negere_evangelical | Unsorted

Telegram-канал negere_evangelical - ነገረ ወንጌላውያን

2910

በወንጌላውያን አማኞች ዘንድ የሚፃፉ ፅሁፎች፣ ዘገባዎችና ዜናዎች ይቀርባሉ! ትምህርቶች፣ መረጃዎችና ምካቴ እምነቶች በዚህ ቻናል ይስተናገዳሉ! በተለያዮ ሶሻል ሚዲያዎች የሚገኙ ፀሐፊያን የሚፅፉቸው ፅሁፎችን እናጋራለን።

Subscribe to a channel

ነገረ ወንጌላውያን

የዳንኤል ንሰሃ

"የከሸፈው ንሰሃ" የሚለውን ልጥፌን ተከትሎ ይነሳሉ ብዬ እኔም ከጠበቅኋቸው አንዳንዶችም በኮሜንት ሳጥን ካነሷቸው ተገቢ ጥያቄዎች መካከል "ዳንኤልስ እግዚአብሔርን በበደሉት በእስራኤላውያን ፈንታ ንሰሃ ገብቶ የለምን...ወንጌላውያኑስ ለሃሳውያኑ ንሰሃ ቢገቡላቸው ምን አለበት" የሚለው አንዱ ነው።

የዳንኤል ንሰሃ

እውነት ነው ዳንኤል ለህዞቡ በደል ንሰሃ ገብቷል። ምክንያቱ ደግሞ ግልፅ ነው። ዳንኤል እስራኤላዊ ስለሆነ፣ በደም እና በኪዳን ከእርሱ ጋር የተሳሰሩትን ህዝቡን ወክሎ ንሰሃ ቢገባ ምንም ችግር የለውምና ነው። ዳንኤልና ህዝቡ የአንድ ማህበረሰብ አካል ናቸውና!

ሃሳውያንን በተመለከተ በመስቀል አደባባይ የቀረበው ሰሞነኛው "የንሰሃ" ጉዳይ ግን በአይነቱም በይዘቱም "ከዳንኤል ንሰሃ" ለየት ያለ ነው። ምክንያቱም ከወንጌላዊው ክርስትና ጋር ምንም ተዛምዶ የሌላቸው ሃሳውያን ለሰሩት በደል "ወንጌላውያን" እንደ በዳይ ሆነው "ንሰሃ ለመግባት" የቀረቡበት ስለሆነ።

በግልፅ እንደሚታወቀው "ሃሳውያኑ" በአስተምህሮም ሆነ በልምምድ "ወንጌላውያን" አይደሉም። ሾልከው የገቡ ተኩላዎች ናቸው እንጂ። በጎችህን ሊበላ የገባን ጨካኝ ተኩላ ደግሞ ታስወግደዋለህ እንጂ "እግዚአብሔር ሆይ የእርሱን በደል እንደ እኔ በደል ቁጠርልኝ" ብለህ እርሱን ወክለህ (ከራስህ ጋር አንድ አድርገህ) ንሰሃ እየገባህ የበለጠ እንዲያጠፋ አትሸፋፍንለትም።

እስኪ አስቡት አንድ ወንጌላዊ ነኝ የሚል መሪ ጆይ ጭሮ እና ሚራክል ተካን የመሳሰሉ አሳቾችን በብቱ አቅፎ "የእነርሱን ማጭበርበር እኔ እንዳጭበረበርሁት አድርገህ ቁጠርልኝ" ብሎ በእግዚአብሔር ፊት ንሰሃ ይገባል? ይህ እኮ "እናንተ ማሳታችሁን ቀጥሉ እኛ ንሰሃ እየገባንላቸው ነው ብለን ሽፋን እንሰጣችኋለን" እንደማለት ነው።

ደግሜ እላለሁ መፅሐፉ "ሃሰተኛውን አስወግደው አትተባበረው ሰላም አትበለው" ይላል እንጂ አቅፈኸው ንሰሃ ግባለት አይልም! በብሉይ ኪዳንም እኮ "ሃሰተኛውን በድንጋይ ውገረው እንጂ ንሰሃ ግባለት" የሚል አልተፃፈም። ዳንኤልም ስለ "ህዝቡ" እንጂ በዚያ ዘመን ስለ ነበሩት "ሃሳውያን" ንሰሃ አልገባም።

ስለዚህ ዳንኤል ለህዝቡ ንሰሃ መግባቱን አጣቅሰን "ከቤተክርስቲያን አስወግዷቸው" የተባሉትን ሃሳውያን "በንሰሃ" ስም "ነፃ ለማውጣት" ጥረት ማድረግ የለብንም። ሃሳውያኑ ሲጀመር አማኞች (ክርስቲያኖች) አይደሉምና!

ቴዎድሮስ ተጫን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

መነኩሴዋ ድመት ስትሆን

በቀደም ስለ ኪሮሽ አካፍዬ ነበር። ሐሰተኞች ሲወጉ ያሳምማሉ፤ ከወጡ፥ ሲወጡ አብዝተው አሳምመው ነው የሚወጡት፥ ልክ እንደ ኪሮሽ ውጊት። ዋጋ አስከፍለው ብቻ ሳይሆን አብዝተው፥ አባዝተው ያስከፍላሉ።

በአንድ አገር አንድ ሰው ሰፊ የገጠር ርስቱን የዱር አራዊት መጎብኛ አደረገው፤ ሰዎችም መጥተው እንዲጎበኙት የማስጎብኛ መኪናዎች፥ የሰለጠኑ አስጎብኚዎች፥ ሌሎችም አስፈላጊ ነገሮችን ሁሉ አሟልቶ ፈቃድ አወጣ። ለመጎብኘት የሚገቡ ሰዎች ክፍያ በአንድ ሰው $50 ዶላር አደረገ። የሚገባ ሰው ጠፋ። በ50% ቀነሰና $25 አደረገው። የሚገባ ጠፋ። አሁንም 50% ቅናሽ አድርጎ $12.50 አደረ። አሁንም ገዢ ጠፋ። በመጨረሻ ቤተ አራዊቱን ለመዝጋት ወሰነና፥ ‘ለአንድ ቀንና ከመዘጋቱ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ብቻ መግቢያ በነፃ!’ ብሎ ለጠፈ። ሰው ተግተልትሎ መጣ። በየመጎብኛው መኪና እየገቡ እየዞሩ ሲጎበኙ ቆይተው ከመውጣታቸው በፊት አራዊቱ ከበዋቸው ሳሉ፥ ‘በሉ እንግዲህ፥ መግቢያው በነፃ ቢሆንም መውጫ በክፍያ ስለሆነ ነፍስ ያለው ሁሉ በነፍስ ወከፍ $200 ዶላር እየከፈላችሁ ነው የምትወጡት።’ ተባሉ። ምን ምርጫ አለ? ሁሉም፥ አንድም ሳይቀሩ፥ ምንም ሳያስቀሩ፥ እየከፈሉ ወጡ።

ሐሰተኛ ነቢያትና ሐሰተኛ ሐዋርያትና ሐሰተኛ አስተማሪዎች ሲያስገቧችሁ አያስከፍሏችሁም። እንዲያውም ይከፍሏችሁም ይሆናል። ስትወጡ ግን፥ (እሱም ከወጣችሁ ነው) ጠጉራችሁን ተላጭታችሁ፥ ቆዳችሁን ተልጣችሁ፥ ሥጋችሁን ተግጣችሁ ጸጋችሁን ተገፍፋችሁና ነው የምትወጡት። አሳቾች አስጎብኚዎች ሳይሆኑ አራዊት ናቸው።

ቆንስላው የጠራውን ክብረ በዓል ዛሬ መጋቢት ፰ ያካሂዳል። ከመሪዎቹ አንዱ፥ በውስጡ የታቀፉት ሁሉ በአንድ መቀነት የተቀነቱ ወንጌላውያን እንደሆኑ አረጋግጦ ይህ ሊደነቅና ሊደሰቱበት የተገባ ጉዳይ መሆኑን ተናግሮአል። እንኳን እኛ ቃሉን የምናነብብ ቀርተን፥ ቃሉን የማያውቁ ጋዜጠኞችም ሐሰተኞች መሆናቸውን የሚያውቋቸውን ሁሉ ነው፥ ‘ወንጌላውያን’ ያለው። ይህን ሲል ትን አላለውም።

ከመሪዎቹ ሌላው ደግሞ፥ ሁሉም ወደየአምላኩ የሚጸልይበት እንደ ሃይማኖቶች ጉባኤ እንድንመለከተው አሳስቦአል። አብሮአቸው መሆን ሳይቀፍፈው፥ ግን አንድ ያለመሆናቸውን አስምሮበታል።

ቆንስላው ብዙ የጻፍኩበት ስለሆነ እንዲያው ለማሳሰብ ብቻ እንጂ ከሰንበራችን እና ጠባሳችን ጋር እንደምንኖርም የታወቀ ነው። ታሪካዊ ስሕተታችን ነው። ችግሩ ድመቷ መመንኮሷ ሳይሆን፥ መነኩሴዋ ድመት መሆኗ ነው።

ዘላለም ነኝ።

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

"ወንጌላውያን" እነማን ናቸው?

"ወንጌላውያን ከተባሉት መካከል በካውንስሉ ውስጥ ያልተካተተ ማንም የለም!" ይላል ጆኒ፤ መጋቢት 8 በመስቀል አደባባይ ስለሚደረገው መርሃ ግብር በሚያብራራበት ጊዜ። የንግግሩም አንድምታ "በካውንስሉ የተካተቱት ሃሳውያን በሙሉ 'ወንጌላውያን' ናቸው!" የሚል ዓይነት ነው። ይህ አይነቱ ንግግር ታዲያ በካውንስሉ አካባቢ ቀስ በቀስ "በወንጌላውያን ማንነት" ላይ ብዥታ እየተፈጠረ መምጣቱን አመላካች ነው።

እስኪ እንጠይቅ በእርግጥ "ወንጌላውያን" የሚባሉት እነማን ናቸው? ሃሳውያንስ በካውንስሉ ጥላ ስር ስለገቡ ብቻ ወንጌላውያን መሰኘት ይችላሉ?

መጋቢት 21 ቀን 2009 ዓ.ም በወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት የነገረ መለኮት ኮሚሽን ተዘጋጅቶ
በህብረቱ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለውይይት መነሻነት የቀረበው ፅሑፍ "የወንጌላውያንን" ማንነት ሲያብራራ:-

"ወንጌላዊነት (Evangelicalism) ከፕሮቴስታንት ንቅናቄ በኋላ የተፈጠሩትን የተለያዩ ቤተእምነቶች የጋራ በሆኑ የሃይማኖትና የስነ ምግባር ዕሴቶች የሚያቀራርብ ጥላ ሆኖ የሚያገለግል ሃይማኖታዊ ማዕቀፍ ነው" ይላል። በተጨማሪም "ወንጌላዊው ክርስትና ቀደምት የክርስትና ትምህርቶችን በማቀጣጠን የተገኘ የሰው እጅ ስራ አይደለም" በማለት "ወንጌላዊው እምነት ከጥንታዊው ርቱዕ ክርስትና ማፈንገጥ" አለመሆኑን አፅንዖት ይሰጣል። ይህ አይነቱ ገለፃ ለሃሰትና ለሃሳውያን ምንም ስፍራ የለውም።

በተጨማሪም ታዋቂው የስነ መለኮት ምሁር ጄ. አይ. ፓከር "ወንጌላዊው ክርስትና በመፅሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ላይ የተመሠረተ ንፁህ የክርስትና እምነት፣ ኢየሱስን ፈፅሞ በመከተልና እርሱን መካከለኛ በማድረግ ላይ የተመሠረተ ተግባር ተኮር እምነት ነው" በማለት የተናገረው ንግግርም ሃሳዊውን ሁሉ ከየመንደሩ ሰብስበን "ወንጌላውያን ናቸው" ከማለት እንድንታቀብ የሚጠቁም ነው።

በእርግጥ ዘንድሮ "ወንጌል አማኝ!" የሚለውን ካባ ያላጠለቀ ማን አለ? "ሰው መንፈስ ነው" የሚለውም፣ ከክርስቶስ ጋር ትከሻ ለትከሻ የሚለካካውም፣ በሃሰት ትንቢቱ ሰው የገደለውም፣ በገስት ሃውስ ስም ገንዘብ የሚበዘብዘውም፣ ዘይትና ጨርቅ ሻጩም.....ሁሉም "ወንጌላዊ ክርስቲያን" የመባልን ሽቶ ከጎፈነነ ልብሱ ላይ ነስንሷል። ያሳዝናል!

ለማንኛውም ግን "ወንጌላዊነት" በርቱዕ ክርስቲያናዊ አስተምህሮ መሠረት ላይ ቆመው መሠረታዊ ያልሆኑ ልዩነቶቻቸውን ያቻቻሉ አብያተክርስቲያናት የሚሰባሰቡበት "ጥላ" እንጂ በሃሰት ትምህርትና በንዋይ ፍቅር የሰከሩ "ተኩላዎች" ተጨማሪ በጎችን እንዲበሉ በመሸፈኛነት እንዲያገለግል የሚታደል "ለምድ" አይደለም!

ቴዎድሮስ ተጫን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ካውንስሉ የፀሎት ጥሪ ማቅረብ አይችልም!

ያኔ...."የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስልን" ለመመስረት ከቤተ-መንግስት እስከ ቤተ-ክህነት ድረስ ከፍተኛ ሩጫ በሚደረግበት ወቅት ከተለያዩ ወገኖች ብዙ ተቃውሞ ይሰነዘር ነበር። ነገር ግን "በአመቻቾቹ" እና "በተመቻቺዎቹ" በኩል የምስረታውን አስፈላጊነት አስመልክቶ"ካውንስሉ "ህጋዊ ማዕቀፍ እንጂ መንፈሳዊ ህብረት አይደለም" የሚል መሞገቻ በአፅንዖት ይቀርብ ነበር።

"አመቻች" እና "ተመቻቾችም" ሙግታቸውን ለማጠናከር በወንጌላውያን ላይ እዚህም እዚያም የሚደርሱ ስደቶችን እንደ ማሳያ በመጠቃቀስ "ለወንጌላውያን ጥብቅና የሚቆም ህገመንግስታዊ እውቅና የተሰጠው አንድ 'ህጋዊ ማዕቀፍ' ያስፈልገናል" የሚል "ሎጂክ" አክለውበት በደረቅና በባህር ብዙ ሮጠዋል። በወቅቱም ጥቂት የማይባሉ ወገኖች ይህ ዐይነቱ የካውንስል ምስረታ "በግና ተኩላውን" በአንድ ጎረኖ የማኖር ያክል ስለሆነ ሊቆም ይገባዋል ብለው አደጋውን እያመላከቱ ቢቃወሙም ሰሚ አልነበረም። ከዚያ ይልቅ የወቅቱ መሪዎች የነበሩት "ህጋዊ ማዕቀፍ እንጂ መንፈሳዊ ህብረት አይደለም" የሚለውን ማታለያ ጮክ አድርገውና እየደጋገሙ መናገሩን መረጡ።

ነገር ግን "ካውንስሉ" በተመሰረተ በማግስቱ "ህጋዊ ማዕቀፍ ነኝ" ከሚለው ለሽፋን ከተጠቀመበት ቅርፊት በፍጥነት ወደ "መንፈሳዊ ማዕቀፍነት" ይለወጥ ጀመር። በአደረጃጀቱም "መንፈሳዊ" የሚባል ዘርፍ በቢሮው አቋቋመ። ይባስ ብሎም በደባባይ (በአዲስ አበባ ስታድየም ) በእውነተኛ አብያተክርሰቲያናት የሚገኙ ምዕመናንን ከሃሳውያኑ እና ከሳቱት ጋር ቀይጦ "መንፈሳዊ" መርሃ ግብር በማዘጋጀት "መንፈሳዊ ማዕቀፍ" መሆኑን በተግባር አረጋገጠ። በዕለቱም ተኩላዎች ከበጎች ጋር ተያይዘው "እጅ ለእጃች ተያይዘን ኢየሩሳሌም እንገባለን" ብለው ዘመሩ።

ቀስ በቀስም ካውንስሉ "ህጋዊ ማዕቀፍ ነኝ" የሚለውን ወደ ጎን ብሎ (ሆን ብሎ ዘንግቶ) "በመንፈሳዊ ማዕቀፍነቴ እወቁኝ" ማለቱን ተያያዘው። ስለዚም ፀሎት ይጠራል፣ ፆም ያውጃል፣ ልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች ያዘጋጃል ወዘተ...። ነገር ግን ይህ ድርጊቱ በፍፁም ተቀባይነት የለውም። ምክንያቱም:-

1."ሃሳውያንን ሰላም አትበሏቸው" በማለት ከሃሳውያን ጋር የሚኖረን ግንኙነት በመራቅ፣ በማራቅ፣ በመለየትና ባለመተባበር ላይ የተመሠረተ መሆን እንዳለበት በግልፅ የተፃፈ መፅሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያ ስላለን።

2. ካውንስሉ "አባላቴ ናቸው!" ብሎ ""በስላሴ አላምንም" የሚለውን ካሳ ኬራጋ "ኢየሱስ ሰይጥኗል" ብሎ የሚያስተምረውን" ዘላለም ጌታቸው፣ "ሰው መንፈስ ነው" ብሎ እያሉ የሚያስቱት ተዘራ እና ጃፒ "የአንደበታችን ቃል ልክ እንደ እግዚአብሔር ቃል መፍጠር ይችላል" ብሎ የሚያስተምረው ዮናታን፣ በሃሰተኛ "ትንቢቶቻቸው" ለሰዎች ሞት እና ጥፋት ምክንያት የሆኑት እዩ ጩፋ እና ኤርሚያስ ሁሴን "ገንዘብ እናበዛለን" እያሉ በማታለል ስራ ላይ የተሰማሩት ሚራክልና ጭሮ....ወዘተ ወዘተ በውስጡ አቅፎ "መንፈሳዊ ህብረት" ማድረግ (አብሮ መፀለይ፣ ማምለክ) ስለማይቻል።

3. ካውንስሉ ከመነሻው "ለመንፈሳዊ ህብረትነት" ሳይሆን "ህጋዊ ጉዳዮችን" ብቻ በተመለከተ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናትን ለማገዝ የተቋቋመ እና ከፈቃድ መስጠትም ጋር በተያያዘ የሠላም ሚኒስትር ህጋዊ ወኪል ሆኖ ስለወንጌላውያን የሚሰራ በህግና በህግ ብቻ የሚመራ ተቋም ሆኖ ስለተቋቋመ።

ስለዚህ "የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል" ከስር በምስሉ ላይ እንደሚታየው ያለ የፀሎት እና የመንፈሳዊ ስብሰባ ጥሪ ማቅረብ የለበትም! አይችልምም!

ቴዎድሮስ ተጫን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ኑ እንዋቀስ

ዮናታን አክሊሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የያየኹት የዛሬ ስድስት ዓመት ነበር። ግንቦት 20, 2010 ዓ.ም በመስራቅ መሠረተ ክርስቶስ በተዘጋጀው "የደስታዬ እልልታ" የዝማሬ ድግስ ላይ ነበር ከዚህ ሰው ጋር የተዋወቅኩት። በካሪዛዊ ቀውስ እጅግ ተስፋ ቆርጬ ስለ ነበር የትኛውንም መንፈሳዊ ቻናል ቤቴ ከፍቼ አላይም ነበር። ቻናሎቹ እንዲኖሩኝም አልፈልግም ነበር። በረከት ተስፋዬ የተወሰኑ ዝማሬዎችን ካቀረበ በኋላ በቃለ እግዚሓር ሚያገለግለን ወንድም ወደ ምስባኩ ተጠራ። መድረክ መሪውም አገልጋዩን ሞቅ ያለ ማስተዋወቂያ ሰርቶለት ወደ ምስባክ ጠራው። ጉባኤውም እጅግ በደመቀ አቀባበል ዮናታንን ተቀበለ። የሕዝቡ አቀባበል አስገርሞኝ ስለ ነበር አጠገቤ የነበሩትን ወዳጆቼን ጠየቅኹ። ይኼን ሰው ታውቁታላቹ ወይ? አገልጋይ ዮናታንን እንዴት አላወቅከውም ብለው እነሱ በኔ ተገረሙ።

ከሮሜ መልእክት ምእራፍ አንድ ቁጥር አራት ሃሳብ በመነሳት ወንጌል ስለ ልጁ ነው ብሎ ዮናታን ሰበከን። የወንጌሉን ምንነት በቅጡ የተረዳ አገልጋይ አገኘን ማለት ነው ብዬ ተጽናናሁ። እጅግ አስረግጦ ሳያወላዳ ወንጌል ያልሆኑትን ነገሮችም እየነቀሰ ነቀፈ። ማያመቻምች ሰው ተነሳልን ብዬ ሀሴት አደረግኹ።

ጉባኤው ከተበተነ በኋላ ወደ ቤት እንደገባሁ አገልጋይ ዮናታን ሚያገለግልበትን ቻናል ጫኑልኝ ብዬ ሰዎችን ጠየቅኩ። በሱ ሰበብ ሌሎቹም መንፈሳዊ የተባሉ ቻናሎች ኹሉ ተግተልትለው ገቡ። ቀልቤን ቶሎ የሰረቁ ነገሮች ብዙ ነበሩ። ከቤተ ክርስቲያኒቱ መጠሪያ ይጀምራል። የአዲስ ኪዳን ካህናት። የእግዚአብሔር ሕዝብ የክህነት አገልግሎት የተሰጠው ሕዝብ ነው። መጽሐፍም በግልጽ እንደሚናገረው የተጠራነው የካህናት መንግስት እንድንኾንም ጭምር ነው። (ዘጸ 19:6, 1ኛ ጴጥ 2:9). የቤተ ክርስቲያኒቱ መጠሪያ ብቻ ግን አልነበረም ቀልቤን የሰረቀው። ማርሲል ሚለው የቲቪ ቻናሉ ስያሜና ይስሃቅ ሰዲቅም ጥሩ አድርጎ በዝማሬ ያቀረበው መሸጋገሪያ ዝማሬም ጭምር እንጂ። በክርስቶስ ኢየሱስ የመስቀል ላይ ጣር ምህረት የተቀበልን ሕዝቦች መኾናችንን ሚያወሳ ስያሜና ዝማሬ ስለ ነበር ወደድኩት።

መደነቄ ቀጥሏል። በወቅቱ ገበያው ላይ ከነበሩ ነብይ ተብለውም ከሚጠሩ ሰዎች ዮናታን በልዩነት ይታየኝ ጀመር። ራሱን አገልጋይ ብሎ በመጥራቱ ደስ አለኝ። ሊዘባነንብን ባይወድ ነው ብዬ ስላሰብኩ። እሱ በሚያገለግልባት አጥቢያም ትምህርት ሰፊ ጊዜ ስለ ተሰጠው ደስ አለኝ። ማርከር ይዞ በነጭ ሰሌዳ እየጻፈ ሲያስተምር ሳየው ይበልጥ ወደድኩት። ወደ ጉባኤው ሚገቡ ሰዎችም መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ከማስታወሻ ደብተራቸው ጋር ይዘው ሚመጡ በመኾናቸው እጅግ ተደሰትኩ። የዩሐንስን ወንጌል በተከታታይነት ሲያስተምር ይበልጥ ወደድኩት። ቃሉ በሃይልና በስልጣን ሚሰበክባት አጥቢያ አገኘን ብዬ ብዙ ተስፋ አደረግኩ። በሃይል አገልግሎቱም ቢኾን ዮናታን ልዩነት ነበረው። ለምሳሌ አጋንንትን ሲያወጣ ቃለ ምልልስ አያደርግም ነበር። ከአጋንንት እስራት የተፈቱ ሰዎችንም ምስል ብዙ ጊዜ ይሸፈን ነበር። ሲወድቁም እርቃናቸው እንዳይገለጥ አገልጋዮች ይጠነቀቁ ነበር። ገበና ሸፋኝ አገኘን አልኩ። ደግሞም ለጋስ መኾኑን አየኹ። ተቸግረው ወደ ጉባኤው ለመጡ ጭምር የትራንስፖርት ሲሰጥ አየኹ። ይኼ ሰው በርግጥም የቃሉ አገልጋይ ነው ብዬ ደመደምኩ።

ስብከቶቹ ላይ ማያቸውን አንዳንድ ጉልህ ስህተቶች የሃቲት እውቀት ክፍተት አድርጌ ነበር የወሰድኩት። አሊጎሪካል ስብከት በብዙዎች ዘንድ የተለመደ አካሄድ ስለኾነ የሱንም ስህተቶች በዚሁ ብርሃን ነበር ያየዃቸው። ለምሳሌ ከመጽሐፈ ኢዮብ ተነስቶ "አዞ" በሚል ርእስ የወንድማማችነት መዋደድ ምን ያህል ብርቱ እንደሆነ ያቀረበበት ስብከቱ ልዩ ትርጉም ከመፈለግ አባዜ የመነጨ ስህተት እንደነበር ግልጽ ነበር። ስለ ቅዱሳን ሕብረት ለማስተማር ኢዮብ 40 ላይ ያለው ገለጻ ልከኛ ምንባብ አይደለም። አጠገቡ ኾኖ ሚያግዘው ሰው ቢያገኝ እነዚህ ክፍተቶቹ ሊቀረፉ እንደሚችሉም አስብ ነበር።

በዚህ መኻል ነው መልካም ወጣት ኹለተኛው ዙር ስልጠና የጀመረው። ከወጣቶቹ ጋር ያለው መስተጋብር ያስቀናል። ወዳጃቸውና ታላቅ ወንድማቸው ኾኖ ይቀርባቸዋል። ልብሳቸውን ለብሶ ቋንቋቸውን ተውሶ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ያገለግላቸዋል። አብሯቸው በማእድ ይሰየማል። ከስብራታቸው ጋር አብሮ ያነባል። ተስፋን ስንቅ አርጎ ሊሰጣቸው ይባትላል። ስለ ሀገር ደግሞም ወገናቸው ተቆርቋሪ እንዲሆኑ ያሳስባቸዋል። ይኼ ሰው ኹለንተናዊ ለውጥ እንድናመጣ ሊሞግተን የቆመ ድምጽ ነው ብዬ ማሰብ ኹሉ ጀመርኩ።

ነገር መበላሸት የጀመረው እዚህ ጋር ነው። በሕግ ሊያስጠይቁ ሚችሉ ወንጀሎች በምስክርነት ስም መቅረብ ጀመሩ። ክፉ ደግ በቅጡ ማይለዩ ታዳጊዎች ካለባቸው ሱስ እስራት ነጻ ለመውጣት ካላቸው ጽኑ መሻት ያልተጨበጠ ምስክርነታቸውን መስጠት ጀመሩ። ዮናታንንም በብዙ ኢትዮጵያዊያን እናቶች ልብ የጭንቅ ቀን ልጅ ኾኖ ተሳለ። በዚህ ጊዜ ነው ዮናታን ወላዋይና ሸንጋይ ደግሞሞ በተጠና አካሄድ ሚራመድ ሰው እንደኾነ ማሰብ የጀመርኩት። ለሱ እስከጠቀመው ድረስ የሃይል ሚዛን ወዳጋደለበት ኹሉ ሚያጋድል እንደኾነ ማየት ጀመርኩ። ስሁት አስተምህሮ አላቸው ብሎ በአደባባይ ከነቀፋቸው ጋር በስውር ይወዳጃል። ምስሎቹ እንዳይወጡ ክትትል ያደርጋል። ንግግር ሚሰምርለት አይነት ተናጋሪ ስለሆነም የሰዎችን ቀልብ ቶሎ ይማርካል። ኦርቶዶክሳዊያንን ማስደሰት ሲፈልግ ትውፊታቸውን ተውሶ ያወራል። የኢትዮጵያኒዝምን ትርክት ጥሩ አድርጎ ይደሰኩራል። በዚህም ተወዳጅነቱና የተጽእኖው አዳማስ ከወንጌላውያኑ አልፎ በሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ደርሷል። ብሔራዊ ቲአትር ተናጋሪ ኾኖ ብዙ ጊዜ መቅረቡም የዚህ ተጽእኖ አድማስ ማሳያ ነው ብዬ አስባለሁ። በቴሌቪዥን መስኮቶቻችንም የወንጌላዊያን እንደራሴ ኾኖ እስከ መቅረብ የደረሰው በዚሁ ቅልጥፍናው ነው።

ዮናታን ከጠቅላዩ ጋር ቀላል በማይባሉ አካሄዶቹ ይመሳሰላል። እንደ ጠቅላያችን ስስ ብልቶቻችንን ጠንቅቆ አውቋል። ስለሆነም ራሱን የዘመናት ጥያቄያችን መልስ አድርጎ አቅርቧል። በጦርነት በምትታመስ ምድር፣ ስራ አጥነት የወጣቱን ሃሞት ባፈሰሰበት ሀገር የተስፋ ጭላንጭል አድርጎ ራሱን አቀረበ። ለመፈረካከስ ቋፍ ላይ ባለች ምድር የአንድነት ቀንዲል ኾኖ ተሳለ። የቤተ መንግስት ድጋፍ ያለው ሰው ኾነ። በግልጽ የወረፋቸውን ነብያትና አስተማሪዎች ከኋላ ሄዶ የአጋርነት ድምጹን ይሰጣቸዋል። ስለሆነም ኢዩ ጩፋ ላይ ግልጽ አቋም ያለው ብዙ አማኝ ዮናታን ላይ ያመነታል። ጃፒን መናፍቅ ብሎ ሚጠራ ሕዝብ ለዮናታን ስስ ልብ አለው። በርግጥ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረትም ለዚህ ግርታ ቀዳሚ ተጠያቂ ነው። በ32ኛው ጉባኤ በግልጽ ብዙ ትምህርቶችንንና ልምምዶችን ካወገዘ በኋላ ዮናታንንና መሰሎቹን በአጋርነት አስጠጋ። ከማስጠጋት አልፎ ግን የሕብረቱ ፕሬዘዳንት ጭምር አዳራሽ ከመመረቅ እስክ የመልካም ወጣት መክፈቻ ፕሮግራሞች ታዳሚ ኾኑ። በሚሊኒየም አዳራሽ በተደረገው የመክፈቻ ዝግጅት ላይ ያልታደመ ሐሰተኛ አልነበረም። በዚህ ኹሉ ግን ዮናታን ከተጠያቂነት ያመልጥ ነበር። ራሱን ያለ ምስክር ማይተው ቸር አምላክ የዚህን ሰው ኹለት ቦታ መርገጥ ደግሞም መሰሪነት ቀድመው ያስተዋሉ ሰዎችን አስነስቶልን ነበር። በአደባባይ የድንጋይ ክምር እናርጋቹ አልናቸው እንጂ! ዮናታን የብልጽግና ወንጌል አስተማሪ የእምነት ቃል ምንፍቅና አቅንቃኝ እንደሆነ እግር በእግር ተከትለው በማስረጃ ሊያሳዩን የሞከሩ ነበሩ። በወንድማችን አሳየኸኝ ለገሰ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ዕውቀት ጠልነትና መዘዙ…

“እውቀትን ጠልተዋልና፥ እግዚአብሔርንም መፍራት አልመረጡምና፤ ምክሬን አልፈቀዱምና፥ ዘለፋዬንም ሁሉ ንቀዋልና፤ ስለዚህ የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፥ ከራሳቸው ምክር ይጠግባሉ። አላዋቂዎችን ከጥበብ መራቅ ይገድላቸዋልና፥ ሰነፎችንም ቸልተኛ መሆን ያጠፋቸዋልና። (ምሳ. 1:29-32)

ዕውቀትን መጥላት ምን ያህል ጉዳት እንዳለው ቃሉ በግልጽ የተናገረበትን ክፍል በመጥቀስ የጀመርኩት እግዚአብሔር ቃሉን እንድናውቅ፣ እራሱን እንድናውቀው፣ ፈቃዱን እንድናውቅ፣ ልጁን ክርስቶስን እንድናውቅ፣ የመዳንን መንገድ እንድናውቅ የሚፈልግ መሆኑን በመግለጽ ጸረ-ዕውቀት መሆን ምን ያህል ጉዳት እንዳለው መዘዞቹን በጥቂቱ ማንሳት የዛሬው ውይይታችን ዋና ሀሳብ ለማድረግ ነው።

እግዚአብሔርን መፍራትና ለእርሱ ተገቢውን ክብር መስጠት የሚመጣው እግዚአብሔርን፣ ፈቃዱንም በውል ስናውቅ ነው። እዚህ ክፍል ላይ እውቀትን የጠሉት ሰዎች የመንገዳቸውን ፍሬ እንደሚበሉና ከእውቀት መራቅ ገዳይና አጥፊ መሆኑንም ይናገራል። እግዚአብሔር የእውቀት ሁሉ ምንጭ ነው። ሁሉን አዋቂ አምላክ ሲሆን እንድንጋራ ከፈለገው ባሕሪያቱ አንዱ ዕውቀት ነው። ሁሉን ማወቅ ባንችልም ዕውቀት እንዲኖረን ፈልጎአል። በሰው በኩል ያለዕውቀት የሚደረግ አምልኮና ስግደት፣ ያለዕውቀት የሆነ መከተል፣ ያለዕውቀት የሚደረግ ፍለጋ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ አይደለም።

አሁን ባለንበት በዚህ ዘመን ራሳቸውን ሱፐር መንፈሳዊ አድርገው የሚቆጥሩ ሰዎች በአብዛኛው ከእውቀት የጸዱ ብቻም ሳይሆኑ ጸረ-እውቀት (Anti-intellectual) ናቸው። እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ራሳቸውን ከሰቀሉበት ቆጥ ላይ አውርደው በትህትና ዕውቀትን ለመፈለግ ምንም ዕድል አያገኙም። ይልቁንም ዕውቀትንና የዕውቀት ሰዎችን የማሳደድ አዝማሚያ ይታይባቸዋል። “ጌታ የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ ባክህ በተማረ አይደለም።” “እስኪ ጎንህ ላለው ሰው ተናገር ባወቀ አይደለም በለው።” በማለት ለዕውቀት ጥሩ ቦታ ያላቸውን በመደዳ ሲጨረግዱ መስማት የተለመደ ነው።

ይህን የሚያደርጉት በውስጣቸው የሚንጫጫውን የበታችነት ስሜት ለማፈን መሆኑን ግን ሳያስነቁ ነው። በአሁኑ ጊዜ ክርስትናችን ለምንድነው ዕውቀትን ጠልቶ ለስሜት ከፍተኛ ሥፍራ መስጠት የጀመረው? በክርስትና ጉዞ ውስጥ ዕውቀት የነበረውና የሚኖረው ሚና ለምን ይኼን ያህል ተዘነጋ? የሚለው ጉዳይ ጥናት የሚያስፈልገው ጉዳይ ይመስለኛል። ስብከቶቻችንም ሆነ ዝማሬዎቻችን በአብዛኛው ለስሜቶቻችን የታለሙ እንጂ ጥልቅ መረዳትና ግንዛቤ እንዲሰጡን ታስበው የሚዘጋጁ የክርስትናን መሠረታዊ የእምነት አቋም የሚያስረዱ አይደሉም።

የግለሰቦች ግላዊና ወቅታዊ ስሜት መኮርኮር መቻልን እንደ መንፈሳዊ መነቃቃት ማየት እየተለመደ መጣ። በክርስቲያናዊ አስተምህሮ፣ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ዘመን ዘለቅ እውነት፣ ያልተመሰረተ የስሜት ስካር ቤተ ክርስቲያናትን አንዴ ወደ ላይ ሌላም ጊዜ ወደታች ሲወዘውዛት ይስተዋላል። የእግዚአብሔር ማንነት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ፍጹምነት፣ የክርስቶስ መለኮትነትና ተስገዎ፣ የድነት መንገድ፣ የቤተ ክርስቲያን ምንነት፣ ሁሉ እውቀት የሚፈልጉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታዎች ናቸው። የመንፈስ ቅዱስሥጦታዎችን፣ መመንፈሳዊ መነቃቃትና ልምምዶችን የምንፈልገውን ያክል መንፈሳዊ ነገሮችን በጥልቀት ለማወቅ ያለን ጥማት፣ ትኩረት፣ ዝቅተኛ ነው።

አማኞች ስለ እምነታቸው በትኩረት ማሰብና በጥልቀት ማወቅ አለባቸው ብዬ አስባለሁ። እውቀትን የሚጠላ ጭፍን እምነት ሊኖረን አይገባም። ምዕመናን ያመኑበትን አምላክ ለምን እንዳመኑ ማወቅ ቢጠየቁም በተገቢው ሁኔታ ለመናገር ዝግጁ መሆን ይጠበቅባቸዋል የሚል እምነት አለኝ። ዕውቀትን ማጣት በቤተ ክርስቲያን እያስከተለ ያለው መዘዝ ምን ምን ሊሆን ይችላል??

1. ጥፋትን ያስከትላል።

“ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቶአል … ።” (ሆሴ. 4:6) ሕዝቤ “በጀት አጥቶ፣ እህል ወሃ አጥቶ፣ ወይም ደግሞ መሪ፣ መጋቢ፣ ነቢይ፣ አጥቶ” እያለ አይደለም። እነዚህ ሁሉ አስፈላጊ ቢሆኑም የዕውቀት እጦት ያህል አጥፊ አይደሉም። ያለ ዕውቀት ብርሃን የሚደረገው ጉዞ በጨለማ የሚደረግ መርመስመስ ነው። መጨረሻው መሰነካከል ነው። ጥፋት ነው። ሆሴዕ ቁ.1 ላይ እግዚአብሔር እርሱን ማወቅን በምድር ማጣቱን እንደተመለከተ ይናገራል። በዚሁ ምክንያት ቁ.5 ላይ በቀን መሰናከል እንደሚመጣባቸውና እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው መሆኑን ይናገራል። ሁል ጊዜም አለማወቅን ጥፋት ይከተላል። ሐሰተኛ ተንባዮች ሰዎችን ወደ ጥፋት የሚመሩባቸው በርካታ መንገዶች ያሉ ሲሆን አንዱ ያለድካም፣ በአቋራጭ መክበር፣ በመልጸግ ማስቻልን ተስፋ በመስጠት ነው። በሬው ሳሩን እንዲያይ ገደሉን ግን እንዳይመለከት በማድረግ ማለት ነው።

2. ስንፍናን ያስከትላል።

“ሰው ሁሉ እውቀት አጥቶ ሰንፎአል፥…” (ኤር. 51:17) ይላል። “ሰነፍ በልቡ:- አምላክ የለም ይላል።” (መዝ. 14:1) እንግዲህ የእውቀት እጦት ቀላል ችግር ሳይሆን የክህደት ምንጭ መሆኑ ነው። ቃሉ አለማወቅ ሰነፍ ያደርጋል ሲል የአዲስ ኪዳኑ ሀብታሙ ገበሬ ትዝ ሊለን ይገባል። በትዕቢት ተነፍቶ ነገን በእግዚአብሔር ከመታመን ይልቅ በጎተራው እህል ታምኖ ሊዘንጥ ሲሞክር “አንተ ሰነፍ ነፍስህን ዛሬ ይፈልጓታል” ነበር የተባለው። አለማወቅ ሰነፍ ትዕብተኛ ያደርጋል ማለት ነው። ባለማወቅ ስንፍና የተወጠሩ የዘመናችን የምቾት ወንጌል ሰባኪዎች ትውልዱንም ወደ ማይወጣበት ስንፍና ውስጥ እየከተቱ መሆናቸውን ለማየት ከፈለጋችሁ አፍቃሪዎቻቸውን በፌስ ቡክ ላይ ተመልከቷቸው። ሀሳብን በሀሳብ የሚሞግቱ ሳይሆኑ በልበ ሙሉነት ተሳዳቢዎች ናቸው። በሰለጠኑበት ሙያቸው ያለ ርህራሄ ያዋርዱአችኋል። የስንፍናቸውን ልክ በዝርጠጣቸው ታያላችሁ። ይኼ ስንፍና ከቃሉ ያርቃል፣ ፊቱን ከመፈለግ ይከለክላል፣ ፈቃዱን ከመሻት ይመልሳል፣ ማለት ነው።

3. ስህተትን ያስከትላል።

“መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ስለዚህ የምትስቱ አይደለምን?” (ማር. 12:24) በክርስቶስ አስተምህሮ መሠረት ስህተት መሠረቱን የሚጥለው በዕውቀት እጦት ላይ ነው። አብዛኛዎቹን የስህተት አስተማሪዎች ዲያብሎስ ሊያስታቸው የቻለው አለማወቃቸውን ተጠቅሞ ነው። ምክንያታዊነትንና ክርስቲያናዊ እምነትን ለያይተው የሚመለከቱ አዕምሮ ለክርስትና እምነት ጠላት እንደሆነ የሚያስቡ ድንዙዝ መምህራን ክርስቲያኖችን አደንዝዘው እንደሚያስከትሏቸው የዘመናችን ነቢያት ምስክሮች ናቸው። በሓዋሳ ከተማ አንዱ አደንዛዥ ከሁለት ዓመት በፊት “የተቀባ መጽሐፍ” ብሎ መጽሐፍ ቅዱስን ለጫረታ አውጥቶ መቶ ሺህ ብር አደባባይ ላይ ሲሸጥ ነበር። “ለምን? ቃሉ ደሞ በማን እጅ ይቀባል?” ብሎ ሊጠይቀው የደፈረ አልነበረም። “ጌታ በእሱ አማካይነት ለቤቴ ያመጣውን በረከት አላስመልጥም” ብለው የተቀባ መጽሐፍ ቅዱስ ከአደንዛዡ ተንባይ ይገዙ ነበር። አለማወቅ ያስስታል። የወንጌል ዋነኛ ዓላማው ሰዎችን በምድራዊ ምቾት ማንደላቀቅ እንደሆነ አድርገው የሚያስቡ የፈውስና ባለጠግነት ሰባኪዎች ጸረ-ዕውቀት መሆናቸውን ከልምምዳቸው መረዳት ትችላላችሁ። “አገላብጠን ሳይሆን ተገላብጠን ያመጣነውን መልዕክት ነው የምናቀርበው” ሲሉ አድምጫቸዋለሁ። ማገላበጥ አይችሉማ ከየት ያምጡት።

4. ጌታን በፍጹም አዕምሮ እንዳንወድደው ያደርጋል።

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ባለፈው "የእግዚአብሔር ዙፋን ክፍል 1" ባልኩት ልጥፍ ላይ ከመዝሙር 89፥ 14 ተመልክተን ነበር። በዚያ ክፍል የእግዚአብሔር መንግሥት መሠረታውያን (basics of God's Kingdom) እና መንግሥቱ መሠረት (the foundation of God's Kingdom) ጽድቅና ፍትሕ እንደሆኑ አይተን ነበር።

በዚህኛው ልጥፍ ደግሞ የመንግስቱ ፊት (the face of the Kingdom) ላይ ከዚያው መዝሙር ለመመልከት ጊዜ እንውሰድ እስኪ።

በመዝ 84፥14 ላይ ዙፋኑ ላይ የተቀመጠው የእግዚአብሔር ዙፋን መሰረት ሁለት ነገሮች እንደሆኑ ሁሉ፥ ከፊቱ የሚሄዱ ሁለት ነገሮች አሉ፦ እውነት እና ታማኝነት (ጽኑ ፍቅር)። እውነት ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጡ emet (ኤሜት) ሲሆን፣ ታማኝነት ተብሎ የተተረጎመው ደግሞ chesed (ኼሴድ) ነው። እነዚህ ሁለቱ ከፊቱ የሚሄዱቱን አንድም እንደመልዕክተኛ፣ ሌላም እንደዝና ልናያቸው እንችላለን፤ ፈረንጆቹ your reputation precedes you እንደሚሉት ማለት ነው።

ኤሜት እውነትን መነጋገርን የሚያሳይ ቃል ነው። በግንኙነቶች ውስጥ በአንደበት ቃል ማታለል ሳይሆን የመተማመንና የጠንካራ ግንኙነት መሰረት የሆነው እውነትን መነጋገርን ይወክላል። በሌላ በኩል ደግሞ emet፣ በተለይ በነብያት ጽሁፎች ውስጥ እንደምናገኘው፣ እውነትንና ውሸትን ለመለየት የሚያስችል የአተያይ ጥራት (discernment) ጭምር ይወክላል። ለምሳሌ እውነተኛ ዳኝነት እውነትን ከውሸት መለየትንና ከእውነት ጋር መቆምን ይመለከታል።

ኼሴድ ደግሞ ታማኝ፣ ጽኑ፣ የማይዘላውልን ፍቅር ይወክላል። ይኽ አይነቱ
ፍቅር በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ሲሆን በሁለት እኩሎች መካከል ያለ ከመሆን ይልቅ በኃይለኛና በደካማ መካከል
የሚሆን ነው፤ ኃያሉ ደካማውን የሚወድድበት ፍቅር! በሰውና በሰው መካከል ደግሞ ሲሆን አንድ ሰው አንዳች ነገር በሚያስፈልገው ሁኔታ ውስጥ ለዚያ ሰው የሚያስፈልገውን በማድረግ ተግባራዊ ምላሽ መስጠት ማለት ነው። ይኽ ለተቸገረ ሰው መስጠት፣ በጥቃት ሥር እንዳይወድቅ ባልንጀራን መጠበቅና የተጠቃውን የመታደግ ኃላፊነትን የሚያጠቃልል ነው። እግዚአብሔር ለእስራኤላዊያን
የሰጣቸው ታላቁ ትዕዛዝ እግዚአብሔርን ከመውደድ ቀጥሎ ባልንጀራን እንደራስ የመውደድ ትዕዛዝ ነው። ባልንጀራን
መውደድ ማለት እነዚህን ያጠቃላል፦ መስጠት፣ መጠበቅና መታደግ።

እነዚህ ሁለቱ፣ ማለትም እውነትና ታማኝ ፍቅር፣ የመንግስቱ ፊት፣ የመንግስቱ መታወቂያ፣ የመንግስቱ ስም ናቸው።

እንዴት ነን? ፊታችን የእግዚአብሔርን ዙፋን ፊት ይመስላል?

ሳራ አብደላ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

3፥29)። ወገኖቼ፣ ለእኛም ክርስቶስን ማግነን፤ ማድመቅ፤ ማሳየት፤ ይሁንል! አሜን!

🛐 እርሱ ከሁሉ እንደሚበለጥ እመሰክራለሁ - ከአብርሃም፣ ከሙሴ፣ ከአሮን፣ ከነቢያት፣ ከእኔም ከመጥምቁ ዮሐንስ ይበልጣል! እኛ ሁላችን ጫማውን እንኳን ለመሸከም የማይገባን አገልጋዩቹ ነን። እርሱ ጌታችን፣ አብን የገለጠ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ልጅ ነው። አብ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” በማለት የመሰከረለት እርሱ ክርስቶስ ከሁሉ ይልቃል! ስለዚህ፣ "እርሱ ሊልቅ፣ እኔ ግን ላንስ ይገባል . . . ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሆነው የምድር ነው፤ የምድሩንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው. . .” (ዮሐ. 1፥30-31)።

የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት መልእክት ያድሰን፤ እርሱ በሁሉ ነገር በቤተ ክርስቲያን ልቆ ይታይ፤ መልእክታችንም እርሱ ብቻ ይሁንልን!

አሜን!

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

እየቀረባችሁ...
*
ጊዜው ቀዝቃዛው የጥር ማለዳ ነበር። በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የከተማ ውስጥ ባቡር ጠቢያ አካባቢ አንድ ሰው ተቀምጦ ይታያል። ከጥቂት ቈይታ በኋላ ቫዮሊኑን አንሥቶ ሙዚቃውን መጫወት ጀመረ። ለ45 ዲቃዎች ያኽልም ስድስት የሙዚቃ እርከኖችን ተጫውቶ ጨረሰ።
.
ሰዓቱ ጥድፊያ የሚበዛበት የማለዳ ሥራ መግቢያ ሰዓት በመኾኑ በጣቢያው የተሳፈሩና የወረዱ በሺህ የሚቈጠሩ ሰዎች እንደ ነበሩ ተገምቷል። የብዙዎቹም ትኵረት ወደ ሥራቸው ለመግባት መጣደፋቸው ላይ ነበር። በነዚያ 45 ደቂቃዎቹ ውስጥ የኾነው እንዲህ ነበር።
.

ሙዚቀኛው መጫወት ከጀመረ ሦስት ደቂቃዎች በኋላ አንድ በመካከለኛ ዕድሜ ውስጥ የሚገኝ መንገደኛ ሙዚቀኛውን ተመለከተ። ለጥቂት ሰከንዶች ከጥድፊያው ተገትቶ ቆም ብሎ ካየው በኋላ ጕዳዩን ሊተኩስ በፍጥነት ወደ ጕዞው ተመለሰ። ከደቂቃዎች በኋላ ግን ባለ-ቫዮሊኑ የመጀመሪያውን የዶላር ስጦታውን ተቀበለ፤ ኾኖም ገንዘቡን የሰጠችው ሴት ቆም እንኳን ሳትል ነው ሳንቲሙን ወርውራለት የበረረችው። ጥቂት ደቂቃዎች እንዳለፉ ደግሞ አንድ ሌላ መንገደኛ ሙዚቀኛውን ለማዳመጥ ከዐንገቱ ሠገግ ሲል ታየ። ኾኖም ሰዓቱን ቢመለከት ረፍዶበት ነበርና፥ ትቶት ወደ ሥራው ሸመጠጠ።
.

አንድ የሦስት ዓመት ልጅ ብቻ ከኹሉም የተሻለውን ትኵረት ሲሰጠው ታይቷል። ልጁ ቆም በማለት ሙዚቀኛውን ማዳመጥ ጀምሮ ነበር። ዳሩ ግን፥ እጁን ይዛው የነበረችው እናቱ፥ በጥድፊያ ላይ ስለ ነበረች፥ ልጁን እየጐተተች በረረች። ልጁም ደጋግሞ ዐንገቱን በማዞር ወደ ሙዚቀኛው ይመለከት ነበር። በሌሎችም ሕፃናትም ተመሳሳዩ ነገር ተደጋግሞ ተደረገ። የኹሉም ወላጆች ደግሞ ያለልዩነት የልጆቻቸውን እጆች እየጐተቱ ከቦታው ተፈትልከዋል።
.

በአጠቃላይ ሙዚቀኛው ቫዮሊኑን በተጫወተባቸው 45 ደቂቃዎች ውስጥ ስድስት ሰዎች ብቻ ለዐጫጭር ጊዜያት ቆም ብለው አድምጠውታል። 20 የሚኾኑ ሰዎች ደግሞ ገንዘብ ሰጥተውታል። ነገር ግን ከተለመደው የጕዞ ፍጥነታቸው ሳይገቱ ዐልፈውት ኼደዋል።
.
ሙዚቀኛው፥ በጠቅላላው የሰበሰበው 32 ዶላር ብቻ ነበር። ዜማውን ጨርሶ ጸጥታው ሲሰፍንም ሙዚቀኛውን ያስተዋለው አንድም ሰው አልነበረም። አንድም ሰው አንኳ አላጨበጨበለትም። “አባ ከና” (ባለዚህ) ያለውም አልተገኘም።
.

የሚገርመውና (ምናልባትም አሳዛኙ) እውነታ ይኸውላችሁ። ባለ ቫዮሊኑ ዜመኛ ከዓለማችን ዝነኛ ሙዚቀኞች አንዱ የኾነው ጆሹዋ ቤል ሲኾን፥ በአደባባይ ላይ፥ በሕዝቡ መካከልና ሕዝቡን መስሎ በተገኘበት ቀን ግን ማንም ሰው ለይቶ ሊያውቀው አልቻለም።
.

ጆሽዋ ቤል በዚያ ጎዳና ላይ ኾኖ ይጫወት የነበረው በቫዮሊን ከተጻፉ ምርጥና ውስብስብ ሙዚቃዎች መካከል አንዱ የነበረውንና 3.5 ሚሊየን ዶላር የተሸጠውን ሙዚቃውን ነበር። በመንገድ ዳርቻ ኾኖ ከተጫወተበት ኹለት ቀናት በፊት በቦስተን ቲያትር ቤት ውስጥ ይህኑ ሙዚቃውን አቅርቧል። በዚያ ዝግጅት ላይ ታዳሚ ለመኾን የመግቢያ ቲኬቱ በነፍስ ወከፍ 100 ዶላር ያስከፍል ነበር።
.

ጆሹዋ ቤል ራሱን ደብቆ የተጫወተበት እውነተኛ ታሪክ የተከናወነው ዋሽንግቶን ፖስት (Washington Post) ባዘጋጀውና የሰውን ልጆች ትኵረት፥ ጣእምና ቀዳሚ ምርጫዎችን ለማወቅ በተደረገ ማኅበራዊ የምርምር ሙከራ ነበር። “አካብዴዎች” የሰውን ልብ በቀላሉ ሲማርኩት መገኘቱ አሳዛኙ ምጸት እንደ ኾነ ቀርቷል።
.

ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ ተገልጦና ዝቅ ብሎ በመካከላችን በመገኘቱ የዘላለም ምሥጢር ይፋ ተደረገ። “እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም። ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ኾኖ ራሱን ባዶ አደረገ፤ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፤ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ኾነ” (ፊል. 2፥6-8)። ነገር ግን ብዙዎች አላወቁትም ነበር (1ቆሮ. 2፥8)።
.
ለእናንተ እና ለእኔም የቀረበው ጥሪ ይህ ነው፤ "በሰውም ወደ ተጣለ፥ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠና ክቡር ወደ ኾነው ወደ ሕያው ድንጋይ ወደ እርሱ እየቀረባችሁ፥ እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ኾናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትኾኑ መንፈሳዊ ቤት ለመኾን ተሠሩ" (1ጴጥ. 2፥4)።

ጸጋ ይብዛላችሁ።

መጋቢ ሰሎሞን አበበ ገብረ መድኅን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

(ከባለፈው የቀጠለ)

#ንስኃና_ውጊያ

ለሁሉ ነገር “ጦሳችንን” የሚሸከም ጠላት መሳላችን ጥሩ አለመሆኑን በባለፈው ጽሑፌ ለመጠቆም ሞክሬያለሁ። ይልቅኑ በደረሰብን ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ጻዲቅና የማይሳሳት፣ እንዲሁም ከእርሱ እውቅና ውጪ ምንም ነገር እንደሌለ አምነን፣ ምናልባት ራሳችንን መፈተሽና ሁልጊዜም ቢሆን በአንድም በሌላም ከመንገዱ ፈቀቅ እንደምንል አውቀን ከውጊያ ንስኃን እንድናስቅደም ለመምከር ነው።

ጠላት ዲያብሎስን በአምልኮአችንና በኅብረታችን [ካኖኒያ] ከአቅሙ በላይ ስፍራ ሰጥተነዋል። ከእግዚአብሔር ጋር ላለን የኪዳን ኑሮ መቼም ቢሆን እንደ እስራኤል ምሳሌ አናገኝም። በእስራኤል [በቀደመው የኪዳን ሕዝብ] ያሕዌ በአምልኳቸውም ኾነ የዕለት ተዕለት ኑሮአቸው ዋና ነው። ምክንያቱም እስራኤል ለእግዚአብሔር ርስቱ ነው [ዘጸ. 19፥ 5]። የተለያዩ ሕዝቦች ከሚያመልኳቸው ጣኦታት ዘወር ብለው እውነተኛውን አምላክ ቢፈልጉ አድራሻው እስራኤል ነው። በእርግጥ ያሕዌን በእስራኤል ላይ እንዳይታይ የሚገዳደረው ካለ ጣኦታት ወይም “ጠላት” አይደለም፤ የገዛ ሕዝቡ እልከኝነትና አለመታዘዝ ወይም አለማመን ነው። እነዚህ አደናቃፊዎች ደግሞ የሚወገዱት [የሚሰባበሩት] በንስኃ ነበር። እስራኤል የተዘጋ ሰማይ ወይም ጸሎቱ የማደመጥበት ኹኔታ ውስጥ ቢገኝ ሰይጣን አየሩን ተቆጣጥሮት ወይም በያሕዌና በእነርሱ መካከል መጋረጃ ሠርቶ እንዳይመስለን - “ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች፥ እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።” [ኢሳ. 59፥ 2] ይላልና።

ለአዲሱ የእግዚአብሔር ሕዝብም ይኸው ነው። የእግዚአብሔር ርስትነት ለማን ነው? በክርስቶስ ኢየሱስ አምነው በደሙ ለተረጩቱ አይደለምን? ለቤተ ክርስቲያንስ አይደለምን? “እናንተ ግን ... ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ” [1ኛ ጴጥ. 2፥ 9] ይላል መጽሐፍ። እግዚአብሔር በሕዝቡ ደኩኗል። የእግዚአብሔር አብሮነት እስከ ዓለም መጨረሻ አብሮን አለ። ይህን የሚሰውር፣ ይህን የሚጋርድ፣ ይህን የሚያደበዝዝ ... ወዘተ ቢኖር በዲያብሎስ ሊያሳብ አይገባም፤ ይልቅኑ አስቀድሞ ካለማመንና ካለመታዘዝ እንዲሁም ከስንፍና ንስኃ ልንገባ ይገባልና። መቼም ይኼ አይጠፋችሁም።

ግና በንስኃ ቦታ ውጊያ ተበራክቶ ባይ ነው ይህንን የጫርኩት። በውጊያ ድል የነሳነው ሕይወት የለም - በየትኛው አቅማችን? በውጊያ ያስለቀቅነው የእግዚአብሔር በረከት የለም - በየትኛው የሕይወት ጀግንነታችን? ከተዋጋን ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ እንዋጋ። ከተዋጋን ከትዕቢተኛ ልብ እየራቅን ትህትናን የሚወደውና ጸጋን የሚያበዛልንን ጌታን በመቅረብ እንውጋ።

በእርግጥ ማኅበረሰባችን ጦረኛ ነው። ጦረኝነቱ ቤተ ክርስቲያንም ሰተት ብሎ ገብቷል። “በምድር የምትሽከረከር” ብሎ የሚገስጽ አይጠፋም - እንደ ምድር ጦር አባል። “በአየር የምትበር” የሚልማ ሞልቷል - እንደ አየር ኃይል። “በባሕር የምትዞር” የሚልም ሰምቻለሁ በእኔ እድሜ - ያው ይኼ ደሞ ከባሕር ኃይል የመጣ ሳይሆን አይቀርም ብያለሁ። ውጊያ ወዳጆችን እንዳፈራን የሚያሳብቀው “በዙሪያችሁ” የሚለውን ጨምረን ስናነብ ነው - “... ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና።” [1ኛ ጴጥ. 5፥ 8]።

ለማለት የፈለግኩት ንስኃን ውጊያ አይተካም ነው። እርግጥ ነው ንስኃም ውጊያን ይተካል እያልኩ አይደለም፤ የውጊያ ስልታችንን ብንቀይር ኹለቱንም ያለመቀያየጥ ይዘናቸው ልንሄድ እንችላለን የሚለውን ነው።

መልካም ቀን።

ተገኝ ሙሉጌታ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

#ንስኃና_ውጊያ
(Just Reflection)

አንድ ክርስቲያን እነዚህን ሁለት (ንስኃንና ውጊያን) ክርስቲያናዊ ግብሮች ሳያተካካ፣ ሳያቀላቅል እና ሳያጣጥል ይተገብራል ተብሎ ይታመናል። በተለይ ንስኃ የእግዚአብሔር መንግሥት ሕይወት እውን የምትሆንበት ድርጊት ነው ለሁሉም። ለአይሁድም ሆነ ለተቀረው ዓለም የእግዚአብሔር መንግሥት ንስኃንና እምነትን እንደጠየቀ እሙን ነው።

የሆነው ሆኖ በእግዚአብሔር መንግሥት ስንኖርና ስንመላለስ ሳለ ንስኃ ቀጣይነት አለው። ውድቀት አርቆ ያቆመንን ያህል ከእውነተኛው አምላክ ሃሳብ ጋ ለመኖርና ለመቆራኘት ንስኃ ግዳችን ነው፤ ንስኃ የሕይወት ዘዬያችን ነው ማለት ይቻላል። ይህን የሕይውት ዘዬአችንን የሚያዛባ አንዳንድ አመለካከቶች፣ አሁን ደግሞ አልፎ ተርፎ ኑሮዎች እየታየብን ነው።

ንስኃና መጸጸት በሚያስፈልገን ነገር ላይ ከጥፋተኝነት ስሜትና ድባብ ለማምለጥ ነገሩን “በጠላት” ማሳበብ እየታየብን ነው። የጠላትን ክፋትና ሴራ ለራሱ ትተነው ሁሌም “የጦስ ዶሮ” መፈለግ ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም።

እስራኤል ከምርኮ በፊት “የጦስ ዶሮ” አያውቅም፤ በመጽሐፎቻቸውም ሰይጣን እምብዛም ስፍራ የለውም፤ የለም አላልኩም - ስፍራ የለውም ነው ያልኩት። የተፈጥሮ ድርቅ፣ ርሃብ፣ ማኅበረሰባዊ አለመግባባትና አንዱ አንዱን ማብጠልጠል ... የጠላት ሥራ ነው ብሎ የጦስ ዶሮ ከመፈለግ ይልቅ ለንስኃ ሲጠራ ነው የምታገኙት። በእርግጥ ይህ የኪዳን አመለካከት ከምርኮ በኋላ የበለጠ አድጓል።

እስራኤል የአለመታዘዝ ቅጣቱን [70 ዓመት የምርኮ ዘመኑን] ቢጨርስም ያለፈውን በደል እያስታወሰ በክስና በጸጸት እድሜ ዘመኑን እንዲጨርስ የሚያደርግ ሦስተኛ አካል እንዳለ ከነበረበት ከምርኮ ምድር የቀዳ ይመስላል። በእግዚአብሔርና በሰው ግንኙነት ምንም ወይም ማንም በጎም ይሁን መጥፎ ተጽዕኖ የሚያመጣ አካል የለም ማለት አይቻልም። ለምሳሌ እስራኤልን የወከለው ሊቀካህኑ ኢያሱ በእግዚአብሔር ፊት እድፋሙን ልብስ ለብሶ ሲቆም ከሳሽ በቀኙ ነበር። ይህ አዲስ ትዕይንት ነው። እስራኤል ከምርኮ ቢመለስም የቀድሞውን እያሰበ በጸጸትና በምሬት ነበር፤ Bad Memories በእግዚአብሔር ፊት በነጻነት አያስቆሙም። ይህን ቆስቋሽ ደግሞ ‘ከሳሽ’ [ሰይጣን] አለ። ይህንን ገሳጩ እግዚአብሔር ነው፤ እርሱም የጠራን የመረጠን አምላክ ነው።

ለምንድነው ይሄን ሁሉ ያነሣሁት? ሁሉን ነገራችን ላይ ጠላት ገባበት ብዬ ነው። ክርስቲያናዊ በሆነው የስርክ ተግባራችን ላይ ሰበበኞች ኾነን አረፍነው፤ የጦስ ዶሮ ፈላጊዎች ሆንን። በንስሃና በ Regression የምመልሰውን ነገር ሁሉ በሰይጣን አሳባቢዎች ሆንን። ...

ተገኝ ሙሉጌታ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

https://www.bbc.com/amharic/articles/c9r2edpe51yo?at_link_origin=BBC_News_Amharic&at_medium=social&at_link_type=web_link&at_campaign=Social_Flow&at_campaign_type=owned&at_link_id=5B0EFF5C-ADE7-11EE-B752-E9818161DE7E&at_bbc_team=editorial&at_ptr_name=facebook_page&at_format=link&fbclid=IwAR3fzqXm7NHJ7UmR3WiWb-H5zTKkSxsaKGyJdI6YUKQKfwPcn0DaqKjLZdM

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የእግዚአብሔር ታማኝነት ይታይ ዘንድ!

ኢየሱስ ክርስቶስ ዘመኑ በደረሰ ጊዜ ከድንግል በመወለድ ኅጢአት ወዳቆረቆሰው ዐለም መጣ። ኅጢአት ያቆረቆሰውን ፍጥረት በመኸከሉ ተገኝቶ ጎበኘው። ከዐለሙ ሕማም የተለየ አልነበረምና ሕመሙን በግርግም በመወለድ ታመመለት። በመስቀልም በመዋል ተቆርሶ እንደ ምግብ ታደለለት። የብርሃናት ፈጣሪ የሆነው አምላክ የባሪያን መልክ ያዘ። ራሱን ባዶ አደረገ። ኅጢአት ባሸነፈው ፍጥረቱ መኸል ተገኝቶ ብሥራት ሆነለት። መስቀል ድረስ ይዘልቅ ዘንድም ግርግም ተገኘለት። እግዚአብሔር ዐለሙን በጣም ስለወደደው አንድያ ልጁን ሰጠለት። ይሄ የምስራች የኅጢአት ስብራት ላደቀቀን ብሥራታችን ነው።

.
እግዚአብሔር በግዞት ለምትጋዘው እስራኤል የትድግናን ተስፋ ችሯል። በኅጢአቷ ምክንያት የእግዚአብሔርን ቁጣ ያስተናገደችው እስራኤል ከግዞት እንደምትሰበሰብ (12 ነገዶች እንደሚመለሱ)፣ ሁለተኛውን መቅደስ እንደምትሰራ (ከመጀመሪያው በክብር የሚልቅ)፣ አሕዛብ ፍርድ ተቀበለው እንደሚቀላቀሉ (ingathering of gentiles) እና ንግሥና (የእግዚአብሔር እንደ ራሴነት) እንደሚመለስ ተስፋ ተገብቶላት ነበር።

.

"ለአባቶች የተሰጠውን የተስፋ ቃል ያጸና ዘንድ ለእግዚአብሔር እውነት ሲል ክርስቶስ የአይሁድ አገልጋይ እንደሆነ እነግራችኋለሁና፤" (ሮሜ 15:8)

እግዚአብሔር በነብያቱ በኩል ትድግናና መቤዠትን ለእስራኤል አብስሯል (ኢሳ 40-42)። ተስፋን ሰጥቷል። ሕዝቡን የማዳን ፍላጎት እንዳለው፣ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ለማዳን ደግሞ ችሎታውና አቅም እንዳለው እንዲሁም ፍላጎትና አቅም ብቻ ሳይሆንጊዜው ሲደርስ የሰጠውን ተስፋ ለመፈጸም በታማኝነት እንደሚያድን አብስሯል። ይሄ የማዳን ተስፋ ፍጥረቱን ሁሉ እንደሚጠቀልል አስቀድሞ ተናግሯል። የማዳን ተስፋው ለአይሁድ ብቻ ሳይሆን ለአሕዛም ጭምር ነው። አሕዛብ ወደ እርሱ ዘወር እንዲሉ የሚያደርጋቸውን ተስፋ ሲናገር (ኢሳ 42፥1-9) ይህንን ይላል፦

“እነሆ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፥ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል [...] አሕዛብም በስሙ ይታመናሉ [...] ለሕዝብ ቃል ኪዳን ለአሕዛብም ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ።”

የጌታ ባሪያ “አሕዛብንና እስራኤልን” በአንድ ላይ በማድረግ የእግዚአብሔርን ትድግና የሚያወጣ አገልጋይ ነው። በምርጡ በኩል ለሁሉም የሚበቃን የትድግና ተስፋ ሰጠ። ታዳጊው ባሪያ እና አገልጋይ መባሉን ልብ ይሏል!

ይሄ ሁሉ የተገባ ተስፋ ፍጻሜን ያገኘው በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ነው። እግዚአብሔር ለእስራኤልም ሆነ ለአሕዛብ የገባው ትድግና ፍጻሜውን በኢየሱስ አገኘ።

ለምን ተወለደ? ስንል ዐለሙን ሁሉ፣ አሕዛብንና አይሁድን ሁሉ እንደ ተስፋ ቃሉ ይታደግ ዘንድ ተወለደ። ስለዚህም እግዚአብሔር የሰጠው ተስፍ ይጸና ዘንድ ወይም እግዚአብሔር ታማኝ መሆኑ ያስመሰክር ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ ተወለደ። መወለዱ የእግዚአበሔር ታማኝነት መገለጫ ነው። ክርስቶስ የእግዚአብሔር እውነት በመሆን የእግዚአብሔር ታማኝነት ማሳያ ይሆን ዘንድ ተወለደ። የተሰጡ የተስፋ ቃሎችን በሙሉ ኢየሱስ በመወለዱ ፈጽሟቸዋል። ርቀን ለነበርነው ለእኛ ለአሕዛብ ታላቅ የምሥራች ነው መወለዱ!

መልካም የልደት መታሰቢያ በዓል!

አማኑኤል አሰግድ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ውልደቱ ስለ ጉብኝት ነው!

እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ኪዳን ገብቷል። እርሱ አምላክ ሊሆናቸው እነርሱ ደግሞ በምድር የእርሱ አገዛዝ ማሳያ ሕዝቡ ይሆኑት ዘንድ የጋራ ኪዳንን ገብቷል። ኪዳኑን ማክበር የሚያስገኘው በረከት የመኖሩን ያህል ኪዳኑን አለመጠበቅ ደግሞ ቅጣት እንዳለው በግልጽ ሰፍሮ ነበር። እስራኤል ከእግዚአብሔር ጋር የገባችውን ኪዳን ማክበር ተሳናት። ኪዳኑን ባለማክበርም ጸናች። ብቸኛ አምላክ የሆነው ያሕዌን በሌሎች አማልክት ተካች። እግዚአብሔራዊ አስተዳደርንም አፈረሰች። የእግዚአብሔር እንደራሴ መንግስትነቷ ብቸኛውና እውነተኛው አምላክ ለዙሪያዋ ማስተዋወቅ መሆኑን በመዘንጋት ጽድቅና ፍትሕን አፋለሰች። እስራኤል በተደጋጋሚ ኪዳኑን ባለማክበሯ በኪዳኑ መሰረት ቅጣቱን አስተላለፈ። በእስራኤል ኅጢአት እግዚአብሔር ከእስራኤል ራቀ። እግዚአብሔር አብሮ የመሆኑ ምልክት መቅደሱ ፈረሰ። በሕዝቡ መኸከል ደኩኖ የነበረው አምላክ ሕዝቡ ኪዳኑን ባለማክበሩ ምክንያት ተለየ፣ ኢካቦድ ሆነ። በኅጢአታቸው ምክንያትም ተዋቸው። መተው ብቻ ሳይሆን እንደ ኪዳኑ ካልታዘዙ ሊደርስባቸው የተገባውን ቅጣት ቀጣቸው። ቅጣቱ በመኸከላቸው ካለመሆን ጀምሮ በጨካኝ ነገስታት እጅ አሳልፎ እስከመሰጠት ሆነ።

በኅጢአታቸው ምክንያት እግዚአብሔር ቀጣቸው። እንደ ተስፋው ቃል 70 ዐመት ሲሞላ ወደ ፍልስጤም ምድር ተመልሰው መቅደስ ቢያቆሙም የቀደመው ክብርና አብሮነት ደብዛው ጠፍቶ ነበር። ነገሮች ከግዞት በፊት እንደነበሩት አልቀጠሉም። ምንም እንኳን እግዚአብሔር በነብያቱ በኩል ቃሉን ያመጣ የነበረ ቢሆንም እንደ ቀደመው ግን በሕዝቡ መኸከል አልደኮነም። ወደ ምድራቸው ቢመለሱም፣ መቅደሱን ቢያቆሙም የእግዚአብሔር ምኅረትን አላገኙም። በኅጢአት የተለያቸው እግዚአብሔር ይቅር ቢላቸው ኖሮ በመገኘቱ ይሞላቸው እንደነበር በማስታወስ መቆሚያ ከሌለው ግዞት (ongoing exile) በምኅረቱ ይጎበኛቸው ዘንድ ይጠብቁ ነበር።

የአዲስ ኪዳን ጸሓፍት የጌታን መወለድ እግዚአብሔር በመኸከላችን ከመደኮኑና ከእኛ ጋር ከመሆኑ አንጻር የሚያነሱት ከዚህ ጥበቃ ጋር በማገናኘት ነው። ወንጌላት «በመካከላችንም አደረ፤ እኛም ጸጋንና እውነትን ተሞልቶ ከአባቱ ዘንድ የመጣውን የአንድያ ልጅን ክብር አየን።» (ዮሐ. 1:14) የሚል ትራኬን የሚያቀርቡት።

ኢየሱስ የእውነተኛ እስራኤል ጉብኝት ምንጭ እንደሆነ ወንጌላት ሲያበስሩ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ በማለት ነው። በእስራኤል አመጽና ኅጢአት ምክንያት በኪዳኑ ሕዝብ መኸል መሆኑን የተወው አምላክ በአንድያ ልጁ በመሲሑ ኢየሱስ የእውነተኛ እስራኤል ተስፋ ትፍጽምት በመሆን በመኸከላችን ደኮነ። በመኸከላችን በመሆን ተዳሰሰ፣ ተጨበጠ፣ ተነካ፣ ታቀፈ! ኢየሱስ ሲወለድ የእግዚአብሔር ምሕረት ወረደ። እግዚአብሔር ዳግም ፍጥረቱን በመሲሑ ጎበኘ። "እግዚአብሔር ከእኛ ጋር" ተባለ።

መሲሑ በመወለዱ እግዚአብሔር ዳግም ከእኛ ጋር ሆነ! በተሽቆጠቆጠ ግርማ ሳይሆን ክብር አልባ በሆነ የከብቶች ግርግም አብሮነቱ ተበሠረ! እንደ ፍቅሩ ባለጠግነት አምለክ በግርግም ዳግም ከፍጥረቱ ጋር ይሆን ዘንድ ድንኳኑን ዘረጋ። እንደተስፋ ቃሉ "እግዚአብሔር ከእኛ ጋር" በልጁ ሆነ።

አሜን!
.
“እነሆ፤ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” ትርጕሙም፣ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” ማለት ነው። (ማቴ. 1:23)

መልካም ዋዜማ!

አማኑኤል አሰግድ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የእኔ ሳይኾን ያንተ ፈቃድ ይኹን።
.
የእግዚአብሔር ፈቃድ ስንል፥ እግዚአብሔር ለራሱ ስም መከበር ያለው መለኮታዊ ዓላማ፥ ሐሳብ፥ ምክር፥ ድንጋጌና መሻት ነው። ከልካይ የሌለበት አምላካዊ መብቱ፥ በልዕልናው የሚወጥነው ዕቅዱና ሥልጣናዊ ውዴታውን ነው የእርሱ ፈቃድ የምንለው።
.
የአምላካችን ፈቃድ ቅዱስ ነው፤ ዓላማው በጎ ነው። በሥነ ፍጥረት፥ በመግቦቱም ኾነ በአድኅኖት ውስጥ የፈቃዱ ግብ የእግዚአብሔር ክብር ነው። ለክብሩ ምስጋና በሚኾነው ማንኛውም ሐሳብና ክንውን ውስጥ እርሱ እንዲፈጸም የሚፈልገውን የእግዚአብሔር ፈቃድ እንለዋለን።
.

ስለዚህ እግዚአብሔር በምናየውም ኾነ በማናየው ዓለም ውስጥ የሚያደርገው የወደደውን እንጂ የተገደደበትን አይደለም። “በሰማይና በምድር በባሕርና በጥልቆች ኹሉ፥ እግዚአብሔር የወደደውን ኹሉ” (መዝ. 135፥6) ከማድረግ አይከለከልም። ውዴታው ይኾን ዘንድ፥ በኀይሉ ብዛትና በችሎቱ ብርታት አንዳች አይታጣውም።
.

ከዚህ እውነት የተነሣ፥ ፈቃዱን ለማድረግ የእርሱ መሣሪያ የሚኾን ፍጥረት እንጂ አማካሪ ወይም ከልካይ የለውም። “በምድርም የሚኖሩ ኹሉ እንደ ምናምን ይቈጠራሉ፤ በሰማይም ሠራዊት በምድርም ላይ በሚኖሩ መካከል እንደ ፈቃዱ ያደርጋል፤ እጁንም የሚከለክላት ወይም፦ ምን ታደርጋለህ? የሚለው የለም” (ዳን. 4፥35)፤ እንዴትስ ሊኖር ይችላል? ኹሉን የሚሠራው በፈቃዱ ምክር ነውና (ኤፌ. 1፥11)።
.
እንግዲያውስ፥ መባረክ ማለት የእርሱን ፈቃድ ለማድረግ መታዘዝ ለሐሳቡም መታመን ነው። ፈቃዱን አለማድረግ ደግሞ ርግማን ነው። ለዚህ ነው፥ ፈቃዱን እንዲያደርግ በጸሎታችን እርሱን የምንማጠነው። “ፈቃድህ በሰማይ እንደ ኾነች እንዲሁም በምድር ትኹን" (ማቴ. 6፥10)።
.
አሜን።

መጋቢ ሰሎሞን አበበ ገብረ መድኅን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የከሸፈው "ንሰሃ"

መቼም "ንሰሃ መግባት" የሚባለውን ሃሳብ የሚጠላ ክርስቲያን ሊሆን አይችልም! ክርስቲያንነት የሚጀምረው ሃጥያተኝነትን ተረድቶ በቅዱሱ አምላክ ፊት በንሰሃ ራስን ከማዋረድ ነውና። ነገር ግን መጋቢት 8 ቀን "የአደባባይ ንሰሃ ምልጃ እና ምስጋና ይደረጋል" በሚል በካውንስሉ የቀረበው "የንሰሃ" ጥሪ ብዙ ተቃውሞ አስተናግዷል። ምንም እንኳን የበዛ ተቃውሞ ከየአቅጣጫው ቢሰማም "የንሰሃ" የተባለው መርሃ ግብር ተከናውኗል። ነገር ግን ይህ የንሰሃ መርሃ ግብር "የከሸፈ ንሰሃ" ነው። ለምን?

1. ባለቤት አልባ መሆኑ

እንደተነገረው ከሆነ መርሃ ግብሩ "የንሰሃ" ነው። ንሰሃ ከሚገባባቸው ጉዳዮች መካከል ደግሞ አንዱ "ወንጌላውያኑ ያሉበት አሁናዊ ችግር" ነው። የችግሩ ባለቤቶች ደግሞ በዋናነት "ሃሳዊ መምህራኑና ነብያቱ" ናቸው። የሚገርመው ግን ከእነርሱ መካከል (ከጃፒ ዘላለምና ፒተር ማርዲንግ በቀር) ብዙዎቹ አልተገኙም። ለምን አልተገኙም? ከካውንሰሉ ተባረው ነው? ወይስ ቤታቸው ተደብቀው ነው? "እናንተ ከተገኛችሁ ስማችን ይጠፋልና ተደበቁ" ተብለው ለስትራተጂ ይሆን? "ንሰሃ" ገቢው (ባለቤቱ) በሌለበት የሚደረገው "ንሰሃ" ፋይዳው የጎላ አይደለም።

እርግጥ ነው ህዝቡ በበኩሉ ሃሳውያንን በጭፍን ለመከተሉ ንሰሃ መግባት ቢያስፈልገውም በዋነኛነት ግን ህዝቡ "ተበዳይ" እንጂ "በዳይ" አይደለም (ቢያንስ በስህተት ትምህርት እና ልምምድ እንዲሁም በዘረፋ ጉዳይ ተበዳይ ነው)። ታዲያ ብዙሃኑ ሃሳውያን ለበደላቸው ህዝቡ "ንሰሃ" እንዲገባላቸው ነው የቀሩት? ወይስ ቄስ ደረጄ ንሰሃ እንዲገቡላቸው ነው? ቄሱ የሃጥያቱ ባለቤት ስላልሆኑ የንሰሃው ባለቤት መሆን አይችሉም። ስለዚህ የንሰሃ የተባለው መርሃ ግብር ባለቤት አልባ ስለ ነበር ከጅምሩ "የከሸፈ ንሰሃ" ነበር ማለት ነው።

2. ፍሬ አልባ መሆኑ

መቼም ንሰሃ መመለስ ነው። አቅጣጫ መቀየርም ነው።ይህ የንሰሃ ትምህርት ሀሁ ነው። ነገር ጥያቄው ከሃሳውያኑ መካከል ማነው "ተሳስቼ ነበር ንስሃ መግባት እፈልጋለሁ" ብሎ የመጣው ወይም በተለያየ መንገድ መግለጫ የሰጠ የለም። ጃፒ እንኳን በቅርቡ ሲጠየቅ "ተሳስቼ አላውቅም" ነበር ያለው። እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ከሃሳውያኑ መካከል ተሳስቻለሁ ያለ አልተገኘም። የካውንስሉም መሪዎች በራሳቸው ተነሳሽነት "የንሰሃ መርሃ ግብር"" አዘጋጁ እንጂ "ከሃሳውያኑ መካከል እነ እገሌ ንሰሃ ለመግባት መወሰናቸውን ነግረውናል" አላሉም። ቆይ "ተሳስቼ ነበር" የሚል በሌለበት ንሰሃ ይገባል እንዴ? "ተሳስቻለሁ" ብሎ ያልተናገረስ ነገ ላለመድገሙ ዋስተና አለ እንዴ? ስለዚህ ተሳስቻለሁ በድያለሁ ብለው ባልተናገሩ ሃሳውያን ምትክ በደፈናው "በድለናል አጥፍተናል" ብለን ብንፀልይ ፍሬ ልናገኝ አንችልም።

መቼም ቁስ ደረጄ ዘይት አልሸጡም፣ የሃሰት ትንቢትም አልተናገሩ። ምን እያልኩ ነው? ለመመለሳቸው ምንም ፍንጭ ላላሳዩ ሃሳውያን በወኪል የሚደረግ ንሰሃ ከጅምሩ "የከሸፈ ንሰሃ" ነው እያልሁ ነው። (ሃሳውያኑ እንደሆነ ማሳታቸውን ቀጥለዋል! ይቀጥላሉም!)።

3. የጋሽ በቄ መገኘት

መዝጊያው ላይ "አባቶች ወደ መድረክ መጥተው ይባርኩናል" ሲባል ወደ መድረክ ከመጡት መካከል ጋሽ በቄ አንዱ ነበሩ። እኒህ ሰው በአንድ ጊዜ የሙሉ ወንጌል ቤተክርሰቲያንም የሃሳውያኑም አባት መሆናቸው ያመሳቀለው ነገር ቀላል እንዳልሆነም ይታወቃል። ከባዱ ነገር ለሃሳውያኑ መብዛት እና በዚህ ደረጃ መፋነን ከሌሎቹ አባቶች በከፋ ሁኔታ ሲለፉ የከረሙት ጋሽ በቄ "ቡራኬ ሰጪ" ሆነው መከሰታቸው በራሱ ንሰሃው ከጅምሩ የከሸፈ መሆኑን አመላካች ነው።

ዋስትና የሚሰጥ አለ?

እሺ ንሰሃ ተገባ እንበልና እንቀበል ቢባል እንኳን ከዚህ በኋላ ዘይት፣ ጨርቅ፣ ውሃ የሚሸጥ፣ በገስት ሃውስ ስም የሚበዘብዝ፣ በሃሰት ትምህርት እና ትንቢት የሚያወናብድ አይኖርም ማለት ነው? (ቢያንስ የካውንስሉ አባል ከሆኑት መካከል)፤ በእኩይ ተግባሩ በማያምኑት ዘንድ "ወንጌላውያኑን" መሳለቂያ የሚያደርግ የጌታን ስም የሚያሰድብ አይኖርም ማለት ነው? ለዚህ ዋስትና የሚስጥ ከሌለ መጋቢት 8 በሃሳዊያኑ ጉዳይ የቀረበው የንሰሃ ፀሎት ከጅምሩ "የከሸፈ ንሰሃ" ነበር ማለት ነው።

ቴዎድሮስ ተጫን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ከፊታችን ሐሙስ እስከ አርብ ድረስ በአባ ሰላማ ወይም በአባ ፍሪሚናጦስ ስም የተሰየመው አደባባያዊ ትምህርት ይከናወናል። በዚህ አመት ታዋቂው የስልታዊ ነገረ መለኮት ምሁሩ ቬሊ-ማቲ ካርኬይነን ይመጣል። የምትችሉ እንድትታደሙ ትጋበዛላችሁ።

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ንሰሃ የገባው ማነው?

እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2012 ዓ.ም "ለወንጌላውያን ህጋዊ ማዕቀፍ ይሆናል" በሚል ሰበብ በጠቅላይ ሚንስትሩ አነሳሽነት "የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል" በሚል ስያሜ በአዋጅ ቁጥር 1208/2012 "ካውንስል" መቋቋሙ ይታወቃል። ካውንስሉም ገና ከምስረታው "በግና ተኩላውን በአንድ ጎረኖ አሳድሯል" የሚል ትችት በበርካቶች ቀርቦበታል። የካውንስሉን የምስረታ አካሔድ ኢ-መፅሐፍ ቅዱሳዊ መሆኑን ገልጠው እና አጥብቀው ከተቹት መካከል አንዱ "የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት" ነበር።

ከሶስት ዓመታት በፊት

የህብረቱ መሪ የሆኑት ፓስተር ፃድቁ አብዶም ሆኑ "ህብረቱ" ወደ "ካውንስሉ" ለመግባት የማይፈልጉበትን ምክንያት ሲያብራሩም ካውንስሉ ካቀፋቸው መካከል "ክርስቶስንና ማንነቱን፣ መስቀልና የማዳን ስራውን፣ የእግዚአብሔርን ቃልና የእግዚአብሔርን ቃል ስልጣን" የማይቀበሉ ሃሳውያን የሞሉበት መሆኑን እንዲሁም "የሰውን ማንነት" በተመለከተ "የኢ ደብሊው ኬንየንን አቋም ከሚያራምዱ የፌዝ ሙቭመንት (የፕሮስፔሪቲ ወንጌል) ሰባኪዎች" መኖራቸውን ጠቅሰው እንዲህ ካሉት ጋራ "በአስተምህሮ አንድ አይደለንም!" ብለው ነበር።

እንዲያውም ንግግራቸውን ጠንከር አድርገው "በአስተምህሮ ሳንስማማ ምን ዓይነት የወንጌል ስርጭት ነው የምናደርገው?" በማለት ጉዳዩ መሠረታዊ እንደሆነ አፅንዖት ሰጥተዋል። በተለያየ ሚዲያ እየቀረቡም "ኢየሱስ ሰይጥኗል ከሚሉ ጋራ አብሬ ማምለክ አልችልም" እያሉም በካውንስሉ የመታቀፍን ጉዳይ አደገኛነት በግልፅ ተናግረዋል።

በዚያን ወቅትም ብዙዎቻችን በነበራቸው አቋም ተደስተን ደገፍናቸውም ነበር። ካውንስሉም "ከህጋዊ ማዕቀፍነቱ" አልፎ ወደ "መንፈሳዊ ማዕቀፍነት" እንዳይለወጥ በምንችለው ሁሉ ጥረት አያደረግን፤ የመረጃ ክፍተት እንዳይኖር መጋለጥ የሚገባውን ለማጋለጥ ተጋን።

ከሶስት ዓመት በኋላ

ነገር ግን እኒሁ ሰው (ፓስተር ጻድቁ) እና የሚመሩት "ህብረት" በየሚዲያው ሲናገሩ እና መግለጫ ሲያወጡበት የነበረውን ያንን ሁሉ ተቃውሞ ወደ ጎን ትተው (ግልፅ ባልሆነ መንገድ) ወደ ካውንስሉ መግባታቸውን በድንገት ይፋ አደረጉ። ይባስ ብለው ደግሞ መጋቢት 8 ቀን በመስቀል አደባባይ በካውንስሉ የተዘጋጀውን "መንፈሳዊ" መርሃ ግብር እባካችሁ ታደሙልን እያሉ "ኢየሱስ ሰይጥኗል" ብሎ ከሚያስተምረው ዘላለም ጋር በአንድ ጠረጴዛ ተቀምጠው ጥሪ እያቀረቡ ነው።

ታዲያ ጥያቄው ምንድነው?

መሠረታዊው ጥያቄ "ንሰሃ የገባው ማነው?" የሚለው ነው።
መቼም "ንሰሃ" የሚለው ቃል ትርጓሜ ሃጥያትን በእግዚአብሔር ፊት ቀርቦ በመናገር ምህረት መለመን የሚለውን ቢያካትትም መሠረታዊ ትርጓሜው ግን መመለስ፣ የወድሞ መንገድን መተው፣ አቅጣጫ መቀየር፣ እንደ ቃሉ የሆነውን አዲስ መንገድ መጀመር ማለት (በአጭሩ) ከሆነ ታዲያ ማነው ንሰሃ የገባው?

"ኢየሱስ ሰይጥኗል ከሚሉ ጋር ህብረት ማድረግ አልችልም" ያሉት ሰው እና በሃሳውያን ላይ የውግዘት መግለጫ ያወጣው ህብረት ካውንስሉ ውስጥ ከተጠቀጠቁት ሃሳውያን ጋር የሚደረገውን "አምልኮና ፀሎት ኑና ተካፈሉ" ብሎ አባላቶቹን የጠራው ንሰሃ ገብቶ ነው? ወይስ ንሰሃ አስገብቶ? ማነው የተለወጠው ፓስተር ፃድቁ ወይስ ዘላለም ጌታቸው? ህብረቱ ወይስ ሃሳውያኑ? ማነው ንሰሃ የገባው ማነው አቅጣጫ የቀየረው? ማነው የቀደመውን መንገድ የተወው?

ማነው ንሰሃ የገባው?
የአቋም ለውጡስ የማነው?

ቴዎድሮስ ተጫን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ተዘጋጅቶ የቀረበው የዮናታን ወንጌል ጥሩ ማንቂያ ነበር። አንሰማም ጆሮ ዳባ ልበስ አልን እንጂ! የባእድ ዘጋቢ ፊልም አዘጋጆች ዮናታንን ዘጋቢ ፊልማቸው ውስጥ ምስሉን ስላስገቡ እጅግ የተቆጡ ነበሩ። ሌሎቹ ኹሉ ስሁታን መኾናቸውን አምነው ሲያበቁ ለዮናታን የማርያም መንገድ ይፈልጉ ነበር። የካውንስሉ ግራጫ ዞን በሚለው ስራቸው ላይም አማኑኤል አሰግድ፣ ፍጹማን ግርማ፣ ሳሚ ቱራና አሳየኸኝ ለገስ የካውንስሉን ጤናማ ያልኾነ ቅይጣዊነት ሊያሳዩን ሞክረው ነበር። ሰሚ መች አገኙ?! መጋቢ ቴዎድሮስ ተጫንም ሳይታክት የዚህን ሰው አደገኛ አካሄድ ነገሮን ነበር። ዘላለም መንግስቱም የዮናታን መንገድ ከሌሎች እጅግ የተጠና በመኾኑ ከኹሉ የከፋ እንደኾነ ሊጠቁመን ደክሞ ነበር። ከኹሉ በላይ ግን የዮናታን የቅርብ ሰው የነበረው አቡና (አቤል ኤሬቻ) ተሳስቼ ነበር ሲለንም አልሰማነውም ነበር። አሁንም ድረስ ለዚህ ሰው ትምህርት መውጫ ቀዳዳ ፍለጋ ሚደክሙ ሰዎችን እያየን ነው። ጃፒ ጋር ሄዶ ጎራውን በመለየቱ ደስተኛ ነኝ። በግልጽ ሰው መንፈስ ነው ሲል ሰምተነዋል። ቢያንስ አሁንም ድረስ ውዥንብር ውስጥ ያሉ ሰዎች ከየት ወገን እንደኾነ ይለያሉ ብዬ አስባለሁ። እነዚህ ኹሉ ሊያነቁን የሞከሩ ድምጾች ዛሬ ላይ ኑ እንዋቀስ ሚሉን ይመስለኛል? አሁንስ እንሰማቸው ይሆን?

ኢብሳ ቡርቃ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

(ማቴ. 22:37) ጌታ አምላክህን በፍጹም ሀሳብህ ውደድ የሚለው ቃል በፍጹም አዕምሮህ የሚል ትርጉም አለው። “with all your mind” ይላል። አዕሮአቸውን የትም ጥለው ወደ ቤተ ክርስቲያን የመጡ እብድ አምላኪዎች ለጌታ ፍጹም የሆነ ፍቅር የላቸውም። ስሜት የሚያስጨፍራቸው ሰዎች ዛሬ ለጌታ ብለው በጨፈሩበት ሳያፍሩ ነገ ለሰይጣን ይጨፍራሉ። አትጠራጠሩ ያደርጋሉ። ቀድሞም አልገባቸውም። አሜን በል ባክህ!፣ ረገጥ አርገህ አሜን!፣ ወፈር አርገህ አሜን!፣ ጨመቅ አርገህ ጠብ ያለ አሜን!፣ አንድ ሰው አሜን!፣ ዘልለህ አሜን!፣ ጠላት ይስማ አሜን!፣ ጮክ ብለህ አሜን! በሚሉና በሌሎችም መቀስቀሻዎች ምክንያት ቢገባንም ባይገባንም አሜን!፣ ትክክል ቢሆንም ባይሆንም አሜን!፣ ቃሉ ላይ ቢገኝ ባይገኝም አሜን!፣ እያልን ያለሀሳብ እየኖርን ነው። ይቅርታ እየሞትን ነው እንጂ ምኑን ኖርን።

“እንግዲህ እግዚአብሔር ያለማወቅን ወራት አሳልፎ አሁን በየቦታቸው ንስሐ ይገቡ ዘንድ ሰውን ሁሉ ያዛል፤ ቀን ቀጥሮአልና፥ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል።” (ሐዋ. 17:30)

እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። (ኤፌ. 5:15)

“… ዕውቀትም ነፍህን ደስ ታሰኛለችና።” (ምሳ. 2:10)

“ነፍስ ዕውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም” (ምሳ. 19:2)

ወርቅነህ ኮየራ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ይድረስ ለወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት መሪዎች

ቁርጡን ንገሩን!!

ከሰሞኑ ዮናታንና ጃፒ በአንድ መሰለፋቸውን የሚገልፀውና "ልዩ" የያሉትን "ኮንፈረንሳቸውን" የሚያስተዋውቀው "ፖስተር" በዚሁ የፌስ ቡክ መንደር እየተዘዋወረ ይገኛል። በበኩሌ በዚህ ፖስተር ዮናታንን ሊመሰገን ይገባል ብዬ አምናለሁ። ምክንያቱም "ጃፒ ሀሰተኛ ዮናታን አንደኛ" ለሚሉ የማያስተውሉ ደጋፊዎቹ እንዲሁም በዚህ ሰው ላይ የጠራ አቋም መያዝ ለቸገራቸው "የህብረቱ አመራሮች" ማንነቱን ፍንትው አድርጎ አሳይቷልና። እስከዛሬ ድረስም በእርሱ ላይ በተደጋጋሚ የተሰሩ የዕቅበተ እምነት ስራዎች ትክክል መሆናቸውን ራሱ በፊርማው (በፖስተሩ) አረጋግጧልና።

እንደሚታወቀው የወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት ህብረት በ2009 ዓ.ም ሚያዚያ ወር ላይ ባወጣው መግለጫ "የቃል እምነት (የብልፅግና ወንጌል)" ትምህርት መምህራንን አውግዞ ነበር። ህብረቱም በመግለጫው "የቃል እምነት" መምህራን እነማን እንደሆኑ ለመለየት ምዕመናን እንዳይቸገሩ በማሰብ ሃሳዌ መምህራኑ የሚያስተምሯቸውን ትምህርቶች በዝርዝር እየጠቀሰ ነበር ያወገዘው። ጥቂት ለማስታወስ ያህል:- "የአንደበታችን ቃል ልክ እንደ እግዚያብሔር ቃል መፍጠር ይችላል" የሚሉ "ሰው መንፈስ ነው" የሚሉ ወዘተ... በማለት ነበር ህብረቱ የተወገዙትን መምህራን "ትምህርቶች" በመግለጫው በግልፅ ለይቶ ያስቀመጠው።

ምንም እንኳን እንደ ህብረቱ የ'ያኔ መግለጫ መሠረት ዮናታን አክሊሉ "የቃል እምነት ስሁት ትምህርቶች አስተማሪ" ተብሎ መወገዝ የነበረበት ቢሆንም ህብረቱ ግን በውል ባልታወቀ ምክንያት እስከ ዛሬ ድረስ በከፍተኛ ሁኔታ ድጋፉን ሲያሳየው ቆይቷል። እዚህ ላይ ህብረቱ ዮናታን የሚመራውን ተቋም "አጋር አባል" አድርጎ ከመቀበል አንስቶ የህብረቱ ፕሬዘዳንት በአዲስ አበባው "የመልካም ወጣት" መክፈቻ ስነ-ስረዓት ላይ መገኘታቸውን እንዲሁም የተወሰኑ የቦርድ አባላት (የህብረቱ) ደግሞ በሀዋሳ አዲስ ኪዳን ካህናት አዳራሽ በአካል በመገኘት ያሳዩትን አጋርነት በእማኝነት መጥቀስ ይቻላል።

ችግሩ ምንድነው?

በርከት ያለው የወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት አባል "ከመፅሐፍ ቅዱስ" ይልቅ ከአገልጋዮች "የመድረክ ላይ ስብከቶች" እና "ዝማሬዎች" በሚቀዳ ቁንፅል የህይወት መርህ "መንፈሳዊ" ህይወቱን እንደሚመራ ይታወቃል። የብዙሃኑ "መንፈሳዊ" አቋምም ሆነ ስነ-መለኮታዊ እሳቤ ከመፅሐፍ ቅዱስ ይልቅ "እወደዋለሁ!" በሚለው አገልጋይ ላይ የተንጠለጠለ ነው። ችግሩ ይሄ ነው።

ታዲያ እንዲህ ያለ ምዕመን ቁጥሩ በዛ ባለበት ሁኔታ ውስጥ የእረኞች (የመሪዎች) ሃላፊነት ከፍ ያለ ይሆናል። በተለይ አንደ "የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት ህብረት" ያሉትን ተቋማት የሚመሩ ወገኖች ላይ "ሃላፊነቱም" ሆነ በሰውና በእግዚአብሔር ዘንድ የሚጠብቃቸው "ተጠያቂነቱ" በእጅጉ የበዛ ነው።

በእርግጥ ይህንን ስል፤ ሃሳዊው ዮናታን የሚያዘጋጃቸውን መርሃ ግብሮች ላይ በመርሃ ግብር ከፋችነት የሚገኝ ሰው "በፕሬዘዳንትነት" ከሚመራው፣ ወይም የሃሳዊውን ነቢይ ኤርሚያስ ሁሴንን ኮንፈረንስ የሚያስተዋውቅ ሰው "በምከትል ፕሬዘዳንት" ከሚመራው፣ እንዲሁም የጃፒን መፅሐፍ ምረቃ ለማጀብ በጃፒ መድረክ ላይ በደስታ ስሜት የሚገኝ ሰው "በቦርድ አባልነት" ከሚመራው የአብያተክርስቲያናት ህብረት "ለቃለ እግዚአብሔር" የወገነ እርምጃ በሃሳዊያን ላይ ይወሰዳል ብዬ የምጠብቅ ቂል ሆኜ አይደለም።

ቢያንስ ግን ህብረቱ "ለርቱዕ አስተምህሮ ቆሜያለሁ" እስካለ ድረስ ዓላማዬም "ወንጌላዊያን አማኞችን ከስህተት መጠበቅ እና አብያተክርስቲያናት ታላቁ ተልዕኮን እንዲፈፅሙ ማገዝ ነው" እስካለ ድረስ በ2009 ዓ.ም ራሱ ላወጣው መግለጫ ታማኝ በመሆን፤ እንደኛ ዮናታን አክሊሉ ከዚህ ቀደም ባስተማራቸው "የቃል እምነት" ስሁት ትምህርቶች ላይ ይቅርታ እንዲጠይቅ ሊያስገድደው ይገባል። ብሎም ከሰሞኑ ከጃፒ ጋር የፈጠረውን እኩይ ጥምረት ሊያስቆመው ይገባል። የሚል የታናሽ ወንድም ምክሬን ለማቅረብ እንጂ።

ዮናታን ከህብረቱ ከተለገሰው ተደጋጋሚ ድጋፍ የተነሳ ባልበሰሉ እና ከቃለ እግዚአብሔር እውነት ይልቅ ዝነኛ በተባለ አገልጋይ ላይ የተንጠለጠለ "መንፈሳዊ" ህይወት ባላቸው አማኞች ዘንድ ያገኘውን ርካሽ "ቅቡልነት" ተጠቅሞ "ጤነኛ" ከምንላቸው ቸርቾች ወደ ጃፒ እና መሰል የሃሳዊያን "አዳራሾች" ብዙዎችን ለማፍለስ አኮብኩቧልና። በዚህም ብዙዎች በእርሱ ስሁት ትምህርቶች ቀድሞውኑ ከእውነት መንገድ ፈቀቅ ማለታቸው ሳያንስ ለተደራራቢ ስህተቶች ተጋላጭ ይሆናሉና። ህብረቱም ይህ ሁሉ ሲሆን የዳር ተመልካች መሆኑ እና ያለፈውን ስህተት በዝምታ ማባባሱ አደጋው የከፋ ነው።

ነገር ግን ህብረቱ በዚህ ወቅት በሃሳዊው ዮናታን ላይ የያዘውን የተሳሳተ አቋም በማስተካከል ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ካልቻለ በ2009 ዓ.ም ያወጣውን መግለጫ እንደገና በማሻሻል እንደ ጃፒና ተዘራ ጩፋ እና ጭሮን ወዘተ... ያሉ ሃሳዊያንንም "በአጋር አባልነት" ማቀፉን በጊዜ ይንገረንና ይቁረጥልን።

ቴዎድሮስ ተጫን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

እግዚአብሔር በየቀኑ በሕይወታቸው ውስጥ የሚያደርገውን በጎነት የማናስተውል ብዙ ነን። ከእንቅልፋችን በሰላምና ጤና ነቅተን የማለዳዋን ፀሓይ ለማየት ስለመታደላችን ምስጋና ስናቀርብ አንታይም። በመሰለን መንገድ ያልተከናወነ ነገር ብንቀበልም፥ መብታችን እንጂ ቸርነት አይመስለንም። በሕይወት መኖር እንደ ቀልድ ይታለፋል። ስፍር ቍጥር የሌላቸው ቅጽበታዊ ዕለታዊና የዘመናችን ሙሉ የበጎነት ስጦታዎቹ በቸልታ ተወርውረው ይኖራሉ። እኛ ሰዎች እንገርማለን እኮ። እናሳዝንማለን።

የገዛ ምራቁ ትን ብሎት ሕይወቱን በሰከንዶች ውስጥ ሊያጣ የሚችል ሰው በሕይወት መቈየት የቻለው በእግዚአብሔር ምሕረት መኾኑን ይዘነጋል። ፍጥረት ሕግና ሥርዐት ጠብቆ የሚኖረው በጌታ ነው። ምድር በአምላካዊ ቸርነት ተጠብቃ ሕይወት ያብብባታል። ሥጋት በወጠረው ዓለም ውስጥ በሰላም ወጥተን መግባት መቻላችን ትርጕሙ የሚገባን አገር ምድሩ ሲታመስ መኾን የለበትም።
.
ከስንት አስፈሪ ነገሮች ተረፍን? ስንቱን የሞት ሸለቆዎች በምሕረቱ ተሻገርን? ስንት ጊዜ ወድቀን ስንት ጊዜ በቸርነቱ ተደግፈን ተነሣን? ዛሬስ ቢኾን ከእጆቹ ምን ተቀብለናል? ወዳጃችን፥ "ነፍሴ ሆይ፥ ውለታውን አትርሺ" ማለቱ ቁምነገረኝነት ያለው ሰው በመኾኑ ነው። ጌታችን ማዳኑ ዛሬም አዲስ ነው።

መጋቢ ሰሎሞን አበበ ገብረ መድኅን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

"'ከእኔ ይልቃል’ ብዬ የመሰከርሁለት እርሱ ነው!"

መጥምቁ ዮሐንስ ከብሉይ ኪዳን ወደ አዲስ ኪዳን የመሸጋገሪያ ድልድይ እንዲሁም የአዳኛችንና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎት መንገድ ጠራጊ እንዲሆን ከእግዚአብሔር የተላከ መልእክተኛ ነበር። “እነሆ፤ በፊቴ መንገድ እንዲያዘጋጅ መልእክተኛዬን እልካለሁ” (ሚልክያስ 3፥1)። እውነተኛ ብርሃን ስለሆነው ስለ ክርስቶስ ምስክር ለመሆን አስቀድሞ እግዚአብሔር የላከው ታላቅ ነብይ የነበረ ሲሆን፣ ስብከቱም፦“መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሓ ግቡ” የሚለው ዐዋጅ ነበር። (ማቴ. 3፥2)​

መጥምቁ ዮሐንስ ያለምንም ፍርሃት፣ ግብዝ ለነበሩት የሃይማኖት መሪዎች፣ ለኀይላትና ለሥልጣናትና ለሕዝብ ሁሉ የሚሆን የንስሓ ጥሪ ነበረው። ይኸው ሥር-ነቀል የሆነ የጽድቅ ዐዋጅ ከጨካኙ ሄሮድስ ጋር አጋጭቶት አሰይፎታል። ሕይወቱን አሳልፎ እስከመስጠት ታማኝና ለጽድቅ የጨከነ ምስክር ነበር። ዮሐንስ እንደ ተጻፈለት፣ በርግጥ “ስለ ብርሃን ምስክር ሆኖ ለመቆም መጣ።” (ዮሐ. 1፥7)።

አገልግሎቱን የፈጸመው በትልቅ ትሕትና ሲሆን፣ ፈጽሞውኑ ወደ ራሱ አላመለከተም። ይልቁንም ወደ ክርስቶስ እንጂ! ዮሐንስ የሰጠው ምስክርነት ይኽ ነበር፦ “እኔ ክርስቶስ አይደለሁም” - ብቸኛ መድኅን ክርስቶስ ብቻ ነው! “አንተ ክርስቶስ ነህን?” የሚል ጥያቄ የቀረበለት ዋነኛ ምክንያት የአገልግሎቱ ተጽእኖ ያስገኘለት ክብርና ዝና ነበር።

ስም፣ ስኬትና ዝና ለብዙ መሪዎች ፈተና እንደሆነ በታሪክም ሆነ በእኛም ዘመን ግልጽ ነው። እግዚአብሔር እንዲሁ ከታላቅ ምሕረቱ፣ ከደግነቱና ከሉዓላዊነቱ የተነሣ ብቻ የቱንም ያህል ክብሩን በእኛ ቢገልጥንም፣ በየትኛውም መልኩ የክርስቶስ ምትክ ልንሆን አንችልም። እኛ እንዲሁ በጸጋ ብቻ ድነት ያገኘን ኀጢአተኞች ነን! ምንጊዜም የምናገልገልውም በማያልቀው ምሕረቱ ተደግፈን እንጂ ብቁ ስለሆንን አይደለም። ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሚለው፣ "ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፣ በራሳችን ብቃት ከእኛ ነው የምንለው አንዳች ነገር የለንም።" (2 ቆሮ. 3፥5)። መሲሕ ግን ከዘላለም እስከ ለዘላለም ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ፤ የስላሴ አካል ነው!

🎚 “ኤልያስ አይደለሁም” - ኤልያስ ታላቅ የእግዚአብሔር ነቢይ ነበር። ክርስቶስ በመስቀል ሞቱ ስለሚፈጽመው የቤዝዎት ሥራ ለመነጋገር፣ ጌታችን በአስፈሪ ግርማ በተለወጠበት ተራራ ላይ ከሙሴ ጋር አብሮ ተገኝቷል። “በክብርም ተገልጠው፣ በኢየሩሳሌም ይፈጸም ዘንድ ስላለው ከዚህ ዓለም ስለ መለየቱ ይናገሩ ነበር።” (ሉቃስ 9፥31)። ሙሴ የሕግ መጻሕፍት ወኪል በመሆን እንደተገኘ ሁሉ፣ ኤልያስም የነቢያት ወኪል በመሆን፣ ክርስቶስ የድነት ታሪክ ፍጹም ፍጻሜ መሆኑን ለመመስከር በዚያ የመለወጥ ተራራ ላይ ተገኝተዋል። የሙሴ ሕግ፣ ነቢያትና መዝሙራት ሁሉ መልእክታቸው ስለሚመጣው መሲሕ ነበር፤ መልእክታቸውም በክርስቶስ ሕይወትና ሥራ ፍጻሜ አግኝተዋል። (ሉቃ. 24:44)። መጥምቁ ዮሐንስ በኤልያስ መንፈስ ከክርስቶስ አስቀድሞ የተላከ ነቢይ ነበር። ሆኖም ከዝናው የተነሣ "ኤልያስ ሳይሆን አይቀረም" የሚለው የወቅቱ ግምት ፈተና አልሆነበትም። ምላሹ፣ "አይደለሁም!" ነበር።

🎚 “ነቢዩም አይደለሁም” - ይኽ ነቢይ በዘዳግም 18፥15 “አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ከገዛ ወንድሞችህ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል፤ እርሱን አድምጥ።” ተብሎ የተተነበየለት ነው። በአይሁድ አረዳድ ይህ ነቢይ ዳግማዊ ሙሴ፣ ኤርምያስ ወይም ከታላላቅ ነቢያት መካከል አንዱ ነው። በወቅቱ ክርስቶስን ራሱን፦ “ኤልያስ፣ ኤርምያስ ወይም በዘዳግሙ ተስፋ የተገባለት ነቢይ" ሳይሆን አይቀርም ብለው የሚገምቱም ነበሩ። “አንዳንዶቹ [ኢየሱስን] መጥምቁ ዮሐንስ፣ ሌሎች ኤልያስ፣ ሌሎች ደግሞ ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ።” (ማቴ. 16፥14)። ሆኖም ይህም የዝና ፈተና ለመጥምቁ ዮሐንስ ማንቆ አልሆነበትም። ይልቁንም፣ "ነቢዩም አይደለሁም!" ለማለት አልተቸገረም።

“እንግዲያስ ማን ነህ . . . ስለ ራስህ ምን ትላለህ?” አሉት፤ በትሕትናው ግራ በመጋባት።
እኛስ እንደግል አማኝ፣ ደግሞም እንደ ክርስቲያን ማኅበረሰብ ስለራሳችንና ስለ ክርስቶስ የምንሰጠው ምስክርነት ምን ይሆን?

መጥምቁ ዮሐንስ ስለራሱም ስለክርስቶስም እንዲህ ሲል መሰከረ፡-

🛐 “በነቢዩ በኢሳይያስ እንደ ተነገረው፣ ‘ለጌታ መንገድ አቅኑለት’ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ድምፅ እኔ ነኝ።’” (ዮሐ. 1፥23)። ዮሐንስ ይኽን ሲመስክር፣ እኔ የእግዚአብሔር መልእከት አብሳሪ ድምፅ ነኝ ማለቱ ነበር። ክርስቶስ የእግዚአብሔር መንግሥት ዐቢይ አጀንዳ መሆኑን የሚናገር ድምፅ፤ የዚህ የምሥራች ዐዋጅ ነጋሪ ነኝ ማለቱ ነበር። ክርስቶስ በቤዛዊ ሞት ዓለምን ከኀጢአት ባርነት ነጻ ለማውጣት የተላከ የእግዚአብሔር ልጅ መሆንን በአጽንዖት መስክሯል። ዐዋጁም ክርስቶስ ካህንም የኀጢአት ስርየት መስዋዕት ለመሆን ስለመምጣቱ ነበር። በጨለማ ለሄደ ሕዝብ ብርሃን የመውጣቱ፤ ለተጠማው ምድረ በዳ፣ የሕይወት ውሃ ምንጭ መፈለቁን የሚያበስር ዐዋጅ ነጋሪ!

እኛም ለእግዚአብሔር እንዲሁ እንሁንለት፤ የድነትና የተስፋ ዐዋጅ ነጋሪዎች! መልእክታችን ስለክርስቶስ እንጂ ስለ እኛ አይሁን! ጌታ ኢየሱስ ኀጢአታችንን ተሸክሞ በመስቀል ላይ ሞተ (ማቴ. 27፥35፤ 1ጴጥ. 2፥24) ። መምትካችን በመሞት፣ ቅጣታችንን ተቀበለ (ኢሳ. 53፥5-6)። ጻድቅና ልዑል እግዚአብሔር በልጁ ሞት ምክንያት የእያንዳንዳችንን ሞትና እርግማን አስወግዷል (ኢሳ. 53፥4፤ ገላ. 3፥13)። ከዚህ ውጪ ያሉ ድርብ፣ ባዕድና ተጻራሪ ትምህርቶች ሁሉ ከቤተ ክርስቲያን ተጠራርገው ሊወጡ ይገባል። ክርስቶስ ብቻ!

🛐 አኔ “የጫማውን ማሰሪያ ለመፍታት እንኳ የማልበቃ” (ዮሐ. 1፥27፣ ማቴ. 3፥11)። ሆኖም፣ የከበረውን የእግዚአብሔርን ልጅ ክርስቶስን የማሳይ ነኝ። በአጭሩ፣ እኔ መሲሑ፣ ኤልያስ ወይም ነቢዩ አይደለሁም፤ ይልቁንም ያልኋችሁ “እነሆ! የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” (ዮሐ. 1፥29)። ከእኔ በኋላ የሚመጣው በባሕርይ፣ በክብርም ከእኔ የላቀ፣ ፊተኛና ኋለኛ፣ "ያልሁት እርሱ ነው!"(ዮሐ. 1፥30)።

🛐 የመጣኹበት፣ የሕይወቴና የአገልግሎቴ ሁሉ ግብ “[እርሱ - የእግዚአብሔር በግ ክርስቶስ] በእስራኤል ዘንድ እንዲገለጥ ነው።” (ዮሐ. 1፥31)። አባቱም "የምወደው ልጄ" በማለት ከሰማያት ሲያውጅለት ሰምቻለሁ። " . . . በውሃ እንዳጠምቅ የላከኝም፣ ‘በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቀው፣ መንፈስ ሲወርድና በርሱ ላይ ሲያርፍ የምታየው እርሱ ነው’ ብሎ እስከ ነገረኝ ድረስ እኔም አላወቅሁትም ነበር፤ አይቻለሁ፣ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ እመሰክራለሁ።” (ዮሐ. 1፥ 32-34)።

ዮሐንስ ከመታሰሩ በፊት የመጨረሻ ምስክርነት ይሰጣል . . .

🛐 እኔ ሚዜ ነኝ - የእኔ ሕይወት ስለ ሙሽራው ነው። የሰርግ መርሐ-ግብር ድምቀት ሙሽራው እንደሆነ ሁሉ፣ እኔም የመጣኹት በእግዚአብሔር የድነት መርሐ-ግብር ውስጥ መካከለኛ የሆነውን ክርስቶስ ለማድመቅ ነው! እርሱ የአብ የክብር ነጸብራቅ ነው፤ የእኔም ሥራ ሙሽራውን ማድመቅ ነው። የደስታዬ ምክንያት ክርስቶስ ሲደምቅ ነው። “ሙሽራዪቱ የሙሽራው ነች፤ ድምፁን ለመስማት በአጠገቡ የሚቆመው ሚዜ ግን፣ የሙሽራውን ድምፅ ሲሰማ እጅግ ደስ ይለዋል፤ ያ ደስታ የእኔ ነው፤ እርሱም አሁን ተፈጽሞአል።" (ዮሐ.

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ሞተዋል? ወይስ እያገለገሉ ናቸው?

ሰሞኑን የቢቢሲን ዘጋቢ ሥራ ተከትሎ የቲቢ ጆሹዋ እርድዕት እየተንፈራፈሩ ይገኛልሉ። አንዳንዶቹ ቢቢሲን ይራገማሉ፥ ያወግዛሉ። ሌሎች የቲቢን ድንቅነቱን ይዘክራሉ፤ ድርሳን ይጽፉለታል። የኛ ሰው ቢሆን ታቦትም በስሙ ይቀረጽለት ብለው ማመልከቻ ሳያስገቡ አይቀሩም። የነዚህ መጋጋጥ እንጂ ሌላ አይደለም። አገልጋዮቹና ተከፋዮቹ በዘጋቢ ቪድዮው የቀረቡት ሰዎች ሐሰተኞች መሆናቸውን ሊያቀርቡ ሞክረዋል።

ከኢትዮጵያ አንድ ሁለቱ ያደረገላቸውን ነገር የሰጣቸውን ገንዘብ ሳይቀር በመናገር ደግ ሰው መሆኑን ተርከዋል። እነዚህ የኢትዮጵያ ቢሮውን ቢከፍት ዋነኞች ሊሆኑ የታጩት ነበሩ። ኢትዮጵያ ሊመጣ ረብጣ ገንዘብ ተቀብለው ሽር ጉድ ያሉ ጉዶቻችንንም አንረሳቸውም። ባለመምጣቱ ጌታ ይመስገን። አንድ ታዋቂ ጴንጤቆስጣዊ አገልጋያችን የሆነ ሰው፥ 'አንድ ቲቢ ጆሹዋ አስቀራችሁ፤ መቶ ቲቢ ጆሹዋዎች ተወልደዋል!' አለ። እየሄደም ቡራኬ ሰጣቸው። ገንዘብ የማይገዛው ጥቂት ነገሮችን ብቻ ነው። ሰይጣን እኮ ጌታን የገንዘብ ስጦታ አቅርቦለት ነበር። ዲያብሎስም፦ ይህ ሥልጣን ሁሉ ክብራቸውም ለእኔ ተሰጥቶአል ለምወደውም ለማንም እሰጠዋለሁና ለአንተ እሰጥሃለሁ፤' ብሎት ነበር። የዲያብሎስ ድፍረት ሁሌም ይገርመኛል።

ቲቢና ምኵራቡ የሰይጣን መሥሪያ ቤት ስለመሆኑ የዛሬ 11 ዓመት ከጻፍኩ በኋላ የተነገረኝ ታሪክ ነው፤ አንድ አባትና እናት ልጃቸው እንድትፈወስላቸው ይዘዋት ናይጄሪያ ይሄዳሉ። ሄደው እዚያ ቆይተው ተጸልዮላት ሳትፈወስ ትቆያለች። ኋላ ጊዜያቸው እያለቀ ሲመጣ፥ እናንተ ተመለሱ ለሷ ለጥቂት ሳምንታት እንጸልይላታለን ይባላል። አባትና እናት ይወዛገባሉ። እናት፥ 'ልጄን ትቼ አልሄድም፤' አባት፥ 'በእግዚአብሔር ሰው እጅ ናት ምንም አትሆንም።' ይላል። የአባት አሳብ አሸነፈ፤ ትተዋት ተመለሱ። ከሳምንታት በኋላ ልጅቱንም አመጧት። ስትመለስም አልተፈወሰችም። አለመፈወስ ብቻ አይደለም፤ እዚያ በቆየችባቸው ሳምንታት በተደጋጋሚ ተደፍራ ነበር።

የቲቢ እኩይ ሥራ ገና ይኖራል። አንዳንዶች፥ 'በቃ ሞቷል ተውት እንጂ! ወይስ አሁንም እያገለገለ ነው?' ይላሉ።

ለነዚህ የምለው ይህ ነው፤
ኬነት ሄግንም እኮ ሞቷል፤ ወይስ አሁንም እያገለገለ ነው?
አርዮስም እኮ ሞቷል፤ ወይስ አሁንም እያገለገለ ነው?

ዘላለም ነኝ።

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

https://www.bbc.com/amharic/articles/cw4kqdy4kgdo?at_format=link&at_campaign_type=owned&at_link_type=web_link&at_bbc_team=editorial&at_link_origin=BBC_News_Amharic&at_medium=social&at_link_id=BA021028-B2AE-11EE-976C-29C554826ABF&at_campaign=Social_Flow&at_ptr_name=facebook_page&fbclid=IwAR2ubJt6JiDGb87BgkDHuJZayaQk23Vezl01Y-Nndn6xaGyMNWC6kgBv-Ds

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የሕይወቴን ሦስት ሰዓታት ያህል ሰውቼ ሁለት ዓመታትን የፈጀውንና ለረጅም ዓመታት የጆሽዋ ደቀ መዝሙር ሆነው የኖሩ ወደ ሠላሳ የሚጠጉ ሰዎች በሰጡት ምስክርነት ላይ ተመሥርቶ የተሠራውን ሦስት ክፍል የቢቢሲ ዶክመንተሪ አየሁት!

ቢቢሲ እንደ ዓላማዊ ተቋሚነቱ እኩይ ዓላማ አንግቦ የዚህን ሰው ክብርና ዝና ለማዋረድና ቤተ ክርስቲያንና አገልጋዮችን ለማጥቃት የሠራው ዘገባ ነው ብሎ ለማስተባባል ቢሞከር እንኳን ወደ ሠላሳ የሚጠጉና እያንዳንዳቸው በግምት ከዐሥር ዓመታት በላይ የዚህ ሰው ታማኝ ደቀ መዝሙር የሆኑ ምስጢር ዐዋቂዎች የተደራጀ ሐሰት ያወራሉ ብሎ መፈረጅ ይከብዳል::

ይህን የቢቢሲ ዶክመንተሪ በቅርቡ አልጀዚራ "The Gold Mafia” በሚል ኡበርት እንጀልና ተባባሪዎቹ ላይ ከሠራው ዶክመንተሪ የሚለየው ጆሽዋ ከሞተ በኅላ መሠራቱ ብቻ ነው::

ይህን ዶክመንተሪ ያየ አእምሮ ያለው ማንኛውን ጤናማ ሰው ማሰብ የሚችለው ነገር በእግዚአብሔርና በክርስትና ስም እንዲህ ዐይነት ነውር እንዴት ሊሠራ ይችላል!? የሚል ነገር ነው:: በተጨማሪም በሐዋርያትና ነቢያት ነን ባይ ግለ ሰብ የሚመሩ ሜጋ ድርጅቶች ምን ያህል የእንዲህ ዐይነት የግለ ሰብ ጣዖትነት: ቅሌትና የምግባር ዝቅጠት ውስጥ የተዘፈቁ የመሆኑን ዕድሉ ከፍተኛ የመሆኑን እውነት ይገነዘባል!

እኛም ሀገር ቢሆን በገስት ሐውስና የጸሎት ክፍሎች ውስጥ የሚደረጉ ጥቃቶችና ሸፍጦች: ለቴለቭዢን የማስታወቂያ ግብዓትነት የሚውሉ ማጭበርበሮች ለጊዜው ለችግሩ ተጋላጭ የሆኑ ግለሰቦች በማናገር ጠንካራ ዶክመንተሪ ሠርቶ ማጋለጥ አደጋች ቢሆንም ጊዜውን ጠብቆ መገለጡ አይቀሬ ነው!

አንዳንድ የጅሽዋ የመንፈስ ልጆች:- "ሞቶም የሰይጣንን ኅይል ያናወጠ ጀግና" ዐይነት ፖስቶችን በጆሽዋ ፎቶ አስደግፈው በመለጠፍ ግለ ሰቡን ቅዱስና ፍጹም ለማድረግ የለፉበት ዐይንን በጨው ያጠበ ክህደት አንድም በተመሳሳይ ድርጊት ውስጥ መሆናቸውን ማሳያ ሊሆን ይችላል ወይም ደግሞ ዶክመንተሪውን ሳያዩ በአደባባይ ለቀረበው ትችት ጭፍን ምላሽ እየሰጡ ሊሆን ይችላል:: ወይም ደግሞ በዚህ ሰው የሥልጣን ሥር ሆነው መንፈሳዊ: አካላዊና ስነ ልቦናዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሰዎች ቅንጣት ርኅራኄና ሰብአዊነት የሌላቸው አረመኔዎች መሆናቸው ያሳያል!

እነዚህ ሰዎች ይህን ነውር ካዮ በኅላ ለራሳቸው መዋል የሚችሉት ትልቁ ውለታ የራሳቸውን ቤትና ሕይወት መፈተሽ ካልሆነም ዝምታ ነበር!!

አንዱ የጥቃት ሰለባና የዶክመንታሪ መስካሪ እንዳለው:- "ቲቢ ጆሽዋን በትክክል የሚያውቀው ከእርሱ ጋር ለዓመታት የኖረ ሰው ብቻ" ነው::

አሌክስ ዘጸአት

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ያለ መንፈስ ቅዱስ ከሚደረግ የመውደቅ የመነሳት ከንቱ ልምምድ ተጠበቁ!!!

ሰሞኑን ስለ መንፈስ ቅዱስ እየስተማርኩ ነበር። ካነሳሁት አንድ ነገር "መንፈስ ቅዱስ መለኮት ስለሆነ ምንም እንኳን በሰው ቢያድርም በሰው ግን ሊታዘዝና በቁጥጥር ስር ሊሆን የማይችል ታላቅ አምላክ ነው።" የሚል ነበር። Man cannot manipulate the Holy Spirit. ነገር ግን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተናል ወይም ተቀብተናል እያሉ በመንፈስ ቅዱስ ስም የማያደርጉት ነገር የለም። በመንፈስ ቅዱስ ስም የሚሰሩት በደልና ግፍ ብዙ ነው። የመንፈስ ቅዱስን ስራም የማስመሰል ጥበባቸው ያስደንቃል። በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችም ሰበብ የሰዎችን ህይወት አራቁተዋል። ለብዙዎች ስብራትና ሐዘን ምክንያት ሆነዋል። መንፈስ ቅዱስ በክርስቶስ ቦታ ምትክ ሆኖ ቤተ ክርስትያንን ለመቀደስ የተላከ መለኮት መሆኑን ዘንግተው የግል ንብረታቸው አድርገውታል። እነሱ መሰላቸው እንጂ መንፈስ ቅዱስ የሰው ንብረት አይደለም። ሊሆንም አይችልም። በገላትያ መጽሐፍ አብ ልጁን ላከ። መንፈሱንም ላከ ይለናል። ይህ የሚያሳየን መንፈስ ቅዱስ ልክ እንደ ኢየሱስ በድነታችን ውስጥ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ሲሆን ከተላከበት አምላካዊ ተልእኮ ውጪ ማንም መንፈስ ቅዱስን ሊያዘውና ሊቆቆጣጠረው አይቻለውም።

የእውነተኛ መንፈሳዊነት ልኩም በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ስር መሆን እንጂ (1ኛ ቆሮ 2) በስጋዊ አእምሮ ተጽእኖ ውስጥ ሆኖ እንደ አልዳነ ሰው (living as if you are in the old age) መኖር አይደለም። በስጦታዎቹ እያገለገሉ መንፈሳዊ አለመሆን ይቻላል። ያለ መንፈስ ቁዱስ ቁጥጥር (influence and control) ስጦታዎቹ ሰጪው ለሰጠበት ግብ ግን አይሆኑም። በዚህ ሁኔታ ስጦታው ያለው ሰው ስጋዊ ከመሆን የዘለለ ነገር አይሆንም። መንፈስ ቅዱስ የተሰጠን በዋናነት ለማንነት ግንባታ (Spiritual formation) ለቅድስና (Sanctification- to make the church sacred) እንዲሁም ለቤተክርስትያን ተልእኮ ፍጻሜ ነው።

በየስፍራው የምናየው በመንፈስ ቅዱስ እና በስጦታዎቹ ስም የሚደረገው አመጽ የተለየ ነው። በጤናማ አስተምህሮ መለኪያነት ለመለየት የሚያስቸግር የተጭበረበረ ነገር በዝቷል። በመንፈስ ቅዱስ ሆኖ በክርስቶስ አእምሮ ካልተኖረ በስተቀር በተለያየ መንፈስ መታለሉ ይቀጥላል። የመንፈስ ቅዱስን ማንነት እና ስራ ካለመለየት የተነሳ መንፈስን ሁሉ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ማደባለቁ አይቀርም። እኛ በአንዱ መንፈስም በመናፍስትም መኖር የምናምን ነን። We believe in One Holy Spirit. We also know that there are spirits. ነገር ግን መሰጠታችን መገዛታችን ለአንዱ መንፈስ ብቻ ነው። ቶዘር እንዳለው መንፈስ ቁዱስ ባይኖር የምናደርጋቸውን ነገሮች እያደረግን እንቀጥላለን። መንፈስ ቅዱስ በነገራችን በልምምዶቻችን ወዘተ ውስጥ አለመኖሩን እስከማንለይ ድረስ ከደረስን አደጋ ውስጥ ነን።

በሃገራችን አንድ የምታዘበው ጉዳይ አለ። ይኸውም መንፈስ ቅዱስን ከመውደቅ ጋራ እኩል አድርጎ የመቁጠር ዝንባሌ። በእርግጥ መውደቅን ከመንፈስ ቁዱስ ጋራ አንድ አድርገውት ላይሆን ይችላል። ነገር ግን ልምምዱ የሚያሳየው የመንፈስ ቅዱስን ስራ ከመውደቅ ጋራ በቀጥታ ማያያዛቸው ነው። ሰው ከእግዚአብሔር ኃይል የተነሳ ሊወድቅ ይችላል። ነገር ግን መውደቅ የዘወትር የመንፈስ ቅዱስ ስራ አይደለም። በመውደቅ በመነሳት ቤተ ክርስትያን ቅዱስ አትሆንም። በመውደቅ በመነሳት ቤተ ክርስትያን አትበስልም። በመውደቅ በመነሳት ቤተ ክርስትያን ተልእኮዋን የምትፈጽም አትሆንም። መንፈስ ቅዱስ ሰዎችን በመጣል አእምሯቸውን እንዲስቱ የሚያደርግ ምትሃታዊ ኃይል አይደለም። መንፈስ ቅዱስ ሰዎችን በማንቀጥቀጥ አእምሯቸውን እንዳይጠቀሙበት የሚያደርግ የኃይል ተጽእኖ አይደለም። ሰው በመንፈስ ሲሆን በክርስቶስ ልብ ያስባል። ያሰላስላል። እንዲያው በጸጋ የተሰጠውን ያውቃል። የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ይረዳል። በመንፈስ ቅዱስ ሰው እየበሰለ ይመጣል። ከመውደቅ መነሳት አልፎ በአእምሮው ይለወጣል። በመንፈስ ፍሬ ይሞላል። ክርስቶስን እየመሰለ ይሄዳል። በመከራ ይጸናል።ተልእኮውን ይወጣል። By the Spirit, we would be formed as a holy community of Christ and by the same Spirit, we would fulfill our mission.

ታምራት ታረቀኝ መንፈስ ቅዱስን እንደ ወንጌል መውደቅን እንደ ትልቅ የመንፈስ ቅዱስ ስራ ቆጥሮ በቅባት አገልግሎት ስም ዓለምን ይዞራል። ሰዎች ይሰበሰባሉ። ከዛም አነቃቂ ንግግሮች ይደረጋሉ። ከዛም የመጣልና የመውደቅ ድራማው ይጀመራል። ይህ በመንፈስ ቅዱስ ስም የሚደረግ የተሳሳተ ልምምድ ነው። መንፈስ ቅዱስን በቅርበት የሚያውቅ ሰው ማለትም በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ስር የሆነ ሰው አግልግሎት ከመንፈስ ቅዱስ ማንነት እና ተልእኮ የተለየ ነገር አይለማመድም። አገልግሎቱን በጉባኤ ውስጥ ከሚታዩ ነገሮች አንጻር አያገለግልም። ልክ እንደ ኢየሱስ ለማንነቱም ለተልእኮውም የተሰጠ ነው። በአስተምህሮው ይዘት እና ትኩረት ከመንፈስ ቅዱስ ማንነትና ተልእኮ ጋራ አይተላለፍም። መንፈስ ቅዱስ ሰዎችን የመጣል መርሃ ግብር የለውም። መንፈስ ቅዱስ ሰዎችን ያለ አእምሮ የማድረግ ትኩረት የለውም። የመንፈስ ቅዱስ ስራ እንደ ቀዶ ጥገና ሰዎቹ ባልተሳተፉበት መልኩ የሚደረግ አይደለም። የሰው አእምሮ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ካልተለወጠ ሰውየው ሲወድቅ ቢውል መቼም አይለወጥም። The Holy Spirit must have access to the mind, so that the mind will be transformed. The powerful presence of Holy Spirit is seen not by falling but by transformation of the mind.

የመውደቅ አገልግሎት ዋና ሲሆን ድራማ ነው። ስህተት ነው። እንዲያውም ድንዛዜ ነው። ያለ መንፈስ ቅዱስ ከሚደረግ የመውደቅ የመነሳት ልምምድ ተጠበቁ።

ዛዲግ ብርሃኑ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

እግዚአብሔር በራልን፤ በልባችን በራ
.
ኀጢአታችንን ያነጻው መሲሕ ኹሉን በሥልጣኑ ቃል ደግፎ ያጸናው የዘላለም ጌታ ነው። የፍጥረተ ዓለሙ ባለቤትና የህልውናው መሠረት፥ ሊታደገው በመጣው ዓለም “ሥፍራ አልነበረውምና” በበረት ተወልዶ በግርግም ዐደረ። እኛ ዘንድ ለመድረስ ያን ያህል ወረደ፤ ተወለደ። ...
.
ዳሩ ግን፥ ገና መወለድ ብቻ አይደለም፤ መምጣትም ነው። እግዚአብሔር ወደ ሰው ወረደ። ሰማይ ወደ ምድር መጣ፤ ዘለዓለም በሥርዐተ-ጊዜ ውስጥ ፈገገ። በመተላለፍ የተዳፈነ ሕይወታችን በማዳኑ ወገገ። በእግዚአብሔር ዓለም ላይ የሠለጠኑ የትኞቹም ዐይነት የዐመፃ ኀይላት ተሰባብረው እንዲዋረዱ ብርሃን በጨለማ አበራ፤ ፍቅር ስቦት የመጣው እርሱ ጸጋና እውነት ተመልቶ ማደሪያ ድንኳኑን በእኛ ደኵኗልና፥ እግዚአብሔር በራልን፤ " በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን ዕውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ፦ በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነውና" (2ቆሮ. 4፥6)
.
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ!

ሰሎሞን አበበ ገብረ መድኅን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ስለእግዚአብሔር  መንግስት ስናስብ ሳናስባቸው ልናልፍ የማንችላቸው መሠረታዊ ጉዳዮች ምንድናቸው?
ዘማሪው  መዝሙር 89:14 ላይ እንዲህ ይላል።
ጽድቅና ፍትሕ የዙፋንህ መሠረቶች ናቸው....

እስኪ የእግዚአብሔር ዙፋን መሰረት የሆኑትን ጽድቅ (ሴዴቃ | sedeqa) እና ፍትህ  (ሚስፓት | mispat)እንመልከት።

ሴዴቃ የሚለውና በአማርኛው ጽድቅ ተብሎ የተተረጎመው ቃል፥ በግንኙነቶቻችን ውስጥ ነገሮች ትክክል ወይም እንደሚገባቸው መሆናቸውን የሚያሳይ ቃል ነው። ሚስፓት ደግሞ በአማርኛው “ፍትሕ” ተብሎ የተተረጎመው ቃል ሲሆን በግንኙነቶቻችን ውስጥ ነገሮች ትክክል ወይም እንደሚገባቸው ስላልሆኑ ያንን ለማስተካከል የምንወስደውን ርምጃ ያሳያል። ለምሳሌ ያክል ሁሉ ሰው በልቶ ጠግቦ፣ ለብሶ ሞቆትና መጠለያ አግኝቶ ያለሥጋት ማደሩ ጽድቅ ወይም ትክክል ነው። ባል ለሚስቱ መታመኑ፣ እናትና አባት ልጆቻቸውን መንከባከባቸው፤ መሪዎች በርሕራሄ መምራታቸው ሁሉ ጽድቅ ነው።

ይህ ሳይሆን ቢቀርና ጽድቅ ቢጓደል ግን የተራበውን ማብላት፣ የተራቆተውን ማልበስና ቤት ካጣው ሰው ራስ በላይ ጣሪያ ማኖር ፍትሕ ይባላል። ፍትሕ የተጓደለውን የማሟላት፣ የተሰበረውን የመጠገን፣ የፈረሰውን መልሶ የመገንባት ሥራ ነው።

የእግዚአብሔር ሕዝብ ሲሆን በጽድቅ የሚኖር፣ ሳይቻል ደግሞ በመካከሉ ፍትሕን የሚለማመድ ነው መሆን ያለበት። ይኽ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር ሕዝብ ለሌላው ሕዝብም ፍትሕን የማድረግ ልምምድ ሊኖረውም ይገባል። ይህ መሰረታዊ ነው! መሰረታዊ ስል basic ማለቴ ነው። ሀ ሁ እንደማለት! መሰረታዊ ስል foundational ማለቴ ነው።

ደህና ነን? ቤታችን በምን ላይ ነው የተመሰረተው?

ሳራ አብደላ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

መጽሐፍ ቅዱስ አግባብ ያለው አፈታት የሚፈልገውን ያህል አግባብ ያለው አተገባበር ይፈልጋል። አንዳንድ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን ለመፍታት የምንሄድበት ርቀት በመጽሐፍ ቅዱሱ ውስጥ የሚገኙትን ግልጽ ምንባባትን ለመተግበር ከምንሄድበት ርቀት ጋር አይጣጣምም። አንዳንዴም ለትርጎሜና ፍታቴ የምንነሳበት ዐላማ ቃሉን ዝም ለማሰኘት ይመስላል። ይህንን ለመግለጥ ሶረን ኪርክጋርድ ሦሥት ምሳሌዎችን ይጠቁማል።

¹

የእግዚአብሔርን ቃል አንብቦ የሚያደርግ ወይም የሚተገብር ሰው ራሱን በመስታወት ተመልክቶ በመስታወት ውስጥ የሚያየውን ሰው የሚያስታውሰውን ይመስላል። እውነተኛ በረከት በእግዚአብሔር ቃል መስታወትነት ውስጥ የሚገኘውን ትክክለኛውን የእኔን መልክ መመልከት ነው። ነገር ግን መስታወቱ ውስጥ ከመመልከት መስታወቱን ወደ መመርመር ካዘነበለ አደጋ ይኖረዋል ይላል ኪርክጋርድ የያዕቆብን መልክት በመጥቀስ (ያዕቆብ 1፥22-27)።

ራስን መመልከት ወይም በመስታወቱ መመልከት ሲል ምን ማለቱ ነው? የሚል ጥያቄን ማንሳት ይኖርብናል። የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ምንም የለም አልያም አንባቢው ራሱን መስታወቱ ውስጥ ይመለከታል እና ራሱን መስታወቱ ውስጥ ያገኛል? ማለታችን ይሆን። አሁን በሚቀነቀኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜዎች ውስጥ ስለ እግዚአብሔር ቃል የሚነሳን መሠረታዊ የሆነ ነገርን ይመልሳል። ከአንባቢው ነፃ የሆነን እውነታ (reality) የመተርጎም ሁኔታ በቃሉ (text) ውስጥ ይገኛል? ወይንስ ቃሉ (the text) የአንባቢውን እውነታና ሁኔታ ብቻ ነው የሚያንጸባርቀው? በቫንሆዘር አገላለጽ "Is there something in the text that reflects a reality independent of the reader's interpretive activity, or does the text only reflect the reality of the reader?

²

አንድ የፍቅር ደብዳቤ ከአፍቃሪው ለተፈቃሪው ግራ በሚያጋባ ቋንቋ ተጻፈ እንበል። በቋንቋው ግራ የተጋባው ሰው መዝገበ ቃላት ይዞ ቃል በቃል መተርጎም (translate not interpret) ይጀምራል። አንድ ታዛቢ ታዲያ "ከተወዳጅህ የተላከልህን የፍቅር ደብዳቤ እያነበብክ ነው?" የሚል ጥያቄ ይሰነዘርለታል። ምላሹም "አይ እዚህ ከመዝገበ ቃላቱ ጋር ተጓልቼ እየዛኩ ነው .... ይህንን ማንበብ ካልከው እያላገጥክብኝ ነው።" ይለዋል። ኪርክጋርድ ማንበብ ብቻ ሳይሆን lingustic & historical scholarship የታከለበት ንባብ ሃቀኛ አነባበብ እንዳልሆነ ለማሳየት የተጠቀመበት ምሳሌ ነው። ልክ በመስታወቱ ውስጥ ራስን ከመመልከት መስታወቱን ብቻ እንደመመልከት ማለት ነው። ይሄ የዘመናዊውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አቃቂራዊ አነባበብን ይሄሳል።

³

በአንድ ንጉሥ በምትመራ አገር ንጉሡ አዋጅን አወጀ እንበል። በንጉሡ ግዛት የሚተዳደሩት ለአዋጁ ከመገዛትና ከመታዘዝ ይልቅ የአዋጁን ጭብጥ በመተንተንና በመተርጎም ተጠመዱ። በየእለቱም አዳዲስ ትርጎሜዎችን ያዋልዱ ያዙ። በሂደትም በአዋጁ የታወጀውን ማድረግ እያቃተቸው መጣ። ችግሩ የንጉሡ አዋጅ ለመተርጎም ተብሎ ተነበበ እንጂ ለመተግበር ተብሎ አለመነበቡ ነው። አዋጁ የሚተገበርና ካልተተገበረ የሚያስከትለው ውጤት መኖሩን መገንዘብ ነው።

.

የእግዚአብሔር ቃል የፍቅር ደብዳቤና እና የንጉሥ ድንጋጌ ነው። ስለዚህ እንተርጉመው ወይስ እንታዘዘው? ራሳችንን በቃሉ እንመልከት አልያስ ቃሉን በጥያቄ እያጣደፍን እንሰልጥንበት? ኬቭን ቫንሆዘር "Is There A Meaning in This Text?" በሚለው መጽሐፉ ላይ እንደታዘበው የእኛ ዘመንን አተረጎጓም አንዳንድ አተረጎጓሞች በአተረጓጎም ሂደታቸው የቃሉን ስልጣን ይጋፉታል ይላል። የዘመናችንን ዘመናዊ አተረጓጎምና ትግበራ "በእምነት" (in the faith) መሆኑን ማረጋገጥ ይፈልጋል።

የኪርክጋርድ ሦሥቱ ምሳሌዎች ዋና ነገር አንባቢ የእግዚአብሔርን ቃል ለመተርጎም መታደሉን እንዲሁም ኅላፊነት መውሰዱን ስለመዘንጋቱ ያወሳሉ። ብዙ ጊዜ ለመተርጎም የምንሮጠው ራሳችንን ሲበዛ "ቢዚ" ለማድረግ እንጂ በቃሉ ራሳችንን ለማየት አይደለም። የኪርክጋርድ ሃሳብን paraphrase ባደርግ፦ "The business of interpretation is busyness: instantly to produce reading again and again to avoid having to respond to the text." ዘመነኛው አንባቢ ቃሉን ለመፍታት የመጣጣር ሂደት የሚያበዛው ለሚፈታው ቃል ምላሽ ላለመስጠት ነው።

ታዲያ ቃሉን የመተርጎም ዐላማ ምንድነው? አሁንም የኪርክጋርድን ሃሳብ ልጥቀስ "Look more closely, and you will see that it is to defend itself against God's Word." አንዳንድ የተሟሉ መሳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጎሜ አሰጣጦች ራስን ከእግዚአብሔር ቃል ለመከላከል የሚደረጉ ሙከራዎች ናቸው። የእግዚአብሔርን ቃል አንባቢ በእግዚአብሔር ቃል መስታወትነት ውስጥ ራሱን ከመመልከት ይልቅ መስታወቱን መመልከት አለበለዚያም በመስታወቱ የራሳቸው አሳሳች መልክ በትርጎሜ ለመሳል ይሞክራሉ።

አማኑኤል አሰግድ

Читать полностью…
Subscribe to a channel