ይህ የየካደ/ም/ቅ ኪዳነ ምህረት እና መድሀኒአለም አካባቢ ወጣቶች ማህበር የቴሌግራም ቻናል ነው። በቻናላችን ላይ ያለዎትን ሀሳብ አስተያየት ⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩ @Mahebranehmyabot ያድርሱን። ከቴሌግራም በተጨማሪ ፌስቡክ ላይም ያገኙናል። https://m.facebook.com/ማህበረ-ነህምያ-ዘ-ኮተቤ
አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ የተወለዱት ጐንደር: የድሮው ስማዳ (ዳኅና) አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ዘክርስቶስና እግዚእ ክብራ ይባላሉ:: የተወለዱት በ1210 ዓ/ም ነው:: ነገር ግን አንዳንድ ምንጮች በ1196 ዓ/ም ያደርጉታል::ጻድቁ ከክርስቲያን ወላጆቻቸው ጋር እንደሚገባ አድገዋል:: በልጅነታቸው በብዛት ወላጆቻቸውን ያግዙ ነበር:: በትርፍ ጊዜአቸው ደግሞ ትምሕርተ ሃይማኖትንና ሥርዓቱን ያጠኑ ነበር:: በ1240 ዓ/ም ግን (ማለትም 30 ዓመት ሲሞላቸው) ይሕቺን ዓለም ይተዋት ዘንድ አሰቡ::
አስበውም አልቀሩ ፈጣሪን እየለመኑ ደብረ ዳሕሞ ገቡ:: በወቅቱ ዳሞ የትምሕርት: የምናኔ ማዕከል ከመሆኑ ባሻገር የአቡነ አረጋዊ 5ኛ የቆብ ልጅ ካልዕ ዮሐኒ ነበሩና የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ሆኑ::
አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በደብረ ዳሞ በነበራቸው ቆይታ ቀን ቀን ሲታዘዙ: ሲፈጩ: ውሃ ሲቀዱ ውለው ሌሊት እኩሉን በጸሎት በስግደትና የቀረውን ሰዓት ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመገልበጥ አሳለፉ::
በመጨረሻም ልብሰ ምንኩስናን ለበሱ:: ይህን ጊዜ 37 ዓመታቸው ሲሆን ዘመኑም 1247 ዓ/ም ነው:: ወዲያውም በዳሞ ሳሉ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ "ወደ ወሎ ሐይቅ ሒድ: ብዙ የምትሠራው አለና" አላቸው::
በአንዴም ከዳሞ (ትግራይ) ነጥቆ ሐይቅ እስጢፋኖስ (ወሎ) አደረሳቸው:: በዚያም ለ7 ዓመታት በዼጥሮስ ወዻውሎስ ቤተ መቅደስ በተጋድሎ: በስብከተ ወንጌል: በማዕጠንትና ሐይቁ ውስጥ ሰጥሞ በመጸለይ ኖሩ::
ቅድስናቸውን የተመለከቱ አበውም በግድ አበ ምኔት አድርገው ሾሟቸው:: ይህ ነው እንግዲህ በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ትልቁ መሠረት የተጣለበት አጋጣሚ:: ነገሩ እንዲህ ነው:-
ስም አጠራሯ የከፋ ዮዲት ጉዲት ለ40 ዓመታት ሃገሪቱን እንዳልነበረች ብታደርጋት ክርስትና ተዳከመ:: ባዕድ አምልኮም ነገሠ:: አቡነ ኢየሱስ ሞዐ (ትርጉሙ ኢየሱስ ክርስቶስ አሸነፈ ማለት ነው) ደግሞ ሃይማኖታቸው የቀና ከ800 በላይ ክርስቲያኖችን ሰበሰቡ::
በሃገሪቱ ትልቅና የመጀመሪያው ሊባል የሚችል ቤተ መጻሕፍት አደራጁ:: እነዚያን አርድእት በቅድስናና በትምሕርት አብስለው አመነኮሱና "ሒዱ! ሃገሪቱን ታበሩ ዘንድ ተጋደሉ" ብለው አሰናበቷቸው::
ክእነዚህ መካከልም ታላላቁን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን: አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እና የሁዋላውን ፍሬ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን መጥቀስ እንችላለን:: በዚህም ምክንያት ጻድቁ "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን - አእላፍ ቅዱሳንን የወለደ" ሲባሉ ይኖራሉ::
ጻድቁ ከዚህ በተጨማሪ የወቅቱን ንጉሥ አፄ ይኩኖ አምላክን በማስተማር ለሃገርና ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ሰው አድርገዋል:: በግላቸው ሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ የብርሃን ምሰሶ ይወርድላቸው ነበር:: ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምንም ከጠፋ ከ300 ዓመታት በሁዋላ አቅንተዋል::
እንዲህ ለቤተ ክርስቲያን ሲተጉ: በተለይ በአበ ምኔትነት በቆዩባቸው 45 ዓመታት ለዓይናቸው እንቅልፍን አላስመኙትም:: ጐድናቸውም ከምኝታ ጋር ተገናኝቶ አያውቅም::
"እንዘ የኀሊ ዘበሰማያት ዐስቦ::
መጠነ ዓመታት ሃምሳ ኢሰከበ በገቦ::" እንዲል::
ከዚህ በሁዋላ የሚያርፉበት ዕለት ቢደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: በተወለዱ በ82 ዓመታቸው (በ86 ዓመታቸው የሚልም አለ) በ1282 ዓ/ም በዕለተ ሰንበት ዐርፈው ተቀብረዋል::
ምንጭ፦ ዝማሬ ዳዊት ከተሰኘው የቴሌግራም ቻናል
@Nehmeya @Nehmeya
❖ የፃድቁ አባት የአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ረድኤት በረከት በሀገራችን በኢትዮጵያና በሕዝቦቿ ላይ ፀንቶ ይኑር ።
❖ መልካም ቀን ይሁንልን።
☞ ለዛሬ የነበረን የጥያቄ መልስ መርሀ ግብር የተጠናቀቀ ሲሆን ለተሳተፋችሁ በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን። 🙏🙏🙏🙏 🙏🙏 መልሶቹ እነዚህ ናቸው።
፩ ጌታችን ስለ መጨረሻው ዘመን ያስተማረበት ተራራ ደብረዘይት ተራራ ይባላል።
፪ ጌታችን መጨረሻ የፈጠረው ፍጥረት አዳም ሲሆን የተፈጠረውም አርብ እለት ነው።
፫ ፃድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በሀገራችን ኢትዮጵያ የኖሩት 362አመት ነው።
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
☞ የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችን በየሳምንቱ እሁድ እሁድ የሚኖረን ሲሆን በቻናላችን ላይ ያለዎትን ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት በ ⇩⇩⇩⇩⇩⇩
@Mahebranehmyabot ያድርሱን።
መልካም ምሽት
☞ የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችን ከምሽቱ 2:00 ላይ የሚጀምር ስለሆነ ሁላችሁም እንድትሳተፉ በልኡል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
Читать полностью… ሽብሸባ
ሽብሸባ በቤተክርስትያናችን በዝማሬ ወቅት የሚደረግ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ የክርስቶስን መስቀል ተሸክሞ ወደ ቀራኒዮ
መጓዝ የሚያሳስብ፤ የጌታችንን መከራ፣ መስቀል ተሸክሞ ወደ ግራ ወደ ቀኝ ወደፊት እና ወደኋላ መውደቅ መነሳትን የሚያመለከት እንቅስቃሴ ነው።ይህን የሰማይ ዜማ ኪሩቤልና ሱራፌል እያሸበሸቡ
ይዘምሩታል። ካህናተ ሰማይ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ እያሸበሸቡ እንደሆነ ቅዱስ ያሬድ ሰማየ ሰማያት ተነጥቆ በሄደበት ወቅት አይቶ ፅፎልናል።ቤተክርስትያናችን በእነዚህ ምክንያቶች እንድናሸበሽብ ታዘናለች።
@Nehmeya @Nehmeya
❖ ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያን ፍፁም ሰላም ያድርግልን።
❖ መልካም ቀን ይሁንልን።
አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ
እግዚአብሔር ፍቅር ነው ፣ መሐሪ ነው ፣ ይቅር ባይ ነው፡፡ ፍቅር ይቆጣል ወይ? ይቅር ባይስ ይቀጣል ወይ? ብዙዎቻችን ስለ ክርስቶስ ሲነገረን መሐሪነቱና ፍቅሩ ብቻ ቢነገረን አንጠላም፡፡ ጨርሶ የማንፈራው እግዚአብሔር እንፈልጋለን፡፡ እንዲህ አታድርግ! የሚለን ሲመጣ ‘አትፍረድ’ እንላለን ፤ ቆይተን ግን የሰማዩን ዳኝም አትፍረድ ማለት ይቃጣናል፡፡ ቅጣት የሌለበት ክርስትና እንሻለን፡፡ይህ ዓይነቱን ክርስትና ‘ጣፋጭ ክርስትና’ {የስኳር ክርስትና ይሉታል} ምንም ምሬት የሌለበት ሁሌም ማር ማር የሚል ሕይወት አድርገው ክርስትናን የሚሰብኩም ብዙ ናቸው፡፡ ‘አይዞህ ብትታመም ትፈወሳለህ ፣ ቤትህ ይሞላል ፣ ቀዳዳህ ይደፈናል ፣ ብትበድልም አትቀጣም’ ብቻ የሚሉ ስብከቶች የስኳር ክርስትና ስብከቶች ናቸው፡፡ ይህንን ብቻ የሚያጮሁ ሰዎች ክርስቶስ ‘የምድር ጨው ናችሁ’ ያለውን ትተው የምድር ስኳር ለመሆንና ዓለምን ለማስደሰት የሚፈልጉ ናቸው፡፡በእርግጥ እግዚአብሔር ይቆጣል ወይ? አዎን ይቆጣል! እንዲህ ይላል መጽሐፉ
‘እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል። በቍጣው ፊት የሚቆም ማን ነው? የቍጣውንም ትኵሳት ማን ይታገሣል? መዓቱ እንደ እሳት ይፈስሳል፥ ከእርሱም የተነሣ ዓለቶች ተሰነጠቁ’ ናሆ 1፡1፣6
‘‘ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች አሕዛብም መዓቱን አይችሉም’’ ኤር 10፡10
‘‘እኛ በቍጣህ አልቀናልና፥ በመዓትህም ደንግጠናልና’’ መዝ. 90፡7
እግዚአብሔር በተቆጣ ጊዜ የሚመልሰው የለም፡፡ ቅዱሳን የቁጣውን መጠን ስለሚያውቁ በትሕትና ይለምኑታል፡፡
ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ቁጣ ደጋግሞ ቢነግረንም አንድ ሌላ ደስ የሚያሰኝ ነገርም ነግሮናል፡፡ የእግዚአብሔር ቁጣው ለዘላለም አይደለም፡፡ "ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" ይላል እንጂ "ቁጣው ለዘላለም ነውና" አይልም:: የእግዚአብሔር ቁጣ ጊዜያዊ ነው፡፡
‘መሐሪ ነኝና ለዘላለም አልቆጣም’ ኤር 3፡12
‘ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን ነው’ መዝ 29፡5
‘ጌታ ለዘላለም አይጥልም ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራል ፤ የሰው ልጆችን ከልቡ አያስጨንቅም አያሳዝንምም’ ሰ.ኤር 3፡31
የፈጣሪን የነነደ የቁጣ እሳት ማጥፋት የሚቻለን በዕንባ ነው፡፡ በደላችንን አምነን ቅጣት ይገባናል ነገር ግን መሐሪ ነህና ማረን ማለት ይገባል፡፡ ንጉሥ ዳዊት ‘አቤቱ በቁጣህ አትቅሠፈኝ በመዓትህም አትገሥፀኝ’ ብሎ የፈጣሪን ቁጣ አበረደ፡፡ /መዝ 38፡1/ ነቢዩ ኤርያስም ‘አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቁጣ አይሁን’ ብሎ ተለማመጠ፡፡ ኤር 10፡24
አንድ ሠዓሊ በጣም ብዙ ደክሞ የተጠበበትን ሥዕሉን የፈለገ ቢበሳጭ ለረዥም ጊዜ ያንን ሥዕል ለመሳል የተጠበበትን ጥበብ አስቦ ሥዕሉን ወደ እሳት አይጨምረውም፡፡ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ሲል ይለምናል ‘ሠዓሊ ሥዕሉን ያጠፋል ወይ? ጌታ ሆይ እኔን ስትፈጥር የተጠበብክበትን የቀደመ ጥበብህን አስብ እንጂ! አስበህም ማረኝ! ያጠፋዖኑ ለሥዕሉ ሠዓሊ ፤ ኪነተከ ዘትካት ኀሊ ይቅርታውን በንስሓ ለሚለምኑ ሁሉ ምሕረቱ ቅርብ ነው፡፡ በቀኝና በግራው ወንበዴዎች በተሰቀሉበት በዕለተ አርብ የግራው ወንበዴ ሲሰድበው ጌታ መልስ አልሠጠም፡፡ የቀኙ ወንበዴ ማረኝ ሲለው ግን ከአፉ ተቀብሎ በገነት ትሆናለህ አለው፡፡ ቁጣው የራቀ ምሕረቱ የበዛ እርሱ የራበው ሰው ለምግብ የሚቸኩለውን ያህል ይቅር ለማለት ይቸኩላል፡፡ ‘ምሕረትን ይወድዳልና ቁጣውንም ለዘላለም አይጠብቅም ተመልሶ ይምረናል ፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል ፤ ኃጢአታችንንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል’ ሚክ 7፡18
ልጆች ሳለን ጥፋት ስናጠፋ ከወላጆቻችን እንደበቃለን፡፡በተደበቅንበት ሰዓት ውስጣችን በፍርሃት ይርዳል፡፡ ‘ዛሬ ገደለኝ’ ‘ዛሬ መሞቴ ነው’ ብለን እንጨነቃለን፡፡ የሚደርስብንን ቅጣት እጅግ አጋንነን ከመፍራታችን የተነሣ መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠን አንጠላም፡፡ በዚያ ሁሉ ጭንቀት ውስጥ ግን ወላጆቻችንም እስኪያገኙን ይጨንነቃሉ፡፡ እግዚአብሔርም እንዲህ ነው፡፡ አጥፍቶ በገነት ዛፎች መካከል የተሸሸገ አዳምን ወዴት ነህ ብሎ የፈለገ እርሱ እኛንም ይፈልገናል፡፡ አዳም ከገነት ሳይባረር ገነት ውስጥ እንደጠፋ ፈጣሪ ሳያባርረን ራሳችንን በኃጢአት ተሸማቅቀን ያባረርን እኛን ይፈልገናል፡፡ እርሱ ስለመጥፋትህ ይጨነቃል አንተ ‘ዛሬስ አይምረኝም’ ትላለህ፡፡
የሚገርመው በጥፋታችን ከተደበቅንበት ወላጆቻችን ካገኙን በኋላ ሁለተኛው ዙር ጭንቀታችን ‘ምን አጥፍተህ ነው የተደበቅከው’ መባል ነው፡፡ ጥፋታችንን ሲያውጣጡን እንንቀጠቀጣለን፡፡ ያጠፋነውን ስለምናውቀው ስንት እንደሚያስገርፈንም እናውቀዋለን፡፡ ‘ብትናገር ይሻላል? ግዴለህም!’ ብለው አግባብተውም አስፈራርተውም ወላጆቻችን ጥፋታችንን ያውጣጡናል፡፡ እየፈራን ያጠፋነውን ጥፋት ስንናዘዝ ግን ወላጆቻችን በጥፋታችን ቅጥል ብለው ‘አልመታህም ተናገር’ ያሉንን ረስተው የዱላ ዝናም ያዘንቡብናል፡፡ እግዚአብሔር ግን ጥፋትህን ስትነግረው ቁጣው የሚገነፍል አባት አይደለም፡፡
’’ኃጢአታችንን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነፃን የታመነና ጻድቅ ነው’ 1ዮሐ 1፡9
ምንጭ፦ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
@Nehmeya @Nehmeya
❖ መሀሪው አምላካችን ሀገራችንን ፍፁም ሰላም ያድርግልን።
❖ መልካም ቀን ይሁንልን።
《 ከቅዱሳን ክብር የማርያም ክብር ይበልጣል የአብቃልን ለመቀበል በተገባ ተገኝታለችና መላእክት የሚፈሩትን ትጉሆች በሰማይ የሚያመሰግኑትን ድንግል ማርያም በማህፀኗ ተሸከመችው።》
ውዳሴ ማርያም
@Nehmeya @Nehmeya
❖ ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያን ፍፁም ሰላም ያድርግልን።
❖ መልካም ቀን ይሁንልን።
☞ ለዛሬ የነበረን የጥያቄ መልስ መርሀ ግብር የተጠናቀቀ ሲሆን ለተሳተፋችሁ በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን። 🙏🙏🙏🙏 🙏🙏 መልሶቹ እነዚህ ናቸው።
፩ እመቤታችን ያረደቸው(የስጋ ሞትን የሞተችው) ጥር21 ቀን ነው።
፪ የእመቤታች ስጋዋን ሐዋርያት ሊቀብሩ ሲሉ ሬሳውን ለማቃጠል ፈልጎ የአልጋውን ሸንኮር ሲይዝ መልአኩ 2እጁን የቀሰፈው ሰው ታውፋንያ ይባላል።
፫ ሙሴ ከሞተ በኋላ እስራኤላውያንን እየመራ ወደ ከነአን(ርስት ምድራቸው) ያስገባቸው ኢያሱ ነው።
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
☞ የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችን በየሳምንቱ እሁድ እሁድ የሚኖረን ሲሆን በቻናላችን ላይ ያለዎትን ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት በ ⇩⇩⇩⇩⇩⇩
@Mahebranehmyabot ያድርሱን።
መልካም ምሽት
☞ የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችን ከምሽቱ 2:00 ላይ የሚጀምር ስለሆነ ሁላችሁም እንድትሳተፉ በልኡል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
Читать полностью…፠ ክፍል ፬
ሥነ ፍጥረት
በክፍል ፫ በእለተ አርብ ስለተፈጠሩ ፍጥረታት የተመለከትን ሲሆን በዚህ ክፍል ደግሞ ስለ በሥነ ፍጥረት ላይ የተሳሳተ ሀሳብ ያለቸውን እና የቤተክርስትያናችን መልስ ምን እንደሆነ እንመለከታለን።
በሥነ ፍጥረት ላይ የተሳሳተ ሀሳብ ያለቸውን እና የቤተክርስትያናችን መልስ
በሥነ ፍጥረት ላይ ብዙ የተሳሳቱ ሀሳቦችን የሚሰጡ ቡድኖች ያሉ ሲሆን ከእነሱ መካከል ጥቂቱን እንመልከት።
፩ ሁለትነት
ይህን ፍልስፍና የጀመረው ዞራስተር የተባለ ፈላስፋ ሲሆን ሀሳቡም ይህች አለም ሁለት አምላክ አላት አንዱ ደጉ አምላክ(አንግራማኑ) አንዱ ደግሞ ክፋው አምላክ(አሁራማዝዶ) ሲሆኑ ደጉ አምላክ ረቂቅ የሆኑ ነገሮችን ነፋስ ፣ብርሀን ወዘተ… የፈጠረ ሲሆን ክፋው አምላክ ደግሞ ይህን አለም፣ስጋ ወዘተ…ፈጥሯል ብሎ ያስተምር ነበር።ይህን ግን ፈፅሞ ሀሰት ነው። ዘዳ ፮፥፬ እንዲህ ይላል « አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው » ይላል ይህም የሚያሳየን ክፉ እና ደግ አምላክ እንደሌለ ያለው አንድ አምላክ ብቻ እንደሆነ ይነግረናል።
፪ መመንጨት
ይህን ትምህርት የሚያስተምሩ ሰዎች የሚሉት ፍጥረታትን የፈጠረው እግዚአብሔር ሲሆን ፍጥራትትን የፈጠረው ከፀሐይ ጨረሯ እንደሚመነጭ ሁሉ ፍጥረታት ከእግዚአብሔር አካል መነጩ ብለው ያምናሉ ይህም አስተምህሮ ፈፅሞ የተሳሳተ ነው እግዚአብሔር ፍጥረታትን በመናገር፣በዝምታ እና በመስራት ፈጠራቸው እንጂ አላመነጫቸውም ለዚህ ማስረጃ ይሆነን ዘንድ መዝ ፻፵፰፥፬ ላይ እንዲህ ይላል « እርሱ ብሏልና ሆኑ እርሱ አዝዟልና ተፈጠሩ » ይላል ይህ የሚያሳየን እግዚአብሔር በማዘዝና በመናገር ፈጠራቸው እንጂ በማመንጨት እንዳልፈጠራቸው ነው።
፫ ከእቁላል መሰል ነገር ተፈጠረ
ይህ ሀሳብ በጣም አስቂኝ የሆነ ሀሳብ ሲሆን ሀሳቡ የሚለው አለም ከመፈጠሯ በፊት የሆነ እንቁላል የመሰለ ነገር አለ እርሱ ሲፈነዳ አለም ተፈጠረች የሚል ይህ ሀሳብ ፈፅሞ የተሳሳተ ሲሆን አለም የተፈጠረችው ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ነው።(መዝ ፻፵፰፣፬ መመልከት ይቻላል)
፬ ድንገታዊ አፈጣጠር
ይህን ሀሳብ የሚያራምዱ ሰዎች የሚሉት በድንገት ይህች አለም ተፈጠረች ነው ይህ ደግሞ ፍፁም ሀሳት ምክንያቱ ዘፍ ፩፥፩ ላይ « እግዚአብሔር በመጀመሪያ ሰማይ እና ምድርን ፈጠረ » ይህም የሚያሳየን የፍጥረታት አስገኚ እግዚአብሔር እንደሆነ ነው።
፭ ዘላለማዊነት
ይህን ሀሳብ የሚያራምዱ ሰዎች የሚሉት አለምን ማንም አልፈጠራትም ማንም አያጠፋትም ዘላለማዊናት ብለው የሚያስቡ ሲሆን ይህ ሀሳብ ፍፁም ስህተት መሆኑ እነዚህን የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅሶች መመልከት እንችላለን።(ዘፍ ፩፥፩ ማቴ ፳፬፥፫ መዝ ፻፩፥፳፭)
፮ ዝግመተ ለውጥ
ይህ ሀሳብ የሚለው የሰው ልጅ የተፈጠረው በዝግመተ ለውጥ ቀስበቀስ ከዝንጀሮ ተቀይሮ ነው የሚሉ ናቸው ይህ ሀሳብ ፍፁም ስህተት ነው።ለዚህ መስረጃ እንዲሆነን ዘፍ ፩፥፫ እንዲህ ይላል « እግዚአብሔር ብርሐን ይሁን አለ ብርሐንም ሆነ » ይህ ቃል የሚያሳየን እግዚአብሔር ፍጥረታትን ሲፈጥር ያለምንም ዝግመተ ለውጥ እንደ ሆነ ነው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ በመንበረ መንግስት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት መፅሀፍ 1 ላይ
@Nehmeya @Nehmeya
❖ ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ።
❖ መልካም ቀን ይሁንልን።
እንኳን ለእመቤታችን ንጽሕት ድንግል ወላዲተ አምላክ ማርያም ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
†✝† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †✝†
† #ዕረፍተ_ድንግል †
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅድመ ዓለም በአምላክ ልቡና ታስባ ትኖር ነበር:: ከነገር ሁሉ በፊት እግዚአብሔር እናቱን ያውቃት ነበር::
ዓለም ተፈጥሮ: አዳምና ሔዋን ስተው: መርገመ ሥጋና መርገመ ነፍስ አግኝቷቸው: በኃዘን ንስሃ ቢገቡ "እትወለድ እም ወለተ ወለትከ - ከ5 ቀን ተኩል (5500 ዘመናት) በሁዋላ ካንተ ባሕርይ ከምትገኝ ንጽሕት ዘር ተወልጄ አድንሃለሁ" ብሎ ተስፋ ድኅነት ሰጠው::
ከአዳም አንስቶ ለ5500 ዓመታት አበው: ነቢያትና ካህናት ስለ ድንግል ማርያም ብዙ ሐረገ ትንቢቶችን ተናገሩ:: መዳኛቸውን ሱባኤ ቆጠሩላት:: ምሳሌም መሰሉላት:: ከሩቅ ዘመን ሁነውም ሊያገኟት እየተመኙ እጅ ነሷት::
"እምርሑቅሰ ርእይዋ: ወተአምኅዋ" እንዲል::
የድንግል ማርያም ሐረገ ትውልድ
- ከአዳም በሴት
- ከያሬድ በሔኖክ
- ከኖኅ በሴም
- ከአብርሃም በይስሐቅ
- ከያዕቆብ በይሁዳና በሌዊ
- ከይሁዳ በእሴይ: በዳዊት: በሰሎሞንና በሕዝቅያስ ወርዳ ከኢያቄም ትደርሳለች::
ከሌዊ ደግሞ በአሮን: አልዓዛር: ፊንሐስ: ቴክታና በጥሪቃ አድርጋ ከሐና ትደርሳለች::
አባታችን አዳም ከገነት በወጣ በ5,485 ዓመት ወላዲተ አምላክ ንጽሕና ሳይጐድልባት: ኃጢአት ሳያገኛት: ጥንተ አብሶ ሳይደርስባት ከደጋጉ ኢያቄም ወሐና ትወለዳለች:: (ኢሳ. 1:9, መኃ. 4:7) "ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ" እንዳለ:: (ቅዱስ ቴዎዶጦስ ዘዕንቆራ)
ከዚያም ከእናት ከአባቷ ቤት ለ3 ዓመታት ቆይታ ወደ ቤተ መቅደስ ትገባለች:: በቤተ መቅደስም ለ12 ዓመታት ፈጣሪዋን እግዚአብሔርን እያመሰገነችና እያገለገለች: እርሷን ደግሞ መላእክተ ብርሃን እያገለገሏት: ሕብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ እየመገቧት ኑራለች:: 15 ዓመት በሞላት ጊዜ አረጋዊ ዮሴፍ ያገለግላት ዘንድ ወደ ቤቱ ወሰዳት::
በዚያም መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ዜና ድኅነትን ነግሯት አካላዊ ቃልን በማሕጸንዋ ጸነሰችው:: ነደ እሳትን ተሸከመችው: ቻለችው:: "ጾርኪ ዘኢይትጸወር: ወአግመርኪ ዘኢይትገመር" እንዳለ:: (ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ለብሐዊ)
ወልደ እግዚአብሔርን ለ9 ወራት ከ5 ቀናት ጸንሳ: እንበለ ተፈትሆ (በድንግልና) ወለደችው:: (ኢሳ. 7:14) "ኢየሱስ" ብላ ስም አውጥታለት በገሊላ ለ2 ዓመታት ቆዩ::
አርዌ ሔሮድስ እገድላለሁ ብሎ በተነሳበት ወቅትም ልጇን አዝላ በረሃብ እና በጥም: በላበትና በድካም: በዕንባና በኃዘን ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ከገሊላ እስከ ኢትዮዽያ ተሰዳለች:: ልጇ ጌታችን 5 ዓመት ከ6 ወር ሲሆነው: ለድንግል ደግሞ 21 ዓመት ከ3 ወር ሲሆናት ወደ ናዝሬት ተመለሱ::
በናዝሬትም ለ24 ዓመታት ከ6 ወራት ልጇን ክርስቶስን እያሳደገች: ነዳያንን እያሰበች ኑራለች:: እርሷ 45 ዓመት ልጇ 30 ዓመት ሲሆናቸው ጌታችን ተጠምቆ በጉባኤ ትምሕርት: ተአምራት ጀመረ:: ለ3 ዓመታት ከ3 ወራትም ከዋለበት እየዋለች: ካደረበትም እያደረች ትምሕርቱን ሰማች::
የማዳን ቀኑ ደርሶ ልጇ ክርስቶስ ሲሰቀልም የመጨረሻውን ፍጹም ሐዘን አስተናገደች:: አንጀቷ በኃዘን ተቃጠለ:: በነፍሷም ሰይፍ አለፈ:: (ሉቃ. 2:35) ጌታ በተነሳ ጊዜም ከፍጥረት ሁሉ ቀድማ ትንሳኤውን አየች:: ለ40 ቀናትም ሳትለይ ከልጇ ጋር ቆየች::
ከልጇ ዕርገት በሁዋላ በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትን ሰብስባ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ አበቃች:: በጽርሐ ጽዮንም ከአደራ ልጇ ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ለ15 ዓመታት ኖረች:: በእነዚህ ዓመታት ሥራ ሳትፈታ ስለ ኃጥአን ስትማልድ: ቃል ኪዳንን ከልጇ ስትቀበል: ሐዋርያትን ስታጽናና: ምሥጢርም ስትገልጽላቸው ኑራለች::
ዕድሜዋ 64 በደረሰ ጊዜ ጥር 21 ቀን መድኃኒታችን አእላፍ ቅዱሳንን አስከትሎ መጣ:: ኢየሩሳሌምን ጨነቃት:: አካባቢውም በፈውስ ተሞላ:: በዓለም ላይም በጐ መዓዛ ወረደ:: እመ ብርሃን ለፍጡር ከዚያ በፊት ባልተደረገ: ለዘለዓለምም ለማንም በማይደረግ ሞገስ: ክብርና ተአምራት ዐረፈች:: ሞቷ ብዙዎችን አስደንቁአል::
"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ::
ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ::" እንዲል::
ከዚህ በሁዋላ መላእክት እየዘመሩ: ሐዋርያቱም እያለቀሱ ወደ ጌቴሴማኒ: በአጐበር ሥጋዋን ጋርደው ወሰዱ:: ይሕንን ሊቃውንት:-
"ሐራ ሰማይ ብዙኃን እለ አልቦሙ ሐሳበ::
እንዘ ይዜምሩ ቅድሜኪ ወመንገለ ድኅሬኪ ካዕበ::
ማርያም ሞትኪ ይመስል ከብካበ" ሲሉ ይገልጡታል::
በወቅቱ ግን አይሁድ በክፋት ሥጋዋን እናቃጥል ስላሉ ቅዱስ ገብርኤል (ጠባቂ መልአክ ነው) እነርሱን ቀጥቶ: እርሷን ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ወስዶ በዕጸ ሕይወት ሥር አኑሯታል:: በዚያም መላእክት እያመሰገኗት ለ205 ቀናት ቆይታለች::
ቅዱስ ዮሐንስ መጥቶ ለሐዋርያቱ ክብረ ድንግልን ቢነግራቸው በጐ ቅንአት ቀንተው በነሐሴ 1 ሱባኤ ጀመሩ:: 2ኛው ሱባኤ ሲጠናቀቅም ጌታ የድንግል ማርያምን ንጹሕ ሥጋ ሰጣቸው:: እየዘመሩም በጌቴሴማኒ ቀብረዋታል::
በ3ኛው ቀን (ነሐሴ 16) እንደ ልጇ ባለ ትንሳኤ ተነስታ ዐርጋለች:: ትንሳኤዋንና ዕርገቷንም ደጉ ሐዋርያ ቅዱስ ቶማስ አይቶ: መግነዟን ተቀብሏል:: ሐዋርያቱም መግነዟን ለበረከት ተካፍለው: እንደ ገና በዓመቱ ነሐሴ 1 ቀን ሱባኤ ገቡ::
ለ2 ሳምንታት ቆይተው: ሁሉንም ወደ ሰማይ አወጣቸው:: በፍጡር አንደበት ተከናውኖ የማይነገር ተድላ: ደስታና ምሥጢርንም አዩ:: ጌታ ራሱ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው:: የበዓሉን ቃል ኪዳን ሰምተው: ከድንግል ተባርከው ወደ ደብረ ዘይት ተመልሰዋል::
ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን: ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን: ለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን::
#ቅዱስ_ጐርጐርዮስ_ሊቅ
ለዚህ ቅዱስ አባት ብጹዕ መባል ተገብቷል:: ክቡር: ምስጉን: ንዑድ ሰው ነውና:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በቂሣርያ ቀዸዶቅያ የተወለደው ቅዱሱ ሰው ለደሴተ ኑሲስ ብርሃኗ ነው:: አባቱ ኤስድሮስ: እናቱ ኤሚሊያ: ወንድሞቹ ቅዱሳን "ባስልዮስ: ዼጥሮስ: መክርዮስና መካርዮስ" ይባላሉ::
የተቀደሰች እህቱም ማቅሪና ትባላለች:: ከዚህ የተባረከ ቤተሰብ ለቅድስና ያልበቃ አንድም ሰው የለም:: ሊቁ ቅዱስ ጐርጐርዮስም ከማር በጣፈጠ ዜና ሕይወቱ እንደ ተጻፈው:-
በልጅነቱ ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምሯል::
ሥጋውያን ጠቢባንን ያሳፍር ዘንድም የግሪክን ፍልሥፍና በልኩ ተምሯል:: በታላቅ ወንድሙ ቅዱስ ባስልዮስ መሪነት ገዳማዊ ሕይወትን ተምሯል:: በመንኖ ጥሪት ተመስግኗል::
ተገብቶትም በኑሲስ ደሴት ላይ ዻዻስ ሆኗል:: እርሱ ሲሔድ በከተማው የነበሩ ክርስቲያኖች 11 ብቻ የነበሩ ሲሆን እርሱ ሲያርፍ ክርስቶስን የማያመልኩ ሰዎች ቁጥር 11 ብቻ ነበር:: ቅዱስ ጐርጐርዮስ ፍጹም ሊቅ ነበርና ከቁጥር የበዙ ድርሳናትን ደርሷል:: ታላቁን ጉባኤ ቁስጥንጥንያን (በ381 ዓ/ም) መርቷል:: ብዙ መናፍቃንንም አሳፍሯል::
ከንጽሕናው የተነሳ መላእክት ያቅፉት: እመ ብርሃንም ትገለጥለት ነበር:: ለ33 ዓመታት እንደ ሐዋርያት ኑሮ በዚህ ቀን ድንግል ጠራችው:: ቀድሶ አቁርቦ: ሕዝቡን አሰናብቶ: የቤተ መቅደሱን ምሰሶ እንደ ተደገፈ ዐርፎ ተገኝቷል:: በዝማሬና በፍቅር ቀብረውታል::
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
፠ክፍል ፪
ሥነ ፍጥረት
በክፍል ፩ ስለ ሥነ ፍጥረት የቃሉ ትርጉም ፣እግዚአብሔር ስንት ፍጥረታትን እንደ ፈጠረ እዲሁም በእለተ እሁድ ስለ ተፈጠሩ ፍጥረታት የተመለከትን ሲሆን በዚህ ክፍል ደግሞ ከሰኞ እስከ ረቡዕ የተፈጠሩ ፍጥረታትን እንመለከታለን።
፪ የእለተ ሰኞ ፍጥረታት
ሰኞ እለት እግዚአብሔር የፈጠረው አንድ ፍጥረትን ነው እሱም ጠፈር ነው።እግዚአብሔር እሁድ እለት የፈጠረውን ውሀ ከሶስት ቦታ ከፈለው አንዱን እጅ ውሀ ከኤረር በታች አኖረው ስሙንም ሐኖስ ብሎ ሰየመው።የሐኖስ ጥቅም ምድር ከፀሐይ የሚመጣው ጨረር እንዳይጎዳት መከላከል ሲሆን ሐኖስን የሚሸከመው ንፋስ ባቢል ይባላል።ሁለተኛውን እጅ ውሀ ደግሞ በዚች ምድር አሰፈረው።ሶስተኛውን እጅ ውሀ ደግሞ ጠፈርን ፈጠረበት።እግዚአብሔር ጠፈርን የሰራው ውሀን አጠንክሮ ነው።
እግዚአብሔር ጠፈርን የፈጠረበት ምክንያት አንደኛ የሰው ልጅ ጠፈርን እያየ ሰማያዊ መንግስት እንዳለው ተስፋ እንዲያደርግ ነው።ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ በእለተ ረቡዕ ለተፈጠሩት ፀሐይ ጨረቃ እና ከዋክብት ማህደር እንዲሆን ነው።
የእለተ ሰኞ ፍጥረት ምሳሌው ምንድን ነው?
በእለተ ሰኞ ጠፈርን ሲፈጥረው አምላካችን ውሀን ከሶስት ቦታ ከፍሎ አንዱን እጅ ውሀ በምድር ላይ ሁለቱን እጅ በሰማይ ማድረጉ ምሳሌነቱ በሰማይ የቀሩት ሁለት እጅ ውሀ የአብ እና የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ሲሆኑ በምድር የሆነው አንድ እጅ ውሀ የወልድ ምሳሌ ነው ምክንያቱም አብ እና መንፈስ ቅዱስ ሰው ሆነው በምድር አልተመላለሱም ወልድ ግን ሰው ሆኖ ተመላልሷል።የሰኞ ፍጥረታት ምሳሌነታቸው ይህ ነው።
፫ የእለተ ማክሰኞ ፍጥረታት
በእለተ ማክሰኞ እግዚአብሔር አምላክ እነዚህ ነገሮች አደላድሏል
፩ በምድር ላይ የነበረውን አንድ እጅ ውሀ ከፍሎት አንዱን ከምድር በታች አደረገው።አንዱን ከምድር በላይ አኖረው ይህም ኩሬ፣ውቅያኖስ፣ባህር ወዘተ… የምንላቸው ናቸው።
፪ ከጠፈር በታች ያሉትን አምስቱን አለማተ መሬት የሚባሉትን አደላድሏል 5ቱ አለማተ መሬት የሚባሉት ገነት(በምስራቅ አቅጣጫ)፣ ብሔረ ህያዋን(በሰሜን አቅጣጫ)፣ ብሔረ ብፁአን(በደቡብ አቅጣጫ)፣የምንኖርባት መሬት እና ሲኦል(በምዕራብ አቅጣጫ) ናቸው።
እግዚአብሔር አምላክ እነዚህን ነገሮች ካደላለደለ በኋላ 3 ነገሮችን ፈጥሯል።(ዘፍ ፩፥፲፩)እነሱም በእጅ የሚለቀሙ አትክልት፣በማጭድ የሚታጨዱ አዝዕርት፣በመጥረብያ የሚቆረጡ ዕፅዋት ናቸው።የተፈጠሩት።
የእለተ ማክሰኞ ፍጥረታት ምሳሌያቸውን
ምንድን ነው?
የእለት ማክሰኞ ፍጥረታት ምሳሌነታቸው የእመቤታችን ነው ምክንያቱም ምንም ዘር ሳይዘራባት ምድር እፅዋትን እንዳበቀለች ሁሉ
እመቤታችን ያለወንድ ዘር ልጅ የመውለዷ ምሳሌ ነው።
፬ የእለተ ዕረቡ ፍጥረታት
እግዚአብሔር በእለተ ረቡዕ የፈጠራቸው ፍጥረታት ሶስት ሲሆኑ እነሱም ፀሐይ፣ጨረቃ እና ከዋክብት ናቸው።እነዚህን ፍጥረታት እግዚአብሔር የፈጠራቸው ጊዜንለመለካት፣ ዘመናት ለመቁጠር እንዲሁም እድሜን ለመለካት ነው።እግዚአብሔር ፀሀይንየፈጠራት ከእሳት እና ከነፋስ ሲሆን በእሳታዊ ባህሪዋ ታቃጥላለች በነፋስ ባህሪዋ ደግሞ ትንቀሳቀሳለች።ፀሐይ ከተፈጠረች በኋላ 7እጅ ብርሐን አደረገባትና ለመላእክት አሳያቸው መላእክት ማየት ከበዳቸወው በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር 2እጅ ቀንሶ ለጨረቃ፣1እጅ ቀንሶ ለከዋክብት እንዲሁም አንድ እጅ ለደመናት ሰጣቸው።ፀሐይም ሶስት እጅ ብርሐን ብቻ ቀራት ማለት ነው።
፭ የዕለተ ሐሙስ ፍጥረታት
በዕለተ ሐሙስ የተፈጠሩት ፍጥረታት 3ሲሆኑ እነሱም በውሀ ውስጥ የሚኖሩ በደረት የሚሳቡ፣በእግር የሚሄዱ እና የሚበሩ እንስሳትን ፈጥሯል።
የዕለተ ሐሙስ ፍጥረታት ምሳሌነታቸው
ምንድን ነው?
የዕለተ ሐሙስ ፍጥረታት ምሳሌነታቸው ውሀው የጥምቀት ምሳሌ ሲሆን ከውሀው ሳይወጡ የሚቆዩት እንስሳት በክርስትና እምነት ፀንተው የሚቆዩ ምእመናን ምሳሌ ነው።አንዴ ከውሀ አንዴ ከመሬት የሚኖሩት ደግሞ አንዴ ወደ ክርስትና እንዴ ምንፍቅና የሚሄዱ ሰዎች ምሳሌ ነው።እንስሳቱን ከሶስት ወገን አድርጎ መስራቱ ጥምቀት ለሶስት ትውልድ(ለሴም፣ለካም እና ያፌት) እንደተሰጠ ለማጠየቅ ነው።ከነዚህ የወጣ ትውልድ የለምና።እዲሁም በአብ፣በወልድ በመንፈስ ቅዱስ የመጠመቃችን ምሳሌ ነው።
@Nehmeya @Nehmeya
✞ ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ።
✞ መልካም ቀን ይሁንልን።
☞ ክፍል ፫ ይቀጥላል
☞ ለዛሬ የነበረን የጥያቄ መልስ መርሀ ግብር የተጠናቀቀ ሲሆን ለተሳተፋችሁ በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን። 🙏🙏🙏🙏 🙏🙏 መልሶቹ እነዚህ ናቸው።
፩ በዘመነ ኦሪት ክርስትያን የምንሆነው በግርዘት(በመገረዝ) ነበር።
፪ ልበ አምላክ ዳዊት ጎልያድን ለመምታት ያነሳቸው ጠጠሮችን 5 ናቸው። (መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 17፥40)
፫ እግዚአብሔር የፈጠራቸው ነገደ መላእክት ብዛት 100ሲሆን የተፈጠሩት በእለተ እሁድ ነው።
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
☞ የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችን በየሳምንቱ እሁድ እሁድ የሚኖረን ሲሆን በቻናላችን ላይ ያለዎትን ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት በ ⇩⇩⇩⇩⇩⇩
@Mahebranehmyabot ያድርሱን።
መልካም ምሽት
☞ የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችን ትላንት ማከናወን ባለ መቻላችን ከልብ ይቅርታ እየጠየቅን ዛሬ ምሽት 2:00 ላይ የጥያቄና መልስ መርሀ ግብራችንን ስላለ ሁላችሁም እንድትሳተፉ በትህትና እንጠይቃለን።
Читать полностью… የማይሸረሸር አለቴ
የማይሸረሸር አለቴ
የማይናጋ መሰረቴ
እየሱስ ክርስቶስ ሞገሴ
አንተ ነህ የጽዴቅ ልብሴ
አዝ
ቀራንዮ ላይ የቆመ
በፍቅር የተሸለመ
ከፊቴ ተነሰነሰ
ደምህ ህይወቴን ወረሰ
እፎይ ልበል ልዘምር
ሆነኸኛል ጌታ ክብር /2/
አዝ
የሲና ምድር ህብስቴ
የተከተልከኝ አለቴ
መርገሜን ሰብሮ አለፈ
ሰላምህ ውስጤ ጎረፈ
እፎይ ልበል ልዘምር
ሆነኸኛል ጌታ ክብር /2/
አዝ
የማትደፈር ክልሌ
የድል አርማዬ አክሊሌ
አለምን ማሸነፍያዬ
አንተ ነህ ክንዴ ጌታዬ
እፎይ ልበል ልዘምር
ሆነኸኛል ጌታ ክብር /2/
አዝ
መዳፎችህን አይቼ
በእንባ ረጠቡ ጉንጮቼ
ትዝታዬ ነው ዘወትር
የእጅህ ወለላ ፍቅር
ትዜታዬ ነው ዘወትር
መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር
@Nehmeya @Nehmeya
❖ ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያን ፍፁም ሰላም ያድርግልን።
❖ መልካም ቀን ይሁንልን።
ደብረ ዠመዳ አቡነ በርተሎሜዎስ አንድነት
ገዳም
በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ እጅግ ድንቅ በሆነው በዚኸ ገዳም ክብርት እመቤታችን በስደቷ ወራት ከከበረ ተወዳጅ ልጇ ጋር በዚኽች ቦታ ላይ ለ7 ቀናት ተቀምጣባታለች፡፡ ጌታችንም ቦታውን ‹‹የኢየሩሳሌም
እኅት ትሁን›› ብሎ ባርኳታል፡፡ ለቦታዋም
በእመቤታችን ስም ቃልኪዳን ገብቶላታል፡፡
ቅዱስ ሉቃስ የሳላት የእመቤታችን ሥዕል የምትገኝበት ወሎ ላስታ ያለችው ጥንታዊቷ ደብረ ዠመዳ አቡነ በርተሎሜዎስ አንድነት ገዳም የሚገኘው ከአ.አ 600ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በቆቦ ወረዳ ከዋጃ ከተማ በስተ ምዕራብ በኩል 27
ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ጻዲቁ አቡነ በርተሎሜዎስ ጥቅምት 4 ዕረፍታቸው ነው፡፡
አቡነ በርተሎሜዎስ ወደ ገዳሟ መጥተው በታላቅ ተጋድሎ የኖሩተ በዐፄ ይምርሐነ ክርስቶስ ዘመነ መንግሥት ነበር፡፡ በገዳሟ ላይ ለ199 ዓመታት በተጋድሎ ኖረዋል፡፡ ባደረባቸው ጸጋ እግዚአብሔር ምክንያት የዱር አራዊትን በቃላቸው እንደሰው ያዟቸው
ነበር፡፡ ነብርን እንደ ድመት በእጃቸው ይታቀፉት ነበር፡፡በእሳቸውም ቃልኪዳን ዛሬም ድረስ ነብሮቹ በገዳሙ ያሉ መናንያንን እንደ ጓደኛ ይቀርቧቸዋል፡፡እመቤታችንንም በጸሎት በለመኗት ጊዜ ጣዕሙ እንደማር የሚጣፍጥ ውሃ አፈለቀችላቸው፤ ነገር ግን
ጻድቁ እመቤታችንን ‹‹ጣዕሙን
እንደማንኛውም ውሃ አድርጊልኝ›› ብለው ጸለየው ጣዕሙ እንደውኃ ሆኗል፡፡
ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ልጆች ውስጥ አንዱ ሲሆኑ ያመነኮሷቸውና የሾሟቸውም እርሳቸው ናቸው፡፡ አቡነ በርተሎሜዎስ በደብረ ዠመዳ ገዳም ብቻ 199 ዓመት ከ9 ወር በተጋድሎ ከኖሩ በኋላ በመጨረሻ
ጌታችን ከድንግል እናቱ ጋር ተገልጦላቸው በቦታውላይ ዳግመኛ ታላቅ ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ መካነ መቃብራቸውን የተሳለመውን የጌታችንን መካነ መቃብር እንደተሳለመ እንደሚቆጠርለት፣ ልዩና የረከሰ
ሃይማኖት ያለው ሰው ወደ ገዳሟ እንደማይገባ ጌታችን በቃልኪዳን አጽንቶላቸዋል፡፡
ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት ከተሰኘው የፌስቡክ ገፅ
@Nehmeya @Nehmeya
❖ ከደብረ ዠመዳ አቡነ በርተሎሜዎስ አንድነት ገዳም ረድኤት በረከት ያሳትፈን።
❖ መልካም ቀን ይሁንልን።
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †††
ውድ የቻናላችን ተከታታዮች የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችንን ከአሁን ሰአት ጀምሮ ተጀምሯል።ጥያቄዎቹም እነዚህ ናቸው
⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
፩ ጌታችን ስለ መጨረሻው ዘመን ያስተማረበት ተራራ ምን ይባላል?
፪ ጌታችን መጨረሻ የፈጠረው ፍጥረት ምንድን ነው?መቼ ነው የፈጠረው?
፫ ፃድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በሀገራችን ኢትዮጵያ ለስንት ዓመት ኖሩ ?
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
☞ መልሶቻችሁን እስከ ምሽቱ 4:00 ድረስ በ
⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
@Mahebranehmyabot ያድርሱን።
☞ መልሱን ከ4:00 በኋላ በቻናላችን የምንለቅ መሆናችንን እንገልፃለን።
እግዚአብሔር እኛን ይወደናል
እግዚአብሔር እኛን ይወደናል
መላዕክቱን ለኛ ልኮልናል
እንዲረዱን እንዲጠብቁን
መላእክቱ እንዲታደጉን/2/
አዝ
መንገደኛ መስሎ መላኩ ሲራራ
በአሞት መስሎ በዚያ በተራራ
የጦቢትን አይኑን ያበራ
ሩፉኤል ነው ለኛ ሚራራ
አዝ
ጦቢያ ጦቢት ይናገሩ
የመላኩን ታምር ይመስክሩ
ይናገሩ ይገለጥ ክብሩ
የታወሩ ሁሉ እንዲበሩ/2/
አዝ
ወለተ ራጉኤል ተናገሪ
የጫጉላ ቤትሽን ታሪክ አውሪ
ተናገሪ ለህዝብ አብስሪ
ታምራቱን ምንም ሳትፈሪ
አዝ
ስባቱ ባሎችሽ መሞታቸው
የሚያሳዝን ነበር ታሪካቸው
ሩፋዬልም ደረስልሽ
ጎጆሽንም ባረከልሽ
አዝ
እንግዲ ተደስች እልል በዪ
አስማንዲዮስ ወቶል ከአንቺ ላይ
ህይወትሽን ሩፋኤል ዋጀው
ስላምሽን ለዓለም አወጀው
አዝ
ጦቢያ ይናገር በተራሁ
ያደረገላትን አለኝታሁ
ወዲያው ደግሞ አባት ሆነው
ሽማግሌ ሆኖ ዳረው/2/
አዝ
እኔም ልናገር በተዬ
ያደረገልኝን አለኝታዬ
ህይወቴን ሁሉ ለውጦታል
ልቦናዬን ፍቅሩ ማርኮታል/2/
አዝ
እኔም ልናገረው በተራዬ
ቀሎክኛልና መከራዬ
ሩፋዬል ነው እናት አባቴ
እለዋለው የስማይ ቤቴ/2/
@Nehmeya @Nehmeya
❖ ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያን ፍፁም ሰላም ያድርግልን።
❖ መልካም እለተ ሰንበት ይሁንልን።
《 አቤቱ፥ እኔ ግን ወደ አንተ ጮኽሁ፤ በጥዋት ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትደርሳለች። አቤቱ፥ ነፍሴን ለምን ትጥላለህ? ፊትህንስ ከእኔ ለምን ትሰውራለህ?እኔ ከታናሽነቴ ችግረኛ ለሞትም የቀረብሁ ነኝ፤ ከፍ ከፍ ካልሁ በኋላ ግን ተዋረድሁ ተናቅሁም። መቅሠፍትህ በላዬ አለፈ፥ ግርማህም አስደነገጠኝ።ሁልጊዜ እንደ ውኃ ከበቡኝ፥ በአንድነትም ያዙኝ።ወዳጄንና ባልንጀራዬን ዘመዶቼንም ከመከራ የተነሣ
ከእኔ አራቅህ።》
መዝሙረ ዳዊት ፹፯፥፲፬―፲፰
@Nehmeya @Nehmeya
❖ እንኳን ለቅዱስ አማኑኤል ወርሐዊ መታሰብያ በሰላም አደረሰን።መሀሪው አምላካችን መዓቱን አስወግዶ ምህረቱን ያምጣልን።
❖ መልካም ቀን ይሁንልን።
እኔ ራሴን ካልጣልኩ
እኔ ራሴን ካልጣልኩ አታውቅም ጥለኸኝ/ ×፪/
ፍቅር ነህ ጌታዬ በፍቅር የምታየኝ
ፍቅር ነህ አባቴ በፍቅር የምታየኝ/×፪/
አዝ
ኃጢአቴ ነው እንጂ ከአንተ የሚያሸሸኝ
በደሌ በዝቶ እንጂ አንገት የሚያስደፋኝ
አምላኬ ይዞኛል ሰፊ መዳፍህ
በበዛው ቸርነት ምህረት ይቅርታህ
አዝ
ዛሬ ይቅር ብለኸኝ ዛሬ እንኳን ባጠፋ
አምላኬ በእኔ ላይ አትቆርጥም ተስፋ
እኔ እየሸሸው ትከተለኛለህ
ጀርባዬን ስሰጥህ ልጄ ትለኛለህ
አዝ
መመለሴን እንጂ ስለማትወድ ሞቴን
መጣህልኝ ብለህ አቀፍከኝ አንገቴን
በአንተ ተጀምሮ ስለማያልቅ በሰው
አምላኬ በአንተ ላይ ተስፋዬ ብዙ ነው
አዝ
እኔ እያጠፋውኝ እኔው ስበድልህ
ፍሪዳውን ማረደ አንተ ግን ነው ልምድህ
የጠፋው ተገኝቷል ተነስቷል የሞተው
ትላለህ አምላኬ ማዳንህ ድንቅ ነው
አዝ
ባስለምድከኝ ምህረት ባስለምድከኝ ፍቅር
ከእኔ ጋር ነህና ተመስገን እግዚአብሔር
ስለሆንከኝ አንተ መጠጊያ ከለላ
ክፉውን አልፈራም ቢሄድ በሞት ጥላ
@Nehmeya @Nehmeya
❖ እንኳን ለፃድቁ አባታችን ለአቡነ ሀብተ ማርያም ወርሐዊ መታሰብያ በአል አደረሰን።
❖ መልካም ቀን ይሁንልን።
ምሥራቅ ጎጃም የሚገኘው ደብረ ኤልያስ እና
አቡነ ኢዮስያስ ገዳም
የሊቃዉንት መፍለቂያ የኾነው ደብረ ኤልያስ ቤተ ክርስትያን በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ በደብረ ኤልያስ ከተማ ይገኛል፡፡ቤተ ክርስትያኑ የተመሠረተዉ በ15ኛዉ ክፍለ ዘመን በዐፄ ዘርዓያዕቆብ ዘመነ መንግሥት በ1466 ዓ/ም በደጅ
አዝማች ድልአሰማ አማካኝነት ነው፡፡ ቤተ ክርስትያኑ በ1912 ልዑል ራስ ሃይሉ ተክለሃይማኖት በጭቃ ጡብ ያሠሩት ላይ ቤት፣ መሃል ቤት እና ምድር ቤት የሚባሉ 3 ክፍሎች ያሉት እቃ ቤት አለዉ፡፡በደብረ ገነት ኤልያስ ቤተ ክርስትያን ለደብሩ
አስተዳዳሪዎች የሚሰጥ የማዕረግ ስያሜ "ድምሐነ- ገነት"የሚል ሲሆን ትርጓሜዉም "የገነት መሃል ወይንም ራስ "ማለት ነዉ፡፡ ይህ ስያሜ የራሱ የሆነ ትርጓሜ ሲኖሩ በሌሎች አብያተ ክርስትያናት እንደማይሰጥ አባቶች ይገልጻሉ፡፡የደብረ ገነት ኤልያስ ቤተክርስትያን ከጥንት እስከ ዛሬ የዜማ ፣ቅኔ ፣አቋቋም ፣መጽሐፍና የቅዳሴ መርጌታዎች መፍለቂያ ማዕከል ነዉ፡፡ ከዚህ ቦታ የእዉቀት መነሻቸን አድርገዉ በዓለምና ሀገር አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆኑ ምሁራንን ይኸዉ ቤተ ክርስትያን
አፍርቷል፡፡ ከእነዚህም ጥቂቶቹ፡-
ታላቁ ደራሲና የቤተ ክህነት ሊቅ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ፣ ሁለተኛዉ ኢትዮጵያዊ ተወላጅ ጳጳስ አቡነ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ ክቡር ደራሲ መላኩ በጎሰዉ፣ ታላቁና
እዉቁ የረጅም ልብ ወለድ ድርሰት አባት ክቡር
ዶክተር ሀዲስ አለማየሁ፣ ዶክተር ኢሳያስ አለሜነህ ከብዙ በትቂቱ መጥቀስ ይቻላል፡፡
አሁንም የታላላቅ ሊቃዉንት መፍለቂያ ቦታ ነው፡፡ በ5ቱ ጉባኤያት በርካታ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል።
ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት ከተሰኘው የፌስቡክ ገፅ ላይ
@Nehmeya @Nehmeya
✞ከታላቁ ደብረ ኤልያስ እና አቡነ ኢዮስያስ ገዳም ረድኤት በረከት ያሳትፈን።ለደጁ ያብቃን።
✞ መልካም ቀን ይሁንልን።
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †††
ውድ የቻናላችን ተከታታዮች የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችንን ከአሁን ሰአት ጀምሮ ተጀምሯል።ጥያቄዎቹም እነዚህ ናቸው
⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
፩ እመቤታችን ያረፈችው(የስጋ ሞትን) የሞተችው በምን ቀን ነው?
፪ የእመቤታች ስጋዋን ሐዋርያት ሊቀብሩ ሲሉ ሬሳውን ለማቃጠል ፈልጎ የአልጋውን ሸንኮር ሲይዝ መልአኩ 2እጁን የቀሰፈው ሰው ማን ይባላል?
፫ ሙሴ ከሞተ በኋላ እስራኤላውያንን እየመራ ወደ ከነአን(ርስት ምድራቸው) ያስገባቸው ማን ነው?
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
☞ መልሶቻችሁን እስከ ምሽቱ 4:00 ድረስ በ
⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
@Mahebranehmyabot ያድርሱን።
☞ መልሱን ከ4:00 በኋላ በቻናላችን የምንለቅ መሆናችንን እንገልፃለን።
@Nehmeya @Nehmeya
❖ ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያን ፍፁም ሰላም ያድርግልን።
❖ መልካም እለተ ሰንበት ይሁንልን።
@Nehmeya @Nehmeya
እንኳን ለእመቤታችን ለንፅህት ቅድስት ድንግል ማርያም በአለ ዕረፍቷ አደረሰን።
፠ ክፍል ፫
ሥነ ፍጥረት
በክፍል ፪ ስለ ሰኞ፣ማክሰኞ፣ረቡዕ እንዲሁም ሐሙስ ስነ ፍጥረታት የተመለከትን ሲሆን በዚህ ክፍል ደግሞ ስለ አርብ ፍጥረታት፣ ምሳሌነታቸው እንመለከታለን።
፮ የዕለተ አርብ ሥነ ፍጥረታት
በእለተ አርብ የተፈጠሩ ፍጥረታት 4 ሲሆን በምድር ላይ የሚኖሩ በደረት የሚሳቡ፣በእግር የሚሄዱ እና በክንፍ የሚበሩ እንስሳት እንዲሁም አዳም ናቸው።
አዳም
የሥነ ፍጥረት የመጨረሻው ፍጥረት (22ተኛ ፍጥረት) ሲሆን አዳም በእነዚህ ምክንያቶች ከሌሎች ፍጥረታት ይለያል።
1 የተፈጠረው በስላሴ አምሳል ነው።(ዘፍ ፩፥፳፮)
2 ሁሉም ነገር ከተስተካከለ ከተመቻቸለት በኋላ የተፈጠረ ነው።
3 እንደ ሌሎቹ ፍጥረታት በመናገር ሳይሆን በተግባር ከአፈር ሰርቶ ነው እፍ ያለበት።
4 ሌሎቹ ፍጥረታት አስጎንብሶ ሲሆን የፈጠራቸው አዳምን ግን ቀጥ አድርጎ ነው የፈጠረው።
5 ሌሎቹ ፍጥረታት ትንሳኤ የላቸውም አዳም ግን ትንሳኤ አለው።
እነዚህ ከላይ በዘረዘርናቸው ነገሮች አዳም ከሌሎቹ ፍጥረታት ይለያል።
አዳም ሲፈጠር የ30አመት ጎልማሳ ሲሆን የተፈጠረውም ከ4ቱ ባህርያተ ስጋ(ነፋስ፣ውሀ፣እሳት እና መሬት) እና ከ3ቱ ባህርያተ ነፍስ(ለባዊነት፣ነባቢነት እና ህያውነት) የተፈጠረ ነው።አዳም የተፈጠረበት ቦታ በማዕከለ ምድር በቀራንዩ ልዩ ስሙ ኤልዳ በተባለ ቦታ ሲሆን የዚህም ምክንያቱ አዳምን ማዕከላዊነህ ሲለው ነው።አዳም በተፈጠረ በስምንተኛው ቀን እግዚአብሔር « ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት » ዘፍ ፪፥፳፫
በማለት አዳምን እንቅልፍ ጥሎበት ከግራ ጎኑ አንዲት አጥንትን ወስዶ የ15አመት ሔዋንን ፈጠረለት።ስሟን ሴት አለው(ዘፍ ፪፥፳፫)
እግዚአብሔር አዳም በፈጠረው በ፵ቀኑ ሄዋን በተፈጠረች በ፹ቀኗ በመላዕክት ታጅበው ወደ ገነት ገብተዋል።
@Nehmeya @Nehmeya
❖ ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያን ፍፁም ሰላም ያድርግልን።
❖ መልካም ቀን ይሁንልን።
☞ክፍል 4 ይቀጥላል
፠ ክፍል ፩
ሥነ ፍጥረት
ሥነ ፍጥረት የሁለት ቃላት ጥምረት ሲሆን እነሱም ሥነ እና ፍጥረት ናቸው።
ሥነ ማለት መልካም ሆነ፣አማረ፣ተዋበ ማለት ሲሆን
ፍጥረት ማለት ደግሞ የተፈጠረ፣ፍጡር ማለት ነው።
እግዚአብሔር ፍጥረታትን ከመፍጠሩ በፊት ይመሰገን ነበር?
ለዚህ ጥያቄ መልሱ አዎ ሲሆን እግዚአብሔር ፍጥረታትን ከመፍጠሩ በፊትም ይመሰገን ነበር።የሚያመሰግነውም ባህሪዩ ባህሪውን ያመሰግነው ነብር።እግዚአብሔር ፍጥረታትን መፍጠር ያስፈለገው ክብሩ፣ጌትነቱ ተወስኖ እንዳይቀር በማሰብ ፍጥረታትን ፈጠረ። ይህን ነገር ቀለሚጦስ እንዲህ ሲል ገልፆታል« ይቅርታዬን እና ክብሬን እሰጣቸው ዘንድ ነው እንጂ የምጠቀምባቸው ኖሮ ከእነርሱ እጠቀም ብዬ አልፈጠርኳቸውም » ሲል ገልፆታል።
እግዚአብሔር ሰንት ፍጥረታትን ፈጠረ?
እግዚአብሔር የፈጠራቸው ፍጥረታት እልፍ አእላፍ ሲሆኑ ብዙውን እንደ አንድ ስንቆጥራቸው 22 ናቸው።22 መሆናቸው የሃያ ሁለቱ ርዕሳነ አበው ምሳሌ ነው።22 ርዕሳነ አበው የሚባሉት አዳም፣ሴት፣ሄኖስ፣ቃይናን፣
መላልኤል፣ያሬድ፣ሄኖክ፣ማቱሳላ፣ላሜህ፣ኖህ፣ሴም፣አርፋክስድ፣ሳላ፣ኤቦር፣ፋሌቅ፣ራግው፣ሴሩህ፣ናኮር፣ታራ፣አብርሐም፣ይስሐቅ እና ያዕቆብ ናቸው።
እግዚአብሔር ፍጥረታትን የፈጠረው በ1ቀን ሳይሆን ከእሁድ እስከ አርብ ባሉት ቀናት ሲሆን ቅዳሜ ደግሞ አርፏል።ይህን ያደረገበት ምክንያት ስራ ስትሰሩ በመጠን በመጠኑ ስሩ ከሰራችሁም በኋላ እረፉ ብሎ ሊያስተምረን ነው።
፩ የእለት እሁድ ፍጥረታት
በዕለት እሁድ የተፈጠሩት ፍጥረታት 8ሲሆኑ አራቱ ባህርያት(ነፋስ፣ውሀ፣እሳት፣መሬት)
፣ጨለማ፣ሰባቱ ሰማያት እና መቶ ነገደ መላእክት ሲሆኑ እነዚህን 8ፍጥረታት በዝርዝር እንመልከት።
እሳት
እሳት አካሉ አንድ ሲሆን ሶስት ግብራት አሉት።
እነሱም፦ ውዑይነት(ሙቀትነት)ሙቀትን ይሰጣል፣ብሩህነት(ብርሀንነት)ብርሀን ይሰጣል፣ይቡስነት(ደረቅነት)ነገሮችን ማድረቅ ናቸው።አካሉ አንድ ሆኖ ሶስት ግብራት መኖሩ የስላሴን አንድነት እና ሶስትነት ይገልፃል።እሳት የእግዚአብሔር ከሃሊነት(ሁሉን ቻይነት)ምሳሌ ነው።
ነፋስ
ነፋስ አንድ አካል ቢኖረውም 3 ግብራት አሉት ይህም የሥላሴ አንድነት እና ሶስትነት ያሳየናል።
ግብራቱም ውዑይነት(ሙቀትነት)፣ርጡብነት(ርጥበት) እና ፅልመት(ጨለማነት) ናቸው።ነፋስ ለእግዚአብሔር የፈታሂነቱ(የፈራጅነቱ) ምሳሌ ነው።
ውሀ
ውሀ አንድ አካል ቢኖረውም 3 ግብራት አሉት ይህም የሥላሴ አንድነት እና ሶስትነት ያሳየናል።
ግብራቱም ብርህነት(ገፅታው ያበራል)፣ርጥቡነት(ርጥበት) እና ቆሪርነት(ቀዝቃዛነት) ናቸው።ውሀ ለእግዚአብሄር የርህራሄው ምሳሌ ነው።
መሬት
መሬት አንድ አካል ቢኖረውም 3 ግብራት አሉት ይህም የሥላሴ አንድነት እና ሶስትነት ያሳየናል።
ግብራቱም ደቡስነት(ደረቅነት)፣
ፅሉምነት(ጨለማነት)፣ ቆሪርነት(ቀዝቃዛነት) ናቸው።መሬት ለእግዚአብሔር ለባዕለ ጠግነቱ ምሳሌ ነው።
ጨለማ
የእለተ እሁድ አምስተኛው ፍጥረት ጨለማ ሲሆን ስሙንም ለሊት ብሎታል።ዘፍ 1፣5
ሰባቱ ሰማያት
የእለተ እሁድ 6ተኛ ፍጥረታት ሲሆን ሰባቱ ሰማያት የሚባሉት ፅረሐ አርያም፣መንበረ መንግስት፣ሰማይ ውዱድ፣ኢየሩሳሌም ሰማያዊት፣ኢዮር፣ራሜ እና ኤረር ናቸው።
መላእክት
የእለተ እሁድ ሰባተኛው ፍጥረታት መላእክት ናቸው።መላእክት ካለምንም ቅድመ ሁኔታ የተፈጠሩ ሲሆን መላእክትን ከስድስት ፍጥረታት በኋላ የፈጠራቸው እኛም ፈጣሪዎች ነን እርሱ ሲፈጥር እኛ አገዝነው እኛ ረዳነው ብለው እንዳያስቡ ነው።እግዚአብሔር 100ነገደ መላእክትን ከፈጠረ በኋላ 10 ነገድ አድርጎ ከፍሏቸው ነበር።እግዚአብሔር መላእክት ከፈጠራቸው በኋላ ተሰወረባቸው የተሰወረባቸው ምክንያት አዋቂ አድርጎ ስለፈጠራቸው ነው።መላእክት ማነው የፈጠረን አሉ። በዚህ ጊዜ ሳጥናኤል የመላእክት አለቃ ነበርና እኔ ነኝ የፈጠርኳችሁ አለ።እነ ቅዱስ ገብርኤል(99ነገደ መላእክት) ባለንበት ፀንተን እንቁም አሉ ሌላው 1 ነገደ መላእክት ግን ግማሹ ፈጥሮናል፣ግማሹ ፈጥሮን ይሆናል እና ግማሹ ፀጥ አሉ።በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር ተገለጠ አንዱ ነገደ መላእክትም ከዳቢሎስ ጋር ወረዱ የመላእክት ቁጥርም 99ነገደ መላእክት ሆነ።
ብርሐን
የእለተ እሁድ የመጨረሻው ፍጥረት ነው።ከብርሐን በፊት የነበሩት ሰባቱ ፍጥረታት የተፈጠሩት በዝምታ ሲሆን ብርሐን ግን ሲፈጠር እግዚአብሔር ብርሐን ይሁን ብሎ በመናገር ነው የፈጠረው።(ዘፍ 1፥3)
@Nehmeya @Nehmeya
† ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ።
† መልካም ቀን ይሁንልን።
☞ ክፍል ፪ ይቀጥላል
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †††
ውድ የቻናላችን ተከታታዮች የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችንን ከአሁን ሰአት ጀምሮ ተጀምሯል።ጥያቄዎቹም እነዚህ ናቸው
⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
፩ በሀዲስ ኪዳን ክርስትያን የምንሆነው በጥምቅት ሲሆን በዘመነ ኦሪት በምን ነበር?
፪ ልበ አምላክ ዳዊት ጎልያድን ለመምታት ስንት ጠጠሮችን ከወንዝ ውስጥ አነሳ?
፫ እግዚአብሔር ስንት ነገደ መላእክት ፈጠረ?
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
☞ መልሶቻችሁን እስከ ምሽቱ 4:00 ድረስ በ
⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
@Mahebranehmyabot ያድርሱን።
☞ መልሱን ከ4:00 በኋላ በቻናላችን የምንለቅ መሆናችንን እንገልፃለን።
አትርፎ ደብረወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ካቴድራል
አትርፎ ማለት አተረፈ ማለት ሲሆን የካቴድራሉ ንብረት ከሌባ በማትረፉ እንዲሁም በአድዋ ጦርነት ጊዜ ንጉሥ ሚኒልክ የክተት ሰራዊት አዋጅ ሲያስነግሩ የአካባቢው ዘማቾች ቤተክርስቲያኒቱ ተሳልመው ሲሄዱ በጦርነቱ ምክንያት ምንም አይነት ጉዳት
ሳይደርስባቸው መመለስ በመቻላቸው ሰማእቱ አተረፈን በማለት አትርፎ ተባለ ። አትርፎ ደብረወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ውስጥ የሚገኝ ታሪካዊ ቅርስ ነው ። ካቴድራሉ ህዳር
7/1270 ዓም የተመሰረተ ሲሆን ታቦቱም ከአክሱም ጽዮን እንደመጣ የካቴድራሉ ዋና አስተዳዳሪ መላከብርሀን ብስራት አካለወልድ ይናገራሉ ።ይህ ታሪካዊ ካቴድራል አመታዊ ክብረበዓሉ ጥር 18 በድምቀት ይከበራል ።ለዚህም ደግሞ በ297 ዓም የሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ አጥንት ተፈጭቶ
የተበተነበትና ተዓምር ያሳየበት እለት በመሆኑ ነው ።በዚህ ክብረበዓል ብዙ ቁጥር ያለው የእምነቱ ተከታዮችና ከእምነቱ ውጪ ያሉት ጭምር ይታደማሉ። የመጀመሪያ የቤተክርስቲያኒቱ ስም ገረሙጀ ቅዱስ
ጊዮርጊስ ቤተከርስቲያን ነበር። በመቀጠልም
በቀድሞ የጉራጌ ከምባታ ሀዲያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ መልከጼዴቅ አትርፎ ደብረመንክር ቅዱስጊዮርጊስ ገዳም ብለው ሰይመውት ነበር። አቡነ ጳውሎስ ደግሞ ወደ ካቴድራልነት ደረጃ በማሳደግ አትርፎ ደብረወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ብለው
ሰይመውታል ።በካቴድራሉ ሙዚየም ታሪካዊ ቅርሶች ለምሳሌ የተለያዩ መጽሐፍት
መስቀል እና ሌሎችም ቅርሶች ይገኛሉ ።
ምንጭ፦ አምደ ገዳማት ከተሰኘው የፌስቡክ ገፅ ላይ
@Nehmeya @Nehmeya
✞ ከአትርፎ ደብረወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ረድኤት በረከት ያሳትፈን።
✞ መልካም ቀን ይሁንልን።
☞ የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችን ከምሽቱ 2:00 ላይ የሚጀምር ስለሆነ ሁላችሁም እንድትሳተፉ በልኡል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
Читать полностью…