ይህ ቻናል በምሥራቅ ኢትዮጵያ ስለምትገኘው ቅድስት ቤተክርስቲያን እና ልጆቿ መረጃ እና ዘገባ የምናደርስበት ነው።
https://chng.it/NgpMnSGpKr
#ፍርማውን ያልፈረማችሁ እየፈረማችሁ
"በአርምሞ የተጀመረው ተጋድሎ በአርምሞ ተቋጨ" ዲ/ን ብርሃን አድማስ
"የአርምሞውን ሚስጢር ሳንደርስበት አመለጡን"
"በዝምታቸው ባረኩን፤ ሳናውቃቸው እያውቅናቸው ተለየናቸው"
"ባለመናገራቸው ብዙ ሚስጢር አመለጠን"
"በመጨረሻም ሁሉም ነገር ለበጎ ነው ብለን ዝም አለን" መምህር ፍሬሰው ደምስ
__________________
እንቋዕ አብጽሐነ!
እንኳን አደረሰን!
ባጋ ጌሳን!
እንኳዕ ኣብፀሐና!
በወሄ አሰናነም!
ኢድ ቤጉ ነጋዲሴ!
ሃዋሌ ኢሊሽንኬ!
ወዝ ችጝዘት!
ሃሹ ሳሩዋን ጋቲስ!
ባጋ ጌኔነን!
________
@orthoateast
https://chng.it/VjRX9cLPL6
Please sign and share it
https://youtu.be/fkgTGD3jFnY?t=273
ክፍል 1
# የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥንን የአቅምዎን ይደግፉ❗️
የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ለሁሉ ያድርሱ!
ለሌሎችም ያጋሩ!
__________________
ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት!
ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ!
Wangeela Uummamtoota hundaaf lallabaa!
ንኹሉ ፍጥረት ወንጌል ስበኹ!
oo uunka oo dhan injiilka ku wacdiya!
ወንጌልድ ፍጥረታኒዝ እንቅ ሲቭቅጥኑ!
Wongellon Shijjerooch Ubba Miixebote!
ወንጌል የኽልቅ እንም ኦዶ!
Wongaliya alamiyaa ubawu oddite!
Wongeela kalaqama baalate kulle!
Wonggaliya meretetawu ubbawu taamarisite!
ወንጌልን ለፊተሪ ሰብ በሙለ አውድም!
________
# የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥንን የአቅምዎን ይደግፉ❗️
የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ለሁሉ ያድርሱ!
ለሌሎችም ያጋሩ!
__________________
ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት!
ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ!
Wangeela Uummamtoota hundaaf lallabaa!
ንኹሉ ፍጥረት ወንጌል ስበኹ!
oo uunka oo dhan injiilka ku wacdiya!
ወንጌልድ ፍጥረታኒዝ እንቅ ሲቭቅጥኑ!
Wongellon Shijjerooch Ubba Miixebote!
ወንጌል የኽልቅ እንም ኦዶ!
Wongaliya alamiyaa ubawu oddite!
Wongeela kalaqama baalate kulle!
Wonggaliya meretetawu ubbawu taamarisite!
ወንጌልን ለፊተሪ ሰብ በሙለ አውድም!
________
https://youtu.be/4-sWJZGdMl8
______________________________________
_____________________
ማኅበረ ቅዱሳን ሲናከስ አይውልም!
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ
ከማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ከአቶ ተስፋዬ ቢሆነኝ
ከዲ/ን ያረጋል አበጋዝ
ከዲ/ን ብርሃኑ አድማስ ጋር የተደረገ ቆይታ።
ዛሬ ግንቦት 6/2013 ዓ.ም
ከምሽቱ 2፡00 ጀምሮ በማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ይጠብቁ
ethiosat
frq. 11105
s/r: 45000
polarization: horizontal
"የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውን እንመሰክራለን"
__________________
_____________________________________
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ወቅታዊ ጉዳዮችን በማስመልከት #ከማኅበረ_ቅዱሳን የተሰጠ መግለጫ
ቤተ ክርስቲያን ስደት ላይ ናት!
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከ1950ዎቹ ጀምሮ ሁለንተናዊ የአስተሳሰብ ውጊያ ሲደረግባት ቆይቷል፡፡ ይህ የአስተሳሰብ ውጊያ በጊዜ ሂደት መዋቅራዊ ወደመሆን እያደገ ሄዶ አሁን ያለንበት ወቅት ላይ ደርሰናል፡፡ በነዚህ ረጅም ዓመታት ውስጥ ሲካሄድ የቆየውን ጥቃት ማሳያ የሆኑ በርካታ ክስተቶች መጥቀስ ይቻላል፡፡
ለምሳሌ ባለፉት ዓመታት በየአካባቢው የሚደረጉ የክርስቲያኖች በክርስቲያንነታቸው ተለይተው መገደል መሰደድ የአብያተ ክርስቲያናት መቃጠልና የምእመናን ሀብትና ንብረት መዘረፍ አንዱ ሲሆን የማንነትዋ መገለጫ የሆኑት ሀብቶችዋን ከዳር እስከ መሀል የመቀማትና የማጥፋት ብሎም ለሌሎች አካላትና አገልግሎቶች እንዲውሉ መደረጉ ደግሞ ሌላኛው ዓይነተኛ ማሳያ ነው፡፡
በተለይም ባለንበት ዘመን በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደረገውን ጥቃት ለየት የሚያደርገው ነጻነት፤ እኩልነት መቻቻልና እና አብሮ መኖር የሚሉ ቃላትን ሽፋን ያደረገ መሆኑ ነው፡፡ ነጻነት፤ እኩልነት እና ሌሎችን እንደራስ አድርጎ መውደድ መሠረታዊ የክርስትና አስተምህሮ እንደመሆኑ መጠን ክርስቲያኑ ይህንን ባህል አድርጎ ሲኖረው ቆይaል፡፡ በመሆኑም ሕዝበ ክርስቲያኑ እስከ አሁን ያለውን መከራና ጥቃት የሀገርን ሰላምና አንድነት በማስቀደምና በአርቆ አሳቢነት እንዲሁም ነገሮች ሊለወጡና ሊሻሻሉ ይችላሉ በሚል ተስፋ በትዕግሥት ሲያልፍ ቆይቶዋል፡፡ ሆኖም ግን ጉዳዩ ከመሻሻል ይልቅ በየቦታው ሲደረግ የነበረው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የማንነትዋ መገለጫ የሆኑ የእምነት ቦታዎች መነጠቅ እየባሰ መጥaል፡፡ ከዚህም የተነሳ በገጠር የተጀመረው ቅድስት ቤተከርስቲያን ለአደባባይ በዓላት የምትጠቀምባቸውን የአምልኮ ቦታዎች መቀማትና ለሌላ አገልግሎት መስጠት እያደገ መጥቶ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዓል የምታከብርበትን የመስቀል በዓል ማክበሪያ ቦታ ለሌላ አገልግሎት የማዋልና አሳልፎ ለመስጠት ሙከራዎች ማየት ደረጃ ላይ መድረሳችን ጥቃቱ ከፍተኛ ደረጃ ለመድረሱ ማሳያ ነው፡፡
ከዚህ ሁሉ ጋር ይዘቱ ምንም ይሁን ምን ቅዱስ ፓትርያርኩ እንደ ሰው የሚሰማቸውን ስሜትና ሀሳባቸውን መግለጽ መቻላቸው ተፈጥሮአዊ መብት ሆኖ እያለ የእርሳቸውን ንግግር ፖለቲካዊ ፍላጎትን ለማሳካት እንደ ምቹ ሁኔታ ተጠቅሞ ሲኖዶሱን ለመከፋፈልና ለማዳከም ብሎም ተÌማዊ አንድነትዋን ለማናጋት የሚደረገው ርብርብ በእጅጉ የሚያሳዝን ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
በተጨማሪም ለዚህ ቤተ ክርስቲያንን የማሳደድ ተግባር የራስዋን አካላት ለጉዳዩ መጠቀሚያ ለማድረግ የተሄደበት ርቀት ጉዳዩን በእጅጉ አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡
እነዚህን ሁሉ በአንድ ላይ ስናያቸው ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብና ለሌሎች አካላት ቀርቶ ለሁሉም ክርስቲያኖች እኩል ግልጽ ባልሆነ መንገድ ቤተ ክርስቲያን በስደት ላይ መሆንዋን ያሳያል፡፡
ስለዚህ:-
1ኛ፡ ሁላችንም ሕዝበ ክርስቲያን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከመቼውም ጊዜ በላይ በስደት ላይ መሆንዋን ተረድተን እንደ ቀደምት አባቶቻችን የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ስደት በተቀበሉበት መንገድ ለመቀበል #መዘጋጀት_አለብን፡፡
2ኛ፡ የቤተ ክርስቲያን አካላት ሆናችሁ ነገር ግን ይህንን በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን ስልታዊ እና የረቀቀ ጥቃት ባለመረዳት በተለያየ ደረጃ የችግሩ አካል በመሆን ላይ ያላችሁ ከዚህ ድርጊታችሁ #እንድትቆጠቡ እናሳስባለን፡፡
3ኛ፡ በቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት ቦታ ላይ ተቀምጣችሁ የቤተ ክርስቲያንን መብት ለማስጠበቅና ምእመናንን ለመጠበቅ የተሰጣችሁን አደራ ለጊዜያዊ ጥቅምና የፖለቲካ ፍላጎት መጠቀሚያ ያደረጋችሁ አካላት ከዚህ ድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ ማሳሰብ እንወዳለን፡፡ በተጨማሪም ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር በተያያዘ #ከቅዱስ_ሲኖዶስ_ዕውቅናና መመሪያ ውጭ እና የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ባልተከተለ መልኩ እንቅስቃሴዎችን የሚያደርጉ አካላት ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማሳሰብ እንወዳለን፡፡
4ኛ፡ ሀገር እና ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ይህንን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ እየተደረገ ያለውን የተቀናጀና የተደራጀ መገፋትና ስደት በመረዳት #ከቤተ_ክርስቲያን_ጎን እንዲቆሙ እና ችግሮቹን ለማስወገድ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡፡
5ኛ፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች #የመንግሥት _መዋቅርን ተጠቅመው ቤተ ክርስቲያናችንን በልዩ ልዩ መንገድ ሲያጠቁ ክርስቲያኖችን ሲገድሉና ሲያሳድዱ ሲያፈናቅሉ እንደነበር መንግሥት ሲገልጽ የቆየ ቢሆንም መንግሥት አንድም ጊዜ #በይፋ_ይቅርታ ጠይቆ አያውቅም፡፡ በአንጻሩ ሌሎች አካላት በቤተ ክርስቲያኒቱ ይዞታዎች ላይ ያለአግባብ ለሚያነሱት ጥያቄ መልስ ለመስጠት በሚያደርገው ሂደት ረጅም ርቀት በመሄድ ይቅርታ ሲጠይቅ ይታያል፡፡ ይህም በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለው ስደት #በመንግሥት_የሚፈጸም _ጥቃት ተደርጎ እንዲወሰድ አድርጎታል፡፡ ስለዚህም መንግሥት ቤተ ክርስቲያን ላይ ያለው ስደት እንዲቆም የማድረግ ድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡
6ኛ፡ መንግሥት ውሳኔዎችን ሲወስን አሁን እየታየ ባለው መልኩ በጩኸትና የቤተ ክርስቲያንን መብት በመግፋት ፍትሕ እያዛባ የሚሄድና በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለው ስደት እንዲቆም የማድረግ ድርሻውን የማይወጣ ከሆነ ለሚደርሰው ሰላም ማጣትና ችግር #ኃላፊነቱን_የሚወስድ መሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን፡፡
7ኛ፡ በመጨረሻም ምእመናንን ከዚህ ጉዳይ ጋር ተያይዞ የሚኖሩ ቀጣይ ሁነቶችን እየተከታተልን የምንገልጽ መሆኑን ተረድተው #በንቃት_ እንዲከታተሉ ማሳሰብ እንወዳለን፡፡
ግንቦት 3 ቀን 2013 ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን
_________________________________
"ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም" ዮሐ 15:13
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤ በሠላም አደረሳችሁ
"በአገርም በቤተ ክርስቲያንም አስጨናቂ ኹኔታ በተከሰተ ቁጥር፥ ባሕታውያን ነን በማለት ለአገርም ተጨማሪ ራስ ምታት የሚኾኑ ሰዎች እንደሚበራከቱ የቤተ ክርስቲያንንም የአገርንም ታሪክ ለሚያውቅ የተገለጠ ሐቅ ነው።
ለመኾኑ 'እውነተኞቹን ባሕታውያን ከሐሳውያኑ እንዴት መለየት ይቻላል? ብሑት ኾኖ በሰው መካከል ሲኖርስ አኗኗሩ ከሌላው በምን ይለያል?' ለሚሉ የብዙዎቻችን ጥያቄዎች መልስ የሚያገኙበት ግሩም መጽሐፍ ነው።"
ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
/የትንሿ ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ አዘጋጅና የቅዱሳት መጻሕፍት ተርጓሚ/
https://youtube.com/eotcmk
# የማኅበረ ቅዱሳን ቲቪ የዮቲውብ ቻናል ሰብስክራይብ ያድርጉ❗️
ለሌሎችም ያጋሩ! Subscribe and share!
______
ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት!
ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ!
Wangeela Uummamtoota hundaaf lallabaa!
ንኹሉ ፍጥረት ወንጌል ስበኹ!
oo uunka oo dhan injiilka ku wacdiya!
ወንጌልድ ፍጥረታኒዝ እንቅ ሲቭቅጥኑ!
Wongellon Shijjerooch Ubba Miixebote!
ወንጌል የኽልቅ እንም ኦዶ!
Wongaliya alamiyaa ubawu oddite!
Wongeela kalaqama baalate kulle!
Wonggaliya meretetawu ubbawu taamarisite!
ወንጌልን ለፊተሪ ሰብ በሙለ አውድም!
Wenigelle dada duchi'a lalabe!
Inkih tan yaalic xaaylol wangelal baarisay!
ኹሉዞሌም ወንጌል ያትኽኪሻል!
preach the gospel to every creature!
يكرز بالإنجيل لكل مخلوق.
_____________
በእንተ አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ!
አስቸኳይ እርዳታ ለአሰቦት ደብረ ወገግ ቅ/ሥላሴ እና አቡነ ሳሙኤል አንድነት ገዳም
እየደረሰ ላለው የእሳት ቃጠሎ ማጥፊያ ርብርብ ይውል ዘንድ የአቅሞን ይርዱ!
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማኅበረ ቅዱሳን አሰበ ተፈሪ ማዕከል 1000023696798 በማለት ያስገቡ።
ትላንት የሰጣችሁት ድጋፍ እቦታው ደርሷል። በርቱልን፡አስተባብሩልን ።ጻዲቁ ይስጡልን
ማኅበረ ቅዱሳን አሰበ ተፈሪ ማዕከል
ዛሬ የካቲት 30 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 4 ሰዓት ጀምሮ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ይካሄዳል።
Читать полностью…ሰበር አሳዛኝ ዜና
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ።
የከበረች በረከትዎ ትድረሰን!
Watch "#እኔምሞዐተዋሕዶነኝ/ #7ቱጥያቄዎችየኔምጥያቄዎችናቸው/ #ከየካቲት13-20ድረስብቻየሚቆይየሞዐተዋሕዶጥብቅመልዕክት" on YouTube
https://youtu.be/wp33-1SO4b8
ቤተክርስቲያንን ማሳደድ እና ክርስቲያኖች መግደል፣ ማንገላታት እና ማሰር ይቁም።
በቃን!
Nu Ga'e!
No More!
ሀገርን እየጠበቅን የቤተክርስቲያንን መብት በሁሉም ዘርፍ እናስከብራለን።
#የእቅበተ እምነት ጉባኤ ከምስራቅ
#በሐረር መካነ ሥላሴ ካቴድራል
#ከታህሳስ 08-10/2014ዓ/ም
__________________
እንቋዕ አብጽሐነ!
እንኳን አደረሰን!
ባጋ ጌሳን!
እንኳዕ ኣብፀሐና!
በወሄ አሰናነም!
ኢድ ቤጉ ነጋዲሴ!
ሃዋሌ ኢሊሽንኬ!
ወዝ ችጝዘት!
ሃሹ ሳሩዋን ጋቲስ!
ባጋ ጌኔነን!
________________
@orthoateast
ታላቅ የምስራች ከወደ ምስራቅ!
በምስራቅ ሐረርጌ ሃገረ ስብከት በሜታ እና ጎሮጉቱ ወረዳ ቤተክህነት የካራሚሌ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ህንፃ ቤተክርስቲያን #ነሐሴ_23_2013 ዓ.ም ይመረቃል!
የጉዞ መርኃ ግብር ስለተዘጋጀ ወደ ስፍራው በመጓዝ የበረከቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል!!
___________________________-
ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን!
kootaa Waaqayyoon haagammannuu!
ንዑ ብእግዚአብሔር ደስ ይበለና!
Hayite Godan Uffaytana!
Kaalay, oo aynu ku rayrreeynno Ilaah!
Come, let us rejoice in God!
____________________
@orthoateast
ታላቅ የምስራች ከወደ ምስራቅ!
በማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ማእከል አስተባባሪነት እና በበጎ አድራጊ ምእመናን አማካኝነት የተሰራው የሴይሊ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን #ሰኔ_5_2013 ዓ.ም ይመረቃል!
የጉዞ መርኃ ግብር ስለተዘጋጀ ወደ ስፍራው በመጓዝ የበረከቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል!!
___________________________-
ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን!
kootaa Waaqayyoon haagammannuu!
ንዑ ብእግዚአብሔር ደስ ይበለና!
Hayite Godan Uffaytana!
Kaalay, oo aynu ku rayrreeynno Ilaah!
Come, let us rejoice in God!
____________________
@orthoateast
_________________
ማኅበረ ቅዱሳን ሲናከስ አይውልም!
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ
ከማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ከአቶ ተስፋዬ ቢሆነኝ
ከዲ/ን ያረጋል አበጋዝ
ከዲ/ን ብርሃኑ አድማስ ጋር የተደረገ ቆይታ።
ዛሬ ግንቦት 7/2013 ዓ.ም
ከምሽቱ 2፡00 ጀምሮ በማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ይጠብቁ።
እንዲሁም ከጸሎት በኋላ ቀጣዩ ክፍል ይቀርባል።
ethiosat
frq. 11105
s/r: 45000
polarization: horizontal
YouTube https://www.youtube.com/user/EOTCMK
Telegram /channel/eotcmk
Facebook https://www.facebook.com/mahiberekidusan.mkusa/
"የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውን እንመሰክራለን"
______________
________________
እንቋዕ አብጽሐነ!
እንኳን አደረሰን!
ባጋ ጌሳን!
እንኳዕ ኣብፀሐና!
በወሄ አሰናነም!
ኢድ ቤጉ ነጋዲሴ!
ሃዋሌ ኢሊሽንኬ!
ወዝ ችጝዘት!
ሃሹ ሳሩዋን ጋቲስ!
ባጋ ጌኔነን!
_________________
@orthoateast
የተወደዳችሁ ወንድሞችና እህቶች እንኳን ለጸሎተ ሐሙስ በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ እያልን ባለፈው በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ እና አባ ሳሙኤል አንድነት ገዳም ተፈጥሮ በነበረው የእሳት ቃጠሎ ገዳሙን ለመርዳት ሁላችሁም በቻላችሁት አቅም በቁስና በገንዘብ ስትሳተፋ መቆየታችሁ ይታወሳል። በማኅበረ ቅዱሳን አሰበ ተፈሪ /ጭሮ/ማዕከል በኩል ከአባላቱ ከበጎ አድራጊዎችና ከወረዳ ማዕከላት እና አጎራባች ማእከላት በማዕከሉ አካውንትና በአካል በእጅ የገቢ ማሰባሰብ ስራ ሲሰራ መቆየቱም ይታወቃል። በዚሁ መሰረት ለገዳሙ በመጀመርያ ዙር ከሰላሳ ሺ ብር በላይ (32,075) ቁስ (ምግብ, ሩዝ,ዘይት ሽንኩርት, ውሃ, የንጽህና መጠበቂያ, ፈርስት ኤይድ ቁሶችና ወዘተ) የረዳን ሲሆን በአሁን ሰዓት ከዛ የተረፈውንና የተሰበሰበ ብር ከገዳማውያን አባቶች ጋር በመወያየት ወደ አካውንታቸው (በገዳሙ የሒሳብ ቁጥር) ሰባ ሺ ብር (70,000) አስተላልፈናል ገዳሙን በመርዳት የተሳተፋችሁ ሁላችሁንም በማዕከላችን ስም ከልብ እያመሰገንን ባወጣችሁት ሁሉ እግዚአብሔር አብዝቶ እጥፍ ድርብ አድርጎ ይስጣችሁ የነብስ ዋጋ ያድርግላችሁ! ምንጭ:-አሰበ ተፈሪ ማእከል
Читать полностью…በዕርቅ ካባ ተሸፍኖ የመለያያ ስንቅ መሰብሰብ ይብቃ!
ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን ክብርና መብት አስጠባቂ ኅብረት
ሰውን እንጂ ሁሉን ዐዋቂ የሆነውን አምላክ ማታለል አይቻልም፡፡ በጥቅምት 2013 ዓ.ም. ጉባኤው ቅዱስ ሲኖዶስ “የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ ነን” በማለት በመዋቅር ላይ መዋቅር፣ በሥርዐት ላይ ሥርዐት ለመዘርጋት የሚሯሯጡትን ሰዎች ወደ ልባቸው ይመለሳሉ በሚል አርቆ አስተዋይነት በይቅርታ የምሕረት ቤት ወደሆነች እናት ቤተ ክርስቲያናቸው እንዲመለሱ አድርጓል፡፡ እነዚህ ሰዎች ከቃላቸው ጋር ባልተጣጣመ ድርጊታቸው አስቀድመው በተገኙበት ከሐመረ ክርስትና ከሚለይ የዘረኝነት አዘቅት ራሳቸውን እንዳላወጡ እየጠራ መጥቷል፡፡ ለቤተ ክርስቲያን የሚበጃት የመለያየት ሰይፍ ይዞ የዘመተባትን ጥንተ ጠላት ደባ ከውግዘት ይልቅ በይቅርታ መርታት ነበርና ብፁዐን አበው በጊዜው የሚያስመሰግናቸው፣ በታሪክ የሚታወስ፣ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ የሚያስለብስ መንፈሳዊ ውሳኔ ነበር ያሳለፉት፡፡ ለዚሕ ሰከን ያለ ውሳኔ በሽምግልና ተግባር በጎ አሳቢ የሆኑ የቤተ ክርስቲያንን ልጆች ያደረጉት ጥረትም ስማቸውን ከታሪክ ማኅደር ባሻገር በመዝገበ ቅዱሳን የሚያስጽፍ ነበር፡፡
የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ ነበር ብሒላችን፡፡ የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደራዊና አንድነት በማፍረስ ሃይማኖታዊ አንድነታችንን ለማፈራረስ የሚያሴሩ ራሳቸውን የኦሮሚያ ቤተ ክህነትን አደራጅ በማለት የሚጠሩት አካላት ግን በሽምግልና የተደረሰበትን ስምምነት፣ በሽማግሌዎች ፊት ወደውና ፈቅደው የተስማሙበትን ቃል ለማክበር ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ በእርቅ ያገኙትን ሓላፊነት ተጠቅመው ቅዱስ ወንጌልን ለምእመናን በቋንቋቸው በማድረስ የሰማያዊ ቤት ወራሾች እንዲሆኑ የበኩላቸውን ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ትኩረት አድርጋ እየሠራችበት ለምትገኘው ኦርቶዶክሳውያንን በየቋንቋቸው ለማገልገል ለሚደረገው መንፈሳዊ ተልእኮ ተጨማሪ ጉልበት ይሆናሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡ ሰዎቹ ግን በእርቅ ያገኙትን በጎ ዕድል በመንፈሳዊነት ካባ ለሸሸጉት ምድራዊ ግባቸውን ለማስፈጸም የሚያስችል መልካም አጋጣሚ አድርገው ወስደውታል፡፡
በሽምግልናው ራሳቸውን የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ በማለት የሚጠሩት የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ወደ ቤተ ክህነት ተመልሰው በሓላፊነት እንዲመደቡ ተወስኗል፡፡ ይሕ የተደረገው የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ወደ ኦሮምኛ ተናጋሪ ልጆቿ ዘንድ በቋንቋቸው በማድረስና ምእመናንን ከነጣቂ ለመጠበቅ የሚደረገው ተልእኮ የቤተ ክርስቲያንን መዋቅራዊ አንድነት በጠበቀ መልኩ በማዕከላዊነት ለማስፈጸም በጋራ ርብርብ ለማድረግ እንዲቻል በሚል በጎ ሐሳብ ነው፡፡ ይሁንና በስምምነት ሰነዱ ላይ ከተቀመጠው በተቃራኒ በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ያገኙትን ቦታ ለልጆቿ አንድነት፣ ለመንፈሳዊ አገልግሎቷ ስኬት ከመጠቀም ይልቅ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚያውክ ተግባራቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡
ትጉሐን እረኞቻችን ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የምሥራቅ ወለጋ፣ የሆሮ ጉድሩ እና የምዕራብ ሸዋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ሔኖክ የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የእነዚህ ሰዎች ተንኮል የገነነበት እንቅስቃሴ በቤተ ክርስቲያን አሁናዊ አገልግሎት እና መጻኢ አንድነት ላይ የጋረጠውን ፈተና በግልጽ ቋንቋ በማስቀመጥ መፍትሔ እንዲፈለግ ለቤተ ክርስቲያናችን ፓትርያርክ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳሳት ዘአኩሱም፣ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በደብዳቤ ዐሳውቀዋል፡፡ ብፁዐን አባቶቻችን በደብዳቤያቸው ራሱን ኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ እያለ ሲጠራ የቆየውና ራሱን ኦሮምኛ የሚናገሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ወኪል አድርጎ ሚቆጥረው አካል በቤተ ክርስቲያኗ አገልግሎት ላይ እያሳደረ ያለውን ጫና እና እየፈጠረ ያለውን እንቅፋት ነቅሰው በማውጣት አጋልጠዋል፡፡
በእርግጥም ሰዎቹ በድርጊታቸው መጽሐፍ እንዳለ ፍቅር የሌላቸው ዕርቅን የማይሰሙ መሆናቸውን እያሳዩ ነው፡፡ የተዋሕዶ ልጅ ነን የምንል፣ ማንኛውም ምእመናን በቋንቋው ቃለ እግዚአብሔር እንዲሰበክለትና ሃይማኖቱን እንዲያጸና መንፈሳዊ ፍላጎት ያለን ሁሉ የብፁዕ አቡነ ሄኖክን እና የብፁዕ አቡነ ናትናኤልን አባታዊ ጥሪ ልንሰማ ይገባል፡፡ ስለ ኦርቶዶክሳዊ አንድነታችን የምንቀና ሁሉ የዘመኑን የዘውግ ፖለቲካ ተገን አድርጎ በሃይማኖት ካባ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር የመለያየትን ግንብ ለማቆም የሚተጋውን ቡድን እኩይ አካሔድ ልናወግዝ ይገባል፡፡ በጸሎት እና በተሰጠን ጸጋ ሁሉ ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት የበኩላችንን አስተዋጽኦ ልናደርግ የምንገደድበት ጊዜ ላይ መሆናችንን ማስተዋል ኖርብናል፡፡ ከፀሐይ በታች ለሚቀረው፣ ሰዎኛ ከሆነው ዘውገኝነት ይልቅ በክርስቶስ ላገኘነው ክርስቲያናዊ አንድነት ክብር የምንሰጥ ኦርቶዶክሳዊ እንሁን፡፡
በእንተ አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ!
_____________________
እሳቱ በገዳሙ ይዞታ ላይ ብዙ ጉዳት ካደረሰ በኋላ ገዳሙ እና ገዳማዊያኑ ላይ ጉዳት ሳያደርስ አሁን ጋብ ብሏል በሃሳባችሁ፡በጉልበታችሁ ፡በገንዘባችሁ፡ የተራዳችሁ፡ ሁላ፡ የጻዲቁን በረከት ያድልልን!
ማኅበረ ቅዱሳን አሰበ ተፈሪ ማዕከል
__________________
__________________________
የአሰቦት ገዳምን ቃጠሎ በተመለከተ በቦታው ሄደው ለማጥፋት ለሚረባረቡ ኦርቶዶክሳውያን ምግብ እና ውሃ ለማድረስ አሰበ ተፈሪ ማዕከል ገንዘብ አሰባስቦ ምግብ እና ውሃ ለማድረስ እየተንቀሳቀሰ ነው። ስለሆነም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማኅበረ ቅዱሳን አሰበ ተፈሪ ማዕከል 1000023696798 ብላችሁ አስገቡ።
ማሳሰቢያ፡-
እሳት ለማጥፋት ወደ ቦታው ለሚሄዱት ተገቢውን ግንዛቤ/orientation/ የመስጠት ስራ እና ጉዳት እንዳይደርስባቸው የማድረጉን ስራ ቸል እንዳንል።
ለሰጣችሁ ሁሉ የጻዲቁን ዋጋ ይስጥልን
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!!
_____________________________