nehmeya | Unsorted

Telegram-канал nehmeya - ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

-

ይህ የየካደ/ም/ቅ ኪዳነ ምህረት እና መድሀኒአለም አካባቢ ወጣቶች ማህበር የቴሌግራም ቻናል ነው። በቻናላችን ላይ ያለዎትን ሀሳብ አስተያየት ⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩ @Mahebranehmyabot ያድርሱን። ከቴሌግራም በተጨማሪ ፌስቡክ ላይም ያገኙናል። https://m.facebook.com/ማህበረ-ነህምያ-ዘ-ኮተቤ

Subscribe to a channel

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

ቅዱስ ሲኖዶስ ባወጀው መሠረት የጸሎትና የምሕላ መርሐ ግብር በየካ ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ኅዳር 16 ቀን 2016 ዓ.ም ተከናውኗል፡፡

የመርሐ ግብሩ ይዘት አድኅነነ ሕዝበከ፣ጸሎተ ወንጌል እና እግዚኦታ ነው። በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 18÷15 ላይ ወንድምህ ቢበድልህ ብቻህን ንገረው፣የሚለው ክፍል ተነቧል።
ስምአነ አምላክነ ወመድኃኒነ ፣
ተስፋሆሙ ለኩሎሙ አጽናፈ ምድር፣
ወለእለሂ ውስተ ባህር ርሑቅ (መዝ65÷5)
በዲያቆኑ ተሰብኳል። ጸሎተ ወንጌልና እግዚኦታ ተደርሷል።
ምእመናን በፍጹም ተመስጦና በእንባ በታገዘ ምሕላውን ተከታትለዋል።

EOTC TV

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

🌼🌼🌼 🌼🌼🌼 🌼🌼🌼
እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ በሰላም አሸጋገረን። አዲሱ አመት የሰላም፣ የፍቅር፣የአንድነት እና መልካም መልካሙን የምንሰማበት አመት ይሁንልን።
            መልካም በአል ፪፻፲፮አ.ም
 🌼🌼🌼 🌼🌼🌼 🌼🌼🌼

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

"ጳጉሜ / ጾመ ዮዲት ማለት"

  ጳጉሜ ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ዮሐንስ ጳጉሜ ስድስት ቀን ይሆናል፡፡ በዚህም ሐገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ በመባል ትታወቃች ፡፡
       ጳጉሜ በዘመነ ዮሐንስ ስድስት በምትሆንበት ጊዜ ጾመ ነቢያት /የገና ጾም/ ህዳር 14 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡ በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዋኑ ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡
እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ ዮዲ.፰፥፪፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡ ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡
የጳጉሜ ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው፡፡ ይህም ጳጉሜ የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና ነው፡፡
ክርስቲያኖች ሁሉ በየዓመቱ በጳጉሜ ወር ሁሉም ተሰብስበው ከሌሊት ጀምረው በቤተክርስቲያን ተገኝተው ጸበል ይጠመቃሉ፡፡ ይህንን የምናደገውም እግዚአብሔር የተባረከ ዓመት እንዲሰጠን፣ ባሳለፍነው ዓመት የሰራነውን ኃጢአት ይቅር እንዲለን ነው የምንጠመቀውም ንስሐ ገብተን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ስም የተቀደሰው ጸበል ደግሞ ከበሽታችን ያድነናል፣ የተቀደስንም ያደርገናል፣ መጪውንም ህይወታችን የተባረከ ያደርግልናል፡፡

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

አባትና ልጅነታቸውን መሠረት በማድረግ የይሰበይ አቡነ ሀብተ ማርያም ገዳም ካህናት፣ መሪጌቶችና ዲያቆናት ግንቦት 4 ቀን ወደ ሚዳ መራቤቴ በመሄድ የአቡነ መልኬጼዴቅን በዓል እጅግ በደማቅ ሁኔታ ያከብራሉ፡፡

አቡነ ሀብተ ማርያምም ምንኩስናን ከተቀበሉ በኋላ ገድላቸውንና ትሩፋታቸውን በማብዛት በሳምንት አንድ ጊዜ ቅጠልን ብቻ የሚመገቡ ሆኑ፡፡ አርባ አርባ ቀን ሰማንያ ሰማንያ ቀንም የሚጾሙበት ጊዜ ነበር፡፡ በሌሊትም ወደ ጥልቅ ባሕር እየገቡ መዝሙረ ዳዊት፣ አራቱን ወንጌላትና ሌሎች የጸሎት መጽሐፍትን ይደግሙ ነበር፡፡ ፊታቸውም እንደ ንጋት ምሥራቅ ኮከብ ያበራ ጀመር፡፡

ከዚህም በኋላ ወደ ምሥራቅ ሄደው ጎሐርብ ወደምትባል ሀገር ደረሱ፡፡ በዚያም በዓት አጽንተው ሲጸልዩ ጌታችን ቅዱስ ገብርኤልንና ቅዱስ ሚካኤልን በቀኝና በግራ አስከትሎ ተገለጠላቸውና ‹‹ወዳጄ ሀብተ ማርያም ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን›› አላቸው፡፡ ያን ጊዜ አባታችን ከፈጣሪአቸው ግርማ የተነሳ ደንግጠው ከመሬት ወድቀው እንደ በድን ሆኑ፡፡ ጌታችንም አንስቶ ክቡራን በሆኑ እጆቹ አጸናቸውና ‹‹የመጣሁት ለጸናህ ነው ሰውነትህንም እንደ ንስር ላድሳት ነው እንጂ ላጠፋህ አይደለም፡፡ ድካምህና ገድልህ ሁሉ ለዘለዓለም መታሰቢያ ሊሆን በኢየሩሳሌም ሰማያዊት ተጽፎልሃል ብዬ በእውነት እነግርሃለሁ፡፡ ለአንተ ለወደድኩህና ለመረጥኩህና ወዳጄ የማቴዎስንና የማርቆስን ወንጌል ባነበብክ ጊዜ ተጭነህ ወደምትሄድበት ቦታ የሚያደርስህ የብርሃን ሰረገላ ሰጥቼሃለሁ፡፡ እንደ አንተም ካሉ በዋሻ በመሬት ፍርኩታ ከሚኖሩ ከመረጥኳቸው ቅዱሳን ጋር ትገናኝ ዘንድ ወደ አራቱም አቅጣጫ ትበር ዘንድ የብርሃን ሠረገላ ሰጥቼሃልሁ፡፡ ዳግመኛም የሉቃስንና የዮሐንስን ወንጌል ባነበብክ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ትሄድ ዘንድ የእሳት ሠረገላ ሰጥቼሃለሁ›› አላቸው፡፡ ዳግመኛም ‹‹በጸሎትህ አምኖ በጎ ሥራ ለሚሠራ ሁሉ፣ ስምህን የጠራውን ዝክርህን ያዘከረውን ሁሉ የሀብተ ማርያም አምላክ ሆይ ከጠላት እጅ አድነኝ ያለኝን በኅሊና ያሰበውን በልቡናው የወሰነውን እፈጽምለታለሁ፡፡ አንተን ገድልህንና ቃል ኪዳንህን የናቀውን ያቃለለውን ሁሉ ፍጹም መበቀልን እበቀለዋለሁ፡፡ እንደ ወዳጄ እንደ ፊቅጦርም በእናቴ በማርያም ድንግል አተምኩህ›› ካላቸው በኋላ ቅዱስ ሚካኤል ከእርሳቸው እንዳይለይ የዘወትር ጠባቂ አድርጎ ሰጣቸውና በታላቅ ግርማ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡

አባታችንም ከጌታችን ይህን ቃል ኪዳን ከተቀበሉ በኋላ ነፍሳቸውን ‹‹ነፍሴ ሆይ ከፈጣሪሽ ከእግዚአብሔር ጋር ፊት ለፊት አፍ ለአፍ ትነጋገሪ ዘንድ ደፍረሻልና በጎም ሥራ ሳይኖርሽ ከፈጣሪሽ ቃልኪዳን ተቀብለሻልና ከዛሬ ጀምሮ እንደ መላእክት ዘወትር አትተኝ›› እያሉ ተጋድሏቸውን አብዝተው ቀጠሉ፡፡

መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልም አባታችንን እንደ ጓደኛ ሆኖ ዘወትር ይጎበኛቸው ነበር፡፡ ቅዱሳን አባታቸንን ሊጎበኟቸው መጥተው ከደጅ ቆመው እንደሆነ ቅዱስ ሚካኤል አባታችንን ‹‹እከሌ ጉዳዩ እንዲህ ነው እንዲህ ብለህ ተናገረው…›› እያለ ያማክራቸው ነበር፡፡ እሳቸውም ቅዱስ ሚካኤል ካዘዛቸው በቀር ምንም አይሠሩም ነበር፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትንም ባነበቡ ጊዜ ኃይለ ቃሉን እየተረጎመ ምሥጢራትን ይነግራቸዋል፤ የተሰወረውንም ይገልጥላቸዋል፡፡ ከእንስሳት ጩኸት ጀምሮ ከዱር አራዊት ድምፅና እስከ አእዋፍ ቋንቋ ያለውን ያስረዳቸው ነበር፡፡

ይኸውም መልአክ አንድ ቀን አቡነ ሀብተ ማርያምን ወደ ቤተ ክርስቲያን አስገብቷቸው ሥጋ ወደሙን ለመቀበል ተዘጋጅተው ሳለ ወንጌል የሚነበብበት ሰዓት ሲደርስ ያልተማረ ቄስ የክርስቶስ ጌትነቱን የምትናገር ወንጌልን ሲያነብ ‹‹ወዮሴፍ ብእሲሃ ለማርያም ጻድቅ ውእቱ›› የሚል ከቄሱ አፍ ይህን ንባብ አባታችን ሲሰሙ እጅግ ደንግጠው ወንጌል ወደሚነበብበት ስፍራ ሄደው የሚያነበውን ቄስ ገሠጹት፡፡ ‹‹ወዮሴፍሰ ፈሃሪሃ ለማርያም ጻድቅ ውእቱ በል እንጂ ብእሲሃ አትበል›› ብለው መከሩት፡፡ ቄሱም አቡነ ሀብተ ማርያም እንዳዘዙት ከስህተቱ ወደ ቀና ንባቡ ተመለሰ፡፡ ይህን ጊዜ ጌታችን ለአባታችን ድጋሚ ተገልጦላቸው ‹‹ሀብተ ማርያም ሆይ ይህን ትምህርትህን ወድጄ አመሰገንኩህ፣ የእናቴን የድንግል ማርያምን የድንግልናዋን ንጽሕና ስለ አከበርክ እኔም በመንግስተ ሰማያት ፈጽሜ አከብርሃለሁ›› አላቸው፡፡ ዳግመኛም ጌታችን ‹‹አሁንም ዮሴፍ ብእሲሃ ለማርያም የሚሉትን ሁሉ ለያቸው እንጂ አትተዋቸው፤ እንዲህ የሚል ጽሑፍም ብታገኝ እንዳይኖር እርሱን ፍቀህ ፈሃሪሃ ለማርያም የሚለውን ጻፍ›› ብሎ አባታችንን ካዘዛቸው በኋላ ሰላምታ ሰጥቷቸው ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ አባታችንም በዚህ ጊዜ ፊታቸው ላይ ብርሃን ስለተሳለባቸውና እንደ ፀሐይ ስላበራ ሰዎችም አይተው ባደነቁ ጊዜ ወደ በዓታቸው ገቡና ጌታችንን ‹‹አቤቱ ጌታዬ ሆይ በሰው ፊት ክብሬን አትግለጥብኝ ሰውርልኝ፣ በቸርነትህም አድነኝ›› ብለው ጸለዩ፡፡ እንዲህም ብለው በጸለዩ ጊዜ ፊታቸው መልኩ ተለውጦ እንደ ቀድሞው ሆነ፡፡

ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አባታችን ታመው ተኝተው ሳለ ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ መጥተው ሥጋ ወደሙን አቀብለዋቸዋል፡፡፡ አባታችን በጸሎት ላይ ሳሉ ቅዱስ ሚካኤል ነጥቆ ወደ ሰማይ ወስዶ ቅዱሳን የሚኖሩባቸውን ዓለማት፣ መንግስተ ሰማያትን እንዲሁም ኃጥአን የሚኖሩበትን ሲኦልን አሳያቸው፡፡ በገነት ያሉትንም ከአዳም ጀምሮ እሳቸው እስካሉበት ጊዜ እስከ አቡነ መርሐ ክርስቶስ ድረስ ያሉትን ቅዱሳን አሳያቸው፡፡ ከዚህም በኋላ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ቆመው ሳለ ሰይጣንም መጥቶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመና ‹‹አቤቱ ጌታዬ ሆይ በሀብተ ማርያም ላይ እንደ ኢዮብ ብዙ መከራ አጸናበት ዘንድ ፍቀድልኝ›› ብሎ እየጮኾ ሲናገር አባታችን እጅግ ፈርተው አለቀሱ፡፡ እግዚአብሔር ግን በሰይጣን ላይ ተቆጥቶ ‹‹በነፍሱም በሥጋውም መከራ ታጸናበት ዘንድ አልፈቅድም›› አለው፡፡ ‹‹እኔ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ መርጨዋለሁና በንጽሕናና በቅድስና ኃጢአት እንዳይሠራ ዘወትር እጠብቀዋለሁ፤ በእርሱ ላይ ማሰልጠንስ ይቅርና በሀብተ ማርያም ጸሎት በተማጸነኝ ሁሉ ላይ እንኳን አላሠለጥንህም›› አለው፡፡ ሰይጣንም ይህን ቃል ሰምቶ አፍሮ እያዘነ ሄደ፡፡

አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ከእርሳቸው በኋላ በመንበራቸው ከተሾሙት ከስምንቱ መምህራን ጋር ለሀብተማርያም ተገለጡላቸው፡፡ እነርሱም ኤልሳዕ፣ ፊሊጶስ፣ ሕዝቅያስ፣ ቴዎድሮስ፣ ዮሐንስ፣ ዮሐንስ ከማ፣ እንድርያስና መርሐ ክርስቶስ ናቸው፡፡ እነዚህም መልካቸው እንደ ፀሐይ ያበራ ልብሳቸው እንደ መብረቅ ያንጸባርቅ ነበር፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ልብሳቸው የእሳት ላንቃ የከበበው መልኩም ነጭ የሆነ የሚያስደንቅ ሆኖ ‹‹በቅድምና ለነበረ ለአብ በቅድምና ለነበረ ለወልድ በቅድምና ለነበረ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል›› እያለ ልብሳቸው በሰው አንደበት ያመሰግን ነበር፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም አቡነ ሀብተ ማርያምን ‹‹ልጄ ሀብተ ማርያም ሆይ! ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ስለወደደህ ብዙ ምርኮ እንዳገኘህ በአንተ ፈጽሞ ደስ ይለኛል፡፡ ነገር ግን የምለምንህ ነገር አለና እሺ በለኝ›› አሏቸው፡፡

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

@Nehmeya  @Nehmeya
እንኳን ለእመቤታችን ለንፅህት ቅድስት ድንግል ማርያም በአለ ዕረፍቷ አደረሰን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

《 ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ》
        መዝ ፻፳፩፥፩

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

<< ዑራኤል የተባለ መልዐክ ሊረዳኝ መጣ >>
           መ/ዕዝ.ሱቱ ፪፥፩

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

《 ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ》
        መዝ ፻፳፩፥፩

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

ሐምሌ ፯ ቀን እግዚአብሔር አምላክ በአብርሃም ቤት የገባበትና ሣራ ይስሐቅን እንደምትወልድ የተናገረበት ዕለት ነው፡፡ ይህ የቅድስት ሥላሴ ክብረ በዓል በቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ በደማቅ ሥርዓት ይከበራል፡፡
 @Nehmeya  @Nehmeya
✥ እንኳን ለአጋዕዝት አለም ቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ  ክብረ በአል በሰላም አደረሰን።
✥ መልካም ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

《 ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ》
        መዝ ፻፳፩፥፩

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

                     ዘመነ ዕርገት
ዕርገት በግእዝ ቋንቋ ማረግ፣ ከታች ወደ ላይ መውጣት ማለት ሲኾን የጌታችን ትንሣኤ በተከበረ በዐርባኛው ቀን የሚውለው ዐቢይ በዓልም ‹ዕርገት› ይባላል (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፯፻፷)፡፡ በዓለ ዕርገት ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለዐርባ ቀናት በግልጽም በስውርም ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለቅዱሳት አንስት መጽሐፈ ኪዳንን፣ ትርጓሜ መጻሕፍትን፣ ምሥጢራትን፣ ሕግጋትንና ቀኖናተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተምር ቆይቶ ወደ ቀደመ ዙፋኑ ወደ ሰማይ በክብር በምስጋና ማረጉን በደስታ የምንዘክርበት ዐቢይ በዓል ነው፡፡ በዓለ ዕርገት በቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ በድምቀት ይከበራል፡፡ በዓሉ የሚውልበት ዕለት ሐሙስን ባይለቅም ቀኑ ግን የአጽዋማትና በዓላት ማውጫ ቀመርን ተከትሎ ከፍ እና ዝቅ ይላል፡፡ በዚህ መሠረት የዘንድሮው በዓለ ዕርገት ግንቦት ፲፯ ቀን  ይውላል ማለት ነው፡፡ ከጌታችን የዕርገት በዓል ጀምሮ (ከበዓለ ትንሣኤ ዐርባኛው ቀን) እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ ዋዜማ (ዐርባ ዘጠነኛው ቀን) ድረስ ያለው ወቅትም ‹ዘመነ ዕርገት› ተብሎ ይጠራል፡፡

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

                    ልደታ ለማርያም
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግንቦት አንድ ቀን (የግንቦት ልደታ) የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት የሚከበርበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ‹‹የመመኪያችን ዘውድ፣ የንጽሕናችንም መሰረት›› ያላት ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም የተወለደችበት ነው፡፡

ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ‹‹ድንግል ትጸንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች (ኢሳ 7፡14)›› ብሎ ትንቢት የተናገረላት ያቺ ድንግል በዚህች ዕለት ተወለደች፡፡

ይህች ቀን ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት ‹‹ የወርቅ ልብስ ተጎናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች (መዝ 44፡9)›› ብሎ የተናገረላት ንግሥት የተገኘችባት ዕለት ናት፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ ‹‹ፀሐይን የተጎናጸፈች፣ ጨረቃን የተጫማች፣ አስራ ሁለት የክዋክብት አክሊል በራሷ ላይ ያላት (ራዕ 12፡1)›› ብሎ የመሰከረላት የብርሃን እናቱ ድንግል ማርያም የተወለደችባት ቀን ናት፡፡ የእርስዋም ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ  እንደ ውኃ ፈሳሽ ድንገት የተከሰተ ሳይሆን አስቀድሞ በትንቢት፣ በምሳሌና በራዕይ የሰውን ልጅ ድኅነት በጉጉት ሲጠባበቁ ለነበሩ ቅዱሳን ሲገለጽ የነበረ ነው፡፡
@Nehmeya  @Nehmeya
✥ እንኳን ለእመቤታችን ለንፅህት ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በአል አደረሰን።
✥ መልካም ቀን ይሁንልን

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

ዘጠኝ ሠዓት ሲሆን
ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን አባት ሆይ
በመስቀል ሆነህ ›› ››
ድምፅህን በማሰማት ›› ››
ነፍስህን ሠጥተህ ›› ››
ክዋክብት ከሰማይ በሙሉ እረገፉ
ጨረቀና ፀሐይ ደም አጎረፉ
ብርሃናት ጨለሙ ከሠው ተለያዩ
ሥጋ በመስቀል ላይ ተጋልጦ ስላዩ
ጌታችን ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ
አሰምቶ ጮኸ ተጠማው እያለ
ማርና ወተትን ለሚመግበው
ሀሞት አመጡለት ይቅመሰው ብለው
አካሉ ሲውጋ ውኃ ደም ፈሰሰ
በምድር ተረጭቶ ዓለምን ቀደሰ
የእስራኤል ሴቶች ዋይ ዋይ ሲሉልህ
ለእነርሱ አሰብክ እንጂ ለአንተስ አላሰብክ
እናቱ ስታለቅስ በመስቀል ስር ሆና
ዮሐንስን ሰጠ ጠብቆ እንዲያጽናና
መላእክትም ታዩ አጋንንትም ሸሹ
የአይሁድ ሠራዊት ፈርተው ተረበሹ

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

                   ሐሙስ
የሰሞነ ህማማት እለተ ሐሙስ ፀሎተ ሐሙስ፣የምስጢር ቀን፣የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ፣ ህፅበተ ሐሙስ ይባላል።ለምን እንደተባሉ ቀጥለን እንመለከታለን
              ፩ ጸሎተ ሐሙስ
ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ በመጸለዩ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።(ማቴ ፳፮፥፴፮)
               ፪ የምስጢር ቀን
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ስለተፈፀመባት የሚስጢርሸቀን ትባላለች። ማቴ፳፮፥፳፮-፳፰ እንዲህ ይላል«ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራ አንስቶ ባረከ ቆርሶም ለደቀመዛሙርቱ ሰጠና እንካችሁ ብሉ ይህ ስጋዬ ነው አለ።ፅዋንም አንስቶ አመስግኖ ሰጣቸው እንዲህም አለ ሁላችሁም ከርሱ ጠጡ ስለ ብዙዎች የሚፈሰው የሀዲስ ኪዳን ደሜ ነው»በዚህ ዕለት ቅዱስ ቁርባን ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል።
             ፫ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ
መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።(ሉቃ ፳፪፥፳ ማቴ ፳፮፥፳፮)
               ፬ የነጻነት ሐሙስ
ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ዮሐ የነጻነት ሐሙስ ይባላል።(ዮሐ ፲፭፥፲፭)
              ፭ ህፅበተ ሐሙስ
ጌታችን አምላክ ሆኖ ሳለ ዝቅ ብሎ የሐዋርያት እግር በማጠቡ ህፅበት ሐሙስ ይባላል።(ዮሐ ፲፫፥፭-፲፪)
   የፀሎተ ሐሙስ እለት ካህናት ለምን የምእመናን እግር ያጥባሉ?
የፀሎተ ሐሙስ እለት ካህናት የምእመናን እግር የሚያጥቡት ምክንያት በዮሐ ፲፫፥፲፬ላይ እንዲህ ይላል«እኔ ጌታና መምህር ስኾን እግራችሁን ካጠብኹ እናንተ ደግሞ ርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ  ዘንድ ይገባችዃል»ስለሚል በዚህ ምክንያት ካህናት የ ምእመናን እግር ያጥባሉ።
 ከፀሎተ ሐሙስ ምን እንማራለን?
                     ፩ ትህትና
 በፀሎተ ሐሙስ ከምንማራቸው ነገሮች ወስጥ አንዱ ሲሆን ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ አምላክ ሆኖ ሳለ ዝቅ ብሎ የሐዋርያትን እግራቸውን አጥቧል (ዮሐ ፲፫፥፭―፲፪) ይሄም ትህትናን ያስተምረናል ካህናትም በዚህ እለት ፆታ፣ቀለም፣ዘር ሳይለዩ የምዕመናን እግር  ያጥባሉ።
               ፪ ፀሎት
ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በፀሎተ ሀሙስ ካስተማረን ነገሮች አንዱ ፀሎት ነው። ጌታችን በጌተሰማኒ ፀልዮ እኛም ፀሎት ማድረግ እንዳለብን ያስተማረን እለት ነው።
               ፫ ስርአተ ቁርባንን
ጌታችን በዚህ እለት ቅዱስ ቁርባንን የጀመረበት እለት ነው።በዚህ ቀን ከተማርናቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ ቅዱስ ቁርባን ነው።
@Nehmeya   @Nehmeya
✥ ሰሞነ ህማማቱን  አሳልፎ በሰላም ለብርሀነ ትንሳኤው ያድርሰን።
✥ ፈጣሪ ኢትዮጵያንን እና ህዝቦቿን ይባርክ።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

                    ስግደት
ስግደት በቤተክርስትያናችን ሁሌም የሚፈፀም ተግባር ነው።ለምሳሌ በቅዳሴ ወቅት ስግዱ ለእግዚአብሔር በፍርሀት ሲለን ካህኑ እኛም ቅድሜከ እግዚኦ ንሰግድ ወንሴብሐከ ብለን እሰግዳለን።በተጨማሪም በንስሀ አባቶቻችን ወይም በራሳችን ፍቃድ እሰግዳለን ነገር ግን በሕማማት ሰሞን ህፃን አዋቂው ዲያቆኑ ጳጳሱ  ሁሉም ይሰግዳል።በሰሞነ ህማማት ከሚፈፀሙ ተግባራት አንዱ እና ዋነኛው ስግደት ነው።
        ስግደት ምሳሌነቱ ምንድን ነው?
ስግደት ምሳሌነቱ ጌታችን በጌቴሰማኒ ሲፀልይ በግባሩ አየወደቀ መነሳቱ ምሳሌ አድርገን እሰግዳለን።በተጨማሪም ጌታችን ለእኛ ሲል በአይሁዳውያን በመንገላታቱ እኛም እሱን እያሰብን እንሰግዳለን።በምንሰግድበት ወቅት ኪርያላይሶን፣ማስያስ፣ታኦስ፣እምኖዲ፣ትስቡጣይ እንላለን የነዚህ ትርጉም እንደዚህ ነው።
              ኪርያላይሶን
ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን» ነው፡፡«ኪርዬ» ማለት «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙም «አቤቱ ማረን» ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን»የምንለው በተለምዶ ነው፡፡
                 ናይናን
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡
                 እብኖዲ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲንል «አምላክ ሆይ ማረን» ማለታችን ነው።
                ታኦስ
የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡«ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡
              ማስያስ
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡«ማስያስ ናይናን» ስንል «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው።
              ትስቡጣ
«ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው።«ትስቡጣ ናይናን»ስንል «ደጉ ገዣችን ማረን» ማለታችን ነው።
@Nehmeya   @Nehmeya
✞ ሰሞነ ህማማቱን አሳልፎ በሰላም ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም ያድርሰን።
✞ ፈጣሪ ኢትዮጵያንን እና ህዝቦቿን ይባርክ።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

ሰላም ውድ የማህበረ ነሕምያ አባላት ይህ ግሩፕ የ መዝሙር ጥናትና ትምህርት ክፍል የከፈተው የ ቴሌግራም ቻናል ሲሆን የሚለቀቅበት
መዝሙሮች
ትምህርቶች
የዕለቱ ስንክሳር ናቸው
/channel/mezmurtinatcomita

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

🙏 ጳጉሜ ፫ (3) ቅዱስ ሩፋኤል🙏

√√√ በየዓመቱ ጳጕሜን ፫(3) ቀን የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት፣ በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ይከበራል፤ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ከከበሩት ቅዱሳን መላእክት ሦስተኛው ነው "ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ” (መ.ጦቢት ፲፪፥፲፭)

√√√ ያለማቋረጥ ፈጣሪያቸውን ልዑል እግዚአብሔርን ከሚያመሰግኑ ቅዱሳን መላእክት መካከል አንዱ የሰላምና የጤና መልአክ የሚባለው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ‹‹ሩፋኤል›› የሚለው የስሙ ትርጓሜ ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ ማለት ነው
የሰው ልጆች ከተያዙበት የኀጢአት ቁስል ይፈወሱ ዘንድ በአማላጅነቱና በጸሎቱ የማይለይ መልአክ ነው ቅዱስ ሩፋኤል በሰውነታችን ላይ የሚወጣውን ደዌም ሆነ ቍስል ይፈውስ ዘንድ ከልዑል እግዚአብሔር ሥልጣን ተሰጥቶታል "በሰው ቍስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው" (መ. ሄኖክ ፮፥፫)

√√√ ለቈሰሉ ፈውስን የሚያሰጣቸው ፣ ለማኅፀን ችግር ሁሉ ለሴቶች ረዳታቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው ፤ በወሊዳቸው ቀን ሴቶች ከሚደርስባቸው ጭንቀትና ሕመም ስሙን ጠርተው ይማጸኑታል፡፡ ፈታሔ ማኅፀን ነውና ቅዱስ ሩፋኤልም ጭንቀታቸውን ያቀላል፦
አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን በወለተ ራጉኤል ላይ አድሮ ባሎቿን እየገደለ ቢያሰቃያት ቅዱስ ሩፋኤል ጋኔኑን አስጨንቆ አስወጥቶላታል ( መ.ጦቢት ፫፥፰-፲፯) ቅዱስ ሩፋኤል "ዳግመኛም እግዚአብሔር ሩፋኤልን፣ አዛዝኤልን እጁን እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ ጣለው አለው" ( መ.ሄኖክ ፫፥፭-፯)

√√√ የጦቢትን ልጁ ጦቢያን በሰው አምሳል ተገልጦ ከተራዳው በኋላ ወደ ሰማይ በሚያርግበት ጊዜ ራሱን ሲገልጥ "የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ወደ ከበረ ወደ ገነነ ወደ እግዚአብሔር ጌትነትም ከሚያገቡ ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ አላቸው" (መ.ጦቢት ፲፪፥፲፭) የቅዱስ ሩፋኤል በዓሉ የሚከበርባቸው ምክንያቶችም ሁለት ናቸው፡፡ እነርሱም አንደኛው በዓለ ሢመቱን ምክንያት በማድረግ ሲኾን ሁለተኛው ደግሞ ቅዳሴ ቤቱ ነው።

√√√ ይህ ቀን የዓመቱ የመጨረሻ ቀናት ውስጥ ስለሚገኝ በየዓመቱ በዚህ ቀን ዝናብ ይዘንባል ይህ ዝናብ እንደ ፀበል በማመን ያለፈውን ዘመን ኃጢያት ከእነሱ እንዲርቅ ኦርቶዶክሶች በእምነት በመጠመቅ ያሳልፉታልና ከታላቁን መልአክ የቅዱስ ሩፋኤል ተራዳዒነት ና ምልጃ አይለየን ዘመኑንን የሰላም ፣ የፍቅርና የአንድነት ያድርግልን !!
👉መምህር ሳሙኤል ግዛው

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ 💚 @uto_pia1 💚 ✥
✥ 💛 @uto_pia1 💛 ✥
✥ ❤️ @uto_pia1 ❤️ ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

አቡነ ሀብተ ማርያምም ‹‹ጌታዬ ነገሩ ምንድን ነው?›› ሲሏቸው አቡነ ተክለሃይማኖት ‹‹ከተቀበርኩበት ቦታ እንድትቀበር ቃል ኪዳን ግባልኝ›› አሏቸው፡፡ አቡነ ሀብተማርያምም ‹‹አባቴ ሆይ ይህንን አደርግ ዘንድ ስለምን ትወዳለህ?›› አሏቸው፡፡ አቡነ ተክለሃይማኖትም በሀገሬ ላይ የታዘዙ አምስት መቅሰፍቶች አሉና ስለዚህ ነው እነዚህም አንዱ መብረቅ ነው፤ ሁለተኛውም ቸነፈር ነው፤ ሦስተኛውም ረሃብ ነው፤ አራተኛውም ወረርሽኝ ነው፤ አምስተኛውም የእሳት ቃጠሎ ነው፡፡ የአንተ አጽም በውስጡ የተቀበረ እንደሆነ አጥንቴ የተቀበረባት ሀገሬ ከነዚህ መቅሰፍታት ትድናለች›› አሏቸው፡፡

አቡነ ሀብተ ማርያምም ‹‹ንዑድ ክቡድ የምትሆን አባቴ ሆይ ልዩ ክቡር በሚሆን በአንተ አጽም መቀበር ያልዳነች በእኔ አጽም መቀበር ድኅነት ታገኛለችን? ይህንስ ተወው›› ብለው በተከራከሯቸው ጊዜ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም መልሰው ‹‹ልጄ ሀብተ ማርያም ሆይ አንተ የማታውቀው ከፈጣሪያችን ከእግዚአብሔር የተሰጠህ እኔ የማውቀው ክብር አለህና ስለዚህ ነው፡፡ ይልቁንስ እንዳልኩህ በተቀበርኩበት ቦታ እንድትቀበርልኝ ቃልኪዳን ግባልኝ›› ብለው ማለዷቸው፡፡ ይህንንም ሲባባሉ እንዲህ የሚል ቃል መጣላቸው፡- ‹‹ከወዳጄ ከሀብተ ማርያም አንደበት ይህ ቃልኪዳን አይወጣም፣ ዳግመኛም ወዳጄ ተክለ ሃይማኖት ሆይ! እርሱ በወደደው የሚቀበር አይደለምና እኔ ከተቀበርኩበት እንድትቀበር ብለህ የምታስገድደው ለምንድን ነው? እኔ በወደድሁት ቦታ ይቀበራል እንጂ›› የሚል ቃል ተነገረ፡፡ አቡነ ተክለሃይማኖትም እየለመኑናና እየሰገዱ ከሥላሴ ዙፋን ፊት ተንበረከኩ፡፡ ሦስተኛውም ‹‹ይሁን እንዳልከው ይቀበርልህ›› የሚል ቃል ተሰማ፡፡ ዳግመኛም ‹‹በአንተም አጽም በሀብተ ማርያምም አጽም ቦታህ ከመቅሰፍታት ትዳንልህ፤ ልጆችህ ግን በቸነፈር ደዌ ቢሞቱ ከሰማዕትነት ተቆጥሮላቸው ወደ መንግሥተ ሰማያት እንዲገቡ በራሴ ምዬ ቃልኪዳን ገብቼልሃለሁ›› አላቸው፡፡ በዚህም ጊዜ አቡነ ተክለሃይማኖት እጅግ ደስ ተሰኝተው ሦስት ጊዜ ሰገዱ፡፡

ከዚህም በኋላ መልአኩ ለአቡነ ሀብተ ማርያም ክብሯ እንደ ጽርሐ አርያም የሆነች አገርን አሳያቸው፡፡ ሥፍር ቁጥር የሌላቸውም ቅዱሳን መላእክት በውስጧ ተድላ ደስታ ያደርጉባት ነበር፡፡ አባታችንም መልአኩን ‹‹ይህች ክብሯ ፍጹም የሆነችን አገር ማን ትባላለች በውስጧ ለመኖር በእጅጉ ወድጃለሁና›› ብለው ሲጠይቁት መልአኩም ‹‹ይህችማ አገር የአባትህ የተክለ ሃይማኖት አጽም ያረፈባት ደብረ ሊባኖስ ናት፤ ከእርሱም ጋር በክብር እስክትነሣ ድረስ በውስጧ ትቀበርባት ዘንድ ለአንተም ተሰጥታሃለችና ደስ ይበልህ፡፡ አባትህም እንደ ኢየሩሳሌም እንደትሆንለት ቃልኪዳን ተቀብሎባታል›› አላቸው፡፡
በአንደኛውም ቀን አቡነ ሀብተ ማርያም ከሌሎች ቅዱሳን ጋር ሆነው ሲሄዱ ብዙ አጋንንት እየተደነባበሩ ወደ ታች ሲወርዱ ተመለከቱና አባታችን ሥራቸውን ለማየት ተከተሏቸው፡፡ አንዱንም ኃጥእ ይዘው ነፍሱን ከሥጋው ለዩዋትና ወደ ሲኦል አወረዷት፡፡ አባታችንም ከሌሎቹ ቅዱሳን ጋር ሆነው ያችን ነፍስ ይምርላቸው ዘንድ ጌታችንን በጸሎት ማለዱት፡፡ ነገር ግን ‹‹ለጣዖት ስትሰግድ ስለኖረች ይህችን ነፍስ አልምራትምና አትድከሙ›› የሚል ቃል ከልዑል እግዚአብሔር ዘንድ መጣላቸው፡፡ ቅዱሳኑም ‹‹ልመናችንን የማትቀበል ከሆነ በከንቱ ሰብስበኸናል›› ብለው ቢያዝኑ እግዚአብሔርም ‹‹ሕገ እግዚአብሔርን የዘነጉ ሰዎችን ቅጣት እንድታዩ ነው›› አላቸው፡፡ እነርሱም ሕገ እግዚአብሔርን የዘነጉ ሰዎችን ሲቀጣቸው ለደጋጎቹ ሰዎች ደግሞ መልካሙን ዋጋቸውን ሲሰጣቸው አይተው አንድ ሆነው አመስግነውታል፡፡

ከዚህም በኋላ መልአኩ ቅዱስ ራጉኤል አንዱን ሰው በመብረቅ ቀሰፈውና ቅዱስ ሚካኤል ሄዶ ቅዱስ ራጉኤልን ሲከራከረው አባታችን ተመለከቱ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ‹‹የእኔ አገልጋይ ነውና ለምን ገደልከው?›› ሲለው ቅዱስ ራጉኤልም ‹‹ሰንበት ሳይለይ ዝሙትን መሥራት የለመደ ሥራውም ዝሙት ስለሆነ በፈጣሪዬ ታዝዤ ነው የገደልኩት፡፡ ኃጥአንን ሊያጠፋ እንጂ ጻድቃንን ለመቅጣት መብረቅ እንዳይታዘዝ አንተስ ታውቅ የለም እንዴ?›› አለው፡፡ ይህንንም ተባብለው ከሥላሴ ፊት ሰግደው ቅዱስ ሚካኤል የተገባለትን ቃልኪዳን በማሳሰብ ምልጃውን አቀረበ፡፡ እግዚአብሔርም በጎና ክፉ ሥራዋን ባስመዘነ ጊዜ በጎ ሥራዋ ስለበለጠ ቅዱስ ሚካኤል ያችን ነፍስ ታቅፎ ወስዶ ለቅዱስ ገብርኤል ሰጠው፡፡ ሰባቱም ሊቃነ መላእክት እየተቀባበሉ ወስደው ከመስቀል ዘንድ አደረሷት፡፡ ለቅዱስ መስቀልም ካሰገዷት በኋላ አሳልመዋት በቅዱስ ሚኤካል አማላጅነት ወደ ገነት አስገቧት፡፡ አቡነ ሀብተ ማርያምም ይህን በተመለከቱ ጊዜ ቅዱስ ሚካኤልን ‹‹መስቀል ታሳልሟት ዘንድ ያችን ነፍስ ወደ መስቀል ለምን ወሰዳችኋት?›› ብለው ጠየቁት፡፡ መልአኩም ‹‹በትልቅም በትንሽም ነገር ክርስቲያናዊትን ነፍስ የሚቃወም ቢመጣባት ድል የምትነሳበትን በመስቀል ፍርድ ይታይላታልና ስለዚህ ነው፡፡ የሚከራከራት ቢኖር ግን እንዳየኸው ወደ መስቀል ባደረሷት ጊዜ የሚቃወማት ሰይጣን ፈጥኖ ይርቅላታል ዳግመኛም ሊከራከራት አይችልም›› አላቸው፡፡

ከአቡነ ሀብተማርያም በረከት ለመቀበል ብዙ ቅዱሳን ከሮም፣ ከግብፅ፣ ከአስቄጥስና ከሲሐት ገዳም ወደ አባታችን ዘንድ ይመጡ ነበር፤ ከየሀገራቸውም በአንበሳ ተቀምጠው የሚመጡ አሉ፤ ክንፍ ተሰጥቷቸው እንደ ንስር የሚበሩም አሉ፤ ብፁዕ አቡነ ሀብተ ማርያምም የቅዱሳኑን ብቃት አይተው ‹‹ሥራችሁ እንዲህ እንዲህ ሲሆን ለምን ወደኔ መጣችሁ?›› ብለው ሲጠይቋቸው ቅዱሳኑም ‹‹በማንኛውም ሥራ እግዚአብሔርን በለመነው ጊዜ በኢትዮጵያ የሚኖር እንደ ሙሴ ያለ ሀብተ ማርያም የሚባል ወዳጄ አለና ሁሉን ስለሚነግራችሁ ዘወትር እርሱን ጠይቁ ብሎ ስላዘዘን ወደ አንተ መጣን›› አሏቸው፡፡ አባታችንም ቅዱሳኑን ከባረኳቸውና ከእነርሱም ከተባረኩ በኋላ አባታችን ለቅዱሳኑ የሚመጣውን እንዳለፈ የሚደረገውንም እንደተደረገ አድርገው ይነግሯቸዋል፡፡ ቅዱሳኑም ከልጅነታቸው ጀምረው እስከዚያች ቀን ድረስ የሠሩትን ሥራ ሁሉ ይነግሯቸዋል፡፡ እነርሱም እጃቸውን እየሳሙ በረከታቸውን ይቀበሉ ነበር፡፡ እንደዚሁም አቡነ ሀብተ ማርያም ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል እየተራዱዋቸው ቀድሰው በሚያቆርቡ ጊዜ ተሰውረው የሚኖሩ 500 ስውራን ቅዱሳን መጥተው ሥጋ ወደሙን ከአባታችን እጅ ተቀበሉ፡፡ ቀድሰውም ወደበዓታቸው እንደገቡ እመቤታችን ተገልጣላቸው ‹‹በነገውም ዕለት ቅዳሴዬን ቀድስ፣ ይህም ቅዳሴ መዓዛ ቅዳሴ ነውና፡፡ የዓለም መሠረት ማርያም ወደኔ ነይ ብለህ በጠራኸኝ ጊዜ ነቢያትን ሐዋርያትን አስከትዬ መጥቼ እባርክሃለሁ›› አለቻቸው፡፡ አባታችንም ‹‹በነገው ዕለት ሌላ ተረኛ ቄስ ይቀድሳልና ይህ እንዴት ይሆንልኛል?›› አሏት፡፡ እመቤታችንም ‹‹ፈቃዴ ስለሆነ አንተ እንድትቀድስ አደርጋለሁ›› አለቻቸው፡፡ በነጋታው ተረኛው ቄስ ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ ቸኩሎ እየተፋጠነ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲገሰግስ ወድቆ ጥርሱ ደማና ስለ ሥጋ ወደሙ ቅዳሴ እጅግ ደንግጦ ወደ አባታችን መጥቶ ‹‹ቅዳሴው በእኔ ስም ከሚታጎል አንተ ቀድስልኝ›› አላቸው፡፡ አባታችንም አስቀድማ እመቤታችን የነገረቻቸውን ነገር አስበው እያደነቁ ሄደው ቀደሱ፡፡ እመቤታችንም ነቢያትን ሐዋርያትን አስከትላ መጥታ ባረከቻቸው፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።

[ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ እና ከገድላት_አንደበት]

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

አቡነ_ሀብተ_ማርያም

ዳግመኛም በዚህች ቀን ቅዱስ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም ፅንሰታቸው ነው። አባታቸው ፍሬ ቡሩክ እናታቸው ዮስቴና የሚባሉ በሕገ እግዚአብሔር፣ በሃይማኖት፣ በትሩፋትና በምግባር ጸንተው የሚኖሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ ቅዱስ አባታችን ፅንሰታቸው ነሐሴ 26፣ ልደታቸው ግንቦት 26፣ ዕረፍታቸው ኅዳር 26 ነው፡፡ አቡነ ሀብተ ማርያምን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ‹‹አምስት መቅሰፍታት እንዲጠፉ በደጄ በደብረ ሊባኖስ ተቀበርልኝ›› ብለው የለመኗቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡

የአቡነ ሀብተ ማርያም እናት ቅድስት ዮስቴና ጻድቁ አቡነ ሀብተ ማርያምን ከመውለዷ በፊት ‹‹ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢገዛ ነፍሱን ካጣ ምን ይጠቅመዋል?›› የሚለውን የወንጌል ቃል አስባ መንና ወደ በረሃ የገባች ቢሆንም በበረሃ ውስጥ ከሰው ተለይቶ የሚኖር የበቃ ባሕታዊ በዋሻ ውስጥ አገኘችና ለምነና ወደ በረሃው እንደመጣች ነገረችው፡፡ ባሕታዊውም በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ካመለከተ በኋላ ‹‹ምንኩስና ለአንቺ አልተፈቀደልሽም፣ ወደ ቤትሽ ግቢ፣ ከሕጋዊ ባልሽ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ እርሱም ለዓለም ሁሉ የሚጠቅም፣ ሰው ሁሉ የሚማፀነው፣ ገድሉ ትሩፋቱ በዓለም የሚነገርለት፣ በነፍስም በሥጋም የሚያማልድ፣ እንደ መልአክትም ክንፈ ጸጋ የሚሰጠው በምድር ሆኖ መንበረ ጸባኦትን የሚያይ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ›› በማለት ትንቢት ከነገራት በኋላ ቅድስት ዮስቴና ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡ እርሷም ሀብተ ትንቢት እስከመሰጠት ድረስ የደረሰች በሃይማኖት በምግባር በትሩፋት ያጌጠች ሆነች፡፡

ቅድስት ዮስቴናም ወደ ቤቷ ከተመለሰች በኋላ አቡነ ሀብተ ማርያም ተወለዱና ወላጆቻቸው ፈሪሃ እግዚአብሔርን እያስተማሩ አሳደጓቸው፡፡ ከዕለታት በአንድ ቀን ካህናቱ በቤተ ክርስቲያን ምህላ ሲያደርሱ ‹‹እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ›› እያሉ ሲጸልዩ ሰምተው በልቡናቸው ‹‹ይህች ጸሎት በጣም ጥሩ መልካም ጸሎት ናት፤ እኔ ይህችን ጸሎት መርጫታለሁ፤ በዚህ ጸሎት ዓለም ከአሳችነት ኅሊና በሚመጣውም ዓለም ከገሃነም እሳት እንድንድንባት አውቃለሁ›› አሉ፡፡ ይህችንም ጸሎት ማዘውተር ጀመሩ፡፡ እናትና አባታቸውም በተኙ ጊዜ ሌሊት ለጸሎት ተነሥተው በዚህ ጸሎት ፈጣሪአቸውን ያመሰግኑ ነበር፤ ስግደትን ይሰግዳሉ ነገር ግን እናትና አባታቸው ከእንቅልፋቸው በነቁ በጊዜ ሮጠው ወደ መኝታቸው ሄደው ይተኛሉ፡፡ የጽድቅ ሥራቸውንም ከአምላካቸው በቀር ማንም አያውቅባቸውም ነበር፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ አባታቸው ፍሬ ብሩክ የበግ ጠባቂ አደረጋቸው፡፡ እግዚአብሔር ግን በኋላ ለብዙዎች ስውራን ቅዱሳንና በዓለም ለሚኖሩ ምዕመናን በጎች ጠባቂ ያደርገው ዘንድ ወዶ መርጦታልና ያ ቀን እስኪደርስ ድረስ ፈጣሪያችን አቡነ ሀብተ ማርያምን ይጠብቃቸው ነበር፡፡

ከዕለታትም በአንደኛው ዕለት አባታቸን በጎችን ሲጠብቁ ሌሎች እረኞች በአመጻ ከሰው ሰርቀው ቆርጠው ያመጡትን እሸት ‹‹ና እንብላ›› አሏቸው፡፡ አባታችን ግን ‹‹ከየት እንዳመጣቸሁት ምንም ስለማላውቅ አልበላም›› አሏቸው፡፡ እረኞቹም ሀብተ ማርምን በቁጣ ዐይን እያዩአቸው ተቀምጠው ሲበሉ አባታችን ‹‹የማንችለው ዝናብ መጥቷልና ተነሡ በፍጥነት ወደቤታችን እንሂድ›› አሏቸው፡፡ እረኞቹም ‹‹ሰማዩ ብራ ነው ምንም ደመና የለውም፤ ነፋስም አይነፍስም፡፡ እኛ የማናየው አንተ ብቻ የምታየው ምን ነገር አለ?›› እያሉ በአባታችን ላይ ተዘባበቱባቸው፡፡ አባታችን ግን በጎቻቸውን እያስሮጡ በፍጥነት ወደ ቤታቸው ሄዱ፡፡ ወዲያውም በጣም ኃይለኛ ዝናብ ዘነበ፡፡ የጥፋት ውኃው በላያቸው እስኪፈጸምባቸው ድረስ እነዚያን እረኞች ከቦታቸው አልተነቃነቁም ነበርና በጥፋቱ ውኃ አለቁ፡፡ በዚያችም ሌሊት አቡነ ሀብተ ማርያን ከሰማይ ሦስት ጊዜ ‹‹ሀብተ ማርያም ሀብተ ማርያም›› የሚል ድምፅ ጠራቸው፡፡ አባታችንም እንደ ሳሙኤል ‹‹ጌታዬ ባሪያህ ይሰማሃል ተናገር›› ሲሉ ጌታችን አናገራቸው፡፡ ‹‹ከዚህ በኋላ ለሚሰሙህ ለመረጥኳቸው ቃሌን ትነግራቸው ዘንድ ከእኔም ጋር በምሥጢር በባለሟልነት ትነጋገር ዘንድ መርጨሃለሁ›› አላቸው፡፡

ከጥቂት ቀንም በኋላ አባታችን በጎችን እየጠበቁ ሳሉ አንድ አመጸኛ መጣና በትራቸውን በኃይል ነጥቆ ወሰደባቸው፡፡ አቡነ ሐብተ ማርያምም ‹‹በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ እቋቋምህ ዘንድ ኃይል የለኝምና በትሬን መልስልኝ›› ቢሉት የትዕቢትን ቃል ተናገራቸው፡፡ አባታችንም ‹‹እምቢ ካልክስ እሺ የእግዚአብሔርን ኃይል ታያለህ›› አሉት፡፡ ወዲያም ያ አመጸኛ ላዩ ታች፣ ታቹ ላይ፣ ግራው ቀኝ፣ ቀኙ ግራ ሆኖ በአየር ላይ ተሰቅሎ ዋለና እየጮኸ አባታችንን ለመናቸው፡፡ አባታችንም ‹‹የቀጣህ እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ›› ባሉት ጊዜ ከተሰቀለበት ወርዶ በእግሩ ቆመ፡፡ በዚያ የነበሩና ይህንን ተአምር ያዩ እረኞችም እጅግ ፈርተው ሄደው ለወላጆቻቸው ያዩትን ተናገሩ፡፡ የሀገሩ ሰዎችም ‹‹ቀድሞ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ እያለ ሲጸልይ ሲሰግድ አይተነዋል አሁንም ጠላቱን በነፋስ የሚቀጣ ይህ ልጅ ወደፊት ምን ይሆን!›› እያሉ አደቁ፡፡ ወላጆቻቸውም ይህን በሰሙ ጊዜ በግ ጠባቂነቱን አስተዋቸውና ወስደው ለመምህር ሰጧቸው፡፡ አቡነ ሀብተ ማርያምም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሁሉ በሚገባ ተማሩ፡፡

ከዚህም በኋላ አባታቸው ከሀገሪቱ ታላላቅ ሰዎች አንዷን እጮኛ አጨላቸው፡፡ ነገር ግን አቡነ ሀብተ ማርያም ‹‹አባቴ ሆይ እኔ ራሴን ለክርስቶስ በድንግልና ለመኖር አጭቻለሁ፣ ተራክቦዬም ቃለ ወንጌልን መስማት እንጂ ሌላ አይደለምና ለምን እንዲህ ትለኛለህ?›› አሉት፡፡ አባታቸውም ይህን ሲሰማ ተቆጥቶ ያለ አቡነ ሀብተ ማርያም ፈቃድ ሙሽራይቱን ለማምጣት ሄደ፡፡ አባታችን ግን ሀገር ጥለው ለመሰደድ ከቤት ተደብቀው ወጡ፡፡ መንፈስ ቅዱስም በመብረቅ አምሳል አባታቸውን ገስጻቸውና በዚህ ድንጋጤ ምክንያት ከዚህ ኃላፊ ዓለም ዐረፈ፡፡

አባታችንም የአባታቸውን ዕረፍት ሳያዩ አፋር ወደምትባል ሀገር ሄደው አባ ሳሙኤል ከሚባል ደግ መነኩሴ ቦታ ገብተው መነኩሴውን እያገለገሉት ኖሩ፡፡ አንድ ቀን አባታችን እንስራ ተሸክመው ውኃ ይቀዱ ዘንድ ወደ ወንዝ ወረዱና ውኃውን ቀድተው ሲመለሱ ድንጋይ አደናቀፋቸውና እንስራው ከላያቸው ላይ ወደቀ፡፡ ነገር ግን መሬት ከመድረሱ በፊት አባታችን ፈጥነው የጌታችን ስም በጠሩ ጊዜ እንስራው ወድቆ ሳይሰበር ተመልሶ በትከሻቸው ላይ ተቀመጠ፡፡ አባ ሳሙኤልም ይከተሏቸው ነበርና ይህን ጽኑ ተዓምር አይተው እጅግ አደነቁ፡፡

እንዲሁ ከዕለታት በአንድ ቀን በሌሊት መብራት ለአባ ሳሙኤል እያበሩ ሳለ መብራቱ ከእጃቸው ላይ ወድቆ ጠፋ፡፡ መምህሩም አባ ሳሙኤል ቁጡ ነበረና ስለ መምህራቸው ቁጣ በጣም ደንግጠው ወድቆ የጠፋውነ መብራት ፈጥነው ባነሱት ጊዜ መብራቱ በእግዚአብሔር ተዓምር ራሱ በርቶ ታየ፡፡ አባ ሳሙኤልም ይህን ተዓምራት አይቶ እጹብ እጹብ በማለት ‹‹የዚህ ቅዱስ ልጅ መጨረሻ ምን ይሆን?›› ብሎ ካደነቀ በኋላ ‹‹የዓለም ሁሉ የጥበብ መብራት ይሆናል›› ሲል ትንቢት ተናገረላቸው፡፡ እመቤታችን ለአባ ሳሙኤል ተገልጣላቸው የአቡነ ሀብተ ማርያምን ክብር ነግራዋለች፡፡ አባታችንም አባ ሳሙኤልን 12 ዓመት ከትሕትና ጋር እየታዘዙ ቤተ ክርስቲያንን እያገለገሉ ኖረው ከዚህ በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ ወጥተው ሄደው እለ አድባር በተባለ ገዳም መኖር ጀመሩ፡፡ ከቦታውም ደርሰው ጥቂት ከቆዩ በኋላ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ከአባ መልኬጼዴቅ እጅ የምንኩስናን ስርዓት ተቀበሉ፡፡ ይኸውም የሚዳው አቡነ መልኬጼዴቅ በደጃቸው የተቀበረውን ሰው አፈር የማያስበሉት ጻዲቅ ናቸው፡፡ ይህንንም የጻድቃኑን

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

ደብረ ታቦር ቡሄ

የደብረ ታቦር በዓል ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በታቦር ተራራ ብርሃነ መለኮቱን ክብረ መንግስቱን መግለጡን በማሰብ በየዓመቱ በድምቀት ይከበራል።

በዚህ በዓል በተዋህዶ የከበረ አምላክ ሲሆን በፈቃዱ የሰውን ባሕርይ ያለመለወጥ የተዋሐደ ጌታ መለኮታዊ ክብሩ የተዋሕዶው ፍፁምነት ይነገርበታል የነብያትና የሐዋርያት ምስክርነት ይተረጎምበታል።

በባሕላዊ ገፅታው ይህ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ቡሄ በመባል ይታወቃል። ቡሄ ማለት መላጣ፤ ገላጣ ማለት ነው ክረምቱ፤ ጭጋጉ፤ ደመናው ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታይበት በዚሁ በዓል አካባቢ ስለሆነ በዓሉ ቡሄ ተብሎ ይጠራል። በዓለ ደብረ ታቦር ጌታችን ምስጢረ መለኮቱን የገለጠበት ብርሃን የታየበትና ድምፀ መለኮቱ የተሰማበት ዕለት ስለሆነ የብርሃን በዓል ይባላል።

              እንኳን አደረሳቹ

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

ሰላመ እግዚአብሔር ከናንተጋር ይሁን ረቡዕ ማለትም 26/11/15 ጀምሮ በየሳምንቱ እሮብ እና አርብ ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ የመዝሙር ጥናት ስለሚኖር ሁላችንም መድሀኒአለም ቤተክርስቲያን እንገኝ:: ማንኛውም መዝሙር ማጥናት የሚፈልግ ሰው መምጣት ይችላል ።

ማህበረ ነህምያ ዘ ኮተቤ
/channel/nehemyamezmur

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

ገብርኤል መልአከ ራማ

ገብርኤል (፪)
ገብርኤል መልአከ ራማ (፪)
ስንጠራህ ፈጥነህ ድረስ ድምጽህን እናስማ

ትንቢቱ ሲፈጸም ዘመኑ ሲያበቃ
ከቀናት ሳትዘግይ ሳይጎድል ደቂቃ
ወደ ድንግል መጥተህ ደስታን አበሰርክ
የአምላክን ሰውን መሆን ለአለሙ ሰበክ(፪)
አዝ
ከውኃ እና ከሳት ከሞት አመለጡ
በእሳቱ መካከል ለጥፋት ቢሰጡ
አንተ ባለህበት በየትኛውም ስፍራ
ምንም ቦታ የለውም ሞትና መከራ(፪)
አዝ
የመንገድ መሪ ፈውስ ነህ ለህመሜ
ገብርኤል ስትመጣ በዛልኝ ሰላሜ
ደስታን አብሳሪ ተሸክመህ ዜና
ዛሬም ለአገራችን ምስራች ይዘህ ና(፪)            
አዝ
አንጌቤናይቱ ቅድስት እየሉጣ
ስለአንተ ትመስክር እስከ ልጇ ትምጣ
እሳተ ነህ ገብርኤል ነባልባልባ አስወጋጅ
የአምላክ መወለድ ለአለም ምታውጅ(፪)
 @Nehmeya  @Nehmeya
✥ እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ  ክብረ በአል በሰላም አደረሰን።
✥ መልካም ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

ሞገድ ሲመታኝ ማዕበሉ
ማን ያድነዋል ሁሉም ሲሉ
በሰላም አለፍኩ በፀጥታ
ሁሉ ተችሎ ባንተ ጌታ

ባንተ ቁስል ተፈወስኩኝ
ጌታ በፍቅርህ ተማረኩኝ
ሞቴን ሽረኸው ባንተ ሞት
ይኸው አቆምከኝ በህይወት

ደጅ ስጠና ስማፀንህ
መቼ ጨከነ ጌታ ልብህ
እንደ ቀራጩ አጎነበስኩ
ምህረት ፀጋህን ከእጅ ለበስኩ

ዘወትር እልል ብል ብዘምር
ስለገባኝ ነው ያንተ ፍቅር
ጌታ ብጠራው ስምህን
ለውጠኸው ነው ታሪኬን

አይኖቼ አያዩም ካንተ በቀር
የምትወደድ የምትፈቀር
ዘመድ ወገኔ ሆነኸኛል
እኔን የሚችል የት ይገኛል

@Nehmeya  @Nehmeya
✞ ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
✞ መልካም ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ ሐምሌ ፭ ቀን ጴጥሮስ ወጳውሎስ በማለት ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እና ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልካሙን የክርስትና ገድል ተጋድለው ሰማዕትነት የተቀበሉበትን ቀን በታላቅና በተለየ ሁኔታ ታከብራለች። ክርስትናን በማስፋፋት ከፍተኛውን ሚና የተጫወቱት እነዚህ ቅዱሳን አባቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መልእክታትን ጽፈዋል። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ስምንት ምዕራፎችን የያዘ ሁለት መልእክታትን ሲጽፍ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ አንድ መቶ ምዕራፎችን የያዘ አሥራ-አራት መልእክታትን ጽፏል። ለአግልግሎት የጠራቸውም የክብር ባለቤት የሆነው አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
 
@Nehmeya  @Nehmeya
✞ ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
✞ መልካም ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

ግንቦት_26 ልደቱ ለ አቡነ ሀብተማርያም ጻድቅ

         #አቡነ_ሀብተማርያም
† ባሕር ውስጥ ሰጥሞ 500 ጊዜ ይሰግዳል፤
† በየቀኑ 4ቱን ወንጌልንና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያል፤
† በ40 ቀናት ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባል፤
† ምግቡ ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው፤
† በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋል፤
† ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላል፥ ክቡር ደሙን ይጠጣል፤
† በልቡ ውስጥ በፍጹም ቂምን፣ መከፋትን አያሳድርም፡፡
† የብረት ሰንሰለት በወገቡ ታጥቆ ይሰግዳል ይጸልያልም፡፡
"ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሀብተ ማርያም"  የተባለላቸው ታላቅ አባታችን ናቸው   ፡፡

† እንኳን ለአባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም የልደት  መታሰቢያ በዓል  አደረሰን አደሰችሁ ::
† መልካም  ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

            ውበት ነሽ

ውበት ነሽ ለቤቴ ለኑሮዬ ፋና
ድንግል ሆይ አትለይኝ ብቻዬን ነኝና
              አዝ
በሃዘን ጠቋቁራ ተከፍታለች ገፄ
አጎንብሻለሁኝ አፈሬ በለምፄ/2/
ወልቋል ከራሴ ላይ የብርሃን ልብሴ
ሃብቴ አንቺ ብቻ ነሽ ያለሽኝ ሞገሴ/2/
                አዝ
ለአምላኬ የማቀርበው አጣሁ በጎ ስራ
ነፍሴ ተጨነቀች በምግባሬ መርራ/2/
ጥላሸቱ በዝቶ ተዳፍኖኗል ጎጆዬ
ብርሃን የለውም ካልበራ ሻማዬ/2/
               አዝ
የምታመንበት አንዳች ነገር የለኝ
በነፍስም በስጋ ሁሉ የጎደለኝ/2/
እጠባበቃለሁ የእጅሽን በረከት
እቤቴ ላይ አርፎ እስክባረክበት/2/
                 አዝ
የጓዳዬ ክብር የቅጥሬ ድምቀት ነሽ
ዓይኔን የምትሞይው በመቅረዜ በርተሽ/2/
የፅልመት ጭላንጭል ጠፍቷል የለም ዛሬ
የብርሃን እናት ስላለች በበሬ/2/
 @Nehmeya  @Nehmeya
✞ፈጣሪ ሀገራችንን ፍፁም ሰላም ያድርግልን።
✞ መልካም  ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

                      ቅዳሜ
የአብይ ፆም የመጨረሻዋ ቀን ስትሆን ቀኗም የተለያዩ ስያሜዎች አሏት ከነሱም መካካል
                 ፩ ቀዳም ሽዑር
ይህች እለት ከሌሎቹ ቅዳሜዎች በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ( ሽዑር ቅዳሜ) ትባላለች።
             ለምለሟ ቅዳሜ
በዚች እለት ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቄጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለሟ ቅዳሜ ትባላለች። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል።
                 ቅዱስ ቅዳሜ
ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል።
   ካህናት ለምን ለምእመናን ቄጤማ ማደሉ የምን ምሳሌ ነው?
የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርሰቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ለምእመናንን
ያበሥሩበታል፡፡
       ቄጤማውን በራሳችን የማድረጋችን የምን ምሳሌ ነው?
ጌታችን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በማድረግ  በራሳችን ላይ እናስረዋለን።
@Nehmeya   @Nehmeya
✥ ፆማችንን በሰላም አስፈፅሞን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም ያድርሰን።
✥ ፈጣሪ ኢትዮጵያን ህዝቦቿን ይባርክ።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

                     ዓርብ
የሰሞነ ህማማት አርብ ብዙ ስያሜዎች ያሉት ሲሆን ከነሱ መካከል እነዚን እንመለከታለን
          ፩ የስቅለት ዓርብ ይባላል
ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ  በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ ስቅለተ ዓርብ ይባላል።
          ፪ መልካሙ ዓርብ ይባላል፡-
ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።
☞ይህች ቀን ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርሰቶስ ምንም በደል እና ጥፋት ሳይኖርበት እኛን ለማዳን ሲል በመስቀል መሰቀሉን የምናስብበት እለት ነው።በዚህች እለት ሰው ከእግዚአብሔር ጋር የታረቀበት እለት ነው።
@Nehmeya   @Nehmeya
† ሰሞነ ህማማቱን አሳልፎን በሰላም ለብርሀነ ትንሳኤው ያድርሰን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

ረቡዕ
የሰሞነ ህማማት እለተ ዕሮብ ምክረ አይሁድ፣የመልካም መዐዛ ቀን እንዲሁም የእንባ ቀን ይባላል። ለምን እደንደተባሉ እንዲህ እንመለከታለን።
                ፩ ምክረ አይሁድ
ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል።
ይህንንም ሉቃ ፳፪፥፩-፮፣ማቴ ፳፮፥፫፣ማር ፲፬፥፲፩ላይ እናገኘዋለን። በዚህ ምክንያት ይህቺ ቀን ምክረ አይሁድ ይባላል
             ፪ የመልካም መዓዛ ቀንም
ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ይህ ቀን የመዓዛ ቀን ይባላል።ይህን ታሪክ በማቴ ፳፮፥፮-፯  ላይ እናገኘዋን።
                   ፫ የእንባ ቀን
ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለች በዚህ ምክንያትም የእንባ ቀን ይባላል።ሉቃ ፯፥፴፯
@Nehmeya   @Nehmeya
✞ ሰሞነ ህማማቱን አሳልፎ በሰላም ለብርሀነ ትንሳኤው ያድርሰን።
✞ ፈጣሪ ኢትዮጵያንን እና ህዝቦቿን ይባርክ።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

                     ማክሰኞ
የሰሞነ ህማማት ማክሰኞ የጥያቄ ቀን እና የትምህርት ቀን ይባላል ለምን እንደሆነ ቀጥሎ እናያለን
           ፩ የጥያቄ ቀን ይባላል
ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል።
          ፪ የትምህርት ቀን ይባላል
በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪።
@Nehmeya   @Nehmeya
✞ ሰሞነ ህማማቱን አሳልፎ በሰላም ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም ያድርሰን።
✞ ፈጣሪ ኢትዮጵያንን እና ህዝቦቿን ይባርክ።

Читать полностью…
Subscribe to a channel