nehmeya | Unsorted

Telegram-канал nehmeya - ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

-

ይህ የየካደ/ም/ቅ ኪዳነ ምህረት እና መድሀኒአለም አካባቢ ወጣቶች ማህበር የቴሌግራም ቻናል ነው። በቻናላችን ላይ ያለዎትን ሀሳብ አስተያየት ⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩ @Mahebranehmyabot ያድርሱን። ከቴሌግራም በተጨማሪ ፌስቡክ ላይም ያገኙናል። https://m.facebook.com/ማህበረ-ነህምያ-ዘ-ኮተቤ

Subscribe to a channel

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

ዕለተ ሰኑይ /ሰኞ/ ይህ ዕለት አንጾሖተ ቤተ መቅደስ /የቤተ መቅደስ መንጻት/ እና መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፡፡ /ማር.11-11፣ ማቴ.21-18-22 ሉቃ.13-6-9/፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ «ወመሰለ ሎሙ ወይቤሎሙ አሐዱ ብእሲ በለሰ ቦቱ ውስተ አጸደ ወይኑ ወየሐውር ይንሣእ ፍሬሃ ወኢይረክብ …»፤ ይህንም ምሳሌ አለ ለአንድ ሰው በወይኑ አትክልት የተተከለች በለስ ነበረችው ፍሬም ሊፈልግባት ወጥቶ ምንም አላገኘም፡፡ በማለት በበለስ ስለተመሰለ የሰው ልጅ ሕይወት በማሰብ እንዲመለስ ንስሐ እንዲገባ በሕይወትም እንዲኖር እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ማሳሰቡን ያጠይቃል፡፡ ንስሐ አልገባም አልመለስም ያለም በለሷ እንደጠወለገችና እንደተቆረጠች ሁሉ ፍሬ ባለማፍራታቸው እንደሚቆረጡ እንዲሁም ወደ እሳት እንደሚጣሉ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል፡፡ በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ፍሬ የተባለ ደግሞ ሃይማኖትና ምግባርን ነው፡፡ ሁላችን ቤተ እስራኤላውያን ፍሬ ሃይማኖት ወምግባር አስተባብረን ይዘን መገኘት ይገባናል፡፡ ፍሬ አልባ እንዳንሆን ጌታ ሲመጣም እንዳናፍር የመጽሐፉን ቃል ልንጠብቅና ልንፈጽም ይገባናል፡፡ በዚህ የሕማማት የመጀመሪያ ቀን ዕለተ ሰኑይ የምናስበው የምንዘክረው የሰው ልጅ ሕይወት በከንቱ በቸልተኝነት እንዳይደክም እንዳይጠወለግ እንዳይደርቅ ወደ እሳትም እንዳይጣል ማድረግ ይገባናል፡፡
@Nehmeya @Nehmeya
☞ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ።
☞ መልካም ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

ሆሣዕና
ሆሣዕና የአብይ ፆም ፰ተኛው ሳምንት ነው።በዕብራይስጡ ‹‹ሆሼዕናህ›› የሚል ሲሆን ትርጕሙም‹‹እባክህ አሁን አድን አንድም መድኀኒት›› ማለት ነው፡፡ይህ በአል የሚከበረው ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ወደ እየሩሳሌም ቤተ መቅደስ በመግባቱ ምክንያት ነው።
ለምን ጌታችን በአህያ ውርንጫ ተቀምጦወደ ቤተ መቅደስ ገባ?
1. የነብያትን ትንቢት ለመፈፀም ትንቢተ ዘካርያስ ፱፥፱ ላይ እንዲህ ይላል«የጽዮን ልጅ ሆይ ደስ ይበልሽ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያና በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፡፡»የተባለውን ቃል ለመፈፀም
2. አህያ የተናቀች እንስሳ ብትሆንም ጌታ ግን ትህትናውን ለማሳየት በአህያ ውርንጫ መጥቷል።
ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ዘመሩ?
1. ዘንባባ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ አይበላውም አንተም ባሕርይህ አይመረመርም ሲሉ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ዘመሩ።
2. ዘንባባ ደርቆ እንደገና ሕይወት ይዘራል፤ አንተም የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ብለው ነው
3.ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው።
4. ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው ዘንባባ ይዘው የዘመሩት።
☞ የሆሳዕና በአል ታሪኩን በ ማቴ ፳፩፥፩-፲፯፣ ማር ፲፩፥፩-፲፣ ሉቃ ፲፱÷፳፱-፴፰ እና ዮሐ ፲፪÷፲፪―፲፭ ላይ እናገኘዋለን።
@Nehmeya @Nehmeya
✞ እንኳን ለበአለ ሆሳዕና አደረሰን።መልካም በአል።
✞ መልካም እለተ ሰንበት ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

           መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር

መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር (2)
ይቀሰቅሰኛል ለስሙ እንድዘምር (2)
             አዝ
ፊቱን እየፀፉት/ እየተንገላታ (2)
በጦር እየወጉት /ይሰጣል ይቅርታ (2)
እነርሱ እየጠሉት/ እርሱ ይወዳቸዋል (2)
አስረው ሲጎትቱት/ ይከተላቸዋል (2)
                 አዝ
ፃድቁን ሃጥእ ነው/ እውነትን ሃሰት (2)
እያሉ ሲጮሁ /ይሰቀል ይሙት (2)
እየመረመረው/ ፍጡር ፈጣሪን (2)
ክርስቶስን አስሮ/ ፈታው በርባንን (2)
                    አዝ
ጀርባውን ሲገርፉት በሚያቃጥል ጅራፍ
በምህረት ያዛቸው በይቅርታው እቅፍ (2)
ጨክነው ሲያጠጡት መራራ ሃሞት (2)
ደሙን አፈሰሰ ጎኑን ሲወጉት (2)
                አዝ
ግምጃን አለበሱት/ ቀሚሱን ገፈው (2)
በራሱም አኖሩ/ እሾህ ጎንጉነው (2)
የአይሁድ ንጉስ ሆይ/ እያሉ ዘበቱ (2)
ለህይወት ሆናቸው/ የክርስቶስ ሞቱ (2)
 @Nehmeya  @Nehmeya 
❖ ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያን ፍፁም ሰላም ያድርግልን።
❖ መልካም  ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

በዚህ መንፈሳዊ ጉዞ የምንመለከታቸዉ 
 * የአባታችንን የአቡነ እጨጌ ዮሐንስ የእግራቸዉ አሻራ
 * አባታችን አቡነ እጨጌ ዮሐንስ መዝሙር ዳዊት ይፀልዮበት የነበረ መቀመጫ
 * አባታችን አቡነ እጨጌ ዮሐንስ የረገሟትና ለ800አመታት ያላደገቸውን የሾላ ዛፍ
 * አባታችን አቡነ እጨጌ ዮሐንስን ከደብረ ሊባኖስ ተከትለው የመጡትን 7አፀዶች
 * አባታችን አቡነ እጨጌ ዮሐንስ  ያፈለቋቸዉን ፀበሎች እንፀበላለን
 * በተጨማሪ ተአምረኛዋን ፀሎት ሰሚዋን ስውሯ ማርያምንም እንሳለማለን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

ሰበር ዜና ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር ) አረፉ
(EOTC TV)
መጋቢት ፲፪
ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ ዕድ የሾሙት ጳጳሳት 14 ኤጲስ ቆጶሳት መካከል አንዱ የሆኑት በቀድሞ ስማቸው አባ ኃይለማርያም መለሰ ዶ/ር በጵጵስና ስማቸው ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር ) የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። ብፁዕነታቸው ለረጅም ጊዜ ከሀገር ውጪና በሀገር ውስጥ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሊሻላቸው ሳይችል ቀርቶ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ተለይተዋል።
በረከታቸው ይደርብን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

በስራዬ
በስራዬ የት ይሆን መግቢያዬ(x፬)
ጨነቀኝ ጠበበኝ ኸረ ወዲያልኝ
ጨነቀኝ ጠበበኝ ነፍሴ ወዲያልኝ
                 አዝ
ተሽክሜ የኃጢያት ክምር(x፪)
ይመሻል ይነጋል በከንቱ ስዞር(x፪)
ገሰገሰ ቀኑ ጨለመብኝ(x፪)
ዋ ለነብሴ ምንም ስንቅ አልያዝኩኝ(x፪)
                  አዝ
በድያለሁ ወዳንተ ጮሃለሁ
ይቅር በለኝ እማፀንሃለሁ
ችላ አትበለኝ ከፊትህ ቆሜያለሁ(x፪)
                 አዝ
አለፈብኝ በከንቱ ጊዜዬ(x፪)
እየጓጓሁ ለዚች ለሥጋዬ(x፪)
በንስሐ ሳላጥበው እድፌን(x፪)
ልትደርስ ነው ያች ፈተና ቀን(x፪)
@Nehmeya   @Nehmeya
❖ እግዚአብሔር ሀገራችንን ፍፁም ሰላም ያድርግልን።
❖  ክፉ ነገር የማንሰማበት የተባረከ ቀን
       ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

《 እውነተኛ ሐሴት ትፈልጋላችሁን? እንግዲያውስ ለድሆች መጽውቱ፤ ክርስቶስን ወደ ቤታችሁ ጥሩት፡፡ ይህን ስታደርጉ ማዕዱ ቢነሣም ሐሴቱ አይነሣም፤ ይቀጥላል እንጂ፡፡ በተለይ ደግሞ በዚህ በወርሐ ፆም ይህን አብዝታችሁ አድርጉት።》
              ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
 @Nehmeya  @Nehmeya 
❖ ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያን ፍፁም ሰላም ያድርግልን።
❖ መልካም  ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

ምኩራብ
ምኩራብ የአብይ ጾም ሶስተኛው ሳምንት ነው።ምኩራብ የአይሁዳውያን ቤተ መቅደስ ሲሆን ይሄ ሳምንት ምኩራብ የተባለው ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ እየገባ ለማስተማሩና በምኩራብ የሚሸጡ የሚለውጡ ነጋዴዎችን ለማስወጣቱ ቤተ መቅደሱን ለማስከበሩ መታሰቢያ  ስለሆነ ነው፡፡ማቴ ፳፩፥፲፪―፲፬ እንዲህ ይላል«እየሱስ ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትና የሚገዙትንም ኹሉ አወጣ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጪወችን ወንበሮች ገለበጠና ቤቴ የፀሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተፅፏል እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችውት አላቸው።በመቅደስም እውሮችና አንካሳዎች ወደ ርሱ ቀረቡና ፈወሳቸው።»
@Nehmeya   @Nehmeya
❖ ፈጣሪ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን።
❖  መልካም ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

《 ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ》
        መዝ ፻፳፩፥፩

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

《 ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ》
        መዝ ፻፳፩፥፩

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በዐድዋ ድል የነበራት ድርሻ
☞ ለጦርነቱ በቤተ ክርስቲያን ጸሎተ ምህላ ታውጇል፤
☞ ዘማች ታቦታት ተመርጠው የአዝማች ኮሚቴም ተቋቁሟል፤ ታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስ የዘማች ታቦታቱ መሪ ነበር።
☞ ለመላው ዘማች ሠራዊት ሥነ ልቡናዊ ጥንካሬን (የሰማዕትነት ወኔን) የሰጠ የሰባት ቀናት የቁም ፍትሐት ተደርጓል።
☞ ሊቃውንቱ ከጦርነቱ በድል እንደምንመለስ በቅኔያቸው ትንቢት ተናግረዋል።
☞ ዐፄ ምኒልክ የክተት ዐዋጅ ካስነገሩ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሄደው “አምላከ ቅዱስ
ጊዮርጊስ ድሉን ቢሰጠኝ ይህን ቤተ ክርስቲያን የሣር ክዳኑን ለውጨ ባማረ ሕንጻ አሠራዋለሁ” ብለው ብፅዓት አድርገዋል፡፡
☞ ከምርኮኛ የጣሊያን ወታደሮች አንዱበዐውደ ውጊያው “በነጭ ፈረስ ተቀምጦ ወደ ቀኝ እና ወደ ግራ እየተመላለሰ ‹ወደ ጦርነቱ ግቡ፤ ኢጣሊያኖችን ማርኩ› እያለ ትእዛዝ ሲሰጥ እና ሲወጋን የዋለ ማነው?” ብሎ ጠይቋል፡፡ በጦር ሜዳ ለበቁት ሰዎች ተገልጦ እየታየ ከአርበኞቻችን ጋራ የዋለው ፍጡነ ረድኤት
ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ዐቃቤ መልአክ (Patron Saint)ነው፡፡
ምንጭ፦ ከደውል የፌስቡክ ገፅ
@Nehmeya     @Nehmeya
❖ እንኳን 127ኛው የአድዋ የድል ቀን
    መታሰብያ በአል አደረሰን።
❖ ፈጣሪ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን
     መልካም ቀን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

ደብረ ማርያም ቆረቆር ቤተክርስትያን

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

☞ ለዛሬ የነበረን የጥያቄ መልስ መርሀ ግብር የተጠናቀቀ ሲሆን ለተሳተፋችሁ በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን። 🙏🙏🙏🙏 🙏🙏 መልሶቹ እነዚህ ናቸው።
  ፩ 1. ሀብተ ክህነት
2. ሀብተ መንግሥት
3. ሀብተ መዊዕ (የማሸነፍ ሀብት)
4. ሀብተ ትንቢት
5. ሀብተ ኃይል
6. ሀብተ በገና
7. ሀብተ ፈውስ ናቸው።
  ፪ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ናቸው።
  ፫ በ 325 ዓ.ም. በአሪዮስ ምክንያት ነበር።
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
☞ የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችን በየሳምንቱ እሁድ እሁድ የሚኖረን ሲሆን በቻናላችን ላይ ያለዎትን ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት በ ⇩⇩⇩⇩⇩⇩በ
@nehmya
ያድርሱን።
                መልካም ምሽት

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

☞ የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችን ከምሽቱ 2:00 ላይ የሚጀምር ስለሆነ ሁላችሁም እንድትሳተፉ በልኡል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

በርጠሚዮስ ነኝ
በርጠሚዬስ ነኝ አይነ ስውር ምስኪን
ከሩቅ የሰማሁት የጌታዬ ድምፁን
ከብዙ ሁካታ ጉርምርምታ መሃል
የክርስቶስ ድምፁ በግልፅ ይሰማኛል
                     አዝ
የልቦናዬ አይን ፈፅሞ ታውሯል
አይኔን ፈውስልኝ በርጠሚዮስ ይላል
አብዝቼ እጮሀለው ጌታ ማረኝ ብዬ
በውስጤ እየታየኝ ሲምረኝ ጌታዬ
                      አዝ
አንተን አይሰማህም ይሉኛል ብዙዎች
በኅጥያት ሰንሰለት ታስረሃል እግር ከወርች
ስለዚህ አትልፋ ሲኦልን ጠብቃት
እንደዚህ ቢሉኝም እጮሀለው ሳልታክት
                       አዝ
የከበበውን ሰው ገለል በሉ እያለ
በደሌን በደሙ ዋጋ እየከፈለ
ስለእኔ የሞተው ኢየሱስ ይመጣል
የልቦናዬን አይን ገልጦ ያሳየኛል
                        አዝ
አብዝቼ እጮሀለው ጌታ ማረኝ ብዬ
በግልፅ እየታየኝ ሲምረኝ ጌታዬ
በውስጤ በደልስ ህይወቴ ዝላለች
በአምላኬ ቸርነት ህይወት ካላገኘች
@Nehmeya   @Nehmeya
✞ እግዚአብሔር ጾማችንን በሰላም እንዳስጀመረን በሰላም   ያስፈጽመን።
✞ መልካም ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

@Nehmeya

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

                 መጋቢት ፳፯
እንኳን ለዚች ቀን አደረሰን አደረሳችሁ ይህች ቀን ለእኛ ለሰው ልጆች ከሲኦል እስራት ነፃ የወጣንባት እለት ነች።በዚች እለት ነው ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ አዳምን ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሀለው ያለውን ቃል ለመፈፀም ምንም በደልና ጥፋት ሳይኖርበት በጎልጎታ የተሰቀለበት ቀን ነች።
ዮሐ ፲፭፥፲፫ ላይ እንዲህ ይላል«ነፍሱን ስለወዳጆቹ  ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።» አምላካችን ነፍሱን ሰጥቶ ነው ፍቅሩን ያሳያን። አባቶቻችን እንደሚሉት እግዚአብሔር አለምን ከፈጠረበት ጥበብ ይልቅ  ያዳነበት ጥበቡ ድንቅ ነው ይላሉ። እውነት ነው አለምን ሲፈጥር ቃል ተናግሮ ይሁን ሲል ሁሉም ነገር ሆነ ሲያድነን ግን ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከንፅህት  ቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና ተወልዶ በምድር ላይ ከሀጥያት በስተቀር ሰው ያደረገውን አድርጎ።በዮሐንስ እጅ በ፴ አመቱ ተጠምቆ በእለተ አርብ መጋቢት ፳፯ በጎልጎታ ተሰቅሎ  በእለተ እሁድ ከሙታን ተለይቶ ተነስቶ ነው ያዳነን እና ከዚህ በላይ ምን የሚደንቅ ነገር አለ።
@Nehmeya   @Nehmeya
✥ እንኳን ለመድሀኒአለም አመታዊ ክብረ በአል አደረሰን አደረሳችሁ።
✥ መልካም በአል ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

እንኳን ለሊቀ መልአኩ ለቅዱስ ገብርኤል ወርሀዊ ክብረ በአል አደረሰን

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

           በርጠሚዮስ ነኝ
በርጠሚዬስ ነኝ አይነ ስውር ምስኪን
ከሩቅ የሰማሁት የጌታዬ ድምፁን
ከብዙ ሁካታ ጉርምርምታ መሃል
የክርስቶስ ድምፁ በግልፅ ይሰማኛል
            አዝ
የልቦናዬ አይን ፈፅሞ ታውሯል
አይኔን ፈውስልኝ በርጠሚዮስ ይላል
አብዝቼ እጮሀለው ጌታ ማረኝ ብዬ
በውስጤ እየታየኝ ሲምረኝ ጌታዬ
               አዝ
አንተን አይሰማህም ይሉኛል ብዙዎች
በኅጥያት ሰንሰለት ታስረሃል እግር ከወርች
ስለዚህ አትልፋ ሲኦልን ጠብቃት
እንደዚህ ቢሉኝም እጮሀለው ሳልታክት
               አዝ
የከበበውን ሰው ገለል በሉ እያለ
በደሌን በደሙ ዋጋ እየከፈለ
ስለእኔ የሞተው ኢየሱስ ይመጣል
የልቦናዬን አይን ገልጦ ያሳየኛል
                አዝ
አብዝቼ እጮሀለው ጌታ ማረኝ ብዬ
በግልፅ እየታየኝ ሲምረኝ ጌታዬ
በውስጤ በደልስ ህይወቴ ዝላለች
በአምላኬ ቸርነት ህይወት ካላገኘች
 @Nehmeya  @Nehmeya 
❖ ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያን ፍፁም ሰላም ያድርግልን።
❖ መልካም  ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

መፃጉዕ
መፃጉዕ የአብይ ፆም አራተኛው ሳምንት ነው። በዚህ ሳምንት ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችንድውያንንስለመፈወሱየሚታሰብበት ሳምንት ነው።በዮሐ ፭፥፪―፲፩ እንዲህ ተፅፎ እናገኛለን«በኢየሩሳሌም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቅያ ነበረች አምስት መመላለሻም ነበረባት በእነዚህ ውስጥ የውሀውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኛዎችና እውሮች አንካሳዎችም ሰውነታቸውም የሰለለ ብዙ ህዝብ ይተኙ ነበር።
አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቅያቱ ወርዶ ውሀውን ያናውጥ ነበርና እንግዲህ ከውሀው መናወጥ በኋላ መጀመርያ የገባው ከማናቸውም ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር በዚያም ከሰላሳ ስምንት አመት ዠምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበር።እየሱስ ይህ ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ እስከ አሁንብዙ ዘመን እንዲሁ እንደነበር አውቆ ልትድን ትወዳለህ አለው። ድውዩም ጌታ ሆይ ውሀው በተናወጠ ጊዜ መጠመቅያቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለሰለት።እየሱስም ተነስና አልጋህ ተሸከም ሂድ አለው።ያም ቀን ሰንበት ነበር።»
@Nehmeya   @Nehmeya
✥ ፈጣሪ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን።
✥  መልካም እለተ ሰንበት። ።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

ለምን አትማሩም?

ከችግር ከመከራ ከስቃይ ከፈተና ስንወጣ እግዚአብሔርን እንረሳለን! ለምን?

''ታሞ የተነሳ አምላኩን እረሳ ''ይላሉ አበው!

አንተም እንደዛው ነህ? ስትታመም መሞቴ ነው በቃ ንስሃ ሳልገባ ምናምን ወደ ቤተ ክርስቲያን እሩጫ ልክ ተጠምቀህ ስትፈወስ ዘወርም ብለህ አታይ ቤተ ክርስቲያን ! ግን ለምን????


እመነኝ ከቤተክርስቲያን ውጪ ህይወት ዋጋ አልባ ናት!

ሥትተኛ በሠላም ያዋልከኝ በሠላም አሳድረኝ ካላልክ
ስትነሳ ደግሞ በሠላም ያሳደርከኝ በሠላም አውለኝ ካላልክ የፈጠረህን ላደረገልህ ነገር ካላመሠገንክ ዋጋ የለህም እመነኝ ማመን ብቻ መንግስተ ሠማያትን አያወርስም አንገትህ ላይ ማዕተብ ስላለ ብቻ መንግስተ ሰማያትን የምትወርስ ከመሠለህ ተሳስተሃል !

መንግስተ ሰማያትስ የሚትገባው ላንተ ሳይሆን ሃይማኖትን ከምግባር ጋር አጣምረው ለያዙ ንስሓ ለገቡ ሥጋ ወደሙ ለተቀበሉ እንጂ እንዳተማ የአፍ የተዋሕዶ ልጅ የኝ ዋጋ አያሠጥም ዋጋ የሚያሠጠውስ መጋደል ነው ወጋ የሚያሠጠውስ መፆም መፀለይ መስገድ መመፅወት ንስሓ መግባት መቁረብ ማስቀደስ ወዘተ.....



ስለዚህ ነቃ በል ወደ ቤተክርስቲያን ሂድ ተማር ንስሓ ግባ ቁረብ!


መልካም ቀን
ዲ/ን ፍቅረ አብ
03/03/2014
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

            ማረኝ መመኪያዬ

ማረኝ ማረኝ ማረኝ መመኪያዬ
አርጅቻለውና በኃጥያት ጎስቁዬ (x፪)
                 አዝ
ከፊቴ ናትና ሀጥያቴ ሁልግዜ
ተውጫለው እኔስ በሃዘን በትካዜ (x፪)
በፍትህ ክፋትን አድርጌአለው እኔ
ምንም ጽድቅ አልሰራው በሕይወት ዘመኔ (x፪)
                   አዝ
ከፍትህ መቅበዝበዝ መሰደድ ፈለኩኝ
ሀጥያት ከሁዋላዬ እያሳደደችኝ (x፪)
ወዴት እሄዳለው መሸሸግያም የለኝ
ምህረት መጠግያ ዋሻ ካልሆነችኝ (x፪)
                   አዝ
የተሰባበረው አጥንቴ እንዲጠገን
በምሕረትና በቸርነት ዳሰኝ (x፪)
የቀና መንፈስን አድስ በልቤውስጥ
ነፍሴ በእሽታ በተስፋ ትለወጥ (x፪)
                    አዝ
ቅዱስ መንፈስን ከኔለይ አትውሰድ
በንስሐ ድኝ በተስፋ እንድላመድ (x፪)
አቤቱ ንጹልብ ፍጠርልኝና
በደስታ ልስከር በፍቅርህ ልጽናና (x፪)
 @Nehmeya  @Nehmeya 
✥ አምላካችን ልኡል እግዚአብሔር ፆማችንን በሰላም አስፈፅሞን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም ያድርሰን።
 ✥ መልካም ቀን  ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

《 ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ》
        መዝ ፻፳፩፥፩

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

《 ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ።ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤》

        2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥1—3
 @Nehmeya  @Nehmeya
✞ፈጣሪ ሀገራችንን ፍፁም ሰላም ያድርግልን።
✞ መልካም ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

《 ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ》
        መዝ ፻፳፩፥፩

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ
ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ 
የአንድ አባት ልጆችኮ ነን
ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ
የአንድ  የእናት ልጆችኮ ነን
ብዙ ነዉ መንግስቱ አብረን እንወርሳለን
ሰፊ ነው ግዛቱ አብረን እንወርሳለን
                  አዝ
የተካፈልኩትን ንብረት
አጥፍቼ ብመለስ ዛሬ
አባቴ ናፍቆኝ ብመጣ
ልቤን አንገቴን ሰብሬ
ለሁላችንም ይበቃል
ብዙ ነው የርሱ መንግስት
አይክፋህ እባክህ  ወንድሜ
ፍቅር ይበልጣል ከሃብት
                አዝ
ፊትህ በሐዘን አይጥቆር
ድንጋዩን ጣለው ወንድሜ
ተቅበዝባዥ እንዳያደርግህ
እጅህ ቆሽሾ በደሜ
ልብህን መልካም ብታደርግ
ያንተም መስዋዕት ያርጋል
ጌታ ለሁሉም እኩል ነው
መታዘዝ ንጉሥ ያደርጋል
                አዝ
ብልጥ ስለሆንኩ አይደለም
የተባረኩት በጌታ
ጽኑ መሻቴን አይቶ ነው
በኩር ያደረገኝ ስመታ
የበቀል ጦርክን ሸሽቼ
በባዕድ አገር ብኖርም
በልጅ በትዳር ባርኮኛል
አብረን እንኑር በሰላም
               አዝ
ብልጥ ስለሆንኩ አይደለም
የተባረኩት በጌታ
ጽኑ መሻቴን አይቶ ነዉ
በኩር ያደረገኝ ስመታ
የበቀል ጦርክን ሸሽቼ
በባዕድ ሀገር ብኖርም
በልጅ በትዳር ባርኮኛል
አብረን እንኑር በሰለም
@Nehmeya     @Nehmeya
❖ ጾማችንን የሀጥያት መደምሰሻ የዳቢሎስ ድል መንሻ ያድርግልን
❖ ፈጣሪ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን።
     መልካም ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

           ደብረ ማርያም ቆረቆር
 ደብረ ማርያም ቆረቆር ከአለት የተፈለፈለ ቤተክርስቲያን ሲሆን በቆረቆር ተራራ፣ ገረአልታ፣ሐውዜን ወረዳ የሚገኝ ሲሆን ለምጋብ ከተማ በጣም
ይቀርባል። አባ ዳንኤል ዘገረአልታ (አባ ዘካርያስ) የማርያም ቆርቆርን ሥርዓተ ገዳም በ13ኛው ክፍለ ዘመን እንደመሰረቱት ታሪክ አጥኝው አይስማን ይጠቅሳል። የገዳሙን ምስረታ ከቤተክርስቲያኑ መታነጽ በኋላ ነው የሚለውን ባለመቀበል የገዳሙን ምስረታ እና መታነጽ ባንድ ዘመን ውስጥ እንደሆነ መላ
ምት ያቀርባል[1]። የአባ ዳንኤል
የወንድማቸው ልጅ የሆነው ዮስጣቴዎስ ከርሳቸው ጋር በዚሁ ደብር ለመኖር በ1272 ዓ.ም. እንደመጣ ታሪክ ያትታል። ደብረ ማርያም ቆረቆር፣ ከዚሁ ዘመን የሚመነጩ
የግድግዳ ላይ ምስላትን እስካሁን ድረስ ጠብቆ በማቆየቱም ይታወቃል።
         ምንጭ፦ አምደ ገዳማት ከተሰኘው የፌስቡክ ገፅ
 @Nehmeya  @Nehmeya 
✥ ከ ደብረ ማርያም ቆረቆር ቤተክርስትያን ረድኤት በረከት ያሳትፈን።ደጇን ተሳልመን በረከት እንድናገኝ የአምላካችን ቅዱስ ፍቃድ ይሁንልን።
✥ መልካም  ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

 †††   በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን  †††
       ውድ የቻናላችን ተከታታዮች የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችንን ከአሁን ሰአት ጀምሮ ተጀምሯል።ጥያቄዎቹም እነዚህ ናቸው
⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
፩ የንጉስ ዳዊት 7ቱ ሀብታት ምን ምን ናቸው?
፪ በ1886 ዓ.ም በፍቼ የተወለዱና ከኢትዮጵያ የመጀምርያ አራት ጳጳሳት አንዱና የምሥራቅ ኢትዮጵያ ጳጳስ የነበሩት። በኋላም ፋሺስት ኢጣሊያ በ1928 ዓ.ም በኢትዮያ ላይ የግፍ ጦርነት ባነሳ ጊዜ እምቢ ለሃገሬ ለሃይማኖቴ በማለታቸው ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም በፋሽስት ኢጣሊያን ሰማዕትነት የተቀበሉት ታላቅ አባት ማን ይባላሉ?
፫  ጉባኤ ኒቅያ የተካሄደው በስንት ዓመተ ምሕረት ነው?? በማንስ ምክንያት ነው የተካሄደው??
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
☞ መልሶቻችሁን እስከ ምሽቱ 4:00 ድረስ በ
 ⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩ በ@nehmyaያድርሱን።
☞ መልሱን ከ4:00 በኋላ በቻናላችን የምንለቅ መሆናችንን እንገልፃለን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

ቅድስት
ቅድስት የአብይ ጾም ሁለተኛው ሳምንት ሲሆን በዚህ ሳምንት ስለ ሰንበት መቀደስ የሚዘከርበት ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው። በተጨማሪ ቅድስት የተባለበት ምክንያት ለ40 ቀን ጌታችን ሲጾም ጾም የጀመረበት ሳምንት ስለኾነም ቅድስት ጾሙን ለማዘከር ቅድስት ተብሏል፡፡
           ሰንበትን ለምን እናከብራታለን?
፩ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ፈጥሮ ከስራው ኹሉ ስላረፈባት፡፡ ዘፍ ፪፥፫
፪ ከአስርቱ ትእዛዛት ውስጥ አንዱ  የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ( ዘፀ ፳ ፥፰) ስለሚል
፫ ጌታችን የተጸነሰባት፣ ትንሣኤውንየገለጠባት፣ ለሐዋርያት ጸጋ መንፈስ ቅድስ የሰጠባት፣ ዳግመኛ ለፍርድ የሚመጣባት ስለሆነች ከሌሎችjn ቀናት ለይተንእናከብራታለን፡፡
@Nehmeya     @Nehmeya
❖ ፈጣሪ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን።
❖   መልካም ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

✥  እንኳን ለእናታችን ለእመቤታች ቅድስት ኪዳነ ምህረት አመታዊ ክብረ በአል አደረሰን።
✥ መልካም ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…
Subscribe to a channel