በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቀ አስተምህሮ ✝መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር ይቀሰቀስኛል ለስሙ አንድዘምር🔔 የማንቂያ ደዉል🔔🔔 ክርስትና ዘር የለውም
እንኳን አደረሳቹሁ
#ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ሩፋኤል
🥀በዕብራይስጥ "ሩፋ" ማለት ጤና አንድም ፈውስ አንድም መድኃኒት ማለት ነው። "ኤል"ማለት ደግሞ አምላክ ማለት ነው። አንድ ላይ ሲሆን ሩፋኤል ማለት ከአምላክ የተሰጠ ፈውስ ማለት መሆኑን ልብ ይሏል። አምጻኤ ዓለማት እግዚአ መላእክት እግዚአብሔር በነገደ መላእክት አለቆች ይኾኑ ዘንድ ሰብዐቱን ሊቃነ መላእክት ሾሟል። ቅዱስ ሩፋኤል ከሊቃነ መላእክት ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በመቀጠል በመዓርግ ሦስተኛ ኾኖ የተሾመ መኾኑን ልብ ይሏል። የቁጥሩንስ ነገር በሚገባ መልኩ የሰው ልጆችን ጸሎት ከሚያሳርጉ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ እንደ ኾነ በመጽሐፈ ጦቢት ላይ ራሱ መልአኩ ሲናገር እናነባለን "የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ወደ ከበረ ወደ ገነት ወደ እግዚአብሔር ጌትነትም ከሚያገቡ ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ" ብሏል ጦቢ 12፥15።
🥀ቅዱስ ሩፋኤል ዓይነ ስውር የነበረውን ጦቢት የዓሣ አሞት ዓይኑን እንዲቀባ ልጁን ጦቢያን በመምከር ብልዙን ከብሌኑ ላይ አንሥቶ ዐይኑን ያበራለት መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል መኾኑ ጦቢ ፲፩ ላይ ተገልጿል። የዓሣ አሞት ሳይቀባ ጦቢት ከዕውርነቱ መላቀቅ ቢችልም የሰው አእምሮ በሚረዳው መንገድ የእግዚአብሔር ሥራ ይገለጥና ለወዳጆቹም ያለው ጠብቆት ይረዳ ዘንድ መልአኩን በሰው አምሳል ወደ ጦቢያ ልኮ በሚጨበት የዓሣ አሞት በኩል ረቂቅ ማዳኑን ለጦቢት አደረገለት። ምናልባትም ራሳቸው በገነቡት የጥርጣሬ ቤት ውስጥ ስሕተትን ተንተርሰው በክሕደት ላይ የተኙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ዐይተው ከማመስገን ይልቅ በጥርጣሬያቸው ጸንተው ቀጥለው ይህ እንዴት ሊኾን ይችላል ይሉ ይኾናል።
🥀በእርግጥም አለማመናቸው በእምነት የሚረዱትን ነገር እንዳይቀበሉት ዓለት ኾኖ ከልክሏቸዋልና እግዚአብሔር አምላክ ምሥጢሩን የሚረዱበትን ኃይል ገንዘብ የሚያደርጉበት ጸጋ ይስጣቸው ከማለት በቀር ሌላ ምን ሊባል ይችላል! ይህ መልአክ በሌላ ምሥጢር አዛርያ እባላለሁ ብሎ ከልጁ ጋር ጦቢትን ሲረዳ ይልቁንም እንደ ሳምራዊቷ ሴት ባሎቿ ጭኗ ላይ በሞት ይሰናበቷት የነበረችውን የራጉኤልን ልጅ ሣራን ከቁራኝ ጋኔን ሲገላግላት ዐይተናል። ይህም ሥራው መናፍስት ርኩሳንን እንዲቀጠቅጥ መሾሙን በግልጽ ያስረዳል። የከበረውን የሰውን ልጅ ሰውነት ለማርከስና ማኅደረ እግዚአብሔር መኾኑን አስቀርተው በክፉ ሥራቸው ሕዋሳቶቹን ተቆራኝተው ወደ እግዚአብሔርና ወደ መንግሥቱን የሚያይበትን ዓይን ለማሳጣት ርኩሳት መናፍስት ሲመጡ ቅዱስ ሩፋኤልን በትኅርምት ኾነን ስንጠራው እነዚህን ክፉዎች አጋንንት ያርቅልናል። ሰውነታችንም የተቀደሰ የእግዚአብሔር መቅደስ ኾኖ እንዲሠራ ያደርግልናል።
🥀መጽሐፈ አክሲማሮስም "...ወለፆታ ዐሠርቱ ስሞሙ መናብርት። ወሊቆሙ ቅዱስ ሩፋኤል እሉ እሙንቱ እለ ይቀልል ሩፀቶሙ እምነፋስ ወነድ። ለእለ ይፀውሩ ወላትወ መብረቅ ወኩናተ እሳት ዘይነድድ። ወአንበሮሙ በዳግሚት ሰማይ። ወእምዝ ነሥአ እም ሠራዊተ ሩፋኤል ፳ወ፬ተ ሊቃናተ። ወአቀሞሙ ዐውደ መንበሩ..." ይላል ትርጓሜውም "ዐሥሩን ነገድ ስማቸውን መናብርት አላቸው። አለቃቸውንም ሩፋኤል ነው። ረቂቅ የኾነ የመብረቅና የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስና ከእሳትና የፈጠኑ ናቸው ... ከዚህም በኋላም ከሠራዊተ ሩፋኤል ሃያ አራቱን ሊቃናት መርጦ በመንበረ ስብሐቱ ዙሪያ አቆማቸው..." ዳግመኛም ከከበሩ ቅዱሳን ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲል ነቢዩ ሄኖክ የተናገረለት ይህ የእሳታውያን መናብርት አለቃ ቅዱስ ሩፋኤል የሰውን ልጆችን ይረዳ ዘንድ ከአምላኩ ከልዑል እግዚአብሔር ብዙ ሹመት ተሰጥቶታል። እሊኽም ፈታሔ ማኅፀን፣ ዐቃቤ ኆኅት፣ ሰዳዴ አጋንን፣ ከሣቴ ዕውራን፣ ፈዋሴ ዱያን..." የተባሉ ናቸው።
ጻድቁ ሄኖክም "በበሽታ ሁሉ ላይ በሰው ልጆች ቁስል ላይ የተሾመ" መልአክ እንደ ኾነ ጽፏል (ሄኖ ፲፥፲፫)። በዮሐ ወንጌል ላይም እንደ ተቀመጠው ብዙ ሕመምተኞች ተጠምቀው የሚድኑበት በቤተ ሳይዳ የሚገኘውን የመጠመቂያ ውኃ በሳምንቱ አንድ ጊዜ ያናወጸው (ይባርከው) የነበረው መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ነበር። ዮሐ ፭፥፬። አንድም ፅንስ በማኅፀን ከተቋጠረ ከአርባኛው ቀን ጀምሮ ቅዱስ ሩፋኤል በጠባቆቱ የማይለየው ሲሆን አንዲት ሴትም የመውለጃዋ ቀን ደርሶ ምጥ በያዛት ጊዜ ሕመሙን የሚያቀልላት እና ማኅፀኗን የሚፈታው ይኸው መልአክ ነው። ከዚህም ሥራው የተነሣ "ፈታሔ ማኅፀን" በመባል ይጠራል።
ከቤተክርስቲያን ሊቃውንት መካከል ስለ ቅዱስ ሩፋኤል በሰፊው በመጻፍ የታወቀው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ነው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በድርሳኑ "መራሔ ፍኖት" ብሎታል። ጦቢያን በቀና መንገድ መርቶታልና። "መልአከ ከብካብ" ብሎታል። ጦቢያና ሣራን ያጋባ ጋብቻቸውንም የባረከ በመሆኑ። /budge,1915 pp.526-533/ በዚህ ድርሳኑ ሩፋኤል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ጠባቂ መልአክ እንደ ኾነ ተገልጿል። "ለአንዲት ሰዓት ለግማሽ ሰዓት ለዓይን ጥቅሻም ቢሆን አይለየውም ነበር" ይላል። ዮሐንስ አፈወርቅን ወደ አርቃድስ ንጉሥ የላከውም ቅዱስ ሩፋኤል ነው። ንጉሥ አርቃድዮስም በቅዱስ ሩፋኤል ስም/ምናልባት የመጀመርያውን/ ቤተክርስቲያን ሠርቶለታል። ፓትርያሪክ ዘእስክንድርያ ቴዎፍሎስ /385-412/ በጻፉት /in raphaelem Archangelum/ ድርሳን ውስጥ የሚከተለው ታሪክ ተገልጧል። ፓትርያሪክ ቴዎፍሎስ ከንጉሥ ቴዎዶስዮስ ጋር የቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን በእስክንድርያ ከተማ እንዲታነጽ ጠየቁ።
🥀በመጨረሻም በሜድትራኒያ ባሕር በምትገኘው ጳጥሬስ በተባለችው ደሴት በቅዱስ ሩፋኤል ስም ቤተክርስቲያን ታነፀ። ይህ ቤተክርስቲያን የታነፀው ደሴት መስሎ በተኛ ዓሣ አንበሪ ላይ በመሆኑ ሕዝበ ክርስቲያኑ ለክብረ በዓል በሄዱበት ጊዜ ዓሣ አንበሪው ተነቃንቆ ቤተክርስቲያኗም ልትፈርስ ደረስች። ሕዝቡም ወደ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ጩኸታቸውን አሰሙ በዚህ ጊዜ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ፈጥኖ ደርሶ ዓሣ አንበሪውን በሰይፈ ወግቶ ጸንቶ እንዲቆም አደረገው። ቅዱስ ቄርሎስ ፓትርያርክ ቴዎፍሎስ ያሠሩትን የቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ጳጉሜን ሦስት ቅዳሴ ቤቱን አክብሮአል። ይህቺ ዕለት በዓለ ሢመቱም እንደ ኾነች ይረዷል።
🥀ዓሣ አንበሪው ደሴት መስሎ የተኛባት ያቺ ቦታ ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶባታል። ዓሣ አንበሪው ሊያነዋውጻት ሲል መልአኩ በሰይፍ ወግቶ አጽንቷታል። ዓሣ አንበሪ በተባለው ዲያብሎስ ምክንያት መቅደስ ሰውነታችን በኃጢአት ተነዋውጾ ሊፈርስ ሲል መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል በምልጃው በትር የዲያብሎስን ፈተና ቀጥ አድርጎ የሚያቆምልን መኾኑን ብንገነዘብና ምልጃውን ከጥልቅ ልባችን ብንጠይቅ እንዴት ያምር!! የአብዛኛዎቻችን ሕይወት የተመሠረተው ደሴት እንደ መሰለው ዓሣማ መልካም በሚመስል ግን ባልኾነ የሕይወት ፍልስፍና ላይ ነው። በዚያውም ላይ የቅዱሳን መላእክት ምልጃ እንዳይረዳን የመላእክትን ተረዳኝነት ከሕይወታችን ገፍተናል። እግዚአብሔርንና የእርሱ የኾኑትን በሙሉ ለሕይወታችን አያስፈልጉም ብለን ተግባቦት አቁመናል። ከእነርሱ ይልቅ ከዓለማዊነትን ጋር ላለመላቀቅ ተጣብቀን ተያይዘናል። የሚያረካን ዘፈን እንጂ መዝሙር አይደለም፤ የሚስማማን ዘረኝነት እንጂ ክርስትና አይደለም፤ የምንመርጠው ምድራዊ ደስታን እንጂ ጣዕመ መንግሥተ ሰማያትን አይደለም። በማይቋረጥ ንውጽውጽታ ውስጥ ነን። ስለዚህ በቅዱሳን መላእክት ምልጃ የሚያፍገመግመንን ኃጢአት እናቁመው። ወደ ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት እንመለስ። ይህ ነው ዓሣማውን ወግቶ ማጽናት!!
፩. ፈዋሴ ዱያን (ሕሙማንን የሚፈውስ)
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማዳን (መድኃኒትነት) ለእርሱ የባሕሪው ነው፤ የማዳንን ጸጋ ለቅዱሳን ሰጥቷል፤ ከቅዱሳን መላእክትም ቅዱስ ሩፋኤል የሰው ልጆች ከተያዙበት የኃጢአት ቍስል ይፈወሱ ዘንድ በአማላጅነቱና በጸሎቱ የሚረዳ መልአክ ነው፡፡ ሄኖክ “በበሽታ ሁሉ ላይ በሰው ልጆችም ቍስል ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው” በማለት ከእግዚአብሔር መልአክ ያገኘውን የምስክርነት ቃል ጽፏል፡፡ (ሄኖክ ፲፥፲፫) ቅዱስ ሩፋኤል በሰውነታችን ላይ የሚወጣውን ደዌም ሆነ ቍስል ይፈውስ ዘንድ ከልዑል እግዚአብሔር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ ሄኖክ “በሰው ቍስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” እንዳለ፡፡ (ሄኖክ ፮፥፫)፡፡ ለቈሰሉ ፈውስን የሚያሰጣቸው መልአክ ዛሬም ሁላችንን በጸሎቱ ከደዌ ሥጋ ከደዌ ነፍስ ይፈውሰን፤ አሜን፡፡
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
የጳጉሜን ወር በጸሎት በንስሓ ተወስነን ወደ አዲሱ ዓመት የምንሸጋገርባት ድልድይ ናት፡፡ ከዚህም የተነሳ እግዚአብሔር የፈቀደላቸው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ጸሎት በመጸለይ ጸበል በመጠመቅ ያስቧታል፡፡ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜን ወር የምንጾመው ሲሆን መሠረት የሚደረገውም ጾመ ዮዲት ነው፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ ይህን መሠረት አድርገው ሕዝቡ ሳይቀር “ጳጉሜን ዕድሜ ትሰጠናለች፤ በኋላም ታድነናለች” ብለው ጾም ይጾሙባታል፡፡ (ምንጭ-ቅዱስ መልከ ጸዴቅ ድርሳን)፤ በሀገራችንም ንግሥት ዘውዲቱ እና ምኒልክ የጾም ሥርዐት ይፈጽሙባት ነበር፡፡ ሌሎችም ሽማግሌዎችና ባልቴቶች አክብረው ይጾሙባታል፡፡ የጳጉሜንን አቆጣጠር አንዱ ከቀን ጋራ ሲደርገው፣ ሌለኛው ደግሞ ከወር ጋራ ቢያደርገውም በሁሉም አቆጣጠር ውስጥ ሕያዊት ሆና መገኘቷ የታወቀ ነው፡፡
የዐውደ ዓመት መሸጋገሪያ ናት፡፡
ይህም ጳጉሜን ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት፣ ከክረምት ወቅት ወደ ጸደይ መሸጋገሪያ ናት፡፡ ጳጉሜን የዓመቱ መጨረሻ ወር ናት፡፡ ወርኃ ጳጉሜ አዲሱን ዓመት ለመቀበል የዝግጅት ጊዜ ናት፡፡ ስለሆነም አዲሱ ዘመን የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የልማት፣ የመተሳሰብ ዘመን እንዲሆንልን በጾምና በጸሎት ማሰብ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡
ነገረ ምጽ አት የሚታሰብባት ናት፡፡
የጳጉሜን ወር የነገረ ምጽአት የሚታሰብባት ስትሆን ምጽአት ማለት የጌታን መምጣት የሚያስረዳ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን የጌታን ምጽአት በዓመት ሁለት ጊዜ ታስታውሳለች፤ ይኸውም በጳጉሜን ወርና በጌታ ጾም እኩሌታ (በደብረ ዘይት) ነው። ቅዱስ ዳዊት ”እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል፤ ዝም አይልም፤ እሳት በፊቱ ይነዳል፤” እንዲል፤(መዝሙረ ዳዊት ፵፱ ፣ ፪-፬)፡፡ ይህ ስለ ነገረ ምጽአት ያስረዳል፡፡
ይህም ጳጉሜን ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት፣ ከክረምት ወቅት ወደ ጸደይ ወቅት መሸጋገሪያ እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ፣ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ፣ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ናትና ነው፡፡ ጳጉሜን የክረምቱ ማብቂያ እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም በመጨረሻው ዘመን መከራ የሚበዛበት የዚህ ዓለም ማብቂያ ናት፡፡ ወርኃ ጳጉሜን አዲሱን ዓመት ለመቀበል የዝግጅት ጊዜ እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ጻድቃን አዲሲቷን ምድር (መንግሥተ ሰማያትን) ለመውረስ ተዘጋጅተው “ኑ የአባቴ ብሩካን ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀላችሁን የእግዚአብሔር መንግሥት ውረሱ” የሚባሉባት ቀን ናት፡፡ የጌታ አመጣጥ ሳይታሰብ ነውና በተሰጠን ጸጋ ቅዱስ አምላካችንን እያመሰገንን ተዘጋጅተን እንድንጠብቀው የድንግል ማርያም ልጅ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይርዳን፤ ቀጣዩ ዘመንም ቃሉን ፈጽመን መልካም ፍሬ የምናፈራበት ዓመት ይሁንልን፤ አሜን !!!
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ አስተዳደር ትናንት ማታ የኦርቶዳክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆኑ ቤቶች ተለይተው መቃጠላቸውና አሁንም በምእመናን ላይ ማስፈራራት እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ተገለጸ።
ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን በስልክ መረጃ ያደረሱን ምእመናን እንደተናገሩት አስቀድሞ ለወራት ዛቻና ማስፈራሪያ ሲደርስባቸው እንደነበረና በነሐሴ 29 ማታ ግን ቤታቸው ተለይቶ እንደተቃጠለ፣የንግድ ሱቆቻቸው ላይም ቃጠሎና ዝርፊያ መፈጸሙን ተናግረዋል።
የጸጥታ ኃይሎች በመድረስ ለጊዜው መቀነስ ቢችልም አሁንም ቤተ ክርስቲያን እናቃጥላለን፤ ምእመናንንም እንጎዳለን በማለት የውስጥ ለውስጥ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው የሚል መረጃ እየደረሰን በመሆኑ ስጋት ላይ ነን፤ በርካታ ምእመናንም ከቤታቸው እየሸሹ ነው ብለዋል።
በተለያዩ ጊዜያት ለከተማ አስተዳደሩና ለሚመለከታቸው አካላት በደብዳቤ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ ቢቆዩም ይሄ ነው የሚባል ምላሽ አለማግኘታቸውንም አብራርተዋል።
በስልጤ ዞን አስቀድሞም በተለያዩ ዓመታት አብያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸው፣ ምእመናን መገደላቸውና መሰደዳቸው ይታወቃል።
ተጨማሪ መረጃዎች እንደደሩስን እናቀርባለን።
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
"ቤተ ክርስቲያን የተፈተነችበት ሥርዓቷን እና ልጆችዋን ያጣችበት ጊዜ ስለሆነ ለሀገራችን እና ለቤተ ክርስቲያናችን ሰላም እንዲመጣ የጳጉሜን 6 ቀናት ወደ እግዚአብሔር እንጸልይ።" ብፁዕ አቡነ አብርሃም
ዛሬ ነሐሴ 29 ቀን 2015 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና በአቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በተሰጠው መግለጫ መሠረት የጳጉሜን ወር 6 ቀናት መላው ኦርቶዶክሳዊ በጸሎት እና በምሕላ እንዲያሳልፍ መታወጁን ነው የገለጹት።
በመግለጫውም ዘመኑ ከደስታ እና የምሥራች ይልቅ ኀዘንን የምንሰማበት ዘመን ስለሆነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን የተቸገሩትን የተራቡትን ፣ የተፈናቀሉትን እና የተጎዱትን እያሰቡ በጾም እና በጸሎት እንዲያሳልፉ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ 13ተኛ ወር በሆነችው ወርኀ ጳጉሜን ዕለተ ምጽዓትን የምናስብበት ፤ ሰማይ የሚከፈትበት ፤ ጸሎት የሚሰማበት ምሥጢራዊ የሆነች ወር ነችና የበደሉንን ይቅር ብለን በንጹሕ ልቡና የቻልን ጾመን ያልቻልን በጸሎት እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት እና የምንለምንበት ወር ሊሆን ይገባል ሲሉ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ገልጸዋል።
@ortodoxtewadochannal
+‹‹ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ ››+
ቤት ሲቃጠል ሚወድ ይኖር ይሆን የብዙ ቀን ልፍትን በቅስፈት ሲያወድም ላየ አያድርስ ማለቱ እንዴት ይቀራል ስለሌላ ሰው ከልባችን በቁጣ ጭረን ያስቀመጥ ነው የክፍት እሳት የመቀጣጠል ጊዜው በረዘመ መጠን በብዙ እያሳጣን አያድርስ ሚል ሲታጣ ይበልጥ ክፍት ልቆ ይገኛል ። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን መልእክቱ "በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት"። (ኤፌ 4፥27) ይለናል ከወዳጃችን የደረሰብንን ጉዳት ከእኛጋ ከማደሩ በፈት ቆርጠን እንጥለው ዘንድ ። ቀንስ ከወዳጅ ስለደረሰብን ክፍ ቃል በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ተወው ወንድምህ አይደል ስለምትቀራረቡ ነው እንጂ ክፍት አስቦ አይደለም በማለት በተወረወረበት ቃል ከተጎዳነው ከተጠቃው ባይነት ክፍ ሐሳብ የሚያስወጡን እና የሚያሰረሱን ብዙዎች ሊኖሩ ይችላሉ ። ሌት ግን ይዞት ሚያድር ከሆነ ብቻውን የቀኑን የእሳት ጭረት እያወጣ እያወረደ ይበልጥ ያነደዋል እና ፀሐይ አይግባብን ብሎ እንድንፈጥን ይነግረናል ። ይህን ካለማድረግ ዛሬ በወዳጅነት ስንኖር የነበርን እንደ ሃገር በአጭር ጊዜ ብዙ እኛነታችንን ሚንዱ ሚያጠፍ አብረን በምናሳድረው ቁጣና ክፍት ወንድሞቻችንን ወዳጆቻችንን እያጠፍን ነው ።
ጠቡቡ በመክብቡ "ቁጣውን የሚያዘገይ ሰው መጥፊያው ይሆንበታል ይለናል "። (መክ 1 ፡ 22)
ጌታችን በስጋዌው ወቅት በሚያስተምርበት ጊዜ “እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ ጊዜ ፥ በዚያም ሳለህ የተጣላህ ወንድምህ እንዳለ ብታስብ ፥ መባህን ከዚያ በመሰዊያው ፈት ትተህ ሂድና አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ፥ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ ። (ማቴ 5፥24) ብሎ ያስተምረናል ስለ ወንድማችን ያለን ፍቅር መስዋዕት ከማቅረብ በላይ በመሆኑ ጌታችን ስለእርሱ ያለንን ክፍት እንድናስወግድ ያስተምረናል ። ከበደል ነው ወንድማችን ጋር ሊያስታርቁ ለሚመጡ ሰዎች ጥፍቱ የእኛ ስለሆነ እንዲህ ብዬ አስቀይሜው እሺ ብሎ ይታረቀኝ ይቻላልን አይ ሌላ ነገር ቢያስብብኝ ነው እንጂማ አያደርገውም የምንል ብዞዎች ነን ። ምክንያቱም ለተበደለው በዳዩን ይቅር ማለቱ ከባድ ነው ብለን ስለምናምን ። ጌታችን ግን ይህን ከባድ ብለን ምናምነውን ጥለን እንድናደርግ ያዘናል “እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን ”። ማቴ 6፥12 ብለን በፀሎት እንለምነው ዘንድ ያስተምረናል ምክንያቱም በፍቅር ስለሌችም አቡነ ዘበሰማያት ብለን ስርየተ ሐጥያትን ሰለወዳጃችንም በመለመን እንጀምራለንና ። እርሱን በድለነው ሳለን የበደልነውን እኛን ከዘመናት ሐጥያታችን ያነፃን ዘንድ በይቅርታው ወደሱ የመለሰን ነውና ።
"በዜና አበው " ላይ ጓደኛን ይቅር ሳይሉ ይቅር በለኝ ብሎ መጠየቅ እንደማይገባ የተቀመጠውን ትምህርት ጠቅሼ ልጨርስ "አንድ ባሕታዊ መነኩሴ ነበርና ጥቅም ያለውን ነገርን(ትምህርትን) የሚተይቀው መነኩሴ በመጣ ጊዜ የእግዚአብሔር ልጅ በኋለኛይቱ ቀን እንደሚጠይቅህ እኔም እጠይቅሀለው ። ምን ላደርግልህ ትወዳለህ ይቅር በለኝ የምትል ከሆነ አንተ አስቀድመህ ጓደኛህን ይቅር በል እኔም ይቅር እልሀለው ይለዋል ። ማቴ 5-24)
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
በዓለ ዕረፍቱ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት
ነሐሴ ሃያ አራት ቀን በምግባር፣ በሃይማኖት ገድል ትሩፋታቸው የታወቁት አቡነ ተክለ ሃይማኖት የዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል ነው፡፡ ተክለ ሃይማኖት ማለት ‹‹የሃይማኖት ተክል፣ ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ›› ማለት ነው፡፡ ጻድቁ አባታችን አባ ተክለ ሃይማኖት በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀሪያ መጋቢት ፳፬ ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ ፳፬ ቀን አንድ ሺህ አንድ መቶ ዘጠና ሰባት ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ጻድቁ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ‹‹አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› ማለትም ‹‹አንዱ አብ ቅዱስ ነው፤ አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው፤ አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው›› በማለት የፈጠራቸውን አምላክ ያመሰገኑ ቅዱስ አባት ናቸው፡፡ ወላጆቻቸውም ስማቸውን ፍሥሐ ጽዮን አሏቸው፡፡ ይኸውም “የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ” ማለት ነው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከልጅነታቸው ጀምሮ በወላጅ አባታቸው በካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ ግብረ ዲቁናን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያጠኑ ቆይተው ከእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ከአቡነ ቄርሎስ (ጌርሎስ) ዲቁናንም ቅስናንም በተለያየ ጊዜ ተቀብለዋል፡፡ ቅዱስ አባታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በወጣትነት ዕድሜያቸው ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡
ጻድቁ አባታችን በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ሕዝቡን ከኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ፣ ከክህደት ወደ ኃይማኖት መልሰዋል፡፡ ከ፩ ሺህ ፪፻፲፱ እስከ ከ፩ ሺህ ፪፻፳፪ ዓ.ም በተከታታይ ሦስት ዓመት፣ ከ፩ ሺህ ፪፻፳፫ እስከ ፩ ሺህ ፪፻፴፬ ዓ.ም ለ፲፪ ዓመታት በዳሞት በወላይታ ሀገር ሕዝቡን በማስተማር ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር፣ ከገቢረ ኀጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ መልሰዋል፤ ቤተ ክርስቲያንንም አንጸዋል፤ በዚሁ ቦታ ዲያብሎስ ‹‹አምላክ ነኝ›› እያለ ለረጅም ዘመናት ሕዝቡን በማሳት የሚጠቀምበትን ዛፍ በተአምራት ከሥሩ ነቅለው አፍልሰውታል፡፡
ከከ፩ ሺህ ፪፻፴፬ እስከ ፩ ሺህ ፪፻፵፬ ዓ.ም ለ፲ ዓመታት በእግዚአብሔር ፈቃድና ትእዛዝ በወሎ ክፍለ ሀገር በአማራ ሳይንት ሕዝበ ክርስቲያኑን በማስተማር፣ ከ፩ ሺህ ፪፻፵፬ እስከ ፩ ሺህ ፪፻፶፬ ዓ.ም አባ ኢየሱስ ሞዐ በሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳም በቅዱስ ሚካኤል መሪነት ሐይቁን በእግራቸው እንደ ደረቅ መሬት በመርገጥ ወደ ደሴቱ በመግባት የአገልግሎትና የትሩፋት ሥራን ሠርተዋል፤ ከ፩ ሺህ ፪፻፶፬ እስከ ከ፩ ሺህ ፪፻፷፮ ዓ.ም ወደ ትግራይ ሄደው ከአቡነ አረጋዊ ገዳም ደብረ ዳሞ ውሰጥ በጊዜው ከነበሩት አበምኔት ከአባ ዮሐኒ ቆብና አስኬማ ተቀብለው ለ፲፪ ዓመታት በገዳሙ መንፈሳዊ ተጋድሎ አድርገዋል፡፡ ጻድቁ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ያመነኮሷቸው እጅግ ብዙዎች ናቸው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በአንብሮተ እድ የሾሟቸው ፲፪ቱ ከዋክብትን፣ ፬ ዐይና የተባሉትን እንዲሁም ነጫጭ ርግብ የተባሉትና ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቀጥሎ በደብረ ሊባኖስ የተሾሙት አፍርተዋል፡፡
ከ፩ ሺህ ፪፻፷፮ እስከ ፩ ሺህ ፪፻፷፯ ዓ.ም ለአንድ ዓመት የትግራይን ገዳማት በሙሉ በመጐብኘት ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ግብፅም በመሄድ በዚያ ያሉ ቅዱሳት መካናትን ትሩፋት ሠርተዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ‹‹ዳዳ›› በተባለ ስፍራ ይመለክ የነበረውን ፸፭ ክንድ የሚረዝመውን ዘንዶ በጸሎት ኃይል በመስቀል ምልክት አማትበው ገድለውታል፡፡ ሦስት ሺህ በጣዖት የሚያመልኩ ወንዶችን አስተምረው አጥምቀው አቊርበዋቸዋል፡፡ ከ፩ ሺህ ፪፻፷፯ እስከ ፩ ሺህ ፪፻፹፱ ዓ.ም ባለው ጊዜ ደግሞ በደብረ ሊባኖስ ካለችው ገዳመ አስቦ ዋሻ ፷ ጦሮችን (ሁለቱን በፊት፣ ሁለቱን በኋላ፣ ሁለቱን በቀኝ፣ ሁለቱን ደግሞ በግራ አስተክለው እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የክርስቶስን ሕማምና ሞት፣ ነገረ መስቀልን በማሰብ በተመስጦ ሌትና ቀን ያለማቋረጥ በጾምና በጸሎት በአርምሞ ተወስነው ሲጋደሉ ከቁመት ብዛት የተነሣ ጥር ፬ ቀን በ፩ ሺህ ፪፻፹፱ ዓ.ም አንድ የእግራቸው ሲሰበር ዕድሜያቸው ፺፪ ዓመት ነበር፡፡ ከ፩ ሺህ ፪፻፹፱ እስከ ፩ ሺህ ፪፻፺፮ ዓ.ም ለሰባት ዓመታት በአንድ እግራቸው እንደ ምሰሶ ጸንተው፤ በተመስጦ በትጋት ለሰው ዘር ሁሉ ድኅነትን ለምነዋል፡፡ ከዚያ በኋላ የመለኮትን ነገር የሚናገር የእሳት አንደበት ያላቸው የመንግሥት ልብስ አለበሳቸው፡፡ በመስቀል ምልክት የተጌጡ ሰባት የሕይወት አክሊላትን አቀዳጅቷቸዋል፡፡ ይኸውም ‹‹ስለ ቀናች ሃይማኖትህ፣ ሃይማኖትን ለማስተማር መላዋን ኢትዮጵያን ስለመዞርህ፣ ከአረማውያን ሕዝብ ጋር በሃይማኖት ስትታገል ደምህን ስለማፍሰስህ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ወርደህ ልዩ ልዩ የቅዱሳን ቦታዎች ስለመሳለምህ፣ በሰባት ዓመታት ቊመት አንዱ እግርህ ስለመሰበሩ፣ ስለብዙ ጾም ጸሎት ስግደትህ፣ ስለልብህ ንጽሕናና ቅድስና›› በማለት የሕይወት አክሊላትን ካቀዳጃቸው በኋላ ዝክራቸውን በማዘከር መታሰቢያቸውን የሚያደርጉ ሁሉ በዚህ ዓለምም ሆነ በወዲያኛው ዓለም ፍጹም ዋጋና ፍጹም ክብር እንደሚሰጣቸው ጌታችን ታላቅ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ በመጨረሻም አባታችን ለ፲ ቀናት ያህል በተስቦ ሕመም ቆይተው ፈጣሪያቸው የገባላቸውን ቃል ኪዳን ለመነኰሳት መንፈሳውያን ልጆቻቸው ከነገሯቸው በኋላ ነሐሴ ፳፬ ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡
ጸሎታቸውና በረከታቸው፣ ረድኤታቸውና ምልጃቸው በመላው ሕዝበ ክርስቲያንና አድሮ ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
ምንጭ፡-ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
+++ የኢየሱስን ልብስ ከላዩ ላይ ገፈፉት ±++
በወንጌል የምናውቃቸው ጌታችን የለበሳቸው ልብሶች አራት ሲሆኑ ሦስቱ ከዕለተ ዓርብ በኋላ የለበሳቸው ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ከመያዙ በፊት ለብሶት የነበረው የራሱ ልብስ ነው ፣ ሁለተኛው ሄሮድስ ለመዘበት ያለበሰው የጌጥ ልብስ ነው ፤ ሦስተኛው ወታደሮቹ ያለበሱት ቀይ ልብስ (ከለሜዳ) ነው ፤ አራተኛው ከትንሣኤው በኋላ ሲገለጥ ለብሶ የታየውና ከየት እንደመጣ የሚያጠያይቀው ነጭ ልብስ ነው፡፡ ጌታችንን መስቀል አሸክመው ከጎልጎታ ኮረብታ ካደረሱት በኋላ ለብሷት የኖራትን ልብሱን ገፈፉት፡፡
‹‹ልብሶቹን ወስደው ለእያንዳንዱ ጭፍራ አንድ ክፍል በአራት አከፋፈሉት ፤ እጀ ጠባቡም ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበር እንጂ የተሠፋ አልነበረም፡፡ ስለዚህ እርስ በእርሳቸው ፡- ለማን እንዲሆን በእርሱ ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ አንቅደደው ተባባሉ፡፡ ይህም ፡- ልብሴን እርስ በእርሳቸው ተከፋፈሉ ፤ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ የሚለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው›› (ዮሐ. ፲፱፥፳፫‐፳፬ መዝ.፳፩፥፲፰)
የጌታችንን ልብስ የገፈፉት ዕርቃኑን ለመስቀል ሲሆን ልብሱን የተከፋፈሉት ደግሞ ሌላ የሚወደው ሰው መጥቶ ልብሱን እንዳይወስደው ነበር፡፡ አብረውት የተሰቀሉትን ወንበዴዎች ልብሶች እንዲህ እንዳደረጉ አልተጻፈም ፤ ይህም ትንቢት የተነገረለት እርሱ ስለሆነና የሚረዳው የሌለ ያማረ ልብስ የማይለብስ ደሃ ነው ብለው በእርሱ ለመሳለቅ እንዲመቻቸው ነበር፡፡
የጌታችን ልብስ ግን እነርሱ እንዳዩት ተራ ልብስ አልነበረም፡፡ ወታደሮቹ አላወቁም እንጂ ከላዩ ገፍፈው በእጃቸው የያዙት ልብስ በታቦር ተራራ እንደ ብርሃን ነጭ የሆነውን ልብሱን ነበር፡፡ (ማቴ. ፲፯፥፪) ይህ ልብስ ከዓሥራ ሁለት ዓመት ጀምሮ ደም ይፈስሳት የነበረችውና ገንዘብዋን ከስራ ልትድን ያልቻለችው ሴት ‹‹የዳሰስሁት እንደሆነ እድናለሁ›› ያለችው ልብስ ነው፡፡ ይህ ልብስ የዚህችን ሴት የደምዋን ምንጭ ያደረቀላት ልብስ ነው፡፡ ጌታችን ሴቲቱን ከፈወሳት በኋላ ‹‹አንድ ሰው ዳስሶኛል ኃይል ከእኔ እንደ ወጣ አውቃለሁ›› ብሎ የተናገረበት ስለዚህ ልብስ ነበር፡፡ (ሉቃ. ፰፥፵፫‐፵፮) ስለዚህ ልብስ ‹‹በገባበት ስፍራ ሁሉ መንደርም ከተማም ገጠርም ቢሆን በገበያ ድውዮችን ያኖሩ ነበር ፤ የልብሱንም ጫፍ እንኳን ሊዳስሱ ይለምኑት ነበር ፤ የዳሰሱትም ሁሉ ዳኑ›› ተብሎ ተጽፎአል፡፡ (ማር. ፮፥፶፮)
ይህንን ተአምረኛ ልብስ የሮም ወታደሮች ተከፋፍለው በእጃቸው ቢይዙትም ደም ይፈስሳት እንደነበረችው ሴት በእምነት ሆነው አልዳሰሱትምና አንዳች ተአምር አላዩም ፤ ‹‹ምንም ተአምር ከልብሱ አላገኙም ፤ ክርስቶስ የማይነገረውን ኃይሉን ገድቦ ነበርና›› ይላል አፈወርቅ፡፡
ሮማውያን ወታደሮች ጌታችን ልብሱን ገፍፈው በአደባባይ ዕርቃኑን አቆሙት ፤ ምድርን በአበባ የሚያስጌጣትን አምላክ ፤ ሰሎሞን እንኳን በክብሩ ለብሶት የማያውቀውን ልብስ ለሜዳ አበቦች የሚያለብሳቸውን አምላክ ልብሱን ገፍፈው ዕርቃኑን አቆሙት፡፡ ‹‹እንደ ሸላቾች ልብሱን ከላዩ ላይ ሁለት ጊዜ ገፈፉት ፤ እርሱም በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ ዝም አለ፡፡ ዕርቃናቸውን ከገነት የወጡትን አዳምና ሔዋንን ለማልበስ ልብሱን ተገፈፈ፡፡ እርሱ በመዋረድ ውስጥ ሆኖ በልብሶቹ ዕርቃናቸውን አለበሰ፡፡ የእርሱ ልብሶች ለተዋረዱት አዳምና ሔዋን እንደሚበቁ ያውቅ ነበርና›› ይላል ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ፡፡
በዚህ ሊቅ ምክንያት እስቲ ለአፍታ አዳምና ሔዋን ከገነት ወደ ወጡባት ቅጽበት እንመለስ፡፡ አዳምና ሔዋን ዕርቃናቸውን ለመሸፈን ቅጠል ባገለደሙ ጊዜ ከገነት ሲወጡ ‹‹እግዚአብሔርም ለአዳምና ሔዋን የቁርበት ልብስን አደረገላቸው አለበሳቸውም›› ይላል፡፡ (ዘፍ. ፫፥፳፩)
እግዚአብሔር ከሌላ ዓይነት ልብስ ይልቅ ስለምን የቆዳ ልብስን ሊያደርግላቸው ወደደ? ብለን ስንጠይቅ ወደ ዕለተ ዓርብ ይመራናል፡፡ እንደሚታወቀው ቁርበት የሚገኘው ከእንስሳ ነው፡፡ አንድ ቁርበት ልብስ እንዲሆን በመጀመሪያ እንስሳው ይታረዳል ፣ ደሙ ይፈስሳል ፤ ቆዳው ይገፈፋል ፣ እንዲደርቅ በእንጨት ላይ ተወጥሮ ይሰጣል ፣ በላዩ ላይ ያለው ነገር እስከሚነጻ ድረስ ይለፋል፡፡ ከዚህ ሁሉ ሒደት በኋላ ልብስ ሊሆን ይችላል፡፡
ይህንን ልብስ በገነት ያለበሳቸው አምላክም የእንስሳ ደሙ እንደሚፈስስ ደሙን አፍስሶ ፣ቆዳው እንደሚገፈፍ ቆዳው አልቆ አጥንቱ እስከሚታይ ተገርፎ ፣ ቆዳ እንደሚወጠር በመስቀል ላይ እንደ ቆዳ ተወጥሮ በዕርቃኑ ዕርቃናችንን ሸፈነልን ፤ እርሱም ለእኛ ልብሳችን ሆነልን፡፡ ‹‹የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋል›› እንዳለ ሐዋርያው (ገላ. ፫፥፳፯)
ወታደሮቹ የጌታችንን ልብስ ለአራት ክፍል ተከፋፈሉ፡፡ ቀሚሱ ግን ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበርና አንቅደደው ተባብለው ዕጣ ተጣጣሉበት፡፡ እነዚህ ወታደሮች ለቀሚሱ ሳስተው ባለመቅደዳቸው ሳያውቁት ትልቅ ምስክርነት መሰከሩ፡፡ ጌታችን ብዙ መንገላታት ሲደርስበት ባደረው በጨለማው ፍርድ ቤት በአይሁድ ሸንጎ ውስጥ ሊቀ ካህናቱ ቀያፋ ከሕግ ውጪ ልብሱን ቀድዶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በዚህም ሥራው ሊቀ ካህናት ልብሱ ሊቀደድ እንደማይገባውና ልብሱን መቅደዱም ሊቀ ካህናትነቱ ማለፍዋን የሚያመለክት እንደሆነ በሥፍራው ተመልክተን ነበር፡፡ እነዚህ ወታደሮች የጌታችንን ቀሚስ ባለመቅደዳቸው የሐዲስ ኪዳን ሊቀ ካህናት ክርስቶስ መሆኑንና ልብሱም ፈጽሞ ሊቀደድ እንደማይገባው የሚያሳይ ታላቅ ምሥጢር ተፈጸመ፡፡
ያልተቀደደችውን የመድኃኔ ዓለም ክርስቶስን ቀሚስና ለአራት የተከፋፈለውን ልብሱን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ብዙ አስተምረውበታል፡፡ ‹ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ› የሚለው ቃል ክርስቶስ ‹ሰው ብቻ ሳይሆን ከላይ የመጣ መለኮት መሆኑን ያመለክታል› ብሎ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አብራርቶታል፡፡ ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬምም ቀሚስ የተባለ መለኮቱ ሊቀደድ (ከሥጋው ተለይቶ ሊከፈል) አይችልም ፤ ለአራት የተከፈለው ልብሱ ግን አራት ሆና የተጻፈችውና በአራቱም ማዕዘን የምትዳረሰው ወንጌል ምሳሌ ናት ሲል ተርጉሞታል፡፡
ይህ የሊቃውንቱ ትርጓሜ ከእግዚአብሔር መንፈስ የተገኘ መሆኑም በቤተ ክርስቲያን ታሪክም ተረጋግጧል፡፡ ዐሥራ ሰባተኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክ ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ አርዮስ የተባለውን በኩረ መናፍቃን ካወገዘው በኋላ የተፈጸመው ነገር ይህን ግልጥ አድርጎ ያሳያል፡፡ አርዮስ ከውግዘቱ በኋላ በፓትርያርኩ ላይና በቤተ ክርስቲያኒቷ ላይ ከንጉሥ መክስምያኖስ ጋር ሴራን ተብትቦ ቅዱስ ጴጥሮስን አሳስሮት ነበር፡፡ ከዚያም አርዮስ ፓትርያርኩ ጴጥሮስ ሊገደል እንደሚችል ሲረዳ እንዳወገዘው እንዳይሞት የዋሃን ካህናትን አማላጅ አድርጎ ምሕረት ሊያስለምነው ሞከረ፡፡ ፓትርያርኩም ለአርዮስ አማላጆች ሆነው ለመጡት ካህናት አርዮስን ከውግዘቱ መፍታት እንዳይችል
ያደረገውን ራእይ እንዲህ ሲል ነገራቸው፡-
@ortodoxtewadochannal
የቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች ለቤ/ያን የተሰጡ ትሩፋቶች ከመሆናቸው ባሻገር የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ከሌሎች አኃት አብያተ ክርስቲያናት በተለየ የራሷ የሆነ እግዚአብሔርን የምታመሰግንበት ሰማያዊ ዜማና ድርሰት በመሆኑ ቤተክርስቲያንን ከፍ ያደርጋታል፡፡
መግለጫው አክሎም የቅዱስ ያሬድ ዜማዎች ለቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ሀገራችን ኢትዮጵያንም በዓለም ስሟን ከፍ አድርገው ከሚያስጠሩ ሀብቶቿ መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ከ6ኛው እስከ 10ኛው ክፍለ ዘመን የዘለቀ ወርቃማ ዘመንን ናኝቶናል፡፡ ይህም ኢትዮጵያ በእውቀትና በጥበብ የተራቀቀችበት ፣ ሰብዓዊነትን እንደ ቀኖና የተቀበለችበት ታላቅ የሥልጣኔ ዘመን ታሪኳ ሆኖ ተመዝግቧል ሲል አብራርቷል፡፡
ለዚህም ዛሬ ሀገራችን ኢትዮጵያ በ ዩኔስኮ በማይዳሰሱ ቅርስነት ያስመዘገበቻቸውና የቅድስት ቤ/ያን ሀብት የሆኑት የመስቀል ደመራና የጥምቀት በዓላትን ያለ ቅዱስ ያሬድ ሥራዎች ድምቀታቸውን ማሰብ አለመቻሉ ለቅዱስ ያሬድ ሀገራዊ አስተዋጽኦ ምስክር ነው በማለትም አፅዕኖት ሰጥቷል፡፡
ይሁን እንጅ ቅዱስ ያሬድ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውጪ እንደ ሀገር በተገቢው ደረጃ ያልተነገረለትና ያልተዘመረለት ፣ የሚገባውንም ክብርና ዕውቅና ያልተቸረው ታላቅ ሊቅና ቅዱስ ነው፡፡
በመሆኑም የቅዱስ ያሬድን የሚዘክረውና ለትውልድ ተሻጋሪ የልማት ፕሮጀክቶች የሚበሠርበት ልዩ መርሐግብር በብጹአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ገዳማውያንና በቅዱስ ያሬድ ልጆች ሊቃውንተ ቤ/ያን የሚመራ የጸሎት ፣ የትምህርትና የቅዱስ ያሬድን ሥራዎች የሚዘክሩ ልዩ ልዩ መርሐግብራትን ያካተተ ለደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ ገዳም የሚውል ልዩ የገቢ አሰባሰብ መርሐግብር ይከናወናል፡፡
በመሆኑም ቅዱስ ያሬድ የሁሉም በሁሉም ቦታ ያለ የኢትዮጵያዉያን ሀብትና ኩራት በመሆኑ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አማኞችና የቅዱስ ያሬድ ልጆች፣ የቅዱስ ያሬድ ወዳጆችና የትሩፋቱ ተሳታፊዎች መርሐግብሩን በማስተዋወቅ ፣ ለመርሐግብሩ መግቢያ የተዘጋጁ ትኬቶችን በመግዛትና በዕለቱ በመገኘት፣ በሀገር ዉስጥና በውጭ ሀገር የምትገኙና በቦታ ርቀትና በሁኔታዎች አለመመቸት ምክንያት በዚህ ታላቅና ታሪካዊ መርሐግብር ላይ መገኘት የማትችሉ የቅድስት ቤ/ያን ልጆችና የቅዱስ ያሬድ ወዳጆች ባላችሁበት ቦታ በመሆን መርሐግብሩን በመከታተልና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ከቅዱስ ያሬድ በረከት ተሳታፊ በመሆን የዚህ ታሪካዊ መርሐግብር አካል እንዲሆኑ በደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳምና በቅዱስ ያሬድ ስም ጥሪውን አቅርቧል።
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
#ነሐሴ_16
#ዕርገተ_ማርያም
ነሐሴ ዐሥራ ስድስት በዚህች ቀን አምላክን የወለደች የእመቤታችን ድንግል ማርያም ሥጋዋ ወደ ሰማይ ያረገበት መታሰቢያዋ ሆነ። ከዕረፍቷም በኋላ ከእርሳቸው ስለመለየቷ ሐዋርያት ፈጽሞ እያዘኑ ነበር።
ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ተገለጠላቸው እርሷን በሥጋ ያዩ ዘንድ እንዳላቸውም ተስፋ ሰጣቸው። ወንጌላዊ ዮሐንስም እስያ በሚባል አገር እያስተማረ ሳለ በነሐሴ ወር ዐሥራ ስድስተኛ ቀን ተድላ ደስታ ወደአለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቀ።
የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ካለበት ከዕፀ ሕይወት ሥር ተቀምጦ አየው። የንጽሕት እናቱንም ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው። እነርሱም የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አሏት። ያን ጊዜም ከዕፀ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ወጣ።
የክብር ባለቤት ጌታችንም እንዲህ እያለ አረጋጋት የተወደድሽ የወለድሽኝ እናቴ ሆይ ዘላለማዊ ወደ ሆነ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ ነዪ። ያን ጊዜም በገነት ያሉ ዕፀዋት ሁሉም አዘነበሉ መላእክት የመላእክት አለቆች ጻድቃን ሰማዕታትም እየሰገዱላትና ፈጽሞ እያመሰገኗት አሳረጓት።
አባቷ ዳዊትም ንግሥት እመቤታችን ወርቀ ዘቦ ለብሳ ደርባ ደራርባ በቀኝህ ትቀመጣለች እያለ በበገና አመሰገናት። በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጣ ከዐረገች በኋላ በልጁዋና በፈጣሪዋ ቀኝ በታላቅ ክብር ተቀመጠች።
ወንጌላዊ ዮሐንስም ከእርሷ በረከትን ተቀብሎ ሰግዶላት ተመልሶ ከሰማይ ወረደ ሐዋርያትን ተሰብስበው ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ ፈጽሞ ሲያዝኑና ሲተክዙ አገኛቸው። እርሱም እንደ አየ እንደ ሰማ ሥጋዋንም በታላቅ ክብር በምስጋና እንደ አሳረጓት ነገራቸው።
ሐዋርያትም በሰሙ ጊዜ ዮሐንስ እንዳየና እንደሰማ ባለማየታቸውና ባለመስማታቸው እጅግ አዘኑ። ከዚህም በኋላ እያዘኑ ሳሉ እነሆ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠላቸውና የፍቅር አንድነት ልጆች ሰላም ይሁንላችሁ ስለ እናቴ ማርያም ሥጋ ለምን ታዝናላችሁ። እነሆ እኔ እርሷን በሥጋ ላሳያችሁ ልባችሁም ደስ ሊለው ይገባዋል አላቸው ይህንንም ብሎ ከእርሳትው ዘንድ ወደ ሰማያት ዐረገ።
ሐዋርያትም ዓመት ሙሉ ቆዩ የነሐሴም ወር በባተ ቀን ለሐዋርያት ዮሐንስ እንዲህ አላቸው አምላክን የወለደች የእመቤታችንን ሥጋዋን ለማየት የተዘጋጀን አድርጎ ያሰየን ዘንድ ኑ ይህን ሁለት ሱባዔ በመጾም የክብር ባለቤት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው በልጅዋ በወዳጅዋ ቀኝ ተቀምጣ አይተን በእርሷ ደስ እንዲለን።
በዚያን ጊዜም ዮሐንስ እንዳላቸው በጾም በጸሎት ሱባዔ ያዙ የነሐሴ ወር እንደ ዛሬ ዐሥራ ስድስተኛ ቀን በሆነ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ሐዋርያት ወደ ሰማይ አወጣቸው። በታላቅ ክብር በተወደደ ልጅዋ ቀኝ ተቀምጣ ከሥጋዋ ተዋሕዳ ተነሥታ እመቤታችን ማርያምን አዩዋት። እጆቿንም ዘርግታ የከበሩ ሐዋርያትን እያንዳንዳቸውን ባረከቻቸው በልባቸውም እጅግ ደስ አላቸው።
የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በከበረ ሥጋውና ደሙ ላይ ሠራዒ ካህን ሆነ። እስጢፋኖስም አዘጋጀ ዮሐንስም በመፍራት ቁሙ አለ። ሁሉም ሐዋርያት በመሠዊያው ዙሪያ ቆሙ በዚያን ጊዜ ከቶ እንደርሱ ሆኖ የማያውቅ ታላቅ ደስታ ሆነ።
ጌታችንም የቅዳሴውን ሥርዓት በፈጸመ ጊዜ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው ። ከዚያም በኪሩቤልና በሱራፌል ሠረገላ ተቀምጣ በምታርግ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ እመቤታችን ማርያምን እንዲህ ብሎ ተናገራት።
በዚች ቀን የሆነ የዕርገትሽን መታሰቢያ በዓለም ውስጥ እንዲሰብኩ ልጆችሽ ሐዋርያትን እዘዣቸው። መታሰቢያሽን የሚያደርገውን ሁሉ ተጠብቆም በዚች ቀን ቅዱስ ቁርባንን የሚቀበለውን ኃጢአቱን እደመስስለታለሁ። የእሳትን ሥቃይ ከቶ አያያትም መታሰቢያሽን ለሚያደርግ ሁሉ በዚች ቀን ለድኆች በስምሽ ለሚመጸውት ቸርነቴ ትገናኘዋለች ይህም ሥጋሽ ወደ ሰማይ ያረገበት ነው።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ክብር ይግባውና ጌታችንን እንዲህ አለችው ልጄ ሆይ እነሆ በዐይኖቻቸው አዩ በጆሮቻቸውም ሰሙ በእጆቻቸውም ያዙ ሌሎችም ታላላቅ ደንቆች ሥራዎችን አዩ። እመቤታችንም ይህን ስትናገር ጌታችን ሰላምታ ሰጥቷቸው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረ ዘይት ተመለሱ።
የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ በፍጹም ደስታ መታሰቢያዋን እናደርግ ዘንድ ይገባናል እርሷ ስለእኛ ወደ ተወደደ ልጅዋ ሁልጊዜ ትማልዳለችና።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን። በረከቷም ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከአባ ማትያስ ከሁሉም ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት ጋራ ሐዋርያት ከሰበሰቧት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ከሁላችን ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ)
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
መንፈሳዊ ጥያቄ
👉ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው ? ችቦ ለምን እና መቼ ይበራል? ሙልሙል ልምን ይታደላል? በቡሄ ወቅት ጭራፍ ለምን ይጮሃል ?
እግዚአብሔር አምላክም ኃዘናቸውን ሰምቶ ሐምሌ ፴ እሷ ለእርሱ ግምጃ ሲያስታጥቁት መቋሚያው አፍርታ ፍጥረት ፍሬዋን ሲመገቡ፣ እሱ ለእሷ ነጭ ርግብ ሰባቱን ሰማያት ሰንጥቃ መጥታ በቀኝ ጆርዋ ገብታ በማኅፀንዋ ስታድር ራዕይ አሳያቸው። እነርሱም ሄደው ለመፈክረ ሕልም/ ሕልም ተርጓሚ/ ነገሩት፤ ሕልም ተርጓሚውም የከበረች ልጅ ትወላዳለችሁ” ሲል ተረጎመላቸው። እያቄም እና ሐናም ሕልማቸው እንዲፈጸምላቸው የእግዚአብሔርን ፈቃድ በጸሎት እየጠየቁ ኖሩ፡፡ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ አብርሃምን እና ሣራን የተመለከተ አምላክ በኢያቄምና ሐና አማካኝነት ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነችውን እና ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ልቡና ታስባ ትኖር የነበረችው እመቤታችን ድንግል ማርያም በነሐሴ ሰባት ቀን ተፀነሰች፡፡
ሐና በእርጅናዋ ጊዜ መፅነሷን የሰሙት ዘመዶቿና ያገሯ ሰዎች ተገርሙው፤ እየመጡ ጠይየቋት፡፡ እመቤታችን ድንግል ማርያም በተሰነፀች ጊዜ ተአምራትን አድርጋለች። ከእነዚህም መካከል ዐይነ ስውር የነበረችው የአርሳባን ልጅ ወደ ሐና መጥታ እውነትም ሐና መፅነሷን ለማረጋገጥ መሕፀን ዳሰሰቻት፡፡ በአድናቆትም ዐይኗን ስትነካ ዐይኗ በራላት፡፡ በሌላ ጊዜም የአጎቷ ልጅ ሳምናስ በሕመም ምክንያት ይሞትና ሐና ትወደው ስለነበር አስክሬኑ በተቀመጠበት አልጋ ዙሪያ ስታለቅስ ድንገት ጥላዋ ቢያርፍበት የሞተው ተነሥቶ ሐና የአምላክ እናት የምትሆን እመቤታችንን እንደምትወልድና በዚህም ሐና እጅግ የከበረችና ምስጋና የሚገባት መሆኗን መሰከረ፡፡ ለዓለም ሁሉ የድኅነት መገኛ የሆነች ክብርት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተፀነሰችበት ዕለት ነሐሴ ሰባት የተባረከች እንደመሆኗ መላው ክርስቲያን በዓሏን ሊያከብር ይገባል፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ልጅሽ ወዳጅሽ ይቅርታውን፣ ቸርነቱን፣ ምሕረቱን በእኛ ላይ ያሳድርብን ዘንድ ለምኝልን፡ አሜን!!
ምንጭ፡- መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ነሐሴ እና መዝግበ ታሪክ
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
#የቅዳሜ_ውዳሴ_ማርያም_ትርጓሜ
ከተለዩ የተለየሽ፣ ከከበሩ የከበርሽ በውስጧም ሕግ የተጻፈበት ኪዳን ያለብሽ የተሠወረ መና ያለበት መሶበ ወርቅ ያለብሽ ደብተራ (ድንኳን) አንቺ ነሽ /ዘጸ.፳፮፡፩-፴/፡፡ ይኸውም መና የተባለው ሰው ኾኖ በማኅፀንሽ ያደረው ወልደ እግዚአብሔር ነው፡፡ መተርጕማኑ ይህን የበለጠ ሲያብራሩት፡- “ድንኳኗ የእመቤታችን ምሳሌ፤ ቅድስት የነፍሷ፤ ቅዱሳን የሥጋዋ፤ ታቦቱ የመንፈስ ቅዱስ፤ ጽላት የልቡናዋ፤ ቃሉ በመንፈስ ቅዱስ የተገለጸላት ምሥጢር ምሳሌ ነው፡፡ አንድም ቅዱሳን የሥጋዋና የነፍሷ፤ ቅድስት የልቡናዋ፤ ታቦት የማኅፀኗ፤ ጽላት የትስብእት፤ ቃሉም የመለኮት ምሳሌ ነው” ይላሉ /ውዳሴ ማርያም ንባቡና ትርጓሜው፣ ገጽ ፻፸፬/፡፡ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በአርጋኖን ዘሐሙስ ላይ፡- “ተፈሥሒ ኦ ደብተራ ብርሃን ማኅደሩ ለዐቢይ ሊቀ ካህናት - የታላቁ ሊቀ ካህናት ማደርያ የብርሃን ድንኳን ሆይ! ደስ ይበልሽ” በማለት የሊቀ ካህናት የባሕርይ አምላክ የክርስቶስ እናት አማናዊት ድንኳን መኾኗን አስተምሯል፡፡
አካላዊ ቃል ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው ኾነ፡፡ የክብር ባለቤት እርሱን በዚህ ዓለም ወለደችው፡፡ ለዘለዓለሙ ጸንቶ የሚኖር አካላዊ ቃል ሰው ኾኖ ከኃጢአታችን ፍዳ አድኖናልና ሰው ኾኖ ያዳነን የነባቢ በግዕ (የሚናገር በግ የክርስቶስ) እናቱ ደስ ይላታል /ዮሐ.፩፡፳፱/፡፡ ለዘለዓለሙ ጸንቶ የሚኖር አካላዊ ቃል ሰው ኾኖ ከኃጢአታችን ፍዳ ካዳነን ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
እርሱን ከወለድሽ በኋላ ማኅተመ ድንግልናሽ ሳይለወጥ ኑረሻልና የክርስቶስ እናቱ ተባልሽ፡፡ ድንቅ በሚያሰኝ ተዋሕዶ አማኑኤልን ወልደሸዋልና ባለመለወጥ አጸናሽ፡፡ ታላቁ የቤተ ክርስቲያን መምህር ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ለማንም ሴት ያልተሰጠ ለድንግል ማርያም ብቻ የተሰጠ ድንግልና ከእናትነት ጋር አስተባብራ ስለ መገኘቷ ሲገልጥ “ወሰቦሂ ወለደቶ ዐቀበ ድንግልና፣ ዘእንበለ ርኩስ ከመ በፀንሳ መንክር ትኩን መራሂተ ለሃይማኖት ዐባይ - ከድንግል ተወለደ፤ በወለደችውም ጊዜ ድንግልናዋ ያለመለወጥ አጸና፡፡ ድንቅ የሚኾን ፅንሷ ለደገኛው ሃይማኖት መሪ ትኾን ዘንድ” በማለት ቅድስት ድንግል ማርያም አምላክን ስትወልድው ማኅተመ ድንግልናዋ እንዳልተለወጠ ጌታም ሰው ሲኾን ባሕርየ መለኮቱ ላለመለወጡ፣ እርሷ ድንግል ወእም (ድንግልም እናትም) ስትባል እንደምትኖር አካላዊ ቃል ክርስቶስም አምላክ ወሰብእ (ሰው የኾነ አምላክ) ሲባል የሚኖር የመኾኑን የተዋሕዶ ልዩ ምሥጢርን ያወቅንባት የተረዳንባት እርሷ ብቻ መኾኗን አስተምሯል /ሃይ.አበ.፷፮፡፴፪/፡፡ እንዲህ ካለ ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
ከምድር እስከ ሰማይ ደርሳ፣ በላይዋ ዙፋን ተነጽፎባት፣ በዚያ ላይ ንጉሥ ተቀምጦባት፣ መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ያዕቆብ በፍኖት ሎዛ ያያት የወርቅ መሰላል አንቺ ነሽ /ዘፍ.፳፰፡፲-፳፪/፡፡ ሰው ከመኾኑ አስቀድሞ ሰውም ከኾነ በኋላ የማይመረመር እርሱን በተፈትሖ በማይታወቅ በማኅፀንሽ ችለሸዋልና እኛን ስለማዳን ከአንቺ ሰው ከኾነ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ሰዋስው (አማላጅ) ኾንሽን፡፡ እኛን ስለማዳን ከአንቺ ሰው ከኾነ ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
ጽርሐ ንጽሕት ሆይ! እነሆ ጌታ የፈጠረውን ዓለም ኹሉ በቸርነቱ ብዛት ያድን ዘንድ ከአንቺ ተወለደ፡፡ ቸር ሰው ወዳጅ ነውና በአፍአ በውስጥ እናመስግነው፡፡ ቸር ሰው ወዳጅ ከኾነ ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
#የሐሙስ_ውዳሴ_ማርያም_ትርጓሜ
ይህ ዕለት ለምስጋና አራተኛ ለፍጥረት አምስተኛ ቀን ነው፡፡ በዚህም ቀን እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ዙፋን ይነጸፋል፡፡ ከዚያ ላይ ኹናም ሊቁን ባርካው ምስጋናዉን ጀምሯል፡፡ ከወትሮ ይልቅም ነቢያትንና ሐዋርያትን አስከትላ መጥታለች፡፡
፩. ነደ እሳት ሰፍሮባት፣ በነደ እሳት ተከባ፣ ጫፎቿ ሳይቃጠሉ ሙሴ በደብረ ሲና ያያት ዕፅ ድንግል ማርያምን ትመስላለች /ዘጸ.፫፡፩-፫/፡፡ አካላዊ ቃል ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው ኹኗልና፤ ባሕርየ (እሳተ) መለኮቱም አልለወጣትምና (አላቃጠላትምና) ሐመልማላዊቱ ዕፅ እመቤታችንን ትመስላለች፡፡ ዳግመኛም እርሱን ከወለደችው በኋላ ማኀተመ ድንግልናዋ አልተለወጠምና ሐመልማላዊቱ ዕፅ እመቤታችንን ትመስላለች፡፡ እርሱም ምንም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷም ነፍስ ነስቶ ፍጹም ሰው ቢኾንም ባሕርየ መለኮቱ አልተለወጠምና እሳቱን ይመስላል፡፡ ሰውም ቢኾን ባሕርየ መለኮቱ አልተለወጠምና ሰው ኾኖ ያዳነን የባሕርይ አምላክ ነው፡፡ ሰው ኾኖ ካዳነን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋዉን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፪. ይቅርታሽ (ምልጃሽ) ለኹላችን ይኾን ዘንድ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ! ኹላችን እናከብርሻለን፤ እናገንሻለን፡፡ ሔዋን ባደረገችው ዐመፅ በባሕርያችን ጸንቶ የነበረ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ በእርሷ ምክንያት የጠፋልን አምላክን የወለደች ድንግል ማርያም የኹላችን መመኪያ ናት፡፡ “ሔዋን ምን አደረገች?” ትለኝ እንደኾነም ዕፀ በለስን በልታለች እልሃለሁ፡፡ “ወአዘዞሙ ለኪሩቤል ወሱራፌል ዘውስተ እደዊሆሙ ሰይፈ እሳት እንተ ትትመያየጥ ከመ ይዕቀቡ ፍኖተ ዕፀ ሕይወት - ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔድን ገነት ምሥራቅ አስቀመጠ” እንዲል /ዘፍ.፫፡፳፬/ በሔዋን ምክንያት የገነት ደጅ ተዘጋ፡፡ “ወአግኃሦ ለሱራፊ ዘየዐቅብ ፍና ዕፀ ሕይወት፤ ወአእተተ እምእዴሁ ኵናተ እሳት - ” እንዲልም በድንግል ማርያም ምክንያት ዳግመኛ ተከፈተልን፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግም፡- “አዳምን እንዲሞት ያደረገች ያቺ ቀን ተለወጠች፡፡ እርሱም ከሞት የሚድንባት ሌላ ቀን መጣች፡፡ እባቧ ሳትኾን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ይናገር ዘንድ ተነሣ፡፡ ሔዋን ሳትኾን ድንግል ማርያምም ቃሉን ትቀበል ዘንድ ተዘጋጀች፡፡ በተንኰል የሚያስተው ሳይኾን ሕይወትን የሚያውጀው ቃል ወጣ፡፡ በሞት ዛፍ መካከል የሞት ዕዳዋን በጻፈችው ሔዋን ፈንታ ልጇ (ማርያም) የአባቷን ዕዳ ኹሉ ከፈለች፡፡ ሔዋንና እባቡ በቅድስት ድንግል ማርያምና በቅዱስ ገብርኤል ተተኩ፡፡ ያ ከመጀመርያው የተበላሸው ነገር አሁን ተስተካከለ፡፡ የሔዋን ጀሮና ቀልብ አታላዩ በሚናገርበት ጊዜ እንደምን እንዳዘነበለ አስተውሉ፤ ያ በገነት ሲመለከታቸው የነበረው መልአክ አሁን በድንግል ማርያም ጀሮ የድኅነትን ተስፋ ሲያሰርጽና የእባቡን ከፉና መርዛማ ቃል ሲያጠፋ ደግሞ አስተውሉ፡፡ ሔዋን ያፈረሰችው ሕንፃ ገብርኤል ገነባው፡፡ በዔደን ገነት ውስጥ ኹና ሔዋን ያፈረሰችውን መሠረት ዳግሚት ሔዋን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ኹና ገነባችው፡፡ ከኹለት መልእክተኞች መልእክት የተቀበሉ ኹለት ደናግላን ኹለት ትውልድን ቀጠሉ፡፡ አንዱም የአንዱ ተቃራኒ ኾነ፡፡ በእባብ ምክንያት ሰይጣን ምሥጢርን ለሔዋን ላከ፡፡ በሌላ ቅዱስ መልአክ አማካኝነት ደግሞ ጌታ የምሥራቹን ወደ ቅድስት ድንግል ማርያም ላከ፡፡ እባብ ለሔዋን የሐሰትን ቃል ለሔዋን ስትናገር ቅዱስ ገብርኤል ግን የእውነትን ቃል ለቅድስት ድንግል ማርያም ተናገረ፡፡ እውነትን በሚናገር አንደበቱ የቀደመውን የእባብ ቃል አደሰው፡፡ እውነትን ተናገረና ሐሰቱን አስወገደው፡፡ አስቀድሞ ሐሰትን ከራሱ አንቅቶ ሰይጣን ሔዋንን በዔደን ገነት አታለላት፡፡ ይህንንም ታላቅ ስሕተት በጀሮዋ አልፎ እንዲሰማት ፈቀደች፡፡ አሁን ግን በመጀመርያዋ ድንግል ፈንታ ሌላ ድንግል ተመረጠች፡፡ በዚህች ድንግል ጀሮም ከአርያም የተላከ የእውነት ቃል ገባ፡፡ ሞት በገባበት በዚያ በር (ጀሮ) ሕይወት ገባ፡፡ ክፉው (ዲያብሎስ) ያጠበቀው ጽኑ የሞት ማሰርያም ተፈታ፡፡ ኀጢአትና ሞት ሠልጥነውበት በነበረ ቦታ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በዝቶ ታየ፡፡ … እባብ የስሕተትን ዜማ ለሔዋን ዘመረላት፤ ሐሰትንም ረጨባት፡፡ በተፈጥሮዋ ገና ድንግል በምትኾን በሔዋን ላይ ክፉ ምክርና ስሕተት አፈሰሰባት፡፡ በመርዝ የተለወሰና ደምን የተጠማ ክፉ ምክር በአዳም ቤት ውስጥ አስገባ፡፡ ኃይለ ልዑል የላከው መልአክ ግን እነዚህን የክፋት ሰይፎች ለመቆራረጥ ክንፉን እያማታ እየበረረ መጣ፡፡ ለሰው ኹሉ የሚኾን የድኅነት ሰነድ ይዞ መጥቶም ለድንግሊቱ (ለማርያም) አበሠራት፡፡ ሰገደላት፡፡ ሕይወትን በውስጧ አሰረጸ፡፡ ሰላም ዐወጀ፡፡ በፍቅር ቀረባት፡፡ የቀድሞውን የሞት ዳባ በጣጠሰው፡፡ እባብ የገነባውን የማታለል ግንብ ዳግም ላይገነባ በወልደ እግዚአብሔር እንደሚናድ ነገራት፡፡ በእባብ የታጠረው የሞት ቅጽር በወልድ መውረድ እንደሚሰባበር ቀጠሮው እንደደረሰ ነግሮ የምሥራች አላት” በማለት ከማር የጣፈጠ ትምህርቱን እያነጻጸረ አስተምሯል፡፡
ከዕፀ ሕይወትም እንበላ ዘንድ አደለን፡፡ ይኸውም እኛን ስለ መውደድ ሰው ኾኖ ያዳነን የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ነው፡፡
ወዮ! ሰውን የሚወድ ሰውም የሚወደው እግዚአብሔር፣ ማኅደርም ኀዳሪም ያይደለ አካላዊ ቃል፣ ሳይለወጥ ቅድመ ዓለም የነበረ እግዚአብሔር ወልድ፣ ከአብ አንድነት ሳይለይ መጥቶ ንዕድ ክብርት ከምትኾን ከእመቤታችን ሰው ኾኗልና፤ እርሱንም ከወለደችው በኋላ እንደ ቀድሞ ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ ኑራለችና፤ ስለዚህም ነገር አምላክን የወለደች እንደኾነች በጎላ በተረዳ ነገር ታውቃለችና ለርሷ ድንቅ ኾኖ የሚነገረውን ነገር መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው? መስማትስ የሚቻለው ምን ጆሮ ነው? ማወቅስ የሚቻለው ምን አእምሮ ነው? የእግዚአብሔር የጥበቡ ምላት ስፋትስ ምን ይረቅ? ምን ይጠልቅ? አንድም ለእግዚአብሔር ለጥበቡ ምላት ስፋት አንክሮ ይገባል፡፡ “በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል” /ዘፍ.፫፡፲፮/ ብሎ የፈረደባት ማኀፀን የሕይወት፣ የድኅነት መገኛ ኾነች፡፡
ሊንኩን ተጭነው ሙሉውን ያንብቡ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
#የማክሰኞ_ውዳሴ_ማርያም_ትርጓሜ
ለምስጋና ኹለተኛ፣ ለፍጥረት ሦስተኛ ቀን በሚኾን በዚህ ቀንም እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ምንጻፍ ይነጸፋል፡፡ ከዚያ ላይ ኾናም፡- “ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ ኤፍሬም” ትለዋለች፡፡ እርሱም ታጥቆ እጅ ነሥቶ ይቆማል፡፡ ክርክር በዕለተ ሰኑይ አልቋልና “ባርክኒ” ብሎ ተባርኮ “አክሊለ ምክሕነ” ብሎ ምስጋናውን ይጀምራል፡፡
፩. ዳዊት ምንም ንጉሠ ነገሥት ቢባል የመመኪያችንን ዘውድ ማምጣት አልተቻለውም /፩ኛሳሙ.፲፮፥፲፫/፡፡ ኢያሱ ምንም የስሙ ትርጓሜ መድኃኒት ቢኾንም የደኅንነታችን መጀመሪያ መኾን አልተቻለውም፡፡ ኤልያስም ምንም ንጹሕ፣ ድንግል ቢኾንም የንጽሕናችን መሠረት መኾን አልተቻለውም፡፡ የመመኪያችን ዘውድ፣ የደኅንነታችን መጀመሪያ፣ የንጽሕናችን መሠረት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የመመኪያችን ዘውድ “አክሊለ ሰማዕት” የሚባል ጌታችን ነው፡፡ የደኅንነታችን መጀመርያ “ጥንተ ሕይወት” የሚባል ጌታችን ነው፡፡ የንጽሕናችን መጀመርያም ኹሉ በእጁ የተጨበጠ፣ ዓለምንም በመዳፉ የያዘ፤ በጠፈር ላይ የሚቀመጥ ፣ ዳግመኛም መሠረቱን ከታች የሚሸከም “መሠረተ ዓለም” የሚባል ጌታችን ነው /ቅዳ.ማር. ቁ.፶፩/፡፡ እርሱም አካላዊ ቃልን በወለደችልን በድንግል ማርያም ተገኘልን፡፡ እኛን ስለማዳን ሰው ኾነ፤ ሰውም ከኾነ በኋላ ግን ፍጹም አምላክ ነው፡፡ ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ እንደ ወለደችው ኹሉ እርሱም አምላክነቱ ሳይለወጥ ሰው ኾነ፡፡ እርሷ “ድንግል ወእም (ድንግልም እናትም)” ስትባል እንደምትኖር ኹሉ እርሱም “አምላክ ወሰብእ (ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው)” ሲባል ይኖራል /ሃይ.አበ.፷፯፡፯/፡፡ ተፈትሖ ሳያገኛት (ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ) እንደምን እንደወለደችው ግን የማይመረመር አንድም ሊነገር የማይችል፣ ከኅሊናት ኹሉ የሚያልፍ ድንቅ ነው፡፡
በማይመረመር ግብር ከወለድሽው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፪. “ቃል ሥጋ ኾነ” እንዲል በእርሱ ፈቃድ /ዮሐ.፩፡፲፬/፣ “ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና” እንዲል በአባቱ ፈቃድ /ዮሐ.፫፡፲፮/፣ “በመንፈስ ቅዱስ በኀይልም እንደ ቀባው” እንዲልም /ሐዋ.፲፡፴፰/ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ሰው ኾኖ አዳነን፡፡ ሊቁ እንዲህ ማለቱ “ወልድ ያለ ፈቃዱ ሰው ኾነ” የሚሉ መናፍቃን ስላሉ ነው፡፡ ሌሎች ሊቃውንትም፡- “የእግዚአብሔር ልጅ ያለ ፈቃዱ ሰው እንደ ኾነ የሚያምን፤ የሚያስተምር፤ ወይም የአብ ፈቃድ ሌላ ነው፤ የወልድ ፈቃድ ሌላ ነው፤ የመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ሌላ ነው የሚል ቢኖር፤ ፈቃዳቸው አንድ፤ መንግሥታቸውም አንድ እንደኾነ የማያምን ሰው ቢኖር ውጉዝ ይኹን” ብለው አስተምረዋል /ሃይ.አበ.፻፳፫፡፪/፡፡
በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ፍጽምት የምትኾኚ እመቤታችን ሆይ! በድንግልና ጸንተሽ ብትገኚ ላንቺ የተሰጠሸ ጸጋ ፍጹም ነው፡፡ እግዚአብሔር ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ካንቺ ጋራ አንድ ባሕርይ ቢኾን አንድም በጸጋ ቢያድርብሽ ባለሟልነትን አግኝተሸልና ለአንቺ የተሰጠ ክብር ፍጹም ነው፡፡ ይህ ከቃላት በላይ የሚያልፈው ባለሟልነቷ ቅዱስ ባስልዮስ ከሌሎች ቅዱሳን ጋር እያነጻጻረ ሲያብራራው፡- “የዚህ ዓለም ነገር ኹሉ አይመጥናትምና የሚመጥናትን ምን ዓይነት ምስጋና እናቅርብላት? ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ቅዱሳን ሲናገር ዓለም አልተገባቸውም /ዕብ.፲፩፡፴፰/ ካላቸው ከከዋክብት በላይ ኾና እንደምታበራው ፀሐይ ለኾነችው ለአምላክ እናትማ ምን ልንል እንችል ይኾን?... ምን ምሥጢር እንደተከናወነ ተመልከት፤ ኅሊናን አእምሮን የሚያልፍ ነገር እንደኾነም አስተውል፡፡ ታድያ የአምላክ እናት ታላቅነት እንደምን ኹሉም ሰው አይናገር? ማንስ ነው ከቅዱሳን ኹሉ በላይ እንደኾነች ያላስተዋለ? እግዚአብሔር ለአገልጋዮቹ የሚልቅ ጸጋን ከሰጠና የሚነኩት ኹሉ ሰው ከበሽታው ከተፈወሰ፣ ጥላቸው ያረፈበት ተአምር ከተፈጸመለት፣ ጴጥሮስ በጥላው ካዳነ /ሐዋ.፭፡፲፭/፣ የጳውሎስ የልብሱ ዕራፊ መናፍስትን ካወጣ /ሐዋ.፲፱፡፲፩/ ለእናቱማ ምን ዐይነት ሥልጣንና ኀይል ተሰጥቷት ይኾን? በምን ዓይነትስ ሥጦታ አስጊጧት ይኾን? ጴጥሮስ፡- ክርስቶስ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ስላለው ብፁዕ ነህ ከተባለና የመንግሥተ ሰማያት ቁልፍ ከተሰጠው /ማቴ.፲፮፡፲፮-፲፱/ እርሷማ ከኹሉም ይልቅ እንዴት ብፅዕት አትኾን? /ሉቃ.፩፡፵፭/ ጳውሎስ ታላቅ ክብር ያለውን የክርስቶስን ስም በመሸከሙ ምርጥ ዕቃ ከተባለ /ሐዋ.፱፡፲፭/ የአምላክ እናትማ የምእመናን ምግብ የኾነ መናውን ሳይኾን የሕይወት ሰማያዊ እንጀራን ያስገኘች እርሷ ምን ዓይነት ልዩ ዕቃ ትኾን? … ነገር ግን ስለ እርሷ ብዙ እናገራለሁ ብዬ ስለ ክብሯ ጥቂት በመናገር ራሴን በኀፍረት ውስጥ እንዳልጨምር እፈራለኁ፡፡ ስለዚህ ከአሁን ወዲህ የንግግሬን መልሕቅ ስቤ በዝምታ ወደቤ ላይ ማረፍን መርጫለሁ” ይላል /መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ፣ ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን፣ ገጽ ፺-፺፩ ይመልከቱ/፡፡
ከምድር እስከ ሰማይ ደርሳ፣ በላይዋ ዙፋን ተነጽፎባት በዚያ ላይ ንጉሥ ተቀምጦባት፣ መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ያያት የወርቅ መሰላል አንቺ ነሽ /ዘፍ.፳፰፡፲፰-፲፱/፡፡ መተርጕማኑ ይህ ምን ማለት እንደኾነ ሲያብራሩ፡- “ከምድር እስከ ሰማይ መድረሷ የልዕልናዋ፣ በላይዋ ላይ ዙፋን ተነጽፎባት ንጉሥም ተቀምጦባት ማየቱ ፱ ወር ከ፭ ቀን በማኅፀኗ ለመሸከሟ፣ መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ማየቱ ደግሞ ጌታችን ከእመቤታችን ሰው ከመኾኑ አስቀድሞ ሰው የጸለየውን ጸሎት ያቀረበውን መሥዋዕት ለማሳረግ አይወጡም አይወርዱም ነበር፤ ጌታችን ከእመቤታችን ሰው ከኾነ በኋላ ግን ለተልእኮ የሚወጡ የሚወርዱ ኾነዋልና ሲል ነው” ይላሉ /ሉቃ.፪፡፲፬፣ ሐዋ.፲፡፫-፬፣ የኦሪት ዘልደትን ትርጓሜ ይመልከቱ/፡፡
ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በአምሳለ ንጉሥ ካየው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
በልጅነታችን ምኑም ሳይገባን በጳጉሜን ሦስት ዝናሙን ጠበል ነው ብለን “ሩፋኤል አሳድገኝ" እያልን ተጠምቀን ነበር:: አሁን ስናድግና መጽሐፍ ቅዱስ ሲገባን ደግሞ ሩፋኤል ማለት የስሙ ትርጉም እግዚአብሔር ፈዋሽ ነው ማለት እንደሆነ ስናውቅ - ቅዱስ ሩፋኤል በቁስል ላይ የተሾመ መልአክ እንደሆነ ስናነብ - የቤተ ሳይዳን ውኃ ያናወጸው መልአክ እንደሆነ ስንረዳ ትናንት ባለማወቅ የተጠመቅነውን ጠበል በደስታ እንጠመቀዋለን::
ልጅ ሆናችሁ "ሩፋኤል አሳድገኝ" ያላችሁ ሁሉ ቅዱስ ሩፋኤልን ያዕቆብ ለቅዱስ ሚካኤል እንደሠጠው ስም "ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ" (ዘፍ. 48:16) ብላችሁ ለመጥራት ውለታ አለባችሁ::
በዚህ ወቅት የታመመ ሰውም ቢኖር የሩፋኤል ዓይነት "... መልአክ ቢገኝለት መጽሐፈ እየራራለት፦ ቤዛ አግኝቻለሁና፡ ወደ ጕድጓድ እንዳይወርድ አድነው፡ ቢለው፥ ሥጋው እንደ ሕፃን ሥጋ ይለመልማል፤ ወደ ጕብዝናውም ዘመን ይመለሳል" ኢዮ. 33:23-25
ይህች በአንድ ወቅት የተጻፈች ስንኝ ነበረች :-
+ ሩፋኤል ይቅር በለኝ +
አሳድገኝ ብዬህ ሮጬ
ከልጆች ጋር ተሯሩጬ
በጠበልህ እየታጠብኩ
የውኃ ጨው እየቀመስኩ
ሩፋኤል አሳድገኝ
እንደ ታላቆቼ አድርገኝ
ብዬ እየጮህኩኝ ስጣራ
ሰምተኸኛል ከልጅ ተራ
ዘንድሮን ግን ተጠለልኩኝ
ጠበል ሲወርድ ተሸሸግሁኝ
ከበረከትህ ሸሸሁኝ
ከቡራኬህ አመለጥኩኝ
ሩፋኤል ሆይ ይቅር በለኝ
ስላበቃ ልጅነቴ
በቆሸሸ ሰውነቴ
በረከሰ ማንነቴ
እንዳላረክስ ጠበልህን
ተጠለልኩት ጥምቀትህን
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጳጉሜን 3 2012 ዓ ም
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
በዓለ ቅዱስ ሩፋኤል
ክፍል አንድ
ጳጉሜን ፪፤ ፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት
በዓለ ቅዱስ ሩፋኤል በጳጉሜን ሦስት ቀን የሚዘከር በዓል ነው፡፡ “ሩፋኤል” የሚለው ስያሜ ትርጉም “ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ” ማለት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከዕብራይስጥ ሁለት ቃላት ጥምረት የተገኘ ቃል ነው፡፡ “ሩፋ” ማለት ጤና፣ ፈውስ፣ መድኃኒት ማለት ሲሆን “ኤል” ሚለው በሌሎቹም መላእክት ስም ላይ የሚቀጸል ስመ አምላክ ነው:: ይህም “መልአኬን በፊትህ እሰዳለሁ፤….. ስሜ በእርሱ ስለሆነ አታስመርሩት” እንዲል፤ (ዘፀ.፳፫÷፳-፳፪)፡፡ በመሆኑም “ሩፋኤል” የሚለው በጥምረት “ከአምላክ ለሰዎች የተሰጠ ፈውስ” የሚለውን ያስረዳል፡፡ “ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ” እንዲል፡፡ (ጦቢት ፲፪፥፲፭) ይህ መልአክ እንደ ሌሎቹ ሊቃነ መላእክት ሁሉ የሰው ልጆችን ይጠብቃቸዋል፡፡
ዠ (ዳን.፬÷፲፫፣ዘፀ.፳፫÷፳፤ መዝ.፺÷፲፩-፲፫) ያማልዳል፤ ከፈጣሪ ያስታርቃቸዋል፡፡ (ሉቃ.፲፫፥፮-፱፣ ዘካ.፩÷፲፪) ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ያለ ማቋረጥ ፈጣሪያቸው ልዑል እግዚአብሔርን ከሚያመሰግኑ ቅዱሳን መላእክት አንዱ ነው፡፡
በተለይም በጳጉሜን ሦስተኛዋ ቀን ቅዱስ ሩፋኤል ዕለት ዓመታዊ ክብረ በዓል የሚታሰብባት ወቅት ናት፤ የተለያየ ትንታኔም ይነገርባታል፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንም ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት አድርገው መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤልን በሰባት መንገዶች ይገልጡታል፡፡
@ortodoxtewadochannal
ጳጉሜን
ጳጉሜን የሚለው ስያሜዋ ግን “ሄፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ መሆኑን አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ተነግሯል፡፡ “ኤፓጉሜኔ” ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ በግእዝ ቋንቋችን ተውሳክ ማለት ነው፡፡ ተውሳክ ማለት ተጨማሪ ማለት ነው፡፡ “ወሰከ - ጨመረ” ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ (ምንጭ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገጽ ፱፻፭)፡፡ ምዕራባዊያኑ ጳጉሜን ተጨማሪ ቀን አድርገዋታል፡፡ እኛ ግን የወር ተጨማሪ አድርገናታል፡፡ በጽርዕ ኤፓጉሜኔ ትባል እንጂ ሊቃውንት ግን ተረፍ ይሏታል፡፡ ጳጒሜን የአሮጌው ዓመት ማብቂያ የአዲሱ ዓመት መንደርደሪያ ዕለት እንደሆነች የክርስቶስ ልደትም የዓመተ ፍዳ ማቆሚያ የዓመተ ምሕረት መጀመሪያ በመሆኑ ዕለታቸው ራሱ በተመሳሳይ ቀን ተቀምሮ ይውላል፡፡
የጳጉሜን ወር ‹‹የምሕረት ወር›› ስለመባሏ፡-
ኢትዮጵያ በዓለም ብቸኛዋ የ፲፫ ወራት ጸጋ ባለቤት ስትሆን የጳጉሜን ወርም በኢትዮጵያውያን ዘንድ የምሕረት ወር ተብሎ ይታመናል። በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ጸሎት የሚያደርግበት ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበት የምሕረት ወር መሆኑን ታስተምራለች፡፡ በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት መሠረት ምእመናኑ በጳጉሜን ጸበል በመጠመቅ ድኅነት በማግኘታቸው የምሕረት ወር መሆኑን ምእመናን ያብራራሉ፡፡
@ortodoxtewadochannal
ብፁዕነታቸው የቤተ ክርስቲያን በዓላት ሲደርሱ ከሥርዓቷ እና ከአስተምሮዋ ውጪ በሆነ መልኩ የተለያዩ አካላት የዳንኪራ ጥሪ በማዘጋጀት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አግባብነት የሌለው መሆኑን እና ምዕመናንም ከዚህ እንቅስቃሴ እራሳቸውን ሊያርቁ ይገባል ነው ያሉት።
የማትደፈረዋን እና የማትነካዋን ቤተ ክርስቲያን የሚነኩ ሰዎች በዝተዋል፤ ቀጣዩ ዓመትም ኢትዮጵያውያን በሰላም በፍቅር የምንኖርበት የሚራቡ የሚፈናቀሉ የሚያዝኑ ሰዎች እንዳይኖሩ ሁሉም ምዕመን ጠዋት ኪዳን ከሰዓት በሠርክ ጸሎት በየአብያተ ክርስቲያን በመሄድ ያልቻለም በየቤቱ ሊጸልይ ይገባል ብለዋል።
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
የጽርሐ ጽዮን ዘተዋሕዶ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም ለ35ኛ ዙር ያሠለጠናቸውን 101 ደቀመዛሙርትን አስመረቀ።
ከ20 አህጉረ ስብከቶች በ21 ቋንቋዎች የሰለጠኑ 69 ሰባኬያነ ወንጌል ከ11 አህጉረ ስብከቶች በ16 የተለያዩ ቋንቋዎች የተማሩ 32 የአብነት ተማሪዎች ተመርቀዋል።
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መሪ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ዮናታን በዩክሬን መንግሥት የአምስት ዐመታት እሥራት ተፈረደባቸው።
ዩክሬንና ሩሲያ መሐል የተነሳውን ግጭት መነሻ በማድረግ የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ከሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እንድትገነጠል መንግሥት ግፊት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል።
ሊቀ ጳጳስ ዮናታን ይህ የመንግሥት ግፊት ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ በመሆኑ እንደማይቀበሉት በመግለጻቸው እሥራቱ ሊፈረድባቸው ችሏል ተብሏል።
አጋጣሚውን በመጠቀም ቤተ ክርስቲያኗን ለመከፋፈል አስቀድሞ በተለያዩ ምክንያቶች ከቤተ ክርስቲያኗ ወጥተው የነበሩ አካላት ተደራጅተው እየተንቀሳቀሱ እንደሆነም ታውቋል።
በአንጻሩ የሁለቱ ሀገራት ጦርነት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ጥሪ ሲያደርጉ የነበሩትና ለቀኖና ቤተ ክርስቲያን መከበር የተሟገቱት ሊቀ ጳጳሱ ግን በቁም እሥር ቆይተው በመጨረሻም ለአምስት ዓመታት እንዲታሰሩ ተፈርዶባቸዋል።
የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከሦስት መቶ ዓመታት በላይ በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ሥር መቆየቷ ይታወቃል።
‹‹መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በሌሊት የተቀደደ ቀሚስ ለብሶ ታየኝ ፤ እኔም ‹ጌታዬ ሆይ ልብስህን ማን ቀደደው?› ብዬ ጠየቅሁት፡፡ ‹አርዮስ ልብሴን ቀደደው ፤ ከባሕርይ አባቴ (ከአብ) ለይቶኛልና ፤ እንዳትቀበለው ተጠንቀቅ› አለኝ›› አላቸው፡፡ ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ በእኔ ደም መፍሰስ የክርስቲያኖች ደም እንደጎርፍ መፍሰሱ ይቁም ብሎ ተስሎ በሰማዕትነት አርፏል፡፡ ጌታችን ‹ልብሴን ቀደደው› ብሎ ለዚህ ፓትርያርክ እንደነገረው የጌታችን የባሕርይ አምላክነት ላይ የክህደት ቃልን የሚናገሩ ሰዎች ሁሉ ሮማውያን ወታደሮች ያልቀደዱትን የክርስቶስን ቀሚስ እንደቀደዱ ይቆጠራል፡፡
ሊቁ ቅዱስ አውግስጢኖስ ደግሞ የጌታችንን ልብስ አለመቀደድ ቤተ ክርስቲያንን ለሚከፋፍሉ ሰዎች ማስተማሪያ አድርጎ ተጠቅሞበታል፡፡ እንደ ሊቁ ትምህርት ያልተቀደደችውና ከላይ ጀምሮ ወጥ የሆነችው ቀሚስ ከዚህ ዓለም ያልሆነችው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ናት፡፡ ለአራት የተከፈለው ደግሞ የምታስተምረው ወንጌል ነው፡፡ ወንጌል ሊከፋፈልና ለዓለም ሁሉ ሊዳረስ ይችላል፡፡ ወንጌል በዘር በቋንቋ በሀገር አይገደብምና የክርስቶስ ወታደሮች የሆኑ ካህናትና መምህራነ ቤተ ክርስቲያን ወንጌልን ተከፋፍለው ለዓለም ማከፋፈል አለባቸው፡፡
አብያተ ክርስቲያናት በየሀገራቱ ቢቋቋሙ ፣ አህጉረ ስብከቶች ቢስፋፉ ፣ ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ካህናት ፣ ዲያቆናት ፣ ሊቃውንት ፣ ሰባክያን በቁጥር በዝተው ፣ በቦታም ተከፋፍለው ቢያገለግሉ እጅግ መልካም ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በሁሉ ጎዳና … ክርስቶስ ይሰበካል ስለዚህም ደስ ብሎኛል›› እንዳለ የመምህራን መብዛት የወንጌል መስፋፋት እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ (ፊል. ፩፥፲፰)
ቀሚሱ የተባለችን ቤተ ክርስቲያንን ከተቃደዷት ግን አደጋ አለው ፤ ‹የሐዋርያት በሆነች በአንዲት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን› ብለን የምንናገርላት ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ቀሚሱ ናት፡፡ በሰው እጅ ያልተሰፋች ፣ ማንምም ሊሠፋት የማይችል ቀሚስ ናት ፤ ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆና በመሠራቷም አትከፋፈልም፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ሊከፋፍሏት የሚፈልጉ ሰዎችን ሊቁ አውግስጢኖስ እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል ፡- ‹‹ሮማውያን እንኳን ያልቀደዱትን የክርስቶስን ልብስ እናንተ ስለምን ትቀድዱታላችሁ?››
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለምን እህተ መላእክት ትባላለች?
እመቤታችን እህተ መላእክት ተብላ ትጠራለች፡፡ ሊቁ አባ ህርያቆስ ‹‹እህተ መላእክት፤ እመ ሰማዕታት፤ ወእግዝዕተ ፃድቃን እያለ ሲጠራት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ደግሞ ‹‹እህተ መላእክት ወእመ ኩሉ ሕዝብ … የመላእክት እህት የህዝቡ ሁሉ እናት›› ብለዋታል፡፡ አባ ህርያቆስም ሆነ አባ ጊዮርጊስ እመቤታችን የሰማዕታት፤ የፃድቃን የህዝቡ ሁሉ እናት ብለው ሲጠሯት እንዴው በራሳቸው ሳይሆን ‹‹እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ (ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል) መዝ (፹፮÷፭) የሚለውን ፍፃሜው ለድንግል ማርያም የሆነውን ቃለ ትንቢት በማስታወስና ‹‹እነኋት እናትህ›› ዮሐ (፲፱÷፪፭) በማለት ጌታችን ድንግልን በዮሐንስ ወኪልነት ከዕፀ መስቀሉ ስር ለተገኙ ክርስትያኖች በእናትነት የሰጠበትን ቃል ኪዳን በማሰብ ነው፡፡ እህተ መላዕክት ሲሏትም በምክንያት ነው፡-
#ከንጽህና_አንፃር
ቅዱሳን መላእክት በባህርያቸው ንፁሐን ንኡዳን ክቡራን ናቸው፡፡ የረከሱ ፍጥረታትን በምልጃቸው ያስምራሉ እንጂ እነሱ ራሳቸው አይረክሱም፡፡ ከሃጢአት ያልተመለሱ ልበ ደንዳኖችን ሊገስጹ አሊያም እንደሰዶምና ገሞራ ሊቀጡ ይላካሉ እንጂ እነሱ ሀጥያት አይሰሩም፡፡ በአምልኮ እግዚአብሔር ፀንተው በምስጋና ተግተው በተሰጣቸው ስፍራ (በኢዮር፤ በራማ፤በኤረር፤ በኢየሩሳሌም ሰማያዊት፣በመንበረ መንግስት ) በንፅህና በቅድስና ዘለአለም እስከ ዘለአለም ይኖራሉ፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንደ መላዕክት በንፅህና በቅድስና ኖራለች፡፡ንፅሕናዋም በሁለት መንገድ ይገለፃል፡፡ አንደኛው ‹‹ ሞት በአንድ ሰው በአዳም ምክንያት ወደ ዓለም ገባ እንዳለ ቅ/ጳውሎስ ሁሉ በአዳምና በልጆቹ ላይ በወረደ መርገመ ሃጥያት(ጥንተ አብሶ) ሲረክስ እመቤታችን ግን ይህ የቀደመ መርገም ያልነካት ንፅህት መሆኗ ነው፡፡ ኢሳ ፩÷፲፱ (የዚህን ምሳሌ በዘመነ ጌዲዮን መ/መሳ ፮÷፴፮ -፵ ይመለከቱ፡፡) 2ተኛው ከሃልዮ ከነቢብ ከገቢር ሀጥያት የነፃች በስጋም በነፍስ ሀጥያት ያላወቃት (ማርያም ድንግል ንፅህተ ስጋ ወነፍስ እንዳለ ደራሲው በመልክአ ማርያም) መሆኗ ነው ፡፡ ይህንንም ቅ/ ገብርኤል (ቡርክት አንቲ እም አንስት… ከሴቶች ሁሉ ተለይተሸ የተባረክሽ ነሽ) በማለት መስክሮላታል፡፡ ይህ ፍፁም ንጽህናዋን አምላክ ተመለከተና በማህፀኗ አደረ በስጋም ወለደችው፡፡ እንግዲህ የድንግል ማርያም ንጽህና እንደ መላዕክቱ የባህርይና ለሁሉም ወገን በመሆኑ በንጽህና ለምትመስላቸው የመላዕክት እህት ተባለች፡፡
#ከግብር_አንጻር
የእግዚአብሔርን የክብር ዙፋን የሚሸከሙ ኪሩብ (በብዙ ኪሩቤል) መላዕክት ናቸው፡፡ እነዚህ መላዕክት እግዚአብሔር ለቅዱሳን እንደታያቸው እሳታዊውን ዙፋን በደመና ይሸከማሉ፡፡ ፯ የእሳት መጋረጃዎች በዙፋኑ ዙሪያ ተከልለዋል፡፡ እመቤታችን በማኅጸኗ ዙፋንነት በሆዷ ያስቀመጠችው ያን ኪሩቤል የሚሸከሙትን እሳተ መለኮት ነው፡፡ በሰማያዊው ዙፋን ፯ የእሳት መጋረጃዎች ጌታን እንደከለሉት በድንግል ማህጸን ዙፋን በተቀመጠ ጊዜ በ፯ቱ ባህርያተ ሰብእ (፫ቱ ባህርያተ ነፍስና ፬ቱ ባህርያተ ሥጋ አምላክነቱን ሰወረ፡፡ በመሆኑም በሰማይ ዙፋኑን ለሚሸከሙ መላዕክት (ኪሩብ) አምላክን ፱ወር ከ፭ቀን በማህጸኗ ዙፋንነት ያስተናገደች እመቤታችን እህታቸው ተባለች፡፡ አንድም መላእክት ዘወትር በዙፋኑ ፊት ቆመው በፍርሐትና በመንቀጥቀጥ ቅዱስ፣ ቅዱስ ፣ቅዱስ እያሉ ያመሰግኑታል፡፡ ይማጸኑታል እመቤታችንም በአማላጅነት በንጉሱ ቀኝ ትቆማለችና እህታቸው ተባለች፡፡ ‹‹ወትቀውም ንግሥት በየማንከ… ንግስቲቱ በቀኝህ ትቆማለች እንዲል›› መዝ.፵፬፡፱
#ከምልጃና_ከመዳን_ሰራ_አንፃር
መዳን በእግዚአብሔር በማመን እና ህጉን ትዛዛቱን በመፈፀም ነው ፡፡ እግዚአብሔርም እንዳንጠፋ ስለሚፈልግ በእርሱ ለምናምን ለእኛ ብዙ የድህነት መንገዶችን ሰጥቶናል ፡፡ ከነዚህ ውስጥ ምልጃ በዋነኝነት ሚጠቀስ ነው፡፡ ድህነት እና ንስሐን በተመለከተ መላእክትንና ድንግልን የሚያመሳስላቸው ነገር አለ፡፡ ሁለቱም የሰው ልጅ በንስሐ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለስ አጥብቀው ይሻሉ፡፡ ተመልሶ ወደ ህፅነ እግዚአብሔር ሲገባም ደስ ይሰኛሉ፡፡ በአንዲት ነፍስ መዳን በሰማይ መላእክት ዘንድ ታለቅ ደስታ እንደሚሆን መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ ድንግል ማርያምም የሰው ልጅ ብቻም ሳይሆን ፍጥረት ሁሉ ቢፅድቅላት ደስ የምትሰኝ ርህርህት እናት ናት፡፡ ስለዚህ ድንግል ማርያምም ሆኑ መላእክት ፍጡራን እንዲድኑ ካላቸው ጽኑዕ መሻት የተነሳ ዘወትር በጌታ ፊት ምልጃን ያቀርባሉ፡፡ ጸሎታቸውም መና የሚቀር ሳይሆን በቅድስናቸው ብዛት ካገኙት ሞገስ የተነሳ እግዚአብሔር የሚሹትን ስለሚፈፅምላቸው ሀይል ያለው ነው፡፡ ያዕ ፭፡፲፮ ስለሆነም ስለዚህ የምልጃና የድህነት ስራ ድንግል ማርያም የመላእክት እህት ተባለች ፡፡
በአጠቃላይ ድንግል ማርያም እህተ መላእክት ስትባል ከላይ ባነሳናቸው ምክንያቶች መሆኑን ልብ ልንል ይገባል፡፡
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
በቅዱስ ያሬድ ላይ ትኩረት ያደረገ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በሚሊኒየም አዳራሽ ሊካሄድ ነው።
++++++++++++++++++++++++++++++++++++
“ስምከ ሕያው ቅዱስ ያሬድ” በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 11/ 2016 ዓ.ም የሚደረገውን ጉባኤው በተመለከተ ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡
በብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ የጅማ፣ የየምና የሰሜን ጎንደር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መልካም ፍቃድና ቡራኬ የሚካሄደው ይህ ጉባኤ በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም ህንጻ አሠሪ ኮሚቴ እና በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት ይዘጋጃል ተብሏል።
በመግለጫው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና አዘጋጆች ተገኝተዋል።
በመግለጫውም ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለሀገራችን ኢትዮጵያም ባለውለታና ታላቅ አስተዋጽኦ ያበረከተ እና መምህር ወሐዋርያ፤ መጻሕፍትን በጣዕመ ዜማ የደረሰ፤ መዝሙረ ዳዊትን ጨምሮ ሌሎችንም ቅዱሳት መጻሕፍትን በዜማው ያመሠጠረ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ሊቅ ነው መሆኑ ተገልጿል።
ቅዱስ ያሬድ የደረሳቸው መጻሕፍትና የዜማ ድርሰቶች የኢ/ያ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አስተምህሮ ከመሆናቸው ባሻገር የቅዱስ ያሬድ ጥልቅ ፍልስፍና፣ የተፈጥሮ ሳይንስ ፣የማኅበራዊ ሳይንስ ፣የክዋኔ ጥበብና የሥነ ውበት ንድፈ ሐሳብ እና የጥበብ መጻሕፍት ናቸውም ተብሏል፡፡
በዚህም ቤተክርስቲያንን በሰማያዊ ጥበብ ሰማያዊት፣ በምድራዊ ጥበቡ ደግሞ ተፈጥሮና ማኅበራዊ ሕይወትን አደላድሎ በውብ ድርሰትና ዜማ ሞሽሯታል፡፡
@ortodoxtewadochannal
🥀አጋፋሪ፤ የድግስ አለቃ ፥ አስተናጋጅ ነገሥታት ግብር ሲያገቡ (ግብዣ ሲጋብዙ ፥ ድግስ ሲደግሱ) ወደ አዳራሹ (ወደ ድግሱ) እንዲገቡ የሚፈቅድ ፥ የማይገባቸውንም የሚከለክል፤ ከገቡም በኋላ እንደ የክብራቸውና እንደየማዕርጋቸው አንተ በዚህ ሁን ፥ አንተ በዚህ ተቀመጥ እያለ የሚያስቀምጥ፤ ኋላ የድግሱ ምግብና መጠጥ መታደል ሲጀምርም፤ እንጀራና ጠጅ አሳላፊዎችን የሚያዝና የሚቈጣጠር ትልቅ ሹም ነውአጋፋሪ፤ የሚለው መጠሪያ በ17ኛወና በ18ኛው ክፍለ ዘመን የታወቀ የቤተ መንግሥት ሹም መጠሪያ ነው፡፡ ‹‹ህዱግ ራስ›› በመባል የሚታወቅም ነው፤ በቤተመንግሥት የሚካሄዱ ሥራዎችንና የፍርድ ሂደቶች ያስተባብራል፤ አንዳንዴ ደግሞ የክፍላተ ሃገር የፍርድ ሰጪ ሰዎች ስም ሆኖም ያገለግላል፤ የስሜን (ከጎንደር በስተሰሜን የሚገኝ ግዛት ነው) አስተዳደር የሚገዛ ሰው ደግሞ የሰሜን አጋፋሪ እየተባለም ይጠራል፤ (ለምሳሌም አፄ ሱስንዮስ ልጃቸውን ፋሲለደስን የስሜን አጋፋሪ ብለው ሹመወት ነበር፤ ይህ የስሜን አጋፋሪ የሚለው ሹመትም እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ቆይቶ ነበር፡፡
#ቡሄ
🥀ቡሄ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጸበት የነሐሴ 13 ቀን መጠሪያ ስሙ ነው የሚሉ ሊቃውንት እንዳሉ ሁሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ፤ ቡሄ የሚባለው፤ ከነሐሴ 13 በኋላ እስከ መስከረም 17 መስቀል ድረስ ሲሆን፤ በተለይም ይህ በዓል የሚታወቀው በሸዋና ወሎ /እስከ ጋይንት ጫፍ መጋጠሚያ) ድረስ ሲሆን፤ በዚህ ወቅትም ክርስትና አባት ለክርስትና ልጁ ተማሪ ከሆነ መጻሕፍትን (ዳዊት፣ …)፣ እንዲሁም አልባሳትን፣ በግና ሙክት ፍየልን የሚሰጥበት ነው፡፡ ሕፃናትና ወጣቱም ‹‹ቡሄ ፥ ሆ ….. ›› እያለ ይጨፍራል ፤ የሚሰጠውንም ሙክትና በግ እስከ መሰቅል ድረስ ሲያጠራቅም ከርሞ ለመስቀል ዕለት አርዶ ይበላል ፥ ደስታ
ያድርጋን ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን ይቆየን።
ቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
#የእሑድ_ውዳሴ_ማርያም_ትርጓሜ
ኹል ጊዜ ንጽሕት የምትኾኚ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ! ስለዚህ ነገር ኹላችን እናከብርሻለን፤ እናገንሻለንም፡፡ ሰውን ከሚወድ ሰው ከሚወደው ከርሱ ይቅርታን እናገኝ ዘንድ ኹል ጊዜ ዓይነ ልቦናችንን ወዳንቺ እንሰቅላለን፡፡
ሸምሸር ሰጢን ከሚባል ከማይነቅዝ (በአምልኮተ ጣዖት ከማይለወጥ) እንጨት የተቀረጸ በአፍአ በውስጥ በወርቅ የተለበጠ ታቦት አካላዊ ቃልን ይመስልልናል /ዘጸ.፳፭፡፱-፳/፡፡ ይህ ንጹሕ የሚኾን፣ መለወጥ የሌለበት እርሱ ባለመለወጡ አለመለወጧን ነገራት፤ ከአብ ዕሪና ባለመለየቱም አለማለየቷን ነገራት (አምላክ ወሰብእ ኾኖ እርሷም እም ወድንግል መኾኗን ነገራት)፡፡ ከጥበብ በሚበልጥ ጥበብም ዘር ምክንያት ሳይኾነው እንደ እኛ ሰው ኾነ፡፡ አበው፡- “ዓለሙን ከፈጠረበት ጥበብ ይልቅ ሰው ኾኖ ዓለሙን ያዳነበት ጥበብ ይበልጣል” የሚሉትም ስለዚሁ ነው፡፡ አደፍ ጉድፍ ሳያገኝሽ መለኮቱን አዋሕዶ ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ሰው ኾነ፡፡ መለኮቱን አዋሕዶ ሰው ከኾነ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡
እግዚአብሔር በፈጠራቸው በኪሩቤል አምሳል፤ ሙሴ የሣላቸው ኪሩቤል የሚጋርዱሽ መቅደሰ ሙሴ አንቺ ነሽ፡፡ አንድም እግዚአብሔር በፈጠራቸው በኪሩቤል አምሳል፣ ሰሎሞን የሣላቸው ኪሩቤል የሚጋርዱሽ መቅደሰ ሰሎሞን አንቺ ነሽ፡፡ ጌታ በማኅፀንሽ ያደረብሽ አማናዊቷ መቅደስ አንቺ ነሽ፡፡ ሳይለወጥ ካንቺ ሰው የኾነው አካላዊ ቃል በውስጥ በአፍአ በነፍስ በሥጋ ኃጢአታችንን የሚያስተሠርይልን ኾነ፡፡ ኃጢአታችንን ከሚያስተሠርይልን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡
መና ያለብሽ መሶበ ወርቅ አንቺ ነሽ /ዘጸ.፲፮፡፴፫-፴፬/፡፡ ይኸውም መና የተባለው ከሰማይ የወረደና ፱ ወር ከ፭ ቀን በማኅፀንሽ የተሸከምሽው ነው፡፡ እርሱም “አበዊክሙሰ መና በልዑ በገዳም ወሞቱ - አባቶቻችሁ በምድረ በዳ መና በሉ፤ ሞቱም” እንዳለው ያይደለ፤ ይልቁንም ለሰው ኹሉ ሕይወት የሚያድል ኅብስት ነው /ዮሐ.፮፡፶/፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በአንቀጸ ብርሃን ላይ፡- “አስተማሰልናኪ ቅድስት ወብፅዕት ስብሕት ወቡርክት ክብርት ወልዕልት በመሶበ ወርቅ ዘውስቴታ ኅብስተ ሕይወት ዘወረደ እምሰማያት ወሃቤ ሕይወት ለኵሉ ዘየአምን ኪያሁ ወይበልዕ እምኔሁ በአሚን ወበልብ ሥሙር ምስለ እለ በየማኑ - የተለየሽና ደግ የኾንሽ የተመሰገንሽና የተባረክሽ የከበርሽና ከፍ ከፍ ያልሽ ሆይ! የሕይወት ኅብስት ባለበት በወርቅ መሶብ መሰልንሽ፡፡ የሕይወት ኅብስትም በቀኙ ካሉ ጻድቃን ጋር እርሱን ለሚያምን በሃይማኖትና ፈቃደኛ በኾነ ልብ ከእርሱ ለሚበላም ኹሉ ሕይወትን የሚሰጥ ከሰማይ የወረደ ነው” ብሏል /ቁ.፯/፡፡ ዳግመኛም አባ ጊዮርጊሥ ዘጋሥጫ፡- ኦ መሶብ ቤተ ልሔማዊት ዘወለደቶ ለኅብስተ ሰማይ ዘኢያብቌልዎ ዝናማት ወዘኢሐፀንዎ አየራት - ዝናማት ያላበቀሉትን አየራት ያላሳደጉትን የሰማዩን እንጀራ የወለድሽው ቤተ ልሔማዊት መሶብ ሆይ” በማለት መስክሯል /አርጋኖን ዘረቡዕ/፡፡ ከአባቶች አንዱም፡- “ድንግል ሆይ! በእውነቱ አንቺ ከታላላቅ ይልቅ ታላቅ ነሽ፡፡ ማኅደረ ቃለ አብ ሆይ! አንቺን ሊተካከል የሚችል ታላቅ ማን ነው? ድንግል ሆይ! ከየትኛው ፍጥረት ጋር አወዳድርሻለሁ? አንቺ ቀድሞ በወርቅ ካጌጠችው የሕጉ ታቦት ይልቅ በንጽሕና ያጌጥሽ ታላቅ ነሽ! እውነተኛውን መና የተሸከምሽ መሶበ ወርቅ አንቺ ነሽ፡፡ መና የተባለውም መለኮት የተዋሐደው ሥጋው ነው” ብሏል፡፡ ኅብስተ ሕይወት ከሚባል ልጅሽ ጸንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
ፅንሰታ ለማርያም
የብሕንሳ ኤጲስ ቆጶስ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ላይ የእመቤታችንን የፅንሰቷን ነገር "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተጺነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ:- ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም ፤በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ" በማለት ተናግሯል፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከመወለዷ በፊት የአባቷ እና የእናቷ ታሪክ እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡ በኢየሩሳሌም አገር የሚኖሩ ኢያቄምና ሐና የተባሉ በጣም ደጋግ ሰዎች ነበሩ፡፡ ልጅ ስላልነበራቸው እጅግ ያዝኑ ነበር፡፡ ወደ ቤተ እግዚአብሔር እየሄዱ እግዚአብሔር አምላክ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ አጥብቀው ይለምኑት ነበር፡፡ መባ ይዘውም ሒደው ለሊቀ ካህናት ሮቤል ሲሰጡት እረሱምሊቀ ካህኑ እንኳ ሳይቀር “እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ያለውን ሕግ በእናንተ ላይ እንዳይፈጸም አድርጎ ልጅ የከለከላችሁ ኃጢአተኛ ብትሆኑ ነውና መባችሁን አልቀበልም” ብሎ በእጅጉ አሳዝኗቸዋል። በሊቀ ካህናቱ እያዘኑና እየተከዙ ሲመለሱ ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ ዛፍ ሥር ተቀምጠው ሳለ ርግቦች ከልጆቻቸው ጋር ሲጫወቱ ተመልክተው “ለእነዚህ ወፎች እንኳ ልጆችን የሰጠህ አምላክ ለእኛስ መች ይሆን ልጅ የምትሰጠን?” ብለው እጅግ አምርረው አለቀሱ፡፡
እንዲሁም ”ልጅ ያልወለደውን ከእግዚአብሔር በረከትን ያጣ ነው‘ እያሉ ያቃልሉት ነበርና በዚህም እያዘኑ እነርሱም ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር ፈጽሞ ይለምኑ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ይኅን በሰሙ ጊዜ “ወንድ ልጅን ወይም ሴት ልጅን ቢወልዱ ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ ሊያደርጉ” ስለትን ተሳሉ፡፡
@ortodoxtewadochannal
#የዓርብ_ውዳሴ_ማርያም_ትርጓሜ
ድንግል ሆይ! የደናግል ኹሉ መመኪያቸው አንቺ ነሽ፡፡ ከእናንተ መካከል “መመኪያነቷ እንዴት ነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡-
፩ኛ) ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ሲል ይመልስልናል፡- “ወበከመ አውፅአ ብእሲ ብእሲተ ዘእንበለ ብእሲት ከማሁ አውፅአት ብእሲት ብእሴ ዘእንበለ ብእሲ ወሀሎ ዕዳ ላዕለ ትዝምደ አንስት፤ ወበእንተዝ ኮነት ፈዳዪተ ዕዳሃ ለሔዋን - ለወንዶች የሚከፈል ዕዳ በሴቶች ላይ ነበረ፤ ያለ እናት ሔዋን ተገኝታ ነበርና፡፡ ስለዚህም የሔዋንን ብድራት ለአዳም ትከፍለው ዘንድ ድንግል ያለ ዘርዐ ብእሲ (ያለ ወንድ ዘር) ክርስቶስን ወለደችው፡፡ አዳም ያለ እናት ሔዋንን ስላስገኘ እንዳይመካ ድንግል ያለ አባት ክርስቶስን ወለደችው፡፡ ድንቅ በሚኾን አንድነት ይህ አንድ የፍጥረት እኩልነት ይታወቅ ዘንድ” /ሃይ.አበ.፷፮፥፳፱/፤
፪ኛ) ቀድሞ ወንዶች ሴቶችን በእናንተ ምክንያት ከገነት ወጣን እያሉ ርስት አያካፍሏቸውም ነበር፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ፡- “ብእሲ ወብእሲት አሐደ እሙንቱ በክርስቶስ - ወንድም ሴትም የለም፤ ኹላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና” ብሎ እስኪያስተምር ድረስ /ገላ.፫፡፳፰/ በሔዋን ምክንያት ከገነት ብትወጡ በእመቤታችን ምክንያት ገነት መንግሥተ ሰማያት ገብታችሁ የለምን? ብለው የሚመኩ ኹነዋልና፤
፫ኛ) ደግሞ ለደናግላን አስበ ድንግልናቸውን (የድንግልናቸውን ዋጋ) ስለምታሰጣቸው ሊቁ “ምክሆን ለደናግል” ብሏታል፡፡
ቅድመ ዓለም የነበረ እርሱ ሰው ኹኗልና (ካንቺ ተወልዷልና) የእኛን ሥጋ ነሥቶ የርሱን ሕይወት ሰጥቶ ከርሱ ጋራ አስተካከለን፡፡ በቸርነቱ ብዛት እንድንመስለው አደረገን /ፊል.፫፥፲-፲፩/፡፡ ከብዙ ሴቶች አንቺ ትበልጫለሽ፡፡ ክብር የክብር ክብር ካላቸው ከብዙ ሴቶች አንቺ ትበልጫለሽ /ሉቃ.፩፥፳፰/፡፡ ንጉሥ በከተማው እንዲኖር ዘጠኝ ወር ካምስት ቀን ማኅፀንሽን ዓለም አንድርጎ ኖሮብሽልና አምላክን የወለድሽ ድንግል ማርያም ሆይ! ልዑል እግዚአብሔር የከተመብሽ ረቂቅ ከተማ ነሽ፡፡ በኪሩቤል በሱራፌል አድሮ የሚኖረው እርሱን በማኽል እጅሽ ይዘሽዋልና ልዑል እግዚአብሔር የከተመብሽ ረቂቅ ከተማ ነሽ፡፡ በቸርነቱ ብዛት ፍጥረቱን ኹሉ በዝናም አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የሚመግበው እርሱ ጡትሽን ይዞ ጠባ፡፡ አንድም ለሰውን (ለመንፈሳውያን) ኹሉ ሥጋውን ደሙን ሰጥቶ የሚመግበው እርሱ ጡትሽን ይዞ ጠባ፡፡ ይኸውም ፈጣሪያችን መድኃኒታችን ነው፡፡ እንሰግድለት እናመስግነውም ዘንድ በሐዲስ ተፈጥሮ በጥንተ ተፈጥሮ ፈጥሮናልና ለዘለዓለሙ ይጠብቀናል /ዮሐ.፮፥፴፯/፡፡ ሰጊድ (አምልኮ) ከሚገባው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፬. ድንግል ማርያም ዕፍረተ ምዑዝ (መዓዛው የጣፈጠ) የተባለ ጌታችንን የወለደች ሙዳየ ዕፍረት (የሽቱ መኖርያ) /፩ኛ ሳሙ.፲፥፩ አንድምታው/፤ ዳግመኛም የማየ ሕይወት (የሕይወት ውኃ የክርስቶስ) ምንጭ ናት /መኃ. ፬፥፲፪ አንድምታው/፡፡ የማኅፀኗ ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውን ኹሉ አድኗልና፡፡ ከእኛ መርገመ ሥጋን መርገመ ነፍስን አጠፋልን፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ፡- “በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ኹሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና” እንዲል /ቈላ.፩፡፲፱-፳/ በመካከል ኾኖ በመስቀሉ አስታረቀን፡፡ ልዩ በኾነ ትንሣኤውም ሰውን ዳግመኛ ወደ ገነት መለሰው፡፡ ከእናንተ መካከል፡- “ልዩ በኾነ ትንሣኤ ሲል ምን ማለቱ ነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡- ከእነ አልዓዛር ትንሣኤ የተለየ መኾኑን ለማሳየት ነው፡፡ ምክንያቱም፡-
፩ኛ) እነ አልዓዛር አስነሺ ይሻሉ፤ እርሱ ግን “ላኖራት ሥልጣን አለኝ፤ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ” ብሎ እንደተናገረ /ዮሐ.፲፥፲፰/ የተነሣው በገዛ ሥልጣኑ ነውና፡፡ በተለያየ ሥፍራ “አብ አንሥኦ (አብ አስነሣው)፤ መንፈስ ቅዱስ አንሥኦ (መንፈስ ቅዱስ አስነሣው)” ቢልም አንድ ነው፡፡ ምክንያቱም ዕሪናቸውን መናገር ነውና፡፡
፪ኛ) የእነ አልዓዛር ትንሣኤ በብሉይ ሥጋ ነው፤ የእርሱ ግን በሐዲስ ሥጋ ነው፡፡
፫ኛ) የእነ አልዓዛር ትንሣኤ ሞትን ያስከትላል፤ የእርሱ ግን ሞትን አያስከትልም፡፡
፬ኛ) የእነ አልዓዛር ትንሣኤ ትንሣኤ ዘጉባኤን ይጠብቃል፤ የእርሱ ግን አይጠብቅምና፡፡
አዳምን ዳግመኛ ወደ ገነት ከመለሰ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፭. አንዳንድ ተረፈ ንስጥሮሳውያን እንደሚሉት ንጽሕት ድንግል ማርያም ላቲ ስብሐትና “ወላዲተ ሰብእ” አይደለችም፤ የታመነች አምላክን የወለደች ናት እንጂ፡፡ የመናፍቃን መዶሻ የተባለው፣ በተለይም የቅድስት ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክነት የካደውን ንስጥሮስን የረታው ቅዱስ ቄርሎስ እሳተ መለኮት አምላክን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኗ የተሸከመች፣ በጀርባዋ ያዘለች፣ በዝናብ አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የፈጠረውን ፍጥረት የሚመግበው አማኑኤልን የድንግልና ጡቶቿን ወተት የመገበችውን የወላዲተ አምላክን ክብር ያልተረዱትን ንስጥሮሳውያን መናፍቃንን ሲወቅስ “ወለዛቲ እንተ መጠነዝ ዐባይ ጾረት መለኮተ እፎ ይከልእዋ እምክብራ ለወላዲተ አምላክ ወላዲተ አምላክኬ ቅድስት ድንግል - ይኸንን ያኽል ታላቅ ኾና መለኮትን የተሸከመችቱን የአምላክ እናት ክብርን እንደምን ይነፍጓታል፤ ይከለክሏታል፡፡ የአምላክ እናት ማለት ድንግል ማርያም ናታ” በማለት የተሰጣትን ክብር በማድነቅ አስተምሯል /ተረፈ ቄርሎስ/፡፡
እንዲህም ስለኾነ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የታመነች የምሕረት አማላጅ ናት፡፡ የዚህ ዓለም ሰዎች አማልዱኝ ቢባሉ ነገር አጽንተው ይመለሳሉ፤ እርሷ ግን “ማእምንት ሰአሊተ ምሕረት - የታመነች የምሕረት አማላጅ ናት” /ዮሐ.፪፥፩-፲፩/፡፡ ሰአሊተ ምሕረት ሆይ! ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ከልጅሽ ዘንድ አማልጅን፡፡ ኃጢአታችንን ከሚያስተሠርይልን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
#የረቡዕ_ውዳሴ_ማርያም_ትርጓሜ
ለምስጋና ሦስተኛ፣ ለፍጥረት አራተኛ ቀን በሚኾን በዚህ ዕለት ከወትሮ ይልቅ መላእክትን አስከትላ እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ምንጻፍ ይነጸፋል፡፡ ከዚያ ላይ ኾናም፡- “ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ ኤፍሬም” ትለዋለች፡፡ እሱም ታጥቆ እጅ ነሥቶ ይቆማል፡፡ ከባረከችው በኋላም ምስጋናዋን “ኵሉ ሠራዊተ ሰማያት ይብሉ ብፅዕት አንቲ…” ብሎ ይጀምራል፡፡
፩. ኵሉ ሠራዊተ ሰማያት ይብሉ ብፅዕት አንቲ ሰማይ ዳግሚት ዲበ ምድር - ከምድር በላይ ያለሽ ኹለተኛ ሰማይ ሆይ! በሦስቱ ሰማያት (በኢዮር፣ በራማ፣ በኤረር) ያሉ መላእክት ንዕድ ነሽ፤ ክብርት ነሽ ይላሉ፡፡ ማርያም የምሥራቅ ደጅ ናት፤ ከእርሷ የጽድቅ ፀሐይ ክርስቶስ ተኝቷልና፡፡ ማርያም ሙሽራዋ ንጹሕ የሚኾን ንጽሕት የሠርግ ቤት ናት፡፡ በሠርግ ቤት የመርዓዊና የመርዓት (የሙሽራና የሙሽሪት) ተዋሕዶ ይደረግበታል፡፡ በእመቤታችንም እንደ መርዓዊና እንደ መርዓት ተዋሕዶ፤ ትስብእትና መለኮት አንድ ኹነዋልና፡፡ በሠርግ አዝማደ መርዓዊና አዝማደ መርዓት አንድ እንዲኾኑባት በእመቤታችንም ምክንያት ሰውና መላእክት፣ ሰውና እግዚአብሔር፣ ነፍስና ሥጋ፣ ሕዝብና አሕዛብ አንድ ኹነዋልና እመቤታችን ንጽሕት የሠርግ ቤት ናት /ኤፌ.፪፡፲፭/፡፡ አባ ሕርያቆስ “አስተንፈሰ ወአጼነወ ወኢረከበ ዘከማኪ፤ ወሠምረ መዓዛ ዚኣኪ ወአፍቀረ ሥነኪ ወፈነወ ኀቤኪ ወልዶ ዘያፈቅር” እንዲል /ቅዳ.ማር.ቁ.፳፬/ አብ ከሰማይ ኾኖ አየ፤ ነገር ግን እንዳንች ያለ ባያገኝ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለውን ልጁን ሰዶ ካንቺ ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ሰው ኾነ፡፡ ተቀዳሚ ተከታይ ከሌለው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት (ክብርት) በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
እዚህ ጋር አንዳንድ ወገኖች የሚያነሡትን ጥያቄ መልሰን እንለፍ፡፡ “ልመናስ ከዚያ በኋላ ስንኳን በሷ (ከበቁ በኋላ) በሌሎችም የለባቸውም፡፡ በቀደመ ልመናዋ የምታስምር ስለ ኾነ እንዲህ አለ እንጂ” ስለተባለ ምሥጢሩን ሳይረዱ “ቅዱሳን በአጸደ ነፍስ አያማልዱም” ለማለት የሚጠቅሱት ወገኖች አሉ፡፡ የዚህ ኃይለ ቃል ትርጓሜ ግን ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የዕብራውያንን መልእክት በተረጐመበት በ፲፫ኛው ድርሳኑ ላይ፡- “ጻድቃን ይረክቡ ኵሎ በአሐቲ ተምኔቶሙ በአሐቲ ስእለት - ጻድቃን አንድ ጊዜ በለመኑት ልመና የሚሹትን ኹሉ ያገኛሉ” እንዳለው /ቁ.፻፶፱/ ቅዱሳኑ በአጸደ ሥጋ ሳሉ እግዚአብሔር አንድ ጊዜ “በስምሽ/ህ ለታረዙ ያለበሰ፣ ሕሙማንን የጐበኘ፣ ዝክርሽ/ህን የዘከረ…” እያለ በገባላቸው ቃል ኪዳን መሠረት በስማቸው የዘከረ፣ በስማቸው ሕሙማንን የጐበኘ፣ የመጸወተ እንደሚምርላቸው የሚያስረዳ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- እግዚአብሔር፣ ዓለምን ዳግም በንፍር ውሃ የማያጠፋትና በየዕለቱ ቀስተ ደመናን የምንመለከተው ፡- “ቃል ኪዳኔንም ለእናንተ አቆማለሁ፤ ሥጋ ያለውም ኹሉ ዳግመኛ በጥፋት ውኃ አይጠፋም፤ ምድርንም ለማጥፋት ዳግመኛ የጥፋት ውኃ አይኾንም” ብሎ /ዘፍ.፱፡፲፩/ ለኖኅ አንድ ጊዜ በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት እንጂ ኖኅ በየዕለቱ እንዲህ ስለሚለምን አይደለም፡፡ “አይለምንም” ሲባል ግን ክብሩን፣ ልዕልናውን፣ መንፈሳዊ ብቃቱን የሚያስረዳ እንጂ ማማለድ አይችልም ለማለት አይደለም፡፡ እንደውም ይህ ኃይለ ቃል ከማማለድ በላይ የኾነ ክብር እንደተሰጣቸው የሚያመለክት ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ ጊዜ ለምኖ በየጊዜው የሚሹትን ማግኘት፤ ዕለት ዕለት እየለመኑ የሚሹትን ከማግኘት በላይ ልዕልናን፣ ክብርን፣ መንፈሳዊ ብቃትን ያሳያልና፡፡ አሁን ቅዱሳንን አማልዱን ስንላቸው አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው ደጋግሞ እንደገለጸው ቃል ኪዳናችሁን አሳስቡልን ስንል ነው /ቅዳ.ማር. ቁ.፻፷፬-፻፸፩ ይመልከቱ/፡፡
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
#የሰኞ_ውዳሴ_ማርያም_ትርጓሜ
ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም እመቤታችን ከባረከችው በኋላ ምስጋናውን የጀመረው #“ፈቀደ እግዚእ…” ብሎ ነው፡፡
፩. በመቅድመ ወንጌል “ወአልቦቱ ካልእ ሕሊና ዘንበለ ብካይ ላዕለ ኃጢያቱ - በኃጢአቱ ከማዘን፣ ከማልቀስ በቀር ሌላ ግዳጅ አልነበረውም” እንዲል ጌታ ፭ ሺህ ከ፭፻ ዘመን በግብርናተ ዲያብሎስ ያዝን ይተክዝ የነበረ አዳምን ነጻ ያደርገው (ያድነው) ዘንድ ወደደ፡፡ ምድራዊ ንጉሥ የተጣላውን አሽከር “ሰናፊልህን (ልብስህን) አትታጠቅ፤ እንዲህ ካለ ቦታም አትውጣ” ብሎ ወስኖ ያግዘዋል፡፡ በታረቀው ጊዜ ግን ርስቱን፣ ጉልበቱን፣ ቤቱን፣ ንብረቱን እንደሚመልስለት ኹሉ ንጉሠ ሰማይ ወምድር እግዚአብሔርም “ጥንቱንም መሬት ነህና ወደ መሬት ተመለስ” /ዘፍ.፫፡፲፱/ ብሎ ፈርዶበት የነበረ አዳምን ይቅር ብሎ ወደ ቀደመ ቦታው ወደ ገነት፣ ወደ ቀደመ ክብሩ ወደ ልጅነት ይመልሰው ዘንድ ወደደ /ሉቃ.፳፫፡፵፫/፡፡
#ሊቁ (ቅዱስ ኤፍሬም) በኦሪ. ዘፍ ፫፥፱ ያለውን ኃይለ ቃል ሲተረጕምም እንዲህ ይላል፡- “ቸር ወዳጅ የኾነው እግዚአብሔር አዳምና ሔዋን ወዲያው እንደተሳሳቱ ፍርዱን አላስተላለፈባቸውም፤ ታገሣቸው እንጂ፡፡ ይኸውም ምኅረት ቸርነቱን ይለምኑት ዘንድ ነው፡፡ እነርሱ ግን አልለመኑትም፡፡ እግዚአብሔርም ምንም ሳይናገራቸው በገነት ውስጥ በእግር እንደሚመላለስ ሰው ኾኖ በድምፅ ብቻ መጥራቱን ቀጠለ፡፡ አዳምና ሔዋን ግን አሁንም አልመለስ አሉ፡፡ በመጨረሻም አምላክ ድምፁን ማሰማት ጀመር፡፡ ‘አዳምን ወዴት ነህ?’ ይላቸው ጀመር፡፡ አስቀድሞ በእግር እንደሚመላለስ ሰው ኾኖ በድምፅ ብቻ መጥራቱ መንገድ ጠራጊው ዮሐንስን እንደሚልክላቸው፣ ቀጥሎ ድምፅ አሰምቶ ወዴት ነህ ብሎ መፈለጉም ወልደ እግዚአብሔር ራሱ በተዋሕዶ ፍጹም ሰው ኾኖ ሊያድናቸው እንደ ፈቀደ ያጠይቃል” ይላል /St. Ephrem the Syrian, Commentary on Genesis/፡፡
#ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ኦሪት ዘልደትን በተረጐመበት በ፲፯ኛው ድርሳኑ ላይ፡- “በዚህ ንግግሩ የእግዚአብሔር ከአእምሮ የሚያልፈውን ፍቅሩን እንመለከታለን፡፡ አንድ አባት ልጁ የማይረባውን ነገር በማድረግ ከክብሩ ቢዋረድም አባቱ እጅግ እንዲወደውና ወደ ቀደመ ክብሩ ይመልሰው ዘንድ እንዲደክም፤ እግዚአብሔርም ከሰው ልጆች ጋር ይህን የመሰለ ፍቅር ሲያሳይ እናስተውላለን፡፡ አንድ ሐኪም ወደ ታማሚው አልጋ ጠጋ ብሎ በሽተኛውን እንዲጠይቀውና አስፈላጊውን ኹሉ እንደሚያደርግለት፣ ሰው ወዳጁ እግዚአብሔርም ወደ አዳም ጠጋ ብሎ ሲያነጋግረው እንመለከታለን” ይላል፡፡
ዳግመኛም #በሌላ አንቀጽ “አዳም ሆይ ወዴት ነህ” ማለቱ፣ ለአቅርቦት መኾኑን ሲገልጥ፡- “አዳም ሆይ! ምን ኾንክብኝ? በመልካም ቦታ አስቀምጬህ ነበር፤ አሁን ግን ቦታህ ተለወጠብኝ፡፡ ብርሃን ተጐናጽፈህ ነበር፤ አሁን ግን ጨለማ ውስጥ አይሃለሁ፡፡ ልጄ! ወዴት ነህ? ይህ ኹሉ እንደምን ደረሰብህ? በአንተ ውስጥ ያኖርኩት መልኬ ማን አበላሸብኝ? በዚህ ያህል ፍጥነት የጸጋ ልብስህን ገፎ የጽልመት ልብስ ያከናነበህ ማን ነው? ውዴ! ባለጸጋ አድርጌ ፈጥሬህ አልነበረምን? ታድያ አሁን ድኽነት ውስጥ የከተተህ ማን ነው? ያን የግርማ ልብስህን ሰርቆ ዕራቆትህ ትኾን ዘንድ ያደረገህ ማን ነው? እኮ የጸጋ ልብስህን እንድታጣ ያደረገህ ማን ነው? ይህን የመሰለ ቅጽበታዊ መለወጥ ከወዴት መጣብህ? የከበረ ዕንቁህን እንድትጥል ያደረገህ ምን ቢገጥምህ ነው? አክብሮ በተወደደ ቦታ ካስቀመጠህና ኹል ጊዜ በስስት ዐይን ሲያነጋግርህ ከነበረው አምላክህ ተደብቀህ እንድትሸሸግ ያደረገህ ምንድነው? ማንም የወቀሰህ ሳይኖር፣ እንዲህ እንዲህ አድርገህ በድለሃል ብሎ የመሰከረብህ ሳይኖር ይህን ያህል በፍርሐት መናጥ ከወዴት አገኘህ?” ይላል /Daily Readings of St. John Chrysostom/፡፡
#ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ሆይ! ፭ ሺሕ ከ፭፻ ዘመን በግብርናተ ዲያብሎስ የነበረ አዳምን ነፃ ካደረገው ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡ #“ቅድስት” ማለቱ ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት ልዩ ሲል ነው፡፡ ይኸውም፡-
· ሌሎች ሴቶች ከነቢብ ከገቢር ቢነጹ ከሐልዮ አይነጹም፡፡ እሷ ግን የዕንቆራው #ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ቴዎዶጦስ “ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ ድንግል በሕሊናሃ ወድንግል በሥጋሃ- ከፈጠራት ጀምሮ በምንም በምን (በሕሊናዋም በሥጋዋም) ከድንግልናዋ አልተለወጠችም” /ሃይ.አበ.፶፫፡፳፪/ እንዲል ከነቢብ፣ ከገቢር፣ ከሐልዮ ኃጢአት ንጽሕት ናትና፡፡
· #ጽንዕትም አለ፡፡ ሌሎች ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው፤ ኋላ ተፈትሖ አለባቸው፡፡ እሷ ግን ቅድመ ፀኒስ ጊዜ ፀኒስ፤ ቅድመ ወሊድ፣ ጊዜ ወሊድ፣ ድኅረ ወሊድ ጽንዕት (ወትረ ድንግል) ናትና፡፡
· #ክብርትም አለ፡፡ ሌሎችን ሴቶች ብናከብቸው ጻድቃንን፣ ሰማዕታትን፣ ጳጳሳትን፣ ሊቃውንትን ወለዱ ብለን ነው፡፡ እሷን ግን ወላዲተ አምላክ ወልዳልናለች ብለን ነውና፡፡
· #ልዩም አለ፡፡ እናትነትን ከድንግልና፣ አገልጋይነትን ከእናትነት፣ ወተትን ከድንግልና ጋር አስተባብራ የተገኘች፤ በድንግልናም እያለች ከጡቶቿ ወተት ተገኝተው በዝናም አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የሚመግብ መጋቤ ፍጥረታት አምላክን የወለደች፤ እሳታውያን የሚኾኑ ኪሩቤል ሱራፌልም በፍርሐት በረዐድ ኹነው ዙፋኑን የሚሸከሙት እሳተ መለኮት ጌታን ፱ ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመች፣ በክንዷ የታቀፈች፣ በዠርባዋ ያዘለች ከእመቤታችን በቀር ሌላ ሴት የለችምና፡፡
#“ለምኚልን” ሲልም ልክ በዚህ ምድር እንደነበረው ዓይነት ልመና ከዚያ በኋላ ኖሮባት አይደለም፡፡ ስንኳን በሷና በሌሎችም የለባቸውም፡፡ በቀደመ ልመናዋ የምታስምር ስለ ኾነ እንዲህ አለ እንጂ፡፡ ይኸውም በቃል ኪዳኗ ማለት ነው፡፡ አንድም በቁሙ ይተረጐማል፡፡ ማዘከር (ማሳሰብ) አለና፡፡
#“ሰአሊ ለነ ቅድስት” የሚለው ቅዱስ ኤፍሬም የተናገረው አይደለም፡፡ “ታድያ ይህን የጨመረው ማን ነው?” በሚለው ላይም ኹለት ዓይነት አመለካከለት አለ፡፡ “ቅዱስ ያሬድ ለዜማ መከፈያ ተናግሮታል” የሚሉ አሉ፤ “የኋላ ሊቃውንት ተናግረውታል” የሚሉም አሉ።
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
@ortodoxtewadochannal @ortodoxtewadochannal