በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቀ አስተምህሮ ✝መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር ይቀሰቀስኛል ለስሙ አንድዘምር🔔 የማንቂያ ደዉል🔔🔔 ክርስትና ዘር የለውም
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፳፬)
ለባለፉት ጥቂት ወራት ያረጋል አበጋዝ የተባለ ሰው በጻፈውና “መድሎተ ጽድቅ” በተባለው መጽሐፉ ላይ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምላሾችን እየሰጠን መኾናችን ይታወሳል፤ ዛሬም የዚያን ተከታዩን ክፍል እናቀርባለን። በባለፉት ጊዜያት፣ የ“መድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊ፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን በተደጋጋሚ የሚቃወምበትንና የሚጥስበትን መንገድ እያሳየን መቆየታችን ይታወሳል። አንዳንድ ቦታዎች ላይ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ተቀባይ ቢመስልም፣ ነገር ግን በሌላ ትምህርት ደግሞ ያንኑ የተቀበለውን እውነት መልሶ ሲክድና በሌላ ትምህርት ሲቃወም እንመለከተዋለን፤ ለምሳሌም፦
1.3. መጽሐፍ ቅዱሳዊውን እውነት “እያመነ” ይክዳል፦ ስለ መጽደቅ ሲናገር፦ “ሰው ያለ እምነት፣ ያለ ምስጢራት፣ … ስለ ጾመ፣ ስለ መጸወተ … ብቻ ይጸድቃል አንልም።[1] “መዳን በእምነት ብቻ” የሚለው ኑፋቄ ነው” ይላል።[2] በሌላ ስፍራ ደግሞ፣ “ለመዳን ወሳኝ ነገሮች ማወቅና ማመን” እንደ ኾነ ይናገራል።
የ“መድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊ፣ በተደጋጋሚ በጻፈው መጽሐፉ ውስጥ የሚጠላው ወይም የማይፈልገው ወይም በግልጥ ሲክድ የምንመለከተው ነገር ቢኖር፣ “መዳን በክርስቶስ ብቻ ነው ወይም ማዳን የእግዚአብሔር ብቻ ነው” ብሎ ሙሉ ለሙሉ መቀበል አይፈልግም። ከክርስቶስ የመስቀል ሥራ በተጨማሪ ምስጢራትም የክርስቶስ የመስቀል ሥራ ያህል ተቀባይነት እንዲኖራቸው ብርቱ ጥረት ይጥራል።
አንድ ጊዜ፣
“ሰውን ሊያድነው የሚችለው እውነተኛና ዘለዓለማዊ መድኃኒት ራሱ እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን እንዲሁም ይኽ ሰውን የማዳን ጉዳይ ከራሱ ከእግዚአብሔር በቀር በሌላ በማንም የማይፈጸምና ለማንም የማይቻል … ነው”[3]
እንዲሁም፣
“የወደቀውንና የሞተውን የሰውን ልጅ ያዳነው የእግዚአብሔር ቸርነት እንጂ የሰው የራሱ ሥራ አይደለም። ሰው በሥራው ብቻ የሚጸድቅ ቢሆን ኖሮ በብሉይ ኪዳን የነበሩ ደጋግ አባቶች ለመዳን ክርስቶስ ባላስፈለጋቸው ነበር። … እኛን ያዳነን የእግዚአብሔር ቸርነት እንጂ ሥራችን አይደለም።”[4]
ይልና፣ መልሶ ደግሞ፣
“ለድኅነት ወሳኝና አስፈላጊ የኾኑ ምሥጢራትን መፈጸም ይገባል።”[5]
በማለት ያለ ምስጢራት ክርስቶስ ብቻውን በቂ አይደለም በማለት ይወላውላል። እንዲያውም በክርስቶስ ማመን መሠረት እንጂ መጨረሻ እንዳልኾነ ደፍሮ ሲናገር እንሰማዋለን። ምስጢራት የክርስቶስን ማዳን ረጂ ወይም ደጋፊ ነገሮች እንደ ኾኑ የሚያስረዳበት መንገድ ለመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን ፈጽሞ የማይታዘዝ መኾኑን በትክክል ያሳያል። ይኸንኑ ለማጽናትም፣ የጥምቀትን ውኃ “የድኅነት ውኃ” በማለት እስከ መጥራት ይደርሳል።[6]
ለዚህም ዋቢ ሲጠቅስ፣ ቆርኔሌዎስ ለመዳን ቅዱስ ጴጥሮስና ቆርነሌዎስ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድና በቤተ ክርስቲያንም ተገኝተው ምስጢራት መፈጸም እንደ ተጠበቀባቸው አስቂ በኾነ መንገድ ያቀርባል። በዚህ ዋቢው “የመድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊ ግልጥ ውሸት ይዋሻል፤ ጴጥሮስም ኾነ ቆርነሌዎስ ወደ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ሄደው ምስጢራት መፈጸማቸውን የሚያመለክት አንድም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የለም።
ይልቁን፣ ቆርነሌዎስ እንደ አሕዛብ-አይሁዳዊ ይፀልይ፣ ምጽዋት ያደርግ፣ እግዚአብሔርን ይፈራ፣ በብዙ ሰዎችም ዘንድ በመልካምነቱ የተመሰከረለት ሰው ነበር እንጂ የመዳንን ወንጌል ሰምቶ፣ በክርስቶስ አምኖ፣ የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት አልተጠመቀም ነበር፤ ነገር ግን ቅዱስ ጴጥሮስ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ከሰበከውና በክርስቶስ ኢየሱስ ባመነ ጊዜ የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት ተጠምቆ የእግዚአብሔር ልጅነትን አገኘ፤ ከመንፈስ ቅዱስ ከተጠመቀ በኋላ ደግሞ ሰዎች ኹሉ እያዩት በውኃ ተጠመቀ፤ (ሐ.ሥ. 10፥28-42)።
በቅዱስ ቆርነሌዎስ የመዳን ሕይወት ውስጥ፣ ቀዳሚው ነገር እርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ ቤዛነት ማመኑ ነው፤ እንዳመነ ወዲያውኑ በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ተጠመቀ፤ ከዚያም በኋላ በውኃ ተጠመቀ፤ ቅዱስ ቃሉ “… በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት እንዲቀበል ነቢያት ሁሉ ይመሰክሩለታል።” (ሐ.ሥ. 10፥43) ብሎ እንደ ተናገረው፣ ቆርነሌዎስ የዳነውና መዳንን የተቀበለው ይህን የቅዱስ ጴጥሮስን ቃል በማመን ክርስቶስን በመቀበሉ በስሙም የኃጢአትን ስርየት በማግኘቱ ብቻ ነው።
ከዚህ ባሻገር እኒህን እውነቶች እያመነ መልሶ ይክዳል፣ ይህ ብቻ ሳይኾን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት በምልዓት ሳይኖረው በድፍረት የሚናገራቸው ብዙ ነገሮች አሉት፤ እኒህም፦
· አስቀድሜ እንደ ተናገርኹት፣ ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አንዳች ዕውቀት ስለሌለው፣ ስለ ውኃ ጥምቀት ብቻ ይናገራል፣
· ክርስቶስን በማመን የሚገኘውን የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀትና ሙላት፣ እርሱ ግን በቅብዐ ሜሮን አማካይነት እንደሚገኝ ወይም እንደምንታተም በድፍረት ይናገራል። የ“መድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊ፣ የሚያትመው መንፈስ ቅዱስ እንደ ኾነ ቢያምንም ምልሶ ግን ይክዳል።[7]
እንግዲህ ይህንና ሌሎችንም እውነቶች በግልጥ በመካድ፣ የ“መድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊ፣ ለመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣንና እውነት የማይታመን መኾኑን እናስተውላለን። ጌታ መንፈስ ቅዱስ ልቡን እንዲያቀናለት እንማልዳለን!
ይቀጥላል …
[1] ገጽ 185
[2] ገጽ 183-184
[3] ገጽ 92 እና 93 (አጽንዖት የእኔ)፤
[4] ገጽ 121
[5] ገጽ 126
[6] ገጽ 137
[7] ገጽ 146
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
✝††† እንኳን ለአባታችን ቅዱስ ብስንድዮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን✝። †††
††† ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!✝ †††
††† ✝ቅዱስ ብስንድዮስ ጻድቅ✝ †††
††† ቅዱስ ብስንድዮስ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ድንቅ ሥራ ከሠሩት እንደ አንዱ ሆኖ ይዘከራል:: ቅዱሱ ግብጻዊ ሲሆን በልጅነቱ ወደ ትምሕርት ቤት ገብቶ ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምሯል:: የሚገርመው የብሉይም ሆነ የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትን በሙሉ ያጠናቸው በቃሉ ነበር::
በእርግጥ ይሕንን ማድረግ የቻሉ በርካታ የሃገራችን ሊቃውንት ዘንድሮም አሉ:: ልዩነቱ ግን ወዲህ ነው:: ቅዱስ ብስንድዮስ መጻሕፍቱን ያጠናቸው ለሕይወት እንጂ ለእውቀት አልነበረምና ሁሌም ነግቶ እስከ ሚመሽ እያንዳንዱን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እያጣጣመ ይጸልይ ነበር:: ይሕንን ሲያደርግ ደግሞ
ባጭር ታጥቆ
ጫማውን አውልቆ:
በባዶ ሆዱ ቁሞ ነው::
ታዲያ እያንዳንዱን የመጽሐፍ ክፍል ሲጸልይ ነቢይ ቢሆን ሐዋርያ ወደ እርሱ ይወርድለት ነበር:: ለምሳሌ ዘፍጥረትን ሲጸልይ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ይመጣና ከፊቱ ተቀምጦ ይሰማዋል:: ትንቢተ ኢሳይያስ ላይ ሲደርስ ኢሳይያስ: ወንጌለ ማቴዎስ ላይ ሲደርስ ቅዱስ ማቴዎስ ይመጡና ደስ እያላቸው ያደምጡት ነበር::
አንዱ ነቢይ: ወይ ሐዋርያ ሲወጣ ቅዱስ ብስንድዮስን ባርኮ ሌላኛውን ተክቶ ነው:: በዚህ ምክንያት የቅዱሱ ሕይወት በምድር እያለ ሰማያዊ ሆነ: ሰማንያ አንዱን አሥራው መጻሕፍት የጻፉ ቅዱሳንን ለማየት በቃ:
በእጆቻቸውም ተባረከ::
የቅዱስ ብስንድዮስ ቀጣይ የሕይወቱ ተግባር ብሕትውና ሆነ:: ዓለምንና ግሳንግሷን ትቶም ወደ በርሃ መነነ:: በአጽንዖ በዓት:
በጾምና በጸሎት:
በትሕርምትም ተጋደለ:: በየደረሰበት ቦታ ሁሉ እግዚአብሔር በእጆቹ ድንቅ ተአምር ይሠራ ነበር:: ብዙ ድውያንን ፈወሰ: አጋንንትንም ከአካባቢው አሳደደ::
በእነዚህ ሁሉ ጊዜያት ግን ስዕለት ስላለበት ሴቶችን ላለማየት ይጠነቀቅ ነበር:: በሆድ ሕመም ትሰቃይ የነበረችና ጥሪቷን በመድኃኒት የጨረሰች አንዲት ሴት ስለ ቅዱሱ ዝና ትሰማለች:: ችግሩ ግን እርሱ ከውዳሴ ከንቱና ከሴት የሚርቅ ነውና እንዴት ብላ ታግኘው? አንድ ቀን ከበዓቱ አካባቢ ተደብቃ ውላ ሲመጣ የልብሶቹን ዘርፍ ለመንካት በእምነት አሰበች::
ልክ ከበዓቱ ሲዘልቅ ስሉጥ(ፈጣን) ነበርና ገና እንዳያት ሩጦ አመለጣት:: እንዳትከተለው ድውይ ናትና አልቻለችም:: አዝና ዝቅ ስትል ግን የረገጠውን ኮቲ ተመለከተች:: በፍጹም ልቧ: በእምነት "የጻድቁ አምላክ ማረኝ" ብላ ከአፈሩ ቆንጥራ በላች:: ደቂቃ አልቆየችም:: ፈጥና ከደዌዋ ዳነች:: እንደ እንቦሳ እየዘለለች ወደ ከተማ ሔዳ ተአምሩን ተናገረች::
ከእነዚህ ዘመናት በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ ቅፍጥ(Qift) በምትባል ሃገር ጵጵስናን (እረኝነትን) ተሹሟል:: ወደ ከተማ ሲገባ የቀደመ ተጋድሎውን ቸል አላለም:: ይልቁኑ ይተጋ ነበር እንጂ:: ከብቃት መዓርግ ደርሷልና ሲቀድስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገሃድ ያየው: ሠራዊተ መላእክትም ይከቡት ነበር::
ሕዝቡ ሊቆርቡ ሲመጡ የእያንዳንዱ ኃጢአት በግንባራቸው ተጽፎ ይታየው ነበር:: የበቁትን እያቀበለ: ያልበቁትን እየመከረና ንስሐ እየሰጠ ይመልሳቸዋል:: እንዲሕ በጽድቅ: በሐዋርያዊ አገልግሎትና በንጽሕና ተመላልሶ ቅዱስ ብስንድዮስ በዚህች ቀን ዐርፏል::
ቅዱስ ብስንድዮስ ካረፈ በኋላ ደቀ መዝሙሩ ከመግነዙ ጥቂት ቆርጦ አስቀርቶ ብዙ ድውያንን ፈውሶበታል::
††† ቸር አምላክ ለአባቶቻችን የሰጠውን ጸጋ ለእኛ ለባሮቹም አይንሳን:: ከቅዱሱ በረከትም ያድለን::
††† ሐምሌ 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ብስንድዮስ ሊቅ ወጻድቅ
2.ቅዱስ አሞን ሰማዕት (ዘሃገረ ጡህ)
††† ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት
3.ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5.አሥራ ሦስቱ ግኁሳን አባቶች
6.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
7.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ
††† "አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር:: ከማን እንደተማርኸው ታውቃለህና:: ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳት መጻሕፍትን አውቀሃል:: የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጐ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምሕርትና ለተግሣጽ: ልብንም ለማቅናት: በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል::" †††
(፪ጢሞ. ፫፥፲፬)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
በትግራይ ክልል የተከሰተውን ወቅታዊ የቀኖና ጥሰት አስመልክቶ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት አስተዳደር ጉባኤ መግለጫ ሰጠ፡፡
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት አስተዳደር ጉባኤ
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በሚመሩት ሰላም ልዑክ በትግራይ ክልል ከሚገኙ ጳጳሳትና ምእመናን ጋር ሊካሄድ ሞክሮ ባልተሳካው የሰላም ጥረትና ያንን ተከትሎ በዚያ የሚገኙ አባቶች ከሕገ ቤተክርስቲያንና ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጭ በሆነ መንገድ 10 ኤጰስ ቆጶሳትን እንሾማለን የሚል ይፋዊ መግለጫ መስጠታቸውን አስመልክቶ በመወያየት መግለጫ ሰጥቷል፡፡
1, የችግሩ አሳሳቢነት ሁሉን አህጉረ ስብከት ለአደጋ የሚያጋልጥን የቤተክርስቲያኒቱን አንድነትና ሉዓላዊነት የሚፈታተን፣ የቤተክርስቲያኒቱ ማዕከላዊ የመንበረ ፕትርክና መዋቅር የሚንድ አድራጎት እንደመሆኑ መጠን ሁሉም አህጉረ ስብከት ድርጊቱን በመቃወም የሰላም ጥሪ እንዲያስተላልፉ እንዲደረግ፣
2. የክልሉ ተወላጅ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና በመንበረ ፓትርያርክ የሚገኙ ሊቃውንት ቤተክርስቲያን የድርጊቱን ኢ ቀኖናዊነት በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት አስመልክቶ በክልሉ ቋንቋ ተደጋጋሚ የሆነ ቀኖና ቤተክርስቲያንን የሚያስጠብቅ አንድነትና ሰላምን የሚያመጣ በትምህርት በቤተክርስቲያኒቱ ሚዲያ እንዲያስተላልፉ፣
3. በየደረጃው ያሉ የቤተክርስቲያኒቱ የሥራ ኃላፊዎች፣ ሊቃውንተ ቤተርክስቲያን እና ምዕመናንና ምዕመናት እንዳሁን ቀደሙ ሁሉ በአንድነትና በኅብረት በመቆም ድርጊቱን እንዲቃወሙና በማዕከል ደረጃ የሚተላለፉትን ውሳኔዎች ተግባራዊ በማድረግ ለቤተክርስቲያኒቱ አንድነትና ሉዓላዊነት የበኩላቸውን አስተዋጾ እንዲያደርጉ ፤
@ortodoxtewadochannal
#ለሲኖዶሳዊ_ልዕልና_መከበር_የምእመናን_ድርሻ_አስፈላጊ_ነው!
ክፍል ፩
ሐምሌ ፲፩፤ ፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ቤተ ክርስቲያን የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና አለመከበር እንዲሁም በርካታ ምእመናን በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ጉዳዮች ባይታዋር የሆኑበት፣ ቤተ ክርስቲያኗን ለካህናቱና ጳጳሳቱ ብቻ እየተው የመጡበት ሁኔታ ይታያል፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስትያንን ፖለቲከኞች፣ አማሳኞች፣ ምንደኞች አገልጋዮች እንዲሁም የውስጥም ሆነ የውጭ ጠላቶቿ አጀንዳ ሲያደርጓት፣ ባልዋለችበት ሲያውሏት፣ የማይገልጻትን ጥላሸት ሲቀቧት፣ ታሪኳን ሲሰርዙ፣ ሲደልዙ፣ የፕሮፖጋንዳ ሰለባ ሲያደርጓት፣ በባሰ ሁኔታ ኵላዊትነቷን፣ ዓለማቀፋዊነቷን ወደ ጎን በማለት በርካሽ የጎሳ ከረጢት ሊከቷት ሲሞክሩ እያዩ ዝም ማለታቸው ነው፡፡
ስለዚህ ቤተ ክርስቲያኗ ክብሯ ተጠብቆ ሲኖዶሳዊ ልዕልና እንዲከበርና በአገልግሎቷና በአስተዳደርዋ ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲመጣ የምእመናን ተሳትፎ ያስፈልጋል፡፡
ይህ ጽሑፍ ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና የምእመናንን ግንዛቤ ለማሳደግ ታስቦ የቀረበ ነው፡፡
፩.፩. ቅዱስ ሲኖዶስ ማለት ምን ማለት ነው?
ሲኖዶስ ቃሉ የጽርዕ ቋንቋ ሲሆን ትርጉሙም ስብሰባ (ጉባኤ) ማለት ነው፡፡ አንድ/ቃለ ዓዋዲ፣ ሀብታችንና ሥርዓቱ/ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት/
ቤተ ክርስቲያናችን በሕግና በሥርዓት እንድትመራ ልዩ ልዩ መመሪያዎች ተሰጥተዋታል፡፡ የመመሪያው ባለቤትም ራሱ መሥራቿ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፡፡ ‹‹በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቋት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው እና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ›› በማለት አደራ የሰጣቸው የሐዋርያት ተከታዮች የሆኑ ሊቃነ ጳጳሳትን ነው፡፡ (፪ኛ የሐዋ.ሥራ ፳፥፳፰) የጳጳሳቱ አንድነት ጉባኤ /ስብስብ /ደግሞ ሲኖዶስ ይባላል፡፡
፩.፪. የቅዱስ ሲኖዶስ ታሪካዊ አመጣጥ፡-
በብዙ ታሪኮች ላይ እንደ መጀመሪያ ሲኖዶስ ጉባኤ ተመዝግቦ የሚገኘው በ፶ ዓ.ም በኢየሩሳሌም የተደረገውን ጉባኤ ነው፡፡ ጉባኤውም በሐዋርያት የተደረገ ስብሰባ ሲሆን መሪውም የኢየሩሳሌሙ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ያዕቆብ እንደነበረና የስብሰባው ምክንያትም ከአይሁድ ወደ ክርስትና የመጡት እና ከአሕዛብ በመጡት መካከል በነበረው አለመግባባት ላይ ለመምከር ነበር፡፡ (የሐዋ.ሥራ ፩፥፲፭) ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በርካታ ስብሰባዎች ተደርገዋል፤ በርካታ ሥርዓቶች እና ሕግጋት ለቤተ ክርስቲያን ተደንግገውበታል፡፡ በዚህም ሲኖዶስ እየተባሉ የሚጠሩ እና እስካሁን ቤተ ክርስቲያን የምትመራባቸው ሕጎች ወጥተውበታል፡፡ በኋላም በብዙ ዓለም አቀፍ ጉባኤያት /ኒቅያ፣ ቍስጥንጥንያ፣ ኤፌሶን ወዘተ/ ዳብረውና ጸንተው የተላለፉ ውሳኔዎች አሉ፡፡ ፍትሐ ነገሥት ዋናውና ትልቁ ሲሆን በርካታ የሐዋርያት ሲኖዶስ ውሳኔዎችና ሌሎች ሕጎችን ይዟል፡፡
፩.፫. የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ተግባርና ኃላፊነት ፡-
ቅዱስ ሲኖዶስ ከላይ እንደተገለጸው በዓመት ሁለት ጊዜ እየተሰበሰቡ የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ አጀንዳ አድርገው እንዲወያዩ ሥርዓት ተሠርቷል፡፡ (ፍ/መ. ፭፥፻፷፭) ይህም ሥርዓት እስካሁን ቀጥሏል፡፡ የስብሰባውም ምክንያት
✍️ ሃይማኖትን ለማጽናት፣ ምግባርን ለማቅናት
✍️ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለማስፋት፣ ምእመናንን ለማብዛት
✍️ መናፍቃንን /ከሐድያንን ለመለየት፣ ሕግንና ሥርዓትን ለማውጣት ብሎም ለማስፈጸም
✍️ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሁለንተናዊ አንድነት ለማጽናትና ሁለንተናዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ መብቷን ለማስከበር አስተምህሮዋን ለማስፋት እና ለማስቀጥል የሚደረጉ ስብሰባዎች ሲኖዶስ እየተባሉ ይጠራሉ፡፡
ምክንያቱም ተሰብሳቢዎቹ ‹‹አደራ ጥብቅ ሰማይ ሩቅ›› እንዲሉ አበው አደራቸውን ለመወጣት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅ፣ ለመንጋው መራራትና ለራሳቸው መጠንቀቅ የተሰጣቸው አደራ ነውና፡፡ (የሐዋ. ሥራ ፳፥፳፰) ዋጋቸውንም በሰማይ ይቀበሉ ዘንድ፡፡ አንድም መክሊታቸውን ቀብረው ክፉ አገልጋይ (ማቴ.፳፭፥፳፬) ተብለው እንዳይፈረድባቸው ተግተው በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ይሠራሉ፡፡
፩.፬. የቅዱስ ሲኖዶስ የክብሩ/የልዕልናውና መገለጫ፡-
ቅዱስ ሲኖዶስ ክብሩ ከፍ ያለ ነው፤ ልዕልናውም እጅግ ታላቅ ነው፤ ቅዱስም ነው፤ ቅድስናው፣ ልዕልናው ክብሩ እንዲሁ አይደለም፤ ምክንያቱም
ሀ. መሪው ሰብሳቢው መንፈስ ቅዱስ ስለሆነ ነው፡፡
ሲሰበሰቡና ሲወስኑ መንፈስ ቅዱስን መሪ ሰብሳቢ አጋዥ አድርገው ስለሆነ ነው፡፡ አርዮስን ለማውገዝ ሃይማኖት ለማጽናት በኒቅያ /የቤተ ክርስቲያን ታሪከ፣ ሃይማኖተ አበው/ የተሰበሰቡ ፫፻፲፰ ሊቃውንትም ጌታ አብሯቸው እንደሚሰበሰብ እንደ ነበር የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል፡፡
ለ. የሐዋርያት ወራሴ መንበር ስለሆነ
‹‹እናንተን የተቀበለ እኔን መቀበሉ ነው ያላቸው የሐዋርያት ተከታዮች ናቸው፤ ሊቃነ ጳጳሳት በክርስቲያኖች ላይ ያላቸው ሹመት ሙሴ በእስራኤል ላይ እንደነበረው ምስፍና ያለ ነው›› ተብሎ ተደንግጓል፡፡ (ፍ/መ/፬፣፶፬ እና ፶፭/
ሐ. ለቅድስና የሚያበቃ ሕግና ሥርዓት ስለሚወጣበት ነው፡፡
ሥጋዊ ያይደለ መንፈሳዊ፣ ምድራዊ ያይደለ ሰማያዊ ሥርዓት የሚሠራበትና ሕግ የሚደነገግበት ስለሆነ ነው፡፡
መ. በቅድስናቸው፣ በንጽሕናቸው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጠባቂነት የተመረጡ ስለሚሰበሰቡበት
ለቅድስና በምታበቃ ክህነት የተሾሙ፣ ሹመታቸው/መመረጣቸው ከሰው ሳይሆን ከእግዚአብሔር የሆነ፣ እኛና መንፈስ ቅዱስ ብለው የሚወስኑ፣ ጥብቅናቸው ለቤተ ክርስቲያን የሆኑ ብፁዓን አበው የሚሰበሰቡበት ስለሆነ ቅዱስ ነው፡፡
ሠ. ሃይማኖት እምነት የሚጸናበት ጉባኤ ስለሆነ
የሃይማኖት አንድነት የሚጸናበት፣ ክሕደት፣ ጥርጥር፣ የሚወገዱበት፣ አጋንንትና ውሉደ አጋንንት የሚገሠፁበት እና የቅዱሳን ቅድስና የሚነገርበት/የሚወሰንበት/ ስለሆነ ነው፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ሲኖዶስ ስንል ቅድስናው የሚመነጨው ከሰው ሳይሆን ከራሱ ሁሉን ከሚቀድስ መንፈስ ቅዱስ ስለሆነ ክቡር፣ ቅዱስና ልዑል ነው፡፡
፩.፭. የልዕልናው መገለጫ የውሳኔዎቹ መፈጸም ነው፡፡
ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው ሲኖዶስ ክቡር ነው፤ ቅዱስ ነው፤ መሪውም መንፈስ ቅዱስ ነው፤ የክብሩ መገለጫ የልዕልናው መታያ መሆን ያለበት በመንፈስ ቅዱስ በብፁዓን አባቶች የተወሰነ ውሳኔ ሁሉ ሲከበር እና ሲተገበር ነው፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ለብዙ ሺህ ዓመታት ጸንታ የቆየችው ወርቃማውን ሥርዓቷን ጠብቃ ለትውልዱ ሁሉ ኩራት የጥበብ፣ የዕውቀት ሥጋዊ ወመንፈሳዊ ቤት፣ የመልካም ሰብእና ማእከል ሆና የዘለቀችው የማይናወጽ ሲኖዶሳዊ ሥርዓት በመጠበቁ በመከበሩ ውሳኔዋ በመፈጸሙ ነው፡፡ በርግጥ አንዳዶች በሊቃውንት ጉባኤ ስትመራ እንደኖረችናየሲኖዶሳዊ ታሪኳ ከ፶ ዓመት ያልዘለዘለ መሆኑን ይሞግታሉ፡፡ (አቡነ ሳሙኤል) ቢሆንም በሐዋርያት ሲኖደስ የምንተዳደር፣ ‹‹ማርቆስ አባታችን እስክንድርያ እናታችን›› ብለን የኖርን ሲኖዶስ አልነበረንም ማለት ተገቢ አይደለም፡፡ ስለሆነም፡-
✍️ የሕግና ሥርዓት ምንጭ፣ የቤተ ክርስቲያን ጠበቃና ዳኛ
✍️ የጾታ ምእመናን ባላደራ፣ የሐዋርያት ወራሴ መንበር የሆነ
✍️ የምሥጢራት ባለቤት፣ የክህነት መገኛ ወዘተ የሆነው
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
✞✞✞✝️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ✝️ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖ ✝️ሐምሌ ፲፪✝️ ❖
✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱስ "ሚካኤል ሊቀ መላእክት"
የተአምር በዓልና ለሰማዕቱ "አባ ሖር" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+*" ተአምረ ቅዱስ ሚካኤል "*+
=>ቅዱስ መጽሐፍ እንደ ነገረን በዚህች ዕለት የመላእክት
ሁሉ አለቃቸው: የቅዱሳንም ረዳታቸው የሆነው ደጉ
መልአክ #ቅዱስ_ሚካኤል ንጉሡን ሕዝቅያስን ግሩም
በሆነ ተአምር ከከተማው #ኢየሩሳሌም ጋር ታድጐታል::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
+ከመድኃኒታችን #ክርስቶስ ልደት 700 ዓመታት በፊት
#ሕዝቅያስ የሚባል ንጉሥ በይሁዳ ላይ ነግሦ ነበር::
ደጋጉ #ዳዊትና #ሰሎሞን ካረፉ በሁዋላ የሕዝቅያስን
ያክል ቅን እና የእግዚአብሔር ሰው በእሥራኤል ላይ
አልነገሰም:: ንጉሡ ጣዖት አምልኮን ነቃቅሎ አጥፍቶ
ሕዝቡ እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልክ አድርጐም
ነበር::
+ነገር ግን ቅዱስ ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዓመት
የአሕዛብ (የአሦር) ንጉሥ ሰናክሬም በጠላትነት ተነሳበት::
ወደ አካባቢውም መጥቶ: ከቦ አስጨነቀው:: ሰናክሬም
በጦር እጅግ ኃይለኛ ነበር:: በዚያውም ላይ ጦር የሚመዙ
ከ185,000 በላይ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩትና ሕዝቅያስ
እንደማይችለው ተረድቶ መልእክተኛ ላከበት::
+"እገብርልሃለሁ:: የፈለግከውንም እሰጥሃለሁ:: ሃገሬን
ግን አታጥፋ:: ኢየሩሳሌምን አታቃጥል:: ሕዝቤንም
አትግደል" በሚል ለመነው:: እጅ መንሻ ግብሩንም
ከከተማዋ የተገኘውን ወርቅና ብር ሁሉ ጭኖ ላከለት::
+ሰናክሬም ግን ሰይጣን ያደረበት ነውና የሕዝቅያስን
ልመና ወደ ጐን ብሎ የእሥራኤልን አምላክ : ቅዱስ
ስሙንም ተገዳደረ:: ለሕዝቅያስም "ከእኔ እጅ የሚያድንህ
ማነው? ሕዝቡንም #እግዚአብሔር ያድናል ብለህ
አታታልላቸው" ሲል ላከበት:: ቅዱስ ሕዝቅያስ በዚህ ጊዜ
የፈጣሪው ስም ሲቃለል ሰምቷልና ፈጽሞ አዘነ::
+መልእክተኞችን ወደ ነቢዩ #ቅዱስ_ኢሳይያስ ልኮ እርሱ
ወደ ቤተ መቅደስ ገባ:: በእግዚአብሔር ፊት ልብሱን
ቀድዶ ማቅ ለበሰ:: ስለ ኢየሩሳሌምና ሕዝቡም ፈጽሞ
አለቀሰ:: በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር የሰናክሬምን
መገዳደርና የሕዝቅያስን ልመና ሰምቷልና በኢሳይያስ
አንደበት እንዲሕ አለ:- "ስለ ባሪያየ ስለ #ዳዊት
ከተማዋን አድናታለሁ::"
+በዚያች ሌሊትም ድንቅ መልአክ #ቅዱስ_ሚካኤል
ከሰማያት በግርማ ወረደ:: ወደ ሰናክሬም የጦር ሠፈር
ደርሶ አንድ ጊዜ የእሳት ሰይፉን መዝዞ ቢያሳያቸው
ከአሕዛብ ሠራዊት 185 ሺ ኃያላን እንደ ቅጠል ረገፉ::
በለኪሶ የነበረው ሰናክሬም በጧት ቢነሳ ሠራዊቱ ሁሉ
ወደ አስከሬን ክምር ተቀይሯል::
+በድንጋጤ ወደ #ነነዌ ሒዶ ወደ ጣዖት ቤቱ ሲገባ የራሱ
ልጆች (አድራማሌክና ሳራሳር) ገደሉት:: ትዕቢተኛው
ሰናክሬም ለአሕዛብ ሁሉ መዘባበቻ ሆነ:: ቅዱስ ሕዝቅያስ
ግን በፈጣሪው ታምኗልና ቅዱስ ሚካኤል ሞገስ ሆኖ
የዓለም ነገሥታት ሁሉ ፈሩት:: (1ነገ. 18:13, 19:1)
+*" ቅዱስ አባ ሖር ሰማዕት "*+
=>ዳግመኛ በዚህ ቀን #አባ_ሖር ሰማዕቱ ይታሠባል::
+ቅዱሱ:-
¤ስርያቆስ በምትባል የግብጽ አውራጃ ተወልዶ ያደገ:
¤ገና በልጅነቱ መንኖ እግዚአብሔርን ያገለገለ:
¤ዘመነ ሰማዕታት በመጣ ጊዜም በመኮንኑ ፊት ቀርቦ
በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ያመነ:
¤ከመኮንኑም ብዙ ስቃይ የደረሰበት:
¤ብዙ ተአምራትን በመስራቱ ያሰቃየው የነበረውን መኮንን
ወደ ክርስትና መልሶ ለሰማዕትነት ያበቃ አባት ነው::
+እርሱም የሰማዕትነትን ክብር በእጅጉ ሽቷታልና ወደ ሌላ
ሃገር ሒዶ በዚህች ቀን አንገቱን ተሰይፎ የክብርን አክሊል
ተቀዳጅቷል:: በሐዋርያዊ አገልግሎቱ ያሳመናቸው 127
ወንዶችና 20 ሴቶችም አብረውት ተሰይፈዋል::
=>እግዚአብሔር በሊቀ መላእክት ክንፍ ሃገራችንን
ከአሕዛብ ስውር ጦር ይጠብቅልን:: ከሰማዕቱም በረከት
ያሳትፈን::
=>ሐምሌ 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ሕዝቅያስ ንጉሥ
2.ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል
3.ቅዱስ አባ ሖር ሰማዕት
4."147" ሰማዕታት (የአባ ሖር ማሕበር)
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
3.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ድሜጥሮስ
5.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
6.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
7.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
8.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
=>+"+ እግዚአብሔር ይላል:- ስለ እኔም ስለ ባሪያየም
#ስለ_ዳዊት ይህችን ከተማ አድናት ዘንድ እጋርዳታለሁ::
በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወጣ::
ከአሦራውያንም ሠፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ::
ማለዳም በተነሱ ጊዜ እነሆ ሁሉ በድኖች ነበሩ:: +"+
(1ነገ. 19:34)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
የኢኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተክርስቲያን ፱ ኤጲስ ቆጶሳትን ሾመች።
ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለዘጠኝ አህጉረ ስብከት የተመረጡት ፱ ቆሞሳት ዛሬ ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በተፈጸመ ሥርዓት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት አንብሮተ እድ በኤጲስ ቆጶስነት ተሹመዋል።
ከሌሊቱ ፱ ስዓት ጀምሮ በተከናወነው ሥርዓተ ሢመት ላይ የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች።፣ ግብዣ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች፣ ከየአህጉረ ስብከቱ የመጡ ሊቃውንት፣ የሥራ ኃላፊዎች እና ምእመናን ተገኝተዋል።
በዚህም መሠረት የሚከተሉት አባቶች በቅድስት ቤተክርስቲያን የተሰጣቸውን ሥያሜ ይዘው ለተጠቀሱት አህጉረ ስብከት ተመድበዋል።
፩- ቆሞስ አባ ክንፈገብርኤል ተክለማርያም ብፁዕ አቡነ ገሪማ ተብለው ተሠይመው ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ ሀገረ ስብከት
፪- ቆሞስ አባ ሣህለማርያም ቶላ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ተብለው ተሠይመው ለምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት
፫- ቆሞስ አባ ስብሐትለአብ ኃይለማርያም ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ተብለው ተሠይመው ዳውሮና ኮንታ ሀገረ ስብከት
፬- ቆሞስ አባ አምደሚካኤል ኃይሌ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ተብለው ተሠይመው ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት
፭- ቆሞስ አባ ኃይለማርያም ጌታቸው ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስም ተብለው ተሠይመው በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት
@ortodoxtewadochannal
የአዳዲስ ተሿሚ ኤጲስቆጶሳት የአስኬማ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም እየተካሄደ ነው !
ሐምሌ 8 ቀን 2015 (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
ቅዱስ ሲኖዶስ ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ፤የተመረጡ 9 ቆሞሳት የአስኬማ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እንዲሁም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።
ሢመቱ ከሕገ ቤተ ክርስቲያን አኳያ ቀኖናን የጣሰ ነው በሚል በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ጥያቄ እያቀረቡ ቢሆንም ፤ ሢመቱ ከመካሄድ እንደማይቀር ማሳያ መሆኑ የተነገረለት የአስኬማ ጸሎት እየተካሄደ መሆኑ ማሳያ ነው።
እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ⤵️
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና በትግራይ ክልል ባለው የቤተ ክርስቲያኒቱ ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ የተሠጠ መግለጫ
“ሃይማኖቶች የይቅርታ፣ እርቅ፣ የሰላም፣ እና የአንድነት መሠረቶች ናቸው”
የተከበራችሁ እና የተወደዳችሁ የሀገራችን ህዝቦች፣ ምዕመናንና ምዕመናት ከሁሉ በማስቀደም በሀገራችን እየሆነ ያለው ሁሉ በእጅጉ አሳሳቢና አስጨናቂ እየሆነ የቀጠለ ሲሆን በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጣዊ የአለመረጋጋት ክስተት በተደጋጋሚ እያስተናገደች መሆኗ በእጅጉ አሳስቦናል፡፡ በተለይም ከሰሞኑ የቤተ ክርስቲያኒቱ ፓትሪያርክን ጨምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የሰላም ልዑካን በትግራይ ክልል፣ በመቀለ ከተማ በመገኘት በክልሉ ካለው የቤተ ክርስቲኒቱ መዋቅር ጋር የተፈጠረውን የግንኙነት ችግር በመፍታት እርቀ ሰላምን ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ ጉዞ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጅ የሰላም ልዑኩ ይዞት የተነሳውን ዓላማ ሳያሳካ ወደአዲስ አበባ ተመልሷል፡፡ ይህም በመሆኑ እኛ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች አሳዝኖናል፡፡
@ortodoxtewadochannal
በወቅታዊ ጉዳይ ከጴጥሮሳውያን የማኅበራት ኅብረት የተሰጠ መግለጫ
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
=>+"+ እንኩዋን ለአጋእዝተ ዓለም #ሥላሴ እና ለቅዱሳን
አበው #አብርሃም: #አባ_ሲኖዳ እና #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ
ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+
+"+ #ሥሉስ_ቅዱስ +"+
=>በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት): በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት)
የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ
#እግዚአብሔር ነው:: #አብ : #ወልድ : #መንፈስ_ቅዱስ
በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት: በባሕርይ: በሕልውናና
በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ
ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና::
+ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት " #ቅድስት_ሥላሴ "
እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም::
የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው
ያድራሉ::
+ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል
በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን
#ቅዱስ_አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን
በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል:: ሥላሴ
አኀዜ ዓለም (ዓለምን በእጁ የያዘ) ነው:: ነገር ግን በፍቅር
ለሚሻው በፍቅር ይመጣል::
+አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ
ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን
አጠበ:: (ወይ መታደል!) በጀርባውም አዘላቸው:: (ድንቅ አባት!)
ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው
ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት:: #ቅድስት_ሣራ ሳቀች::
እንደ ዘንድሮ ወገኖቻችን የማሾፍ አይደለም:: ደስታና ጉጉት
የፈጠረው እንጂ:: ሥላሴ "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ"
ብለው ነበርና በዚህም ምክንያት ነው " #ይስሐቅ" የተባለው::
+ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን (ሐይመት) የድንግል
እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ #አብ
ለአጽንኦ: #መንፈስ_ቅዱስ ለአንጽሖ: #ወልድ በተለየ አካሉ
ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና::
+"+ #ታላቁ_አባ_ሲኖዳ +"+
=>የባሕታውን ሁሉ አለቃቸው ታላቁ ቅዱስ ሲኖዳ:-
¤በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ
¤በእናቱ ማሕጸን ሳለ መላእክት በሰይፈ እሳት ይጠብቁት የነበረ
¤የታላቅነት ትንቢት የተነገረለት
¤ገና ሳይወለድ ሥውራን አበው የሰገዱለት
¤በሕጻን ሰውነቱ ጾምና ጸሎትን የጀመረ
¤የልጅነት ቁርስና ምሳውን ለነዳያን ያካፍል የነበረ
¤በ9 ዓመቱ ወደ በርሃ የመነነ
¤የአባ አብጐል ደቀ መዝሙር የሆነ አባት ነው::
+ሲመነኩስም በእግዚአብሔር ትእዛዝ #የሠለስቱ_ደቂቅ
አስኬማ: #የኤልያስ ቆብዕ እና የመጥምቁ #ዮሐንስ ቅናትን
(መታጠቂያ) ከያሉበት መላእክት አምጥተውለት የመነኮሰ
¤ዓለምን በሙሉ በጸሎቱ ይጠብቅ የነበረ
¤የግብፅን በርሃ በብርሃን የሞላ
¤በርካታ ድርሰቶችን የደረሰ
¤ያለ ማቇረጥ በየቀኑ ከ100 ዓመታት በላይ ከጌታችን ክርስቶስ
ጋር የተነጋገረ
¤ደመናትን ተጭኖ ይሔድ የነበረና
¤ያለ ዕረፍት ለ111 ዓመታት ከ2 ወራት ፈጣሪውን ያገለገለ
አባት ነው::
+በዚህም ምክንያት አንድ ቀን ገዳማውያን ሁሉ እየሰሙ
እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ መጣ:: "ሲኖዳ ተሠይመ
#አርሲመትሪዳ " (ሲኖዳ አርሲመትሪዳ ሆኗል:: ማለትም
ለባሕታውያን ሁሉ አለቃ ሁኖ ተመርጧል ማለት ነው:: )
+ቅዱሱ የጌታችንን እግር እያጠበም ይጠጣ ነበር::
+በዚህች ዕለት በ120 ዓመቱ ጌታችን ወርዶ ሲያሳርገው
#አቡነ_ኪሮስ "ታላቅ ምሰሶ (ታላቅ ዛፍ) ወደቀ" ብለው
አልቅሰዋል:: #ሲኖዳ ማለት "ደግ ሰው" ማለት ነው::
+"+ #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ ( #GIYORGIS_OF_SEGLA )
+"+
=>ታላቁ ኢትዮዽያዊ ሊቅና ጻድቅ የተወለደው ወሎ #ጋስጫ
ውስጥ በ1358 ዓ/ም ነው:: ከልጅነቱ ትምሕርት አልገባሕ
ቢለውም በልቡናው ግን ቅን እና ታዛዥ ነበር:: መምሕሩ
"ትምሕርት አይገባውምና ውሰዱት" ቢላቸው "የእግዚአብሔር
ነውና ያገልግላችሁ" ብለው መለሱት:: መገፋቱን የተመለከተ
#አባ_ጊዮርጊስ #እመቤታታችንን ከልቡ ይወዳት ነበረና
ይማጸናት ገባ::
+ቀን ቀን ገዳሙን ሲረዳ: እሕል ሲፈጭና ሲከካ: ላቡንም
ሲያፈስ ውሎ ሌሊት ደግሞ ሲጸልይ ያነጋ ነበር:: ድንግል
እመቤታችን ጸሎቱን ሰምታለችና #ቅዱስ_ዑራኤልን አስከትላ
መጣችለት:: በንጹሐት እጆቿ ባርካው ምሥጢርንም ነገረችው::
"ወነገረቶ ሐምስተ ቃላተ" እንዲል:: ጽዋዐ ልቡናን አጠጥታው
ተሠወረችው::
+ከዚህች ሰዓት ጀምሮ አባ ጊዮርጊስ ፍጹም ተለወጠ:: በጽድቁ
ላይ የሊቅነትን ካባ ደረበ:: ቅዱሳት መጻሕፍትን ይተነትናቸው:
መናፍቃንንም ምላሽ ያሳጣቸው ገባ:: የተረጐማቸውና
ያተታቸውን ሳይጨምር 41 ድርሰቶችን ደረሰ:: (መጽሐፈ
ሰዓታት: መጽሐፈ ምሥጢር: አርጋኖን: ኆኅተ ብርሃን: ውዳሴ
መስቀል: ወዘተ . . . የእርሱ ድርሰቶች ነበሩ)
+ስለ ሃይማኖትም ጠበቃ ነበር:: ስለ ቅድስናውና ውለታው የኢ/
ኦ/ተ/ቤ እንዲህ ትጠራዋለች:-
1. #ሊቀ_ሊቃውንት
2. #በላዔ_መጻሕፍት
3. #ዓምደ_ሃይማኖት
4. #ዳግማዊ_ቄርሎስ
5. #ጠቢብ_ወማዕምር
+ጻድቁ ሊቅ በተወለደ በ60 ዓመቱ በ1418 ዓ/ም በዚህች ቀን
ዐርፏል:: አባ ጊዮርጊስ የተወለደውም ያረፈውም ሐምሌ 7 ቀን
ነው::
=>የሥላሴ ቸርነት: የአብርሃም ደግነት: የአበው አባ ጊዮርጊስና
አባ ሲኖዳ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን::
=>ሐምሌ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን አብርሃምና ሣራ (ሥላሴን ያስተናገዱ)
2.ብሥራተ ልደተ ይስሐቅ
3.ታላቁ አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን ሁሉ አለቃ)
4.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (ሊቀ ሊቃውንት: ኢትዮዽያዊ
የሃይማኖት ምሰሶ)
5.ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ (ምጥው ለአንበሳ)
6.አባ መቃቢስ
7.አባ አግራጥስ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
2.አባ ባውላ ገዳማዊ
3.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
=>+"+ እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ:-
'በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ:: እያበዛሁም አበዛሃለሁ'
ብሎ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ በራሱ ማለ::
እንዲሁም እርሱ ከታገሠ በሁዋላ ተስፋውን አገኘ:: +"+ (ዕብ.
6:13)
=>+"+ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር:
የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን:: +"+
(ቆሮ. 13:14)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
ቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪ አቀረበ።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
በክልል ትግራይ በተካሄደው ጦርነት በቤተ ክርስቲያናችን የበላይ መዋቅርና በክልል ትግራይ አህጉረ ስብከት መካከል የነበረው አስተዳደራዊ መዋቅር ተቋርጦ መቆየቱን ተከትሎ የተፈጠረው አለመግባባት በውይይት ተፈቶ መዋቅራዊ አንድነታችን በድጋሚ ተጠናክሮ እንዲቀጠል ሀገራዊ የሰላም እርቁ ከተፈጸመበት ማግስት ጀምሮ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ፊርማ በተደጋጋሚ በደብዳቤ ሲጠየቅ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
ምንም እንኳን ቅዱስ ሲኖዶሱ ችግሩ በውይይት እንዲፈታ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ሲያደርግ የቆየ ቢሆንም በክልሉ ያሉት ብፁዓን አባቶችና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በተከፈተው የሰላምና የውይይት በር ከመጠቀም ይልቅ መዋቅራዊ አደረጃጀቱን በመጣስ መንበረ ሰላም የትግራይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት መሥርተናል በሚል ተገቢነት የሌለው መግለጫ ከመስጠትም አልፎ ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት መፈጸም አለበት የሚል ውሳኔ በማሳለፍ 10 ኤጲስ ቆጶሳትን ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዐ.ም. ለመሾም ፕሮግራም መያዙን በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ በጉዳዩ ላይ ከተወያየ በኋላ በጦርነቱ ወቅት ለነበረው የመዋቅራዊ ግንኙነት ጉድለትና የሰብአዊ ድጋፍ እጥረት በይፋዊ መግለጫ ይቅርታ የተጠየቀ ቢሆንም ለይቅርታው አዎንታዊ ምላሽ አለመሰጠቱ በእጅጉ አሳዛኝ መሆኑ፤
@ortodoxtewadochannal
በሰፊው ተጽፎ ይገኛል፡፡
እኛም በዓለ ዕረፍታቸውን ለማስታወስ ያህል ታሪካቸውን በአጭሩ አቀረብን፤ ቅዱሳን ሐዋርያት ያቆዩልንን የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ጠብቀን፣ በክርስቲያናዊ ምግባር ጸንተን እንድንኖር፣ በመጨረሻም የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ እንድንበቃ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን!
ምንጭ፡-
• ገድለ ሐዋርያት፣ ዜና ሐዋርያት፤
• መጽሐፈ ስንክሳር፣ ሐምሌ ፭ ቀን፤
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
‹‹መኑ ያኀድገነ ፍቅሮ ለክርስቶስ፤ ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየኝ ማን ነው?›› (ሮሜ.፰፥፴፭)
ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በፍጹም እምነት አምላኩን የሚወድ ቢኖር መራብም፣ መጠማትም፣ መታረዝም፣ መደብደብም፣ መታሰርም ሆነ መገደል ቢሆን ይህንን ፍቅረ እግዚአብሔር የሚለይ ምንም ነገር ሊኖር እንደማይችል በዚህ አንቀጽ አስረድቷል፡፡ ሐምሌ ፭ የሚዘከረውም በዓል ቅዱስ ጳውሎስ እና ቅዱስ ጴጥሮስ ስለ ሃይማኖታቸው ምክንያት በሮማው ንጉሥ ኔሮን ሰማዕትነት የተቀበሉበትን በማሰብ ነው፡፡ በየዓመቱ የብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ በዓለ ዕረፍትም በዚህ ዕለት ይከበራል፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስ በአባቱ ከነገደ ሮቤል በእናቱ ደግሞ ከነገደ ስምዖን ወገን ነው፤ የተወለደውም በገሊላ አውራጃ በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ እናትና አባቱ ‹ስምዖን› ብለው ጠርተውታል፡፡ በግሪክ "ስምዖን"፣ በዕብራይስጥ "ኬፋ" ይባላል፡፡ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ‹ጴጥሮስ› ብሎ ጠርቶታል፤ ትርጕሙም ዓለት (መሠረት) ማለት ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ልዩ ስሟ ጌንሴሬጥ በምትባል መንደር ዓሣ ያሠግሩ ነበር፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ የሚተዳደረው በዓሣ አጥማጅነት የነበረ ሲሆን፣ ሰዎችን በወንጌል መረብ እያጠመደ ወደ ክርስትና ሕይወት ይመልስ ዘንድ ጌታችን ለሐዋርያነት ጠርቶታል፡፡ (ሉቃ.፭፥፲፣ማር.፩፥፲፮)
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ የተወለደው በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው በቤተሳይዳ ነው። ከአምስት ዓመቱ ጀምሮ ያደገው በቅፍርናሆም ከተማ ነበር፤ በጐልማሳነቱ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ዓሣ ማሥገር ጀመረ።
@ortodoxtewadochannal
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በትግራይ የሚገኙ አባቶች ችግሮችን በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በትግራይ ክልል በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ርዳታ ለመስጠትና በትግራይ ከሚገኙ አባቶች ጋር የተፈጠረው ችግር በውይይት ለመፍታት ዛሬ ፣ሐምሌ ፫ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም ማለዳ መቀሌ ከተማ መግባታቸው ይታወቃል።
ቅዱስ ፓትርያርኩ ከክልሉ ጊዜያዊ መስተዳድር ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ ጋር በሰጡት የጋራ መግለጫ በትግራይ የሚገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የተፈጠረውን ችግር ወደ ጠረጴዛ መጥተው በውይይት እንዲፈቱ አባታዊ ጥሪ አስተላልፈዋል።
በዚሁ ጊዜ ቅዱስነታቸው እንደገለጹት "ሁኔታው አስከፊ ቢሆንም የመጣነው ለመወያየት ነው፤ ቅዱስ ሲኖዶስ በአሁኑ ጉባኤ ይቅርታ ጠይቋል።ይህ ከሆነ መወያየት ጥሩ ነው ብለን መጥተናል።
መወያየት ክፉ አይደለም ። ሰው አሳቡን ለመግለጽም ሆነ ለመስማማትና ላለመስማማት መገናኘትና መወያየት ክፉ አልነበረም" ብለዋል።
"መቼም ብፁዓን አባቶች በምን ምክንያት እንደቀሩ እኛ የምናውቀው ነገር የለም" ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ "በጤና ነው ወይስ አውቀው ነው ሳያውቁ ነው አምነውበት ነው ሳያምኑበት ነው የቀሩት የሚለውን እኛ የምናውቀው ነገር የለም" ብለዋል።አያይዘውም ቅዱስነታቸው "መወያየት ጥሩ ነበር። በመወያየት አሳብን መግለጽ ይቻላል። የደረሰውን ችግር መግለጹና ማስረዳቱ አንድ ቁም ነገር ነበር። ይሁንም አይሁንም ለማለት ውይይት ጥሩ ነበር ።የሆነው ሆኖ አልተገኙም" በማለት በክልሉ የሚገኙ አባቶች በውይይቱ አለመገኘታቸውን ገልጸዋል ።
@ortodoxtewadochannal
አቶ አያሌው ቢታኒ በሰጡት ማብራሪያ አክለው እንደገለጹትም በማኅበራት ምዝገባና ክትትል መምሪያ ከሚካተቱት የማኅበራት ዘርፎች ከስምንት ያላነሱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የማኅበራት አንድነት፣የሙያ ማኅበራት፣የበጎ አድራጎት ማኅበራት፣የሐዋርያት ማኅበራት ፣መንፈሳዊ አስጎብኚ ማኅበራት ይገኙባቸዋል።
ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደቡብ ትግራይ ማይጨው እና ደቡብ ምሥራቅ ትግራይ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የማኅበራት ምዝገባና ክትትል መምሪያ የበላይ ሐላፊ ሊቀ ጳጳስ ባስተላለፉት አባታዊ መልእክት የማኅበራት ምዝገባና ክትትል መምሪያ ዋና ዓላማው ልዩ ልዩ ፈተና በበዛበት በዚህ ዘመን ምእመናን አንድነታቸውን እያጠናከሩ ባንድ ላይ በመቆም ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ እንዲረዳቸው ታስቦ ሲሆን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንንም ባንድ ላይ ሆነን ለማሻገር እንድንችል ነው ብለዋል።
ዘገባው የኢኦተቤ ቴቪ ነው
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
"እናንተን ንጹሐን ቅዱስ ሲኖዶስን ተወቃሽ የሚያደርገው አንዳችም ነገር የለም"
"በትግራይና በፌደራል መንግሥት፣ በትግራይና በአማራ ክልል ባለው አለመግባባት ችግሮችን ለመፍታት በምልዓተ ጉባኤ ቅዱስ ሲኖዶስ ፊት እናንተም ባላችሁበት ይህ ችግር በዚህ ሊቀጥል አይገባውም ችግር ከመፈጠሩ በፊት የሰላም ኮሚቴ ይቋቋም ብሎ ቅዱስ ሲኖዶስ ጮሗል? አልጮህም? እናንተስ በዚያን ጊዜ ምን ትሉ ነበር?
በመጨረሻም ቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳዩን ተመልክቶ ችግሩን ለመፍታት በፌደራል መንግሥት፣ በትግራይና በአማራ ክልል ያለው ችግር እንዲፈታ እንደ ጥንቱ ታቦት ይዘን፣ መስቀል ይዘን፣ ሕዝባችንን እናገናኝ ዝም ብለን ማየት የለብንም ብሎ ቅዱስ ሲኖዶስ ሲጮህ ምን ነበር ያላችሁት አባቶች?
ደም በሚፈስበት ቦታ ላይ ሄዳችሁ አስታርቁ ትግራይ ለምን ሰላም ሆነ ነው ወይ ይህንን የምትሉ አላላችሁንም?
ቤተክርስቲያን ዝም አለች አላችሁ፤ ምነው ቤተክርስቲያን ምንም እንዳልተናገረች ደግማችሁ ደጋግማችሁ ተናገራችሁ፡፡ ያውም ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ስሕተትን ለማረም ስሕተት መደገም የለበትም፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬም ጉዳዩን አይቶ ችግሩን ለመፍታት ይቅርታ የሚለውን ጥያቄም አቅርቧል፡፡ ነገም ያቀርባል በሚገባው በመልኩ በአንጻሩ ደግሞ የሠራው ያደረገው ነገር ሊቀበር አይገባውም ሊነገርለት ይገባል፡፡ ስለዚህ በዚህ ጥፋት ከሆነ እናንተም እኛም የጋራ ተወቃሾች እንሆናለን እንጂ እናንተን ንጹሐን ቅዱስ ሲኖዶስን ተወቃሽ የሚያደርገው አንዳችም ነገር የለም፡፡"
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት
ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
4. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር በልዩ ልዩ የሥራ አገልግሎት ላይ የሚገኙ የክልሉ ተወላጆች የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በሚያመቻቸው የውይይት መድረክ የችግሩን አሳሳቢነት አስመልክቶ ግንዛቤ በማስጨበት የመፍትሔው አካል እንዲሆኑ ጥሪ እንዲተላለፍ፣
5. በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ላይ እየተከሰቱ ያሉ የሕገ ቤተክርስቲያንና የቀኖና ጥሰቶች ከቤተክርስቲያኒቱም አልፎ ሀገራዊ አንድነትና ሉዓላዊነትን የሚያናጋ ብሎም ሀገራዊ ቀውስ የሚያስከትል እንደመሆኑ መጠን የፌዴራል መንግሥቱና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ለችግሩ ልዩ ትኩረት በመስጠት የውይይት መድረክ በማዘጋጅት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ እንዲደረግ፣
6. የሕገ ቤተክርስቲያንና የቀኖና ጥሰት የሚያስከትለውን ቀውስ በመረዳት ዛሬም ድረስ ለቤተክርስቲያናችን አንድነትና ሉዓላዊነት መጠበቅ በሐሳብና በጸሎት ዘወትር የሚተጉ በትግራይ የሚገኙ ሊቃውንት እንዳሉ አስተዳደር ጉባኤው በጽኑ ያምናል፤
በመሆኑም ይህ ኃላፊነታቸውም በክልሉ የሚገኙ ምዕመናን በየደረጃው ላሉ የቤተክርስያኒቱ የሥራ ኃላፊዎች ተገቢውን ምክረ ሐሳብ በመስጠት የተጀመረው የሰላምና የዕርቅ ተልዕኮ ለውጤት እንዲበቃ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ እናስተላልፋለን።
7. በክልሉ የሚገኙ አበው ሊቃነ ጳጳስት ሕገ ቤትክርስቲያንና ቀኖና ቤቴክርስቲያንን ጠብቀው በማስጠበቅ በቀኖና ጥሰት እንሾማለን የሚሉትን አቁመው የሰላም በራቸውን ለውይይት ክፍት እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
8. ከላይ የተገለፁት የሰላም አማራጮችን እስከ መጨረሻው ድረስ አሟጦ በመጠቀም ሰላማዊ ተልዕኮው ግቡን እንድመታ ማድረጉ እንደተጠበቀ ሆኖ በቤተክርስቲያናችን ላይ እየደረሰ ያለውን የሕግና የቀኖና ጥሰቶች አስመልክቶ እንዳሁን ቀደሙ ሁሉ በሕግ አገልግሎት መምሪያ በተቋቋመው የሕግ ዐቢይ ኮሚቴ በኩል ተገቢውን የሕግ አግባብ ተከትሎ የቤተክርስቲያኒቱን መብትና ጥቅም እንዲያስከብር ይህም በቋሚ ሲኖዶስ ቀርቦ መመሪያ እንዲሰጥበት እንዲደረግ በማለት ውሳኔውን አስታውቋል፡፡
©Eotc tv
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
ቅዱስ ሲኖዶስ ክብሩ ልዕልናው ካልተከበረ ውሳኔው ካልተፈጸመ ህልውናው ጥያቄ ውስጥ ይገባል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀርቶ ሀገርና ትውልድ አደጋ ላይ ይወድቃሉ፡፡ ምክንያቱም ሕግ ሁሉ ከሰው ከሆነ ሕገ ሰብእ መሆኑ ይቀርና ሕገ አራዊት ይሆናልና፡፡ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ መገለጫዋ መሪዋ የሕግ ሁሉ ምንጭ ሲኖዶሷ ነውና፡፡
ቸር ይግጠመን!
ይቆየን!
መቃብር ቆፋሪዉ መንፈሳዊ ትረካ
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
፮- ቆሞስ አባ ጥላሁን ወርቁ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ተብለው ተሠይመው በቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት
፯- ቆሞስ አባ ዘተክለሃይማኖት ገብሬ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ተብለው ተሠይመው በሆሮ ጉድሩ ሀገረ ስብከት
፰- ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ ገብሬ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ተብለው ተሠይመው በምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት
፱- ቆሞስ አባ ወልደገብርኤል አበበ ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞ.ስ ተብለው ተሠይመው በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ተመድበዋል።
ምንጭ: ሕዝብ ግንኘነት መምሪያ
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
አዲስ ለሚሾሙት ኤጲስ ቆጶሳት የጸሎተ አስኬማ ሥነ ሥርዓት ተከናወነ።
በነገው ዕለት ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም ሢመተ ኤጲስቆጶስነት ለሚፈጸምላቸው ፱ ቆሞሳት የጸሎተ አስኬማ ሥርዓት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መሪነት ብፁፅ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዩወርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ክቡር ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶችና በርካታ ቁጥር ያላቸው ምእመናን በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናወነ።
በሥርዓተ ቤተክርስቲያን በተቀመጠው መሠረት አዲስ ለሚሾሙ ኤጲስቆጶሳት በሲመቱ ዋዜማ የሚፈጸመው ጸሎተ አስኬማ የደረሰላቸው ዘጠኝ ቆሞሳት ሰኔ ፳፱ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተመረጡና በነገው ዕለት ሥርዓትተ ሢመተ ኤጲስ ቆጶስና ተፈጽሞላቸው በዘጠኝ አህጉረ ስብከት የሚመደቡ ናቸው።
በዛሬው ዕለት በተፈጸመው ጸሎተ አስኬማ ለሥርዓቱ የተሠራው ጸሎት በቅዱስነታቸው መሪነት ከደረሰ በኋላ ቡራኬ የተሰጠበትን ቅናተ ዮሐንስ ቅዱስነታቸው ለተሿሚ ቆሞሳት አስታጥቀዋል።
ሥርዓቱ ከደረሰ በኋላ በቅዱስነታቸው ቃለ ምዕዳንና ጸሎት ተጠናቋል።
ምንጭ: የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
እንደሚታወቀው በትግራይ ክልል የተፈጠረው ሁኔታ እጅግ ከባድና ፈታኝ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ እኛ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባቶችም ከመነሻው ይህ ሁሉ ችግር ከመከሠቱ በፊት አለመግባባቱ በሰላምና በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈታ ጥሪ ስናደርግ ቆይተናል፡፡ ይሁን እንጅ አስከፊውን ጦርነትና የእርስ በርስ እልቂት አስተናግደናል፡፡ በዚህም በአወደ ወጊያውና ጦርነቱ ከተሠለፉት ባለፈ በርካታ ንፁኃን ወገኖቻችን ተገድለዋል፤ ከፍተኛ ለሆነ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ተዳርገዋል፤ ዜጎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፤ በአጠቃላይ በትግራይ ክልል ከፍተኛ የሆነ ሰብኣዊና ኢኮኖሚያዊ ወድመት መድረሱ በእጅጉ ያሳዝነናል፡፡ የሃይማኖትና የእምነት መሠረት በሆነው እና ሃይማኖተኛና አማኝ የሆነው የትግራይ ሕዝብ ላይ ይህ ሁሉ ስቃይ፣ በደልና ኢሰብኣዊነት መድረሱ ችግሩን ይበልጥ እንዲወሳሰብ ማድረጉንም እንገነዘባለን፡፡ ይህም በትግራይ ክልል የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አህጉረ ስብከቶች ከማዕከላዊው የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ጋር አስተዳደራዊና መንፈሳዊ ግንኙነታቸውን ማቋረጣቸውን እና ክልላዊ መዋቅር እያደራጁ እንደሆነ ሲገልፁ ቆይተዋል፡፡
በአንፃሩ በክልሉና በፌዴራል መንግስቱ መካከል በተካሄደው የሰላም ድርድር በተደረሠው ስምምነት መሠረት የጦርነት ምዕራፉን ተዝግቶ የሰላም ንግግሮችና ግንኙነቶች ተጀምረዋል፤ ከጊዜ ወደጊዜም መሻሻሎች እና አመርቂ ውጤቶች እየታዩ ነው፡፡ ይህ የሰላም ሂደት ይበልጥ ለማጠናከር እንዲቻል የሕዝብ ለሕዝብ እና የሲቪልና የሃይማኖት ተቋማት ግንኙነት ሊጠናከር ይገባዋል፡፡ ከዚህ አንፃር ሰላም ወዳዱ የትግራይ ሕዝብም ይህን ዓይነቱን ግንኙነት ከምንምና ከማንም በላይ እንደሚደግፈው እናምናለን፡፡ በፖለቲከኞች መካከል የተጀመረው እርቀ ሰላምም በሃይማኖት አባቶች፣ በሀገር ሽማግሌዎች እና በመላው ማኅበረሰብ ተስፋፍቶ የሆነውን ሁሉ በይቅርታና እርቅ በማከም ሀገራዊና ሃይማኖታዊ አንድነታችን ወደ ቀድሞ ሁኔታው ይመለሳል በማለት በተስፋ ስንጠብቅ ቆይተናል፡፡
ሆኖም ሕዝቡ በጦርነቱ የደረሠበትን በደልና ስቃይ ደጋግሞ በመንገር ሀገራዊ አንድነታችን እንዳይመለስና እንዳይፀና የሚፈልጉ አካላት ትግራይን ለመነጠል ተግተው እየሠሩ እንደሆነም ተረድተናል፡፡ በተለይም በቅዱስነታቸው መሪነት ወደትግራይ የተጓዘውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላም ልዑካን ቡድንን መንፈሳዊ አቀባበል ባለማድረግ እና ለመወያየትም ፍቃደኛ ባለመሆን የተወሠደው አቋም የችግሩን ስፋትና ጥልቀት የበለጠ እንድንረዳ አስችሎናል፡፡ ስለሆነም እኛ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ አባቶች በጉዳዩ ላይ በስፋትና በጥልቀት በመወያየት የይቀርታና እርቅ ጥሪ እና የሰላም መልዕክት በፈጣሪ ስም እናቀርባለን፡፡
1. የተወደዳችሁ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊያት ልጆቻችን አሁን የምንገኝበት ሁኔታ ፍፁም ሰላማዊና መልካም እንዲሆን ወደፈጣሪ በጸሎት እንድትበረቱ አደራ እንላለን፤
2. የተወደዳችሁ በትግራይ ክልል የምትገኙ የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አባቶችና ካህናት ባሳለፍነው አስከፊ ጦርነት የደረሠባችሁን ስቃይ፣ በደልና እንግልነት ታሪክ መዝግቦታል፤ ስቃይና በደላችሁም ይሠማናል፤ ይሁንና በሆነውና ስለሆነው ሁሉ በግልጽ በመነጋገርና በፍትህ አደባባይ ፍትህና ርትዕ መጠየቅ ተገቢ እንደሆነ እናምናለን፡፡ ለዚህ ደግሞ ለመነጋገር ብሎም ለመደራደር ፍቃደኛ መሆን ይገባል፡፡ ሆኖም የመነጋገርና የመደራደር አማራጭን ዝግ በማድረግ የተወሠደው አቋም ከቤተ ክርስቲያን መሠረታዊ አስተምህሮ ጋር የሚቃረን ብቻ ሳይሆን በቤተ ክርስቲያንና በሀገር አንድነት የሚኖረው ውጤትም የከፋ እንደሚሆን በንፁህ ወንድማዊና አባታዊ መንፈስ ልናሳስባችሁ እንወዳለን፡፡
3. የተወደዳችሁና የተከበራችሁ ተጋሩ ወገኖቻችን ትግራይ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መገለጫ እና ሉዓላዊነቷን ለማክበርና ለማስከበር በትግራይ መሬት የተደረገውን ተጋድሎና በተጋሩ ወገኖቻችን የተከፈለውን መስዋእትነት በታሪክ ድርሳናት በደማቅ የተጻፈ ሐቅ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም የዚህ ሁሉ የታሪክ ባለውለታ የሆነው ወገናችን ዛሬም የደረሠበት ሁሉ የመጥፎ ታሪካችን አንዱ ገጽታ መሆኑን በመቀበል ልቡን ለይቅርታ፣ ክንዱንም ለእርቅ በመዘርጋት ታሪካዊ ስህተት እንዳይፈፀም መሪዎቹን እንዲያሳስብ በአባታዊ መንፈስ በአጽንኦት እንጠይቃለን፤
4. የተከበራችሁ የፌዴራል መንግስት እና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ከምንምና ከማንም በፊት ስኬታማ ድርድር በማድረግ ጦርነቱን ለማቋም የወሠዳችሁት አቋምና በሂደትም ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን እያደረጋችሁ ስላለው ጥረት እናመሰግናችኋለን፡፡ ጥረታችሁ የበለጠ እንዲሳካም የሕዝብ ለሕዝብ እና የተቋማት ግንኙነት እንዲጠናከር ተገቢውን አመራር እንድትሠጡ እየጠየቅን በተለይም የትግራይ ክልል የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከማዕከላዊው መዋቅር ጋር የተፈጠረው አለመግባባት እና በክልሉ ለማከናውን የታቀደው ሹመትም በማዘግየት ይቅርታና እርቅ በማድረግ የሀገርና የቤተ ክርስቲያን አንድነት እንድታስጠብቁ አባታዊ ምክራችንን ከአደራ ጭምር እናሳስባለን፤
5. የተወደዳችሁ በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገራት ያላችሁ ተጋሩ የፖለቲካ ኃይሎች፣ የማኅበረሰብ አንቂዎች እና በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ተሠልፋችሁ ሀሳብና አስተያየታችሁን የምታጋሩ ሁላችሁም፣ ከሆነውና ከደረሠው አንፃር ስለትግራይና ተጋሩ መቆርቆራችሁና መቆጨታችሁ የሚጠበቅና ተፈጥሯዊ ባህሪይ እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ ሆኖም ስለምርጫችሁና ወሳኔያችሁ ደጋግማችሁ እንድታስቡበት በአጽንኦት ልናሳስባችሁ እንወዳለን፤
6. በመጨረሻም በየደረጃው የምትገኙ የሃይማኖት አባቶችና አገልጋዮች የሀገር አንድነትና ሰላም ለማክበርና ለማስከበር ተግታችሁ እንድትጸልዩና ምዕመናንን እንድታስተምሩ ከአደራ ጭምር እናሳስባለን፡፡
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ
ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የጋራ መግለጫ
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
በወቅታዊ ጉዳይ ከማኅበረ ቅዱሳን የተሰጠ መግለጫ
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለችግሩ መፈታት ባላት ቁርጠኝነት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ የሰላም ልዑክ ወደ ክልሉ በመላክ በክልሉ ለደረሰው ጉዳት ሰብአዊ ድጋፍ የሚውል ብር20,000,000.00(ሃያ ሚሊየን ብር) ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ያስረከበች ሲሆን በዚህም ወቅት ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ለተደረገው የከበረ አቀባበል ቅዱስ ሲኖዶስ አመስግኗል፡፡
ይሁን እንጁ የሰላም ልዑኩ ዋና ተልእኮ የሆነውን በክልሉ ከሚገኙ ብፁዓን አባቶች ጋር ለመወያየት የተያዘውን አጀንዳ በተመለከተ በብፁዕ ወቅዱስ አባታችን የተመራው የሰላም ልዑክ በመቀሌ ሀገረ ስብከት በደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል የተገኘ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያን በመዘጋቱ ምክንያት ቅዱስ ሲኖዶሱ ምልዓተ ጉባኤ በእጅጉ አዝኗል፡፡
በመሆኑም የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አንቀጽ 19 ንዑስ ቁጥር 13 የሕግ ድንጋጌ መሠረት ሐምሌ 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡
በትግራይ ክልል ሐምሌ 9 ይደረጋል የተባለው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ የሕገ ቤተ ክርስቲያንና አንቀጽ 37 እና 38 ያላከበረና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር ተገቢ ያልሆነ የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊነት የሚጥስ፣ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚጎዳና በጦርነት የተጎዳውን ሀብት ንብረቱ የወደመበትን ገዳማቱና አብያተ ክርስቲያናቱ የተጎዱበትን ሕዝብ የማይጠቅም ተገቢነት የሌለው በመሆኑ እንዲቆም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
በትግራይ ክልል ተከስቶ የነበረውን ችግር የፌዴራል መንግሥትና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ችግሩን በውይይት የፈቱት መሆኑ እየታወቀ የሰላም ባለቤት የሆነችው ቤተ ክርስቲያን እስካሁን ሰላም መፈለጓ ያልተቋረጠ ቢሆንም አለመሳካቱ የሚያሳዝን በመሆኑ ለሰላም የሚደረገው ጥረት ዘላቂ መፍትሔ እስከሚገኝ ድረስ የማይቋረጥ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ይገልጻል፡፡
በመሆኑም ክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ክቡር አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እንዲሁም የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እየተደረገ ያለውን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ያልተከተለ የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ እንዲያስቆሙልን ብሎም ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ችግሮቹ በውይይት እንዲፈቱ መንግሥታዊ እገዛ በማድረግ የውይይት መድረክ እንዲያመቻቹልን ሲል የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
በመላው ዓለም የምትገኙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ሕዝበ ክርስቲያን እናት ቤተ ክርስቲያናችሁ ያስተላለፈችውን የሰላም ጥሪ ተግባራዊ ሆኖ አንድነቷ ጸንቶ ይኖር ዘንድ በጸሎት ተግጋችሁ ከቤተ ክርስቲያናችሁ ጎን እንድትቆሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ሐምሌ 6 ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
🟢 🟡 🔴 | ሐምሌ 5
#ቅዱስ_ጳውሎስ_ሐዋርያ
የቤተ ክርስቲያን ብርሃኗ #ቅዱስ_ጳውሎስ ከነገደ ብንያም ሳውል የሚባል የጠርሴስ ሰው ሲሆን ምሑረ ኦሪት፣ ቀናተኛና ፈሪሳዊ ነበር።
ጌታ በደማስቆ ጎዳና ጠርቶ በ3 ቀናት ልዩነት ምርጥ ዕቃ አደረገው። ይህ የሆነው በ42 ዓ/ም ጌታ ባረገ በ8ኛው ዓመት ነበር። ከዚያማ ብርሃን ሆኖ አበራ። ጨው ሆኖ አጣፈጠ።
ከኢየሩሳሌም እስከ ሮም፣ ከእንግሊዝ እስከ እልዋሪቆን (የዓለም መጨረሻ) ወንጌልን ሰበከ። ስለ ወንጌል ተደበደበ፤ ታሠረ፤ በእሳት ተቃጠለ። በድንጋይ ተወገረ፣ በጦር ተወጋ።
ባፍም በመጣፍም ብሎ አገለገለ። በየቦታውም ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ሠራ። ለ25 ዓመታት ቀንና ሌሊት ያለ መታከት ወንጌልን ሰበከ።
እርሱን የመሰሉ እርሱንም ያከሉ ብዙ አርድእትን አፍርቶ፣ በ67 ዓ/ም በኔሮን ቄሳር ትእዛዝ አንገቱ ተቆርጧል። ከ14ቱ መልዕክታቱ ባሻገር ቅዱስ ሉቃስ ወንጌልን ሲጽፍ አግዞታል። ልክ ቅዱስ ጴጥሮስ ማርቆስን እንዳገዘው።
የቅዱስ ጳውሎስ መጠሪያዎች፦
1. ሳውል (ከእግዚአብሔር የተሰጠ)
2. #ልሳነ_ዕፍረት (አንደበቱ እንደ ሽቱ የሚጣፍጥ)
3. #ልሳነ_ክርስቶስ (የክርስቶስ አንደበቱ)
4. #ብርሃነ_ዓለም
5. #ማኅቶተ_ቤተ_ክርስቲያን (የቤተ ክርስቲያን መቅረዝ)
6. #የአሕዛብ_መምሕር
7. #መራሒ (ወደ መንግስተ ሰማያት የሚመራ)
8. #አእኩዋቲ (በምስጋና የተሞላ)
9. #ንዋይ_ኅሩይ (ምርጥ ዕቃ)
10. #መዶሻ (ለአጋንንትና መናፍቃን)
11. #መርስ (ወደብ)
12. #ዛኅን (ጸጥታ)
13. #ነቅዐ_ሕይወት (የሕይወት ትምህርትን ከአንደበቱ ያፈለቀ)
14. #ዐዘቅተ_ጥበብ (የጥበብ ምንጭ / ባሕር)
15. #ፈዋሴ_ዱያን (ድውያንን የፈወሰ) . . .
እግዚአብሔር የአባቶቻችንን ብርሃን ያብራልን። ከበረከታቸውም ያድለን።
◦🌿◦🌿◦🌿◦
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
ቅዱስ ጴጥሮስ ለሐዋርያነት ሲጠራ መተዳደሪያው ዓሣ በማጥመድ ነበር፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለሐዋርያነት ሲጠራ መተዳደሪያው የነበረውን መረቡንና ታንኳውን እንዲሁም አባቱን እርግፍ አድርጐ ትቶ ጌታውን የተከተለ ሐዋርያ ነው።
ቅዱስ ጴጥሮስ የሐዋርያት አለቃ ሆኖ ተሹሟል፡፡ ለአገልግሎት ከተጠራበት ጊዜ ጀምሮም በእስያ፣ በሮም፣ በሰማርያ፣ በልዳ፣ በኢዮጴ፣ በአንጾኪያ፣ በገላትያና በሌሎችም አገሮች እየተዘዋወረ ወንጌልን ሰብኳል፡፡ በስብከቱ ምክንያትም ልዩ ልዩ መከራን ተቀብሏል፡፡ በክርስቶስ ኀይል በመታመኑ በክርስቶስ ስም ጣቢታን ከሞት አስነሥቷል፤ ይህም አንዱ ድንቅ ተአምራቱ ነው (ሐዋ.፱፡፴፮)፡፡ ከተሰጠው ጸጋ ብዛት የተነሣ በጥላው ሕሙማን ይፈወሱ ነበር (ሐዋ. ፭፥፲፭)፡፡ ሐዋርያው በቃል ካስተማረው ትምህርት በተጨማሪ በመጽሐፍ ቅዱስ በስሙ የተመዘገቡ ሁለት መልእክታትን ጽፏል፡፡ (፩ኛእና ፪ኛ ጴጥሮስ)
የቅዱስ ጴጥሮስ በሰማዕትነት
በቅዱስ ጴጥሮስ ምድራዊ የአገልግሎት ዘመን የክርስቲያኖች ጠላት የነበረው የሮም ንጉሥ ወደ አካይያ ዘምቶ ድል አድርጎ በደስታ ወደ ሮሜ ሲመለስ መኳንንቱን ለማስደሰት፣ ጣዖታቱንም ለማክበር ሲል በቅዱስ ጴጥሮስና በሌሎችም ክርስቲያኖች ላይ የሞት ፍርድ ዓወጀ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም በሮም ሲያስተምር ቆይቶ የሀገሪቱ መኳንንት እንዳይገድሉት ትጥቁን ለውጦ ከሮም ሲወጣ ጌታችን መስቀል ተሸክሞ ሣለ በተገለጸለት ጊዜ ‹‹አቤቱ ጌታ ሆይ ወዴት ትሔዳለህ?›› በማለት ጠየቀው፡፡ ጌታችንም ‹‹ዳግም ልሰቀል ወደ ሮም እሔዳለሁ›› አለው፡፡ ‹‹ዳግመኛ ትሰቀላለህን?›› ባለው ጊዜም ‹‹አንተ ስትፈራ ጊዜ ነው›› በማለት መለሰለት፡፡ ያን ጊዜም ‹‹ጐልማሳ ሳለህ ወገብህን ታጥቀህ ወደ ወደድኸው ትሔድ ነበር፡፡ ስትሸመግል እጅህን ታነሣለህ፤ ሌላ ሰው ያስታጥቅሃል፤ ወደ ማትወደውም ይወስድሃል›› በማለት አሟሟቱን የሚያመለክት መሆኑን አስታውሶ ወደ ሮም ተመልሶ ስብከቱን ቀጠለ፡፡ (ዮሐ.፳፩፥፲፰)
ቅዱስ ጴጥሮስ ዜግነቱ ሮማዊ ስላልነበረ በግርፋትም፣ በእስራትም በሞትም እንዲቀጣ ተፈረደበት፡፡ እንደ ሥርዓታቸውም ቅዱስ ጴጥሮስን ከገረፉት በኋላ ሊሰቅሉት ሲሉ ወታደሮቹን ‹‹እንደ ክብር ንጉሥ እንደ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አቁማችሁ ሳይሆን፣ ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ›› አላቸው፡፡ እነርሱም እንዳላቸው አድርገው ሐምሌ ፭ ቀን ዘቅዝቀው ሰቅለውታል፡፡ በመስቀል ላይ ሳለም ተከታዮቹን በሃይማኖታቸው እንዲጸኑ ካዘዛቸው በኋላ ነፍሱን ለእግዚአብሔር ሰጠ፡፡ ሥጋውንም መርቄሎስ የሚባለው ደቀ መዝሙሩ ሽቱ ቀብቶ፣ በነጭ ሐር ገንዞ ዛሬ ቫቲካን በምትባለዋ ስፍራ በክብር ቀብሮታል፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ
ቅዱስ ጳውሎስ የጥንቱ ስሙ ‹ሳውል› ይባል ነበር፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ ደግሞ በ ፲፭ ዓመት ዕድሜው በገማልያ ትምህርት ቤት በመግባት የአይሁድን ሕግና ሥርዓት ተምሯል፡፡ በ፴ ዓመቱም የአይሁድ ሸንጎ አባል ሆኗል፡፡ (፩ኛቆሮ.፩.፲፯፣ሐዋ.፳፪.፫) ከኦሪቱ ምሁር ከገማልያል ሕገ ኦሪትንና መጻሕፍተ ነቢያትን ተምሯል፡፡ ለኦሪታዊ እምነቱ ቀናተኛ በመሆኑ ክርስቲያኖችን በማናቸውም አጋጣሚ ይቃወም ነበር፡፡ በ፴፪ ዓመት ዕድሜውም ከኢየሩሳሌም ሁለት መቶ ሃያ ሦስት ኪሎ ሜትር ርቀት በስተሰሜን በኩል በምትገኘው የደማስቆ ከተማ ብዙ ክርስቲያኖች መኖራቸውን ሲሰማ ክርስቲያኖችን ለማሳደድ የሚያስችለውን የፈቃድ ደብዳቤ ከባለሥልጣናቱ አገኘ፡፡ ለሕገ ኦሪት ቀናኢ ከመሆኑ የተነሣም የክርስቶስ ተከታዮችን ሁሉ ያሳድድ ነበር፡፡
ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ ተደብድቦ በሰማዕትነት በሞተ ጊዜ ቅዱስ ጳውሎስ የገዳዮቹ ልብስ ጠባቂ ነበር፡፡ (ሐዋ.፯፥፶፰፣ ፳፪፥፳) ክርስቲያኖችን ለማሳደድ ወደ ደማስቆ ሲሔድ ከመንገድ ላይ ለሐዋርያነት ተጠርቷል፡፡ (ሐዋ.፱፥፩-፴፩፣፳፪፥፩-፳፩) ለሐዋርያነት ከተጠራበት ጊዜ ጀምሮም በመላው ዓለም እየተዘዋወረ ወንጌልን በመስበክ ብዙዎችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሳምኗል፡፡ ሲሰብክም ጣዖት አምላኪ፣ ሕመምተኛ፣ ችግረኛ፣ አረማዊና አይሁዳዊ እየመሰለ ብዙዎችን አስተምሮ ለእግዚአብሔር መንግሥት አዘጋጅቷል:: (፩ኛቆሮ.፱፥፲፱-፳፫) ዐረብ፣ አንጾኪያ፣ እልዋሪቆን፣ ሊቃኦንያ፣ ሦርያ፣ ግሪክና ልስጥራን ካስተማረባቸው አገሮች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ወንጌልን በመስበኩ ምክንያትም ከአይሁድና ከአረማውያን ዘንድ ብዙ መከራና ሥቃይ ደርሶበታል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ከእግዚአብሔር በተሰጠው ጸጋ ብዙ ድንቆችንና ተአምራትን አድርጓል፡፡ በልብሱ ቅዳጅም ሕሙማን ይፈወሱ ነበር፡፡ (ሐዋ.፲፱፥፲፩) ሐዋርያው በቃል ካስተማረው ሌላ በመጽሐፍ ቅዱስ በስሙ የተመዘገቡ ፲፬ መልእክታት አሉት፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ ሰማዕትነት አገልግሎቱን ሊፈጽም ሲልም የሮም ንጉሥ ኔሮን ቄሣር የክርስቲያኖች ቍጥር እየጨመረ የመጣው በቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት በመማረካቸው ምክንያት መሆኑን ተረድቶ፣ ይልቁንም የቤተ መንግሥቱ ሰዎች ሳይቀር በቅዱስ ጳውሎስ በመማረካቸው ተቈጥቶ ቅዱስ ጳውሎስን ወደ ፍርድ ሸንጎው አስቀረበው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም በቀኝ እጁ ከሰንሰለቱ ጋር መስቀሉን ይዞ ንጉሡንና ወታደሮችን ሳይፈራ የኢየሱስ ክርስቶስን የእግዚአብሔር ልጅነትና አምላካዊ ሥልጣን ይመሰክር ነበር፡፡ ንጉሡም በቍጣ እንዲሞት ፈረደበት፡፡ ከላይ እንደ ተገለጸው ሮማውያን የሞት ፍርድ ሲፈርዱ የሚቀጣው ሰው የሌላ አገር ዜጋ ከሆነ ከፍርዱ ውጪ ተጨማሪ ቅጣት ይቀጡትና ይገድሉት ነበር፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ግን የሮም ዜግነት ስለ ነበረው ሳይገርፉ በአንድ ቅጣት ብቻ በሰይፍ እንዲገደል ወስነውበታል፡፡ ወደሚገደልበት ስፍራ ሲወስዱትም በንግግሩና በአስተያየቱ ሁሉ ምንም ፍርሃት አይታይበትም ነበር፡፡ እንዳውም በጦርነት ድል አድርጎና ማርኮ እንደ ተመለሰ ወታደር ይደሰት ነበር እንጂ፤ ለሚገድሉትም ይቅርታን ይለምን ነበር፡፡
በገዳዮቹና በተከታዮቹ ፊትም የክርስትና ሽልማቱ የእግዚአብሔር መንግሥት መሆኑን የሚያስገነዝብ ቃል እያስተማረ እግዚአብሔር የሚሰጠውን የጽድቅ አክሊል ለመቀበል ይቻኮል ነበር፡፡ (፪ኛቆሮ. ፬፥፮-፲፰) ወታደሮች ሊገድሉት ሲወስዱትም ከንጉሥ ኔሮን ወገን የሆነችውን የአንዲት ብላቴና መጐናጸፊያ ‹‹ዛሬ እመልስልሻለሁ›› ብሎ ከተቀበላት በኋላ ‹‹መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤ ሩጫዬን ጨርሻለሁ፡፡ ሃይማኖቴን ጠብቄአለሁ፤ ወደፊትም የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል›› በማለት ራሱ በመልእክቱ እንደ ተናገረው ፊቱን በብላቴናዋ መጐናጸፊያ ተሸፍኖ አንገቱን በሰይፍ ተቀልቶ አገልግሎቱን በሰማዕትነት ፈጽሟል፡፡ (፪ኛጢሞ.፬፥፯-፰)
ደቀ መዛሙርቱም ራሱን ከአንገቱ ጋር ቢያደርጉት እንደ ቀድሞው ደኅና ሆኖላቸው በክብር ገንዘው ቀብረውታል፡፡ ሰያፊው ቅዱስ ጳውሎስን እንደ ገደለው ለመናገር ወደ ንጉሡ ሲመለስም ያቺ መጐናጸፊያዋን የሰጠችው ብላቴና ‹‹ጳውሎስ ወዴት አለ?›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹ራሱን ተቈርጦ በመጐናጸፊያሽ ተሸፍኖ ወድቋል›› ሲላት ‹‹ዋሽተሃል፤ እነሆ ጴጥሮስና ጳውሎስ በእኔ በኩል አልፈው ሔዱ፤ እነርሱም የመንግሥት ልብስ ለብሰዋል፤ በራሳቸውም በዕንቍ ያጌጡ አክሊላትን አድርገዋል፤ መጐናጸፊያዬንም ሰጡኝ፤ ይህችውም እነኋት፤ ተመልከታት›› ብላ ሰጠቸው፤ ከእርሱ ጋር ለነበሩትም አሳየቻቸው፤ አይተውም አደነቁ፤ ስለዚህም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ፡፡ ቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳውሎስ በስብከተ ወንጌል አገልግሎታቸው ጨለማውን ዓለም በማድመቃቸው ‹ብርሃናተ ዓለም› ተብለው ይጠራሉ፤ የቅዱሳኑ አገልግሎት፣ ገድላቸው እና ተአምራቸው በመጽሐፈ ስንክሳር፣ በዜና ሐዋርያት እና በገድለ ሐዋርያት
ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅዱስነታቸው በመቀሌ ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና ወደ ሚገኘው ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለጸሎት ቢያመሩም የቤተ ክርስቲያኑ በር ተዘግቶባቸው ቅዱስነታቸውና የመሩት የሰላም ልዑክ በር ላይ ጸሎት ለማድረስ ተገደዋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው "ቤተ ክርስቲያን ዘግይታም ቢሆን ተጎጂዎችን ለመጎብኘትና ከብፁዓን አባቶች ጋር ለመወያየት ልዑካን መላኳ ተገቢ መሆኑን ገልጸው ጉዳዩ በውይይት መፈታት እንዳለበት እናምናለን" ብለዋል። አያያይዘውም "ይሄ ነገር አንድ እምነት በሚከተሉ ወንድማማቾች ዘንድ አንድ ማኅበር ውስጥ ባሉ ዘንድ የሚፈጠር ልዩነት በምክክር ነው መፈታት ያለበት ግን እንደ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አንገባም።
በሃይማኖት መካከል ጣልቃ አንገባም ማለት በእንደዚህ ዓይነት ምክንያቶች የሚፈጠሩ ልዩነቶች የሚፈጥሯቸው ጣጣዎች አይመለከቱንም ማለት ግን አይደለም" ብለዋል።
የልዑካን ቡድኑ በትግራይ የሚገኙ ተፈናቃዮችን የጎበኙ ሲሆን በነገው ዕለትም በጉዞው ዙሪያ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘገባው የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
ለትግራይ ክልል የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገች
********
(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለትግራይ ክልል የ፳ ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገች፡፡በድጋፍ ርክክብ መርሐ ግብሩ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና ልዑካን ቡድኑ ተገኝተዋል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና የልዑካን ቡድኑ መቀሌ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ርዕሰ መስታድር አቶ ጌታቸው ረዳ እና የመስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አማኑኤል አሰፋ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ቅዱስናውና የሰላም ልዑካን ቡድኑ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር በመቀሌ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ተገናኝተው ተወያይተዋል።
ምንጭ: EOTC PUBLIC REALTION
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የማኅበራት ምዝገባና ክትትል መምሪያ ቀጣዩን የሥራ አተገባበር አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያ የማኅበራት ምዝገባና ክትትል መምሪያ በጥቅምት ወር ፳፻፲፭ ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ዕውቅና ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ የውስጥ አሠራሩን ሲያመቻች የቆየ መሆኑን የሕግ ባለሙያው አቶ አያሌው ቢታኒ ሐምሌ ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።
የሕግ ባለሙያው አቶ አያሌው ቢታኒ ከዚሁ ጋር አያይዘው እንዳብራሩት የማኅበራት ምዝገባና ክትትል መምሪያ የመተዳደሪያ ደንብና የአፈጻጸም መመሪያ ተዘጋጅቶለታል።
ለተመዝጋቢ ማኅበራትም ሞዴል የሚሆን ቅጽ ተዘጋጅቷል ያሉት የሕግ ባለሙያው ወደ ምዝገባ የሚገቡ ማኅበራት የጠቅላላ አባላቱ ቁጥር ሰባት መቶ ሀምሣ እና ከዚያ በላይ የሆኑ ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ መሆናቸው በማስረጃ የተረጋገጠላቸው፣የንስሐ አባት የያዙ፣ በትምህርተ ሃይማኖት በቂ ዕውቀት ያላቸው ይሆናሉ ብለዋል።
@ortodoxtewadochannal