጋ ነው። የከፋ ያደረገው ደግሞ የቀያጮቹ ሁኔታ ነው። በቀዳሚው ልጥፍ ቀያጮቹ ሁለት ዓይነት እንደሆኑና የመጀመሪያው ዓይነቶቹ ቀያጮች እኛ የምንወዳቸው በተለያየ የአመራር እና አገልግሎት የተሰማሩ በርቱዕ አስተምህሮ ጉዳይ የማንጠረጥራቸው ነገር ግን በሃሳዊያኑ ወይም በመሀል ሰፋሪዎቹ መድረክ የሚገኙ አገልጋዮች ናቸው። እኒህ አገልጋዮች "ለቅይጣዊነት" ያላቸው ሚና የትየለሌ እንደሆነ እንዲሁም በሃሳዊያን መድረክ ለመገኘታቸው የሚያቀርቡትም ሎጂክ የከሸፈ እንደሆነ በቀዳሚው ልጥፍ ተመልክተናል።

ዛሬ ሁለተኛ ብዬ የማስባቸውን ቀያጮች እንመልከት። እኒህ ዓይነቶቹ ሃሳዊያኑ በግልፅ የሚያስተምሯቸውን ዋና ዋና ትምህርቶች በፊት ለፊት አያንፀባርቁም። ነገር ግን ከሃሳዊያኑ ጋር እጅና ጓንት ሆነው ይሰራሉ። ደግሞም ሃሳዊያኑ ቅቡልነት እንዲያገኙ በየመድረኩ እና ውስጥ ለውስጥ "ሎቢ" በማድረግ ይተጋሉ። እነኚህ መሃል ሰፋሪዎች ናቸው። ሁለቱም ጋር ለመገኘት የሚወዱ ወሃና ዘይት ለመቀየጥ የሚጨነቁ ናቸው። እነማን ናቸው?

ቀያጩ ቶማስ

ከመሀል ሰፋሪ ቀያጮች መካከል ቀዳሚው ቶማስ ምትኩ ነው። ቶማስን መጀመሪያ ያየሁት በዘጠናዎቹ መጀመሪያ ጥቁር አንበሳ አካባቢ ዊነርስ ቻፕል በተከራየው የእርሻ ሰብል አዳራሽ ነበር። መርሃ ግብሩን የሚያካሂደው ቅዳሜ ቀን ነበር። የተወሰኑትን ተካፍያለሁ። ይህንን የቃል እምነት ስሁት ትምህርት ታዳሚውን ይግተው ነበር። የተቋሙንም ስም የእምነት ሰራዊት እያለ ነበር የሚጠራው። በእርግጥ ኋላ የመፅሐፍ ቆዱስ ሰራዊት በሚል ቀይሮታል። ቶማስ የእነ ሃገንን የብልጥግና ትምህርት በትጋት ነበር የሚያስተምረው። በተለይ በእምነት መፈወስን ትኩረት ሰጥቶ ነበር የሚያስተምረው።

ምን ዋጋ አለው እርሱ ላይ አልሰራምና ከሸፈበት። ከድህነትና ከበሽታ በላይ ትሆናለህ ባዩ የቃል እምነት ሰባኪና "የእምነት ሰራዊት" መሪው ታመመ። የማይደበቅ ህመም። በእርግጥ በህመም ላይ ምንም አይባልም። በማንም ላይ ሊከሰት ይችላልና። የእርሱን ለየት የሚያደርገው ከሰብከቱ ጋር መጣረሱ ነው።

ለረጅም ጊዜ መራመድ አቅቶት በዊልቸር ለመንቀሳቀስ ተገደደ። ይህ አጋጣሚ እግዚአብሔር በቸርነቱ ትምህርቱን እንዲመረምር የሰጠው ትልቅ ዕድል ነበር። በሚያሳዝን ሁኔታ አልተጠቀመበትም። ቢሆንም ግን ከዚያ በኋላ ያንን ትምህርት እንደ ቀድሞው ለማስተማር አልደፈረም። አቅም አጣ። በቃ ጡረታ ወጣ። ያው መቼም "ጡረተኛ ሚኒስትር አምባሳደር ይሆናል" እንዲሉ፤ ቶማስም ከዚያ ጊዜ በኋላ የቃል እምነት መምህራንን ተንከባክቦ በማሳደግ እና ከነባሩ ወንጌላዊ ክርስትና ጋር ለመቀየጥ በሚደረገው ስራ ላይ ተጠመደ።

አንዳንዶች ቶማስ ተለውጧል ይበሉ እንጂ እርሱ ግን አልተለወጠም። ዛሬም። ምክንያቱም ሃሳዊያኑን በትጋት በመንከባከብ ትምህርቱን ከልቡ እንደሚወደው እያሳየን ነውና። ተለውጧል የሚለውን እንደ ሽፋን እየተጠቀመ ግን የዚያ እኩይ ትምህርት አምባሳደር ሆኖ "ያገለግላል"። እንዲሁም ሃሳዊያኑ በነባር አብያተክርስቲያናት ውስጥ ባሉ "ተሰሚ አባቶች" ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኙ የዲፕሎማሲ ስራ ይሰራል።

የሃሳዊያኑ ሰብሳቢ "አባት" በመሆንም ሲጣሉ ያስታርቃል። ተሰደው ሲጠፉ ይመልሳል (ጃፒን ከአሜሪካ እንደመለሰውና ከአባላቱ ጋር እንዳስታረቀው ማለት ነው)። ብቻ ለሃሳዊያኑ መንገድ መንገዱን ያሳያቸዋል! ያግዛቸዋል! አዳራሽ ከፈለጉም ይሰጣቸዋል። የሚያሳዝነው ግን ይኸው ሰው "ጤነኛ ናቸው" በምንላቸው መድረኮችም ላይ "የእግዚአብሔር ሰው ቶማስ" ተብሎ ይቆማል። "ቅይጣዋዊነት!" ስለዚህ ቶማስ "በቅይጣዊነት" ሂደት ውስጥም ከዋነኞቹ ቀያጮች መካከል አንዱ ነው ማለት ነው።

ቀያጩ ሲንገሌ

ሄኖክ መንግስቱ (ሲንገሌ) ደግሞ ሌላው ነው። የዚህ ሰው አቋም በጊዜ ቅደም ተከተል ሲታይ ከካውንስሉ በፊትና በኋላ በሚል በሁለት ይከፈላል። ከምስረታው በፊት ትምህርቱ ምንም እንኳን ቀልድና ቧልት የበዛበትም ቢሆን ከሃሳዊያን ጋር በግላጭ አይገኝም፤ በአደባባይም የእነርሱ ደጋፊ ሆኖ አይታይም ነበር።

እንዲያውም እዚያች መምህራን ክበብም ሆነ ኢትዮጵያ ሆቴል አዳራሽ በነበረበት ጊዜ ሃሳዊያንን ሲቃወም አልፎ አልፎም ቢሆን ይሰማ ነበር። አዲሱ የኢትዮጵያ መንግስት ከመጣ ካውንስሉም ከተመሠረተ በኋላ ግን በቃ ፈፅሞ ሌላ ሰው፣ የሃሳዊያን ደንበኛ ደጋፊ፣ ተከላካይ፣ ጠበቃ እና ህዝብ ግንኙነት ሆኖ ተገለጠ። በአጭሩ ሃሳዊያንን ከነባሩ ወንጌላዊ ክርስትና ጋር ለመቀየጥ ላይ ታች የሚታትር ቀያጭ ሆነ። ምን እንዳገኘው እንጃ!

እንዲህ አያልን ብንዘረዝር በመሀል ሰፋሪነት ተራ የቆሙና በቀያጭነት የሚሰሩ እንደ ዳዊት ሞላልኝ፣ ታሪኩ ቴዎድሮስ፣ ዮሐንሰ ግርማ (ጆን ዘፀዓት) ከዘማሪዎች ደግሞ አውታሩ ከበደን፣ ተከስተ ጌትነትን፣ እንዳለ ወልደጊዮርጊስን፣ መስፍን ጉቱን ከወጣቶቹ ደግሞ እነ ይሰሃቅ ሰዲቅን ወዘተ ወዘተ ማንሳት ይቻላል።

እና ምን ለማለት ነው? ሃሳዊያኑ፤ ወዲህ "ጤነኛ" የምንላቸውን አገልጋዮች አሊያም መሀል ሰፋሪዎችን ሲችሉ በገንዘባቸው ካልሆነ በአታላይ አካሄዳቸው እየጠለፉ ራሳቸውን ከነባሩ ወንጌላዊ ክርስትና ጋር ለመቀየጥ እየተጠቀሙባቸው ይገኛሉ።

ስለዚህ ቅይጣዊነትን ማውገዝ "የቃል እምነት" ስሁት ትምህርቶችን የመስፋፋት ፍጥነት ለመከላከል አይነተኛ መንገድ ነውና፤ የቤተክርስቲያን መሪዎች እንዲሁም ለንፁህ ወንጌል ግድ የሚለን ሁሉ በአንድነት ቅይጣዊነትን ልናወግዝ ይገባናል እላለሁ። ታናሽ ወንድማችሁ።

ቅይጣዊነትን እንፀየፋት!!!

ቴዎድሮስ ተጫን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ኀጢአትን ይቅር የማለት ጉዳይ! (ዮሐ. 20፥23)


ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ፣ ለደቀ መዛሙርቱ ከሰጣቸው ሥልጣን መካከል አንዱ፣ “ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል” (ዮሐ. 20፥23) የሚል ነው፤ ብዙዎች የዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ዓውዳዊ ትርጕም ለሌላ ነገር ሲጠቀሙበት ብንመለከትም፣ በቀጥታ ሲተረጐም የሚሰጠን ትርጕም ግን፣ “እናንተ ኀጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ኀጢአታቸው ይቅር ተብሎአል፤ ያላላችኋቸው ግን ይቅር አልተባለም” የሚል ነው።

ይህ የሚያመለክተው ቅዱሳን ሐዋርያት በቀጥታ ይቅር የማለትና ያለማለት ሥልጣን እንዳላቸው የሚያመለክት አይደለም፤ ነገር ግን ሥልጣኑ ከእነርሱ የሚመነጭ ሳይኾን ወይም ደግሞ እግዚአብሔር የሐዋርያትን ወይም የአማኞችን ይቅር ማለት ተከትሎ ይቅር ይላል፣ ይቅር ሳይሉ ሲቀሩ ይቅርታ ይነፍጋል ማለት ሳይኾን፣ ወንጌልን በእውነትና በጽድቅ የሚመሰክሩ ኹሉ፣ ኀጢአትን ይቅር የማለትና ያለማለት ሥልጣን እንዳላቸው የሚያመለክት ነው።

ይኸውም፣ ሰዎች አንድ ሐዋርያ ወይም አማኝ የሚነግራቸውን ቅዱስ ወንጌል ሰምተው ቢያምኑና መታዘዝ ቢጀምሩ ኀጢአታቸው ይቅር ይባላል፤ ነገር ግን የሰሙትን ወንጌል ባያምኑና ባይታዘዙ ኀጢአታቸው ፈጽሞ ይቅር አይባልላቸውም ማለት ነው። ምክንያቱም፣ “በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ያላመነ አሁን ተፈርዶበታልና።” (ዮሐ. 3፥18)። ይህም የኀጢአት ይቅርታና ፍርድ የሚያገኘን፣ ክርስቶስን በማመንና ባለማመን የሚመጣ እንጂ ክርስቶስ የሰዎችን ኃጢአት ይቅር እንዲሉ ወይም እንዳይሉ ፍጹም ሥልጣን እንደ ሰጣቸው አያመለክትም።

ሐዋርያት ወንጌልን ለመላው ፍጥረት ሲያውጁ፣ የይቅርታና የፍርድ አዋጅን ነው የሚያውጁት። ይህን የማወጅ ሥልጣንን የሰጣቸው ጌታችን ኢየሱስ ነው። ይህን የወንጌል አዋጅ ለሚሰማና ለሚታዘዝ ኹሉ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚሰጥ ይቅርታ አለ፤ በማያምን ኹሉ ላይ ግን ኀጢአቱ በእርሱ ላይ አለ፤ በእግዚአብሔር ልጅ አለማመን ሕይወትን አለማየት ነውና (ዮሐ. 3፥36) የደቀ መዛሙርት ትልቁ ሥልጣን፣ ይቅርታው የሚገኝበትን የመዳን ወንጌል ለሰዎች ኹሉ ማወጅ ነው፤ የኀጢአትን ይቅርታ የሚሰጠው ደግሞ አንዱ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ (ማር. 2፥7)።

እንግዲህ እንዲህ ማለት እንችላለን፤ ሰዎች በክርስቶስ ካላመኑ፥ ይቅርታን እንዳላገኙ ለማወጅ ሥልጣን አለን፤ ከዚህ ውጭ ግን በጌታችን ኢየሱስ በማመን ለኀጢአቱ ሥርየት ይኾን ዘንድ፣ የመዳን ንስሐ ያልገባውን ሰው ትድናለህ፣ በጌታችን ኢየሱስ አምኖ ንስሐ የገባውን ሰው አትድንም እንል ዘንድ አንችልም። “ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኃጢአት ሊያስተሰርይ የሚችል ሌላ የለም” ስንልም፣ እኛ በመዳን ወንጌል ላይ ቆመን፣ ሰዎች በክርስቶስ እንዲያምኑ የመዳንን ወንጌል ማወጅና በደስታ ሲቀበሉ እንደሚድኑ የተስፋውን ቃል መናገር፣ ብሎም ደግሞ አልቀበልም ሲሉና ሲክዱ ወይም ሲገፉ ግን ይቅርታን እንደማያገኙና ሕይወትን እንደማያዩ ልናስጠነቀቅ ተጠርተናል።

በኢየሱስ በማመን የዘላለም ሕይወት አለ፤ የኀጢአት ይቅርታም ይገኛል፤ በማያምኑና ኢየሱስንና የመስቀል የማዳን መንገዱን በሚገፉ ላይ ግን ኀጢአታቸው ተይዞባቸዋል፤ የኀጢአት ይቅርታም አያገኙም። ከዚህ በዘለለ የኀጢአት ይቅርታ በማናቸውም ሌላ መንገድ አይገኝም! የለምም!

“በማያቋርጥ ፍቅር ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለሚወዱ ሁሉ ጸጋ ይሁንላቸው።” (ኤፌ. 6፥24)

ዲያቆን አቤኔዜር ተክሉ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ቅይጣዊነት #1

“የቃል እምነት እንቅስቃሴ” አስተምህሮ የወንጌላዊያን አብያተክርስቲያንናት ዋነኛ ተግዳሮት የመሆኑ ጉዳይ የተገለጠ ሆኗል። ይህንን ስሁት ትምህርት ለመቋቋም የሚደረገው ትንቅንቅ ላይ ከባድ እንቅፋት ሆኖ እየመጣ ያለው “ቅይጣዊነት” የሚባለው ፈተና ነው።

ትርጓሜ

በእኔ አረዳድ ቅይጣዊነት ማለት በሃሰተኛ እና በእውነተኛ ትምህርቶች መካከል ያለው ግልፅ መስመር ሲጠፋ የሚፈጠረው “ብዥ ያለ መልክ” ማለት ነው። “ቅይጣዊነት” ስንል አንድ “እውነተኛ” የተባለ አገልጋይ አንድ “ሃሰተኛ” የተባለ አገልጋይ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ተገኝቶ “ቡራኬ” ሲያቀርብ ወይም አብረን “የእግዚአብሔርን ስራ እየሰራን ነው” የሚል አንድምታ ያለው ንግግር ሲያቀርብ፥ አልፎም ያንን “ሃሰተኛ ነው!” ተብሎ በብዙዎች ዘንድ የሚታሰበውን ሰው “የእግዚአብሔር ሰው ነው፥ የተቀባ ነው፥ የተጠራ ነው” ወዘተ እያለ ሲያንቆለጳጵሰው የሚፈጠረው “ዝብርቅርቅ” ያለ "የክርስትና መልክ" ማለት ነው።

ቅይጣዊነት ፅዩፍ ናት!

መፅሐፍ ቅዱሳችንም እውነተኛውን አስተምህሮ ከሃሳዊው ለመጠበቅ (ለመለየት) ሊደረግ የሚገባው ጥንቃቄ የት ድረስ ሊሆን እንደሚገባው ለማሳየት፤ ሀሰት የሚያስተምረውን ሰው “ሰላም አትበሉት በቤታችሁም አትቀበሉት” ብሎ ነው ያዘዘው። በሀሰኛውና በአውነተኛው ወንጌል መካከል ቅይጣዊነት "ፅዩፍ" ስለሆነች ነው።

የወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረትም በሰላሳ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔው ባወጣው መግለጫም ላይ በሃሰተኛው እና በእውነተኛው ወንጌል መካከል በጣም ግልፅ የሆነ መስመር አስምሮ ቅይጣዊነትን እንደተፀየፋት ነግሮን ነበር። በመግለጫውም “የቃል እምነት” ስሁት አስተምህሮ ምን ምን እንደሆነ ነቅሶ አውጥቶ ዉጉዝ ከመ አርዮስ እንዳለውም እናስታውሳለን።

ይህ የህብረቱ አቋም “የቃል እምነት” የተባለው ትምህርት በህብረቱ አባል አብያተክርስቲያናት ዘንድ ይፋዊ ቅቡልነት እንደሌለው ማሳያ ሆኖ ሊወሰድም ያስችላል። በዚህ ረገድ ካየነው ህብረቱ በሃሰትና በእውነት መካከል በግልፅ የሚታይ መስመር እንዲኖር የሰራው ስራ ትልቅ ነው።

ወቅታዊ አቋም

ወቅታዊውን የወንጌላዊያን መንፈሳዊ አቋም ስንገመግመው በርከት ያለው “ወንጌላዊ ነኝ” የሚለው ማህበረስብ በመሪዎቹ ላይ የተንጠለጠለ ክርስቲያናዊ ህይወት ነው ያለው። ይህንን ለማወቅ መቼም ለየት ያለ ጥናት አይፈልግም። በግል መፅሐፍ ቅዱስን በማጥናትና በመፀለይ የሚተጋው ጥቂቱ ነው። የብዙሃኑ ህይወት የተመሰረተው ከመድረክ በሚቀርብ ስብከትና ከዝማሬ በሚገኝ ግጥምና ዜማ ላይ ነው። እንደ ቤሪያ ሰዎች “እንዲህ ይሆንን?” እያለ የተሰበከውን እና የተዘመረውን በቤቱ ቁጭ ብሎ የሚመረምረው ጥቂት ነው።

ብዙሃኑም የቃሉ ማንፀሪያ ስለሌለው እውነትን ሲለካ በአገልጋይ ላይ ተንጠላጥሎ ነው። “እገሌ የተባለው ሰባኪ ወይም ዘማሪ እነ እገሌ ቸርች ከተገኘ ያ ቸርች ጤነኛ ነው ማለት ነው” የሚል ዓይነት መስረሪያ ነው የሚከተለው። ይህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ከአንዳንድ ቀደምት እና ቅቡል አገልጋዮች ቸልተኝነት ጋር ሲዳመር “ቅይጣዊነት” በወንጌላዊያን መካከል እንዲንሰራፋ ትልቅ መደላድል ፈጥሯል።

ጥቂት ማሳያ

ለምሳሌ ብንወስድ ፓስተር ጻድቁ የህብረቱ ፕሬዘዳንት ናቸው። ሃሳዊያንንም በግልፅ በመቃወም ይታወቃሉ። ህብረቱ በሰላሳ ሁለኛው መደበኛ ጉባዔው በሃሳዊያኑ ላይ ላወጣው መግለጫ የእርሳቸው ሚና ቀላል እንደማይሆን ይገመታል። እኒህ አባት ቀንደኛ ሃሳዊ በሆነው ዮናታን አዳራሽ ተገኝተው “ቡራኬ” ሲያቀርቡ ብታይ፤ “ቅይጣዊነት” ምን ያህል እተስፋፋ እንደሆነ ማወቅ ትችላለህ። ዮናታን ደግሞ ጃፒን “የእግዚአብሔር ሰው” እያለ ሲያሞካሸው ጨምረህ አስበው። ባናቱ ደግሞ ይኸው ዮናታን ከኤልሳዳይ አበራ ጋር ደቡብ አፍሪካ ላይ "እንድ ነን" ዓይነት ሲዘምር ደምርበት። ቅይጣዊነት!

ወዲህ ደግሞ ፓስተር ታሪኩ ቴዎድሮስን ሙሉ ወንጌል መድረክ ላይ ሲሰብክ አይተኸው፤ የመድረኩም ባለቤቶች “የጌታ ባሪያ ነው!” ብለው ሲመሰክሩለት ሰምተህ፤ በሳምንቱ ይኸው ሰው (ፓሰተር ታሪኩ) ጃፒ መድረክ ላይ ቆሞ “ጃፒ የተቀባ ነው” ሲልህ እና ጩፋ ከደሃ ለቅሞ የገዛው የሃያ አራት ሚሊየን ብር ስክሪን ስር ቆሞ “ጩፋ አንደኛ” ሲል ብትሰማውስ? “ቅይጣዊነት” በሀገራችን ላይ ረበበች ማለት አይደል?

“እስራኤል ዳንሳ፥ እዩ ጩፋ ወዘተ ሃሰተኛ ናቸው” ብለህ ደምድመህ ስታበቃ፤ ጋሽ በቄ መጥተው “የለም እዩ ሆነ እስራኤል የጌታ አገልጋይ ናቸው” ሲሉህና በየሚዲያው እየቀረቡ ሃሳዊያኑ ቅቡልነት እንዲያገኙ ሌት’ተቀን ሲለፉ ያየሃቸው እኚህኑ ሰው (ጋሽ በቄ) ቀጠና ሁለት መድረክ ላይ “አባታችን ጋሽ በቄ ያገለግሉናል” ተብሎላቸው በጭብጨባ ሲቆሙ ብታይ ምን ትላለህ?

“እድሜውን ሁሉ ሲያስተምር ከኖረው የቃል እምነት ኑፋቄ በይፋ ንሰሃ አልገባም፤ አሁን ደግሞ ደንበኛ የሃሰተኞች አሳላጭ ሆኗል” ብለህ የደመደምኸው ቶማስ ምትኩ፤ ሃሳዊውን ታምራት ታረቀኝን አዳራሽ ሰጥቶ አደልቦ፥ ጃፒና መሰሎቹን “ልጆቼ” እያለ ሲንከበከብ አይተኸው፤ ዘፀዓት ቤተክርስቲያን ደግሞ “ቶሚ አባታችን” ተብሎ ሲሰብክ ብታገኘውስ? “ወንጌላዊያን ናቸው” ከተባሉት መድረኮች መካከል አንድም ሳይቀር ሁሉም ላይ እየዞረ “እየተሞገሰ” ሲያስተምር ብታየውስ?

እንዳለ ወልደጊዮርጊስ የተባለውን ዘማሪ ከተዘራ ጋር “ማን ኦፍ ጋድ” ሲባባል አይተኸው በማግስቱ “ጤነኛ” ነው ያልኸው መድረክ ላይ “እንዳለ የጌታ ባሪያ” ሲባልስ? ዘማሪ ተከስተን ቢኒያም ሁሴን አዳራሽም መሰረተ ክርስቶስም በአንድ ጀምበር ብታገኘው ምን ትላለህ? ቃለ ህይወትና መካነ ኢየሱስ መሪዎች ከዘላለም ጌታቸው ጋር በካውንስሉ ጥላ ስር ሆነው “እጅ ለእጃችን ተያይዘን” እያሉ ሲዘምሩስ? ሄኖክ ሲንገሌስ በክርስቶስ ሳምራ ትጋት በየመድረኩ ሲዞር ብትመለከተውስ?

እና ምን ለማለት ነው?

“ቅይጣዊነት” አደገኛ እና በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ የሚገኝ ወቅታዊ ችግራችን ነውና አፋጣኝ መፍትሔ ያስፈልገዋል ለማለት ነው። ሃሳዊያኑም ከቀደመውና በአንፃራዊነት “ጤነኛ” ከነበረው የወንጌላዊያን መልክ ጋር ራሳቸውን “ለመቀየጥ” በብዙ ትጋትና ባጀት እየሰሩ ነውና።

እስኪ አስቡት አንድ “እውነተኛ” የተባለ አገልጋይ በሃሳዊያን መድረክ ላይ ሲቆም ምን ማለቱ ነው? "ይህን ሃሰዊ የተባለውን ሰው እኔ ተቀብዬዋለሁና እኔን የምትቀበሉኝ ሁሉ ተቀበሉት፥ ወድጅዋለሁና ውደዱት፥ እኔ ጋር እየመጣችሁ የምትማሩ እርሱም ጋር ሂዱና ተማሩ" ማለቱ አይደለምን? ወይም አንዲት “ጤነኛ” የተባለች ቤተክርስቲያን አንድን “ሃሳዌ” በመድረኳ ላይ ስታቆመው ምን ማለቷ ነው? “አባላቶቼ ሆይ እዚህ ሰው አዳራሽ እና እርሱ የሚደግፋቸው ጋር ሁሉ እየሄዳችሁ ተማሩ” ማለቷ አይደለምን?

"ቅይጣዊነት" የቃለ እምነት ስሁት ትምህርቶች ጋር ከምናደርገው ትግል ጎን ለጎን ልንታገለው የሚገባን አሁናዊው ችግራችን ነውና በጊዜ መፍትሔ ያስፈልገዋል!

ቅይጣዊነት ፅዩፍ ናት!

ቴዎድሮስ ተጫን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ዕለተ ዓርብ - ስቅለት፤ ሞት፤ ጨለማ፤ ስርየት

ጌታ፣ "ይህን ጽዋ ከእኔ አርቀው፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይሁን” አለ። ተከዳ፤ ተሸጠ፤ ተተወ፤ በአንድ ወቅት ከፊቱ ይከተለው የነበረውና “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ፤” “በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤” “ሆሣዕና በአርያም!” እያለ ያከበረው ሕዝብ “ይሰቀል!” በማለት አሳልፎ ሰጠው፤ ልብሱን ተገፈፈ፤ የእሾኽ አክሊል ተደፋበት፤ በወንበዴዎች መካከል ተሰቀለ፤ ተሰደበ፤ ተሾፈበት፤ ተጨነቀ፤ ተሠቃየ፤ እንደ ጠቦትም ለዕርድ ተነዳ፤ በሸላቾች ፊት ዝም እንደሚል በግ፣ አፉን አልከፈተም፤ “ኤሎሄ! ኤሎሄ! ላማ ሰበቅታኒ?” እያለ ጮኸ፤ ጨለማ ወረሰው!

መድቀቁና መሠቃየቱ ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር። የመስዋዕቱም በግ፣ ካህንም ሆነና ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ ጫነው። ደዌያችንን ወሰደ፤ ሕመማችንንም ተሸከመ፤ ተሠቃየም፤ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የብዙዎችን ኀጢአት ተሸከመ፤ ስለ ዐመፀኞችም ማለደ። ለአሰቃዮቹ ሁሉ፣ “አባት ሆይ፤ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” በማለት ጣር ውስጥ ማለደ። የፍጥረት ፈጣሪ፣ ተጠማ፤ በታላቅ ድምፅ ጮኾ፤ ነፍሱን ሰጠ፤ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ተቀደደ፤ የዘላለም ቤዛነት ሊያስገኝ የራሱን ደም ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ገባ፤ ድነት ኾነ! በእርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።

ዕለተ ቅዳሜ - መቃብር፤ ታላቅ ዝምታ

አምላክ ወደ መቃብር ወረደ፤ “ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ግን ማዳን አይችልም!” ተባለ። "የታመነበት እግዚአብሔር ትቶታል" ተባለ፤ ስለራሱ የተናገረው ሐስት፣ የሰጠውም ተስፋ መና ነበር ተባለ። በልመና በድኑ ተቀበረ! በትልቅ ድንጋይ የመቃብሩ በር ተዘጋ፤ መቃብሩን በማኅተም አሽገው ጠባቂ አቆሙበት፤ ታሪኩ ተዘጋ፤ ፍርሃት ወደቀ፤ ላመኑበትና ለተከተሉት ጨለማ ኾነ፤ እግዚአብሔር ዝም ያለ፣ ሞትም ለዘላለም የነገሠ መሰለ፤ ተስፋ ሁሉ ተሟጠጠ። ታላቅ ዝምታ ኾነ!

ዕለተ እሁድ - ትንሣኤና ሕያው ተስፋ

እንደ ተናገረው ተነሣ፤ ድንጋዩ ተንከባለለ፤ መቃብሩ ባዶ ኾነ፤ በፈቃዱ ነፍሱን ሰጠ፤ እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አስወግዶ አስነሣው፤ ሞት ይዞ ሊያስቀረው አልቻለምና! ግዛትን፣ ሥልጣንና ኀይልን ሁሉ ደመሰሰ፤ ጨለማው ነጋ! ልቅሶ በደስታ ተለወጠ፤ ፍቅር አሸነፈ፤ ወዳጆቹን ፍለጋ ሄደ። በፍርሃት በተዘጋ ደጅ የለበሩት “ሰላም ለእናንተ ይሁን አለ!” ስብራታቸው ጠግኖ፣ ተስፋቸውንም አድሶ ወደ ዓለም ሁሉ ላካቸው። ከአምላክ ጋር ዕርቅ ሆነ፤ ድነታችን ሙሉ ኾነ፤ ተስፋችንም ዘላለማዊና ሕያው! ያለ ትንሣኤው፣ ክርስቶስ ሰማዕት፣ መልክታችንም ታሪክ ብቻ ነበር የሚሆነው! ሞት በድል ተዋጠ፤ የሞት መንደፊያ ኀጢአት ተወገደ፤ ሰይጣን ተረታ። እንደ ተናገርው ሞተ፤ እንደ ተናገረው ተነሣ፤ እንደ ተናገረው ወደ ሰማይ ዐረገ፤ እንደ ተናገረው መንፈስ ቅዱስን ላከ፤ እንደ ተናገረው እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር አለ፤ እንደ ተናገረው በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ፣ በክብር የመለሳል!

እንደ ግል አማኝ፣ እንደ ቤተ ሰብ፣ እንደ ቤተ ክርስቲያን፣ እንደ አገር የምናልፍባቸው ብዙ የፈተና ወቅቶች አሉ። በእግዚአብሔር የተተውን፣ እርሱም የማያየን፣ ዝም ያለን፣ እንዲሁም ይህቺ ምድር ለክፉዎች ዐልፋ የተሰጠች እስኪመስል ድረስ የፍትሕ ጨኸት የማይሰማበት፣ ክፋት ያሸነፈና ሰይጣን ለዘላለም የነገሠ የሚመስልባቸው የተስፋ መቁረጥ፣ የዝምታና የጨለማ "ዓርቦችና ቅዳሜዎች" አሉ።

ሆኖም፣ "ዓርብና ቅዳሜ" የመጨረሻ ቃሉች አይደሉም! የእኛም ኾነ የመላ ዓለሙ ታሪክ በእነዚህ ሁለት ቀናት በሆኑ ኹነቶች አልተቋጨም። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ተነሥቶአል! ስለዚህ ይቅር መባላችን፣ የዘላለም ሕይወት ማግኘታችን፣ የትንሣኤ ተስፋችን፣ ከአቤል ጀምሮ እስከ አሁን እየፈሰሰ ያለው የንጹሓን ደም ጩኸት ምላሽ ማግኘቱ፤ መከራ መወገዱ፤ እንባ መታበሱ፣ ኀጢአት፣ ሞትና ሰይጣን ለዘላለም መወገዳቸው፣ በመጨረሻም አዲስ ሰማይን አዲስ ምድር የማየታችን ተስፋዎች እውነት ናቸው። እንደ ተናገረው ይመጣል!

“እነዚህን ነገሮች የሚመሰክረው፣ “አዎ፣ ቶሎ እመጣለሁ” ይላል። አሜን፤ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፤ ና። የጌታ የኢየሱስ ጸጋ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር ይሁን፤ አሜን።” (ራእይ 22:20-21)

አሜን!

መልካም የትንሣኤ በዓል!

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ሞቱና ኑሮአችን
———————-

“በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ።” (2ቆሮ. 5:15)

የክርስቶስ የመስቀል ላይ ሞት የተከታዮቹን የወደ ፊት የኑሮ ዓላማና አቅጣጫ ለማስቀየር ነው። ክርስቶስ የሰዎችን ለራስ የመኖር ስግብግብ ዓላማ ለማስቀየር ሞቶአል። “ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ” ይላል።

መኖር ትርጉም የሚኖረው ለክርስቶስ ሲሆን ብቻ ነው። አማኝ ከእንግዲህ ለራሱ የመኖር ዕድል የለውም ቃሉ እንደሚለው ለሞተለት እንጂ።

አንዳንድ አማኞች ጌታ ለኑሮአቸው ዓላማና ግብ ዴንታ ቢስ እንደሆነ ያስባሉ። ከዚህም የተነሳ “ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ” ዓይነት በእኔ ጀምሮ በእኔ የሚያልቅ “እኔ”… “ለእኔ”… “በእኔ”… “ከእኔ”… ሕይወት ይኖራሉ።

ከዚህ የንባብ ክፍል የምንረዳው እውነት ግን “አሁን የምኖረው ሕይወት ለሞተልኝ ነፍሱን መስዋዕት አድርጎ ለሰጠኝ ጌታ እንጂ ለራሴ አይደለም” ወደሚል አቋም ሊያመጣን ነው ክርስቶስ የሞተው የሚለውን ነው።

ክርስትና በግንባር ቀደምነት ራሳችንን አዝለንና አቅፈን … ራሳችንን ተሸክመንና ተንከባክበን… የምንኖረው ሕይወት አይደለም። የሰቀልንበትና የገደልንበት ነውንጂ።

ያለንበት ዘመናዊ ዓለም ለራስ ኖሮ ለራስ መሞትን መርሕ ያደረገ የራስ ዓለም ነው። የዓለማችን የኑሮ ፍልስፍና ግድግዳውም ማገሩም የተዋቀረው በ”ከራስ በላይ ነፋስ” ዓይነት እይታና ልምምድ ነው።

ይህ ዓለማዊነት በአማኙም ኑሮ ላይ ምን ያህል ተጽዕኖ እንዳደረሰ ለማወቅ ጥልቅ ጥናት አያስፈልግም። በአማኙ ማኅበረሰብ ዘንድ የምናስተውለው ሌብነትና ብልሹ አሠራር፣ አለመከባበርና አለመደማመጥ፣ ባጠቃላይ ኢ-ግብረ ገባዊነትና የዘቀጠ የኑሮ ሁኔታ የመስቀሉን ሞት ዓላማ ካለመረዳት የመነጨ ነው።

በቀደሙት የጌታ ተከታዮች ሕይወት “ለራስ መኖር” የሚባል ነገር ጉልህ ችግር አልነበረም። ለጌታ መኖራቸውን የየዕለት ውሳኔያቸው፣ ምርጫቸው፣ እርምጃቸው፣ ንግግራቸው ሁሉ ይናገር ነበር። ድምጹን ከፍ አድርጎ ኑሮአቸው ራሱ ይሰብክ ይዘምር ነበር።

ሐዋርያው ጳውሎስ “ለኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው” ያለበትንና “ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤” ያለበትን ዐውድ የተመለከትን እንደሆነ የምናስተውለው ለራስ መኖር በነሱ ኑሮ ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ ያልነበረው መሆኑን ነው።

“ለእኔ … ለዘሬ… ለወገኔ…” የሚል ኑሮ የመስቀሉን ሞት ዓላማ በውል ያለመረዳት ውጤት ነው። ክርስቶስን ለማስደሰት ጊዜ የማይኖረን፣ ወንጌሉን ለመመስከር ዕድል የማይኖረን፣ ሌሎችን ለማገልገልና ለመርዳት ምቾት የማይኖረን ለምንድነው? ብለን ራሳችንን ብንጠይቅ መልሱ ክርስቶስ የሞተው እኛን ለኛ ከመኖር ሊለየን መሆኑን ያለማስተዋል ነው ብዬ አምናለሁ።

በአሜሪካ ምድር በሚኖሩት ክርስቲያኖች ዘንድ የሚታየው ዓይነት ራስ ተኮርነት የትም የለም ብል እገደል ይሆን? ራሴንም ጨምሮ ስለሆነ ማን ይገድለኛል? በርግጥ ሥልጣኔ መስሎን የተቀበልነው የኑሮ መርሕ ይሆናል ግን ቀስ በቀስ ሁለንተናችንን እየዋጠው መሆኑ አሳዛኝ ታሪክ ነው።

ለራስ የመኖር ችግር ወይም ከራስ ያለመላቀቅ ፈተና of course ዓለም አቀፋዊ ነው። የሰውን ዘር ሁሉ ያለ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ያለ ቀለምና ቋንቋ ልዩነት እያጠቃ ነው። ውለን የምናድረው ለራሳችን ነው። ወጥተን የምንገባውም ለራሳችን ነው። የሚያራውጠን … የሚያጋድለን የራሳችን ጉዳይ ነው።

ክርስቶስ … የክርስቶስ … ለክርስቶስ … የሚባል ነገር ተጥሎአል። ዳሩ ግን ክርስቶስ ለራስ ከመኖር በሽታ ሊፈውሰን ነው መስቀል ላይ የሞተው።

ከወንጌሉ መልዕክት ውስጥ “ራስን መካድ”ን ያስወገደው ጠላት እንጂ ጌታ እርሱን ማመናችንን ራሳችንን ከመካዳችን ጋር አቆራኝቶታል። ይኼው ነው እውነቱ።

ወርቅነህ ኮየራ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ከናዝሬት የሆነው የእስራኤል መሲሕ የዓለም ንጉሥ ሞተ። በሞቱ የመጨረሻ እስትንፋስ ይቅርታን፣ እምነትንና ድነትን ተናገረ። ይህን ድምጽ ግን አሁን ዝም አለ፤ ዕርቅን ያበሰረው ያ የመኸሪ ጌታ ሳንባ መስራት አቆመ፣ መተንፈስ ተወ። ይሄ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞተ።

የሚቅበዘበዘውን መንጋ በብዙ ርህራሄ ተመልክተው ያነቡ አይኖችን ተከደኑ። ምኅረትን ለማይገባቸው ተዘርግተው ያቀፉ እጆች ተዝለፈለፉ። ለምጻሞችን የዳሰሱ መዳፉች ኅልው አልባ ሆኑ። የብዙዎችን ለቅሶ የሰሙ ጆሮዎች ተዘጉ። ኢየሱስ ክርስቶስ ሞተ።

የእግዚአብሔርን መንግሥት ያወጁት አንደበቶቹ ረጭ አሉ። የሚናወጥ ማዕበልና ወጀብ ዝም ያሰኘው ድምጽ ፀጥ አለ። በውሃ ላይ የተራመዱ እግሮቹ መስራት አቆሙ። ኢየሱስ ክርስቶስ ሞተ።

ለኅጥአን የሚደማው ልቡ ስራውን አቆመ። የዓለም ብርሃን በሞት ጥላ ውስጥ ገባ። ወደ እግዚአብሔር መግቢያ በር የሆነው በታተመ መቃብር በር ገባ። የበጎች እረኛ በበጎቹ ተገደለ። ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ተገደለ። ኢየሱስ ክርስቶስ ሞተ።

ወዶኛል፤ ራሱንም ለእኔ አሳልፎ ሰጥቷል። (ገላ. 2፥20)

አማኑኤል አሰግድ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

“ተጨነቀ፤ ተሠቃየም፤ ነገር ግን አፉን አልከፈተም፤ እንደ ጠቦትም ለዕርድ ተነዳ፤ በሸላቾች ፊት ዝም እንደሚል በግ፣ አፉን አልከፈተም" ( ኢሳ. 53:7)።

ለዕርድ እንደሚነዳ በግ፣ ያለምንም ተቃውሞ ለአሰቃዮቹ የጭከና ፈቃድ ራሱን ሙሉ ለሙሉ አሳልፎ በመስጠት፣ ክርስቶስ ስለ ኀጢአታችንና በደላችን በመስቀል ላይ ተቸነከረ። በግ እንኳን መታረድ ሲጀምር ባለው ኀይል ሁሉ ለማምልጥ ይታገላል እንጂ በፈቃድኝነት ራሱ አይሰጥም። ጌታችን ግን በፍጹም መታዘዝ በአንድ ጊዜ ካህንና የመስዋዕት በግ በመሆን፣ በመስቀል ቤዝዎት ሞቱ ከእግዚአብሔርና እርስ በእርስ አስታረቀን።

ሰለበደላችን ደቀቀ፤ ኀጢአታችን ተሸከመ፤ የእግዚአብሔርን ቁጣና ፍርድ ወሰደልን። ልንቀበለው የተገባውን ሞት፣ በሞቱ ወሰደልን። ክብር አጥቶ፣ ኀጢአት የገፈፈንን የእግዚአብሔርን ክብር መለሰለን። በመስቀሉ ላይ የእግዚአብሔር ፍጹም ፍትሕና ፍጹም ምሕረት ተገናኙ። ይህ ሁሉ ስለ እኛ ነው! ቅዱስ ስሙ ለዘላላም የተባረከ ይሁን!

ጌታችን በአካል ብቻ ሳይሆን በክፉ ቃላት ውስጡ ተጐድቷል፤ ተከድቷል፤ ስሙ ጠፍቷል፤ ብቸኛ ሆኗል፤ “ሆሣዕና! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው!" ያለው ያው ሕዝብ፣ ለስቅለት ሞት ዐሳልፎ ሰጥቶታል። ወዳጆቹ ተራ በተራ ሸሽተውታል። ከካህናት ከአለቆችና ከነገሥታት ጀርባ በመሆን፣ ሰይጣን በማንነቱና በመጣበት ዐላማ ላይ የመጨረሻውን የሥነ-ልቦና ጦርነት ዐውጆበታል:-

"ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ግን ማዳን አይችልም! የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ አሁን ከመስቀል ይውረድ፤ እኛም እናምንበታለን። በእግዚአብሔር ታምኖአል፤ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ይል ስለ ነበር እስቲ ከወደደው አሁን ያድነው!” (ማቴ 27:42-43)፣

ይህን ፈታኝ ጥያቄ በፍጹም ትዕግሥትና በዝምታ ያሳለፈው፣ ከፊቱ ያለውን የእግዚአብሔርም ዘላለማዊ የድነት ዐላማ በማሰብ ነበር።

ይህ የሕማም ሰው፣ ስለራሱ ማንነት፣ ስለንጽሕናውና ስለ መብቱ አልተሟገትም። መከራው ሁሉ ኢ-ፍትሐዊ ነበር፤ ሆኖም እኛን ለማዳን እስከ መስቀል ሞት ድረስ የታዘዘ ሆነ። ዝም አለ። በኋላም ዐይኑ የበራለት ጴጥሮስ እንዲህ አለ፦

“እርሱም ኀጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ” (1ጴጥ 2:22-23)።

ያዳነን ዝምታውም ነው -- ያለፍትሕ በትዕግሥት የተቀበለው መከራ! በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር ሳይቆጥር፥ ራሱን በፈቃዱ ባዶ የማድረጉ ጫፍ በፍጹም ዝምታውና ትዕግሥቱ ተገልጧል። የሥላሴ አካል ሆኖ ሳለ ዐቅም እንደሌለው ዝም አለ። ፍጡር ጲላጦስ በአምላክ ላይ ያልተገደበ ስልጣን አንዳለው በማሰብ፣ "ልፈታህ ወይም ልሰቅልህ ሥልጣን እንዳለኝ አታውቅም?" (ዮሐ. 19:10) በማለት ሲናገር፣ አምላክ ዝም አለ! ኢሳይያስም በመገረም “እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው” አለ። ክርስቶስ ባሳለፈው መከራ ውስጥ፣ የመታገሡ ጉልበት ያረፈው፣ “በጽድቅ ለሚፈርደው [ራሱን] አሳልፎ” ለእግዚአብሔር በመስጥት ላይ ነበር። ይህም በእግዚአብሔር ሉዓላዊነት ላይ የነበረውን፣ ፍጹም መደገፍ ያሳየናል።

ይህ የሕማም ሰው፣ ስለ እኛ ድነት ዝምታን መረጠ! እርሱ “የሚስብ ውበት ወይም ግርማ አልነበረውም፤ እንድንወደውም የሚያደርግ መልክ አልነበረውም። በሰዎች የተናቀና የተጠላ፣ የሕማም ሰውና ሥቃይ ያልተለየው ነበር . . . በርግጥ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ፤ ሕመማችንንም ተሸከመ፤ እኛ ግን በእግዚአብሔር እንደ ተመታ . . . ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤. . . በእርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን . . . እግዚአብሔርም፣ የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ ጫነው። ስለ እኛ ተጨነቀ፤ ተሠቃየም፤ ነገር ግን አፉን አልከፈተም፤ እንደ ጠቦትም ለዕርድ ተነዳ፤ በሸላቾች ፊት ዝም እንደሚል በግ፣ አፉን አልከፈተም። በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ኀጢአት ተመቶ . . . ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ . . በአፉ ተንኰል ሳይገኝበት፣ ምንም ወንጀል ሳይሠራ፣ አሟሟቱ ከክፉዎች፣ መቃብሩም ከባለጠጎች ጋር ሆነ . . . የብዙዎችን ኀጢአት ተሸከመ፤ ስለ ዐመፀኞችም ማለደ።" (ኢሳ. 53)

ወሰን የሌለው ፍጹም ፍቅር! ምላሻችን ምን ይሆን? ይህ ፍቅር የተራበ ትውልድ፣ ይህን የክርስቶስ ፍቅር በእኛ ውስጥ ያይ ይሆን?

አቤቱ ቅዱስ አባት ሆይ፤ የመስቀሉ ፍቅር እንደገና ያድሰን።

አሜን!

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የ"ጸሎተ ኀሙስ" አይረሴ ትምህርት

ሰው በመኾን ከአእምሮ በላይ የኾነውን ትሕትና ያሳየው መምህረ ትሕትና ኢየሱስ ክርስቶስ፣ በዚህ ምድር ሰው ኾኖ ሲመላለስ ካስተማራቸው አይረሴ ትምህርቶች አንዱ ትሕትና ነው። ትሕትናን ያስተማረበት መንገድ ደግሞ ከሰው የማስተማር ዘዴ ወጣ ያለና ብዙ ያልተለመደ ነው፤ ትምህርቱን የጀመረው ከንድፈ ሐሳብ ሳይኾን ከተግባር ነውና።

እኔ እበልጥ፥ እኔ እበልጥ ይሉ ለነበሩ ደቀ መዛሙርቱ ትሕትናን ለማስተማር እግራችሁን ልጠብ አለ። የመጀመሪያው የልጠብህ ግብዣ የቀረበለት ጴጥሮስ ግን አይኾንም ብሎ አሻፈረኝ አለ። ካላጠብኹኽ ከእኔ ጋር ዕድል ፈንታ የለኽም ሲለው የግዱን ታጠበ። ሌሎቹም ታጠቡ።

ኢየሱስ የተግባሩን ትምህርት ፈጽሞ ወደ ንድፈ ሐሳቡ ትምህርት ተመለሰ። ተግባራዊ ትምህርቱ ግን በውስጡ የንድፈ ሐሳቡንም ትምህርት ይዞ ነበርና ትሕትና ምን እንደ ኾነ ማብራራት አላስፈለገውም። ከዚያ ይልቅ ርሱ በተግባር ያሳያቸውን ጠለቅ ብለው እንዲያስተውሉት ወደዚያ አቅጣጫ መራቸው፤ "ያደረግኹላችኹን ታስተውላላችኹን?" ሲልም ጠየቃቸው። አክሎም፥ "እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችኹ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችኹ። እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስኾን እግራችኹን ካጠብኹ፥ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችኹ እግራችኹን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል። እኔ ለእናንተ እንዳደረግኹ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለኹና። እውነት እውነት እላችኋለኹ፥ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም። መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም። ይህን ብታውቁ፥ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችኹ።" (ዮሐ. 13፥13-17)።

ኢየሱስ በዚህ ተግባራዊ ትምህርቱ ትሕትናን ያቀረበው ሰው ከሚያስበውና ከለመደው ውጪ ነው። የተለመደው ትሕትና በዕድሜ፣ በዕውቀት፣ በሀብት፣ በሥልጣንና በመሳሰለው ለሚበልጠው ሰው፣ በእነዚህ ነገሮች የሚያንሰው ሰው የሚያሳየው አክብሮት ነው። ኢየሱስ ግን ይህን የተለመደ ትሕትና ገለበጠው። ትሕትና በዕድሜ፣ በዕውቀት፣ በሀብት፣ በሥልጣንና በመሳሰለው የሚያንሱ ለሚበልጧቸው የሚያቀርቡት ሳይኾን፣ የሚበልጡት ለሚያንሷቸው ሊያደርጉት የሚገባ ተግባራዊ ሕይወት መኾኑን አሳየ።

ሰው ለሚበልጠው እንጂ ለሚያንሰው መገዛት ይከብደዋል። ይህን የሚከብደውን ነገር መለማመድና በዚህ አቅጣጫ የጠባይ ለውጥ ማድረግ ግን ከጌታ ደቀ መዛሙርት ይጠበቃል። ኢየሱስም በተግባር ያሳየውና በቃልም የተናገረው ይህንኑ ነው።

ኾኖም ከደቀ መዛሙርቱ የተጠበቀው ትሕትና ጌታ ያሳየውን ያኽል አይደለም፤ ከዚያ መለስ ያለውን ትሕትና ነው እንጂ። ይኸውም ባልተለመደ ኹኔታ የሚበልጡ ለሚያንሷቸው የሚያሳዩትን ትሕትና ሳይኾን፣ በእኩል ደረጃ ላይ ያሉ እርስ በርሳቸው ትሕትናን እንዲያሳዩ ነው። ይህ ጌታ ካሳየው ደረጃው ዝቅ ያለ ቢመስልም፣ አኹንም ከባድ ነው፤ ምክንያቱም ሰው ብዙ ጊዜ የሚወዳደረውና የሚፎካከረው ከእኩያው ጋር ነው። እንደርሱ ላለው ቢጤው ዝቅ ማለት ደግሞ ለዝቅ ባዩ ውርደት መስሎ ስለሚታይ የማይታሰብ ነው። ቢኾንም፥ "እናንተ ደግሞ #እርስ በርሳችሁ# እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል።" አለ (ቍ. 14)።

ሰው መክበርን የሚወድደውንና ለዚያም የሚዋደቀውን ያኽል ዝቅ ማለትን (ትሑት መኾንን) አይፈልግም። ወደ መክበር የሚወስደው መንገድም ራስን ከፍ ማድረግና እዩኝ እዩኝ ማለት እንደ ኾነ ያስባል። አንዳንዱ የእግዚአብሔር መርሕ ግን ከሰው መርሕ ይለያል። መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው፣ ከፍ ማለት ከፈለግኽ ዝቅ በል፤ መክበር ከፈለግኽ ተዋረድ (ትሑት ኹን) የሚል ነው። የኢየሱስም ትምህርት እንዲህ ይላል፤ "ራሱን ከፍ የሚያደርግ ኹሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ኹሉ ከፍ ይላል።" (ማቴ. 23፥12)።

ኢየሱስም ያሳየው ትሕትና ውርደት ቢመስልም የተደመደመው በክብር ነው። መጽሐፍ ሲመሰክር፦ "ርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ኾኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ኾነ። በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ኹሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ኹሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ መላስም ኹሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ኾነ ይመሰክር ዘንድ ነው።" (ፊል. 2፥6-11)።

ትሕትና በቃል እያብራራንና እያስረዳን የምንማረው፥ የምናስተምረውም አይደለም፤ በተግባር የምናሳየው ኑሮ ነው እንጂ። መጽሐፍ ቅዱስም የሚለው ይህን ነው፤ "የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ" (ሮሜ 12፥16)። እንዲሁም "ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥" (1ጴጥ 5፥5)።

እግዚአብሔር ይርዳን!

ዲያቆን አግዛቸው ተፈራ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

እግዚአብሔር ራሱ በፈጠረው አለም ምስኪን ሆኖ ገባ። ኅጢአት ወዳንኮታኮተው አለም የህማም ሰው ሆኖ መጣ። ዐመፃው ላዳሸቀውና በጠና ህማም ለሚያቃስተው የሰው ልጅ እግዚአብሔር ራሱን ቆረሰ። በባለሙያ አሰቃዮች እጅ በመገረፍ፣ በመዘለፍ፣ በመዋረድ እና በመስቀል በመቸንከር የዚህን አለም ውድቀት ግፍ በደስታ ተጎነጨ። ደሙን አፈሰሰ። ስጋውን ቆረሰ። በስቃዮና በፍዳው መኸል በእግዚአብሔርም ተተወ። በውድቀቱ ከእግዚአብሔር ለተለየው ፍጥረት እግዚአብሔር እግዚአብሔርን ከፈለለት። እግዚአብሔር ለአለሙ ራሱን ሰጠለት። ከጠና ሕመሙ ፍጥረቱን ይፈውሰ ዘንድ አንድ ውድ ልጅ ተቸረው። ሰውን ከውድቀት ሸለቆ ያወጣው ዘንድ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠው።

ትዝ ይለኛል ያ መድኅኔ
በመስቀል ላይ የሞተው ስለኔ
ትውስ ይለኛል የመስቀል ፍቅሩ
ያደረገልኝ ውለታው ሁሉ

"ጥቂት የደም ጠብታ መላውን ዓለም ዐደሰው። በወተት ውስጥ ኾኖ ወተትን እንደሚያጣብቀው ፈሳሽ ደሙ የሰውን ዘር አንድ ላይ አያያዘው።" —ጐርጐርዮስ ዘኢንዚናንዙ (ኒዛናዙ)

አማኑኤል አሰግድ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

አንዱ ፍራንክ ሰባኪ ድህነት ከአጋንንት ነው ብሎ ይለፍፋፋል። በሱ አእምሮ እናስብ ካልን ባለጠግነት (ሁሉ) ከእግዚአብሔር ነው ማለቱ ነው። ይህን ዲስኩሩን የሚለፍፈው አንድ ሐሳዊ ተንባይ ግዙፍ ስክሪኑን እዩልኝ ባለበት ወቅት ነው።

በግሌ ሐሳዊው ነባይ ለምን ስክሪን ገጠመ ብዬ አልንጨረጨርም። በሐሰት ትንበያ ስንት ግፍ ሲሠራ የነበረ ሰው፤ በግፍ በሰበሰበው ገንዘብ ያሻውን ማድረግ መብቱ ነው። እዛ ተሰብሰብው ወዮ አጃኢባ እንኳን የእኛ ኾንክ ያሉት ሰዎችም አያስገርሙኝም። ባለ ተመሳሳይ ክንፎች ናቸው፤ አብሮ ከመብረር ውጭ አማራጭ የላቸውም። አጀንዳቸውም ፍራንክ እና ፍራንክ ብቻ ነው። ይመቻቸው😉

ይህን የምጽፈው ድሀነትን ለማንቆለጳጰስም (ድሀነት ምኑ ይንቆለጳጰሳል?) አይደለም። የሸፍጥ እና የአመጻ ገንዘብ በሙሉ ከአጋንንት መኾኑን ለማሥመር እንጂ።

እንደ አገር ካለብን ጥልቅ ደሀነት ለመውጣት ብዙ ትጋትና መፍጨርጨር ይኖርብናል። ባለጠግነት የብርቱ እጆች የሥራ ውጤት እንደኾነ ከአምላክ የለሾቹ (የእኛን አምላክ ከማያመልኩ) ሕዝቦች መረዳት ይቻላል። የዓለምን ኢኮኖሚ የሚዘውሩት ብዙዎቹ ግለሰቦች አምላክ የለሾቹ ናቸው።

ፎጋሪዎቹ ነባያት በሞቅታ እንደሚለፍፋት ጌታ አምላክ የእጆችን ሥራ እየባረከ ትጉኃንን ያበለጥግ ይኾናል እንጂ፤ የሰው ላብ እየነጠቀ በመስጠት ቅዱሳንን አያበለጥግም (ይህንን ያደርግ ዘንድ በቅዱሱ አምላክ ዘንድ ዐመፃ የለም)። እርግጥ ቀማኞቹ ይሉኝታ የለሾቹ ነባያት በሰው ድካም እና ላብ እየበለጠጉ ናቸው። ለሆዳም በሬ ጭድ ያዝለታል ነውና ይመቻቸው😉።

በጌታችን ቅዱስ ወንጌልም ኾነ፣ በሐዋርያቱ ትምህርት ግን ይህ ጉዳይ ዋነኛ የአስተምህሮ ማጠንጠኛ አልነበረም።

ደሀነት ብዙዎች እንዳሉት አጋንንት በኾነና በጌታች ስም አሳሩን ባሳየነው። ድሀነት ዘርፈ ብዙ የኾነ መንስዔ ያለው ክስተት ነው። ሁነኛ ማምለጫው የሚመስለኝም፣ በፈሪሃ እግዚአብሔር ጽድቅ ተላብሶ በሥራ መትጋት ነው። አዎን የትጉህ እጅ መግዛቷ ዘመን አይሽሬ መርህ ነው። ለዚህ ነው ዘማሪው መጋቢ ታምራት ኃይሌ

እስቲ እንጨብጥ እርፍ ማረሻ
ሥራ ነውና የአገር መነሻ
ብሎ የተቀኘው (በነገራችን ላይ እንዲህ ያለ መዝሙር አለን🙏🙏🙏)

እናም ውንብድናችሁ ለራሳችሁ ይሁን!! ለስግብግብ ማንነታችሁ ስትሉ በአመጻ ጡንቻ ፈርጥማችሁ ወደ ፊት አትገስግሱ። በእወጃ እና በእምነት ስም ትውልዱን አታኮላሹ፤ አታበላሹም።

መጋቢ ስንታየሁ በቀለ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

‘ብዙ ተባዙ፤ ኢትዮጵያንም ሙሉአት’

ሐሰተኛው ነቢይ ኡበርት ኤንጅል (Uebert Angel) ከዋናዎቹ ተዋናዮች አንዱ የሆነበትን የሕገ ወጥ የወርቅና የገንዘብ ዝውውር፥ የቆሻሻ ገንዘብ አጠባ (dirty money laundry) ሂደት የአልጀዚራው Investigative journalistቶች የሠሩት የመጨረሻው ክፍል ትናንት ተለቅቋል። የቪድዮዎቹን ሊንኮች ከታች በአስተያየት መጻፊያው አስቀምጣለሁ። ጊዜ ስታገኙ ተመልከቷቸው። በተለይ ክፍል 1 እና 3ን።

እኛ አገርም እንደ እስራኤል ዳንሳ ያሉት አልማዝ ከመድረክ እንዲጠፋ የሚያደርጉት፥ እንደ ኢዩ ጩፋ ያሉት በጥቁር ገበያ ከአሜሪካ ዶላር እንዲላክላቸው የሚያደርጉት፥ ድኅነት እርግማን ነው እያሉ በአሜሪካ ከተሞች እራሳቸውን በግድ አስጠርተው፥ እንደ ፌንጣ ከዚህ እዚያ እየዘለሉ፥ በሕጋዊ መንገድ የወጣና የገባ ገንዘብ ሳያሳውቁ የሚያወጡና የሚያገቡና ሁለት አገር የሚግጡ፥ ገንዘብ ፈጠርን እያሉ (ኢዩ ጩፋና ኢዮብ ጪሮ) የአገር ኢኮኖሚን ለማጋሸብ፥ መንግሥትን ለማናጋትና ሕዝብን ለመመዝበር እጅጌያቸው ሁሌም ወደ ላይ እንደታጠፈ የሚኖሩ ርካሽ ዝነኞች፥ ‘ብዙ ተባዙ፤ ኢትዮጵያንም ሙሉአት’ የተባሉ ይመስላሉ።

ከገንዘብ ጋር የተያያዘው ጉዳይ ከመንግሥት ቆሻሻ ባለ ሥልጣኖች ጋርም የተቆራኘ ነው። እንደዚህ ያለ በአገራችን ገንዘብ አምላክ የሆነበት ዘመን ደግሞ ኖሮ አያውቅም። ይህ ወደፊት በሌሎችም የሚባልበት ጉዳይ ነው።

በወንጌል የሚነግዱት ሐሰተኛ ነቢያትና ሐሰተኛ ሐዋርያት የአሁኑን አካሄዳቸውን ከየት እንደተማሩት፥ እንደኮረጁት፥ እንደሠለጠኑት፥ እንደተለማመዱት ምንም ምስጢር አይደለም። ገና ሲጀምሩ ስንናገርበት የነበረ ጉዳይ ቢሆንም ሰሚ ወይ የለም፤ ወይ ጥቂት ነው። እናም ይህን በቀላሉ አማኝ የሆነ ማኅበረ ሰብ በስለታም ማጭድ እያጨዱ፥ በደረቅ ምላጭ እየላጩ ይገኛሉ።

ማጨዱና መላጨቱ አያበቃም፤ ቆሻሻ ገንዘብ ለጊዜው ማለቂያ የለውም፤ አግበስባሾቹም ደም መጥጠው እንደማይጠግቡ እንደ አልቅት ናቸው፤ አልቅት ደም መጥጠው በደም መሞላታቸውን ስለማያውቁት ፈንድተው እንደሚሞቱ እናውቃለን? በአቋራጭ ለመበልጠግ የሚወድዱ ደግሞ አዕላፋት ናቸው። የውሸት ተስፋው ጽዋም ሞልቶ የተረፈ ነው። ገንዘብ ደግሞ አምላክ የመሆን አቅም ያለው ጣዖት ነው።

ኤንጅል ኡበርትን መጥቀሴ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገራችን ለፈነዳው የሐሰተኞች እሣተ ገሞራ የእርሱና የቡሺሪ እጅ ስላለበትና ይህ ሰው ደግሞ ጥሬ አጭበርባሪና የገንዘብ አጣቢ (money launderer) ስለሆነ ነው። ከአፍሪቃ የነዚህ ከርሳሞች፥ ከምዕራቡ ዓለም ደግሞ የነኮፕላንድና መሰሎቻቸው የቃለ እምነት ሰባኪዎች እንጀራ ልጆች ናቸው እየበዙና እየተባዙ ያሉት።

በሐሰተኛ ነቢያትና በሐሰተኛ ሐዋርያት እንብርት ውስጥ፥ እመካከለኛው ቦታቸው ውስጥ የሚገኙት ሁለት ነገሮች ርካሽ ዝና እና ፍቅረ ንዋይ ናቸው።

እንግዲህ እነዚህ ሁለቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው፤

ይቅርታ! ማለቴ፥ ፍቅረ ንዋይ!

ዘላለም ነኝ።

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

“እርሱ ሊልቅ እኔ ላንስ ይገባል” (ዮሐ. 3፥30)


ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኪደተ እግሩ ተመላልሶ ባስተማረበት ወቅት፣ ስለ ራሱ የሰጠውን ምስክርነት የተቀበሉ ጥቂቶች ናቸው። ምስክርነቱን ያልተቀበሉት እርሱ እውነተኛ ስላልኾነ ሳይኾን፣ ብዙዎች ከኢየሱስ ሕይወትና ትምህርት ይልቅ የጨለማ ሥራን በመምረጣቸው ነው፤ (ዮሐ. 1፥6-11)። መጽሐፍ እንደሚል፣ ኢየሱስን የደኅንነታቸው ምንጭ አድርገው የተቀበሉ ሰዎች፥ እግዚአብሔር ለዘላለም ለልጆቹ የሚሰጠውን ልዩ ሕይወት ያገኛሉ። ይህን የማይቀበሉ ግን ለዘላለም ፍርድና ቍጣ የሚጠብቃቸው ናቸው።

መጥምቁ ዮሐንስ በዚህ ረገድ ስለ ኢየሱስ የተናገረው ምስክርነት ግልጽና የማያወላዳ ነው። ስለ ራሱ ሲናገር፣ ራሱን በመካድና በኢየሱስ ፊት ፍጹም በማሳነስ ነው። የመሪዎችና የአማኞች ትልቁ ችግር ራስ ወዳድነት ነው። ሰው ራሱን ካልካደ በቀር ኢየሱስን ማላቅና ከፍ አድርጎ ማክበር አይችልም።

ራስ ወዳድነት ፈርጀ ብዙ ነው፤ አንዳንዶች የራስ ወዳድነት ምንጫቸው ራሳቸውን ከማተለቅና ከገንዘብ መውደድ ሊመነጭ ይችላል። ሌሎች ደግሞ የእግዚአብሔርን ሥራ ለማበላሸትና ራሳቸውን ከፍ ለማድረግ ከሚሠሩት ሥራ የተነሣ እጅግ ራስ ወዳድ ሊኾኑ ይችላሉ። እኒህና በሌሎች መንገዶች የሚንጸባረቁ ራስ ወዳድነቶች እጅግ አደገኛና መራዥ ናቸው።

መጥምቁ ዮሐንስ ለኢየሱስ ዘመድና የቅርብ ወዳጅ ነው፤ በአገልግሎትም ኾነ በዕድሜ ጌታችን ኢየሱስን ይቀድመዋል፤ በአይሁድ ማኅበረ ሰብና በሮማውያን ባለሥልጣናት ዘንድም ከፍተኛ ተደማጭነት ነበረው።

በተደጋጋሚ ሰዎች ከኢየሱስ ይልቅ ክብሩን በእነርሱ ፊት እንዲገልጥ ዮሐንስን ጐትጉተውታል፤ እንዲያውም ከመጥምቁ ዮሐንስ ይልቅ፣ ኢየሱስ ሊልቅ፣ ዮሐንስ ደግሞ ዝቅ ዝቅ ሊልና ሊያንስ እንደሚገባ ተናገረ እንጂ በመቅናት የኢየሱስን አገልግሎት ሊያደናቅፍ ፈጽሞ አልፈለገም።

አገልጋዮች በሰዎች ልብ ሲገንኑና ሲተልቁ፣ ኢየሱስ በአገልግሎታቸው ይደበዝዛል፤ መሪዎችና አገልጋዮች ዝቅ ዝቅ ሲሉና ኢየሱስን እጅግ ሲያተልቁ ከክርስቶስ የተነሣ በሰዎች ልብ እግዚአብሔር ይከብራል፤ መንግሥቱም ትሰፋለች። መጥምቁ ዮሐንስ ይህን በሚገባ ያስተዋለ የጌታ አገልጋይ ነው።

ፍሬያማ አገልጋይ ለመኾን ዮሐንስ፣ ኢየሱስን ባገለገለበት መንገድ ልናገለግል ይገባናል፤ እንዴት?

1. ኢየሱስ ከሰማይ ነውና ዘወትር ሊገንና ሊከብር ይገባል፤ እኛ ኹላችን ከምድር ወይም ፍጡራን ነን፤ እርሱ ግን ታላቅና ገናና ከሰማይ የኾነ አምላክ ነው።

2. “እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራልና፤ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና።” (ዮሐ. 3፥30) የተባለለት ኢየሱስ ብቻ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ሲናገር እንከን የማይገኝለት፣ የታመነና የታተመ ምስክርነት ያለው ኢየሱስ ነው።

ከዚህም የተነሣ እውነትን በትክክል መናገር የሚችለው ኢየሱስ ብቻ ነው፤ ምከንያቱም እግዚአብሔርን ያየም ሆነ የመንግሥተ ሰማይን እውነቶች ኹሉ የሚያውቅ እርሱ ክርስቶስ ብቻ ነው። የኢየሱስ ቃል የእግዚአብሔር ቃል በመኾኑ ልንታዘዘው ይገባል። እግዚአብሔር ለማንም የሰው ልጅ ያልሰጠውን መንፈስ ቅዱስን በምልአት ለክርስቶስ ሰጥቶታል። እግዚአብሔር ክርስቶስን ስለሚወደው በምድር ላይ ሥልጣንን ሰጥቶታል። እናም ዘወትር ሊልቅና ሊገንን የሚገባው፣ ትኵረት ሊሰጥም የሚገባው ለክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው!

3. ኢየሱስ ኹሌም ትኵረት የሚገባው ሙሽራ ሲኾን፣ መጥምቁ ዮሐንስ ደግሞ ሚዜ ነው። የዮሐንስ ደስታ የኢየሱስ ፈቃድና ዐሳብ በትክክል ሲፈጸም ነው። ዮሐንስ ከዚህ በቀር ሌላ ደስታ የለውም። በኢየሱስ አገልግሎት ብዙ ተከታይ ሲገኝ፣ የዮሐንስ ተከታዮች ደግሞ እየቀነሱ መኾኑን ቢያውቅም ዮሐንስ ግን በዚህ እጅግ ደስተኛ ነበር። ለዚህም ነው “እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ይገባኛልና” በማለት የተናገረው።

የአደባባይ ጉባኤያትን የሚያደርጉ መሪዎችና አገልጋዮችን ከምንመዝንበት መመዘኛ ውስጥ አንዱ፣ “በአገልግሎታቸው ይበልጥ አነጋጋሪና ታዋቂ እየኾነ ያለው ማን ነው? ትኵረት እየሳበስ ያለው ማን ነው? … “ የሚሉና ሌሎች ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ጥያቄዎች ናቸው።

“በማያቋርጥ ፍቅር ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለሚወዱ ሁሉ ጸጋ ይሁንላቸው።” (ኤፌ. 6፥24)

አቤኔዘር ተክሉ (ዲያቆን)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ኤግስት በየአመቱ የሚያከናውነው በአባ ፍሪምናጦስ የተሰየመው ትምህርት ከዛሬ መጋቢት 19 እስከ አርብ 22 ድረስ ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ያከናወናል። ለሁሉም ሰው ክፍት የሆነውን ይህንን ትምህርት ትታደሙ ዘንድ ተጋብዛችኋል!

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ፓለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዎ መስተጋብሮች፣ በማወቅም ባለማወቅም በ “ብሔርተኝነት” መነጽር በሚቃኙበት በዚህ ዘመን፣ ቤተ ክርስቲያን ከእግዚአብሔርም እንዲሁም እርስ በእርስ የታረቀ አስታራቂ አማራጭ ማኅበረ ሰብ ልትሆን ተጠርታለች። የዕርቅና የፈውስ መንበር መሆን የምትችልበት የጽድቅ ዐቅም ከዚሁ ተልእኳዊ የራስ ግንዛቤና አተገባበሩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው።

እንደ ክርስቶስ ማኅበረ ሰብ፣ የሚገዛን ዋናው ገዢ ማንነት በመስቀሉ ሥራ ከነገድና ከቋንቋ የተዋጀንበት የቤዝዎት ሥራ ከሆነ፣ ራሳችንንም ሆነ ሌሎችን በዘረኝነት መነጽር ልንመለከት አንችልም። “ለእግዚአብሔር የተለየ ሕዝብ” መሆን ምን ማለት እንደሆነ ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል። (1ጴጥ.2፥:9)። በበያኝነት፣ የክርስቶስ ማኅበረሰብ መታወቂያውም ሆነ ውቅሩ ዘር፣ ቋንቋ፣ ባህል፣ መደብ ወይም ፖለቲካዊ ርእዮተ-ዓለም አይደለም። ምድራዊ ልዩ ልዩነቶች አንጻራዊ ናቸው። ገዢውና ፍጹሙ ማንነት፣ የጥል ግድግዳ በመስቀሉ በመፍረሱ የተገኝው አንድ ቤተ ሰብነት፣ የአንድ አገር ዜግነትና ዘላለማዊ አንድነት ነው። የክርስቶስን ማኅበረሰብ ልዩ የሚያደርገው ይኸው አዲሱ ማንነት ነው። የመስተጋብሮች እሴት በበላይነት የሚዳኘው በዚህ ማንነት ነው። ለእግዚአብሔር የተለየ ማኅበረ ሰብ ወገንተኝነት ከእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅ ሥራ ጋር—ከሰላም ወንጌል፣ ዕርቅ፣ ፍትሕ፣ ምሕረትና እውነት ጋር ብቻ ነው።

በዚህ ሰዓት በሰማይ የሚዘመሩ ሁለት መዝሙራት አሉ፦

“ጌታችንና አምላካችን ሆይ፤ ክብርና ሞገስ፣ ኀይልም ልትቀበል ይገባሃል፤ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና፤ በፈቃድህም ተፈጥረዋልና፤ ሆነዋልምና።” - (ራእይ 4 : 10 - 11 )

"ማኅተሞቹንም ልትፈታ ይገባሃል፤ ምክንያቱም ታርደሃል፤ በደምህም ከነገድ ሁሉ፣ ከቋንቋ ሁሉ፣ ከወገን ሁሉ፣ ከሕዝብ ሁሉ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ዋጅተሃል። ለአምላካችንም መንግሥትና ካህናት አድርገሃቸዋል፤ እነርሱም በምድር ላይ ይነግሣሉ።” - ( ራእይ 5 : 9 - 10 )

ቤተ ክርስቲያን፣ የእውነተኛ ሰላም፣ የይቅርታ፣ የዕርቅና የፈውስ አማራጭ ማኅበረ ሰብ መሆን የምትችለው፣ እነዚህን መዝሙራት የአምልኮዋ፣ የተልእኮዋና የየዕለት ሕይወቷ መካከለኛ ስታደርግ ብቻ ነው።

አቤቱ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፤ በዚህ እውነት አድሰን። አሜን!

* Gregory of Nazianzus, Select Orations, trans. Martha Vinson (Baltimore, UNITED STATES: Catholic
University of America Press, 2004), http://ebookcentral.proquest.com/lib/abdn/detail.action?docID
=3134806, 9.

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)

Читать полностью…
Subscribe to a channel