oneummha | Unsorted

Telegram-канал oneummha - One ummah

188

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 👉🏾ይህ ቻናል በ አላህ ፍቃድ የተለያዩ ኢስላማዊ ሙሀደራዎች፣ሐዲሶች ፣ወደናንተ ለማቅረብ ታስቦ የተዘጋጀ ቻናል ነው ፡፡ ቻናላችንን በመቀላቀል የኸይር ተካፋይ ይሁኑ..... ለሃሳብ አስተያየቶ @oneummha_bot

Subscribe to a channel

One ummah

ቢክራሽን (ድንግልናሽን) በሀራም
አትስጭው!!
——-------------

ፈገግግግግ እያላቹህ እችን ድንቅ ምክር አዳምጡ ሴቶችየ❗️

ምላሱ ከጦር ይሰላል፣ ምታሀታዊ የፍቅር ቃላቶቹ ልብሽን ሰቅዞ ይይዝሽና የደም ዝውውርሽ ቀጥ እስኪል ካለሱ እንዳታስቢ ያደርግሻል!። በየ ደቂቃው ይደውላል፣ ያስመስላል፣ መወደዱን መፈቀሩን እስኪያረጋግጥ የፍቅረኛ ገፀ ባሀሪን ይተውነዋል። አቤት! ከዚያማ የአይንሽ ረሀብ፣ የልብሽ ስስት መሆኑን ሲረዳ በፍቅሩ መነደፍሽን መምበርከክሽን ሲያረጋግጥ ሰወር ያለ ቦታ ይቀጥርሻል፣ የወደፊቱ ባልሽም አይደል¡ ታምኚዋለሽ ትከተይዋለሽ እንዴትስ አታምኚው?!....ምሎ ተገዝቶ ምንም አይፈጠርም ብሎ ዋሽቶ ፀጥ ያለ ስፍራ ይጋብዝሻል። አንቺማ ተላላዋ የመቃወም አቅምሽ ክዶሽ እሺ ብቻ፣ መከተል ብቻ፣ ለምኖም አልቅሶም ያሰበውን በአላህ ዘንድ የተጠላውን የተወገዘውን ዝሙት ይፈፅማል። ድንግልናሽን ይገረስሰዋል.....

ብዙ እህቶች ተታለን ነው ድንግልናችንን ያጣነው ሲሉ መስማት ተለምዷል፣ እና ፎቶ ልትነሱ ነበር እንዴ ፀጥ ያለ ሰው ዝር የማይልበት ቦታ የወሰደሽ?፣ ግንኮ መንበርከክ የነበረብሽ ልብሽ ታፈቅር ዘንድ አሳምሮ ለፈጠራት አላህ ነበር....

አንዳንድ እራስ ወዳድ ነብሲያና ሸይጧን ያለ ልጓም የሚጋልቧቸው ወንዶች በጦር ምላሳቸው በእህቶች ልብ ላይ መርዛቸውን ይረጩና ክልክሉን መንገድ ጥሰው ይሄዳሉ። ክብሯን ጥብቅነቷን ያበላሹና "የናቴ መቀነት አደናቀፈኝ" በሚል ተልካሻ ሰበብ ከሴቶች አጠገብ ይሰወራሉ፣ ባለ ተራዋን ማንቆለጳጰስ ይጀምራሉ፣ አበድኩልሽ ከነፍኩልሽ፣ እህል አልበላ፣ ውሃ አልጠጣ አለኝ፣ እያለ ሲፎትት ይውላል። እስኪ ሽማግሌ ላክ በይው!፣ ሀላል አርግልኝ በይው!፣ ዛዛታ አያስፈልግም!!።

ወንድነቱ ከተመቸሽ ለጌታው ያለው ቀረቤታ ከተስማማሽ መስራት ከቻለ፣ ህልምና አላማውን ከተረዳሽ፣ ሀያ አግባኝ በይው!፣ ግራ በገባው ምርጫሽ ግራ አታጋቢው ቆርቆሮና ብልጭልጭ ነገሮች ከውስጥሽ አስወግጂ በቃ "ምርጥዬ ነገር ሁኚ!"።

እርሱ ግን አስመሳይ ውሸታሙ ከሆነ እመኚኝ ልሞክርሽ ይልሻል፣ ሲያስቅ¡¡ አንቺ የላብራቶሪ አይጥ ነሽ እንዴ?! ከዚያም መቼስ ትዳር አይቀርምና እርሱ ለማግባት ሲፈልግ ግን ድንግል መሆን አለባት ይላል፣ ይገርማል፣ ይደንቃል፣ እርሱ ገጠርም ቢሆን ሂዶ ድንግል ፈልጎ አግኝቶ ሊያገባ ይችላል፣ ግንኮ ያስቃል¡¡፣ ከስንቷ ጋር ሲጨማለቅ ከርሞ ሳቅ ስላቅ፡፡

አንቺ ግን የባልሽን ሀቅ አሳልፈሽ ሰጠሽ ፀፀት!፣ ከንቱ እሪታ ብቻ፣ እሺ ጥብቅ አላህን የሚፈራ ሰው ቢፈልግሽ ምን ልትይ ነው?!። ለአወናባጁ ፊት አትስጪው! የሚፈልግሽ ከሆነ አንቺም ምርጫሽ ከሆነ ለምን በሀላል በኒካህ አትጣመሩም?! ለነገሩ አሁን ላይ ምን አለሽ ስንት አለሽም ሊልሽ ይችላል፡፡

እዚህ ጋር በቅርብ ቤተሰቧ ግራ እስኪጋባ የትዳር ጥያቄዎችን የምትመልስ እህትን ለምን? ስል ጠይቄያት የሰጠችኝ መልስ እጅግ አሳዛኝ ነው፡፡ "የኔ የምለው ሰው እራሴን አሳልፌ የሰጠሁት ሰው ካደኝ እና የቤተሰቤን አባል(የአክስቴን ልጅ) አገባ" አለችኝ፣ እናም በቤተሰብ የሚመጡ ጥያቄዎችን ለዛ ነው የማልቀበለው ያለችኝ አሳዝኖኛል፡፡

ስንት እህቶች በወንዶች ስል ምላስ ተታላቹህ ቢክራቹህን እንዳጣችሁ ቤቱ ይቁጠረው፣ ከዚህም አልፎ አንዳንድ በስነ ተዋልዶ ላይ የሚሰሩ ሆስፒታሎች ፅንስ ለማጨናገፍ ያለው ግፍያ በዛ ላይ እጅግ በጣም ትንንሽ ልጆች መሆናቸው እጅግ አደገኛ ሁኔታ ላይ መሆናችንን ያሳያል፡፡የቅርብ ጊዜ ጥናት የሚያሳየው ደሞ postpill የሚባል የፅንስ መከላከያ በፋርማሲዎች ተፈላጊነቱ ከፍተኛ እንደሆነና ለወደፊቱ ከባድ የወሊድ ችግር እንዳለው ተጠቁሟል፡፡
አንቺ ምርጧ ሴት! አንቺ ከዱኒያ የላቅሽ የተከበርሽ ደግ የሆንሽው እህቴ! ስለምን ትታለያለሽ?! እንሞካከር ካለሽ ዳግም ዐይኑን በማታይው ርቀት ራቂው!!።
[Copy ከኻሊድ ሙኒር ከተወሰነ ማስተካከያ ጋር]

#join ⤵️

@oneummha

Читать полностью…

One ummah

አቡ ቂላባህ አል በስሪይ ረሂመሁሏህ፡
"የቢድዓ ባለቤቶችን #አትቀማመጡ - እነርሱ #በገቡበት ነገር ውስጥ #ባትገቡ እንኳ #የምታውቁትን_ሀቅ_ያጠፉባችሗል "
📚 አል ኢባንቱል ኩብራ ሊብኒ በጧህ
@oneummha

Читать полностью…

One ummah

አንድ ቀን በዚህ መንገድ እንጎዛለን...መስጂደል አቅሶንም ከወራሪወች ነፆ አውጥተን ሶላት እንሰግድበታለን።
@oneummha

Читать полностью…

One ummah

👌👌🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
@oneummha

Читать полностью…

One ummah

☞የንጉሱ ፍላጎት ትዳር ያላቸው ወጣቶች እንዳይኖሩ ነበር ይህ ማለት ሴሰኛ ወጣቶች እንዲበዙ ነበር ያደረገው፣ ታዲያ ዛሬ የዚህ ቀን አላማ ሴሰኝነትን ወይስ ትዳርን ነው የሚያበዛው?? የቄሱን አላማ ወይስ የንጉሱን አላማ ነው እየተገበሩ ያሉት??
እነዚህ ጥያቄዎች የሚመለከቱት ቄሱን ለተከተሉ ክርስቲያኖች ነው። ምክንያቱም የዚህ በአል ጠንሳሾቹ ተግባሪዎቹና አንፀባራቂዎቹ ስለሆኑ የሚመለከተው እነርሱን ይሆናል።
ሙስሊም እህትና ወንድሞቼ ሰው የራሱ እምነትና ስርአት ካለው የሰው እምነትና ስርአትን መኮረጅ አይጠበቅበትም። ይህን ቀን የምናከብር ከሆነ
1ኛ, ቫለንታይን ማለት ሌላ ሳይሆን የሰው ስም ነው።ይህ ስም የአንድ ቄስ ስም ነው። በዚህ ሰው ስም የተሰየመና የሚተገበር ቀንን አስበለ መዋል ሌላን አማኝ መከተል ነው። ይህ ደግሞ ክልክል ነው። 2ኛ, የተከተልነው ሰው ሼኽ ሳይሆን ቄስ ነው።
3ኛ, ቀኑ የሚከበረው ሀራም ግንኙነት ውስጥ በመዘፈቅ ነው፣ ይህ ደግሞ ለዛሬም ይሁን ለነገ ህይወታችን አደጋ ይፈጥራል።
4ኛ, በቀኑ ውስጥ በአለባበሳችን (ቀይ ስለሆነ)፣ በግንኙነታችን (ሀራም ስለሆነ)፣ በኒያችን (ፍቅረኛ በኢስላም ስለሌለ)፣ በውሏችን (የምንውልባቸው ቦታዎች በሙሉ ሀራም ቦታ ስለሆኑ) አጠቃላይ ተግባሩ ሀራም የሆኑ ነገሮችን ያካተተ በመሆኑ ልንርቀው ይገባል።
5ኛ, አላህ በቁርዐን ውስጥ "የሸይጧንን መንገዶች አትከተሉ" ይለናል። ይህ ቀን ከሸይጧን መንገዶች ውስጥ አንዱ ነው። የዚህ ቀን መጨረሻው ዚና ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም።
6ኛ, ፍቅር ማለት የተከበረ የአላህ ስጦታ ነው፣ ይህን ስጦታ ማጣጣም ከፈለግን ከትዳር ውጭ የትም ቦታ አናገኘውም። ይህ ቀን የአንችን ክብር ለመውሰድ የሚደረግ ሽወዳ እንጅ እውነታ አይደለም።

ያፈቅሩናል ብለን በሀራም የተጠጋናቸው ሰዎች በሀላል አለመፈለጋቸው መገለጫው ይህ ቀን ነው። የሚወድሽ ያገባሻል፣ የምትወጂውን በሀላል እንጂ በሀራም አትፈልጊውም። የፈጠረሽና ያከበረሽን አላህ፣ የምድር ምትክ ያደረገህና ያላቀህን አላህን እወዳለሁ ካል እርሱ የማይወደው ቦታ አትገኝ!!!
||
2) ኢስላማዊ ብይን፦
================
ሙስሊሞች ከኢስላማዊ ባህልና በዓል ውጪ የሌሎችን ሊከተሉ አይገባም።
∞∞∞∞∞≈≈≈≈∞∞∞∞
አላሁ ሱብሃነሁ ወተዓላ ከከሃዲያን፣ የፈጣሪን ህልውና ከከዱት ጋር በባህላቸው፣ በበዓላቸውም ሆነ በእምነታቸው "ተሸቡህ" መመሳሰልን እርም አድርጎብናል። ይህንንም የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم
"من تشبه بقوم فهو منهم" رواه أبو داود وصححه الألباني.
"በኒያ ህዝቦች የተመሳሰለ ከነሱው ነው።" በማለት በነሱ መለያ መመሳሰል የነሱን መንገድ መከተልን እንደሚያሳይ በመግለፅ አውግዘዋል።
ስለሆነም ከሙስሊሙ ተለምዶ ውጪ በሆነ መልኩ የከሃዲያኑና የጣዖታውያኑ መሃይማን ማህበረሰብ የሚለዩበትን መገለጫቸው የሆነን ተለምዷዊ በዓላቸውን መጋራት የተከለከለ ነው። ነቢዩ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ ከመካ ወደ መዲና ተሰደው በሄዱበት ወቅት የመዲና ነዋሪዎች የሚያከብሯቸው ሁለት የተለያዩ የበዓል ቀናት ነበሯቸውና فَقَالَ : مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ؟ "እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድናቸው?" በማለት ጠየቋቸው
قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ.
"በጃሂሊያው ዘመን በነዚህ ቀናት [ተሰባስበን] የምንጫወትበት ቀን ነው።" በማለት መለሱላቸው። የአላህ መልእክተኛም صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ ( إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا : يَوْمَ الأَضْحَى ، وَيَوْمَ الْفِطْرِ )
صححه الألباني .
"አላህ ከነዚህ ቀናት በተሻሉ በአድሃ (በአረፋ) ቀንና በፊጥር (በረመዳን ፆም ፍቺ) ዕለታት በመቀየር ተክቶላችኋል።» በማለት የሙስሊሙ ማህበረሰብ በዓል ያልሆነውን ትተው በኢስላም የተደነገገውን ብቻ እንዲይዙ መክረዋል።
በዚህም መሰረት በየትኛውም የአለም ክፍል ያሉ ሙስሊሞች በተመሳሳይ ባህል የዒድ ቀን በማለት በማክበር ደስታቸውን ጌታቸውን በማመስገን፣ በመሰባሰብ፣ አንዱ አንዱን በመዘየር፣ በመገባበዝ፣ በመጫወት እና በመሳሰሉት የበዓል መገለጫዎች ዘና ብለው እንዲያሳልፉ አስገንዝበዋቸዋል።
ይህም ግልፅ በሆነ ቁርኣናዊና ሱንናዊ መረጃ የተገለፀ ነው። የዚህ ማህበረሰብ ሰለፎችም በዚሁ ላይ የጋራ አቋም እንደያዙ አስተላልፈውልናል። ስለሆነም ለሙስሊሙ ክብረ በዓል፣ ወይም የሚዘከር እለት፣ ወይም የሚታሰብ እለት ወይም የሚወደስና ቅዱስ እለት ተብሎ አመታዊ ስነስርኣት የሚፈፀምለት ቀን ቢኖር ዒድ አልፊጥር እና ዒድ አል አድሃ የተባሉት ሁለቱ የዒድ እለታት ብቻ ናቸው።
ከሁለቱ ዒዶቻችን ውጭ በዓላት የሚባሉ በሆነ ክስተት ወይም በሆነ ግለሰብ ሆነ ቡድን ወይም በሆነ ሀገር ታሪክ የተሳበቡ በዓላት ሁሉ አዳዲስ ፈጠራዎች ናቸውና የኛ አይደሉም።
ስለዚህም እነዚህ በዓላት አይመለከቱንምና ሙስሊሞች ሊሳተፉባቸውም፣ በይሁንታ ሊቀበሏቸውም ሆነ የደስታቸው ተካፋይ ሊሆኑላቸው እንዲሁም ስጦታ ሊሰጣጡባቸው፣ ከመገለጫዎቹ አንዱ በሆነው ሻማ እንደማብራት፣ ካርድ እንደመለዋወጥ፣ የጣፋጭም ሆነ የሌሎች ምግብና መጠጥ ዝግጅቶችን በመከወን ከነሱ መተባበር፣ እንኳን ደረሳችሁም ሆነ አደረሰን በማለት መልካም ምኞትን መግለፅ ሁሉ አይፈቀድላቸውም።
ምክንያቱም የኛ ባልሆኑ በዓላት ላይ ትብብር ማድረግ የአላህን ድንጋጌ በመዳፈር ነው የሚቆጠረው። የአላህን ድንበር ከመተላለፍ መጠንቀቅ አለብን ።
وَمَن يَتَعَدَّ حُدُودَ اللَّهِ فَقَدْ ظَلَمَ نَفْسَهُ ۚ
"የአላህን ድንበር (እሱ የደነገገውን) የጣሰ በእርግጥም ራሱን በደለ።" ብሏልና በዚህ ጥፋቱ ሰበብ ለሚደርስበት ቅጣት ማንንም መውቀስ አይችልምና።
በተጨማሪም ከሀዲያኑ በፈጠሩት በዓላት ላይ መሳተፍ ቀላል ጥፋት ሳይሆን ወንጀል ላይ ወንጀልን መደረብ ነው የሚሆነው። ምክንያቱም ከነሱ መመሳሰልና እነሱን መውደድን ያቅፋልና። ሁለቱም ባህሪ ደግሞ በሙስሊሙ ላይ እርም ተደርገዋል።
በዚህም መሰረት ለፍቅር የተሰኘው የ"ቫለንታይን ቀንስ" ምን ይሆን?
====∞∞∞===∞∞∞===
2.1) የሳዑዲ ዓረቢያ ቋሚ የፈታዋ ኮሚቴ ስለ ጉዳዩ ተጠይቆ የተናገረው፦
وسئلت الجنة الدائمة : يحتفل بعض الناس في اليوم الرابع عشر من شهر فبراير 14/2 من كل سنة ميلادية بيوم الحب فالنتين داي . day valentine . ويتهادون الورود الحمراء ويلبسون اللون الأحمر ويهنئون بعضهم وتقوم بعض محلات الحلويات بصنع حلويات باللون الأحمر ويرسم عليها قلوب وتعمل بعض المحلات إعلانات على بضائعها التي تخص هذا اليوم فما هو رأيكم :
أولاً : الاحتفال بهذا اليوم ؟
ثانياً : الشراء من المحلات في هذا اليوم ؟
ثالثاً : بيع أصحاب المحلات ( غير المحتفلة ) لمن يحتفل ببعض ما يهدى في هذا اليوم ؟
@oneummha

Читать полностью…

One ummah

ልትናገር ስትፈልግ ከመናገርህ በፊት ቆም ብለህ አስተውል (አገናዝብ)!!
,,,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,,,,
አንዳንድ ሰዎች ማገናዘብ የሚባል ነገር የተራቆተው የሆነን ንግግር በማህበራዊ ሚዲያም ሆነ በሌሎች አጋጣሚዎች ስለ ዲንም ሆነ ግለሰቦች ጉዳይ እንዳሻቸው ይናገራሉ፣ ምን ያህል አደጋው የከፋ መሆኑን ዘንግተውት ይሆን?!

ከአቢ ሁረይራ - ረዲየላሁ ዐንሁ - ተይዞ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:-
“አንድ ባሪያ አንዲትን ንግግር በውስጧ ምን እንዳለባት ሳያገናዝብ ይናገራል፣ በርሷ ምክንያትም በጀሀነም ከምስራቅና ምእራብ ርቀት በላይ ይወርዳል (ይወረወራል)።” ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

ታላቁ ዓሊም ኢማም ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁላህ) ይህን ሀዲስ ሲያብራሩ እንዲህ አሉ:-
“ይህ ሀዲስና ሌሎችም በዚህ ሀዲስ ትርጉም የመጡ ሀዲሶች ሁሉም የንግግርን አደገኝነት ያመላክታሉ። የሰው ልጅ በምላሱ ምክንያትም አደጋ ላይ ነው ያለው። በአንድ ሰው ላይ ግድ የሚሆነው ምላሱን ሊጠብቀው ሊታገለው ነው፣ በዚህም ከክፉ ነገር (ከሸር) ሰላም ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ምክንያቱም ምላስ እንቅስቃሴው በመልካም አለያም በሸር ነገር ላይ በጣም ፈጣን ነው። በመሆኑም ግዴታ የሚሆነው በነገሮች ላይ ማረጋገጥና መጠንቀቅ ነው። አንተ በዝምታ ላይ ከዘውተርክ ሰላም ላይ ነህ። ከተናገርክ ደግሞ ወይ ለአንተ ነው ወይም በአንተ ላይ ነው።” ከሪያዱ ሷሊሂን ተዕሊቅ ሀዲስ ቁ 477

ማንኛውም ሰው እያንዳንዱ የሚናገረው ቃል ክፉም ይሁን መልካም ተመዝግቦ ነገ አላህ ፊት ቀርቦ እንደሚጠየቅበት ፈፅሞ ሊዘነጋ አይገባውም!። አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-

مَّا يَلْفِظُ مِن قَوْلٍ إِلَّا لَدَيْهِ رَقِيبٌ عَتِيدٌ

«ከቃል ምንም አይናገርም በአጠገቡ ተጠባባቂና ዝግጁ የሆኑ (መላእክት) ያሉበት ቢሆን እንጅ፡፡» ቋፍ 18
✍🏻ኢብን ሽፋ: ጀማዱል ኡላ 25/1442 ዓ. ሂ

#Join ⤵️

@oneummha

Читать полностью…

One ummah

[አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው]

@oneummha

Читать полностью…

One ummah

‏ويبقى الله معك ‏حينَ لا يبقىَ أحد.💛🕊
አላህ ካንተ ጋር ይሆናል ማንም ካንተ ጋር ሳይሆን ሲቀር ‼️


@oneummha

Читать полностью…

One ummah

وكيف الحزن و الله راب
እንዴት አዝናለሁ ፈጣሪየ አላህ ሁኖ❤️
@oneummha

Читать полностью…

One ummah

በልብህ ውስጥ ያለውን ጭንቅ ለማስወገድ አንድ የቁርአን አንቀፅ በቂ ነው።

@oneummha

Читать полностью…

One ummah

💥💥 #ጁመዓ_ታላቅ_ቀን 💥💥
💥ከኩራት ራስህን አርቅ
💥ቁጣን ተጠንቀቅ
💥ከኔ በላይ አዋቂ የለም ብለህ አትንበጣረር ሸይጣን አያታልህ
💥ሰዎችን አሳንሰህ አትይ
💥ቀልብህን በገዛ እጅህ አታድርቃት
💥ሁሉን አውቃለው አትበል ትዋረዳለህ

💥 ለሰዎች ተናነስ
💥 ታጋሽና ሁሉን ቻይ ሁን
💥 ከአሊሞች ከታላላቅ የዕውቀት ባለቤቶች ተማር
💥 ለስላሳና ውብ ፈገግታን ተላበስ
💥 ዚክር አብዛ ቀልብን ታረጥባለችና
እማታቀውን ጠይቅ ተማር

@oneummha

Читать полностью…

One ummah

"ለራስህ ክብር ካለህ በእውቀት ተናገር"!
~
ሸይኽ ረቢዕ ሀፊዘሁሏህ እንዲህ ይላሉ;-
ራሱን የሚያከብርና ጥሪን(ዳዕዋን) የሚያከብር የሆነ ሰው በእውቀት ይናገር ።
እውቀት የሌለው ሰው ኢንተርኔትም ላይ ሆነ ሌላ ቦታ ለሰዎች ሊፅፍ አይገባም (አይፃፍ) ።
ምንጭ;-📚(الذريعة ج ٣ ص٢١٥)
@oneummha

Читать полностью…

One ummah

በአላህ ቤት ሁሉም የተረጋጋ ና ደስተኛ ነው።
@oneummha

Читать полностью…

One ummah

እህቴ_ሆይ!

አሏህ ይዘንልሽና እወቂ
ነብዩ ሙሐመድ ﷺ የሚከተሉትን ሴቶች መርገማቸውን ታውቂያለሽን❓

لعن رسول الله ﷺ الواصلة والمستوصلة
الواشمة والمستوشمة
النامصة والمتنمصة
ነብዩ ሙሐመድ ﷺ እነዚህ 6 ሰወችን እረግመዋል👇👇

①ቅንድብ አስቀንዳቢ
③አርቴፊሻል ፀጉር ቀጣይ
④አርቴፊሻል ፀጉር አስቀጣይ
⑤ንቅሳት ተነቃሽ
⑥ንቅሳት ነቃሽ

አህቴሆይ……!

አሏህ ሰውን በአማረ አፈጣጠር ነውና የፈጠረው አሏህ የሰጠሽን ፀጋ እረስተሽ እሱን ከመውንጀል ተጠንቀቂ።

@oneummha

Читать полностью…

One ummah

እቺናት ሂወት......
ቀጣይ ምንይሁን ???
አናውቅም የነገን መምረጥ አንችል??
ወይ ቀጣዩን???


ብቻ
ማለት ያለብን
(አልሀምዱሊላህ) እና አላህ የፃፈልንን መቀበል❤️
@oneummha

Читать полностью…

One ummah

😞😞😭😭😭😭😭😭😭
@oneummha

Читать полностью…

One ummah

"ኒካህ ሲታሰር መስፈርቶችን ማስቀመጥ "

ሴት ልጅ በምትዳር ግዜ የተለያዩ መስፈርቶችን ማስቀመጥ ትችላለች ከነዚህ መስፈርቶች መሀከል እንደምሳሌ
 ሌላ ሚስት እንዳያገባ መስፈርት ማድረግ ትችላለች።
 ከቤቷ ወይም ከሀገሯ እንዳያወጣትና እዛው በቤቷ ወይም በሀገሯ እንዲያኖራት መስፈርት ማድረግ ትችላለች
 መንገድ ይዟት እንዳይሄድም መስፈርት ማድረግ ትችላለች
እነዚህን የመሳሰሉ መስፈርቶችን ማስቀመጥ ትችላለች
 ባል ሲጋቡ የተስማሙባቸውን መስፈርቶች የሟሟላት ግዴታ አለበት።እነዚህን መስፈርቶች ካጓደለ (ካላሟላ)
ሚስት ትዳሩን የማፋረስ ስልጣን አላት።ከፈለገችም ደግሞ በዛው ልትቀጥልበት ትችላለች ኒካውን ለማፍረስ ዳኛ
ጋር መሄድም አይጠበቅባትም

(አሸርሁል ሙምቲእ (5/216)ዳር ኢብንል ጀውዚ

ወንድ ልጅም ቢሆን ኒካህ ሲያስር የተለያዩ መስፈርቶችን ማስቀመጥ ይችላል እንደ ምሳሌ
 በአዳር ከሌላኛዋ ሚስቱ ያነሰ ቀንን እንደሚሰጣት ከተስማሙ ይህን መስፈርት ማስቀመጥ ይችላል።ለምሳሌ
አንደኛዋ ሚስቴ ጋር ሁለት ቀን እያደርኩ አንቺ ጋር አንድ ቀን አድራለው በሚለው ከተስማሙ ይችላሉ።ልክ
ሰውዳ የሷን ቀን ለአኢሻ እንደሰጠችው
ቡኻሪ (2593)
 ወይም ልጃገረድ መሆኗን መስፈርት ካደረገ ይችላል።ሆና ካልተገኘች ማፋረስ ይችላል

" በሷ ላይ ሌላን እንዳያገባ መስፈርት ስለማድረግ "

ኒካህ በሚታሰር ግዜ ሚስት ባሏ ከሷ ውጪ ሌላ እንዳያገባ መስፈርትን ማስቀምጥ ትችላለች።ባል ፍቃደኛ ሆኖ
እስከገባበት ድረስ ይህንን ማክበር ይጠበቅበታል ካላከበረና ሌላ ሚስት ከደረበባት ለሚስት ኒካኋን የማፍርስ ስልጣን
አላት ሀቆቿንም አትከለከልም።
ኢብን ቁዳማ ሙግኒ ላይ እንደጠቀሰው ይህ አቋም ከኡመር፡ ከሰአድ ቢን አቢ ወቃስና አምር ቢን አስ ተወርቷል
ከፊል ኡለሞች ይህ አላህ የፈቀደለትን የባልን ሀቅ መከልከል ነው ብለው ስለዚህ አይቻልም ያሉ ቢሆንም ነገር ግን ይህ
ባል ራሱ ተስማምቶ ያወደቀዉ ሀቁ ስለሆን ሚከለክል ነገር አይኖረውም።
ኢማም ኢብን ቁዳማ (رحمه الله (እንዲህ ይላል
“ከቤቷ ወይም ከሀገሯ ላያወጣት ወይም መንገድ ይዟት ላይሔድ አልያ ደግሞ ሌላ ላያገባባት መስፈር ካደረገላይ
መስገርቱን መሙላት ይገባዋል።”
ሙግኒ 9/483

ሸይኽ ሳሊህል ፈውዛን (حفظه الله )እንዲህ ይላሉ
“ኒካህ ላይ ካሉ ትክክለኛ መስፈርቶች መሀከል ሌላ እንዳያገባ መስፈረት ካደረገችና ይህንን ካልፈጸመ ለሷ ኒካውን
ማፋረስ ትችላለች”
(ሙለኸሱል ፊቅህ 2/345)

አላመት ኢብን ባዝም ባሏ ሌላ እንዳያገባ መስፈርት ስለማድረግ ተጠይቀው
“ምንም ችግር የለውም......” ብለው መልሰዋል(ሙጁሙእ አል ፈታዋ ኢብኑ ባዝ)
@oneummha

Читать полностью…

One ummah

የአላህ መልዕክተኛﷺእንዲህ አሉ፡-

"ሰባቱን አጥፊዎች ተጠንቀቁ:- የአላህ መልዕክተኛ ሆይ እነሱ ምንድናቸው አሏቸው❓
🚫በአላህ ላይ ማጋራት፣

🚫ድግምት፣
🚫በአግባቡ እንጂ አላህ ክልክል ያደረጋትን ነፍስ ማጥፋት(መግደል)፣

🚫አራጣን/ወለድን መብላት፣
🚫የወላጅ አልባ የ(ቲምን)ህፃናትን ገንዘብ መብላት፣

🚫ከጠላት ጋር ትግል በሚደረግበት ግዜ ጀርባ ሰጥቶ መሸሽ፣

🚫ጥብቅና አማኝ ከዝሙት ዝንጉዎችን (ፍፁም የማያስቡትን ጨዋ ሴቶች)በዝሙት(በዚና) ማነወር፣ናቸው አሉ፡፡"

📚ቡኻሪ 2615 📚ሙስሊም 89 ሁለቱም ከአቢ ሁረይራ ዘግበውታል፡፡

@oneummha

Читать полностью…

One ummah

በሌላ በኩል ታላቁ ፈቂህ ሸይኽ ሙሀመድ ሷሊህ አልዑሰይሚን رحمه الله ይህንን የ"ፍቅር በዓል" የተሰኘውን የ"ቄስ ቫላንታይን" ወይም ፍቅር ሰጪ ብለው ተኩላዋን በሚያከብሩበት ቀን በተለይ ወጣቶች ቀያይ ልብሶችንና ጫማዎችን መልበሳቸውና ፅጌረዳ አበባ መሰጣጣታቸውን በተመለከተ የሸሪዐን ብይን ተጠይቀው ይህን በዓል ማክበር የማይፈቀድበትን የተለያዩ ምክንያቶች ሲገልፁ☞
«የ"ፍቅር በዓል" የሚባለውን ነገር አስቦ መዋል (ማክበር) በተለያዩ ገፅታዎች አይፈቀድም።
1ኛ: በሸሪዓችን መሰረት የሌለው ቢድዓዊ በዓል በመሆኑ
2ኛ: [ከትዳር ክልል ውጭ ለብልግና ወደሚዳርግ] አደገኛ ወደሆነ አጣብቂኝ ፍቅር የሚገፋፋ በመሆኑ
3ኛ: የደጋግ ቀደምቶቻችንን رضي الله عنهم የሀቅ ጎዳና ወደሚፃረር አስነዋሪ ህይወት እንዲገባ ልቦችን ወደሚያሸፍት ጉዳይ የሚስብ በመሆኑ ይህንን በዓል ማክበር የለበትም።
በመሰረቱ ሙስሊም የሆነ ሰው በዲኑ ሊኮራ እንጂ የእያንዳንዱን ጩኸት በመከተል የሚያስተጋባ ሊሆንም አይገባውም።» በማለት አስጠንቅቀዋል።
مجموع فتاوى ورسائل ابن عثيمين (16/199-200)
*
2.3) ሸይኽ ዐብደልሏህ አልጀብሪን ስለዚህ ጉዳይ ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ፦
وسئل الشيخ ابن جبرين حفظه الله :
" انتشر بين فتياننا وفتياتنا الاحتفال بما يسمى عيد الحب (يوم فالنتاين) وهو اسم قسيس يعظمه النصارى يحتفلون به كل عام في 14 فبراير، ويتبادلون فيه الهدايا والورود الحمراء ، ويرتدون الملابس الحمراء ، فما حكم الاحتفال به أو تبادل الهدايا في ذلك اليوم وإظهار ذلك العيد ؟
فأجاب :
أولاً : لا يجوز الاحتفال بمثل هذه الأعياد المبتدعة؛ لأنه بدعة محدثة لا أصل لها في الشرع فتدخل في حديث عائشة رضي الله عنها أن النبي صلى الله عليه وسلم قال: (من أحدث في أمرنا هذا ما ليس منه فهو رد) أي مردود على من أحدثه.
ثانياً : أن فيها مشابهة للكفار وتقليدًا لهم في تعظيم ما يعظمونه واحترام أعيادهم ومناسباتهم وتشبهًا بهم فيما هو من ديانتهم وفي الحديث : (من تشبه بقوم فهو منهم).
ثالثا : ما يترتب على ذلك من المفاسد والمحاذير كاللهو واللعب والغناء والزمر والأشر والبطر والسفور والتبرج واختلاط الرجال بالنساء أو بروز النساء أمام غير المحارم ونحو ذلك من المحرمات، أو ما هو وسيلة إلى الفواحش ومقدماتها، ولا يبرر ذلك ما يعلل به من التسلية والترفيه وما يزعمونه من التحفظ فإن ذلك غير صحيح، فعلى من نصح نفسه أن يبتعد عن الآثام ووسائلها.
وقال حفظه الله :
وعلى هذا لا يجوز بيع هذه الهدايا والورود إذا عرف أن المشتري يحتفل بتلك الأعياد أو يهديها أو يعظم بها تلك الأيام حتى لا يكون البائع مشاركًا لمن يعمل بهذه البدعة والله أعلم "
----------------
በመጨረሻም ባሳለፍነው መልእክት መሰረት ለእምነታችን ቦታ ልንሰጥና ክብራችንንም ልንጠብቅ ይገባናል። እኛ ለስሜታችን የምንገዛ የልቅ ፍቅር ባሮች ሳንሆን የአላህ አዝዘ ወጀልለ ባሮችና በመመርያው ስር የምንኖር፣ የምንደሰት፣ የምንረካ፣ የምንዋደድ፣ የምንተዛዘንና አብረን የምንጓዝ ህዝቦች ነን።በትዳር ህይወት ውስጥ ቅመም የሆነውን መተዛዘንና መፈቃቀርን ያደረገልን ፈጣሪያችን
وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً ۚ
"በመካከላችሁ ፍቅርንና እዝነትን አደረገላችሁ" በማለት ትክክለኛውን የፍቅር ቦታና መግለጪያ በመጠቆም የጋብቻን ፀጋ ስላበሰረንም ምስጋና ይገባዋል። አልሀምዱ ሊላህ።
በእስልምና የፍቅር ቀን ከአመት አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን መላውን አመቱን ሙሉ ነው።
የፍቅር ጊዜም ከኒካሕ በፊት ሳይሆን ከትክክለኛ ኒካሕ በኋላ ነው።
ከኒካሕ በፊት ሴት የወንድ ጓደኛ መያዟና ወንድም የሴት ጓደኛ መያዙ ዝሙት እንጅ ፍቅር አይደለም።


የAbufewzan Ahmedን ጽሑፍና ሌሎች ጥንቅሮችንም ወስጃለሁ።
||
ጥንቅር፦ ወንድማችሁ ሙራድ ታደሰ
======
የካቲት 04, 2012 E.C
February 14, 2020 G.C
||
@oneummha

Читать полностью…

One ummah

Valentine's Day (የፍቅረኞች ቀን) በኢስላም‼️
===================================
«ጽሑፉን ለሌሎችም በማሰራጨት፤ ስለ ጉዳዩ በቂ ግንዛቤ የሌላቸውን ሙስሊሞች በማንቃት ከወንጀል እንታደግ‼️»
||
✍️ በእንግሊዝኛ ቋንቋ «Valentine's Day» የተሰኘውን ቀን በእኛ አማርኛ ስንመልሰው «የፍቅረኞች ቀን» የሚለው ገለፃ ይተካዋል።
በዐረብኛ ቋንቋ «عيد الحب» ይሰኛል።
ይህ ቀን በምዕራባዊቷ ቤተ ክርስቲያን በየ አመቱ ሐምሌ (አንዳንድ ሃገሮች ውስጥ July 6 እና ሌሎች ዘንድ ደግሞ July 30) ላይ ይከበራል።
የምሥራቃዊቷ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን (Eastern Orthodox Church) ግን ይህን ቀን የምታከብረው በየ አመቱ አሁን ባለንበት የየካቲት ወር (February 14) ላይ ነው።
ታዲያ ይህን ቀን አስመልክቶ ታሪካዊ አመጣጡንና ኢስላማዊ ብይኑን በተመለከተ የሚከተለውን ለማለት ወደድን።
||
1) ታሪክ፦
========
በቅድሚያ ይህ የ"ፍቅር በዓል" ወይም "የቫለንታይን ቀን" በመባል በክርስቲያኑ ማህበረሰብ በሰፊው የሚዘከረው አመታዊ ባህል መነሻው ባጭሩ ምንድነው?
ለሙስሊሙ ማህበረሰብ እውነታን በማሳወቅ ከተለያዩ ፀረ ኢስላም ተለምዶዎች እንዲጠነቀቅ ከፍተኛ ተጋድሎ ከሚያደርጉት የዳዕዋና የትምህርት ማእከላት አንዱ የሆነው በሳዑዲ ዓረቢያ ቅድስቲቷ ከተማ የሚገኘው ኡመልቁራ ዩኒቨርሲቲ "ኩሊየቱ-ዳዕዋ ወኡሱሉዲን" የጥናትና ምርምር ማዕከል ስለዚህ ጉዳይ ከምንጩ ለማወቅ ባደረገው ጥናት "ባርት" የሚባል የምዕራቡ አለም ደራሲ ስለ የዓለም በዓላት ሲዘረዝር ስለ "ቫለንታይን" የፃፈውን ወደ አረብኛ ከመለሱት እንደምንረዳው የ "ዒዱል ሁብ" ማለትም "የፍቅር በዓል" ስለሚባለው ባህል ትክክለኛ ምንነት በአራት ዋና ዋና ምክንያቶች ላይ በማንጠልጠል አብራርቷልና እንደሚከተለው ያንብቡት።☞
የ"ቫላንታይን ዴይ" መነሻ መላምት
∞∞∞∞∞=======∞∞∞∞∞
ደራሲው በሚለው መላምት
1ኛ/ ከ1700 አመታት በፊት በሮማ ላይ ጣዖታውያኑ የበላይ በነበሩበት ዘመን "ቫለንታይን" የተባለ ግለሰብ ከጣዖት አምላኪነት ወደ ክርስትና ተቀየረ። ሆኖም ሮማውያኑ ወዲያው ገደሉት። ከግዜ በኋላ ግን አብዛኞቹ ሮማውያን ወደ ክርስትና ሲቀየሩ "በቫለንታይን" ላይ በፈፀሙት ግድያ ተፀፀቱ። ስለዚህም የሞተበትን እለት ለሱ ማስታወሻ በሚል የበዓል ቀን አደረጉት። ይላል።
2ኛ/ ጥንታውያን ሮማውያኑ አንዲት "ዮኖ YoNo" የምትባል አማልክትን ያመልኳት ነበረ። እሷም የአማልክቶቻቸው ሁሉ ንግስት ናት በሚል ፌብሩዋሪ 14ን የሷ መዘከሪያ አደረጉት። እሷንም የሴቶችና የጋብቻ ተምሳሌት ናት በሚል እለቱን የ"ፍቅር ቀን" ኣሉት። ይላል።
3ኛ/ በሮማውያኑ ዘንድ አንዲት ቅድስት ናት በሚል የሚያመልኳት አማልክት ነበረች። ስሟንም "ሊሲየስ Licious" ይሏታል። የሚገርመው ነገር ይህች አማልክት ተኩላ የምትባል እንሰሳ ናት። ተኩላዋን የሚያመልኳት ለምንድነው ከተባለ ጉዳዩ እንዲህ ነው። ይህች "ሊሲየስ" የሮማ ከተማ መስራች የነበሩን ሁለቱን ሰዎች በህፃንነታቸው አጥብታቸው ነበር በሚል አመታዊ ቀንና ቦታ ወስነው የአምልኮ ቦታውንም "ፍቅር" ኣሉት። ይህም ያቺ "ሊሲየስ" የተባለቿ ተኩላ ለእነዚያ ህፃናት ታዝን ነበርና ፍቅር ሰጥታቸዋለች በሚል ይቀድሷታል።
4ኛ/ ከዘመናት በፊት በነበረው የሀገሪቱ መሪ ወንዶችን ለጦርነት ለማሰማራት ማሰባሰብና ማዘጋጀት ሲሳነው ምክንያቱን ሲያጠና ወንዶቹ ከሚስቶቻቸውና ከቤተሰቦቻቸው ላለመለየት ሲሉ ጥሪውን እንዳልተቀበሉና ከሱ ጋር መዝመትን የጠሉ መሆኑን ደረስኩበት ኣለና ለዚህ ጉዳይ መፍትሄ ይሆነው ዘንድ መንግስቱ ከዚህ በኋላ ማንም እንዳይጋባ በማለት አወጀ። በወቅቱ ሰዎች የሚጋቡትም በካቶሊካውያኑ ስርዓት በቀሳውስቱ እጅ በቤተክርስቲያናቱ ነበርና ለቀሳውስቱም ከማጋባት እንዲታቀቡ ትእዛዝ ተላለፈላቸው። ይሁንና "ቄስ ቫለንታይን" የተባለ ሰው ትእዛዙን ባለማክበር ለጋብቻ ወደ ቤተክህነቱ የመጡትን በድብቅ ያጋባ ነበርና ይህንን መንግስቱ ሲደርስበት ያንን ቄስ በፌብሪዋሪ 14/ 269ዓል ገደለው ኣሉ። ስለዚህም ከዚህ ክስተት በኋላ ይህ ቄስ ቫለንታይን ለኛ ፍቅር ሲል ሞተ በሚል ክብር ይገባዋልና አመታዊ መዘከሪያ እናብጅለት ብለው የ"ፍቅር በዓል" ፈጠሩ የሚል ነው።
==∞===∞==
ይህ እንግዲህ ስለ በዓሉ ራሳቸው ፅፈው ያስነበቡት ኣፈታሪካቸው ነው። ይሁንና ከረዥም አመታት በኋላ ቤተክርስቲያኗ የ"ፍቅር ቀን" የሚባለውን በዓሏን "ሊሲየስ" ከምትባለዋ ተኩላ ጋር የሚያያዘውን ታሪክ ትቻለሁ ኣለችና "ቅዱስ" በሚሉት "ቫለንታይን" ላይ ብቻ በማንጠልጠል የ"ቫለንታይንን" ምስሎችና ቅርፃ ቅርፆች በመላው አውሮጳ እና አሜሪካ ከማሰራጨት ጋር በዓሉን አስፋፋች። ሆኖም ለሁለተኛ ግዜ በቅርቡ በእኤአ 1969 የ"ቫለንታይን ቀን" ብላ ታከብር የነበረውንም ትቻለሁ ኣለችና በቤተክርስቲያን ደረጃ ገሸሽ አደረገችው።
በዚህም መሰረት ይህ የ"ቫለንታይን" ቀን የሚባለው በዓል መነሻው ጣሊያን ሮማ ሲሆን ባለታሪኮቹም የሀገሪቱ ቀደምት ነዋሪ የሆኑት ጣዖታውያኑና ሃይማኖት ኣለን የሚሉት ካቶሊካውያን ክርስቲያኖች መሆናቸው ግልፅ ይሆንልናል።
እንደሚታወቀው ሙስሊም ያልሆኑ ህዝቦች ባእድ አምልኮ ላይ የተመሰረቱ በርካታ በአላትን በአመት ውስጥ ያከብራሉ። ከፊሉ በቅዱሳን ስም ሲሆን ከፊሉ ደግሞ ተራ በሆኑ ሰዎች ወይም እንስሳትና ግዑዛን ጭምር ነው። ለዚህማ ማሳያ ይህን የ"ቫለንታይን ቀን" የሚባል በዓል ከተኩላ አምልኮት ጋር ሁሉ የተያያዘ መሆኑን ሙስሊሞቹ ልብ ሊሉት ይገባል። እርግጥ እያመለኩ ያሉት ቅዱስ ሚካኢል ወይም ቅዱስ ጅብሪል ወይም ነቢይን ወይም ሌላ ደጋግ ፍጡራንንም ቢሆን ለአላህ ብቻ የሚገባን አምልኮ ለፍጡር ማዋል በመሆኑ ሁሉም ባእድ አምልኮ ነውና ተቀባይነት የለውም።
እንደሚታወቀው ሮማውያኑ ጣዖታውያን ለፍቅርም፣ ለዝናብም፣ ለአዝርዕትም አምላክ፣ ለብርሃንም፣ ለጭለማም አምላክ፣ ለባህርም፣ ለወንዙም አምላክ እያሉ ለሁሉም ነገር የተለያየ አምላክ እንዳለው አድርገው አማልክትን ያምኑም ያመልኩም ነበረ። ይህንንም ባህላቸውን ወደ ክርስትናው ሲገቡ ክርስቲያናዊ ቃና አላብሰው አስፋፍተውታል።
*
በሶስተኛው ክፈለዘመን በ ሮም ውስጥ በ ከላውዲዎስ ሁለተኛ የንግስና ዘመን የኖረ ቅዱስ ቫለንታይንስ በመባል የሚታወቅ ታዋቂ ቄስ አገልጋይ ነበር። በዚያን ዘመን የነበረው ንጉስ ገላውዲዎስ ሁለተኛ ውሳኔ አስተላለፈ። ውሳኔውም ምን ነበር፤ ያላገቡ ወጣት ወንዶች ሚስት እና ቤተሰብ ካላቸው ወንዶች ይልቅ ጥሩ ወታደሮች መሆን ስለሚችሉ በ እነሱ ላይ ጋብቻን እንዳይፈፅሙ ውሳኔን አስተላለፈ። ይህ የንጉሱ ፍትሃዊ ያልሆነ ውሳኔ ያልተዋጠለት ቄስ ቫለንታይንስ ፍትሃዊ አይደለም ብሎ ያሰበውን የንጉሱን ውሳኔ ባለመቀበል በድብቅ ወጣት ፍቅረኞችን ማጋባቱን ተያያዘው። ነገር ግን ይህ ድርጊቱ በንጉስ ከላውድዎስ ሲደረስበት ንጉሱም ከላውዲዎስ እንዲገደል ትዛዝ አስተላለፈ፡፡ ተገደለ።

☞ጥያቄ አለኝ ቀኑ የሚከበረው ቄስ ቫለንታይን የሰሩትን መልካም ስራ ለማሰብ ከሆነ ታዲያ ለምን በቀኑ ሰዎች ትዳር አይመሰርቱም?? ምክንያቱም የቄሱ ስራ ማጋባት ነበር።
☞ቄሱ ፍቅረኛነትን አልነበረም የደገፉት የዘመናችን ሰዎች ግን ከትዳር ውጪ ያለን ጋጠወጥነት ደግፈው ቀኑን በአለም ደረጃ በሴሰኝነት ያከብራሉ።
@oneummha

Читать полностью…

One ummah

: بسم الله الرحمن الرحيم
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
↪🍃በቁርዐን የተ ገለፁትን 25 ነብያቶች ያዉቃሉ?

1፨ አደም (አለይሂ.ሰላም)
2፨ ኢድሪስ (አለይሂሰሰላም)
3፨ ኑህ (አለይሂሰላም)
4፨ ሁድ (አለይሂሰላም)
5፨ ሷሊህ (አለይሂሰላም)
6፨ ኢብራሒም (አለይሂ ምሰላም )
7፨ ሉጥ (አለይሂሰላም)
8፨ እስማኤል (አለይሂሰላም)
9፨ ኢስሃቅ (አለይሂሰላም)
10፨ ያዕቆብ (አለይሂሰላም)
11፨ ዩሱፍ (አለይሂሰላም)
12፨ አዩብ (አለይሂ.ሰላም)
13፨ ሹዐይብ (አለይሂሰላም)
14፨ ሃሩን (አለይሂሰላም)
15፨ ሙሣ (አለይሂሰላም)
16፨ ኢልያሥ (አለይሂሰላም)
17፨ ዙልኪፍል (አለይሂሰላም)
18፨ ዳዉድ (አለይሂሰላም)
19፨ ሡለይማን (አለይሂሰላም)
20፨ አልየሠዕ (አለይሂሰላም)
21፨ ዩኑስ (አለይሂሰላም)
22፨ ዘከሪያ (አለይሂ ሰላም )
23፨ የህያ (አለይሂሰላም)
24፨ ኢሳ (አለይሂ ሰላም) እና
25፨ ሙሐመድ {{ሶለሏሁ አለይሂ ወሠለም}} ናቸዉ::

↪🍃፨ ከነዚህ ከላይ ከተጠቀሱት 25
ትታላላቅ ነብያቶች መካከል ደግሞ 5tu (አምሥቱ) ዑሉል-
ዐዝም {መከራና ስቃይ ታጋሽ} በመባል ይታወቃሉ::

↪🍃፨እነሱM:-
👉1፨ ኑህ(አ.ሰ)
👉2፨ ኢብራሂም(አ.ሰ)
👉3፨ ኢሳ(አ.ሰ)
👉4፨ ሙሣ እና(አ.ሰ)
👉5፨ ነብዩ ሙሐመድ {ሰዐወ} ናቸዉ!!!

↪🍃፨በተጨማሪም:- በቁርዐን ዉስጥ የተጠቀሱትን አሥሩን
መላዕክቶችን, አንዲሁም የሥራ ድርሻቸዉንስ ምን ያህሎቻችን
ለማወቅ ጥረት አድርገናል???

↪🍃ዝርዝራቸዉን እነሆ! :-->.

👉1፨ጂብሪል => መልዕክትን ማድረስ
👉2፨ሚካኤል => የዝናብ ተወካይ
👉3፨አስራፊል=> የትንሳኤ ቀን ነፊ (ጥሪንባዉን)...
👉4፨መለከል-መዉት=> ነፍስ አዉጭ
👉፨5ረቂብ ና አቲድ =>
ጥሩ ና መጥፎ ስራችንን የሚመዘግቡ
6፨ ነኪር ና ሙንከር => ቀብር ዉሥጥ ጥያቄ የሚጠይቁ
👉7፨ ማሊክ => የጀሀነም በር ዘበኛ
👉8ሪድዋን => የጀነት በር ዘበኛ።

____"===______🌹"ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ምንም አይነት
የሚያስከፋና አሳዛኝ ዜና ሲሰሙ፦🌸 "አልሃምዱ ሊላህ አላ ኩሊ ሃሊን"
በሁሉም ነገር (ጥሩም ሆነ መጥፎ) ለአላህ ምስጋና ይገባው ይሉ ነበር : አይ የሰው ልጅ

ገና እንደተረገዘ በእናቱ ሆድ
ጉብ ብሎ ይታያል
ሙቶ ከተቀበረ በሗላ ቀብሩም
ጉብ ብሎ ይታያል

ሲወለድ እናቱ በምጥ ትሰቃያለች
ሲሞት ደግሞ እራሱ
በጣረ ሞት ይሰቃያል

ሲወለድ ጭንቅላቱ
ቀድሞ ወደ ምድር ይወጣል
ሲሞትም ጭንቅላቱ ቀድሞ
ወደ ቀብር ይገባል

ሲወለድ እራሱ ያለቅሳል
ሲሞት ደግሞ ይለቀስለታል

ሲወለድ በአንሶላ ይጠቀለላል
ሲሞትም በአንሶላ ይከፈናል

ሕፃን እያለ ያገንኘውን ነገር
ወደ አፉ ይልካል ሲሞቶ
ደግሞ አፉ በጥጥ ይወተፉል

ሲወለድ ባዶ እጁን ይወለዳል
ሲሞትም ባዶ እጁን ይቀበራል

ሲወለድ ማን እንዳዋለደው
ማን እንዳጠበው አያውቅም
ሲሞትም ጀናዛውን ማን
እንዳጠበው ማን ለህድ
እንዳስገባው አያውቅም

ሲወለድ ወንድ ከሆነ
አዛን ይባልበታል
ሴት ከሖነች ኢቃም ይባልባታል
ሲሞቱ ደግሞ ይሰግድባቸዋል

አጃኢብ
አጃኢብ
አጃኢብ

ከ አዛን እስከ ኢቃም ላለች
ጊዜ ነው ???
እንደዚህ የምንባዝነው?

አላህ ይዘንልን
አላህ ይዘንልን
አላህ ይዘንልን

ሼር በማድረግ ወንድም
እህቶችን ለተፈኩር ጋብዙ

የአላህ መልእክተንኛ
ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም
እንዲህ ብለዋል
ቲኒሽ ደቂቃ ስለ አኼራ መፈከር ወይም ማስተንተን ከ አንድ አመት ዒባዳ ይበልጣል ብለዋል: ምርጥ ምክሮች

⚀, ምርጥ ነገር ልምከርህ:
➢የትም ብትሆን አላህን ፍራ!
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀
⚁, ወደ ስኬት የሚያደርሱ ጎዳናዎችን ላመላክትህ:
➢ቁርዓን እና
➢ሐዲስን አጥብቀህ ያዝ!
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀
⚂, ምርጥ ነገሮች ይኑሩህ:
➢ዲን,
➢መልካም ስነ-ምግባር,
➢ከሰዎች የሚያብቃቃህ ገንዘብ
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀
⚃, 4 ነገሮች ካሉህ ብዙ ነገር አለህ:
➢ኢማን,
➢የሰው ፍቅር,
➢እናት ሃገር,
➢መልካም የትዳር ጏደኛ
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀
⚄, 5 ነገሮች ከእጅህ ሳይወጡ ተጠቀምባቸው:
➢ወጣትነት,
➢ጤና,
➢ትርፍ ጊዜ,
➢ገንዘብ,
➢ህይወትህ
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀
⚅, ሀቆች እንዳሉብህ አትዘንጋ:
➢የአላህ(ሱ.ወ),
➢የረሱል(ሰ.ዐ.ወ)
➢የራስህ,
➢የወላጅህ,
➢የሙስሊም ወንድምህ,
➢የሌሎች ፍጥረታት..."

👉እነዚህን ምርጥ ምክሮች ለወዳጅ ዘመድዎ በስጦታ መልክ ያበርክቱ!!!
➖〰➖〰➖〰➖~ይህን ያውቁ ኖሯል?~~~

ሶስቱ እጅግ በጣም አስፈሪ የጀሃነም ሸለቆዎች

1 وادي الغَّي......አል ገይ ሸለቆ
2 وادي الوَّيل......አል ዋይል ሸለቆ
3 وادي سقر......አል ሰቀር ሸለቆ!

ዝርዝሩን እነሆ ፦
1ኛ وادي الغَّي......አል ገይ ሸለቆ
............................................

[ فخلفهم من بعدهم خلف اضاعوا الصلوات واتبعوا الشهوات فسوف يلقون غياً ]

ከነሱም ቦሃላ ሶላተን ያጓደሉ ፥ (የተዉ)፥ ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች (ትውለዶች) ተተኩ ! (وادي الغَّي......አል ገይ ሸለቆ ) የገሃነም ሸለቆ በርግጥ ያገኛሉ ። {መርየም ፡59} ይህቺ የጀሃነም ሸለቆ (የተለያዩ ሰላቶችን አንድ ላይ ሰብስበው ለሚሰግዱ) እጅግ በጣም ምታቃጠል ከመሆኗ የተነሳ ጀሃነም እራሷ የአሏህን እርዳታ ትጠይቃለች ! የሰው ልጆች ይቋቋሙታልን ?

2ኛ وادي الوَّيل......አል ዋይል ሸለቆ
............................................

[ ويل للمصلين الذين هم عن صلاتهم ساهون ].

ወዮላቸው ፥ ለሰጋጆች ፣ ለነዝያ እነሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለኾኑት (ሰጋጆች ) ። {አል-ማኡን ፡ 4-5} ይህቺ የጀሃነም ሸለቆ (ሶላትን ያለ አግባብ ለሚያዘገዩ ) የተዘጋጀች ስትሆን እጅግ በጣም ከሚያስፈሩ የጊንጥ እና የ እባብ አይነቶች የተሞላችዋ የጀሃነም ሸለቆ ነች ። አሏህ እራሱ ይጠብቀን !

3ኛ وادي سقر......አል ሰቀር ሸለቆ
..........................................

[ماسلككم في سقر ، قالوا لم نكن من المصلين ] و قال [وماأدراك ماسقر ، لاتبقي ولا تذر ]

(ይሏቸዋልም)፦ በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ" ? (እነርሱም) ይላሉ ፦ ከሰጋጆች አልነበርንም ።
ሰቀር ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ ? (ያገየችውን ሁሉ) አታስቀርም ፣ አትተውምም።
{ አል-ሙደሲር ፡27-28/42፡43} ይህቺ የጀሃነም ሸለቆ የተዘጋጀችው (ሶላትን ለማይሰግዱት) ሲሆን ሰላትማይደግዱት ገና ሲገቡባት (ከሙቀቷ የተነሳ) አጥንታቸውን ምታቀልጥ የሆነች ነች። ሶላት የማይሰግዱ ሰዎች የሚቀሰቀሱት (ለፍርድ ሚቀርቡት ) ከነ ፊርኦን ከነ ሃማን ጋር ሲሆን!የነብያችንን ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሸፋእ እንዳያገኙ አሏህ (ሱ.ወ.) ያደርጋቸዋል ። አሏህ ይጠብቀን !!
እባክህን !!
በተቻለህ አቅም ይህቺን ለምታቀውም ላማታቀውም share አድርግ ምን ታውቃለህ በዚህ ምክንያት ከጀሃነምና ከሸለቆዎቿ ትጠብቃቸውና ሰላታቸውን ወቅቱን ጠብቀው በጀማዓ መስጂድ ሄደው እንዲሰግዱና ሰላታቸውም ላይ ጠንካራ እንዲሆኑ ሰበብ ትሆን ይሆናል !!ያአሏህ ያ አርሃም አልራሂሚን ከጀሃነም እና ከሸለቆዎችዋ አንተ ጠብቀን ፡፡

@oneummha

Читать полностью…

One ummah

👇👇👇👇👇👇👇👇👇

አንብበው ለሌሎችም ማካፈል አይዘንጉ!!
ረሱል ሰ.ዐ.ወ ከሶሃቦቻቸው ጋር ቁጭ ብለው በዱኒያ ላይ በጣም ስለሚዎዷቸው ነገሮች
አየተጨዋወቱ እያሉ ነብዩ አቡበክርን "ያ አባ በከር አንተ በዱኒያ ላይ በጣም የምትወደው
ነገር ምንድነው?" ብለው ጠየቁት።
አቡበክርም "3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.ከአንተ ጋር መቀመጥ፣
2.አንተን ማየት፣
3.አንተ ባዘዝካቸው ነገሮች ላይ በሙሉ ገንዘቤን መለገስ" ብሎ መለሰ።
°
ዑመርን በተራው ጠየቁት "አንተስ ያዑመር ?"
"በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ
1.በድብቅ እንኳን ቢሆን በመልካም ነገር ማዘዝ፣
2.በግልጽ እንኳን ቢሆን ከመጥፎ ነገር መከልከል፣
3 መራራ እንኳን ቢሆን እውነትን መናገር።" ብሎ መለሰ።
°
ዑስማንን ጠየቁት "አንተስ ያዑስማን?
በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.ሰዎችን ማብላት፣
2.ሰላምታን ማብዛት፣
3.ሰዎች በተኙ ጊዜ ሶላትን ማብዛት፣
°
አልይን በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአልይ ?"
"በዱኒያ ላይ 3ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.እንግዳን ማክበር፣
2.በሙቀት ወቅት ፆምን መፆም፣
3.ጠላቴን በሰይፍ መቅላት፣
°
አባ ዘርን በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአባ ዘር?"
"በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ :-
1.እርሃብን እወዳለሁ፣
2.በሽታን እወዳለሁ፣
3.ሞትን እወዳለሁ፣
ነብዩም "ያ አባ ዘር ለምን እነዚህን ወደድክ?"
አቡዘር መለሰ "ረሃብን ወደድኩት ቀልቤን ፈሪ ሊያደርግልኝ ዘንድ፣
በሽታን ወደድኩት ወንጀሌን ሊያቀልልኝ ዘንድ፣
ሞትን ወደድኩት ከጌታየ ጋር ሊያገናኜኝ ዘንድ።" ብሎ መለሰ።
°
ነብዩ ሰለላሁ አለየሂ ወሰለም " እኔም በዱኒያ ላይ
3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.ሽቶን እወዳለሁ፣
2.ሚስቶቼን እወዳለሁ፣
3.የአይኔ ማረፊያ ሶላቴን እወዳለሁ፣
በዚህ መካከል ድንገት ጅብሪል ዱብ አለ ሰላምታ ካወረደ በኋላ እንዲህ አለ
"አንቱ የአላህ መልዕክተኛ በዱኒያ ላይ እኔም 3 ነገሮችን እወዳለሁ
ነብዩም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም "ምንድናቸው ያ ጀብሪል?" ብለው ጠየቁት።
1.መልዕክትን ማድረስ፣
2. አማናን አደራን መጠበቅ፣
3.ሚስኪኖችን መውደድ፣
ጅብሪል ተመልሶ ወደ ሰማይ ከወጣ በኋላ ረሱልና ሱሃቦቻቸው ከመቀመጫቸው ሳይነሱ
ተመልሶ ወደ መሬት ዱብ አለ አሁንም ሰላምታውን አቅርቦ:-
"አላህም ሰላም ብሏችኋል ካለ በኋላ አላህም እንዲህ ብሏል:-
በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.አላህን አውሺ የሆነችን ምላስ፣
2.አላህን ፈሪ የሆነችን ቀልብ፣
3.መከራ የበዛበት ታጋሽ የሆነችን ጀሰድ።
አላህ ታጋሾች አድርጎ ነብዩና ሱሃቦች የወደዱትን ያስወድደን!
°
ይህን ጣፋጭ ሐዲስ በማንበባችሁ ከፍ ያለ አጅር ታገኛላችሁ -ኢንሻ አሏህ።
ሼር በማድረግ ለሌሎች ብታካፍሉ ግን እነሱ ባነበቡት ልክ ለናንተም ሀሰናት ይፃፍላችኋል!
ኢንሻ አሏህ!!
አላህ አንብበው ከመጠቀሙት ያድርገን!!!
@oneummha

Читать полностью…

One ummah

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#አስተማሪ_ቂሷ

አንድ ትንሽዬ ልጅ ለወላጆቹ፦"3 ጥያቄዎቼን የሚመልስልኝ ጠንካራ ዑለማ አምጡልኝ" አላቸው።

ወላጆቹም በአከባቢያቸው ያለ አንድ ኡስታዝ አመጡለትና አገናኙት።

ልጁ፦"ማን ነህ አንተ? እኔ ስለምጠይቀውስ ጥያቄ መልስ እንዳለህ ምን ያህል እርግጠኛ ነህ?"

ኡስታዙ፦"ስሜ ዐብዱላህ ይባላል ከአላህ ባሪያዎችም አንዱ ነኝ።ለምትጠይቀኝ ጥያቄዎችም በአላህ ፍቃድ መልስ እሰጥሀለሁ።"

ልጁ፦"አንተ ግን ብዙ ዑለማኦች ሊያብራሩልኝ ያልቻሉትን ጥያቄዬን እንደምትመልስልኝ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ነህ?

ኡስታዙ፦"ልመልስልህ እሞክራለሁ በአላህ እገዛ።"

ልጁ፦" 3 ጥያቄዎች አሉኝ።

1=>እውነት ፈጣሪ አለ? አዎ አለ የምትል ከሆነ አሳየኝ የት ነው ያለው?
2 => ቀዷ እና ቀደር ምንድነው?
3 =>እውነት ሸይጣን ከእሳት የተፈጠረ ከሆነ እንዴት በእሳት ይቀጣል? ከእሳት ተፈጥሮ እሳት አያቃጥለውም።

"ይሄን ግዜ ኡስታዙ እሳት በሆነች ጥፊ ልጁን አጮለው።

ልጁ፦"እንዴ!!! ለምን ትመታኛለህ? ምን ሚያስመታ ነገር ተናገርኩ?

ኡስታዙ፦"አረ!!! እኔ አልተቆጣሁም ግን ያሁኗ ጥፊ ለሶስቱም ጥያቄዎችህ መልስ ናት።

ልጁ፦"እንዴት? አልገባኝም...
ኡስታዙ፦"በጥፊ ስመታህ ምን ተሰማህ?

ልጁ፦"በጣም ህመም ተሰማኝ።
ኡስታዙ፦"ህመም እንዳለ ታምናለህ?"

ልጁ፦"አዎ አምናለሁ።"
ኡስታዙ፦"አሳየኝ የት ነው ያለው?"

ልጁ፦"አይ አለ ግን ማየት እንኳን አይቻልማ"
ኡስታዙ፦"ይህ ለመጀመሪያ ጥያቄህ መልስ ነው።ሁላችንም አላህ እንዳለ እናምናለን ነገር ግን ማየት አንችልም።

እሺ ዛሬ እንደምመታህ ትናንት ማታ ገምተህ ነበር?"

ልጁ፦"አልገመትኩም።"
ኡስታዙ፦"እሺ እኔስ አንተን ዛሬ እንደምመታህ ትናንት ማታ አስቤ ነበር?

ልጁ፦"አላሰብክም።"
ኡስታዙ፦"ለ2ኛ ጥያቄህ መልስ ይህ ነው ቀዷ ቀደር የሚባለው።

እሺ እኔ አንተን የመታሁበት እጄ ከምንድነው የተፈጠረው?"

ልጁ፦"ከአፈር"
ኡስታዙ፦"እሺ በእጄ የመታሁት ያንተ ፊትስ ከምንድነው የተፈጠረው?"

ልጁ፦"ከአፈር"
ኡስታዙ፦"ስመታህ ምን ተሰማህ?"

ልጁ፦"አመመኝ"
ኡስታዙ፦"ከአፈር የተሰራ አፈርን ሲመታው
እንደሚያሳምመው ሁላ ከእሳት የተሰራውም ሸይጣን በእሳት ሲቀጣ በጣም ያመዋል።"

ክብር በየሀገሩ ላሉ ዑለማኦች ይገባቸዋል

ምንጭ፦" ﻋﺠﺎﺋﺐ ﻭﻏﺮﺍﺋﺐ ﻭﻃﺮﺍﺋﻒ ﺣﻮﻝ ﺍﻟﻌﺎﻟﻢ
ከተሰኘው የዐረብኛ ፔጅ

@oneummha

Читать полностью…

One ummah


😭😭😭😭😭😭😭😭😔😔😔😔😞
@oneummha

Читать полностью…

One ummah

የመሰተር ፀጋ
፨፨፨፨
የምድር ላይ ትልቅ ዱዓኤ “አላህ ሆይ ሰትረኝ” የሚለው ነው፡፡ “ሰትረኝ” ብዬ ሳልማፀን የዋልኩበት ቀን አለ ብዬ አላስታውስም፤ አልላሁም ስቱር ዐውራቲ፤ ወኣሚን ረውዓቲ፡፡

አላህ በእዝነቱ ሰተረን እንጂ ቢያጋልጠን ኖሮ ስንት ጉዳችን በታየ፡፡ ስንቱ ነውራችንም ይፋ በሆነ!፡፡
መሰተር ከኃጢኣት ብቻ አይደለም ወዳጀቼ፡፡ አላስተዋልንም እንጂ አላህ በብዙ መልኩ ሰትሮናል፡፡
፨ አብልቶ አጠጥቶ አዉሎን ከረሃብ አለንጋ ሰተረን፡፡
፨ ለገላችን መሸፈኛ ልብስ ሠጥቶን ከብርድ ዉጋት ሰተረን፡፡
፨ ጤናና ጥንካሬ ሰጥቶን በሰው እጅ ከመውደቅ እፍረት ሰተረን፡፡
፨ መሳቅ መጫወትን ችሮን ከሐዘን ስብራት ሰተረን፡፡
፨ ጥሩ ወንድሞችና ጓደኞች ሰጥቶን ከባይተዋርነት ህመም ሰተረን፡፡
፨ ማንበብና መረዳትን አስተምሮን ከመሃይምነት ጨለማ ሰተረን፡፡
፨ የምንወዳቸው ቤተሰብና ልጆች ሰጥቶን ከብቸኝነት ሕይወት ሰተረን፡፡
፨ ሥራና መዋያ ረዝቆን ከልመና ዉርደት ሰተረን፡፡
፨ አገርና ቤት ሰጥቶን ከስደት ግርፋት ሰተረን፡፡
፨ ምርጡን ሃይማኖት እስልምናን ሰጥቶን ከማያባራ የነፍስ ሥጋ ጥያቄ ሰተረን፡፡

መሰተር ትልቅ ፀጋ ነው፡፡ የአላህ ሲትር አይለያችሁ፡፡

@oneummha

Читать полностью…

One ummah

ስህተትህን ብረት ላይ ያስቀምጡታል....መልካምነትህን ደሞ ውሀ ላይ ያስቀምጡታል።
@oneummha

Читать полностью…

One ummah

-------------------------------------
ሁሌም ከአንተ የባሰውን እንጂ፤
የተሻለውን አትመልከት። ምክንያቱም
አሏህ በአንተ ላይ የዋለው ኒዕማ/ፀጋ
ትረሳለህና።

አሏህ ሆይ! አንተ ለእኔ ያጎደልክብኝ
ነገር የለም። እኔ ግን ለአንተ አምልኮየን
አጉድያለሁ! አንተ ሁሉን ተመልካች ነህና
ድክመቴን አይተህ በዲኔ አጽናኝ።
--------------------------------------

@oneummha

Читать полностью…

One ummah

ከሙእሚኖች ሁሉ በላጩና አስተዋይ ማነው?
~~~~~~~~~~~~
ታላቁ ሰሓቢይ ዐብዱላህ ኢብኑዑመር ረዲየላሁዐንሁማ የሚከተለውን
ይላሉ:–
ከነቢዩ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ጋር ቁጭ ባልኩበት ከመዲና ሰዎች መሀል
አንዱ ወደ ነቢዩ መጥቶ ሰላምታ ካቀረበ በኋላ
ከሙእሚኖች ሁሉ በላጩ ማነው? ብሎ ጠየቃቸው ?

እሳቸውም፦ በስነ-ምግባር ከሁሉም በላጭ የሆነ ሰው ነው አሉት፣
ቀጥሎም ከሙእሚኖች ሁሉ የበለጠ አዋቂው(ብልሁስ)ማነውብሎ
ጠየቃቸው?

➳እሳቸውም፦ ከማንም በላይ ሞትን አብዝቶ የሚያስታውስና ከሞት
በኋላም ላለው ህይወት፣ የበለጠ የተዘጋጀ ሰው ነው፡
ብልህ ማለት እንዲህ ዓይነት ሰዎች ናቸው አሉት።

📚ኢብኑ ማጀህ እና አጦበራኒይ ዘግበውት አልባኒይ ሰሒሕ ነው ብለውታል

@oneummha

Читать полностью…

One ummah

♡ ለሙስሊሙ ኡማ ኸይርን
የፈለገ ሰው ...
⇨ በህፃናት ልብ ውስጥ
የቁርአን ፍቅርን ይዝራ ።

@oneummha

Читать полностью…

One ummah

*

💙لاتكن أسيرا لإعجاب الناس بك ،

ለሰዎች አድናቆት እስረኛ አትሁን
ሰጡህም አልሰጡህም
የሰዎች ውዴታ ያንተ አላማህ አይደለም
ያንተ አላማ የአላህን ውዴታ ብቻ ነው❤️‼️‼️

*
:¨·.·¨: ❀
 `·. @oneummha

Читать полностью…
Subscribe to a channel