ይህ የየካደ/ም/ቅ ኪዳነ ምህረት እና መድሀኒአለም አካባቢ ወጣቶች ማህበር የቴሌግራም ቻናል ነው። በቻናላችን ላይ ያለዎትን ሀሳብ አስተያየት ⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩ @Mahebranehmyabot ያድርሱን። ከቴሌግራም በተጨማሪ ፌስቡክ ላይም ያገኙናል። https://m.facebook.com/ማህበረ-ነህምያ-ዘ-ኮተቤ
ዘጠኙ ቅዱሳን
በኢትዮጵያ ውስጥ የክርስትና እምነት እንዲስፋፋ ጉልህ አስተዋጽዖ ካበረከቱ ቅዱሳን መካከል ተሰዓቱ ቅዱሳን ወይም ዘጠኙ ቅዱሳን በጣም ተጠቃሽ ናቸው።
ዘጠኙ ቅዱሳን ወይም ተሰአቱ ቅዱሳን
በኬልቄዶን ጉባኤ ምክንያት በተዋሕዶዎች
ላይ በአውሮፓ፣ በእስያና በመካከለኛው
ምሥራቅ በተነሣው ፈተና የተነሳ ከሮም፣ ከእስያ፣ ከአንጾኪያ፣ከቁስጥንጥንያ፣ ከቂሳርያና ከኪልቂያበስደት የመጡ ናቸው። ስማቸውም ፦
1.አባ አሌፍ፣
2.አባ አረጋዊ፣
3.አባ ጰንጠሌዎን፣
4.አባ ገሪማ፣
5.አባ ጽሕማ፣
6.አባ አፍጼ፣
7.አባ ሊቃኖስ፣
8.አባ ይምዓታ
9.አባ ጉባ ይባላሉ።
ዘጠኙ ቅዱሳን በኢትዮጵያ የክርስትና እምነት እንዲስፋፋ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረከቱ ሲሆን በተለይም ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን አጽንተዋል፣ የተለያዩ መጽሐፍትን ተርጉመዋል፣ ስብከተ ወንጌልን አስፋፍተዋል፣ በርካታ ገዳማትን መስርተዋል፣ ሥርዓተ ምንኩስናን አደራጅተዋል።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@Nehmeya @Nehmeya
❖ ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያን ፍፁም ሰላም ያድርግልን።
❖ መልካም እለተ ሰንበት ይሁንልን።
《 ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።》
የዮሐንስ ወንጌል ፲፭፥፲፫
@Nehmeya @Nehmeya
✞ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያን ፍፁም ሰላም ያድርግል።
✞ ደግ ደጉን የምናደርግበት በጎ በጎውን የምንሰማበት መልካም ቀን ይሁንልን።
ከተራ
ከተራ ከተረ (ዘጋ፣ አቆመ፣ አገደ፣ ከለከለ)
ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ውሃን መከተር ወይም ውሃ መገደብ (መዝጋት፥ ማቆም፥ማገድ፥ ማጠር፥ ዙሪያውን መያዝ፥ መክበብ፥መከልከል) ማለት ነው፡፡
ከተራ ለምን ተባለ ?
በጥምቀት በዓል ዋዜማ በጥር 10 ቀን ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውሃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ወይም ጉድጓድ ተቆፍሮ፤ ድንኳን ይተክላል፥ ዳስ ሲጣል ይውላል።
(ምክንያቱም ጌታችን የተጠመቀበት ወርኀ ጥር በእስራኤላውያን ዘንድ የዝናምና የበረዶ ወራት ስለሆነ ቅዝቃዜውም በወንዞች አጠገብ ስለሚያይል በባሕረ ዮርዳኖስ፥ በዕደ ዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄዱ ሰዎች ድንኳን ተክለው፥ ዳስ ጥለው ያድሩ ስለነበረ ነው)፡፡
ነገር ግን በዚህ ወቅት የምንጮች ውሃ ደካማ
በመሆኑ ውሃው እንዲጠራቀም ወንዶች ጉድጓድ እየቆፈሩ፥ ሴቶች ውኃ በእንስራ እየቀዱ ከወንዞችናከምንጮች ውኃውን ይከትራሉ፥ ይገደባሉ (አሁን በከተሞች ሰው ሰራሽ ግድብ ይገደባል)፡፡ የምዕመናኑ
አብዛኛው ስራ ውሃውን መከተርና መገደብ በመሆኑ ዕለቱ ከተራ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡አንድም በኢያሱ መሪነት እስራኤላውያን የዮርዳኖስን ባሕር ሲሻገሩ ታቦቱን ያከበሩ (የያዙ) ካህናት ሕዝቡ ተሻግሮ እስከሚያበቃ ከወንዙ መሃል ቆመው ነበር ውኃውም እንደ ባሕረ ኤርትራ ግራና ቀኝ
ተከፍሎ እንደ ግድግዳ ቆሞ ነበርና ይህንንም
ለማስታወስ ከተራ እየተባለ ይጠራል፡፡
አንድም ጌታችን በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ
የላይኛው ሸሽቶ እንደ ክምር ተቆልሏል (ከአዳም ጀምሮ እስከ መድኅን መወለድ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ተቋርጦ ለመቅረቱ፥ከአበው ወደ ውሉድ ላለመተላለፉ ምሳሌ)፤
የታችኛውም ወደ ታች ሸሽቶ በመድረቁ (የአዳም ኀጢአት ከሥሩ እንደተነቀለ ዛፍ ሆና ለመውደቋ ምሳሌ) ከተራ እየተባለ ይጠራል፡፡
ውኃ የሚከተርበት ቦታ ባሕረ ጥምቀት፣ ጥምቀተ ባሕር፣የታቦት ማደሪያ እየተባለ
ይጠራል፡፡ ውኃው የሚከተረውም በማግስቱ ጥር 11ቀን ለሚከበረው የጥምቀት በዓል መጠመቂያናየጥምቀትን በዓል ለማክበር እንዲሆን ነው፡፡ ሌሊትማኅሌት ተቁሞ፥ ቅዳሴ ተቀድሶ፥ ጠዋት ጸሎት ተደርሶ የሚጠመቅ ሕፃን ካለ እዚያው ውስጥ ይጠመቃል፡፡ ጐበዛዝትም ለቡራኬ ይዋኙበታል።
ምዕመናንም እንዲሁ ለቡራኬ ይረጩታል፡፡ ያ ስፍራ በዘልማድ ጥምቀተ ባሕር ተብሎ ይጠራል፡፡
# ሥርዐተ_ከተራ
፠ ታቦተ ሕግ ይዞ መጓዝና ወደ ወንዝ መውረድ
የተጀመረው በአሮን ልጅ በአልዓዛር ጊዜ ነው፡፡ ነገር
ግን ቀድሞ በሙሴ ኋላ በኢያሱ መሪነትም ታቦተ
ሕጉን ይዘው የዮርዳኖስን ባሕር መሻገራቸውንም ልብ
ይሏል፡፡ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ሌዋውያን
ካህናት ተሸክመውት ባያችሁት ጊዜ ከስፍራችሁ
ተነስታችሁ ተከተሉት፡፡ /ኢያ.3፥3/ እንዲል፡፡
በከተራ ዕለትየሚከናወኑድርጊቶች ምሳሌነት
አላቸው እነዚሁም
፩ ታቦቱ የጌታችን ምሳሌ
፪ ታቦቱን አክብሮ ይዞ የሚሄደው ካህን የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ምሳሌ
፫ ባሕረ ጥምቀቱ የዮርዳኖስ ወንዝ ምሳሌ
ታቦታቱንአጅበው የሚሄዱት ምዕመናን ወደ_
ቅዱስ ዮሐንስ እየመጡ የንስሐ ጥምቀት
ሲጠመቁ የነበሩ ሰዎች ምሳሌ
፬ ታቦታቱ በከተራ ዕለት ከመንበራቸው ወደ
ጥምቀተ ባሕር መውረዳቸው መድኀኔዓለም
ክርስቶስ በእደ_ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ
ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ከማታው
ጀምሮ መውረዱንና ተራውን ሲጠብቅ አድሮ
መጠመቁን_ያጠይቃል፡፡ ‹‹ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡›› /ማቴ፡ 3፥13/
፭ ጥምቀቱ የሞቱ አርአያ የመቃብሩ አምሳል ነው፡፡
@Nehmeya @Nehmeya
✞እንኳን ለከተራ በአል በሰላም አደረሳን።
✞ መልካም በአል ይሁንልን።
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †††
ውድ የቻናላችን ተከታታዮች የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችንን ከአሁን ሰአት ጀምሮ ተጀምሯል።ጥያቄዎቹም እነዚህ ናቸው
⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
፩ በየአመቱ የከተራ እለት የሚፆመው ፆም ምን ይባላል?
፪ ጌታችን ለምን በ30አመቱ ተጠመቀ?
፫ በጥምቀት በአል ወቅት ታቦታተ ህጉ ወደ ጥምቀተ ባህሩ የሚወርዱት ለምንድን ነው?
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
☞ መልሶቻችሁን እስከ ምሽቱ 4:00 ድረስ በ
⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
@Mahebranehmyabot ያድርሱን።
☞ መልሱን ከ4:00 በኋላ በቻናላችን የምንለቅ መሆናችንን እንገልፃለን።
ዝም ብለን የምንጠላው ሰው
ከሩቅ የምናውቀው አንዳንድ ሰው የለም? ብዙም አናውቀውም:: ቀርበን አውርተነው አናውቅም:: ስናየው ግን እንዲሁ ደስ የማይለንና ያለ ምክንያት የምንጠላው ሰው የለም?
"እሱን ሰውዬ ጥሎብኝ አልወደውም"
"አይ እሱን ልጅ ቀልቤ ትከሻዬ አልወደደውም"
"እኔ እንጃ ለምን እንደሆነ ባላውቅም አልወዳትም:: ምክንያቴን አትጠይቀኝ ግን በቃ እንዲሁ አልወዳትም"
ምንም ምክንያት ሳይኖረን እንዲሁ የምንጠላው ሰው አለ::
እግዚአብሔር ግን
"አንድያ ልጁን እስኪሠጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአል" (ዮሐ 3:16)
ጠላቶቹ ሳለን በልጁ ሞት አዳነን እንደሚል እርሱ እኛን ለመጥላት ብዙ ምክንያት ነበረው:: እርሱ ግን እንዲሁ ወደደን:: ከእኛ ምንም ባያገኝም ስለ እኛ ያለው ፍቅር የእንዲሁ ፍቅር (unconditional love) ነበረ:: እርሱ እንዲሁ ወዶናል እኛ ግን እንዲሁ ሰው እንጠላለን:: ያለ ምክንያት መውደድ ቢያቅተን እንኳን ያለ ምክንያት መጥላታችን (unconditional hate) ቢቀር ምናለ?
የሚያሳዝነው ያለ ምክንያት የጠላናቸውን ሰዎች የበለጠ ለመጥላት በልባችን እስር ቤት ውስጥ በጥላቻ ሰንሰለት እናስራቸውና የበለጠ ለመጥላት ስለእነርሱ ክፉ ክፉ ማስረጃ ለመስማት እንተጋለን:: ጥሩ ነገራቸውን ለመስማት አንፈልግም:: ክፉ ስንሰማ ግን "እኮ እኔ እኮ ዝም ብሎ ትከሻዬ ይነግረኝ ነበር" ብለን በደስታ እንፈነድቃለን:: እንዲሁ የጠላነውን ሰው በምክንያት ለመጥላት በመቻላችን ደስ ይለናል::
እኛ ሰውን ለመጥላት ምክንያት የምንፈልገውን ያህል እንዲሁ የወደደን እግዚአብሔር ግን እኛን ለመማር ሰበብ ይፈልጋል:: ትንሽ በጎነት ቅንጣት ቅንነት ሲያገኝ እጅግ ይደሰታል:: ባለቅኔው "እግዚአብሔር መንግሥቱን በርካሽ ዋጋ ሸጠው:: በቀዝቃዛ ውኃ በዘለላ ዕንባ እና ማረኝ በሚል የወንበዴ ጩኸት!" እንዳሉት እሱ እኛን ይቅር ለማለት የሚታይ በጎነት ቢያጣ ልባችን ውስጥ ገብቶ ትንሽ መጸጸት ካለ ይፈልጋል:: እንዲሁ ወዶናልና እንዲሁ ሊተወን አይፈልግም::
"እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለሆነ
ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳን በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወትን ሠጠን" ኤፌ 2:4
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ ከ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ የቴሌግራም ቻናል ላይ
@Nehmeya @Nehmeya
✞ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያን ፍፁም ሰላም ያድርግል።
✞ ደግ ደጉን የምናደርግበት በጎ በጎውን የምንሰማበት መልካም ቀን ይሁንልን።
☞ ከዛሬ ማለትም 6/5/2013አ.ም ከ10:00ጀምሮ ባንዴራ ስለሚሰቀል ሁላችንም አንገኝ።
Читать полностью…《 በአባቱ ፈቃድ ወረደ በማርያም ዘንድ እንግዳ ሆነ። እግዚአብሔር በንጹሕ ድንግልናዋ ተወለደ። በእንስሳት በረት ተጨመረ፣ የንግሡንም እጅ መንሻ ተቀበለ፣ ከእናቱ ጡቶች ምግብን እየለመነ እንደ ሕጻናት አለቀሰ።》
ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ
@Nehmeya @Nehmeya
† እንኳን ለአባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወርሀዊ መታሰብያ በአል አደረሰን።
† መልካም ቀን ይሁንልን።
☞ ለዛሬ የነበረን የጥያቄ መልስ መርሀ ግብር የተጠናቀቀ ሲሆን ለተሳተፋችሁ በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን። 🙏🙏🙏🙏 🙏🙏 መልሶቹ እነዚህ ናቸው።
፩ ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የተወለደው በቤተልሔም በከብቶች በረት ነው።
፪ ሰብአ ሰገል ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ እጅ መንሻ ያቀረቡት ዕጣን፣ከርቤ እና ወርቅ ናቸው።
፫ ሰብአ ሰገል ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ወደ ተወለደበት በረት የመጡት በኮከብ ተመርተው ነው።
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
☞ የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችን በየሳምንቱ እሁድ እሁድ የሚኖረን ሲሆን በቻናላችን ላይ ያለዎትን ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት በ ⇩⇩⇩⇩⇩⇩
@Mahebranehmyabot ያድርሱን።
መልካም ምሽት
☞ የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችን ከምሽቱ 2:00 ላይ የሚጀምር ስለሆነ ሁላችሁም እንድትሳተፉ በልኡል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
Читать полностью…☞ ነገ ማለትም እሁድ በ2/5/2013አ.ም ፅዳት ስላለ ከጠዋቱ 12:00 ሰአት ላይ ኪዳነ ምህረት በር ላይ እንገናኝ።
Читать полностью…@Nehmeya @Nehmeya
† ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ።
† መልካም ቀን ይሁንልን።
ዮሃንስኒ
ዮሃንስኒ ያጠመቀ/4/
በሄኖን/4/በማዕዶተ ዮርዳኖስ
አዝ
እዩት ትህትናው ያጠመቀ
ፅድቁን ተመልከቱ » »
በባርያው እጅ ሆኖ » »
የጌታ ትምክህቱ » »
አዝ
አንተ መናኝ ሠው ያጠመቀ
ቅዱስ ባዕታዊ » »
በእጅህ ተጠምቆ » »
ኢየሱስ ናዝራዊ » »
አዝ
ተሠውሮ ሣለ ያጠመቀ
ከአለም ተለይቶ » »
አዋጁን ስሙ አለ » »
በጉን አሳይቶ » »
አዝ
ንሠሀ እየገቡ ያጠመቀ
እየተናዘዙ » »
በዮሃንስ ስብከት » »
ለእግዚዐብሄር ተገዙ » »
አዝ
የሠማዩን ጌታ ያጠመቀ
ምድራዊ ሲያጠምቀው » »
ሚስጥር ተገለጠ » »
አለም ሁሉ አወቀው » »
@Nehmeya @Nehmeya
✞ እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዩሐንስ
ወርሀዊ መታሰብያ ክብረ በአል አደረሰን አደረሳችሁ።
✞ ደግ ደጉን የምናደርግበት በጎ በጎውን የምንሰማበት መልካም ቀን ይሁንልን።
ተወለደ
ተወለደ ጌታ ተወለደ(2)
ተወለደ አምላክ ተወለደ
አዝ
አንዲት ብላቴና አስራአምስት ዓመት ልጅ
ጌታን ወለድችው በመላዕክት አዋጅ
በፍፁም ድንግልና ተወለደ ጌታ
ዓለምን የሚታደግ የሰዎች አለኝታ
አዝ
ይህ ዓለም በቃሉ ከተፈጠረበት
ይበልጣል አምላክ ሠው የሆነበት
እንደምን ይገርማል ይሄ ተዋህዶ
አየነው አምላክን እንደሰው ተወልዶ
አዝ
ፍፁም ድንግልና ክብር የተምላሽ
እንደምን አምላክን በማህፀንሽ ያዝሽ
ዓለምን በቃሉ የፈጠረ ጌታ
ወለድችው ድንግል የሄዋን አለኝታ
አዝ
አንቺ ብላቴና እናታችን ማርያም
በምድር ተፈልጎ እንደአንቺ አላገኘም
በሀሳብ በግብር ንፁሕ ስለሆነች
ለአምላኩ ማደሪያ ድንግል ተመረጠች
@Nehmeya @Nehmeya
❖ እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሰላም አደረሰን።
❖ መልካም በአል ይሁንልን።
《 ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻልናል።》
ቅዱስ አትናቴዎስ
@Nehmeya @Nehmeya
† ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ።
† መልካም ቀን ይሁንልን።
አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ
አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ
መነኮስ ሃያል ቤቴ ግባ
ታስባርካለህ ሰውን ምድር
ቅርብ ነህ አንተ ለእግዚአብሔር
አዝ
የበረሃው መናኝ ግሩም ነው ገድልህ
ምድርን አስባርከሃል ከፍ አድርገህ በእጅህ
ተአምር ነው ገዳምህን ላየ
ረድኤት በረከት ገበየ
ልጆችህ በገዳም ውስጥ ያሉ
ሳሙኤል ሳሙኤል ይላሉ
አዝ
አይሻገርብሽ እህልም ኃጥአት
ጌታችን ብሏታል ዋልድባን መሬት
ሕርመት ይዘው ልጆቹ በሙሉ
ቋርፍ ነው ዘውትር የሚበሉ
የጣመ የላመ አጥተን
ዮርዳኖስ ፀበል ምግብ ሆነልን
አዝ
አስኬማውን ለብሶ በገዳም ሲኖር
የትሕትና አባት ነው የሕግ መምህር
ሃሌ ሉያን ሄደን አይተን
አብረን ካንተ እንኑር አልን (x፪)
@Nehmeya @Nehmeya
❖ ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያን ፍፁም ሰላም ያድርግልን።
❖ መልካም ቀን ይሁንልን።
☞ ለዛሬ የነበረን የጥያቄ መልስ መርሀ ግብር የተጠናቀቀ ሲሆን ለተሳተፋችሁ በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን። 🙏🙏🙏🙏 🙏🙏 መልሶቹ እነዚህ ናቸው።
፩ የከተራ እለት የምንፆመው ፆም ፆመ ገሀድ ይባላል።
፪ ጌታችን በ30አመቱ የተጠመቀበት ምክንያት አዳም በ30አመቱ ያጣውን ልጅነቱን(ፀጋውን) ለማስመለስ ነው።
፫ ታቦታት ወደ ጥምቀተ ባህር መውረዳቸው ምሳሌነቱ የጌታችን የአምላካችን የመድሀኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ለመጠመቅ ወደ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ መሄዱን ምሳሌ በማድረግ ታቦታት ወደ ጥምቀተ ባህሩ ይወርዳሉ።
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
☞ የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችን በየሳምንቱ እሁድ እሁድ የሚኖረን ሲሆን በቻናላችን ላይ ያለዎትን ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት በ ⇩⇩⇩⇩⇩⇩
@Mahebranehmyabot ያድርሱን።
መልካም ምሽት
☞ የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችን ከምሽቱ 2:00 ላይ የሚጀምር ስለሆነ ሁላችሁም እንድትሳተፉ በልኡል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
Читать полностью…@Nehmeya @Nehmeya
† እንኳን ለአባታችን ለአጋዕዝት አለም ቅድስት ስላሴ አመታዊ ክብረ በአል አደረሰን።
† መልካም ቀን ይሁንልን።
@Nehmeya @Nehmeya
❖ እንኳን ለእናታችን ቅድስት አርሴማ ወርሀዊ መታሰብያ በአል አደረሰን።ቅድስት አርሴማ ሀገራችንን ፍፁም ሰላም ታድርግልን።
❖ መልካም መልካሙን የምንሰማበት በጎ በጎውን የምናደርግበት መልካም ቀን ይሁንልን።
ምስጉን ነው
ምስጉን ነው የተመሰገነ
ባሪያውን እኔን ይቅር ያለ
ይመስገን ይመስገንልኝ
ጎጆዬን አምላክ ሞላልኝ
አዝ
እጅህ ሰፊ እንደሆነ አውቃለሁ ጌታዬ
የጎደለው ሞልቷል ይድረስ ምስጋናዬ
ያጣሁትን ካንተ አግኝቻለሁ
ሁሉን ነገር ለበጎ ብያለሁ(x፪)
አዝ
ማቄን የቀደደው ደስታ አስታጠቀኝ
ባዶ የነበርኩኝ ደስታ ተሰጠኝ
ሰጪም ነሺም እግዚአብሔር ብቻ ነው
የሰው ድርሻ በር ማንኳኳት ነው(x፪)
አዝ
እገፋለሁ እንጂ እኔ አልጨነቅም
መሠረቴ አንተ ነህ ከቶ አልናወጥም
ስትሰጠኝ የሚታየውን
እንዳትነሳኝ የዘላለሙን(x፪)
አዝ
ቢሰጥ አያልቅበት ለጋስ ክቡር ጌታ
ሁሉን ከወነልኝ በልዩ ችሮታ
ድሆች ስንሆን ሁሉ አለንና
አማላካችን ይድረሰው ምስጋና(x፪)
@Nehmeya @Nehmeya
✞ ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
✞ መልካም ቀን ይሁንልን።
እመጓ ኡራኤል
እመጓ ኡራኤል የሚገኘው ከሞላሌ ከተማ በስተምእራብ አቅጣጫ የ2 ሰአት ከ30 ደቂቃ የእግር ጉዞ ከተጓዙ በኋላ የሚገኝ ሲሆን ቤተ ክርስትያኑን ያሰሩት አጼ ናኦድ እንደሆኑ
በድርሳኑ ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡ በዚህ ቦታ በአመት አንድ ጊዜ የእርገት በአል
በድምቀት ተከብሮ ይውላል፡፡ ቦታው ቅዱስ ዑራኤል የጌታችንን ቅዱስ ደም የረጨበት ሲሆን በአሁኑ ሰአት በየአመቱ የእርገት
በአል ሲከበር መላኩ ቅዱስ ኡራኤል የጌታን ደም የረጨበት ቦታ ድረስ ምእመናን
ከተለያዩ አካባቢዎች በመምጣት እየጎበኙ በረከትን እያገኙ ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በዚሁ አካባቢ የቅዱስ ጊወርጊስ ፈረሶች ከተራራ ተራራ እየዘለሉ ለብዙ ዘመናት
የአካባቢውን ማህበረሰብ ያሰቃይ የነበረውን ሰይጣን ድል ለመንሳት ሲዋጉ ፈረሶቹ የረገጡት የእግራቸው ኮቴ ቅርጽ ድንጋይ ላይ
ቀርቶ የሚታይበት ተአምረኛ ቦታ ነው፡፡ በተጨማሪም ከዚህ ቦታ በስተ ደቡብ
ምእራብ በኩል በገደሉ ስር በአፄ ናኦድ ዘመነ መንግስት የተመሰረተች ቀጭን አምባ ማርያም የምትባል ቤተክርስትያን ስትገኝ በዚች ቅድስት ቦታ ብዙ ተአምራት የተደረጉ ሲሆን ከነዚህም መካከል በጌታችን የስቅለት እለት አጋንንት ወደ ሲኦል የወረዱበት አስደናቂ ቦታ ይገኛል፡፡ በዚህ ገዳም ብዙ አስደናቂ ነገሮች የሚገኙ ሲሆን
፩ ድንግል ማርያም ከልጅዋ ጋር በተሰደደች ግዜ የተቀመጠችበት ቦታ ነው፡፡
፪-የቦታውን ስም እራሱ ጌታቸን ነው ስሙን
ያወጣው /እመጋል/ብሎ፡፡እመጋል
ሲለው /የእኔና የአንች ሀገር (የእናትና የልጅ)ሀገር ብሎታል
፫-በቦታው 2ተራራ አለ
1-ገሊላ(ክሊና)ተራራ:-ይህ ተራራ እመቤታችን
የተቀመጠችበት ና ጌታችን ኢትዮጵያን አስራት ሀገርሽ ትሁንሽ ብሎ ያረገበት ቦታ ነው፡፡
በተራራው ላይ በአየር ላይ የቆመ ድንጋይ ይታያል።በድንጋው ላይ ተወጥቶ 3ግዜ ይዞራል።
2-ቆጵሮስ ተራራ:-ይህ ተራራ ቅዱስ ኡራኤል የጌታን ደም የረጨበት ጽዋ (መነሳነስ) የሰወረበት ተራራ ነው የሰወረበት ቦታ
ይታያል።
፬-በዚህ ቦታ ጌታችን ለቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያን አስራት ሀገርህ ነች ብሎት
ያረገበት ቦታና የቅዱስ ጊዮርጊስ የፈረሱ የ4ቱ
የእግሩ አሻራ በድንጋይ ላይ ታትሞ ይታያል፡፡
፭-በቦታው ላይ ዋሻ አለ ::በዋሻው ውስጥ:-
-የድንግል ማርያም የእጅዋ አሻራ በድንጋይ
ታትሞ ይታያል
-ያልፈረሰ ያልበሰበሰ ክንፍ ያላቸው አፅመ ቅድሳን አጽም ይታያል።
-የድንግልና የልጅዋ ልብስ እንዳለ ይነገራል
-የሚጠበቀው ዋሻው በነጭ ነብርና በነጭ አንበሳ ሲሆን እነሱም ይታያሉ።
፮-በዚሁ አካባቢ የማርያም ገዳም አለ የማርያም ቤተክርስቲያን ያረፈበት ቦታ
ድንግል የተቀመጠችበትን ቦታ ቅዱስ ኡራኤል በክፉ የጠረገው ቦታ ነው ቤተክርስቲያን የተሰራው።
የቦታው ቃልኪዳን :-ቦታው የረገጠ የቦታውን አካባቢ አሻግሮ ያየ 189ትውልድ ያለ ንስሀ እምረዋለሁ የጠየቀውን የሀሳቡን እሰጠዋለሁ እምረዋለሁ፡፡
@Nehmeya @Nehmeya
✞ ከእመጓ ዑራኤል ቤተክርስትያን ረድኤት በረከት ያሳትፈን።
✞ መልካም ቀን ይሁንልን።
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †††
ውድ የቻናላችን ተከታታዮች የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችንን ከአሁን ሰአት ጀምሮ ተጀምሯል።ጥያቄዎቹም እነዚህ ናቸው
⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
፩ ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የተወለደው የት ነው?
፪ ሰብአ ሰገል የጌታችን ለመድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ እጅ መንሻ ያመጡት ምን ምን ነበር
፫ ሰብአ ሰገል ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ወደ ተወለደበት በረት እየተመሩ የመጡት በምንድን ነው?
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
☞ መልሶቻችሁን እስከ ምሽቱ 4:00 ድረስ በ
⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
@Mahebranehmyabot ያድርሱን።
☞ መልሱን ከ4:00 በኋላ በቻናላችን የምንለቅ መሆናችንን እንገልፃለን።
《 እግዚአብሔር ሆይ ኃጢአተኛ ሆነን ኃጢአተኞችን መውደድ በማንችልበት ዓለም ላይ፣ አንተ ግን ንጹህ ሆነህ፣ ኃጢአተኞችን ትወደናለህ፣ማግኔት ተቃራኒውን ይስባል የሚመስለውን ግን ይገፋል በደለኞች ሆነን
በደለኞችን ስንገፋ በደል የሌለብህ አንተ ግን
በደለኞችን ታቅፈናለህ።በእውነት በሆነው ሳይሆን በምንሆነው የምትጠራን አንተ ነህ።እሬሳን አልአዛር ብለህ በስሙ የምትጠራ፣ሳኦል ላይ ሳትዘገይ፣
ጳውሎስ ለማለት የምትፈጥን ፣ አንተ ብቻ ነህና ክብር ላንተ ይሁን።》
መምህር ምህረትአብ አሰፋ
@Nehmeya @Nehmeya
❖ ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያን ፍፁም ሰላም ያድርግልን።
❖ መልካም እለተ ሰንበት ይሁንልን።
☞ ዛሬ ማለትም 30/4/2013አ.ም ምንጣፍ ስለሚፀዳ እንዲሁም ባንዴራ ስለሚስተካከል ጠዋት 2:00 ጀምሮ ኪዳነምህረት ቤተክርስትያን እንገናኝ።
Читать полностью… @Nehmeya @Nehmeya
❖ እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሰላም አደረሰን።
❖ መልካም በአል ይሁንልን።
《 እነሆ ለሕዝብ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምስራችን እነግራችኋለሁና አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።》
ሉቃ ፪÷፲-፲፪
@Nehmeya @Nehmeya
❖ እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ በአል በሰላም አደረሰን።
❖ መልካም በአል ይሁንልን።
በዘባነ ኪሩብ
በዘባነ ኪሩብ ለሚቀመጠው
በእሳት ድንጋዮች ቅጥሩን ላጠረው
ዘምሩ ለእግዚአብሔር ለጌታ ዘምሩ
የተከበረ ነው በሰማይ በምድሩ(፪)
አዝ
ኢሳያስ ሲያየው እጅግ አፈረ
የተፈራ ነው የተከበረ
የሰማይ ደጆች ተንቀጠቀጡ
ለቅዱስ ስሙ ክብርን ሲሰጡ
አዝ
ያልተቀደሰ ለምጽ ያነደደው
እንዴት ይችላል ሊያመሰግነው
በል ፍቀድልኝ ፍቅር ነህና
ልግባ መቅደስህ ላቅርብ ምስጋና
አዝ
ዙፋንህ ታየኝ ትምክህቴ ሆይ
ስትመሰገን በሰማይ ላይ
ሲያመሰግንህ የተደሰተ
ባይተዋር አልሁን አልውጣ ካንተ
አዝ
ቅኔ የሞላበት ያን ሰገነት
ልቀላቀለው ተመኘው በእውነት
ልዘምርልህ ባይገባኝም
ዝም የሚል ልሳን አልሰጠኸኝም
@Nehmeya @Nehmeya
❖ እንኳን ለቸሩ መድሀኒአለም ወርሐዊ መታሰብያ በሰላም አደረሰን።መሀሪው አምላካችን መዓቱን አስወግዶ ምህረቱን ያምጣልን።
❖ መልካም ቀን ይሁንልን።