negere_evangelical | Unsorted

Telegram-канал negere_evangelical - ነገረ ወንጌላውያን

2910

በወንጌላውያን አማኞች ዘንድ የሚፃፉ ፅሁፎች፣ ዘገባዎችና ዜናዎች ይቀርባሉ! ትምህርቶች፣ መረጃዎችና ምካቴ እምነቶች በዚህ ቻናል ይስተናገዳሉ! በተለያዮ ሶሻል ሚዲያዎች የሚገኙ ፀሐፊያን የሚፅፉቸው ፅሁፎችን እናጋራለን።

Subscribe to a channel

ነገረ ወንጌላውያን

የማንነትና የተልእኮ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቅኝት ያስፈልገናል።

“ሕዝብህ በአንተ ሐሤት ያደርግ ዘንድ፣ መልሰህ ሕያዋን አታደርገንምን? 7 እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህን አሳየን፤ ማዳንህን ለግሰን።" (መዝ. 85፥5-6)

አሜን!

ይቀጥላል . . .

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ይሁዳ እንደኛው ሰው ነበረ

ኤልያስ እንደኛው ሰው ነበረ የሚለውን ስንሰማ በእምነት ህይወታችን ልንበረታ እንደምንነሳሳ ይሁዳ እንደኛው ሰው ነበረ የሚለውን ስንሰማ ደግሞ በእምነት ህይወታችን ጥንቃቄ እንድናደርግ ያሳስበናል፡፡

የዐለም ታሪክን ከገለባበጡና ዘመናትን ለሁለት ለከፈለ የአዲስ ኪዳን ታሪክ ከፍተኛና መሪ ሚና ከተጫወቱት፣ የተናቁ መስለው ኅያላንን ካንበረከኩ የዐለማችን ምርጥ አስራ ሁለት ሰዎች ውስጥ አንዱ ይሁዳ ነበር፡፡

እነዚህ 12 ሰዎች ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን በማመን አብረውት እጅግ የሚገርም አገልግሎት ማገልገላቸው በወንጌላት ላይ ተዘግቦልናል፡፡ ከሁሉም በተለየ መልኩ የሚታወሰው ግን የአስቆሮቱ ይሁዳ ነው፡፡

እንደውም መጽሐፍ ቅዱስን ያላነበቡ ሁሉ “ይሁዳ” ለሚለው የተጸዎ ስም እንግዳ አይደሉም፣ እገሌ “ይሁዳ ነው” ማለትና እገሌ ከዳተኛ ነው ማለት የቃላት ልዩነት ብቻ ነው፡፡ አንዳንድ ፎቶግራፎችም ከአስራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት መሀል ነጥለው ያጠቁሩታል (ይህ በምንም መለኪያ ልክ አይደለም)፡፡

ይሁዳ ተወልዶ ያደገው በደቡባዊ የይሁዳ ግዛት “ቂርያት ሐይር” በምትባል ከተማ ነው (ኢያሱ 15፡25) አባቱም ስምኦን የተባለ ሰው ሲሆን እርሱም ልክ እንደ ይሁዳ “የአስቆሮቱ ስሞኦን” ተብሎ ተጠቅሷል “የአስቆሮቱ ስሞዖን ልጅ ይሁዳ” ተብሎ በዮሐንስ 13፡26 ተጠቅሷል፡፡
የደቀ መዛሙርቱ ስም ዝርዝር በተጠቀሰበት ቦታ ሁሉ በስተመጨረሻው ላይ ይጠቀሳል፣ አብሮም ግብሩ ይነገራል ዮሐ12፡6 ለምሳሌ “ሌባ ነበረ” ይለናል፡፡

የቤተ ክርስቲያስን ቀዳሚ አባቶች ጽሑፎች ላይ የከሃዲዎች አለቃ፣ የገሃነም ልጅ ወኪል ሆኖ ተገልጿል፡፡ በወንጌላት የምናየው ታሪኩ ግን እንደወረደ ነው የተጻፈልን፡፡

በሙስሊሙ መጽሕፍት ግን የምናየው ይሁዳ አይሁዶች ኢየሱስን አግኝተው እንዳይገድሉት ያታለላቸውና በእርሱም ፈንታ ኢየሱስን መስሎ ስለ እርሱ የተሰቀለ ነው ብለው ይተርኩታል፣ ምክንያቱም ክርስቶስ ተሰቅሏል ብለው አያምኑምና፡፡በአንዳንድ ዐለማዊ ፊልሞችም ላይ ይሁዳን ንጹህ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡

አዲስ ኪዳን ከ12 ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ማቴዎስ፣ በርተለሜዎስ፣ እንድርያስ፣ ማቲያስ የይሁዳን ግማሽ ያህል እንኳ አልተጠቀሱም፣ የይሁዳን ማንነት መገንዘብ ለሥጋዊም ሆነ ለመንፈሳዊ ህይወታችን እጅግ ከፍተኛ ትምህርት ይሰጠናል፣ በጭፍን ከሃዲነቱ ላይ ብቻ በማተኮር ሌባ ነው፡፡ ገንዘብ ወዳጅ ነው፡፡ ብለን ብቻ ነው የምናልፈው፣ እኛን ንጹህ ለማድረጊያ ዐይነተኛ መሳሪያ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ከዚያ ባለፈ ልናየውና ልንማርበት የምንችል አሳዛኝ ገጸ ባህሪ ነው፡፡ ጴጥሮስም “ከእኛ ጋር ተቈጥሮ ነበርና፥ ለዚህም አገልግሎት ታድሎ ነበርና።” የሐዋ 1፡17 ይለዋል፡፡ ትክክለኛ ምንጫችንም የአዲስ ኪዳን ወንጌላት ናቸው፡፡

ይሁዳ የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ/ተማሪ/ደቀ መዝሙር ነበር

ከምሩ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል የወሰነ ፤ ጴጥሮስም “ሁሉን ትተን ተከተልንህ” ሲል ይሁዳንም ጨምሮ/ወክሎ ነበር ያለው፡፡ ሉቃስም ስለ 12 ቱ ሲነግረን 9፡1_2 “አሥራ ሁለቱንም ሐዋርያት በአንድነት ወደ እርሱ ጠርቶ በአጋንንት ሁሉ ላይ ደዌንም ይፈውሱ ዘንድ ኃይልና ሥልጣን ሰጣቸው፤ የእግዚአብሔርንም መንግሥት እንዲሰብኩና ድውዮችን እንዲፈውሱ ላካቸው፥” ሲል እርሱም ድውያንን የመፈወስ ስጦታ ተቀብሎ በሚያስደንቅ መንፈሳዊ ስጦታ ያገለገለ የወንጌል ሰባኪ፣ የፈውስ ስጦታም የነበረው፣ አጋንንትንም በኢየሱስ ስም የሚያስወጣ ነበር፣ እነዚህ ሁሉ መንፈሳዊ ንብረቶች ይሁዳን የሆነውን ከመሆን ግን አላገዱትም ነበር፡፡

ይሁዳ ታላቅ የሕይወት ሞዴል አግኝቶ ነበር

ይሁዳ በምድር ላይ ማንም የማያገኘውን የድነት ታሪክ እድል፣ የቃል ስጋ መሆን ታሪካዊ ጊዜና ቦታ ላይ በመገኘቱ በምድር ላይ እጅግ በጣም ጥቂት ሰዎች ያጋጠማቸው “ክርስቶስን በዐይኑ የማየትና የመዳሰስ” እድል ነበረው፡፡ ዮሐንስ ይህ እድል ስለመገለጡ እርግጠኛነት የተናገረበት “ያየነውንና የሰማነውን....” እንዳለ፡፡ ባጭሩ ከእኛ የተሻለ የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ ያለው ሰው ነበረ፡፡

እኛ ከዘመናት በኋላ አንብበን የምንታመንበትን የአዲስ ኪዳን ታሪክ እርሱ ኖሮ አይቶታል፡፡ 5000 ሺህ ሰው በ5 እንጀራና በሁለት አሳ ሲመገብ የተረፈውን መሶብ ሰብሳቢ ነበር፣ አልዐዛር ከሞት ሲነሳ ከቀሩት ደቀ መዛሙርት ጋር አብሮ ሔዶ አይቷል፡፡

ይሁዳ የተራራው ትምህርት ሲነገር አብሮ ነበር ሰምቷል፣ ፈሪሳውያንና የሃይማኖት መሪዎች ማስጠንቀቂያና ወዮታ ሲቀርብላቸው ከኢየሱስ ጋር ነበር፡፡ ወንጌል እግዚአብሔር እምቢ ብለው የሚባክኑ ተጸጽተው ቢመለሱ እጁን ዘርግቶ እንደሚቀበል ሉቃስ በጸፋው የባከነው ልጅና በተቀባዩ አባት ታሪክ የተናገረው የእግዚአብሔርን ፍቅር ትምህርት ተምሯል፡፡ ይሁ ሁሉ ሆኖ ግን መጨረሻ ይሁዳ ይሁዳ ከመሆንና ጌታውን ከመካድ አላገዱትም ነበር፡፡

የሰው ልብ እጅግ ክፉ ነው ኤር 17፡9 _ ይህ የሁሉም ሰው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከፍተኛ የጸጋ ሽፋን እና የግል ዲሲፕሊን የሙጥኝታ ኑሮ ይጠይቃል፡፡

መጋቢ ሰሎሞን ጥላሁን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ወንድሞችና እኅቶች፣ እንግዲህ ወንጌል ወደ እኛ የደረሰው በዚህም መንገድ ነው። አናሲሞስ፣ ሕይወታቸው በወንጌል እውነት ሥር ነቀል በኾነ መልኩ የተቀየረ፣ ሰባኪ፣ እረኛ፣ ዘማሪ፣ ሙዚቃ ተጫዋች፣ መጸሐፍ ቅዱስ ተርጓሚ፣ የሥነ ጽሑፍ ሰው፣ ድንበር ተሻጋሪ ሚስዮናዊ የቤተ ክርስቲያን ተካይ ሐዋርያዊ አገልጋይ . . . ሕይወታቸው ይሞግታል። በእውነት እኛ አሁን መከራ በዛብን ማለት እንችላለን? ልባችንስ የተያዘው በምን ይኾን?

“አቤቱ ምሕረት አድርግልን፣ አድሰንም” - አሜን!

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ጌታ ኢየሱስን የሕይወታቸው አዳኝ አድርገው በተቀበሉ ጊዜ፣ አናሲሞስ የሚል ስም የወሰዱት የወንጌል አገልጋይ ወላጆቻቸው ያወጡላቸው ስም ሒካ ነበር። የስያሜውም ትርጕም፣ “ተርጓሚ” ነበር። ምናልባት ወላችጆቻቸው የኾነ እንቆቅልሽ የነበራቸውና እንዲሁም ያንን የሚፈታ የተስፋ ልጅ አንዲሆን በመመኘት የሰየሟቸው ይመስልኛል። በኋላ የወንጌል ተልእኮ ታሪክ እንደሚያስረዳን፣ አናሲሞስ ከቤተ ሰብ ላለፈ እንቆቅልሽ በመፍትኄነት እግዚአብሔር በልዕለ ኀያልነቱ ያሰነሣቸው ታላቅ አገልጋይ ነበሩ።

አንዳንዶቻችን “እንደ መከራ” የምንቆጣራቸውን ተግዳሮቶች ነቍጥ የሚደርግ፣ በርካታ የመከራ ጐርፍ አሳልፈዋል። በቀድሞ የግዛት አጠራር ኢሉባቦር ክፍለ ሐገር ውስጥ ሑሩሙ በምትባል ትንሽ መንደር ነበር እ.ጎ.አ በ 1855 የተወለዱት። ወላጅ አባታቸው ሲሞቱት፣ ሒካ የአራት ዓመት ሕጻን ነበሩ። የእናትየው የዘወትር ሥጋት ልጆቻቸውን ባርያ ፈንጋይ እንዳይነጥቋቸው ነበር። አልቀረም የ 13 ዓመት ዕድሜ አካባቢ ነበር ሒካ ለባርነት የተሸጡት። ያቺን የጨለማ ቀን እንዲህ በማለት ያስታውሳሉ፦

. . . ድንገት በርያ ፈንጋዮች መጡና መደራችንን በሽብር ወረሩት። አባቴ ከሞተ በኋላ የእናቴ የየዕለት ሥጋት የነበረው አፈና እውነት ኾነ። ታናሽ ወንድሜን፣ እኅቴንና እኔን አፈኑን። እናቴ እጄን አልለቀ አለች። አንደኛው ጨካኝ ፈንጋይ ሰይፍ መዘዘና ‘የማትለቂው ከኾነ ኹለታችሁንም እሰይፋችኋለሁ አለ’ እየዛተ። የእናቴ አንጀት አልችል አለ። እናም ‘ከሚሞት ባሪያ ቢሆን ይሻላል’ በማለት ከእንባ ጋር ለቀቀችኝ።” እያለቀስሁ ስጮኽ፣ ፈንጋዬ ያቺን ትንሽ ጉንጬን በተደጋጋሚ በቡጥ ያነርታት ጀመር። ኾኖም እቤቱ እስክ ደርስ ጩኸቴን አላቆምሁም ነበር። አባቴን አጣሁ፤ ጨካኝ ባሪያ ፈንጋይ ከእናቴ ቦጭቆ ወሰደኝ። ያ የጨለማ ቀን፣ ክፉ ቅዠነት ኾኖ ቢያልፍ እመኝ ነበር . . . ባርነቱ እጅግ የከፋ ነበር። ኹሉ እንዳሻው የሚጠቀምብኝ ዕቃ ነበርሁ። ሌላው ቀርቶ ለቀደምት ባርያዎችም፣ ባሪያ ነበርሁ። የባሪያ ባሪያ። የእናቴን ፍቅር እያሳብሁ ምግብ መበላት እስኪሳነኝ፣ ልቤ ዘወትር በጥልቅ ሐዘንና ትካዜ ይሞላ ነበር . . . አንደ ቀን ለማምለጥ ያደርግሁት ሙከራ ባለመሳካቱ ጀርባዬ ላይ ያልደማ አንፍም ስፍራ እሰከማይገኝ ድረስ በጅራፍ ተለተሉኝ። አንዳገግምሁ፣ በአራት ላሞች ዋጋ ተሽጥሁ . . . ብዙም አላረፍሁም። ውሃ ልቀዳ በሄድሁብት ሌላ ፈንጋይ አፍኖ ወሰደኝና በ 200 ብር ሸጠኝ። ራሴን ምጽዋ አገኘሁ - ሌላ ለማምለጥ የማይታሰብበት ዓለም። ከዚያ በኋላ ስምንት የተለያዩ ጌቶች ነበሩኝ። በዚህ ኹሉ የእናቴ ፍቅር ውስጤን ይሰረሰረው ነበር። እናም ዘወትር እንባዬ ምግቤ ነበር።” Paul Persson, Ed., 𝑴𝒐𝒓𝒆 𝒕𝒉𝒂𝒏 𝑯𝒐𝒑𝒆: 𝑨𝒏 𝑶𝒏𝒆𝒔𝒊𝒎𝒐𝒔 𝑵𝒆𝒔𝒊𝒃 𝑨𝒏𝒕𝒉𝒐𝒍𝒐𝒈𝒚, (EECMY, Addis Ababa, 2024), 13.

የሒካ መከራ ብዙ ነበር። የማምለጥ ተስፋ ባልነበርበት ኹኔታ እግዚአብሔር የሚቤዥ ሰው አዘጋጀላቸው። ይኼ ሰው፣ ባሪያዎችን መቤዠት ዋና ተልእኮ ያደረገው ቨርነር መዚንገር የተባለ ጀርመናዊ ሚስዮናዊ ነበር። ለዚያች ትድግና ስላገኙባት ቀን ሒካ እንዲሁ ብለው ይጽፋሉ፦
“መዚንገር ገዛኝና በቀጥታ ወደ ቤቱ ወሰደኝ። “አይዞህ ከአሁን በኋላ ማንም አሸጥህም” ሲል ከፍርሃትና ከጥልቅ ድባቴ ውስጥ ሊያወጣኝ ሞከረ። ኾኖም አለማንሁትም። ምክንያቱም የማውቃቸው ጌቶች በሙሉ እጅግ ጨካኝ ነበሩና! እርሱ ግን ልዩ መኾንን እያደር ነበረ የተረዳሁት። በእርግጥም ከባርነት ብቻ ሳይሆን፣ ከኀጢአት ባርነትም ዐርነት ለማግኘቴ ምክንያት የኾነ ሩኅሩኅና የፍቅር ነው ነበር።” (𝑴𝒐𝒓𝒆 𝒕𝒉𝒂𝒏 𝑯𝒐𝒑𝒆, 15.)

ሒካን በምጽዋ የነበሩ የስዊድን ሚስዮናውያን እንደ ልጃቸው አድርገው ወሰዷቸው። በዚያም በሚገኘው የስዊድን ወንጌላዊ ሚሽን Swedish Evangelical Mission (SEM) ትምህርት ቤት አምስት ዓመታት ያኽል የተማሩ ሲሆን፣ አእምሮአቸው ክፍትና እጅግ ብርህ ከመሆኑ የተነሣ አስተማሪዎቻቸው ይደነቁ ነበር። ኢየሱስ ክርስቶስን የግል አዳኝና ጌታ አድረገው የተቀበሉትም እዚሁ ትምህርት ቤት በነበሩበት ወቅት በሰሙት ወንጌልና ባዩት ፍቅር ነበር። የመዚንገርና የሚስዮናውያኑ ሥራ ጳውሎስ ለፍሊሞና ከጻፈለት ደብዳቤ የሚከተለውን ያስታውሰኛል፦

“በእስር እያለሁ ስለ ወለድሁት ልጄ ስለ አናሲሞስ እለምንሃለሁ። የልቤ ሰው የሆነውን እርሱን መልሼ ወደ አንተ ልኬዋለሁ። ስለ ወንጌል በታሰርሁበት ጊዜ በአንተ ፈንታ ሆኖ እንዲያገለግለኝ ለራሴ ላስቀረው ፈልጌ ነበር። ከእንግዲህ ወዲህ ግን እንደ ባሪያ ሳይሆን ከባሪያ በላይ የሆነ ተወዳጅ ወንድም ነው። ለእኔ ተወዳጅ ነው፤ ለአንተ ግን በሥጋም በጌታም ይበልጥ ተወዳጅ ነው።” ( ፊልሞና 1 : 10 , 12 - 13 , 16) ።

ሒካ ተጠመቁ። ስማቸው አናሲሞስ ኾነ። ዕለቱ ፋሲካ፤ March 31, 1872 ነበር። በክርስቶስ ፍቅር ውስጣቸው የነደደና ለወጌል ተልዕኮ ፈጽሞውኑ ራሳቸውን የሰጡ የአስራ ሰባት ዓመት ወጣት ነበሩ። ከአራት ዓመታት የወንጌል ሥራ በኋላ ለከፍተኛ ትምህርት ስዊድን በሚገኘው የጆሃንለንድ የነረ መለኮት ትምህርት ቤት (Johannelund School of Theology) እንዲከታተሉ ተላኩ። ወርሃ June 1876 ነበር። ጕዞው አድካሚና ረጅም ነበር። ከምጽዋ ስዊዝ ሰርጥ፣ ግብፅ፣ እስክንድርያ፤ ቪዬና፣ ትሪስት፣ በርሊንና ሉቤክ፣ በመጨረሻም ስዊድ፣ ስቶክሆልም።

ከአምስት ዓመታት በኋላ ትምህርታቸውን አጠናቅቀው ተመለሱ። ወርሃ September 1881 ነበር። በክርስቶስን የአንድ አገር ዜጋ፤ ሰማያዊ የሆነ፤ አዲስ ቤተ ሰብ አግኝተዋል። ወደ ምጽዋ ሲመለሱ፣ ግብፅ እስክንድርያ ላይ ዐረፍ ብለው የሚከተለውን ማስታወሻችው ላይ አስፍረው ነበር፦

“በክርስቶስ ካገኘኋቸው ቤተ ሰቦቼ መለየት እጅግ ነው የከበደኝ። ወሰንና ድንበር የሌለው ፍቅራቸው ልቤ ውስጥ አለ። እጅግ ብርቱ ነበር። ስሜቴን የሚገልጸው፦ ‘ፍቅር እንደ ሞት የበረታች፣ ቅናቷም እንደ መቃብር ጨካኝ ናትና፤ እንደሚንቦገቦግ እሳት፣ እንደ ኀይለኛም ነበልባል ትነድዳለች።” የሚለው የሶሎሞን ቃል ነው። (ማሕልየ መሓልይ 8 : 6)’። ኾኖም የክርስቶስ ወንጌል በጨለማ ላሉ ለብዙዎች ለማካፈል የነበረኝ ጽኑ የተልእኮ ፍቅር፣ መለየቱ የፈጠረብኝን የብቸኝነት ስሜት ቀንሶልኛል፤ በእጅጉም አጽናንንቶኛል።” (𝑴𝒐𝒓𝒆 𝒕𝒉𝒂𝒏 𝑯𝒐𝒑𝒆, 25.)

የባርያ ንግዱ ግብፅ ድረስ ዘልቆ ስለነበር፣ ሒካ መርከብ ላይ እያሉ የግብፃውያንን ፈንገጋዮችን ሤራ ይሰሙ ነበር። መርከቢቷን ዐልፎ ዐልፎ የሚያናውጣትን ማዕበልና የግብፃውያንን ሤራ እያሰቡ እንዲህ በማለት ጽፈዋል፦

“. . . መንገድ ላይ እያለሁ ዕንቅልፍ እንቢ ብሎኝ ተቸግሬ ነበር። ዐውሎ ንፋስ ቍጠኛ ሞገድ ያሰነሣ ነበር። ጌታ ግን አጠገቤ እንደ ቆመ ይታወቀኝ ነበር። የባሪያ ፈንጋዮቹንም ሤራ እሰማ ነበር። ውስጤ ግን በሰላም ተሞልቷል። እግዚአብሔር ድንበር ስላበጀላቸው እንጂ አፍነው ሊሸጡኝ፣ ካልተቻለም ሊገድሉኝ ይሹ ነበር። በክርስቶስ ያገኘሁትን ዐርነት ማንም ሊነጥቀኝ እንደማይችል ጽኑ እምነት ነበረኝ፤ ማንም ድጋሚ ሊሸጠኝ ወይም ባሪያው ሊያደርገኝ በማይችልበት ኹኔታ ክርስቶስ በክቡር ደሙ ለዘላለም ዋጅቶኞልና! ‘ሥጋን መግደል እንጂ ነፍስን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ፤ ይልቁንስ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የዝማሬ አገልግሎታችን የገባባት ቅርቃር እጅግ ያሳስበኛል። ምናልባትም ከአስተምህሮ ዝንፈት በላይም ሚያሰጋኝ በዝማሬዎቻችን በኩል ያለ ከልካይ ሚንቆረቆሩ መልእክቶች ናቸው። የተዘመረ በቀላሉ ከልብ አይፋቅም። ስብከትም የመዝሙርን ያክል በልባችን አይሰነብትም። በተለይም ደግሞ ቀልብንም በሚስብ ሙዚቃና፤ ስሜትን ሰቅዞ መያዝ በሚችል ዜማ የተሰራጨን መርዝ ሐቲትና ገላጭ ስብከት (Exegesis and expository preaching) ሊያረክሱት ሲቸገሩ እልፍ ጊዜ አይቻለሁ። ባጭሩ የተዘመረ ይወረሳል!

የዝማሬ አገልግሎታችን ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች ተደግነውበታል። በአንድ ወገን ነጠላ ዜማ እንኳ ሳይኖራቸው፤ ቆየት ያሉ ተወዳጅ ዝማሬዎችን በማሽሞንሞን ብቻ ዘማሪ ሚለውን መጠሪያ ሰልቅጠውና ቀርጥፈው በበሉ የመድረክ አድምቄዎች ይፈተናል። በሌላ ወገን ደግሞ መልእክት ያለቀባቸው በሚመስሉና በቀድሞ ዝናቸው ተማምነው ብቻ አልበም የሚያወጡ በሚመስሉ አንጋፋ ዘማሪያን ይፈተናል። በሌላ ወገን ዘፈን ሲኮሞኩሙ ከመሰንበታቸው የተነሳ ዜማም ቅንብርም ከዘፋኝ በሚመነትፉ ቀማኞች አገልግሎቱ ይበደላል። ብቻ ውስብስብ ችግሮች የዝማሬ አገልግሎት ገጥሞታል።

ወደ መልእክቶቹም ስንመጣ ተመሳሳይ ፈተና ይታየኛል። ጽድቃቸውን ያለ እረፍት "ሚዘምሩ" ሰዎች ቁጥራቸው እየናረብኝ ነው። ለጋስነታቸውን፣ ወደር የሌለው መገዛታቸውን፣ ተነጻጻሪ የሌለው ፈረሀ አምላካቸውንና ውልፍት ብሎ ማያውቅ እምነታቸውን በዜማ ሊግቱኝ ሚሞክሩ ቁጥራቸው የዋዛ አይደለም። እንደ ዜማቸው ቃል ከኾነ ሲያስነጥሱ እንኳ የእግዚአብሔርን መንግስት እያሰቡ ነው። ለቤተሰብ እንኳ ሚተርፍ መውደጃ ቦታ እስኪያጡ ጌታቸውን በመውደድ ልባቸው ቀልጧል። ከነዚህ ዜማዎች ጋር ማበር ነፍሴ ስትቸገር አያለሁ። እምነቴ በቀን ስልሳ ጊዜ ሲውተረተር እያየሁ በልቤም እልፍ ስለ መንግስቱም ስለ ፈቃዱም ስለ ስሙም ያልኾኑ መሻቶች ሲተራመሱ እያየሁ በዜማቸው ላብር አልችልም።

ከነገረ መለኮት ብይን፣ ከስነ ቃልና ግጥም አንጻር ነገሮች ይታረሙ ለማለት ስንሞክር ግላዊ ጠብ፣ ቅናት፣ እውቅናን ፍለጋና ሌሎች አጀንዳዎች እንዳሉን ሕዝበ ክርስቲያኑ አበክሮ ይናገራል። ክሶቹ እውነትነት ሊኖራቸው ቢችልም ኹሌ ግን ልክ አይደሉም። ለመተራረም ሚኾንንም ቦታ የቀሙን ይመስለኛል። የልባችንን ማዘንበልና እውነተኛ መሻት አንድዬ ቢያውቅም ለማቅናት ሚመክሩም ሊኖሩ እንደሚችሉ ማሰቡ አይጎዳንም። ስለኾነም ቀጥሎ ማነሳውን በዚህ ብርሃን ተመልከቱት።

አውታሩ ከበደ ቀደምት ከሚባሉ ዘማሪያን መኻል ነው። ሰባት አልበሞችን አበርክቷል። ለሌሎች ዘማሪያንም ግጥምና ዜማ ሰጥቶ እንደሚያውቅ ሰምቼ አውቃለሁ። እውነቱን ለመናገር አዲሱ አልበሙን በስስትና መንሰፍሰፍ ውስጥ ኾኜ ስጠባበቅ አልነበረም። ይኼኛው ጥበቃ ብዙ ጊዜ ኩምና ሙሽሽ አድርጎኝ ስለ ሚያውቅ ጥበቃዬን ማስተካከል ከጀመርኩ ሰነበትኩ። ማስታወቂያዎቹን ግን ሰምቻለሁ። ዘማሪዎቻችን በአንድ ድምጽ ኾነው በአይነቱና ይዘቱ ለየት ያለ ስራ ይዞልን እንደመጣ ምስክርነታቸውን ሲሰጡ ነበር። ለነሱ ዝማሬዎቹ እንዳሉት ኾኖላቸው ይሆናል። እኔ ግን ከሶስት ትራክ በላይ ከሰማሁት ራሴን መበደል ሲመስለኝ መስማቴን ገትቻለሁ። የግድ ወዳጃችን ስለኾ፤ ነግ በኔ በማለት፤ ደግሞም የአገልግሎት አጋርነት (solidarity) ለማሳየት ስንል ብቻ ማበል ተገቢ አይመስለኝም።

ቀላል ማይባሉ ዘማሪዎቻችን በዜማ ድግግሞሽ ይቸገራሉ። አውታሩም በዚህ የተጠቃ ይመስላል። ለምሳሌ በመጀመሪያ የሰማሁት ትራክ "አንድ ቀነ ኾነ" ከ "ምን ልሁና" ዜማው ጋር መሳ ለመሳ ሚሄድ ነው። ቀጥሎ የሰማሁት "የዮሐንስ ወንጌልም" ከዚህ ቀደም ከምናውቀው "ሰው ፊትን ያያል ያያል ቁመት እግዚአብሔር የጠራው በቂ ነው ዳዊት" ዜማ ጋር ቀላል ማይባል ተወራራሽነት አለው። ከኹሉ በላይ ግን የአውታሩ መዝሙሮች ላይ ለመቁጠር ሚታክት የቃላት ደግግሞሽ አሉ። "ወደ ፊት" የሚለውን ስድስተኛ አልበሙን ብቻ እንኳ ላንሳ። የመጀመሪያው ትራክ ላይ ብቻ እንኳ "የኔማ" እና "አገዘኝ" የሚሉት ቃላት ብዙ ጊዜ ይደጋገማሉ። ወደ ፊት ሚለው ሶስተኛው ትራክ ላይ "ወደ ፊት" የሚለው ቃል ብቻ ወደ 30 ጊዜ ተደጋግሟል። ከሁሉ በላይ ግን "እንደ ንስር ወደላይ" በሚለው የአምስት ደቂቃ ዝማሬ ውስጥ "ወደ ላይ" ሚለው ቃል 125 ጊዜ ያክል ሲደጋገም የምር ይሰለቻል።

የአውታሩ የግጥም አወቃቀር በግሌ ስቦኝ አያውቅም። በግጥሞቹ ውስጥም ጥልቅ እውነቶችን አልጠብቅም። የጸጋ ኹሉ ባለቤት በጥንቃቄ በተዋቀረም ሰነፍ በኾነም ግጥም ሕዝቡን ሊባርክ እንደሚችል ባምንም ግጥሞች መደዴ ሲኾኑ እንደ ግለሰብ በግናለሁ። አንድ ቀን ኾነ፥ ኹለት ቀን ኾነ፣ ሦስት ቀን ኾነ ምንም የለም። አራት ቀን ኾነ፣ አምስት ቀን ኾነ፣ ስድስት ቀን ኾነ ምንም የለምን ግን ግጥም አድርጌ ለመቀበል አልፈልግም። የዮሐንስ ወንጌል ላይም ያለው ግጥም አስቂኝ ነው ብዬ ማለፍ ብቻ ነው ምፈልገው።
" አሃሃ የዮሐንስ ወንጌል ምእራፍ አስራ አራት
አሃሃ ቁጥር ስድስት ላይ ያነበብኩት ለት" የሚልን "ግጥም" ገጣሚያን በማይደርሱበት መቀመጥ አለበት ብዬ አምናለሁ። ባጭሩ ቢያንስ እድሜያችን እየገፋ ሲሄድ በአምላካችንም ቤት ዘመን ስንቆጥር ስር እየሰደድን መሄድ ያለብን ይመስለኛል። ቸሩ ይርዳን! የአውታሩ አዲሱ አልበም በሶስት ትራክ ስላደከመኝ ሌሎቹን ለመስማት ፍላጎት አጥቻለሁ። ሳገግም ባይሆን ሌሎቹ ትራኮች ልዩነት ካላቸው አደምጣቸዋለሁ።

ኢብሳ ቡርቃ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

. . . የክርስቶስ ማኅበረ ሰብ የራስ ግንዛቤው እንዲሁም ከእግዚአብሔርና ከሰው ጋር ያለው ግንኙነት ለአንዴና ለዘላላም ተቀይሯል። ማንነቱና ተልእኮው በማይነጣጠሉ መልኩ ሥር ነቀል በሆነ መልኩ በክርስቶስ ለአንዴና ለዘላለም ተቀይሯል!

እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር በገባው ቃል ኪዳን መሠረት፣ በቤዛዊ የድነት ሥራ ውስጥ የእስራኤል ሕዝብ የመሲሑ ዘር ተሸካሚ እንዲሆኑ ከግብፅ የባርነት ቤት ነጻ አወጣቸው። (ዘጸ 2÷24)። ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ የመታሰባቸውና ከፍትሕ የለሽ፣ ጨቋኝና ጨካኝ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘረኛ አገዛዝ ዐርነት የማግኘታቸው ዋነኛ ምክንያት፣ ለእግዚአብሔር የተለየ ሕዝብ በመሆን በጨለማ ላለው ሕዝብ ብርሃን ለመሆን ነበር። ወደ ተስፋዪቱ ምድር ከመግባታቸው በፊት በሲና ተራራ ላይም የተሰጣቸው ዐሥርቱ ትእዛዛት፣ ዐርነቱ ያጎናጸፋቸው ማንነትና (identity) የተቀበሉት ተልእኮ (mission) የማይነጣጠሉ መሆናቸው በአጽንዖት ለማሳወቅ ነበር።

“ከዚያም ሙሴ ወደ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ወጣ፤ እግዚአብሔርም (ያህዌ) ከተራራው ጠራውና እንዲህ አለው፤ “ለያዕቆብ ቤት የምትለው ለእስራኤልም ሕዝብ የምትናገረው ይህ ነው፤ ‘በግብፅ ላይ ያደረግሁትን፣ በንስርም ክንፍ ተሸክሜ ወደ ራሴ እንዴት እንዳመጣኋችሁ እናንተ ራሳችሁ አይታችኋል። አሁንም በፍጹም ብትታዘዙኝና ቃል ኪዳኔን ብትጠብቁ እነሆ ከአሕዛብ ሁሉ እናንተ የተወደደ ርስቴ ትሆናላችሁ፤ ምንም እንኳ ምድር ሁሉ የእኔ ብትሆንም፣ እናንተ ለእኔ የመንግሥት ካህናት የተቀደሰ ሕዝብ ትሆናላችሁ፤’ ለእስራኤላውያን የምትነግራቸው ቃሎች እነዚህ ናቸው።” ( ዘጸ. 19፥1-6)

ግብፃውያንን እንዲሁም ተስፋይቱን ምድር በወረሱ ጊዜ በዙሪያቸው እንዳሉት ሊሆኑ አይገባም፤ ለእግዚአብሔር ተለይተዋልና! “በኖራችሁበት በግብፅ እነርሱ እንደሚያደርጉት አታድርጉ፤ እኔ በማስገባችሁ በከነዓን እንደሚያደርጉትም አታድርጉ፤ ልማዳቸውንም አትከተሉ።” (ዘሌ. 18፥1-3)

በተመሳሳይ መልኩ፣ ይኸው ማንነትና ተልእኮ የአዲሱ የክርስቶስ ማኅበረ ሰብም ነው። ቃሉ እንደሚል፣ “እናንተ ግን ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁ የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ።” (1ጴጥ 2÷9)። የክርስቶስ ማኅበረ ሰብ ፈጽሞውን ለእግዚአብሔር የተለየ ነው። ይህ "ለእግዚአብሔር የተለየ" መሆን ለዓለም ብርሃንና ጨው የመኾን ወይም ያለመኾን ጕዳይ ነው። በእውነት ለእግዚአብሔር የተለየ አማኝ እንደ ዓለም ሊያስብና ሊኖር አይችልም፤ ከእግዚአብሔርና ከሰው ጋር ያለው ግንኙነት ለአንዴና ለዘላላም ተቀይሯልና!

አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደሚደነቅ ብርሃን እንደተጠራ፣ ኹከት፣ የሰላም ዕጦት፣ ብዙ ስብራትና ሐዘን በሞላባት በምድራችን በጎነትህን እንድንናገር እንደተመረጠ ትውልድ፥ ቅይጥነት በበዛበት በዚህ ዘመን ለአንተ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስትህ የተለየ ወገን እንድሆነ አድሰን።

አሜን!

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የመዝሙር ምህዳራችን ቢሰፋስ?
ዝማሬና መንፈሳዊ ቅኔ ለክርስቶስ ማሕበረሰብ ንዋየ ቅዱሳቱ ነው። የአምላኩን ትድግና፣ በክብር ከፍ ማለቱን፣ የመጥራቱንም ተስፋ፣ በቅዱሳንም መካካል ያለን የርስት ባለጠግነት እንዲዘምር በአምላኩ ተጠርቷልና። በዘመናት መኻልም በነበሩት የዜማ እቃዎች የክርስቶስ ማሕበር ይኼን ስርየት፣ ይኼን ተስፋ፣ ይኼን የምስራች ሲዘምር ከርሟል። ስለዚህም እግዚአብሔር ይመስገን።

እርሱ ከጨለማው ስልጣን ስላዳነን፣ የሞትንም ቀንበር ስለ ሰበረልን፣ ወደ ብርሃኑም ስለ መጣን እንዘምራለን። ዝማሬያችንም ዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን ዳስሷል። ግላዊ በኾኑ ፈተናዎቻችንና ድሎቻችን ጉዳይ ዘምረናል። እንደ እምነት ማሕበረሰብ በሕብረት ስለኾነልንም ስለኾነብንም ምስጋናና ምልጃን አቅርበን እናውቃለን። ይኼም ልከኛ ነው ብዬ አምናለሁ። የዚህ ልጥፍ አላማ በዝማሬዎቻችን ሚዳሰሱት ርእስ ጉዳዮች ክበባቸው እንዲሰፋ መሞገት ነው።

ድነታችን ኹለንተናዊ ከኾነ፣ ወንጌላችንም ለኹለንተና የተሰበከ ከኾነ፣ እምነታችንም የማይነካው የኑረታችን ክፍል ከሌለ በዜማ ምናቀርበውም ዝማሬ መዳረሻው ሰፊ መኾን አለበት ብዬ አምናለሁ። ሃጢያት መልኩ ሰፊ ከኾነ( personal, corporate and structural) አልፎም sin of omission እና commission'ን ከጨመረ፤ በውጤቱም ኹለንተናችንን ካንኮታኮተ፤ አምላካችንም በቸርነቱ መድሃኒትን ከላከልን፣ መድኅናችንም በደሙ ከተቤዠንና ለአዲስና ህያው ተስፋ እንደ ምሕረቱ መጠን ዳግም ከወለደን የኑረትን ብዙ ገጾች በዜማችን ለመዳሰስ ምንገደድ ይመስለኛል። ለምሳሌ በሰማያት ያለ አባት አለን እያልን፣ አብ አባት ብለን ምንጣራበት የልጅነት መንፈስም ተቀብለን፣ ከእናትም በላይ አምላካችን ይራራልናል እያልን፣ በማደጎ ቤተሰብ እንድኾን ረድኤታችን ዋጅቶናል እያልን በዝማሬዎቻችን ውስጥ ቤተሰብን አለማንሳታችን ልክ አይመስለኝም። እናት አባትህን አክብር እድሜህ በምድር ይረዝማል የሚልን ግልጽ መመሪያን ይዘን ወላጆችን ስለ ማክበር በዜማ አለማቀንቀናችን ተገቢ መስሎ አይታየኝም። ድነት Ecclesial ብቻ ሳይሆን cosmological ነው እያልን ፍጥረተ ዓለሙ በጭንቅ ስለ መያዙ ደግሞም ስለ ማቃሰቱ ትንፍሽ አለማለታችን የጤና አይደለም። ሰማያት ክብሩን የሰማይም ጠፈር የእጆቹን ስራ በግልጥ ይለፍፋሉ እያልን መደነቂያችን ወደ ጫማ ዝቅ ማለቱ መንሻፈፍ ይመስለኛል። ስለ ብዙ ነገር ቀድመን መዘመር የነበረብን እኛ ነን ብዬ አምናለሁ። በጦርነት በምትታመስ ሀገር እየኖርን፤ ሚያስተራርቁም ብጹአን ናቸው የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉ እያልን ለእርቅ ሚኾን በዜማ የቀረበ ተማጽኖ ከኛ አለመጀመሩ ልክ አይመስለኝም። አምላካችን ለተገፉ ተገን ነው፤ መጠለያ ለቸገራቸው መጠጊያ ነው እያልን በግፍ ለሚሰደዱና ከቀዬአቸው ለሚፈናቀሉ ማጽናኛ ዜማ ከኛ ከአማኞች አለመሰማቱ ጥፋት ነው። ባጭሩ የዝማሬ አድማሳችን ደግሞም ምህዳር ኹለንተናን ሚነካ እንዲኾን መስራት ያለብን ይመስለኛል። በአምላካችን ማዳን ያልተነካ የኑረት ክፍል ሊኖረን አይገባም! ነገ እግዚአብሔር ቢፈቅድና በሕይወት ብንኖር በዚህ ረገድ ፍር ቀዳጅ ናቸው የምላቸውን አንዳንድ ዝማሬዎች አንስቼ ጥዊት እላለሁ። ልኡል አምላክ ለአካሉ መታነጽ ደግሞም ለአደባባይ ምስክርነታችን ያመነውን ኹሉ የምንዘምርበትን፤ መልእክታችንም ሙሉ ሚኾንበትን ጸጋ ይስጠን!

ኢብሳ ቡርቃ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

በየፊናችን የተንታኝ ስብከት ባሕልን እናዳብር

የእግዚአብሔር ቃል በራሱ በቂ ነው የምንል ከሆነ፣ ቃሉ ሲሰበክ መንፈሱ ይሰራል /አይነጣጠሉም/ የምንል ከሆነ፣ ቃሉን በአደባባይ ማንበብ፣ መስበክና ማስተማር የአገልጋዩ ቀዳሚ አገልግሎት ነው የምንል ከሆነ፣ በታሪክ ለቤተ ክርስቲያን ታላላቅ ተሃድሶዎች /መነቃቃቶች/ ምክንያት የሆነው የቃሉ ንባብ /ስብከተ ወንጌል እንደሆነ የምናምን ከሆነ፣ እየተዛለልን የራሳችንን ሐሳብ የምንሰጥበት ስብከትን ትተን ተንታኝ ስብከትን ሙያዩ ብሎ መያዝ አማራጭ አደለም ምርጫ ነው!

በተንታኝ ስብከት ባይሆን ኖሮ የማንሰብካቸውን ምንባባት እንድንሰብካቸው ግድ ይለናል (በተንታኝ ስብከት ዝግጅት ፊት የተቀመጠ የወንጌል ሰባኪ ምንባቡን ሊያመልጠው አይችልም ቃሉ አሽቶ አፍረጥርጦ ሰውየውን መጀመሪያ ይሰራዋል)፣ ስራዓታዊ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ተንታኝ ስብከት የሰባኪውን የነገረ መለኮት እውቀት ያሳድገዋል። ተንታኝ ስብከት ሰባኪ ለሚቀጥለው እሁድ ምን ልስበክ የሚል ጭንቅ የለበትም፣ ተንታኝ ስብከትን ልማድ ማድረግ “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” ብሎ ለመናገር ድፍረት ይሰጣል።

ተንታኝ ስብከት ቃሉ ሲገለጥ መንፈሱ አብሮ እንደሚገለጥ የሚያስተማምን ስብከት ነው። በተንታኝ ስብከት ያሳደግናቸው ደቀ መዛሙርት በቀላሉ ለስሕተት የማይጋለጡና በግል ጥናታቸውም የበረቱ ይሆናሉ። በተንታኝ ስብከት ርእሳዊ ስብከትም መስበክ ይቻላል። (የእግዚአብሔር ፍቅር፣ ፍርድ፣ ምህረት፣ ...ደቀመዝሙርነት...የመሳሰሉት በስብከት መልክ በርእስ ሲቀርቡም የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባቱ ስለእነዚህ ጕዳዮች የሚናገሩትን አስተንትኖታዊ ስብከት እንድናደርግባቸው ግድ ይሏል)።

ይሁን እንጂ ተንታኝ ስብከት ማለት አንድ የተወሰነ ቤተ እምነት በያዘው የአቀራረብ ባሕል፣ ቅርጽ፣ ዘዴ ብቻ መሆን አለበት ማለት አይገባም! ምንባባቱ ሰዋሰዋዊ ታሪካዊና ስነ ጽሑፋዊ ዐውዳቸው ተጠብቆ የጸሐፊው መልክት በሰባኪው መተላለፍ እስከቻለ ድረስ በቅርጹ ሊለያይ ይችላል ብዬ አምናለሁ! ይሁን እንጂ የእውነተኛ ስብከተ ወንጌል ውቅር ምላተ ቃሉን ይዳሣል “የእግዚአብሔርን ምክር ሁሉ ነግሬአችኋለሁና፥ ምንም አላስቀረሁባችሁም።” የሐዋ 20:27 ማለት የሚያስችል፣ ስብከተ ወንጌል ይጠበቅብናል።

መጋቢ ሰሎሞን ጥላሁን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ኢየሱስ ፊቱን ወደ ኢየሩሳሌም አቅንቷል። ተከታዮቹ ፍርሃት እስኪገባቸው ድረስ ፍጥነቱ ጨምሯል “ወደ ኢየሩሳሌም ለመውጣት በመንገድ ላይ ሳሉ፣ ኢየሱስ ፊት ፊታቸው ይሄድ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱ ተገረሙ፣ ሌሎች የተከተሉት ደግሞ ፈርተው ነበር።” (ማር 10፥32)። በማርቆስ ወንጌል ትራኬ ውስጥ፥ ኢየሱስ አንድ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ይወጣል፣ እርሱም ብዙ መከራ ይቀበላል፣ በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በጸሐፍት ይናቃል፣ ይገደላል፣ ከሦስት ቀንም በኋላ ይነሣል። ማቴዎስም ኾነ ሉቃስ ይህንን የማርቆስን ትራኬያዊ አቅጣጫ በቅርበት ይከተሉታል። ነቢዩ ኢሳያስ “የጌታን መንገድ አዘጋጁ” እንደሚል፣ ይህ መንገድ ተጠርጓል፣ ጌታም እየተራመደበት ይገኛል። ይህ ሥጋ ለባሽ ኹሉ ወደ ሚመለከተው ክብር የሚወስደው መንገድ የሚያመራው ወደ ቀራንዮ ጎልጎታ ነው።

ታዲያ፣ኢየሱስ በዚህ መንገድ ላይ ሳለ ፦

  1. ሶስት ጊዜ ስለ መከራው፣ ሞቱና ትንሳኤው አስቀድሞ ይተነብያል (ማር 8፥31፣ 9፥31፣ 10፥33-34)።

  2. ሶስቱንም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ለዚህ ትንበያ ምላሽ ይሰጣሉ (8፥32፣ 9፥33-34፣ 10፥35-41)። ሆኖም ግን የሚሰጡት ምላሽ የእርሱን ተልዕኮ እንዳልተገነዝቡ ያሳያል። ጴጥሮስ ኢየሱስን “ይገሥጸው ጀመር” (8፥32)፣ ሐዋርያት “ከሁሉ የሚበልጥ ማን ነው” እያሉ ይከራከራሉ (9፥34)፣ የተወሰኑትም “በክብርህ ጊዜ አንዳችን በቀኝህ፣ አንዳችን በግራህ እንድንቀመጥ ፍቀድልን” የሚል ጥያቄ ያቀርባሉ፣ ይህንን ያደመጡም በመቀደማቸው ይቆጣሉ (10፥37)።

  3. ሶስት ጊዜም ኢየሱስ እርሱን መከተል ምን ማለት እንደኾነ የደቀ መዝሙርነትን ምንነት እየገሰፀ ያስተምራቸዋል (8፥34-37፣9፥35-37፣ 10፥42-45)። ዐይነ ስውሩን ሁለት ጊዜ እደፈወሰው (8፥22-26) ደቀ-መዝሙርቱም እንዲኹ ሁለት ጊዜ መዳሰስ እስኪያስፈልጋቸው ድረስ ታውረዋል፣ ልባቸው ደንዝዟል። የኢየሱስ ተልእኮ አልገባቸውም ነበር።

1. “ሊከተለኝ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ” (8፥34)

2. “መጀመሪያ ለመሆን የሚፈልግ፣ ከሁሉ መጨረሻና የሁሉም አገልጋይ ይሁን” አላቸው” (9፥35)

3. “ከመካከላችሁ ታላቅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋይ ይሁን፤ 44ፊተኛ ለመሆን የሚፈልግ ሁሉ፣ የሁሉ ባሪያ ይሁን፤ 45የሰው ልጅ ሊያገለግልና ሕይወቱን ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ ሊሰጥ መጣ እንጂ ሊገለገል አልመጣምና።” (10፥43–45)

እንዳንዘነጋ፣ ይህ ቀን ክርስቶስ ስለ ኀጢአታችን ቤዛ የኾነበት ቀን እንደኾነ ኹሉ፣ የእርሱን ፈለግ የምንከተልበትም ቀን ነው።

ኢየሱስ ሞቶ ከተነሣ በኋላ፣ እነዚህ ደቀ መዛሙርት የደቀ መዝሙርነት ትርጕም ገባቸው። ከራሳቸው በላይ ዝቅ ብለው ሌሎችን አገለገሉ። አልፎም እነርሱም እንደ ጌታቸው ለመሰቀል፣ ለመሠየፍና ለመወገር ፈቃደኞች እስኪሆኑ ለሌሎች ኖረው አለፉ።

የማርቆስ ጥያቄ አሁን ያነጣጠረው በእኛ ላይ ነው! ተልእኮው ገብቶናል? የደቀ-መዝሙርነት መንገዱ ገብቶናል? ግን ገብቶናል?

የማርቆስ ግሣጼ፣ ኢየሱስ ‘ተልእኮው ያልገባቸው ተከታዮች የሉትም’ የሚል ነው።

ሳምሶን ጥላሁን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

መስቀሉ- መግቢያም መሰንበቻም

ሰው በኅጢአቱ አመጽ ምክንያት ሙት ነው። አመጻው ሰው መሆኑን አጉዱፎበታል። በአንዱ መሳት መላው የአዳምና የሔዋን ዘር በሙሉ በኅጢአት ተበክሏል። ከፈጣሪው ጋር ተለይቷል። ኅጢአት የሰውን ተፈጥሮ በክሎታል። ሰላሙን ነስቶታል። ለዚህም ነው ኅጢአት የፍጥረተ ዐለሙ ነውጥ ነው የሚባለው።

ውድቀት ከአምላኩ ጋር የነበረውን ኅብረት አጥፍቶበታል። ከወንድሙ/እህቷ ጋር የነበረውን የግንኙነት መረብ በጥሷል። ከተፈጥሮም ጋር ያለው መስተጋብር ተበላሽቷል። የገባበት የጨለማ ጥልቀት በምንም የሚገለጽ አይደለም። ሰው ከአምላኩ ፊት ከወጣበት ቅጽበት ጀምሮ የተሰበረ ሆኗል፣ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ሕይወቱ ስምረት አልባ ነው።

የኅጢአቱ ጣር በያዘው ዐለም ውስጥ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን በመላክ ስቃዮን በአካሉ ተካፍሎ ሕማሙንም ተጎንጭቷል። እግዚአብሔር በሕማሙ ለታፈነው ዓለም ሩቅ አልነበረም። ሰው የአመጻው ጥልቀት ባስገኘለት የጭካኔ መንገድ በመሞት አመጻውን አስወገደ።

መስቀል በወቅቱ የነበረው የመጨረሻው አሰቃይቶ መግደያ ነበር። በአይሁድ ሕግም ሆነ በአሕዛብ መርሕ የመስቀል ሞት ቅቡል አይደለም። መስቀልን አይሁድ እርግማን አድርጎ ሲቆጥረው አሕዛብ ደግሞ ሞኛ ሞኝነት ያደረገዋል። ይህንን የውርደት መንገድ ግን ጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መረጠ።

ዐለምን ይቤዠው ዘንድ የመጨረሻውን አዋራጅ ሞት በመሞት በአመጻው ዳፋ ከአምላኩ የራቀውን ሰው አስታረቀው። የወንጀለኞች አውራ በሚቀጣበት መስቀል ላይ በመዋል "ከኅጢአታችን ሁሉ በደሙ አጠበን"።

አሁን እንደ ጌጥ የምንጠቀምበት መስቀል ለመጀመሪያ ክፍለ ዘመን ነዋሪዎች የሚሰጠውን ሰቅጣጭ ምስል ማሰብ አስፈላጊ ነው። ከመስቀል ጭካኔ ባሻገር መስቀልም ሆነ መሰቀያው ስፍራ ውብ አይደሉም። እንደውም መሰቀያ ስፍራው ተሰቃዮች በመስቀል በሚደርስባቸው መከራ የተነሳ ራሳቸውን መቆጣጠር ስለማይችሉ ክርፋቱ አያስቀምጥም። ሞተው እዛው የተቀመጡ የሬሳዎች ሽታም ያለበት ስፍራ ነው። ለዐይንም ሆነ ለፍንጫ የማይሆን ነው። ሰዎች አይደለም ሊቀርቡት ይቅርና ሊያዮት የሚፈልጉት አይደለም። ክርስትና ምልክቴ ያለው ይህንን ነው። የእግዚአብሔር ኅይል ነው ተብሎ የተጻፈው ይህ መንገድ ነው።

የቤተክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊው ብሩስ ሼሊ ክርስትና የክርስቶስ ኢየሱስ የመስቀል ሞት ላይ ሙጭጭ ማለቱን ለማስረዳት «የአምላኩን ውርደትና ፍዳ በማጠንጠኛነት የያዘ ብቸኛው እምነት ክርስትና ነው» ይላል። በዚህ በውርደትና ፍዳ በሞላበት የመስቀል መንገድ ወልድ ከአብ ጋር አስታረቀን። ሮማውያን በዜጎቻቸው ላይ እንዳይፈጸም ብሎም እንዳይታሰብ በህግ በደነገጉት የመስቀል ሞት እግዚአብሔር ራሱን በመስቀል ገለጠ።

ከተሰቀለው መሲሕ መኸከለኝነት ውጪ የሚገኝ ክብር የለም። ሐዋርያቱም ደጋግመው ደብዳቤ ሲልኩ "ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱም እንደተሰቀለ ሆኖ አይናችሁ ስር እንዲሳል" እንጂ ለሌላ ነገረ መለኮት ትኩረት ያልሰጡት። ይህ የተሰበረው ዐለም አለኝ በሚለው የመጨረሻ እኩይ እግዚአብሔር መንግሥቱን ያበሰረበት መሆኑን አጽንኦት ችረውታል።

መስቀል ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መዝለቂያ ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር መንግሥት መሰንበቻም ነው። መስቀል እዳ ሁሉ ተጠርቆ የተወገደበትን፣ የእግዚአብሔር የዘላለም የትድግና እቅድ የሰመረበት ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን ግን በመስቀል አማከኝነት ከእግዚአብሔር ጋር እርቅ በመፈጸም የእግዚአብሔር ቤተሰብ የሆነው ሰው መመሪያውና የኑሮ ቀመሩ መስቀል ነው። መዳኛችንም በመንግሥቱ ውስጥ መኖሪያችንም ነው።

እግዚአብሔር ለመላ ዐለሙ የቀጠረው ቀን ሲመጣም በግ-አንበሳው ድል ነሺው ጌታችን ኢየሱስ ድል የመንሳቱ ነጻብራቅ ይኸው የመስቀሉ ገድል ነው። በመስቀሉ የተጀመረው የእግዚአብሔር መንግሥት ብስራት የሚጠናቀቀውም በመስቀሉ በተደረገው ሥራ ነው።

ያለስቅዮው ሎሌና መሲሕ የሚገኝ ክርስትና የለም። የክርስትና ልበ ምቱ ይህ ስቃይና መከራ ነው። ሁሉም ነገረ ክርስቶስ መስቀሉን ከመፈከር ካልጀመረ ክሹፍ ይሆናል። "ሞቱን አስታውሱ" የተባለው ትርጓሜው ጥልቅ፣ ለምንኖረው ክርስቲያናዊ ሕይወት ማጠንጠኛ ነው።

ጌታችንና መድኅኒታችን ሆይ፥ ክርስትና ያለ ኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ላይ ፍዳ እንዳይታየን አይናችንን አሳውር። በመስቀሉ ላይ በመገፋት ከሞተው፣ መልኩን የመከራ ብዛት በደም ካጨቀየው እና የተሰበረ ዐለምን ይዋጅ ዘንድ በሕማም ከተሰበረው እውነተኛ ፍቅር እንዲይዘን እርዳን። ስቅዮውን ክርስቶስ ብቻ አሳየን፣ በ'ሱ እግዚአብሔር እግዚአብሔርን ገልጧልና፤ የመገለጥ ሙላት ተከናውኗልና። እንደ ክርስቶስ መውደድን አስተምረን። አሜን!

አማኑኤል አሰግድ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

----------------------------------------
  “የመስቀሉንም ውርደት ንቆ በእግዚአብሔር
   ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአል” (ዕብ 12:2)
----------------------------------------

2. አቤት የውርደት ቀን - በውርደት የተከወነ ስርየት

ስለ ክርስቶስ መከራ ስናንስብ ወደ ልባችን ፈጥኖ የሚመጣው የተቀበለው ሥቃይ ነው። እውነት ነው። ከዚህ በኋላ የምጽፈው ነገር የሞቱን አሠቃቂ ሥቃይ በምንም መልኵ አይቀንሰውም። ግን ከሥቃዩ አንድ ክፍል የኾነውን የዘነጋነው ይመስለኛል። የተሰቀለበት ቀን ታላቅ የውርደት ቀን ነበር።

ጌታችን ኢየሱስ በምድራዊ አገልግሎቱ በሰዎች መሰደብና መዋረድ ይባስም ብሎ “ብዔልዜቡል ያለብህ” እስከ መባል መድረስ ለእርሱ ብርቅ ነገር አልነበረም። ሆኖም ይህች ከዕለታት አንድ ቀን የነበረችው አርብ ግን፥ ከሌሎች አርቦች ሁሉ የተለየች የውርደት ቀን ነበረች። በዚህች ቀን ላይ እንደ ደረሰበት ያለ ውርደት ደርሶበት አያውቅም። ውርደቱ የቤዝዎታዊ ሥራው ገጽታ ነው እያልኳችሁ ነው።

አዲስ ኪዳን በበቀለበት በሜድትራኒያኑ ባህል ውስጥ፥ ውርደትና ከበሬታ (Honor and Shame) የሞትና የሕይወት ጕዳይ ነበር። ዲሲልቫ የተሰኘ ጸሐፊ (David deSilva) እንደሚነገረን ከኾነ፥ በዚህ ባህል ውስጥ የተገኘ አንድ ወጣት የሚጠበቅበት ግዴታ ውርደትን በማስወገድና ክብርን በመፈለግ የማኅበረሰቡን እሴት መላበስ ነው። ከዚህ የተነሣ፣ ውርደት በምንም ዓይነት ዐውድ አግባብነት አልነበረውም። እንዲያውም ከሞት የከፋ ነገር ቢኖር ውርደት በመኾኑ ‘ከመዋረድ ይልቅ መሞት ይሻላል’ ይሉ ነበር። ለምሳሌ ዕውቍ ሰኔካ እንዲህ ይላል፦

“የተከበረው ነገር የተከበረ ነው የምንለው የተከበረ ስለሆነ እንጂ በሌላ ምክንያት አይደለም” (that which is honorable is held dear for no other reason than because it is honorable”።

በዚህ ባህል ውስጥ፣ ከበሬታ በራሱ የሚፈለግ እሴት ነው። በአንጻሩ ደግሞ፣ ውርደት እስከ ሞት ድረስ እንኳ መፋለም ያስፈልጋል። ብሂሉ “ከምዋረድስ ልሙት” ነው። ለዚህ ነው፣ በዚህ ባህል ውስጥ ያሉ አባቶችና እናቶች በማኅበረሰቡ ዘንድ ተዋርደው ከመገኘት ይልቅ ልጆቻቸውን መግደል የቀለላቸው። ከበሬት-ውርደት እውን ኀይል ነው።

እናም፣ እያንዳንዱ ባህል ‘መዋረድ ይገባዋል’ ብሎ የፈረጀበትን ሰው ለማዋረድ የሚጠቀማቸው ግልጽና ስውር ስልቶች አሉት። ከእነዚህ መካከል ለምሳሌ ያህል፣ ጭንቅላትን መምታት አንዱ ነበር። ፊትን በጥፊ ማጮል፣ ጭንቅላትን በዱላ መቀጥቀጥ ተመቺውን ከክብር ያዋርዳል። በኢየሱስ ላይ፣ የሰውን ክብር የሚገፉ አዋራጅ ተግዳሮቶች በሙሉ በዚህች ቀን ደርሰዉበታል። ይህች ቀን ለጌታችን ታላቅ የውርደት ቀን ነበረች!

“ከእሾህም አክሊል ጎንጉነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፥ በፊቱም ተንበርክከው። የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን እያሉ ዘበቱበት፤ 30ተፉበትም መቃውንም ይዘው ራሱን መቱት። 31ከዘበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፥ ልብሱንም አለበሱት ሊሰቅሉትም ወሰዱት።” (ማቴ 27:29–31)።

አቤት አዋረዱት። የኛ ክብር ዕንቍ በአፈር ላይ አንደበለሉህ፣ ረገጡህ፣ ተፉብህ፣ ልብስህን ገፈው ዕርቃንህን ገለጡ፣ ለንጉሥ እንደሚሰገድ እየሰገዱ አላገጡብህ፣ አሾፉብህ። አንተም ዝም አልህ። የውርደትን ጽዋ ጨለጥኻት። የኔ ውብ! የኔ ትሁት። ይህ ሁሉ እኮ ለእኛ ነው! ተዋርደህ የተዋረደውን ሰው አከበርህ። ያዋረዱህን አከበርህ። የውርደትን ጥግ ነክተህ፥ ክቡር ሥጋህን እንመስል ዘንድ እጩዎች አደረግኸን። ምስጋና ይግባህ እንላለን!

በርግጥ ጳውሎስ ሰው ኾኖ መገለጡ በራሱ ውርደት ሆኖ ሳለ፥ ኢየሱስ የወረደበትን የውርደት ልክ ሲያመላክተን እንዲህ ይለናል፦ የባሪያን መልክ ይዞ “እስከ ሞት፣ ያውም በመስቀል ላይ እስከ መሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ”። ከክብር ልእልናው ወርዶ፥ ኀጢአተኞች በዐመጽ በጸቀየ እጃቸው ንጹሁን እርሱን እንዲያዋርዱት ፈቀደላቸው። እኛ ያንተን ያኽል ክብር የሌለን በአንተ የደረሰው ውርደት አንዲቷ እንኳ ብትደርስብን፥ አምባጋሮውን ማን ይችል ነበር?

የእብራውያንም ጸሐፊ እንዲኹ፣ ኢየሱስ የደረሰበትን መከራ ‘ውርደት’ በማለት ይገልጠዋል፦ “ኢየሱስን እንመልከት... የመስቀሉንም ውርደት ንቆ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአል” (ዕብ 12:2)። እኛም የተጠራነው የእርሱን ፈለግ ልንከተል ነው። ስለዚህ ስለ እርሱ መመስከር ውርደት ሳይኾን ክብር ነው “በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፣ የሰው ልጅም በአባቱ ግርማ፣ ከቅዱሳን መላእክት ጋር ሲመጣ ያፍርበታል” (ማር 8:38)። “ስለ ጌታችን ለመመስከር ወይም የእርሱ እስረኛ በሆንሁት በእኔ አትፈር” (2 ጢሞ 1:8)።

ይህንን ውርደት ከመስቀሉ ላይ አንስተን፥ ኢየሱስን ዝነኛ ልናደርገው አንችልም። መልካሙ ዜና ውርደትን ገንዘቡ ያደረገ ነው። የምናመልከው ጌታ የተሰቀለ-ክርስቶስ ነው። ይህ ለሰው ጥበብ አይመችም። ለሥጋችን አይመችም። ይህ የኢየሱስ መስቀል ለዚህ ዓለም ገዢዎች አይመችም። ስለዚህ ነው፣ ‘ኢየሱስ አይፖተለክም’ ወይም ድምፅ መስጫ ሳጥን ለማግኘት ሲባል ለፖለቲካ ፍጆታ አይውልም የሚባለው። መንገዱ እጅግ ጠባብ ነውና። ማንም ሊከተለኝ የሚወድ ‘መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ’ አይደል ያለው? ስለዚህ በእነዚህ ቀናት የኢየሱስን ውርደትና ክብር እናውጅ።

በመጨረሻም የእብራውያን ጸሐፊ እንዲህ እያለ መልእክቱን ይዘጋል፦

“እርሱ የተሸከመውን ውርደት ተሸክመን ከሰፈር ውጭ ወደ እርሱ እንውጣ። ምክንያቱም በዚህ ቋሚ ከተማ የለንም፤ ነገር ግን ወደ ፊት የምትመጣዋን ከተማ እንጠብቃለን።” (ዕብ 13:13–14)

የህማማቱ ሰሞን
_____
[1] David A. deSilva, Honor, Patronage, Kinship & Purity: Unlocking New Testament Culture (Westmont, IL: InterVarsity Press, 2012), 22–23.

ሳምሶን ጥላሁን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

1. 27፡32-44፡ ስድብን የጠገበው፥ መስቀለኛው ንጉሥ

ከአልበርት አንስታይን አጠገብ የተቀመጠ አንድ ተማሪ አንስታይንን “ምን እያጠናህ ነው?” ብሎ ይጠይቀዋል። አልበርት አንስታይንም “የፊዝክስ ተማሪ ነኝ” ብሎ ይመልስለታል። ከዚያም ያ ተማሪ “ኦ ፊዚክስ... እኔስ ባለፈው ዓመት አጥንቼው ጨርሻለሁ” አለው ይባላል። ይህ ምልልስ ምጸት አዘል የሚኾነው ታሪክን የኋሊት የሔድን እንደኾን ነው። አንስታይን ፊዝክስን ማጥናት ብቻ ሳይኾን ራሱ ፊዝክስን ለውጦታልና።

ልክ እንዲሁ፥ ኢየሱስ ሲሰቀል አራት ቡድኖች አንገታቸውን እየነቀነቁ ይሳለቁበት እንደነበር ማቴዎስ ከቍ.32-44 ባለው ያስመለክተናል።

1. 27፡27-31 በሮማውያን ወታደሮች ተሰደበ
  የእሾህ አክሊል ደፍተው የአይሁድ ንጉሥ እያሉ አሾፉበት (ቍ. 29)

2. 27፡27-31 በአላፊ አግዳሚው ሕዝብ ተሰደበ
  [ሕዝቡ] በኀይል እየተሳደቡና ራሳቸውን እየነቀነቁ አሾፉበት (ቍ. 40)

3. 27፡41-42 በአይሁድ መሪዎች ተሰደበ
  የካህናት አለቆች፣ ጸሐፍትና የአይሁድ ሽማግሌዎች አሾፉበት "ሌሎችን አዳነ፥ ራሱን
  ሊያድን አይችልም፤ የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ፥ አሁን ከመስቀል ይውረድ... በእግዚአብሔር
  ታምኖአል... ከወደደውስ አሁን ያድነው" (ቍ. 42-43)

4. 27:43 አብረውት በተሰቀሉ ወንበዴዎች እንዲሁ የስድብ ናዳ ያወርዱበት ነበር

ይህንን እኔ ብቻ ያየሁት አይደልም፣ ብዙ የአዲስ ኪዳን ነባብያን ያስተዋሉት ጉዳይ ነው። እኛም ከትንሳኤው፣ ዕርገቱና በአብ ቀኝ መቀመጡ ባሻገር ያለን ታሪክን የኋሊት ስንቃኝ፥ ማቴዎስ እንድንመለከት የሚፈልገውን ምጸት እንመለከታለን።

► “ንጉሥ ከሆንክ ከመስቀሉ ውረድ?” አሉት? ንጉሥ ቢኾንሳ፣ ጭራሽ እንዲያውም በመስቀሉ እየነገሠ ቢኾንስ?

► “እስቲ ራስህን አድን?” አሉት? አዳኝ ቢኾንሳ? ጭራሹንም ከመስቀሉ ባለመውረዱ ቢኾንስ ድነትን የሚፈጽመው? ይባስ ብሎም፣ መስቀሉ ወደ ምጡቅ ዙፋን የሚወጣበትና “ባሪያዬ እጅግ ከፍ ከፍ ይላል” እንደሚል የሚነግሥበት መንገድ ቢኾንሳ?

አይ ሰው! ሰው ሆይ፥ ከጥበብህ በላይ “የእግዚአብሔር ሞኝነት ይጠበባልና፥ የእግዚአብሔርም ድካም ከሰው ይልቅ ይበረታልና።” (1 ቆሮ. 1:25)

“የጌታን ልብ ማን አውቆት ነው? እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።” (1 ቆሮ. 2:16)

የህማማቱ ሰሞን

ሳምሶን ጥላሁን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

"እኔ እስክመጣ ድረስ ለማንበብ [ልታነብላቸው]፣ ለመምከርና ለማስተማር ትጋ" (1 ጢሞ 4፡13)

ከወደቅንባቸው ታላላቅ ነገሮች መካከል ብዬ ከማስባቸው አንዱ፣ የቅዱሳት መጻሕፍትን ንባብ «የግል መንፈሳዊ ልምምድ» ብቻ ማድረጋችን ነው። እንደ ክርስቲያናዊ ማኅበረብ፣ የኅብረት ጾም፣ የኅብረት ጸሎትና አምልኮ እናደርጋለን። እንደ ክርስቲያናዊ ማኅበረሰብ ግን በጉባኤ ረጃጅም የቅዱሳት መጻሕፍትን ንባባት የማንበብ ልማድ (public Scriptural reading) ግን አላዳበርንም። ይህ በመንፈሳዊ ሕይወታችን ላይ ያስከተለው አያሌ ጉዳት ያለ ይመስለኛል። ዕዝራ "ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው ድረስ፣ ዕዝራ በየዕለቱ ከእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ ያነብ" ነበር። ጳውሎስም ለሌሎች ያስነብብ ነበር። ኢየሱስ በሙኹራቦቻቸው መጻሕፍትን ያነብ ነበር። አቡቀለምሲሱ ዮሐንስ ጠቅላላ የራዕዩን መጽሐፍ ለታዳሚው "የሚያነብ ብፁዕ ነው" ይላል፤ "የሚሰሙትም የሚያደርጉትም ብፁዓን" ናቸውም ብሎናል።

እውነት ነው፣ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ቅዱሳት መጻሕፍትን ከሞላ ጎደል በግል ማንበብ እድል ስላልነበራቸው (በዋነኝነት የግል ቅጂ መያዝ እጅግ ውድ በመሆኑ፣ አንዳንዱም ማንበብ ስለማይችሉ) በጉባኤ እንዲነበብ መታዘዙ የግድ ነው። ግን ይህ ብቻ ነው ብሎ ለመስውሰድ ያዳግተኛል። ሲጀመር፣ ብዙዎቻችን በግል ዲሲፕሊን ኖሮን ለማንበብ የምንቸገር ስንት ነን? የቃሉስ ንባብ "በግልህ ብቻህን የምትጋፈጠው እንጂ የጉባኤ ልማድ አይደለም" ብሎስ ማን አዘዘን? ይህን ስል በግል ቅዱሳት መጻሕፍት ማንበብና ማሰላሰል (Personal Bible reading) «ጣል፡ ጣል እናድርግ» እያልኩ አይደለም። ተቃራኒውን እንጂ። እንደ ሕዝብ አንድን ንባብ አንብበን፣ መንፈስ ቅዱስ እንደ አንድ ሕዝብ ቢመክረን፣ ቢገስጸን፣ ቢናገረን...አንዳንዴ በሳቅና በእንባ...አንዳንዴም ተንበርክከን ቃሉ እንደ ወንዝ ቢፈስ፣ ምን አለበት ግን? ሁለት ሰዓት ቁጭ ብለን ፊልም እያየን? አራት ሰአት "በቢንጅ" ተከታታይ ፊልም እያየን? ሦስት ሰአት አምልኮ በፉጨት እየዘመረን? ምን አለበት? ግን ደግሞ ወደ እግዚአብሔር «ኧረ ጠፋን መልሰን!» ብለን እንጮኻለን አይደል? መጮኹስ አይቅር። አብዝተን እንጩኽ። ግን ሠይፍ የሆነውንና ኀያል-ቃሉ እየተደመጠ ብንጮህ እንደቃሉ ቃሉ ይሠራል። በምስባኮቻችን «አንድም ቀን ተነበው የማያውቁ የቅዱሳት መጻሕፍት ንባባት አሉ» ብላችሁ ታምናላችሁ? ተነበው ያልተመከርንባቸው፣ የልተገሰጽንባቸውና ያልተጽናናንባቸው አያሌ ምንባባ አሉ ብላችሁስ! አታምኑኝም። ይህ የኔ ብቻ ልምምድ ነውና። እግዚአብሔርም ያድርገው። ይህ የኔ ብቻ ገጠመኝና ቅዠት ሆኖ እኔ በጠፋሁ። እኔ ውሸተኛ በሆንኩ። ግን ከዚህ ቅዠት አልነቃ አልኩ።

የሮሜ ደብዳቤ እኮ፣ በአንድ ቁጭታ ነበር ለጉባኤው የተነበበው። እውነት ነው ምናልባት አገልጋይቱ ፌበን አሊያም የቤተ ክርስቲያኑ መሪዎች ለረጅም ሰዓታት፣ በተከታታይ ሰንበት ለሕዝቡ እየተነተኑ ማብራሪያ እንደሰጡ ጥርጥር የለውም። ግን የ16ቱ ምዕራፍ ንባቡ አላጠረም:: እናም፣ የቃሉ ንባብ ጋር ስንመጣ ረጅም ንባብ አይደብረን። ለምን በስቅለቱ ሰሞን ወንጌላት አይነበቡም? ቢያንስ ኢየሩሳሌም ከገባበት ቀናት ጀምሮ እስከ ስቅለቱ የወንጌል ትራኬ በጉባኤ ቢተረክልን ምናለበት? ቁጭ ብለን። ተንበርክከን። ቆመን። ደግሞ እሁድ የትንሳኤውን ንባባት፣ እያጨበጨብን!

ማን ነው የቃሉ አገልግሎት በ30-40 ደቂቃ ስብከት ብቻ ይወሰን ያለን? ማለቴ፣ እንዴት በሳምንት በ30 ደቂቃ ሕዝብ እንዲለወጥ፣ የአስተሳሰብ ተሓድሶ እንዲመጣ እንጠብቃለን? ምንስ እንደዚያ ይመጣል? ሕዝብ እንዲያ ተለውጦ ያውቃል? አድማሳዊ የሆነ (የፓራዳይም) ለውጥ በቅጽበት መጥቶ ያውቃል? ግን ደግሞ "ጸጋው" ጎደለብን አይደል? ለመቆም ጉልበት አጣን፣ ኀጢአት በላይና በታች አወከን አይደል? የስህተት ትምህርት በግራና በቀኝ አጣፋን አይደል? ላዩም ጆሯችን ጭው እስኪል ድረስ። ልጆቻችን እንግዳ ልምምድ ውስጥ ገቡ አይደል? ግራ ተጋባን! ይህ ሁሉ በጉባኤ ንባብ አይፈታም። መች በቀላል። ግን ወደ መሠረታዊውና ወደ ዋነኛው መመለስ፣ የት እንደወደቅን አውቀን ወደ ሚበጀን መመለስ ጥበብ ይመስለኛል። ደግሞስ "ሊያንጻችሁና በቅዱሳኑ ሁሉ መካከል ርስት ሊያወርሳችሁ ለሚችለው ለጸጋው ቃል ዐደራ" ሰጣቸው (ሐዋ 20፡32) ሲል፣ ቃሉ ጉልበት እንዳለው ታሳቢ ያደረገ ነው አይደል? እንደ ጉባኤ አንድን ነገር ሰምተን፣ ተመሳሳይ ምላሽ ለቃሉ ስንሰጥ እድገታችንም እንዲሁ ብስለታችንም እንዲሁ እያደገ የሚመጣ ይመስለኛል።

ጳውሎስ በአንድ ከተማ ለጥቂት ሳምንታት ቢበዛ ለጥቂት ወራት ነበር ሰብኮ፣ ቤተ ክርስቲያን ተክሎና መሪዎችን ሾሞ የሚሔደው። ለምሳሌ በተሰሎንቄን የነበረው ቆይታ ቢያንስ ለሦስት ሰንበታት ወይም ቢያልፍ ጥቂት ሳምንታት ነበር (ሐዋ 17፡2-10)። ከኤፌሶንና ከቆሮንቶስ በስተቀር ይህ ልማዱ ነበር። ግን ምን ያህል በየዕለቱ የትየሌለ የሚያህል የብሉይ መጻሕፍትን (ከሰብዓ-ሊቃናቱ? ወይም መሰል የግሪክ ትርጉም?) ቢያነብላቸው ይሆን፣ በመልእክቱ ሁሉ ከልጅነታቸው ጀምሮ ብሉይን እንዳነበቡ ሰዎች የሚጽፈው። የገላትያን መልእክት ተመልከቱ። እነዚህ ሰዎች ብሉይ ንባባትን ከልጅነት ጀምሮ የሚያውቁ እንጂ ለአፍታ ከጥቂት ጊዜ በፊት አብርሃም የሚባል ሰውና የድነቱን ትራኬ፣ ኢሳያስ የተባለ ትንቢትና የትድግናውን ተስፋ (ከነትንታኔው) የማያውቁ እንደነበሩ የሚጠቁም የለም። በተጨማሪም፣ ለከፍ አድርጎ የሚያልፋቸው፣ ብሉይን ንባባት አስደምመው (allusions) የሚያልፉ ጽሑፎቹ፣ ከአንባቢያኑ ምን ያህል የብሉይ ንባባትን እውቀት እንደሚጠብቅ ያስረዳል። እነዚህ ሰዎች በአጭር ጊዜ በቅዱሳት መጻሕፍት ባህር ውስጥ እንደሚዋኙ ሰዎች ነበር የሞገታቸው። ምን እያልኩ ነው? የቅዱሳት መጻሕፍት ንባባት የመጀመሪያይቱ ቤተ ክርስቲያን ልማድ ነበር።

በጉባኤ ማንበብ ግን ብቸኛ አማራጭ አይደለም። ዛሬ ዙም አለ። ስልክ አለ። በአካል የሚገኝ በአካል፣ ካልሆነም በርቀት ቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ጉባኤ ማንበብ ይቻላል። የግድ በሰንበት ስብስባችን መሆን የለበትም። ዋናው ቁም እንደ ጉባኤ በአንድነት መነበባቸው ላይ ነው። የዚያን ጊዜ አንድ ነገር ይሆናል። በስብከት እንዲተጋ የእግዚአብሔር ጸጋ የበዛለት "በዚህ ቃል እስኪ አበረታታንና ምከርን" ሕዝብ ይላል። በማስተማር የሚተጋውን "እዚህ ጋር ጥያቄ አለን፦ በዚህ ንባብ ጸሐፊው 'ምን ለማለት ፈልጎነው' ተንትነህ አስረዳን" ጉባኤው ይጠይቃል። የጸሎት ኮረንቲ የሚያቀጣጥለውም፣ "ኧረ በዚህ ቃል ላይ እንጸልይ" ይላል። የቅኔው ሰውም፣ ቃሉን በዜማ ቅኔ አድርጎ ይዘርፈዋል። ተሓድሶ ዝም ብሎ አይመጣም። ለመታደስ ማደስ ያሉብንም ነገሮች አሉ። ከእነዚህ መካከል፣ በዋነኛነት፣ የቃሉ ንባብ ወደ ሕዝበ ክርስቲያኑ መመለሱ ነው።

ጌታ ሆይ ከቃልህ ረሃብ፣ ቃልህን ወደ መራብ አምጣን!

"ነገር ግን እኔ ወደዚህ፣
ትሑት ወደ ሆነና መንፈሱ ወደ ተሰበረ፣
በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ።" (ኢሳያስ 66:2)

ሳምሶን ጥላሁን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

"ዩቲዩበሮች" ወይስ "ክርስቲያን ጋዜጠኞች"

ጋዜጠኝነት የተከበረ ሙያ ነው። በተለይ ክርሰቲያናዊ ጋዜጠኝነት ደግሞ ለምድራዊው ሳይሆን ለእግዚአብሔር መንግስት መስፋት የሚተጋ ስለሆነ እጅጉን የተከበረ ሙያ ነው። እንዲያውም አንዳንዶች ክርሰቲያን ጋዜጠኛ የክርስቶስ መስቀል መልዕክተኛ ስለሆነ "የመስቀሉ - ሚዲያ" (Cross - Media) ተብሎ መጠራት አለበት እስከ ማለትም ይደርሳሉ (ሙያውን ከፍ ሲያደርጉት)።

ነገር ግን ክርስቲያናዊ ጋዜጠኝነት በትክክለኛው "ተልዕኮ" ካልተቀነበበ የእግዚአብሔርን መንግስት ሳይሆን ግለሰቡን ብቻ ነው የሚጠቅም ይሆናል። ለመሆኑ የክርሰቲያን ጋዜጠኛ ተልዕኮ ምንድነው?

1. ክርስቲያናዊ እውነትን መግለጥ

በ2011 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) የዓለም የጋዜጠኝነት ተቋም (World Journalism Institute) ዳይሬክተር የነበሩት ሮበርት ቤዝ (Robert Base) ስለ ክርሰቲያናዊ ጋዜጠኝነት ተልዕኮ ሲናገሩ "የክርሰቲያን ጋዜጠኞች ተልዕኮ በየሚዲያው የሚነገረውን የተሸቀጠ መረጃ የሚያጠራውን 'ክርሰቲያናዊ እውነት' መፈለግ ነው" ይላሉ። እኒሁ ሰው ጨመር አድርገው ክርሰቲያን ጋዜጠኞች በተልዕኳቸው "የተረጋገጠ ክርስቲያናዊ እውነት እንዲገለጥ የሚተጉ ናቸው" ይላሉ።

ከሮበርት ትንተና ተነስተን በሀገራችን የሚገኙትን በተለይ በማህበራዊው ሚዲያ ላይ (በዩቲዩብ ገፅ) "ጋዜጠኞች ነን" ብለው የቀረቡትን አንዳንዶቹን ስንመለከት "ክርስቲያናዊ ተልዕኮ" አልባ ሆነው እናገኛቸዋለን። ምክንያቱም በቃሉ ለተረጋገጠው ክርስቲያናዊ እውነት ሲጨነቁ አይታዩምና! ይህንንም እውነታ በተደጋጋሚ ከሚጋብዟቸው እንግዶቻቸው፣ ለእንግዶቻቸው ከሚያቀርቧቸው ሞጋች'ነት የጎደላቸው ልምጥምጥ ጥያቄዎች አልፎም ለሚጋብዟቸው እንግዶቻቸው (ሃሳውያንም ቢሆኑ) በሚያቀርቧቸው መወድሶች እና የሃሰተኞችን ገፅታ ለመገንባት ከሚያደርጉት መፍጨርጨር መረዳት ይቻላል።

ለምሳሌ "ምኩራብ ሾው" በሚባለው የዩቲዩብ ገፅ ላይ አቅራቢ የሆነውን አክሊለ ሽመልስ ብንመለከት እንደ ሃይሉ ዮሐንስ ያለውን እልም ያለ አሳች ይጋብዝና "የወንጌል አስተማሪ የሆነውን ሃይሉ ዮሐንስን ጋብዤላችኋለሁ እንደምትባረኩበትም እርግጠኛ ነኝ" ይላችኋል። ከፈለገ ደግሞ ከሃይሉ የከፋውን ሜሮን የተባለውን ሃሰተኛ ያቀርብና "ተወዳጁ ሜሮን" እያለ ሲያሞግሰው ይገኛል።

ሲለው ደግሞ "ዕቅበተ እምነት መሰራት ያለበት እንዴት ነው?" እያለ በአቃብያኑ የሰላ ሂስ የተጨነቀውን ሃሳዊውን ዮናታንን ይጠይቃል። ታዲያ ሮበርት እንዲህ ያለውን "ጋዜጠኛ" "ከክርስቲያናዊ ተልዕኮ የተፋታ ነው" ይለዋል። በዘመኑ አጠራር ደግሞ እንዲህ ያለው ሰው "ዩቲዩበር" ነው የሚባለው። ምክንያቱም ክርስቲያን ጋዜጠኛ ስራው "ክርሰቲያናዊው እውነት" እንዳትጭበረበር መጠበቅ እንጂ የዩቲዩብ ሰዓት መሙላት አይደለምና።

"ኒቆዲሞስ ሾው" የሚባለውን የዩቲዩብ ቻነል የምታቀርበው ትዕግስት እጅጉም የዚሁ ህመም ሰላባ ነች። እንግዶቿን ከመሞገት ይልቅ ጭንቅላቷን እየነቀነቀች ስሁት ትምህርታቸውን እንዲያሾልኩ መድረክ ታመቻቻለችና። አንድ ወቅትም የእርሷ ሚዲያ የጃፒ ድምፅ ሆኖ ሲያገለግል እንደቆየ ይታወቃል። በቃ! ታዋቂ ሰው ታግኝ እንጂ "ሃሳዊ" ይሁን "እውነተኛ" ምንም ግድ የላትም ታቀርበዋለች። ዩቲዩቡ ከሸቀለ እና ዝና ካመጣ "ክርስቲያናዊ ተልዕኮ" አፈር ይብላ ነው ነገሩ።

ለማንኛውም ለክርሰቲያናዊው እውነት (ለርቱዕ አስተምሮ) ግድ የሌላቸው የዩቲዩብ ገፅ ባለቤቶች ትክክለኛ ስያሜ "ክርስቲያን ጋዜጠኞች" ሳይሆን "ዩቲዩበሮች" የሚለው ነው። ምክንያቱም ዩቲዩበሮች የተገኘውን ወሬ ሁሉ ዘግበው እና የተገኘውን ሰው ሁሉ አቅርበው ገንዘብ ከማግኘት የተለየ ተልዕኮ የላቸውምና!
ይቀጥላል...

ቴዎድሮስ ተጫን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ለዘብተኝነት ያስነቅፋል! (ራዕይ 2:13-15)

የጴርጋሞን ቤተ ክርስቲያን የትንሿ እሲያ (Minor Asia) ዋና ከተማ በሆነችው ጴርጋሞን ከተማ የምትገኝ ቤተ ክርስቲያን ናት። የዛሬዋ ቱርክ ማለት ነው። ከተማዪቱ የምትታወቀው በጣኦታት ብዛት ሲሆን የሰይጣን መሰውያ የሚገኝባት ከተማ የአምልኮተ ቄሳር ማዕከል ናት። አንዳንድ ማብራሪያዎች እንደሚያስረዱት ወሲባዊ ርኩሰት ያለባትና የሌሎችም ክፋቶች ሁሉ መገኛ ናት። ቤተ ክርስቲያኒቱ በዚህ ዓይነት ውጫዊ ጫና መካከል የጌታን ስም የጠበቀች በመሆኗና ኃይማኖቱን ያልካደች በመሆኗ ተመስግናለች፣ ተሞግሳለች።

ሆኖም ግን ቤተ ክርስቲያኒቱ ከሙገሳና ምሥጋና ጎን ለጎን ከባድ ወቀሳና ነቀፋ አስተናግዳለች። ምንድነው ያስነቀፋት? ችግሯማ ለዘብተኝነት ነው። የሐሰትን አሰራር በግዴለሽነት ታግሳለች። በመካከሏ አቅፋ ይዛለች። ክርስቶስ ሲናገር "የበለዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ።" ነበር ያለው። ደግሞም "የኒቆላውያንን ትምህርት እንደነዚህ የሚጠብቁ ሰዎች ከአንተ ጋር ደግሞ አሉ። እንግዲህ ንስሓ ግባ አለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ በአፌም ሰይፍ እዋጋቸዋለሁ።" ብሏል።

በዚች ቤተ ክርስቲያን ስሙ ተይዞአል። ኃይማኖቱም ተጠብቆአል። "የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፤ ሰይጣንም በሚኖርበት በእናንተ ዘንድ ... ሃይማኖቴን አልካድህም።"(ቁ. 13) ታዲያ ይህንን በካይ የሆነውን ትምህርት ለምን በለዘብተኝነት ተመለከተች? ነቀፋው እዚያ ላይ ነው። ነገ ላይ ጠብቃ የያዘችውን ያስመሰገናትን ክቡር ነገር ሁሉ ሊያስጥላት የሚችል ይህ ልምምድ በትምህርት መልክ ገብቶ እውነትን ሲበረዝ፣ በለዓማውያንና ኒቆላውያን ሲጨፍሩ፣ አንዳንዶቹን ለነዚያ የአመጽ ትምህርት አራማጆች በመሰዋት ዝም አለች። ስለዚህ በሽታዋ በዘመናችን አጠራር Compromise (ለዘብተኝነት ወይም ማመቻመች) የሚባለው ካንሰር ነው።

በነገራችን ላይ ሰይጣን ለእውነት አቋመ ቢስ በማድረግ ነው ቀስ በቀስ ልባችንን አማጺ የሚያደረገው። ያኔ በኤደን ገነት ሔዋን በሰማቺው መለኮታዊ ትምህርት ጸንታ ቢሆን ኖሮ፣ ለዘብተኛም ባትሆን ኖሮ ለሰይጣን ድምጽ ልቧ ቦታ ባልነበረው። ዛሬም ሰዎች እውነትን እንዲሸቃቅጡ ለማድረግ በሰዎች ልብ ይኼው Compromise (ማመቻመች) ነግሶአል። "ምን ችግር አለው?" "ምን አለበት?" "አትፍረድብኝ አልፈርድብህም" "አታካብድ“ ...ወዘተ። ሲባል መስማት እየተለመደ መጥቶአል። በእውነትና በውሸት ወይም በትክክልና በእኩይ መካከል ያለውን የልዩነት መስመር ማደብዘዝ ለዘብተኛና ግዴለሽ ከመሆን ባሻገር የትውልድ ባለአደራነትን መዘንጋት ነው።

ለጌታና ለቃሉ ያለን ፍቅር የጠዋቱ ሳይሆን ሲቀር እየቀዘቀዘም ከመጣ ከሚታዩብን የበሽታ ምልክቶች አንዱ ለዘብተኝነት ወይም ማመቻመች ለእውነት መወገን አለመቻል ነው። በክርስትና እምነት ልዝብ ከማንሆንላቸው ወይም ግዴለሽ ከማንሆንላቸው ነገሮች አንዱ የእግዚአብሔር ቃል የበላይነት (የቃሉ ሥልጣን) ነው። በእግዚአብሔር ቃል ፍጹምነት፣ እውነተኛነት፣ የሥልጣን ምንጭነት ላይ ያለን እምነት በምንም ምልኩ የማረግብ አቋማችን ነው። ግንባራችንን አናጥፍም።

ተብሎ የተጻፈውን እውነት በምንም መልኩ አቅልለን አናይም። ይኽ የእግዚአብሔር ቃል "ታየኝ"፣ "ተሰማኝ"፣ "ፍሬሽ መልዕክት አለኝ" የሚል በተነሳ ቁጥር አሽቀንጥረን የምንጥለው ቃል አይደለም። የእግዚአብሔርን ቃል ሥልጣን ከእግዚአብሔር ሥልጣን ለይተን አናይም። ከቃሉ በስተጀርባ ተናጋሪው ስላለ ቃሉ የሚለው ሁሉ የጸና ነው። የቅዱሱ መጽሐፍ እውነት የምንይዘው፣ የምንቆምበት፣ የምንኖርለት፣ የምንሞትለትም ነው። ቃሉ ላይ ያለን እይታ ለዘብተኛ ከሆነ መሪ አልባ፣ መርህ አልባ፣ ከመሆናችን ባሻገር ለዛሬዎቹ በለዓማውያንና ኒቆላውያን የተጋለጥን እንሆናለን። ነውረኛ የሆኑ ምድራዊ አስተሳሰቦችና ፍልስፍናዎች ዥዋዥዌና ጥባጥቤ ይጫወቱብናል።

ወርቅነህ ዳዊት

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ክፍል አንድ - መግቢያ

". . . . አባት ከሆንሁ፣ መከበሬ የት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ የት አለ?” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት” (ሚል. 1፥6)

የክርስትና ማዕከል ከሉላዊ ሰሜን ክፍል (Global North - በተለምዶ የምዕራቡ ዓለም) ወደ ደቡብ ተሻግሯል። በ 1910 (እ.ጎ.አ.) በስኮትላድ መዲና ኤዴንብራ ላይ የተካሄደውን የዓለም ዐቀፍ የተልእኮ ኮንፍራንስ እንደ አንድ የታሪክ መገንጠያ ካየን፣ በዚያን ወቅት 82% የሚሆነው አማኝ የሚኖረው በሰሜኑ ክበብ ነበር። አሁን ግን ወደ 67% የሚሆነው የሚኖረው በአፍሪካ፣ እስያና ላቲን አሜሪካ ነው። ከ2018 (እ.ጎ.አ.) ጀምሮ የአፍሪካ አህጉር ከዓለም ላይ አብላጫውን ሕዝብ ክርስቲያን ያቀፈ ሆኗል። ላቲን አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ እስያና ሰሜን አሜሪካ በቅደም ተከተል አፍሪካን ይከተላሉ።

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን እንቅስቃሴ በዓለም ዐቀፍ መድረክ ፈጣንና ትልቅ ከሚባሉት ዐሥረኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ለዚህ ፍሬያማነት የሥራው ባለቤት የሆነው ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን። ሰማዕት እስከ መሆን በፍጹም መሰጠት የድነትን ወንጌል ስላሰራጨችው ሰሜኑ ዓለም እኅት ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን። ቤተ ክርስቲያን አንድ ናት። የሰሜኑ የክርስትና ውድቀት የኹላችንም ነው። ለተሐድሷቸው ልንጸልይ ይገባል እንጂ፣ ፈራጅ ልንሆን አይገባም። ይልቍንም መመለሳቸውንና መታደሳቸውን የሚወድውን የእግዚአብሔርን የተልእኮ ልብ ልንጋራ ይገባል።

የሰሜኑ ክርስትና አሁን ለደረሰበት የራስ ውድቀት ትልቅ አስተዋጽዖ ያደረገው የራስ-ግንዛቤ ዝግመታዊ ዝመት፣ የወንጌልን ንጽሕና ያጠለሹ ልቅ/ልዝብ ኢኪዩሚኒዝም (ecumenism) እንዲሁም ሃይማኖታዊ ሸማችነት (religious consumerism) እንደሆኑ ታሪክ ያስገነዝበናል። ሃይማኖታዊ ሸማችነት ሰብእ ተኮር ነው። የ “ሰው” (የሸማቹ) ሃይማኖታዊ የገበያ ፍላጐት ገዢው ፋይዳ ነው። በዚህ ሃይማኖታዊ የንግድ ለውውጥ ጌታ ከአጥር ውጭ ነው። በዚህ ላይ ኹሉን ዐቃፊነት (ሃይማኖት፣ ባህልና ፓለቲካ) መርሖ መሠረት ያደረገው “ዶክትሪን ይለያያል ፍቅር አንድ ያደርጋል” የሚለው የአንድነት ፍለጋ፣ የሰሜኑንን ክርስትና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማንነት አሳጥቶታል። ዓለምና ቤተ ክርስቲያን ተወዳጅተዋል። ይኽም ጌታ "በኖራችሁበት በግብፅ እነርሱ እንደሚያደርጉት አታድርጉ፤ እኔ በማስገባችሁ በከነዓን እንደሚያደርጉትም አታድርጉ፤ ልማዳቸውንም አትከተሉ።" (ዘሌዋውያን 18፥3)፤ እንዲሁም "ነገር ግን የጠራችሁ እርሱ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተም በኑሯችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ፤ ምክንያቱም 'እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ' ተብሎ ተጽፏል።" (1 ጴጥሮስ 1፥1516)። በማለት ለኪዳኑ ህዝብ ከሰጠው ማንነት ጋር በተቃርኖ የቆመ ድብልቅነት ነው።

ቢያንስ በስኮትላንድ የዛሬ መቶ ዐሥር ዓመት የነበረውን ወርቃማ ዓለም ዐቀፋዊ የወንጌል አጀንዳ መነሻ ካዳረግን፣ የእኛን የወቅቱን ፈርጀ ብዙ ቀውስ ስመለከት በፈጣን ሩጫ የገባንበት ይመስለኛል። በአሁኑ ጊዜ የአማኞች ብዛት ከ22-25 % ደርሷል። ሆኖም ብዙ አሳሳቢና ዘመን የተሻገሩ የአመራር፣ የአስተምህሮ፣ የሥነ ምግባርና የሞራል ቀውሶቻችን ቅቡልነትና ተአማኒነት ነፍገውናል። ከባህልና ፓለቲካ ኀይላት ጋር ያሉን ቍርኝቶች ለማንነታችን ቀውስ አስተዋጽኦ አድርገዋል። አሁን ካሉን የቤተ ክርስቲያን ስመ-ጥር አባቶች መካከል አቶ ሽፈራው ወ/ሚካኤል ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት እንዲህ በማለት ያቀረቡት ትንቢታዊ መልእክት፣ በብዙ መልኩ አሁንም አግባብነት አለው።

“ዕድገት አለ፤ ግን ቡፍታ ነው። ድምቀት አለ፤ ግን በብዙ መልኩ ውጫዊ ነው። መሳሳም አለ፤ ግን ልባዊ ያይደለ አፋዊ ነው። ለእግዚአብሔር ‘መገዛት‘ አለ፤ ግን እኔ ያልኩት እስካልተነካ ድረስ ብቻ ነው። መቀባበል አለ፤ ግን መሄጃ እስኪመቻች ድረስ ነው። ‘አምልኮ’ አለ፣ ግን ያለ [ፈሪሐ] እግዚአብሔር ነው። እምነት አለ፤ ግን በሕይወት ያልታጀበ ነው።” (የአባቶቼ ከተማ ተፈትታለችና በሮችዋ በእሳት ተቃጥለዋልና ፊቴ ስለምን አያዝን?)

ከምንጊዜውም በላይ ይኽ አሁን የበለጠ እውነት ይመስለኛል። "ከአራት ኢትዮጵያዊ አንዱ የወንጌል አማኝ ነው" ማለት በሚያስቸግር ኹኔታ አገራችን በጽኑ ታማለች። በመካከላችን ያለው መከፋፈል፣ ክብርና ሞገስ የራቀው አመራራችን፣ አገርን እያመሰ ባለው ብሔርተኛ ጽንፈኝነት ስንኮፍ መነደፋችን፣ እንዲሁም ቅዱሱ መጽሐፍ እንደ “ግድያ” የሚያየው ወንድምን የመጥላት ጭከና፣ "ዕድገታችን" የቍጥር እንጂ እንጂ ደቀ መዝሙራዊ የሕይወት ጥራት ያለመኾኑ አመልካች መኾናቸውን በትሕትና ልንገነዘብ ይገባል።

ውጪ ሲዘንብ ወደ ቤት ይሸሻል፤ የቤቲ ጣራ ካፈሰሰ ግን ወዴት ይኼዳል? ምስክርነታችን በብዙ ተቃርኖ የተጠላለፈ ነው። ዘረኝነትን ከምስባካችን እንቃወመዋለን፤ ተግባራችን ግን አይመሰክርም። ስለ አንድነት እንሰብካለን፤ እርስ በርስ እንወጋገዳለን። አንድነት እንፈልጋለን፤ ኾኖም ለእኛ ሥጋዊ ፍላጐት እስከተመቸ ድረስ ብቻ ነው። ፍቅርን ከአደባባይ እናውጃለን፤ ሆኖም የግብዝነት ዐረም ውጦናል። ንስሓ እንገባለን፤ ኾኖም በፍሬ ያልታጀበ ነው። የእግዚአብሔርን ምሕረት አጥብቀን እንድንሻ ግድ ከሚሉ ከብዙ ምጸቶች ጋር እንታገላለን። እግዚአብሔርም እንዲህ በማለት ሕዝቡን የወቀሰበት ቃል ለእኛም አግባብነት አለው፦

“ልጅ አባቱን፣ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፤ እኔ አባት ከሆንሁ፣ መከበሬ የት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ የት አለ?” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት” (ሚል. 1፥6)

ውሉ እንደጠፋ ማግ ብዙ የተወሳሰበው የአገራችን ፓለቲካ እንዴት ሊፈታ እንደሚችል ምክር ለመሰጠት ከሙያዬም ሆነ ከሕይወት ጥሪዬ ውጭ ነው። ሆኖም የወንጌል መልእክት ማኅበራዊ፣ አኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንድምንታዎች እንዳሉት አምናለሁ። የአገራችን ክርስቲያናዊ ተልእኮ ሊጋፈጣችው ከሚገባቸው ተግዳሮቶች መካከል ዘረኝነትና የሰላም ጥያቄ ዐበይት ናቸው። ሁለቱም ተመጋጋቢ ናቸው። እንደ ኢትዮጵያ የብዙ ብሔሮችና ቋንቋዎች መናኸሪያ ለሆነች አገር፣ በምንም የማይተኩ ውድ ዕሴቶች ከልብ የኾነ መቀባበልና መተማመን ነው። የሰው ኑባሬአዊ ዋጋ በቀዳሚነት ሰው - “አምሳለ መለኮት (አርአያ ሥላሴ)” መኾኑ ቀርቶ፣ ወደ ጐሣና ሃይማኖታዊ ጐራ ዝቅ ሲደረግ ጥርጥር፣ ፍርሃት፣ አለመተማመንና መወጋገድ ይገሣሉ።

ፓለቲካዊ ስብራቶች፣ አስከፊ ድኽነት፣ የፍትሕና የሰላም ነውጥ ላወካት አገራችን፣ ቅቡለነት ያለው ምስክርነት ማጣታችን ተጨማሪ ሐዘን ኾኗል። መንግሥትንና የፓለቲካ ኀይላትን እንደ እግዚአብሔር ቃል ተጠያቂ ማድረግ የሚያስችል የመንፈሳዊ፣ የሥነ ምግባርና የሞራል ልዕልና አጥተናል። ይኽም ግፉአን ለፍትሕ ለሚያሰሙት ጩኸት ባይተዋር፣ ዝምተኛ ወይም ወገንተኛ እንድንሆን አድርጐናል። ዘውግንና ሃይማኖትን መሠረት ካደረገ ደም አፍሳሽ ፓለቲካዊ የዐመፅ ዑደት መውጣት በተሳናት ምድራችን ውስጥ፣ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን፣ ማንነቷን፣ ተልእኮዋን እንዲሁም ሊኖራት የሚገባትን መሲሐዊ ሚና ቆም ብላ በእግዚአብሔርን በትውልዱ ፊት ማሰብ ግድ ያላል። በተለይም የክፍፍሉ ጽልመት በከበደበት በዚህ ወቅት ያለንበትን ኹኔት በጌታ ፊት ልንመረምር ይገባናል። አገር በታመመችበት ሕመም እኛም ከታመምን ምን መድሃኒነት አለ? አማራጭ የክርስቶስ ማኅበረሰብ መሆናችን ሲጐዳ፣ ማኅበረሰባዊ፣ ፓለቲካዊና ሞራላዊ ስብራቶች እንደሚብሱ ሊሰወረብን የማይችል ሐቅ መኾኑኑ ልብ የምንል ይመሰለኛል።

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

If you are interested, register!

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ነፍስንና ሥጋን በገሃነም ማጥፋት የሚቻለውን ፍሩ።’ ( ማቴዎስ 10 : 28)። የሚለው የጌታ ቃል ውስጤን በእምነት ሞላው ። ልዑል እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን መፈራት ትቼአለሁ።” (𝑴𝒐𝒓𝒆 𝒕𝒉𝒂𝒏 𝑯𝒐𝒑𝒆, 26.)

አናሲሞስ ኦሮምኛ፣ አማርኛ፣ ትግርኛ፣ ዐረብኛ፣ ስዊድን፣ ጀርመንኛ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቻ ሳይሆን፣ የሥነ ጽሑፍ ችሎታቸው ልዩ ነበር። ከስዊድን እንደ ተመለሱ በ November 1871 ነበር የ 19 ዓመት ወጣት የነበሩትን ኤርትራዊት ምሕረት ኀይሉን ያገቡት። አናሲሞስ ሰውን ሁሉ የሚያዩት በክርስቶስ ብቻ ነበር። የዘር ጽንፈኝነት ለሚያውከው የወቅቱ የአገራችን ክርስትና ትልቅ ይኽ ምስክረነታቸው እንድምታ አለው። ምሕረት ለሰባት ዓመታት አብረዋቸው በብዙ ተቃውሞ፣ ስደት፣ መከራና ችግር ድንበር ተሻጋሪ በኾነ ሐዋርያዊ ተልእኮ አጋር በመሆን አብረዋቸው የደከሙ ሲሆን፣ ሦስት ልጆች አፍረተው ነበር። ኾኖም በተለያየ ሕመም ምክንያት ኹሉም ተራ በተራ ሞተውባቸዋል። በወርሃ 1888 November ውድ ባለቤታችውን በድንገተኛ ሕመም ያጡት የመጽሐፍ ቅዱስንና ሌሎች መንፈሳዊ የትርጕም ሥራዎችን እንደ ጀመሩ ነበር። ሐዘን ስላደቀቀው ልባቸው እንዲህ በማለት ጽፈዋል፦

“. . . ልቤ በሐዝን ደምቷል። እንባዬም በቀንና በሌሊት የማያቋርጥ ምንጭ ኾኗል። መቆም እስኪሳነኝ ድርስ መላው አካሌ ዐቅም አጥቶ ዝሏል። እጅጉ ልቤ ተሰብሯል። ጥልቅ ሐዘን እንደ ጐዳኝ ልሰውር አልችልም። ኾኖም ሐዘኔ ተስፋ እንደሌላችው እንደ አሕዛብ ሳይሆን በጽኑ [የትንሣኤ] ተስፋ የተሞላ ነው።” (𝑴𝒐𝒓𝒆 𝒕𝒉𝒂𝒏 𝑯𝒐𝒑𝒆, 42.)

በዚህ ሁሉ መከራ መካከል እያለፉ ነበር፣ 100 መዝሙራት (hymns)፣ መዝሙረ ዳዊትን እንዲሁም የሉተርን ካታኪዝም በአፋን ኦሮሞ የተርጐሙት። ዐሥራ ሦስት ዓመታታ (እ.ጎ.አ 1886-1897) የዘለቀው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጕም ሥራ በብዙ የመከራ ማዕበል፣ በብዙ እንባና ተስፋ አስቆራጫ ፈተና የታጀበ ነበር። ደስታቸውን እንዲህ ሲሉ ገልጸውታል፦
“ዕለት June 19, 1897 የትርጕም ሥራው የተጠናቀቀበት ልዩ የደስታ ቀን ነው። ያለኝ ኀይል በሙሉ ከውስጤ ተሟጥጦ አልቋል። ኾኖም ድካም የሚያድስና መከራን ሁሉ የሚያስረሳ የደስታ ቀን ነበር!” (𝑴𝒐𝒓𝒆 𝒕𝒉𝒂𝒏 𝑯𝒐𝒑𝒆, 45.)

የሒካ መከራ እንደማያበራ የክረምት ዝናብ ነበር። ለሕትመት ሥራ ወደ ስዊዘር ላንድ ሲሄዱ ከኹለተኛ ሚስታቸው ሊድያ ዲንቦ የወለዷቸው ሕጻናት ታመው ስለነበር ልባችው እጅግ ከብዶና ተከፍሎ ነበር። ሥጋታቸው አልቀረም፣ የመጀመሪያ ልጃቸውን ማረፍ መርዶ ሰሙ። ሊድያ ልክ እንደ ምሕረትም ዐጥንት ብርቱ የወንጌል አጋርም ነበሩ። የባለቤታቸው የአናሲሞስ ልብ እንዲበረታ እንዲሁም የሕትመት ሥራው ሳይጠናቀ እንዳይመለሱና በእግዚአብሔር ሉዓላዊነት እንዲደገፉ በጌታ ቃል ያበረታቷቸውና ያጽናኗቸው ነበር።

ከዘጠኝ ወራት በኋላ የሕትመቱ ሥራ ተጠናቀቀ። ወሰን የሌለውን ደስታቸውን ስዊድን ላሉ ቅዱሳን እንዲህ በማለት ገልጸውታል፦

“በሰማይም ኾነ በምድር ላይ ያለ ማናቸው ኀይል ከኦሮሞ ሕዝብ ላይ ሊነጥቀው የማይችለውንና ሕያው ሀብት የሆነውን ቅዱስ ቃሉን እግዚአብሔር ሰጥቶናል። ብርቱ ጸሎቴ የታተሙት 2000 መጽሐፍ ቅዱስና 5000 የአዲስ ኪዳን ድነትን የታራቡ አንባቢዎች እጅ እንዲደርሱ ነው። ይኽ ክንውን መፈጠሬን የጠላሁባቸውን እነዚያን የጨለማ ጊዜያት ፍጽሞ አስረስቶኛል። ይልቁንም ለዚህ ታላቅ ሥራ መወለዴ የገባኝ አሁን ነው። ከቅዱሳን ጋር አብሬ የምወርሰውን የእግዚአብሔርን ክብር በማሰብ እስከ መጨረሻ እስትንፋሴ ድረስ አምላኬን አገልገለዋለሁ። ውድ የወንጌል ማኅበረተኞች፣ ይኽ የመዳንን መንገድ የሚያሳይ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል እንዲሰራጭ አጥብቀን ልንጸልይ ይገባል። ይኽንን ለማሳካት የምንሄድበት አስቸጋሪ የመከራ መንገድ በፊታችን አለ። ኾኖም በጌታ ጸጋ ሁሉ ይቻላል፣ የጻድቅ ሰው ጸሎት ኀይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል።’” (ያዕቆብ 5 : 16)። 𝑴𝒐𝒓𝒆 𝒕𝒉𝒂𝒏 𝑯𝒐𝒑𝒆, 65-66. 47.

ለአናሲሞስ የመጽሐፍ ቅዱሱ ትርጕም ሥራ ማለት፣ በድቅድቅ ጨለማ ላለ ለኀጢአተኛ የተጻፈን የእግዚአብሔርን የፍቅር ደብዳቤ መተርጐም ነው። የእግዚአብሔርን የተልእኮ ልብ መካፈል ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስን መኖር፣ መስበክና መተርጐም የሕይወትና የሞት ጕዳይ ነው። ማንብብ ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ክርስቶስ ለመኖር ራስን የመስጥት ጥሪ ነው። ቅዱስ እግዚአብሔርን በቃሉ ውስጥ ያገኘ ሰው ያው አይሆንም። ራሱንም ኾነ ሌሎችን የሚያይበት ዕይታ ለአንዴና ለዘላለም ተቀይሯልና!

አናሲሞስ ማብቂያ ከሌለው መከራ ጋር እይታገሉ፣ በጌታ ጸጋና በድነት ደስታ በመደገፍ ያገለገሉ ትልቅ የወንጌል ሰው ነበሩ። በእኔ ግምት ከፍተኛው ስብራት የመጀመሪያ ልጇን በወለደች በወሯ ከቁስል ጋር በተገናኘ የጤና እክል ልጃቸው ዲና መሞቷን አዲስ አበባ ለሥራ በመጡበት ወቅት መስማታቸው ነበር። በአገልግሎት ዘመናቸው አምስት ልጆች እንዲሁም 18 የቅርብ ዘመዶች አንዲሁም ሚስዮናዊ የወንጌል አጋሮቻቸውን በሕምም፣ በአደጋና በወረርሽ አጥተዋል። ወንጌልን ወደ ማኅበራዊ “የስኬት ጐራ” ዝቅ ላደረገው፣ ዋጋ መክፈል ለማይፈልገውና ወንጌልን መከራ የለሽ አድርጐ ለሚያቀረበው የወቅቱ ክርስትና፣ የአናሲሞስ ሕይወትና አገልግሎት በቀጠተኛ ተቃርኖ የቆመ ነው። ይልቁንም እንደ ጳውሎስ መከራቸው ሳይቆጥሩ ዘወትር ልባቸው የተያዘው በወንጌል ነበር፦ “ሌላውን ነገር ሳልቈጥር፣ ዕለት ዕለት የሚያስጨንቀኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሐሳብ ነው።” (2 ቆሮንቶስ 11 : 28)።

መከራን እንዴት ተቋቋሙት? አብሮአቸው ያገለግል የነበረው ወጣቱ ሚስዮናዊ ማርቲን ኖርድፌልት እንዳስተዋለው፣ “ኹሉን ለጌታ በመተው . . . ይኽ የአናሲሞስ የጽናት ቃል ነበር”። ሐዋርያው ጴጥሮስ እንደ ጻፈው “ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ።” (1 ጴጥሮስ 2 : 23)። 𝑴𝒐𝒓𝒆 𝒕𝒉𝒂𝒏 𝑯𝒐𝒑𝒆, 65-66. 243-244.

ከስዊድን ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ አገር ቤት ከመመለሳቸው በፊት እዚያ ላሉ ቅዱሳን ያቀረቡት የመጨረሻው ስብከተ ወንጌላቸው “ብንኖር ለጌታ እንኖራለን፤ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን። ስለዚህ ብንኖርም ብንሞትም የጌታ ነን።” ( ሮሜ 14 : 8) የሚል ነበር። የስብከታቸው ድምዳሜም፣ “ክርስቲያን በመከራ ብዛት ሊዝል አይገባም” የሚል ነበር። ይኽው ጽኑ እምነት መከራን ኹሉ ከምስጋና ጋር ታግሥው ለማገልግል ዐቅም ኾኖአቸዋል። ከማረፋችው ጥቂት ወራት በፊት፣ ወደ ጌታ እንደሚሄዱ መንፈሳቸው ይመስክር ነበር። ማስታወሻቸው ላይ እንዲህ ሲሉ አስፍረዋል፦

“አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈጽሞውኑ ሊበጠስ በማይችል ጽኑ የፍቅር ገመድህ አጥብቀኽ ያዘኝ፤ ለዘላለምም ከአንተ ጋር ልኹን . . . ቅዱስ እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለ ታላቁ ስምህ ስትል ነፍሴንና አካሌን አድስ።”። የመጨረሻ ስብከተ ወንጌል ያቀርቡት እሁድ June 21, 1931 ነበር። ማምሻው ላይ ሰማያት ተከፍተው ወደ ጌታ ሄዱ። መቃብራቸው ላይ የተከተበው ቃል እንዲህ ይላል፡- “ምድር ሆይ፤ አንቺ ምድር፣ አንቺ ምድር፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሚ!” ( ኤርምያስ 22 : 29)። (𝑴𝒐𝒓𝒆 𝒕𝒉𝒂𝒏 𝑯𝒐𝒑𝒆, 65-66.)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

እባካችን አንድ አፍታ አብረን እንጸልይ!

ክፍለ ምንባብ፡ ኤፌ. 6፡10-18 በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ (ዐ.መ.ት. “ጠንክሩ”)። 11 የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። 12 መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ። 13 ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ።

ጌታ ሆይ በእህል ያገኘነው ጉልበት እህል የማይበሉ ክፉ መንፈሳዊያን ሰራዊትን ሊያሸንፍልን እንደማይችል እናምናለን። የሁሉ ነገር ኃይልና መታመኛችን አንተ ብቻ ስለሆንህ ከእንጀራ የማይገኘውን መንፈሳዊ ጉልበት ስጠን! ህይወት በሆነ ውጊያና ውጊያ በሆነ ህይወታችን ስንመላለስ፣ ጠልፎ እንዳይጥለን ተራ ያልሆነውን የዲያብሎስን ሹሩባ በትኖ የሚፈታልን ሰው ያልሰራውን የጦሩን ሜዳ ልብስ የአንተኑ የጦር ዕቃ አስታጥቀን! ይህንን ልብስ ለብሰን እንዳንተኛም እንደ ተዋጊ የምንቆምበትን ንቃት ስጠን!

ምንጫቸው መንፈሳዊ የሆነ ስውርና ብርቱ ኅይል ያላቸውን የአጋንንት ኃይልና ሥልጣን በየቀኑ ስለምንጋፈጥ በሰዎችና በእነዚህ ሰውንም በሚጠቀሙ መንፈሳውያን ሰራዊት መካከል ያለውን ልዩነት እንድናውቅ መንፈሳዊ ዐይኖቻችንን አብራልን!

እውነት፣ ህይወት፣ መንገድ፣ የሆንከውን ጌታ በሁለት ምላስ መከተል እንደማይቻል አውቀናልና መንፈሳዊ ልብሳችን እንዳይዝረከረክ የእውነትን ቀበቶ አስታጥቀን፣ በኑሮ ፈተና ወገባችን ሲላላ መንፈስ ቅዱስ ረዳታችን እንዲሸክፍልን አድርግልን።

በኃጢአተኛው ዓለም ስንኖር በአመጽ በተገኘ ልብስ ተሽቀርቅረን በፊትህ ግን ቡቱቶ እንዳንሆን፣ አንድ ሳይሆን ሺህ የጽድቅን ጥሩር አልብሰን። ከፊትና ከኋላ የአመጻ ጦር እንዳይወጋን በጽድቅ ክሳድ ዙሪያችንን ሸፍነን።

የጽዮን ተጓዥ መንገደኞች እንደሆንን እንዲገባን ከሁካታ ተርፈን እንድናተርፍ መጓጓዣ ጫማችን የምስራች ቃል፣ “ኢየሱስ ሞቶልሃልና ወደ እርሱ ና!” ብሎ የሚያናግር የሰላም ጫማ አጫማን! የወንጌል ትምህርት መልእክተኞች፣ የምሥራች ቃል አብሳሪዎች አድርገን። ህይወታችን ሁሉ በሰላም እንዲሞላ ቀዳሚ ድኅረ ትንሳኤ ጥሪ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” የሚለው እንደሆነ እንዳንረሳ ታግሰህ ዘወትር አስታውሰን!

ጌታ ሆይ በየቀኑ ከየጠርዙ እምነታችንን ፈታኝ የሆነ እንደ እሳት የሚንበለበል የክህደት ፍላጻ ይወረወርብናል፣ እምነታችን እንደጋሻ እንዲነሳ ክንዳችንን አበርታ፣ አባብሎ ከሚፈትን፣ አስፈራርቶ ከሚያስበረግግ የጠላት ቀስት የሚያተርፈውን የእምነት ኃይል አስታጥቀን!
የድነታችን ትምክህት መሰረት የእኛ ሥራ እንዳልሆነ አውቀን ከአንተ የተቀበልነውን ጽድቅ በራሳችን ላይ እንድናጠልቅ ከሐሳቦች ሁሉ ውጊያ እንድንተርፍ፣ ተስፋ መቁረጥ በተፈጻሚ በተስፋ እምነት እንዲሸነፍ፣ በነጻ የተቀበልነውን ባለ ሙሉ አቅም የጽድቅን ጥሩር ከራሳችን እንዳናወልቅ እርዳን!

በማይሰለች ትጋት ሌትና ቀን ውሸትን ከራሳቸው በሚያፈልቁ የሐሰት ትምህርቶች የሚመራውን የዲያብሎስ ትምህርት አናት አናቱን የሚሰይፈውን ባለሁለት ጎን የቃሉን ሰይፍ እንደ ሥልጡን ሰራዊት አስታጥቀን፣ ኑሮና አረማመዳችን በቃሉ ታርቆ በጨለማ የምናበራ የቃሉ ባለ አደራዎች አርገን።

ወድ አባታችን ሆይ! ከአንተ ጋር አንዳንዴ እየተገናኙ መኖር አይቻልም! መንፈሳዊ ምሪትህን፣ ጥበብህንና ኃይልህን ዘወትር ለመቀበል ዘወትር በጸሎት ህይወት እንድንኖርባልተቋረጠ የጸሎት ህይወት ባርከን።

ይህንን ልመና ጸሎትም ህይወትም አድርግልን! በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

መጋቢ ሰሎሞን ጥላሁን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ፍትሕ ለኢዮብ ጭሮ ! ✋

ራሱን፣ "ሜጀር ዋን ፕሮፌት ጆይ ጭሮ" እያለ የሚጠራው ከሥር ምስሉ የሚታየው ጎረምሳ፣ ቀደም ብሎ ከኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል፣ የቤተ ክርስቲያን ፈቃድ የተሰጠው፣ እርሱ እንደሚለው ደግሞ ፈቃዱ መሰረዙን በሶሻል ሚዲያ እስከሰማበት ዕለት ድረስ ንጹሁን ወንጌል ሲሰብክና 😀 ከ"ድርጅቱም" ጋር በሰላምና በትብብር እያገለገለ የቆየ የእግዚአብሔር ሰው ስለመሆኑ አስታውሷል ። ይሁንና ባለፈው ሳምንት የቤተ እምነቱ ፈቃድ መነጠቁን እንደማንኛው ሰው በሶሻል ሚዲያ እንደሰማና እንዳዘነ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቋል። የቅሬታ ድምጹንም ለካውንስሉ አሰምቷል። "ጥፋትህ ይኼ ነው!" ብለው ሳይነግሩት ድንገት ከመሬት ተነስተው በወሰኑት ውሳኔ እሱና የቤተ እምነቱ ምዕመና ጥልቅ ሀዘን ውስጥ ስለመግባታቸውም አውስቷል።

ካውንስሉ ሚዲያዎች እንዲያውቁት በሚል ማኅበራዊ ድረ ገጹ ላይ ባኖረው ደብዳቤው፣ ፈቃድ ተነጣቂዎቹን ሲመክርና ሲዘክር ቆይቶ አሻፈረኝ በማለታቸው ምክንያት አራት ግለሰቦችንና የሚመሩትን አገልግሎት ፈቃድ እንደነጠቃቸው ቢጠቅስም፣ እነሆ "ሜጀር ዋኑ" ጎረምሳ ግና በቅድሚያ የደረሰው ደብዳቤም ሆነ አካላዊ ንግግር እንዳልነበረ ብቻ ሳይሆን ይልቁንም በእሱ ባለቤትነት የምትተዳደረው ቤተ እምነቱና ካውንስሉ እጅና ጓንት ሆነው፣በሰላማዊና ጤናማ ግንኙነት ላይ እንደቆዩ ተናግሯል። የጭሮ ልጅ ስለዚያ ተግባቦታቸው ሲገልጽ፦

"ሌላው ቀርት ባለፈው፣ በመጋቢት ወር ላይ መስቀል አደባባይ ተደርጎ ለነበረው የጸሎትና የምሥጋና ፕሮግራም የድርጅቱ ቄስ፤ ቄስ ደረጄ እኔጋ ደውሎ፣ ቢሮ ጠርቶኝ መስቀል አደባባይ ለነበረው ፕሮግራም እርዳታ እንዳደርግ፣ 'ካንተ የሚጠበቀውን ማድረግ አለብህ' ሲለኝ ፣ እኔም እንደ ቤተ ክርስቲያንና የዚያ ድርጅ አባል እንደመሆኔ ደብዳቤው እንደደረሰኝ በግሎሪ አለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን ስም የድርሻችንን ከፍለናል፣ ከዚህ ቀደምም በጠየቁን ጊዜ ሁሉ በተደጋጋሚ ድጋፍ እናደርጋለን። ከድርጅቱ ጋር ምንም ዓይነት ችግር ወይም ጸብ አልነበረንም።" ብሏል።

እናም በወቅቱ በዚሁ ገጽ ላይ ያልኩትን እደግመዋለሁ፣ ካውንስሉ ውስጥ ከተሰገሰገው የሃሰት መንጋ ተለይቶ የኢዮብ ጭሮን ፈቃድ ያስነጠቀው የተለየ ጥፋት ምንድነው? ብዬ በድጋሚ እጠይቃለሁ። ካውንስሉ ይኼን እርምጃ የወሰደው የሃሰት ትምህርትና ልምምድ ተቃዋዊ ነኝ ለማለት ከሆነ፤ መጋቢ ዕዮብ ደምሴ እንዳለው፣ በጣም የሚያስተዛዝብና የካውንስሉን ተአማኒነት ይበልጥ የሚያሳጣ ነው። ለዚህ ጥያቄ ከተቋሙ አርኪ ምላሽ ካልተገኘም ዳኝነቱ ፍርደ ገምድል ነውና ብቻዬንም ብሆን "ፍትሕ ለዕዮብ ጭሮ" ብዬ ሰላማዊ ሰልፍ የምንወጣበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። 😀

©ሽመልስ ይፍሩ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የርገን ሙልትማን!

ዘመናዊዋ ነገረ መለኮትና ፍልስፍና ለጀርመኖች ታሸረግዳለች ይባላል። ሲያስቡ፣ ሲፈላሰፉና ነገረ መለኮታዊ ብይን ሲሰጡ የሚያክላቸው የሉም። ከሉተር እስከ ካንት፣ ከሄግል እስከ ሹላማኸር፣ ከኒቼ እስከ ባርዝ፣ ከራህነር እስከ ፓነንበርግ፣ ከፖል ቲልኪ እስከ የርገን ሙልትማን። የዘመናዊውን ዓለም ንጽረታተ ዓለም ለመቀየስ እንደነሱም የተቻላቸው አሳቢ የለም።

የርገን ሙልትማን ነገረ መለኮት ላይ ፍላጎት ያሳደረው ጀርመንን ወክሎ በሚዋጋበት ወቅት ኖቲንግኸም አካባቢ የጦር እስረኛ በነበረበት ጊዜ ነበር። በወቅቱ የሬንሃርድ ኔቡርን The Nature and Destiny of Man (1941) መጽሐፍ ማንበቡን ያስታውሳል። ወደ ጀርመን ተመልሶም ነገረ መለኮትን ማጥናት ጀመረ።

በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ተሳትፎው ክርስትና ሲሰብክ የከረመው ተስፋ አይኑ እያየ ሲበን መመልከቱ ትልቅ አስተዋጽኦ ነበረው። ቲልክም በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት መሳተፉ ፍልስፍናውንና ነገረ መለኮቱን ለውጦታል። ለሙልትማን አምላክ ዓለሙ የመከራ ዶፍ ሲወርድበት ከሩቅ ሆኖ የሚከታተል ታዛቢ አለመሆኑን በሦሥት ድርሳናትን አስረድቷል፤ The Tehology of Hop, The Crucified God and The Church in the Power of the Spirit።

ነገረ ፍጻሜያዊ እሳቤ የስልታዊ ነገረ መለኮት የመጨረሻ ክፍል ሳይሆን ዋና ልበ ምት በማድረግ ነበር ስራውን የጀመረው። የቅዱስ አንሰለምን (Canterbury) ቃላት ማለትም 'መረዳት የምትሻ እምነት' (faith seeking understanding) የሚለው በመዋስ 'መረዳት የምትሻ ተስፋ' (hope seeking understanding) በማለት ተስፋ ለክርስትና ማእከላዊ ሃሳብ መሆኑን ይሞግታል። በክርስቶስ መላ ዐለማሙን የቀየረ ስራ ምክንያት ተስፋ የእምነት ልበ ምት መሆኑን ያስረዳል። ቤተክርስቲያን ክርስትና የያዘውን ተስፋ በአግባቡ ብትገነዘብ ለማኅበረሰቡ ፈያጅ ማኅበር መሆንና ዙሪያዋን በተቀበለችው ተስፋ የማነጽ ድርሻዋን ለመወጣት ይቻላታል ይላል።

ስለ ተሰቀለው አምላክ ለመስረዳት ጊዜ ቢያስፈልግም የሚከተለውን ግን ማለት ይቻላል። ለሙልትማን የክርስቶስ መስቀል ሁሉም ነገር ነው። የሉተርን 'crux probat omnia ማለትም 'መስቀሉ የሁሉም ነገር ማእከል ነው' የሚለውን አንደ ሰንደቅ ያነሳል። The Crucified God ክርስቶስን መከራ ለሚቀበለው ዓለም ፈያጅ አድርጎ በማቅረብና አብሮት መከራ የሚቀበል አምላክ መኖሩን በማጉላት ግንበር ቀደም ነው። በፍጥረቱ መከራና ሕመም የተካፈለ አምላክን በሕማሙ ቅሩብ መሆኑን ይጠቁማል። ሩቅ ሆኖ የሚከታተል ሳይሆን ቅርብ ሆኖ ከዓለሙ ጋር አብሮ የታመመ የተሰቀለ አምላክ አለ ባይ ነው። ይህ ደግሞ ተገዶ ሳይሆን ወዶና ፈቅዶ መሆኑን ያሰምርበታል።

'የተሰቀለ አምላክ' በሚለው ሃሳብ ውስጥ 'አምላክ መከራን መቀበል የማይችል ወይም impassible ነው' የሚለውን ሃሳብ በማእከልነት ይቃወመዋል። "At the heart of the prophetic proclamation there stands the certainity that God is interested in the world to the point of suffering." በዚህ መንገድ ሥሉስ አሐዱው አምላክ ራሱን ገልጧል ይላል። "የክርስቶስን መስቀል መለኮታዊ ኩነት አድርገን የምንረዳው ከሆነ ማለትም በልጅና በአባት መኸከል የተደረገ ኩነት ከሆነ መስቀሉን ልንረዳውና ልንገልጸው የሚገባን ሥላሴያዊ በሆነ መልኩ ነው። የመስቀሉ ኩነት እግዚአብሔር አብ፣ እግዚአብሔር ወልድ እና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ገላጭ ነው።" ይላል።

"ክርስትና የሚቆመውም ሆነ የሚወድቀው የተሰቀለው ክርስቶስን በምንረዳበት መንገድ ነው። እግዚአብሔርን በተሰቀለው መሲሕ በኩል ማወቅ ወይም በሉተር ቃላት "የተሰቀለውን አምላክ" መረዳት ክርስትናን በአግባቡ መረዳት ነው።" የተሰቀለው አምላክ የመገለጥ ሁሉ ማጠንጠኛ ነው!

ከላይ የጠቀስኩት መጽሐፍ በህይወቴ ካነበብኳቸውና አመለካከቴን ከነቀነቁ ምርጥ መጽሐፍት መኸከል ነው። ይህን የነገረ መለኮት መምህርና አሳቢ ሲናገረ ወደ ከረመው በእግዚአብሔር ክርስቶስ መስቀል የተገለጠው ተስፋ ሰብኮ አንቀላፍቷል። መልካም እረፍት የርግን!

አማኑኤል አሰግድ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የነገረ ወንጌላውያንን የዮቲዮብ ቻናል ሰብስክራይብ ታደርጉ ዘንድ እንጠይቃለን! በቪዲዮ ለመምጣት ስለምናስብ ሰብስክራይብ ማድረጋችሁ ይጠቅመናል። ሊንኩ ከታች ያለው ነው

negerewengelawyan7068?si=9RokjJu_90VoCl23" rel="nofollow">https://youtube.com/@negerewengelawyan7068?si=9RokjJu_90VoCl23

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

የመገኘቱ ስሜት ውጤቱ ምንድን ነው?

አንድ በጽኑ የምንፈልገው ነገር ሲገኝ በመጀመሪያ የሚሰማን ስሜት ከዚያ ካገኘነው ነገር ምንነት አንጻር የደንነት (ሴኪዩሪቲ) ስሜት ነው፣ ቤት ብንገዛ የሚሰማን የረፍት ስሜት መኪና ስንገዛ ከሚሰማን ይለያል፣ የናፈቅነውን ሰው ስናገኝ የሚሰማን የሸሸነውን ሰው ስናገኝ ከሚሰማን ይለያል፣ እግዚአብሔርን ማግኘት ወይም በህልውናው ውስጥ መገኘት ስሜቱ በምድር ላይ ካሉ ስሜቶች ሁሉ የተለየነ ነው፣ ዓይነቱም ብዙ ነው።

ስለዚህ እግዜር ሲገለጥ ምን ይሆናል? አናውቅም- ብዙ ነገር ነው የሚሆነው ሲሆን ብቻ ነው የምናውቀው እግዚአብሔር እንደ እኛ አቪየስ አይደለም።

ለአዳም ሲገለጥ ራቁትነቱን አሳየው - ለአብርሃም በድምጽ ተገልጦ አገር አስኮበለለው፣ ለሙሴ ተገልጦ ፈርቶ ወደ ሸሸበት ከአንዲት በትር ጋር መለሰው፣ ለያቆብ ተገልጦ የሚያስነክስ በረከት ባረከው፣ ለዮሴፍ ተገልጦ አገር ከችጋር የሚያድን ሕልም አሳየው፣ ለኢሳይያስ ተገልጦ በኅጢአት ወቀሳ መሞቴ ነው አሰኘው፣ ለዮሐንስ መጥምቁ ተገልጦ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ .. ብሎ ስለ ልጁ መሰከረ.. በደብረ ታቦር ተገልጡ ሶስቱንም እዚህ እንቅር አሰኛቸው፣ ለጳውሎስ ተገልጦ ዐይኑን አሳወረው፣ መልሶም አበራው ለጴጥሮስ ተገልጡ ከእስርቤት አወጣው፣ ለዮሐንስ ተገልጦ ሩኹን አሳተው …ስለዚህ ሪስክ የሌለው የእግዚአብሔር መገለጥ የለም! በዚህ ሁሉ ግን ተዝናንተው የተገለጠላቸው የሉም።

የእግዚአብሔርን ህልውና አለ እና የለም በሚል የሚጠየቅ አይደለም - እኛ ዘንድ ስሜቱና ንቃቱ ነው የሚለዋወጠው፣ ለዚህ ነው በአንድ ጕባኤ እንኳን አንድ ላይም ሆነን አንዳንዶች የመገኘቱን ስሜት ተለማምደው ሌሎች ግን ያ የመንፈስ ስሜት የማይኖራቸው፣ ከእግዜር ጋር ልምምዳችን ቅርርባችን፣ መፈለጋችን፣ መጸለይ ማንበባችን በዳበረ ቍጥር የመገኘቱን ስሜት ይበልጥ እንረዳዋለን። ኤልሣዕ ለብላቴናው ኅልዎቱ የመለኮቱ የሰራዊቱ እንዲታየው ዐይኑን አብራ አለው ልዩነቱ የኅልዎቱ መኖር እና አለመኖር ሳይሆን የዐይን ማየትና አለማየት ነው -

አቤቱ ዐይኖቻችንን አብራ!

መጋቢ ሰሎሞን ጥላሁን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ቤዛዊ ድነት ያመጣልን የአምላክ ዝምታ . . .

መድኅናችን ክርስቶስ ዝም አለ - እኛን በሞቱ በማዳን እግዚአብሔርን ለዘላለም በቅድስናው እንድናመልክ! ያለፍትሕ በትዕግሥት በተቀበለው መከራ፣ እኛ ከዘላለም ሞትና ፍርድ ወደ ዘላለም ሕይወት ተሻገርን ! በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር ሳይቆጥር፥ ራሱን በፈቃዱ ባዶ የማድረጉ ጫፍ በፍጹም ዝምታውና ትዕግሥቱ ተገለጠ። የሥላሴ አካል ሆኖ ሳለ፣ ዐቅም እንደሌለው ዝም አለ። ፍጡር ጲላጦስ፣ "አታናግረኝምን? ልፈታህ ወይም ልሰቅልህ ሥልጣን እንዳለኝ አታውቅም?” በማለት በአምላክ ላይ እንደ አምላክ ተሰየመ። (ዮሐ. 19፥ 10)። ያልተገደበ ስልጣን አንዳለው ጲላጦስ ሲናገር፣ አምላክ ዝም አለ! "እስኪገረም ድረስ ለቀረበበት ክስ አንዲት ቃል እንኳ አልመለሰም (ማቴ. 27፥ 14)።

ኢሳይያስም በትንቢት መንፈስ ሆኖ በመደነድ፣ "በሸላቾች ፊት ዝም እንደሚል በግ፣ አፉን አልከፈተም" አለ። ይህ ሁሉ መታገሥ በኀጢአት ፍርድ ውስጥ ላለን ለእኛ ነበር። “እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።”ክርስቶስ ባሳለፈው መከራ ውስጥ፣ ትልቁ የመታገሡ ጉልበት ያረፈው፣ “በጽድቅ ለሚፈርደው [ራሱን] አሳልፎ” ለእግዚአብሔር በመስጥት ላይ ነበር። ይኽም በእግዚአብሔር ሉዓላዊነት ላይ የነበረውን፣ ፍጹም መሰጠት ያሳየናል።

"እርሱም ኀጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤” (1ጴጥ 2:22-23)።

ሆኖም ይህ የሕማም ሰው፣ ስለ እኛ ድነት በፍጹም መታዘዝ ዝምታን መረጠ! እርሱ “የሚስብ ውበት ወይም ግርማ አልነበረውም፤ እንድንወደውም የሚያደርግ መልክ አልነበረውም። በሰዎች የተናቀና የተጠላ፣ የሕማም ሰውና ሥቃይ ያልተለየው ነበር። ሰዎች ፊታቸውን እንደሚያዞሩበት ዐይነት፣ የተናቀ ነበር፤ እኛም አላከበርነውም። በርግጥ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ፤ ሕመማችንንም ተሸከመ፤ እኛ ግን በእግዚአብሔር እንደ ተመታ፣ እንደ ተቀሠፈ፣ እንደ ተሠቃየም ቈጠርነው። ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤. . . በእርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን . . . እግዚአብሔርም፣ የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ ጫነው። ስለ እኛ ተጨነቀ፤ ተሠቃየም፤ ነገር ግን አፉን አልከፈተም፤ እንደ ጠቦትም ለዕርድ ተነዳ፤ በሸላቾች ፊት ዝም እንደሚል በግ፣ አፉን አልከፈተም። በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ኀጢአት ተመቶ . . . ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ . . በአፉ ተንኰል ሳይገኝበት፣ ምንም ወንጀል ሳይሠራ፣ አሟሟቱ ከክፉዎች፣ መቃብሩም ከባለጠጎች ጋር ሆነ . . . የብዙዎችን ኀጢአት ተሸከመ፤ ስለ ዐመፀኞችም ማለደ።" (ኢሳ. 53)

ገደብ የሌለው ፍቅር! የእኛስ ምላሻ ምን ይሆን? እርሱን የመውደዳችን እውነተኛነት የሚለካው፣ አምላክ በአምሳሉ የፈጠረውንና አንድ ልጁን ለመስቀል ሞት አሳልፎ የሰጠለትን ጐረቤታችንን እንደ ራሳችን ስንወድ ነው። በአጥናፈ ዓለም ታሪክ ውስጥ፣ ወሳኝና መካከለኛ የሆነው የመስቀሉ ወንጌል እንደገና እኛንም የምድራችንንም ገጽ ያድሰ። አሜን!

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

#Identification /#መታወቂያችን

የሕማማት ሰሞን ማስታወሻ

ደጉ ጌታ ሰው ሆኖ ሲመላለስ የእግዚአብሔር ልጅ መኾኑ፣ ለዘመናት ይጠበቅ የነበረው መሢሕ መኾኑ፣ አማኑኤል (የእግዚአብሔር በሕዝቡ መካከል መገኛ ምክንያት) መኾኑ ... እንደምን ታወቀ?

ኢሳይያስ ይህን ስቅዩ ሎሌ 'እንድንወደውም የሚያደርግ መልክ አልነበረውም' ማለቱንስ (አሁንም) ያስተዋለ አለን? የእግዚአብሔር መሆኑ ወይም ከእግዚአብሔር ዘንድ መሆኑን መለያው ታዲያ ምንድነው?

እግዚአብሔር የታወቀው በመስዋትነት ፍቅሩ ነው። ይህ ዓለም ያውቀው ዘንድ የወደደው በፍቅሩ ነው። 'እግዚአብሔር ፍቅር ነው።' ያለው ሐዋርያ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ/እንድንታወቅ አባት እግዚአብሔር 'አትረፍርፎ ያፈሰሰልን ፍቅር' ምንኛ ታላቅ ነው! ይለናል [1 ዮሐ. 3፥ 1]።

በዚህ በወደቀው ዓለም፣ በዚህ እርሱን በማታውቀው ዓለም፣ በዚህ ጠላትነትና እርስ በእርስ መፈራራት በሰፈነበት ዓለም፣ በዚህ ኃያላን ነን ባዮች በጡቻቸው ለመታወቅ በሚንደፋደፉበት ዓለም፣ በዚህ ጦርና የጦር ወሬ ዜና ሆኖ በገነነበት ዓለም፣ በዚህ ለድሆችና ለምስኪኖች ሥፍራ በሚነፍግ ዓለም፣ ... ወዘተ የታራቂውና የሰላሙ ንጉስ፣ የድሃ አደጉ አባትና የመበለቲቱ ዳኛ የሆነው አምላክ - ልጆቹ ተብለን እንድንጠራ መታወቂያችን የእርሱ ፍቅር ይሆነን ዘንድ አፈሰሰልን።

ሽንቁር የመላው ሕይወታችን፣ ለመብታችን ስንሯሯጥ የተሰበረው መያዣችን አስቸገረን እንጂ እርሱማ 'ፍቅሩን' አትረፍርፎ አፈሰሰልን። የምንታወቅበት የእግዚአብሔር ፍቅር አብዮተኛ ነው። ለምስኪኖች ይወግናል፣ የድምፅ አልባዎች ምትክ ያረጋል። የታመሙትንና ያልጋ ቁራኞችን ምንጣፍ አራግፎ ያነጥፋል፣ የተራቡትን ከአፉ ነጥቆ ያጎርሳል፣ ከራሱ ቁስል ይልቅ የሌላውን ያክም ዘንድ የቀረችውን ትንሽዬ ዘይት በባልንጀራው ቁስል ላይ ያደርጋል።

የእግዚአብሔር ፍቅር ሙሉ መልክ ኢየሱስ ነው። የመስቀል አርበኛ። የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ፈሰሰ ሲለን - 'ውይ እግዜር እንዴት ይወደኛል' እያልን የኮንፍረንስ መዓት፣ የፍቅር ዜማ መዓት ... ወዘተ እንዲኖረን አይመስለኝም። እርሱ ኢየሱስ እንደተመላለሰ እንድንመላለስ ነው እንጂ።

የእግዚአብሔር ፍቅር የደቀመዛሙርቱን እግር አጠበ።

ዕለተ - ሐሙስ የፍቅር አብዮት ተገለጠ። ጌታ የባርያውን እግር አጠበ!

ተገኝ ሙሉጌታ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ቅዱስ ማቴዎስ እንደሚነግረኝ፥ ጌታዬ ኢየሱስ ከመወለዱ ጀምሮ በኃያላን ሊቀላ የሚፈለግ ስደተኛ፣ ተፈናቃይ ሕጻን ነበር። ከተፈናቀለበት ሲመለስም ወደቤቱ ሊመለስ ስላልቻለ በናዝሬት አደገ። በውሃ ተጠምቆ ሲወጣ ከሰማይ የተወደደ ልጅ መሆኑ ቢነገርለትም በገዛ ቀየው የተገፋ፣ ማስጠንቀቂያው፣ ትምህርቱ፣ ልምምዱ ሁሉ ብዙ ንትርክ የሚያስነሳበት ዓይነት ነበር። ስልጣን አልነበረውም። የሚያደርገውን ሁሉ በምን ስልጣን እንደሚያደርግ ማብራራት ይጠበቅበት ነበር። የሚበላውን ሌሎች የሚሰጡት ድኻ ነበር።

እርሱ ግን ለማስረዳት በሚከብድ ኃይል የተሞላ ነበር። በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ወደምድረበዳ ሄዶ ለአርባ ቀናት ተርቦና ተጠምቶ፣ በሰይጣን ተፈትኖ ይመጣል። ሕሙማንን ሲነካ ይፈወሳሉ። አጋንንት በፊቱ ይርዳሉ። "እውነትም ኃያል!" በማለት የመጥምቁ ዮሐንስን ምስክርነት ለማጽናት እገደዳለሁ። ከማቴዎስ ገጾች ላይ ብቅ የሚለው በስደት የሚኖረው፣ ተፈናቃዩና "ጎዳና አዳሪው" ኢየሱስ በአንዳች ኃይል የተሞላ የተስፋ ገንቦ ሆኖ ነው።

________

ብጹዕ ሆኖ

በመንፈሱ ድኻ ... የመንግሥተ ሰማያት የእርሱ የሆነ፣ የሚገባ፣ ሌሎችን የሚያስገባ ድኻ

የሚያዝን... የሚጽናናና ሌሎችን አልቃሾች የሚያጽናና።

የዋሕ... በመስቀሉ ሞት ምድርን የሚወርስ፣ ቀሊል ቀንበሩን ሌሎች ላይ አድርጎ ራሳቸውን ወደመካድ የሚመራ ልዝብ፣ ልስልስ መሪ፣ ዓለምን የሚያንበረክክ ጽኑ ፍቅር።

ጽድቅን የሚራብ፣ የሚጠማ... የሞቱን ጽዋ ጨልጦ የራሱን ብቻ ሳይሆን የሌሎችን የጽድቅ ረሃብ የሚያረካ።

ምህረትን የሚያደርግ፣ ለጠላቶቹ የሚሞት ... በእግዚአብሔር አብ የትንሳዔን ምህረት የሚያገኝ፣ የትንሳዔን ምህረት የሚያስገኝ።

ሰላምን የሚያወርድ፣ ጨቋኞቹ እየሰቀሉት የሚመሰክሩለት ... "እውነትም ይኽ ሰው የእግዚአብሔር ልጅ ነበር!" (ማቴ. 27፥54)

ስለጽድቅ ብሎ የተሰደደ ባለመንግሥት።

_________

እኔ ደካማዋ ላይ በረከትህ ይውረድብኝ ጌታዬ! 🤲

ሳራ አብደላ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ኢየሱስ ክርስቶስ የአጽናፈ ዓለሙ ጌታ የቤተክርስቲያን ራስ ነው!!!

የሐዋርያው ጳውሎስ የቆላስይስ ደብዳቤ ስለክርስቶስ ኢየሱስ አጭር ነገር ግን አስደናቂ የሆነ እውነታን ይዟል። በተለይ ቆላስይስ 1:15-20 ያለው "መዝሙር" ለአጠቃላይ መልእክቱ መሰረት ነው። "ክርስቶስ እርሱ የአጽናፈ ዓለሙ ጌታ ነው" በሚል እውነታ ክርስቶስን ከአንድ ቡድን ወይም ከአንድ የተወሰነ ጉዳይ አውጥቶ እጅግ በላቀ መልኩ የአሮጌውም የአዲሱም ዓለም (ፍጥረት) ጌታ አድርጎ ይስለዋል። ይህ በሰው ብልሃት የተፈጠረ ሳይሆን በክርስቶስ በራሱ ስራ የተረጋገጠ እውነታ ነው። ታዲያ ለአጽናፈ ዓለሙ ክርስቶስ (cosmic Christ) ምላሻችን ምንድን ነው? እርሱ ጌታ እንደሆነ መቀበል። እንደተቀበልነውም ጌትነቱ ራሳችንን አስተካክለን መኖር።

ምላሻችን ቆላስይስ 1:15-20 ላይ ያለውን እውነት ከመዘመር ማለፍ አለበት። ስለክርስቶስ ያለን መረዳት እያደገና ጥልቅ እየሆነ ሲሄድ ለሕይወት የምንሰጠው ትርጉምና ዋጋ በእጅጉ እየተለወጠ ይሄዳል። በመረዳት ባለጠጋ ስንሆን ክርስቶስን እያወቅን ስናድግ ስለሁሉም ነገር ያለን እይታ (interpretation) ይቀየራል። "የተሰወረ የጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ በእርሱ ነውና።" (ቆላ 2:3)። ክርስቶስን በመሐል ስናደርገው (ስለሆነ) ማለትም የፍጥረት ሁሉ መዓከለኛ (center) አድርገን ስናየው አዲስ የአስተሳሰብና የትኩረት መዓከል (new center of consciousness and orientation) ይፈጥርልናል። እርሱ ራሱ ሁሉን ነገር ለማየት የምንቆምበት ዓለት ይሆነናል።
ክርስቶስ ከጨለማ ስልጣን ሁሉ የዳንበት ወደአዲስ ዓለም የተሻገርንበት የድነታችን ራስ ነው (ቆላ 1:12-13)። ይህ ከመዘመርም ሆነ ከማሰብ የሚያልፍ እጅግ የላቀ ዋጋ ያስከፈለ ሥራ ነው። ይህንን በማወቃችን ልባችን በደስታ አንደበታችን በምስጋና ይሞላል። በውድ ልጁ ሞት በመስቀሉ ላይ ባፈሰሰው የከበረ ደም ከእርሱ ጋር ታረቅን (ቆላ 1:19-22)።

በአሁኑ ዓለም ስንኖርም ህይወታችን በተስፋ የተሞላ ነው። ተስፋንም የሚያንጸባርቅ ነው። ህይወታችን ያለው መጨረሻው ጥፋት በሆነ ምትሃታዊና ምስጢራዊ ዓለም ውስጥ አይደለም። ህይወታችንን የምንኖረው በአምላካችን ማለትም በጌታችን በክርስቶስ በተፈጠረና በተጠበቀ ዓለም ውስጥ ነው (ቆላ 1:16, 3:3)። የአጽናፈ ዓለሙ ጌታ አስደናቂና የከበረ ፍጻሜን ከምንጠብቀው በላይ የሆነ የአዲስን ፍጥረት ተስፋ ሰጥቶናል። ይህ ተስፋ በሰማይ ተዘጋጅቶልናል (ቆላ 1:5)። ተስፋውም የወንጌላችን ተስፋ ነው (ቆላ 1:23)። ተስፋውም ህይወታችን የሆነው የራሱ የጌታችን መምጣት ነው (ቆላ 3:4)።

ክርስቶስ የህይወታችን (በአሳብ በተግባር) መዓከል (the center) ሲሆን የእኛን መገዛትና ታማኝነት (allegiance) በመጠየቅ ሚዛን ሊያሳጡን የሚፈልጉ ብዙ አመለካከቶች ድምጾችና እሴቶች ባሉበት የአእምራችንንና የተግባራዊ ህይወታችንን ሚዛን ያስጠብቅልናል። በዚህም በሰማይ ከተዘጋጀልን ተስፋ ሳንጎድል ጸንተን እንቆማለን (ቆላ 1:23)። ዋስትናችን በክርስቶስ ላይ ያለ ጽኑ እምነት ብቻ ነው (ቆላ 1:27-28)። ዋናው ክርስቶስ ተስፋችን በእኛ መኖሩ ነው። ይህንን የሚተካ የሰው ፍልስፍና ትምህርት ወግ ቀኖና ባህል የለም። ከክርስቶስ ውጪ ሁሉም የሰው ሥርዓትና ትምህርት ነው (ቆላ 2:22)። የሚያስፈልገን እርሱ ብቻ ነው። በእርሱ ሆነን ከቀጠልን ሙሉ ነንና።

አምልኳችን ክርስቶስን ያማከለ ነው። በመንፈስ የሆነ ከልብ የሚፈልቅ ክርስቶስን በሚገባ ከማወቅ የሚመነጭ አምልኮ በቅዱሳም ህብረት መካከል የሚተገበር ዋና ነገር ነው (ቆላ 3:16)። የተቀበልነው ወንጌል ማለትም የጌታ ቃል በህብረት ለምናደርገው ነገር ሁሉ (ማስተማር መገሰጽ መቀኘት መዘመር) መሰረት ነው። ለአምልኳችንም ሆነ ለምናደርገው ነገር ሁሉ ጌታችን ምክንያት ነው (ቆላ 3:17)።

የአጽናፈ ዓለሙ ክርስቶስ የህይወታችን ጌታ ሲሆን ራሳችንን መምራት እናቆማለን። እርሱ በተግባር የቤተክርስቲያን ራስ ሲሆን በሰዎች መካከል ያለው የዘር የቀለም የጎሳ የጾታ ልዩነቶች እንደተወገዱና ሁሉ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት እንደሆነ የሚያሳይ ህይወት እንኖራለን (ቆላ 3:10-11)። የክርስቶስን ጌታነት መቀበል ትሁት ቸር ታጋሽ እውነተኛ የታመነ ይቅር ባይ የሚያደርግ ልምምድ ነው (ቆላ 3:12)። በክርስቶስ የሆኑ ራሳቸውን ያጡ ናቸውና በሌላው ላይ አይሰለጥኑም። ሌላውን አያታልሉም። የሚያሳፍር ንግግር የላቸውም። በማህበረሰቡ መካከል ያላቸውም የቤተሰብና የስራ ህይወት የክርስቶስ መዓዛና ክርስቶስ በጌታነቱ የሚታይበት መድረክ ነው (ቆላ 3:5-4:6)።

ዛዲግ ብርሃኑ

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

"ዩቲዩበሮች" ወይስ "ክርስቲያን ጋዜጠኞች" #2

ነፍሱን ይማረውና ቢኒያም ሽታዬ ባክ ሳያደርግ በፊት (መጀመሪያውኑስ በጌታ ነበረ እንዴ የሚል ጨካኝ መቼም አይጠፋም😂) "ጴንጤ ነኝ" ባይ "ዩቲዩበር" ነበር። (አሁን እንኳን "የኦርቶዶክስ ዩቲዩበር" ሆኗል - ወደ ጥልቁ ፈቀቅ ብሏል😂) እኔም (ያኔ) በገፄ ላይ "ቢኒያም ዩትዩበር ነው" ብዬ ፅፌ ነበር። ልጥፌን ተከትሎ ከእርሱ ጋር በስልክ የመገናኘትና የማውራት (የመነታረክ ማለት ይሻላል) አጋጣሚው ተፈጥሮ ነበር።

እርሱም "ሃሰተኞችን በዩቲዩብ ቻነሌ የምጋብዘው ሃሳዊነታቸውን የበለጠ ለማጋለጥ ነው" የሚል "ሃሳዊ" መከራከሪያ አቅርቦ ነበር። እኔም በወቅቱ የመልስሁለት:- አንደኛ ሃሳውያኑን በበቂ ሁኔታ ስህተታቸውን ለመሞገት አልቻልህም። ሁለተኛ የጋበዝሃቸውን ሃሳውያን "የተወደደው ወንድም እገሌ ...፣ የእግዚአብሔር ሰው እገሌ....ወዘተ" እያልህ ማቅረብህ መርሃ ግብርህ ሃሳውያኑን ለመጥቀም የተዘጋጀ ያስመስለዋል ብዬው ነበር። ነፍሱን ይማረውና። ዛሬም ዩቱበሮቹ ተመሳሳይ መንገድ እየሄዱ ተመሳሳይ መልስ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

በቀዳሚው ልጥፍ የክርስቲያን ጋዜጠኞች ተልዕኮ ምንድነው? በማለት ጠይቀን በአንደኝነት "የክርስቲያን ጋዜጠኞች ቀዳሚው ተልዕኮ ክርስቲያናዊ እውነት እንዲገለጥ መትጋት ነው" የሚለውን "የሮበርት ቤዝን" ንግግር አጣቅሰን ነበር። እዚህ ላይ "ኪያ ሾው" የሚባለው የዩቲዩብ ቻነል ላይ የሚያቀርበውም ሰው (አብይ) በቀዳሚው ልጥፍ ካነሳኋቸው ሁለት ሰዎች የተለየ አለመሆኑን መጠቆም እፈልጋለሁ። እንዲያውም ይህ ሰው በጃፒ አዳራሽ ፊት ወንበር ተቀማጭም ገፅታ ገንቢም ነው። ወደ ሁለተኛው እንለፍ:-

2. ክርስቲያናዊ ንፅረተ ዓለም መፍጠር

እንደ ሮበርት ቤዝ ገለፃ "የክርስቲያን ጋዜጠኞች" ሁለተኛው "ተልዕኮ" "ክርስቲያናዊ ንፅረተ ዓለም (Christian world view) መፍጠር ነው" ይህም ማለት አማኞች በሚኖሩበት ማህበረሰብ መካከል በሚያቀነቅኑት ሃሳብ ቅቡልነት እንዲያገኙና ትምህርቶቻቸው፣ የአምልኮ ስረዓታቸው እንዲሁም ገፅታቸው ገዢ ሆኖ እንዲወጣ ማድረግ ነው ማለታቸው ነው።

እዚህ ጋር ደግሞ "Divine Show" በሚባለው የዩቲዩብ ገፅ ላይ የሚያቀርበውን ሶፎንያስን ሞላልኝን ማንሳት ይቻላል። ይህ ሰው ክርሰቲያናዊ ንፅረተ ዓለም በምንኖርበት ማህበረሰብ መካከል "ገዢ እንዲሆን" የሚደረገውን ጥረት በማበላሸት ረገድ አቻ አልተገኘለትም። በሌሎች ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ ወንጌል አማኙን "የአይምሮ ህመምተኞች" መከማቻ አድርጎ በመሳል እና የቤተክርሰቲያንን ገፅታ በማበላሸት "ክርስቲያናዊ ንፅረተ ዓለም" ጎልቶ እንዳይወጣ ይለፋልና።

ሶፎንያስ በርካታ የአይምሮ ህመምተኞችን በመድረኩ አቅርቧል። እንዲያውም እንግዶቹን ፍለጋ አማኑኤል ሆስፒታል አካባቢ ነው የሚውል ነው የሚመስለው።
በእርግጥ አይምሮውን ስቶ "ከእግዚአብሔር ጋር እደባደባለሁ" እንዳለው አይነት ሰው መሆን የሚያሳዝን ነገር ነው። ነገር ግን ይህንን አይነቱን "የአእምሮ ህመምተኛ" ወደ ህክምና ተቋም ከመውሰድ ይልቅ "በቶክ ሾው" ስም ወደ አደባባይ በማምጣት የዩቲዩብ መሸቀያ ማድረግ እጅጉን አሳዛኝ አሳፋሪም ነው።

የመንግስት ጋዜጠኛ እንኳን ርዕዮተ (ንፅረተ) ዓለሙን አይዘነጋም። ምንም ዓይነት መርሃ ግብር ያዘጋጅ ከተልዕኮው ዝንፍ አይልም። እንግዳ ቢጋብዝ፣ ዜና ቢዘግብ፣ ሙዚቃ እንኳን ቢመርጥ ከተልዕኮው ዝንፍ አይልም። የመንግስት ጋዜጠኛ ነዋ! ለርዕዮተ ዓለሙ ይጨነቃላ!

እና ምን ይሻላል?

መፍትሔው፤ እነኚህ ስማቸውን በቀዳሚውና በዚህኛው ልጥፍ ያነሳኋቸው ሰዎች "ክርስቲያን ጋዜጠኛ ነኝ" ካሉ በቅድሚያ ሞቲቫቸውን ቢመረምሩ ደግ ነው። እንዲሁም ስለ "ክርስቲያናዊ ጋዜጠኝነት ተልዕኮ" ምንነት ቁጭ ብሎ ማጥናቱም ተገቢ ነው። ስለ ነገረ ክርስቶስ ጠንቅቀው ሳያውቁ በነገረ ክርስቶስ ላይ የሳተን ሰው ጋብዞ ስቃይ ከመብላት በጎችንም ከማስበላት ወደ ነገረ መለኮት ትምህርት ቤት ጎራ ማለቱም አስፈላጊ ነው።

ሌላው፤ መቼም ምንም ሃሳዊ የሆነ መምህር አትጋብዙ አይባልም። እውነተኛ ብለው የጋበዙትም ሰው ሊዘባርቅ ይችል ይሆናል። ነገር ግን ክርሰቲያናዊ እውነቶችን ጠንቅቆ ማወቅ እና በቃለ መጠይቆች መካከል ስህተት ሲገኝ መሞገት፤ ሞመገት ሲያቅታቸውና ከተለያየ አቅጣጫ ሂስ ሲቀርብባቸው በቶሎ ማረም። እንዲሁም የሚጋብዙትን ሰው "የአይምሮ ጤና" ቀድሞ ማረጋገጥ ይህንን ከጠሉ ደግሞ ስራውን ማቆም እና ለሚችሉት መተው ይጠቅማቸዋል እላለሁ። "እንቢኝ!" ካሉ ግን "ከክርስቲያናዊ ተልዕኮዎች" ተፋቶ "ክርስቲያን ጋዜጠኛ" መሆን አይቻልምና "በዩቲዩበርነቱ" ገንዘባቸውን እየሰሩ መቀጠል ይችላሉ። ፈራጅ ግን በደጅ አለ!

ቴዎድሮስ ተጫን

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

https://youtu.be/3RFLC7uX1UU?si=0SeHovVWQEwwMV-B

Читать полностью…

ነገረ ወንጌላውያን

ዶክትሪን ወይስ ፍቅር?

ዶክተር ቤተ (ብዙዎች ጋሼ ይሏቸዋል) ለቅዱሳን ፍቅር ተጨናቂ እንደሆኑ ገፅታቸውን እና ቃለ መጠይቃቸውን የተመለከተ በቀላሉ የሚረዳው ነው። "ዶክትሪኑን ቀነስ ይበልና ፍቅር ይብዛልን" የሚለው ንግግራቸው ደግሞ ቅንነታቸውን የበለጠ ያመለክታል።

ነገር ግን መሠረታዊ አስተምህሮዎችን ሳይቀር እየዳጡ "በፍቅር ተቀበሉን" የሚሉና "ሃሳውያንን በፍቅር እንቀበላቸው" ባዮች በበዙበት በዚህ ዘመን እንደ እንደ ጋሽ ቤተ ያሉ አባቶች "ከዶክትሪን ይልቅ ፍቅር እንዲበዛ እመኛለሁ" ብለው የሚናገሯቸው "የየዋህነት" ንግግሮች በጌታ በጎች መካከል ላደፈጡ ጨካኝ ተኩላዎች ጥሩ ለምድ ነው የሚሆናቸው።

ይኸው በጋሻው እንኳን መቼ እንደመጣ የትኛው የወንጌላውያን አጥቢያ የክትትል ትምህርት እንደተማረ በውል ሳይታወቅ "ስላሴ በስም አንድ ነው" እያለ በወንጌላውያን መድረክ ሰባአልዮሳዊ ትምህርት ማስተማር ጀምሯል። (ለመሆኑ ግን ከሰባቱ አዕማደ ትምህርቶቹ ዋነኛው በበጋሻው መናዱን ካውንስሉ ሰምቷል?)

ለማንኛውም ሐዋርያው ጳውሎስ “እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ” (ኤፌ 4፥15) ብሎ መናገሩን ማስታወሱ ጥሩ ነው። እውነት (ዶክትሪን) እና ፍቅር በአንድ ተጠምደው ሊጓዙ ይገባልና። እንዲያማ ካልሆነ ራስ ወደሆነው "ክርስቶስ" እንዴት ማደግ ይቻላል? ስለዚህ ከዶክትሪን ይልቅ ፍቅር እንዲበዛ ከመመኘት ይልቅ ሁለቱንም ለመያዝ መልፋት ቢበዛ ደግ ነው እላለሁ። (እንደ ታናሽ ወንድም)

ቴዎድሮስ ተጫን

Читать полностью…
Subscribe to a channel