+ሠራዊቱን ወደ ከተማ አሰናብቶ እርሱ ብቻውን ወደ ገዳሙ ዘለቀ:: ወደ አበ ምኔቱም ቀርቦ ሰገደላቸውና እንዲያጠምቁት ተማጸናቸው:: እርሳቸውም አስተምረው አጠመቁት:: በዚያውም መንኖ መነኮሰ::
+ለዘመናትም በጠባቡ መንገድ ተጋድሎ ከጸጋ (ከብቃት) ደረሰ:: በአካባቢው ሰውና እንስሳትን የፈጀውን ዘንዶም ባሪያ አድርጐ ለ10 ዓመታት ገዝቶታል:: ከብዙ ተጋድሎ በሁዋላም በዚህ ቀን ዐርፏል::
+አምላከ ቅዱሳን መላእክት እነርሱን ለረድኤት ይላክልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
+ኅዳር 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን 4ቱ እንስሳ (ኪሩቤል)
2.ቅዱስ አፍኒን ሊቀ መላእክት
3.አባ ቅፍሮንያ ጻድቅ
4.ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ንጉሥ (ዘምስለ ቅዱስ መስቀል)
5.ቅድስት እግዚእ ክብራ
++"+ በዙፋኑም መካከል: በዙፋኑም ዙሪያ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሏቸው አራት እንስሶች ነበሩ:: ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል:: ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል:: ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው:: አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል:: አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሏቸው:: +"+ (ራዕይ. 4:6)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)
=>+"+ የሚበልጠውን ትንሳኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ::
ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ
ተፈተኑ:: በድንጋይ ተወግረው ሞቱ:: ተፈተኑ: በመጋዝ ተሰነጠቁ: በሰይፍ
ተገድለው ሞቱ:: ሁሉን እያጡ: መከራን እየተቀበሉ: እየተጨነቁ: የበግና
የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ:: ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ:
በዋሻና በምድር ጉድጉዋድ ተቅበዘበዙ:: +"+ (ዕብ. 11:35-38)
✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞✞✞ ኅዳር 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞
✞✞✞ በዓለ ደብረ ቁስቁዋም ✞✞✞
✞✞✞ የአርያም ንግሥት: የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ አምላክ ልጇን አዝላ ወደ ምድረ ግብፅ ወርዳለች:: በወንጌል ላይ (ማቴ. 2:1-18) እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በ2 ዓመቱ የጥበብ ሰዎች (ሰብአ ሰገል) ወደ ቤተ ልሔም መጥተው ሰግደውለት ወርቅ: እጣን: ከርቤውን ገበሩ: አገቡለት::
+ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 1 አምላክ ልጇን አዝላ: በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቁዋጥራ: ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት ወጣች::
+ከገሊላ ተነስታ በጭንቅ: በመከራ: በረሃብና በጥም: በሐዘንና በድካም: በላበትና በእንባ ተጉዛ በዚሕች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታለች::
*የአምላክ እናቱ እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች::
*ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች::
*የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች::
*የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች::
*የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች::
*እመ አምላክ ተራበች: ተጠማች: ታረዘች: ደከመች: አዘነች: አለቀሰች: እግሯ ደማ: ተንገላታች::
+ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት: ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኳ ለአመላክ እናት ክብር ይሰጣሉ::
+አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅድስት ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል:: ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን መርጠዋልና::
+"መድኃኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰደደ? ለምን ስደቱን ወደ ግብፅና ኢትዮዽያ አደረገ?"
1.ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ ተነግሯልና (ኢሳ. 19:1, ዕን. 3:7)
2.ምሳሌውን ለመፈጸም:: የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም: ያዕቆብ (እሥራኤል): ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና::
3.ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: (ኢሳ. 19:1)
4.የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ::
5.ሰው መሆኑ በአማን እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: (ሰው ባይሆን ኑሮ አይሰደድም ነበር:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም:: ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና:: )
6.ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና
7.የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው::
+እመ ብርሃን ድንግል ማርያም ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት (ወይም ለ42 ወራት) በስደት የቆየችባቸው ቦታዎች አሉ:: ድንግል ማርያም ከርጉም ሔሮድስ ስትሸሽ መጀመሪያ የሔደችው ከገሊላ ወደ ሶርያ ደንበር (ደብረ ሊባኖስ) ነው::
+በዚያ የሸሸጋት ቅዱስ ጊጋር መስፍኑ በሔሮድስ ሲገደል ወደ ምድረ ግብጽ ወረደች:: በግብጽም ለብዙ ጊዜ ከአንዱ ወደ ሌላው ስትሸሽ ቆየች::
"እንዘ ከመ በግዕት ግድፍት አመ ሳኮይኪ ውስተ ምድረ በዳ" እንዲል:: (እሴብሕ ጸጋኪ)
+ቀጥላም በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል ገብታ ደብረ ቢዘን ላይ (አሁን ኤርትራ ውስጥ ነው) ዐረፈች:: ከደብረ ቢዘን በደብረ ዳሙ: አክሱም: ደብር ዓባይ: ዋልድባ አድርጋ እየባረከች ጣና ደርሳለች:: በጣና ገዳማትም: በተለይ በጣና ቂርቆስ ለ100 ቀናት ቆይታ ቀጥታ በጐጃም ወደ ሽዋ ሒዳ ደብረ ሊባኖስን ቀድሳለች::
+ቀጥላም እስከ ደብረ ወገግና ደብረ ሐዘሎ ደርሳለች:: በእግሯ ያልደረሰችባቸውን የሃገራችን ክፍሎች በደመና ተጭና ዐይታ ባርካቸዋለች:: ከልጇም በአሥራትነት ተቀብላለች:: ሔሮድስ መሞቱን መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል የነገራትም እዚሁ ኢትደዮዽያ ውስጥ መሆኑን ትውፊት ያሳያል::
+እመ ብርሃንም ከሃገራችን ሰዎች (ከሰብአ ኦፌር) የተቀበለችውን ስንቅና ስጦታ በ5 ግመሎች ጭና ከቅዱሳኑ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር በዚህች ቀን ደብረ ቁስቁዋም ውስጥ ገብተው ከድካም ዐርፈዋል:: ሐሴትንም አድርገዋል::
+ዳግመኛም ከክርስቶስ ስደት 400 ዓመታት በኋላ በዚህች ቀን የግብጿ ደብረ ቁስቁዋም ታንጻ ተቀድሳለች:: የቅዱሳን ማደሪያም ሁናለች:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
+ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ390ዎቹ አካባቢ ድንግል እናቱን: ቅዱሳን ሐዋርያትን: አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን: አስከትሎ ወረደ::
+የወቅቱ የግብጽ ፓትርያርክ ቅዱስ ቴዎፍሎስና ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስ ቤተ ክርስቲያኑን አንጸው: ሕዝቡን ሰብስበው ይጠብቁት ነበርና ወርዶ ቀድሶላቸው ታላቅ ደስታ ሁኗል::
+ስደቷን መሳተፍን ሽተው አበው:-
"እመ ኀሎኩ በጐይዮቱ ውእተ መዋዕለ:
እምተመነይኩ ኪያሁ በዘባንየ ሐዚለ:
ወበልሳንየ እልሐስ ዘአእጋሪሁ ጸበለ:
ወከመ አዕርፍ ምስሌሁ በትረ ዮሴፍ ኀበ ተተክለ:
ለወልደ ማርያም በሐጸ ፍቅሩ ልቡናየ ቆስለ::" እንዳሉ:: (ሰቆቃወ ድንግል)
እኛም እመ ብርሃንን ልንሻት ያስፈልገናል::
+ይህቺ ቀን ለእኛ ለክርስቲያኖች ሁሉ እጅግ የደስታ ቀን ነውና ሐሴትን እናድርግ:: የሰማይና የምድር ጌታ ለእኛ ሲል ካደረገው ስደቱ በዚህች ቀን ተመልሷልና:: ስደቷን አስበን ካዘንን: መመለሷን አስበን ደስ ልንሰኝ ይገባልና::
"አብርሒ አብርሒ ናዝሬት ሃገሩ:
ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መጾሩ" ልንልም ይገባል::
+" አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ "+
+ጻድቁ አቡነ ጽጌ ድንግል በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበሩ ሊቅና ገዳማዊ ናቸው:: የዘር ሐረጋቸው ምንም ከቤተ እሥራኤል እንደሚመዘዝ ቢታወቅም ኢትዮዽያዊ ናቸው:: አስቀድመው አይሁዳዊ በመሆናቸው ኢየሱስ ክርስቶስንና ድንግል እናቱን አያምኑም ነበር::
+የተማሩትም ብሉይ ኪዳንን ብቻ ነበር:: በጊዜውም "ክርስቶስ አልተወለደም: ትክክለኛው እምነት ይሁዲ ነው" እያሉ ከክርስቲያኖች ጋር ይከራከሩ ነበሩ:: አንድ ቀን ግን ከታላቁ ሊቅና ገዳማዊ አቡነ ዜና ማርቆስ ጋር ተገናኙ::
+ጻድቁን ስላልቻሏቸው ተሸንፈው በክርስቶስ አመኑ:: አቡነ ዜና ማርቆስም አስተምረው ክርስትና ሲያነሷቸው /ሲያጠምቁዋቸው 'ጽጌ ድንግል' አሏቸው:: ሲመነኩሱም 'ጽጌ ብርሃን' ተብለዋል:: ቀጥለውም በጾምና በጸሎት ሲጋደሉ: እመቤታችንንም ሲለምኑ ምሥጢር ተገለጠላቸው::
+የእመ ብርሃንን ስዕለ አድኅኖ በአበባ ተከባ: በብርሃንም ተውጣ ተመለከቱ:: በዚህ ምክንያትም ዛሬ በጣፋጭነቱ የሚታወቀውን ማኅሌተ ጽጌን 150 ዓርኬ አድርግው ደረሱ:: እስከ ዕለተ ዕረፍታቸውም እመቤታችንና ልጇን በገዳማቸው (ወለቃ አካባቢ የሚገኝ) ሲያመሰግኑ ኑረዋል:: ጻድቁ ያረፉት ጥቅምት 27 ሲሆን ዛሬ የቃል ኪዳን በዓላቸው ነው::
✞✞✞ ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግስተ ሰማያት ስደት ይሠውረን:: ከስደቱ በረከትም ያድለን::
✞✞✞ ኅዳር 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም (ሚጠታ ለማርያም)
2.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
3.ቅድስት ሰሎሜ ቡርክት
4.ቅዱስ ዮሳ (ወልደ ዮሴፍ)
5.ቅዱስ ቴዎፍሎስ ሊቅ
6.አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ
7.አባ ፊልክስ ዘሮሜ
++"+ ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕጻኗን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ:: አሕዛብንም ሁሉ በብረት ዘንግ ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ: ወንድ ልጅ ወለደች:: ልጇም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ:: ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቧት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ሥፍራ ወደ በረሃ ሸሸች:: +"+ (ራዕይ. 12:4-7)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ አሜን፡፡፡✞✞✞
=>+"+ እንኩዋን ለታላቁ ጻድቅ "አባ ዮሐኒ" እና "ቅዱስ ለንጊኖስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+
(በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ትግራይ ውስጥ የሚገኘው አስደናቂው የጻድቁ ገዳም ነው)
+"+ ታላቁ አባ ዮሐኒ +"+
=>በምድረ ኢትዮዽያ ዝናቸው ከወጣና ቀደምት ከሚባሉ ጻድቃን አንዱ ቅዱስ አባ ዮሐኒ ("ኒ" ጠብቆ ይነበብ) ነው:: አበው ሊቃውንት የቅዱሱን ታሪክና ገድል ገና በልጅነት ስለ ነገሩን አንረሳውም:: እጅግ ጣፋጭ ዜና ሕይወት ያለው አባት ነውና:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
+በ6ኛው መቶ ክ/ዘመን በሃገራችን ቅዱስ አፄ ካሌብ ነግሦ ሳለ: አንድ ቅዱስ ሰው ከግብጽ ወደ ኢትዮዽያ መጡ:: እኒህ ሰው "አሞኒ ዘናሕሶ" ይባላሉ:: ቅዱሱ ዓለምን ላለማየት ቃል ገብተው በትግራይ በርሃ ይጋደሉ ነበር::
+በዘመኑ አፄ ካሌብ የናግራን (የመን) ክርስቲያኖችን ለመታደግ ዘመቻ አድርጎ ነበር:: ታዲያ አንድ የንጉሡ ወታደር ወደ ዘመቻ ሲሔድ ሚስቱን ይጠብቅለት ዘንድ ትንሽ ወንድሙን አደራ ይለዋል:: ወንድሙ ግን አደራውን ትቶ የትልቅ ወንድሙን ሚስት አስገድዶ ይደርስባትና ትጸንሳለች::
+ከዘመቻ የተመለሱት ከ1 ዓመት በሁዋላ ነውና ሚስቱን ምጥ ላይ ያገኛት ወታደር ደነገጠ:: ተቆጣ:: የጸነሰችው ከእርሱ እንዳልሆነ ያውቃልና ምጥ ላይ ሆና ሊያዝንላት አልፈለገም::
+ለገልጋይ አስቸግሮ ሚስቱን ይደበድባት ገባ:: በዚህ ምጥ: በዚህ ዱላ ነፍሷን ከሥጋዋ ሊለየው የደረሰችው ያቺ ሴት ግን "ወንድማማችን አላጋድልም" ብላ ቻለችው:: በዚህ ጊዜ ቅዱስ መልአክ ያን ግብጻዊ ባሕታዊ (አባ አሞኒን) አምጥቶ ከሰዎቹ በር ላይ አቆመው::
+"ከእሱ ነው በይ" አላት:: እርሷም "ከዚያ ባሕታዊ ነው" ብላ ተናገረች:: ወታደሩ ባሏም በቁጣ ወጥቶ ቅዱስ አሞኒን በዱላ ስብርብር እስኪል ድረስ ደበደበው:: ልጁ ልክ ሲወለድም ከእናቱ ነጥቆ ለባሕታዊው አሳቅፎ አባረረው::
+ቅዱስ አሞኒም ሕጻኑን አቅፎ ወደ ተምቤን በርሃ አካባቢ ወሰደው:: ግን ምን ምግብ: ምን ልብስ: ምን መኝታ እንደሚሰጠው ጨንቆት ጻድቁ አለቀሰ:: በዚህ ጊዜም ቅዱስ መልአክ የጸጋ ምንጣፍን አነጠፈለት::
+ጆፌ አሞራ መጥቶ ክንፉን ሲያለብሰው አጋዘን መጥታ ጡት አጠባችው:: በዚህ የተደነቀው ቅዱስ አሞኒ ሕጻኑን "ዮሐኒ" ሲል ስም አወጣለት:: ትርጉሙም "ወልደ አራዊት - ወላጆችህ (አሳዳጊዎችህ) አራዊት ናቸው" እንደ ማለት ነው::
+ሕጻኑ ዮሐኒ በዚህ መንገድ ከአሞኒና ከአራዊቱ ጋር አደገ:: 5 ዓመት በሞላው ጊዜም ትምሕርተ ሃይማኖትን: የቅድስና ሕይወትን ተማረ:: ልክ እንደ መንፈሳዊ አባቱ በጾምና በጸሎት ተወሰነ:: ግን እርሱ ከእርሱ: ከአሞኒና ከአራዊቱ በቀር ሌላ ፍጥረት: ዓለም (ብዙ ሰዎች) መኖራቸውን አያውቅም::
+12 ዓመት በሞላው ጊዜ ግን ክህነት ይገባዋል ብሎ መንፈስ ቅዱስ ስላሳሰባቸው ቅዱሱ አሞኒ ዮሐኒን ወደ ዻዻሱ ወሰዱት:: መንገድ ላይም ቅዱስ ዮሐኒ ወጣት ሴቶች ተሰብሰበው ሲጫወቱ ተመልክቶ "አባ! እነዚህ ጸጉራቸው የረዘመ: ደረታቸው ወደ ፊት የወጣ ፍጥረቶች ምንድን ናቸው?" ሲል ጠየቀ::
+አባ አሞኒም "ልጄ! እነዚህ ሴቶች ናቸው:: ግን ለእንደ እኔና አንተ ያሉ የበርሃ ሰዎች አይሆኑምና አትቅረባቸው" አለው:: ቅዱስ ዮሐኒ መልሶ "አባቴ! ድንገት ቢመጡብኝ ምን ላድርግ?" ሲል ጠየቀ:: አባ አሞኒም "ልጄ! ከዘለዓለም ርስት ከምትነቀል ሩጠህ ብታመልጥ ይሻላል" አለው::
+ከ6 ዓመታት በሁዋላ (ዮሐኒ 18 ዓመት ሲሞላው ማለት ነው) ቅዱስ አሞኒ ኅዳር 5 ቀን ዐረፈ:: ለ14 ዓመታትም ቅዱስ ዮሐኒ ከአራዊትና አባ አበይዶን ከመሰሉ አባቶች ጋር ኖረ:: ከንጽሕናው የተነሳም ቅዱሳን መላእክት ያነጋግሩት ነበር::
+ስም አጠራሩ በምድረ ትግራይ ሲወጣ ወላጅ እናቱ በሕይወት ነበረችና ሰማች:: የአካባቢዋን ሴቶች ሰብስባም ልትገናኘው ወዳለበት ተራራ ገሰገሰች:: ወደ ተራራው ደርሳ ስትጠራው ቅዱሱ ተመለከታት::
+ወዲያው ትዝ ያለው አባቱ ቅዱስ አሞኒ "ሴት ስታይ ሩጥ" ያለው ነውና እግሩን አንስቶ ሮጠ:: እናቱ ስትከተለው: እርሱ ሲሮጥ ከገደሉ ጫፍ ደረሰ:: ወደ ሁዋላ ሲመለከት ሊደርሱበት ነው::
+በስመ ሥላሴ ፊቱን አማትቦ ወደ ገደሉ ተወረወረ:: በዚህ ጊዜ ግን መንፈሳዊ ክንፍ ተሰጥቶት ተሰወረ:: ቅዱስ መልአክም ብሔረ ሕያዋን አስገብቶታል:: ይህንን ታሪክ ሲያደንቁ አበው እንዲህ ብለዋል::
"ሰላም ዕብል ለዘኮነ ሱቱፈ::
ምስለ እለ ገብሩ ሰብእ ብሔረ ሕያዋን ምዕራፈ::
እምሥርዓተ መላእክት ዮሐኒ ምንትኒ ኢያትረፈ::
ከመ ሕይወቶሙ ሕይወተ ተጸገወ ዘልፈ::
ወከመ ክንፎሙ አብቆለ አክናፈ::" (አርኬ)
+"+ ቅዱስ ለንጊኖስ ሰማዕት +"+
=>ለንጊኖስ ማለት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስብከት ዘመን የዺላጦስ ወታደር የነበረ ሰው ነው:: ስለ ጌታችን ተአምራት በየጊዜው ይሰማ ነበር:: ሔዶ እንዳያገኘው ግን አይሁድን ይፈራ ነበር:: እነርሱ "በክርስቶስ ያመነ ሁሉ ከምኩራብ ይባረር" ብለው ነበርና:: (ዮሐ. 9:22)
+ጌታችን በተሰቀለባት ዕለተ ዐርብ ግን ጭንቅ ሆነበት:: ጌታን እንዲሰቅሉ ከታዘዙ ወታደሮች እንደ አንዱ ተመርጦ ነበርና በዘዴ አሞኛል ብሎ እስከ 9 ሰዓት ድረስ ቆየ::
+በሁዋላ ግን አይሁድ "በክርስቶስ ሞት ያልተባበረ ሁሉ ወንጀለኛ ነው" የሚል አዋጅ በማስነገራቸው እየፈራ ወደ ቀራንዮ ሲደርስ "ጐኑን ውጋው" ብለው ረዥምና ጥቁር ጦር ሰጡት:: ለንጊኖስ ወደ ጌታችን ዐይን ተመለከተ:: እያየው እንዳልሆነ ገመተ::
+ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በባሕርይ ሥልጣኑ ለይቷልና ጦሩን ጨብጦ ወደ ጌታ ጐን ልኮ ወጋው:: ከጌታ ቀኝ ጐንም በ"ለ" አምሳል ትኩስ ደምና ውሃ ፈሰሰ:: አንዷ ፍንጣቂ ሔዳ የታወረች ዐይኑ ላይ ዐርፋ ዐይኑን አበራች::
+ለለንጊኖስ ታላቅ ደስታ ሆነ:: ለእኛ ግን ማየ ገቦና ደመ ገቦ ፈለቀልን:: የጌታችን ትእግስቱና ቸርነቱ ግን ይደንቃል::
"ከመ ኢየሐስብ ቦቱ ዘኩናተ እዱ ርግዘቶ::
በኃጣውኢሁ ለዘኢፈቀደ ሞቶ::
ምሕረቶ እሴብሕ ወዐዲ ትዕግስቶ::" እንዳሉ ሊቃውንት::
+ጌታችን ከተነሳ በሁዋላ ለንጊኖስ ወደ ቅዱስ ዼጥሮስ ዘንድ ሒዶ ስለ እውነት: ስለ ሃይማኖትም ተማረ:: ተጠምቆ: ምድራዊ ወታደርነቱን ትቶ እየሰበከ ከኢየሩሳሌም ወደ ቀዸዶቅያ ወረደ:: ለዘመናትም ጌታችን ክርስቶስን በሥርዓተ ወንጌል አገለገለ::
+በመጨረሻ በጢባርዮስ ቄሣር ዘመን አይሁድ አሳደዱት:: አንገላቱት:: የነርሱ ወገን ስለነበረም መከራ አጸኑበት:: የጽቅድ አርበኛና የክርስቶስ ሐዋርያ ቅዱስ ለንጊኖስ ግን ጸና:: አይሁድም አንገቱን ቆርጠውት ለሰማዕትነት በቃ:: ቅዱሱ በሕይወቱም በዕረፍቱም ተአምራትን ሠርቷል::
< አስተርዮተ ርዕሱ >
=>ይሕች ዕለት አስተርዮተ ርዕሱ ትባላለች:: እርሱን ከገደሉ በሁዋላ አይሁድ ራሱን ወደ ኢየሩሳሌም ወስደው ጥለዋት ነበር:: የእርሱን ሰማዕትነት ያየች አንዲት ክርስቲያንም ከለቅሶ ብዛት ዐይኗ ቢጠፋ ሕጻን ልጇን ይዛ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች::
+ወዲያው ግን ሕጻን ልጇ ሞተባትና ሐዘኗ ከልኩ አለፈ::
ለአንዲት እናት ዐይንንና ልጅን በአንዴ ማጣት እጅግ ጭንቅ ነው:: በሌሊት ግን ቅዱስ ለንጊኖስ በራዕይ ተገልጦ ደስታ ነገራት::
✝✝✝ እንኩዋን ለቅዱሳን ሰማዕታት "ቶማስ" : "ያዕቆብ ወዮሐንስ" : "አቢማኮስ ወአዛርያኖስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✝✝
+"+ ቅዱስ ቶማስ ዘደማስቆ +"+
=>ቅዱስ ቶማስ በ7ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ተወልዶ ያደገ ሶርያዊ ክርስቲያን ነው:: ከልጅነቱ እንደሚገባ መጻሕፍትን ተምሮ ለዲቁና: ለቅስና: ከዚያም ለዽዽስና በቅቷል:: በወቅቱ የሶርያ ዋና ከተማ በሆነችው ደማስቆ ላይ ተሹሞ ያገለግልም ነበር::
+ታዲያ ዘመኑ በየቦታው ደም የሚፈስበት ነበርና የክርስቶስን መንጋ መጠበቁ ቀላልና የዋዛ ሥራ አልነበረም:: በዘመኑ የክርስቲያኖችን ደም ያፈሱ የነበሩት ደግሞ ተንባላት (የመሐመድ ተከታዮች) ናቸው:: 7ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲደርስም ተንባላት ግብጽንና ሶርያን በቁጥጥር ሥር በማድረጋቸው ክርስቲያኖች ተቸገሩ::
+በወቅቱም ቅዱስ ቶማስ ሲያስተምር የሰማው አንድ መሐመዳዊ "እንከራከር" አለው:: ቅዱሱም ሊቅ ነበርና ስለ መሐመድ ሐሰተኛነት: ስለ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት ካስረዳው በሁዋላ ንጹሕና ሰማያዊ ሕግ ቅዱስ ወንጌል እንጂ ቁርዓን እንዳልሆነ ነገረው::
+በአደባባይ በመረታቱ ያፈረው መሐመዳዊም በብሽቀት ሒዶ ለደማስቆው ገዢ ከሰሰው:: ቅዱስ ቶማስም ተይዞ ቀረበ:: "እንዴት እምነታችን እስልምናን ትሳደባለህ?" ቢለው ቅዱሱ "እውነቱን ተናገርኩ እንጂ አልተሳደብኩም" ሲል መለሰለት::
+መኮንኑም "እሺ! ክርስቶስ ማን ነው? ስለ ወንጌልና ቁርዓንስ ምን ትላለህ?" ሲል የተሳለ ሰይፍ አውጥቶ ጠየቀው:: የቀናችው እመነት ክርስትና ክብርነቷ በሰማይ ነውና መጨከንን ትጠይቃለች::
+ቅዱስ ቶማስ ምንም ሳይፈራ "ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰማይና የምድር ፈጣሪና አምላክ ነው::
ቅዱስ ወንጌል ሰማያዊና የሕይወት ሕግ ሲሆን ቁርዓን ደግሞ የመሐመድ የፈጠራ መጽሐፍ ነው::" ይህንን የሰማው መኮንን በቁጣ አንገቱን እንዲመቱት አዘዘ:: ቅዱስ ቶማስም በዚህች ቀን ስለ ቀናች ሃይማኖቱ አንገቱን ሰጠ::
+"+ ቅዱሳን ያዕቆብ ወዮሐንስ +"+
=>አሁን ደግሞ ወደ 4ኛው መቶ ክ/ዘመን ተመልሰን: ወደ ምድረ ፋርስ (ኢራን) ወርደን ቅዱሳንን እናዘክር:: እነዚህ ቅዱሳንም በሃገረ ፋርስ (ኢራን): በመንግስተ ሳቦር ዘመን የነበሩ አበው ናቸው:: ሳቦር ማለት ጸሐይንና እሳትን የሚያመልክና እጅግ ጨካኝ የነበረ ንጉሥ ነው::
+ቅዱሳኑ ያዕቆብና ዮሐንስ የሐዋርያትን ስም ብቻ ሳይሆን ግብራቸውን: ቅድስናቸውንም የያዙ ነበሩ:: ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት ባይሆንም ፋርስ ግን በዚህ ዘመንም ለክርስቲያኖች የግፍ ከተማ ነበረች::
+ከቅዱስ ጊዮርጊስ እስከ ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ: ከቅዱስ መርምሕናም እስከ ቅዱስ ኮቶሎስ ሰማዕትነትን የተቀበሉት በዚህችው ሃገር ውስጥ ነው:: ቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስም ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በልኩ ተምረው: መጻሕፍትንም ተረድተው ለክህነት ተመርጠዋል::
+በሁዋላም ቤተ ክርስትያን "ይገባቹሃል" ስትል ዻዻሳት አድርጋ ሾመቻቸው:: እነርሱም አላሳፈሯትም:: የክርስቶስን መንጋ እያስተማሩ: እየናዘዙ ጠበቁላት:: ንጉሡ ሳቦር ግን ሕዝቡን ለፀለሐይና ለእሳት ሊያሰግድ ላደረገው ጥረት እንቅፋት ሁነውበታልና ጠላቸው::
+በወታደሮቹ አስይዞም በፍርድ አደባባይ አቆማቸው:: ሕዝቡን በአዋጅ ጠርቶ: አስፈሪ እሳት አስነድዶ "ሕዝቡ ለፀሐይ እንዲሰግድ እዘዙ" ቢላቸው "እንቢ" አሉት::
+ከነ ልብሳቸው አንስተው ወደ እሳቱ ወረወሯቸው:: ቅዱሳኑም በመከራው (በነደደው እሳት) መካከል ሆነው ለሕዝቡ ተናገሩ::
"አምላክ አንድ እግዚአብሔር ነውና እንዲህ በሃይማኖታችሁ ጽኑ" አሏቸው:: እሳቱም አቃጥሎ ገድሏቸው የክብርን አክሊል ተቀዳጁ::
+"+ ቅዱሳን አቢማኮስ ወአዛርያኖስ +"+
=>አሁን ደግሞ ወደ 3ኛው መቶ ክ/ዘመን: ወደ ዋናው ዘመነ ሰማዕታት እንመለስ:: በዘመነ ሰማዕታት ከነበሩ ቅዱሳን ሰማዕታት 2ቱ አቢማኮስና አዛርያኖስ ናቸው:: አውሬዎቹ መክስምያኖስና ዲዮቅልጥያኖስ ዓለምን ለ2 ተካፍለው በክርስቲያኖች ላይ ግፍን ሲሰሩ 2ቱ ቅዱሳን በሮም ግዛት ሥር ይኖሩ ነበር::
+በዘመኑ እንኩዋን ቤተ ክርስቲያን ማነጸ: መዘመር: እምነትን መግለጥ ይቅርና ሲያማትቡ መታየት እንኩዋ ያስገድል ነበር:: ነገሥታቱ የሾሟቸው ተከታዮቻቸው ክርስቲያኖችን ከዋሉበት አላሳድር: ካደሩበትም አላውል አሉ::
+ታላቅ ግፍ: ሰቆቃና ጭንቅ በሆነበት በዚያ ወራት የሞተው ሙቶ እኩሉ ሲሰደድ: አቢማኮስና አዛርያኖስ ግን በከተማ መሐል ተረጋግተው ክርስቶስን ያመልኩ ነበር:: ይህም ተደርሶባቸው ተከሰሱና ተይዘው ቀረቡ::
+መኮንኑ 2ቱን ክርስቲያን ወጣቶች ሲመለከታቸው ምንም የፍርሃት ምልክት አልተመለከተባቸውምና ተገረመ:: "ማንን ታመልካላችሁ?" አላቸው:: እነርሱም "የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን!" ሲሉ መለሱለት::
+"ክርስቶስን ትክዳላችሁ ወይስ ትሞታላችሁ?" ቢላቸው "ሰነፍ!" ሲሉ በአደባባይ ገሰጹት:: "የፈጠረ: ያከበረ: ሥጋውን ደሙን የሰጠ ጌታ እንዴት ይካዳል?!" ሲሉም እቅጩን ነገሩት:: በድፍረታቸው የደነገጠው መኮንኑም በዚያች ሰዓት ሞትን አዘዘባቸው:: በዚህች ቀንም አንገታቸውን ተሰይፈው ለክብረ ሰማዕት በቅተዋል::
=>አምላከ ቅዱሳን ሰማዕታት በነርሱ ያሳደረውን ትእግስትና ጽናት በእኛም ላይ ያሳድርልን:: ከበረከታቸውም ያድለን::
=>ኅዳር 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ቶማስ ዘደማስቆ
2.ቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስ
3.ቅዱሳን አቢማኮስ ወአዛርያኖስ
4.አባ አበጊዶ ዘትግራይ
5.ታላቁ አባ ዘካርያስ
6.ጉባኤ ቅዱሳን ሰማዕታት
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ
2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት)
=>+"+ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን?
'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን'
ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው::
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን:: +"+ (ሮሜ. 8:35-38)

✝✝✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን። ✝✝✝
✝ኅዳር 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+" አቡነ መድኃኒነ እግዚእ "+
+መዘንጋታቸው እጅግ ከሚያስቆጭ ኢትዮጽያውያን አባቶች ትልቁን ሥፍራ እኒህ አባት ይወስዳሉ:: የማር ወለላን በሚያስንቅ ጣዕመ ሕይወታቸው ሃገራችንን ያጣፈጡ: ብርሃን ሆነው ብዙ ቅዱሳንን የለኮሱ ታላቅ ጻድቅ ናቸው::
+አባ መድኃኒነ እግዚእ የተወለዱት በ13ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ትግራይ (አዲግራት) ውስጥ ነው:: ወላጆቻቸውም ቀሲስ ሰንበትና ሒሩተ ማርያም ይባላሉ:: በደግነትም እጅግ የታወቁ እንደ ነበሩ ገድላቸው ይናገራል:: "መድኃኒነ እግዚእ" ማለት "ጌታ መድኃኒታችን ነው" ማለት ነው::
+ብዙ ጊዜም "ዘደብረ በንኮል-ሙራደ ቃል" እየተባሉ ይጠራሉ:: "ደብረ በንኮል" ማለት ትግራይ ውስጥ የሚገኝና ጻድቁ በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ያነጹት ገዳም ነው:: "ሙራደ ቃል" ደግሞ "የቃል (የምሥጢር) መውረጃ" እንደ ማለት ሲሆን በቦታው ሱባኤ የያዘ ሰው ልክ እንደ ቅዱስ ያሬድ ምሥጢር እንደሚገጥለት የሚጠቁም ስም ነው::
+ጻድቁ መድኃኒነ እግዚእ በልጅነታቸው ከሊቁ ካህን አባታቸውና ከሌሎችም መምሕራን ተምረው: ምናኔን መርጠው ገዳም ገብተዋል:: በጾም: በጸሎትና በስግደት ተግተው ጸጋ እግዚአብሔር ሲሰጣቸው ወደ ደብረ በንኮል ሒደው ገዳም መሠረቱ::
+በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መካከለኛው ዘመን (በተለይ ከ13ኛው እስከ 15ኛው መቶ ክ/ዘመን ድረስ ያለው) የብርሃን ዘመን ይባላል:: ምክንያቱም ዘመኑ *ክርስትና ያበበበት: *መጻሕፍት የተደረሱበት: *ስብከተ ወንጌል የተስፋፋበት: *ገዳማዊ ሕይወት የሠመረበት ወቅት በመሆኑ ነው::
+ለዚህ ትልቁ አስተዋጽኦ ደግሞ *አቡነ ተክለ ሃይማኖት: *አቡነ ኤዎስጣቴዎስ: *አባ ሰላማ ካልዕ: *አቡነ ያዕቆብ: *ቅዱሱ ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ: *አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ: *አቡነ መድኃኒነ እግዚእን የመሰሉ አበው መነሳታቸው ነው::
+በተጨማሪም *12ቱ ንቡራነ ዕድ: *7ቱ ከዋክብት: *47ቱ ከዋክብት: *5ቱ ከዋክብት የሚባሉ አበው አስተዋጽኦም ልዩ ነበር:: ከእነዚህ መካከልም የ7ቱ እና የ47ቱ ከዋክብት አስተማሪ: የአበው 3ቱ ሳሙኤሎች (ዘዋልድባ: ዘጣሬጣና ዘቆየጻ): የሌሎችም እልፍ አእላፍ ቅዱሳን አባት የሆኑት አባ መድኃኒነ እግዚእ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ::
+ጻድቁ ቅዱሳኑን ሰብስበው: አስተምረው: አመንኩሰው: መርቀው ሰደው: ሃገራችንን እንዲያበሩ በማድረጋቸው እንደ አባ ኢየሱስ ሞዐ እርሳቸውም "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን" ይባላሉ:: ታላቁ ጻድቅና ሰባኬ ወንጌል አባ ዓቢየ እግዚእም (ጐንደር ውስጥ እባብና ጅብ እንዳይጐዳ የገዘቱ አባት ናቸው) የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ነበሩ ይባላል::
+ጻድቁ መድኃኒነ እግዚእ በተትረፈረፈ የቅድስና ሕይወታቸው ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: አራዊትን ገዝተዋል: በአንበሳ ጀርባ ላይ እቃ ጭነዋል:: ከረዥም የተጋድሎ ሕይወት በኋላም ኅዳር 3 ቀን ዐርፈዋል:: እድሜአቸውም 180 ነው::
"መድኃኒነ እግዚእ አቡነ መስተጋድል:
ምንኩስናሁ ምዑዝ ከመ ኮል:
በመንፈሰ ጸጋ ክሉል::" (መጽሐፈ ሰዓታት)
"ተአምረ ኃይልከ አባ መድኃኒነ እግዚእ አቡነ:
እም አፈ ዜናዊ ሰማዕነ: ወበዓይነ ሥጋ ርኢነ:
መንክርኬ አእላፈ ቤትከ ንሕነ:
ባሕቱ በዝ ተአምሪከ ርድአነ:
ለሰይፈ አርዕድ ንጉሥ ዘወሀብኮ ኪዳነ:
ከመ ረድኤቱ ታፍጥን ጊዜ ጸብዕ ኮነ::" (አርኬ)
+" ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል "+
+የዚህ ቅዱስ ኢትዮዽያዊ ዜና ሕይወት ለሁላችንም ትልቅ ትምርትነት ያለው ነው:: በተለይ በምክንያት ከቅድስና ሕይወት እንዳንርቅ ያግዘናል ብየም ተስፋ አደርጋለሁ:: የቅዱሱ ወላጆች ገላውዴዎስና ኤልሳቤጥ ሲባሉ በምድረ ሽዋ በበጐ ምጽዋታቸው የተመሰከረላቸው ነበሩ::
+ፈጣሪ ሰጥቷቸው ኅዳር 8 ቀን (በበዓለ አርባዕቱ እንስሳ) ወልደውታልና 'ዓምደ ሚካኤል-የሚካኤል ምሰሶ' ሲሉ ሰይመውታል:: ገና በልጅነቱ ብዙዎችን ያስገርም የነበረው ቅዱሱ አንዴ በ3 ዓመቱ ከቅዳሴ መልስ ጠፋቸው::
+ወላጆቹ እያለቀሱ በሁሉ ቦታ ፈለጉት:: ግን ሊገኝ አልቻለም:: በ3ኛው ቀን የሞቱን መታሠቢያ ሊያደርጉ ካህናትና ምዕመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲገቡ ግን ባዩት ነገር ተገረሙ:: ሕጻኑ ዓምደ ሚካኤል ከቤተ መቅደሱ መሃል: ከታቦቱ በታች ካለው መንበር (ከርሠ ሐመር ይሉታል) ቁጭ ብሎ ይጫወታል::
+ያየ ሁሉ 'ዕጹብ ዕጹብ' ሲልም አደነቀ:: ምክንያቱም በተፈጥሮ ሥርዓት ሕጻን ልጅ ያለ ምግብ 3 ቀን መቆየት ስለማይችልና ሕጻኑ በዚያ የቅድስና ሥፍራ ላይ ምንም ሳይጸዳዳ በመገኘቱ ነው::
+ብጹዕ ዓምደ ሚካኤል ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እየተማረ: በጾምና በጸሎት አደገ:: በ14ኛው ክ/ዘመን አጋማሽ ላይ ንጉሥ የነበረው ጻድቁ አፄ ዘርዓ ያዕቆብም ቅዱሱን የሠራዊት አለቃ (ራስ ቢትወደድ): ወይም በዘመኑ አገላለጽ የጦር ሚኒስትር አድርጐ ሾመው::
+መቼም እዚህ ቦታ ላይ ተቀምጦ መልካምን መሥራት ልዩ ነገርን ይጠይቃል:: በተለይ ደግሞ በዙሪያው የሚከቡትን ተንኮለኞች ድል መንሳቱ ቀላል አልነበረም:: ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል ግን በዘመነ ሲመቱ እነዚህን ሠራ:-
1.በጠዋት ተነስቶ ነዳያንን ይሰበስብና ቁርስ: ምሳ ያበላቸዋል:: ይሕም ዕለት ዕለት የማይቋረጥ በመሆኑ ሃብቱ አልቆ ደሃ ሆነ::
2.ከቀትር በኋላ ዘወትር ቆሞ ያስቀድስና ጸበል ተጠምቆ ይጠጣል:: ማታ ብቻ እህልን ይቀምሳል::
3.ሽፍታ ተነሳ ሲባል ወደ ዱር ወርዶ: ጸልዮ: ሽፍታውን አሳምኖት ይመጣል እንጂ አይጐዳውም::
4.ጦርነት በሚመጣ ጊዜ ክተት ሠራዊት ብሎ ይወርዳል:: ግን ለምኖ: ጸልዮ: ታርቆ ይመጣል እንጂ ጥይት እንዲተኮስ አይፈቅድም ነበር::
+በዚህ መንገድ በ3ቱ ነገሥታት (በዘርዐ ያዕቆብ: በዕደ ማርያምና እስክንድር) ዘመን ሁሉ አካባቢውን ሰላም አደረገው:: ዓለም ግን ዓመጸኛ ናትና በአፄ እስክንድር ዘመን (በ1470ዎቹ) በሃሰት ተከሶ ስደት ተፈረደበትና ወደ በርሃ ተጋዘ::
+በዚያም ቅዱስ ሚካኤል ሰማያዊ መናን እየመገበው: ሥጋ ወደሙን እያቀበለው ኖረ:: ትንሽ ቆይቶ ግን የሞት ፍርድ ተፈርዶበት በንጉሡ አደባባይ ተገደለ:: ለ30 ቀናትም በመቃብሩ ላይ የብርሃን ምሰሶ ወረደ በዚህም ንጉሡ በእጅጉ ተጸጸተ::
+" ቅዱስ ኪርያቆስ "+
+ሊቅነትን ከገዳማዊ ሕይወት የደረበው ቅዱስ ኪርያቆስ የቆረንቶስ ሰው ሲሆን አበው "ጥዑመ ቃል-አንደበቱ የሚጣፍጥ" ይሉታል:: ገና በልጅነቱ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲያነብ ከአንደበቱ ማማር: ከነገሩ መሥመር የተነሳ ከዻዻሱ እስከ ሕዝቡ ድረስ ተደመው ያደምጡት ነበር::
+በወጣትነቱ ጣዕመ ዓለምን ንቆ ከቆረንቶስ ኢየሩሳሌም ገብቷል:: ቀጥሎም ወደ ፍልስጥኤም ተጉዞ የታላቁ አባ ሮማኖስ ደቀ መዝሙር ሁኖ መንኩሷል:: በገዳሙ ለበርካታ ዘመናት ሲኖርም እጅግ ብዙ ተአምራትን ሠርቷል::
+በ381 ዓ/ም መቅዶንዮስ: አቡሊናርዮስና ሰባልዮስ በካዱ ጊዜም ለጉባኤው ወደ ቁስጥንጥንያ ከሔዱ ሊቃውንት አንዱ ይሔው ቅዱስ ኪርያቆስ ነው:: ወደ ጉባኤው የሔዱትም ከታላቁ ሊቅና የኢየሩሳሌም ሊቀ ዻዻሳት ቅዱስ ቄርሎስ መንፈሳዊ ጋር ነው::
+ሁለቱ እጅግ ወዳጆች ነበሩና:: በጉባኤውም መናፍቃንን ረትተው: ሃይማኖትን አጽንተው: ሥርዓትን ሠርተው ተመልሰዋል::
ቅዱስ ኪርያቆስም በተረፈ ዘመኑ በቅድስና ኑሮ በዚህች ቀን ዐርፏል::
✝አምላከ አበው የወዳጆቹን የቅድስና ምሥጢር ለእኛም ይግለጽልን:: በረከታቸውንም አትረፍርፎ ይስጠን::
✝ኅዳር 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ጻድቅ (ዘደብረ በንኮል)
2.ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል ጻድቅ (የሠራዊት አለቃ)
3.ቅዱስ ኪርያቆስ ሊቅ
4.ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ ንጉሥ (ልደቱ)
5.ቅዱሳን አትናቴዎስና እህቱ ኢራኢ (ሰማዕታት)
++"+ በረከት በጻድቅ ሰው ራስ ላይ ነው:: የኀጥአንን አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል:: የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው:: የኀጥአን ስም ግን ይጠፋል:: +"+ (ምሳሌ 10:6)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
✝✝✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ✝✝✝
"✝" ኅዳር 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት "✝"
+✝" ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ "✝+
✝ሃገራችን ኢትዮዽያ በሁሉም ዘርፍ ቅድስና ያላቸው ቅዱሳን ባለቤት ናት:: በዘመኑ ያለን ወጣቶችም ሆነ ጐልማሶች ከቤተ ክርስቲያንና ከቅድስና ሕይወት ለምን እንደራቅን ስንጠየቅ ከምንደረድራቸው ምክንያቶች አንዱ ሥራችን ነው::
+ነገር ግን ሥራው በራሱ ኃጢአት እስካልሆነ ድረስ በየትኛውም የሥራ ዘርፍ ቢሆን ቅድስናን ማስጠበቅ እንደሚቻል አበው አሳይተውናል:: ቅዱስ ነአኩቶ ለአብም ከእነዚህ ቅዱሳን አንዱ ነው::
*እርሱ ንጉሥ ነው: ግን ገዳማዊ ሕይወትን በቤተ መንግስቱ ውስጥ ያሳየ ጻድቅ ነው::
*ሁሉ በእጁ ነው: እርሱ ግን ንጹሕና ድንግል ነው::
*እርሱ የጦር መሪ ነው: ግን በእጁ ደም አልፈሰሰም::
*እርሱን 'ወደድንህ: ሞትንልህ' የሚሉ ብዙ ሰዎች በአካባቢው ነበሩት:: ለእርሱ ግን ፍቅር ማለት ክርስቶስ ነበር::
*የሃገር መሪ: የኢትዮዽያ ንጉሠ ነገሥት እንደ መሆኑ እጅግ ባተሌ (busy) ነው:: ግን ደግሞ ለክርስትናው ጊዜ ያጣ ሰው አልነበረም::
+እኛ ቤተ ክርስቲያንን "በሐኪ" ለማለት (ለመሳለም) እንኳ 'ጊዜ የለኝም' ስንል እርሱ ግን አብያተ ክርስቲያናትን ይፈለፍል: ያንጽ: በክህነቱ ያገለግል: ማዕጠንት ያጥን: ለረጅም ሰዓትም ይጸልይ ነበር::
+እኛ 'ሥራ ውያለሁና ደክሞኛል' ብለን ከስግደት ስንርቅ እርሱ ግን ንጉሥ ሆኖ ሳለ: ጦር በፊት: በኋላ: በቀኝና በግራ ተክሎ ይሰግድ ስለ ነበር ደሙ እንደ ውሃ በምድር ላይ ፈሷል:: ይህንን ሁሉ ያደረገው ቅዱሱ የኢትዮዽያ ንጉሠ ነገሥት አፄ ነአኩቶ ለአብ ነው::
"ለመሆኑ ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ ማን ነው?"
#ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ በዛግዌ ሥርወ መንግስት ከነገሡ 11 ነገሥታት አንዱ ሲሆን ከመጨረሻውም 2ኛ ነው:: እርሱን በ12ኛው መቶ ክ/ዘመን የወለዱት ቅዱሱ ንጉሥ ሐርቤ (ገብረ ማርያም) እና መርኬዛ ናት:: ዘመኑ ቅድስና በላስታ ዙሪያ የመላበት በመሆኑ ቅዱስ ሐርቤ ከመነኑ በፊት ነበር ነአኩቶ ለአብን የወለደው::
+እናቱ መርኬዛ እርሱን ልትወልድ ምጥ ተይዛ ሳለ ጀሮዋ ቅዳሴን ይሰማ ነበር:: ቅዳሴው ሲጀመር የጀመራት ምጥ ድርገት ሲወርዱ (ሥጋ ወደሙ ሲሰጥ) ተፈታላትና ልጇን ተገላገለች:: ሕጻኑን አንስታ ስትታቀፈው ዲያቆኑ ማቁረቡን ፈጽሞ "ነአኩቶ" እያለ ሲዞር ሰማችው::
+እዚያው ላይም 'ነአኩቶ ለአብ' (አብን እናመስግነው) ስትል ስም አወጣችለት:: ወዲያው ግን አባቱ ቅዱስ ሐርቤ መንግስቱን ለቅዱስ ላሊበላ ሰጥቶ በርሃ በመግባቱ ቅዱሱ ሕጻን ወደ አጐቱ ላሊበላ ቤተ መንግስት ውስጥ ገባ::
+የቅዱስ ላሊበላ ቤት ደግሞ በቅድስና ያጌጠ ነውና ከርሱና ከሚስቱ (ቅድስት መስቀል ክብራ) ሕጻኑ ነአኩቶ ለአብ ምናኔና ፍቅረ ክርስቶስን ተማረ:: በዘመኑ ብዙ ሊቃውንት ስለ ነበሩ ቅዱሳት መጻሕፍትን በደንብ አጠና:: ክህነት ተቀብሎ ቤተ ክርስቲያንን ሲያገለግልም እድሜው 30 ደረሰ::
+በወቅቱ ቅዱስ ላሊበላና ባለቤቱ መስቀል ክብራ ልጃቸው ይትባረክ እያለ ንግሥናቸውን ለቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አወረሱ:: ቅዱሱ ነአኩቶ ለአብም ምን እንደሚሠራ ሲያስብ አንድ ነገር ተገለጠለት:: ቤተ መንግስቱን እንደሚገባ ካደራጀ በኋላ በቤት ውስጥ አንድ ጉድጓድን በቁመቱ ልክ አስቆፈረ::
+በውስጡም በ4 አቅጣጫ ጦሮችን ተከለባቸው:: ድንግል ካህን ነበረና ቀን ቀን ሃገር ሲያስተዳድር: ቅዳሴ ሲቀድስ: በጾም ይውላል:: ሌሊት ደግሞ ወዳስቆፈረው ቦታ ገብቶ ያለማቁዋረጥ እየጸለየ ይሰግዳል::
+ወደ ምድር ሲሰግድ በፊቱ ያለው ጦር ይወጋዋል:: ቀና ሲል ደግሞ የጀርባው ይቀበለዋል:: እንዲህ እያለ የፈጣሪውን ሕማማት ይካፈላል:: በተለይ ዐርብ ዐርብ ሲሆን ደሙ: እንባውና ላበቱ ተቀላቅሎ ይፈስ ነበር:: እርሱ መስቀሉን ተሸክሞ ጌታውን ይከተል ዘንድ መርጧልና::
+ከተጋድሎው ጐን ለጐን ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አብያተ ክርስቲያናትንም ያንጽ ነበር:: በተለይ በ1211 አካባቢ ያነጻት አሸተን ማርያም ልዩ ናት:: እርሷን ካነጸ በኋላ ከቤተ መንግስቱ በደመና ሠረገላ ተጭኖ እየሔደ ያጥናት: ይቀድስባትም ነበር::
+ታዲያ አንድ ቀን አጥኖ ከቤተ መቅደስ ሲወጣ ብዙ ሥውራን ቅዱሳን መቅደሱን ከበው ተመለከተ:: እርሱም "ወገኖቼ! ከወዴት መወጣችሁ?" ቢላቸው "መዐዛ እጣንህን አሽተን መጣን" ሲሉ መለሱለት:: በዚህ ምክንያትም እስከ ዛሬ ድረስ "አሽተን (አሸተን) ማርያም" ስትባል ትኖራለች::
+ዛሬ ታቦቱ ያለበት ገዳሙም በእርሱ የታነጸ ሲሆን እጅግ ተአምረኛ ቦታ ነው:: ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ የነገሠ በ30 ዓመቱ ነው:: ለ40 ዓመታት በእንዲህ ያለ ቅድስና ኑሮ 70 ዓመት ሞላው:: በዚህ ጊዜም ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ሰላምታንም ሰጠው::
+"ወዳጄ ነአኩቶ ለአብ! አንተ ስለ እኔ ፍቅር ለ40 ዓመታት መከራን ተቀብለሃልና ሞት አያገኝህም:: ከፍልህ ከነ ኤልያስ ጋር ነውና:: የሚያከብርህን አከብረዋለሁ:: ደጅህን የሳመውን: ይህ ቢያቅተው በሩቁ ሆኖ በአድናቆት የተመኘህን: መታሰቢያህን ያደረገውን ሁሉ እምርልሃለሁ" አለው::
+ቀጥሎም "ይሕች ቤት አንተ ስትደማ እንደኖርክባት እርሷም እስከ ምጽዓት ድረስ ለመታሰቢያህ ስትደማ ትኑር" አለው:: እነሆ ዛሬም ድረስ ከመቅደሱ ጸበል ይንጠበጠባል:: ለዚህም ደግሞ እኛ ኃጥአን ምስክሮች ነን:: ሳይገባን የቅዱሱን ደጅ ተመልክተናልና::
+ቅዱስ ነአኩቶ ለአብም የዚህን ዓለም ተጋድሎውን ፈጽሞ ወደ ብሔረ ሕያዋን መላእክት ወስደውታል:: የተሰወረበትን ዕለት ስንክሳር ሕዳር 1 ሲያደርገው አንዳንድ መዛግብት ደግሞ በ3 ነው ይላሉ:: በዙፋኑም ላይ የአጐቱ የላሊበላ ልጅ አፄ ይትባረክ ተተክቷል::
+አምላከ ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ በቃል ኪዳኑ ይማረን:: ከበረከቱም አትረፍርፎ ይስጠኝ::
✝ኅዳር 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
2.ቅዱሳን መክሲሞስና ባልንጀሮቹ (ሰማዕታት)
++"+ ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን: ትንሳኤውን በሚመስል ትንሳኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን:: ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን:: +"+ (ሮሜ. 6:5)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ:: ዼጥሮስም የደጁን መዝጊያ ባንኳኳ ጊዜ ሮዴ የሚሏት አንዲት አገልጋይ ትሰማ ዘንድ ቀረበች:: የዼጥሮስ ድምጽ መሆኑንም ባወቀች ጊዜ ከደስታዋ የተነሳ ደጁን አልከፈተችም:: ነገር ግን ወደ ውስጥ ሮጣ ዼጥሮስ በደጅ ፊት ቆሞ እንዳለ አወራች:: +"+ (ሐዋ. 12:12-15)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በ97 ዓመታቸው አረፉ
ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በጎንደር ክፍለ ሀገር በደብረ ታቦር አውራጃ በፋርጣ ወረዳ ልዩ ስሟ መገንታ ቍስቋም በተባለች ደብር ከቄስ ወርቅነህ ትኩና ከወይዘሮ አንጓች አታሌ በ1916 ዓም ነበር የተወለዱት።
ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ከፍተኛ የሃይማኖት ትምህርትን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ተምረው ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሙሉ እድሚያቸውን ያገለገሉ አባት ነበሩ።ጥቅምት 28 ቀን 2013ዓም በ97 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መፅናናቱን አብዝቶ ይስጣችሁ።
ምንጭ:—EOTC TV
---------------------
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
በዛሬው ዕለት ( ጥቅምት 29) የእግዚአብሔር ወልድ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የተከበረ ቅዱስ በዓል ነው።
ለጌታዬ ለአምላኬ ለመድኃኒቴ ለእግዚአብሔር ወልድ ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና ይገባዋል። ይህንን ዓለም በፍቅር ለፈጠረ ስንበድለው በፍቅር ወርዶ ተወልዶ ተሰቅሎ በቅዱስ በንጹሕ ደሙ ላዳነን። በፍቅር ለገዛን በፍቅር በነጻነት ለሚያኖረን ሁሉን በነጻ ለሰጠን ከሁሉ በላይ ራሱን በቅዱስ መስቀል ላይ ሰጥቶ ከርኩሳን ጠላቶች እጅ ነጻ ላወጣን። ለእርሱ ምስጋና ይገባል ለእርሱ አምልኮ ይገባል ለእርሱ ዕልልታ እና ዝማሬ ይገባል ታላቅነት ውዳሴ ለእርሱ ይገባል ። እርሱ የሰላም አለቃ የፍቅር መገኛ ምንጭ ነው። ለእርሱ ስግደት ይገባል። ከእርሱ ጋር ለቸር አባቱ እግዚአብሔር አብ ለቸር አጽናኝ ለሆነ ለመንፈስቅዱስ አምልኮ ስግደት ምስጋና ውዳሴ ይገባል። አሜን።
የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ምዕ 4 ቁ 4-7
" ሁል ጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ፤ ደግሜ እላለሁ ፥ደስ ይበላችሁ። ገርነታችሁ ለሰው ሁሉ ይታወቅ። ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል። "
በ #MichaelMisrue
በምንኖርበት ዓለም እና በኢትዮጵያ በራሳችን ባመጣነው ኃጥያት እየተጨነቅን ነው። በአራቱም አቅጣጫ መልካም ዜና የለም። ሁሌ የምንሰማው የሚያስፈራ ዜና ነው።ነገር ግን በየትኛውም ጊዜ "እግዚአብሔር ትክክል ነው።" መከራ ሥቃይ እና ችግር በሁለት ነገሮች ምክንያት ይመጣል አንደኛው ልክ እንደ አሁኑ እጅግ በጣም ከባድ በደል እና ኃጥያት ሥንሰራ ለቅጣት ይመጣል። ሁለተኛው ጸጋ እና ክብር እንድናገኝ ደግሞ ይመጣል በዚህ ምሳሌ ከመጽሐፍ ቅዱስ የምናደርገው ጻድቁ ቅዱስ ኢዮብ ነው በመጽሐፈ ኢዮብ ምዕ 1 ቁ 22 ላይ " በዚህ ሁሉ ኢዮብ አልበደለም ለእግዚአብሔርም ስንፍናን አልሰጠም።" በተጨማሪም በምዕ 2 ቁ 10 ላይ " …… በዚህ ሁሉ ኢዮብ በከንፈሩ አልበደለም።" ይላል ። ጻድቁ ቅዱስ ኢዮብ ያን ሁሉ መከራ ሰይጣን ሲያመጣበት በጌታ እግዚአብሔር ፊት በድሎ ኃጥያት ሰርቶ አይደለም ነገር ግን ምን ያህል እምነቱ በእግዚአብሔር ላይ ጠንካራ እና ትልቅ እንደሆነ ታይቶበታል። እግዚአብሔር ራሱ ለቅዱስ ጻድቅ ኢዮብ መስክሮለታል " … በምድር ላይ እንደ እርሱ ፍጹምና ቅን እግዚአብሔርን የሚፈራ ከክፋትም የራቀ ሰው የለም አለው።" ኢዮብ ምዕ 1 ቁ 8። ሌሎች ብዙ ቅዱሳን እና ጻድቃን አባቶቻችን እና እናቶቻችንን ምሳሌ ማድረግ እንችላለን።
"የኛ ግን ከዚህ እጅግ በጣም የራቀ ነው።" እኛ በጌታ እግዚአብሔር ወልድ ፊት እጅግ በጣም ትልልቅ በደሎችን እና ኃጥያቶችን ስንሰራ የነበረው። ስለዚህ ለቅጣት ነው የሚገባን … ግን አሁን ባለን አጭር ጊዜ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ወደ የሚያድነው ይቅርታ ለማድረግ ወደ ሚፈጥነው ንስሐ ከተመለስን ከላይ በሐዋርያው በቅዱስ ጳውሎስ የተጻፈውን ቃል በትክክል በሕይወታችን መስራት ይጀምራል። " ገርነታችሁ" ገርነት ማለት እኔ እንደማምነው አንድ ሰው (በተለይ ክርስትያን) የተለያየ ዓይነት ክፉ ነገር በሰዎች ሲደርስበት በደልን ሳያስብ ይቅርታን በሙሉ ልብ ማድረግ የሚችልበት ክፉ ኃሳቦችን ከልቡ አውጥቶ የሚጥለበት የጸጋ መንገድ ነው። ይህ ጸጋ የሚገኘው ደግሞ በንስሐ እና የመሲሁን የበጉን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና የተከበረ ቅዱስ ደም በመብላት እና በመጠጣት የሚገኝ ጸጋ ነው። "ገርነት" ካለን በደልን የማናስብ ከሆነ ይቅርታን የምናደርግ ከሆነ ለአገርም ለዓለምም ምህረትን እግዚአብሔር ይልካል። አባቶቻችን ቅዱሳን መነኮሳት እንዲህ ይላሉ " ሰው( ክርስትያን) እግዚአብሔርን ማስደሰት ከፈለገ መጀመር ያለበት ንስሐ ከመግባት እና ከቅዱስ ቁርባን ከመቀበል ነው ይላሉ። ስለዚህ ክርስትያኖች ኦርቶዶክሳውያን ከልብ መዘጋጀት ያስፈልጋል የተዘጋጀ ልብ ካለን ሁሌም ደጋግመን በጌታ ደስ ይለናል ቅዱስ ቁርባን ከተቀበልን ገርነታችን በሰው ሁሉ ፊት ይታወቃል ምክንያቱም የበላነው ቅዱስ ሥጋ እና ደም የአምላካችን ነው አምላካችን ደግሞ ገርነትን የተመላ ነው ስንበድለው ኃጥያት በፊቱ ስንሰራ ከዚያ በንስሐ ስንመለስ በደላችንን ሳይቆጥር ይቅር ስለሚለን እኛም ይቅርታን ለበደሉን ሰዎች ለማድረግ አንቸገርም። ንስሐን ስንገባ ቅዱስ ቁርባን ስንቀበል ጌታ ቅርብ እንደሆነ እናውቃለን የንስሐ እና የቅዱስ ቁርባን ሕይወት ካለን በአንዳች ሳንጨነቅ በእግዚአብሔር ፊት ልመናችንን ከምስጋና እና ከምልጃ ጋር እናቀርባለን ከዚያም ውጤቱ የእግዚአብሔር ወልድ የጌታችን የክርስቶስ ኢየሱስ ሰላም አዕምሮአችንን እና ልባችንን ይጠብቃል። ይህ በሕይወታችን እንዲሆን የእግዚአብሔር ወልድ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት የቅድስት ድንግል የእመቤታችን ማርያም ጸሎትና አማላጅነት የቅዱሳን ሰማዕታት የቅድስት ባርባራ እና የቅድስት ዮልያና አማላጅነት አይለየን። አሜን አሜን አሜን።
ክብር ምስጋና አምልኮ ለእግዚአብሔር ወልድ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለቸር አባቱ ለቸር አጽናኝ ለመንፈስቅዱስ አንድ አምላክ ይሁን። አሜን አሜን አሜን።
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞✞✞ ኅዳር 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞
✞✞✞ ዐርባዕቱ እንስሳ ✞✞✞
✞✞✞ እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ መቶ (100): በክፍለ ነገድ አሥር (10) አድርጉዋቸዋል:: አቀማመጣቸውንም በ3 ሰማያትና በ10 ከተሞች (ዓለማት) አድርጉዋል::
+መላእክት ያሉባቸው ከተሞች ከታች ወደ ላይ 'ኤረር: ራማና ኢዮር' ይባላሉ:: አሥሩ ክፍለ ነገድ ደግሞ ከነ አለቆቻቸው ይህንን ይመስላሉ:-
1.አጋእዝት (የቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል: አህን የተረፉት በቅዱስ ሚካኤል ሥር ናቸው)
2.ኪሩቤል (አለቃቸው ኪሩብ)
3.ሱራፌል (አለቃቸው ሱራፊ)
4.ኃይላት (አለቃቸው ሚካኤል)
5.አርባብ (አለቃቸው ገብርኤል)
6.መናብርት (አለቃቸው ሩፋኤል)
7.ስልጣናት (አለቃቸው ሱርያል)
8.መኳንንት (አለቃቸው ሰዳካኤል)
9.ሊቃናት (አለቃቸው ሰላታኤል)
10.መላእክት (አለቃቸው አናንኤል) ናቸው::
+ከእነዚህም *አጋእዝት: *ኪሩቤል *ሱራፌልና *ኃይላት መኖሪያቸው በኢዮር (በ3ኛው ሰማይ) ነው:: *አርባብ: *መናብርትና *ስልጣናት ቤታቸው ራማ (2ኛው ሰማይ) ነው:: *መኩዋንንት: *ሊቃናትና *መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር (በ1ኛው) ሰማይ ነው::
+መላእክት ተፈጥሯቸው እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ ነው:: አይራቡም: አይጠሙም: አይዋለዱም: አይሞቱም:: ተፈጥሯቸውም ረቂቅ ነው:: ተግባራቸውም ዘወትር "ቅዱስ: ቅዱስ: ቅዱስ" እያሉ ፈጣሪያቸውን ማመስገን ነው:: ምግባቸውም ይሔው ነው::
+ዕረፍት ብሎ ነገርን አያውቁም:: "አኮቴቶሙ ዕረፍቶሙ: ወዕረፍቶሙ አኮቴቶሙ" እንዲል:: በተጨማሪም መልአክ ማለት ተላላኪ (አግገልጋይ) ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም: ለመዓትም ይላካሉ::
+ምሕረትን ያወርዳሉ:: ልመናን ያሳርጋሉ:: ቅጡ ሲባሉም ይቀጣሉ:: ስነ ፍጥረት (አራቱ ወቅቶች) እንዳይዛቡ ይጠብቃሉ::
*ዘወትርም ስለ ሰው ልጆች ያማልዳሉ (ዘካ. 1:12)
*ምሥጢርን ይገልጣሉ (ዳን. 9:21)
*ይረዳሉ (ኢያ. 5:13)
*እንዳንሰናከል ይጠብቃሉ (መዝ. 90:11)
*ያድናሉ (መዝ. 33:7)
*ስግደት ይገባቸዋል (መሳ. 13:20, ኢያ. 5:13, ራዕ. 22:8)
*በፍርድ ቀንም ኃጥአንን ከጻድቃን ይለያሉ (ማቴ. 25:31)
*በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ሕይወትና ድኅነት ሲባል ከፈጣሪያቸው የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ሲጠብቁና ፈቃዱን ሲፈጽሙ ይኖራሉ::
+ከእነዚህ ቅዱሳን መላእክት መካከል ደግሞ ትልቁን ሥፍራ ዛሬ የምናከብራቸው ነገደ ኪሩቤል (ዐርባዕቱ እንስሳ) ይይዛሉ:: መንፈሳውያን ከመሆናቸው በላይ መንበረ ጸባኦትን እንዲሸከሙ ስላደላቸው ክብራቸው ታላቅ ነው:: ከመላእክት ወገንም ቅሩባን እነርሱ ናቸው::
+ዘወትርም ስለ ፍጥረታት (ሰዎች: እንስሳት: አራዊትና አዕዋፍ) ምሕረትን ይለምናሉ:: ለዚህም ነው በ4 እንስሳት (በሰው: በንስር: በላምና በአንበሳ) መልክ የተሳሉት:: ቅዱስ መጽሐፍም ስለ እነርሱ ብዙ ይላል:: (ሕዝ. 1:5, ራዕ. 4:6, ኢሳ. 6:1)
+በተለይ ግርማቸው እንደሚያስፈራ ተጽፏል:: "ምሉዓነ ዐዕይንት-ዐይንን የተሞሉ" ይላቸዋል:: ይህንንም መተርጉማን "ምሥጢር አዋቂነታቸውንና ግርማቸውን ያጠይቃል" ሲሉ ተርጉመውታል::
+ዐርባዕቱ እንስሳን 4 ሆነው በስዕል ብናያቸውም "ከመ ርዕየተ እለ ቄጥሩ" እንዲል እያንዳንዱ ከወገብ በላይ አራት በመሆናቸው ተሸካሚዎቹ 16 መልክ አላቸው:: በ2 ክንፋቸው ፊታቸውን: በ2ቱ እግራቸውን ሸፍነው በ2 ክንፋቸው ይበራሉ:: ይህም ብዙ ምሥጢር ሲኖረው ዋናው ግን አርአያ ትእምርተ መስቀል ነው::
+"4ቱ" እንስሳ (ኪሩቤል) በሐዲስ ኪዳንም ልዩ ክብር አላቸው:: 4ቱ ወንጌል ሲጻፍ እየተራዱ ስላጻፉ በስማቸው ተሰይሟል:: ቅዱስ ማቴዎስን ገጸ ሰብእ: ቅዱስ ማርቆስን ገጸ አንበሳ: ቅዱስ ሉቃስን ገጸ ላህም: ቅዱስ ዮሐንስን ገጸ ንስር እየተራዱ ስላጻፏቸው እነሆ እስከ ዛሬ ድረስ 'ዘብእሲ ማቴዎስ': 'ዘአንበሳ ማርቆስ': 'ዘላሕም ሉቃስ' ና 'ዘንስር ዮሐንስ' እየተባሉ ይጠራሉ::
+እነዚህ ቅዱሳን መላእክት የሰው ልጆችን ስለ መራዳታቸውም በብዙ ገድላትና ድርሳናት ላይ ተጽፏል:: የራሳቸውን 'ድርሳነ ዐርባዕቱ እንስሳን' ጨምሮ በገድለ አባ መቃርስና በገድለ አባ ብስንድዮስ ላይ በስፋት ግብራቸው ተጽፏል::
+እኛም ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ክብራቸውን: ረድኤታቸውንና ምልጃቸውን አምነን ዘወትር እናከብራቸዋለን:: አባቶቻችን እንዲህ እያሉ እንደ ጸለዩ:-
"ሰላም ለክሙ ኪሩባውያን አፍራሱ:
ለመሐይምን ወጻድቅ እንተ ወርቅ አክሊለ ርዕሱ:
ኀበ ዝ አምላክ ለእለ ትጸውርዎ በአትሮንሱ:
ለእለ ጌገዩ ወለእለሂ አበሱ:
ሰአሉ መድኃኒተ ወምሕረተ ኅሡ::" (አርኬ)
+" ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ "+
+ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ለቤተ ክርስቲያን የፈፀመውን መልካም ተግባር ያሕል መሥራት የቻለ ንጉሥ በሐዲስ ኪዳን የለም:: ጻድቁ ንጉሥ ከቅድስት እናቱ እሌኒና ከአረማዊ አባቱ ቁንስጣ በበራንጥያ ተወለደ::
+ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ /የመከራ ጊዜ/ ወይም የሰማዕታት ዘመን በመሆኑ ክርስቲያኖች በግፍ የሚጨፈጨፉበት ወቅት ነበር:: ክርስቲያኖችን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት በተደረገው የ40 ዓመታት ዘመቻ አብያተ-መቃድስና መጻሕፍት ተቃጠሉ::
ብዙዎቹ በየበርሃው ተሰደዱ:: ሚሊየኖች በግፍ አለቁ::
+የዚሕን ዘመን መከራ በውል ያልተረዳ ሰው ቅዱስ ቆንጠንጢኖስን ሊያከብር አይችልም:: ምክንያቱም ምክንያቱም ይህን የመከራ ዘመን በፈቃደ እግዚአብሔር አስቁሞ: ቀርነ-ሃይማኖት የቆመው: ብዙ ሥርዓት የተሠራው: ቤተ ክርስቲያንም ያበራችው በዘመኑ ነውና::
+ቅዱሱ ንጉሥ ለሁሉም ነቢያት: ሐዋርያትና ሰማዕታት አብያተ ክርስቲያናትን ራሱ በመሠረታት በቁስጥንጥንያ አንጿል:: በዘመኑ ቤተ ክርስቲያን በሰላም ኖራለት: በኃይለ መስቀሉ ጠላት ጠፍቶለት ኑሮ በዚህች ቀን አርፏል::
+ይህቺ ቀን ታላቁ ንጉሥ በፈለገ ኮቦር ቅዱስ መስቀልን የተመለከተባት ናት:: መክስምያኖስን ሊወጋ ወደ ሮም በተጓዘ ጊዜ በሰማይ ላይ መድኅን መስቀል ተዘርግቶ በላዩ ላይ "ኒኮስጣጣን" የሚል በዮናኒ ልሳን ተጽፎበት ተመልክቷል::
+ይህንንም "በዚህ ጠላትህን ድል ታደርጋለህ" ማለት ነው ብለው ተርጉመውለታል:: እርሱም በጋሻው: በጦሩ: በሰይፉ: በፈረሱ ላይ የመስቀል ምልክትን አድርጐ ማሕደረ ሰይጣን መክስምያኖስን ድል ነስቶታል:: እኛንም በሞገሰ መስቀሉ ይጠብቀን::
+" አባ ቅፍሮንያ ጻድቅ "+
+ይህ ቅዱስ ሰው በቀደመ ሕይወቱ አረማዊ ነበር:: ነገር ግን በውስጡ ቅንነት ተገኝቶበታልና እግዚአብሔር በቸር አጠራሩ ወደ ቤቱ አመጣው:: አባቱ አረማዊ: በዚያውም ላይ አገረ ገዢ ነበርና ለቅፍሮንያ ይህንኑ እያስተማረ አሳድጐታል::
+አንድ ቀን ግን ፈጣሪ ጥሪውን ላከለት:: ይኸውም ገና ወጣት ሳለ የገዳም አበው ያዩትና ትንቢት ይናገሩለታል:: "ይህ ሰው በጐ ክርስቲያን: ምርጥ ዕቃም ይሆናል" ሲሉት እንኳን ሌሎቹ ለእርሱ ለራሱም ምንም አልመሰለውም ነበር:: በዚህ መንገድ (በአረማዊነቱ) ዓመታት አልፈው ቅፍሮንያ የከተማው መኮንን (አገረ ገዢ) ሆነ::
+የግብጽ አረማውያን ገዢዎች እንደ ትልቅ ሥራ የሚያዩት አድባራትን ማቃጠል: ገዳማትን መመዝበር ነውና እርሱም ለዚሁ ሥራ ተነሳ:: ሠራዊትን አስከትቶ በሠረገላው ተጭኖ ወደ አንድ ገዳም ደረሰ:: ልክ የገዳሙን መሬት ሲረግጥ ግን በአንዴ ልቡናው ተሰበረ::
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞✞✞ ኅዳር 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞
=>+"+ እንኩዋን ለቅዱስ # ጊዮርጊስ_ሊቀ_ሰማዕታት እና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ
በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+
✞✞✞ ቅዱስ ጊዮርጊስ ልዳዊ "+
=>መጽሐፈ ገድሉ እንደሚለው የሰማዕታት አለቃቸው: አንድም ሞገሳቸው
ታላቅና ክቡር ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ7 ዓመታት ስቃይ በሁዋላ
ተሰይፏል:: ይሕስ ጥንተ ነገሩ እንደምን ነው ቢሉ:-
+ቅዱሱ የተወለደው ከአባቱ # ዘረንቶስ ( # አንስጣስዮስ ) እና ከእናቱ
# ቴዎብስታ የድሮው ፋርስ ግዛት # ፍልስጥኤም ( # ልዳ ) ውስጥ ነው::
የተባረኩ ወላጆቹ ክርስትናን ጠንቅቀው አስተምረውት አባቱ ይሞታል::
+ቅዱስ ጊዮርጊስ 20 ዓመት ሲሞላው የአባቱን ስልጣን እጅ ለማድረግ
ሲሔድ የቢሩት (የአሁኗ ቤይሩት-ሊባኖስ) ሰዎች ዘንዶ/ደራጎን ሲያመልኩ
አገኛቸው:: እርሱ ግን የከተማውን ሕዝብ አስተምሮ: አሳምኖ: ደራጎኑንም
በፈጣሪው ኃይል ገድሎ መንገዱን ቀጥሏል::
+ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ዱድያኖስና 70 ነገሥታት ዘንድ ሲደርስ ክርስቶስ ተክዶ
ለጣዖት ይሠገድ ነበር:: በዚያች ሰዓት ድንግል እመቤታችን ወደ ሰማዕቱ
መጥታ መከራውንና ክብሩን ነገረችው:: እርሱም በክርስቶስ ስም መሞት
ምርጫው ነበርና ከእመቤታችን ተባርኮ ወደ ምስክርነት አደባባይ (ዐውደ
ስምዕ) ደረሰ::
+ከዚያም ለተከታታይ 7 ዓመታት ብዙ ጸዋትወ መከራዎችን ተቀበለ:: 3 ጊዜ
ሙቶ ተነሳ:: ከሰው ልጅ የተፈጥሮ ትዕግስት በላይ የሆነ ስቃይን ስለ ቀናች
ሃይማኖት ሲል በመቀበሉ የሰማዕታት አለቃቸው: ፀሐይና የንጋት ኮከብ በሚል
ይጠራል::
"ተውላጠ ጻማሁ ወሕማሙ:
ዘተለዐለ ሞገሰ ስሙ" እንዲል መጽሐፍ::
+ከ7 ዓመታት መከራ በሁዋላም ከብዙ ተዓምራት ጋር ተሰይፎ ደም: ውሃና
ወተት ከአንገቱ ፈሷል:: 7 አክሊላትም ወርደውለታል::
=>ይህቺ ዕለት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ኃያል ቅዳሴ ቤቱ ናት:: እርሱ በ390ዎቹ
አካባቢ ሰማዕት ከሆነ ከጥቂጥ ዓመታት በሁዋላ በዚያው በሃገሩ ደብር
አንጸው: አጽሙን አፍልሠው በዚህች ቀን ቀድሰዋታል::
+ቅዱሱ ሰማዕት ከሰማዕትነቱ በፊትም ሆነ በሁዋላ ተአምረኛ ነውና አንዷን
እንመልከት:: በዘመኑ የክርስቲያኖችን ደም ሲያፈሱ ከነበሩ አራዊት (ነገሥታት)
መካከል አንዱ የሆነው ዲዮቅልጢያኖስ ርጉም የ47 ሚሊየን ክርስቲያኖችን
ደም አፍስሶ ነበርና ፈጣሪ ደመ ሰማዕታትን የሚበቀልበት ጊዜ ደረሰ::
+በ305 ዓ/ም አካባቢ አረመኔው ንጉሥ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን
ተአምረኛነት ሰምቶ እንዲያፈርሱት ሠራዊት ላከ:: የሠራዊቱ አለቃም ወደ ቤተ
ክርስቲያኑ ገብቶ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስዕል ላይ ተሳለቀ::
+ከፊቱ የነበረውን ቀንዲል በሰይፍ እመታለሁ ሲል ግን ቀንዲሉ ተገልብጦ
መሐል አናቱን መታው:: እንደ እብድ ሆኖ ሞተ:: ሠራዊቱም ሰምቶ ወደ ንጉሡ
ሸሸ:: ይሕን ሰምቶ የተበሳጨው ዲዮቅልጢያኖስ ግን ራሱ ሊያፈርሰው ሔደ::
ከቤተ ክርስቲያኑ በር ላይ ሲደርስ ሚካኤልና ገብርኤል ዐይኑን አጠፉት::
+እገባለሁ ሲል ቅዱስ ጊዮርጊስ ከላይ መረዋውን (ደወሉን) ለቀቀበት:: ራሱን
ቢመታው ደነዘዘ:: የብዙ ቅዱሳንን ደም የጠጣው ርጉሙ ንጉሥም አብዶ ለ7
ዓመታት ፍርፋሪ ሲለምን ኑሮሰ ይጣን ከገደል ጫፍ ወርውሮ ገድሎታል::
=>አምላካችን እግዚአብሔር ከኃያሉ ሰማዕት ጽናትና ትእግስት: ከበረከቱም
ይክፈለን::
+" ቅዱስ ጊዮርጊስ እስክንድርያዊ "+
=>በቤተ ክርስቲያን 'ጊዮርጊስ' የሚባሉ ብዙ ቅዱሳን አሉ:: ከልዳዊው
ቀጥሎም ይህንን ግብጻዊ ሰማዕት እንጠቅሳለን:: ስሙ ጊዮርጊስ የተባለውም
በታላቁ ሰማዕት አማላጅነት ስለ ተገኘ ነው::
+አባቱ ኅዳር 7 ቀን የሊቀ ሰማዕታትን ቅዳሴ ቤት ሊያከብር ሒዶ ስለተማጸኑ
የሚስቱ ማሕጸን ተከፍቶለት ልጅ ወልዷል:: ስሙንም ጊዮርጊስ ብሎታል::
ባደገም ጊዜ እጅግ ብርቱ ክርስቲያን ሆነ::
+የግብጻዊ ቅዱስ ጊዮርጊስ ብርታቱ ምንድን ነው ቢሉ:-ንጹሕ አምልኮቱ
ጾምና: ጸሎቱ: በጐ ምጽዋቱ ነው:: "ስም ይመርሕ ኀበ ግብር-ስም ወደ
ተግባር ይመራል" እንዲሉ አበው የሰማዕቱን ስም ይዞ እሱም ይሔው እድል
ገጠመው::
+በአጋጣሚ ወላጆቹ ሲሞቱ የሚኖረው ከከተማው መኮንን ቤት ነበር::
ምክንያቱም የመኮንኑ ሚስት እህቱ ናትና:: ችግሩ ግን መኮንኑ አርማንዮስ
ጣዖት አምላኪ: በዚያ ላይ ጨካኝ መሆኑ ነው::
+አንድ ቀን ግብጻዊ ቅዱስ ጊዮርጊስ የመኮንኑን ሴት ልጅ ወደ በርሃ ወስዶ
የደብረ ቁስቁዋም መነኮሳትን ዝማሬ አሰማት:: ክርስትናንም አስተማራት::
ይህንን የሰማው መኮንኑ ግን በብስጭት ቅዱስ ጊዮርጊስንና የራሱን ሴት ልጅ
በአደባባይ አሰይፏቸዋል:: የክብርን አክሊልም ተቀዳጅተዋል::
+" ቅዱሳን ዘኖቢስና ዘኖብያ "+
=>እነዚህ ቅዱሳን እናትና ልጅ ናቸው:: ዘኖብያ እናቱ ስትሆን ዘኖቢስ ደግሞ
ወጣት ልጇ ነው:: የቅዱሳኑ ሃገር ደግሞ ተበይስ ትባላለች:: በዘመነ ሰማዕታት
ድንቅ በሆነ ሕይወታቸውና ተአምራቸው እንደ ኮከብ አብርተዋል:: ከ5 ጊዜ
በላይም ከተደገሰላቸው የሞት ወጥመድ በእግዚአብሔር ኃይል አምልጠዋል::
+"ክርስትናችን አንክድም: ከክርስቶስ ፍቅር አንለይም በማለታቸው:-
1.ልብሳቸውን ገፈው: በዓየር ላይ ሰቅለው: ደማቸው እስኪንጠፈጠፍ
ገረፏቸው:: በክርስቶስ ኃይል ተረፉ::
2.የእንጨት መስቀሎችን አሰርተው በአደባባይ ቸንክረው ሰቀሏቸው:: ከዚህም
ዳኑ::
3.2 ወንበሮች ላይ ችንካሮችን ተክለው በዚያ ላይ አስቀመጧቸው:: አሁንም
በፈጣሪ ኃይል ዳኑ::
4.ጥልቅ ጉድጉዋድ ተቆፍሮ: እሳትም ነዶ በዚያ ውስጥ ተጨመሩ:: ቅዱስ
መልአክ ግን ወርዶ አጠፋላቸው::
5.አንዴ ደግሞ በቤት (በውሽባ ቤት) እሳት ነዶ በውስጥ ተጨመሩና
ተዘጋባቸው:: እግዚአብሔር ግን ከዚህም ታደጋቸው:: ስለ ክብራቸውም ቅዱስ
መልአክ ወርዶ እነሱን አክብሮ: መኮንኑን ዙፋኑን አሸክሞ በአደባባይ
አዙሮታል::
+አንዴም ጋን አሸክሞ በሁዋላቸው አስከትሎታል:: በነዚህ ሁሉ ድንቆች ብዙ
ሕዝብ እያመነ በሰማዕትነት ሙቷል:: በመጨረሻ በዚህ ቀን ዘኖብያና ዘኖቢስ
ሲሰየፉ መብረቅ ወርዶ 54 አሕዛብን ገድሏል:: በዚህም መኮንኑ ተገርሞ
በክርስቶስ አምኗል::
+" አባ ሚናስ ዘተመይ "+
=>ይህ ቅዱስ አባት ደግሞ ጣዕመ ሕይወቱ ድንቅ ነው:: ክርስቲያን ወላጆቹ
በሥርዓት አሳድገው በተክሊል አጋቡት:: ወደ ሙሽራይቱ ገብቶም "እህቴ! ይህ
ዓለም ኃላፊ ነውና ለምን በድንግልና አንኖርም?" አላት::
+እርሷም በደስታ "ይሁን" አለችው:: ለበርካታ ዓመታትም ቀን ቀን ሥራቸውን
ሲሠሩ: እንግዳ ሲቀበሉ ይውላሉ:: ሌሊት ደግሞ ወገባቸውን ታጥቀው
ሲሰግዱና ሲጸልዩ ያድራሉ::
+ከዓመታት የቅድስና ሕይወት በሁዋላም ቅዱስ ሚናስ ሚስቱን አስፈቅዶ በርሃ
ገብቷል:: በተጋድሎ ሳለም እግዚአብሔር ለእረኝነት መርጦት: ተመይ
በምትባል የግብጽ አውራጃ ላይ ዽዽስናን ተሹሟል:: በዚያም እስካረጀ ድረስ
ተጋድሎ በዚህች ቀን ዐርፏል::
=>እንደ ደመና የከበቡን የእነዚህ ሁሉ ቅዱሳን አምላክ በቸርነቱ ይማረን::
ከበረከታቸውም ይክፈለን::
=>ኅዳር 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት (ቅዳሴ ቤቱ)
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ እስክንድርያዊ
3.ቅዱሳን ዘኖቢስና ዘኖብያ (ሰማዕታት)
4.ቅዱስ ሚናስ ዘተመይ
5.ቅዱሳን መርቆሬዎስና ዮሐንስ (ጻድቃን ወሰማዕት)
6.አባ ናሕርው ሰማዕት
=>ወርሐዊ በዓላት
1.
++"+ ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕጻኗን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ:: አሕዛብንም ሁሉ በብረት ዘንግ ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ: ወንድ ልጅ ወለደች:: ልጇም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ:: ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቧት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ሥፍራ ወደ በረሃ ሸሸች:: +"+ (ራዕይ. 12:4-7)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
+ "ልጅሽ በገነት ሐሴትን ያደርጋል:: አንቺ ግን ራሴን ከተቀበረችበት አውጪ" አላት:: ወደ ጠቆማት ቦታ በመሪ ስትቆፍር ብርሃን ወጥቶ ዐይኗ በራላት:: በታላቅ ሐሴትም ቅድስት ራሱን ወደ ሃገሯ ወስዳታለች::
=>አምላከ ቅዱሳን የቀደምቶቻችንን የዋህነት ለእኛም ያድለን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
=>ኅዳር 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ታላቁ ቅዱስ ዮሐኒ (ዘትግራይ)
2.አባ አሞኒ ዘናሕሶ
3.ቅዱስ ለንጊኖስ ሰማዕት
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት
5.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሰማዕት
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
3.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ)
4.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ
=>+"+ ወደ ጌታ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን እርሱ ፈጽሞ እንደ ሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም:: ነገር ግን ከጭፍሮች አንዱ ጐኑን በጦር ወጋው:: ወዲያውም ደምና ውሃ ወጣ:: ያየውም መስክሯል:: ምስክሩም እውነት ነው:: እናንተም ደግሞ ታምኑ ዘንድ: እርሱ እውነት እንዲናገር ያውቃል:: ይህ የሆነ:- "ከእርሱ አጥንት አይሰበርም" የሚል የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው:: ደግሞም ሌላው መጽሐፍ:- "የወጉትን ያዩታል" ይላል:: +"+ (ዮሐ. 19:33)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
✝✝✝ እንኩዋን ለቅዱሳን ሰማዕታት "ቶማስ" : "ያዕቆብ ወዮሐንስ" : "አቢማኮስ ወአዛርያኖስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✝✝
+"+ ቅዱስ ቶማስ ዘደማስቆ +"+
=>ቅዱስ ቶማስ በ7ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ተወልዶ ያደገ ሶርያዊ ክርስቲያን ነው:: ከልጅነቱ እንደሚገባ መጻሕፍትን ተምሮ ለዲቁና: ለቅስና: ከዚያም ለዽዽስና በቅቷል:: በወቅቱ የሶርያ ዋና ከተማ በሆነችው ደማስቆ ላይ ተሹሞ ያገለግልም ነበር::
+ታዲያ ዘመኑ በየቦታው ደም የሚፈስበት ነበርና የክርስቶስን መንጋ መጠበቁ ቀላልና የዋዛ ሥራ አልነበረም:: በዘመኑ የክርስቲያኖችን ደም ያፈሱ የነበሩት ደግሞ ተንባላት (የመሐመድ ተከታዮች) ናቸው:: 7ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲደርስም ተንባላት ግብጽንና ሶርያን በቁጥጥር ሥር በማድረጋቸው ክርስቲያኖች ተቸገሩ::
+በወቅቱም ቅዱስ ቶማስ ሲያስተምር የሰማው አንድ መሐመዳዊ "እንከራከር" አለው:: ቅዱሱም ሊቅ ነበርና ስለ መሐመድ ሐሰተኛነት: ስለ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት ካስረዳው በሁዋላ ንጹሕና ሰማያዊ ሕግ ቅዱስ ወንጌል እንጂ ቁርዓን እንዳልሆነ ነገረው::
+በአደባባይ በመረታቱ ያፈረው መሐመዳዊም በብሽቀት ሒዶ ለደማስቆው ገዢ ከሰሰው:: ቅዱስ ቶማስም ተይዞ ቀረበ:: "እንዴት እምነታችን እስልምናን ትሳደባለህ?" ቢለው ቅዱሱ "እውነቱን ተናገርኩ እንጂ አልተሳደብኩም" ሲል መለሰለት::
+መኮንኑም "እሺ! ክርስቶስ ማን ነው? ስለ ወንጌልና ቁርዓንስ ምን ትላለህ?" ሲል የተሳለ ሰይፍ አውጥቶ ጠየቀው:: የቀናችው እመነት ክርስትና ክብርነቷ በሰማይ ነውና መጨከንን ትጠይቃለች::
+ቅዱስ ቶማስ ምንም ሳይፈራ "ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰማይና የምድር ፈጣሪና አምላክ ነው::
ቅዱስ ወንጌል ሰማያዊና የሕይወት ሕግ ሲሆን ቁርዓን ደግሞ የመሐመድ የፈጠራ መጽሐፍ ነው::" ይህንን የሰማው መኮንን በቁጣ አንገቱን እንዲመቱት አዘዘ:: ቅዱስ ቶማስም በዚህች ቀን ስለ ቀናች ሃይማኖቱ አንገቱን ሰጠ::
+"+ ቅዱሳን ያዕቆብ ወዮሐንስ +"+
=>አሁን ደግሞ ወደ 4ኛው መቶ ክ/ዘመን ተመልሰን: ወደ ምድረ ፋርስ (ኢራን) ወርደን ቅዱሳንን እናዘክር:: እነዚህ ቅዱሳንም በሃገረ ፋርስ (ኢራን): በመንግስተ ሳቦር ዘመን የነበሩ አበው ናቸው:: ሳቦር ማለት ጸሐይንና እሳትን የሚያመልክና እጅግ ጨካኝ የነበረ ንጉሥ ነው::
+ቅዱሳኑ ያዕቆብና ዮሐንስ የሐዋርያትን ስም ብቻ ሳይሆን ግብራቸውን: ቅድስናቸውንም የያዙ ነበሩ:: ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት ባይሆንም ፋርስ ግን በዚህ ዘመንም ለክርስቲያኖች የግፍ ከተማ ነበረች::
+ከቅዱስ ጊዮርጊስ እስከ ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ: ከቅዱስ መርምሕናም እስከ ቅዱስ ኮቶሎስ ሰማዕትነትን የተቀበሉት በዚህችው ሃገር ውስጥ ነው:: ቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስም ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በልኩ ተምረው: መጻሕፍትንም ተረድተው ለክህነት ተመርጠዋል::
+በሁዋላም ቤተ ክርስትያን "ይገባቹሃል" ስትል ዻዻሳት አድርጋ ሾመቻቸው:: እነርሱም አላሳፈሯትም:: የክርስቶስን መንጋ እያስተማሩ: እየናዘዙ ጠበቁላት:: ንጉሡ ሳቦር ግን ሕዝቡን ለፀለሐይና ለእሳት ሊያሰግድ ላደረገው ጥረት እንቅፋት ሁነውበታልና ጠላቸው::
+በወታደሮቹ አስይዞም በፍርድ አደባባይ አቆማቸው:: ሕዝቡን በአዋጅ ጠርቶ: አስፈሪ እሳት አስነድዶ "ሕዝቡ ለፀሐይ እንዲሰግድ እዘዙ" ቢላቸው "እንቢ" አሉት::
+ከነ ልብሳቸው አንስተው ወደ እሳቱ ወረወሯቸው:: ቅዱሳኑም በመከራው (በነደደው እሳት) መካከል ሆነው ለሕዝቡ ተናገሩ::
"አምላክ አንድ እግዚአብሔር ነውና እንዲህ በሃይማኖታችሁ ጽኑ" አሏቸው:: እሳቱም አቃጥሎ ገድሏቸው የክብርን አክሊል ተቀዳጁ::
+"+ ቅዱሳን አቢማኮስ ወአዛርያኖስ +"+
=>አሁን ደግሞ ወደ 3ኛው መቶ ክ/ዘመን: ወደ ዋናው ዘመነ ሰማዕታት እንመለስ:: በዘመነ ሰማዕታት ከነበሩ ቅዱሳን ሰማዕታት 2ቱ አቢማኮስና አዛርያኖስ ናቸው:: አውሬዎቹ መክስምያኖስና ዲዮቅልጥያኖስ ዓለምን ለ2 ተካፍለው በክርስቲያኖች ላይ ግፍን ሲሰሩ 2ቱ ቅዱሳን በሮም ግዛት ሥር ይኖሩ ነበር::
+በዘመኑ እንኩዋን ቤተ ክርስቲያን ማነጸ: መዘመር: እምነትን መግለጥ ይቅርና ሲያማትቡ መታየት እንኩዋ ያስገድል ነበር:: ነገሥታቱ የሾሟቸው ተከታዮቻቸው ክርስቲያኖችን ከዋሉበት አላሳድር: ካደሩበትም አላውል አሉ::
+ታላቅ ግፍ: ሰቆቃና ጭንቅ በሆነበት በዚያ ወራት የሞተው ሙቶ እኩሉ ሲሰደድ: አቢማኮስና አዛርያኖስ ግን በከተማ መሐል ተረጋግተው ክርስቶስን ያመልኩ ነበር:: ይህም ተደርሶባቸው ተከሰሱና ተይዘው ቀረቡ::
+መኮንኑ 2ቱን ክርስቲያን ወጣቶች ሲመለከታቸው ምንም የፍርሃት ምልክት አልተመለከተባቸውምና ተገረመ:: "ማንን ታመልካላችሁ?" አላቸው:: እነርሱም "የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን!" ሲሉ መለሱለት::
+"ክርስቶስን ትክዳላችሁ ወይስ ትሞታላችሁ?" ቢላቸው "ሰነፍ!" ሲሉ በአደባባይ ገሰጹት:: "የፈጠረ: ያከበረ: ሥጋውን ደሙን የሰጠ ጌታ እንዴት ይካዳል?!" ሲሉም እቅጩን ነገሩት:: በድፍረታቸው የደነገጠው መኮንኑም በዚያች ሰዓት ሞትን አዘዘባቸው:: በዚህች ቀንም አንገታቸውን ተሰይፈው ለክብረ ሰማዕት በቅተዋል::
=>አምላከ ቅዱሳን ሰማዕታት በነርሱ ያሳደረውን ትእግስትና ጽናት በእኛም ላይ ያሳድርልን:: ከበረከታቸውም ያድለን::
=>ኅዳር 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ቶማስ ዘደማስቆ
2.ቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስ
3.ቅዱሳን አቢማኮስ ወአዛርያኖስ
4.አባ አበጊዶ ዘትግራይ
5.ታላቁ አባ ዘካርያስ
6.ጉባኤ ቅዱሳን ሰማዕታት
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ
2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት)
=>+"+ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን?
'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን'
ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው::
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን:: +"+ (ሮሜ. 8:35-38)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
✝✝✝ እንኩዋን ለቅዱሳን ሰማዕታት "ቶማስ" : "ያዕቆብ ወዮሐንስ" : "አቢማኮስ ወአዛርያኖስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✝✝
+"+ ቅዱስ ቶማስ ዘደማስቆ +"+
=>ቅዱስ ቶማስ በ7ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ተወልዶ ያደገ ሶርያዊ ክርስቲያን ነው:: ከልጅነቱ እንደሚገባ መጻሕፍትን ተምሮ ለዲቁና: ለቅስና: ከዚያም ለዽዽስና በቅቷል:: በወቅቱ የሶርያ ዋና ከተማ በሆነችው ደማስቆ ላይ ተሹሞ ያገለግልም ነበር::
+ታዲያ ዘመኑ በየቦታው ደም የሚፈስበት ነበርና የክርስቶስን መንጋ መጠበቁ ቀላልና የዋዛ ሥራ አልነበረም:: በዘመኑ የክርስቲያኖችን ደም ያፈሱ የነበሩት ደግሞ ተንባላት (የመሐመድ ተከታዮች) ናቸው:: 7ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲደርስም ተንባላት ግብጽንና ሶርያን በቁጥጥር ሥር በማድረጋቸው ክርስቲያኖች ተቸገሩ::
+በወቅቱም ቅዱስ ቶማስ ሲያስተምር የሰማው አንድ መሐመዳዊ "እንከራከር" አለው:: ቅዱሱም ሊቅ ነበርና ስለ መሐመድ ሐሰተኛነት: ስለ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት ካስረዳው በሁዋላ ንጹሕና ሰማያዊ ሕግ ቅዱስ ወንጌል እንጂ ቁርዓን እንዳልሆነ ነገረው::
+በአደባባይ በመረታቱ ያፈረው መሐመዳዊም በብሽቀት ሒዶ ለደማስቆው ገዢ ከሰሰው:: ቅዱስ ቶማስም ተይዞ ቀረበ:: "እንዴት እምነታችን እስልምናን ትሳደባለህ?" ቢለው ቅዱሱ "እውነቱን ተናገርኩ እንጂ አልተሳደብኩም" ሲል መለሰለት::
+መኮንኑም "እሺ! ክርስቶስ ማን ነው? ስለ ወንጌልና ቁርዓንስ ምን ትላለህ?" ሲል የተሳለ ሰይፍ አውጥቶ ጠየቀው:: የቀናችው እመነት ክርስትና ክብርነቷ በሰማይ ነውና መጨከንን ትጠይቃለች::
+ቅዱስ ቶማስ ምንም ሳይፈራ "ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰማይና የምድር ፈጣሪና አምላክ ነው::
ቅዱስ ወንጌል ሰማያዊና የሕይወት ሕግ ሲሆን ቁርዓን ደግሞ የመሐመድ የፈጠራ መጽሐፍ ነው::" ይህንን የሰማው መኮንን በቁጣ አንገቱን እንዲመቱት አዘዘ:: ቅዱስ ቶማስም በዚህች ቀን ስለ ቀናች ሃይማኖቱ አንገቱን ሰጠ::
+"+ ቅዱሳን ያዕቆብ ወዮሐንስ +"+
=>አሁን ደግሞ ወደ 4ኛው መቶ ክ/ዘመን ተመልሰን: ወደ ምድረ ፋርስ (ኢራን) ወርደን ቅዱሳንን እናዘክር:: እነዚህ ቅዱሳንም በሃገረ ፋርስ (ኢራን): በመንግስተ ሳቦር ዘመን የነበሩ አበው ናቸው:: ሳቦር ማለት ጸሐይንና እሳትን የሚያመልክና እጅግ ጨካኝ የነበረ ንጉሥ ነው::
+ቅዱሳኑ ያዕቆብና ዮሐንስ የሐዋርያትን ስም ብቻ ሳይሆን ግብራቸውን: ቅድስናቸውንም የያዙ ነበሩ:: ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት ባይሆንም ፋርስ ግን በዚህ ዘመንም ለክርስቲያኖች የግፍ ከተማ ነበረች::
+ከቅዱስ ጊዮርጊስ እስከ ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ: ከቅዱስ መርምሕናም እስከ ቅዱስ ኮቶሎስ ሰማዕትነትን የተቀበሉት በዚህችው ሃገር ውስጥ ነው:: ቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስም ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በልኩ ተምረው: መጻሕፍትንም ተረድተው ለክህነት ተመርጠዋል::
+በሁዋላም ቤተ ክርስትያን "ይገባቹሃል" ስትል ዻዻሳት አድርጋ ሾመቻቸው:: እነርሱም አላሳፈሯትም:: የክርስቶስን መንጋ እያስተማሩ: እየናዘዙ ጠበቁላት:: ንጉሡ ሳቦር ግን ሕዝቡን ለፀለሐይና ለእሳት ሊያሰግድ ላደረገው ጥረት እንቅፋት ሁነውበታልና ጠላቸው::
+በወታደሮቹ አስይዞም በፍርድ አደባባይ አቆማቸው:: ሕዝቡን በአዋጅ ጠርቶ: አስፈሪ እሳት አስነድዶ "ሕዝቡ ለፀሐይ እንዲሰግድ እዘዙ" ቢላቸው "እንቢ" አሉት::
+ከነ ልብሳቸው አንስተው ወደ እሳቱ ወረወሯቸው:: ቅዱሳኑም በመከራው (በነደደው እሳት) መካከል ሆነው ለሕዝቡ ተናገሩ::
"አምላክ አንድ እግዚአብሔር ነውና እንዲህ በሃይማኖታችሁ ጽኑ" አሏቸው:: እሳቱም አቃጥሎ ገድሏቸው የክብርን አክሊል ተቀዳጁ::
+"+ ቅዱሳን አቢማኮስ ወአዛርያኖስ +"+
=>አሁን ደግሞ ወደ 3ኛው መቶ ክ/ዘመን: ወደ ዋናው ዘመነ ሰማዕታት እንመለስ:: በዘመነ ሰማዕታት ከነበሩ ቅዱሳን ሰማዕታት 2ቱ አቢማኮስና አዛርያኖስ ናቸው:: አውሬዎቹ መክስምያኖስና ዲዮቅልጥያኖስ ዓለምን ለ2 ተካፍለው በክርስቲያኖች ላይ ግፍን ሲሰሩ 2ቱ ቅዱሳን በሮም ግዛት ሥር ይኖሩ ነበር::
+በዘመኑ እንኩዋን ቤተ ክርስቲያን ማነጸ: መዘመር: እምነትን መግለጥ ይቅርና ሲያማትቡ መታየት እንኩዋ ያስገድል ነበር:: ነገሥታቱ የሾሟቸው ተከታዮቻቸው ክርስቲያኖችን ከዋሉበት አላሳድር: ካደሩበትም አላውል አሉ::
+ታላቅ ግፍ: ሰቆቃና ጭንቅ በሆነበት በዚያ ወራት የሞተው ሙቶ እኩሉ ሲሰደድ: አቢማኮስና አዛርያኖስ ግን በከተማ መሐል ተረጋግተው ክርስቶስን ያመልኩ ነበር:: ይህም ተደርሶባቸው ተከሰሱና ተይዘው ቀረቡ::
+መኮንኑ 2ቱን ክርስቲያን ወጣቶች ሲመለከታቸው ምንም የፍርሃት ምልክት አልተመለከተባቸውምና ተገረመ:: "ማንን ታመልካላችሁ?" አላቸው:: እነርሱም "የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን!" ሲሉ መለሱለት::
+"ክርስቶስን ትክዳላችሁ ወይስ ትሞታላችሁ?" ቢላቸው "ሰነፍ!" ሲሉ በአደባባይ ገሰጹት:: "የፈጠረ: ያከበረ: ሥጋውን ደሙን የሰጠ ጌታ እንዴት ይካዳል?!" ሲሉም እቅጩን ነገሩት:: በድፍረታቸው የደነገጠው መኮንኑም በዚያች ሰዓት ሞትን አዘዘባቸው:: በዚህች ቀንም አንገታቸውን ተሰይፈው ለክብረ ሰማዕት በቅተዋል::
=>አምላከ ቅዱሳን ሰማዕታት በነርሱ ያሳደረውን ትእግስትና ጽናት በእኛም ላይ ያሳድርልን:: ከበረከታቸውም ያድለን::
=>ኅዳር 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ቶማስ ዘደማስቆ
2.ቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስ
3.ቅዱሳን አቢማኮስ ወአዛርያኖስ
4.አባ አበጊዶ ዘትግራይ
5.ታላቁ አባ ዘካርያስ
6.ጉባኤ ቅዱሳን ሰማዕታት
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ
2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት)
=>+"+ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን?
'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን'
ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው::
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን:: +"+ (ሮሜ. 8:35-38)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
✝✝✝ እንኩዋን ለቅዱሳን ሰማዕታት "ቶማስ" : "ያዕቆብ ወዮሐንስ" : "አቢማኮስ ወአዛርያኖስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✝✝
+"+ ቅዱስ ቶማስ ዘደማስቆ +"+
=>ቅዱስ ቶማስ በ7ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ተወልዶ ያደገ ሶርያዊ ክርስቲያን ነው:: ከልጅነቱ እንደሚገባ መጻሕፍትን ተምሮ ለዲቁና: ለቅስና: ከዚያም ለዽዽስና በቅቷል:: በወቅቱ የሶርያ ዋና ከተማ በሆነችው ደማስቆ ላይ ተሹሞ ያገለግልም ነበር::
+ታዲያ ዘመኑ በየቦታው ደም የሚፈስበት ነበርና የክርስቶስን መንጋ መጠበቁ ቀላልና የዋዛ ሥራ አልነበረም:: በዘመኑ የክርስቲያኖችን ደም ያፈሱ የነበሩት ደግሞ ተንባላት (የመሐመድ ተከታዮች) ናቸው:: 7ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲደርስም ተንባላት ግብጽንና ሶርያን በቁጥጥር ሥር በማድረጋቸው ክርስቲያኖች ተቸገሩ::
+በወቅቱም ቅዱስ ቶማስ ሲያስተምር የሰማው አንድ መሐመዳዊ "እንከራከር" አለው:: ቅዱሱም ሊቅ ነበርና ስለ መሐመድ ሐሰተኛነት: ስለ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት ካስረዳው በሁዋላ ንጹሕና ሰማያዊ ሕግ ቅዱስ ወንጌል እንጂ ቁርዓን እንዳልሆነ ነገረው::
+በአደባባይ በመረታቱ ያፈረው መሐመዳዊም በብሽቀት ሒዶ ለደማስቆው ገዢ ከሰሰው:: ቅዱስ ቶማስም ተይዞ ቀረበ:: "እንዴት እምነታችን እስልምናን ትሳደባለህ?" ቢለው ቅዱሱ "እውነቱን ተናገርኩ እንጂ አልተሳደብኩም" ሲል መለሰለት::
+መኮንኑም "እሺ! ክርስቶስ ማን ነው? ስለ ወንጌልና ቁርዓንስ ምን ትላለህ?" ሲል የተሳለ ሰይፍ አውጥቶ ጠየቀው:: የቀናችው እመነት ክርስትና ክብርነቷ በሰማይ ነውና መጨከንን ትጠይቃለች::
+ቅዱስ ቶማስ ምንም ሳይፈራ "ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰማይና የምድር ፈጣሪና አምላክ ነው::
ቅዱስ ወንጌል ሰማያዊና የሕይወት ሕግ ሲሆን ቁርዓን ደግሞ የመሐመድ የፈጠራ መጽሐፍ ነው::" ይህንን የሰማው መኮንን በቁጣ አንገቱን እንዲመቱት አዘዘ:: ቅዱስ ቶማስም በዚህች ቀን ስለ ቀናች ሃይማኖቱ አንገቱን ሰጠ::
+"+ ቅዱሳን ያዕቆብ ወዮሐንስ +"+
=>አሁን ደግሞ ወደ 4ኛው መቶ ክ/ዘመን ተመልሰን: ወደ ምድረ ፋርስ (ኢራን) ወርደን ቅዱሳንን እናዘክር:: እነዚህ ቅዱሳንም በሃገረ ፋርስ (ኢራን): በመንግስተ ሳቦር ዘመን የነበሩ አበው ናቸው:: ሳቦር ማለት ጸሐይንና እሳትን የሚያመልክና እጅግ ጨካኝ የነበረ ንጉሥ ነው::
+ቅዱሳኑ ያዕቆብና ዮሐንስ የሐዋርያትን ስም ብቻ ሳይሆን ግብራቸውን: ቅድስናቸውንም የያዙ ነበሩ:: ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት ባይሆንም ፋርስ ግን በዚህ ዘመንም ለክርስቲያኖች የግፍ ከተማ ነበረች::
+ከቅዱስ ጊዮርጊስ እስከ ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ: ከቅዱስ መርምሕናም እስከ ቅዱስ ኮቶሎስ ሰማዕትነትን የተቀበሉት በዚህችው ሃገር ውስጥ ነው:: ቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስም ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በልኩ ተምረው: መጻሕፍትንም ተረድተው ለክህነት ተመርጠዋል::
+በሁዋላም ቤተ ክርስትያን "ይገባቹሃል" ስትል ዻዻሳት አድርጋ ሾመቻቸው:: እነርሱም አላሳፈሯትም:: የክርስቶስን መንጋ እያስተማሩ: እየናዘዙ ጠበቁላት:: ንጉሡ ሳቦር ግን ሕዝቡን ለፀለሐይና ለእሳት ሊያሰግድ ላደረገው ጥረት እንቅፋት ሁነውበታልና ጠላቸው::
+በወታደሮቹ አስይዞም በፍርድ አደባባይ አቆማቸው:: ሕዝቡን በአዋጅ ጠርቶ: አስፈሪ እሳት አስነድዶ "ሕዝቡ ለፀሐይ እንዲሰግድ እዘዙ" ቢላቸው "እንቢ" አሉት::
+ከነ ልብሳቸው አንስተው ወደ እሳቱ ወረወሯቸው:: ቅዱሳኑም በመከራው (በነደደው እሳት) መካከል ሆነው ለሕዝቡ ተናገሩ::
"አምላክ አንድ እግዚአብሔር ነውና እንዲህ በሃይማኖታችሁ ጽኑ" አሏቸው:: እሳቱም አቃጥሎ ገድሏቸው የክብርን አክሊል ተቀዳጁ::
+"+ ቅዱሳን አቢማኮስ ወአዛርያኖስ +"+
=>አሁን ደግሞ ወደ 3ኛው መቶ ክ/ዘመን: ወደ ዋናው ዘመነ ሰማዕታት እንመለስ:: በዘመነ ሰማዕታት ከነበሩ ቅዱሳን ሰማዕታት 2ቱ አቢማኮስና አዛርያኖስ ናቸው:: አውሬዎቹ መክስምያኖስና ዲዮቅልጥያኖስ ዓለምን ለ2 ተካፍለው በክርስቲያኖች ላይ ግፍን ሲሰሩ 2ቱ ቅዱሳን በሮም ግዛት ሥር ይኖሩ ነበር::
+በዘመኑ እንኩዋን ቤተ ክርስቲያን ማነጸ: መዘመር: እምነትን መግለጥ ይቅርና ሲያማትቡ መታየት እንኩዋ ያስገድል ነበር:: ነገሥታቱ የሾሟቸው ተከታዮቻቸው ክርስቲያኖችን ከዋሉበት አላሳድር: ካደሩበትም አላውል አሉ::
+ታላቅ ግፍ: ሰቆቃና ጭንቅ በሆነበት በዚያ ወራት የሞተው ሙቶ እኩሉ ሲሰደድ: አቢማኮስና አዛርያኖስ ግን በከተማ መሐል ተረጋግተው ክርስቶስን ያመልኩ ነበር:: ይህም ተደርሶባቸው ተከሰሱና ተይዘው ቀረቡ::
+መኮንኑ 2ቱን ክርስቲያን ወጣቶች ሲመለከታቸው ምንም የፍርሃት ምልክት አልተመለከተባቸውምና ተገረመ:: "ማንን ታመልካላችሁ?" አላቸው:: እነርሱም "የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን!" ሲሉ መለሱለት::
+"ክርስቶስን ትክዳላችሁ ወይስ ትሞታላችሁ?" ቢላቸው "ሰነፍ!" ሲሉ በአደባባይ ገሰጹት:: "የፈጠረ: ያከበረ: ሥጋውን ደሙን የሰጠ ጌታ እንዴት ይካዳል?!" ሲሉም እቅጩን ነገሩት:: በድፍረታቸው የደነገጠው መኮንኑም በዚያች ሰዓት ሞትን አዘዘባቸው:: በዚህች ቀንም አንገታቸውን ተሰይፈው ለክብረ ሰማዕት በቅተዋል::
=>አምላከ ቅዱሳን ሰማዕታት በነርሱ ያሳደረውን ትእግስትና ጽናት በእኛም ላይ ያሳድርልን:: ከበረከታቸውም ያድለን::
=>ኅዳር 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ቶማስ ዘደማስቆ
2.ቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስ
3.ቅዱሳን አቢማኮስ ወአዛርያኖስ
4.አባ አበጊዶ ዘትግራይ
5.ታላቁ አባ ዘካርያስ
6.ጉባኤ ቅዱሳን ሰማዕታት
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ
2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት)
=>+"+ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን?
'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን'
ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው::
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን:: +"+ (ሮሜ. 8:35-38)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
የብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ሊቀ ጳጳስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ
የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ሥርዐተ ቀብር ተፈጸመ፡፡
ብፁዕነታቸው፣ ሀገረ ስብከቱን በመምራት ላይ እያሉ ባደረባቸው ሕመም ከሓላፊነት ተገልለው እና በሕክምና ሲረዱ ቆይተው፣ ትላንት ኅዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም. በተወለዱ በ72 ዓመት ዕድሜያቸው ያረፉ ሲኾን፣ ዛሬ ጠዋት፣ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ሓላፊዎች፣ የገዳማት እና አድባራት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ምእመናንና ወዳጆቻቸው በተገኙበት በተፈጸመው ሥርዓተ ቀብር፣ የብፁዕነታቸው ዜና ሕይወት እና ሥራ፣ በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የሲዳማ እና ጌዲዮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በንባብ ተሰምቷል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩም፣ “ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ፣ መንፈሳዊ አገልግሎት አበርክተው በሕግ እና በሥርዓት ኖረው ወደ አምላካቸው ሔደዋል፤” በማለት የማጽናኛ ትምህርት እና ቡራኬ ሰጥተዋል፡፡
የብፁዕነታቸው በረከት ይድረሰን፤ አሜን፡፡
የዘገባ ምንጭ እና ፎቶዎች: ኢኦተቤ ቴቪ እና የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
#ንስሐ (በቅዱስ ኤፍሬም)
ወንድሞቼ ሆይ! ጊዜ ሳለልን ንስሐ እንግባና ለንስሐ የሚገባ ፍሬ እናፍራ፡፡ ጌታችን ምን እንዳለ እስኪ አድምጡ፡- “ንስሐ
ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይኾናል” /ሉቃ.15፡7/፡፡
ወንድሞቼ ሆይ! ስለምን ታድያ በኃጢአት፣ በስንፍና፣ በንዝህላል እንደተያዘዝን እንቆያለን? ስለምንድነው ተስፋ ቆርጠን የምንቆዝመው? በእኛ ንስሐ መግባት ምክንያት በሰማያት ታላቅ ደስታ የሚሆን ከሆነ ምንድነው የሚያስፈራን? ቅዱሳን መላዕክት ስለ እኛ ንስሐ እጅግ ደስ የሚላቸው ከሆነ ስለምንድነው እኛ ልል ዘሊል፣ ደንታ ቢስና ፈዛዛ የምንሆነው? የመላዕክት ጌታ ንስሐ ግቡ እያለ አስተምሮን ሳለ ምንድነው የምንፈራው? የማይከፈሉ ሦስት፣ የማይጠቀለሉ አንድ የሚሆኑ ሥላሴ ንስሐ እንገባ ዘንድ እየጠሩን ሳለ እኛ ያለምንም የንስሐ ፍሬ እንቆይ ዘንድ አግባብ ነውን?
ተወዳጆች ሆይ! በዚህ ጊዜአዊ ዓለም ርኵሰት ጣዕም አንታለል፡፡ እንዲህ ካልሆነ ግን እሳቱ የማይጠፋ ትሉ የማያንቀላፋ ምረረ ገሃነም ይጠብቀናል፡፡ ስለዚህ ከዘለዓለማዊው እሳት እንድን ዘንድ አሁን ጥቂት ብናለቅስ ይሻለናል፡፡
ተወዳጆች ሆይ! እስኪ እናስተውል፡፡ ስለምንናገረው ነገርም ችላ የሚለው ሰው ከቶ አይገኝ፡፡ ክርስቶስ ድንገት እንደ ብርሃን ብልጭታ ይመጣልና፡፡ ክርስቶስ ድንገት በመጣ ጊዜ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦም ለሁሉም እንደየሥራው ሲከፍለው ማየት አያስፈራምን? የዚያን ጊዜ ሁሉም የየራሱን ሸክም ይሸከማል፡፡እያንዳንዱ ሰው በዚህ ምድር የዘራውን ያጭዳል፡፡ ሁሉም ዕራቆቱ ይቆማል፡፡ ሁሉም ወደ ክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ይቀርባል፡፡ የዚያን ጊዜ ማንም ማንንም መርዳት አይችልም፡፡ ወንድም ወንድሙን ወይም ጓደኛ ጓደኛውን መርዳት አይችልም፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን መርዳት አይችሉም፡፡ ልጆች ወላጆቻቸውን መርዳት አይችሉም፡፡ ባሎች ሚስቶቻቸውን መርዳት አይችሉም፡፡ ሁሉም በፍርሐትና በረዐድ በመንቀጥቀጥም የእግዚአብሔርን ፍርድ ይጠብቃል እንጂ ማንም ማንንም መርዳት አይችልም፡፡
ወንድሞቼ ሆይ!ታድያ ለምንድነው ጊዜ ሳለልን የምንሰንፈው? ለምንድነው ልል ዘሊል የምንሆነው? ለምንድነው በምግባር በሃይማኖት የማንዘጋጀው? ለምንድነው ጊዜ ሳለልን የማናስተውለው? ለምንድነው ቃለ ሕይወትን ለመስማት የማንቻኰለው? ስለምንድነው ቃለ እግዚአብሔርን የማንሰማው? ስለምንድነው ቃለ ክርስቶስን ችላ የምንለው? ቃሉ በዚያ ሰዓት እንደሚፈርድብን አትገነዘቡምን? ቃለ ነቢያት ቃለ ሐዋርያት በዚያ ሰዓት እንደሚፈርድብን አታውቁምን? ካላወቃችኁ ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ ያላቸውን አድምጡ፡- “የሚሰማችሁ እኔን ይሰማል፤ እናንተንም የጣለ እኔን ይጥላል፤ እኔንም የጣለ የላከኝን ይጥላል” /ሉቃ.10፡16/፡፡ ዳግመኛም በሌላ አንቀጽ እንዲህ ብሏል፡- “የሚጥለኝ ቃሌንም የማይቀበለው ርሱ የሚፈርድበት አለው፤ እኔ የተናገርኩት ቃል ርሱ በመጨረሻው ቀን ይፈርድበታል” /ዮሐ.12፡48/፡፡ በመጨረሻው ቀን የሚፈርድብን ቃሉስ የትኛው ነው? በወንጌሉ እንዲሁም በሐዋርያትና በነቢያት አድሮ የተናገረው ቃሉ፡፡ እንኪያስ ወንድሞቼ ሆይ! ቃሉን ችላ የምንለው አንኹን፡፡ “ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም” ያለውን አንርሳው /ማቴ.24፡35/፡፡
እንኪያስ እጅግ የምወዳችሁ ሆይ! ኑ! አስፈሪው ቀን ሳይመጣ ቃሉን ሰምተን ንስሐ እንግባ፡፡ የእግዚአብሔርን ምሕረት እንቀበል፡፡ እግዚአብሔር ዛሬ ምሕረቱን እንድንቀበል እንዲህ እያለ ያበረታታናልና፡- “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ” ማቴ.11፡28፡፡ በዚህ ቃሉ ትዕግሥተኛው፣ አፍቃሪውና ሰው ወዳጁ ጌታ ሁላችንም እንድን ዘንድ ይጠራናል፡፡ የጠራው የተወሰኑ ሰዎችን ብቻ አይደለም፤.“ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ” ብሎ ሁላችንም እንጂ፡፡ “ባለጸጋም ቢሆን ድኻም ቢሆን ሁሉም ወደ እኔ ይምጣ፡፡ ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም፡፡ ወደ እኔ የሚመጣውስ ማን ነው ትዕዛዛቴን የሚጠብቀው፤ ቃሌን የሚሰማው፤ በላከኝም የሚያምነው፡፡” የክርስቶስን ቃል ሰምቶ ንስሐ የሚገባው ንስሐም ገብቶ የንስሐን ፍሬ የሚያፈራ ሰው ንዑድ ክቡር ነው፡፡ የማይሰማው ግን እጅግ ጐስቋላ ሰው ነው፡፡ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፡- “በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው” /ዕብ.10፡31/፡፡
✝✝✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን። ✝✝✝
✝ኅዳር 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+" አባ ዼጥሮስ ሣልስ "+
✝'ዻዻስ' ማለት 'አባት-መሪ-እረኛ' ማለት ነው:: በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ በሐዲስ ኪዳን የመንፈሳዊ ስልጣን ደረጃዎች በጥቅሉ 3 ናቸው:: እነሱም ዲቁና: ቅስና: ዽዽስና ሲሆኑ በሥራቸው ወደ 9 ያህል ክፍሎች አላቸው:: ከእነዚህም ከፍተኛው ስልጣን ዽዽስና ነው::
+ዽዽስና ማለት የክርስቶስን መንጋ እንደ ባለቤቱ አድርጐ መጠበቅ ማለት ነው:: ሥልጣኑ በምድር 'ሸክም: ዕዳ' ሲሆን በሰማይ ግን 'ክብር' ነው:: ማንም በሥጋው ላይ ካልጨከነ በቀር ዽዽስናን አይመኝም::
+ቅዱስ ዻውሎስ "ሠናየ ግብረ ፈተወ-ማንም ዽዽስናን ቢመኝ መልካም ሥራን ተመኘ" (1ጢሞ. 3:1) ማለቱን ይዞ 'ሹሙኝ' ማለት ወደ ማይጠፋ እሳት የሚያስጥል ከባድ ውሳኔ ነው:: ምክንያቱም አንድ ክርስቲያን የሚጠየቅ በራሱ ኃጢአት ሲሆን አንድ ካህን ደግሞ ስለ ልጆቹ ይጠየቃል:: የከፋው ግን የዻዻሱ ነው::
+አንድ ዻዻስ ቢጾም ቢጸልይም እንኳ ለድኅነቱ በቂ አይደለም:: ምክንያቱም በመንበሩ ላይ ያስቀመጠው መንጋውን እንጂ ራሱን እንዲያድን አይደለምና:: ጌታ እንዳለ መልካም እረኛ "ይሜጡ ነፍሶ ቤዛ አባግኢሁ-መልካሙ እረኛ ስለ በጐቹ ቤዛ ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ ነው::" (ዮሐ. 10) ስለዚህም ክህነት / ዽዽስና ሐዋርያዊ አገልግሎት ከባድም ኃላፊነት ነው::
+አባቶቻችን ሐዋርያትና ተከታዮቻቸው ሐዋርያውያን ታላላቅ የዽዽስና መንበሮችን መሥርተው: ትምሕርቱን ከነ ወንበሩ አስተላልፈዋል:: ከእነዚህ መንበረ ዽዽስናዎች 4ቱ የበላይ ናቸው:: እነዚህም የቅዱስ ዼጥሮሱ የሮም: የቅዱስ ዮሐንሱ የአንጾኪያ: የቅዱስ ማርቆሱ የእስክንድርያና የቅዱስ ዻውሎሱ የኤፌሶን መናብርት ናቸው::
+እነዚህ መንበሮችም ከክርስቶስ ዕርገት እስከ 443 (451) ዓ/ም: ጉባኤ ኬልቄዶን ድረስ በአንድነት ቆይተው ተለያይተዋል:: ከእነዚህ መናብርት መካከል የእስክንድርያው (የግብጹ) እና የአንጾኪያው (የሶርያው) ዛሬም ድረስ በተዋሕዶ እምነት የጸኑ ናቸው::
+የእኛ ቤተ ክርስቲያንም ሐዋርያዊት እንደ መሆኗ ሐዋርያትን መስለው: ሐዋርያትን አህለው የተነሱ አበው ዻዻሳትን በየጊዜው በበዓላት ታስባለች: ታከብራለች::
+በተለይ ደግሞ የእስክንድርያና የአንጾኪያ በርካታ አባቶችን እናከብራለን:: እነርሱ ለቀናች ሃይማኖትና ለመንጋው ሲሉ ብዙ መከራን በአኮቴት ተቀብለዋልና:: ከእነዚህም መካከል አንዱ አባ ዼጥሮስ ሣልሳዊ ነው::
+ሣልሳዊ መባሉ ከእርሱ በፊት በዚህ ስም ተጠርተው በመንበረ ማርቆስ ላይ የተቀመጡ 2 ፓትርያርኮች ስለ ነበሩ ነው:: ቅዱስ ዼጥሮስ ቀዳማዊ 'ተፍጻሜተ ሰማዕት' (የሰማዕታት ፍጻሜ) የተባለው ሲሆን 17ኛ ሊቀ ዻዻሳት ነው::
+ቅዱስ ዼጥሮስ ካልዕ ደግሞ በ370ዎቹ አካባቢ 21ኛ ሊቀ ዻዻሳት ሆኖ የተሾመና የቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ደቀ መዝሙር የነበረ አባት ነው:: ዛሬ የምናስበው አባ ዼጥሮስ ደግሞ በ470ዎቹ አካባቢ ሊቀ ዽዽስናን በግብጽ ተሹሞ ያገለገለውን ነው::
+ወቅቱ መለካውያን (የኬልቄዶን ጉባኤ አማኞች) የሰለጠኑበት በመሆኑ ሁኔታዎች ትንሽ አስቸጋሪ ነበሩ:: አንደኛ ቤተ ክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ ከ2 የተከፈለችበት ጊዜ በመሆኑ ፈተናው ለእረኞች ቀላል እንዳይሆን አድርጐታል:: ሌላውና ዋናው ፈተና ግን በዘመኑ የነበሩ ነገሥታት ለመለካውያን (ለመናፍቃን) ወግነው ምዕመናንን ማሳደዳቸው ነው::
+አባ ዼጥሮስ ከተመረጠ በኋላ አስቀድሞ ያደረገው አጋዥ መፈለግ ነበር:: እግዚአብሔር ሲረዳው የታላቂቱ ሃገር የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ የሆነው ቅዱስ አካክዮስን አገኘ:: ከእርሱ ጋርም ደብዳቤ ይጻጻፉ ያዙ::
+ደብዳቤ ሲባል ግን እንዲህ እኛ በዘመኑ እንደምንጽፈው ያለ አይደለም::ይልቁን 5ቱ አዕማደ ምሥጢራትን የተሞሉ ጦማሮች ነበሩ እንጂ:: 2ቱ አበው በየሃገራቸው እየዞሩ እየሰበኩ: አልደርሱበት ባሉበት ቦታ ደግሞ ክታቦችን እየጻፉ በአንድነት ስለ ቀናች ሃይማኖት ደከሙ::
+በእግዚአብሔር ቸርነትም ተሳካላቸው:: አባ ዼጥሮስ በዚህች ቀን ሲያርፍ መሰሉ 'ካልእ አትናቴዎስ' ተክቶታል:: ከፈጣሪውም እሴተ ኖሎትን (የእረኝነት ዋጋውን) ተቀብሏል::
+አምላከ አበው ዻዻሳት መንጋውን በርሕራሔ የሚጠብቁ እረኞችን ያድለን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
+ኅዳር 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ ዼጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት ሣልስ
2.አባ ሱንቱዩ ሊቀ ዻዻሳት
3.ቅድስት ሴቴንዋ ነቢይት
4.ቅድስት አንስጣስያ
>+"+ ማንም ትምክህቴን ከንቱ ከሚያደርግብኝ ሞት ይሻለኛልና:: ወንጌልን ብሰብክ እንኩዋ የምመካበት የለኝም:: ግድ ደርሶብኝ ነውና:: ወንጌልንም ባልሰብክ ወዮልኝ:: ይህን በፈቃዴ ባደርገው ደመወዝ አለኝና:: ያለ ፈቃዴ ግን ባደርገው መጋቢነት በአደራ ተሰጥቶኛል:: እንግዲህ ደመወዜ ምንድን ነው? ወንጌልን እየሰበክሁ በወንጌል ካለኝ መብት በሙሉ እንዳልጠቀም ወንጌልን ያለ ዋጋ ብናገር ነው:: +"+ (1ቆሮ. 9:15)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በ97 ዓመታቸው አረፉ
ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በጎንደር ክፍለ ሀገር በደብረ ታቦር አውራጃ በፋርጣ ወረዳ ልዩ ስሟ መገንታ ቍስቋም በተባለች ደብር ከቄስ ወርቅነህ ትኩና ከወይዘሮ አንጓች አታሌ በ1916 ዓም ነበር የተወለዱት።
ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ከፍተኛ የሃይማኖት ትምህርትን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ተምረው ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሙሉ እድሚያቸውን ያገለገሉ አባት ነበሩ።ጥቅምት 28 ቀን 2013ዓም በ97 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መፅናናቱን አብዝቶ ይስጣችሁ።
ምንጭ:—EOTC TV
---------------------
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞✞✞ ጥቅምት 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞
+" ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ "+
✞✞✞ በዚሕች ዕለት ከ72ቱ አርድእት አንዱ የሆነ: ወንጌላዊ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ዘአንበሳና ርዕሰ ሊቃነ ዻዻሳት የተባለ ቅዱስ ማርቆስ ተወልዷል ::
+ቅዱስ ማርቆስ እናቱ ማርያም: አባቱ አርስጥቦሎስ ይባላሉ:: በልጅነቱ ኦሪትንና የዘመኑን ጥበብ ሥጋዊ በሚገባ ተምሮ ክርስቶስን ከቤተሰቦቹ ጋር ተከትሏል:: የመጀመሪያ ስሙ ዮሐንስ ሲሆን ከ120ው ቤተሰብ በእድሜ በጣም ትንሹ /20 ዓመት/ እርሱ ነበር::
+ለ3 ዓመታት ከጌታ እግር ሥር ተምሮ: በበዓለ ሃምሳ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ብዙ ደክሟል:: በተለይ የግብፅና የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን አባት ነው:: ክህነትን ያገኘን ከርሱ ነውና::
+ቅዱስ ማርቆስ 16 ምዕራፍ ያለውን ወንጌሉን ሲጽፍ ኪሩብ ገጸ አንበሳ በቀኙ: ሊቀ ሐዋርያት በግራው ሆነው ይራዱት ነበር:: ቅዱሱ ክቅዱስ ዻውሎስ: ከበርናባስና ዼጥሮስ ጋር ተጉዟል:: ከብዙ ስቃይና መከራ በኋላ ሰሜን አፍሪካ አካባቢ አረማውያን ገድለውታል:: ይህቺ ዕለት የልደቱ መታሠቢያ ናት::
+ዳግመኛ በዚህ ቀን የቅዱስ ማርቆስን ወላጆችን እናስባቸው ዘንድ ይገባል:: ቅዱስ አርስጥቦሎስ (አባቱ) የጌታ ቅን አገልጋይ የነበረ: ቅድስት ማርያም (እናቱ) ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ: ጌታችንን ያገለገለች ቤቷን ለሐዋርያትና ለጌታ በስጦታ ያበረከተች ቅድስት ናት::
+ቤቷም (ጽርሐ ጽዮን) የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ስትሆን ይህች ቤት መንፈስ ቅዱስ ወርዶባታል:: የእመቤታችን ግንዘትም ተከናውኖባታል::
+እግዚአብሔር ከሐዋርያዊው ቅዱስ ቤተሰብ በረከትን ያድለን::
+" ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ "+
+ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)
*የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል!
እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር::
*ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::
*ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::
*የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በኋላ በዚህች ቀን (ሰኔ 30) ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::
*ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ 2 ዓመት ከ6 ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ::
*እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 (5) ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ 5 (7) ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው ቀበሯት::
*ሕጻኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ ድንግል ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ::
*ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በኋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ25 (23) ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም::
*ከዚህ በኋላ 30 ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጀን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" (ሉቃ. 1:76) ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና::
*ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና::
*ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሃ ሰበከ: ለንስሃም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ6 ወራት ቆይቶ ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነልብሱ የያዘ ፈጣሪ 'አጥምቀኝ' ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው::
*"እንቢ ጌታየ! አንተ አጥምቀኝ" አለው:: ጌታ ግን "ፈቅጄልሃለሁ" አለው: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ ዛሬም "መጥምቀ መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ ለ7 ቀናት አሠረው::
*በዚህች ቀንም ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: (ማቴ. 3:1, ማር. 6:14, ሉቃ. 3:1, ዮሐ. 1:6)
*ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በኋላ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት ጌታችን ወዳለበት ደብረ ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች:: ቅዱሳን ሐዋርያት በአዩት ነገር ተገርመው ራሱን እጅ ነሷት::
*ከዚሕ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት:: በመላው ዓለም ለ15 ዓመታት ስትሰብክ ኑራ ዓረቢያ ውስጥ ዓርፋለች::
✞✞✞ ይህች ዕለት ለቅዱሱ 'አስተርዕዮተ ርዕሱ' ወይም ቅድስት ራሱ ከተወረችበት የተገለጠችበት ነው::
+ጥቅምት 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ አርስጥቦሎስ (አባቱ)
3.ቅድስት ማርያም (እናቱ)
4.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
5.አባ አብርሃም ገዳማዊ
6 ቅዱስ ይስሐቅ ንጉሥ
++"+ ...
እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ:: ዼጥሮስም የደጁን መዝጊያ ባንኳኳ ጊዜ ሮዴ የሚሏት አንዲት አገልጋይ ትሰማ ዘንድ ቀረበች:: የዼጥሮስ ድምጽ መሆኑንም ባወቀች ጊዜ ከደስታዋ የተነሳ ደጁን አልከፈተችም:: ነገር ግን ወደ ውስጥ ሮጣ ዼጥሮስ በደጅ ፊት ቆሞ እንዳለ አወራች:: +"+ (ሐዋ. 12:12-15)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
=>+"+ እንኩዋን ለአበው ቅዱሳን "ሳሙኤል ዘወገግ": "ጸቃውዐ ድንግል" እና "ድሜጥሮስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+
+"+ አባ ሳሙኤል ዘወገግ +"+
=>ሃገራችን ኢትዮዽያ ማኅደረ ቅዱሳን (ምዕራፈ ቅዱሳን) እንደ መሆኗ ፍሬ ክብር: ፍሬ ትሩፋት ያፈሩ ብዙ አባቶችና እናቶችን አፍርታለች:: ብርሃን ሁነው ካበሩላት ቅዱሳን መካከል አንዱ ደግሞ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ ናቸው::
+በእኛው ሃገር ብቻ ብዙ "ሳሙኤል" የሚባሉ ቅዱሳን በመኖራቸው ስንጠራቸው "ዘእንትን" እያልን ነው:: ለምሳሌም:
*ሳሙኤል ዘዋሊ
*ሳሙኤል ዘወገግ (የዛሬው)
*ሳሙኤል ዘጣሬጣ
*ሳሙኤል ዘቆየጻ
*ሳሙኤል ዘሃሌ ሉያና
*ሳሙኤል ዘግሺን መጥቀስ እንችላለን:: ሁሉም የመካከለኛው ዘመን ሐዋርያዊ አባቶች ናቸው::
+ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ የተወለዱት በ13ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ሃገረ ሙላዳቸው የብዙ ቅዱሳን ቤት የሆነችው ሽዋ ናት:: መንደራቸውም ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ብዙም አይርቅም::
+የጻድቁ ወላጆች እንድርያስና አርሶንያ የሚባሉ ሲሆን ደጐች ነበሩ:: ጻድቁ በተወለደ ጊዜ የቤታቸው ምሰሶ ለምልሞ ተገኝቷል:: አቡነ ሳሙኤል ከልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው በጉብዝናቸው ወራት ይህችን ዓለም ንቀዋል::
+የታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ሆነው በደብረ ሊባኖስ መንነዋል:: ከ12ቱ ኅሩያን (ምርጦች) አርድእት አንዱ ነበሩና በክህነታቸው ደብረ ሊባኖስን ተግተው ያጥኑ ነበር:: በዚያውም በንጹሕ ልቡና በጾምና ጸሎት ይተጉ ነበር::
+አቡነ ተክለ ሃይማኖት ካረፉ በሁዋላ በደጉ ዻዻስ በአቡነ ያዕቆብ ዘመን 12ቱ ንቡራነ እድ ተመረጡ:: እነዚህ አባቶች በወንጌል አገልግሎት: በተለይ ደቡብና ምሥራቁን የሃገራችን ክፍል ያበሩ ናቸው:: ቅዱሳኑ ሲመረጡም ከአቡነ ፊልዾስ ቀጥለው በ2ኛ ደረጃ የተመረጡ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ ናቸው::
+ሃገረ ስብከታቸውም ሐረርና ሱማሌ ነበር:: ጻድቁ በሃገረ ስብከታቸው ወርደው በሐረርና ሱማሌ አካባቢ ለዘመናት የወንጌልን ዘር ዘርተው እልፍ ፍሬን አፍርተዋል:: አካባቢውንም መካነ ቅዱሳን አድርገውታል::
+ቀጥለው ገዳማዊ ሕይወትን ያጸኑ ዘንድ በምሥራቁ የሃገራችን ክፍል በአፋር ሱባኤ ገቡ:: ቦታውም ደብር ሐዘሎ ነበር:: በቦታው ለ155 ቀናት ከቆሙ ሳያርፉ: ከዘረጉ ሳያጥፉ: እህል ውሃ ሳይቀምሱ ጸለዩ::
+በሱባኤያቸው ፍጻሜ ግን ቅዱስ መልአክ መጥቶ "ሳሙኤል ወደዚያ ተራራ ሒድ:: የስምህ መጠሪያ እርሱ ነውና:: ይህ ግን የሌላ ሰው (የአባ አንበስ ዘሐዘሎ) ርስት ነው" አላቸው:: ጻድቁም ወዳላቸው ተራራ ሒደው ቢጸልዩ ከሰማይ ብርሃን ወረደላቸው::
+በመንፈቀ ሌሊት የበራው ብርሃን እስከ ጐረቤት መንደር ሁሉ በመድረሱ የአካባቢው ሰው "ወገግ አለኮ-ነጋ" ብለውዋል:: በዚህ ምክንያት ዛሬም "ደብረ ወገግ" ይባላል:: ይህ ቦታ ዛሬም ድረስ ንጹሕ ልብ ላላቸው አበው በብርሃን ተከቦ ይታያል::
+ጻድቁ የወለዷቸው ብዙ ሥውራንም በሥፍራው ይገኛሉ:: ቦታው የአንበሶች መኖሪያ በመሆኑ ጠላት መናንያኑን ማጥቃት አይችልም:: ሳሙኤል ዘወገግም የሚጸልዩት በአናብስት ተከበው ነበር::
+በቦታው አንዳንዴም አንበሶች ሲሰግዱ ይታያል ይባላል:: ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ግን እንዲህ በቅድስና ተመላልሰው በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ሱማሌ ክልል ውስጥ በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: የጻድቁ ልደት ሐምሌ 10: ፍልሠታቸው ደግሞ ግንቦት 27 ነው::
+"+ አባ ጸቃውዐ ድንግል +"+
=>እኒህ ጻድቅም ኢትዮዽያዊ ናቸው:: የስማቸው ትርጉም "የድንግል ማርያም ወለላ ማር" ማለት ሲሆን ዜና ሕይወታቸው እንደ ስማቸው ጣፋጭ ነው::
+የእኒህ ጻድቅ አባታቸው የተመሰከረላቸው ሊቅና የገዳም መምሕር ናቸው:: ምክንያቱም ጸቃውዐ ድንግልን ከወለዱ በሁዋላ መንነዋልና:: አባት የደብረ ዘኸኝ መምሕር ሳሉ ልጃቸው ጸቃውዓ ድንግልን ወደ ገዳሙ ወስደው አሳደጉዋቸው::
+በዚያውም ጾምና ጸሎትን: ትዕግስትና ትሕርምትን አስተማሯቸው:: ቅዱሳት መጻሕፍትንም በወጉ አስጠኗቸው:: አባ ጸቃውዐ ድንከግልም በጐውን የምናኔ ጐዳና ከተማሩ በሁዋላ መዓርገ ምንኩስናን ተቀበሉ::
+40 ዓመት ሲሞላቸው ግን አባታቸው ዐረፉ:: መነኮሳት አበውም ተሰብስበው "ከአንተ የተሻለ የለም" ሲሉ ጸቃውዐ ድንግልን የደብረ ዘኸኝ መምሕር አድርገው ሾሟቸው:: ጻድቁም ቀን ቀን ሲያስተምሩ ይውሉና ሌሊት ባሕር ውስጥ ሰጥመው ሲጸልዩ ያድሩ ነበር::
+በሌሊትም ከባሕሩ ወጥተው የአካላቸው ርጥበት ደርቆ ላበታቸው እስኪንጠፈጠፍ ድረስ ይሰግዱ ነበር:: በዚህ መንገድም ራሳቸውን ገዝተው: መነኮሳትንም ገርተው ያዙ:: እግዚአብሔርም ክብራቸውን ይገልጽ ዘንድ ብዙ ተአምራትን በእጃቸው አሳይቷል::
+አንድ ቀን አባ ጸቃውዐ ድንግል መንገድ ሲሔዱ ሁለመናው በቁስል የተመታ አንድ መጻጉዕ ነዳይ ወድቆ አዩ:: ወደ እርሱ ሲደርሱ ምጽዋትን ለመናቸው:: ጻድቁ ግን "የምሰጥህ ነገር የለኝም:: ግን የፈጣሪየን ስጦታ እሰጥሃለሁ" ብለው: በውሃ ላይ ጸልየው ረጩት::
+ያ መጻጉዕም አካሉ ታድሶ: እንደ እንቦሳ ዘሎ ተነሳ:: ደስ እያለው: ፈጣሪውንም እያከበረ ወደ ቤቱ ሔዷል:: አባ ጸቃውዐ ድንግልም በዚህች ቀን ዐርፈው በገዳማቸው ተቀብረዋል::
+"+ ቅዱስ ድሜጥሮስ ሰማዕት +"+
=>ይህ ቅዱስ በዘመነ ሰማዕታት: በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከነበሩ ክርስቲያኖች አንዱ ነው:: ቅዱስ ድሜጥሮስ ስቅጣር ከሚባል ደግ ባልንጀራው ጋር በበጐው ጐዳና ሲኖሩ የመከራው ዘመን ደረሰ:: መወሰን ነበረባቸውና ፈጣሪያቸውን ከሚክዱ ሞትን መረጡ::
+አስቀድሞም ሲያስተምር በመገኘቱ ቅዱስ ድሜጥሮስ በንጉሡ እጅ ወደቀ:: ንጉሡ መክስምያኖስም እሥራትን አዘዘበት:: በዚያ ወራት ደግሞ የንጉሡ ወታደር የሆነና በጣዖት የሚመካ አንድ ጉልበተኛ ነበር::
+ማንም በትግል አሸንፎት ስለማያውቅ ጣዖታዊው ንጉሥ ይመካበት ነበር:: አንድ ቀን ግን አንድ ክርስቲያን ወደ እሥር ቤት ገብቶ ቅዱስ ድሜጥሮስን "ባርከኝና ያንን ጣዖታዊ ጉልበተኛ እጥለዋለሁ" አለው::
+የቅዱሱን ጸሎትና በረከት ተቀብሎም በንጉሡ አደባባይ ታግሎ ጣለው:: ንጉሡና የጣዖቱ ካህናትም በእጅጉ አፈሩ:: በሁዋላ ግን ይህንን ያደረገው ቅዱስ ድሜጥሮስ መሆኑ በመታወቁ ከባልንጀራው ቅዱስ ስቅጣር ጋር በዚህች ቀን ገድለዋቸዋል::
=>አምላከ አበው ቅዱሳን ጸጋ ክብራቸውን ያብዛልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
=>ጥቅምት 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አቡነ ሳሙኤል ጻድቅ (ዘደብረ ወገግ)
2.አባ ጸቃውዐ ድንግል (ዘደብረ ዘኸኝ)
3.ቅዱስ ድሜጥሮስ ሰማዕት
4.ቅዱስ ስቅጣር ሰማዕት
=>ወርኀዊ በዓላት
1.የፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት
2.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
3.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
4.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
5.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ
6.ቅድስት አርሴማ ድንግል
=>+"+ በእሸቅድምድም ሥፍራ የሚሮጡት ሁሉ እንዲሮጡ: ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ:: የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል:: እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው:: እኛ ግን የማይጠፋውን:: +"+ (1ቆሮ. 9:24)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>