ማስታወሻ
ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
ሱሁር የሚበላው ለበረከት ነውና አትተው ከናንተ አንዳችሁ አንድ ጎንጭ ወሃ ቢጎነጭምንኳ ምክንያቱም አላህና መላአክቶች ሰሁር በሚጠቀም ላይ ሶለዋትን ያውርዳሉና ።
📚ሳሂህ አል-ጃሚዕ 3683
🤲ያ ﭐﻟﻠَّﻪَ 🤲ሪዝቃችን ከሰማይ እንደሆነ አውርድልን🤲
ከምድር ከሆነ አውጣልን፣ ከሩቅ ከሆነ አቅርብልን፣🤲
ቅርብ ከሆነ ገር አድርግልን፣ ትንሽ ከሆነ አብዛልን፣🤲
ብዙ ከሆነ በረካ አድርግልን።🤲
@oneummha
عن سُفْيانَ بنِ عبد اللَّه رضي اللَّه عنه قَالَ:
قُلْتُ: يَا رَسُول اللَّهِ قُلْ لِي في الإِسلامِ قَولاً لاَ أَسْأَلُ عنْه أَحداً غيْركَ. قَالَ:[ قُلْ: آمَنْت باللَّهِ: ثُمَّ اسْتَقِمْ ]
📚رواه مسلم.
🖊ከሱፍያን ቢን ዐብዲላህ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተወራው እንዲህ አሉ:-
የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! "በእስልምና ውስጥ ካንቱ ሌላ አንድንም ሰው የማልጠይቅበት የሆነን ነገር ንገሩኝ" አልኳቸው። እሳቸውም እንዲህ አሉኝ:- [ በአላህ አመንኩ በል። ከዚያም ቀጥ በል።] *
@oneummha
✅ ጥሩ ጓደኛ ካለህ በተኛህበት አላህ ሊምርህ ትችላለህ
💎 قال كعب الأحبار رحمه الله تعالى:
♻️ ከእብ አልአህባር አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል
📌【«رُب قائم مشكورٌ له، ورب نائم مغفور له؛ وذلك أن الرجلين يتحابان في الله، فقام أحدهما يصلي؛ فـ رضي الله صلاته ودعاءه، فلم يرد عليه مِن دعائه شيئًا، فذكر أخاه في دعائه من الليل، فقال:يا ربّ أخي فلان اغفر له؛ فغفر الله له وهو نائم።】
✅ አንደኛው በሰራው የሚመሰገንና ሌላኛው ደሞ በተኛበት ወንጀሉ የሚማርለት አለ።
♻️👇ይህም የሚሆነው ሁለት ለአላህ ብለው በጣም የሚዋደዱ ጓደኛሞች ነበሩ። አንደኛው ሌሊት ሊሰግድ ቆመ። አላህም ሶላቱና ዱአው ወደደለት። ከዱአውም ምንም ነገር ሳይመልስ አላህ ተቀበለው። በዚህ በሚሰግድ ጊዜ ዱአ ሲያደርግ የተኛው ወንድሙን አረሳውም ዱአ አደረገለት። ጌታዬ ሆይ እገሌ የሚባለው ወንድሜ ወንጀሉን ማረው አለ። በዚህ ወንድሙ ዱአ አማካኝነት በተኛበት አላህ ወንጀሉን ማረው።
📚[ حلية الأولياء (٦ /٣١)].
@oneummha
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ውድ የ one ummah ተከታታዮች ለብዙ ጊዜይት መጥፋታችን ይታወሳል ለዛም ይቅርታ እየጠየቅን ኢንሻ አላህ ከዚህ በኃላ active ለመሆን ዝግጅታችንን ጨርሰን መተናል
@oneummha
ወቅታዊ ማስታወሻ ለሙስሊሞች‼
🔹🔸🔹🔸🔹
ውድ ሙስሊም ወንድም ና እህቶች
ይህን ወቅታዊ ማስታወሻዬን ጥቂት ጊዜያችሁን ሰውታቹ እንድታነቡት አደራ አደራ እላለሁ❗️
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ አና በጣም አዛኝ በሆነው
ያለንበት ወቅት በ ዱንያ ካሉት ቀናቶች በጣም በላጭ የሆኑ እና አላህ ዘንድ በእነዚህ ቀናቶች የሚሰሩ ስራዎች ከሌሎች በተለየ ና በበለጠ ተወዳጅ የሚሆንበት 10ቱ ቀናት ላይ ነው ያለው
ማስታወሻዬም የሚያተኩረው በእነዚህ ውስጥ በሚገኘው በጣም ታላቅ ና ትሩፋቱ የበዛ ስለሆነው ስለ ዓረፋ
(የዙልሂጃ 9ኛው ቀን) ነው
📌የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም የዚህን ቀን ትሩፋቶች በሚገባ አብራርተዋል
ነብያችን እንዲህ ይላሉ : አላህ ሱ.ወ ከዐረፋ ቀን የበለጠ ባሮቹን ከእሳት ነፃ የሚያወጣበት የሆነ አንድም ቀን የለም
ከዛም በመቀጠል ያሉት :እኔም ከኔም በፊት ከነበሩት ነብያት ካሉት ንግግር በላጩ
لا ﺇﻟﻪَ ﺇﻻَّ ﺍﻟﻠَّﻪ ﻭﺣْﺪﻩُ ﻻَ ﺷَﺮِﻳﻚَ ﻟﻪُ، ﻟَﻪُ ﺍﻟﻤُﻠْﻚُ، ﻭﻟَﻪُ ﺍﻟﺤﻤْﺪُ، ﻭَﻫُﻮ ﻋَﻠَﻰ ﻛُﻞِّ
ﺷَﻲﺀٍ ﻗَﺪِﻳﺮ
ላ ኢላሃ ኢሏሁ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር የሚለው ነው::
ይህን ዚክር በብዛት በማለት እንበርታ ❗️
ሌላው ነብያችን እንዲህ ብለዋል
በላጬ ዱዓ ማለት የዓረፋ ቀን የሚደረግ ዱዓ ነው
📌በዚህ በላጭ በሆነው የዓረፋ(ዙልሂጃ 9) ቀን አላህ ሱ.ወ
⏳-ከእሳት ነፃ ከሚያደርጋቸው
⏳-ወንጀላቸው ከሚማርላቸው ባሮቹ መሆን የፈለገ ሰው
👉የዓረፋን ቀን ይፁም
ነብያችን እንዲህ ይላሉ :
{የዐረፋ ቀን በመፆም አላህ ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል እንደ ሚምር እተሳሰባለሁ}
{የዐረፋ ቀን የፆመ የሆነ ሰው ተከታታይ የሆኑ የሁለት አመት ወንጀሎቹን ይማርለታል}
👉የተውሂድ ቃል ዚክር ማለትን ያብዛ
ላ ኢላሃ ኢሏሁ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር
👉አላህ እንዲምረው እና ከእሳት ነፃ ከሚሆነው እንዲያደርገው መለመንን ያብዛ
አሏሁመ አእቲቅ ሪቃበና ሚነን ናር የምትለዋን ዱዓ በማለት አላህን እንለምን
በዚህ ቀን ዱኣ ተቀባይ መሆኑ በጣም የሚከጀልበት ነው❗️
📌ለዚህም ቀን ኸይር ፈላጊ የሆነ
ሙስሊም ራሱን ባለቤቱን እህት ወንድሞቹንና ልጆቹን ይህንን የተከበረ ቀን እንዲፆሙ ይቀሰቅሳል
📌አላህ ሱ.ወ የዚህን ቀን ትሩፋቶች ከሚያገኙ እና ወንጀላቸው ከሚማርላቸው ሰዎች እንዲያደርገን እለምነዋለሁ በመልካም ዱዓቹ አትርሱኝ
📌ይህን አንገብጋቢ ማስታወሻ ለምታውቁትም ለማታውቁትም ሙስሊም ለሆነ አካል እንድታሰራጬ እና የመልካም ስራ ተቋዳሽ እንድትሆኑ በአላህ ስም እጠይቃለሁ ❗️❗️
ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ
.
@oneummha
📌قلـوبنا ماتت
مر إبراهيم بن أدهم رحمه الله بسوق البصرة ؛ فاجتمع الناس إليه ، وقالوا : يا أبا إسحاق : ما لنا ندعوا فلا يستجاب لنا ؟
ኢብራሒም ኢብኑ አድሀም (ረሂመሁላህ) በበስራ ገበያ ሲያልፉ ሰዎች ተሰብስበው ወደሳቸው ከበቧቸውና እንዲህ አሏቸው፦
"ያ አባ ኢስሐቁ! ዱዓ አድርገን ዱዓችን ለምን ምላሽ አጣ?"
قال : لأن قلوبكم ماتت بعشرة أشياء.!
➲እሳቸውም ፦"ቀልባችሁ በአስር ነገሮች ሙታለች።" አሏቸው።
قالوا : وما هي ⁉️
➲እነሱም፦"ምን ምንድ ናቸው?" ብለው ጠየቋቸው።
قال (الأول) : أنكم عرفتم الله ؛ فلم تؤدوا حقه .
➲እሳቸውም፦
1️⃣አላህን አውቃቹት።ሐቁን አልተወጣችሁም።
(الثاني) : زعمتم أنكم تحبون رسول الله ﷺ ثم تركتم سنته
2️⃣ ነቢዩን ﷺ እንወዳለን ብላችሁ ሞገታችሁ ከዚያም ሱናውን ተዋችሁ።
(الثالث) : قرأتم القرآن ، ولم تعملوا به
3️⃣ ቁርኣንን አነበባችሁት ፣አልሰራችበትም።
(الرابع) : أكلتم نعمة الله ، ولم تؤدوا شكرها .
4️⃣ የአላህን ፀጋ በልታችሁ ምስጋናውን አልተወጣችሁም።
(الخامس) : قلتم إن الشيطان عدوكم ، ووافقتموه
5️⃣ ሸይጣን ጠላታችነው ብላችሁ ከሱ ጋ ገጠማቹ።
(السادس) : قلتم إن الجنة حق ، فلم تعملوا لها.
7️⃣ጀነት ሐቅ ናት ብላችሁ ለርሷ ሚሆን ስራ አልሰራችሁም።
(السابع) : قلتم إن النار حق ، ولم تهربوا منها
7️⃣ የጀሀነም እሳት ሐቅ ነው ብላችሁ ለሷ የሚዳርጋችሁት ስራ አልተዋቹም።
(الثامن) : قلتم إن الموت حق ، فلم تستعدوا له
8️⃣ሞት ሐቅ ነው ብላችሁ ለሱ አልተሰናዳችሁም።
(التاسع) :انتبهتم من النوم ، واشتغلتم بعيوب الناس ، وتركتم عيوبكم
(9) ከእንቅልፋቹ ነቅታቹ፣ የራሳችሁን ነውር ትታችሁ በሰዎች ነውር ተጠመዳችሁ።
(العاشر) : دفنتم موتاكم ، ولم تعتبروا بهم
(10) ሙታናችሁን ቀብራችሁ በነሱ አልተገሰፃችሁም።
[جامع بيان العلم وفضله (2/12)]
@oneummha
"ረመዳን እኮ የተባለው ወንጀሎችን በመልካም ስራዎች አቃጥሎ አመድ ስለሚያደርጋቸው ነው"
ኢማሙል ቁርጡቢ
ማነው በዚህ በተከበረ ወር መልካም ስራዎችን አብዝቶ በመስራት ዓመቱን ሙሉ ያከማቸውን ወንጀል አቃጥሎ አመድ ለማድረግ ቆርጦ የተነሳ!?
⭐️⭐️⭐️
ለዚህ የላቀ ወር ላይ በሰላምና በጤና በመድረስ የታደልክ ፆመኛ ሆይ! ሳያመልጥህ በፊት ተጣደፍ፣ ከመሞትህ በፊት ነፍስህን ከጥልቅ እንቅልፏ ቀስቅሳትና የሁለቱንም ዓለም ስኬት እንድታጣጥም አድርጋት፣ ነገ ጀነትን እንድታሸንፍ ዛሬ አበርታት።
⭐️⭐️⭐️
ማሊክ ኢብን አነስ የረመዳን ወር በገባ ጊዜ የሐዲስና የዕውቀት ማዕዶች ላይ መገኘታቸውን እርግፍ አድርገው በመተው ፊታቸውን ወደ ቁርኣን ብቻ ያዞሩ ነበር።
⭐️⭐️⭐️
አቡ ቀታዳህ በረመዳን ውስጥ በየሦስት ሌሊቶች፣ እንዲሁም በመጨረሻዎቹ አሥር ቀናት ውስጥ ደግሞ በያንዳንዷ ሌሊት ሙሉ ቁርኣንን አንብበው ይጨርሱ ነበር።
⭐️⭐️⭐️
አል-አስወድ የረመዳን ወር ሲገባ፣ በየሁለት ሌሊት ቁርአንን አንብበው በመጨረስ ሙሉ ወሩን ያጠናቅቁ ነበር።
@oneummha
💢ልንጠነቀቀው የሚገባ ትልቅ አደጋ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
▪️ قال رسول الله ﷺ :(( إنَّ اللَّعَّانين لا يكونون شهداءَ ولا شفعاءَ يومَ القيامةِ ))
✅ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል።
🔘መራገምን የሚያበዙ ሰዎች የውመል ቂያማ
🔹መስካሪ አይሆኑም (ምስክርነታቸው ተቀባይነት የለውም)
🔹ሸምጋይ (አስታራቂ) አይደረጉም (ሽምግልናቸው ተቀባይነት የለውም)
📚 صحيح مسلم - رقم: (2598)
⏺ በሆነ ባልሆነው ለሚራገሙ ሰዎች ይጠነቀቁ ዘንድ እናሳውቃቸው❗️
-----------------------
@oneummha
ሁሉም ሲሞት ወደ አላህ ይሄዳል ፣ እድለኛ ማለት ግን በህይወት እያለ ወደ አላህ የሄደ ፣ ኑሮውን ለአላህ ያረገ ነው
@oneummha
▪️#ሙሐረም_እና_የዐሹራ_ፆም
🔻በሙስሊሞች አቆጣጠር የመጨረሻው ወር ዙልሒጃህ ሲሆን የአዲሱ አመት የመጀመርያ ወር ደግሞ ሙሐረም ይባላል። ሙሐረም ከተከበሩት ኣራቱ ወራቶች ማለትም (ዙልቂዕዳህ ፣ ዙልሒጃህ ፣ ሙሐረም እና ረጀብ) ውስጥ አንዱ ነው። የአሏህ ወርም በመባል ይጠራል። ወሩን መፆምም ተወዳጅ ነው። ከአቡሁረይራ ተይዞ እንደተወራው የአሏህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ ከረመዷን ወር በኋላ በላጩ ፆም ፤ የአሏህ ወር የሙሐረም ፆም ነው። ] (ሙስሊም ፥ 1163).
°
🔻የሙሐረም ወር ለየት ከሚያደርገው ውስጥ አንዱ በውስጡ የዐሹራ ቀንን መያዙ ነው። ይህም የዐሹራ ቀን የረመዷን ወር ፆም በሙስሊሞች ላይ ግዴታ ከመደረጉ በፊት በግዴታነት ይፆም ነበር። ይህን የሚያመላክት (ቡኻሪ ፥ 2001) ላይ የተዘገበ ሐዲስ አለ።
°
🔻በሱናነት መልኩ ይህንን ቀን መፆም ተገቢ ነው። ምክንያቱም አሏህ ነብዩሏህ ሙሳ - ዐለይሂሰላምን - እና ህዝቦቹን ከፊርዓውን በደልና ግፍ ያላቀቀበት ቀን ነው። ይህን በማስመልከትም ዐብደሏህ ኢብን ዐባስ - ረዲየሏሁ ዐንሁማ - [ ረሱል - ﷺ - የዐሹራን ቀን ፁመውታል ሰዎችም እንዲፆሙ አዘዋል። ] በማለት ተናግረዋል። (ቡኻሪ ፥ 2004 እና ሙስሊም ፥ 1130)
°
🔻የዐሹራን ቀን መፆም ያለፈውን አንድ አመት ወንጀል(ማለትም ትናንሹን) ያስምራል። የአሏህ መልእክተኛ - ﷺ - ስለዐሹራ ፆም ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል ፦ [ የዐሹራን ቀን መፆም አላህ ዘንድ ከዚህ በፊት ያለውን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ] (መሰሊም ፥ 1162 ላይ ዘግቦታል). የዐሹራን ቀን መፆም እንጂ #እንደዒድ_አድርጎ_መያዝ ክልክል እና አዲስ መጤ የሆነ ተግባር ነው እና ልንርቀው ይገባል። ቢድዓ ሁሉ ጥሜት ነው።
°
🔻ከአስረኛው ቀን አብሮ 9ኛውንም ቀንም መፆም ተገቢ ነው። ምክንያቱም ረሱል - ﷺ - (ሙስሊም ፥ 1134) በዘገቡት ሐዲስ ላይ [ የሚቀጥለው አመት ብደርስ 9ኛውንም ቀን ፆመዋለው። ] ስላሉ ማለት ነው። በዚህም ምክንያት ከአይሁዶች ጋር መቃረን ይገኝበታል።
°
🔻ዘጠነኛውን ቀን መፆም ካልቻሉ 10ኛውን እና 11ኛውንም ቀን መፆም እንደሚቻል ዑለማዎች ተናግረዋል። ማስረጃቸውም ተከታዩ ሐዲስ ነው ፦ [ የዐሹራን ቀን ፁሙ የሁዳዎችንም ተቃረኑ ፤ ከሱ በፊት ያለውን ቀን ፁሙ ወይም ከሱ በኋላ ያለውን ቀን ፁሙ። ] (ሙስነድ ኢማሙ አሕመድ ፥ 2154 ላይ ተዘግቧል / አሕመድ ሻኪር ሐሰን ብለውታል).
°
🔻በመሆኑም የዐሹራ ፆም ደረጃዎች ጠቅለል ሲደረጉ እንደሚከተለው ይሆናል ፦
1ኛ ደረጃ ፡ 9ነኛው እና 10ኛውን ቀን መፆም
2ኛ ደረጃ ፡ 10ኛው እና 11ኛውን ቀን መፆም
3ኛ ደረጃ ፡ 10ኛውን የዐሹራን ቀን ብቻ መፆም ነው ፤ በእርግጥ አንዳንድ ዑለማዎች 10ኛውን ቀን ብቻ መፆምን ጠልተውታል ምክንያቱም ነብዩ - ﷺ - አይሁዶችን በመቃረን ስላዘዙ ይላሉ ሌሎች ደግሞ ችግር የለውም ብለዋል።
°
🔻እነዚህን ሶስት ደረጃዎች ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን (ሸርሕ ሪያዱሷሊሒን ፥ 3/463) ላይ አስቀምጠውታል። ❶. ኢብኑልቀይዪም (ዛዱል መዓድ ፥ 2/75) ላይ ደግሞ 9 ፣ 10 እና 11ኛውን ሶስቱንም ቀን መፆም የመጀመሪያ ደረጃ ነው በማለት ተናግረዋል። ሌሎቹ ደግሞ ኢብኑልቀይም ይህን ያሉት ደከም ያለ ሐዲስ ላይ ተንተርሰው ነውና በላጩ ደረጃ 9ኝ እና 10ኛውን ቀን መፆም ነው ብለዋል። ወሏሁ አዕለም።
°
🔻ሌላው የሚነሳው ነጥብ #ቀዷእ_ያለበት_ሰው የዐሹራን ፆም መፆም ቢፆም አጅሩን ያገኛል ወይስ አያገኝም የሚለው ነው። እዚህ ላይ አንዳንድ ዑለማዎች የቀዷእ ፆም ግዴታ ስለሆነ ለብቻው መፆም አለበት ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ አብሮ ነይቶ ቢፆምም በአሏህ ፍቃድ የሁለቱንም አጅር ያገኛል የሚሉ አሉ።
°
🔻ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን (ፈታዋ-ሲያም ፥ 438) ላይ የሚከተለውን ብለዋል ፦ |" የረመዷን ቀዷእ እያለበት የዐረፋን ወይም የዐሹራን ቀን ፆም ቢፆም ፆሙ ትክክል ነው ፤ ነገር ግን ይህን ቀን ለቀዷኡም አብሮ ቢነይት የሁለቱንም አጅር ያገኛል። "|. ሸይኽ ኢብንባዝም በተመሳሳይ በአሏህ ፍቃድ የሁለቱንም ምንዳ ያገኛል ብለን ተስፋ እናደርጋለን በማለት ተናግረዋል።
ንግግራቸውን በዚህ ሊንክ ማዳመት ትችላላችሁ ፦ bit.ly/2YkwxpA
የቀዷእ ፆማችንን ቶሎ በማውጣት ላይ ልንተጋ ይገባናል።
°
🔻#በተጨማሪም በየወሩ ሶስት ቀን መፆም ያስለመደ ሰው 9ነኛው 10ኛውን እና 11ኛውን ቀን ለሁለቱም ነይቶ ቢፆም የዐሹራውንም እና በየወሩ ሶስት ቀን የመፆምን የሁለቱንም አጅር ያገኛል። ምክንያቱም በየወሩ ሶስት ቀን መፆም ግዴታ "#አያመል-#ቢድ" ላይ ብቻ አይገደብም። ማስረጃውም (ሙስሊም ፥ 1160) በተዘገበ ሐዲስ ላይ ነብዩ - ﷺ - ከየወሩ ሶስት ቀን እንደሚፆሙና ቀናቶችን በተመለከተ ደግሞ መጀመሪያም ላይ ይሁን መካከለኛም ላይ ይሁን መጨረሻ ቀናቶች ላይ እንደተመቻቸው ይፆሙ እንደነበረ ተገልጿልና ነው።
°
🔻9ነኛውን እና 10ኛውን ቀን ፁሞ በተጨማሪም "አያመል-ቢድ" የተባሉት 13 ፣ 14 እና 15 ቀናቶችን ቢፆም ደግሞ በአሏህ ፍቃድ ምንዳው የበለጠ ይሆናል። ምክንያቱም 1ኛ. አያመል-ቢድን መፆም ለብቻው ትሩፋት እንዳለው በተለያዩ ሐዲሶች ላይ መዘገቡ 2ኛ ደግሞ ወሩ ሙሐረም በሙሆኑ ከላይ ባሳለፍነው ሐዲስ መሰረት ፆም ማብዛት ተወዳጅ ስለሆነ ነው።
°
🔻#በመጨረሻም የዐሹራ ቀን ከቅዳሜ ቀን ጋር ከተገጣጠመ ቅዳሜን መፆምን የሚከለክል ሐዲስ ስላለ እንዴት እናድርግ? የሚለው ላይ ሸይኽ ኢብኑዑሰይሚን (መጅሙዓል ፈታዋ ወረሳኢል ፥ 20/57) ላይ የዐረፋ የዓሹራ እና መሰል ፆሞች የቅዳሜን ቀን ቢገጥሙ መፆም ችግር የለውም ምክንያቱም አንድ ሰው እነዚህን ቀናቶች የሚፆመው መፆማቸው የተደነገጉ ፆሞች ስለሆኑ ነው በማለት አስቀምጠዋል። የዐሹራ ቀን የጁሙዓ ቀንን ቢገጥምም ተመሳሳይ ብይን እንደሚሰጠው ዑለማዎች ተናግረዋል።
°
🔻ስለዚህም ወንድሞቼ እና እህቶቼ አሏሁ ተዓላ ለኛ የሚፈጥርልን የኸይር አጋጣሚዎች ችላ በማለት ልናሳልፍ አይገባንም። ራሳችንም ፁመን ሰዎችንም ማነሳሳት ይጠበቅብናል። ወሏሁ አዕለም.
_
❶.ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን በሌላ ቦታ ላይ ደግሞ የመጀመሪያው ደረጃ 3ቱንም ቀን መፆም ነው በማለት የኢብኑልቀይዪምን ንግግር የሚያጠናክር አባባል አላቸው።
@oneummha
አንድ ቀን...
አንድ ሰው ወደ ነብዩ (ሰዐወ) በመምጣት የአላህ መልዕክተኛ ሆይ የትኛው የሰደቃ አይነት ነው ትልቅ ምንዳ ያለው ሲል ጠየቃቸው "ጤነኛ ሆነህ (ገንዘብህ) እየፈለከው ፣ ድህነትን እየሰጋህ ፣ ሀብትን ተስፋ እያደረግክ መመፅወት ነው፡፡ ሩህ ጉሮሮህ ስትደርስ ይህንን ለእከሌ ይህንን ለእከሌ ወደምትልበት ጊዜ አታዘግይ ባትለውም ለከሌ ሆኗል" አሉት (ቡኻሪና ሙስሊም)
#ሼር #share
#join
@oneummha
《የአላህ መልክተኛ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም》
በአንድ ወቅት "ሐሜት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" በማለት ባልደረቦቻቸውን ጠየቁ።
"አላህና መልእክተኛው ያውቃሉ።" የሚል ምላሽ ተሠጣቸው። እንዲህ አሉ፦
«ሐሜት ማለት ስለ አንድ ወንድምህ እርሱ የሚጠላውን ነገር ማውሳት ነው።» "እርሱ ላይ የምለው ነገር በእውነትም ከርሱ ላይ ያለበት ቢሆንስ?" የሚል ጥያቄ አንዱ አቀረበላቸው። እሳቸውም ፦ «የምትለው ነገር በርሱ ላይ ካለ አምተኸዋል፤ ከሌለበት ደግሞ የሌለበትን ነገር ለጥፈህበታል(ቀጥፈህበታል)።»በማለት መለሱለት።
(ሙስሊም ዘግበውታል)
@oneummha
❥::::::::::ሴት ልጅ: ::::::::::::❥
❥የአሏህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ይላሉ❥
لا تمنعوا إماءَ اللهِ مساجدَ اللهِ وبيوتهنَّ خيرٌ لهنَّ. متفق عليه
"የአሏህን ባርያት የአሏህን(ቤት) መስጂድን አትከልክሏቸው፡ ቤታቸው ግን ለነሱ በላጭ ናት፡፡"
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል ].
ቤታቸው ለነሱ በላጭናት ከሁሉም ነገር፡፡ እንዲሁም ከመስጂድ ሁላ ቤታቸው በላጭ ናት ከተባለ እንዴት ሊሆን ነው ታዲያ ሱቅን ተገላልጠው መውጣታቸው?
አሏህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል
وَٱلْقَوَٰعِدُ مِنَ ٱلنِّسَآءِ ٱلَّٰتِى لَا يَرْجُونَ نِكَاحًۭا فَلَيْسَ عَلَيْهِنَّ جُنَاحٌ أَن يَضَعْنَ ثِيَابَهُنَّ غَيْرَ مُتَبَرِّجَٰتٍۭ بِزِينَةٍۢ ۖ وَأَن يَسْتَعْفِفْنَ خَيْرٌۭ لَّهُنَّ
ٌۭ
እነዚያም ከሴቶች እድሜየቸው የገፋ የሆነ እንዲሁም ጋብቻን የማይፈልጉት ተቀማጮች (ባልቴቶች)፤ በጌጥ የተዋቡ ሳይኾኑ የላይ ልብሶቻቸውን ቢጥሉ በእነሱ ላይ ኀጢአት የለባቸውም፡፡ ነገር ግን መጠበቃቸው ለእነርሱ ጥሩና የተሻለ ነው፡፡
አሮጊት-በእድሜ የገፋች- የሆነች ሴት በጌጥ መገላለጥን ከተከለከለች፡ እንዴት ይሆናል ታዲያ በወጣቷ ያቺ የፊትናን በር ከፋች የሆነችዋ ተውባና አምራ ከቤት መውጣቷ?
አሏህ እንዲህ ይላል
وَلَا يَضْرِبْنَ بِأَرْجُلِهِنَّ لِيُعْلَمَ مَا يُخْفِينَ مِن زِينَتِهِنَّ
"እግሮቻቸውንም ከምድር ጋር አይምቱ ከእግራቸው ስር ያለው ጌጥ እንዲታወቅ ብለው፡፡"
ሴት ልጅ ከእግሯ ውስጥ ያለውን እንዳታሰማ አሏህ ከከለከላት እንዴት ልትሆን ነው ታዲያ ያቺ እግሯን ሳይቀር የምታሳየው?
ለምን ከተባለ የእይታ ፈተና ልክ እንደሚታወቀው ከመስማት የበለጠ ስለሆነ ነው፡፡
የአሏህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ይላሉ
"ሁለት አይነት ባህሪ ያላቸው የእሳት ሰዎች እኔም በፍፁም የማላያቸው የሆኑ...ከነዚህም ሴቶች ናቸው ለብሰው እንዳለበሱ፤ተዘንብለው ሌሎችን የሚያዘነብሉ፤ጸጉራቸውንም እንደ ግመል ሻኛ የቆለሉ የሆኑ እነዚህ ጀነትን አይገቡም፡ከሽታዋም ምንንም አያገኙም፡፡"
እንዲሁም በሌላ ሀዲስ የአሏህ መልእክተኛ ﷺእንዲህ ብለዋል
" የትኛዋም ሴት ጭስን(እጣን) የነካች የሆነች ከእኛ ጋር እንዳትጣድ፡፡"
የአሏህ መልእክተኛ ጭስን ወይም እጣንን በመንካቷ ሶላት እንዳትጣድ ካሉ እንዴት ሊትሆን ነው ታዲያ ከጭስ የበለጠ ሽታ ያለውን ሽቶ ተለቅልቃ የምትወጣው?
ከአሏህ መልእክተኛ ﷺተዝግቧል እንዲሁ እንዲህ እንዳሉ
" ለሴቶች ጥሩ የሚባለው ሰፋቸው(በሶላት ላይ) ኀላ መሆናቸው ነው፡ መጥፎዎቸው ደግሞ ፊት መሆናቸው ነው✍
@oneummha
🖐 كلام اعجبني ..................
ካስገረሙኝ ንግግሮች 🖐
🔲 عندما تولد لا تعلم
من الذي أخرجك من بطن أمك
🔲በምትወለድበት ጊዜ ከእናትህ ሆድ ያወጣህን ፈፅሞ አታውቅም።
🔳 وعندما تموت لا تعلم
من الذي أدخلك إلى قبرك
🔳 በምትሞትበት ጊዜ ማን ወደ ቀብርህ እንዳስገባህ ፈፅሞ አታውቅም።
*🔲 عجبا لك ياابن آدم*
*🔲 የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ።*
🔳 عندما ولدت تغسل وتنظف
🔳 በተወለድክ ጊዜ ትታጠባለህ፣ ትፀዳለህ።
🔲 وعندما تموت تغسل وتنظف
🔲 በምትሞትበት ጊዜ ትታጠባለህ፣ ትፀዳለህ።
*🔳 عجبا لك ياابن آدم*
*🔳 የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ።*
🔲 عندما تولد لاتعلم من فرح واستبشر بك
🔲 በተወለድክ ጊዜ በውልደት ማን እንደተደሰተ እና እንደተበረሰ አታውቅም።
🔳 وعندما تموت لاتعلم من بكى عليك وحزن
🔳 በሞት ጊዜ በመሞትህ ማን እንዳለቀና እንደአዘነ አታውቅም።
*🔲 عجبا لك ياابن آدم*
*🔲 የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ*
🔳 في بطن أمك كنت في مكان ضيق ومظلم
🔳 በእናትህ ሆድ ውስጥ በጠባብ ቦታና በጨለማ ውስጥ ነበርክ።
🔲 وعندما تموت تكون في مكان ضيق ومظلم
🔲 በምትሞትበት ጊዜ በጠባብ ቦታና በጨለማ ውስጥ ትሆናለህ።
*🔳 عجبا لك ياابن آدم*
*🔳 የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ*
🔲 عندما ولدت تغطى بالقماش ليستروك
🔲 ስትወለድ በጨርቅ ትጠቀለላህ ሊሸፍኑህ!
🔳 وعندما تموت تكفن بالقماش ليستروك
🔳 ስትሞት በከፈን ይጠቀልሉሃል ሊሸፍኑህ!
🔲 عجبا لك ياابن آدم
🔲 የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ
🔳 عندما ولدت وكبرت يسألك الناس
عن شهادتك وخبراتك
🔳 በተወለድክና በአደግክ ጊዜ ሰዎች ስለምስክር (ወረቀትህና) ስለሙያህ ይጠይቁሃክ።
🔲 وعندما تموت تسألك الملائكة عن عملك الصالح
🔲 በሞትክም ጊዜ መልዓይኮች ስለመልካም ስራህ ይጠይቁሃል።
*🔳 فماذا أعددت لآخرتك ؟*
*🔳 ለመጨረሻው ሃገርህ ምን አዘጋጀህ?*
🔲 جرب تقولها من قلب :
آشهد آن لآ آله آلآ آلله
واشهد آن محمد رسول آلله
🔲 ከልብህ ይህችን (ቃል) ለመናገር ሞክር! ።ከአላህ ሌላ በፍፁም የሚመለክ አምላክ እንደሌለ መስክር። እንዲሁም ሙሃመድ የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን መስክር።
🔳 مستحيل تقرآها بدون ما ترسلها
🔳 (ይህን መልእክት) በፍፁም ሳታነባድ እንዳትልካት!!
& & &
بسم الله الرحمن الرحیم
*{ قل هو الله أحد * الله الصمد * لم يلد ولم يولد * ولم يكن له كفواً أحد }*
*ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ*
*{ በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው። አልወለደም፤ አልተወለደምም። ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።}*
إرسل وتخيل في هالساعه 🕗
መልዕክቱን ላክ! ሰአትህን አስተውል🕗
كم شخص يقرأ ثلث القرآن 📘 بسببك لاتحرم نفسك مٍن الاجر
በአንተ ሰበብ የቁርዓን አንድ ሶስተኛን ይቀራሉ(ያነባሉ) 📘
ነፍስህ አጅር አትከልክላት!!
@oneummha
በዙልሒጃ ወር መደረግ ያለባቸው ኢባዳዎች
🎙 አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Join ➤➤ t.me/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
10 የዙልሂጃ ቀናቶች 🙏🙏
በመልካም ስራዎች ምናሳልፍ ያድርገን
በ ዱአ እንተዋወስ 🙏
እኔንም በ ዱአቹ አትርሱኝ በ @oneummha_bot ዱአቹን ማድረስ ትችላላቹ 🙏
@oneummha
ዛሬ ሒጃብ በሥርኣት አልለብስ ያለው ገላ ነገ ከፈንን በግድ ይለብሳል፡፡ ዛሬ መሬት ላይ ሥርኣት ያልያዘን ወጣት ነገ መሬት ሥር መቃብር ሥርኣት ያስይዘዋል፡፡
እንደ ዩሱፍ መሸሽ የሚችል ወጣት ጠፋ!
እንደ መርየም ለንጽህናዋ የምትጨነቅ ሴት ታጣች፡፡
አምላኬ ሆይ! ሀይለኛ ንፋስ ሊገልጠው በማይችል መሰተሪያ ሰትረን፡፡ ጉልበት አጣን አግዘን፡፡ መሆን አቃተን ደግፈን፡፡🙏🙏
@oneummha
የባጢል ሰዎች ንግግራቸው ስላማራ አንደበታቸው ስለጣፈጠ እውነተኛ ሊሆኑ አይችሉም!!
""" """" """"
አንዳንድ ሰዎች ንግግራቸውንና አንደበታቸውን በማሰማመርና በማጋጌጥ ይዘውት የተነሱትን ባጢል እውነት ለማስመሰል ይሞክራሉ። ልክ እንደዚያው ንግግሩ አላማረለትም ብለው የሚያስቡት ሀቅ ተናጋሪ ውሸታም ሊሆን አይችልም!!
የሀቅ ሰዎች ዘንድ ደግሞ አልፎ አልፎም ቢሆን የሚናገሯቸው ጠንከር ያሉ ቃላቶች ካሉ እነሱን ለቅመው አውጥተው በማራገብ የሚናገሩትን ሁሉ እውነታ ለማበላሸት "ይሀው ተሳዳቢ ናቸው፣ ተራጋሚ ናቸው…" እያሉ ይዳክራሉ። ዳሩ ግን ሀቅ ሀቅ ናት! የገላጯ አንደበት አማረም አላማረም፣ ተጋጌጠም አልተጋጌጠም ሀቋን በማስረጃ ፈትሾ መቀበል ነው። ሀቅ የሚመዘነው በማስረጃና እውነትን በመከተል ብቻ ነው።
ዛሬ ላይ ሰነድ ያውቃሉ፣ ጠንከር ያሉ የጀርህ ቃላቶችን ከደጋግ ቀደምቶች ተገንዝበዋል የሚባሉ ሰዎች ሳይቀሩ ታች ወርደው እንደ ቲፎዞዎቻቸው የመንደር ወሬ ሲያወሩ ስትሰማ ሀቂቃ ከመቼው እንዲህ ባከኑ?! ብለህ ታዝናለህ።
ይሁንና ሀቅ የሚለካው ንግግሩ በተጋጌጠና አንደበቱ በጣፈጠ ልክ ሳይሆን በማስረጃና ሀቅን በመከተል ነው!! የሀቅ ሰዎች አንደበታቸው ባይጣፍጥም፣ ንግግራቸው ባይጋጌጥም የሚናገሩት ሀቅ እስከሆነ ድረስ ሀቅ ፈላጊ በሆነ ሰው ላይ የመቀበል ግዴታ አለበት!!
ኢማሙል አውዛዒ (ረሂመሁላህ) የሚባሉ ታላቅ ሊቅ 157ኛ ዓ.ሂ ላይ ነው ወደ አኼራ የሄዱት፣ ከአትባዑ ታቢዒን ናቸው፣ እንዲህ ሲሉ ይመክራሉ:-
“ሰዎች ቢጋጩህ አለያም ቢርቁህ እንኳ የደጋግ ቀደምቶችን ትውፊት በመከተል ላይ አደራ! (ንቃት ይኑርህ!)። ወዮልህ የሰዎችን (የተዛባ) አስተሳሰብ ተጠንቀቅ! በንግግር ቢያጋጌጡልህ እንኳን።” [ጃሚዕ በያኑል ዒልሚ ወፈድሊሂ 2/114]
ሸይኽ ሷሊህ አሉ ሸይኽ (ሀፊዘሁላህ) ይህን ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ:- “አስተሳሰባቸውን ቢያጋጌጡልህም፣ አንደበታቸውን ቢያሳምሩም ወዮለት ወዮልህ ንግግራቸውን ስላሳመሩና ቃላቶችን ስላሳመሯቸው ከሱንና ዘወር አትበል። ሱንናን እና የሱና ባለቤቶችን አንደበታቸውና የሚጠቀሟቸው ቃላቶች ባያምሩ እንኳን አጥብቀህ ያዝ!። ምክንያቱም ሚዛኑ ሱናን በመከተል ላይ ነው፣ ሱናን የተከተለ ድኗል፣ አዲስ ነገር የፈጠረ እርሱ ጠፊ ነው፣ አላህ ከጥፋት ይጠብቀን!።” አሉ
ሸይኽ ሷሊህ ቢን ፈውዛን አል-ፈውዛን (ሀፊዘሁላህ) ይህን የኢማሙል አውዛዒን ንግግር ሲያብራሩት እንዲህ ብለዋል:-
“ደጋግ ቀደምቶችን በመከተልህ ሰዎች ቢጋጩህም፣ ደረቅ ነህ ቢሉህም ወደነሱ ዘወር አትበል። ለሚያወግዙህ ነገር ቦታ አትስጠው ምክንያቱም አንተ ሀቅ ላይ ነህ፣ ሀቅ ላይ እስከሆንክ ደግሞ ፅና!። አንተ የሰዎችን ውዴታና ሙገሳ አይደለም የምትፈልገው፣ የምትፈልገው አላህን ማስወደድ እና ሀቅን ነው፣ ሀቅ ደግሞ ጥርጥር የለውም የደጋግ ቀደምቶችን መንገድ በመከተል ላይ ነው። በግብዝነት፣ በተቃርኖ ሀሳብ አራማጅነትና መሰል ቃላት የሚገልፅህም ስታገኝ በጭራሽ ወደሱ ዘወር አትበል!። ምክንያቱም አንተ ሀቅ ላይ ነህ እነሱ ግን ባጢል ላይ ናቸው!!።” አላህ ሀቁን አውቀን በመከተል ላይ የምንፀና ያድርገን!!
✍🏻 ኢብን ሽፋ: ጁማዱል አኺር 22/1442
@oneummha
አንድ ሰውዬ ውሃውን ክፍት ትቶት አጠገቡ ቆሞ ዝምምምምም ብሎ ውሃው ይፈሳል፤ በዛ በኩል የሚያልፉ ሰዎችም ትኩረት አልሰጡትም፤ ባላየ ያልፉታል።
ሰውየው ይሄድና ውሃውን ይዘጋዋል፤ ሰውዬውም ምንም ሳይለው መጥቶ ለመዝጋት ምን እንዳነሳሳው ጠየቀው...
ሲመልስም... "እኔም አንተም በአንድ ሃገር ውስጥ ነው የምንኖረው የሃገራችንን ሁኔታ ደግሞ እናውቀዋለን። አንተ እድሉን ስላገኘህ ውሃውን ታፈሳለህ ስንት የሚጠማ፣ ስንት ከንጹህ መጠጥ ውሃ የራቀ አለ። እነዚህም ወገኖቻችን ናቸውና ልናስብላቸው ይገባል። ደግሞ ውሃው ያለ አግባብ ቢፈስ ከተማው ይጨመላለቃል፣ ያንተን ገንዘብ ያራቁታል፣ ለመንገዱ ጠር ነው፣ለ እግረኛ እንቅፋት ነው፤ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል። ሃገር ልእልናዋን የምታስጠብቀው ሁሉም ያገባኛል የሚል ስሜት በውስጡ መፍጠር ሲችል ነው። የዚህኔ የአጥፊዎች ቁጥር ያንሳል፣ እጃቸውም ያጥራል..."
So
ዛሬ ብደዐ እየተስፋፋ
፤ የድናችንን ጉዳይ እንደት ነው ስጨማለቅ እያየን ዝም ማለታችን ፤ ሁሉን ነገር ወደ ለላ መግፋት ሳይሆን እኛ እራሳችን የእራሳችን ድን ሲጠፋ ማስቆም፣ ሲለማ አብሮ ማልማት፣ የጎበጠውን ማቃናት፣ ከማውራት መተግበር...የስልምና ግዴታችንን መወጣት ይኖርብናል። አለያ ሲወድም ዝም የምንል ከሆነ፣ ሲለማ የራሱ ጉዳይ ብለን የምንተው ከሆነ...ወደ ፊት ሳይሆን ወደኋላ ነው ሽምጥ የምንጋልብ። የድኔ ጉዳይ ያገባኛል ይመለከተኛል... የሚል አንድምታ ውስጣችን መስረጽ ይኖርበታል።
@oneummha