ortodoxtewadochannal | Unsorted

Telegram-канал ortodoxtewadochannal - ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

1920

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቀ አስተምህሮ ✝መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር ይቀሰቀስኛል ለስሙ አንድዘምር🔔 የማንቂያ ደዉል🔔🔔 ክርስትና ዘር የለውም

Subscribe to a channel

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ነሐሴ 2-ቅድስት ኢዮጰራቅስያ እና ዲያቆናዊት ኢዮኤልያም ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት አባ ዮሐንስ ሐጺር ለንስሓ ያበቋት ቅድስት አትናስያ ዕረፍቷ ነው፡፡
+ ሰማዕቱ ቅዱስ ደሚና እና ሰማዕታት የሆኑ ወንድሞቹ መታሰቢያቸው መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሳቸዋል፡፡
ቅድስት ኢዮጰራቅስያ፡- አባቷ ኢጣጎኖስ የንጉሡ አማካሪ የነበረ ሲሆን እርሱም ሆነ ባለቤቱ በጾም ጸሎት የሚተጉ ደጋግ ክርስቲያኖች ነበሩ፡፡ ልጃቸውን ቅድስት ኢዮጰራቅስያን በወለዱ ጊዜ በእናቲቱ ስም ሰየሟት፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ አባቷ ስላረፈ እናቷ ኢዮጰራቅስያን ገና በ6 ዓመቷ ይዛት ወደ ገዳም ገባች፡፡ መነኮሳቱንም አይታ እናቷን ‹‹ለምን እንዲህ ይደክማሉ?›› አለቻት፡፡ እናቷም ‹‹ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ሲሉ ነው እንዲህ የሚደክሙት›› አለቻት፡፡ ከዚህም ጊዜ ጀምሮ የመነኮሳቱን የተጋድሎና የጾም ጸሎት ሕይወት እያየች አደገችና ከፍ ስትል እርሷም መነኮሰችና በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመረች፡፡ ጾም ጸሎቷን በማብዛት በየሰባት ቀን ትጾም ጀመር፡፡ ከዚህ በኋላ ሰይጣን በቅናት ተነሣባትና በተለያየ ፈተና ይጥላት ጀመር፡፡ ውኃ ልትቀዳ ወደ ወንዝ ብትሄድ ውኃ ውስጥ ይጥላት ነበር፤ እንጨት ስትፈልጥ ቢያያት በመጥረቢያው እየመታ ያቆስላታል፡፡ እርሷ ግን መነኮሳቱን እያገለገለች ሌሊቱን ሙሉ ለጸሎት ቆማ ታድራለች፡፡ እስከ 40 ቀን ድረስ ቆማ ስትጸልይ ቢመለከቷት ደናግል ሁሉ ይደነቁባት ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን የተለያዩ አስገራሚ ተአምራትን የማድረግ ጸጋ ሰጣትና አጋንንትን ማስወጣት፣ ሕሙማንን መፈወስ፣ የዕውራንን ዐይን ማብራት ጀመረች፡፡
ቅድስት ኢዮኤልያም የምትባል ዲያቆናዊት ጓደኛ ነበረቻትና መጸሕፍትን ሁሉ አብረው ተምረው በተጋድሎ ሲኖሩ ከዕለታት በአንዱ ቀን ይህች ዲያቆናዊት የቅድስት ኢዮጰራቅስያን ነፍስ ቅዱሳን መላእክት ሲያሳርጓት በራእይ አይታ ለደናግል ነገረቻቸው፡፡ ተያይዘውም ሄደው ቅድስት ኢዮጰራቅስያን ጠየቋት፡፡ እርሷም መርቃቸው ከተሰናበተቻቸው በኋላ በዚህች ዕለት ዐርፋ በእናቷ መቃብር ቀብረዋታል፡፡ ወዳጇ ኢዮኤልያም ወደ መቃብሯ ሄዳ ከጸለየች በኋላ በሦስተኛው ቀን ዐርፋ እርሷንም ከቅድስት ኢዮጰራቅስያ ጋር ቀበሯት፡፡ የሰማዕታቱ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
+ + + + +
ቅድስት አትናስያ፡- መኑፍ በሚባል አገር የሚኖሩትና ከመንግሥት ወገን የሆኑት ወላጆቿ ባለጸጎች ስለነበሩ እነርሱ በሞቱ ጊዜ ቅድስት አትናስያ ቤቷን ለእንግዶች ማረፊያ አደረገችው፡፡ እንግዶችን በመቀበልና በገንዘቧ ገዳማትንና መነኮሳትን የምትረዳ ደገኛ ሴት ናት፡፡ በዚህም በጎ ተግባሯ እርሷን ሁሉም መነኮሳት ይወዷት ነበር፡፡ የበጎ ነገር ጥንተ ጠላት ሰይጣን ግን በቅናት ተነሥቶ ክፉ ሰዎችን አነሳሥቶ ክፉ ምክር እንዲመክሯት አደረጋቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ሰይጣን በክፉ ሰዎች አስመክሮ በወጥመዱ ጣላትና በዝሙት እንድትወድቅ አደረጋት፡፡
አትናስያም ዘማዊ ሴት ሆነችና አብዝታ ኃጢአትን ትሠራ ጀመር፡፡ በቀድሞ የቅድስና ሕይወቷ የሚያውቋት የአስቄጥስ ገዳም መነኮሳት ሁሉ ስለ እርሷ መውደቅ እጅግ አዘኑ፡፡ እነርሱም መክረው ሊመልሷት ቢሞክሩ አልመለስላቸው አለች፡፡ ይልቁንም ሊመክሯት ሲመጡ እየሳቀችባቸው ታሾፍባቸው ጀመር፡፡ በመጨረሻም መነኮሳቱ ታላቁን ጻድቅ አቡነ ዮሐንስ ሐፂርን ላኳቸው፡፡ ምክንያቱም አስቀድማ ከአባ ዮሐንስ ሐፂር ጋር ብዙ በጎ ተግባራትን ሠርታ ስለነበር ነው፡፡ አባ ዮሐንስም በጸለት እንዲያስቡአቸው መነኮሳቱን ጠይቀው ተራ ሰው መስለው  ወደ ከተማ ከወጡ በኋላ አትናስያ ቤት ደረሱ፡፡ ለጠባቂዋም ‹‹ለእመቤትሽ እኔ ወደ እርሷ መግባት እንደምፈልግ ንገሪልኝ›› አሏት፡፡ አትናስያም ለዝሙት የመጣ ተራ ሰው መስሏት አጊጣ ተኳኩላ በአልጋዋ ላይ ሆና በደስታ ተቀበለችው፡፡ ልታጫውተውም ስትሞክር አባ ዮሐንስ ግን ማልቀስ ጀመረ፡፡ ‹‹ለምን ታለቅሳለህ?›› ብትለው ‹‹መልክሽ ደስ ብሎኝ›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹ታዲያ ደስ የሚል መልክ ያስቃል እንጂ መች ያስለቅሳል?›› ስትለው ‹‹የለም ነገ ገሃነም እንደምትወርጂ ታይቶኝ ነው፣ እነሆ የሰይጣን ማደሪያ ሆነሽ ብዙ አጋንንት በሰውነትሽ ሲወጡ ሲወርዱ አያለሁ… ›› እያሉ ብዙ አስተማሯት፣ መከሯት፡፡ እርሷም ዓይነ ልቡናዋ ተከፍቶላት ወደ ልቧ ተመለሰችና ቃሉን ሰምታ ደነገጠች፡፡ በመጸጸትም ‹‹ታዲያ ምን ባደርግ ይሻለኛል?›› አለቻቸው፡፡ ‹‹ንስሃ ግቢ›› አሏት፡፡ ‹‹በውኑ አሁን እኔ ምሕረት አገኛለሁን? ኃጢያቴ ብዙ ነው፣ ከእግዚአብሔር ጋር ማን ያስታርቀኛል?›› ስትላቸው ‹‹እኔ አስታርቅሻለሁ ተከተይኝ›› ብለው ወጥተው ሄዱ፡፡ እርሷም ልዋል ልደር ሳትል በሯ እንደተከፈተ ቤት ንብረቷን ትታ አባ ዮሐንስን ተከተለቻቸው፡፡ እሳቸው ላይ ለመድረስ እየሮጠች ስትሄድ በልስላሴ የኖረ እግሯ እየቆሰለና እየተሰነጣጠቀ ደሟ እንደ ውኃ መሬት ላይ ፈሰሰ፡፡ ሲመሽ ከገዳሙ በር ላይ ደርሳ የምታርፍበትን ቦታ ለይተው ሰጧትና እዚያ ተኛች፡፡ አባ ዮሐንስ ሌሊት ለጸሎት ሲነሡ መላእክት ሲወጡ ሲወርዱ ተመልክተው ‹‹ይህ የማየው ነገር ምንድን ነው?›› በማለት አንዱን መልአክ ጠየቁት፡፡ ‹‹ትላንትና አንተን ተከትላ የመጣችው ሴት ሞታ ነፍሷን እያሳረግን ነው›› አላቸው፡፡ አባ ዮሐንስም ‹‹እግዚኦ ንስሓ ሳትገባ›› ብለው ደነገጡ፡፡ መልአኩም ‹‹አንተን ልትከተል ገና አንድ እግሯን ከቤት ስታወጣ ኃጢአቷ በሙሉ ተፍቆላታል፤ አሁን ወደ ገነት እየወሰድናት ነው›› አላቸው፡፡ አባ ዮሐንስ ሐጺርም ወደ አትናስያ ሮጠው ቢሄዱ ዐርፋ አገኟትና ተገርመው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ‹‹የመቃብሯስ ነገር እንዴት ነው?›› ብለው ጠየቁት፡፡ መልአኩም ‹‹አንበሶች ይመጣሉ የመቃብሯን ቦታ ለክተህ አሳያቸው›› ብሏቸው ተሰወረ፡፡ አንበሶቹም መጥተው አባ ዮሐንስ ቦታውን ለክተውላቸው አንበሶቹ መቃብሩን ቆፍረው በክብር ቀብረዋታል፡፡ ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን  አሜን፡ @ortodoxtewadochannal @ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

​​ሱባዔ ለምን?
#ክፍል_ሁለት

የሰው ልጅ፤ ኃጢአት በሚስማማው የሥጋ ሰውነቱ ዘወትር ፈጣሪውን ይበድላል፡፡ በፈጸመው በደል ኅሊናው ይወቅሰዋል፤ ይጸጸታል፡፡ በመጀመሪያ ደፍሮ በሠራው ኃጢአት በኋላ ይደነግጣል፡፡ ይህ በማንኛውም ሰብአዊ ፍጥረት ኅሊና ውስጥ የሚፈራረቅ ክስተት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ የፈጣሪውን ይቅርታ ለማግኘት ያስባል፤ ይተክዛል፡፡

በውስጡ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛል. ነገር ግን በብልቶቼ ባለ በኃጢአት ሕግ የሚማርከኝ ሌላ ሕግ አያለሁ፡፡ እኔ ምንኛ ጐስቋላ ሰው ነኝ ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል? እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ፡፡ ሮሜ.7.22-25፡፡

ሰው በደፋርነቱ የኃያሉን አምላክ ትእዛዝ ተላልፎ ትካዜ ሽክም ሲያስጨንቀው ሸክሙን የሚያቃልልበትና የሚያስወግድበት መንፈሳዊ ጥበብ ከቸሩ ፈጣሪ ተሰጥቶታል፡፡ ይኸውም በጥቂት ድካመ ሥጋ ጸጋ እግዚአብሔር የሚያገኝበት ሥርዓት ሱባዔ ነው፡፡ ከጥንት እስከ ዛሬ አንድ ሰው በትካዜ ሽክም መንፈሱ ሲታወክ የነፍስና የሥጋ ጸጥታውን ለመመለስና ለማስከበር መጾምና መጸለይ ግድ ይሆንበታል፡፡ በዚህ ጊዜ አመክሮ /ሱባዔ/ ይገባል፡፡

እግዚአብሔርን ለመማፀን ሰው ሱባዔ ከሚገባባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች አንዱ እግዚአብሔርን ለመማፀን ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ሱባዔ ሲገባ በቁርጥ ወደ ፈጣሪው የሚያቀርበው ተማኅፅኖ ሊኖረው ይገባል፡፡ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታና ዝግጅት ሱባዔ የሚገቡ ሰዎች ከሱባዔ በኋላ ምን እንደ ተመለሰላቸው የሚያውቁት ነገር ስለማይኖር ሱባዔ በመግባታቸው የሚያገኙት ነገር የለም፡፡

ስለዚህ ሱባዔ ከመግባታችን በፊት፡- ሱባዔ የምገባው ለምንድን ነው? በማለት ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ ለምሳሌ አንድ ክርስቲያን በግል ሕይወቱ ዙሪያ ስለ ሀገር ሰላም፣ ስለ ጓደኛው ጤና ወዘተ ጉዳዮች ላይ ፈጣሪውን ይማፀናል፡፡ በዚህ ጊዜ በግል ሕይወቱም ሆነ በሀገር ጉዳይ ለገባው ሱባዔ ወዲያውኑ መልስ ሊያገኝ ይችላል፤ እንዲሁም መልሱ ሊዘገይ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ከተሐራሚው ትዕግሥት /መታገሥ/ ይጠበቅበታል፤ «ለምን ላቀረብኩት ጥያቄ ቶሎ መልስ አልተሰጠኝ?» በማለት ማማረርና እግዚአብሔርን መፈታተን ተገቢ አይደለም፡፡

ለምሳሌ በጓደኛው ውድቀት ምክንያት ሱባዔ ገብቶ በአንድ ሳምንት ውስጥ መልስ ያገኘ የአንድ ገዳም አገልጋይ ታሪክ መመልከት ተገቢ ነው፡፡

አኃው ለተልእኮ በወጡበት አንዱን ድቀት አግኝቶት ያድሯል፡፡ በነጋው ወንድሜ እኔ ድቀት አግኝቶኛልና እንግዲህ ወዲህ ተመልሼ ከዚያ ገዳም አልሔድም፤ ሽለሙን መስዬ እኖራለሁ አለው፡፡እኔም እንዲሁ አግኝቶኛል፤ ይልቁንስ ሔደን ኃጢአታችንን ለመምህረ ንስሐችን ነግረን፤ ቀኖናችንን ተቀብለን እንደ ቀደመው ኾነን እንኖራለን ብሎ አጽናንቶ ይዞት ሔደ፡፡

ሔደው ለመምህረ ንስሐቸው ነግረው ቀኖናቸውን ተቀብለው 1 /አንድ/ ሱባዔ፣ ቀኖና እንዳደረሱ ሰረይኩ ለከ በእንተ ዘኢገብረ እኁከል፤ ኃጢአት ስላላደረገው ወንድምህ ይቅር ብዬሃለሁ የሚል ድምፅ አሰምቶታል፡፡ /ዜና አበው/፡፡

ከላይ ታሪካቸው የሰፈረው የገዳም አገልጋዮች ለአገልግሎት በተላኩበት አገር አንዱ ድቀት አግኝቶት በዝሙት ሲወድቅ ጓደኛው እንደ እርሱ ድቀት እንዳገኘው አድርጐ ጓደኛውን በማጽናናት ወደ ገዳም በመመለስ አንድነት ኾነው ሱባዔ ይገባሉ፡፡ አንድ ሱባዔ /ሰባት ቀን/ እንደ ጨረሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ኃጢአት ሳይሠራ ለአንተ ብሎ ሱባዔ ስለገባው ወንድምህ ስል ይቅር ብዬሃለሁ የሚል ፈጣን መልስ አግኝቷል፡፡

ስለዚህ ሱባዔ በግል ሕይወትም ሆነ በጓደኛችን ሕይወት ዙሪያ ስንገባ ፈጣን ወይም የዘገየ መልስ ሊሰጠን ስለሚችል በትዕግሥት መጠባበቅ ይኖርብናል፡፡

#ይቀጥላል
በቀጣይ ክፍል ሱባዔ ለመግባት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታና ዝግጅት?

ለእህት ወንድሞች ይማሩበት ዘንድ አጋሩ
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

ቅበላ_ዓላማው_ምንድን_ነው?
         #አንብቡት🗣

🥀ስለ ቅበላ ያለን አመለካከት በልማዳችን ውስጥ የተንሸዋረረ ነው። ከጾም ጋር ተያይዞ በሕዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ ከሚፈጸሙ ተግባራት መካከል በአጽማት መግቢያ የሚደረገው የአቀባበለ ሥነ ሥርዓት ነው። ይህ ሥርዓት በራሱ መጸሐፍ ቅዱሳዊ ይዘት ያለውና በጥንታዊቷ ቤተክርስቲያንም የተለመደ ትውፊታዊ ቅብብሎሽ ያለው ሥርዓት ነው። ይህ ግን አሁን ከምንፈጽመው የቅበላ ሥርዓት የተለየ ነበር። ጥቂት ማሳያዎችን እንመልከት።

❶➪🥀በመጸሐፍ ቅዱስ አይሁድ ቀዳሚት ሰንበት ከመግባቷ በፊት በዋዜማው የተለየ አቀባበል ያደርጉ ነበር። ዓርብ ፀሐይ ሲገባ ካህኑ ደውል
ይደውላሉ አሊያም በቤት ያለ የቤቱ አባወራ የሰንበት
መግቢያ ሰዓት መቃረቡን ድምጽ በማሰማት ያሳውቃል፡፡ በአካባቢው ያሉ ሁሉ ይሰበሰባሉ፡፡ በአንድ ላይ ሆነው ወደ ፀሐይ መውጫ ይሰግዳሉ፡፡ ጸሎት ይደረጋል፡፡ ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ እስራኤል፣አሥርቱ ቃላት ሌሎችም ንባባት ይደገማሉ፡፡ ማብራት ተይዞ “ዕለተ ሰንበት እንኳን
ደህና መጣሽ” ብለው ያከብሯታል፡፡ ከሦስት ሰዓት በኋላእራት ይበላሉ፡፡ ሌሊቱን በሙሉ እግዚአብሔርን
ሲያመሰግኑ ያድራሉ፡፡"  ከዚህም ጎን ለጎን ከግብጽ ባርነት መውጣታቸውን ምክንያት በማድረግ ለሚያከብሩት የፋሲካ ሏዓል በታዘዞት መሠረት ጠቦት አዘጋጅተው አቀባበል ያደርጉለት ነበር። ኦዘጸ 25:12

❷➪🥀ትክለኛው ቅበላ ግን ከሕሊና ዝግጅት ጋር ተያያዥነት ያለው ነው። ቀደምት አበው አጽዋማት ከመግባታቸው በፊት ለቤተመቅደስ አገልግሎት የሚሆኑ መገልገያዎችን ያዘጋጃሉ እነርሱም እራሳቸውን ለአገልግሎት ያዘጋጃሉ። ምእመኑም ሱባኤውን የሚያሳልፍበትን ቦታ መርጦ ይጠብቃል ንሰሐ ገብቶ እራሱን ለቅዱስ ቁርባን ያዘጋጃል። የቀማውን ይመልሳል የበደለውንም ይክሳል። ማጠናቀቅ ያለበትን ተግባረ ሥጋ ፈጽሞ ይጠብቃል። በጥቅሉ በጾም ወቅት ሊሟሉ የሚገቡ ውጫዊና ውስጣዊ ዝግጅቶችን በዋዜማው ይፈጽማሉ። ካገኙ  በመጠኑ መቀበያ የፍስክ ምግብ ይመገባሉ ካላገኙ ግዴታ ስላልሆነ ጥሬ ቆሬጥመው ውሀ ተጎንጭተውም ቢሆን ይቀበሉታል።

❸➪🥀አሁን ያለው ደግሞ ፍጹም የተለየ አቀባበል ነው። በጾሙ ላይ ተሳትፎ የሌለውም ያለውም በጠቅላላ የህሊና ዝግጅት የለውም አቀባበል ሲባል ቀጥታ ግንኙነት ያለው ከመብላትና ከመጠጣት ጋር ይመስለዋል። በየቦታው ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሲበላ ሲጠጣ ሲያልፍም ወዳልተገባ ሥጋዊ ስሜት ውስጥ ይገባል። ብዙ ነዳያን የሚቀምሱት ባጡበት ዘመን ከገደብ ያለፈ የአመጋገብ ሥርአት በቅበላ ወቅት የተለመደ ነው። ይህ ከክርስትናው ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም ሰው ለፈቃደ ስጋው ሲያደር የፈጠረው እንጂ። እግዚአብሔር ለቅበላው ስለበላነው እና ስላልበላነው ጉዳይ ሳይሆን ሚያሰበው የእኛ በኃጢአት መኖር መሆኑን ልብ እንበል። ስጋ በልቶ የተቀበል ቆሎ በልቶ ከተቀበለው ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ብልጫ የለውም። ከሁሉ ሚያሳዝነው በቅበላውም በፍቺውም የፍስከ ምግቦች ለመብላት የሚሰለፉት ማይጾሙት መሆናቸው ነው። ስለዚህ በቅበላ ጊዜ "የግድ እነዚህን ካለበላችሁ የሚል ህገ የለም ያገኘም በመጠኑ እና በማያስነውር መልኩ ቢመገብም ነውር የለውም። በአጽማት ስጋ መብሊት አለመብላት ግዴታ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ዝግጅቶች ምናደርግበት ነው።   የሞዐ
  ወስብሐት ለእግዚአብሔር
  ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን ይቆየን

ተቀላቀሉ ቴሌግራም➘ @ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

#መልእክተ_ቅዱስ_ፓትርያርክ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን |

በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንና ምእመናት እንዲሁም ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ እግዚአብሔር አምላካችን በይቅርታውና በምሕረቱ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ አምስት ዓመተ ምሕረት የድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ:: “ወእምኵሉስ ዘይቀድም ተፋቀሩ በበይናቲክሙ በምልአ ልብክሙ እስመ ተፋቅሮ' ይደፍኖን ወይደመስሶን

ለኵሎን ኃጣውእ! ከሁሉ አስቀድሞ በሙሉ ልባችሁ እርስ በርሳችሁ ተፋቀሩ፣ መፋቀር ሁሉንም

ዓይነተ ኃጢአት ይሸፍናልና ይደመስሳልምና (፩ ጴጥ.፬-፰)

ሁላችንም እንደምናውቀው የቅዱስ ወንጌል አስተምህሮ መሠረትና ጣርያ ወለልና ግድግዳ በፍቅርና በፍቅር ብቻ የተገነባ ነው፡ ፍቅር እግዚአብሔር ዓለምን ያዳነበት መድኃኒት ነው፣ ፍቅር የጥላቻና የመለያየት ግንብን ንዶ ይቅርታንና አንድነትን የሚገነባ ጠንካራ ዓለት ነው፣ ፍቅር መጽናናትንና ደስታን የሚያፈራ ጣፋጭ ተክል ነው፤ በፍቅር ለፍቅር የሚደረግ ሁሉ ፍሥሐን እንጂ ጸጸትን አያስከትልም

በመሆኑም በሰብአዊ ድክመት ምክንያት ሰዎች ፍቅርን ሙሉ በሙሉ በሚፈለገው ደረጃ ባንጠብቀውም በዓለማዊም ሆነ በመፈንሳዊ ሕይወት ከፍቅር የበለጠ ጠቃሚ ነገር የለም ፍቅር የማይሻርና ለዘላለሙ ጸንቶ የሚኖር እንደሆነ በቅዱስ መጽሐፍ ተመዘግቦአል፤ ምክንያቱም ፍቅር ከሞት በኋላም ቢሆን በእግዚአብሔር መንግሥት ይቀጥላልና ነው ዛሬ የሚጀመረው የድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታም በፍቅር ለፍቅር የተፈጸመ ነው፣ ይኸውም ቅዱሳን
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በመጣስ ባልተሰጣቸው ስልጣን 9 ኤጴስ ቆጰሳትን ሾመናል፤ ሲኖዶስ አቋቁመናል በማለት በተለያዩ ሚዲያዎች በሰጡት መግለጫና በክልሉ መንግሥት ሚዲያ በተላለፈው የቀጥታ ስርጭት የተረጋገጠ በመሆኑ በዚሁ ድርጊታቸው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለም የሚኖረውን ሕዝበ ክርስቲያንን በማታለል የክህደት እና የኑፋቄ ተግባር በመፈጸማቸው በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ፤ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸውን ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት በመሻር አውግዞ ለይቷቸዋል፡፡
 
በመሆኑም፡- 

ሀ. ሥልጣነ ክህነታቸውና የማዕረግ ስማቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ውሳኔ የተነሣ ስለሆነ ከዛሬ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በቀድሞ ዓለማዊ ስማቸው እንዲጠሩ፤

ለ. በቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ አገልግሎት ዙርያም በሕይወትም ሆነ በሞት ማናቸውንም መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳያገኙ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ ከቤተ ክርስቲያን ለይቷቸዋል፡፡

• ይሁን እንጅ ከላይ በስም ተጠቅሰው የተወገዙት ግለሰቦች በሠሩት የቀኖና ጥሰት ተጸጽው ይቅርታን ቢጠይቁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምህረት ደጆች ሁል ጊዜ ክፈት መሆናቸውና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት የምንቀበላቸው መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳውቃል፤  
  
2ኛ. የቅዱስ ሲኖዶሱንና የቤተ ክርስቲያኒቱን ልዕልና በመዳፈር እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ በተነሳሱ ግለሰቦች አማካኝነት የኤጲስ ቆጶስነት ሹመት አግኝተናል፤ ተሹመናል እያሉ የሚገኙ 9 መነኮሳት

፩. አባ ዘሥላሴ ማርቆስ

፪. አባ ኃይለ ሚካኤል አረጋይ

፫. አባ እስጢፋኖስ ገብረ ጊዮርጊስ

፬. አባ መሓሪ ሀብቶ
  
፭. አባ ኤልያስ ታደሰ ገብረ ኪዳን

፮. አባ ጽጌ ገነት ኪዳነ ወልድ

፯. አባ ዘርአ ዳዊት ብርሃነ

፰. አባ ዮሐንስ ከበደ

፱.  አባ የማነ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል
በሕገ ወጥ መንገድ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንንን ጥሰው የተገኙ በመሆኑ አስቀድሞ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸው ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት ተሽሮ ከዛሬ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ አገልግሎት ዙርያ በሕይወትም ሆነ በሞት ማናቸውንም መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳያገኙ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ ከቤተ ክርስቲያን ለይቷቸዋል፡፡
  
3ኛ. ይህ ህገወጥ ሢመት እንዲፈጸም ከመጀመሪያው ጽንሰ ሀሳብ ጀምሮ መሪ ተዋናይና ቀስቃሽ በመሆን ኢትዮጵያን ኤልዛቤል በማለትና ስሟን የሚጠራ የተረገመ ይሁን በማለት እንዲሁም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጋር የዶግማ ልዩነት አለን በማለት የኑፋቄ ትምህርት በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የተናገሩትና በህገወጥ ሢመቱ ላይም በእጩነት ተመርጠው በሂደት ላይ ያሉት አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤልና ሂደቱን በዋና አስፈጻሚነት በመምራትና መግለጫ በመስጠት ላይ ያሉት መ/ር ተስፋዬ ሐደራ ከዛሬ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተወግዘው ከቤተክርስቲያን ተለይተዋል።

ከላይ በስም ተጠቅሰው የተወገዙት ግለሰቦች በሠሩት የቀኖና ጥሰት ተጸጽው ይቅርታን ቢጠይቁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምህረት ደጆች ሁል ጊዜ ክፈት መሆናቸውና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት የምንቀበላቸው መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳውቃል።

4ኛ. “መንበረ ሰላማ” የሚለው ሕገወጥ ሥያሜን በተመለከተ በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ትውፊትም ሆነ በቀደምት አብያተ ክርስቲያናት ትውፊት የማይታወቅ፣ ሃይማኖታዊ መሠረት የሌለው፣ ከቀኖና የወጣ፣ አስተዳደራዊ መዋቅርን የሚያዛባ በመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አትቀበለውም፤ በተጨማሪም ከአንዲት፣ ቅድስት፣ ሐዋርያዊትና ዓለም አቀፋዊትየሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ መንበር መሠረተ እምነት፣ ታሪክና ቀኖና፣ ከአስተዳደር እና ሕግ ባፈነገጠ ሁኔታ ትውፊትን በመዳፈር ጎሣን መሠረት አድርጎ የተፈጠረ ሕገ ወጥ አደረጃጀት በመሆኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አውግዞታል፡፡ ይሕንንም የክርስትናን ትውፊት እና ሐዋርያዊ መሠረት የሚዛባና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የማይወክል መሆኑ ታውቆ በመላው ዓለም ለሚመለከተው ሁሉ በደብዳቤ እንዲገለጽ እንዲደረግ፤

6. በየደረጃው የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥራ ኃላፊዎች፤ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ መነኮሳት፤ አገልጋይ ካህናት፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፤ ልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ ማህበራት እና ምእመናን እና ምእመናት ይህን ሕገ ወጥ አድራጎት ከመከላከል እና የቤተ ክርስቲያናችሁን ደህንነት ከመጠበቅ በተጨማሪ ለዚህ ሕገ ወጥ አድራጎት ልዩ ልዩ ድጋፍ የሚያደረግ ተቋማት እና ግለሰቦችን አስፈላጊውን ክትትል እና ቁጥጥር በማድረግ የመከላከል ሥራችሁን እንድትወጡ ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

8. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስምን ከፊትም ሆነ ከኃላ በመጨመር እና በመቀነስ በከፊልም ሆነ በሙሉ መጠቀም፤ ዓርማዋን፤ አድራሻዋን፤የአምልኮ እና የሥርዓት መፈጸሚያ የሆኑ ንዋያ ቅዱሳትንና አልባሳት እንዲሁም መጻሕፍት መገልገል የማይችሉ መሆኑ ታውቆ ይህንን ጉዳይ በየደረጃው ያሉ መንግሥታዊ አካላት እና የቤተ ክርስቲያኒቱ  የሥራ ኃላፊዎች ተከታትለው እንዲያስፈጽሙ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነ ሲሆን በተጨማሪም ይህን ውሳኔ ተላልፈው በሚገኙ ማናቸውም ግለሰቦች እና ተቋማት ላይ ተገቢውን ሕግ አግባብ ተከትሎ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ዓለማት የሚያስፈጽም ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የሕግ ባለሙያዎች በመመደብ ተገቢውን ሁሉ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በኩል እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

9. በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የሚገኙ መንግስታዊም ሆነ መነግስታዊ ያልሆነ ተቋማት፤ አኃት አቢያተ ክርስቲያናት፤ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት፤ የሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እና ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት፤ የዓለም አቢያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት፤ የመላው አፍሪካ አብያት ክርስቲያናት ጉባዔ እና ሌሎች የአብያተ ክርስቲያናት እና የሃይማኖት ጉባኤዎች በሙሉ እነዚህ የተወገዙት ግለሰቦች የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ እና ምንም አይነት የሥራ ግንኙነት የሌላቸው መሆኑ ታውቆ ማናቸውም ግንኙነት በቤተ ክርስቲያኑቱ ስም እንዳያደርጉ በጽሑፍ አንዲገለጽ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
  
11. እነዚህ ግለሰቦች የፈጸሙት ተግባር ሃይማኖቱን የሚወድ፣ አባቶቹን የሚያከብር እና አስተዋይ የሆነውን የትግራይ ሕዝብ የማይወክል፣ የራሳቸውን የሥልጣን ጥማት ለማርካት ያደረጉት ሕገወጥ የቀኖና ጥሰት መሆኑ እንዲታወቅ፤ በተጨማሪም ለሚያሠራጩት የሐሰት አሉባልታ ወደፊት ተገቢው መልስ እንዲሰጥበት ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

12. ይኽ ሕገወጥ አደረጃጀት ከረጅም ጊዜ ጀምሮ የታሰበበት፤ በየጊዜው የነበሩ የፖለቲካ እና የመንግሥት ኃላፊዎች በመታገዝ ሥር የሰደደ ድብቅ አጀንዳ በሚያስፈጽሙ ግለሰቦች የተቀናበረ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ተገንዝቦ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞታል፡፡ በመሆኑም ሕገ ወጥ አደረጃጀትን ማምከን እና ቤተ ክርሰቲያንን ነፃ ማድረግ የሚቻለው ጠንካራ ውስጣዊ አደረጃጀት እና ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ ሲደረግ በመሆኑ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጀምሮ ሊቃውንት፣ መላው ውሉደ ክህነት፣ ወጣቶች ሰንበት ትምሀርት ቤት አባላት፣ መንፈሳውያን ማኅበራት፣ ምእመናን እና
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ።
**

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ
ው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ አምስትና በሕገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ 19 ቁጥር 3 አስቸኳይ ጉዳይ ሲያጋጥም ምልዓተ ጉባኤ እንደሚያደርግ በተደነገገው መሠረት ሐምሌ 26ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በተፈጠረው ወቅታዊ የዶግማ፣ የቀኖናና የአስተዳደራዊ ጥሰቶችን አስመልክቶ ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡

ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊትና ዓለም አቀፋዊት የሆነች ቅድስት ቤተክርስቲያን ሕዝብና አሕዛብን፣ ሰውና መላእክትን፣ ፍጡራን እና ፈጣሪን አንድ አድርጋ የሰው ልጆች ሁሉ በቋንቋ፣ በቀለምና በጐሣ ሳይከፋፈሉ ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና አግኝተው ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማህፀነ ዮርዳኖስ የተወለዱ በማየ ገቦ ተጠምቀው የቤተ ክርስቲያን ልጆች በመሆን ልዩነት የሌለባትን ዘለዓለማዊት መንግሥተ እግዚአብሔር እንዲወርሱ በደመ ክርስቶስ የተመሠረተች ስትሆን በየዘመናቱ የተነሣባትን ፈተና ሁሉ አልፋ ከእኛ ዘመን ደርሳለች፤ 

  ምንም እንኳ ከኦርቶዶክስ ትምህርተ ሃይማኖት ፈጽሞ በተለየ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያንን በጐሣና በቋንቋ የመለየት ሂደት በዓለም አቀፍ ደረጃ እንግዳ ክስተት ቢሆንም ቤተ ክርስቲያን ከሃይማኖታዊና መንፈሳዊ ጠባይዋ በተለየ፣ ታሪኳንና ሥርዓቷን በማይመጥን፣ ከሕግ መንፈሳዊ፣ ከሕግ ጠባይአዊ እና ከሕገ አእምሮ በወጣ መልኩ የደረሰባት የዶግማ፣ የቀኖናና የአስተዳደር ጥሰት ቅዱስ ሲኖዶስን እጅግ አሳዝኖታል፤
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ባወጣው የድርጊት መርሐ ግብር መሠረት ዛሬ በጸሎት የተጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልአተ ጉባኤ ነገ ሐምሌ ፳፮ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም ጠዋት ፪ ሰዓት ከ፴  በተያዙት አጀንዳዎች ላይ በመወያየት የቤተክርስቲያናችንን ቀኖናትና ሕግጋት የሚያስከብሩ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።

የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

በሀገር አቀፍ ደረጃ የፖለቲካ ተሰሚነት እና ውክልና እንዳይኖራት፣ እጅግ ብዙ ችግር እንዲከባት ተሠርቷል፤ አሁንም እየተሠራ ይገኛል፡፡ ይህንም ለማድረግ የተቻለው በተቀናጀ ስልት ሲሆን ሲኖዶሱ ክብሩ ልዕልናው እንዳይጠበቅ በማድረግ፣ የመሪነት ሚናውን እንዳይወጣ፣ የተጠራበትን ሰማያዊ ተልእኮውን እንዳያሳካ፣ በመከፋፈል እና በራሱ ውስጣዊ አጀንዳ እንዲጠለፍና፣ ውሳኔው መሬት እንዳይነካ በማድረግ ነው፡፡ ከምንም በላይ መሪና ተመሪ እንዳይገናኙ፣ ሲኖዶሱ በምእመናን ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጣ አድርጎታል፡፡ ‹‹መሪ የሌላቸው ሕዝቦች እንደረገፉ ቅጠሎች እንደተረበረቡ ግንዶች ናቸው›› እንዲሉ መሪ የማሳጣት መሪና ተመሪን የማለያየት ሥራ ነው፤ የተሠራው አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡

ለዚህም የችግሮቹ ምንጭ ከሁለት ወገን የመጡ ናቸው ብሎ መናገር ይቻላል፡፡
፩. ውስጣዊ ምክንያቶች    ፪.ውጫዊ ምክንያቶች ናቸው፡፡

፪.፩.፩. ውስጣዊ ምክንያቶች /የችግር ምንጮች/

ውስጣዊ የሆነው ችግር ዘርፈ ብዙ ነው፡፡ የተወሰነውን ለማየት ያክል
ሀ. ከራሱ ከቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት የሚመነጩ ችግሮች እየተበራከቱ መምጣታቸው
•  የራሱ የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ዘመኑን የዋጀ አሠራርን አለመከተል፤
•  ክብረ ክህነት ተገቢውን ቦታ አለማግኘቱ፤
•  የፖለቲካና የብሔርተኝነት ዝንባሌ ያላቸው አንዳንድ የሲኖዶስ አባላት መታየታቸው፤
•  የጳጳሳት አመራረጥና ሹመት አሰጣጥ ተአማኒነት የጎደለው ከሲሞናዊነት፣ ከብሔርተኝነት እና ከፖለቲካ አመለካከት ጋር በተያያዘ የሚነቀፉ፣ በኅብረተሰቡ ዘንድ የመልካም አስተዳደር ችግር ፈጥረዋል ተብለው ነቀፌታ የገጠማቸው እንዲሁም የሥነ ምግባር ጉድለት ያለባቸውን ወዘተ ወደ ሹመት መምጣት፤ 
•  ከመንፈስ ቅዱስ ከሥራ ይልቅ የመንግሥትን አቋምና አጀንዳ የሚያራምዱ መኖራቸው
•  የወሰኑት ውሳኔ የት እንደደረሰ ወረድ ብለው መፈጸሙን የመከታተልና ባልፈጸሙት አካላት ላይ ተገቢውን ርምጃ የመውሰድ ቁርጠኝነት አለመኖር፤
•  የውጭ/የፖለቲከኞችን/ ጣልቃ ገብነት የመፍቀድ/የመፈለግ ዝንባሌ መታየት፤
•   መንፈሳዊ እና ቁሳዊ አስተዳደሩ አለመለየቱና በተገቢው ሰው አለመመራቱ
•  ‘አጥማቂ ነን፤ ነቢይ ነን፤ ባሕታዊ ነን’ የሚሉ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የሚጥሱ ሕዝቡን በሐሳብ የሚከፋፍሉ ሥርዓት አልበኞችን አለመገሥፅ ዝምታን መምረጣቸው ወዘተ፡፡

በመጽሐፈ ዲድስቅልያ ላይ ‹‹ሴቶችና ሕዝባዊ የክህነትን ሥራ አይሥሩ፤ እንዳያጠምቁ፤ በአንብሮተ እድም እንዳይባርኩ፤ በረከተ ኅብስቱንም እንደይሰጡ›› ሲሉ ቅዱሳን ሐዋርያት አዘዋል፡፡ (ዲድስቅልያ ፲፬፥፮ እና አንቀጽ ፲፭፥፩)

•  አሁን ግን ሲኖዶሱንና አባላቱን ብሎም የክህነትን ክብር ያቃለሉና የተዳፈሩ፣ በማን ክህነት እንደተሰጣቸው፣ የትና በማን እንደመነኮሱ የማይታወቁ ምእመኑን የሚበዘብዙ ሥርዓት የጣሱ ‘አጥማቂ ነን፤ ባለ ሕልም ነን፤ እንባርካለን” እያሉ የሚያውኩትን ዝም በማለታቸው፣ ደረጃው አድጎ በብሔር ተደራጅቶ ማኅበር ማቋቋም፣ ቤተ ክህነት ማቋቋም እያለ ሲኖዶስ እስከማቋቋም የደረሰ ድፍረትን በእንቁላሉ መቅጨት አለመቻላቸው፤

•  የመንግሥትን ጣልቃ ገብነት ባለመቃወማቸው፣ ሥርዓት አልበኞችን መገሠፅ፣ ድኃ ተበደለ ፍርድ ተጓደለ ብሎ መናገር ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ አለመሆናቸው ነው፡፡ አንዳድ አባቶች አልፎ አልፎ ደፍረው መንግሥትን ሲገሥፁ እንደብርቅና ድንቅ እየታየ እንደ ጀግና እንዲቆጠሩና እነርሱን ለማጀግን ብዙኃኑን ለመተቸት ዕድል ሲፈጥር ይታያል፡፡

ለ. በቅድስት ቤተ ክርስቲያን መዋቅሮች ግልጸኝነትና ተጠያቂነት መጥፋቱ፡-
በመምሪያዎች፣ በሀገረ ስብከቶች፣ በወረዳ ቤተ ክህነትና በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ያለው አሠራር ግልጸኝነትና ተጠያቂነት የለውም፡፡ ከዚህም የተነሣ የሰው ሀብት፣ የፋይናንስና የንብረት አስተዳደሩ ሁሉም በራሱ አሳታፊ፣ ግልጽ እና ከአድልዎ የጸዳ በሆነ መንገድ አለመመራቱ፤ ሙሰኞች፣ ፖለቲከኞች፣ አማሳኞች፣ ያልተማሩ እና ቤተ ክርስቲያኒቱን በውል የማያውቋት፣ ጥቅመኞች፣ መናፍቃን ሳይቀሩ በመዋቅሩ ተሰግስገው እንዲዘርፏት፣ ስሟ እንዲጠፋ፣ ትክክለኞቹ ልጆቿ አንገት እንዲደፉና ከመዋቅሯ እንዲገፉ፣ ምእመናንም እንዲያፍሩና እንዲሸማቀቁ በር የከፈተ መሆኑ ነው፡፡ ይህም ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመፍጠሩም በላይ ሲኖዶሳዊቱን ልዕልናው እንዲጠፋ፣ ውሳኔውም እንዳይከበር አንድ ምክንያት ሆኗል፡፡

ሐ. ምእመኑ ከዕለት ወደ ዕለት እያደገ የመጣውን መንፈሳዊ ዕውቀቱን ለትችትና ለነቀፋ መጠቀሙ ወቅቱ ምእመኑ በተለይም ወጣቱ ትውልድ አንጻራዊ መንፈሳዊ ዕውቀት በንባብም በትምህርትም በልዩ ልዩ መንገድ ያገኘበት ነው፡፡ የሚያውቀውን የሚኖርበት የሕይወት ለውጥ አምጥቷል ማለት ባይቻልም፡፡ ነገር ግን ያወቀውን ዕውቀት አባቶቹን ለመተቸትና ለማቃለል ምክንያት ሆኖታል፡፡ ይህም በራሱ በአሁኑ ወቅት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታላቅ ፈተና እየሆነባት ይገኛል፡፡ ምክንያቱም አባቶችን ነቅፎ ለነቀፋ እየሰጠና ክብረ ክህነትን እያዋረደ በመሆኑ ነው፡፡

የተወደዳችሁ አንባብያን! ውስጣዊ ችግሮች እነዚህ ብቻ አይደሉም፤ ነገር ግን ለማሳያ ያክል እነዚህን ጠቀስን እንጂ፡፡ በክፍል ሦስት ውጫዊ ምክንያቶችን ይዘን የምንቀርብ ይሆናል፤ እስከዚያው ቸር ይግጠመን!

ይቆየን!
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

የደቡብ ምሥራቅ አሜሪካ ሀገረ ስብከት በትግራይ የተፈጸመውን ሕገወጥ ሢመት በመቃወም መግለጫ አወጣ።
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

2. ይህንን ሕገ ወጥ የኢጲስ ቆጶሳት ሢመት የፈጸሙ ያስፈጸሙና የተሳተፉ አባቶች መነኮሳትና በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ድርጊታቸው ምንም ዓይነት ምድራዊ ችግሮች ቢኖሩና እንደምክንያት ቢጠቀሱም ድርጊቱ ሰማያዊት የሆነችውን የቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ልዕልና የተዳፈረና ቀኖና ቤተክርስቲያንን የጣሰ አስተዳዳራዊ አንድነቷን የተፈታተነ መሆኑን በመገንዘብ ከዚህ የተሳሳተ ድርጊት ወጥታችሁ ወደ ቤተክርስቲያን አንድነት እንድትመለሱ በቤተክርስቲያን ስም ጥሪያችንን
እናቀርባለን፡፡

3. የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ባስተላለፈው ጥሪ መሠረት ብፀዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በምልዓት ተገኝተው ታሪካዊ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት የቅድስተ ቤተክርስቲያንን ልዕልናና አንድነት የሚያስጠብቅ፣ እንዲሁም ወደፊት መሰል ሕገ ወጥ ድርጊቶች እንዳይደገሙ የሚያደርግ አስተማሪ ውሳኔ እንደሚያስተላልፉ እንጠብቃለን፡፡

4. በትግራይ ክልል የምትገኙገኙ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አባቶች ካህናትና ምእመናን ሰንበት ትምህርት ቤቶችና ልዩ ልዩ ማኅበራት “ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለተሰጠች ሃይማኖት እንድትጋደሉ ” እንዳለ መጽሐፍ (ይሁዳ 1፡3) የቤተክርስቲያን ህልውና፣ ቀኖናና አንድነት እንዲጠበቅ እንደቀደሙት ቅዱሳን አበው የበኩላችሁን ሃይማኖታዊ ግዴታችሁን ትወጡ ዘንድ በድጋሚ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

5. በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልጆች ሁሉ ቤተክርስቲያን ከገጠማትን ችግር እንድትወጣ በሚያስፈልጋት ሁሉ  በመደገፍ ሃይማኖታዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ እናሳስባለን

6. የአኅት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተክርስቲያን አባላትና ኦርቶዶክሳዊያን፣ እንዲሁም ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማትና የቤተክርስቲያን አንድነት እንዲኖር በጎ ሐሳብ ያላችሁ ሁሉ ቤተክርስቲያን ከገጠማት ችግር እንድትወጣ ያልተቆጠበ ድጋፋችሁን ታደርጉ ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

7. ቀደም ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተክርስቲያን ቀኖናዊ አንድነትዋ እንዲከበር በተደጋጋሚ ጥሪ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ አሁንም ቅዱስ ሲኖዶስ በጠራው ምልዓተ ጉበኤ ተወያይቶ በሚያስተላልፈው ውሳኔ መሠረት መንግሥትም የቤተክርስቲያንን ልዕልናና ሕጋዊ መብት በሚያስጠብቅ መልኩ የበኩሉን ድርሻ  እንዲወጣ እንጠይቃለን፡፡
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

ቁልቢ እና ሐዋሳን ጨምሮ በመላው ሀገሪቱ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ-በዓል በሰላም ተጠናቋል።

ፎቶ፦ ከማኅበራዊ ሚዲያ
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

በትግራይ በተከናወነው የሕገ ወጥ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ለሐምሌ 25/2015 ዓ.ም ምልዐተ ጉባኤ ጠራ።

  1. በክልል ትግራይ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በክልሉ ከሚገኙት አህጉረ ስብከት ጋር ተቋርጦ የነበረውን መዋቅራዊ ግንኙነት ችግር በውይይት እንዲፈታ ቅዱስ ሲኖዶስ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪና ልዑካኑን በአካል ልኮ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ባለበት ወቅት በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አባቶች ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ ቅዱስ ፓትርያርኩ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ተብለው በሚጠሩበት በማዕከላዊ ትግራይ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 15 እና 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በተከናወነ ሕገ ወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት መፈጸሙን በመገናኛ ብዙኃን ለማወቅ ችለናል፡፡ በመሆኑም በዚህ የዶግማና የቀኖና ጥሰት ተግባር የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በእጅጉ አዝኗል፡፡ 

2. በመሆኑም የተከሰተው የዶግማ፣ የቀኖና እና አስተዳደራዊ ጥሰት አስመልክቶ ተወያይቶ ተገቢውን ለመወሰን ለሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪ ተላልፏል፡፡

3. የስብሰባው ቀን ሊራዘም የቻለው በውጭው ክፍለ ዓለማት ያሉት ሊቃነ ጳጳሳት መገኘት ስላለባቸው የጉዞ ቀኑ እንዳያጥር እና በሀገር ውስጥ የሚገኙትም ሊቃነ ጳጳሳት ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት ለአገልግሎት ወደ አህጉረ ስብከታቸው የሄዱ በመሆኑ ለመመለሻ የሚያስፈልገውን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ ነው፡፡
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

#ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ገብርኤል

🥀እንኳን ለታላቁ መልአክ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!!!

🥀በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ በዓል ነው፡፡ ይህ ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት እየሉጣንና ልጇን ቅዱስ ቂርቆስን ከሞት አደጋ እንደታደገበት የሚታሰብበት ዕለት ነው። የሐምሌ 19 ስንክሳርና የሐምሌ ወር ድርሳነ ገብርኤል እንዲህ ተርከውታል፡፡

🥀በዘመነ ሰማእታት ከሐድያን ነገሥታትና መኳንንት በክርስቲያኖች ላይ መከራ አጽንተውባቸው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙዎች ሰማእትነትን ሲቀበሉ የተቀሩት አገር ጥለው ተሰደዱ። እየሉጣም የሦስት ዓመት ህፃን የነበረውን ቅዱስ ቂርቆስን ይዛ ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኮንን አገኘችው ሰዎችም ነገር አሰሩባት ወደእርሱ አስቀረባት እና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም መኮንን ሆይ ዕድሜው ሦስት አመት የሆነው ህፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እሱን ጠይቅ አለችው፡፡

🥀ህፃኑም ወዳለበት ጭፍራውን ልኮ ወደእርሱ አስመጣው ህፃኑም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ህፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው፡፡ ህፃኑም መልሶ አዎ ለኔ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ሐዘንና ለቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው፡፡ መጻሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏል እና አለው፡፡ እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስካስደነገጣቸው ድረስ ንጉሱን መኳንንቱንና ጣኦታቱን ረገማቸው፡፡ከብርታቱም የተነሳ አደነቁ፡፡

🥀መኮንኑም በአፈረ ጊዜ በያይነቱ በሆነ ስቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ስቃይን አሰቃየው እናቱንም ከእርሱ ጋር አሰቃያት፡፡ እግዚአብሔርም ያለ ምንም ጉዳት ያነሳቸው ነበር፡፡ ብዙዎች አህዛብም ይኸንን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አምነው በሰማእትነት አረፉ፡፡ የሰማእትነትንም አክሊል ተቀበሉ፡፡ በህፃኑም ላይ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት፡፡ ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው፡፡

🥀መስፍኑም በውስጡ ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ ሙጫ የዶሮ ማር፣ እርሳስ፣ ብረት፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል ጨምራችሁ ታላቅ የብረት ጋን አንጡልኝ ብሎ ጭፍሮቹን አዘዛቸው፡፡ ጭፍሮቹም እንዳዘዛቸው ካአደረጉ በኋላ ያዘዝከንን ሁሉ ፈጽመን እሳቱ ነዶ ፈልቷል፡፡ ድምፁ እንደነጐድጓድ ይጮኸል ወላፈኑም እንደጸሐይ ነጸብራቅ በሩቁ ይጋረፋል፡፡ የፍላቱም ኃይል በ14 ክንድ ያኽል ከፍታ ወደ ላይ ይዘላል፡፡ እንግዲህ በውስጡ የሚጣሉትን እዘዝ አሉት በዚህ ጊዜ ህፃን ቂርቆስና እናቱ እየሉጣ በክርስቶስ ስም ስለሚያምኑ አስረዋቸው ነበርና ከፍላቱ ሊጨምሯቸው ከእስር ቤት አወጧቸው፡፡

🥀በዚያም ፍላቱ ወደላይ በሚዘል ብረት ጋን ውስጥ ለመጨመር ሲወስዷቸው የነዚህን ቅዱሳን አሟሟት ያዩ ዘንድ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲሰበሰቡ አዘዛቸው፡፡ በዚህን ጊዜ ቅድስት እየሉጣ የፍላቱን ጩኸት በሰማችና ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተዘጋጅቶላት ከነበረው ክብር ልታፈገፍግ ሞከረች፡፡ ልጇ ቅዱስ ቂርቆስ ግን እናት ሆይ ከዚህ የብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ ድንጋጼም አይደርብሽ አናንያንና አዛርያን ሚሳኤልንም እግዚአብሔር ከእቶነ እሳት እንዳወጣቸው ሁሉ እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ሊያወጣን ችሎታ ያለው መሆኑን አትጠራጠሪ፡፡

🥀እናት ሆ ከዚህ ከሚያልፈው ዓለም ጭንቅና መከራ ለመዳን ስትይ በማያልፈው ዘላለማዊ እሳት ለመቀጣት ትመርጫለሽን ይኽስ አይሆንም ይቅርብሽ፡፡ በአሁኑ ጊዜ እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡ እናት ሆይ ሶስናን ከእደ ረበናት /መምህራነ አይሁድ/ ዳንኤልን ከአፈ አናብስት ያዳነ እርሱ እኛንም ከጋን ፍላት ያወጣናል፡፡ ይልቁንም እግዚአብሔር በዚህ የብረት ጋን ውስጥ ግዳጃችንን ልንፈጽም ፈቅዶ ከሆነ ኢዮብ ንብረቱንና ገንዘቡን ልጆቹንና ሚስቱን በመጨረሻም የተፈጥሮ አካሉን ባሳጣው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ እግዚአብሐር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ እግዚአብሔርም እንደወደደ አደረገ ከማለት በስተቀር ምንም የተናገረው ነገር እንደሌለ ሁሉ እኛም የሱን ዓላማ በመከተል ይኽንን መከራ ልንታገስ ይገባናል፡፡

🥀ነገር ግን እናቱ በዚህ ምክር ልትጽናና ባለመቻሏ ቅዱስ ቂርቆስ ዐይኑን ወደ ሰማይ አቅንቶ አቤቱ አምላክ ሆይ ይችን ባሪያህን ከርስትህ የምትለያት ከሆነ ከባለሟልነትህ መጽሐፍ ፋቀኝ፤ አቤቱ አዝመራውን አቃጥለ ፍሬውን ልትባርክ ትወዳለህን ይኽን እንዳታደር ግን ቸርነትህ ትከለክልኸለች አቤቱ እንጨቱን ቆርጣችሁ አንድዱት ቅጠሉን ግን ጠብቁት ብለኽ ልታዝ መለኮታዊ ባሕሪህ አይደለም፡፡ ነገር ግን እንጨቱንም ቅጠሉንም በአንድ ጠብቁት ብለኽ ታዝዛለኽ እንጂ፡፡ እንግዲህ በዚህ ምክንያት ይኽንን ያየ ሁሉ ማዳን የሚችል አምላክ ቢኖራቸውስ ኖሮ ከእሳት ባልሸሹም ነበር ብሎ አይጠራጠር፡፡

🥀አቤቱ ዲያብሎስም ከባለስልጣኑ ይልቅ እኔ በረታሁ ቅዱሳኖቹንም ድል ነሳኋቸው ብሎ እንዳይመካ ከመንጋውም አንድ በግ ቀማው በማለት እንዳይደነፋ ለእናቴ ጽኑ የሆነ ኃይለ መንፈስ ቅዱስን ስጣት ብሎ በጸለየ ጊዜ ዲያብሎስ ከእየሉጣ አጠገብ ብን ብሎ ጠፋ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ በሰማያዊ መንግሥት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታኽ ኃይልን ሰጥቶኛልና የሚጠብቀንን ገድላችንን ፈጽመን ድል እናድርግ እነሆ በብረት ጋን ውስጥ የሚነደውን እሳት በማይበት ጊዜ በለምለም /በምንጭ/ ላይ እንደሚወርድ ጠል ሆኖ አይቸዋለሁና አለችው፡፡
​​

🥀እኒኽም ቅዱሳን ይኽንን በሚነጋገሩበት ጊዜ በውስጡ አንገትን የሚቆለምም ልብንም የሚያቀልጥ ሆድን የሚሰነጥቅ ሥርን የሚበጣጥስ መሳሪያ ካለበት የብረት ጋን ውስጥ ጨመራቸው፡፡ ከዚህ በኋላ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወረደና የብረቱን ጋን እሳት አጠፋው፡፡ ከቅዱሳኑም አንዳቸውንም ሳያቃጥላቸው የብረቱ ጋር ማቃጠሉና መፍላቱ ጸጥ አለ፡፡

🥀ወንድሞቻችን ሆይ እንግዲህ በጭንቃቸው ጊዜ ገድላቸውን እስኪፈጽሙ ድረስ ይህ መልአክ ከሰማእታትና ከጻድቃን ጐን እንደማይለይ እወቁ ለኃጥአንም ኃጢአታቸውን ይቅር ይላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ይጸልይላቸዋል፡፡ እኛም የዚህ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በዓሉን እያከበርን አማላጅና ወዳጅ እናድርገው። በዚህም በሚመጣውም ዓለም ሊረዳን ይችላልና፡፡

🥀ዳግመኛም መስፍኑ ሐሳቡ ሳይሳካለት ስለቀረ 14 የሾሉና የጋሉ የብረት ችንካሮች አምጥተው ሰባቱን በእናቱ በኢየሉጣ አካል ሰባቱን በራሱ በቂርቆስ አካል ማለት ሁለቱን በጆሮዎቹ ሁለቱን በዐይኖቹ ሁለቱን በአፍንጫዎቹ አንዱን በልቡ ይቸነክራቸው ዘንድ ጭፍሮቹን አዘዘ፡፡ ዳግመኛም የህፃኑን የእራስ ቆዳ ገፈው እሳት ውስጥ ይጨምሩ ዘንድ አዘዘ፡፡ @ortodoxtewadochannal

🥀አሁንም መልአኩ መጥቶ ይህንን መከራ ከእርሱ አራቀለት፡፡ ቀጥሎም በመቃን ውስጥ ጨምረው በገመድ እንዲጎትቱት አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ መልአኩ አዳነው፡፡ ሕዝቡም ይህንን ሁሉ ተአምር ባዩ ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገኑት ቅዱስ ገብርኤልንም አከበሩት፡፡ ቅዱስ ቂርቆስና ቅድስት እየሉጣ ብዙ መከራ ከተቀበሉ በኋላ ጥር 15 በሰይፍ ተመትተው ስማትነትን ተቀብለዋል።
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

በወቅታዊ ጉዳይ ከጴጥሮሳውያን የማኅበራት ኅብረት የተሰጠ መግለጫ
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

#ኪዳነ_ምህረት_እናቴ🥰
   #አንቺ_ባትኖሪልኝ
የመኖሬ ትርጉም ቅኔው ሲጠፋብኝ
የህይወቴ መፅሐፍ ገፁ ሲምታታብኝ
የኔነቴ ዋጋ ባዶ ሲሆንብኝ
የኃጢያት ሐረግ ሲንጠላጠልብኝ
ሙቼ መራመዴ ለኔ ሲታወቀኝ
ምን ይውጠኝ ነበር አንቺ ባትኖሪልኝ
አልቅሼ ስነግርሽ አለሁሽ ባትዪኝ
የመዳንን መድህን ልዑል ባትወልጂልኝ
በምልጃ ፀሎትሽ ቤቴ ባይሞላልኝ
በይቅር ባይነትሽ ኑሮ ባይቀናልኝ
ማን ያስበኝ ነበር አንቺ ባታስቢኝ
ኃጥያት ተፀይፈሽ ፊት ያላዞርሽብኝ
ብርሃንን ወልደሽ ፀኃይ የሆንሽልኝ
ለውለታሽ ገላጭ ምንም ቃላት የለኝ
አማላጇ እናቴ ሁሌም ክበሪልኝ
ድንግል እመቤቴ ከፍ ከፍ በይልኝ🥰

🥀የእናታችን ኪዳነ ምህረት ምልጃዋ
እናትነቷ ፍቅሯ ጣዕሟ ፆሎት ልመኗ ምልጇዋ ጥበቃዋን አይለየን🥰
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

​​ሱባኤ ለመግባት መደረግ ያለበት ዝግጅት
ክፍል ሦስት

ሱባዔ መግባት የሚፈልግ ምእመን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ያለምንም ዝግጅት ሱባዔ መግባት ለፈተና ያጋልጣል፡፡ ስለዚህ ቅድመ ሱባዔ /ሱባዔ ከመግባት ኣስቀድሞ/፣ ጊዜ ሱባዔ/ በሱባዔ ጊዜና ድኅረ ሱባዔ /ከሱባዔ በኋላ/ ዝግጅት ኣስፈላጊ ነው፡፡

ቅድመ ዝግጅት

ቅድመ ሱባዔ /ሱባዔ ከመግባት አስቀድሞ/ በመጀመሪያ ሱባዔ የምንገባበትን ምክንያት ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ኣንድ ሰው ሱባዔ የሚገባበትን ዓላማ ለይቶ ካስቀመጠ ከሱባዔ በኋላ የሚጠበቀውን ነገር ማግኘት ኣለማግኘቱን ይረዳል፡፡ ይህ ሳይሆን ሱባኤ ቢገባ ከሱባኤው በኋላ የጠየቀው ነገር ስለሌለ ትርጉም ያጣል፡፡ ስለዚህ ሱባዔ ከመግባታችን በፊት ለምን ሱባኤ ለመግባት እንዳሰብን ለይተን ማወቅ ይኖርብናል፡፡

ሱባዔ ለመግባት የወሰንበትን ምክንያት ከለየን በኋላ ምክንያታችንን ይዘን የንስሓ ኣባታችንን ማማከር ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም በምክረ ካህን መጓዝ መጀመር ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር በኣባትነታቸውና በሕይወት ልምዳቸው ምን ማድረግ እንደሚገባን ምክር ለማግኘት እገዛ ያደርግልናል፡፡ ቅድመ ሱባኤ ከንስሐ ኣባት ጋር መመካከር ተገቢ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ኣንድ ሰው በሱባዔ ወቅት የተለያዩ ፈተናዎች ቢያጋጥሙት የተሰጠውን ምክር በመጠቀም ፈተናውን ለመቋቋም ይችላል፡፡ እንዲሁም የንስሓ ኣባቱ በሱባዔ ወቅት በጸሎት እንዲያስቡት መማከር የራሱ የሆነ ድርሻ አለው፡፡

ሱባዔ ለመግባት ስናስብ ለምን ያህል ቀናት መቆየት እንዳለብን መወሰን ያስፈልጋል፡፡ ሱባዔ ከዚህ እስከዚህ እቆያለሁ ብለን ዕቅድ የምንይዝበት ነው፡፡ እንደ ኣቅማችንና እንደ ችሎታችን ከዚህ ቀን እስከዚህ ብለን በመወሰን ሱባዔ መግባት ተገቢ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ፡- ምንም ዓይነት ልምድ ሳይኖረው ኣንድ ሰው «በዋሻ እዘጋለሁ» ቢል ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል፡፡ ምክንያቱም በሱባዔ ወቅት ፈተና ስለሚበዛ የሚመጣበትን ፈተና መቋቋም ባለመቻል ሱባዔው ሊቋረጥ ይችላል፡፡ ስለዚህ ቅድመ ሱባዔ ዓቅምንና ችሎታን ኣገናዝቦ መወሰን ተገቢ ነው፡፡

ሌላው ቅድመ ሱባዔ ለሱባዔ ተስማሚ የሆነ ወቅትና ቦታ መምረጥ ተገቢ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን በኣብዛኛው ሱባዔ የሚገባው ኣጽዋማትን ተከትሎ ነው፡፡ ስለዚህ ሱባዔ የምንገባበት ወቅት የጾም ወቅት መሆን ኣለመሆኑን መለየት ያስፈልጋል፡፡ በኣጽዋማት ወቅት የሚያዝ ሱባዔ ለተሓራሚ ጠቀሜታው እጅግ የጐላ ነው፡፡ ምክንያቱም በኣጽዋማት ወቅት ብዙ ኣባቶች ሱባዔ ስለሚይዙ ከኣባቶች ጸሎት ጋር ልመናችንና ጸሎታችን ሊያርግ ይችላል፡፡ ስለዚህ ወቅትን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

እዚህ ላይ «ከወርኃ አጽዋማት ውጭ ሱባዔ ኣይያዝም» የሚል ኣቋም ለመያዝ ኣይደለም፡፡ አንድ ሰው ፈተና ካጋጠመው በማንኛውም ጊዜ ሱባዔ ሊገባ እንደሚችል እዚህ ላይ ለመጠቆም እንወዳለን፡፡ ከዚህም ባሻገር ሱባዔ የምንይዝበትን ቦታ መምረጥ አለብን፡፡ ለሱባዔ የምንመርጣቸው ቦታዎች ለፈተና የማያጋልጡ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ይኸውም ሱባዔ ከተገባ በኋላ ኅሊናችን እንዳይበተን እገዛ ያደርግልናል ልናል፡፡ ጫጫታና ግርግር የሚበዛበት ቦታ በሰቂለ ኅሊና ለመጸለይ ኣያመችም፡፡ ስለዚህ ሱባዔ የምንይዝባቸው ቦታዎች ከከተማ ራቅ ያሉ ገዳማትና ኣድባራት ተመራጭ ናቸው፡፡

በክፍል 4 :- በሱባዔ ጊዜ ምን እናድርግ?

ለእህት ወንድሞች ይማሩበት ዘንድ አጋሩ
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

​​ሱባዔና ሥርዓቱ
ቃለ እግዚአብሔር ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ Share ያድርጉ

ያለንበት ወቅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ጾመ ፍልሰታን የሚጾሙበት ሱባዔ የሚገቡበት ወቅት ነው፡፡ ለዚህ ወቅት ምእመናን ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ መልካም የሱባዔ ጊዜ ይሁንልን፡፡

ሱባዔ ምንድን ነው?

ሱባዔ በሰዋሰው ትርጉሙ ሰባት ማለት ነው፡፡ ሱባዔ በመንፈሳዊ አተረጓጎም አንድ ሰው ከዚህ ቀን እስከዚህ ቀን በጸሎት ከፈጣሪዬ እገናኛለሁ ብሎ የሚያቅደው መንፈሳዊ ዕቅድ ነው፡፡ ሰባት ቁጥር በእስራኤላውያን ዘንድ በሥራም በቃልም የሚገለጥ ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ሥነ ፍጥረትን ከመፍጠር ማረፉ፣ ለጸሎት የሚተጉ ምእመናን በቀን ለሰባት ጊዜ ማመስገናቸው የሰባት ቁጥርን ፍጹምነት ያመለክታል፡፡ ዘፍ.2፥2፤ መዝ.118፥64፡፡

ከዚህ አንጻር አንድ ሰው ለሰባት ቀናት ቢጾም አንድ ሱባዔ ጾመ ይባላል፡፡ ለዐሥራ አራት ቀን ቢጾም ሁለት ሱባዔ ጾመ እያለ እየጨመረ ይሄዳል፡፡

ሱባዔ መቼ ተጀመረ?

ሱባዔ የተጀመረው ከውድቀት በኋላ በመጀመሪያው ሰው በአዳም ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክት አዳምን ጸሎት መጸለይን እንዳስተማሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ መላእክት ለአዳም ጊዜያትን አስተምረውት ነበር፡፡ ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ፡፡ አዳም ጥፋቱን አምኖ ከባሕር ውስጥ ሱባዔ በመግባቱና በመጸለዩ እግዚአብሔር በማይታበል ቃሉ ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንኀለሁ ሲል ቃልን ገብቶለታል /መጽሐፈ ቀሌምንጦስ አንቀጽ አራት/፡፡

#ይቀጥላል ....
በቀጣይ ሱባዔ ምንድን ነው ጥቅሙ?
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

ሐዋርያት የድንግል ማርያምን የማረፊያ ቦታ ለማየት ሲሉ የጾሙት ጾም ነው! ቅዱሳን ሐዋርያት የገለፁት ፍቅረ ድንግል ማርያምን ብቻ ሳይሆን ያረፈችበትንም ቦታ ጭምር ያመለከተ ነበረ፤ ይህ ሊሆን የቻለው ከልብ የሆነ እውነተኛ ፍቅር በሐዋርያት ዘንድ ስለነበረ ነው፡፡ እኛም ዛሬ የምንጾመው ይህንን የማርያም ጾም እንደ አበው ሐዋርያት ፍቅረ ድንግል ማርያም በልባችን ውስጥ ተተክሎ ስላለ ነው፤ እግዚአብሔር በፍቅርና በሃይማኖት የሚቀርብለትን ሁሉ ይቀበላልና የሐዋርያትን ጾምና ጸሎት ተቀበሎ ጥያቄአቸውን መልሶአል።

ዛሬም ይህንን ጾም የምንጾመው እግዚአብሔር ጾማችንን ተቀብሎ የልባችንን መሻት ይፈጽምልናል ብለን

ነው፣ በፍቅርና በሃይማኖት አስክ ጾምን ደግሞ እግዚአብሔር ይቀበለናል፤

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት !

እንደ እግዚአብሔር ቃልም እንደ አባቶቻችን ትውፊትም የጾመ ፍልሰታ ጾም ሲጾም የበደለ ይቅርታ ጠይቆ፣ ተገቢውንም ካሣ ከፍሎ፣ ቂም በቀሉን አሰርዞ፣ ፍቅርን መሥርቶ ነበረ የተበደለም በበኩሉ ዕርቅን አውርዶ፣ ይቅርታን ሰጥቶ የእእምሮ ማለስለሻና ማስረሻ የሆነውን ካሣውን ተቀብሎ ተሙንና በቀሉን ከአእምሮው አውጥቶና አጽድቶ፤ ለእግዚአብሔር ስል ከልቤ ይቅር ብያለሁ ብሎ፣ ስመ እግዚአብሔርን ጠርቶ በፍቅር ይታረቃል

በዚህ ሁኔታ ፍጹምና ልባዊ ፍቅር ተይዞ ሲጾም ሁሉም ዓይነተ : ኃጢአት ሙሉ በሙሉ ይደመሰስለታል ፤ እግዚአብሔርም ይቅርታ ጠያቂውንም፣ ይቅርታ ሰጪውንም አሸማጋዩንም ይባርካል፤ ማኅበረ ሰቡም በዚህ ቅዱስና ሃይማኖታዊ ባህልና ትውፊት ተጠብቆ ለብዙ ዘመናት አንድነቱንና ሃይማኖቱን ወንድማማችነቱንና ነጻነቱን አስጠብቆ እስከ ዛሬ ደርሶአል | ይህ ለሀገራችን ታላቅ የሆነ የእግዚአብሔር በረከት ነበረ፣ ይህ እውነተኛ በረከት በአሁኑ ጊዜ ቸል በመባሉ ፈተናችን በዝቶአል፤ እንደ እውነቱ ከሆነ ሰው በኃጢአት ከወደቀበት ጊዜ ጀምሮ ጥልና መገዳደል በየትኛውም ጊዜ፤ በየትኛውም ሀገር በየትኛውም ማኅበረ ሰብ ይከሠታል፤ ዛሬም በሀገራችን በተፈጠረው አለመግባባት

ከባድ ችግር ተፈጥሮአል የሚያስገርመው ነገር ቢኖር እንዴት እንደባህላችንና እምነታችን በቀላሉ በዕርቅና በይቅርታ ማስተካከል አቃተን የሚለው ነው፡ የዘመናችን ልዩ ነገር ይህ ነው ለዚህም ብዙ የተለያየ ምክንያት ሊኖረው ይችላል፣ በሃይማኖት ዓይን ሲታይ ግን ለእግዚአብሔር ቃል የምንሰጠው ክብር በእጅጉ ስለተቀነሰ ነው የሚል ሆኖ ይገኛል፣ ይህ ዝንባሌ አሁን ላለውም ሆነ ለሚመጣው ትውልድ አደገኛ ስለሆነ የኦርቶዶክስ ሕዝበ ክርስቲያንም ሆነ ሌሎቹ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይህንን በጥልቀት ሊያጤኑትና ሊያርሙት ይገባል።

የተወደዳችሁ የመንፈስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናንት | ሽማግሌ የሀገር በረከት ነው፤ አስታራቂ ሽማግሌ የችግር ሐኪምና ፈዋሽ ነው፣ የፍቅርና የተግባቦት መሐንዲስም ነው፤ በእግዚአብሔርም የሚያስታርቁ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው” ተብሎ ውዳሴ ተችሮአቸዋል፣ እነዚህን ሽማግሌዎች ተጠቅመን ችግሮቻችንን መፍታት ጊዜው የሚጠይቀው አስገዳጅ ጉዳይ ሆኖአል፤ ሁሉም ታየ፤ ሁሉም ተሞከረ፣ ዘላቂ መፍትሔ ሲያመጣ ግን አልታየም፤ እንዲያውም ችግሩ ወደ ሃይማኖት ተዛምቶ ቤተ ክርስቲያንም የገፈቱ ቀማሽ ለመሆን ተገዳለች፡፡

በተጨባጭ እንደሚታውቀው ሕዝብንና ሃይማኖትን ነጣጥሎ ሰላምን ማረጋገጥ ከቶውኑ ሊታሰብ

አይችልም ምክንያቱም ሕዝብ የሃይማኖቱ ቤተሰብ ነው፤ ሃይማኖቱም በሕዝቡ መንፈስ ውስጥ ነግሦ

የሚኖር መለኮታዊ ኃይል ነውና፣ ከዚህ አንጻር “ወልድ ሲነካ አብ ይነካ" እንደሚባለው ሕዝቡ ሲነካ

ሃይማኖቱ ይነካል፣ ሃይማኖቱ ሲነካ ደግሞ ሕዝቡ ይነካል፤

በመሆኑም በተካሄደው ግጭት ብዙ ነገሮች መመሳቀላቸው የማይካድ ቢሆንም ችግሩ በዕርቅና በካሣ

በይቅርታና በመተው ካልተዘጋ ለማንም ስለማይበጅ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ለዕርቅ ዝግጁ እንዲሆነ፣ የበደሉም እንዲክሱ የሀገር ሽማግሌዎችም የማስታረቅ ስራን በሐቅ በገለልተኝነትና ዕንባን በሚያደርቅ ስልት እንዲሸመግሉ መንግሥትም የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ በዚህ አጋጣሚ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ የገጠመንን ፈተና ሁሉ ሊያቀልልንና ሊያስወግድልን የሚችል እግዚአብሔር ስለሆነ፤ በዚህ የጾመ ማርያም ወቅት ምእመናን በተመሥጦና በንሥሐ ሕይወት ለእግዚአብሔር በመንበርከክ ስለ ሰላምና ፍቅር እንዲማፀኑ፣ ካላቸውም በረከት ለተራቡትና ለተፈናቀሉት እንዲለግሱ ሁሉም ወገኖች በሆነው

በመጨረሻም

ነገር ይብቃን ብለው ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲቀርቡ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን

እናስተላልፋለን፡፡

መልካም የጾመ ማርያም ሱባዔ ያድርግልን እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም.
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

የቤተ ክርስቲያን ወዳጆች በሙሉ በመጾም፣ በመጸለይ፣ የቤተ ክርስቲያንን ተልእኮና መዋቅር በጠበቀ መልኩ  በመደራጀት አፍራሽ እና የጥፋት መረጃዎችን፣ በመሰብሰብ፣ በመተንተን፣ ለውሳኔ በማቅረብ የቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ደኅንነት እስኪረጋገጥ ድረስ ያለማቋረጥ በመንፈሳዊ ተጋድሎ መበርታትና የመጣብንን ፈተና በጽናት መታገል እንደሚገባ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡ 

13.  በአሁኑ ወቅት በሀገራችን በተለያዩ ክፍሎች እየተከሠተ ያለውን የሰላም መደፍረስ እና የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት የሰው ሕይወትና የንብረት ውድመት የተፈጠረ አለመግባባት ካለፈው ስህተታችን በመማር ችግሩን ተቀራርቦ በውይይትና በእርቅ እንዲፈታ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም አካላት የሰላም ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡

14.  እንደ ሀገር የገጠመንን የሰላም መደፍረስ በተመለከተ ዘላቂ መፍትሔ በማፈላለግ እንደ ቤተ ክርስቲያን ስለ ሰላም ጉዳይ የሚሠሩ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ምሁራን ያካተተ ዐቢይ ኮሚቴ በቋሚ ሲኖዶስ በኩል ተቋቁሞ ሥራው እንዲሠራ ወስኗል፡፡ 
  
በመጨረሻም እስከ አሁን ድረስ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጎን በመሆን አጋርነታችሁን ያሳያችሁ፣ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት እና ሉዐላዊነት መከበር የበኩላችሁን በመወጣት መግለጫ የሰጣችሁ ሁሉ በልዑል እግዚአብሔር ስም እያመሰገንን ለወደፊቱም በጸሎታችሁ እና በመልካም አጋርነታችሁ ከጎናችን እንድትሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

             እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
                ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. 
                     አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ምንጭ: የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለሀገር አንድነት፣ ለፍትሕ፣ ለጥበብ፣ ለሕዝብ ትስስር፣ ለማኅበራዊ ዕድገት፣ ለጤና፣ ለሥነ-ምግባር መሠረትና ዐምድ፤  ሆና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተፈራች፣ የተከበረችና የተወደደች፤ ዕሴቷ እና ዕምቅ የዕውቀት ሀብቷ በምሁራን የታወቀ፣ በትምህርተ ዓለም ሳይቀር የተቀረጸ፤ በእውነተኛ ሊቃውንት የተመሠከረ፣ ቅርሶቿ የተመዘገቡላት ስትሆን፤ ከፍተኛውን ሐዋርያዊ ተልእኮ እንዲወጡ አደራ በተሰጣቸው ሊቃነ ጳጳሳት በማኅበረሰብ ዕድገትና አስተዳደር ውስጥ ከሕዝብ ጋር በቆመች፣ ከፖለቲካ በጸዳች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ መንፈሳዊና ሕዝባዊት ተቋምነቷን በመካድ ከፍተኛ የሆነ ሕገ ወጥ ድርጊትና ተቋምን የመናድ እንደሁም መዋቅሯን የማፍረስ ተግባር ተከናውኗል፡-  

በዚሁ መሠረት፡-

ሐምሌ 16 እና 23 ቀን 2015 ዓ/ም በክልል ትግራይ በማእከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ገዳም ውስጥ የተፈጸመውን ሕገወጥ የሆነ አስነዋሪ፤ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት አስመልከቶ ቅዱስ ሲኖዶስ ሐምሌ 26ቀን 2015 ዓ/ም አስቸኳይ ምልዐተ ጉባዔ አድርጓል፤ 

   ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በደመ ክርስቶስ ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ ያለፈተና የኖረችበት ጊዜ እንደሌለ ቅዱሳት መጻሕፍትና የታሪክ መዛግብት ሲመሰክሩ በዘመነ ሐዋርያት ቢጽ ሐሳውያን፣ በዘመነ ሊቃውንት የተለያዩ መናፍቃን፣… በየጊዜው እየተነሡ ሲፈታተኗት ኑረዋል፡፡ አሁንም በግልጽ እንደሚታየው ከውጭም ከውስጥም በተደራጁ ምንደኞች በመፈተን ላይ ትገኛለች፡፡ ይህንኑ በመረዳትም ቅዱስ ሲኖዶስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባዔ፣ የሊቃውንት ጉባኤ፤ የሕግ አገልግሎት መምሪያና የህግ ባለሙያዎች አቢይ ኮሚቴ፤ የውጪ ግንኙነት መምሪያ፣ ካቀረቡት ዶግማዊ፣ቀኖናዊ፣ታሪካዊና ትውፊታዊ ሰነዶች በመነሣት የቤተ ክርስቲያንን ልዕልና ለማስከበር ያስችል ዘንድ ጥልቅ ውይይት አድርጓል፡፡
  
  በዚህም መሠረት ሐምሌ 16 እና 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በክልል ትግራይ በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ገዳም ውስጥ በትግራይ ክልል በሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት፡-

1. አባ ኢሳይያስ
2 አባ መቃርዮስ
3. አባ መርሐ ክርስቶስ
4 አባ ጴጥሮስ  መሪነት እጅግ አሳዛኝ ኢ-ሲኖዶሳዊ የሆነ አስነዋሪ፣ ሕገ-ወጥ፣ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት በመፈጸም 10 መነኮሳትን በእጩነት በመምረጥና ለዘጠኙ ህገወጥ ሲመት በመፈጸም፣ ሥርወ ትውፊት ዘሐዋርያት የሆነውን የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ መንበር በመካድ "መንበረ ሰላማ" የሚባል ህገወጥ መንበር በመሠየምና በህገወጥ መንገድ የሾሟቸውን ግለሰቦች ሊቃነ ጳጳሳት በሚመሯቸው በሀገር ውስጥና በውጪ በሚገኙ አህጉረ ስብከት በሕገ ወጥ መንገድ በመመደብ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት አልፎ አንዲት ኩላዊትና ዓለም አቀፋዊት የሆነችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን የሚከፋፍል፤ የሀገር አንድነትን የሚሸረሽር እና የሚያፈርስ፣ ምእመናንን ከምእመናን፣ ካህናትን ከካህናት፣ ሊቃውንትን ከሊቃውንት ወጣትን ከወጣት የሚያጋጭ ሰላም የሚያናጋ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ተገንዝቧል። በመሆኑም፤ 


- የቤተ ክርስቲያን መንበር ሐዋርያዊ ነው፡፡ ሐዋርያዊ መንበር ጌታችን አስተምሮ ከሾማቸው ከዐሥራ ሁለቱ ከሐዋርያት የወጣ አይደለም፤ ሥልጣነ ክህነት የሚተላለፍበት፣ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ትምህርተ ሃይማኖት እና ቀኖና ምንጩ ወይም ሥሩ የሚነገርበት፣ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን አማናዊና ሐዋርያዊ ታሪክ፣ ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት የሚጀመርበት መነሻ ነው፡፡ 


- ቤተ ክርስቲያን የምትመራው በሐዋርያት ሥልጣነ ክህነት ነው፤ ይኽንን ሥልጣን ማንም እንደፈለገው ሊከፋፍለው አይችልም፤ በየትም ቦታ ያሉ ጳጳሳት ከቅዱስ ሲኖዶስ እና ከቅዱስ ፓትርያርክ ዕውቅና ውጭ እንደፈለጉ በቡድኑ እየሆኑ መንበር አቋቁመናል ሊሉ አይችሉም፤ ይህ ከቤተ ክርስቲያን ትውፊትና ታሪካዊ ቅብብል ውጭ የሆነ መናፍቅነት ነው፡፡ ከቅዱስ ሲኖዶስ ሕግ እና ሥርዓት ውጭ መውጣት ሕገ ወጥነት፣ ቀኖናን መሻር፣ ኃይማኖትን ማፍረስ ነው፡፡ የገቡትን ቃል መጣስ ነው፤ ከጥንት ጀምሮ መንበር ያለ ፓትርያርክና ከሀገሪቱ ርእሰ ከተማ ውጭ  የማይሰየም መሆኑ እየታወቀ መንበር አቋቁመናል ማለት የፓትርያርክን እና የሲኖዶስን ሥልጣን መቃወም፤ ከሃይማኖትም፣ ከቀኖናዊ ትውፊትም፣ ከአስተዳደራዊ መዋቅርም መውጣትና ራሳቸውን ከቤተ ክርስቲያን መንበር የለዩ በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ድርጊቱን አውግዟል፡፡  

  ይህን ህገወጥ ተግባር ለመፈጸም በሀገራችን ተከስቶ የነበረው ጦርነት እንደ ምክንያት የተጠቀሰ ቢሆንም ቤተክርስቲያን ከጦርነቱ በፊት ጦርነት እንዳይከሰት ያደረገችውን ጥረት በጦርነቱ ወቅት ለተደረጉ ድጋፎችና ከጦርነቱ በኋላ ለተደረጉ የእንወያይ ጥረቶች እንዲሁም በቤተክርስቲያን በኩል የተዘረጋውን የሰላምና የእርቅ በር ይልቁንም ለሰላም ሲባል በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ የተጠየቀውን ይፋዊ ይቅርታ በመግፋት የተደረገ ኢ-ክርስቲያናዊ ተግባር ነው።
  
  በመሆኑም

•  በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 16 ንዑስ ቁጥር 30 የአጲስ ቀጶሳት መሾም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፣ በቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት እንዲመረጡና እንዲሾሙ የመወሰን ሥልጣን የቅዱስ ሲኖዶስ መሆን የሚደነግገውን ክፍል በግልጽ የጣሰ በመሆኑ

•  በሕገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ 31 ንዑስ ቁ 1 እና 3 የቅዱስ ፓትርያርኩን የመዓርግ ስምና መንበር በተመለከተ የተደነገገውን ድንጋጌ የሚያፋልስ ህገወጥ ተግባር የተፈጸመ በመሆኑ
 
• በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 37 ንዑስ ቁ.1 የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ የሚፈጸመው ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ አስፈላጊ መሆኑ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሲታመንበትና ሲወሰን ብቻ እንደሚፈጸምና መደንገጉ፤ 

• በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 18 ንዑስ ቁጥር 5 የቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖታዊ ሕግጋትንና ቀኖናን የሚያፋልስ ሊቀ ጳጳስ /ኤጲስ ቆጶስ/ ከአባልነት እንደሚሰረዝ በመደንገጉ፤ 

• በአጠቃላይ የተፈጸመው ሕገ ወጥ ተግባር በሕገ ሰብእም ሆነ በሕገ እግዚአብሔር ሚዛን የተወገዘ ከመሠረተ እምነት የተለየ፣ በአበው ቀኖና፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያን እና በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር  ተቀባይት የሌለው ነው፡፡ ስለዚህ
1ኛ. በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 138 መሠረት ሐምሌ 16 እና ሐምሌ 23 ቀን 2015 ዓ.ም በክልል ትግራይ በማዕከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን ውስጥ 

1. ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ የመቀሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የእንቅስቃሴው ሰብሳቢ

2. ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ በክልል ትግራይ የማዕከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

3. ብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ የአዲግራት ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

4. ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የሽሬ እንዳሥላሴ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በጸሎት ተከፈተ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በትግራይ ክልል ባሉ አህጉረ ስብከት ለመንፈሳዊ አገልግሎት ተመድበው የነበሩ አራት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሐምሌ ፲፮ እና ፳፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም በፈጸሟቸው የቀኖና ቤተክርስቲያን እና የሕግጋተ ቤተክርስቲያን ጥሰቶች ዙሪያ ለመወያየትና ሕግጋተ ቤተክርስቲያንን መሠረት ያደረጉ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ ጉባኤውን በጸሎት ጀምሯል።

ሕገወጥ ድርጊቱ መፈጸሙን ተከትሎ በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በኩል የተጠራውን  አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ለመጀመር ዛሬ ሐምሌ ፳፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቀኖና ቤተክርስቲያንና ሕገ ቤተክርስቲያን በሚያዘው ሥርዓት መሠረት የመክፈቻ ጸሎቱ ደርሷል።

የመክፈቻ ጸሎቱ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተመራ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ሌሎች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ባሉ አህጉረ ስብከቶች ተመድበው የቤተክርስቲያንን አገልግሎት የሚመሩ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተዋል።
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

+ #ሰማዕተ_ጽድቅ_ብጹዕ #አቡነ_ጴጥሮስ ዘኢትዮጵያ  +

     +   #ለእውነት የቆሙ ለሚጠብቁት ሕዝብ ከቃላት ባለፈ በተግባር #እስከሞት ድረስ የታመኑት ብጹዕ #አቡነ_ጴጥሮስ ጳጳስ ዘምስራቅ ኢትዮጵያ ተላዌ አሠሩ ለአቡነ ኢየሱስ ሞዓ :

ሐምሌ 22 / 1928  እንዲህ ሆነ ፦
      ጊዜው የጠላት ፋሺስት ጦር አዲስ አበባን በጠቆጣጠረበት ሰዓት ነው። ለእውነት የቆሙ ለሚጠብቁት ሕዝብ ከቃላት ባለፈ በተግባር አስከሞት ድረስ የታመኑት ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ ጳጳስ ዘምስራቅ ኢትዮጵያ ተላዌ አሠሩ ለአቡነ ኢየሱስ ሞዓ የአዲስ አበባን ሕዝብ  አያስተማሩና እያጠነከሩ ለመጣው ጠላት ሕዝቡ አጅ አንዳይሰጥ ሲያበረቱ ይህን ተግባራቸው ባስቆጣቸው የጠላት ጦር ፊት ሊቀርቡ ተገደዱ።

" ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ ቁመታቸው ረዘም ፊታቸው ዘለግ ያለና መልካቸው ጠየም ያለና አላዋቂነታቸውና ትሕትናቸው ከገጻቸው የሚነበብ ሲሆን በዚህ ጊዜ ለብሰውት የነበረው ልብሰ ጵጵስና ጥቁር ካባ ያውም በጭቃ የተበከለ ነበር ። በዚህ ሁኔታ ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ችሎት ቀረቡ ። ለፍርድም የተሰየሙት ዳኞች ሲሆኑ እነዚህም ጣሊያኖች እና የጦር ሹማምንት ናቸው ። የመካከለኛው ዳኛ ኮሎኔል ነበር ። የቀረበባቸውም ወነጀል ፦

ሕዝብ ቀስቅሰዋል ራስዎም አምጸዋል ሌሎችም እንዲያምጹ አድርገዋል የሚል ነበር ። ዳኛውም ካህናቱም የሆኑት ሆኑ የቤተ ክህነት በለስልጣኖች ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ቄርሎስ የኢጣልያንን መንግሥት ገዥነት አምነው አሜን ብለው ሲቀበሉ እርሶ ለምን ዓመጹ ፣ ለምን ብቻዎን አፈንጋጭ ሆኑ ? ሲል ጠየቃቸው አቡነ ጴጥሮስም የሚከተለውን መለሱ ። "

" #አቡነቄርሎስ ግብጻዊ ናቸው ። ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን  የሚገዳቸው ነገር የለም ። እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ ኃላፊነትም ያለብኝ የቤተክርስቲያን አባት ነኝ ።ስለዚህ ስለ ሀገሬና ስለ ቤተ ክርስቲያኔ እቆሮቆራለው ። ከዚህ በቀር ለእናንተ ችሎት የማቀርበው ነገር የለኝም ። ለፈጣሪዬ ብቻ  የምናገረውን እናገራለው ። እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ ዐውቃለሁ ። ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለገችሁትን አድረጉ ። ግን ክርስቲያኖችን አትንኩ ።"  አሉ ።

ይህንንም ብለው በጥይት ተደብድበው ሲገደሉ እንዲያይ ተጋብዞ  ለተሰበስበው ሕዝብ የሚከተለውን ሕያው መልእክት አስተላለፉ ።

" አረማዊ የሆነው የፋሺስት መንግስት ቤተክርስቲያንን ለማቃጠል ፤ ሕዝበ ክርስቲያንን ለመግደል ሐይማኖትን ለማጥፋት  ፤ ታሪካችንን ለማበላሸት የመጣ ነው እንጂ በጎ ለመስራት ፤ እውነተኛ ፍርድ ስላልመጣ ለዚህ ለግፈኛ አትገዙ ። ስለ ውድ ሀገራችሁ ፣ ስለ ቀናች ሐይማኖታችሁ ተከላከሉ ።ነጻነታችሁ ከሚረክስ ሙታችሁ ስማችሁ ሲቀደስ ታላቅ ዋጋ ያለው ክብር ታገኛላችሁ ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዚህ ጠላት እንዳይገዛ አውግዣለው ፣ የኢትዮጵያ መሬት ጠላትን ብትቀበል

የተረገመች ትሁን ። በፈጣሪዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተገዘተች  ትሁን ።"

አስተርጓሚው በጳጳሱ ላይ ተጽዕኖ ስላሳደረባቸው እውነተኛ ንግግራቸው ሳይገለጥ ቀረ ። ቀጥሎም ብጹዕነታቸው በፍርድ ችሎት ላይ እንዳሉ ሕዝቡ ሁሉ ስለ ርሳቸው እያዘነ ሳለ መስቀላቸውን አውጥተው እየጸለዩ ሕዝቡን ባረኩ ። ወዲያው የሞታቸው ፍርድ ሲሰማ ሕዝቡ በኢጣልያ የእጅ ሰላምታ አይነት እጁን እንዲያነሳ ታዘዘ ። በዚያን ጊዜ አቡነ ጴጥሮስ የሞታቸውፐ ሰዓት መድረሱን አውቀው ሰዓታቸውን ከኪሳቸው አውጥተው ተመለከቱ ። በዚህ ጊዜ ሁሉ ምንም አይነት ፍርሀት አይታይባቸውም ነበር ። የሞታቸውን ፍርድ ያነብ የነበረው ኢጣሊያዊ ዳኛ ግን ይንቀጠቀጥ ነበር ። ታላቅ ፍርሀትም በፊቱ ላይ ይታይ ነበር።

ይሞቱ ዘንድ የተፈረደባቸው በጹዕ አቡነ ጴጥሮስ በችሎቶ ፊት ለብዙ ሰዓታት ቆመው ስለዋሉና ደክሟቸው ስለነበር ለመቀመጥ ፈልገው ዳኛውን በትሕትና በፈገግታ ጠየቁት ። እንዲቀመጡ ፈቀደላቸው ። በሞታቸው ፍርድ ከተነበበ በኋላ የፈረዱባቸውን ዳኞች በመስቀላቸው ባረኳቸው ።

ከመካነ ፍትሑ 10 ሜትር ርቆ በሚገኝ ቦታ ተወሰዱ።
ከገዳዮቹም አንዱ " ፊትዎን ለመሸፈን ይፈልጋሉን ?" ሲል ጠየቃቸው ። ይህ የአንተ ስራ ነው ሲሉ ብጹዕነታቸው መለሱ።

ከዚያም በኋላ 8 ወታደሮች በስተ ጀረባቸው ሃያ ርምጃ ርቀው ተንበርክከው በተጠንቀቅ ቆሙ ።ወዲያው አዛዡ " ተኩስ " በማለት ትዕዛዝ ሲሰጥ ። ስምንቱም ተኩሰው መቷቸው ። ግን  በስምንት ጥይት ሳይሞቱ ቀሩ ። መሞታቸውን እና አለመሞታቸውን ለማረጋገጥ ዶክተር ተጠራ ። ዶክተሩም እንዳልሞቱ አረጋገጠ ። ከዚያም ሌላ ወታደር በሦስት የሽጉጥ ጥይት ራስቅላቸውን መትቶ ገደለቻው ።

አቡነ ጴጥሮስ ሲገደሉ ይዘውት የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ መሐል ለመሐል በጥይት ተሰንጥቆ ነበር ። መስቀላቸውም በመሐከሉ ላይ ጥይት በስቶት ወጥቷል።

/ ኮርዬር ዴላሴር ( corriere della sera ) የተባለ ጋዜጠኛ ወኪል እና የምስራቅ አፍሪካ ዜና መዋዕል አዘጋጅ የነበረው " ፖጃሌ" የተባለ ጋዜጠኛ እ.ኤ.አ  ሰኔ 15 ቀን 1936 ዓ/ም ያየውን ና የተመለከተውን እንዲህ ጽፎታል /

የሰማእቱ አባታችን አቡነ ጴጥሮስ
የእምነታቸው ጽናት ይደርብን
🙏__

ምንጭ
* ዜና ጳጳሳት ኢትዮጵያውያን (ዲ/ን መርሻ  አለኸኝ )
* ታሪካዊ መዝገበ ሠብ ( ፈንታሁን እንግዳ )

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @ortodoxtewadochannal
🔸🔹🔸 @ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

ለሲኖዶሳዊ ልዕልና መከበር የምእመናን ድርሻ ከፍተኛ ነው!

ክፍል ሁለት

፪.፩. ሲኖዶሳዊ ልዕልና እንዲሸረሸር ያደረጉ ምክንያቶች፡-
ተወዳጆች በክፍል አንድ ስለ ሲኖዶሳዊ ልዕልና መከበር የምእመናን ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን አንድ ጽሑፍ አድርሰናችሁ ነበር፤ ክፍል ሁለትን እነሆ ብለናል!

ከጥቂት ዓመታት ወዲህ እንደ ሀገር ትልቅ ችግር ገጥሞናል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና የሚዳፈሩ፣ የሚያወጣቸው ሕጎች እና ውሳኔዎች እንዳይፈጸሙ የሚሠሩ፣ ሲኖዶሱን ለመከፋፈል፣ ሚዛኑን እንዲስት፣ ለአገልግሎት እንዳይተጋ፣ አደራውን እንዳይጠብቅ፣ በሕዝቡ ዘንድ ውዥንብሮች የሚፈጥሩና የሚከፋፍሉ፣ ከሲኖዶሱ የበለጠ ሐሳባቸው የሚደመጥ ግለሰቦችና ቡድኖች መፈጠራቸው ብዙ ውጫዊና ውስጣዊ ቅንጅት የፈጠሩ አካላት ቀላል የማይባል ችግር እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡

ይህም ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ደካማና መሪ የሌላት አስመስሏታል፤ ቁሳዊና መንፈሳዊ ሀብቷን መጠበቅ እንዳትችልና ለውስጣዊና ለውጫዊ ጠላት እንድትጋለጥ ያደረገ ሲሆን የከፋው ደግሞ ያለስሟ ስም እንዲሰጣት፣ የታሪክ ሽሚያ እንዲደረግባት፣ ትውልዱ በተዛባ መንገድ እንዲረዳት፣ በእርሷ እንዳይጠቀም፣ ይልቁንም በጥላቻ እንዲነሣባት ሀገራዊ ውለታዋንም እንዳያስታወሰው አድርጎታል፡፡ ከፍተኛ የሆነ የሚድያ ዘመቻ ይከፈትባታል፤ የጥቃት ሰለባ እንድትሆን፣ ሀብቷ ለውድመት አማኞቿም ለሞትና ለስደት እንዲዳረጉ አድርጓል፡፡
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

✝✝††† እንኳን ለሰማዕታት አበው አቡነ ጴጥሮስ ኢትዮጵያዊ : ቅዱስ መቃርስ እና ቅዱስ ለውንትዮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ታላቁ ኢትዮጵያዊ ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስ †††

††† ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ምንም እንኳ ለሃገራቸውና ሃይማኖታቸው ያን ያህል ዋጋ ቢከፍሉም ትውልዱም : መንግስቱም : ራሷ ቤተ ክርስቲያናችንም ተገቢውን ክብር ሰጥተው እያሰቧቸው አይደለም:: እስኪ እንዲያው ቢያንስ እንደ ክርስቲያን : አንድም እንደ ኢትዮጵያዊ እነዚህ ነገሮቻቸውን እናስብ::

ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ከልጅነታቸው ጀምረው ትምሕርት : ትሕርምትና ደግነት ወዳጅ እንደ ነበሩ ይነገራል:: ወቅቱ ኢትዮጵያ የራሷን ጳጳሳት የምትሻበት ጊዜ ነበርና በፈቃደ እግዚአብሔር ለመጀመሪያ ጊዜ የሃገራችን አራት አባቶች ጵጵስናን ተሾሙ::

እነርሱም ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ እና አበው አባ ሚካኤል: አባ አብርሃም እና አባ ይስሐቅ ናቸው:: የተሾሙትም ግንቦት 18 ቀን 1921 ዓ/ም ነው:: አቡነ ጴጥሮስ ከተሾሙ በኋላ በሐዋርያዊ አገልግሎትና በጸሎት ተግተው ኑረዋል::

በ1928 ዓ/ም ፋሺስት ጣልያን ሃገራችንን በወረረች ጊዜ ቆራጡ ጳጳስ በዱር በገደል ለመሔድ ተነሱ:: በየበርሃው እየሔዱ አርበኞችን ሲያጽናኑ : ሲናዝዙ : ሲባርኩም ቆይተዋል:: ለሃገራቸውና ለሃይማኖታቸው ረሃብ : ጥም : እንግልትን ታግሰዋል::

በተያዙባት በዚያች ሌሊትም በጣልያኖች ለሮም እምነትና ለአገዛዙ እንዲያጐበድዱ ተጠየቁ:: ቆራጡ ሰው ግን እንቢ ቢሉ የሚደርስባቸውን እያወቁ "አይደረግም" አሉ:: በማግስቱ በአደባባይ መትረየስ ተደግኖባቸው አሁንም ጥያቄ ቀረበላቸው::

አቡነ ጴጥሮስ አፋቸውን ከፍተው ሊናገሩ ጀመሩ:- "የሃገሬ ሕዝብ ሆይ! ለሃገርህ : ለሃይማኖትህ ባትጋደል ትውልድ ይፋረድህ:: ለጣልያን ግን እንኳን ሰው ዛፍ ቅጠሉ መሬቱ እንዳይገዛለት አውግዣለሁ" አሉ:: በደቂቃዎች ልዩነት በግራዚያኒ ትዕዛዝ የመትረየስ ጥይት ዘነበባቸው::

አካላቸው ተበሳስቶ በሰንሰለት እንደ ታሠሩ መሬት ላይ ወደቁ:: አንዱ ወታደር ቀርቦ ቢመለከት ትንሽ ትንፋሽ ነበረቻቸው:: "ይሔ ቄስ አልሞተም" ብሎ ጭንቅላታቸው ላይ ተኮሰባቸው::

አቡነ ጴጥሮስ ለሃገራቸውና ሃይማኖታቸው ተሠው:: ነገሩ በአርበኞች ዘንድ ሲሰማ ትግሉ ተቀጣጠለ:: ይሄ የተደረገው ሐምሌ 22 ቀን በ1928 ዓ/ም ነው:: አቡነ ጴጥሮስም በተ/መ/ድ (UN) የሺህ ዓመቱ ምርጥ ሰማዕት (MARTYR OF THE MILLENIUM) በመባል ይታወቃሉ::

††† ቅዱስ መቃርስ ሰማዕት †††

††† ሰማዕቱ ተወልዶ ያደገው በአንጾኪያ (ሶርያ) በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን የታላቁ ቅዱስ ፋሲለደስ እና የቅድስት ሶፍያ ልጅ ነው:: ምንም በቤተ መንግስት ውስጥ ቢያድግም ከወላጆቹ ፍቅረ ክርስቶስን : ንጽሕናንና ደግነትን ወርሷል::

በተለይ ነዳያንን ሰብስቦ ዕለት ዕለት ያበላ ነበር:: (መቃርስ ማለት በልሳነ ዮናኒ ብጹዕ : ንዑድ : ክቡር ማለት ነው::) ቅዱሱ ያ የመከራ ዘመን ሲመጣ ሁሉም ቤተሰብ ስለ ክርስቶስ መሞትን በመምረጡ እርሱም ደስ እያለው የመከራው ተካፋይ ሆኗል::

ያን የመሰለ የቤተ መንግስት ክብር ስለ ክርስትና ናቀው:: ተገረፈ:: ተሰቃየ:: በእሳትም ተቃጠለ:: አንድ ጊዜም በአደባባይ የሞተ ሰው በጸሎቱ አስነስቶ "መስክር" አለው:: ከሞት የተነሳውም የክርስቶስን አምላክነት በመመስከሩ በአደባባይ የነበሩ ብዙ አሕዛብ በክርስትና አምነው ተሰይፈዋል::

ቅዱስ መቃርስን ግን ብዙ አሰቃይተው በዚህች ቀን አንገቱን ቆርጠውታል:: ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ አጽሙን አፍልሶ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በስሙ ቤተ ክርስቲያን አንጾለታል::

††† ቅዱስ ለውንትዮስ ሰማዕት †††

††† ቅዱሱ የተወለደው በተመሳሳይ ዘመን (በቅዱስ መቃርስ) ሲሆን ሃገሩ ጠራብሎስ ትባላለች:: በወቅቱ በወታደርነት ነገሥታቱን ያገለግል ነበር:: ድንግል : ደም ግባት የሞላለት ወጣት ስለ ነበር በሰዎች ፊት ሞገስ ነበረው::

እርሱ ግን ምንም ወታደር ቢሆን ጾምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር:: በተለይ ደግሞ የዳዊትን መዝሙር እየመላለሰ ይጸልየው : ይወደው ነበር:: ንግግሩ ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ጨውነት የታሸ ነውና ብዙ ጓደኞቹን ከክህደት ወደ ሃይማኖት : ከክፋት ወደ ደግነት መልሷል::

የመከራ ዘመን በደረሰ ጊዜም በገሃድ ስመ ክርስቶስን ይሰብክ ነበር:: ክፉ ሰዎች ከሰውት በመኮንኑ ፊት በቀረበ ጊዜም አልፈራም:: ወታደሮቹ መሬት ላይ ጥለው እየደበደቡት : ደሙ እንደ ጐርፍ እየተቀዳ እርሱ ግን ይዘምር ነበር::

በመጨረሻም ስለ ክርስቶስ ፍቅር በዚህች ቀን አንገቱን ተሰይፏል:: ቅዱስ ለውንትዮስ እጅግ ተአምረኛ ሰማዕት ነውና በእምነት እንጥራው::

††† እግዚአብሔር ዐጽመ ሰማዕታትን ይጠብቅልን:: ከሰማዕታቱ ጽናትን : ጸጋ በረከትን ይክፈለን::

††† ሐምሌ 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕት (ኢትዮጵያዊ)
2.ቅዱስ መቃርስ ሰማዕት (የፋሲለደስ ልጅ)
3.ቅዱስ ለውንትዮስ (ክቡር ሰማዕት)
4.አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት (ቅዳሴ ቤታቸው)
5.ቅዱስ መርካሎስ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
3.ቅዱስ ደቅስዮስ (የእመቤታችን ወዳጅ)
4.አባ ጳውሊ የዋህ

††† "እንግዲህ አትፍሯቸው:: የማይገለጥ የተከደነ: የማይታወቅም የተሠወረ ምንም የለምና:: በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ:: በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ:: ሥጋንም የሚገድሉትን: ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ:: ይልቅስ ነፍስንም: ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ::" †††
(ማቴ. ፲፥፳፮)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

ማኅበረ ቅዱሳን በትግራይ በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓ.ም የተካሄደውን ሕገ ወጥ ሢመተ ኢጲስ ቆጶሳት የፈጸሙ አባቶችና የተሳተፉ አካላት ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ኅብረት እንዲመለሱ ጥሪ አቀረበ።

ማኅበሩ ዛሬ ሐምሌ 20/2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ "ቅዱስ ሲኖዶስ ወደፊት መሰል ሕገ ወጥ ድርጊቶች እንዳይደገሙ የሚያደርግ አስተማሪ ውሳኔ እንደሚያስተላልፉ እንጠብቃለን" ብሏል።

ቤተክርስቲያን ለገጠማት ችግሮች በውስጥና በውጭ ብዙ ገፊ ምክንቶች ቢኖሩም ከዚህ የሕግና የቀኖና ጥሰት በስተጀርባ ያለው አንዱ በግንቦት 15 ቀን 2004 ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ  ተወግዞ የተለየው ማኅበረ ሰላማ የሚባል ድርጅት እንደሚገኝበት መገመት አያዳግትም ያለው ማኅበሩ ይህ ድርጅት በ1994 ዓ.ም የተመሠረተ ሲሆን በትግራይ ክልል ፍትሕ ቢሮ “ማኅበረ ሰላማ ምትሕግጋዝ ማህበር” በሚል ስያሜ በልማት ስም ፈቃድ ያለው ቢሆንም ከቤተክርስቲያን እውቅና ውጭ በመንቀሳሰቀስ አባቶችን ተመሳስሎ በየገዳማቱ በመግባት የኑፋቄ ሥራ ላይ በመገኘቱ የመቐለ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በቁጥር 781/737/97 በቀን 11/11/97 ዓ.ም የማገጃ ደብዳቤ እንደጻፈበት ጠቅሷል።

አሁንም ይህ ማኅበር በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የተከሰተው የቤተክርስቲያን የአስተዳደር ግንኙነት ክፍተት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የኑፋቄ ተግባሩን አጠናክሮ የቀጠለ ይመስላል በማለት 7 ነጥቦችን ዘርዝሯል።

1. በትግራይ ክልል በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሄደው ሕገ ወጥ ሢመተ ኢጲስ ቆጶሳት  ማኅበረ ቅዱሳን እጅጉን አዝኖአል፡፡
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

4. በየደረጃ ያሉ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሥራ ኃላፊዎች እና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ምዕመናን ከአሁን ቀደም በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በደረሰው ፈተና በሐዘንና በጸሎት ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን በመቆም ላሳያችሁት ጽናት እያመሰገንን አሁንም በደረሰው ፈተና እንዳሁን ቀደሙ ሁሉ በሐዘንና በጸሎት ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን ጸንታችሁ እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

5. በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ ተገቢውን ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ በትግዕስት እንድትጠብቁ እናሳስባለን፡፡

6. ምንም እንኳን ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ ጥሪው በደብዳቤ የተላለፈ ቢሆንም የመልእክቱ በፍጥነት መድረስ ካለው ስጋት አንጻር የችግሩን ተደጋጋሚነትና አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ክፍለ ዓለማት የምትገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ተጠቃላችሁ ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ እንድትመጡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡


7. ሁሉም የቤተ ክርስቲያናችን ሚዲያዎችና ሌሎች መገናኛ ብዙኃን ይህን መልዕክት ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን መልእክቱን በማስተላለፍ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ በቤተ ክርስቲያናችን ስም እንጠይቃለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም.

ምንጭ: ኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

🥀የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል ፣ ቅዱስ ቂርቆስና የእናቱ የቅድስት እየሉጣ ተራዳኢነት ጸሎት አይለየን። ከዚህ በኋላ ሕፃኑን አስፈልገው ቢጠይቁት ነቢዩ ዳዊት የተናገረው ኃይለ ቃል መንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት፤ ‹‹የአሕዛብ ጣዖታት የወርቅና የብር የሰው እጅ ሥራዎች ናቸው፡፡ የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ›› መዝ. ፻፴ በማለት ሲዘልፏቸው አገር ገዥው ሰምቶ ተቆጣና የብረት ጋን አስመጥቶ ውኃ ሞልቶ ከዕቶን እሳት ላይ ጥዶ ልዩ ልዩ ማገዶዎች በመጨመር ነበልባሉ ከመጠን በላይ ሆነ፡፡ የብረት ጋኑም ድምፅ እንደ ክረምት መብረቅና ነጎድጓድ እስኪያስፈራ ድረስ አስነድዶ ሕፃኑን ከነእናቱ ወስዳችሁ ጨምሩአቸው ብሎ አዘዘ፡፡

🥀በዚህ ጊዜ ቅድስት ኢየሉጣ በጣም ፈራች፡፡ የእግዚአብሔር ሥራ እፁብ ድንቅ ግሩም ረቂቅ ነው፡፡ ገና አፉን ያልፈታ የሦስት ዓመት ሕፃን ‹‹እናቴ ሆይ! ገድላችን እንፈጽም ዘንድ ጨክኝ በርቺ›› አላት፡፡ ቅድስት ኢየሉጣም ‹‹ልጄ የነፍስ አባት ሁነኝ›› አለችው፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ከዘመናቸው ሳይደርስ፣ ታሪካቸውን ሳይማር የሠለስቱ ደቂቅን ታሪክ መንፈስ ቅዱስ ገልጾለት ‹‹አናንያን፣ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ ያድነናል›› ቢላት ፍርሃቱ ሊለቃት ባለመቻሉ፣ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፡፡
@ortodoxtewadochannal
🥀‹‹ጌታ ሆይ! የወይኑን ፍሬ ስትሻ ግንዱን ታጠፋለህን? እንደዚህስ ሁሉ እኔን አድነህ እናቴን ታጠፋታለህን?›› ብሎ በጸለየጊዜ መንፈስ ቅዱስ አደረባትና መንግሥተ ሰማያትን በዓይነ ሥጋ እንድታይ አደረጋት፡፡ ከዚህ በኋላ ፍርሃቱ ለቀቃትና ‹‹ልጄ ሆይ! ከዛሬ ጀምሮ መምህሬ፣ አባቴ፣ መካሪዬ እልሃለሁ እንጂ ልጄ አልልህም›› ብላ በጭካኔ ከልጅዋ ጋር ወደ ፈላው የብረት ጋን ገባችበት፡፡

🥀በዚህ ጊዜ ሕፃኑ ቂርቆስ አናንያን፣ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ ያድነናል ያለውን ቃል ለመፈጻም እግዚአብሔር አምላክ መልአኩ
ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው፡፡ መልአኩም በትእምርተ መስቀል እሳቱን ቢባርከው እንደ በረዶ ቀዝቅዞላቸዋል፡፡ በመልካቸውም እንደ ፀሐይ አበራ፡፡ ከእግር ጥፍራቸው እስከ ራስ ጠሩራቸው አንድም ሳይጎዳቸው በደህና ወጡ፡፡

🥀በመጨረሻም ሕፃኑ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ እንዲህ አለ፡፡ ይህን ያህል ገድል ተጋድዬ ምን ዋጋ ትሰጠኛለህ ቢለው፣ ጌታ በልብህ ያለውን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው፡፡ ዳግመኛም ሥጋህ በምድር ላይ እንዳይፈርስ እንዳይበሰብስ በኤልያስ ሠረገላ ላይ አኖርሃለሁ አለው፡፡

🥀ስለሆነም በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያናችን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለእናታችን ለቅድስት ኢየሉጣ እና ለሕፃኑ ለቅዱስ ቂርቆስ ያደረገውን ይህን ታላቅ ተአምር ድንቅ ሥራ በማሰብ ከዋዜማው ጀምራ እግዚአብሔርን ስታመሰግን ትውላለች ታድራለች፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር

🥀የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል በረከት ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይኑር አሜን፡፡

🥀የአመት ሰው ይበለን🤲 የሞዐ

    ተቀላቀሉ ቴሌግራም
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
    ( ፍቅርተ ኢየሱስ)

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

የ፸፪ቱ አርድእት ስም (ምንጭ:-መጽሐፈ ግንዘት)
#፲፪ቱ ሐዋርያት #፬ቱ ወንጌላውያንና ስያሜያቸው
      ፩) እስጢፋኖስ
      ፪) ጢሞቴዎስ
      ፫) ሲላስ
      ፬) በርናባስ
      ፭) ቲቶ
      ፮) ፊልሞና
      ፯) ቀሌምንጦስ
      ፰) ዘኬዎስ
      ፱) ቆርኔሌዎስ
      ፲) ቴዎፍሎስ
      ፲፩) ኤውዴዎስ
      ፲፪) አግናጥዮስ
      ፲፫) ጳውሎስ
      ፲፬) አርንያኖስ
      ፲፭) ማልኮስ
      ፲፮) ኤሌኖስ
      ፲፯) አርሳጢስ
      ፲፰) አስትራትዮስ
      ፲፱) አርስጦስ
      ፳) ጋይዮስ
      ፳፩) አድማጥስ
      ፳፪) ሉኪዮስ
      ፳፫) ዲዮናስዮስ
      ፳፬) መርአንዮስ
      ፳፭) አርክቦንዮስ
      ፳፮) አናሲሞስ
      ፳፯) ከርሳጊስ
      ፳፰) አኪላስ
      ፳፱) ሉቃስ
      ፴) ዮሴፍ
      ፴፩) ኒቆዲሞስ
      ፴፪) ያዕቆብ እኁሁ ለእግዚእነ
      ፴፫) ብርኮሮስ
      ፴፬) ንኪትስ
      ፴፭) ቀርስጶስ
      ፴፮) ክርስቶፎሮስ
      ፴፯) ፊልጶስ
      ፴፰) ጰርኮሮስ
      ፴፱) ኒቃሮና
      ፵) ጢሞና
      ፵፩) ጰርሚና
      ፵፪) ኒቆላዎስ
      ፵፫) ማርቆስ
      ፵፬) ሮፎስ
      ፵፭) እለእስክንድሮስ
      ፵፮) አንሞስ
      ፵፯) ስልዋኖስ
      ፵፰) ሰንቲኖስ
      ፵፱) ኢዮስጦስ
      ፶) አክዩቁ
      ፶፩) አፍሮዲጡ
      ፶፪) ገማልኤል
      ፶፫) እንድራኒቆስ
      ፶፬) አናንያ
      ፶፭) ጵርስቅላ
      ፶፮) አቂላ
      ፶፯) ኤጴንጤስ
      ፶፰) ዩልያል
      ፶፱) ጰልያጦስ
      ፷) መርማራያን
      ፷፩) ኬፋ
      ፷፪) ዑርባኖስ
      ፷፫) ሰጠክን
      ፷፬) አጤሌን
      ፷፭) አክሌምንጦስ
      ፷፮) ሄሮድያኖስ
      ፷፯) ጥርፌና
     ፷፰) ጠሪፌስ
     ፷፱) አስከሪጦስ
     ፸) ሉቅዮስ
    ፸፩) ሱሲ
    ፸፪) ጴጥሮስ
ናቸው። ቅዱስ ጳውሎስ ፲፬ቱን መልእክታት የጻፈው ከ፸፪ቱ አርድእት ውስጥ አይደለም። ከዚህ የተጠቀሰው ሌላ ጳውሎስ ሊሆን ይችላል። ሌሎችም በኋላ የተነሡ ስም ቢኖር ሞክሼ ሊሆን ስለሚችል በደንብ ማየቱ የተሻለ ነው።
                #፲፪ቱ #ሐዋርያትና የሚከበሩበት ቀን
        ፩) መስከረም ፩_በርተሎሜዎስ
        ፪) ጥቅምት ፲፪_ማቴዎስ
        ፫) ህዳር ፳/፲፯____ፊልጶስ
        ፬) ታኅሣሥ ፬_እንድርያስ
        ፭) ጥር ፬___ዮሐንስ
        ፮) የካቲት ፲_ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ
        ፯) መጋቢት ፲____ማትያስ
        ፰) ሚያዝያ ፲፯____ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ
        ፱) ግንቦት ፳፯_ቶማስ
        ፲) ሐምሌ ፪___ታዴዎስ
        ፲፩) ሐምሌ ፭_ጴጥሮስ
        ፲፪) ሐምሌ ፲_ናትናኤል
አራቱ ወንጌላውያን ከነምሳሌያቸው ደግሞ እንደሚከተለው ቀርበዋል።
                  #ወንጌላውያን
፩) ዘብእሲ ማቴዎስ__ጌታ ከዳዊት ዘር መወለዱን ስለሚገልጽ ዘብእሲ ተባለ።

፪) ዘአንበሳ ማርቆስ__አንበሳ ላምን ሰባብሮ እንደሚበባ ማርቆስም በግብጽ አውራጃዎች ያሉ ጣዖታትን አስተምሮ አጥፍቷልና ዘአንበሳ አለ።

፫) ዘላሕም ሉቃስ__ለጠፋው ልጅ ፍሪዳ መታረዱን አውስቶ ይጽፋልና ዘላሕም አለው።

፬) ዘንስር ዮሐንስ__ንስር ከፍ ብሎ እንደሚበር ዮሐንስም ከፍ ብሎ ምሥጢረ መለኮትን ይናገራልና ዘንስር አለው።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

ሐምሌ17
#ቅዱስ_እስጢፋኖስ

   👉አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ለሰማእቱ #ቅዱስ_እስጢፋኖስ ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን

   👉ጸሎቱና በረከቱ በህዝበ ክርስቲያን ላይ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኑር እና ወር በገባ በ 17 ቅዱስ እስጢፋኖስ ነው እስጢፋኖስ የግሪክ ቋንቋ ሲሆን ትርጓሜውም አክሊል ማለት ነው ቅዱስ እስጢፋኖስ በግሪክ ሀገር እንደተወለደ የሚነገርለትና ከክርስቶስ እርገት በኋላም አስራ ሁለቱም ሐዋርያት በጋራ ተሰብስበውና ለአገለግሎት ከመረጡዋቸው ሰባት ዲያቆናት አንዱና ዋነኛው ነበር  
  
   👉ሕዝቡን በማዕድ ያገለግሉ ዘንድ ሰባት ዲያቆናት ተመርጠዋል ከእነዚህ መካከል ቅዱስ እስጢፋኖስ አንዱ ሲሆን ለስድስቱ ዲያቆናት ደግሞ አለቃ ሊቀ ዲያቆን ሆኖ ተሹሟል ቅዱስ እስጢፋኖስ በማዕድ አገልግሎት ሕዝቡን ከማገልገሉ በተጨማሪ ወንጌልን ይሰብክ ነበር

   👉ተዐምራትን የማድረግ ጸጋም ተሰጥቶት ነበር በዚህም አገልግሎቱ ብዙዎችን ወደ ክርስትና መልሷል

   👉በዚህም አይሁድ በቅናት ተነሳስተው በሐሰት ከሰሱት ከከተማውም ወደ ውጭ አውጥተው ቄዳር በተባለ ቦታ በድንጋይ ወገሩት በሚወግሩትም ጊዜ ሰማያት ተከፍተው ምሥጢረ ሥላሴን እግዚአብሔርን በሦስትነቱ ተመለከተ

   👉ኢየሱስ ክርስቶስንም በአብ ቀኝ ተቀምጦ አየ  ለሚወግሩትም ሰዎች ከአምላኩ እንዲህ በማለት ምሕረትን ለመነ ጌታ ሆይ ይህንን ኃጢአት አትቁጠርባቸው በመጨረሻም ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ነፍሱን ሰጠ

   👉ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚሉት በአንድ ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ እስጢፋኖስም ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር ተንበርክኮም ጌታ ሆይ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ ይህንም ብሎ አንቀላፋ ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር ዮሐ ሥራ 7፥58—60  

   👉የቅዱስ እስጢፋኖስ ረድኤት በረከትና ምልጃው ፀሎቱ አይለየን ቃል ኪዳኑ ይጠብቀን
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

ምክረ አበው
የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል ምክረ አበው
የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትስራው ከሰራኸው እንደምትጠፋበት እወቅ።(መጽሐፈ ምክር)

"አንደበቱን ከቧልት ያየውን ሚስጥር ከመናገር የሚከለክል ሰው ልቦናውን ከኅልዮ ኃጢአት ያርቀዋል ።(አረጋዊ መንፈሳዊ)

ጸጋ ቢሰጥህ  በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እዳታጣ " (ማር ይስሃቅ)

‹‹ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ እውቀትን ያገኛል አዋቂ ነኝ የሚል ሰው ከፈጣሪው ‹ጥበብ ይለየዋል።›› /አረጋዊ መንፈሳዊ/

‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው  ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ።›› /አባ እንጦንስ/
‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻልናል።›› /ቅዱስ አትናቴዎስ/

‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል።›› /ቅዱስ ሚናስ/

‹‹በማንም ላይ ክፈትን አትስሩ አትፍርዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና።›› /ታላቁ አባ መቃርስ/

‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም።›› /ቅዱስ አርሳንዮስ/

‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል።›› /ቅዱስ እንድርያስ/

‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ነጹሕ ካደረግነው በጸጋ መንፈስቅዱስ የተሞላን እንሆናለን።›› /አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን/

‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው።›› /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ/

‹‹የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ህይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ።›› /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ/

‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር።›› /ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ/

‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል  ኃጥያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል።››  /ቅዱስ እንጦስ/
"አንደበቱን ከቧልት ያየውን ሚስጥር ከመናገር የሚከለክል ሰው ልቦናውን ከኅልዮ ኃጢአት ያርቀዋል ።(አረጋዊ መንፈሳዊ)

ጸጋ ቢሰጥህ  በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እዳታጣ " (ማር ይስሃቅ)

‹‹ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ እውቀትን ያገኛል አዋቂ ነኝ የሚል ሰው ከፈጣሪው ‹ጥበብ ይለየዋል።›› /አረጋዊ መንፈሳዊ/

‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው  ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ።›› /አባ እንጦንስ/
‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻልናል።››
/ቅዱስ አትናቴዎስ/

‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል።››
/ቅዱስ ሚናስ/

‹‹በማንም ላይ ክፈትን አትስሩ አትፍርዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና።››
/ታላቁ አባ መቃርስ/

‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም።››
/ቅዱስ አርሳንዮስ/

‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል።›› /ቅዱስ እንድርያስ/

‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ነጹሕ ካደረግነው በጸጋ መንፈስቅዱስ የተሞላን እንሆናለን።››
/አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን/

‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው።›› /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ/

‹‹የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ህይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ።››
/ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ/

‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር።›› /ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ/

‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል  ኃጥያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል ።
/ቅዱስ እንጦስ/
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…
Subscribe to a channel