orthoateast | Unsorted

Telegram-канал orthoateast - ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

-

ይህ ቻናል በምሥራቅ ኢትዮጵያ ስለምትገኘው ቅድስት ቤተክርስቲያን እና ልጆቿ መረጃ እና ዘገባ የምናደርስበት ነው።

Subscribe to a channel

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

ያልጠበቅነው ዜና
ከምሥራቅ ኢትዮጵያ ከሱማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማ ሙስጠፌ ከሚመራው እንዲህ ይሆናል ብለን አልጠበቅንም ነበር። የሆነው ግን ምዕመናን ወደ ቤተክርስቲያን ገብተው ምህላ እንዳያደርሱ የጸጥታ ሥጋት ነው በሚል በጸጥታ አካላት ተከልክለዋል
ቀጣዩ ምን እንደሚሆን እናሳውቃችኋለን።

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

ምዕራብ ሐረርጌ አሰበ ተፈሪ (ጭሮ) ከተማ ኦርቶዶክሳዊያን ላይ ጫና እያሳደረ ያለው የካቢኔ አባል ይህ jemal Abrahim ነው። FB ገብታችሁ አናግሩት አቁም በሉት
ስሙ ከላይ አለ

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

አሁናዊ የአሰበ ተፈሪ(ጭሮ) ዜና
ሕዝበ ክርሰቲያን በጸጥታ ሃይል ጭስ ከተጣለባቸው በኋላ የክልሉ ልዩ ሃይል የቤተክርስቲያን በር ሰብረው በመግባት እና የቤተክርስቲያን አዳራሽ በድንጋይ በመሰባበር ሕዝቡን ከቤተክርስቲያን አስወጥተዋቸዋል። አሁን ለይ ሕዝቡን በመሳሪያ እያሳደዱ ይገኛሉ።
ሕገ ወጡን ቡድን ካረፉቀት ሆቴል ለማስገባት ዝግጅት ላይ መሆናቸው ተሰምቷል።

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

#stop_orthodoxGenocide_inEthiopia በአሁን ሰዓት የምእራብ ሐረርጌና የጭሮ(አሰበ ተፈሪ)ከተማ የመንግስት አካላት ከአባቶች ጋር  ተወያይተዋል።
በዉይይቱም መሰረት ህገ ወጡ ቡድኖች ከተማዋን ለቀዉ እንዲሄዱና ህዝቡ በሰላም ወደ ቤታቸዉ እንዲገቡ ተስማምተዋል።
ህዝበ ክርስቲያኑ ግን ከከተማዉ መዉጣታቸዉን ሳናረጋግጥ አንገባም ብለዉ በቤተክርስቲያን ፀንተዉ ቆይቷል።

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

የጴጥሮሳውያን ዘምስራቅ ሐረርጌ "ጥብቅ ማሳሰቢያ"- ለመንግሥት አሁንም ህግን እንዲያስከብር ለህገወጦቹ ደግሞ የቤተክርስቲያን አባቶችን ከማዋከብ እንዲታቀቡ በድጋሚ አሳስቧል

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

ምሥራቅ ሃረርጌ ሀገረስብከት"ሐረር ቅዱስ ሚካኤል ወሩፋኤል" የምህላ ጸሎት እና የቤተክርስቲያን ሉአላዊነት የተሰበከበት ጉባኤ
_________________________
ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንተ ላእለ ኲሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት!
#ቤተ ክርስቲያን አሐቲ

ከሁሉም በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሠሯት በአንዲት ክብርት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን!
#ቤተ ክርስቲያን አንዲት ናት

Hundaa ool kan taate duka bu'oonni kan hundeesan mana amantaa tokkittiin ni amanaa!
#Mani amantaa tokkittidha!

ካብ ኩሉ ንላዕሊ ብዝኾነት ሐዋርያት ብዝሃነፅዋ ብሓንቲ ኽብሪቲ ቤተክርስቲያን ንኣምን!!
#ቤተክርስቲያን ሓንቲ እያ

ኡብዬ በሾ ቱኔም ወችየችናኦና ሹኔት እከ ኦገት ባሬ ከጥና ግበነሆን!
#ባሬከጥ እኬነ

Baalu alee ikkitinotenni Hawariyate loossinottenni mitte ayirado qulawa betekirisitaanenni ammaneemo!
#Betekirisitaane mittete!

Waxaas oo dhan ka sii sarreeya, waxaan aaminsanahay kaniisad ammaanta leh oo rasuulladu ay dhiseen!
#Kaniisadu_waa_mid

ትንም በረን በኽረ ሐዋረርያት በቶተዊ ብማት ንቅ በኽረ ቤተክርስትያን ናምነ!
#ቤተክርስቲያን እማትያ

ubbappe bolla adhidayisan hawariyatetti ottidayisan issi bonchettida bataskannen ammanos!
#Bataskkaniya issinno

ንቅት ንየ አረይ ሐዋርያት ሰራሽጘይ ላይ ኪብርሽረይ ምከንስ አምነኩን
#ምከን ላይ ጚ

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

አስቸኳይ መልእክት!!!
Ergaa Hatantamaa!!!

በሁሉም የሃገሪቱ ክፍል ያላችሁ የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ልጆች በየአከባቢያችሁ ተደራጅታችሁ አቢያተ ክርስቲያናትን እንድትጠብቁ በእግዚአብሔር ስም ለማሰሰብ እንወዳለን።ይህንን የምንለው የምንሰማቸው ጭምጭምታዎች ስላሉ ነው።ይህንን መረጃ ላልሰሙት ወገኖቻችን በማሰማት መንፈሳዊ ግዴታችንን እንወጣ።ወገኖቻችን ሆይ እንበርታ፣እንጸልይ ፣ተባብረንም እንሥራ!!!

ሰማዕትነት አያምልጠን!!!

Kutaa Biyyaatti hundumaa keessa kan jiraattan ijoollee Ortodooksi Tawaahidoo Kan taatan Bakka Jirtaan hundatti gurmooftanii mana kiristaanaa keessan akka eegdan maqaa waaqayyootiin isin beeksisee barbaadina.kana kan jennu odeeffannoowwan gara gara dhagahamaa waan jiraaniif.
warroota odeeffannoo kana hin dhageenye dhageessisuun dirqama Ortodoksummaa Keenya akka bahannu.Aantoota Keenya haa jabaannu!kadhannaadhanis haa jabannu!tokkummaan gurmaa'uunis haa hojjennu.

~Mana Kiristaanaa Tokkitti=  kan Itoophiyaa Ortodoksi Tawaahidoo!!!

TeessooTokko=kan Itoophiyaa Ortodoksi Tawaahidoo!

Paatriyaarkii Tokko=Abbaa Keenya Qulqulluu Maatiyaas!!!
Biyya Tokkitti=Itoophiyaa!!!


         waereegamni nu jala hin darbiin!!!

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

በሶማሌ ሀ/ስብከት በጅግጅጋ ደብረ ሰዋሰው ቅድስት አርሴማ ገዳም በማኀበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት የተገነባው የአብነት ት/ቤት ፕሮጀክት ተመረቀ።

በማኅበረ ቅዱሳን የአብነት ት/ቤቶች ባልተስፋፉባቸውና የአገልጋይ እጥረት ባሉባቸው አካባቢዎች በሚከናወነው የአብነት ት/ቤቶች ማስፋፊያ መርሐ ግብር አካል የሆነው የጅግጅጋ ደ/ሰዋሰው ቅድስት አርሴማ ገዳም የአብነት ትምህርት ቤት ፕሮጀክት የሶማሌና የምሥራቅ ሐረርጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ፣የሀገረ ስብከቱ ዋና ስራ አስኪያጅ እና ልዩ ልዩ የሀ/ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ፣ጥሪ የተደረገላቸው የጅግጅጋ ከተማ ምእመናን በተገኙበት ህዳር 11 ቀን 2015 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ተመርቋል።

የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ማኅበረ ቅዱሳን የቤተክርስቲያንን አገልግሎት ለማገዝ ሰፊ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጸው ይህ ዛሬ የተመረቀው ፕሮጀክት የአካባቢውን ባህልና ቋንቋ የተረዱ ተተኪ አገልጋይ ካህናትና ዲቆናትን ለማፍራት አስፈላጊነቱ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል። ብፁዕነታቸው አያይዘውም ምእመናን የአብነት ትምህርት ቤት ፕሮጀክቶችን በዕውቀትና በገንዘብ ከመደገፍቸው በተጨማሪ ልጆቻቸውን ወደ አብነት ትምህርት ቤቶች በመላክ የቤተ ክርስቲያንና የሀገር ታማኝ አገልጋይ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚገባ በማሳሰብ የአብነት ትምህርት በመማር የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ከመሆናቸው በተጨማሪ በጥሩ ሥነ ምግባር የታነጹ እንደሚሆኑም አስረድተዋል፡፡

የማኅበረ ቅዱሳን ምክትል ዋና ጸሐፊ ዲ/ን አንድነት ተፈራ በመልእክታቸው ማኅበረ ቅዱሳን ባለፉት ዓመታት ገዳማትንና አብነት ት/ቤቶችን ለማጠናከርና ለማስፋፋት ከ 156 በላይ ፕሮጀክቶችን በገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ላይ መተግበሩን በመግለጽ ይህም ፕሮጀክት ተተኪ አገልጋዮችን በማፍራት በአካባቢው የሐዋርያዊ ተልእኮን ለማስፋፋት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ በመልእክታቸው አንስተው የአብነት ትምህርት ቤቶች ባልተስፋፋባቸው አካባቢዎች ማኅበረ ቅዱሳን አዳዲስ ጉባኤ ቤቶችን በመሥራት በአካባቢው ቋንቋ የሚያገለግሉ ካህናትና ዲያቆናትን ማፍራት እንደተቻለ አስገንዝበው በዚህም የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትን ማስከፈትና ከቤተ ክርስቲያን የወጡ ምእመናንን መመለስ እንደተቻለም ገልጸዋል፡፡

የሶማሌ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ መዊዕ ቆሞስ አባ ጽጌ ደስታ በበኩላቸው የአብነት ትምህርት ቤቶች መስፋፋት ተተኪ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን ለማፍራት የላቀ ድርሻ እንዳላቸው ጠቁመው ተተኪ የቤተ ክርስቲያን አገልገዮችን ማፍራት ካልተቻለ ግን የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ጥያቄ ውስጥ ሊገባ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ ደረጃቸውን የጠበቁ የአብነት ትምህርት ቤቶችንም ማስፋፋት ከዚህ ቀደም በአብነት ትምህርት ቤቶች የነበሩ ችግሮችን ለመቅረፍ የላቀ ድርሻ እንደሚኖራቸው ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ወጭ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ በሚገኙ ምእመናን ድጋፍ የተገኘ ሲሆን በአሜሪካ ሀገር ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኙ ምእመናን ፕሮጀክቱ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛውን አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ተገልጿል።
______________________________
ምንጭ፡-ማኅበረ ቅዱሳን

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

#ማኅበረ ቅዱሳን 30ኛ ዓመት 15ኛውን ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ።

#የሁለት ዓመት(2013-14ዓ/ም)  ክንውን የቀረበ ሲሆን

#አጠቃላይ 80,317 አዳዳሲ ምዕመናን ከሀገረ ውስጥ የቅድስት ሥላሴ ልጅነት ያገጁ ሲሆን 55 የሚሆኑ ከኢትዮጵያ ውጪ የሥላሴ ልጅነት አግኝተዋል።

#በግቢ ጉባኤያት ዙሪያ 55ሺ ተማሪዎችን በዚህ ሁለት ዓመት ብቻ በአባቶች ቡራኬ በቅድስት ቤ/ን አስመርቋል።

#እንዲሁም ሌሎች መጠነ ሰፊ የቤተክርስቲያንን አገልግሎት እንዳከናወነ ያገኘነው ማስረጃ ያመለክታል።

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

በመምህር #ፋንታሁን_ዋቄ የተዘጋጀው "ሥዝም ሰብአዊነት" መጽሐፍ በገበያ ላይ ውሏል

ዋና አከፋፋይ፦ ሀሁ መጻሕፍት መደብር

አድራሻ ፦
1 ስታድየም ናሽናል ታወር ግራውንድ ፍሎር
2 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ሕንጻ

ስ.ቁ 0911006705/0924408461

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

https://youtu.be/Tz39UygKgIk?t=4889

የምናውቀውን እንናገራለን፥ ያየነውን እንመሰክራለን!
ይስሙ :ያሰሙ
ሰብስክራይብ ያድርጉ ለሌሎችም ያጋሩ!
subscribe and share!

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

#ከወቅታዊ ጉዳይ ጋር ተያይዞ የማህበራቱ ህብረት መግለጫ አውጥተዋል

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

#ጥንቃቄ/ofeganno!

#የነገ አርብ /ጁምዐ/ ወደ መስጊድ ሲሄዱ ተቃውሞ ሊያሰሙ ወይም ጥቃት ሊያደርሱ ስለሚችሉ፦

#በሐረር

#በድሬደዋ

#በጅግጅጋ

#በጭሮ

#የምትገኙ ኦርቶዶክሳዊያን ቅድስት ቤተክርስቲያናችሁን እና እራሳችሁን እንድትጠብቁ ዘንድ ጥሪ እናስተላልፋለን!

#waaqayyoo nagaa isaa nuuf ha erguu!

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

"በዚያም በዓል የለመኑትን አንድ እስረኛ ይፈታላቸው ነበር። በዓመፅም ነፍስ ከገደሉት ከዓመፀኞች ጋር የታሰረ በርባን የተባለ ነበረ። ሕዝቡም ወጥተው እንደ ልማዱ ያደርግላቸው ዘንድ እየጮኹ ይለምኑት ጀመር። ጲላጦስም የአይሁድን ንጉሥ እፈታላችሁ ዘንድ ትወዳላችሁን? ብሎ መለሰላቸው፤ የካህናት አለቆች በቅንዓት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና። የካህናት አለቆች ግን በርባንን በእርሱ ፈንታ ይፈታላቸው ዘንድ ሕዝቡን አወኩአቸው። ጲላጦስም ዳግመኛ መልሶ። እንግዲህ የአይሁድ ንጉሥ የምትሉትን ምን ላደርገው ትወዳላችሁ? አላቸው። እነርሱም ዳግመኛ 'ስቀለው' እያሉ ጮኹ።"
ማር ፲፭÷፮-፲፫

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

https://youtu.be/CSjpg21mHdA

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

የነነዌ ጾም ሥርዓተ ጸሎት መርሐ ግብር

ምንጭ: EOTC TV

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

አስቸኳይ መረጃ፡፡፡
በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በጭሮ ከተማ  በሕገ ወጥ የተሾሙት አካላት  በጥር 27/2015 ዓ/ም እንደሚመጡ በቂ መረጃ ለሕቡ ሰለደረሰ ምዕመናን ቤተ ክርስቲያናቸውን  ከሕገ ወጦች ወረራ በንቃት እንዲጠብቁ ብሎ ቅዱስ ሲኖዶስ  ባስተላለፈው መመሪያ መሠረት የጭሮ ከተማ ሕዝበ ክርስቲያን በከተማው የሚገኙትን 4 አብያተ ክርስቲያናት በንቃት እየጠበቀ መዋ ይታወቃል፡፡
ከቀኑ 11፡45 ስዓት ላይ የተፈጠረ
1, የመጡት ሕገወጥ ቡድን መንግስት አንሄድም ሲሉት ሙሉ ወጪ ችሎ ከብሽ አልጋinternational ይዞ እንዲያድሩ ካደረገ በኋላ 10 የማይሞሉ ዱላ ይዘው እየዘፈኑ በመጡ ምክንያት ቤተክርስቲያ እየጠበቁ ባሉት ላይ ተኩስ ተከፈተ, በተኩስና አስለቃሽ ጭስ እስከ 2ስዓት ምዕመናን አሰቃዩን፡፡
2, ከተረጋጋ በኋላ በጀርባ ሙሉ ከበው ህዝቡን በተኩስና አስለቃሽ ጭስ, በሰደፍ በዱላ እያሰቃዩ ሙሉ ህዝቡን እንዳስወጡና የሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ, አንዳንድ የመምሪያ ሓላፊና ሞታችን በልደታ ብለው ግቢ ውስጥ እንደቀሩ አይተናል አባቶቻችንን በጸሎት አስቦቸው፡፡
3,  ከምሽቱ 4ስዓት በደረሰን መረጃ ቤተክርስቲያን ማን እንደሚገባ መመሪያ ከመንግስት እንጠብቃለን እንዳሉ እና 5ስዓት ላይ ከሆቴል ጠርተው ካሃዲውን ሕገወጢን እንዳስገቡ ተሰምቶል፡፡
4, የጸጥታ እና የመንግስት አካላት ዛሬ እሁድ 4ስዓት ንብረት እስረክቡ ብለው አባቶችን እያስገደዱ ነው ያሉት፡፡
5, ህዝቡ/ምዕመኑ አሁንም ዝም እንደማይል እንዲታወቅልን ... ሲሉ ጥሪ አቅረበዋል።
ሰላም ለቤተ ክርስቲያን !!!
ሰላም ለኢትዮጵያ !!!!

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

        †      

ሰበር ❗️

ቅዱስ ሲኖዶስ ሰላማዊ ሰልፍ ዐወጀ !

በቤተ ክርስቲያን ላይ የተጀመረው አደጋ እየቀጠለ ስለኾነ በመስቀል ዐደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወሥኗል።

የሰልፉ ቀን የካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም. ነው።

የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም !

              †   †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

Dargaggoonnii Mana isaanii eeggachaa jiru.
ወጣቶቹ ቤታቸዉን እየጠበቁ ነዉ።
Mana Kiristaana Qulqulleettii Lidataa Lamaariyaamii Ciroo yeroo ammaa.
የጭሮ(አሰበተፈሪ) ቅ/ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን በአሁን ሰዓት።
kan hin dammaqne Dammaqi!
ያልነቃህ ንቃ።

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

https://youtu.be/ln_T11WTGnU

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

Waldaan Qulqullootaa Wiirtuu Olaana Wiirtuulee Ciroo fi Harar waliin  ta'uun  Kutaalee lallaba Harargee Lixaa fi Harargee bahaarraa Kan walitti dhufan barsiisota Wangeelaa baay'inaan 48 ta'aniif Magaalaa Cirootti  leenjii Kennaa jira. Leenjiin kun guyyoota 12'f itti fufaa jedhameera.

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

4. በዚህ ጸረ ቤተ ክርስቲያን እና ኢ-ቀኖናዊ ድርጊት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ እየኖሩ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ወይም በቦታው በመገኘት የጥፋት ድርጊቱ ተባባሪ የሆኑ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በሥራ ላይ የሚገኙ ሠራተኞችን በተመለከተ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተገቢውን ክትትልና አስተዳደራዊ ውሳኔ እንዲሰጥ፤

5. ይህን ታሪክ ይቅር የማይለውን ሕገ ወጥ አድራጎት እና የቀኖና ጥሰት በሐሳብ፤ በገንዘብ እና በሌላ በማንኛውም ሁኔታ ድጋፍ ሲያደርጉ የቆዩ እና በማድረግ ላይ ያሉ ማናቸውም ተቋማት እና ግለሰቦች ከዚህ ሕገ ወጥ አድራጎታቸው እንዲቆጠቡ ቅዱስ ሲኖዶስ በጥብቅ እያሳሰበ ይህ ባይሆን በሕግ አግባብ ተገቢው እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

6. በየደረጃው የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥራ ኃላፊዎች፤ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ መነኮሳት፤ አገልጋይ ካህናት፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፤ ልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ ማህበራት እና ምእመናን እና ምእመናት ይህን ሕገ ወጥ አድራጎት ከመከላከል እና የቤተ ክርስቲያናችሁን ደህንነት ከመጠበቅ በተጨማሪ ለዚህ ሕገ ወጥ አድራጎት ልዩ ልዩ ድጋፍ የሚያደረግ ተቋማት እና ግለሰቦችን አስፈላጊውን ክትትል እና ቁጥጥር በማድረግ የመከላከል ሥራችሁን እንድትወጡ ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

7. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስምን ከፊትም ሆነ ከኃላ በመጨመር እና በመቀነስ በከፊልም ሆነ በሙሉ መጠቀም፤ ዓርማዋን፤ አድራሻዋን፤የአምልኮ እና የሥርዓት መፈጸሚያ የሆኑ ንዋያ ቅዱሳትንና አልባሳት እንዲሁም መጻሕፍት መገልገል የማይችሉ መሆኑ ታውቆ ይህንን ጉዳይ በየደረጃው ያሉ መንግሥታዊ አካላት እና የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥራ ኃላፊዎች ተከታትለው እንዲያስፈጽሙ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነ ሲሆን በተጨማሪም ይህን ውሳኔ ተላልፈው በሚገኙ ማናቸውም ግለሰቦች እና ተቋማት ላይ ተገቢውን ሕግ አግባብ ተከትሎ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ዓለማት የሚያስፈጽም ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የሕግ ባለሙያዎች በመመደብ ተገቢውን ሁሉ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በኩል እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

8. አሁን የተከሰተውን ችግር አስመልክቶ ዝርዝር ጥናት እና የመፍትሔ ሐሳብ የሚያቀርብ አንድ ዐቢይ ኮሚቴ በቋሚ ሲኖዶስ እንዲሰየም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

9. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ያሳለፈውን ውሳኔ ከክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጀምሮ በየደረጃው ላሉት የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች እንዲከናወኑ እና ይህ ውሳኔ ከሸኚ ደብዳቤ ጋር እንዲደርሳቸው ተወስኗል፡፡

10. ይህን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ውሳኔ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ክፍለ ዓለማት ለሚገኙ የቤተ ክርስቲኒቱ አገልጋዮች እና ምእመናን የግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄ መድረኮች እንዲካሔዱ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ በማእከል የአህጉረ ስብከት ሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ታላቅ የንቅናቄ እና የግንዛቤ መድረክ እንዲከናወን ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

11. በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የሚገኙ መንግስታዊም ሆነ መነግስታዊ ያልሆነ ተቋማት፤ አኃት አቢያተ ክርስቲያናት፤ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት፤ የሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እና ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት፤ የዓለም አቢያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት፤ የመላው አፍሪካ አብያት ክርስቲያናት ጉባዔ እና ሌሎች የአብያተ ክርስቲያናት እና የሃይማኖት ጉባኤዎች በሙሉ እነዚህ የተወገዙት ግለሰቦች የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ እና ምንም አይነት የሥራ ግንኙነት የሌላቸው መሆኑ ታውቆ ማናቸውም ግንኙነት በቤተ ክርስቲያኑቱ ስም እንዳያደርጉ በጽሑፍ አንዲገለጽ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

12. እነዚህ ግለሰቦች ከሚሰጡት የተሳሳተ መረጃ አንዱ እኩይ ተግባራቸው የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ እንደሆነ ማስመሰል ሲሆን ይኽ ተግባር ሃይማኖቱን የሚወድ፣ አባቶቹን የሚያከብር እና አስተዋይ የሆነውን የኦሮሞ ሕዝብ የማይወክል፣ የራሳቸውን የሥልጣን ጥማት ለማርካት ያደረጉት ሕገወጥ የቀኖና ጥሰት መሆኑ እንዲታወቅ፤ በተጨማሪም ለሚያሠራጩት የሐሰት አሉባልታ ወደፊት ተገቢው መልስ እንዲሰጥበት ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤

እስከ አሁን ድረስ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጎን በመሆን አጋርነታችሁን ያሳያችሁ፣ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት እና ሉዐላዊነት መከበር የበኩላችሁን በመወጣት መግለጫ የሰጣችሁ ሁሉ በልዑል እግዚአብሔር ስም እያመሰገንን ለወደፊቱም በጸሎታችሁ እና በመልካም አጋርነታችሁ ከጎናችን እንድትሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
ጥር 18 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ምንጭ: የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

ክርስቲያኑ በጅምላ እየታረደና እየተሰደደ ዝም ይላል። ወንድሞቻችን ግን "የአረብ ስም አገሩን ወሰደ" ለሚለው የሽመልስ ንግግር ተቆጥቷል። ራሱን ማስከበር መማር ይገባል። ክርስቲያኑ ግን ብሔር እየቆጠረ ክርስቶስን በመርሳቱ፣ አባቶችም ሰው እያለቀ ስለ ሕንፃ ግንባታ፣ ስለ ሰዎች ከቦታ ቦታ መቀየር፣ ስለ ውስጥ የምሥጢራት መፈጸሚያና በዜና መነገር ያልነበራባቸው ነገሮች አጀንዳ ሲያደርጉ፣ አንዳንዶች ደግሞ ንቅናቄዎችን ሲቃወሙና ለመቆጣጠር ሲሯሯጡ መታየቱ የምን አዚም ይሆን https://youtu.be/qeAPuzUYpg0

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

√ማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ማእከል የተቀናጃ የህክምና አገልግሎት በምስራቅ ኢትዮጵያ በሚገኘው በአሰቦት ቅድስት ሥላሴ እና አቡነ ሳሙኤል አንድነት ገዳም ውስጥ ለሚገኙ መነኮሳት እየሰጠ ይገኛል።

√ማኅበረ ቅዱሳን እንደ ቀድሞው ሁሉ ዛሬም የልጅነት ሥራ ለቅድስት ቤተክርስቲያን በተለያዩ ዘርፎች እየከወነ የሚገኝ የቅድስት ቤተክርስቲያናችን ልጅ በመሆኑ ሥራው ሊበረታታ እና ሊታገዝ ይገባል!

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

‹‹ጌታችን በመለከት ድምጽ ዐረገ›› (መዝ. ፵፮፥፭)
ነቢዩ ዳዊት አስቀድሞ በመንፈሰ ትንቢት ‹‹አምላካችን በዕልልታ፥ ጌታችንም በመለከት ድምጽ ዐረገ፥ ዘምሩ፥ ለአምላካችን ዘምሩ፤ ዘምሩ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ›› በማለት እንደተናገረ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራውን ፈጽሞ ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ በዐርባኛው ቀን ዐርጓል።
በዕርገቱም ዕለት ሐዋርያት በተሰበሰቡበት እንዲህ አላቸው፤ ‹‹እነሆ፥ እኔ የአባቴን ተስፋ ለእናንት እልካለሁ፤ እናንተ ግን ከአርያም ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ተቀመጡ፡፡›› ከዚያም እስከ ቢታንያ አውራጃ መውጫ ድረስ ወሰዳቸውና ባረካቸው፡፡ እየራቃቸውም ሄደ፤ በደመናም ወደ ሰማይም ዐረገ፡፡ በአባቱ ቀኝም ተቀመጠ፤ ሐዋርያቱም ሰገዱለት፤ እጅግም ደስ ብሏቸው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፡፡ አምላካቸውን እግዚአብሔርንም ዘወትር በምስጋና ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡ (ሉቃ ፳፬፥፵፱-፶፪፣ማር፲፮፥፲፱)
እንኳን አደረሳችሁ!

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

#እንኳን ለ30ኛ ዓመት የማኅበረ ቅዱሳን የምሥረታ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

#በፅንፈኛው_ኃይል_ጥቃት_የደረሰባቸው_የወራቤ_ዩኒቨርስቲ_ግቢ_ጉባኤ_ተማሪዎች_የተሟለ_ህክምና_ያስፈልጓችዋል!

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

____________
እንቋዕ አብጽሐነ!

እንኳን አደረሰን!

ባጋ ጌሳን!

እንኳዕ ኣብፀሐና!

በወሄ አሰናነም!

ኢድ ቤጉ ነጋዲሴ!

ሃዋሌ ኢሊሽንኬ!

ወዝ ችጝዘት!

ሃሹ ሳሩዋን ጋቲስ!

ባጋ ጌኔነን!
_____________
@orthoateast

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

በመምህር #ፋንታሁን_ዋቄ የተዘጋጀው "ኦርቶዶክሳዊነት እና የሰይጣን መንግሥት" መጽሐፍ የፊታችን አርብ በገበያ ላይ ይውላል

መጽሐፉን ለማግኘት

ኢትዮ ፋጎስ መጽሐፍ ማእከል ይምጡ ይደውሉ

#አድራሻ፦ 4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ሕንጻ ውስጥ የቤት ቁጥር 0-03
#ስልክ፦ 0911456866
___________________

Читать полностью…

ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ-Gara Bahaatti Ilaalaa

"የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ ልብ አድርገህ ተመልከት"

Читать полностью…
Subscribe to a channel