ይህ ቻናል በምሥራቅ ኢትዮጵያ ስለምትገኘው ቅድስት ቤተክርስቲያን እና ልጆቿ መረጃ እና ዘገባ የምናደርስበት ነው።
#ሀገረ ስብከቱ ተደጋጋሚ ቅሬታዎችን ለሚመለከተው የመንግስት መዋቅር ቢያቀርብም መልስ እስካሁን አለተገኘም።
#ተገቢውን መልስ ያላገኘቺው ቅድስት ቤተክርስቲያን ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ ፍርድ ቤቱ ግዚያዊ እገዳ ቢያደርግም ቦታውን ለሌላ ግንባታ የፈለገው የመንግስት አካል ሥራውን ሊያቆም አልቻለም።
#የቦታው ይዞታ፦የሐረር መካነ ሥላሴ ካቴድራል ነው።
#የሚገኝበት ቦታ፦ በተለምዶ ካናል እንቁላል ፋብሪካ
የመንግስት እና የሃይማኖት ግንኙነት በአግባቡ ይሁን!!!
Читать полностью…ሊንኩ ካልከፈተላችሁ PDF አያይዘንላችኋል። ለሌሎችም አዳርሱ
Читать полностью…በመንግሥት መዋቅር ደረጃ እንዲህ ኦርቶዶክሳዊያንን ለማጽዳት ቅስቀሳ እያደረጉ ስለሆነ ሁሉም በያለበት በማስተዋል መንቀሳቀስ አለበት
Читать полностью…#ማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ማእከል በምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ገቢ እያሰባሰበ ይገኛል።
#የዚህ መርኃ ግብር ዋና ዓለማው በምስራቅ ሐረርጌ በተለያዩ ወረደ ቤተክህነት ሥር ለሚገኙ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤያትን ማካሄድ፤አዳዲስ የስብከተ ኬላዎችን ማስፋፋት፤እንዲሁም ሐዋርያዊ ጉዞ ማድረግ ነው።
#ይሄንን መርኃ ግብር እንድታስተባብሩ በገጠሪቷ ቤተክርስቲያን ስም አደራ ስንላችሁ ረድኤተ እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግ ነው!
እንኳን ለ20ኛው ጠቅላላ ጉባኤያችሁ በሠላም አደረሳችሁ!
Читать полностью…እኔ የተዋሕዶ ድምጽ ነኝ!
ኣነ ናይ ተዋህዶ ድምፂ እየ!
Anis Sagalee Tawaahidooti!
ታኒ ተዋሕዶስ ጨንጉርሳ!
Ani tewahido qaaleti!
ያን ተዋሕዶቱ ድመ የጝ!
Taani Tewahido gaanna!
እያ የተዋሕዶ ቃርንሑ!
https://youtu.be/qIVsATUQ6rY
እንዳያመልጣችሁ።
ለሌላውም አዳርሱ
#stop_orthodoxGenocide_inEthiopia
ብፁዕ አባታችን አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘ አክሱም ወጨጌ ዘ መንበረ ተክለ ሃይማኖት:ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አባቶቻችን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የወሰናችሁትን ውሳኔ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እና መሸራረፍ የምንቀበል የምንፈፅም እና የምናስፈፅም መሆኑን በትህትና እንገልፃለን --------
@orthoateast
የቀጥታ ስርጭት የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ በማኅበረ ቅዱሳን ቴቪ : በፌስቡክ https://fb.watch/iCWiMCftrl/ እና በEotc ዩቲውብ https://youtube.com/live/t4BNPgDVsu8?feature=shares በማኅበረ ቅዱሳን https://www.youtube.com/live/c555JhtNIBs?feature=share
Читать полностью…በሕገ ወጡ ሹመት ላይ የተሳተፉ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳትና ግለሰቦች ከዛሬ የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት እንዳይገቡ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አግዷል።
ዛሬ በነበረው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀጠሮ የሕግ አማካሪዎች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም ሹመት የሰጡት በቀድሞ ስማቸው “አባ ኤዎስጣቴዎስ”፣ “አባ ዜና ማርቆስ”፣ “አባ ሳዊሮስ” እና እነርሱ በሕገ ወጥ መልኩ ሾመናችኋል ብለው ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ውጪ አስኬማ ያቀዳጇቸው 25 ግለሰቦች እንዲሁም አቶ ኃይለ ሚካኤል ታደሰ የተባሉ ግለሰብ በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 156 መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግቢ እንዳይገኙ በጊዜያዊነት አግዷቸዋል። ይህንን እግድ የተላለፈ ማንኛውም አካል የወንጀል ተጠያቂነት ይኖርበታል። በሀገሪቱ የሚገኙ የሕግ አስፈጻሚ አካላት እግዱን እንዲያስፈጽሙ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። ቤተ ክርስቲያኗ በቀጣይ በሰብአዊ መብት፣ በአስተዳደር፣ በወንጀልና በፍትሐ ብሔር ለደረሰው ኪሣራ ተጠያቂዎችን በመለየት በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት በሕግ ትጠይቃለች።
በዚህም በሕገ ወጡ ሹመት ላይ የተሳተፉ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳትና ግለሰቦች ከዛሬ የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት እንዳይገቡ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አግዷል።
https://www.youtube.com/live/Tu1c6OKlN3U?feature=share
Читать полностью…ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት የውይይታቸውን ውጤት በይፋዊ መግለጫ እስኪያሳውቁ ድርስ እንደተለመደው በትህትና እና በትእግስት እንጠብቅ::
@orthoateast
https://www.youtube.com/live/13MBP4QrczY?feature=share
Читать полностью…#stop_orthodoxGenocide_inEthiopia
የጴጥሮሳውያን ዘምሥራቅ ሃረርጌ አስቸኳይ ማሳሰቢያ:-
የማኅበራት ኅብረቱ በሃረሪ ክልል እና በምሥራቅ ሃረርጌ ዞን በአንዳንድ የመንግስት ቢሮዎች በኦርቶዶክሳዊያን አለባበስ ላይ የሚደረገውን ማዋከብ እና ማስፈራራትን ህገ ወጥ ተግባር ሲል ገልፆታል :: መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ከሚገባ ህግ ቢያስከብር የተሻለ ነው::
https://www.youtube.com/live/W5Pcegye1Cs?feature=shared
Читать полностью…ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያን ህልውና በላይ የሚያስቀድመው አንዳች ነገር የሌለ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የገጠማትን ፈተና ለማለፍ የሚጠበቅበትን መንፈሳዊ ግዴታ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ዛሬ የካቲት 19/2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።
ማኅበሩ በመግለጫው የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን መንፈሳዊ አንድነት የጠየቀ ሲሆን "ቤተ ክርስቲያንን በማይጠቅማት ጉዳይ የግል ፍላጎትንና ምድራዊ ዓላማን መሠረት አድርገው ከቤተ ክርስቲያን ሕግና ቀኖና ውጭ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊን ለመተካት፣ ፓትርያርክ ለመሾምና የመሳሰሉትን ለመፈጸም" የሚንቀሳቀሱ ያላቸውን "አንዳንድ አባቶች" ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በማሳሰብ ጉዳዩንም በመከታተል መረጃውን ለምእመናን አደርሳለሁ ብሏል።፡፡
ይመለከታቸዋል ላላው ሌሎች የቤተ ክርስቲያን አካለትም ጥሪውን አስተላልፏል።
በሐረር ከተማ የምትገኙ ወንድም እህቶች በዚህ መርኃ ግብር ብትገኙ
Читать полностью…* ይህንን መልእክት ለሁሉም ኦርቶዶክሳውያን በመላክ የድርሻችንን እንወጣ **
8ኛ ዙር የውይይት መድርክ
"በኢትዮጵያ የሚደረጉ ጦርነቶች በቤተ ክርስቲያን ላይ ለምን ያነጣጠሩ ሆኑ? " በሚል ርእስ
ቅዳሜ ጥቅምት 17 2016 ከምሽቱ 2 ሰዓት በኢትዮጵያ/ Saturday October 28 1pm (New York)/ 18:00 (London)/ 19:00 (Berlin)/ 8pm (Beijing) ይካሔዳል።
ይህን በዓይነቱ ልዩ የሆነ መድረክ ይሳተፉ። መድረኩ በባለሙያዎች የተደገፈ ትንታኔንና ውይይት ይዞ ይጠብቅዎታል። እንዳያመልጥዎ! እኛም ተሳትፈን ሌሎችም እንዲሳተፍ እናድርግ።
Join Meeting/መድረኩን ለማሳተፍ ከታች የተቀመጡትን አማራጮች ይጠቀሙ
Join Zoom Meeting Meeting ID: 894 2219 4931 Passcode: 976793 Zoom link: https://us06web.zoom.us/j/89422194931?pwd=bbHBkELjvfheJBq5RtDailmsRZ0bwr.1
YouTube Live: https://www.youtube.com/watch?v=xj5pT0gR4c4
ጥያቄ ካለዎት በኢሜላችን office@eotcadvocacy.org ያኙን::
ዛሬ ሚያዚያ 27 አርበኞች ሀገራችንን ከወራሪ ፣ፅኑአን አባቶቻችን ሃይማኖታችንን ከሃሳዊ የጠበቁበት የድል ቀን የሚታሰብበት ነው:: ____________
እንቋዕ አብጽሐነ!
እንኳን አደረሰን!
ባጋ ጌሳን!
እንኳዕ ኣብፀሐና!
በወሄ አሰናነም!
ኢድ ቤጉ ነጋዲሴ!
ሃዋሌ ኢሊሽንኬ!
ወዝ ችጝዘት!
ሃሹ ሳሩዋን ጋቲስ!
ባጋ ጌኔነን!
_____
@orthoateast
ሰበር ዜና
በዛሬው ዕለት ሕገወጡን ቡድን የሚደግፉ ሁለት አካላት ሽጉጥ በመያዝ ምዕራብ ሐረርጌ ጭሮ/አሰበ ተፈሪ ከተማ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን ገብተው የአገልግሎት ማስመሰል ሥራ ሠርተው የቤተክርስቲያን አንዳንድ ንዋየ ቅዱሳት ሠርቀው ሲወጡ በህዝቡ ቁጥጥር ሰር ዉለው አሁን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ገብተዋል።።
#ዲ/ን ዶ/ር ያዕቆብ ጨመረ የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ሐረር ጤናና ህክምና ሳይንስ ግቢ ጉባኤ ተመራቂ።
#በግቢ ጉባኤያት አገልግሎት በልዩ ልዩ ክፍላት አገልግሏል።
#ተመርቆ ከወጣ ብኃለም በድሬደዋ ዩኒቨርስቲ በመምህርነት እና ድል ጮራ ሆስፒታል በህክምና ዶክትሬት ሲያገለግል ቆይቷል።
#አሁን ላይ በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ በዓይን ህክምና ስፔሻላቲ የሶስተኛ ዓመት ተማሪ ነው።
#በጭንቅላት እጢ ታሞ የሀኪሞች ቦርድ ሕንድ ሄዶ እንዲታከም ፅፈውለታል።
#ለሕክምናው የሚያስፈልገው ከ1ሚሊየን ብር በላይ በመሆኑ ለወንድማችን እንድረስለት
1000474028864 Dr. YAKOB CHEMERE
#ማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ማእከል
#stop_orthodoxGenocide_inEthiopia
"ሰልፉ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል" እንደተለመደው በየአብያተ ክርስቲያናቱ በምልአት እየተገኘን በጸሎት እና በቅዳሴ እንድንሳተፍ ብጹአን አባቶቻችን አሳስበዋል -------- @orthoateast
እግድ ተሰጠ ማለትም ክስ ቆመ ማለት እንዳልሆነ ያስታወሰው ኮሚቴው የምንጠይቃቸው የወንጀልና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ይቀጥላሉ ብሏል።
የፌደራል ፖሊስ ፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ የኦሮሚያ ፖሊስና ሰላም ሚኒስቴር እግዱን እንዲያስፈጽሙ ኃላፊነት የተጣለባቸው ተቋማት ናቸው።
"እግዚአብሔር ጸሎታችንን ሰምቶናል" ብለውናል አባቶቻችን በአጭር መግለጫቸው ::ብጹአን አባቶቻችን ነገ ቅዳሜ የካቲት 4 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት አጠቃላይ ጉዳዮችን በተመለከተ መግለጫ እንሰጣለን ብለዋል:: እንደለተመደው በጸሎት:በትህትና እና በትእግስት እንጠብቃለን::
Читать полностью…https://www.youtube.com/live/5m0qgfjKolU?feature=share
Читать полностью…በስመ አብ ወወልድ ወንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ህዝብ ግንኙነት የተሰጠ አስቸኳይ ሰበር መግለጫ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በየካቲት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መሠረት መንግሥት ቤተ ክርስቲያኒቱ መግለጫውን ባወጣች ፵፰ ስዓታት ውስጥ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሃይማኖት፣ ቀኖና እና አስተዳደራዊ ሕግጋትን ባልጣሰ መልኩ ከመንግሥት ጋር በጉዳዩ ላይ ለመወያየት መነፈሳዊ በሯ ክፍት መሆኑን በመግለጽ ጥሪ ማስተላለፏ ይታወሳል፡
ከዚህ ጋር በተያዘ የኢፌዴ ጠቅላይ ሚኒስቴር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ እህመድ ይህንን የቤተ ክርስቲያናችንን ጥሪ መሠረት በማድረግ ለውይይይት ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ሆኖም ግን ውይይቱ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ሊሆን የሚገባ ነው በሚል በተነሳው ሐሳብ በጉዳዩ ላይ ከሽማግሌዎች ጋር ጥልቅ ውይይት በማድረግ የደህንነት ተሽከርካሪዎች እና የጸጥታ አካላት ብዛት ሲታይ ምእመናንን ስጋት ላይ እንዳይወድቁ እና ልተጋባ ጕዳት እንዳይዳረጉ በማሰብ የስላም ጥሪውን መንግሥት ከተቀበለ እና በቤተ መንግሥት መገኘቱ ለሕዝባችን የሚያመጣው መፍትሔ የሚኖር እንደሆነ በማሰብ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትያርካችንን ጨምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተተ ልኡክ በቤተ መንግሥት የሚገኝ መሆኑን እያሳወቅን ሕዝበ ክርስቲያኑም አባቶች የደረሱበትን ውጤት እስኪያሳውቁ ድረስ በትእግስት ትባበቁ ዘንድ እናሳስባለን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
የካቲት ፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ተባብሶ መቀጠሉን የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት አሳወቀ።
Читать полностью…ጅግጅጋ ምዕመናን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ጨምሮ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ በመከላከያ፣ ፌደራል ፖሊስ እና ልዩ ሃይል ተከልክለው ወደ ቤታቸው እየተመለሱ ነው። ኦሮቶዶክሳዊያን ጊዜው ለኛ ወርቃማ ነው በአግባቡ እንጠቀምበት ከልባችን ወደ አምላካችን እንጩህ።
Читать полностью…