#ኦርቶዶክሳዊ ጥያቄዎችን ከነመልሶቻቸዉ ለማግኝት ቻናላችንን ይጎብኙ! #በቻናላችን እንዲቀርብላቹ የምትፈልጉት ጥያቄ ካሎት @kiya17 ይጠይቁን @ortodox_tyake @ortodox_tyake @ortodox_tyake
🕯• ┈••●◉ ✞✟✞ ◉●••┈ •🕯
ሰኔ ፲ወ፩
እንኳን ለቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት፣ ለቅዱስ ገላውዴዎስ ማኅበረ ሰማዕታት፣ ለአባ ክርዳኑ ሊቀ ጳጳሳት፣ ለቅድስት ክርስቶስ ክብራ እንዲኹም ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ቅዳሴ ቤት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ 🙏
🕯• ┈••●◉ ✞✟✞ ◉●••┈ •🕯
ዳግመኛም ዛሬ ቅዱስ ያሬድ ካህን፣ አቡነ ሐራ ድንግል፣ ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት እንዲኹም ብፁዓን ኢያቄም ወሐና ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው 🙏🙏🙏
አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን 🤲 አሜን!
🕯• ┈••●◉ ✞✟✞ ◉●••┈ •🕯
/channel/yekdset_selase_lejoch
ይህን ከታች የለቀቅንላችሁን ድምፅ (voice) የምታዳምጡ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች በሙሉ ይህ አስተምሮ የቤተ ክርስትያናችን አይደለምና ሼር እንዳታደርጉ በቅድስት ሥላሴ ስም እናስተላልፋለን።
@yekdset_selase_lejoch
*አስደናቂ ምስጢር....
*ጣና ባህላዊ ታሪካዊ፣ጂኦሎጂካዊና ሥነ ውበታዊ እሴት ባለፈ ከባድ ምስጢር አለ።እጅግ በጣም ከባድ ምስጢር።በጣና ሐይቅ ዙሪያ ከሚገኙት አብያ ክርስቲያናት ደኖች እና የአበባ ዝሪያዎች ያለምንም ጥርጥር የእውቀት ማነስ እንጅ መድሀኒት ናቸው።
*እነዚህ አብያተ ክርስቲያኖች ከባድ ምስጢር አለ በእጅ የያዙት ወርቅ እንደ መዳብ ይቆጠራል ሆኖብን እንጅ ገዳማቱን ለማወቅ በመጨረሻም ለማጥፋት የምስጢር ማህበረሰቡ በPedro Paez፣Jeronimo Lobo፣Alfonsi Mendes፣ ፖርቱጋላዊው ሚሲዮናዊ ማኖኤሊ ደ አልሜዳ፣ጀምስ ብሩስ አማካኝነት ሲመረመር ቆይቷል። 'The hidden of treasure Ethiopia' በሚለው መጽሐፍ ውስጥ ጣናን ከነቅርሶቹ እንደሰለሉ ገልጾ ዋና ዓላማቸው "አዲሱ የኢሉሚናቲና 666 የአገዛዝ እቅድ ሊከሽፍ የሚችለው ጣና ደሴቶች በሚገኝ ጥበብ ነው" ብለው እንደሚያምኑ መጽሐፉ አስቀምጦታል።
*በጣና ደሴቶች ዙሪያ ያለው የተደበቀው ምስጢር ምንድነው? አባቶቻችን ያካተተ ሰፊ ጥናት ይጠይቃል።
1.ከኤዶም እየወጣ ገነትን ከሚያጠጡ ወንዞች መካከል ሁለተኛው ግዮን ነው።ግዮን ወይንም አባይ የኢትዮጵያን ምድር (7) ጊዜ ይከብባል።የሚያበራ እና የሚያብረቀርቅ ዕንቁም ይገኝበታል። (ዘፍ 2፥13)
2.አዳም የተፈጠረው የግዮን ወንዝ ከሚወጣበት ኤዶም ነው።
3.ኖህ ከማየ አይኅ የጥፋት ውኃ ልጆቹ፣ሚስቱና የልጆቹ ሚስቶች የዳኑት በመርከብ ነው። በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት በአቡነ ሒሩት አምላክ የተመሰረተው የዳጋ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን የተሠራው በኖኅ መርከብ ቅርፅ ነው።
4.የኖኅ መርከብ ማየ አይኅ መጉደል ሲጀምር በ7ኛ ወር ከወሩም በ27ኛው ቀን በአራራት ተራሮች ላይ ተቀመጠች።አራራት ተራራ ደግሞ የሚገኘው ከዚሁ ጣና ነው።
5.ከክርስቶስ ልደት በፊት በጣና ቂርቆስ የኦሪት መስዋዕት ይቀርብ ነበረ፥ዛሬም አራት ማዕዘን ቅርጽ ያለው ከአናቱ ላይ እንደ ሙቀጫ የተቦረቦረው ድንጋይና የኦሪት የብረት መስዋዕት ማቃጠያ በሥፍራው ይገኛሉ።
6.ጣና ቂርቆስ ገዳም ለሙሴ የተሰጠው የቃል ኪዳን ታቦቱ ለ800 ዓመት የተቀመጠችበት ቦታ ነው።
7.አስገራሚ ነገር የኦሪት መስዋዕት እና ታቦተ ጽዮን ምስጢር ለሚገባው ሰው ከእነዚህ ቀጥሎ ድግሞ
ድንግል ማርያም ልጇን ይዛ ወደ ምድረ ግብጽ በተሰደደችበት ወቅት ለ3 ወራት ከ10 ቀን በዚሁ ገዳም ከልጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ቆይተዋል። ድንግል ማርያም በገዳሙ የነበራትን ቆይታ አጠናቃ ስትመለስ “ፀአና በደመና” በደመና ጫናት የተባለው በጊዜ ብዛት ለአሁኑ የሐይቁ መጠሪያ ስም “ጣና” መሠረት ሆኖታል።
8.ቅዱስ ያሬድ የመጀመሪያውን የዜማ መጽሐፉን የፃፈውና ብዙ ተግባራትን ለመከወን የመረጠው ጣና ቂርቆስን ነው፡፡መጽሐፍ ሲጽፍ ለጥቁርና ቀይ ቀለማት መበጥበጫነት ይጠቀምባቸው የነበሩ ከድንጋይ ተቦርቡረው የተሠሩ ጉድጓዶች፣የቅዱስ ያሬድ ድጓና ካባ
በገዳሙ ይገኛሉ።በተጨማሪም በጣና ቂርቆስ፦
*የአቡኑ ሰላማ መቋሚያና የብረት መስቀል፣
* ከብርጭቆ የተሠራ የብርሌ ቅርጽ ያለው የንጉሥ ሰለሞን የእጅ ማስታጠቢያ፣
*ከአንድ ሜትር በላይ ቁመት ያላቸው ሁለት የእንጨት መቅረዞች፣
*ቁመቱ 75 ሳ.ሜ ርዝመቱ ደግሞ 5 ሜትር የሆነ በሐዋርያትና በነቢያት ሥዕል ያሸበረቀ ከብራና የተሠራ ተጣጣፊ የብራና ሥዕል (ልፋፈ ፅድቅ)፣ የመሳሰሉት ይገኙበታል።
*ዋናው ነጥብና ሊመረመሩ የሚገባቸው አስደናቂ ምስጢሮች ግን ዛሬም እንደተሰወሩ ናቸው።
+ ኤዶም እና ግዮን (አባይ)
+ ኤዶም፥አዳም፥ግዮንና ጣና
+ ኖኅ፥መርከቧና ጣና
+ ኖኅ፥መርከቧ፥አራራት ተራራ፥ጣና እና ግዮን
+ ኖኅ፣መርከቧ፣ታቦተ ጽዮን፣ቅድስት ድንግል ማርያም፣ክርስቶስ፣ጣና ቂርቆስ፣አራራት ተራራ እና ግዮን
ይኼ ሁሉ ከጣና እና ከግዮን ጋር የተቆራኘ አስደናቂ ምስጢር ሊመረመር ይገበዋል።በርግጥም የሚገለጥበት ዘመን ሩቅ አይሆንም!!
ከታደለ ጥበቡ የተወሰደ
/channel/yekdset_selase_lejoch
የቴሌ ኮም ዘርፍ ሽያጭና ሰሞነኛው ዛቻ::
የዓለም አቀፍ ተቁዋማት አመራሮችና የኅያል አገራት መንግስታት በጋራ የቀረጹትን ፖሊሲ ያለ አንዳች ጉርምርምታና ተቃውሞ ወደ ተግባር ለመለወጥ ይረዳቸው ዘንድ ልዩ ጥንቃቄ ያደርጋሉ:: ዕቅዳቸውም በጥንቃቄ የተጠናና የግድ መፈጸም የሚኖርበት ዕቅድ ነውና ለተፈጻሚነቱ ሲሉ ማናቸውንም አይነት መስዋዕትነት ይከፍላሉ:: ከተራ ትችት ጀምሮ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በብሄራዊ ደረጃ እስከ መብጠልጠል ድረስ ያለውን ውርጅብኝ በደስታ ያስተናግዳሉ::
የማይግባቡ መስለው ነገር ግን ተናብበው የሚሰሩ ናቸውና በመካከላቸው አንዳችም ጸብ ሳይኖር ውጊያ ቀረሽ ግብግብ ውስጥ የገቡ መስለው ይታያሉ::በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በቃላት ከመወራረፍ ያለፈ ሃሰተኛ የሚሳኤል ውጊያም ሊያደርጉ ይችላሉ:: ዕቅዳቸው ዳር ይድረስ እንጂ የዓለምን ህዝብ ጫጫታና ሃሜት እንዲሁም ትንተና ከመጤፍ አይቆጥሩትም!
በዚህ አይነት ሁኔታ "መስለው" ሳይሆን "ሆነው!" ስለሚተውኑ ለብዙዎች እንዲህ ያለውን እውነት ማስረዳት አይቻልም:: ማስረዳት ቢቻልም አስረድቶ ማሳመን አይቻልም::
እንዲህ ያለውን የረቀቀ አካሄዳቸውን ደግሞ በተቀደደለት የሰበር ዜና ቦይ በሚፈሰው በብዙሃኑ ህዝብ የፕሮፖጋንዳ ጫጫታ ያጅቡታል ሂደቱንም ከህዝብ ዕይታ ይጋርዱታል::የህዝቡን ትኩረት ሌላ ላይ እንዲሆን አድርገው ያቀዱትን ስራም ይሁን ሴራ በመንግስታዊ ህግ ያለ አንዳች ውይይትና ጉርምርምታ በምክር ቤት ደረጃ በሙሉ ድምጽ ያስጸድቁታል::መሻታቸውን በህጋዊ መንገድ በቁጥጥር ስር ያውሉታል::
በዚህ መሰሉ አካሄዳቸው ምክንያትም የነጠሩ ሴራ አዘል እውነቶቻቸው በጩኸት ብዛትና በተደጋጋሚ ሃሰተኛ የሰበር ዜና ርግብግቦሾች ይዳፈኑላቸዋል...::
******
አብይ አህመድ ስልጣን በያዘ ማግስት ከአንደበቱ የወጣው የመጀመሪያው ቃል "ፕራይቬታይዜሽን..." የሚለው ቃል ነው:: ለዚህም የኖቤል ቀብዱን ወስዶዋል:: ህወሃት (ለራሱና ለቢዝነስ ኢምፓየሩ ሲልም ቢሆን) በአብዮታዊ ዲሞክራሲና በልማታዊ መንግስት ስም ዘግቶ ይዞት የነበረውን ርዕዮት ማስለወጥና ፕራይቬታይዜሽንን ተግባራዊ ማስደረግ ይፈልጉ ነበር::ነገር ግን ኢህአዴግ "ይህ የሚሆነው በኢህአዴግ መቃብር ላይ ነው!" የሚል ቁርጥ ያለ አቁዋም ይዞ በድርቅናው ቀጥሎ ነበር የቆየው::
አሜሪካና እንግሊዝ ደግሞ ይህን ጉዳይ የግድ ተግባራዊ ማድረግ ነበረባቸውና ህወሃት መራሹን ኢህአዴግንና የፕራይቬታይዜሽንን ጉዳይ ዘግቶ የያዘባቸውን የቢዝነስ ኢምፓየር ኤፈርትን ጥለው በኢህአዴግ መቃብር ላይ ብልጽግናን ተክተዋል::
በብልጽግና አማካኝነትም የቴሌኮሙን ዘርፍ የመቆጣጠር የረጅም ጊዜ ፍላጎትና ህልማቸውን በትላንትናው ዕለት አሳክተዋል::(የቴሌ ኮም ዘርፍ ሲባል የስልክና የኢንተርኔት ዘርፍ ብቻ ማለት ለሚመስላቸው የዋህ ዜጎች እንደዚያ ማለት እንዳልሆነ ወደፊት በስፋት ለማስረዳት ይሞከራል) እናም ያ የአሜሪካና የእንግሊዝ የቀደመ ህልማቸው ዛሬ ተሳክቶ የቴሌኮሙን ዘርፍ እንግሊዝና አሜሪካ በቁጥጥር ስር አውለውታል ወይም ገዝተውታል::
ወይም የመጠቅለል ጅምራቸውን በፓርላማ አስጸድቀው ዘርፉን በበላይነት ይዘውታል::
ሁኔታው ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዘ እንዲመስልና ዘርፉ ከኢትዮጵያ መንግስት እጅ እየወጣ እንደሆነ እንዳናስብም ከ24 ሰዓት በፊት በሰየሙት አዲስ ስያሜ "Global partnership for ethiopia" ከሚለው አዲስ ስያሜ ጋር አገናኝተው የዘርፉን ሽያጭ ጨረታ ያሸነፉትን አካላት ይፋ አድርገዋል::”አሜሪካና እንግሊዝ የኢትዮጵያን የቴሌኮም ዘርፍ ገዙት” ከማለት ይልቅም በዚህ መንገድ አጨናብሮ መግለጹ የተሻለ እንደሚሆን ያውቃሉና ዜናውን በዚያ መንገድ ነው ይፋ ያደረጉት::
ዞሮ ዞሮ ግን Vodafone, Vodacom safari com, sumitomo corporation,and CDC group ሄድ ካርተራቸውን የተለያዩ አገራት ያድርጉ እንጂ የሁሉም ተቁዋማት መስራችና ዋና ባለቤት እንግሊዝና አሜሪካ ናቸው::የቴሌኮሙ ዘርፍ የተሰጠውም ለእነርሱ ነው::
ይህ በመሆኑም አሜሪካና እንግሊዝ ደስታቸው ወደር የለሽ ሆኖዋል:: የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚ/ርም ከእነሱ በላይ በደስታ ጮቤ መርገጡን ገልጾዋል:: ለ1.5 ሚሊዮን ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጥራል, 8 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት ማድረግ ይችላል, 850 ሚሊዮን ዶላር ጨረታውን አሸንፎዋል,ወዘተ የሚለውን ዜናም ለ "መጡልን" ባዮች አብስረዋል::ለ"መጡብን" ባዮች አርድተዋል::
ህዝቤ ደግሞ "አሜሪካ በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ የጉዞ እቀባ ልታደርግ ነው"
"አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ልትጥል ነው"
"በፍርሃት ኢምባሲዎቻቸውን ዘግተው ዋሉ...
"አሜሪካ ተላላኪዋ ህወሃት ስለወደቀባት ተበሳጭታ የኢትዮጵያን መንግስት ጠምዳ ይዛዋለች...የቀድሞ ወዳጁዋ የህወህት መውደቅ አበሳጭቶዋት... የመንግስት ህግ የማስከበር ዘመቻ ከንክኖዋት ጥምድ አድርጋ ይዛናለች... ይቺን መሰሪ ሰልፍ እንወጣባታለን... ባንዲራዋንም በአደባባይ እናቃጥልባታለን..." ምናምን የሚል ሌላ ጫዋታ ውስጥ ነው::
ብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ ይህን አይነቱን ሰበር ዜና በመሰባበር ላይ ነው!
በትናንትናው ዕለት በተወካዮቹ አማካኝነት" ተስማምቻለሁ ይሁን" ብሎ ስለፈረመበት ጉዳይ ግን ምንም የገባው ነገር የለም!
ህዝቡ እንዲህ ይነሆልል ዘንድም እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ አፈቀላጤው መሪ ተብየ መድረክ እያመቻቸ "ማንም እንደፈለገ የማያዘን አገራችንን ቁርስ ይህን ብይ እራት ምን በላሽ ይሄን ቀሚስ ልበሽ...የሚሉን ሉዓላዊነታችን ያልገባቸው የአባቶቻችን ልጆች መሆናችንን ያልተረዱ..." እያለ የሃሰት ዛቻውን እያንበለበለ በመፎተት የግርዶሹን ቀዳዳ ይደፋፍን ነበር::
በተቀደደለት ቦይ መፍሰስ...የሚለው ጉዳይ በዚህ መንገድም ይገለጻል ለማለት ነው...::
ዲጂታል ሲስተም ውስጥ ከመግባት ጋር ተያይዘው የሚነሱ ዘርፈ ብዙ ነገሮችን ወደፊት በስፋት የምናያቸው ይሆናል::
/channel/yekdset_selase_lejoch
መስቀል አደባባይን መጠቀም መብትም ነው፣ የነፃነት ምልክት ነው። ይህ ካልሆነ በባርነት ለመኖር መፍቀድ ነው ይላል አህመዲን ጀበል። ይህን ነገር ሳሰላስል ትምህርቱ የመጣው አርመንን ጨርሶ፣ ቤተክርስቲያናቸውን ወርሶ ያለ ሀፍረት ሲሰግድበት የማያፍረውን የኦቶማን ቱርከል የልጅ ልጅ ኤርዶጋን ሆነብኝ። ይህንን መረጃ በጥሞና አንብቡና አነጻጽሩት። #በመተከል፣ በአጣዬ፣ በዶዶላ፣ በኮፈሌ፣ በሐረርጌ፣ በወለጋ በብሔረሰብ ፖለቲካ ሥር ተሰውሮ እና ከዘረኞች ጋር ተባብሮ ኦርቶዶክሳዊያንን ሲያፈናቅልና ሲጨፈጭፍ የቆየው የመካከለኛው ምስራቅ መንፈስ ወራሽ አዲሱ የጥቂት የውጭ አካላት ተከፋይ አክራሪ ወጣቶች እምነት በዋና ከተማችን እንደ ኤርዶጋን ዘረፋን "መብትና ነፃነት" እያለ ሲሰይመው እናያለን። መንግሥት የአጀንዳው አካል መስሎ ለፍትሕ ሳያቀርበው የፖሊስና የተራ ፀጥታ ጉዳይ ብቻ አስመስሎ ጥፋቱን ወደ መሀል እየሳበ ነው።
መንግሥት ዜጎቹን እንዴት እንደሚያስተዳድር በግልፅ ፍትሐዊ፣ ትውፊታዊ፣ ሃይማኖታዊ ሚዛን ከውጭ ገብ ክፉ አመል መታደግ ነበረበት። ለነጀሩ የመንግሥት የራሱ አካላት ኦርቶዶክስን የመግፋት ከፍተኛ ፍላጎት ስላላቸው አገሪቷን ወደ አደገኛ ጠርዝ እየገፏት ነው።
======
ለአአዳዲሶቹ "የሙስሊም" ጠባይ ፊት መሪዎች ጥያቄዬ፦
የኤርዶጋንን ሠርቆና ነጥቆ መጸለይ፣ የአህመድ ግራኝ ጂሃድ ናፍቆት ያናወዛቸው ናችሁ ወይስ ይህ ጠባይ ከቁራንና ከሀዲዝ ያገኛችሁት ነው? ካልሆነ ሰውዬው (ኤርዶጋን) ሠርቆ ይጸልያል። የሌባን ጸሎት የሚቀበል አምላክ ካለ እርሱ ቅዱስ ፈጣሪ ነውን?
=======++++
#አምሳለ ኤርዶጋን በኢትዮጵያ
ዘር ፍጅት ፈጽሞ፣ ሠርቆ፣ ዘርፎ የሚጸልይና የሚፎክር የአርመንን ኦርቶዶክስ ያጠፉት ኦቶማኖች የልጅ ልጅ ኤርዶጋን አምላኩ ማነው?
ይህን መንፈስ ኢትዮጵያ ውስጥ ማየት እጅግ ያሳፍራል። ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የማናውቀውን አዲሱን የልጆች እምነት አንድ በሉልን። ነባሩን እምነታችሁን አስተምሯቸው።
መጤዎቹ ለመካከለኛ ምሥራቅ አገራት ያመጡትን መቅሰፍት ልብ በሉት። ሊቢያ ሲያርዱን የነበሩት ደማችንን እዚሁ ቤት ድረስ መጥተው እያፈሰሱት ነው። ቀጥሎ አካሄዳቸው ለከፋ ጥፋት መሆኑ በየተነሱበት አገራት ሁሉ ካደረሱት ሰቆቃ እናውቃለን።
በነገራችን ላይ ቴክኖሎጂ፣ ሥርዓተ መንግሥት፣ አስተሳሰብ፣ ፖለቲካ ወዘተ ሁሉን ተውሰን እችለዋለን?
አረ በሃይማኖት እንኳ ራሳችንን እንሁን!
#_ታላቅ_የስቅለት_እና_ከሲኦል_ነፍሳትን_የማውጫ_ጸሎት!
ዛሬ አርብ ይህንን ታላቅ ጸሎት ሳትጸልዩ አትዋሉ!
እጅግ ግሩም የስቅለት እና የሁል ጊዜ ጸሎቶ!
ኦርቶዶክሳውያን እባካችሁ ይህንን ጸሎት እየጸለያችሁ አንድ እልፍ /አሥር ሺ/ ነፍሳትን ከሲኦል አውጡ። የመድኃኔዓለም ቸርነት ከምናውቀው መጽሐፍ ቅዱስ በላይ ነው።
አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ይህን ጸሎት ሲጸልዩ ነፍሳትን ከሲኦል በቀን ሰባት ጊዜ በሌሊት ሰባት ጊዜ ያወጡበት ነበር!
ይህ ታላቅ ጸሎት የጌታችንን ሰቅለት እና የደረሰበትን መከራ በሰላምታ የሚያመሰግን ልዩ ጸሎት ነውና ጸልዩት!
በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም
ሼር በማድረግ ለምዕመናኑ አድርሱ፣የቃል-ኪዳኑን በረከት ተቋደሱ!
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ይህን ጸሎት በእግዚአብሔር አጋዥነት እጀምራለሁ፡፡ ኃጢአትን የምታስተሰርይ ንስሐን የምትቀበል በደልን ይቅር የምትል ለኃጥአን ተስፋ የአብ የባሕርይ ልጁና የሕይወት ቃል የዓለምን ኃጢአትን የምታሰተሰርይ የካህናት አለቃ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የእኔ ኃጢአትና የወገኖቼን ኃጢአት ይቅር በል፡፡
ጸሎትና ልመና ወደ እግዚአብሔር ምልጃ ለነፍስና ለሥጋ የሚጠቅም ነው፡፡ በሕይወተ ሥጋ ያሉ ሰዎች ይህንን ጸሎት በሚጸልዩነት ጊዜ አባቶቻቸውን፣እናቶቻቸውን፣ዘመዶቻቸውንና ወዳጆቻቸውን በአንዲት ጊዜ ከሲኦል ያወጡበታል፡፡
የእሾህ አክሊል ጎንጉነው ያቀዳጁሽ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እራስ ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ ሥጋችንን ለማንጻትና ነፍሳችንን ለመቀደስ እስከ መመታት ደርሰሽ ንጹሕ ደምን አፈሰስሽ፡፡ /ከቤተሰባችሁ የሞቱትን ሰዎች ክርስትና ስም አስገቡና ….. ማርልን ብላችሁ አባታችን ሆይ በሉ …../
ሰይጣን የተፋውን የኃጢአት ምርቅ ከእኛ ለማስወገድ ስለእኛ አይሁድ ርኩስ ምራቃቸውን የተፉብሽ የዓለም ቤዛ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የከበርሽ ፊት ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ ዛሬም የእኔን ኃጢአት አስወግጂ፡፡ /አባታችን ሆይ በል …../
አላዋቂ በሆኑ በሰቃልያን አይሁድ እጅ በጥፊ የተመታችሁ የዓለም ቤዛ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጉንጮች ሆይ ለእናንተ ሰላምታ ይገባችኋል፡፡ በእናንተ ምክንያት ፈጽሞ የተዘጋ ገነት ተከፈተ፡፡ እንዲሁም የልቦናዬ በር ፈጽሞ ይከፈትልኝ፡፡ /አባታችን ሆይ በል …./
የነፍሳችንንና የሥጋችንን መድኃኒት ትሰጭን ዘንድ የመረረ ሐሞትና ከርቤ ትጠጪ ዘንድ የወደድሽ የዓለም ቤዛ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የከበርሽ አፍ ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ እንደዚሁ ለእኔ የሕይወት መጠጥ አጠጪኝ፡፡ /አባታችን ሆይ በል …../
ስለ እኛ በአደባባይ የሞት መስቀልን የተሸከምሽ የዓለም ቤዛ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የከበርሽ ከፍ ከፍ ያልሽ ክንድ ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ ሁላችን የእጅሽ ፍጥረቶች ነንና የኃጢአቴን ሸክም ተሸከሚልኝ፣የበደሌን ሸክም አቅልይልኝ፡፡ /አባታችን ሆይ በል …../
ስለ እኛ ስለ ፍጥረቶሽ የመስቀል ግንድ የተላከብሽ የዓለም ቤዛ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልዩ የሆንሽ ጀርባ ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ ዛሬም የኃጢአቴን ግንድ አንሽልኝ፡፡ /አባታችን ሆይ በል …../
የተረገሙ አይሁድ በችንካር ይቸነክሩሽ ዘንድ የወደድሽ የመድኃኒታችን የፈጣሪያችን የኢየሱስ ክርስቶስ የከበርሽ ቀኝ እጅ ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ እንደዚሁ በስንፍናዬ የሠራሁትን በደሌን አጥፊልኝ፡፡ /አባታችን ሆይ በል …../
አስቀድመሽ ስለበደላችን ከሐድያን አይሁድ በችንካር ይቸነክሩሽ ዘንድ የወደድሽ ያለመለወጥ ፍጹም እግዚአብሔር ፍጹም ሰው የሚሆን የመድኃኒታችን የፈጣሪያችን የኢየሱስ ክርስቶስ ግራ እጅ ሆይ ላንቺ ሰላታ ይገባሻል፡፡ እንደዚሁ የእኔን በደል ቸንክሪ፡፡ የሞት ችንካር ከሚሆን ከዲያቢሎስ አድኚኝ፡፡ /አባታችን ሆይ …../
ስለ ኃጢአታችን ክፉዎች አይሁድ ይቸነክሩሽ ዘንድ ፈጽመው ያሰሩሽ የፈጣሪያችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የከበርሽ ቀኝ እግር ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ እንደዚሁ ኃጢአቴን አስተስርይልኝ፡፡ /አባታችን ሆይ በል …../
በእውነት የታመነ እውነተኛ ቅን ንጉሥ የሚሆን የዓለም ቤዛ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የከበርሽ ግራ እግር ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ ያለ በደል በቅዱስ መስቀል ላይ ተቸነከርሽ፡፡ እንዲሁ ኃጢአቴን ቸንክሪልኝ፣የበደሌን መጽሐፍ ደምስሽልኝ፡፡ /አባታችን ሆይ ……/
ኃጢአታችንን የምንታጠብበትና የምናተሰርይበት ውኃና ደምን ከጎንሽ እስከምታፈሺ ድረስ በመስቀል ላይ ሳለሽ በጦር ጎንሽን የተወጋሽ የጌታችን የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልዩና የከበርሽ ጉን ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ ተዘግቶ የነበረው የሰማይ ምስጢር ባንቺ ምክንያት ተገለጠ፣ተከፈተ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የልቤ በር ይከፈትልኝ፡፡ /አባታችን ሆይ በል …../
በመስቀል ላይ መከራን ለተቀበሉ ለጌታችን ለፈጣሪያችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ አካላት ሁሉ ሰላምታ ይገባቸዋል፡፡ የጌቶች ጌታ፣የንጉሦች ንጉሥ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ላንተ ክብር ምስጋና ይገባሃል፡፡ በታላላቅ ችንካሮች ይቸነክሩህ ዘንድ ለእኛ ስትል የወደድክ ዛሬም በፍቅርህ ትቸነክረኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ ከእኛ ጋር መከራን ስለተቀበልክ እኛም ካንተ ጋር መከራን እንቀበላን፡፡ በመስቀል ላይ የተቀበልከው የመከራህ ተሳታፊዎች አድርገኸናልና በመከራ ስለመሰልንህ እንደዚሁ በጌትነትህ በምትመጣበት ጊዜ በዕለተ ምጽአት ከአገልጋዮችህ ከቅዱሳን ጋራ ክብርን አድለን፡፡ /አባታችን ሆይ በል ……/
ታዖስ ወዖ አልፋ ቤጣ የምትባል ጌታዬ ኢየሱስ ክርቶስ ሆይ የባሕርይ አባትህ አብ መጠግያ ኃይል ይሁነኝ፡፡ እግዚአብሔር ዕድል ፈንታዬ ጽዋዕ ተርታዬ ነው፡፡ አቤቱ እንደ ቸርነትህ ጎዳናዬን አስተካክልልኝ፡፡ አንተ ለወደድከው መራራው ከማር ወለላ ይልቅ ጣፋጭ ይሆናል፡፡ እኔም ይህን እወደዋለሁ፡፡ እግዚአብሔር ሆይ አንተን መውደድ ስጠኝ፡፡ ፈጣሪዬ አስመልክተኝ፣አስተዋይ ልቦና ስጠኝ፣ፈጣሪዬ ጥበበኛ አድርገኝ፣ፈጣሪዬ አድነኝ፡፡ በውስጥና በውጭ ያለው የሚታየውንና የማይታየውን አበሳ የምታውቅ አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ አውግዮን፣ አውሎግሶን ልቦናዬንና ሰማያዊውን ቤት ክፈትልኝ፣ዐይነ ልቦናዬንም አብራልኝ፡፡ ኃጢአቴንም ይቅር በለኝ፡፡ .አባታችን ሆይ …../
መሐሪ የሆን አምላክ ሆይ፣ ይቅር ባይ አምላክ ሆይ፣ ቸር አምላክ ሆይ የእኔን የበደለኛውን ኃጢአት ይቅር በል፡፡ /አባታችን ሆይ በል/
ዓለም ሳይፈጠር አስቀድመህ የነበርክ ዛሬም ያለህ ዓለምን አሳልፈህ የምትኖር የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ልባቸው አብ ሆይ ላንተ ሰላምታ ይገባሃል፡፡ ዓለም ሳይፈጠር አስቀድመህ የነበርክ ዛሬም ያለህ ዓለምን አሳልፈህ የምትኖር የአብ የመንፈስ ቅዱስ ቃላቸው ወልድ ሆይ ላንተ ምስጋና ይገባሃል፡፡ ዓለም ሳይፈጠር አስቀድመህ የነበርክ ዛሬም ያለህ ዓለም አሳልፈህ የምትኖር የአብና የወልድ ሕይወታቸው እስትንፋሳቸው መንፈስ ቅዱስ ሆይ ላንተ ስላምታ ይገባሃል፡፡ /ሦስት ጊዜ በል/ አቤቱ ፈጣሪዬ ሥጋዬንና ነፍሴን ባርክ፡፡ አባቴ ፈጣሪዬ ሕይወቴንና ሞቴን ባርክ፡፡ አቤቱ ፈጣሪዬ ጸሎቴንና ልመናዬን ባርክ የእኔን የኃጥኡን የ ……….. /አባታችን ሆይ በል ……./
ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የሚያስጨንቅ ለአንተ ቀላል ነው፡፡ የራቀ ላንተ ቅርብ ነው፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ይቅርታህን ከእኔ አታዘግይብኝ አታርቅብኝ፡፡ የሚያደንቁህን ክፍ ከፍ አድርጋቸው፡፡ ላንተ ቀላል
ሰላም "የኦርቶዶክሳዉ ጥያቄዎች" አባላት በሙሉ🙌 በጥያቄዉ ዙርያ ብዙም ተሳትፎ የለንም ስለዚህ መልሱን ለመልቀቅ 100 እይታ እናከ 20 ሰዉ በላይ መሳተፋ አለበት።
መልሱን ለመመመለስ ነጭ ከሆነ የ ነጭ ምልክቱን (⚪️)
ቀይም ከሆነ የቀይ ምልክቱን(🔴)
በመጫን መመለስ ይችላሉ።
አገልግሎታችንን እንድናሰፋ ሊንኩን ሼር ያርጉልን
👇👇👇👇👇👇
@ortodox_tyake
ሰላም ለእናንተ የኦርቶዶክሳዊ ጥያቄዎች ቻናል ተከታታዮች በጥያቄዉ በኩል ስለጠፋን ይቅርታ እየጠየቅን🙏
ከዛሬ ጀምሮ መንፈሳዊ ጥያቄዎችን እናቀርባለን እናንተም በመመለስ ቃለ እግዚአብሔርን እንማማር።
ሼር በማድረግ ጎደኞትን ይጋብዙ
@ortodox_tyake
@ortodox_tyake
@ortodox_tyake
የዐብይ ፆምን ምክንያት በማድረግ
#ታላቅ_የንግስ_በዓል_ጉዞ_ወደ_ሳማ_ሰንበት_ቤተክርስትያን
#መነሻ_ቀን መጋቢት 25/2013
#መመለሻ_ቀን መጋቢት 26 ከሰአት በኃላ
ለመመዝገብ በ 0922_476538 ወይም 0955_400247 በመደወል ተመዝገቡ የቀረን ጥቂት ቦታዎች ብቻ ናቸዉ።
በማርያም ሼር በማድረግ ቢያንስ ድምጻችንን እናሰማ!!! የቻልን በአቅማችን ካልቻልን በአይነት እንደግፍ
•➢ SHARE "SHARE "SHARE •➢
• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
ለየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ
ለOffice of the Prime Minister-Ethiopia
ለ ጠቅላይ ቤተክህነት
•➢ የአባታችሁ የአባታችን የአባ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ታላቅ ቦታ አሰቦት ገዳም ከነገዳማውያኑ ከሰአታት በኋላ ታሪክ ሊሆን ነው።
•➢ እሳቱ በአስፈሪ ፍጥነት ወደገዳሙ ተጠግቷል። ከገዳሙ በፊት እኛ እንጥፋ የሚሉ ኦርቶዶክሳውያን በእሳቱ ውስጥ በጭስ እየታፈኑ ራሳቸውን እየሳቱም ግብ ግብ ላይ ናቸው።
-ገዳማውያኑ በአባታችን ቦታ እሳት ይብላን አብረን እንቃጠላለን እንጂ አንሸሽም ብለው በአቋማቸው ፀንተዋል።
-መጨረሻው እየተቃረበ በመሆኑም ንዋየ ቅድሳትና ታቦታቱን ለማሸሽ እንቅስቃሴ ተጀምሯል። በኛ ዘመን አይናችን እያየ የስውራኑ የግሁሳኑ ቦታ አሰቦት ታሪክ ይሁን? ከዚህ በላይ ዳግም ሞት አለ?
እንረባረብ!
በሰው ሀይል የማይጠፋ እሳት ነው ነገር ግን በጣም ከአቅም በላይ እየሆነ ነው ። ብፁዓን አባቶች በአስቸኳይ የሄሊኮፕተር ትብብር ይጠይቁ ቢያንስ ገዳሙንና ገዳማውያኑን እናትርፍ
✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከዚህ በላይ አስቸኳይ ጉዳይ የለም!
✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
💚 •✥• @Z_TEWODROS •✥• 💚
💛 •✥• @Z_TEWODROS •✥• 💛
ሀገርህም ቤተ ክርስቲያንህም ይፈልጉኻል
▫️▫️▫️▫️▫️▫️▫️
ከማንም በላይ ቤተ ክርስቲያንህ ሰው ሁሉ እኩል መሆኑን አስተምራሃለች፡፡ ቤተ ክርስቲያንህ በመጨረሻው ቀን አድልኦ በማያውቅ ፈታሔ በጽድቅ በሆነ አምላክህ ፊት እንደምትቆም እየነገረች አሳድጋሃለች፡፡ ቤተ ክርስቲያን እውነትን እውነት፣ ሐሰትን ሐሰት ማለት በሰማይ ቤት ያለውን ዋጋ ከልጅነት ጀምሮ እያስታወሰችህ አድገሃል፡፡ አትግደል፣ አትስረቅ፣ አረጋውያን አክብር፣ ወንድምህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ ወዘተ… እያለች ሰብእናህን ቀርፃለች፡፡ ዓለም እንኳ ወርቃማው ሕግ ያለውን “በአንተ እንዲሆን የማትሻውን በሌላ ላይ አታድርግ፣ እንዲሆንበትም እትፍቀድ” የሚለው ሕግ ምንጭ ቤተ ክርስቲያንህ ናት፡፡
በዚሕ ሕይወት ማለፍ ወደ ልዕልና ጫፍ እንደሚያደርስ እየተማርክ ባደግኸው/ሽው በአንተ/በአንቺ ሚና ፖለቲካውን እንደገና መውለድ ይቻላል፡፡ ፖለቲካው ያንተን ፊት ዐይቶ በማያዳላ አስተሳሰብ የተሞረደ፣ በፈሪሐ እግዚአብሔር የታሸ አስተዋጽኦ ይፈልጋል፡፡ ሀገርህም ቤተ ክርስቲያንህም ይፈልጉኻል፤ ምንም እንደሌለውና እንደማይፈለግ ውጭ ቆመህ አታልቅስ፡፡ ግባና ፖለቲካውን ኢትዮጵያዊ አጨዋወት ዐሳየው፤ ሥነ-ምግባራም አድርገው፡፡ የወደድከው ብቻ፣ የመረጥከው ብቻ እንዲመራህ ምረጥ፣ ተመረጥ፤ ሐቅን ይዘህ በምርጫው ሒደት በጎ ቦታ ይኑርህ፡፡ ሕዝብህን ምራ፣ አስተዳድር፡፡ ሓላፊነት የሚሰማው መሪ ሁን፡፡ ሀገርህም ቤተ ክርስቲያንህም ይፈልጉኻል፡፡ ድምፅህ ለሀገርህም ለቤተ ክርስቲያንህም ይፈልጋታል።
#እንኳን #ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_በዓል_በሰላም_እና_በጤና_አደረሳችኹ፡፡
መጋቢት ፭ በዓለ ዕረፍት ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (አቦ፥ አቡዬ)፤
* እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ብርሃነ ዓለም የኾኑ፤
* እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋን እና ክብርን የተሞሉ፤
* ኮከበ ገዳም፥ መናኔ ዓለም፥ ምድራዊ መልአክ፤
* ስማቸውን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ያወጣላቸው፤
* በአክናፈ መባርቅት ተጭነው የሚጓዙ፤
* ፷ አናብስት እና ፷ አናብርት ይታዘዙላቸው የነበሩ፤ የእግራቸው ትቢያ ለአራዊቶቹ ምግብ የኾነላቸው፤
* ለብዙ አእላፍ ቅዱሳን ወላዴ የኾኑ እና በረከትን የሠጡ ታላቅ አባት (ለአብነትም፤ ለቅዱስ #ላሊበላ፥ ለአቡነ #ሳሙኤል ዘዋልድባ፥ ለአባ #አንበስ ዘደብረ ሐዘሎ፥ ለአባ ብንያም ዘግብጽ)
#ምድረ_ከብድ_፤ /ዝ_ምድር_ክቡድ_ውእቱ_/ ፤ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ)
ምድረ ከብድ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያረፉባት ቦታ ናት፤ ቀጥሎ ወደ ደብር ቅዱስ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ) ለጸሎት ሒደው ለሀገራችን ኢትዮጵያ እና ለዓለማችን ምሕረት እና በረከትን ከአምላካችን ለ፻ ዓመታት በባሕር ውስጥ ኾነው ለምነዋል፤
ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው ለ፯ ዓመታት ጸልየዋል፤ ቊራም በሰይጣን ተመስሎ መጥቶ ዓይናቸውም ቢያጠፋውም ከ፯ ሱባዔያት በኋላ ሊቀ መላእክት ሚካኤል እና ገብርኤል ዓይናቸውን መልሰውላቸዋል፡፡
ወደ ዝቋላ በመመለስም አጋንንትም ከምድረ ዝቋላ አጥፍተዋል፤ እንደገና ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው በነበሩበት ጊዜ ታላላቆቹ እና በአንበሳ ዘባን ላይ የሚሔዱት #አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ ፣ #አባ_አንበስ_ዘደብረ_ሐዘሎ_አፋር)፣ #አባ_ብንያም_ዘግብጽ ከአባታችን ቡራኬ ለመቀበል መጡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ተሠውረው ነበርና፤ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አናብስት የ፫ቱን አባቶች አናብስት በሉባቸው፤ በ፯ኛው ቀን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ተገልጠው የኾነውን ነገር በማየት የተበሉትን አናብስት እንዲመልሱ የራሳቸውን አናብስት አዘዟቸው መልሰውም እንደነበሩ በተዓምራት አስነስተው ሰጧቸው፤ በደመና ጠቅሰው ቅዱስ ፋኑኤል ፫ት ሰማያዊ ኅብስትና ፫ት ጽዋዕ ይዞ ለእንግዶቻቸው ይዘው ሠረገላ በሚባለው ዋሻ አመጡላቸው እና ሰጥተው ሸኟቸው፤ እነዚኾን ቅዱሳን በሸኙ በ፯ኛው ቀን ወደ ተለያዩ ሀገራት ሔደው አስተምረዋል፡፡
እድሜያቸው ረዥም እንደመኾኑ፤ ቅዱሱ ንጉሥ አፄ ላሊበላን ጨምሮ ሌሎችም ቅዱሳን ወደ ርሳቸው እየመጡ በረከትን ተቀብለዋል፡፡
#በግብፅ_300_ዓመታት_፥ #በኢትዮጵያ_ምድር_ላይ_262_ዓመታት (በዋነኛነት #በምድረ_ከብድና_በዝቋላ_ ቢኖሩም ሌሎችም የመሠረቷቸው እና የኖሩባቸው ገዳማት አሉ፤ ለአብነትም ደቡብ ወሎ የሚገኘውን #ገዘዛ_አቦን_ መጥቀስ ይቻላል)
በድምሩ ፭፻፷፪ ዓመታት ከኖሩ በኋላ በንጉሥ ሕዝብናኝ(እንድርያስ) ዘመነ መንግሥት፤ መጋቢት ፭ ቀን ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ብዙ ቃል ኪዳንን ጌታችን ሰጣቸው፥ ፲፪ አክሊላትንም አቀዳጃቸው፤ የነበሩባት ምድረ ከብድ ገዳም ግን ራደች፥ ተንቀጠቀጠች፥ በብርሃንም ተጥለቀለች፤ ዝቅ እያለችም መንሸራተት ጀመረች፤ ጌታችንም አንቺ መሬት ኾይ ጽኚ ይኽንን ኹሉ ስለቻልሽ ምድር ክቡድ /ኋላ ምድረ ከብድ/ ተብለሽ ተጠሪ አላት፤ የጻድቁም ነፍስ ከሥጋቸው ከሌሊቱ ፮ ሰዓት ተለየች፡፡
ይኽችውም ምድረ ከብድ ጻድቁ የኖሩባት እና የቀደሱባት፥ የመሠረቷት እና ያነጽዋት፣ ሠራዊተ መላአክት የከተሙባት፣ ታላላቅ አበው መጥተው በረከት ከአባታችን የተቀበሉባት፣ አርምሞ እና ጸጥታ የማይለያት፤ ዐጸዷና ቅጥሯ ልቡናን የሚመስጥ፤ ከአ.አ ፻፳፭ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ናት፡፡
/channel/yekdset_selase_lejoch
🤴 ስለ ንጉስ ቴዎድሮስ 🤴 🤴 🤴
🩸 ትንቢት የተነገረለትን ንጉስ የቴዎድሮስ የሚነሳበት አስደናቂና ምስጢራዊ ስፍራ
🩸 እውነት ትንቢት የተነገረለት ንጉስ ቴዎድሮስ ይመጣል ?
🩸 በፍካሬ ኢየሱስና በገድለ ፊቅጦር ስለ ትንቢታዊው ንጉስ ቴዎድሮስና ተጽፎ ይገኛል
🩸 የየረር ተራራ አስገራሚ ምስጢሮች
እነዚህን እና ሌሎች ሚስጥራትን 🤴 ስለ ንጉስ ቴዎድሮስ ማወቅ ከፈለጉ
join join join
👇👇👇👇👇
/channel/yekdset_selase_lejoch
#ልጅኽን_በፖለቲካዊ_ጉዳዮች_ላይ_እንዲሳተፍ_አድርገው፤
እንደ ችሎታው መጠን እና ከኀጢአት ነፃ በኾነው ነገር ላይ እንዲሳተፍ አድርገው፤
ወታደር ቢኾን ደመወዙ ብቻ እንዲበቃ አስተምረው፤ ለተበደሉት ኹሉ ጠበቃ እና መከታ እንዲኾንላቸው ምከረው፤ አስተምረውም።
በሌሎች የሥራ ዘርፎች ላይ ሲሰማራም ኀጢአት ባለ መሥራት፣ በአግባቡ እና በሥርዐቱ ሰዎችን ማገልገልን አስተምረው "
( ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
[ ኦርቶዶክሳውያን እና ፖለቲካ ፤ በዳዊት ደስታ ፤ ገጽ 9 ፤ 2013 ዓ.ም. ]
@yekdset_selase_lejoch
@yekdset_selase_lejoch
@yekdset_selase_lejoch
ቶ መስቀል እና የሰለ(የ)ጠነው አለም/ Ankh and modern world/
ከዚህ ቀደም በየ ድህረ ገፁ የተለጠፉትን ስለ ቶ መስቀል የሚገልፁ ፅሁፎች ከራሳችን እሳቤ ጋር በማዛመድ ፅፈንላችሁ ነበር። አሁን ደግሞ ከቤተክርስቲያን ስርአት አንፃር ያለውን ለቀንላችኋል። ሀሳባችሁን ሰብሰብ፣ አዕምሯችሁን ከፈት አድርጋችሁ አንብቡና፤ ለጓደኞቻችሁ #ሼር አድርጉላቸው።
የዳቢሎስ ማህበርተኞች በአንገታቸው፣ በልብሶቻቸው፣ በቦርሳቸው፣ በንቅሳት መልክ ሲጠቀሙበት ይስተዋላል። እንደ እውነቱ ከሆነ የቶ መስቀልን እውነተኛ ምንነት መናገር እጅግ ከባድ ነው። ነገረ ግን በሰለጠነው ዘመን ፓጋኖች ምልክታየው አድርገው ሲጠቀሙበት ይስተዋላል። ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀልም ቢሆን ይጠቀሙበታል። እንዲያውም በጆሮ ጌጥ እና በልብስ ማድረግ አንሷቸው በጫማ ሶል ላይ ያደርጉታል።
ክርስቶስ በወንጌሉ ዮሐ 6:47 "በኔ የሚያምን የዘለአለም ህይወት አለው" ይላል። ታዲያ የዘለአለም ህይወት ቁልፉ ቶ መስቀል ወይስ ክርስቶስ??
የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን በማጭበርበር ወደ ገሀነም መንገድ መምራት የጀመሩት ማህበረ ስላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ የተሰኘው ማህበርም ቶ መስቀልን የማህበሩ መለያ አድርገውታል። አንድ በዚህ ማህበር ዋና አባል የነበሩ አባትም ከስህተታቸው ታርመው ወደ እናታቸው ቅድስት ቤተክርስቲያን መመለሳቸውን በማህበረ ቅዱሳን ቴቪ/EOTC/ ላይ ተናግረዋል።
ከአንድ ኦርቶዶክሳዊ የዩቲዩብ ቻናል የተለቀቀ ቪድዮ ላይ ደግሞ አባ ተስፋ ስላሴ ሞገስ፣ መሪ ራስ አማን በላይ እና ፕ/ሮ ፍቅሬ ቶሎሳም ስለ ቶ መስቀል በስፋት የተናገሩ ሲሆን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በሚለው ሳይሆን ተዋህዶ በሚለው ብቻ የሚያምኑ ግለሰቦች ነበሩ ይላል። ነገር ግን የታሪክ መፅሀፎቻቸውን ሪፈር ማድረግ የለብንም ማለት አይደለም። እውነት የሆነውን ታሪክ በማስረጃ እንቀበላለን።
ልብ የምትሉት ግን ሰይጣናዊ ማንነት አለውም እያልኩ አይደለም። ምክንያቱም አሁን ትልቅ ውዝግብ እየፈጠረ ያለው ይኼው ጉዳይ ነው።
ገላትያ 6:14 "አለም ለኔ ከተሰቀለበት እኔም ለአለም ከተሰቀልኩበት ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት የለም" ይለናል። ህይወታችን ክርስቶስ ነው። ትምክህታችንም በ34 ዓ.ም በእለተ አርብ በቀራንዮ አደባባይ የተሰቀለበት መስቀል እንጅ 3000 B.C ላይ በግብፃውያን ዘንድ የነበረው "ቶ" አይደለም። "ኢትኤል ቆ በትርን ወንድሙ ሀሙኤል ቶ በትርን ይይዙ ነበር" የሚለውን ታሪክ እንቀበላለን። ነገር ግን በትረ መንግስት እንጅ የድህነት ምልክት እንዳልሆነ በዘመኑ የነበሩት እነ ኢትኤል ይመሰክራሉ።
ፊልጵስዩስ 3:18-20 "ብዙዎች #ለክርስቶስ #መስቀል #ጠላቶች ሆነው ይመላለሳሉና ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኳችሁ፤ አሁንም እንኳ እያለቀስኩ እላለሁ #መጨረሻቸው #ጥፋት ነው ሆዳቸው አምላካቸው ነው፤ ክብራቸው በነውራቸው ነውና፤ #ሀሳባቸው #ምድራዊ ነው እኛ #ሀገራችን #በሰማይ ነውና፤ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድሀኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ #ክርስቶስን #እንጠባበቃለን።"
ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል በቶ መስቀል ለውጣችሁ አንገታችሁ ላይ ያደረጋችሁ፤ የድሮውን የድህነት ማዕተብ አድርጉ፤ ቶ መስቀልንም አውልቃችሁ አስቀምጡ። ቶ መስቀል ታሪካዊ ማንነት እንደሚኖረው ግልፅ ነው። ሀይማኖታዊም ማንነትም ይኖረው ይሆናል። መቼም ቢሆን ግን ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል አይተካም ዶግማ ነውና።
ሁሌም ቢሆን አባቶች ከእኛ ይበልጣሉና "መታዘዝ ከመስዋዕት ይበልጣል" የሚለውን እናስታውስ።
አዋጅ አዋጅ አዋጅ! ያልሰማህ ስማ የሰማህ ላልሰማ አሰማ!
/channel/yekdset_selase_lejoch
/channel/yekdset_selase_lejoch
/channel/yekdset_selase_lejoch
የ 666 ተከታይ አግብታ ፤
ሰይጣን የወለደችው ኢትዮጵያዊት!!
_______________________________
[ ይሄን የኢትዮጵያዊት እህታችንን ታሪክ አንብባችሁ ማትጨርሱት ከሆነ አትጀምሩት! ]
እኔ መልከመልካም ከሚባሉ ሴቶች መካከል አንዷ ነኝ።እናትና አባቴ ቆንጆዎች በመሆናቸው የሁለቱንም መልክ ተጋርቻለሁ።እናቴ አንድ ቀን እንኳን በስሜ ጠርታኝ አታውቅም።መልኬን በጣም ስለምትወደው " የኔ ቆንጆ " እያለች ነበር እምጠራኝ።አባቴ ደግሞ ብዙ ግዜ በተለይ ደግሞ ማታ ሞቅ ብሎት ሲመጣ " የኔ ሞናሊዛ" ይለኛል።እነዚህ የቤተሰቤ ቁልምጫና ቃላት የኔ የውበቴ ማረጋገጫ በመሆናቸው ከልቤ እፈነድቃለው።እኔ ሁለተኛ ልጅ ስሆን ከኔ በታች አምስት ሴቶች አሉ።የመጀመሪያው ልጅ ወንድ ነው።በትምህርታችን ሁላችንም ጎበዞች ነበርን።አባቴ በደርግ ዘመን የመንግስት ፓርቲ ውስጥ ሠራተኛ ስለነበር በወር 800 ብር ደሞዝ ያገኝ ነበር።ይህም ገንዘብ በወቅቱ ከነበረው የኑሮ ሁኔታ አንፃር ሲታይ በጣም ብዙ ስለነበር ምንም አይነት ችግር አይተን አናውቅም።በትምህርቴም ጥሩ ውጤት በማምጣቴ አዲስአበባ ዩንቨርስቲ ገብቼ አስፈላጊ በሆነ የሙያ ዘርፍ ተመርቄአለሁ።ከዛም የውጭ ሀገር ትምህርት እድል በማግኘቴ ወደ ባህርማዶ ተሻገርኩ።እዛም መንግስት እየረዳኝ ትምህርቴን በጥሩ ሁኔታ አጠናቀኩ።የተማርኩበት ሀገር መንግስትም ሙያዬን ስለወደደው እዛው በጥሩ ደሞዝ ተቀጠርኩኝ።
...
ነገር ግን በወቅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው የደርግ መንግስት ሲወድቅ ያባቴ ደሞዝ ተቋረጠ።አባታችን እኛን ከማስተማር ውጭ አንድም ቀን ደሞዙን በባንክ የማስቀመጥ እድል አላገኘም ነበር።ስለዚህ የርሱ ገቢ ሲቀር ቤተሰባችንን የመርዳትና የማስተዳደር ሀላፊነት በኔ ትክሻ ላይ ወደቀ።አባቴም በፖለቲካው ውስጥ አባል ስለነበር ለ 5 አመታት ያክል ቃሊቲ ታሰረ።በ 6ኛው አመት ቢፈታም የጤናው ሁኔታ የተሟላ አልነበረም።ስለዚህ እኔ የሚከፈለኝን ገንዘብ ሁሉ ላባቴ ህክምና ፤ ለህቶቼ የት/ቤት ክፍያ ፤ ለቤተሰብ እንዲሁም ለራሴ የቤት ክራይና ቀለብ ስለማወጣ ይሄን እንዴት ብዬ ላብቃቃው?? በጣም ከበድ ነበር።ከዛም ትዳር ብይዝ ያለብኝ ጫና ይቀንስልኛል ብዬ አሰብኩ።እንደተመኘውትም አንድ የዛን ሀገር ዜጋ ነጭ ባል ቢጤ አገኘው።" የኔ ቆንጆ " እያለ ሲያደንቀኝ እናቴን አስታወሰኝ።ቋንቋው ከሷ ቢለይም ፍቅሯን ያገኘው ስለመሠለኝ ይሄን ነጭ ሰው ወደድኩት።እሱም እንጋባ ብሎ ሲጠይቀኝ በወቅቱ የነበረብኝን የሀገር ቤት ችግር ስለማውቀው ፤ ምንም አይነት ግዜ መስጠት አልፈለኩም ነበር።ስለዚህ ደጋፊ በማግኘቴ ተደስቼ በሱ ቤት ውስጥ ተጋባን።
...
እኔ ፀሎት ፀልዬ አላውቅም።አንዳንድ ግዜ ግን በአቅራቢያዬ በሚገኘው የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እሄድ ነበር።ይሄን ሰው ካገባሁ በውሀላ ግን መሄድ አቆሙኩ።ባሌን ለማስደሰት ስልና ችግሮቼን ለማሳለፍ ስል እሱ እሚወደውን ነገር ሁሉ ማድረግ ነበረብኝ።ስለዚህ ከአርብ ማታ ጀምሮ እስከ እሁድ ማታ ድረስ የሌሊት ጭፈራ ቤት እንዝናና እያለ ይወስደኝ ነበር።በጣም እሚገርመው ብዙ ገንዘብ እሚሰጠኝ ጭፈራ ቤት ስንሆን ነው።በየሳምንቱ በሚሰጠኝ ገንዘብ የቤተሰቦቼን ችገር ማቃለል በመቻሌ ለማገኘው ገንዘብ ብቻ ስል የሌሊቱን ዳንኪራ ወደድኩት።ባሌ ነጭ ፈረንጅ ስለሆነ የሀገሬን አለባበስ በኔ ላይ አልወደደውም።ስለዚህ እርሱን ለማስደሰት ስል ብቻ ልክ እንደ ነጮቹ ከእርቃን ገላ እኩል የሆነ ብጥሌ ጨርቅ መልበስ ጀመርኩ።እርሱም አንደዛ ሁኜ ሲያዬኝ የፈገግታው አድናቆት በጣም ይገርመኛል።
...
የሠው ሀገር ባህል በጣም አስቸጋሪ ነው።አንድ ቀን እምንዝናናበት ያ የሌሊት ጭፈራ ቤት " ዛሬ የመርሀግብር ለውጥ አድርገናል " ሲል ማስታወቂያ ለጠፈ።ማስታወቂያውም " የራቁት ጭፈራ " እሚል ነበር።ሁሉንም የግብዣ አይነት ድርጅቱ የሚከፍል በመሆኑ ደንበኞቹ ሁሉ የመራቆት ግዴታ እንዳለባቸው አሳወቀ።በዚህ ግዜ ሁሉም ሰው በጭብጨባ ተቀበለው።በመቀጠል ጭፈራ ቤቱ ውስጥ የፍየል ቀንድ አይነት ያለው ፤ የድብርት መንፈስ እሚመስል ጥርሱን ያገጠጠ አይኑን ያፈጠጠ አውሬ መሳይ ቅርፀ-ቢስ ፍጡር እንዲሁም ነፍስ እንዳለው አይነት አፉን የሚከፍት ዘንዶ መሳይ አውሬ በዛ ምሽት በግድግዳው ላይ እሚታዩ ትርኢቶች ነበሩ።እኔም ራቁቴን ቁጭ ብዬ የሚሆነውን ስመለከት በጣም አዘንኩ።በዳንሱ የደከመ ሰው መስዬ አንገቴን ደፍቼ አለቀስኩ።
...
በዚያች ቅፅበት ጨዋው የኢትዮጵያዊነት ባህልና እምነቴ እጅግ ናፈቀኝ።ባሌም ሁኔታዬን ሲያይ በአንድ ትንሽ መለኪያ ነጭ አረቂ የሚመስል ነገር ሰጠኝ ስቀምሰው ትንሽ ይጣፍጣል።ከዚያ ከ 5 ደቂቃ በውሀላ ሀይል ብርታት ጉልበት ሳቅና ፍንደቃ ሆነ።ብቻ ኧረ ምኑ ቅጡ!! ሁሉንም አይነት ሰው ሁኜ የለየላት ዳንሰኛ አደረገኝ።እዛው ውስጥ የነበሩት ነጮቹ ወንዶቹና ሴቶች ጭራሽ እኔን አድናቂ ሁነው ሳይ በጣም ገረመኝ።የመልኬ ቀይ ዳማነት የሀበሻነቴ ፥ ሽንጥና ዳሌ እሚሉት ውበት ነጮቹን ሰዎች ስለማረካቸው ፤ " ጠይም ውበት የሴት መልአክ ትመስያለሽ " በማለት ሸለሙኝ።የቅዳሜው ምሽት ላይ ደግሞ ድርጅቱ ሸለመኝ።
...
እሁድ ሌሊት ለሰኞ አጥቢያ ባሌ አንድ ትልቅ በአል እንደምናከብር አሳወቀኝ።እሱም " የሰይጣን ቀን...ሀሎዊን " ነበረ።ባሌ " እኔ የባፎሜት እምነት የላዕላይ ሀላፊ ቡድን መሪ ነኝ።" ብሎ ነገረኝ።እኔም እምነቱ ምን እንደሆነ ያወኩት ሰኞ ጠዋት ነበር።ያን ለት ጠዋት ከዳንስ ቤቱ ውስጥ ለበአሉ ድምቀት እሚሆን የሀሎዊን ጭርንቁስ ጨርቅና የፍየል ቀንድ እሚመስል ማስክ ለሁሉም ሲታደል ለኔም ደረሰኝ።በዚህ ግዜ የሀገሬ እምነት ባህሉ እንቁጣጣሹ ፤ ጥምቀቱ ፤ ገናው ፤ ተንሳኤው ፤ ፍልሰታው ፤ የቅዳሴው ድምፅ ሁሉ ልቤ ውስጥ ጮኸ።የኢትዮጵያ የጥበብ ቀሚሱ ነጠላው ኩታው ፤ ጋቢውና የናቴ መቀነት ሁሉ ታወሰኝ።እንዴት በ Halloween ጭርንቁስ ቡቱቱና የአውሬዎች የቀንድ ምስል ልለውጠው እያልኩ ውስጤ ታመመ።ይሁን እንጅ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ሁኜ ሳልወድ በግድ የባሌን የ Halloween እምነት አከበርኩ።
...
ሰኞ ለት ማታ ሁላችንም ግማሽ መለኪያ አረቂ መሳይ በትንሹ ጠጣን።እኔም እንደተለመደው ከሁሉ የተሻልኩ ፈንዳቂ ነበርኩኝ።እድሜዬ 26 አመት ቢሆንም ነጮቹ ግን " የ 16 አመት ወጣት ልጅ ትመስያለሽ።" እያሉ ይነግሩኛል።እንደዛሬው ሳይሆን ድሮ በደርግ ግዜ የሀበሻ ልጆች እድሜ ቀስ ብሎ ስለሚያድግ አይቸኩልም።ታዲያ የኔም እድገት እንደዛው ነበር።የሰይጣኒዝም በአል ባከበርንበት ቀን ባሌ ያልኩት ሰው የተለዬ ስሜትና የሚያስፈራ ድምፅ እያሰማ ይጮህ ነበር።በተለይ ድምፁ ከሰባዊ ፍጡር እማይጠበቅ ጎፍናኝ የጎረና እና ዘግናኝ አይነት ነበር።ከበአሉ አከባበር በውሀላ ባለቤቴ " ዛሬ የማምነውና የምወደው መንፈስ በቋንቋው አናግሬው ወንድ ልጅ እንደምትፀንሽ ነግሮኛል።"ብሎ ነገረኝ።እኔም ይሄን ስሰማ በጣም ደንቅጬ የምናገረው ግራ ስለገባኝ ዝም አልኩኝ።ምክንያቱም ያን ለት የባሌን ድምፅ የሰማሁት በሚሰቀጥጥ አኳኋን ነበር።እንደዚህ አይነት ድምፅ ግን ከዛን ቀን በፊት አልሰማውም ነበር።ይሁን እንጅ ይህ ባሌ ያልኩት ሰው ነው?? የሚለውን ጥያቄ ደጋግሜ ለማሰብ ተገደድኩ።ነገር ግን መልስ የሌለው ጥያቄ ሆነብኝ።
...
የሰው ሰይጣን ይሁን ፤ ወይስ ሰይጣን የሆነ ሰው እያልኩ ነገሮችን ማብሰልሰል ጀመ
ተመላኪው አብይ😁
___________________
"ህዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል" ይላል ቅዱሱ መፅሐፍ
ዘመኑ የሀሰተኛ ትምህርትና የክህደት መፍለቂያ መሆኑን የበለጠ ለማስረዳት ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩትን ማሳየት ጠቃሚ ይመስለናል።
የሰው ልጅ በወንጌል ላይ የተገለጠውን ክርስቶስን ሳይሆን በሰው ብልሃት የተቋቋመችውን ምድራዊ ተቋም፣ የሰዎች ድርጅት፣ የአስተምህሮ መንገድና ስብከት እየተከተሉ ከእውነት ሲያፈነግጡ ማሳየት ተገቢ እንደሆነም ይሰማናል።
በኢትዮጵያ አብይ እንደሚመለክ ያውቃሉ?
ቃል በቃል አብይ አህመድን የሚያመልኩ ጉዶች መከሰት ጀምረዋል፤ እስካሁን ባለኝ መረጃ 5102 [ ይህ ቁጥር በፌስቡኩ አለም ብቻ ነው ] የሚደርሱ የእምነቱ ተከታዮችን አፍርቷል ፤ እንዲህም በማለት ያመልካሉ ይዘምራሉ!
" ሕይወት ያለአንተ ባዶ ናት። ቃልህ ከምግብና ውሀም በላይ ነው። የነገስታት ንጉስ የጌቶች ጌታ። ቅዱስ ቅዱስ ዶ/ር አብይ የዘለዓለም ሕይወት ባንተ ነው ነፍሴን አድናት መንፈሴን በሀሴት ሙላው። ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል የምሰግድልህ አንተ አዳኜ ነህ። በዶ/ር አብይ አመንኩ የዘላዓለም ሕይወትም አገኘሁ።"
" አንተ ጌታ ነህ አንተ ቅዱስ ነህ
ኢትዮጵያ ባንተ ፊት ትንበረከካለች
እጆቿን ይዘህ ታሻግራት ዘንድ ትማፀናለች፤ ዶ/ር አብይ የነገስታት ንጉስ የጌቶች ጌታ "
በማለት ይጸልያሉ... እንዴት ሰው አዕምሮውን ይስታል እንዴትስ ላልፈጠረው ይፀልያል ፣ እንዴትስ ይሰግዳል።
የሚገርመው ነገር ይህን ነገር በመፃፌም ሆነ በማሳወቄ " ምን አገባህ፣ ምን አናደደክ፣ ምን.... " እያላችሁ የምትዘልፉኝ ሁላ እኔ ሰዉ አሳዝኖኝ ፣ ገርሞኝ ነው የፖሰትኩላችሁ እንድትጠነቀቁም በሚል ብዬ ነው!
ከፈለጋችሁ ለማረጋገጥ የ Pageን ስም ልንገራችሁ ፌስቡክ ድህረ ገፅ ላይ ነው
" በኢትዮጵያ የዶ/ር አብይ አምልኮ ማህበር " ብላቹ Facebook ድህረገፅ ላይ Search አድርጉ!
የበለጡ መረጃዎችን ለማግኘት ወደ ቻናላችን ጎራ ይበሉ
/channel/yekdset_selase_lejoch
ልቦናህን ሰብስበህ መጸለይ አትችልምን?
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
እንግዲያውስ ይህን ልብ ብለህ አንብብ
*,,*********,,*****
ልቡናውን ሰብስቦ መጸለይ አልችል ያለው ሰው አንድ ታላቅ አባትን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦ "አባቴ የጸሎት መጽሐፍ ይዤ ስጸልይ ልቡናዬ አይሰበሰብልኝም፡፡ አፌ ቢያነበንብም ልቡናዬ አይተረጕምም፡፡ እርስዎ እንደነገሩኝ ደግሞ ቅዱሳን በፍጹም አሳባቸው እያሰቡና እያራቀቁ እንባንና ጸጸትን እየጨመሩ የደረሱትን እኛ በልባችን ሌላ እያሰብን በአፋችን ብቻ እንደእነርሱ ብንናገር እንደ ገደል እንደ ዋሻ ሆነን በእግዚአብሔር እንደመቀለድ ነው፤ ጸሎትም አይሆንልንም፡፡ እንግዲህ የአፍ ጸሎቴ ቅድመ እግዚአብሔር የማይደርስ ከሆነ ጸሎቴን ብተወው ይሻላል ወይስ ባልተወው ይሻላል?"
እርሳቸውም፦ "ዕውር ሰው በዘንጉ ምድር እየመታ ሲሄድ ከመንገድ ላይ ያለ እባብ ለጊዜው ድምጹን ሰምቶ ይመታኛል ብሎ እንደሚሸሽለት ሁሉ አንተም አስተውለህ ባትጸልይም በአፍህ ውስጥ የቃለ እግዚአብሔርን መንኳኳት እየሰሙ አጋንንት መሸሻቸው አይቀርምና ምንም ቅድመ እግዚአብሔር ባይደርስም ጸሎትህን አትተው። አጋንንትን ለማባረርም ጥቅም ነውና። ብዙ ከምትጸልየውም አንዳንድ ጊዜ ልብህ የሚወድቅባት ቃል ተጠራቅማ ወደ እግዚአብሔር ትደርሰልሃለች፤ ምንም ዝርወ ልብ ብትሆንም አፍህም ፍጥረቱ ነውና አንተው በዳይ አንተው አኵራፊ እንዳትሆን ባፍህም ብቻ ቢሆን መነጋገሩን አትተወው፡፡" ሲሉ መለሱለት።
(ምንጭ፦ ፍኖተ አእምሮ)
/channel/yekdset_selase_lejoch
/channel/yekdset_selase_lejoch
ከቴሌ-ብር አገልግሎት ጀርባ
-----------------------------------------
ሁል ጊዜ አዲስ ነገር ሲመጣ
ፍርሀት ይኖራል ፍርሀት ጥሩ ባይሆንም ከነገሮች ጀርባ ማጥናት
እና መመርመር መልካም ነው (ሁሉን መርምሩ የተሻለውንም
ያዙ ይላል ቅዱሱ መፅሀፍ )
...ባንክ ያንን ሁሉ ሰራተኛ ቀጥሮ ሲስተም ዘርግቶ ለገንዘባችን
ዋስትና ሰጥቶ ከአገልግሎቱ ተጠቀሙ ሲለን ያለ መክነያት
አልነበረም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚያገኘውን
20%ኮሚሽን በማሰብ እንጂ ....
at this time everything give and take ሰጥቶ መቀበል
ነው የነፃ የሚባል ነገር የለም የሆነ ሰው የሆነ ነገር ያለ
ምክንያት ሲያደርግላችሁ ከናንተ የሚፈልገው የሆነ ነገር አለ
ማለት ነው ....
#ቴሌ_ብር 15 ብር ካርድ ...70MB....15%የአየር ሰአት ግዢ
ቅናሽ ሲስተም ዘርግቶ የነፃ የስልክ ጥሪ መስመር (127) ክፍት
አድርጎ በዚህ ሁሉ ማባበያ ስልካችን እስኪሞላ ቴክስት እየላከ
የተመቻቸ አገልግሎት ልስጣችሁ የሚለን ከምን አንፃር ነው
የሚለው ጥያቄ ነው ወሳኙ ነገር....
ባለፈው አመት በዘመነ ኮኖራ መጋቢት 26 ላይ ነበር
የሚኒስተሮች ምክር ቤት የኤሌክትሮኒክ ትራንዛክሽን ረቂቅ አዋጅ
ያወጣው እና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲያፀድቅ
ያቀረበው።......ይኸው ዛሬ አንደኛ
አመቱን እንደያዘ አዋጁ አገልግሎቱን ጀመረ በኢትዮ ቴሌኮም
በኩል # ቴሌ_ብር የተሰኘ መተግበሪያ በስማርት ስልኮች እና
በቴሌኮም ኔትወርክ ሲሰተም አማካኝነት ጥሬ ገንዘብን ወደ
ኤሌክትሮኒክ ገንዘብ የመቀየር ሂደቱ አሀዱ አለ .....
ይህ አገልግሎት 3.5 ትሪሊዮን ብር ወደ ኤሌክሮኒክ ገንዘብ
በመቀየር 33 ሚሊዮን ሰወችን የዲጅታል ከረንሲ ተጠቃሚ
ያደርጋል ተብሎ ይታሰባል !
ይህ ዲጂታል ከረንሲ አጠቃቀሙ እና ጉዳቱ ምንድነው ?
ዲጂታል ከረንሲ ማለት በቁጥሮች የተመሳጠረ በኮምፒውተር
ሲስተም እና ኔትወርክ የሚንቀሳቀስ የወረቀት ብር ኖቶችን
የሚያስቀር የመገበያያ ገንዘብ ማለት ነው .....ከዚህ በፊት
የምንጠቀምባቸው በኤሌክሮኒክ ትራንዛክሽን አዋጅ የሚጠቃለሉ
...ሞባይል ባንኪንግ ....ሲቢኢ ብር....ATM የመሳሰሉ
ዲጂታላይዝድ የሆኑ የምንጠቀማቸው አገልግሎቶች ገንዘባችንን
በአንድም በሌላ መንገድ በጥሬው ማለትም በወረቀት የብር
ኖቶች ማውጣት እና ማንቀሳቀስ እንችላለን
ይህ ግን ዋነኛ አላማው ይህን ነገር ማስቀረት የወረቀት ብር
ኖቶች ወደ ኤሌክትሮኒክ ገንዘብ በመቀየር ህብረተሰቡን
የዲጂታል ከረንሲ ሙሉ በሙሉ የዲጅታል ከረንሲ ተጠቃሚ
ማድረግ እና የወረቀት ኖቶችን ማስቀረት ነው ...
ታዲያ ይህ የወረቀት ገንዘብ መቅረት እኛን ምን ይጎዳናል ነው
ያላችሁት .....
ትገርማላችሁ.......ይህ ነገር ዋና አላማው ህብረተሰቡን ሙሉ በሙሉ
የዲጂታል ከረንሲ ተጠቃሚ በማድረግ ወደ Micro Chip [ RIFD ] በሰውነት ላይ ማስቀበር ማሸጋገር ነው ያኔ የራዲዮ ፊሪኮየንሲ አደንቲ
ፊኬሽን ሲስተም ጉዳት ሲገባህ መልሰህ ወደ ወረቀት ብር ኖት
እንዳትመለስ እና RFID የመጨረሻ አማራጭህ አድርገህ
እንድትጠቀም ማድረግ እና በመጨረሻም ሰወችን ወደ ሮቦት
Artificial intelligence የመቀየር ሂደቱን ያለ ምንም እንቅፉት
ማሳካት ማስቻል ነው።
ሼር ይደረግ!
/channel/yekdset_selase_lejoch
ነውና ኃጢአቴን አስተስርይልኝ አንተ መከራ በደሌን ይቅር በለኝ፡፡
እግዚአብሔር ፈጣሪዬ ሆይ በሦስትነትህ ተማፀንኩህ፣ በትክክል ሥልጣንህ ተማፀንኩህ፣ በአንድነትህ ተማፀንኩህ፣ አንተን በወለደችህ በድንግል ማርያም እናትህ ተማፀንኩህ፣ በቅዱስ መስቀልህ ተማፀንኩህ፣ በምትወደው በወዳጅህ በቅዱስ ዮሐንስ ተማፀንኩህ፣ አንተን በአጠመቀህ በቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ተማፀንኩህ፣ መልአከ ምክርህ በሆነ በቅዱስ ሚካኤል ተማፀንኩህ፣ ያንተን መወለድ ለድንግል ማርያም የደስታ ብሥራትን በነገራት በቅዱስ ገብርኤል ተማፀንኩህ፣ እኔ ኃጢአተኛው በወዳጅህ በእስትንፋሰ ክርስቶስ ተማፀንኩህ፡፡ የእኔንም የሕዝቡንም ኃጢአት ይቅር በል፡፡ /አባታችን ሆይ በል ……/
የዚህች ጸሎት ክብር ፈጽሞ በሰማይም ቢሆን በምድርም ቢሆን አይገኝም፡፡ በአምላክ ልቦና፣ በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ በጸናች አምላክን በወለደች በድንግል ማርያም ልቦና፣ በደጋጎቹ በጻድቃን፣ በሰማዕታት፣ ፍጹማን በሚሆኑ በመነኮሳት፣ በደናግል ልቦና፣በተመረጡ በዘጠና ዘጠኙ ቅዱሳን መላእክት ልቦና፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቦና ይገኛል እንጅ፤እነርሱም ይህችን ጸሎት በጸለዩ ጊዜ ሁለት መቶ አርባ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጣሉ፡፡ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያምም በየዕለቱ ፵፻፼ ነፍሳትን ታወጣለች፡፡ ንስሐ የገባ ኃጢአተኛ እንኳን በጸለየባት ጊዜ አንድ እልፍ ነፍሳትን ያወጣል፡፡ ይህችን ጸሎት አታወጣም ብሎ የሚጠራጠር ቢኖር መንግሥተ ሰማያትን አያያትም፡፡ /አባታችን ሆይ በል ……/
ተወዳጆች ሆይ ይህንንታ ታለቅ ጸሎት ዘወትር ብትጸልዩት በሥጋ ላላችሁ ለእናንተም እንዲሁም ንስሐ ሳይገቡ፣ቅዱስ ቁርባን ሳይቀበሉ ለሞቱ ቤተሰቦቻችሁና ወገኖቻችሁ ትተርፉበታላችሁ፡፡ ከሲኦል ሲወጡን አምላከ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ በሕልም ክብራቸውንና ያሉበትን ቦታ ያሳያል።
ምንጭ፦ የታላቁ የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ የሐሙስ ገድል ገጽ 39 ቁጥር 1 እስከ ገጽ 43 ቁጥር 19!
🕯• ┈••●◉ ✞✟✞ ◉●••┈ •🕯
ሚያዝያ ፲ወ፪
እንኳን ለአቡነ ሳሙኤል ዘቆየጻ (ኢትዮጵያዊ)፣ ለቅዱስ ኤርምያስ ነቢይ፣ ለቅዱስ አቤሜሌክ (ኢትዮጵያዊ)፣ ለቅዱስ ባሮክ እንዲኹም ለቅዱስ እለእስክንድሮስ ዘኢየሩሳሌም ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ 🙏
🕯• ┈••●◉ ✞✟✞ ◉●••┈ •🕯
ዳግመኛም ዛሬ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፣ ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ፣ ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ ሰማዕት፣ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ እንዲኹም ቅዱስ ድሜጥሮስ ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው 🙏🙏🙏
አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን 🤲 አሜን!
🕯• ┈••●◉ ✞✟✞ ◉●••┈ •🕯
/channel/yekdset_selase_lejoch
1⃣ዳዊት የተወለደው በየት ነበር?
⚪️.ናዝሬት
⚫️.ደማስቆ
🔴.ገሊላ
🔵.ቤተልሄም
1⃣2⃣.ሥላሴ ስንት ናቸው
⚪️.አንድና ሶስት
⚫️.አንድ ወይም ሶስት
🔴.አንድም ሶስትም
🔵.አንድ ግን ሶስት
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ
አምላክ አሜን!
#ታላቅ_የንግስ_በዓል_ጉዞ_ወደ_ሳማ_ሰንበት
ቤተ-ክርስትያን
#መነሻ_ቀን፦ መጋቢት 25/2013 ዓ.ም ከቦሌ አራብሳ ሰፈራ ቅድስት ማርያም ቤተ-ክርስትያን ፤
#የጉዞ_መመዝገቢያ_ዋጋ፦ መስተንግዶን ጨምሮ #280 ብር ደርሶ መልስ
#የመመዝገቢያ_ቦታ፦ ቦሌ አራብሳ ሰፈራ ኆህተ ምስራቅ ቅድስት ማርያም ቤተ-ክርስትያን።
#ለበለጠ_መረጃ፦#0922-476538
#0955-400247
#አዘጋጅ_ሐመረ_ኖህ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት
✝ሰላመ እግዚአብሄር ከሁላችን ጋር ይሁን✝
#ትንሿ_ቤተክርስቲያን
(ቤታችን ውስጥ ያለችው የእናት የአባት እና የልጆች አንድነት፤ ኅብረት)
...የሳምንቱ መልእክታችን
ዓለም ኹሉ በንፍር ውኃ ሲጠፋ ከዚያ ጥፋት የቀረው የኖኅ ቤተሰብ ብቻ ነው - በትንሿ ቤተ ክርስቲያን !
በትንሿ ቤተክርስቲያን በደንብ ሲሠራ ከአንድ ቤተሰብ ብቻ ብዙ ቅዱሳን
ማፍራት ይቻላል፡፡ ለዚህ ጥሩ ማሳያውም የኤስድሮስ ቤተሰብ ነው። ከዚህ ቤተሰብ አምስት ቅዱሳን ተገኝተዋል፡፡ ሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው፡፡ ኹለቱ ደግሞ ደናግል መነኮሳት ናቸው፡፡ ከሦስቱም ጳጳሳት መካከል ኹለቱ እጅግ የታወቁ ናቸው - ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ እና ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ !
እንደ ጲስጢስ፣ አላጲስና አጋጲስ የመሰሉ ልጆች ለማፍራት እንደ ሶፍያ የመሰሉ ወላጆች መኖር አለባቸው፡፡ እነዚህ የሚኖሩት ደግሞ ትንሿ ቤተ ክርስቲያን በአግባቡ ስትከፈት፣ ተከፍታም አገልገሎት ስትሰጥ ነው፡፡
ሰንበት ትምህርት ቤቶች ሲመሠረቱ የኢአማንያን ልጆች (ንኡሰ ክርስቲያኖችን) መሠረታዊ የቤተክርስቲያን ትምህርትን ለማስተማር እንጂ የምእመናን ልጆችን ለማስተማር አልነበረም፡፡ የምእመናን ልጆች መሠረታዊ የሃይማኖት ትምህርት መማር ያለባቸው ቤት ውስጥ ነው - ትንሿ ቤተክርስቲያን ውስጥ! ሰ/ት/ቤት መኼድ ያለባቸው ከሊቃውንት ብቻ የሚገኝ ትምህርትን ለመማር ወይም ለማገልገል ነው፡፡ ይህ ግን አሁን እየተደረገ አይደለም፡፡ ለምን? ትንሿ ቤተክርስቲያን ስለተዘጋች፡፡ እንደ ተዘጋች እንኳን የሚያስተውላት በጣት የሚቆጠር ሰው ነው፡፡
ዛሬ ትውልዱ በብዙ ነገሮች እየተፈተነ ያለው ከልጅነቱ አንሥቶ በተግባር የሚማርበት ትምህርት ቤት ስለ ተዘጋበት ነው - ትንሿ ቤተክርስቲያን !
በገጠር አብያተ ክርስቲያናት ተዘጉ ብለን የምንቆጨውን ያህል ስለዚህች ቤተክርስቲያን ብዙ ልናስተምር፣ ብዙ ልንደክም፣ ብዙ ልንለፋ ያስፈልጋል፡፡
በተለይ በተለይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ይህቺን ቤተክርስቲያን ከተመረቁ በኋላ ለመክፈት ሰፊ ዕድል ስላላቸው ስለ ትንሿ
ቤተክርስቲያን ሰፊ ትምህርትና ግንዛቤ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
©ከመምህር ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
@yekdset_selase_lejoch
@yekdset_selase_lejoch
@yekdset_selase_lejoch
#የሳማ_ሰንበት /ደብረ ዘይት/ ቤተ- ክርስቲያን ምን ያህል ያውቃሉ።
እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የደብረ ዘይት ጾመ እኩሌታን በዓል በሳማ ሰንበት ለማክበር አስበናል። በዚህ መንፈሳዊ ጉዞ ተካፋይ የምንሆን ሰዎች ስለ ሳማ ሰንበት ትንሽ ልንላቹ ወደድን።
የሳማ ሰንበት/ደብረ ዘይት/ ቤተ- ክርስቲያን ከአዲስ አበባ በስተ ደቡብ ምስራቅ 110 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ልዮ ስፍራ ሳማ ቀበሌ የሚገኝና በሀገራችን ብቸኛ የሆነ ትልቅ ደብር ነው።
ደብሩ/ገዳሙ/ ከ 300 ዓመት በላይ እንዳስቆጠረ ከገዳሙ የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ። የሳማ ሰንበት ቤተ-ክርስቲያን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ከሚገኙ የቱሪስት መስህቦች ባልጪ አማኑኤል፣ ሸንኮራ ዮሐንስ፣ ዶፋ ሚካኤል፣ አረርቲ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም፣ ጉራምባ ማርያም መካከል አንዱ ነው።
የሳማ ሰንበት ክብረ በዓል በዓመት አንድ ግዜ ማለትም በእኩለ ፆም (ደብረ ዘይት በዓል) የሚከበር ሲሆን በክብረ በዓሉ ላይ ከሁሉም የአገሪቱ ክፍል የሚመጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምእመናን ይሳተፋበታል።
ከሃገር ውጭ ያሉ ቱሪስቶችም ይገኙበታል። በፈዋሽነቱ የታወቀ ጸበልም ይገኝበታል።
በሰላም ደርሰን ረድኤት በረከት ተካፍለን እንድንመለስ የእርሱ ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን! አሜን
#ሼር
+ ተማሪዎች ከፈተና በፊት ምን ብለው ይጸልዩ?
ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ ከሚታወቁባቸው በርካታ በጎ ነገሮች አንዱ ለተማሪዎች የነበራቸው ልዩ ፍቅርና ቅርበት ነበረ፡፡ አባ ሚናስ ተብለው ይጠሩ ከነበረበት የምንኩስናቸው ዘመን ጀምሮ አቡኑ በተማሪዎች የተከበቡ ነበሩ፡፡ ከልዩ ልዩ ክፍለ ሀገራት ካይሮ ዩኒቨርሲቲ ሊማሩ ለሚመጡ ተማሪዎች የማደሪያ አገልግሎት በቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሰጡ ነበር፡፡ ይህ አገልግሎታቸውም በግብፅ ለዘመናዊው ቤተ ክርስቲያንን የሚያካትት የማደሪያ አገልግሎት(church- affiliated dormitory) መወለድ ምክንያት ሆኗል፡፡ የዚህ የማደሪያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የነበሩ ተማሪዎችም ቀሳውስትና ጳጳሳት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለመሆን በቅተዋል፡፡(ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሳሙኤልና ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊተጠቃሽ ናቸው፡፡) በወቅቱ መነኩሴ የነበሩት አባ ሚናስ (አቡነ ቄርሎስ) ለእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያኑ ካህን በተማሪዎቹ መኖሪያ ውስጥ የሥራ ድርሻ ሰጥተው ነበር፡፡ የእርሳቸውን የሥራ ድርሻ ምን እንደነበረ ግን ማንም ሰው አላወቀም ነበር፡፡ በሌሊት በድብቅ የሚሠሩት ሥራ ካህናቱና በቤተ ክርስቲያኑ የሚኖሩ ተማሪዎች የሚጠቀሙበትን መጸዳጃ ቤት ማጽዳት ነበር፡፡
ይህ ለተማሪዎች ያላቸው በጎ አመለካከት በፓትርያርክነት ዘመናቸው አልተለያቸውም፡፡ ተማሪዎች ፈተና ሲደርስባቸው ወደ እርሳቸው እየመጡ ጸልዩልን ይሉአቸው ነበር፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ የሚያጠኑበትን መጽሐፍ ይዘው መጥተው ያስባርኩ ነበር፡፡ ቅዱስ አባ ቄርሎስ አንዳንዴ መጽሐፉን ገለጥ ያደርጉና ‹ይህንን አጥኑ› ብለው ይሠጡ ነበር፡፡ የፈተናውም አብዛኛው ጥያቄ ከዚያ ገጽ ይወጣ ነበር፡፡ እንዲሁም ለተማሪዎች ፈተና በሚፈተኑበት ጊዜ የሚገጥማቸውን የመንፈስ ጭንቀትና የአእምሮ ውጥረት በመረዳት የሚከተለውን ከፈተና በፊት የሚጸለይ ጸሎት አዘጋጅተውላቸዋል፡፡
+ ጸሎት +
‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ
‹‹በችግርህ ቀን ጥራኝ ፤ አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ›› ብለህ የአንተን መጠጊያነት መፈለግን ስላስተማርከኝ አመሰግንሃለሁ!
አሁንም ጌታ ሆይ! በዚህ የፈተና ሰዓት ጥበብና ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እማጸንሃለሁ፡፡
ይህን ፈተና በሰላም አልፍ ዘንድ ጸጋን (ሞገስን) ስጠኝ፡፡ ፈተናውን በምሠራ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ሰላምህንና በረከትህን ስጠኝ፡፡
ጌታዬ ኢየሱስ ውጤት በሚሰጡኝ ጊዜ በመምህራኖቼ ዓይን መወደድን ትሰጠኝና ልባቸውን ታለሰልስልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ የከበርከው ጌታእኔ ኃጢአተኛ ነኝ ፤ ዓመቱን ሙሉ አንተን ደስ አላሰኘሁህም ፤ ውስጤንም ጭምር ፤ ነገር ግን ከልቤ ደንዳናነትና ከኃጢአቶቼ የተነሣ ሳይሆን ከምሕረትህ እና ከርኅርኄህ የተነሣ እንደትረዳኝ እለምንሃለሁ፡
ጌታ ሆይ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋል፣ እሹ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል›› ብለሃል፡፡ እናም እነሆኝ እየለመንኩ ነው፤ የምሕረትህንም ደጅ እያንኳኳሁ ነው፡፡ ‹‹ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ከእኔ አላወጣውም›› ብለሃልና ጸሎቴን አትናቅ፡፡በቅድስት ድንግልና በመላእክትህ ሁሉ አማላጅነት መልስልኝ!! አሜን!"
ታሪክ በማይረሳው የተወሳሰበ የትምህርት ዘመን አልፋችሁ ለምትፈተኑ ለዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን! የልባችሁን ዓይን ያብራላችሁ! ያጠናችሁትን ይባርክላችሁ የተማራችሁትን ያስታውሳችሁ! ባለቀ ሰዓት የሚደረግ ጥናት ከጭንቀት ውጪ ምንም አያተርፍምና ራሳችሁን በጸሎት አረጋግታችሁ ተፈተኑ::
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የካቲት 27 2013 ዓ.ም
/channel/yekdset_selase_lejoch
ኢትዮጲያውያን ሊቃውንት እንዲህ የሚል #ብሒል አላቸው....
"አንድ መንገደኛ ካሰበበት በታ ሳይደረስ ቀኑ መሽበት። በጨለማ ሄጄ በአውሬ ከምበላ ስመ እግዚኣብሔርን ጠርቼ በእናቱ በቅድስት ድንግል ማርያም ስም ተማጽኜ የመሸበት እንግዳ እባካችሁ አሳድሩኝ ብዬ እለምነለሁ ብሎ ያወጣ ያወርድ ጀመር።
አስቦም አልቀረም፣ የአንድ አርሶ አደር ቤት አጋጣመው። ከበር ላይ ቆሞ ስመ እግዚአብሔርን ጠራ፡፡ አርሶ አደሩም ቤት የእግዚአብሔር ነው ብሎ #እግሩን_አጠበው፤ #ራቱን_አበላው፤ #መኝታ_ሰጠው። ይህ በመንገድ ሲንገላታ የዋለ መንገደኛ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ሌሊቱን በጥሩ እንቅልፍ አሰለፈ።
ጠዋት ረፋዱ ላይ ቁርሱን በልቶ የቀረ መንገዱን ለመቀጠል ተነሣ። አባወራውም ልሸኘው ተዘጋጅ። መንገደኛውም "#ጌታዬ_ቤትዎን_ከመልቀቄ_በፊት_አንድ_ነገር_እንድናገር_ይፈቀድልኝ_አለ። አርሶ አደሩም እሺ ብሎ ፈቃዱን ገለጠ።
መንገደኛውም መቼም ውሎ ውሎ ከቤት፤ ኑሮ ኑሮ ከሞት አይቀርም። ሞት እንዳማይቀረው ሁሉ ምጽአተ ክርስቶስም አይቀርም።
*"#ያንጊዜ_ለፍርድ_በቆምን_ጊዜ_ሰይጣንን_ከሳሽ፣ #እርስዎን_ተከሳሽ፣ #እኔን_ምስክር_አድርጎ_ያገናኘን"🙏 ብሎ መረቀ።*
አርሶ አደሩም ነገሩ ገብቶት ኖሯልና #አሜን #ይሁን_ይደረግ ብሎ እንግዳውን ሸኘው ይባላል። 😊
===================
#ለካስ_ሲርባቸው_ያበላናቸው፣ #ሲጠማቸው_ያጠጣናቸው፣ #ሲታረዙ_ያለበስናቸው፣ #ሲታመሙ_የጠየቅናቸው፣ #ሲታሰሩ_የጎበኘናቸው_ሰዎች_በዕለተ_ምጽአት_ይመስክራሉ፣ #ምግባራችን_ይከተለናልና። #በጎ_ነገር_ማድረግ_ትርፍ_እንጂ_ኪሣራ_ከሌለው_ለጋስ_ብንሆንስ?🤔
ምንጭ ፦ ፍጹም አምልኮ (መጽሐፍ)
@yekdset_selase_lejoch
@yekdset_selase_lejoch
@yekdset_selase_lejoch
🇪🇹ኢትዮጵያ እጆቾን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች🇪🇹
ኢትዮጲያ ግን እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር እምትዘረጋበት ቀን እጅግ ቀርቧል:: አሁን የጦር ዛቻ እያየንበት ያለው መዘዘኛው አባይንም በተመለከተ በአንድ በኩል እንደሚያጋድለን በትንቢቱ :~
" አባይ ደፈረሰ ጣናንም ያ'ሙታል:
እንዳትከተሉት ሙት ይዞ ይሞታል" ብለው: ሼህ ሁሴን ተናግረውለታል::
ወደፊት ምን እየተካሄደ እንዳለ እንኳን እንደዚህ ሀሳብ እምንለዋወጥበት እድል እማይኖርበት ግዜ ይመጣል::ዛሬ የተጋራነው ሀሳብ በመጭው ግዜ ትዝታ ይሆናል :: የብሔርና የሃይማኖት ጦርነት የተነሳ ግዜ ያኔ ሁሉ እንዳልነበር ይሆናል:: ከዚህ እሚያድነን አንድ እና አንድ መፍትሄ አሁንም ዛሬ ላይ ሆነን ተግተን እምናረገው ፀሎት እና የእግዚያብሔር ምህረት እንጂ የታጠቅነው የጦር መሳሪያ አይደለም::
አባ ዘወንጌል ስለ አንበጣውም ሆነ ስለጦርነቱ ተናግረውት ያለፉትን ከዚህ ትንቢት ጋር እሚጋራውን ብዙ ነጥቦች አስታውሱ::
ይህን ፖስት ያረኩት የቅርብ ሩቁን ነገን እያሰብክና/እያሰብሽ ጭንቀት ውስጥ ገብተህ/ሽ መኖር እንድታቆም/ሚ አይደለም::ይልቁንም ግዜው እየጠበበ እየጠበበ እንደሄደ አስተውለን ቦታው
ላይ ሲደርስ የተዘጋጀ ልብ እንዲኖረን :ግዜው
እንደ ወጥመድ ድንገተኛ እንዳይሆንብን መጭውን አውቀን ህፀፃችንን እያረምን ራሳችንን እያስተካከልን በፀሎት ከመፃኢው መከራ አትርፎ ለትንሳኤዋ ዘመን እንዲያበቃን እየተማፀንን ኑሮዋችንን እንድንቀጥል ነው::
ምክንያቱም የኛ አይን መጨፈን እሚሆነውን ከመካሄድ አያስቆመውም : ጆሮዋችንን መድፈን እሚነገረውን ከመነገር አይከለክለውም::ይልቁንም አውቀነው መፀለያችን ነገሩን እንደነነዌ ያረግልናል ሊያስቀርልን ይችላል::"
እግዚአብሔር የኢትዮጲያችንን መከራ ያሳጥርልን :ከመፃዒው ጥፋትም ያድንልን!
መድሃኔአለም ኢየሱስ ክርስቶስ ከዘላለም እስከዘላለም ያው ነው:: መንገድም እውነትም ህይወትም መድሃኒትም እርሱ ነው!!! ወደርሱ እንመለስ ።
ከገባህ ለአንድ ወንድምህና እህትህ ሼር አድርግ።
@yekdset_selase_lejoch
@yekdset_selase_lejoch
@yekdset_selase_lejoch