negere_evangelical | Unsorted

Telegram-канал negere_evangelical - ነገረ ወንጌላውያን

2910

በወንጌላውያን አማኞች ዘንድ የሚፃፉ ፅሁፎች፣ ዘገባዎችና ዜናዎች ይቀርባሉ! ትምህርቶች፣ መረጃዎችና ምካቴ እምነቶች በዚህ ቻናል ይስተናገዳሉ! በተለያዮ ሶሻል ሚዲያዎች የሚገኙ ፀሐፊያን የሚፅፉቸው ፅሁፎችን እናጋራለን።

Subscribe to a channel

ነገረ ወንጌላውያን

በሕይወት ዘመናችሁ በአስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ በገባችሁ ጊዜ እንዲህ ማለትን ልመዱ። በመጀመሪያ፥ “እዚህ ቦታ ያቆመኝ እግዚአብሔር ራሱ ነው። በዚህ አጣብቂኝ ውስጥ ያለሁትም በእርሱ ፈቃድ ነው”በሉ። ቀጥሎ፥ “በዚህ ውስጥ እያለሁ እግዚአብሔር በፍቅሩ ይንከባከበኛል፤ ልጁ እንደ መኾኔም መጠን፥ እንድመላለስበት ባሠመረው የሕይወት ልክ ለመኖር እንድችል በዚህ የፈተና ወቅት ጸጋውን ይሰጠኛል”በሉ። በዚያ ላይ፥ “መከራውን ወደ በረከት ይለውጥልኛል፤ እንድማር የሚፈልገውን ነገር እንድቀስም እኔን ከማስተማሩ ጐን ለጐን ሊሰጠኝ የሚፈልገውን ጸጋ በእኔ ውስጥ እንዲሠራ ያደርገዋል”በሉ። በመጨረሻም፥ እንዲህ በሉ፥ “የእርሱ ትክክለኛ ጊዜ ሲደርስ ካለሁበት ኹኔታ ውስጥ መልሶ ሊያወጣኝ ይችላል። እንዴትና መቼ የሚለውን ግን የሚያውቀው እርሱ ነው።” ስለዚህ፥ “አኹን ባለሁበት ያለሁት (1) በእግዚአብሔር ቀጠሮ፥ (2) በጥበቃው ተከብቤና (3) በእርሱ ሥልጠና ሥር ሲኾን፥ (4) የምቈየውም እርሱ እስከ ወሰነው ጊዜ ድረስ ነው” በሉ።

— አንድሪው መሪይ

(መጋቢ ሰሎሞን አበበ ገብረ መድኅን እንደተረጎመው)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ሃሰተኛ መምህራን እውነተኛ የሆነውን ትምህርት በመንፈቅ አፈንግጠው የሚወጡ ናቸው። አፈንግጠው ወጥተው ግን አርፈው የሚቀመጡም የሚያስቀምጡም አይደሉም። ራሳቸውንና አስተምኅሯቸውን አስረገው በማስገባት የመንጋውንና የቤተክርስቲያንን ጤና ለማወክ ይዳክራሉ። ትምህርታቸውና እምነታቸው ከቅዱሳት መጽሐፍት በተቃርኖ የቆመ ቢሆንም ትምህርታቸውን አስርገው ለማስገባት ይጥራሉ።

ይህ ዶክመንተሪ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረቶችን እየፈተሸ፣ ትውፊትን እያጣቀሰ ከአጉል ተስፋዎች ይጠብቀናል። ብዙ ትኩረት ለሃሰተኞች በሚሰጥበት በዚህ ዘመን ሃሰተኞቹ ስለሚያወድሙት ምስኪን መንጋ ግድ የሚላቸው አገልጋዮች እንደ እግዚአብሔር እውነት ሙግት ይቀርባል።

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሃሰተኛ መምህራን ምን ይላል? የሐዋርያት ቤተክርስቲያን ሃሰተኛ ሆነው ለተገኙ ትምህርቶች ምን ምላሽ ሰጡ? የቤተክርስቲያን አባቶችስ ምላሻቸው ምን ነበር? ለሃሰተኛና ሰርጎ ገብ ትምህርት ምላሽ መስጠት ለምን አስፈለገ? ግንኙነታችን ምን መሆን አለበት? ሃሰተኞች በንስሃ ሲመለሱ ምን መደረግ አለበትና እቅበተእምነት እንዴት መከወን እንዳለበት የሚናገረ ዘጋቢ ነው!

በቅርብ ቀን ይወጣልና እያጋራችሁ ጠብቁን!

ethiopianevangelicalreform7708" rel="nofollow">https://youtube.com/@ethiopianevangelicalreform7708

አማኑኤል አሰግድ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ኤልያስ ከበኣል ነብያት ጋር በቀርሜሎስ ተራራ ነብያዊ 'ትርኢቱን' በሚያቀርብበት ወቅት የበኣል ነብያት ወደ በኣል እየጮኹና እንደለመዱት ሰውነታቸውን እየጎዱ ልመና አቀርበውለት ነበር። ነገር ግን «ድምፅ የለም፤ የመለሰና ከቁም ነገር የቈጠረውም አልነበረም።» [וְאֵֽין־ק֥וֹל וְאֵין־עֹנֶ֖ה וְאֵ֥ין קָֽשֶׁב]."(1 ነገሥት 18:29) ይላል።

በኤልሳዕ አገልግሎት ወቅት በተመሳሳይ የሱናማዪቷ ልጅ ሲሞት «ድምፅም፣ ምላሽም አልነበረም። ስለዚህ ግያዝ ወደ ኤልሳዕ ተመልሶ፣ [וְאֵ֥ין ק֖וֹל וְאֵ֣ין קָ֑שֶׁב] ልጁ አልነቃም” አለው።» (2 ነገሥት 4:31) ይላል።

"ድምጽ የለምና ምላሽ የለም" የሚሉት ሁለት ቃላት በእብራይስጡ ሐረጎች ተደጋግመው በሁለቱም ስፍራ ተገልጸዋል። በሌላ አባባል የነገሥት ተራኪዎች በበኣልም ሆነ በሞተው ብላቴና ውስጥ ህይወትን የሚገልጽ ድምጽና ምላሽ አለመኖሩን ለመግለጽ የተጠቀሙባቸው ቃላት ተመሳሳይ ናቸው።

ከቃላት ምስስሎሽ ባሻገር አንደኛና ሁለተኛ ነገሥት ላይ የሚገኙት ታሪኮች የተሳሰሩ ይመስላል። የቃላት አጠቃቀማቸው መመሳሰል ተመሳሳይ ትርጓሜን እንድንሰጥ ሆን ተብሎ የተደረገም ይሆናል። በሁለቱ ታሪኮችና የአጻጻፍ ስልቶች መኸከል ያለው የረቀቀ ቁርኝት የሚጠቁመው በኣል የተባለው አምላክ ህይወት አልባ በመሆኑ ምላሽ ለመስጠት እንደማይችል በጉልህ ያሳያል። ይህንን በአካል ከሞተ ሰው ጋር ማመሳሰሉ በኣል ሙት መሆኑን ይጠቁማል። በኣል ሙት አምላክ መሆኑን ለአንባቢያን ይገልጻል። መንቀሳቀስም መናገርም የማይችል ህልውና አልባ ነው።

እስራኤልን በባዕድ ምድርና በሃሰተኛ 'አማላክት' መኸል ሲተክላት ብቸኛውና እውነተኛው ህያው አምላክ እርሱ መሆኑን እንድትጠቁም ነበር። በእርሱ ህይወት እንዲትረፈረፍ ማሳያ ነበረችና እግዚአብሔር ደጋግሞ ብቸኛ ህያው አምላክ መሆኑን ለአስራኤል፣ ለከባቢውና ለዓለሙም ሲገልጥ እንመለከታለን።

ስለዚህም የነገሥት ጸሐፍት ህይወት የሚሻ ካለ ወደ ያህዌ መሄድ ግድ ነው እያሉ ነው። ህያው ከመሆኑ የተነሳ ድምጽም ምላሽም የሚሰጥ ብቸኛ አምላክ እርሱ ነው። እርሱ ብቸኛ ህያው አምላክ የተትረፈረፈ ህይወት ምንጭ ነው። ትንሣኤና ህይወት እርሱ ብቻ ነው።

ቻድ በርድን መነሻ በማድረግ

አማኑኤል አሰግድ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ኦርቶዶክስ ነኝ... ይኸው ክሬን እዩ..... ቤተክርስቲያን እሄዳለሁ... ወዘተ.. የሚል ማታለያ ማቅረብ በእውነት ላይ መዋሸት ነው። ነጭ ውሸት ነው።

ነጭ ውሸት #5

በጣም ያሳዘኑኝ እና ያስገረሙኝ ደግሞ መጨረሻ ላይ የቀረቡት "መስካሪዎቹ" ናቸው። "ዳዊት ድሪምስ ጋር መጥቼ በመማሬ መንፈሳዊ ህይወቴ አደገ" ዓይነት ቀልድ ቀልደዋል። የትኛው መንፈሳዊነት? መንፈሳዊነት'ኮ "ፈቃድህ ትሁን ብሎ ለእግዚአብሔር መገዛት፣ መስቀል ተሸክሞ፣ እኔ አልችልም እግዚአብሔር በእኔ ይችላል እያሉ እግዚአብሔር በመረጠልን መንገድ መሄድ ነው። እንጂ የዳዊትን የገንዘብና የፍቅረ ነዋይ ትምህርት እየተጋቱ በአወንታዊ ንግግር የስበት ሃይልን ተጠቅሞ የስጋዊነትን ፍላጎት ለማርካት መጣርና ዓለምንና በዓለም ያለውን መመኘት (መጎተት) አይደለም። የዳዊት እና የዳጊን ትምህርት ተምሬ "መንፈሳዊ ህይወቴ አደገ" ብሎ መመስከር ነጭ ውሸት ነው።

ለማንኛውም እንዲህ ተብሎ የተፃፈውን እናስተውል “ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል።” (1ኛ ዮሐ 2፥17)

ቴዎድሮስ ተጫን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

እግዚአብሔር ያስታውሳል!

በዘገየ የጸሎት መልስና በእግዚአብሔር ዝምታ አንዳንድ ጊዜ ልባችን በተስፋ መቈረጥ ይሞላል። በሕይወታችን “ዝምታዎችም” መካከል እግዚአብሔር በሉዓላዊነቱ በሥራ ላይ ነው። ልጅን ያለመወለድ ከርግማን፣ ከኀጢአት ወይም የእግዚአብሔር ሞግስ ከማጣት ጋር በሚያቆራኝ ማኅበረ ሰብ ውስጥ፣ ዘካርያስና ባለቤቱ ኤልሳቤጥ በታማኝነት ያገለግሉ ነበር። ይህ በነበሩበት ማኅበረ ሰብ ትውፊትና መንፈሳዊ ዐውድ ከባድ “መሰቀል ነበር”። “ለምን እግዚአብሔር ዝም አለ?”፣ እፍረታችንንስ ለምን “አይመለከትም?” የሚሉት ጥያቄዎች ዘወትር በነዝናዥነት ይከተሏቸው ነበር። አስነካሽ፣ ቀና የማያሰኙና ልብ አዛይ መልስ የሌላቸው ጥያቄዎች ነበሩ።

ኾኖም፣ እየታገሉም በመሰጠት ጌታን ያገለግሉ ነበር። በኋላ እንደምናስተውለው ያገለግሉ የነበረበት ቤተ መቀደስና መሪዎቹ በብዙ መፈሳዊ ቀውስ ውስጥ ነበሩ። ለማገልገል ቀርቶ ለማምለክም ዐቅም የሚያሳጣ መንፈሳዊ ብሉሽነት እንደ ነበረ ጌታ ቤተ መቀዱስን ሲያጸዳ ከተናገረው መገመት ይቻላል፦

“ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ፣ ሻጮችን ከዚያ አስወጣ፤ ደግሞም “ ‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል’ ተብሎ ተጽፏል፤ እናንተ ግን ‘የወንበዴዎች ዋሻ’ አደረጋችሁት።” (ሉቃስ 19፥45᎓6)።

ይሁን እንጂ በዚህም ልብን በሚጥል ሁኔታ ውስጥም ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ስሜታቸውን በመከተል ሳይሆን፣ እግዚብሔርን ተመልካች በማደረግና ልባቸውንም በእርሱ ሉዓላዊነት ላይ በማሳረፍ እያመለኩ ያገለግሉ ነበር። ዋጋቸው እርሱ ብቻ እንደሆነ ተገንዝበዋልና! እንደሚመስለኝ በዚህ ወቅት ስለ ልጅ መጸለይ አቁመዋል። የሚመለስ አይመስልም ነበርና። ስለዚህ ጸሎታቸው በመሲሑ መምጣት ስለሚሆነው የእግዚብሔርን ጕብኝት ይመስለኛል። በአጭሩ “መንግሥትህ ትምጣ” ሳይሆን አይቀርም። ከስምዖን ጸሎት እንደምንረዳው ይህ የትሩፋኑ ሕዝብ የመለኮታዊ ጕበኝት ናፍቆትና ጕጕት ነበር።

“በዚያን ጊዜ ጻድቅና ትጉህ የሆነ ስምዖን የሚባል አንድ ሰው በኢየሩሳሌም ይኖር ነበር፤ እርሱም የእስራኤልን መጽናናት የሚጠባበቅና መንፈስ ቅዱስ በላዩ ያደረ ሰው ነበር።” (ሉቃስ 2፥25)

እኛ በምንፈለገው መንገድ ወይም ጊዜ ባልተመለሰ ጸሎትና የሕይወት እንቆቅልሽ ውስጥ እግዚአብሔር ተመልካችና አድማጭ በማድረግ እንድናመልከና እንደናገለግል የሚያስችል የጌታ ጸጋ አለ። ለዘካርያስና ለኤልሳቤጥ ዘመን መጣ - የእግዚአብሔር ጊዜ። ራሱ በወደደው ጊዜ በድነት ታሪክ ውስጥ በሕይወታቸው ውስጥ የነበረው ዝምታ ተሰበረ። በእግዚአብሔር የድነት ዓላማ ውስጥ ዮሐንስ መምጣት ነበረበት። ይህ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ካሰቡት፣ ከጠበቁትና ከተመኙት በላይ ትልቅ ዕቅድ ነበር። የእግዚአብሔር መግሥት በደጅ ነበር!

“የጌታም መልአክ ከዕጣን መሠዊያው በስተ ቀኝ ቆሞ ታየው። ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፤ በፍርሀትም ተዋጠ። መልአኩ ግን እንዲህ አለው፤ “ዘካርያስ ሆይ፤ አትፍራ፤ ጸሎትህ ተሰምቶአል፤ ሚስትህ ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ። በእርሱ ተድላና ደስታ ታገኛለህ፤ ብዙዎችም እርሱ በመወለዱ ደስ ይላቸዋል፤ በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና። ከእስራኤልም ሰዎች ብዙዎቹን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳቸዋል፤ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆቻቸው፣ የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ፣ ለጌታ የተገባ ሕዝብ ለማዘጋጀት በኤልያስ መንፈስና ኀይል በጌታ ፊት ይሄዳል።” (ሉቃስ 1፥11-16)

ሳይመለስ በዘገየ ጸሎት ልባችሁ የዛለና ለጊዜው መልስ ከሌለው ውስብስብ ችግር ጋር የምታገለግሉ ትኖሩ ይሆን? ያልታየን ስንመስል፣ በርግጥ እርሱ ያየናል! ያልተሰማስን ሲመስለን በርግጥ እርሱ አስቀድሞ ሰምቷናል። ሕይወት በዝምታና በጸጥታ ስትዋጥና የእግዚአብሔር አብሮነት ሳይሰማንም ሲቀር እግዚአብሔር በአጠገባችን አለ። በቅንነትና በታማኘት እናምልከው፤ እናገልግለውም! እንደ ስሙ፣ ዘካሪያስ - እግዚአብሔር ያስባል፤ እግዚአብሔር ያስታውሳል፤ እግዚአብሔር ይመለከታል።

አሜን!

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

በቤተ ሰብ እሴት ላይ ግልጽ ጦርነተ ታውጆብናል። በአስተማሪ፣ በጓደኛ ወይም በማኅብራዊ መገናኛ ብዙሃን ተጽዕኖ ተገፋፍተው የጾታ ለውጥ ማደረግ የሚፈልጉ ልጆችን ትለዋዋጭ ውሳኔ፣ ወላጆች ማስቆም አይችሉም። ከሞከሩም እንደ “ልጅ በዳይ” ተደርገው ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፤ ልጆቻቸውንም ያጣሉ። በአሜሪካ አንዳንዳድ ግዛቶች (ለምሳሌ በካሊፎርኒያ)፣ ወላጅ ሳያውቅ የጾጥ ለውጥ ይደረጋል። መንግሥት፣ ፓለቲከኞችና ልዝብ አብያተ ክርስቲያናት የወንድነትንና የሴትነትን የጾታ ልዩነት የማጥፋት ዘመቻ ላይ ናቸው። በዚህ ላይ በየትኛውም መንገድ ትርፍ ማግኘትን ግብ ያደረጉ የምርምር ማዕከላትና መድኀኒት አምራችች የችግሩ ዘዋሪዎች ናቸው። ለምሳሌ ዐቅመ አዳም/ሔዋን የመድረሻ ምልክት የሆነውን የጉልምስና የተፈጥሮ ሂደት የሚያፍን መድኀኒት (puberty blocker) በማምረት የሚታወቀው አብቪይ AbbVie፣ ከአንድ ዓይነት ምርቱ ብቻ የ2018 ትርፉ 726 ሚሊዮን ዶላር ነበር።

በወንድሙ ስቃይ የታመመው መንታ ወንድሙ ብራየንም ነበር። እርሱም ከገባበት ጥልቅ የሆነ የድባቴ ስቃይ ለማረፍ፣ ከተዘዘለት በላይ በርካታ መድኀኒ በመውስድ July 2002 ውስጥ ራሱን አጠፋ። ይህም እውነት ብዙ እንዳይነገር የሊበራል ሚዳያ፣ የሆርሞንና የጾታ ለውጥ መድኀኒት አምራቾች፣ የግበረ ሰዶም አራማጅ ፓለቲከኞችና ባለሐብቶች ከፍተኛ መረባረብ አድርገዋል። ይህን ተከትሎ May 2፣ 2004 ብሩስ ራሱን በመሣሪያ አጥፍቷል። ዕድሜው 38 ነበር። መንትዮቹ ያለደስታ የተኖረ ከንቱ ሕይወት ነበራቸው። ወላጆቻቸው ለልጆቻቸውን ስቃይና ራስ ማጥፋት ተጠያቂው፣ በሐሰት ተስፋ የመራቸው ፕሮፌሰር መኒ መሆንን በይፋ ተናገረዋል። ስብራት!

ለመንትዮች የተጻፈው “Hymn of the Medical Oddity” ("የእንግዳው ሕክምና መዝሙር") የመጀመሪያና የመጨረሻ ቁጥሮች እንዲህ ይላሉ፦

Oh, all the words I should not know
Those doctors wrote on me
Swell up and from their syllable
Won't let me get to sleep
The sun will start late and clock out early . . .
. . .
And if they remember me at all
Make them remember me
As more than a queer experiment
More than a diagram in their quarterly
Make them remember me

ኦ፤ ላውቅ የማይገቡኝ ቃላት
እነዚያ ሐኪምች የከተቡብኝ
ከቃላት [መዝገባቸው] ሞለተው የተረፉት
እንቅልፍ ነስተውኛል . . .

በርግጥ የሚያስታውሱኝ ከሆነ
እንዲያስታውሱኝ አድርጉልኝ
ግራ ከተጋባ ጠያቂ በላይ
በሥራቸው ቦታ ካለው ንድፍ በላይ

እንዲያስታውሱኝ አድርጉልኝ . . .

እንንቃ! እንጸልይ፣ ግን ልጆቻችንን በየቤታችን እናስተምር። እኛ ካላስተማርናቸው፣ ክፉው ባህል ያስተምራቸዋል።

“እግዚአብሔር ሰውን ፈጠረ። “ስለዚህ እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክ ፈጠረው፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጐ ፈጠራቸው። እግዚአብሔርም፣ ‘ብዙ ተባዙ፤ ምድርን ሙሏት፤ ግዟትም፤ የባሕርን ዓሦች፣ የሰማይን ወፎች፣ እንዲሁም በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሕያዋን ፍጡራንን ሁሉ ግዟቸው’ ብሎ ባረካቸው።” (ዘፍ 1፥27-28)።

ሁለት ጊዜ የማይሽራቸው እውነቶች፦

1) “ወንድና ሴት አድርጐ ፈጠራቸው፤”- ወንድ እና ሴት እኩል ናቸው፤ አንድ ዐይነት ግን አይደሉም። በኑባሬ እኩል፣ በተፈጥሮ ተደጋጋፊ የድርሻ ልዩነት አላቸው (complementary functional distinctiveness)

2) የማኅበረ ሰብ መሠረት ቤተ ሰብ ነው፤ የቤተ ሰብ መሠረት “የወንድ እና የሴት” ጾታዊ ልዩነት ነው።

በብዙ ሞራል ዝቅጠት ውስጥ በተዘፈቀ፣ አምላክ የለሽ፣ እውነት በተሰወረበት በዚህ በማኅብረ ሰብ መካከል የሚያድጉ ልጆቻቻንን፣ በብዙ የልበ ስፋት፣ በብዙ ትዕግሥት፣ በበዙ በፍቅርና በብዙ ጸሎት አብዝተን ልንይዛቸው ይገባል። ከግብረ ሰዶም አጀንዳ፣ ከመጠጥ፣ ከአድንዛዥ ዕፅና ከማኅብረዊ ሚድያ ሱስ ፈተና ጋር የሚፈለሙትን ልጆቻንን በእግዚብሔር ቃል በየዕለቱ ልናስታጥቃቸው ይገባል። ቤትም ውስጥ እያሉ ሊጠፉበን ይችላሉ። ቤታችንም፣ ቤተ ክርስቲያናችንም ለልጆች ንጹሕና የሚመች ስፍራ ይሁኑ። በርዳታና በሰብ አዊ መብት ሽፋን በአገራችን ላይ ያኮበኮበው የምዕራቡን ዓለም የግብረ ሰዶምን አጅንዳ ቸላ ልንል አንችልም። በዘረኝነት፣ በክፍፍልና በዓለማዊነት እንቅርት ላይ፣ ልጆቻችንን ሊበላ በውጪ ያለው የሞራል ልቅነት ተጨምሮበት ምን ይተርፈናል?

"አቤቱ፤ እግዚአብሔር ሆይ ጥበቃህ በልጆቻችን ላይ ይሁን። ለወላጆችም ጸጋህንና ጥበብህን ስጠን።

አሜን!

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

በፈረንጆች አቆጣጠር በግምት 2008 ዓ.ም በአራት ኪሎ ዳግማዊ ምኒልክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አዳራሽ ሁለት ሺህ ለሚሆኑ የኮሌጅ/ ሃይስኩል (?) ክርስቲያን ተማሪዎች ኢቫሱ ባቀረበልን ጥያቄ መሰረት እኔ ሰሎሞን ጥላሁን፣ ወንድም ምኒልክ አስፋውና ወንድም ተስፋዬ ሮበሌ ስለ Secret / "ሚስጥሩ" ትምህርት እንድናቀርብ ተጠይቀን አቅርበን ነበር፡፡

አሁን በዚህ ሰሞን ወንድም ጌታነህ ሔራሞ ያቀረበውንም ሙግት ተመለከትኩና ትውልድ አልፎ ትውልድ ሲተካ የሁላችንም ዘመን ጩኸት አንድ ኣይነት መሆኑ አስደነቀኝ

አሁን ሚስጥሩ ግልጥ ሆኖ አገር እያተራመሰ ስናይ "ይህ ህዝብ..." በሚል ስሜት ተይዘናል፡፡ ያን ጊዜ እኔ ያቀረብኩትን ወረቀት ከድሮው ፎንት እንደምንም ለመቀየር ሞክሬ የሚከተለውን መክፈቻ ንግግር አገኘሁና አንድ ገጽ ለምትታገሱ አንባብያንና ምናልባት ከሁለት ሽሆቹ ጥቂቶች ካላችሁ ለማስታወስ እነሆ ልበለችሁ... የዛሬ 15 ኣመት ከተናገርኩት ላይ አንዲት ፊደል እንኳ አልጨመርኩበትም!

[በመጻሕፍት ገበያ እሽቅድድም በድንገት ፈትልኮ የወጣ፣ ቀድመውት ከወጡ አቻዎቹም ከእነ ዳቬንቺ ኮድና ሃሪ ፖተር ይልቅ በድንገት የገበያውን ማእበል ያግለበለበ መጽሐፍ ነው። ርእሱ መልስ ፈላጊ ለሆነው የሰው ልጅ አእምሮ ማራኪ ነው ቀለሙና የሽፋኑ ገጽታ በዘይት ያማረ ጥርብ ጣውላ ይመስላል፣ ደምቆ ዓይን አይወጋም፣ ፈዞም አይሰወርም።

በመጽሐፉ ውስጥ የተነሱ ርእሰ ጉዳዮች አይመለከተኝም የሚል ከቶውንም ቢሆን አይኖርም። የጥረትና የግረት ምክንያቶች በመሪ ርእሰ ጉዳይነት ከነፈጣን መፍትሔአቸው ተዘርዝረዋል። እሺ ባይ ሁሉ ተጠቃሚ እንደሆነ ሙሉ ተስፋ ይሰጣል። ደሃን እንደሚያበለጽግ፣ ባለጠጋን እንደሚያናጥጥ፣ በሽተኛን እንደሚፈውስ፣ ጤነኛን እንዳይታመም እንደሚያደርግ የጠበቀና የማያወላዳ ተስፋ ይሰጣል።

በትዳር በሥራ በሕይወትህ ወይ ደግሞ ገንዘብ በማጣት አዝነሃል? አዕምሮህን ተጠቀም የተሻለውን ማንነትህን አስብ ፕዘቲቭ አስተሳሰቦች ይለውጡሃል የምታውቃቸውን ማንኛውንም ዓይነት መልካም ነገሮች ሁሉ ይስቡልሃል ይህ የማይታመን ይመስልህ ይሆናል ግዴለም ደግመህ አስብ በሳይንስም የተደገፈ ነውና
ታዋቂው የሲ ኤን ኤን ቶክ ሾው አቅራቢ

ታዲያ እርሱ እንዲህ ያስተዋወቀውን መጽሐፍ ማን በቀላሉ ያየዋል!

በእንግድነት በሔድኩበት በአንድ ቤ ት ውስጥ ከአልጋው ፊት ለፊት በቁም ሳጥኑ ከፍ ባለ የመዝጊያ ጠርዝ የተለጠፉ ሁለት ብሮች አየሁ የመለጠፋቸው ምክንያት የገባኝ ከጥቂት የቆይታ ቀናት በኃላ ነው በዚያ ቤት ውስጥ ነዋሪ የሆነ ወጣት ካነበበው አንድ መጽሐፍ የተነሣ የብር ሐሳብ ብርን ይስባል ለዚህም ብርን ግድግዳ ላይ ለጥፎ ማፍጠጥ ወይም ስለ ብሩ ማሰላሰል የብር ሐሳብን ወደ ብር ይለውጣል

በውጪ አገር የሚኖር አንድ ኢትዮጵያዊ የኮሌጅ ተማሪ ቡና እየጠጣን ስለ ትምህርት ቤት ጉዳይ ስናወራ የአንድ ትምህርት ፕሮፌሰር ቫይብ /ቫይብሬሽን/ ወይም ከውስጡ የሚወጣው ነዛሪ ኤሌክትሪክ ሲያስቸግረው እንደ ከረመ አጫወተኝ ምንድን ነው ይሄ ቫይብ ብዬ ብጠይቀው የሰውየው ኔጋቲቭ የኤሌክትሪክ ንዝረት ከእኔ ከሚወጣው ጋር በመጋጨት ተጽእኔ ያሳድርብኛል በኃላ ሁኔታውን ሳጣራ የሚከተለው አንድ ህቡዕ /ስውር/ እምነት ያለው ሰው እንደሆነ አወቅሁ

«ሚስጥሩ´ ሚስጥሩ አንድ ነው እርሱ ሃይማኖታዊ መልእክት ነው መልእክቱም ሰው አምላክ ነው የሚለው ነው ለዚህ ነው ኢ አማኒያኑ /ኢቲስቶች/ የዚህ መጽሐፍ መልእክት ከሌሎች ሃይማኖች ይልቅ ያሳሰባቸው ምክንያቱም አሁን በሚስጥሩ የተነሳ ነባሩ አምላክ አለወይም የለም የሚለው ክርክር ሰው አምላከ ነው ወይስ አይደለም ወደሚለው ዞሯልና ነው

ዘ ሴክሬት የተባለው መጽሐፍ በቁሳዊው ዓለም ስላሉ ልዩ ልዩ ስኬቶችና የማግኛ ቀመራቸው /ፎርሙላ/ አኮብኩቦ ተሳፋሪውን ከያለበት ስፍራ ስበትን አስለቅቆ ሲያንሳፍፍ ከዋለ በኃላ ወደ ማክተሚያው ሲደርስ አንተ አንቺ አምላክ ነህ ከዚህ በኃላ በራስህ መንገድ ማረፍ ትችላለህ በማለት በሚሊዮን የሚቆጠሩትን ተሳፋሪዎቹን አየር ላይ ጥሎአቸው የሚሔድ በራሪ ቅዥት ነው:: ይሁን እንጂ በርካታ ክርስቲያናዊ ቃላትን በመውሰዱ አስተሳሰቡ በሙሉም ሆነ በከፊል ያመነው ማሕበረሰብ ውስጥ ለመግባት ያመቸዋል በተለይም የእምነትን ትምህርት በተለጠጠ መልኩ በሚያስተምሩት ቤተ ክርስቲያኖች አካባቢ ከምስባኩ /ከመድረኩ/ የተለመዱ ቃላትን ስለሚጠቀም እነዚህ ቤተ ክርስቲያኖች ትምህርቶቻቸውንና የሚጠቀሙባቸውን ቃላት ሊመረምሩ ይገባል ...]

መጋቢ ሰሎሞን ጥላሁን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የ"New Age" ዕሳቤ ግብና ዓላማ በፎቶ ሲገለጥ!

ከፅሁፌ መጨረሻ ላይ የተቀመጠውን ፎቶ ያወረድኩት ከዳዊት ድሪምስ የፌስ ቡክ ገፅ ላይ ነው። ራሱ ዳዊት አቀናብሮ የለቀቀው ነው። በእኔ አረዳድ ፎቶው የ"New Age Thought" ግብና ዓላማን በግልፅ የሚያውጅ ነው። ዳዊት ይህን ሆን ብሎ ያድርግ ወይ አያድርግ አይመለከተኝም። ሐሳቤን ለመግለፅ ግን ፎቶው እጅግ ይጠቅመኛል።

የ"New Age Thought" ዕሳቤ ወደ የትኛውም የሃይማኖት ካምፕ ማጋደል አይፈልግም፤ የትኛውንም ሃይማኖት ነጥሎ ትክክል ነው ወይም ስህተት ነው አይልም፤ ሁሉንም አንድ ላይ ይዞ በመጓዝ ወጥ የሆነ ዓለም አቀፍ ማንነትን በመገንባት ሰላምን ማምጣት እንደሚቻል ግን አስተምህሮው አፅንዖት ሰጥቶ ይደሰኩራል። ለረዥም ዓመታት በ"New Age Thought" አስተምህሮና ልምምድ ውስጥ ያሳለፉ አሁን ግን በንስሐ ወደ ክርስትና እምነት የተመለሱ "Steven Bancarz እና Josh Peck" ይህን የአስተምህሮውን ግብና ዓላማ በተመለከተ በ"THE SECOND COMING OF THE NEW AGE...2018" መፅሐፋቸው ውስጥ የከተቡት እንደዚህ በማለት ነው።

"The New Age movement is a spiritual system of thought and practice composed of beliefs, values, and traditions from various schools and religions throughout the world."

በገለፃው መሠረት የ"New Age" ዕሳቤና እንቅስቃሴ ወጥ የሆነ የሚከተለው ሃይማኖትም ሆነ ዶክተሪን የለውም፤ ሁሉንም አስተሳሰብ ከጥንቆላ እስከ ሃይማኖት፣ ከባህላዊ አስተሳሰብ እስከ ሳይንሳዊ ምልከታ አቃፊ ነው። ከላይ በጠቀስኩት ፅሁፍ ውስጥ የተቀመጠው ይኸው ነው፦ "...traditions from various schools and religions throughout the world."

እንዲሁም ከላይ የጠቀስኳቸው ደራሲያን የ"New Age" ግብ ምን እንደሆነ በመፅሐፋቸው ያሰፈሩት እንደዚህ በማለት ነው፦

"The goal, at a global level, is to initiate world peace by uniting the religions of the world under an impersonal, universal god, restoring the forgotten wisdom traditions of ancient cultures and incorporating them into our civilization."

"Uniting the religions of the world" አስምሩልኝና ዳዊት ድሪምስ ራሱ አቀናብሮ በሶሻል ሚዲያ ከለቀቀው ከሥር ካያያዝኩት ፎቶ ጋር አነፃፅሩት። ሃይማኖቶችን ሁሉ በአንድ ቋት ከትቶ መፍጨትን የትኛውም ሃይማኖት የሚቀበለው አተያይ አይደለም። በጣም የማከብራቸው የኦርቶዶክስ ክርስትና መምህር መጋቢ ሐዲስ እሸቱ የፕሮቴስታንቱ ፓስተር ቸሬ እና የእስልምናው ኡስታዝ አቡባከር አህመድ ዳዊት ድርምስ ከኋላው ሲያሰልፋቸው ይህን ስውር የ"New Age" ዕሳቤን በውል የተገነዘቡት አይመስለኝም።

የዳዊት ድሪምስ አስተምህሮ ምሰሶ የሆነችው ሮንዳ በርን በደረሰችው መፅሐፍና ቪዲዮ ውስጥም ተመሳሳይ ሐሳብ በግብረ አባሯ "James Ray" ተቀምጧል። "James Ray" በመፅሐፉ ስለ "አላዲን መብራት" በተረከበት...አላዲን የተባለ ልጅ ኩራዙ ላይ የተከማቸውን አቧራ በሚያስወግድበት ቅፅበት ጂኒው(The Genie) የአላዲንን መሻት ለማስፈፀም ተአምራዊ በሆነ ሁኔታ ይከሰትና የልጁን መሻት (Wishes) ለመስጠት "Your wish is my command!" በማለት ቃል ይገባል።

የአፈታሪኩን ዝርዝር ለጊዜው እናቆየውና ዋና ጥያቄው በ"New Age" ዕሳቤ መሠረት ተከታዮቹ በስበት ሕግ በውስጣቸው የፈጠሩትን አብርሆት (ኩራዝ) ተጠቅመው መሻታቸውን ወደ ዩኒቨርስ በሚለቁበት ወቅት ዩኒቨርስ ለጥያቄአቸው ምላሽ ይሰጥ ዘንድ ጣልቃ ገብቶ ሰዎችን፣ ሁኔታዎችንና ሁነቶችን የሚያመቻችላቸው "ጂኒ"(The Genie) ማን ይሆን? የ"New Age Thought" ዕሳቤ የስበት ሕጉ እስከሰራ ድረስ ለዚህ ጂኒ ማንነት ግድ የለውም፤ ሁሉም እንደየመረዳቱ ለጂኒው የራሱን ስያሜ እንዲሰጥ ተፈቅዶለታል። ክርስቲያኖቹና ሙስሊሞቹ ለዚህ ጂኒ "ጠባቂ መልአክ" የሚል ስያሜ ሊሰጡ ይችላሉ፤ ለሌሎች ደግሞ ጂኒው የላቀው ማንነት(Higher self) ሊሆን ይችላል። ለሳይታኒክ እምነት ተከታዮች ደግሞ ጂኒው ዲያቢሎስ ሊሆን ይችላል። የ"New Age" ዕሳቤ መምህራን የሁሉም እምነት ተከታዮች ለጂኒው እንደየእምነታቸው የመሰላቸውን ስያሜ እንዲሰጡ ይፈቅዱላቸዋል፤ እንግዲህ ይህ የተፃፈው በሮንዳ በርን መፅሐፍ ውስጥ ነው፤ እንደሚከተለው ይነበባል፦

"Remember Aladdin is the one who always asks for what he wants. Then you’ve got the Universe at large, which is the Genie. Traditions have called it so many things—your holy guardian angel, your higher self. We can put any label on it, and you choose the one that works best for you, but every tradition has told us there’s something bigger than us. And the Genie always says one thing: 'Your wish is my command!'

ከላይ በጠቀስኩት ውስጥ "We can put any label on it, and you choose the one that works best for you..." የሚለውን አስምሩልኝ። "The New Age Thought" ወጥ የሆነ ዓለም አቀፍ አቃፊ እምነትን በመቀመር የግለሰብን አልፎ ተርፎ የዓለምን ሰላም ማስጠበቅ ይቻላል የሚል ዕሳቤ ነው ስንል በምክንያት ነው።

በመጨረሻም አንድ እውነት ላስምር፦ ይህን አስተምህሮ የሚከተሉ ሰዎች በሙሉ ይህን የዕሳቤውን ስውር ተልዕኮ በተለይ ጅምር ላይ ያውቁታል ማለት አይቻልም፤ አብዛኛው ሰው አስተምህሮውን የሚደግፈው አዕምሮውን ከጊዜያዊ ችግሮች አፋትቶ ዘና ስለሚያደርገው እንጂ የ"New Age" ዕሳቤ ዓላማና ግብ እንዲሁም ከበስተጀርባ ያለው ተልዕኮ ገብቶት አይደለም። በሂደት ግን ሁሉም ይገለጣል። አሜሪካ ውስጥ በተደረገው ጥናት ራሳቸውን ክርስቲያን ብለው ከሚጠሩት መካከል 60% አውቀውም ይሁን ሳያውቁ የዚህ አስተምህሮ ተከታዮች ሆነው እንደተገኙ በ"Law of Attraction : A Gateway Drug to Spiritual Heroin Jon Clash, 2023" መፅሐፍ ውስጥ እንደሚከተለው ተቀምጧል፦

"We now live in a time when millions of people, as well as most Christians, usually unknowingly, hold to at least one major New Age teaching that conflicts with standard, traditional, Bible teaching.

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ዴይስቶቹ

ዴይዝም (Deism) በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው ግንኙነት "በመገለጥ" (Revelation) ላይ ሳይሆን "በአመክንዮ" (Reason) ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት ብሎ የሚያምን በዘመነ "አብርሆት" (enlightenment) የምዕራቡን ዓለም አስተሳሰብ ቅርፅ ያስያዘ "ሃይማኖት ቅብ" ፍልስፍና ነው። የፍልስፍናው ተከታዮችም በስነ መለኮት ምሁራኑ ዘንድ "ዴይስቶች" ተብለው ይጠራሉ።

ታዲያ ዴይስቶቹ ትምህርታቸውን የሚጀምሩት "አፅናፈ ዓለሙን የፈጠረው ፈጣሪ አለ" ብለው ነው። ነገር ግን "ይህ ፈጣሪ መላ ዓለሙን ከፈጠረ በኋላ የፈጠረውን ፍጥረት በሙሉ "ለተፈጥሮ ህግጋት" አሳልፎ ሰጥቶታል። ስለዚህ ፈጣሪ በዕለት ተዕለትም ሆነ በአጠቃላዩ የሰው ህይወትና ኑሮ ውስጥ ጣልቃ እየገባ የሰውን ህይወት አይመራም አይቆጣጠርም። ፍጥረተ ዓለም የሚተዳደረው በራሱ "የተፈጥሮ ህግጋት" ነውና ብለው ያስተምራሉ።

ዴይስቶቹ ይህንኑ አቋማቸውንም በምሳሌ ሲያስረዱ፤ "እግዚአብሔርን እንደ ሰዓት ሰሪ ቁጠሩት" ይላሉ። ሰዓት ሰሪ ሰዓቱን ይሰራና ይሸጥልናል እኛም ሰዓቱን ይዘን ወደ ቤታችን እንሄዳለን። ሰዓቱም በራሱ ጊዜ ይዞራል (ይቆጥራል) እንጂ ሰዓት ሰሪው ቤታችን እየተመላለሰ አያዞርልንም። "ፈጣሪም" እንዲሁ ነው፤ ተፈጥሮን ፈጠረና "ለተፈጥሮ ህግጋት" ሰጠው። "የተፈጥሮን ህግጋት አውቀህ መኖር ታዲያ የአንተ ድርሻ ነው። ህይወትህ በእጅህ ናት! ማለታቸው ነው። ዴይስቶቹ።

በነገራችን ላይ ዴይዝም "የቃል እምነት" ወይም "የብልፅግና ወንጌል" ስሁት አስተምህሮ "ቅድመ አያት" ነው። ለዚያ ነው ከቃል እምነት መምህራን መካከል እንደ ማይልስ ሞንሮይ ያሉት "እግዚአብሔር በምድር ላይ የሚሰራው እኛ ስንፈቅድለት ነው" በማለት እግዚአብሔር በምድር ባለ ጉዳይ "አያገባውም" የሚል ዓይነት የድፍረት ቃል የሚጠቀሙት። እንዲሁም "በአንደበታችን ቃል" (word of faith) "የተፈጥሮ ህግጋቱን" አንቀሳቅሰን የምንፈልገውን ሁሉ ማግኘት እንችላለን የሚሉት ። (ትይይዙን በቀጣይ ልጥፍ እመለስበታለሁ)

ችግሩ ምንድነው?

ታዋቂው የስነ መለኮት ምሁር ኤን. ቲ. ራይት "ዴይዝም የኤቲዝም (እግዚአብሔር የለሽነት) ምንጭ ነው ብሎ ያምናል። ራይት ሲናገር "ዴይዝም በመጀመሪያ የመፅሐፍ ቅዱሱን እግዚአብሔር እንደ ባላባት (Landlord) እንድትቆጥረው ያደርግሃል። ቀጥሎ ይህ ባላባት (Landlord) የሆነ እግዚአብሔር በሰርክ ኑሮህ ውስጥ የለም ይልሃል። በመጨረሻ እግዚአብሔር ራሱ የለም ይልሃል" ብሏል። እውነቱን ነው። እግዚአብሔር በሰርክ ህይወታችን ላይ መሪ እና ተቆጣጣሪ ካልሆነ በጊዜ ሂደት "እግዚአብሔር የለም!" የማንልበት ምንም ምክንያት አይኖርም። ስለዚህ አንዱ እና ትልቁ ችግር ዴይዝም "ለእግዚአብሔር የለሽነት" አስተሳሰብ መንገድ ጠራጊ መሆኑ ነው።

ሌላው ችግር፤ ዴይስት (Deist) ስትሆን "ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን" ብለህ መፀለይ አለመቻልህ ነው። "እግዚአብሔር በሰማይና በምድር የወደደውን አደረገ" ብለህም አታመሰግንም። "እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ" እያልህ ለእግዚአብሔር ስልጣን እውቅና አትሰጥም። ዴይስት ስትሆን ተንበርክከህ "ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ?" ብለህ እግዚአብሔርን አትለምንም። "እግዚአብሔር እረኛዬ ነው" ብለህም አትዘምርም።

ዴይስት ስትሆን "እግዚአብሔር ምን ይፈልጋል" ሳይሆን "እኔ ምን እፈልጋለሁ" ብለህ ነው ህይወትህን የምትቃኛት። በአይምሮህ ብቻ ነው የምትመራው። ዴይዝም በተፈጥሮ ህግጋት ተጠቅመህ የመረጥኸውን ማምጣት የጠላኸውን ማስወገድ የምትችልበትን ሃይል እንደ ተጎናፀፍህ እንድታስብ ያደርግሃልና።

በአጭሩ "ዴይዝም" በክርስትናችን ውስጥ መሠረታዊ የሆነውን "እግዚአብሔርን የመታዘዝ" እና "ለእግዚአብሔር ክብር" የመኖር ፍላጎታችንን የሚቀማና "ትዕቢተኛ" የሚያደርግ ክፉ ትምህርት ነው።

ከስር በፎቶው ላይ የምትመለከቷቸው ዳዊትም እና ዳጊ "ዴይስቶች" እንደሆኑ "በአወንታዊ የአስተሳሰብ ሃይል የተፈጥሮ ህግጋትን በመጠቀም ሃብትም ሆነ የምትፈልገውን ነገር ሁሉ" ማግኘት ትችላለህ" በሚለው ዘውትራዊ ትምህርታቸው እና "አነበብናቸው፣ መመሪያዎቻችንም ናቸው" በሚሏቸው መጻሕፍት እንዲሁም "ጀግኖቻችን ናቸው!" እያሉ በሚጠቅሷቸው ሰዎች በቀላሉ መለየት ይቻላል። ዶ/ር ወዳጄነህም በተለያዩ መድረኮች ላይ በሚያቀርባቸው መርኸ አልባ (አይጨበጤ) "አነቃቂ" ንግግሮቹ እንዲሁም ከዳዊትና ከዳጊ ጋር ከፈጠረው ጥምረት ዴይስት እንደሆነ ማወቅ ይቻላል። (ታዲያ ጥንታዊያኑ ዴይስቶች በፎቶው ላይ እንደሚታዩት እና መሰሎቻቸው በገንዘብና በዝና ፍቅር የወደቁ ነበሩ ለማለት አይደለም)

ስለዚህ ሰሞነኛው የሶስቱ ሰዎች ጥምረትና ዘመቻ ምንም እንኳ ዓለማዊ (Secular) ቢመስልም፤ "ሃይማኖት ቅብ" የሆነው፣ "ፈጣሪ" ወይም "አምላክ" የሚሉ ቃላትን ለማታለያነት የሚጠቀመው፣ "ለአዲሱ አስተሳሰብ" (New Tought) እንዲሁም "ለቃል እምነት እንቅስቃሴ" መሠረት የሆነው
"የዴይዝም" (Deism) ፍልስፍና በሀገራችን እየተስፋፋ መምጣቱን አመላካች ስለሆነ ቅዱሳን ወገኖች በተለይ ወጣቶች "ከቃል እምነት" ስሁት ትምህርቶች ብቻ ሳይሆን እንዲህ ካለ ዘመናዊ አስተሳሰብ መስሎ ከሚቀርብና ወደ "ትዕቢት" ብሎም ወደ "ክህደተ እግዚአብሔር" ከሚመራ "የዴይስቶች" ትምህርት ተጠበቁ ለማለት እወዳለሁ።

ከዴይስቶቹ ተጠበቁ!!

ቴዎድሮስ ተጫን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ብስለት ያጡ አስተምህሮቶችን እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የጐደላቸው ሥነ ምግባራዊ አካሄዶችን ልናሰወግድ ይገባል።

በእነዚሁ ሁለት ታላላቅ ቤተ-እምነቶች ውስጥ ያለው የእርስ በርስ መከፋፈል፣ ጐሣዊ፣ ብሔርተኛና ፖለቲካዊ ጽንፈኝነትን የተላበሰ መሆኑ፣ የአገሪቱን ፈርጀ ብዙ መከራ የበለጠ አክብዶታል። በማኀበራዊ መገናኛ ብዙኀን፣ ከሁለቱም ወገን የሚሰሙት፣ ብስለት የጐዳለቸው የግለሰብ አመለካከቶች ሁለቱን ቤተ-እምነቶች ሊወክሉ አይገባም። የጋራ ድንበር ላይ በመቆምና በተሻለ መቀባበልና መከባበር፣ ለአገራችን ፈውስ ዘለቄታ ዐብረን መሥራት ይኖርብናል።
ልክ እንደዚሁ በአገራችን ክርስትናና እስልምና ሃይማኖቶች መካከል የኖረውን አንጻራዊ ሰላምና መቻቻል፣ ከምንጊዜውም በላይ ከአክራሪነት አደጋዎች ልንጠብቀው ይገባል። የኅሊናና የማሰብ ነጻነት፣ ዐሳብን የመግለጥና ያሹትን እምነት መከተል ወይም መለወጥ በምንም መልኩ ሊፋቁ የማይገባቸው ለሰው ልጆች ሁሉ የተሰጡ አምላካዊ ስጦታዎች ናቸው። ይህንን ቤተ እምነቶችም ሆኑ ቤተ መንግሥት በንቃት ሊጠብቁት ይገባል። የእምነት መሪዎች፣ በውጥረቶች መካከል በጋራና በልብ ስፋት ጣልቃ እየገቡ የሰላም ድልድይ በመሆን ሕዝባችንን አንድ ያድርጉ! ሰላምን የሚያወርዱ ብፁዓን ናቸውና! በሕዝቦች መካከል ጥላቻን የሚዘሩ የሃይማኖት መሪዎች በራሳቸውም ላይ ሆነ በአገር ላይ ፍርድን ከሚያመጣ እኵይ ተግባር ሊታቀቡ ይገባል። እግዚአብሔር ያያልና!

7️⃣ የአገር ለውጥ የእያንዳዳችንን የልብ ለውጥ ይጠይቃል። ሰላም፣ ዕርቅና ፈውስ የሁላችንንም ድርሻ ይጠይቃል።

በመጨረሻም፣ ብዙ ተግዳሮቶችን እንዳሳለፈ ሕዝብ፣ አገራችን በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ማዕቀፍ ውስጥ እንደተያዘች ልንዘነጋ አይገባም። ወደ እርሱ እንመለስ፣ ተስፋችን ነውና። ይፈውሰን፤ በብርሃኑና በእውነቱም ይምራን!

አሜን!

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

እንደ አገር ካለንበት እጅግ የተወሳሰቡ ችግሮች የተነሣ በሰላም ዕጦት፣ በፍርሓትና በስጋት ልባችን ከብዷል። በልዕልናው በዙፉኑ ላይ ወደ ተቀመጠው እግዚአብሔር ስለ ምሕረት፣ ስለ መለኮታዊ ጣልቃ ገብነትና ትድግና ያለተቋረጠ ጸሎት እናደርጋለን። ተስፋችን እርሱ ነውና! በተለየ ዐውድም ቢሆን፣ የግፉዓን ጩኸትና ጥልቅ የልብ ሐዘን የነቢዩ ኤርምያስን ሰቆቃ ይጋራል።

"የሕዝቡ ልብ፣ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፤ ቀንና ሌሊት፣ እንባሽ እንደ ወንዝ ይፍሰስ፤ ለራስሽ ዕረፍትን አትስጪ፣ ዐይኖችሽ ከማንባት አያቋርጡ። የሌሊቱ ሰዓት ሲጀምር፣ ተነሺ በሌሊት ጩኺ፤ በእግዚአብሔር ፊት፣ ልብሽን እንደ ውሃ አፍስሺ፤ በየመንገዱ ዳር ላይ፣ በራብ ስለወደቁት፣ ስለ ልጆችሽ ሕይወት፣ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ። አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ እይ፤ ተመልከትም፤" (ሰቆቃ 2፥18-20)

ለውጡን ተከትሎ ያየናት የተስፋ ፀሓይ፣ በመከፋፈል፣ በመወጋገድ፣ በጥርጥር በዐመፅና በመከራ የዑደት ጽልመት ተጋርዳለች። የዕርቅና የፈውስ አዝጋሚ ረጅም መንገድ ውሉ እንደ ጠፋ ማግ ተወሳስቧል። ጐሣዊና ሃይማኖታዊ ጽንፈኝነቶች ሥር ሰደዋል፤ ፈሪሓ እግዚአብሔር ርቈናል። የአስከፊ የድኽነታችን ቀንበር ክብደቱ የኑሮው ውድነት ይገልጠዋል። እንደ ፈረንጆቹ አቈጣጠር በ 2018 ዓ. ም የኢትዮጵያ የሰው ዕድገት መለኪያ (Human Development Index) 173/189 ሲሆን፣ በ2022 ዓ. ም ላይ ደግሞ 175/191 ነበር። በሙስና ደግሞ በእነዚሁ ዓመታት ውጤታችን ከመቶ 33 እና 34 ነበር። የሰሜኑ ጦርነት 1.5 ትሪልዮን ብር አስከፍሎናል፤ እስከ አንድ ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ ብዙዎችም አካላቸው ጐድሏል። ይህን አኃዝ ይፋ ያደረጉት የጦርነቱ ተዋናይ የነበሩ አካላት መሆናቸውን ልብ ይሏል። በ 2023 ካለን ዓመታዊ ጥቅል ምርት አንጻርም ዕዳችን እስከ 54% እንደሚደረስ ይገመታል። ጊዜ ቢፈጅም፣ የፈረሱ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና የመሠረተ ልማት አውታሮች ተመልሰው ይገነባሉ። የአካልና የሥነ ልቡና ጕዳተኞች ፈውስ ግን እጅግ አዝጋሚ ነው። ከሁሉም በላይ በሕዝቦች መካከል የፈረሱ ማኅበራዊ መስተጋብሮችን ለመገንባት የእግዚአብሔርን ርዳታ በብዙ ይፈልጋል።

ፓለቲካችን በብዙ ተቃርኖ ክፉኛ ታሟል። በታሪካችን ሰላማዊ የሆነ የሥልጣን ሽግግር የለንም፤ በደም የተለወሰ እንጂ። የአገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ ፓለቲካዊ ታሪክ እንደሚያሳየን፣ ነጻ አውጪዎች፣ የሥልጣን መንበር ለመያዝ ሲታገሉም ሆነ ሥልጣን ሲጨብጡ እንዲሁም ሲወድቁ የበለጠ አስጨናቂ ይሆናሉ። ለንጹሓን ደም መፍሰስ፣ ለሕዝብ መጨነቅ፣ መመረርና በሰቆቃ ውስጥ መኖር ምክንያት በመሆን የዐመፅ ዑድቱን ያስቀጥላሉ።

ዐድዋ የኢትዮጵያዊ ማንነታችንና የአንድነታችን መለያ አንዱ ምልክት ብቻ ሳይሆን፣ የመላው ጥቍር ሕዝብ ኵራት የነጻነት ተምሳሌት መሆኑን ለ127 ዓመታት ዘክረናል። ይህ አግባብ ነው። ሆኖም የቅኝ ግዛት ባርነትን አሻፈረኝ ብለን፣ የዘረኝነት፣ የቂምና የጥላቻ ባሪያዎች ሆነናል! “በልማት” ሰበብ በሺሕዎች የሚቈጠሩ ተፈናቅለዋል፤ በገዛ አገራቸው ቤተ አልባና ተንከራታቾች ሆነዋል። ለብዙዎች ዕልቂት ምክንያት ከሆነው ጦርነት ማግሥት ምሕረት አድርገናል፤ ለሰላምም አስተዋጽዖ አድርገዋል ላልናቸውና ቀድሞ በጠላትነት ለፈረጅናቸው ሽልማት ሰጥተናል። በአንጻሩ፣ “ሕገ ወጥ” እንኳ ቢሆኑም የብዙ ድኾችን ቤት ያለርኅራኄና ያለ አማራጭ መፍትሔ አፍርሰናል። እናቶችንና ሕጻናትን ሜዳ ላይ በትነናል። ለብዙዎች ዋይታና እንባ ልባችን አልራራም። የ “እውነት” ነባራዊ ዋጋ በፓለቲካዊ ወይም በገንዘብ ጥቅም ተሸርሽሯል። ይህ ትልቅ ምጸት ነው።

በመልካም አስተዳደር ዕጦት፣ በፍትሕ ጥሰት፣ በተደራጀ የአገር ዘረፋ፣ በገዛ አገር ስደተኝነት አስከፊ ከሚባሉት አገሮች አንዷ የእኛዩቱ ኢትዮጵያ ናት ቢባል ፈጽሞ ማጋነን አይሆንም። በዚህች ምድር፣ ሰው በዘሩ ብቻ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቈጥሮ የሚፈናቀልባት ምድር ሆናለች። በፌደራልና ክልላዊ አስተዳደር መካከል ሊኖረው የሚገባው ጤናማ፣ ተኣማኒነትና ተደጋጋፊት ያለው የኀይል ሚዛን፣ “ብቻዬን፤ ወይም “የእኔ ብቻ” የሚል ንፉግነት በተጠናወተው የዘር ⶒለቲካ ተናግቷል። በአንድ ወቅት ዓለምን ያስደመመው የሰላም፣ የፍቅርና የብሔራዊ አንድነት መነቃቃቶች ዛሬ እጅግ ከከረረ “ክልላዊነት” ጋር ግብ ግብ ፈጥረዋል። የሰሜኑ ጦርነትና እንዲሁም በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በጋምቤላና በሌሎችም ቦታዎች ያሉ ግጭቶች ለዚህ ጥሩ ማሳያ ናቸው። እንደ ኢትዮጵያ የብዙ ብሔሮችና ቋንቋዎች መናኸሪያ ለሆነች አገር፣ በምንም የማይተካው ውድ እሴት መተማመን ነው። የሰው ኑባሬአዊ ዋጋ በቀዳሚነት ሰው - “አምሳለ መለኮት (አርአያ ሥላሴ)” መሆኑ ቀርቶ፣ ወደ ጐሣና ሃይማኖታዊ ጐራ ዝቅ እያለ የሄደበት የአገራችን ፓለቲካ፣ ይህን “መተማመን” ሸርሽሮታል። ሳይረፍድ ልብ ልንል ይገባል።

ቢያንስ ከእስክንድርያ ከተማ በቅዱስ አትናቴዎስ የተሾሙት የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ጳጳስ፣ አባ ፍሬምናጦስ (ከሣቴ ብርሃን፣ አቡነ ሰላማ) ጀምሮ ያለውን የታሪክ መገንጠያ ካሰብን፣ ክርስትና አገራችን ከገባ 1700 ዓመታት ሊያስቈጥር ነው። የኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ ታሪክ ታሳቢ ካደረግን ደግሞ ወደ 1980 ዓመታት ይደርሳል። ብዙ የአስተምሮ ልዩነት ቢኖረንም ሰው አምሳለ መለኮት መሆኑን ኦርቶዶክሳውያን፣ ፕሮቴስታንቶችና ካቶሊካውያን በጋር እናምናለን። የአገራችን አብላጫው ሕዝብ ክርስቲያን ነው። ሆኖም ዘረኝነትን መሠረት ያደረገ የክፍፍል ጽልመት ያጠላባት አገራችን፣ "አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፤ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፤ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና" (ገላ 3፥28) የሚለው የወንጌል ቃል፣ በጥብቅ የሚሞግታት ምድር እየሆነች መምጣቷ ከሁላችንም የተሰወረ አይመስለኝም። ይህ ትልቅ ስብራት ነው። ይህም በሕዝቦች መካከል ሊኖር የሚገባውን መግባባት አስቸጋሪና የግንኙነቶቻችንን ፈውስ ሩቅ ያደርገዋል።

እኔ አባል የሆንሁበት የወንጌላዊው ክርስትና አማኞች ቍጥር ወደ 25% ደርሷል የሚል ግምት አለ። ከአራት ኢትዮጵያዊ አንዱ የወንጌል አማኝ ነው ማለት ነው። ይህም የእግዚአብሔር ቸርነት ነው። ክብር ለስሙ ይሁን! ሆኖም ያለንበት ፈርጀ ብዙ ቀውሶች፣ ተሐድሶ እንደሚያስፈልገን በግልጽ ያሳዩናል። በእኛ መካከል ያለው ወንጌልን ከፓለቲካና ከባሕል ጋር ያጋባ ቅይጥ መንፈሳዊነት፣ የአስተምህሮና የሞራል ቀውስ ለምድራችን ተጨማሪ ስብራት ሆኗል። በአብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለው መከፋፈል፣ ክብርና ሞገስ እየራቀው ያለው የአብያተ-ክርስቲያናት አመራር፣ አገርን እያመሰ ያለው ዘረኝነት፣ እንዲሁም ቅዱሱ መጽሐፍ እንደ “ግድያ” የሚያየው ወንድምን የመጥላት አባዜ፣ የዚህ "ዕድገት" ተቃርኖ እየሆኑ መምጣታቸውን በትሕትና ልንገነዘብ ይገባል። ውጭ ሲዘንብ ወደ ቤት ይሸሻል፤ የቤት ጣራ ካፈሰሰ ግን ወዴት ይኬዳል? ዘረኝነትን ከምስባካችን እንቃወመዋለን፤ ምስክርነታችን ግን ተኣማኒነት በማጣት ተጐድቷል። ስለ አንድነት እንሰብካለን፤ እርስ በርስ እንወጋገዳለን። ፍቅርን ከአደባባይ እናውጃለን፤ ሆኖም በተመጣጣኝ ተግባር የታጀበ ባለመሆኑ ከንግግር ብዙ ያለፈ አይደለም። ንስሓ እንገባለን፤ ፍሬው ግን አናሳ ነው። የእግዚአብሔርን ምሕረት አጥብቀን እንድንሻ ግድ ከሚሉ ብዙ ተቃርኖዎች ጋር እንታገላለን።

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ማለዳ ላይ ለጥቂት ጊዜ ታይቶ እንደሚረግፍ ጤዛ፣ እንደሚያልፍ ጥላ ወይም ለጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፋሎት በተመሰለው በዚህች ምድር አጭር ሕይወት፣ ቢመችም፤ ባይመች እንደ እግዚአብሔርን ቃል መኖር ትልቅ ማትረፊያ ነው። የጌታን ቃል በትክክል መረዳት፣ መስማት መታዘዝና ለትውልድም በታማኝነት በዐደራ ማሳተላለፍ፣ የዘላላማዊትን መዳረሻ ይወሰናል።

የምድራዊ የኑሮአችን ዋስትና የተመሠረተው የምንኖርበትን አገር ሕጐች በማክበር ላይ ነው። ከዚያ የላቀው ግን እንደ እግዚአብሔር መንግሥት ዜጐች መኖራችን ነው። የሕይወታችን መገኛውም ማብቂያውም በእርሱ እጅ የሆነውን እግዚአብሔር መስማትና ያለመስማት፣ በዚህ ምድር ላይ "ወሳኝ" የምንላቸውን ማናቸውንም ውሳኔዎች ሁሉ ነቁጥ የሚያደርግ የውሳኔዎች ሁሉ ታላቅና በያኝ ውሳኔ ነው። ዘላለማዊነትን የሚወስን ነውና!

“እንግዲህ ይህን ቃሌን ሰምቶ በተግባር የሚያውል፣ ቤቱን በዐለት ላይ የሠራን ብልኅ ሰው ይመስላል። ዶፍ ወረደ፤ ጐርፍም ጐረፈ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ያንን ቤት መታው፤ በዐለት መሠረትም ላይ ስለ ተመሠረተ አልወደቀም። ይህን ቃሌን ሰምቶ በተግባር የማያውለው ግን ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራን ሞኝ ሰው ይመስላል። ዶፍ ወረደ፤ ጐርፍም ጐረፈ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ያንን ቤት መታው፤ ቤቱም ወደቀ፤ አወዳደቁም የከፋ ነበር።” (ማቴ 7፡24-27)

🔨 ሁለቱም ቤቶች ነበሩ - ልዩነታቸው ግን መሠረታቸው ነበር
🔨 ሁለቱም የሰው መኖሪያ ነበሩ- አንደኛው ጊዜአዊ፤ ሌላኛው ቋሚ
🔨 ሁለቱም ቤቶች ነበሩ - አንደኛው አወዳደቁ የከፋ፣ ሌላኛው እንደጸና የቀረ
🔨 ሁለቱም ቤቶች ተመሳሳይ ፈተና ደርሶባቸዋል - አወዳደቁ ለከፋውም ሆነ ጽንቶ ለቀረውም ዋነኛ ምክንያቶች *የማይታዩት* መሠረቶች ነበሩ
🔨 የቤቶች ባለቤቶች እንዴት "ቤታችውን" መሥራት እንዳለባችው ሰምተዋል - መታዘዝ፣ ማድረግ፣ ሆኖ መገኝት ፍጻሜአቸውን ወስነዋል
🔨 ሁለቱም የተመሠረቱበት "ጥበብ" አለ - አንደኛው በራሱ ሞኝነት ላይ፤ ሌላኛው በአሠሪው ጥበብ ላይ።

እግዚአብሔር በወሰነው አንድ ቀን፣ በፍርዱ ዙፋን ሥር መቆማችን፣ "የይሆናል ወይም የአይሆንም" ጥያቄ ሳይሆን "የመቼ" ጉዳይ ነው። የፍርዱ ዶፍ ይወረዳል፤ ጐርፍም ይጐረፋል፤ ነፋሱም ይነፍሳል፣ ቤታችን ጸንቶ ይቅር ይሆን? የዚህን ጥያቄ መልስ ጌታችን እራሱ እንዲህ ሲል መልሶታል፤-

"እንግዲህ ይህን ቃሌን ሰምቶ በተግባር የሚያውል፣ ቤቱን በዐለት ላይ የሠራን ብልኅ ሰው ይመስላል።"

የፍርድ ቀን ታልቅ መደነቅን፣ እንዲህ ሲል አስቀድሞ ተናገሯል፡-

“በዚያ ቀን ብዙዎች፣ ‘ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህ አጋንንት አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ታምራት አላደረግንምን?’ ይሉኛል።’ በዚያ ጊዜ፣ ‘ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንት ክፉዎች፤ ከእኔ ራቁ’ ብዬ በግልጽ እነግራቸዋለሁ።’’
(ማቴ. 7:22-23 )

ስለዚህ፣ በዚህ ምድር ላይ ብርቱና ወሳኙ ጉዳይ፣ ዊሊያም ቲንዴል እንዳለው፣ "የፓፓው፣ የቢሾፑ፣ ወይም የእነርሱ ኅይል መገለጫ የሆኑት የነገሥታት፣ የልዑላንና የአገር ገዢዎችቃል አይደለም፤ የክርስቶስን ቃል መስማትና ያለመስማት ነው!" በአገርኛ፣ “የነቢያት፣ የመጋቢዎች፣ የሽማግሌዎች” እንደ ማለት ነው።

ክርስትና በእግዚአብሔር ፊት የሚኖር ኑሮ ነው፤ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ራስን ማግኘትና "በቤተ ክርቲያን" መዋቀር ውስጥ፣ መገኝት፣ አባል መሆን፣ ወንበር፣ ስምና ዝና ይዞ ማገልገል" ለየቅል ናቸው። የቤተ ክርስቲያና አባል መሆንና ማገልግል ምንም ፋይዳ የላቸውም ማለቴ ግን ፈጽሞ አይደለም። ይህ እጅግ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን፣ መጸሐፍ ቅዱሳዊም እውነት ነው። ሆኖም፣ በቤተ ክርስቲያን "ግቢ" እየተኖረ፣ ከዋናው "ግቢ" - ከእግዚአብሔር መግሥት መታጣት ይቻላል። ዋስትናችን ዐለቱ ክርስቶስ ላይ መቆማችን ብቻ - ይኽ ብቻ ነው! ሐዋርያው ጳውሎስ፣ የቆርንቶስን አማንያን በብርቱ ያስጠነቀቀበት ጉዳይ ነው፡

". . . እያንዳንዱ እንዴት እንደሚገነባ መጠንቀቅ አለበት። ምክንያቱም አንድ ጊዜ ከተመሠረተው መሠረት በቀር ሌላ መሠረት መጣል የሚችል ማንም የለም፤ ይህም መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ማንም በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ወይም በብር፣ በከበረ ድንጋይ ወይም በዕንጨት፣ በሣር ወይም በአገዳ ቢያንጽ፣ ሥራው እንዴት እንደሆነ ይታያል፤ ምክንያቱም ያ ቀን ወደ ብርሃን ያመጣዋል። በእሳት ስለሚገለጥ እሳቱ የእያንዳንዱን ሰው ሥራ ምንነት ይፈትናል።" (1ቆሮ. 3:10-13)

ወገኖች፣ በብርቱ እናስብ፤ “ክርስትና” ብለን የቆምንበት መሠረት ምን ይሆን? ሕይወታችንስ በእግዚአብሔር ፊት ምን ይመስላል? "ጌታ ሆይ፣ የቆምንበትን መሠረት እንድንፈትሽ እርዳን፤ ወደ ራስህም መልሰን።"
~ አሜን!

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ግለሰቡ እስካሁንም ተስፋ ሳይቆርጥ በሃሳቡ ገፍቶበታል። የገዛ ይዞታችንን እና ንብረታችንን የራሱ ለማድረግ ጥረቱን ቀጥሏል። እስካሁንም ቤቱና ቦታው የራሱ እንደሆነ ዓይነት ነው አክት እያደረገ ያለው። በዚህም ምክንያት በተለያዩ አካላት ማስፈራራትና ዛቻ እንዲደርስብኝ እያደረገ ይገኛል።...." ብሎኛል።

የዚህ "እርስትህን ሽጥልኝ አልሸጥም" ክርክር የናቡቴን እና የንጉሥ አክዓብን ታሪክ አስታወሰኝ ያልኩትም የመመሳለል ነገር ስላለው ነው። በእርግጥ የዚህኛው ታሪክ መጨረሻ ገና ስላልታወቀ ስለ ፍጻሜው ደምድሞ መናገር ባይቻልም ሁኔታው ግን ናቡቴ የሚባልን ሰው የወይን ቦታ ካልሸጥክልኝ ብሎ ግድ ያለውን ንጉሥ አክዓብ እና "የአባቶቼን እርስት አልሸጥም" ያለውን ናቡቴን ያስታውሰናል።

"ለኢይዝራኤላዊውም ለናቡቴ በሰማርያ ንጉሥ በአክዓብ ቤት አጠገብ የወይን ቦታ ነበረው። አክዓብም ናቡቴን፦ በቤቴ አቅራቢያ ነውና የአትክልት ቦታ አደርገው ዘንድ የወይን ቦታህን ስጠኝ፤ ስለ እርሱም ከእርሱ የተሻለ የወይን ቦታ እሰጥሃለሁ፤ ወይም ብትወድድ ግምቱን ገንዘብ እሰጥሃለሁ ብሎ ተናገረው። ናቡቴም አክዓብን፦ የአባቶቼን ርስት እሰጥህ ዘንድ እግዚአብሔር ያርቅልኝ አለው።..." እያለ ታሪኩ ይቀጥላል።" (መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ምዕራፍ 20ን በሙሉ ያነብቧል)

እነሆ ይኼን ጽሁፍ የምቋጨው የምድር ሕግም ከላይ ሆኖ የሚቆጣጠረው ሰማያዊ ዳኛ አለውና ፓስተር ተዘራ ያሬድ ደምሴ እየሄደበት ካለው የእልከኝነት መንገድ ተመልሶ ሕግን ያከብር ዘንድ "በሕግ አምላክ" በማለት ነው።

©ሽመልስ ይፍሩ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የ"ካውንሰሉ" ቀልዶች

ያው እንደሚታወቀው ካውንስሉ (ቆንስላው ይለዋል ዘሌ) ከተመሠረተበት ቀን ጀምሮ በርካታ ቀልዶችን አቅርቦልናል። የሰሞኑን ቀልዶቹን የሚተካከል ቀልድ ግን አልተገኘም። ታዲያ ሁል ጊዜ ለቀልዱ "መግለጫ" የሚል ስያሜ ነው የሚሰጠው። በእርግጥ አንዳንዶች የካውንስሉን መግለጫ "መግለጫ" ከማለት ይልቅ "ልግጫ" ብሎ መጥራት ይቀላል ይላሉ (ምህረት ያድርግላቸውና😂)። ለነገሩ እንደ ሲንገሌ ባሉ ቀልደኞች ተደግፎ የቆመ ካውንስል ቀልደኛ ባይሆን ነበር የሚገርመው።

የሆነው ሆኖ ብቻ በመግለጫው (በቀልዱ) እንደሰማነው ከሆነ "ካውንስሉ " ለአራት "ቤተክርሰሰቲያን" እያለ ለሚጠራቸው የዝርፊያ ተቋማትና ለመሪዎቻቸው እንዲሁም ለአንድ ግለሰብ ብሎም "የሲዳማ ነፃ አውጪ ነው" ላለው አካል ማስጠንቂያ ሰጥቻለሁ ብሏል። ሁለቱን "ቤተክርሰሰቲያን" በሚል የጠቀሳቸውን ቡድኖች ደግሞ ከአባልነት ማገዱንም ጨምሮ አሳውቋል።

ለቀልድ ችኮላ

ካውንስሉ ለቀልዱ (ለመግለጫው) በጣም የቸኮለ ይመስላል። አቀራረቡ በደንብ ያልታሰበበትና የይድረስ ይድረስ ነበርና። አንድ ማሳያ እንውሰድ፤ ለምሳሌ በመግለጫው የመጀመሪያ ገፅ አንቀፅ ሶስት ላይ "በፀጋ ስጦታዎች እና አጠቃቀማቸው" ላይ በአንዳንድ "ቤተክርስቲያን" (በስም አልተጠቀሰም) ባላቸው ላይ ይታያሉ ያላቸውን ችግሮች በሚዘረዝርበት ጊዜ "የፀጋ ስጦታዎች አጠቃቀም ችግር" ብሎ በአንደኝነት የጠቀሰው "ሚዛኑን ያልጠበቀ ስላሴያዊ አስተምህሮ" የሚል ነው። "የስላሴያዊ አስተምህሮ" ጉዳይ "ከፀጋ ስጦታዎች አጠቃቀም" ችግርነት መፈረጁ መግለጫው ያልታሰበበት መሆኑን ያሳያል። ወደ ቀልዶቹ ልውሰዳችሁ:-

ቀልድ 1

ቀዳሚው ቀልድ "ካውንስሉ በአስተምህሮ ግድፈት እና ልምምዶች ዙሪያ ችግር ያለባቸውን ጠርቶ በመምከር ዙሪያ ሰፊ ሰራ ሲሰራ ቆይቷል" ይላል

አስቡት እስኪ በብዙሃኑ የማይፈለጉ፣ በአሳችነት የተፈረጁ፣ የአስተምህሮና የልምምድ ችግር ያለባቸውን፤ ሌቦችና አሳቾችን ሰብስቦ "የወንጌላዊነት" ማዕረግ አጎናፅፎ ለቅቡልነታቸው ሲለፋ ከርሞ ሲያበቃ "መክረን አስመክረን" የምትለውን ሽሙጥ ይዞ ደግሞ መጣ። ቀልደኛ አይደለም ታዲያ? ቆይ እነማን ተመክረው ነው "አስተካከሉ'ኮ" የሚል ሞገስ የተደፋላቸው? ምንስ ይሆን ያስተካከሉት?

የካውንስሉ አባላት የሆኑት ሃሳዊያን እንደሁ በማጭበርበራቸው ቀጥለዋል። በተለይ ከሰሞኑ ጩፋ በዘይት ንግዱ ብሶበት የሀገር ውስጥ ገበያውን ካዳረሰ በኋላ ወደ ደቡብ አፍሪካ (ደቡብ ፋፍሪካ) አቅንቶ ሽያጩን አጧጡፎ ቀጥሏል። ካውንስሉም ደግሞ እንዳየነው የጩፋን አዳራሽና ስክሪን ሲመርቅ ነው የከረመው። ታዲያ ዛሬ ደርሶ "ተመክረው ተስተካከሉ" የሚለን እነማንን ነው? እየቀለደብን ካልሆነ በቀር።

ቀልድ 2

ቀጣዩ ቀልድ እንዲህ ይላል "እነዚህ ችግሮች ....የቤተክርስቲያንን ስም የሚያጠለሽ በማህበረሰቡ ዘንድ ያላትን (ቤተክርስቲያን) ተቀባይነት...ጥያቄ ውስጥ የሚከት...ቤተክርስቲያን በሀገር አቀፍ ደረጃ....ያላትን ሃላፊነት እንዳትወጣ እንቅፋት እንደሆኑ ካውንስሉ አምኖበታል" ይላል። (በመግለጫው ገፅ አንድ እና ገፅ ሁለት ላይ በአሁኑ ወቅት የሚታዩ ችግሮች ብሎ አስር ነገር ከዘረዘረ በኋላ)

ታዲያ ይሄ ቀልድ አይደለም ትላላችሁ? ያውም በትውልድ ላይ የተደረገ ቀልድ። ፀሃይ የሞቀውን ሀገር ያወቀውን ብዙዎች ሲጮሁበት የነበረውን ችግር ባልሰማ ሆኖ ከርሞ እነ ጩፋ፣ ጭሮ፣ ሚራክል፤ ተዘራ፤ ጃፒና ዘላለም ወዘተን ትቶ አንድ ጆሲን ብቻ የጦስ ዶሮ አድርጎ አቅርቦ (በእርግጥ እርሱ የበለጠ ይገባዋል)፤ ደርሶ "ያጠለሻል..እንቅፋት....ይሆናል" ይሉት የዓዞ እምባ ይዞ ብቅ አለ። ከቀለዱ አይቀር እንዲህ ነው እንግዲህ። ዋናውን ሌባ አቅፈህ ጀሌውን ማባረር። "አህያውን ፈርቶ..." እንዲሉ ማለት ነው። "እንቅፋት" ሲከምር የኖረው ካውንስል "እነ እገሌ እንቅፋት እየፈጠሩ ነው" ቢልህ ምን ትለዋለህ? "ቀልደኛ!!"

ቀልድ 3

ሶስተኛው ደግሞ አይጣል ነው "ምክር ሰምተው የተመለሱ እና በትከክለኛው የአገልግሎት ጎዳና ላይ የገቡ አሉ" ይላል። ቀልዱን ከፍ ወዳለ ደረጃ ሲያሳድገው።

እንግዲህ አስቡት መካሪው ካውንስሉ ነው። ተመካሪዎቹ ደግሞ እነ ሃሳዊያኑ ናቸው። ተመለሱ የተባሉት ደግሞ እነማን ናቸው? እነ ጩፋ ሚራክል እና ጭሮ ጃፒ ተዘራ ወዘተ መሆናቸው ነው። በእነርሱ ላይ ምንም አላለማ። ጉድ!! የቀልድ ደረጃው ከፍ ሲል ማለት ይሄ ነው እንግዲህ። የስህት ትምህርታቸውን፣ ዘይት ሽያጫቸውን፣ ገንዘብ አበዛ ነኝ ማለታቸውን እና ዘረፋቸውን ያላቆሙ ማፍያዎችን "ተመክረው ተመለሱ" ይልሃል። ተመክረው በዚህ ደረጃ አሳችና ዘራፊ ከሆኑ ባይመከሩ ምን ነበር የሚያደርጉት ማለት ነው?😂

ቀልድ 4

በእርግጥ የመግለጫው ዋና ዓላማ ጆሲ የተባለውን ዱሩዬ ለማገድ እንደሆነ ግልፅ ነው። የሚያስቀው ግን ጆሲን ለማገድ የቀረበው ምክንያት ነው። እንዲህ ይላል:- "ከመፅሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ውጪ የማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም የስሀተት ልምምዶችን በማሰራጨት ያልተገባ ገንዘብ መሰብሰብ" ይላል።

ያንን ሁሉ ዘራፊ ሃሳዌ ነቢይና መምህር ሰብስቦ ከያዘው ካውንስል እንዲህ ያለ የእግድ ሰበብ ሲናገር ቢሰማ "ካውንስል ሆይ ቀልድህ እኮ አይጠገብም" ከማለት ውጪ ምን ይባላል?

ለማንኛውም

የካውንስሉ ባለ አራት ገፅ መግለጫ ዋና ዓላማ መፅሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮና ልምምድን ለመከላከል ያለመ አይደለም። ካውንስሉ ቀድሞውኑ ወላጅ አባቱን እንጂ ርቱዕ እስተምህሮን ለመከላከል አልተቋቋመምና። ምክንያቱም ከሁሉ በላይ ያሳሰበው "ሁከትና ግጭት የሚፈጥሩ" የተባሉት የሃሳዊው ጆሲ ቃላት ናቸውና። ለዚያ ነው የከፉ ሃሳዊያንን ባላየ ወይም በተራ ማስጠንቀቂያ አልፎ ጆሲን ከአባልነት ያገደው። ተቋማዊ ቀልድ ማለት እንግዲህ ይህ ነው።

("ብቸኛው" ለተባለው የሲዳማው ልብ ወለድ ነፃ አውጪ ሳያጣራ የሰጠው ምላሽ ደግሞ አሳፋሪም አስቂኝም ነው።)

ቴዎድሮስ ተጫን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ሌላ ኢየሱስ… ልዩ መንፈስ… ልዩ ወንጌል

“የሚመጣውም ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ፥ ወይም ያላገኛችሁትን ልዩ መንፈስ ወይም ያልተቀበላችሁትን ልዩ ወንጌል ብታገኙ፥ በመልካም ትታገሡታላችሁ።” (2ቆሮ. 11:4)

1. “ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ” -
————————-
ከተሰበከው … መጽሐፍ ቅዱስ ከሚነግረን … የቀደሙን ምስክሮች እነጳውሎስ ከሰበኩት ጋር የማይመሳሰል ሌላ ኢየሱስ የሚሰብኩ አሉ።

Then, ሁል ጊዜ በመድረኮቻችን እየተሰበከ ስላለው ኢየሱስ ትክክለኛነት ወይም እውነተኛነት እርግጠኞች መሆን ይኖርብናል።

የተሰቀለውን ለሰው ልጆችም ኃጢአት የሞተውን ክርስቶስ ኢየሱስን ሳይሆን የሰውን ሥጋዊ ምኞትና ፍላጎት ለማሟላት የሚታዘዘውን ኢየሱስ እየተነሡ የሚልኩትን ኢየሱስ የሚሰብኩ ሸቀጣሞች ምትሐተኞችና አስመሳዮች ሰባኪዎች አሉ። እንደዚህ ያሉትን ሰባኪዎች አትታገሡ። እንደ ቆሮንቶሶች አትሁኑ።

2. “ልዩ መንፈስ ብታገኙ” -
—————————
ያላገኘነውን ልዩ መንፈስ ሊሰጡ የሚመጡ የክርስቶስ ያልሆነውን መንገስ የሚያከፋፍሉ የውሸትን መንፈስ የሚያሰራጩ አሉ።

ያኔ ክርስቶስን ስናምን ከተሰጠን ከታተምንበት ቅዱሱ መንፈስ ጋር የማይናበብ፣ ለክርስቶስ ተገዢ እንድንሆንና ትዕዛዙን አክባሪ እንድንሆን የማያበረታታንን መንፈስ ሊያስተላልፉልን የሚመጡ የልዩ መንፈስ አቀባዮች አሉ።

ክርስቶስን ወደመምሰል የማያሳድገን መንፈስ በተቃራኒው ግን ምድራዊና ቁሳዊ ፍላጎቶቻችንን እየተከተልን እንድንከንፍ የሚጠይቀን መንፈስ የሚያናፍሱ ራሳቸውንም እንደ መንፈስ የሚቆጥሩ ሰባኪዎች አሉ። ይህ መንፈስ ስሙ ብቻ ነው እንጂ ዓይነቱ ሌላ ነው። አትታገሡአቸው። እንደቆሮንቶስ አትሁኑ።

3. “ልዩ ወንጌል ብታገኙ” -
—————————-
ከክርስቶስና ከርሱ ታማኝ አገልጋዮች ከተቀበልነው ወንጌል የሚለይ፣ ሰምተን ከዳንንበት ወደ ሕይወት መንገድ ካመጣን ከጌታችንና ከመድኃኒታችን ወንጌል ጋር የማይጣጣም ልዩ ወንጌል ይዘው በየከተማው የሚዞሩ ሰባኪዎች አሉ።

የዘር የጎሳ የክፍፍል ወንጌል፣ የጥቅም የክብርና የዝና ወንጌል፣ የባሕል የልምድ የወግና የሥርዓት ብቻ ወንጌል፣ ስሜት ቀስቃሽ ብቻ ወንጌል፣ የፖለቲካ የኢኮኖሚ ማኅበራዊ ጉዳዮች ወንጌል … የሚሰብኩ ዙሪያችን ላይ ቁጥራቸው ከፍ እያለ ነው።

የተሰቀለውን ክርስቶስን የሚሰውር ወንጌል፣ አሰናካይና ወደ ኋላ ጎታች ወ ጌል፣ የግልሰቦችን ልምምድ ብቻ የሚያራግብ ወንጌል ይዘው ወደ ቤታችን፣ ወደ ሠፈራችን፣ ወደ ሀገራችን የሚመጡ ሰባኪዎችን አትታገሡአቸው። እንደቆሮንቶስ አትሁኑ።

ወርቅነህ ኮየራ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

https://youtu.be/BmJ4G2Di6Rw

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

"የሚጠሉኝ ሰዎች እኔን ሰድበው እንጀራ ይበላሉ!" ?

"እኔ በጣም የታደልኩ ሰው ነኝ። ለሚወዱኝ አገልጋይ ለሚጠሉኝ እንጀራ ያደረገኝ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን። የሚወዱኝን ሰዎች አገለግላቸዋለሁ፣ የሚጠሉኝ ሰዎች ደግሞ እኔን ሰድበው እንጀራ ይበላሉ፣ ኪሳቸው ገንዘብ ያስገባሉ። ይኼ ደግሞ የሚያሳየው ምን ዓይነት ዕድለኛና የተባረክሁ ሰው መሆኔን ነው። እናቴ እንዴት ብትመርቀኝ ነው።"

ይኼን ያለው ባለ ሐብቱ አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ነው። ከዚህ ቀደም በተናገራቸው በርካታ ትንቢቶች አለመፈጸም ላይ ለተነሳበት ሰሞነኛ ጥያቄ ምላሽ የሰጠበት ስለመሆኑ ቪዲዮውን አባሪ ያደረገው ወንድም ገልጿል። ሊንኩን በአስተያየት መስጫ ሳጥን ውስጥ አኖራለሁ። ከዮናታን ንግግር መሀል ትኩረቴን የሳበው ግን "የሚወዱኝን ሰዎች አገለግላቸዋለሁ፣ የሚጠሉኝ ሰዎች ደግሞ እኔን ሰድበው እንጀራ ይበላሉ፣ ኪሳቸው ገንዘብ ያስገባሉ።" የሚለው ነው። ጭብጡ ባልተገባ መንገድ ገንዘብ ማግኘትን የሚጠቁም ነው።

ይሁንና ከጥቂት ዓመታት በፊት ምንም ያልነበረውን፤ ቸርች በከፈተ አጭር ጊዜ ውስጥ ከሚሊዬነሮቸ ተርታ የተሰለፈውን ሰው የሀብት ምንጭና ምክንያት መጠየቅም አግባብ ነው። አሁን ላይ በእጁ ያለው አጠቃላይ የገንዘብ መጠን፣ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረት ሳይቆጠር በቅርቡ ETHO FM 107.8 ላይ በአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ስም በተመዘገቡ ንብረቶች ላይ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የሃራጅ ማስታወቂያ ማውጣቱን ተከትሎ አገልጋዩ የሰጠው ምላሽ ራሱንም ጠልፎ የሚጥለው መሆኑን የዘነጋ ይመስላል።

ባንኩ ሰኔ 13 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ባወጣው የሃራጅ ማስታወቂያ፣ በአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ስም የተመዘገቡ ንብረቶች በሃራጅ እንደሚሸጡ ማስታወቁ ይታወሳል። በዚህም መሰረት በዮናታን ስም የተመዘገበ ሃዋሳ ከተማ ላይ የሚገኝ 400 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ ያለው ባለ ሶስት ወለል መኖሪያ ቤት አንደኛው ሲሆን፣ በ22 ሚሊዮን ብር የሃራጅ መነሻ መሸጫ ዋጋ ተቀምጦለታል፡፡

እንዲሁም በዮናታን አክሊሉ አንጄሎ ዜብራ ግሪል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተመዘገበ ሃዋሳ ከተማ ምስራቅ ክፍለ ከተማ የሚገኝ 1ሺህ 271 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ህንጻ ሌላኛው በሃራጅ እንዲሸጥ ጫረታ የወጣበት ሲሆን 30 ሚሊዮን ብር የሃራጅ መነሻ ብር ተቀምጦለታል፡፡

ሌላኛው በሃራጅ እንዲሸጥ ጨረታ የወጣበት ደግሞ በዮናታን አክሊሉ አንጄሎ ዜብራ ግሪል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተመዘገበ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኝ በካርታ ቁጥር የተመዘገበ 500 ካሬ ሜትር ይዞታ ያለው መኖሪያ ቤትም ይገኝበታል፡፡

አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ በሪሀብሊቴሽን ማዕከል ስም ገነባው የተባለውን 1ሺህ 271 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ህንጻ ጨምሮ በሃዋሳና አዲስ አበባ ላሉት ቅንጡ ቤቶቹ ብድር የወሰደው በስሙ ሲሆን፥ ይህንን መሰረት በማድረግ "አገልጋይ ዮናታን አክሊሉን በስልክ አናግሬ ስለ ሁኔታው አጣርቻለሁ" ያለው ሮሀ ቲቪ የሚከተለውን ዘገባ ሠርቷል ፦

"አገልጋይ ዮናታን እነዚህ ለጨረታ የቀረቡት ንብረቶች ከዚህ ቀደም የእነሱ የነበሩ አሁን ግን በሽያጭ አቶ አለም ሰገድ ለተባሉ ግልሰብ የተላለፉ መሆናቸውን ተናግረዋል።...ገዢ አቶ አለምሰገድ ከነብድሩ በመግዛታቸው ብድሩ ተከፍሎ እስከሚያልቅ የግድ በእርሳቸው ስም መሆን ስለነበረበት ነው ሲሉ ለሮሃ ቲቪ ተነግረዋል፡፡ በመሆኑም አሁን ላይ ንብረቶቹ የእኔ አይደሉም በወቅቱ አትርፌ የሸጥኳቸው ናቸው ሲሉ አስረድተዋል፡፡" ይላል ዘገባው።

እናስ እንዲህ ዓይነቱ በወንጌል አገልጋይነት ስም የሚነግድ ጮሌ ሌሎችን "የገንዘብ ማግኛ አደረጉኝ" የሚልበትን ሞራል ከወዴት አገኘው? ባለፈው ዓመት የመልካም ወጣት መርሀ ግብር መክፈቻ ላይ በክብር ዕንግድነት ፊት ወንበር ላይ ከደረደራቸው የብልፅግና ወንጌል ሰባኪዎችና ሃሰተኛ ነቢያት አንዱ፦ "በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የሚዘወረው በፓስተሮች ነው" ማለቱም አይዘነጋም።

አንዳንዶች እንዲህ ዓይነት ነገር በተነሳ ቁጥር "ቅናት ነው!" ለማለት ቢጣደፉም በመንፈሳዊነት ካባ ባጭር ጊዜ ውስጥ ሚሊየነር ሆኖ መገኘት ግን ከጮሌነት አሊያም ከሌላ ነገር ጋር የተያያዘ እንጂ ለልጇ መልካምን ከምትመኝ ኢትዮጵያዊት እናት ምርቃትም ሆነ ከእግዚአብሔር አለመሆኑን ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው። እኔም ይኼን በማለቴ ያደረብኝ ቅናትም ሆነ የማገኘው ሰባራ ሳንቲም አለመኖሩንም ጭምር!

©ሽመልስ ይፍሩ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ዛሬ የጆን ካልቪን የልደት ቀን ነው። ( July 10, 1509 - May 27, 1564)። ልደቱን ስናስብ ቀጥሎ ያሉትን ሁለት ማሳሰቢያዎች ልተውላችሁ:-

ከሐዋርያው ከጳውሎስ:-

“ከሙታን የተነሣውን፣ ከዳዊት ዘርም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ፤ የእኔም ወንጌል ይኸው ነው።” (2 ጢሞ. 2:8)

ከካልቪን:-

“እረኞች በቃሉ እውነት ደፋሮች ይሁኑ . . . ማንኛውንም የዓለም ኅይል፣ ክብርና ልቀት ለቃሉ መለኮታዊና ግርማዊነት ያስገዙ። ከትልቁ እስከ ትንሹ ሁሉን በቃሉ ሥልጣን ይምሩ፤ የክርስቶስንም አካል ያንጹ። የሰይጣንን አገዛዝ ያፍርሱ፤ መንጋውን ያሰማሩ፤ ተኩላውን ይግደሉ፤ ዐመፀኛውን ይገስጹ፣ ይምከሩም። ካስፈለገም ነጐድጓድና መብረቁን ይሰሩና ይፍቱ፤ ነግር ግን ሁሉን እንደ እግዚአብሔር ቃል ያድርጉ። ” (Sermons on the Epistle to the Ephesians, xii).

ጌታችን ሆይ፣ “ክብርህን ተጠሚዎች፣ ቅዱስ ቃልህን ብቻ ሰባኪዎች፣ ለራሳቸው ፈቃድ የሞቱ ታማኝ ባሪያዎችና የወንጌል ዐደራ ጠባቂዎች አድርገን።”

አሜን!

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የእነ ወዳጄነህ "ነጭ" ውሸት

"ዴይስቶቹ" በሚል ርዕስ የፃፍሁት እኔ ነኝ። ሰሞነኛው የእነወዳጄነህ "ትውልድ አምካኝ" መሰረታዊ አስተሳሰብ ዴይዝም ስለሆነ። ሌሎችም "ከአዲሱ አስተሳሰብ (New Thought) እና ከስበት ህግ (Law of Attraction) አንፃር "ተችተው" ፅፈዋል፤ ተናግረዋል። ተገቢ ነበር። በተለይ ወንድሜ ጌትሽ Getahun Heramo በነገረ ጉዳዩ ላይ በሰፊው በመስራት ረገድ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል። ታዲያ ትችቱ የቀረበባቸው (ወዳጄነህ፣ ዳዊትና ዳጊ) ከየአቅጣጫው የቀረበባቸውን ትችቶች ተከትሎ በወዳጄነህ አጋፋሪነት በዳዊት አዳራሽ ተሰይመው በደቀ መዛሙርቶቻቸው ፊት "መግለጫ" በሚል ሽፋን "ልግጫ" (ያውም በትውልድ ላይ) አቅርበዋል።

"ለመልስ አልቦ" ምላሻቸው "እግረኛው" በተባለው ዩቲዩብ ቻነል ላይ አንድ ቀን ቀደም ተደርጎ በተለቀቀው የወዳጄነህ ቃለ መጠይቅ አስቀድመው መንገድ ለመደልደል ሞክረዋል። እርሱም (ወዳጄነህ) በቃለ መጠይቁ ላይ ራሱን ከዴይዝምም (Deism) ሆነ ከአዲሱ አስተሳሰብ (New Thought) ብሎም ከእነ ሮንዳ በርን የስበት ህግ ትምህርት ጋር (Law of Atraction) ጋር በምንም የተዛመደ እንዳልሆነ ለማስረዳት ሰማይ ሲቧጥጥ ቆየ።

በማግስቱም (ትናንትና) ዳዊትና ዳጊ "ተጨንቄ ነበር....ከመቶ በላይ ስልኮች ተደወለልኝ... ቤተሰቦቼ..." ወዘተ እያሉ "በተጨነቀ" ፊት መድረካቸው ላይ ቀረቡ። በቀረበባቸውን ምክንያተዊ ትችት መደንገጣቸውን ለመሸፈን በሚመስል መልኩ በቧልት በተሞላ እና የተነሳባቸውን ጥያቄ በማይመጥን መልኩ "ምላሽ" ለመስጠት ሞክረዋል። ምላሻቸው ተከታዮቻቸውን የናቀ፣ የተሰጣቸውን ሳይመዝኑ (ሳያመነዥጉ) የሚውጡ ታዳሚያን እንዳፈሩ በግልፅ የሚያሳይ እና "በነጭ ውሸቶች" የታጨቀ ነበር።

ነጭ ውሸት #1

ወዳጄነህ በሁለቱም ስፍራዎች (በእግረኛው ቻነልም ሆነ በዳዊት መድረክ) ላይ "ዴይስቶቹ ያለን ሰውዬ በእርግጠኝነት "ዴይስት" የሚለውን ነገር የሰማው ከእኔ ነው" ብሏል።
ይህ ነጭ ውሸት ነው። በበኩሌ ወዳጄነህ ስለ ዴይዝም ሲናገር በየትኛውም መንገድ ሰምቼውም አይቼውም አላውቅም። አስቂኝ ነው። ስለ "ዴይዝም" እኮ ማንኛውም ሰው አሁን "ጎግል" ቢያደርግ በቀላሉ በርካታ መረጃዎች ያገኛል። እኔ ደግሞ እንደ የወንጌል ባለአደራነቴ ላለፉት ሃያ ዓመታት በወንጌል ንፅህና ላይ የሚነሱ ስህተት ትምህሮቶችን በቃሉ ሚዛን እቃወማለሁ። አሁን ባለንበት ዘመንም በወንጌላዊያን መካከል ዋነኛ ተግዳሮት ሆኖ የመጣው "የቃል እምነት" ወይም "የብልፅግና ወንጌል" የሚባለው ስሁት አስተምህሮ እና እርሱን የሚከተለው ስሁት ልምምድ ስለሆነ ይህንን አስተምህሮ በትጋት አጋልጣለሁ።

በከሁኑ ወቅትም ይህን ስሁት አስተምህሮ በቃሉ እውነት ለመፈተሽ የሚያግዝ መፅሐፍ "አሁናዊ ተግዳሮት" በሚል ርዕስ እያዘጋጀሁ ነው (እግረ መንገድ ማስታወቂያ😀) ። "የቃል እምነት" ስሁት ትምህርት "ቅም አያት" የእነፕላቶ "ዱዋሊዝም" ቢሆንም ቅድመ ከያቱ "ዴይዝም" ነውና ለዚህ የመፅሐፍ ስራ ግብዓት እንዲሆን "ስለ ዴይዝም" ቀደም ሲል ከማውቀው በተሻለ ለመረዳት ጥናት አድርጌያለሁ። እንግዲህ በዚህ መካከል ነው የነወዳጄነህ "ትውልድ አምካኝ" የ60 ሚሊየን ብር ፕሮጀክት የመጣውና "ዴይስቶቹ" በሚል ርዕስ በገፄ ላይ የፃፍሁት።

ከ17ኛው ክ/ዘመን ጀምሮ የሚታወቅን ጎግል ላይ በርካታ መፅሐፍትና ጥናቶች የተቀመጡለትን "ዴይዝም" "እኔ ብቻ ነው የማውቀው" ሌላ ሰው ከተናገረው "ከእኔ ሰምቶ ነው" ማለት
አንድም ለራስ ያለን የተዛባ ግምት ያሳያል (ከእኔ ውጪ አዋቂ የለም ማለት ነውና) ሲያልፍ ትዕቢት፣ ከከፋም ዕብደት ነው።

ወዳጄነህ በአካል ተገናኝተን ሳናውቅ፣ ስለ "ዴይዝም" ከእርሱ ለመማሬ ምንም ዓይነት ማስረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ በደፈናውና "ዴይስቶቹ ያለን ሰውዬ በእርግጠኝነት ዴይስት የሚለውን ነገር የሰማው ከእኔ ነው" ብሎ "በእርግጠኝነት" መናገሩ "ነጭ ውሸት" ነው።

ለነገሩ ወዳጄነህ ከድሮም "ውሸታም" ነበር። ከዓመታት በፊት የወንጌላዊያን መድረክ ላይ በሚቆምበት ዘመን "የጠረፏ ንግስት" ብሎ ሰብኮ "ልክ አይደለህም" ብለው "አሜን" ጋዜጣ ላይ የፃፉበትን ዐቃቢያን "የተቀባ" ቤተክርስቲያን መድረክ ላይ ቆሞ "አሜን የሚባል ጋዜጣ ላይ የሚፅፉ ሰዎች ጫት እየቃሙ ነው የሚፅፉት" ብሎ በአደባባይ ውሸት ለመናገር ያልፈራ ውሸታም ነው። ያኔ አሜን ጋዜጣ ላይ የፃፈበት እኮ ዳኒ (Daniel Yilma) ነበር። አስቡት ዳኒን "በቃሚነት" ሲከስ።
ተጨማሪ ካስፈለገ የቀደመችውንም ሆነ ሁቸተኛዋን ሚስቱን በፈታበት ጊዜ "ለፍቺው ምክንያት" አድርጎ ያቀረባቸውን በርካታ ውሸቶች በአስረጂነት ማቅረብ ይቻላል (አስፈላጊ አይደለም እንጂ)።

ነጭ ውሸት #2

ዴይሰቶቹ የክረምት ፕሮጀክታችን ዓላማ ለገንዘብ አይደለም! ብለዋል። ነጭ ውሸት ነው። ለገንዘብ ካልሆነ ታዲያ ሶስት ሺህ ብር ለምንድነው የተፈለገው? በነፍስ ወከፍ አንድ ወጣት 3000 ብር ይከፍላል ተብሏልና። ስልጠናው የግማሽ ቀን ነው። የምሳ ወጪ የለውም። ስልጠናው የሚሰጠው ደግሞ በተለመደው ቦታ (ባታ ላይ) ነው (ዳዊት ያንን አረጋግጧልና)። የአዳራሽ ወጪ የለም ማለት ነው። ታዲያ ምንድነው ወጪው? ምሳ የለው የአዳራሽ ክፍያ የለው። ዮናታን እንኳን "መልካም" ወጣቶቹ ይብሉት አይብሉት ባይታወቅም ሺ አምስት አስከፍሎ ሰንጋ በሬ በመልካም ወጣት ስልጠና ግቢ ሲንጎማለል ቀርፆ ያሳያል። እነኚህኞቹ በሬ እናርዳለን፣ ቁርጥ እናበላለን አላሉም። ስለዚህ ፕሮጀክቱ በአስር ሳምንት 60 ሚሊየን ብር የማተም ፕሮጀክት ነው ማለት ነው። ምንም ማስተባበያ አያስፈልገውም፤ "ለገንዘብ ብለን አይደለም" ያሉት "ነጭ ውሸት" ነው።

ነጭ ውሸት #3

ወዳጄነህ ዘ ሴክሬት (The Secret) የተባለውን ጉዳይ እቃወመዋለሁ። ትክክል አይደለም። የእኔ ስልጠና የተመሠረተው "የወጣቶች ችግሮች" ላይ በተጠናው ጥናት ላይ ነው። የሚያሰለጥኑት (ዳዊትና ዳጊን ማለቱ ነው) ከዚህ "ማኑዋል" (ማኑዋል በእጁ ይዞ እያሳየ) አይወጡም ብሏል። "በእግረኛው" ዩቲዩብ ቻነል ላይ። ነጭ ውሸት ነው። ምክንያቱም በዳዊት መድረክ ላይ ለሶስት በሰጡት መግለጫ ላይ ዳዊት "እኔ የእኔን ቤስት አቀርባለሁ...ዳጊም የራሷን ቤስት ታቀርባለች....ወዳጄነህም የራሱን ቤስት ያቀርባል" ብሏልና። ጥያቄው የዳዊት "ቤስት" ትምህርት ምንድነው? የዳጊስ "ቤስት" ትምህርት ምንድነው የሚለው ነው። የሁለቱም "ቤስት" "የሮንዳ በርን የስበት ህግ (Law of Attraction) ትምህርት" አይደለምን? ስለዚህ ወዳጄነህ "እኔ ካዘጋጀሁት "ማኑዋል" ነው የሚያስተምሩት ያለው ነጭ ውሸት ነው ማለት ነው። ዳጊና ዳዊት "ቤስታቸውን" (ኒው ቶውታቸውን) ሊያስተምሩ ነውና የተዘጋጁት።

ነጭ ውሸት #4

እንደ ከምዕራቡ እና ከምስራቁ ዓለም በተቀዱ እንደ "ዴይዝም፣ አዲሱ አስተሳሰብ፣ የስበት ህግ፣ የተለጠጠ አወንታዊነት ወዘተ ላይ የተመሠረቱ እሳቤዎችን በማስተማር ትውልዱን አግድም አደግ ልታደርጉት ነው። በሚል ከተለያየ አቅጣጨ ለቀረበው "አሳማኝና ምክንያታዊ" ጥያቄ፤ በግልፅ (በተለይ ዳዊትና ዳጊ) "ዘ ሴክሬት የሚባለውን መፅሐፍ አላምንበትም... ዓለም በስበት ህግ ነው የምትንቀሳቀሰው ብዬ አላምንም.... በትምህርቶቼ ላይ የተናገርኋቸውንም ሆነ በመፅሐፍ የፃፍኋቸው ፅሆፎቼ ይቅርታ እጠይቃለሁ....ተሳስቻለሁ...ብሎ ከመመለስ ይልቅ፤ "በእግዚአብሐር መኖር አምናለሁ...

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

በአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ስም በተመዘገቡ ንብረቶች ላይ የሃራጅ ማስታወቂያ ወጣ፡፡

በአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ስም በተመዘገበ ንብረት ላይ የሃራጅ ማስታወቂያ ያወጣው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ነው፡፡

ባንኩ ሰኔ 13 ቀን 2015 አመት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ባወጣው የሃራጅ ማስታወቂያ፣ በአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ስም የተመዘገቡ ንብረቶች በሃራጅ እንደሚሸጡ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት በዮናታን ስም የተመዘገበ ሃዋሳ ከተማ ላይ የሚገኝ 400ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ ያለው ባለ ሶስት ወለል መኖሪያ ቤት አንደኛው ሲሆን፣ በ22 ሚሊዮን ብር የሃራጅ መነሻ መሸጫ ዋጋ ተቀምጦለታል፡፡

እንዲሁም በዮናታን አክሊሉ አንጄሎ ዜብራ ግሪል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተመዘገበ ሃዋሳ ከተማ ምስራቅ ክፍለ ከተማ የሚገኝ 1ሺህ 271 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ህንጻ ሌላኛው በሃራጅ እንዲሸጥ ጫረታ የወጣበት ሲሆን 30 ሚሊዮን ብር የሃራጅ መነሻ ብር ተቀምጦለታል፡፡

ሌላኛው በሃራጅ እንዲሸጥ ጨረታ የወጣበት ደግሞ በዮናታን አክሊሉ አንጄሎ ዜብራ ግሪል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተመዘገበ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኝ በካርታ ቁጥር የተመዘገበ 500 ካሬ ሜትር ይዞታ ያለው መኖሪያ ቤትም ይገኝበታል፡፡

በሄኖክ ወ/ገብርኤል

ሰኔ 23 ቀን 2015 ዓ.ም
(ኢትዮ ኤፍ ኤም)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ብሩስ ፒተር ሪይመር የተወለደው እ.አ.አ August 22፣ 1965 በካናዳ፣ በማኒቶባ ክፍለ አገር በበዊኒፔግ ከተማ ነበር። ብሩስና መንታ ወንድሙ ብራየን ሲወለዱ ብልቶቻቸው ከጤናማ ሕጻን የተለየ ችግር ነበሯችው። በውቅቱ ለወላጆቹ ሮንና ጃኔት እጅግ ልብ የሚሰብር ክስተት ቢሆንም፣ በኋላ እንደተረዱት የተፈጥሮ እድገታቸው በጠበቀ መልኩ በህምና መፍትኄ ይገኝለት ነበር።

ይህንን መጠነኛ ችግር ለማስተካከል በጆን ሆፕኪንስ ሆስፒታል በተደረገ የግዝረት ሂደት ውስጥ በብሩስ ብልት ላይ ትልቅ ስህተት ተፈጸመ። ሕክምናው በተለምዶ ደንቡ በሚፈቅደው የግዝረት መርሕ ሳይሆን፣ በአሌትሪክ ኀይል በጋለ ቀጭን ብረት በማቃጠል (Electrocauterization) በመከናወኑ የተፈጠረ ጉዳት ነበር። ብሩስ በየማይመለስና ሊስተካከል በማይችል መልኩ ብልቱን አጣ። ዕለቱ April 27፣ 1966 ነበር። በዚህ የተደናገጡት ወላጆች መንታ ወንድሙ ብራየን እንዳይገረዝ ወሰኑ።

የብሩስ ወላጆች መፍሔ ቢገኝ ብለው በጆን ሆፕኪንስ ሆስፒታል ታዋቂ የሕፃናት ሕክምናና የሥነ ልቡና ፕሮፌሰር የሆነበረውን የ ጆን መኒ ርዳታ ይሻሉ። በትውልደ ኒውዚላድ የሆነ አሜርካዊው ፕሮፌሰር መኒ (8 July 1921 – 7 July 2006)፣ “ጾታ ተፈጥሮአዊ ሳይሆን” ማኅብራዊ ውቅር (social construct)” ነው የሚል የጾታ ርዕዮተ ዓለም (Gender Ideology] ፊት አውራሪ ነበር። በአሜሪካም የመጀመሪያ የሆነውን የጾታ ዝውውር ቀዶ ጥገና (sex reassignment surgery) ክሊኒክ በ 1965 የመሠረተው መኒ ነው።

የጾታ ድርሻና (gender role) የጾታ ዝንባሌ (sexual orientation) የሚሉ ዕሳቤዎች የፈጠረውም ይኸው ፕሮፌሰር ጆን መኒ ነው። ጭካኔ በሞላበት ሁኔታ የአስገድዶ መደፈር በመፈጸማቸው የተፈረዳባቸውን እስረኞ የወሲብ ፍላጐት የሚያጠፋ፣ (testosterone blocker) እንዲሁም አኮላሽ ኪሜካል (chemical castration) ፍለጋ ፈር ቀዳጅና ስኬታማ ምርመራ የመራ ሰው ነው። በግብረ ሰዶም ወታደራዊ አራማጆች ዘንድ “የጾታ ለውጥ ንቅናቄ መንፈሳዊ መሪ አባት (The spiritual father of trans movement)” በመባል ይታወቃል።

በልጃቸው የወደፊት ዕጣ ፈተና የተጨነቁት የብሩስ ወላጆች የመኒን ምክር ፍለጋ ይሄዳሉ። የልጃችው ብቸኛ ተስፋ ጾታ መቀየር ብቻ እንደሆነና ያም በቀላሉ ሊደረግ እንደሚችል አሳመናቸው። “ወሳኝ የሕክምና ጊዜ እያለፈ” ነው በሚል ጫና በፍጥነት እንዲወስኑ አስጨነቃቸው። ብሩስ ለዐቅመ አዳምም ሲደርስ ራሱን የማጥፋት ዕድሉ ሰፊ እንደሆነም በማስረገጥ፣ ምንም ሳይንሳዊ መሠረት የሌለውን የራሱን መላምት ነገራቸው። ሌላ አማራጭ እንደሌለ ስለተነገራቸውና ለልጃቸው የወደፊት ሕይውት በማሰብ፣ በፍጹም እምነት ምክሩን በመቀበል “ሴት” ሆኖ እንዲያድግ ተስማሙ። ጃኔት እንዲህ ትላለች፦ “መኒን የማየው ልክ እንደ አምላክ ነበር . . . ያለውን ሁሉ [በፍጹም እምነት] እቀበል ነበር።”

ሆኖም በወቅቱ ለልጃቸው እጅግ የተጨነቈትና ተላላ የሆኑት ወላጆች የመኒ አዲስ የሙከራ ላቦራቶሪ የሕጻን ገላ መተልተያ፣ ልጃቸውም የመጀመሪያው መስዋዕት መሆኑን የተረዱት እጅግ ከዘገየ በኋላ ነበር። ወዲያው የሕጻኑ ብልቶች ከነዘር ከረጢታቸው ተቆርጥው ተጣሉ፤ ጡት እንዲያበቅል ቀዶ ጥገና ተደረገለት፤ እንዲሁም የሴትት ሆርሞን (estrogen) ይሰጠው ጀመር። “ብሪንዳ” የሚባል የሴት ስምም ተሰጠው። ከአልባሳት ጀምሮ መጫወቻዎቹ ለሴት ሕጽናት የተዘጋ ፣ ጓደኞቹም ደግሞ ሴቶች ብቻ እንዲሆኑ ተደርጐ ማደግ ጀመረ።

ከነዚህ በተጨማሪ ጾታው “ሴት” መሆኑንን እንዲያምን ለሰዓታት የሥነ ልቡና ቴራፒ ይወስድ ነበር። “ሴትነቱን በጊዜ ቶሎ እንዲለምድ” በሚል መላምት፣ ከስድስት ዓመቱ ጀምሮ “የወሲብ ልምምድ ጨዋታ” የሚል ቴራፒ ( sexual rehearsal play) ይወስድ ነበር። ይህም ቴራፒ ከመንታ ወንድሙ ጋር የ'ግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግን ልምምድ ይጨምር ነበር። ርቃናቸውን ሆነው ለጥናት በምርምር ተማሪዎች ፊትም በተደጋጋሚ ጊዜያት ይቆሙ ነበር። ይህ ሁሉ ሲደረግ፣ ወላጆች እንዳያውቁ በቤተ ሰብ ማቆያ ክፍል እንዲጠብቁ ይደረጋል።

ሆኖም ዕድሜው እየጨመረ ሲመጣ ከጾታ ማንነት ቀውስ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች ጥልቅ ድባቴና ጭንቀት ብሩስን ያሰቃዩት ጀመሩ። መኒ የተለያዩ መድኀኒቶች መሞከሪያ አደረገው። ይሁን እንጂ የማንነት ጥያቄ ቀውሱ እየጨመረ መጣ። ከማይደበቀው የወንድነቱ ባሕርይ የተነሣ የአስቸጋሪ ተማሪዎች መሳለቂያ ሆነ። ይህም ውስጡን እጅግ እይጐዳው ይመጣ ጀመር። ወንድ ሆኖም መወለዱን ከወላጆቹና ከፕሮፌሰር መኒ ክሊኒክ በስተቀር ማንም አያውቅም ነበር። ከፍ እያለ ሲመጣ በፕሮፌሰር መኒ የሙከራ ሕክምናና ቴራፒ ላይ ማመፅ ጀመረ። ይህ የማንነት ጥያቄ፣ በሕክምናና በቴራፒ የማይመለስ አየሆን መጣ። ጥልቅ ድባቴውም እየባሰ ራስን ወደ ማጥፋት ስሜት ውስጥ ይገፋፋው ጀመር።

መኒ ልቡ እጅግ የደነደነ ጨካኝ የሕጻናት ሐኪም ነበር። ያለምንም እፍረት፣ በድፍረት የብሩስን የጾታ ለውጥ “ስኬትማና ፈር ቀዳጅ ሥራ” በማለት በርካታ የምርምር ጽሑፎችም እንዲታተሙ አደረገ። ይህም የሐሰት “የምርመራ ውጤት” ለብዙ የሕክምና ውሳኔዎች እስከ አሁን ድረስ በማስረጃነት ይጠቀሳሉ። ይህ ልምድ በአሜሪካና በበርካታ የምዕራቡ ዓለም “የጾታ ለውጥ ክሊኒኮች” የሚተገበር ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በግብረ ሰዶም ፊተኛ ከሆኑት አገራት አንደኛዋ የሆነችው ስዊድን ይህን በምንም መልኩ ሊሆን የማይችልና ጭከና፣ የአካልና የስሜት ስቃይ ያለበት የጾታ ለውጥ ሕክምና በልጆች ላይ እንዳይደረግ መከልከሏን ልብ ይሏል።

የብሩስ አባት የልጁን ጭንከትና የዓመታት የመንነት ውሽት መሸከም አልቻለም። ልጁ 15 ዓመት ሲሆነው እውነቱ ነገረው። ብሩስም ለዓመታት የማንነት ጥያቄው ምላሽ ሆነለት። ወዲያው በሆርሞን ብዛት ያደጉትን ጡቶቹ አስቆረጠ፤ በርካታ ቀዶ ጥገና አደረገ፤ የወንድ ሆርሞንም በቋሚነት መውስድ ጀመረ፤ ስሙንም ዴቪድ ሲል ቀየረ። በ22 ዓመቱ ጄን ፎንቴይ የተባለች የሦስት ልጆች እና በማግባት መደበኛ ኑሮ ለመኖር ሞክሮ ነበር፤ ምንም እንዃን በፍቺ ቢጠናቀቅም።

የፕሮፌሰር መኒን ውሽት፣ የአካልና የቃላት ጭከና በአደባባይ ማጋለጥ ጀመረ። አሳዛኙ እውነታ ግን ከዋናው ባለጕዳይና ጕዳተኛው ከሆነ ከብሩስ ይልቅ የመኒ ቃልናና አሳፋሪ ሳይንሳዊ ጥናቶቹ “ተአማኒ የሕክምና ዶክትሪን” ሆነው እስከ አሁን ዘልቀዋል። ይህ ትልቅ የዘመኑ የሕክምና ሳይንስ ክህደት ነው።

የጆን መኒ የጾታን ርዕዮተ ዓለም የብዙ የልጆች አካልና ስሜት መሠዊያ ሠርቷል። በወላጅ እውቅና፣ ሳያውቁም ሆነ ተገድደው ልጆች ይገበራሉ። መኒ የለም፣ ሆኖም በምዕራቡ ዓለም ዛሬም በሐስት ሥራዎቹ ብዞዎች ይሰቃያሉ። በሌላ ዐውድም ቢሆን፣ መኒ የጣለው መሠረት እስራኤላውያንን ያሳተውን የኢዮርብዓምን ድርጊት ያስታውሰኛል፦

“በማምለኪያ ኰረብቶች ላይ ላሠራቸው አብያተ ጣዖታት በቤቴል ካህናቱን መደበ። ራሱ በመረጠው በስምንተኛው ወር፣ በዐሥራ አምስተኛው ቀን በቤቴል ባቆመው መሠዊያ ላይ መሥዋዕት አቀረበ፤ ስለዚህ ለእስራኤላውያን በዓል ወሰነላቸው፤ ዕጣንም ለማቅረብ ወደ መሠዊያው ወጣ።” (1 ነገሥት 12:32-33)።

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

In 2017, the Pew Research Center conducted a survey in which they tested only four New Age teachings against Christians to see if New Age was indeed creeping into the church...shockingly a whopping 60 percent of Christians hold to at least one of those views."

በነገራችን ላይ የጠቀስኩት መፅሐፍ ደራሲ የሆነው Jon Clash ለዓመታት በ"New Age Thought" ልምምድ ውስጥ ያለፈ እና ታይላንድ ድረስ በመሄድ ፕሮፌሽናል የዮጋ አሰልጣኝ ለመሆን የበቃ ወጣት ነው። በአሁኑ ወቅት ግን ሰዎች ወደ አስተምህሮው እንደዋዛ ገብተው እዚያው ሰምጠው እንዳይቀሩ በዩ-ቲዩብ ገፁ የ"New Age Thought" አስተምህሮን አደገኛነት በማጋለጥ ላይ ይገኛል።

አሁንም እደግመዋለሁ፦ ይህን አስተምህሮ አደገኛ የሚያደርገው የአቃፊነት ባሕሪዩ ነው፤ መገፋትን እንጂ መታቀፍን ደግሞ የሚጠላ የለም። አስተምህሮው በሩን ሰፋ አድርጎ ከፍቶ የሚያቅፈው ግን በሂደት ሁሉንም ሃይማኖቶች ወደ አንድ ወፍጮ ከትቶ አንድ ወጥ ግሎባል የሆነ አስተሳሰብን ለመፍጠር ነው። በክርስትና አስተምህሮ ይህ አካሄድ ለክርስቶስ ተቃዋሚ(The Anti-Christ) መከሰት መንገድ እንደመጥረግ ይቆጠራል።

የ"Law of Attraction" መፅሐፍ ደራሲ የሆነው "Jon Clash"ም ቢሆን አብዛኞቹ ወጣቶች ወደ "New Age" አስተምህሮ የሚገቡት የአስተምህሮውን ግብና ዓላማ እንዲሁም ስውር መንፈሳዊ አሠራሩን ተገንዝበውት አይደለም ይለናል። ለአብዛኞቹ ዕሳቤው ከአዕምሮ መነቃቃት ጂምናስቲክ በዘለለ ሌላ ዓላማ ያለው አይመስላቸውም። በወቅቱ ድባቴ ስሜቱ ተጎድቶ ድባቅ የተመታ ሰው ከችግሩ ለመውጣት የቀረበለትን ሁሉ በመሞከሩ መፍረድ እጅግ ይከብዳል፤ ሆኖም ጉዞው ከድጡ ወደ ማጡ እንዳይሆን ጥንቃቄ ያሻል!

ጌታሁን ሄራሞ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

#ሰባኪው

ሞጋች ነበር፤ 'እስቲ እንሞክረው' እያለ ከልቡ ይማጠነን ነበር። የሞከርናቸውንና ፈቀቅ ያላደረጉንን ይዘረዝራቸው ነበር። በእምነት አንቀጽ 'perfecto' 👌 መሆናችንን ፣ ያላሰለሰ 'የእቅበት' ሥራችንን፣ አባላት ባሉበት የሚያቆዩ ታክቲኮቻችንን፣ ባለንበት ማሕበረሰብ ልቀን እንድታይ ያለፉንን መርሆቻችንን... ወዘተ ዘረዘራቸው። እኛም ጥርስ የነቀልንባቸው ነበሩና ሲናገረን እስከ መጨረሻ አንገታችንን ወደላይ ወደታች ከማረግ አላረፍንም ነበር። እናም...

የአንድ ጸሐፊን ትርክት እንደማመሳከሪያ አቀረበ። እስካሁን ብዙ ሞክረናል። ነገር ግን ሕዝብ ሕዝብ እንደሆነ አልቀጠለም፣ እየተጠፋፋን ነው። ፊውዳሊዝምን ሞከርነው - ከእግር እስከ ራሱ፤ አብዮትም መጣ በኃያል ፈረሱ ፤... ብዙ መርሆችን አየን... ጦርነት፣ ረሃብ፣ ጭቆና፣ dehumanizing factors... መቼ ቀሩ?

እስቲ አሁን ደግሞ ከጥንት የነበረውን ነገር ግን ንቀነው የጣልነውን የክርስቶስን መርህ እንከተል (ፍቅርን፣ አንዱ ለሌላው መኖርን እናንሳ ብሎ ይሞግታል) አለን። ሰባኪው ያለውን ሃሳብ ቃል በቃል እንዳነበብኩት ባላስታውስም ሃሳቡ ግን የሊዮ ቶልስቶይ እንደሆነ ገብቶኛል - በ Art of War መጽሐፉ።

'እስቲ እንሞክረው እኛም' - ይለናል በየመኻሉ። እውነትም እስቲ እንሞክረው በጌታ። አጓጉል ጀብዱዎች ምን አመጡልን? የስንቱን የስህተት አፍ ለማዘጋት የተወራጨነው ምን ፈየደልን? 'የመንፈስ ቅዱስ ኃይል' ወረደብኝ ብለን እንደ አዲሱ የእግዚአብሔር ሕዝብ እንድንኖር ምን አበረከትን?... ፍቅርን እስቲ እንሞክረው።

እንዲህ ዓይነት ሰባኪ የሚቆም ከሆነ በረባ ባልረባ ሰበብ ከ'ቸርች' አልቀርም ብዬ ተመልሻለሁ።

ሰናይ ሰንበት!

ተገኝ ሙሉጌታ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የክረምቱ ፈተና

መጪው ክረምት ለየት ያለ ይመስላል። የኑሮ ውድነቱ ዙሩን አክርሮታል። አእላፍ አዲስ ስራ ፈላጊዎች ቢመረቁም ገንዘብ ሚኒስቴር ግን ከወዲሁ ለመጪው ዓመት ምንም ዓይነት የሰራተኛ ቅጥር እንደማይኖር መርዶውን አሰምቷል። የስራ አጡ ቁጥር የትየለሌ ነው በተለይ ወጣቱ። በሱስ እስራት የተቸገረውም እንዲሁ መዓት ነው። ቤት የፈረሰባቸው እና መጠለያ ያጡ ምስኪኖችም በዚህ የዝናብ ወቅት በየጥጋጥጉ ወድቀዋል። ክረምቱ ፈታኝ ነው።

ወዲህ ደግሞ ባለ "መፍትሔ ነን" ባይ ነጋዴዎች ይህንን አስከፊ ሁኔታ እንደ ጥሩ አጋጣሚ ተጠቅመው "በአወንታዊ ቃል ሃይል የስበት ህግን በመጠቀም ብቻ ሁሉንም ነገር በቅፅበተ ዓይን መለወጥ ይቻላል!....ሚሊየነር መሆን ይቻላል!..ከሱስም በቅፅበት መላቀቅ ይቻላል...ቪዛ ማግኘት በተዓምር ማግኘት ይቻላል..ወዘተ..ማግኘት ይቻላል" በማለት የማይጨበጥ ተስፋ እየሰጡ ሀብት ለመሰብሰብ አኮብኩበዋል። ይህ ደግሞ ሌላኛው የክረምቱ ፈተና ነው። (ይህኛው በተለይ ለወጣቱ አደገኛ ነው)

የሆነው ሆኖ ግን እነኚህ አራት ሰዎች ለምንድነው አንድ ላይ የማይጣመሩት። አንድ ዓይነት ትምህርት በተለያየ መድረክ ለምን ያቀርባሉ? ቢያንስ ወጣቱን ምንም ለማይፈይድለት ትምህርት ሁለት ቦታ ከመክፈል ኪሳራ ያድኑት ነበር። ትውልዱን በዚህ እንኳን ቢያግዙት ምናለበት። ለነገሩ ለትውልድ የሚያስብ ሰው ቀድሞ ነገር በባዶ ተስፋ ትውልድን ለማታለል መች ይነሳል?.. አትሉም?

ለማንኛውም ወጣቶች በተለይም አማኝ ወጣቶች መጠቀሚያ ከመሆን ራሳቸውን መጠበቅ አለባቸው የሚል ምክሬን አቀርባለሁ። እንዲህ ያለውን ከንቱ ትምህርት ለመለየት ጥቂት ማሰብ ብቻ በቂ ነውና። በነገራችን ላይ ወደ "ስበት ህግ" ትምህርት ቤቶች ከሚሄዱት መካከል በርከት ያሉት ከወንጌላዊያኑ ወገን እንደሆኑ ይሰማል። ይህ ደግሞ የበለጠ ፈታኝም! አሳዛኝም ነው።

ቴዎድሮስ ተጫን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ይህ ወቅት እጅግ ከባድና ፈታኝ ነው። እንደ አገር የፍትሕ ዕይታችን በጅምላ ከመወገንና ከመጥላት ጋር ተቈራኝቷል። ይህም በብሔርና በቋንቋ እየመረጥን እንድንኰንንና እንድናጸድቅ አድርጐናል። በርግጥ እግዚአብሔርን እንፈራለን ካልንና የሰው ሁሉ ክቡርነትና እኵልነት መሠረት ሰው በአርአያ ሥላሴ መፈጠሩን ካመንን፣ ሰው በብሔሩ፣ በቋንቋውና በባህሉ ምክንያት አናሳ ተድርጐ ሲቈጠር፣ ሲናቅ፣ ሲፈናቀልና ሲገደል እያያን እንዴት ዝም ልንል እንችላለን?። በተለይም፣ ሕጻናት፣ አረጋውያንና ዐቅመ ደካሞች የዘረኝነት ሰይፍ ሲያሳድዳቸው እያየን፣ ዐይናችንን ልንጨፍን አንችልም!

ልማት ያስፈልገናል። መንግሥት በዚህ በኩል ያለው ተነሣሺነትና ጥረት የሚያስመስግነው ነው። ሆኖም ልማት የሰውን አምሳለ መለኮት ተሸካሚነትና ክቡርነት ታሳቢ ያደረገ ሊሆን ይገባዋል። ማንኛውም ሰው ያለ አድሎ የምድር በረከት በኵል ተካፋይ የሚሆንበት ቀዳማዊ ምክንያት፣ በእግዚአብሔር መልክ መፈጠሩ ነው። ቤተ ክርስቲያንም ለድኾችና ለተገፉ የፍትሕ ጩኸት ጥብቅና የምትቈምበት ፋይዳ መሠረት፣ “እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክ ፈጠረ” (ዘፍ. 1፥27) የሚለው ጊዜ የማይሽረው ቃል ነው። የየትኛውም መንግሥት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ የአስተዳደር መርሕ፣ አወቃቀርና ተኣማኒነት የሚለካው እግዚአብሔር ከእርሱ በሚጠብቀው የጽድቅ አገዛዝ ማዕቀፍ ነው። ልዑል እግዚአብሔር፣ መንግሥት፣ “ለመልካም ነገር የሕዝብ አገልጋይ” እንዲሆን ይጠብቃል (ሮሜ. 13፥4)።

መንግሥታት ዕውቅና ሰጡ አልሰጡ፣ ለመልካም አስተዳዳር የእግዚአብሔር አገልጋዮች ብቻ ሳይሆኑ፣ የሥልጣናቸውም ምንጭ ራሱ ልዑል እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ የአገር መሪዎች የሥልጣን ሁሉ ባለቤት የሆነውን፣ እግዚአብሔርን በመፍራት በፍትሕ፣ ለሕዝብ መልካሙን በማሰብና በማድረግ፣ በጥበብና በማስተዋል ሊያስተዳድሩ ይገባል። ቤተ ክርስቲያንም ለመንግሥት የመጸለይ፣ የመምከርና ተጠያቂ የማድረግ ኀላፊትነት አለባት። አገራችን ባለችበት በዚህ ፈታኝ ወቅት፣ ለወንጌል እውነት እኖራለሁ የምትል ቤተ ክርስቲያን፣ ባላት ዐቅም ሁሉ ዘረኝነትንና ኢ-ፍትሐዊነትን ፊት ለፊት በመቃወም፣ የዕርቅና የሰላም መንበር ልትሆን ይገባታል።

🔈 ዳግማዊ ዐሳስቦት - “ሰላምን የሚያወርዱ ብፁዓን ናቸው”

1️⃣ በፍትሕና ሰላም ላይ ወደ ተመሠረተ አገራዊ መግባባት፣ ይቅር ባይነት፣ ዕርቅና ፈውስ ልንሄድ ይገባናል። ይህንን እንዳናደርግ ዕንቅፋት የሚሆንብን ራሳችን የገነባነውና መውጫ የሌለው በአሉታዊነትና በቂም ላይ የተመሠረተ የታሪክና የትርክት እስር ቤት ውስጥ ኅሊናችንን ማጐራችን ነው። እውነታው ግን እንዳንለያይ ተደርገን የተሰናሰልንባቸው ብዙ የጋራ ፋይዳዎች በአንድ የገመዱን የገመዱን ሕዝቦች ነን።

2️⃣ ከታሪክ ልንማር እንጂ፣ የታሪክ እስረኛ ልንሆን አይገባም። ታሪክ መስታወት (መታዘቢይ) ነው። ያለፈውን ትውልድ ጥንካሬና ድካም ይነግረናል። በጐው ላይ በመገንባት፣ ጥፋትን ላለመድገም እየተማርን ልንሄድ ይገባል። የቂም እስረኛነት የጅምላ ፍረጃና ጥላቻ ውስጥ ይከተናል። ይህ መንገድ ፍጻሜ የሌለውና ለትውልድ የሚተላለፍ የዐመፅና የድህነት ዑደት አዙሪት ነው። ማኅበራዊ መሰተጋብራችን፣ በቂም ከታሰርንበት ብሔርተኝነት ዐርነት መውጣት ያስፈልገዋል። ሰላማችንን፣ የብሔርተኝነት ካባ ደርበውና ለብሔራቸው ዐሳቢ በመምሰል፣ የተለያዩ ማኅበራዊ መገናኛዎችን በመጠቀም ሕዝቦችን ለቍጣና ለእርስ በርስ እልቂት ከሚያነሣሱ ክፉዎች ልንጋርደው ይገባል። አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላማዊ ነው፤ የአክራሪዎቹን ርእዮተ ዓለም፣ አክራሪዎቹ ከተገኙበት ብሔር ጋር በአንድ አያይዘን ልንመለከት አይገባም።

3️⃣ ከዐመፅ የተፋታ ፓለቲካ ያስፈልገናል። በደም ከተነከረ የዐመፅ ፓለቲካ ያጨድነው ስብራትና ድኽነት፣ ክፍፍልና ጥላቻ ብቻ ነው። ይህም የማያዋጣ፣ ዕድሜና ትውልድ አክሳሪ የስብራት ዑደት መንገድ መሆኑን (ቢያንስ ካለፈው ግማሽ ምእተ ዓመት) በሰቆቃ ተምረናል! “የተሻለ የዐሳብ ልዕልና” ሊገዛን ይገባል። ሕገ መንግሥቱን ጨምሮ ሌሎች ያማያግባቡንን ጕዳዮች ለመፍታት አዋጩ መንገድ ሰላምን መርሕ ያደረገ ውይይት ብቻ ነው። ቅቡልነት፣ ተኣማኒነትና ትርጕም ያለው አገዛዝ የሚኖረው እግዚአብሔር ሞገስ ሲሆንና ሕዝብ ልቡን ሲሰጥ ብቻ ነው። መንግሥት እጅግ እየደማ ያለውን ቅቡልነቱን፣ ቆም ብሎ ሊያክም ይገባዋል። ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ፣ የዐሳብ ልዩነቶችና አግባብነት ያላቸውን ትችቶች ለመስማት፣ ለመማርና ለመታረም ፈቃደኛ የሆነ ሰፊ ልብ ያስፈልገዋል። ከሁሉ በላይ የሕዝብን መመረርና ሐዘን ማድመጥ አለበት። በሌላ አንጻር ራሳቸውን በአማራጭ የሚያዩ የፓለቲካ ፓርቲዎች ሥልጣን ለመያዝ በመጓጓት በየትኛውም መንገድ መንግሥት እንዲወድቅ ከመፈለግ ጥማት ሊታቀቡ ይገባል። በተለይም ከምዕራቡ ዓለም የድሎት ሰፈር ሆኖ በማኅበራዊ መገናኛ በሕዝቦች መካከል ያለመተማመን፣ ጥላቻንና ዐመፅን በመቀስቀስ ድኾችን ማብቂያ ለሌለው ጦርነት ማነሣሣት፣ ርኅራኄ የለሽና ኢሞራላዊ እኵይ ተግባር ነው። እስከ አሁን የፈሰሰው የግፉዐን ደም ወደ እግዚአብሔር ይጣራልና። ሁል ጊዜ አፍርሶ የሚስሠራና “አሐዱ” ብሎ ከወለል የሚጀምር ፓለቲካዊ አካሄድ አክሳሪ መሆኑን፣ ቢያንስ አሁን ማስተዋል ይኖርብናል።

4️⃣ የሰው ክቡርነት መሠረት በአምሳለ እግዚአብሔር መፈጠሩ ነው። ይህ የዐስተሳሰባችን አልፋም ዖሜጋም ነው። በዘርና ሃይማኖት ተኰር ጥላቻ ዲያብሎሳዊ በሆነ ጭካኔ እየፈሰሰ ያለው የንጹሐን ደም፣ ከሰብአዊነት እጅግ የወረደ አዘቅት ውስጥ እንደገባን ያሳያል። ዘረኝነት ኀጢአት ነው - ያውም እግዚአብሔር እጅግ የሚጸየፈው ኀጢአት! ዘረኛ ሰው የሚጋጨው ሰውን በገዛ መልኩና አምሳሉ ከፈጠረው ከልዑል እግዚአብሔር ጋር ነው። የብሔር ልዩትነት እግዚአብሔር በፍጥረት መግቦቱ ያደለን ጌጥ እንጂ፣ በወገንተኝነት፣ በአግላይነትና በአድሎአዊነት ሌሎችን እንደ ሁለተኛ ዜጋ የምናይበት ማንነት አይደለም። ማንኛውም ኢትዮጲያዊ፣ የትኛውም ግዛት ያለሥጋት እንዲኖር የሚያስችል ፍቅርና ሰላም በአገሪቱ መስፈን አለበት። ይህም የእውነተኛ ሰብዓዊነት ተሐድሶን ይጠይቃል። ሕግ ዐብረን እንድንኖር ያስገድደን ይሆናል እንጂ፣ እንድንቀባበል አያደርገንም። ለእውነተኛ መግባባት፣ መቀባበልና መቻቻል፣ ልባችን ሊፈወስ ይገባዋል።

5️⃣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት። የዘረኝነት አንዱ ክፋት፣ ኅብረ-ብሔራዊ አንድነትን፣ “ለእኔ ወይም የእኔ ብቻ” በሚል አግላይ የክልልነት ንፉግነት ማክረሩ ነው። ተከፋፍሎ በሰላም የኖረና ያደገ ሕዝብ እንደሌለ ታሪክ ምስክር ነው። የተከፋፈለ ከተማ ወይም ቤት አይጸናም” (ማቴ 12፥25)። ይህን ወቅታዊና ብርቱ የክርስቶስ ድምፅ ሁላችንም፣ ከልብ ልንሰማው ይገባል።

6️⃣ ሃይማኖታዊ መቻቻል። ሃይማኖታዊ አክራሪነት ወትሮም እየነደደ ያለውን ዘር ተኰር ፓለቲካዊ የጥላቻ እሳት የበለጠ የሚያቀጣጥል ነዳጅ ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንና በወንጌል አማኞች ቤተ ሃይማኖቶች ውስጥ ያለው መከፋፈል እንዲሁም አንዱ ከሌላው ጋር ያለው የግንኙነት ውጥረት፣ በብዙ ትርምስ ውስጥ ያለችን አገር መከራ ያብሳል። ሁለቱም ከመንግሥትና ከፓለቲካ ኀይላት ተጽዕኖ መላቀቅ አለባቸው። ይህ አለመሆኑ በሁሉም ላይ ትልቅ ጕዳት አምጥቷል። እነዚህ ነገሮች ለምስባኩም ሆነ ለዙፋኑ፣ ለቤተ-መቅደሱም ሆነ ለቤተ-መንግሥቱ አይጠቅሙም። ስለዚህ በመካከላቸው ያለውን ታሪካዊ የአግላይነት ውጥረት ይበልጡን የሚያከሩ ድርጊቶችን፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚዛንና

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የክርስትንና መንገድ እንደ "አስቸጋሪ፣ የማይቻልና ጠባብ" አድርገን እንደናስብ የሚያደርገን፣ ለሥጋችን የሚመቸውን ሰፊውን መንገድ ስለምንመረጥ ነው። ከክርስቶስ ፍቅር ይልቅ በሰፊው በር በኩል የምናገኘው የኀጢአት ደስታ ስለሚበልጥብን ነው። ስለ በደላችንና ስለኀጢአታችን በመስቅል ሞት ሕይወቱን ስለ ለእኛ አሳልፎ የሰጠው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "አስጨናቂ ገዢ" አይደለም።

በመስቀሉ ላይ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ፍቅር የተረዳ ሰው ጠባቡን መንገድ እንደ ዕዳ አያየውም። ይልቁንም ለዓለምና ለሥጋው ፈቃድ በየጊዜው ይሞቷል። ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሚለው፣ “ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ፤ ከእንግዲህ እኔ አልኖርም፤ ነገር ግን ክርስቶስ በውስጤ ይኖራል። አሁንም በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን አሳልፎ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለኝ እምነት ነው።” ( ገላትያ 2 : 20) ክርስቶስን መሲሕ ብቻ ሳይሆን ጌታ አድርጐ በልቡ ላይ አንግሧል።  ከኀጢአት ከሚገኘው ደስታ ይልቅ በማይወዳድር መልኩ በክርስቶስ ፍቅርና ክብር ደስ ይለዋል። የዓለም ሳይሆን የክርስቶስ ፍቅር እስረኛ በመሆኑ በጠባቡ በር ይገባል። ጠባቡ በር የፍቅርና የክብር በር ነው። በአንድ ጊዜ የጌታም የዓለምና የሥጋ መሆን አይቻልም። የት ይሆን ያለነው?

አቤቱ፤ የመስቀልህ ፍቅር ያድሰን። አሜን!

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ወልድን ተሳለሙት!
https://www.youtube.com/watch?v=GxaXL2U8Cj8
***
በኀጢአት የተበከለውን የሰው ልጅን ልብ አስፈሪ ነው። ሰው የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመዋጋት ካሰፈሰፉ ማናቸውም ኀይላት ጋር ዐብ’ሮ ከመሰለፍ የማያመነታ ግብዝ ነው። በቋሚነት በእግዚአብሔር አገዛዝ ላይ የሚያምፅ ፍጥረት ነው። ለነገሩ ይኸን ጕድ በኤደን ገንት ነው የጀመርነው። ገና ያኔ ጥንት። መዝሙሩ በግልጽ እንደሚነግረን፥ የተለያዩ አሕዛብና ሕዝቦች፥ መንግሥታት፥ ነገሥታትና አለቆች ኹሉ “የጋራ ጠላታችን” ያሉትን እግዚአብሔርና እርሱ የቀባውን ለመቃወም ግንባር ፈጥረው ተከማቹ። …
.

ኀጢአተኛው የሰው ልጅ እግዚአብሔርን አሸንፋለው ብሎ ከሌሎች ነገሥታትና ሕዝቦች ጋር እስከ መተባበር ያደረሰው በእግዚአብሔር አብና በልጁ ላይ ባለው ጥላቻ ነው። አዎ፥ እርሱ ባይታረቀን “ጠላቶቹ” (ሮሜ 5፥9-10) ነበርን። ልቀቀን ባዮች ነን። እንደ ፈለገን እንኹን፥ በኀጢአት እንፈንጭ ባዮች ነን። …
.

የኀጢአተኛው ሰው ዓላማ ግልጽ ነው። ከእግዚአብሔር ቍጥጥር ነጻ ለመውጣት፥ የዘላለም አባትና የቀባውን መሲሕ ለማሸነፍ ነው። ከእግዚአብሔርና ከቀባው መሲሕ መንግሥታዊ ሥልጣን ለመውጣት ነው። አንገዛም ነው። independence ነው። …
.
ወገኔ ሆይ፥ ዝም ያለህ፥ አንድም ንቆህ፥ አንድም ታግሦህ ነው እንጂ በርትተህበት አይደለም። የለም ብትል አታጠፋውም። ስትሳደብ ብትውል ቍጣን በራስህ ታከማቻለህ እንጂ፥ ክብሩን አትቀንሰውም። በዛቻህ አይፈራም። በምክርህ አይናወጥም። ደፍሮትስ በሰላም የኼደ ማንነው? ከቀደምት ገዦች አትማርም። መሻትህ አይኾንልህም። በመሲሑ ሹመት ክብር ዐመፀኞች የተናቁ ናቸው፤ ከቅጣትም አያመልጡም። …
.
መሲሑን በመጥላት የሚደረግ መላለማዊ የዐመፀኞች ትብብር አለ። ኀይላቸውንና ሥልጣናቸውን ለአውሬው የሰጡበት ውጊያቸው ከንቱ ይኾናል። በዘመን ፍጻሜ፥ የሚደረግ ሠልፋቸው በበጉ ድል ነሺነት ይደመደማል። …
.
እንግዲያው ያላችሁ ተስፋ ምንድር ነው? ተስፋችሁማ የተቃወማችሁት መሲሕ ራሱ ነው። “እንዳይቈጣና በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ዝቅ ብላችሁ ልጁን ሳሙት። … በወልድ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው።
.
ዛሬም ለሰው ልጆች ኹሉ የቀረበ ማስጠንቀቂያና ተስፋ ይህ ነው። “እንዳይቈጣና በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ዝቅ ብላችሁ ልጁን ሳሙት። ቍጣው ፈጥኖ ይነዳልና። እርሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ኹሉ የተባረኩ ናቸው።” ከክርስቶስ የዘመን ፍጻሜ ቍጣ የሚያድናችሁ ራሱ ክርስቶስ ነው። ወልድን ተሳለሙት። ተቈጥቶ እንዳያጠፋችሁ በመንቀጥቀጥ ስገዱለት። ...

(ሙሉ መልእክቱን ለማግኘት ሊንኩን ከታች አኑሬአለሁ)

https://www.youtube.com/watch?v=GxaXL2U8Cj8

መጋቢ ሰሎሞን አበበ ገ/መድኀን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

እርስታቸውን በግፍ "የተነጠቁት" የእኛ ዘመን "ናቡቴዎች"

መገናኛ አካባቢ በሚገኘው "የክብር ሕይወት ቤተ ክርስቲያን" አስተዳዳሪና መጋቢ በሆነው፤ ከስሙ በፊት "ሬቨረንድ" ከሚል ቅጽል ጋር በሚጠራው ተዘራ ያሬድ በሚባል ግለሰብና ለአሥራ አንድ ዓመታት ቸርቹን ካከራዩት የይዞታ ባለቤቶች ጋር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ስለተነሳው ውዝግብ ሰምቼና አንብቤ በዚህ ዘመን አገልጋዮች ዐይን አውጣነት ስገረምና ስደነቅ ቆይቻለሁ።

በተከሰሰበት የፍርድ ቤት መጥሪያዎቹ ላይ በተገለጸው መሠረት በቀጣዩ ትረካዬ "ፓስተር ተዘራ ያሬድ " እያለኩ ታሪኩን የምጠቅሰው ሰው ከዚህ ቀደም ለቤተ እምነቱ ምዕመናን የክርስቶስን የመካከለኝነት ሚና በራሱ ተክቶ "በእግዚአብሔር እና በእናንተ መካከል ሆኜ ከእርሱ ጋር የማገናኛችሁ እኔ ነኝ፣ ግንኙነነቱን ካቋረጥኩባችሁ ይቋረጣል" እያለ ያስፈራራበት ንግግሩ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተለቆ "ሚስተር ዲስኮኔክት" የሚል የሹፈት ስያሜ ያገኘ መሆኑንም ያስታውሷል። ከልቡ አምኖበት ወይም ንግግሩ አደባባይ ስለወጣ አፍሮ ይሁን አይሁን ባይታወቅም ለዚህ የድፍረት ንግግሩ ይቅርታ ጠይቆበታል።

ወደ ዛሬው ዋና ጉዳይ ስመለስ ትናንት ዕለተ ሀሙስ ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም ከዚህ ቀደም ከማላውቀውና ከጉዳዩ ባለቤቶች አንዱ ከሆነው ወንድም ጋር ባልታሰበ አጋጣሚ ስለዚሁ ውዝግብ የማውራት ዕድል አግኝቼ ያጫወተኝ ታሪክ በመጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ምዕራፍ 20 ከቁጥር አንድ ጀምሮ ተጽፎ የሚገኘውን የናቡቴን እና የንጉሥ አክዓብን ታሪክ አስታውሶኛል።

ነገርን ከሥሩ እንዲሉ፥ ፓስተር ተዘራ ያሬድ ለአሥራ አንድ ዓመት መንፈሳዊ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየበት ቤት ህጋዊ ባለቤት ቄስ ወልደማርያም ኡርጂ ይባላሉ። የመካነ ኢየሱስ ቄስ የነበሩ ሰው ናቸው። ጉጂ ላይ የወንጌልን ሥራ በትጋት ሠርተዋል፣ ብዙ ቤተ ክርስቲያናትንም ተክለዋል። ከልጆቻቸው መካከልም አንዱ ዛሬ ላይ በመጋቢነት ያገለግላል።

ቄስ ወልደማርያም ኡርጂ አራት ወንድ ልጆች ያሏቸው ሲሆን፤ ፓስተር ዋጋዬ ወልደማርያም፣ ድነናል ወልደማርያም፣ አማኑኤል ወልደማርያም እና ኤርምያስ ወልደማርያም ይሰኛሉ። ሦስቱ ውጪ ሀገር ነዋሪዎች ናቸው፤ ኤርምያስ ወልደማርያም ብቻ እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ይኖራል።

ቄስ ወልደማርያም ኡርጂ እና ባለቤታቸው በሕይወት ስለሌሉ ፓስተር ተዘራ ያሬድ ለዓመታት በኪራይ ሲገለገልበት ቆይቶ በባለመብቶቹ የልቀቅልን ጥያቄ ሲቀርብለት ያንገራገረበት ይኸው ቤትና ይዞታ አራቱ ልጆቻቸው በውርስ ያገኙት ነው። ግቢው ውስጥ ለቸርች ተብሎ የተሠራን አዳራሽ በመጠነኛ ዋጋ ሲያከራዩም ነበር። ፓስተር ተዘራ ያሬድ "የክብር ሕይወት" ብሎ ለሰየማት ቤተ እምነት ከመከራየቱ በፊትም ሌሎች ቸርቾች በኪራይ ሲገለገሉበት ነበር።

ፓስተሩ አሀዱ ብሎ የቸርች አገልግሎት የጀመረው እዚያ ግቢ ቤት ውስጥ ሲሆን ቤቱን ተከራይቶ ከገባበት 2004 ዓ.ም እስከ 2012 ዓ.ም ድረስ የኪራይ ውል እያደሰና ኪራዩን ለአራቱ ልጆች የጋራ ወኪል ለሆነ ሰው ባንክ እያስገባላቸው ሲጠቀምበት ቆይቷል። 2013 ዓመተ ምህረት ላይ እዚያው አካባቢ ሲገነባ የቆየው አዲስ ቸርች ግንባታ አልቆ ስለነበር የቀድሞው ቸርች አከራዮች ቤቱን እንዲለቅላቸው ከመጠየቅ ባሻገር የኪራይ ውላቸውም እንዲቋረጥ ያደርጋሉ።

ፓስተር ተዘራ ያሬድ ግና "ለተጨማሪ አንድ ዓመት መቆየት እፈልጋለሁ" በማለት የልቀቅልኝ ጥያቄውን ሳይቀበል ይቀራል። ያንንም ታሳቢ በማድረግ ፈቃዳቸውን ሳይጠይቅ መጠነኛ ዕድሳት አከናውኗል። ከሌሎች ሰዎች እንደሰማሁት እርሱ በሚያምንበት የአንደበት ቃል አዋጅ መሠረት "ሠፈሩን እወርሰዋለሁ፣ ይኼንንም ቤት ገዝቼዋለሁ" ብሎ ኮንፌስ አድርጓል፤ ለጉባኤውም ለራሱም ይኼንኑ አውጇል። ግለሰቡ አካባቢውን የመውረስ ከፍተኛ ፍላጎት ስላለው ከፍ ብሎ የተጠቀሰውን አዲስ ቸርች እዚያው አካባቢ መሬት ገዝቶ ቢገነባም የቀድሞውንም መልቀቅ አልፈለገም።

የቤቱ ባለንብረቶች ደግሞ ቤታችንን የማትለቅ ከሆነ ኪራይ መጨመር አለብህ የሚል ውሳኔ ላይ ይደርሳሉ። የጨመሩትን ተመንም ያሳውቁታል። ምላሽ ባልሰጣቸው ጊዜም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ይወስዱታል። እርሱም በፋንታው በይዞታው ላይ ብዙ ገንዘብ አውጥቼ የእድሳት ግንባታ ስላከናወንኩ የቤት ባለቤትነት ስሙ ወደ እኔ መዞር አለበት የሚል ክርክር ያቀርባል።

ይሁንና ፍርድ ቤቱ ባለመብቶቹ ባልፈቀዱበትና ውል በሌለበት ሁኔታ በምን አግባብ ግንባታ ሊያከናውን እንደቻለ ያፋጥጠዋል። በዳኝነት ሂደቱ ፓስተር ተዘራ ያሬድ ሳይከፍል የቀረውን ውዝፍ ኪራይ ከፍሎ ቤታቸውን እንዲለቅም ብይን ይሰጣል። ፓስተሩ ብያኔውን ባለመቀበል አፈጻጸሙ እንዲዘገይ እስከ ሰበር ሰሚ ችሎት ቢሄድም ብይኑ የሕግ ክፍተት ስላልነበረው ሰበር ሰሚ ችሎቱም የታችኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ ያጸናል። ይኼኔም ነው ሰዎችን እየላከ ዛቻና ማስፈራራት የጀመረው።

ምንም እንኳ ቤት ለማደስ የባለመብቶቹን እና የአካባቢውን አስተዳደር የግንባታ ፈቃድ ማግኘት ግድ ቢሆንም ፓስተር ተዘራ ያሬድ ግና ቤቱን ከሦስት ሚሊየን ብር በላይ ወጪ አድርጌ ስላደስኩት የዚያ ክፍያ ካልተሰጠኝ አፍርሼ እቃዬን እወስዳለሁ የሚልን ኮንትራክተር አዘጋጅቶ በእልሁ ይገፋበታል። የፓስተሩ ይኼ ሁሉ ትግል ይዞታውን የራሱ ገንዘብ የማድረግ ምኞት እንደሆነ ትናንት ስለዚህ ጉዳይ ያወጋኝ የቄስ ወልደማርያም አራተኛ ልጅ ኤርምያስ ወልደማርያም አጫውቶኛል።

ከዚህ በታች ያለውን ታሪክ እርሱ ራሱ ይተርከው ዘንድ ስለወደድኩ እንደሚከተለው አስቀምጬዋለሁ። (ኤርምያስ ወልደማርያም ፓስተሩን በ"አቶ" እየተካ ስለሚጠራ እኔም እርሱ ያለውን ነው በቀጥታ የወሰድኩት። ኤርሚያስ ፍርድ ቤት ቆሞ ምላሽ በሚሰጥበት ወቅትም "አቶ ተዘራ" እያለ በመጥራቱ ዳኞች "ፓስተር" እንዲል በጠየቁት ሰዓት እንኳ ግለሰቡን "ፓስተር" የማይልበትን ምክንያት በመጥቀስ አሻፈረኝ ማለቱን ነግሮኛል ።)

"አሁን ላይ የክብር ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ያለበት ቤታችን አቶ ተዘራ ያሬድ ለሚመራው ለዚሁ ቤተ እምነት ከመከራየቱ በፊት ግቢያችን ውስጥ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሠርተን በትንሽ ገንዘብ ለቸርች አገልግሎት እናከራይ ነበር። ከእርሱ በፊትም ሌላ ቸርች ነበረበት። አቶ ተዘራ ቤታችንን የተከራየው ከ2004 አንስቶ ነው። አገልግሎት አንድ ብሎ የጀመረውም እኛው ቤት ነው። ወንድሞቼ በፊት እንደ መልካም አገልጋይ ይመለከቱት ስለነበር ግንኙነታችን ጥሩ ነበር።

አቶ ተዘራ ያሬድ እስከ 2012 ዓ.ም ድረስ በውላችን መሠረት ኪራይ ሲከፍል ቆይቶ 2013 ዓ.ም ቤቱን እንዲለቅልን በነገርነው ጊዜ ነው የሽጡልኝ ጥያቄ ያቀረበው። የእኛ ፍላጎት ደግሞ እንዲለቅ ነው። ግለሰቡ እዚያው አቅራቢያ ሌላ ቸርች ገንብቶ ሳለ ይኼኛውን መልቀቅ ያልፈለገበት ምክንያት ምን እንደሆነ አናውቅም። ሌሎቹ ወንድሞቼ የሚኖሩት ውጪ ሀገር ስለሆነ ጉዳዩን በቅርበት የምከታተለውና ኃላፊነቱን ወስጄ ነገሮችን የማስፈጽመው እኔ ነኝ።

ስለዚህ እኔ ልቀቅልኝ እላለሁ፣ እርሱ ካልሸጥክልኝ ሞቼ እገኛለሁ እያለ ነው። ይባስ ብሎም "ቦታው ላይ ብዙ ወጪ አውጥቼ ስላደስኩት የኔ ነው" እስከማለትና ንብረቱን ወደ ራሱ ለማዞር እስከመሞከር ብዙ መንገድ ሄዷል። ሁሉም መረጃዎች በእጄ ላይ ይገኛሉ። ቀደም ብዬ እንደነገርኩህ የግለሰቡ አካሄድ ስላላማረን ፍርድ ቤት ከሰነው ፍርድ ቤቱ ተገቢና ትክክለኛ ብይን ቢሰጠንም ያንን ለማስቀልበስ ከታችኛው ፍርድ ቤት እስከ ሰበር ድረስ ሄዶ ሞክሯል። ያም አልተሳካለትም።

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

መዝሙር 107፣ በነውጡ ዓለም ውስጥ ሁሉን የሚገዛውን የሉዓላዊ እግዚአብሔር ትድግና ያሳየናል። ስፐርጀን እንደሚለው:-

“እግዚአብሔር ሲያዝ፣ ዐውሎ ነፋስ ማዕበልና ሞገድ በፊቱ በፍጹም ጸጥታ የሰግዳሉ . . . በሕይወት ማዕበልና ነውጥ መካከል አእምሮን ሁሉ የሚያልፍ እውነተኛ ሰላም የሚሰጥ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ በርግጥ የእርሱ ሰላም ብቻ ፍጹም ሰላም ነው - ፍጹም የውስጥ ረፍትና ጸጥታ።" (Treasury of David, Psalm 107)

ይህ መዝሙር አራት ምሳሌዎችን በመጥቀስ፣ በሕይወት ነውጦች መካከል ስለሚገለጥ የእግዚአብሔር ሰላም ይናገራል።

* መውጫ መግቢያው በማይታወቅ የምድረ በዳ ጉዞ ለደከሙ፣ ለዛሉና የሕይወት ውሉ ለጠፋባቸው (4-9)
* በጨለማና ጥልማሞት እስር ቤት ውስጥ ለተጣሉ (10-16)
* በሰቆቃ፣ በሕመምና በስቃይ ላሉ (17-22)
* በኀይለኛና ቁጡ የሕይወት ማዕበል ውስጥ ላሉ (23-32)

እነዚህ ነውጦች በሙሉ የሚዘጉት፣ "በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው" በሚለውና የእግዚአብሔርን ሉዓላዊ ትድግና በሚያበስር የምስጋና ቃል ነው። እንደ ክርስቲያኖች ተስፋ የምናደርገውና በሕይወት ነውጥ ውስጥ እንድንቆም የሚያደርገን የእግዚአብሔር አብሮነት ነው። ቢታወቀንም፤ ባይታወቀንም!

ከእግዚአብሔር ሉዓላዊ አገዛዝ ውጭ የሆነና እርሱ የማያየው ምንም ዓይነት መከራ አይደርስብንም። ድቅድቅ ባለ ጨለማ ውስጥ "አውራቂስ" የሚሉትን ብርቱ ዐውሎ ነፋስ ተከትሎ በተነሣው ማዕበል በምትናወጠው መርከብ ውስጥ እግዚአብሔር ከእስረኛው ሐዋርያው ጳውሎስ ነበር። የመትረፍ ተስፋ ሁሉ በተሟጠጠበት ሁኔታ ውስጥ፣ እግዚአብሔር ጳውሎስን "አትፍራ" ሲለው እንመለከታለን። (ሐዋ. 27፡24)። "ሁሉን የምገዛና የምቆጣጠር እኔ ነኝ - I AM" ማለቱ ነበር።

መቼስ በዚህች ምድር ላይ ሕይወት ፈርጀ ብዙ ሰልፍ አለባት። በአንድ ወቅት የክርስቶስ ደቀመዛሙርት ኀይለኛ ዐውሎ ነፋስ ባሰነሳው ማዕበል መካከል ነበሩ። ጀልባቸው እንደ ሌሎች ጀልባዎች ሁሉ በነውጥ መካከል ነበረች። ሆኖም ልዩነቱ፣ በጨለማና በሞገድ ትናወጥ በነበረችው ጀልባቸው ውስጥ ክርስቶስም አብሮአቸው መሆኑ ነበር። ይህን እውነት የተረዱት ዘግይተው፣ ዐቅምና ተስፋ በተሟጠጠበት ሰዓት ነበር። ጌታም ተነሥቶ፣ "ነፋሱን ገሠጸው፤ ባሕሩንም፣ “ጸጥ፣ ረጭ በል!” አለው። ነፋሱም ጸጥ፣ ረጭ አለ፤ ፍጹምም ጸጥታ ሆነ።" (ማር. 4:39)።

ቅዱሳን፣ በምንም ሁኔታ ውስጥ ሁኑ፣ “ነፋሱም ሞገዱም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው?” በማለት የተደነቁበት ጌታ ከእናንተ ጋር አለ! እንደ አገርና እንደ ክርስቲያን ማኅበረስብ በነውጥ መካከል እንገኛለን። እንዲሁም መጠኑ ይለያይ እንጂ ሁላችንም በግል የምናልፍበት ነውጥና መከራ ይኖራል። ዘማሪው እንዳለው አንዳንድ ጊዜ በሕይወት፣ "እንደ ሰከረ ሰው ዞሮባቸው ወዲያ ወዲህ ተንገዳገዱ፤ መላው ጠፍቶባቸው የሚያደርጉትን አጡ" ተበሎ እንደተዘመረላችው የሚሰማን ወቅት አለ (ቁ. 27)። ሆኖም፣ ይኸው ዘማሪ እንዳለው፣ በዚህ ውስጥም እግዚአብሔር ኹነቶችን ሁሉ በሉዓላዊነቱ እየገዛ አለ።

"ጸጥ በማለቱም ደስ አላቸው፤ ወዳሰቡትም ወደብ አደረሳቸው. . . ምድረ በዳውን ወደ ውሃ መከማቻ፣ ደረቁንም ምድር ወደ ውሃ ምንጭ ቀየረ" (30-33)።

ይህ መዝሙር ሲጀምርም ሲጨርስም፣ ስል እግዚብሔር ምሕረትና ትድግና በማወጅ ነው። “ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና"(1) . . . "እንግዲህ ማንም ብልህ ቢሆን፣ ይህን ነገር ልብ ይበል፤ እርሱም የእግዚአብሔርን ምሕረት ያስተውላል"(45)። በመካከል ባለው የሕይወት ነውጥ ውስጥ ደግሞ እግዚአብሔር "ልዑል" ነው።

በተዘጋ ደጅ ውስጥ በፍርሃት ለነበሩት ደቀ መዝሙርት ተገልጦ፣ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" ያለው የሰላም አለቃ ጌታ ክርስቶስ የሚሰጠው ሰላም በልባችን ይንገሥ፤ ምድራችንንም ያሳርፍ።

“እግዚአብሔር አዳኛችን ሆይ፤ በጽድቅ ድንቅ አሠራር መልስልን፤ አንተ ለምድር ዳርቻ ሁሉ፣ በርቀት ላለውም ባሕር ተስፋ ነህ። ተራሮችን በብርታትህ መሠረትህ፤ ኀይልንም ታጥቀሃል። አንተ የባሕሮችን ማስገምገም፣ የማዕበላቸውን ፉጨት፣ የሕዝቦችንም ሁከት ጸጥ ታደርጋለህ።” (መዝሙር 65:5-7 )።

አሜን!

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ዕቅበተ እምነትና እና ዐቃቢያን #1

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ "ዕቅበተ እምነት" ወይም "ዐቃቢ" የሚል ቃል እየተለመደ መጥቷል። አንዳንዶች በአወንታዊነት ሲቀበሉት ሌሎች ደግሞ በአሉታዊ መልኩ ይመለከቱታል። በአገልግሎቱ ላይ ዋጋ እየከፈሉ የሚጋደሉ ጥቂት አቃቢያን ቢኖሩም የዕቅበተ እምነት አገልግሎትን እየቸረቸሩ ለመሸጥ ያጎፈሩ ጥቅመኛ "ዐቃቢያንም" ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል። ስለዚህ "ዕቅበተ እምነትና እና ዐቃቢያን" በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ጥቂት ማለት የሚያስፈልግ ይመስለኛል።

ዕቅበተ እምነት ምንድነው?

የዕቅበተ እምነት አገልግሎት የማስተማር አገልግሎት ነው። “እናንተ ስላላችሁ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁል ጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ” (1ኛ ጴጥ3:15) የሚለውን የመፅሐፍ ቅዱስ ቃል ለመፈፀም እና አማኞች "መልስ" እንዲኖራቸው በብርቱ የሚተጋ የማስተማር አገልግሎት ነው።

በዚህ ምንባብ ላይ "መልስ ለመስጠት" የሚለውን ቃል በእንግሊዘኛው "to defence" በግሪክ ደግሞ "apologian" ከሚለው ቃል ጋር የተዋረሰ እምነትን "ዕያቀቡ ማስተማር" የሚለውን ሃሳብ የሚያፀና ቃል ነው። "ማቀብ" (apologia) የሚለውም ቃል በፍርድ ቤት በሚደረግ ክርክር ወቅት የሚደረገውን "ሙግት" ለማሳየት ጥቅም ላይ የሚውል ቃል እንደሆነ የጳውሎስን የፍርድ ቤት ውሎዎች በምናነብበት ጊዜ ጥቅም ላይ ውሎ እናገኘዋለን።

ስለዚህ ዕቅበተ እምነት (Apologetics) የማስተማር አገልግሎት ነው። የክርሰትና አስተምህሮዎች ሲሸረፉም (ሲነፍቁ) ሆነ ከዚያ በፊት በቃሉ እውነትና በርቱዕ አመክንዮ ላይ ቆሞ የሳተውንም ያሳተውንም እየሞግተ "መልስ" ለሚያስፈልገው ሁሉ መልስ እየሰጠ በክርስቶስ ተከታዮች ዘንድ ያለው "ተስፋ" በቃሉ እውነት ላይ የፀና እንዲሆን የሚተጋ የማስተማር አገልግሎት ነው (አጠር ባለ መልኩ ካስቀመጥነው)።

እውነቱን ብቻ መናገር?

አሁን አሁን ግን በአንዳንዶች ዘንድ "የተጠራሁት እውነቱን ብቻ እንዳስተምር ነው" ይሉት ፈሊጥ መጥቷል። እውነቱን ሲያስተምሩ የነበሩት (ኢየሱስና ሐዋርያቱ) ሃሰቱንና አሳቹን እየጠቀሱ ሲያልፍም እየሞገቱ ማስተማራቸው ተዘንግቶ "እውነትን ብቻ ማስተማር" በሚል ግማሽ እውነት አስታኮ ሃሳዊያንን እንዳላዩ የማለፍ ዝንባሌ "ከእኛ በላይ መምህሬነት ላሳር" በሚሉቱ ዘንድ ይታያል።

በርከት ያለው የዋህ ጴንጤም ይህን መርዛማ አስተሳሰብ ገዝቶ አቃብያኑ (ተሟጋች መምህራኑ) ሃሳውያኑን ሲቃወሙ አስተያየት ይሰጣል። "ለምን ዝም ብላችሁ እውነትን አታስተምሩም....ዝም ብላችሁ እውነትን ብታስተምሩ እኮ ሃሰት በራሱ ጊዜ ይጠፋል" የሚልም የቃለ እግዚአብሔር ድጋፍ የሌለው ከንቱ መከራከሪያ ያቀርባል። የሚሳዝነው ግን "እውነትን ማስተማር ብቻውን በቂ ነው" የሚሉት መምህራን በየምስባኩ በቆሙበት ሃሰቱ እና አሳቹ በዝቶ እና ሞልቶ መፍሰሱን ትውልድም ወደ ሃሳዊያኑ መንደር መፍለሱን አላቋረጠም።

የሚገርመው "እውነቱን ብቻ መናገር" የሚለውን የጅል ፈሊጥ ኢየሱስም ሆነ ሐዋርያቱ ያልተከተሉት መሆኑ ነው። "እውነት እውነት እላችኋለሁ" እያለ እውነቱን ሲያስተምር የነበረውና ራሱንም "እኔ እውነት ነኝ" ብሎ የገለጠው ኢየሱስ ሃሳዊያንን በትምህርታቸው፣ በባህሪያቸውና በስማቸው እየገለጠ ነበር እውነትን ያስተማረው። እንጂ "እውነቱን ብቻ መናገር" በሚል "ሾላ በድፍን" አልነበረም ትምህርቱ። ጳውሎስም ቢሆን ሃሳዊያን ምን እንደሚያስተምሩ፣ ዓላማቸው ምን እንደሆነ፣ ሲያስፈልግም ስማቸውን እየጠቀሰ ነበር "እውነቱን" የሚያስተምረው።

አንድ "የእውነት አስተማሪ ነኝ" ባይ ሃሰትን በስሙ ሳይጠራው አሳቹን በግብሩና በህቡዕ ዓላማው ሳያጋልጠው ሲያስፈልግም በስሙ ሳይጠቅሰው እንዲያው በደፈናው "የእውነት መምህር ነኝ" እያለ በየመድረኩ ቢዞር "አድር ባይ" ወይም "ሰብኮ አደር" ጥቅመኛ መሆኑ መታወቅ አለበት። ምክንያቱም "እውነት" የሚስተውን ትውልድ የሚታደገው "ሃሰቱን" ብሎም "አሳቹን" ለመግለጥ ሲደፍር ብቻ ነውና።

እና ምን ለማለት ነው?

ዕቅበተ እምነት ምንድነው? ለሚሉ ሁሉ፤ ዕቅበተ እምነት የኢየሱስንና የሐዋርያቱን ፈለግ (ሞዴል) የሚከተል የማስተማር አገልግሎት ነው። እውነቱን ብቻ ሳይሆን ሃሰትንና አሳቹን ጭምር እየገለፀ ትውልድን የሚታደግ አገልግሎት ነው።

ስለዚህ ዕቅበተ እምነትን ማጣጣል የማስተማር አገልግሎትን ማጣጣል ነው። ዕቀበተ እምነትን መቃወም የማስተማር ፀጋ የሚሰጠውን መንፈስ ቅዱስን መቃወም ነው። ዕቅበተ እምነትን መግፋት ለሃሳዊያን በሩን መክፈትና በጎችን ወደ ተኩላዎች መግፋት ነው። ዕቅበተ እምነትን ማንቋሸሽ አማኞች ከየአቅጣጫው ለሚመጣባቸው ስሁት ትምህርትና ልምምድ መልስ እንዳይኖራቸውና ሞጋች እንዳይሆኑ ሆን ብሎ መስራት ነው። በአጭሩ የዕቅበተ እምነት አገልግሎትን ማክበር የእግዚአብሔርን ቃል ማክበር ነው።

አቃቢያን መምህራን ናቸው!!!

ቴዎድሮስ ተጫን

Читать полностью…
Subscribe to a channel