ortodoxtewadochannal | Unsorted

Telegram-канал ortodoxtewadochannal - ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

1920

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቀ አስተምህሮ ✝መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር ይቀሰቀስኛል ለስሙ አንድዘምር🔔 የማንቂያ ደዉል🔔🔔 ክርስትና ዘር የለውም

Subscribe to a channel

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

#ሊቀ_መላእክ_ቅዱስ_ገብርኤል

🥀ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ኢትዮጵያውያን እሳት ውስጥ ከገባን ቆይተናል:: የሠለስቱ ደቂቅ እምነት ግን የለንም::
እንዲያውም ከእኛስ ናቡከደነፆር ሳይሻል አይቀርም:: ከእሳት እንዳወጣ እርስ በእርሳችን እየተባላን ከእሳቱ በላይ ጥላቻ እያቃጠለን ነው:: አንዱ በሌላው ሞት እየዘበተ አንዱ የሌላው ለቅሶ እያሳቀው የኢትዮጵያ ሠለስቱ ደቂቆች ለፈጣሪም አልመች ብለን ተጨካክነናል::
🥀አንዴ አናንያና አዛርያ ሚሳኤል ላይ ሲወርዱበት አንዴ አዛርያ ከአናንያ ሲጣላ እየዋልን እርስ በእርሳችን ተራ በተራ እየተናከስን በእሳት ውስጥ ሆነን እንኳን መደማመጥ አልቻልንም:: ናቡከደነፆርና ወዳጆቹ በጥላቻ ዓይናቸው እያዩን እንኳን መስማማት አቅቶናል::
ቅዱስ ገብርኤል ሆይ እንደ ሠለስቱ ደቂቅ ከእሳት ሳታወጣን በፊት እኛን ከእኛ ውስጥ አውጣን::

🥀ራሳችን እያራገብን ከምንቃጠልበት እሳት አድነን::
ናቡከደነጾርን ግራ ያጋባ መገዳደላችንን እና መበሻሸቃችንን በምልጃህ አስቁምልን:: ከሞትህ ሞቴ ከደምህ ደሜ ይበልጣል ከዕንባህ ዕንባዬ ይበልጣል ብለን ልናልቅ ነውና ለኢትዮጵያውያን ድረስልን::

🥀በግፍ የረገፉትን ንጹሐን በክንፎችህ ነፍሳቸውን ጋርድልን:: ተሰድደው ተፈናቅለው ያሉትን ሰብስብ::
ለኢትዮጵያም ድንግልን ባረጋጉ ቃላትህ "ዕንባን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው" ብለህ አረጋጋት
አሜን🙏::        ቴሌግራም ቻናልን ተቀላቀሉ
 @ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

​​​​​​👆 #የቀጠለ

የቅዱስ ሚካኤል አለቅነት በሐዲስ ኪዳንም አንደሚቀጥል ይህ ነቢይ በትንቢቱ “በዚያ ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ ሚካኤል ይነሣል..” (ዳን.12፡1) በማለት ተናግሮለታል ፡፡

ስለዚህም ቅዱስ ሚካኤል እኛን ከሰይጣን አሽክላና ወጥመድ ይጠብቀንና በጸሎቱ በእግዚአብሔር ፊት ይቆምልን ዘንድ በእኛም ላይ ሹም ነው። ምክንያቱም እኛ የእግዚአብሔር ሕዝቦችና የርስቱ ወራሾች ነንና፡፡

እግዚአብሔር ነቢዩ ሙሴን የሕዝቡ መሪ አድርጎ መሾሙ እጅግ ትሑትና ስለመንጎቹ ነፍሱን እንኳ አሳልፎ እስከመስጠት ደርሶ ስለሚወዳቸው ነበር፡፡ (ዘኁል.12፡3፤ዘጸአ.32፡32)በሕዝቡም ላይ እርሱን መሾሙ እንዲሠለጥንባቸው ወይም እንዲገዛቸው ሳይሆን በትምህርቱና በጸሎቱ እነርሱን እንዲያግዛቸው ነው፡፡ እንዲህም ስለሆነ ቅዱስ እስጢፋኖስ ስለሙሴ ሲመሰክር “እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው”አለ፡፡ (የሐዋ.7፡35)

እንዲሁ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል እጅግ ትሑትና ለሠራዊቱ ተቆርቋሪ የሆነ መልአክ በመሆኑ በመላእክትና በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ተሾመ፡፡ በመላእክትና በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙ ልክ እንደ ሙሴ በእነርሱ ላይ ሊሠለጥንባቸው ወይም ሊገዛቸው ሳይሆን መላእክትን ሊመራ ፣ እኛን ደግሞ ከሰይጣን ጥቃት ሊጠብቀንና በጸሎቱ ሊራዳን ነው (ይሁዳ.12) ፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን መላእክት እኛን እንደሚጠብቁና እንደሚራዱ እንዲሁም ስለእኛ በፊቱ አንደሚቆሙ ሲያስተምረን “ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ስንኳ እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ሁል ጊዜ በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁ” (ማቴ.18፡10) ብሎናል፡፡

እኛን ይጠብቁ ዘንድ የተሰጡን ቅዱሳን መላእክት ስለእኛ እንዲህ የሚቆረቆሩና ስለመዳናችን የሚተጉ ከሆነ በቅድስናው ልቆ የመላእክት አለቃ ሆኖ የተሾመው ቅዱስ ሚካኤል እንዴት ስለእኛ በእግዚአብሔር ፊት ይበልጥ አይቆም? (ሉቃ.13፡6-9) እንዴትስ በተሰጠው ሥልጣንና ኃይል አይረዳን? (መዝ.33፡7) እርሱ “ስለሕዝብህ ልጆች የሚቆመው” መባሉም እኛን በጸሎቱና በተራዳኢነቱ የጽድቅ ሕይወታችንን በሚገባ እንድናከናውን እንደሚራዳን የሚያሳይ ኃይለ ቃል ነው፡፡

የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ጸሎቱና በረከቱ በእኛ ላይ ለዘለዓለሙ ይደርብን አሜን፡፡

💚 @ortodoxtewadochannal 💚
💛 @ortodoxtewadochannal 💛
❤️ @ortodoxtewadochannal ❤️

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
.......ከክፍል አንድ የቀጠለ
➠ክፍል ሁለት
●●●●●●●●●●●●●●●●
አብዛኛው ሰው እራሱ በእጁ ጎትቶ ባመጣው ነገር ነው ነፍሱን እየገበረ የሚገኘው።

ወጣቶች በብዛት እራሳቸውን ሊያጠፉ የበቁት እድሜአቸው ሳይደርስ በልጅነታቸው የፍቅር ግንኙትተ ጀምረው ነው።
የፍቅር ግንኙነት ጀምረው ከሆነ ጊዜ በኋላ ግን የግንኙነታቸው ገመድ ሲበጠስ አንገታቸውን ለገመድ ይሰጣሉ።
በዚህ መሰረት ሌሎች ሌሎች ነገሮችንም እየጠቀስን መናገር ይቻላል።

በሌላ መንገድ ደሞ ወጣቱ ባልደረሰበት መከራውም ሆነ ችግሩ ተደራርቦ ይመጣል በዚህም ምክንያት እራሳቸውን ሊያጠፉ ይችላሉ።
ሰፊ ቦታዎችን የሚይዙት ደሞ መከራን ያልቀመሰ በችግር ያልተገረፈ ሰው ሁሉ ነገር አዲስ ስለሚሆንበት ለትዕግስት ጊዜ አይሰጡም።
በተለይ ደግሞ ቤተሰብ ወላጅ አቀማጥሎ ያሳደገው ልጅ ሁሉ ነገር ድንገት ቢጠፋ እነሱም አብሮ ለመጥፋት ቦታ ይሰጣሉ።

የሆነው ሆኖ ግን ይህንን ሁሉ በብልሃት ማለፍ የሁሉም ግዴታ ነው።
ኦርቶዶክስ ከሆንክ ኦርቶዶክስ ብልሃት ስላስተማረችህ ፤ሙስሊም ከሆንክ ብልሃት ተምረሃል እራን ማጥፋት ምን እንደሆነ ታውቀዋለህ ስለዚህ ሞትን በእምነትህ ልታሸንፈው ትችላለህ።

በተረፈ እራሳቸውን የሚያጠፉትን ሰዎች ዜና ማድረግ በተዘዋዋሪ ሌሎችን ለሞትን መጋበዝ አይሆንም ብላችሁ ታስባላችሁ ?

@ortodoxtewadochannal
 @ortodoxtewadochannal

✝️ወደ ቻናላችን ጎራ በሉ ሃሳብ እና አስተያየታችሁን አትንፈጉን!

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

ብፁዕ ወቅዱስ #አቡነ_ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሰሜን አሜሪካን የነበራቸውን ቆይታ በማጠናቀቅ ላይ ናቸው።

ከነሐሴ 27 ቀን 2015 ዓመተ ምሕረት ጀምሮ በሰሜን አሜሪካን የሚገኙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ቀደም ሲል በተያዘው  የጉዞ መርሐ ግብር መሠረት ጥቅምት  1 ቀን 2016 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱ ይሆናል።

የብፁዕ ወቅዱስ አባታችን በረከት አይለየን

ምንጭ፡ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

ሰውም ሲኖርም ሲሞትም ፈጣሪውን ማስደሰት አለበት እንጅ ያለ ፍሬ ንስሓ መሞት የለበትም፤ "ግበሩኬ እንከ ፍሬ ሠናየ ዘይደልወክሙ ለንስሓ፤ እንግዲህስ ለንስሓ የሚገባ ፍሬ አድርጉ እንዲል፡፡ (ማቴ.፫፥፰)
 
ወርኃ ጽጌ የእናታችንን ስደት ከተወደደው ልጇ ጋር የምናስብበት ነው። በተለይም ማሕሌተ ጽጌ በተባለው ድርሰት ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል እርሷን በአበባ ጌታችንን በፍሬ፣ እርሷን በፍሬ ጌታን በአበባ እየመለሰ ብሉይን ከሐዲስ አጣጥሞ የተናገረው ምሥጢር ድንቅ ነው። ክርስቶስን በአበባ ሲመስለው ነቢዩ ኢሳይያስ በትንቢቱ ቅዱስ ያሬድ በድጓው "ትወፅእ በትር እም ሥርወ እሴይ ወየዐርግ ጽጌ እም ጉንዱ" በማለት ድንግል ማርያምን በጉንድ ክርስቶስን በጽጌ መስሎ ይናገራል። እርሷን በአበባ ሲመስልም ከአበባ ፍሬ እንዲገኝ ፍሬ ሕይወት ፍሬ መድኃኒት ክርስቶስ ከእርሷ እንደሚገኝ ለማመልከት ነው። (ኢሳ.፲፩፥፩)
 
ከማሕሌተ ጽጌ አንድ ማሳያ አቅርበን ክርስቶስ ለምን ተሰደደ የሚለውን እንመልከት፤ “በጌጋየ አዳም ወሔዋን ሱራፊ ዘዐፀዋ፣ እንበለ ጽጌኪ መኑ ለአንቀጸ ገነት ዘአርኀዋ፣ ተፈሥሒ ድንግል መያጢተ አዳም እምጼዋ፣በተአምርኪ ውስተ ምድረ ጽጌ አቲዋ፣ ከመ ጣዕዋ አንፈርዓፀት ሔዋ፤በአዳምና በሔዋን በደል ሱራፊ የዘጋውን የገነትን በር ከጽጌ ልጅሽ በቀር ማን ከፈተው? አዳምን ከምርኮ የመለስሽው ድንግል! ደስ ይበልሽ  በተአምርሽ ወደ አበባይቱ ምድር ገብታለችና ሔዋን እንደ እንቦሳ ዘለለች።” ሊቁ በዚች ክፍል ብቻ ሐዲስን ከብሉይ እንዴት እንዳገናኘው ልብ ይሏል።
 
በሰውነቱ መሰደድ፣ መራብ፣ መጠማትን ገንዘብ ያደረገው ክርስቶስ እንደ አምላክነቱ ማንም በማይቀርበው ብርሃን የሚኖር ነቢዩ ዕንባቆም እንደተናገረው “እግዚአብሔር ከቴማን፥ ቅዱሱም ከፋራን ተራራ ይመጣል። ክብሩ ሰማያትን ከድኖአል፥ ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል። ጸዳሉም እንደ ብርሃን ነው፤ ጨረር ከእጁ ወጥቶአል፤ ኃይሉም በዚያ ተሰውሯል። ቸነፈር በፊቱ ይሄዳል፥ የእሳትም ነበልባል ከእግሩ ይወጣል። ቆመ፥ ምድርንም አወካት ተመለከተ፥ አሕዛብንም አናወጠ፤ የዘለዓለምም ተራሮች ተቀጠቀጡ፥ የዘለዓለምም ኮረብቶች ቀለጡ፤ መንገዱ ከዘለዓለም ነው” (ዕን ፫፥፴፮)  በማለት የገለጸው አምላክ ለምን ተሰደደ ቢሉ፡-
 
ለካሣ፦ የመጀመርያውን ሰው አዳምን በበደሉ ምክንያት ከገነት አስወጥቶት ነበርና ካሣ ይሆነው ዘንድ ዳግማዊ አዳም ክርስቶስም ተሰደደ። በገድለ አዳም ተመዝግቦ እንደምናገኘው አዳም ገነት ከወጣ በኋላ ተራበ ተጠማ ክርስቶስም በግብጽ ምድር ተራበ ተጠማ፣ አዳም ከገነት ሲወጣ ከሔዋን በቀር አብሮት ማንም አልነበረም፤ ዳግማዊ አዳም ክርስቶስም ከዳግማዊት ሔዋን ከድንግል ማርያም በቀር ማንም አልነበረውም፤ “ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ፣ ወላህዉ ፍሡሓን ተዘኪረክሙ ብዝኀ ሠናይታ፣ ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕቲታ፣ ተአወዩ በኀጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ፤ እናንተ ኀዘንተኞች የእመቤታችንን ስደቷን አስባችሁ አልቅሱ፣ እናንተ ደስተኞች የቸርነቷን  ብዛት አስባችሁ አልቅሱ። ድንግል ማርያም እንደ ወፍ በግብፅ ተራራዎች ብቻዋን ትዞራለች የአባቷ የኢያቄም ሀገር የምትሆን ኤፍራታን አጥታ ታለቅሳለችና እናተ ኀዘንተኞች አልቅሱ።” እንዲል (ሰቆቃወ ድንግል)
 
ስደትን ለሰማዕታት ለመባረክ፦ ሰማዕትነት እሳት፣ ስለት ብቻ መቀበል አይደለም ሀገር ጥሎ መሰደድም ሰማዕትነት ነውና። በመዋዕለ ስብከቱ  “በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ” ብሎ የሚያመጣው ነውና። (ማቴ.፲፥፳፫) የስደተኞች ተስፋ ክርስቶስ ገና በእናቱ እቅፍ ሳለ ስደትን ባረከው። “ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን ኢየሱስ ግፉዕ ምስካየ ግፉዓን፤ኢየሱስ በመሰደዱ የስደተኞች ተስፋ፣ በመገፋቱ የግፉዓን መጠጊያ ሆነ” እንዳለ ሊቁ (ሰቆቃወ ድንግል) ለዚህም ነው ዛሬ ቅዱሳን ፍቅሩ አገብሮቸው ከዘመድ ባዳ ከሀገር ምድረ በዳ አሰኝቶ በዱር በጫካ ከአራዊትና ከእንስሳት ጋር እየታገሉ መኖርን የሚመርጡት።
 
ቅድስት ድንግል ማርያም ከተወደደው ልጇ ጋር በስደት ሳለች ያጋጠማትን መከራዎች ከሰቆቃወ ድንግል አንዲትን ቃል አንሥተን እንመልከት። ገና የዐሥራ አምስት ዓመት ብላቴና ሳለች ሕፃን ታቅፋ መሰደዷን ተመልክቶ “ምዕረ በዘባንኪ ወምዕረ በገቦኪ ማርያም ብዙኀ በሐዚ ለሕፃን ደከምኪ ሶበኑ የሐውር  በእግሩ ከመ ትጹሪዮ ይበኪ” በማለት አንድ ጊዜ በጀርባዋ አንድ ጊዜ በጎኗ እያለች ልጅ አዝላ በግብጽ በርኃ ስትንከራተት የሚዘክራት ሰው አጥታ ይልቁንም የልጇን የወርቅ ጫማ ሲወስዱባት ምርር ብላ ስታለቅስ፣ ክርስቶስን ታቅፋ ይዛ ዓይኑን እየተመለከተች ስታልቅስ ልብ በሉ። ሊቁ ይህን ተመልክቶ እናንተ የገሊላ ሰዎች እንቦሳይቱ ማርያም ወዴት ሔደች በለቅሶ እከተላት ዘንድ  መንገዷን ነገሩኝ በማለት ይማጸናል። (ሰቆቃወ ድንግል)
 
ዛሬም ሊቃውንቱ ስደቷን እያሰቡ ሌሊቱን በማሕሌት ወደ ግብጽ እየወረዱ ያድራሉ። የቤተ ክርስቲያን ልጆች አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ! በእውኑ ዛሬስ ድንግል ማርያም ከስደት ተመልሳለችን? በልባችን ላይ ያነገስነው ሄሮድስን ወይስ ክርስቶስን? የቤተ ክርስቲያን ልጆች ዛሬም ድንግል ማርያም ተመልሳ የምታርፍበት የንጹሕ ልቡና ሀገር ያስፈልጋልና ማረፊያ ለመሆን እንዘጋጀ፡፡ ቅድስት ድንግል ወደ ሀገሯ ስትመለስ ከናዝሬት መልካም ሰው ይወጣልን የተባለላት ናዝሬት የተወደደ የተመሰገነ ክርስቶስን አስገኘች። ይህን ሳስብ ዛሬ የእኛ ሀገርም ድንግል ከስደት ከመመለሷ በፊት ያለችዋ ናዝሬት ትመስለኛለች፤ መልካም ሰው ደግ ሰው የለባትምና። "አድኅነኒ እግዚኦ እስመ ኀልቀ ኄር ወውኅደ ሃይማኖት እም እጓለ መሕያው፤ አቤቱ ደግ ሰው አልቋልና አድነኝ ከሰው ልጆችም መተማመን ጠፍቶአልና” እንዳለ ነቢዩ ዳዊት (መዝ.፲፩፥፩)
 
በመጨረሻም በየቀኑ የምትሰደደውን ድንግል ዓመት ጠብቀን ስደቷን ከምናስብ አሳዳጁን ሄሮድስን አስወግደን ዘወትር ሕፃኑንና እናቱን በልባችን ጽላት አንግሠን እንድንኖር አምላካችን ይርዳን።የልባችን ንጉሥ ክርስቶስ ሲሰደድ አብራ ትሰደዳለችና። ድንግል ሆይ "እስከ ማእዜኑ ትሄልዊ በምድረ ነኪር ሀገረኪ ገሊላ እትዊ፤ እስከመቼ ድረስ በባዕድ ሀገር ትኖሪአለሽ? ወደ ሀገርሽ ገሊላ ተመለሽ።” የሰላም መገኛ ሰላማዊት ርግብ ሱላማጢስ ሆይ፥ ሰላምን ትሰጭን ዘንድ ወደ ዐሥራት ሀገርሽ ገሊላ ኢትዮጵያ ተመለሽ።
 
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
 @ortodoxtewadochannal
 @ortodoxtewadochannal
 

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

የሰማዕታቱ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ  ይፈጸማል።
በአዳማ ዙሪያ ወረዳ ቤተ ክህነት በአርቱ መካነ ቅዱሳን ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ሁለት አገልጋዮች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገለዋል፡፡
          ---------------------------------------------
መስከረም 24/2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያንን በማገልገል ላይ የሚገኙ ታላቁ የጸሎት አባት አባ ተክለ አብ እና ቀሲስ መሠረት በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሲሆን መሪጌታ ፍሰሐ እና መርጌታ ተቅዋም የተባሉ አገልጋዮችን ታፍነው ባልታወቁ ኃይሎች መወሰዳቸውን የሀገረስብከቱ ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ዘግቧል።

በአዳማ ወረዳ ዙሪያ በቤተ ክርስቲያንና አገልጋዮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የቀጠለ ሲሆን በታላቋ የጸበል ቦታ በመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ የተፈጸመው ይኼ አሰቃቂ ድርጊት ነውርና ግፍ አሰቃቂና አሳዛኝ ጥቃት ስለሆነ አሁንም መሰል ጥቃት እንዳይስተናገድ የሚመለከተው አካል በርካታ ጸበልተኛ በቦታው ስለሚገኝ አስፈላጊ ጥበቃ እንዲደረግ ጥያቄ ቀርቧል።

በተፈጸመው ግፍና በደል የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ማዘኑን የገለጸ ሲሆን ከሚመለከተው አካል ጋር በጉዳዩ ዙሪያና ጥብቅ ጥበቃ በሚደረግበት ዙሪያ  እየተነጋገረ መሆኑን የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት     ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ  ገልጿል::
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

#እንኳን_አደረሳቹሁ  
            ቴሌግራም ቻናል⤵️
                                
  🥀በስመ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ  አሜን!
መስከረም 21-ብዙኃን ማርያም (የእመቤታችን የበዓሏ መታሰቢያ ነው፡፡)

🥀ዳግመኛም በዚኽች ዕለት አስቀድሞ ኃይለኛ ሥራየኛ ጠንቋይ የነበረውና በኋላም አምኖ ለክርስቶስ ምስክር ሆኖ አንገቱን የተሰየፈው ቅዱስ ቆጵርያኖስ በሰማዕትነት ያረፈበት ዕለት ነው፡፡

🥀ቆጵርያኖስን ያሳመነችውና ስሟ በተጠራበት ቦታ ሰይጣናት እንደ ትቢያ በነው የጠፉት ድንግሊቱ ዮስቴናም በሰማዕትነት ያረፈችው በዚሁ ዕለት ነው፡፡

🥀ዳግመኛም ይህች ዕለት የከበሩ ሃይማኖታቸው የቀና 318ቱ አበው ሊቃውንት በ325 ዓ.ም አርዮስን አስተምለው ለመመለስ በኒቅያ የተሰበሰቡባት ዕለት ናት፡፡ የጉባኤውም ፍጻሜ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓሉ ኅዳር ዘጠኝ ነው፡፡
+ የጌታችን ቅዱስ መስቀል ግሸን ደብረ ከርቤ የገባበት ዕለት ነው፡፡ (የመስከረም ዓሥራ ሰባቱን ይመለከቷል፡፡)

🥀 ከ72ቱ አርድእት አንዱ የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ጢባርዮስ ዕረፍቱ መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሰዋል፡፡
ቅዱስ ቆጵርያኖስና ድንግሊቱ ዮስቴና፡- ይኽም ቆጵርያኖስ አስቀድሞ ከሃዲና ሥራየኛ ነበር፡፡ እንዲያውም ለሥራየኖች ሁሉ አለቃቸው ነበር፡፡ በዚህ በጥንቆላ ሥራው ከመመካቱ የተነሣ ‹‹ሥራይ በማድረግ የሚስተካከለኝ ካለ ልይ እስቲ…›› በማለት ወደ አንጾኪያ አገር ሄደ፡፡ ቆጵርያኖስም አንጾኪያ በገባ ጊዜ ወሬው ሁሉ በሀገሪቱ ተሰማ፡፡ በአንጾኪያ የሚኖር አንድ ወጣት በመልኳ እጅግ ውብ የሆነችውን ወጣት ዮስቴናን ወደ ቤተ ክርስቲያን ስትሄድ እያያት እጅግ አድርጎ ወደዳት ነገር ግን እርሷ የክርስቶስ ሙሽራ ናትና እሺ ልትለው ስላልቻለች ሊያገኛት አልቻለም፡፡ ገንዘብ በመስጠት፣ በጉልበት በማስፈራራት፣ በሥራይ ሥራ በእነዚህ ሁሉ ሊያገኛት ስላልቻለ ወጣቱ አሁን የቆጵርያኖስን ወደ ከተማው መምጣትና ዝናውን በሰማ ጊዜ ደስ ብሎት ሄዶ ዮስቴናን እጅግ አድርጎ እንደወደዳትና ሊያገኛት እንዳልቻለ ነገረው፡፡
ቆጵርያኖስም ያንን ወጣት ‹‹እኔ የልብህን እፈጽምልሃለሁ አትዘን›› አለው፡፡            
                                       
  🥀ከዚህምም በኋላ ቆጵርያኖስ ድንግሊቱን ዮስቴናን እንዲያመጧት በሥራዩ የአጋንንትን ሠራዊት ላካቸው፡፡ እነዚያ በሥራይ ወደ እርሷ ተላኩ አጋንንትም ወደ ድንግሊቱ ዮስቴና በፍጹም ሊቀርቧት አልቻሉም ምክንያቱም እርሷ ዮስቴና በጾም በጸሎቷ የጸናች ናትና ከጸሎቷ የተነሣ አጋንንቱ ተቃጠሉ፡፡ ቆጵርያኖስ በሥራዩ ኃይል ዮስቴናን ያመጡለት ዘንድ ደጋግሞ ላካቸው ነገር ግን አጋንንቱ ቅድስት ዮስቴና በፍጹም ሊቀርቧት አልቻሉም፡፡ ከዚም በኋላ ቆጵርያኖስ ሁሉንም አጋንንት ጠርቶ ‹‹ድንግል ዮስቴናን ይዛችሁ ካላመጣችሁልኝ እኔ ከእናንተ ተለይቼ ክርስቲያን እሆናለሁ›› አላቸው፡፡ ከዚህም በኋላ የሰይጣናት አለቃ ቆጵርያኖስን ሊሸነግለው አሰበና ከሰይጣናት ውስጥ አንዱን ሰይጣን በዮስቴና ተመስሎ ለቆጵርያኖስ እንዲታየው አደረገ፡፡ ሰይጣኑም አለቃው እንዳዘዘው እንዲሁ አድርጎ (ዮስቴናን መስሎ) ተዘጋጀ፡፡

🥀ሰይጣኑም ለቆጵርያኖስ ‹‹እነሆ አሁን ዮስቴና መጥታለች›› አለው፡፡ ቆጵርያኖስም እውነት ዮስቴና የመጣች መስሎት እጅግ ደስ ብሎት ሊቀበላት ተነሣ፡፡ በዮስቴና አርአያ የተመሰለውንም ምትሀት ባየ ጊዜ ‹‹የሴቶች እመቤት ዮስቴና ሆይ! መምጣትሽ መልካም ሆነ›› አላት፡፡ ቆጵርያኖስም የቅድስት ዮስቴናን ስሟን መጥራት በጀመረ ጊዜ በእርሷ ተመሰለው ሰይጣን እንደጢስ በኖ ጠፋ፡፡

🥀ቆጵርያኖስም በዚህ ጊዜ የሽንገላው ምክንያት ምትሐቱ ሁሉ ከንቱ እንደሆነ ዐወቀ፣ አስተዋለ፡፡ በልቡም እንዲህ አለ፡- ‹‹ስሟን በጠሩበት ቦታ አጋንንት እንደ እንደጢስ የሚበኑ ከሆነ በቅድስት ዮስቴና ፊት ሊቆሙ ሊሸነግሏትስ እንዴት ይቻላቸዋል?›› አለ፡፡ ይህንንም ብሎ ወዲያውኑ የጥንቆላ መጻሕፍቶቹን አቃጠላቸው፡፡ ሄዶም ቅድስት ዮስቴናን አገኛትና ሰገደላት፡፡ እርሷም ሃይማኖትን አስተማረችውና ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ ዘንድ ሄዶ ንስሓ ገብቶ ተምሮ አምኖ ተጠመቀ፡፡ የምንኩስና ልብስንም ለበሰ፡፡ ከጥቂት ጊዜም በኋላ ሊቀ ጳጳሳቱ ዲቁና ሾመው፡፡ አገልግሎቱንና መንፈሳዊ ተጋድሎውንም ባየ ጊዜ ዳግመኛም ቅስና ሾመው፡፡  

🥀ቆጵርያኖስም በተጋድሎና በአገልግሎት ከኖረ በጎ ምግባሩ፣ ሃይማኖት፣ ትሩፋቱ ከፍ ባለ ጊዜ በምዕራባዊቷ ግዛት ኤጲስ ቆጶስነት ተሾመ፡፡ ቅድስት ዮስቴናንም ወስዶ ለደናግል ገዳም እመ ምኔት አደረጋት፡፡
በግርጣግና የቅዱሳን ስብሰባ በሆነ ጊዜ ቅዱስ ቆጵርያኖስ ከጉባው አባላት አንዱ ነበር፡፡ ከብዙ ወራት በኋላም ከሃዲው ንጉሥ ዳኬዎስም ስለ ቅዱስ ቆጵርያኖስና ስለ ቅድስት ዮስቴና ሰማ፡፡ ንጉሡም ወደ እርሱ አስመጣቸውና የክብርን ባለቤት ክርስቶስን ክደው ለጣኦት እንዲሰግዱ አዘዛቸው፡፡ ቅዱስ ቆጵርያኖስና ቅድስት ዮስቴና ግን የጌታችንን አምላክነት ክብር በመመስከር ጣዖታቱን ረገሙበት፡፡ ንጉሡም እነርሱ ክርስቶስን በማመን እስከመጨረሻው ድረስ መጽናታቸውን ባየ ጊዜ ልዩ ልዩ በሆኑ ጽኑ ሥቃዮች እጅግ አድርጎ አሠቃያቸው፡፡ በመጨረሻም ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ የቅዱስ ቆጵርያኖስን የቅድስት ዮስቴን እንዲሁም የሌሎች ሦስት ወንዶችን በየተራ ራስ ራሶቻቸውን በሰይፍ አስቆረጣቸውና የሰማዕትነታቸው ፍጻሜ ሆነ፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!

        «ግሸን ደብረ ከርቤ»

🥀ግሸን ደብረከርቤ ዳግማዊት ጎልጎታ ከደሴ ከተማ 82 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በደቡብ ወሎ ዞን በአንባሰል ወረዳ ውስጥ በሃይቅ እና በመቅደላ በደላንታና በየጁ መካከል በበሽሎ ወንዝ አዋሳኝ ከፍተኛ በሆነ ተራራ ላይ የምትገኝ ገዳም ናት፡፡ የበሸሎን ወንዝ ተሻግረን ሰማይ ጥግ የደረሱ የሚመስሉትን ተራሮች ወጥተን በስተመጨረሻ መግቢያ አንድ በር የሆነ እና ከተራራው አናት ላይ በሚገኝ ስፋራ ላይ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም የታነጸ እና ግማደ መስቀሉ የሚገኝበት የእግዚአብሔር አብ አብያተ ክርስቲያናት እና ፈዋሽ ጸበል ይገኛሉ፡፡ በ1942 ዓ.ም አቡነ ሚካኤል ጳጳስ ዘጎንደር ከዚህም ጋር ''መንፈሳዊ መናኝ'' በመባል የሚታወቁት ደገኛ አባት ያሰሩት ቤተ ክርስቲያንም ይገኛል፡፡

🥀ግሸን ይህን የአሁኑን መጠሪያ ስም ከማግኘትዋ በፊት በተለያየ መጠሪያ ስሞች ትታወቅ ነበር:: በመጀመሪያ በአጼ ድልነአድ ዘመነ መንግስት በ896 ዓ.ም ሃይቅ ደብረ እስጢፋኖስ ሲመሰረት ''ሐይቅ ደብረ ነጎድጓድ'' ተብሎ ሲሰየም ግሸንም በሃይቅ ግዛት ውስጥ ስለሆነች ስምዋ ''ደበረ - ነጎድጓድ'' ተባለች፡፡ ይህን መጠሪያ ስም እንደያዘች እስከ 11ኛው ክ/ዘመን ድረስ ቆየች፡፡ በ11ኛው ክ/ዘ በኢትዮጵያ ነግሶ የነበረው ጻድቁ ንጉስ ላሊበላ ከቋጥኝ ድንጋይ ፈልፍሎ የሰራው ቤተ መቅደስ በእግዚአብሔር አብ ስም ይጠራ ስለነበር ግሸንም ''ደብረ እግዚአብሔር'' ተብላ መጠራት ጀመረች፡፡ ነገር ግን በዚህ ስም በመጠራት ብዙም ሳይቆይ ስሟ ተለውጦ ''ደብረ ነገሥት'' ተባለች፡፡ ደብረ ነገስት የተባለችውም ነገስታቱ ይማጸኑባት የክብርና የማእረግ እቃዎች የሚያሰቀምጡባትና የነገስታቱ የመሳፍንቱ ልጆችም የቤተ መንግስት አስተዳደር የሚማሩባት ስፍራ ስለነበረች ነው፡፡ እንደገና ደግሞ በ1446 ዓ.ም ኢትዪጵያዊው ፈላስፋ እየተባሉ በሚጠሩት በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግስት ግማደ መስቀሉ

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

የብፁዕ አቡነ ሰላማ አጭር የሕይወት ታሪክ
****

ብፁዕ አቡነ ሰላማ በቀድሞ ስማቸው ሊቀ ሥልጣናት አባ ሐረገ ወይን ገብረ ሥላሴ ከአባታቸው ከአቶ ገብረ ሥላሴ ገ/መድኅንና ከእናታቸው ከወ/ሮ ብዙነሽ ወንድሙ በትግራይ ክፍለ ሀገር በመቀሌ ከተማ ልዩ ቦታው በዓታ ለማርያም በተባለው ቦታ 1934 ዓ.ም ተወለዱ።

ፊደልና ንባብና የቃል ትምሕርት በመማር ለግብረ ዲቁና የሚያበቃቸውን ትምሕርት ከየኔታ ክንፈ ገብርኤል በመማር  ማዕረገ ዲቁናን ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ  ተቀብለዋል።

ብፁዕ አቡነ ሰላማ በቀድሞ ስማቸው ሊቀ ሥልጣናት አባ ሐረገ ወይን ገብረ ሥላሴ ዜማ ከየኔታ ተክለ ማርቆስ ማየ አንበሳ ገዳም ተንቤን፤ ቅኔ ከየኔታ ንጉሤ መነዌ ገዳም ተንቤን  እንዲሁም ቅኔን  ከየኔታ አክሊሉ ደበጋ ጎንደር  ትርጓሜ መጻሕፍት፣ እንድባ ጊዮርጊስ ከየኔታ ማርያም ቀረፃ ማርያም ከምትባል ገዳም ፤ ቅኔና ትርጓሜ መጽሐፍት እንድባ ጊዮርጊስ ከየኔታ ልሣነ ወርቅ ጎጃም ፤ ቅኔ ከየኔታ ዲበኩሉ ጎጃም በሚገባ ከተማሩ በኋላ ለመምህርነት በቅተዋል፡፡

በተጨማሪም መዝገብ ቅዳን ከየኔታ ልዑል ቦረራ ሚካኤል ተምረዋል፡፡በወቅቱ የጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ የቅስናና የቁምስና ማዕረግ ተቀብለዋል፡፡ብፁዕነታቸው በሊቀ ጵጵስና በአክሱም፣በምሥራቅ ሐረርጌና በታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም አገልግለዋል።

የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

በእንተ ቅዱስ መስቀል (#በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ)

የጌታችን የክርስቶስ መስቀል ለእንደ ምን ያለ ታላቅ በረከት ምክንያት እንደ ኾነልን እናስበው፡፡ ምንም እንኳን ከአፍአ ሲታይ የጌታችን መስቀል አሳዛኝና አሰቃቂ ቢመስልም፥ እንደ እውነቱ ግን ደስታንና ሐሴትን የተሞላ ነው፡፡ መስቀል የቤተ ክርስቲያን መድኃኒት ነውና፤ መስቀል ተስፋ ለሚያደርጉት መመኪያቸው ነውና፤ መስቀል ጠላቶች [ደቂቀ አዳም] ከእግዚአብሔር ጋር የሚታረቁበት [የታረቁበት]፥ ኃጥአንም ወደ ክርስቶስ የተመለሱበት [አሁንም የሚመለሱበት] ነውና፡፡

በመስቀል ከጠላትነት ድነናል፤ በመስቀል ወደ እግዚአብሔር አንድነት ተመልሰናል፡፡ በመስቀል ከግብርናተ ዲያብሎስ አርነት ወጥተናል፤ በመስቀል ከሞትና ከጥፋት ድነናል፡፡ ብሥራተ መስቀል ባልተነገረበት ዘመን በሞት ጥላ ሥር ተይዘን ነበር፤ አሁን ብሥራተ መስቀል በተገለጠበት ጊዜ ግን ህልውና እንኳን እንደሌለው አድርገን ቈጥረን የዘለዓለም ሕይወትን እየናፈቅን ሞትን ንቀነዋል፡፡ ብሥራተ መስቀል ባልተነገረበት ዘመን ለገነት እንግዶች ነበርን፤ መስቀል በተገለጠ ጊዜ ግን ወንበዴስ እንኳን ለገነት የተገባ ኾኖ ተገኘ፡፡ የሰው ልጅ እንደዚህ ካለ ጨለማ መጠን ወደ ሌለው ብርሃን፣ ከሞት ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት፣ ከመዋቲነት ወደ ኢመዋቲነት ታድሶ ተሸጋገረ፡፡ ዓይነ ልቡና ባለማወቅ ጽልመት ከመታወር ድኖ በመስቀል የዕውቀት ብርሃን ተጥለቀለቀ፡፡ እዝነ ልቡና ካለማመን ድንቁርና ወጥቶ የእግዚአብሔርን ቃል ወደ መስማት ተመለሰ፤ ዕውራንም [መንፈሳዊ] ብርሃናቸው ተመልሶላቸው የእግዚአብሔርን ክብር ማየት ተችሎአቸዋል፡፡ በቅዱስ መስቀሉ የተሰጡን ሀብታት እነዚህ ናቸው፡፡ በቅዱስ መስቀሉ ያልተሰጡን በረከቶችስ ምን አሉ?

እነሆ ቅዱስ መስቀሉ ተገልጧል፤ በእግዚአብሔር ማመንም ተመልሷል፤ እውነትም [ወንጌልም] ወደ ዓለም ኹሉ ደርሷል፡፡ ቅዱስ መስቀሉ ተገልጧል፤ ሰማዕታትም [ከመስቀል በኋላ ሞት ሞት መኾኑ እንደ ቀረና የሹመት የሽልማት ማሳ መኾኑን ዐውቀው አብረው] ተገልጠዋል፤ በክርስቶስ ማመንም በኹሉም ዘንድ ተሰራጭቷል፡፡ ቅዱስ መስቀሉ ተገልጧል፤ [በእርሱም ሞት ራሱ ሞቷልና] ትንሣኤ ሙታንም ተገልጧል፤ ሕይወትም ታይታለች፤ መንግሥተ እግዚአብሔርም እንደዚሁ እርግጥ ኾናለች፡፡ ቅዱስ መስቀሉ ለእነዚህ ኹሉ ነገሮች ምክንያት ኾኗል፡፡ በመስቀሉ እግዚአብሔርን ማመስገን ተማርን፡፡ እንግዲህ ከቅዱስ መስቀሉ ይልቅ ሌላ የተወደደ ምን አለ? እኮ ከቅዱስ መስቀሉ በላይ ለነፍሳችን የሚረባት [የረባት፣ የጠቀማት] ሌላ ምን አለ? ስለዚህ በሙሉ ልባችን ይህን እንመስክር እንጂ ስለ ቅዱስ መስቀሉ ለመናገር ቅንጣት ታህልስ እንኳን አንፈር፡፡

ክርስቶስ በቅዱስ መስቀል ላይ ተሰቀለ፤ ዲያብሎስም በድን ኾነ፡፡ ክርስቶስ በቅዱስ መስቀል ላይ እጆቹን ዘረጋ፤ ለዓለምም የመዳን መንገድ ተሰጠ፡፡ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተቸነከረ፤ ነፍሳትም ኹሉ ከእስራታቸው ተፈቱ፡፡ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ዋለ፤ ፍጥረታትም ኹሉ ከጥፋት ባርነት ነፃ ወጡ፡፡ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ፤ እንግዳ ነገርም ለዓለም ኹሉ ታየ ፀሐይ ብርሃኗን ከለከለች ንዑድ ክቡር የሚኾን ነቢዩ አሰምቶ እንደ ተናገረው - እንዲህ ሲል፡- “በዚያን ቀን ፀሐይ በቀትር ይገባል፤ ብርሃንም በምድር ላይ በቀን ይጨልማል” (አሞ.8፡9)፡፡ ተወዳጆች ሆይ! የነቢዩ ቃል እንደ ምን ያለ ግሩም ምሥጢር በውስጡ ቋጥሮ እንደ ያዘ ታያላችሁን? እዚህ ላይ የኹላቸውም -የእስራኤላውያንም የአሕዛብም - ግብር ተገልጧል፤ ኹላቸውም በአንድነት በድለዋልና፡፡

እንደ ኦሪቱ ሕግ በዓላትን የሚያከብሩት ያዝናሉ፤ በመዝሙር ፈንታም በኢየሩሳሌም ላይ.ያለቅሳሉ፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ ኢየሩሳሌም የተቀደሱትን ሥርዓተ አምልኮዎችን ይዛ አትቀጥልምና፤ ከእንግዲህ ወዲህም በእርሷ ዘንድ በዓላት አይከበሩምና፡፡ የአሕዛብ አገራትም እንደዚሁ ኃጢአታቸውን እየተናዘዙ ያዝናሉ፤ መጽሐፍ “የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው” እንዳለ ኀዘን የበረከት ምንጭ ነውና ይተክዛሉ (ማቴ.5፡4)፡፡ አዎ! ትርጉም ለሌላቸው በዓላቶቻቸውና ሥርዓት ለሌላቸው ዘፈኖቻቸው ለርኵሳት መናፍስት ይቀርብ እንደ ነበረ ዐውቀው ያዝናሉ፤ ይተክዛሉም፡፡ ዛሬ አሕዛብ ያከናውኑአቸው ለነበሩት ክፉ ክፉ ነገሮች እንዴት እንደሚጸጸቱባቸው አስተውሉ፤ ከነቢዩ ጋር በአንድነት እንዲህ ይላሉና፡- “በድለናል፤ በሐፍረታችንም ጠፍተናል፤ በዓመፃ ተሞልተናልና ኃጢአታችን ሸፍናናለች፡፡ እንደ አባቶቻችን በድለናል፡፡”

እንግዲያውስ እኛም ስለ ሠራናቸው ኃጣውእ እናልቅስ፤ እንዘንም፡፡ ተስፋችንን በእርሱ ላይ.አኑረን ወደ ቅዱስ መስቀሉ እንጠጋ፡፡ እኛ ሥራ ሠርተን አንበቃምና ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ክብሩና ጌትነቱ አንድ በሚኾን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቸርነትና ሰውን መውደድ የመንግሥቱ ወራሾች እንኾን ዘንድ በመስቀሉ [ቃል] ተምረን አሳባችንን በሰማያት እናኑር፤ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ለዓለም ወለዓለም፥ አሜን!!!

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
    

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

"ዓለም በሚቀማበት ወቅት ጊዜውን፣ እውቀቱን፣ ገንዘቡን ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጥ እንደእናንተ አይነት ልጆች ስላሉን እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን"

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በማኅበረ ቅዱሳን የ2016 ዓ.ም የ6 ወራት የሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ቡራኬና ቃለ ምእዳን ሰጥተዋል።

በዚህ አስፈሪ ጊዜ እግዚአብሔር ሥራ እንድንሠራ ፈቅዷል ያሉት ብፁዕነታቸው በርካታ ችግሮችን አልፋችሁ መጥታችኋል። ዓለም በሚቀማበት ወቅት ጊዜውን፣ገንዘቡን ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጥ እንደእናንተ አይነት ልጆች ስላሉን እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን ብለዋል።

ብፁዕነታቸው በመልእክታቸው "የቤተ ክርስቲያን ጥቅም እንጂ ቤተ ክርስቲያን በአእምሯችን የሌለች ሁነናል። እግዚአብሔር ግን በተለያዩ መከራዎች ውስጥ ሁነው ስለሚያለቅሱት ሲል ያሻግረናል፤ራሳቸውን ለመስጠት በተዘጋጁ ምእመናን እናልፈዋለን፤ እነዚህን ከደገፍናቸው ቤተ ክርስቲያን ጸንታ ትኖራለች። እናንተም እነሱን ነው ምታግዙት"ሲሉ ገልፀዋል ።

ከእኛ የሚጠበቀውን በመንፈሳዊነት ከሠራን ሀገር ትለወጣለች፤ ግን አንድ ሁነን፣ በእግዚአብሔር አምነን በጸሎት ሲሆን ነው በማለት አጽዕኖት የሰጡት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ተደማምጠንና ተናበን መሥራት ከቻልን እናልፈዋለን ሲሉ አጽንዖት ሰጥተዋል።

ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ በማሳለፍና አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል።
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሥርዓቱ መሠረት የበዓላቱና የአጽዋማቱ መደብ የሚታወቅበትና የዘመናቱ ሂደት ተቀምሮ የሚታወጅበት ዕለት መስከረም አንድ ቀን ርእሰ ዐውደ ዓመትን ታከብራለች፡፡ የኢትዮጵያ የወራት ሁሉ መጀመሪያ መስከረም ነው፡፡ በዚህ ወር የመጀመሪያው ቀን የተለያዩ መጠሪያዎች አሉት፡፡ እነርሱም ዘመን መለወጫ፣ ዕንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል፡፡

አዲስ ዓመት መስከረም አንድ ቀን ለምን ይከበራል?

በኢትዮጵያ (ርእሰ ዐውደ ዓመት) ዘመን መለወጫ በመስከረም ወር የሆነበትን ምክንያት ሊቃውንቱ ሲያትቱ ብርሃናት ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ክዋክብት የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ አጠናቀው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው፡፡ ያን ጊዜ ሌሊቱ ከቀኑ ጋር እኩል ፲፪ ሰዓት ይሆናል፡፡ ዓመቱን ጠንቅቀው ሲቆጥሩ ፫፻፰፬ ቀናት ይሆናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ “ለዘመን መታወቂያው ይሆን ዘንድ ፀሐይና ጨረቃ ከዋክብትንም ፈጠረ” ይላልና (ሄኖክ. ፳፩፥፵፱)፡፡ በሌላ በኩልም በዘመነ ኖኅ ከንፍር ውኃ ምድር የተገለጠችበት ወር ነው፡፡ (ኩፋሌ. ፯፥፩)፡፡ “በመጀመሪያው ወር ምድር ታየች የንፍር ውኃም ከምድር ደረቀ” የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል መሠረት አድርገው የአቡሻኸር ሊቃውንት የዘመን መለወጫን ታሪካዊ አመጣጥን አብራርተው አስቀምጠዋል፡፡

የቤተ ክርስቲያንን ቀኖናዊ ሥርዐት ያጠኑ ሊቃውንት ደግሞ አዲስ ዓመት መስከረም አንድ ቀን መሆኑን አስመልክተው በጽሑፋቸው ዘመኑን በአራቱ ወንጌላውያን ይከፍሉታል፡፡ ምክንያቱም በዘመነ ዮሐንስ ተፀንሶ በዘመነ ማቴዎስ ተወልዶአል፡፡ የጌታን መጠመቅ፣መሰቀልን፣ ዓለምን ከፍዳና ከመርገም ነጻ ማውጣትን አራቱ ወንጌላውያን እያወሱ ዘመናትን ተከትለው ያለ እንቅፋት እንደሚጓዙ ያስረዳሉ፡፡ ወንጌላዊውን ወይም ዘመኑን ለማወቅ ዓመተ ፍዳ(ኩነኔ) አምስት ሺህ አምስት መቶ  እና ዓመተ ምሕረት (አሁን ያለንበትን ዓመት) በመደመር ውጤቱ ለአራቱ ወንጌላውያን ማለትም ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስና ዮሐንስ በማካፈል የምናገኘው ነው፡፡ ይህም የአንዱ ወንጌላዊ ድርሻ ማለት ነው፡፡ በዚህም መሠረት ቀሪው አንድ ከሆነ ዘመኑ ማቴዎስ፣ ሁለት ከሆነ ዘመነ ማርቆስ፣ ሦስት ከሆነ ዘመነ ሉቃስ ምንም ቀሪ ባይኖር ደግሞ ዘመነ ዮሐንስ ነው፡፡ ስሌቱም ከዚህ በታች የተቀመጠውን ምሳሌ መነሻ አድርጎ ወንጌላዊውን ማን እንደሆነ ማወቅ ይቻላል፡፡ስለ አዲስ ዓመት በተለያየ ስም የመጠራቱ ታሪካዊ አመጣጥና ስያሜ መነሻ አሳቡ ምን እንደሆነ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡

አዲስ ዓመት ለምን ቅዱስ ዮሐንስ ይባላል...?

የቅዱስ ዮሐንስ ተግባር በቕዱስ ዮሐንስ አወርቅ የተጠቀሰ ሲሆን ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ለዘመነ ወንጌል በር ወይም መነሻ እንዲሆን ለኢትዮጵያ ዐውደ ዓመት መስከረም አንድ ቀን እንዲከበር አባቶች ወስነዋል፡፡ (ድርሳነ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ ፩-፫)፡፡ መጽሐፈ ስንክሳር “የመስከረም ወር የተባረከ ነው፡፡ እርሱም የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመቶች መጀመሪያ ነው፡፡ የዚህ ወር ቀኑና ሌሊቱ እኩል ፲፪ ሰዓት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ቀኑ እየጎደለ ይሄዳል” እንዲል፡፡ በአጠቃላይ ዘመን መለወጫ ከላይ ባየናቸው የተለያየ ስያሜ ይጠራ እንጂ ዘመኑ አዲስ እየተባለ ቢጠራም አዲስ መሆን ያለበት ወርና ወቅቱ ብቻ ሳይሆን የእኛ የክርስቲያኖች ሥርዓት ነው፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነታችሁን አታርክሱ የእግዚአብሔር ማደሪያ ነውና እያለ በመዋዕለ ሥጋዌው ያስተምር ነበር፡፡ አዲስ ዓመት ሲመጣ በኃጢኣት፣ በተንኮል፣ በክፋት የቆሸሸው ሰውነታችን በንስሓ፣ በቅዱስ ቊርባን፣ በመልካም ተግባር አዲስ ልናደርገው ይገባናል፡፡

ዘመነ ማቴዎስም፣ ዘመነ ማርቆስም፣ ዘመነ ሉቃስም ሆነ ዘመነ ዮሐንስ፤ በአራቱም ዘመናት አስቀድሞ ርእሰ ዐውደ ዓመት ቅዱስ ዮሐንስ ይዘከራል፡፡ ዮሐንስ የስሙ ትርጉም «ጸጋ እግዚአብሔር» ማለት ነው፡፡ ዘመናት ዘመናትን እየወለዱ፣ ሰዓታት ደቂቃን ቅጽበትን (ሰኮንድን) ሳይቀር እየሰፈሩ(እየቆጠሩ) ዕለታት ሳምንታትን፣ ሳምንታት ወራትን፣ ወራት ዓመታትን አሁን ላለንበት ዘመን ደርሰናል፡፡

ዕንቁጣጣሽ

ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚያስረዱት ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜው አመጣጥ ወይም ጥንተ ታሪክ በመጀመሪያ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በዕጣ ሲያካፍላቸው አፍሪቃ ለካም ደረሰችው፡፡ በአፍሪቃ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በሀገረ ኢትዮጵያ በወርኀ መስከረም ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኃ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት «ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ» ይህችን ወቅት ዕንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡ በመቀጠል የሀገራችን ንግሥት ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ዜና ጥበብ በጆሮዋ የሰማችውን በዓይኗ ዓይታ ለመረዳት ስለፈለገች ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፡፡ ንግሥተ ሳባም ከንጉሡ ሰሎሞንም ተገናኝተው ቤተ መንግሥቱንም አስጎበውኝቶ ሲያበቃ «ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ» ሲል እጅግ በጣም የከበረ ዕንቁ አበረከተላት/ሰጣት/፡፡ ወሩም ወረኃ መስከረም ነበር፡፡

ንግሥቷ ጠቢቡ  ሰሎሞንን ለመጎብኘት በሔደችበት ወቅት ፀንሳ ቀዳማዊ ምኒልክን በወለደች ጊዜ ሕዝቡ ንጉሥ ተወለደ እልል እያሉ «አበባ ዕንቁ (አብረቅራቂ ድንጋይ) ጣጣሽ (ገጸ በረከት)» እያለ ገጸ በረከት ለንግሥቲቱ አበረከቱ፡፡ ያ የዘመን መለወጫ በዓልም ልጃገረዶች የአበባ ገጸ በረከት የሚያቀርቡበት ስለሆነ ዕንቁጣጣሽ ተባለ፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው መጥቷል፡፡ አሁን ከሚፈጸመው ሥነ ሥርዓት ደርሶ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ የሚከበረውም መስከረም አንድ ቀን ነው፡፡ አንድም «ዕንቁ ዕፅ አወጣሸ»ብሎ የአበባውን መፈንዳትን ያስረዳናል፡፡ የዘመን መለወጫ (ርእሰ ዐውደ ዓመት) ዕንቁጣጣሽ ተብሎም እንደሚጠራ ታሪክ ያወሳናል፡፡  ስያሜውም ለበዓሉ የተሰጠው በንግሥተ ሳባ ዘመነ መንግሥት ነበር፡፡

አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የአንድነትና የመተሳሳብ ዘመን እንዲሆንልን የእግዚአብሔር ቸርነት የቅደስት ደንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁንልን አሜን፡፡
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

ዕንቁጣጣሽ በወርኃ መስከረም ስለመከበሩ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ዕይታ፡-
 

የዕንቁጣጣሽ በዓል በመስከረም ወር ላይ ለምን እንደሚከበር ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚከተለው ያብራራሉ፡፡ ብርሃናት (ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት) የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜን ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ይጀምራሉ፤ ያን ጊዜ ሌሊቱ ከቀኑ ጋር እኩል ዐሥራ ሁለት ሰዓት ይሆናል፡፡ ለዘመን መታወቂያ ይሆን ዘንድ ፀሐይና ጨረቃ ከዋክብትን ፈጠረ እንዳለ፤ (መጽሐፈ ሄኖክ ፳፩፥፵፱)፡፡ በሌላ በኩልም በዘመነ ኖኅ ዓለምን ውኃ አጥለቅልቋት ከቆየ በኋላ ዳግመኛ ከነበረው ውኃ የተገለጠችበት ወር «በመጀመሪያም ወር በምድር ታየች የንፍር ውኃው ከምድር ደረቀ» የሚለውን መሠረት አድርገው የአቡሻኽር ሊቃውንት የዘመን መለወጫን ታሪካዊ አመጣጥ ያስረዳሉ፡፡ (መጽሐፈ ኩፋሌ ፯፥፩)
 
ዘመን ሲለወጥ የሰው ልጆች ሕይወት ሊለወጥ ይገባል፡፡ ተማሪው ተምሮ ወደ ቀጣዩ ክፍል ያልፋል፤ በዚህ መልኩም ከኬጂ እስከ ዩኒቨርስቲ ደረጃ ይደረሳል፡፡ ገበሬውም የክረምትን ወራት በሚገባ ተጠቅሞ የሚቀጥለውን የበጋ ወራት የልፋቱን ዋጋ የምድርን በረከት የሚያገኝበት፣ ሠራተኛው የክረምቱን ዝናብ ታግሦ ከፀሐይ ወራት ይደርሳል፤ ክርስቲያንም ዓመት ሲለውጥ በኃጢአት የነበረ ሰው ከገቢረ ኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣  ከክፋት ወደ በጎነት፣ ከጥላቻ ወደ ፍቅር፣ ከመጀመሪያው የክርስትና ደረጃ እስከ ዐሥረኛው ማዕረግ የሚደረስብትን እያቀደ መኖር ይገባዋል፡፡ ምን ጊዜም ዘመን በተለወጠ ጊዜ የዓመታት እና የወራት ለውጥ ብቻ ሳይሆን የክርስቲኖችም የሕይወት ለውጥ የሚገባ መሆኑን ከተፈጥሮ ክስተት መረዳት ይቻላል፡፡ መጪውን አዲሱ ዓመት ዘመነ ዮሐንስን የቤተ ክርስቲያን ከፍታ የምናይበት፣ በክርስትናችን  የሕይወት ለውጥ የሚያድግበት፣ ሰላም፣ አንድነት፣  የምናይበት እንዲሆንልን የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁንልን፤ አሜን፡፡
 
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

“በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ” መዝ 65፥11

ስለሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን እንደ ኃጥአታችን ያይደለ እንደቸርነቱ የንስሃ ጊዜ የፍሬ ጊዜ ሰጥቶናልና እናመሰግነው ዘንድ ይገባናል፡፡ ምስጋናችንም ይህን የተወዳጅ ሐዋርያ የቅዱስ ጳውሎስን ቃል በመተግበር እንግለፅ፡፡

“ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።” ኤፌ 4፥22

መልካም አዲስ አመት!
🌻🌻🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌻🌻
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

🟢🟡🔴
ጳጒሜን 3 | በዚህች ቀን፦
የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ የሩፋኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው። እርሱም ከመላእክት አለቆች ሦስተኛ የሆነ ነው። ደግሞም ከእስክንድርያ ውጭ በደሴት የታነፀች ቤተ ክርስቲያኑ በከበረ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎፍሎስ ዘመን በውስጧ ተአምር የተገለጸባት የከበረችበት ነው።
ያቺ ደሴት በታላቅ አንበሪ ጀርባ ላይ የቆመች ናትና የሰዎች ብዛትም በከበደው ጊዜ ቤተ ክርስቲያኒቱን ያፈርሳት ዘንድ ሰይጣን አነሣሣው። ወደ ክብር ባለቤት እግዚአብሔርም በከበረ መልአክ ሩፋኤል ስም ጮኹ።
ያን ጊዜ ይህ የከበረ ሩፋኤል ያንን አንበሪ በጦሩ ወግቶ እንዲህ አለው፦ እግዚአብሔር አዞሃልና ከቦታህ ሳትናወጽ ጸጥ ብለህ ቁም። አንበሪውም ጸጥ ብሎ ቆመ አልታወከም። በውስጧም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። ለሕሙማንም ፈውስ ሆነ።
-🍀-
ለእግዚአብሔር ልጅ ምሳሌው የሆነ የመልከጼዴቅ መታሰቢያው ነው።
አብርሃምም ከጦርነት ነገሥታትን ድል አድርጎ በተመለሰ ጊዜ ኅብስትንና ወይንን አቀረበለት። አብርሃምም ከገንዘቡ ሁሉ ከዐሥር አንድ ሰጠው እርሱ ካህንም ንጉሥም ሁኖ ተሹሟልና።
-🍀-
የኢትዮጵያ ንጉሥ መልካም ስም አጠራር ያለው ዘርዐ ያዕቆብ ዐረፉ።
ተአምረ ማርያምን ጨምሮ ከ11 ያላነሱ መጻሕፍትን በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ደርሰው ለአገልግሎት አብቅተዋል፡፡ ብዙ መጻሕፍትን ከውጪ አስመጥተው አስተርጉመዋል፡፡ ሰው ሁሉ ለእመ ብርሃንና ለቅዱስ መስቀሉ ፍቅር እንዲገዛ ጥረት አድርገዋል፡፡
እመቤታችንን በፍጹም ልባቸው ከመውደዳቸው የተነሣ ዛሬም ድረስ በሃገራችን ድንግል ማርያም "የዘርዓ ያዕቆብ እመቤት" እየተባለች ትጠራለች፡፡
-🍀-
ሰንዱን ከሚባል አገር ቅዱስ ሰራጵዮን አረፈ።
ይህም ቅዱስ ራሱን ባርያ አድርጎ እየሸጠ አሕዛብን ወደ ክርስቶስ የሚመልስ ነው።

@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

🌹እንኳን ለጽዮን ማርያም ማሕደረ አምላክ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ



🌹ጽዮን ማለት ጸወን፣ አምባ ፣ መጠጊያ ማለት ነው። አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው። ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም፣ ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል።




🌹አምላከ ቅዱሳን የአማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያምን ጣዕሟን ፍቅሯን ጸጋ በረከቷን ያሳድርብን አሜን
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
.....ከክፍል ሁለት የቀጠለ

ሌሎች መከራን በመጋፈጥ ላይ ያሉ ሰዎች እንደዚህ አይነት ዜናዎችን ሲሰሙ ውሳኔያቸው ምን ሊሆን ይችላል?
መቼም የዚህ ዘመን ሰው ሞት ክፉ ነው ብትሉት እስቲ ሞቼ ልየው የሚል ህዝብ ነው።
መርዝ ጥሩ አደምለ ብትሉት እስቲ ጠጥቼ ልየው የሚል ህዝብ ነው። /ጥሩ መሆኑን እና አለመሆኑን ለማወቅ/

ሌላው ደሞ እራሳቸውን እያጠፉ ያሉ ሰዎችን መቆጣት ይሻላል ፤መርዳት ይሻላል፤ ወይስ እንደ እንቁላል መንከባከብ ይሻላል?

መቆጣት ፦እነዚህን ሰዎች መቆጣት እራሳቸውን እንዳያጠፉ ሊረዳቸው ይችላል አልያም ይባስ ለሞት ሊዳርጋቸው ይችላል።

መንከባከብ፦እነዚህን ሰዎች መንከባከብ እራሳቸውን እንዳያጠፉ ሊረዳቸው ይችላል ተቃራኒም ሊሆን ይላለል።

መርዳት ፦ይሄኛው መልካም የሆነ ሃሳብ ነው ነገር ግን ዛሬ እራሳቸውን ሊያጠፉ የነበሩትን መርዳት ተመልካቹን ደሞ ሌሎች እንዲረዱኝ በማለት እራስን የማጥፋት ሙከራ እንዲያረጉ ሊገፋፋቸው ይችላል። 

ግን ደግሞ ሶስቱም  /3/  ሃሳቦች ጊዜያቸውን ከጠበቁ ትክክለኛ ውሳኔዎች ናቸው።

ስለዚህ በቦታው የነበረውን ሁኔታ አውቆ እንደሁኔታው የቻልነውን ማድረግ ደሞ የሁሉም ግዴታ ነው።
የሚጠቅማቸውን ለይቶ በማወቅ

እራሳችሁን በማጥፋት የሚገኘው ነገር እራስን ማጥፋት ብቻ ነው።
ቤተክርስቲያንን ማሳዘን፣ቤተሰብን ማሳዘን፣ህብረተሰቡን ማሳዘን.........ከዚህ ውጪ ምንም ትርፍ የለውም።

➠መልካም በማሰብ መልካም እናድርግ።

          
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

✝️ወደ ቻናላችን ጎራ በሉ ሃሳብ እና አስተያየታችሁን አትንፈጉን!✝️

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

⚠️እራሳቸውን_የሚያጠፉ!⚠️
●●●●●●●●●●●●●●●●●●
/ሁላችሁም ብታነቡት ትጠቀሙበታላችሁ/
     🔥🔥🔥🔥
➠ክፍል አንድ


ሰሞኑን እራሳቸውን እያጠፉ ያሉ ወጣቶች እየተበራከቱ ነው።
ለእራስ ማጥፋታቸው የሆነ ምክንያት እንዳላቸው ደግሞ በማህበራዊ ሚዲያቸው እየገለፁ እንደሆነ አይተናል።

በማህበራዊ  ሚዲያ ላይ አንገታቸውን  ለገመድ፣አፋቸውን ለመርዝ እየሰጡ እራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎችን ዜና ማበራከቱ ለሌሎቹ ሰዎች ተፅዕኖ የለውም?
ሌሎቹ ሰዎች እራሳቸውነሰ እንዲያጠፉ እንደመጠቆም አይሆንም?  /አጢኑት/
        

እራሳቸውን ለማጥፋት ምክንያታቸው በጣም ከባድ እንደሆነ እና ሊወጡት የማይችሉት እንደሆነም ከፃፉት ፅሁፍ እንፃር መገመት ይቻላል። 

በዕርግጥ የሁሉም ሰዎች መከራንም ሆነ ችግርን ችሎ  ተቋቁሞ በትዕግስት የማለፍ አቅሙ ሊለያይ ይችላል።
አስዳደደጉም ወሳኝ ነው።

ነገር ግን የትኛው ከፍተኛ እና ልትወጡት ወይም ደሞ ልትቋቋሙት የማትችሉት ነገር ገጥሟችሁ ነው?
(የገጠመህን ተረጋግተህ አጢነው።)

በዚህ ምድር ላይ መከራንም ሆነ ማንኛውንም ነገር ያላለፈ ሰው የለም ብዬ ነው የምገምተው።
ሁሉም ሰው በችግር ተገርፎ ተሰቃይቶ ነው እኮ እየኖረ ያለው።
ስለዚህ ዛሬ እራሳቸውን እያጠፉ ያሉ ወጣቶች የትኛው ክፉ ነገር ቢገጥማችሁ ነው?
በእናንተ ላይ የደረሰውን ነገር ደግሞ በሌላው ሰው ላይ አልደረሰም ማለት አይቻልም።
መደፈርም ቢሆን፣ የሚወዱትን በማጣትም ቢሆን፣መከዳትም ቢሆን ያልደረሰበት እና ያላለፈው ሰው የለም ብሎ መገመትም አይቻልም። 

ዛሬ እራሳቸውን እያጠፋችሁ ያላችሁ ወጣቶች በእናንተ ላይ ምንም የተፈጠረ  አዲስ ነገር  የለም ስለዚህ እስከ ዛሬ መከራን ሁሉ  አልፈው እየኖሩ ያሉ ሰዎች እንዳይታዘቧችሁ!

እስኪ ተጠየቁ፦

●ምነው ግን እናንተው በእናንተው ዘመን ላይ በጦርነት ሙሉ ቤተሰቡን ያጣ ሰው አላያችሁም?

●በአይኑ እያየ እናት አባቱን የተገደለበትን ወጣት አላያችሁም?

●ሰዎች ያመኑት ሰው ሲከዳቸው አላያችሁም አልሰማችሁም?

●ብዙ የጭንቀት ዘመናትን በጭንቀት ያሰለፈ ሰው አላየህም ?

●በብቸኝነት የኖረ ሰው አላየህም?

●ልቡ የቆሰለ በሃዘን የተዋጠ አላየህም?

●ቤቱ ንብረቱ ሁሉ ወድሞባቸው  ከተወለዱበት ሀገር እና እትብታቸው ከተቀበረበት ቀዬ ሲሰደዱ አላያችሁም አልሰማችሁም?

●በየመንገዱ ላይ በጎዳና የሚተዳደሩትን ግለሰቦች የቀድሞ ታሪካቸውን አላየህም አልሰማህም?
ምን የመሰለ ባለ ሃብት............የጎዳና ተዳዳሪ ሆና አላየህም?

●የሚያፈቅሩት እና ተስፋ ያረጉበት ሰው ከድቷቸው አላየህም አልሰማህም?

●በየጫካው እየታፈኑ ከ500,000 ሺህ ብር በላይ ተጠይቀው በስቃይ የሰው ፊት እየገረፋቸው ብሩን ለምነው  ሲሰጡ አላየህም?

●ሙሉ ቤተሰቡ በር ተዘግቶባቸው እሳት ለኩሰው ሲያቃጥሉበት አላየህም አልሰማህም?

●እውነት እያለው በሃሰት ብዙ አመታትን ወህኒ ቤት ተወርውረው በተስፋ የቆዩትን አላየህም አልሰማህም?

●ብር የነበረው አትቶ ሲሰቃይ እና የሰው ፊት ሲገርፈው አላየህም አልሰማህም?

●ሰው ታሞበት ማሳከሚያ አቶ የሞተበትን ሰው አላየህም አልሰማህም?.....................

አዎ ሰምተሃል፣አይተሃልም።
አላየህም ፣አልሰማህም ማለት ደሞ ቅጥፈት ነው።
እነዚህ ሰዎች እኮ ታግሰው እየኖሩ ነው ለዚህ ነው አንተን ዛሬ እራሴን ላጠፋ ነው የምትለውን እያዩ እንዳይታዘቡህ ያልኩህ!

ታድያ አንተ ከዚህ የከፋ የትኛው አዲስ ነገር ቢደርስብህ ነው እራስህን ልታጣፋ የበቃከው?

ችግርህን እኮ አረፍ ብለህ ብታስበው በቀላሉ ልትወጣው የምትችለው ሊሆን ይችላል።

የአይምሮ ታማሚ ካልሆንክ ሰው ነህና ማሰብ እና ማገናዘብ ትችልበታለህ።

አንተ ዛሬ እራስህን ካጠፋህ ማን ይጎዳል ብለህ ታስባለህ።
እናንተ እራሳችሁን ስታጠፉ ቀጣይ ወንድምህን እራሱን አለማጥፋቱን በምን እርግጠኛ ሆንክ? /አንተ እራስክህን አጥፍተህ ካየህ እራስን ማጥፋት ቀላል መስሎት/
ያሳደገህን ወላጅ እና ህብረተሰቡ አንተን በማጣት ያዝናሉ።

ቤተክርስቲያን አንተን በማጣቷ ደግሞ የከፋ ሃዘን ውስጥ ትገባለች። 

እራሳችሁን የምታጠፉ እና ልታጠፉ ያሰባችሁ ሰዎች ቤተክርስቲያንን ተጠያቂ አታድረገጓት ።

🏮እራሱን ያጠፋ ሰው ምን እንደሚሆን ቤተክርስቲያን አላስተማረችም አታሰኟት!
🏮ቤተክርስቲያንን በልኳ ብታውቃት እራስህን ለማጥፋት ክፉ አታስብም ነበር።
🏮እግዚአብሔርም የለም አታሰኙት!
🏮ቤተክርስቲያን በቃኝ ብለህ እስክትናገር ድረስ አስተምራሃለች ይህንን መካድ አታሰኘው!
🏮መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ካለው ዕዮብ በላይ መከራን ያየ ይኖራል ? አንተስ ብትሆን ከዕዮብ የለበለጠ የትኛውን መከራ ተጋፍጠህ ነው ዛሬ በቃኝ ለማለት የበቃከው?

አብዛኞቻችሁ  እራሳችሁ ባመጣችሁት ጣጣ ስትሰቃዩ መሰቃየቱን ደሞ ትጠሉታላቹ።
በኋላ ምን እንደሚመጣባቹ እያወቃችሁ የማይጠቅማችሁ ነገር ውስጥ ትገባላችሁ ሰው ሲነግራችሁም አትሰሙም ለዚህ ደሞ ተጠያቂው አንተ ነህ። ...እራስህ ጎትተህ ያመጣከውን ጣጣ ደሞ መወጣት ግዴታህ ነው። ይህ የሚሆነው ደሞ እራስን በማጥፋት መስሎህ ከሆነ ተሳስተሃል በብልጠት እንጂ።
ስህተት ስትሰራ የጀገንከውን ያህል ለማረምም መጀገን አለብህ።

መርምር አስተዳደግህን ተመልከተው እንዴት ነው ያደኩት በልና እራስህን ጠይቅ።
ወላጆችህን ሳታከብር አድገህ ከሆነ የሚጠቅምህን ቢነግሩህ እንኳን አትቀበላቸውም ወደ እማይጠቅምህ ስትጓዝ በእጅህ ገመድ ይዘህ ታገኛለህ።

ክፍል ሁለት➠

@ortodoxtewadochannal   @ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

በወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ዙሪያ ውይይት የሚያደርግ ጉባኤ በፍራንክፈርት እየተካሄደ ይገኛል።
*

የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ከነሐሴ ፳፮ - ፳፯ ቀን  ፳፻፲፭ ዓ.ም በተደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በተወሰነው መሠረት ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የጀርመንና አካባቢው እና የምሥራቅ ጎጃም አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ በሀገረ ስብከቱ ሥር የሚገኙ ጠቅላላ ካህናት፣ የሰበካ ጉባኤ አስተዳደር አባላትና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች በተገኙበት በወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ዙሪያ ውይይት የሚያደርግ ጉባኤ ዛሬ ጠዋት መስከረም ፳፮ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም (October 7, 2023) በፍራንክፈርት ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ስብከተ ወንጌል አዳራሽ እየተከናወነ ይገኛል።

ምንጭ: የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚድያ
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

ዘመነ ጽጌ
 
ዘመነ ጽጌ የሚባለው ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፭ ያለው ነው። ይህ ወቅት ዐቢይ የምስጋና ቀናት ያለው ሊቃውንቱ በማሕሌት፣ ምእመናን በፍቅር ሆነው የእናታችን የድንግል ማርያምን ስደት ከተወዳጅ ልጇ ጋር የሚያዘክሩበት ወር ነው። ከማሕሌቱም በተጨማሪ ምንም እንኳን የዐዋጅ ጾም ባይሆንም የእመቤታችን ፍቅር የበዛላቸው በጾም ሆነው የሚያሳልፉት ዐቢይ የምስጋና ወቅት ነው።
 
ጽጌ ማለት ጸገየ አበበ ከሚል የግእዝ ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን አበባ፣ ውበት፣ ደም ግባት ማለት ነው። አበቦች ውብ፣ ማራኪና አስደሳች ከመሆናቸው የተነሣ የሰው ልጆች በሙሉ አበቦችን ይፈልጋሉ። ምድርም በአበቦች አጊጣ ተሸልማ ስትታይ ክረምት ከለበሰችው ልምላሜ ይበልጥ ታስደስታለች። ዘመነ ጽጌ ዝናምና ወጨፎ፣ ዶፍና ጎርፍ፣ መብረቅና ነጎድጓድ የሚፈራረቅበት የክረምት ቀናት አልፎ ምድር በአበቦች የምትሸለምበት፣ ደመናው ከሰማይ ተወግዶ ሰማይ በከዋከብት የሚያሸበርቅበት፣ የሰው ልጆች ይህንን በማየት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ደስ የሚሰኙበት ወር ነው።
 
ወርኃ ጽጌ የዘመናት ባለቤት ዘመነ ክረምቱን አሳልፎ የደስታ እና የመልካም ምኞት መግለጫ በሆኑ አበቦች ወደ አሸበረቀው ዘመነ ጸደይ ስላደረሰን "ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት ተሠርገወት ምድር በሥነ ጽጌያት፤ ክረምት አለፈ በረከት ተተካ ምድርም በአበቦች አጌጠች” እየተባለ የሚዘመርበት ወቅት ነው። በዚህ ወራት ሰውም ዕድሜው እንደ አበባ አጭር በመሆኑ ሞቱን ማሰብ እንዳለበት ማስገንዘብ ተገቢ ነው። አበባ የሚወድቀው የሚረግፈው ፍሬ ለማፍራት ነው፤ አበባ ሲኖር በመዓዛው፣ ሲረግፍ በፍሬው ያስደስታል።
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አዳማ ዙሪያ የመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ሁለት አገልጋዮች በታጠቁ ኃይሎች መገደላቸው ተገለጸ፡፡
(ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት)
በኤልሳቤጥ ቤተ
+++++++++++++++++++++++++++++++++

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አዳማ ዙሪያ የመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ሁለት አገልጋዮች በጥይት መገደላቸው ተገለጸ፡፡

ድርጊቱ  የተፈጸመው መስከረም 23 ቀን  2016  ዓ.ም  ከምሽቱ 2፡30 አካባቢ ሲሆን  ከተገደሉት  አንድ  ካህን  እና  ዲያቆን  በተጨማሪ  ሁለት  ካህናትና  አንድ  ምእመን  በታጣቂ ኃይሎቹ   መታገታቸውን  ያገኘነው  መረጃ  ይጠቁማል፡፡

የታገቱት  ካህናትና ምእመኑ  ይህንን  ዜና  እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ  ያሉበት አልታወቀም፡፡
ለደህንነታቸው  ሲባል   ስማቸውን  ያልጠቀሱት   መረጃ  ሰጭያችን በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አዳማ ዙሪያ በተደጋጋሚ  ጊዜ  ካህናትና  ምእመናን ላይ ጥቃቶች እንደሚደርሱ ገልፀዋል ። 
በዚህም  ምክንያት  በርካታ  ምእመናን  አካባበቢውን  እየለቀቁ  መሰደዳቸውንም ነግረውናል፡፡

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አዳማ ዙሪያ የመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን መስከረም 23 ቀን  2016  ዓ.ም  ከምሽቱ 2፡30  የተፈጠረውን  ግድያና  አፈና  በተመለከተ  የሚመለከተው  የጸጥታ  አካላት   የወሰደው   እርምጃ  አለ  ወይ    ብለን  ላነሳንላቸው  ጥያቄም  የጸጥታ  አካሉ ጥቃቱ ከተፈፀመ በኋላ  መድረሱን  ተናግረዋል፡፡ 

በመሆኑም  በአዳማ  ዙሪያ  በተደጋጋሚ  የሚፈጠረውን  የንጹሃን  ግድያ  ማስቆም  የመንግስት  ዋና  ሥራ  በመሆኑ   የሚመለከተው  አካል  ትኩረት  ሊሰጥ  ይገባልም  ብለዋል፡፡
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

የብፁእ አቡነ ሰላማ ሥርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እየተከናወነ ይገኛል።

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

🟢🟡🔴
✨መስከረም 17 | #በዓለ_መስቀል ✨
                   🌼◦✞◦🌼

መስከረም ዐሥራ ሰባት በዚች ቀን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ለከበረ መስቀል በዓሉ ነው። ይህም የጻድቁ ንጉሥ የቈስጠንጢኖስ እናት ንግሥት ዕሌኒ ከተሠወረበት የገለጠችው ነው።

የጎልጎታን ኮረብታ በአስጠረገች ጊዜ የከበረ መስቀልን አገኘችው። ታላቅ ኮረብታም የሆነበት ምክንያት እንዲህ ነው፦

ብዙዎች ድንቆች ተአምራት ክብር ይግባውና ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመቃብሩና ከመስቀሉ የሚገለጡ ሁነው ሙታን ይነሡ ነበርና የጎበጡና በሽተኞች ሁሉ ይፈወሱ ነበር።

ስለዚህም አይሁድ ተቆጡ እንዲህም ሥርዓትን ሠርተው አዘዙ። "በይሁዳ አገር ሁሉና በኢየሩሳሌም ቤቱን የሚጠርግ ሁሉ ወይም አፈር ወይም ጉድፍ የሚጠርግ በናዝሬቱ ኢየሱስ መቃብር ላይ ይጥል ዘንድ" እንዲህም እያደረጉ ዕሌኒ ንግሥት እስከ መጣች ድረስ ከሦስት መቶ ዓመት በላይ ኖሩ።

እርሷም በመጣች ጊዜ ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብርን እስከ አሳዩዋት ድረስ አይሁድን ይዛ አሠቃየቻቸው። ያንን ኮረብታም እስከ ጠረጉ ድረስ አስገደደቻቸው የከበረ መስቀሉም ከተቀበረበት ተገልጦ ወጣ።

ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ተሠራች። በዚች ቀንም አከበሯት። ለመስቀሉም በዓልን መስከረም ዐሥራ ሰባት ቀን አከበሩለት።
              
✨ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በምሕረቱ አደረሳችሁ ✨
                         🌼◦✞◦🌼
              @ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

ንስጥሮሳውያን ማናቸው

ንስጥሮሳውያንን ለመረዳት በመጀመሪያ ስለ ንስጥሮስ እንመልከት። ንስጥሮስ በ5ኛው ክፍለ ዘመን የነበረ ሲሆን በአንጾኪያ ቤተክርስቲያን የተማረና ከ 428 እስከ 431 የቁስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳስ የነበረ ነው። ነገር ግን በ431 ዓ.ም በተካሄደው ሶስተኛው የቤተክርስቲያን ጉባኤ ተወግዞ ከጵጵስናው የተሻረ ነው።

ንስጥሮስ የተወዘገው በኤፌሶን ጉባኤ በ431 ሲሆን ይህም የሆነው የቤተ ክርሰቲያን መከፋፈል ሳይመጣ ነው። ማለትም ኦሪየንታል ኦርቶዶክስ፣ ምስራቅ ኦርቶዶክስ እና ካቶሊክ የሚባሉት መከፋፈሎች ሳይመጡ በፊት፣ የቀድሞዋ ቤተ ክርስቲያን (early church) በሚባለው ዘመን ነው።

የንስጥሮስ አስተምህሮ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና እመቤታችን ድንግል ማርያም ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ እመቤታችን ድንግል ማርያም የአምላክ እናት አይደለችም የሚል ነበር። እንዲሁም ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ባሕርይ ነው የሚል ነበር።


ይህም ማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወለድ አምላክ ሆኖ አልተወለደም የሚልን ሀሳብ የሚፈጥር ነው። ጌታችን አምላክነቱ እና ሰውነቱ አንድ ሳይሆኑ የተነጣጠሉ ናቸው የሚል ነው። ይህም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ለሰው ልጆች የከፈለውን ዋጋ የሚያሳንስ (እሱ ስላለ ጌታችን የከፈለልን ዋጋ አይቀንስም)፣ እመቤታችን ድንግል ማርያምንም ክብሯን የሚቀንስ ነው (እሱ ስለተናገረ ክብሯ አይቀንስም)።

በዚህም ምክንያት በፈረንጆች አቆጣጠር በ431 ዓ.ም በኤፌሶን ከተማ ሶስተኛው የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ተደረገ። ከ200 በላይ አባቶች ጳጳሳት፣ ከሮም፣ ከእስክንድርያ፣ ከአንጾኪያ ከሁሉም ቦታ የመጡ አባቶች በተኙበት ጉባኤ ንስጥሮስ ተወገዘ። የጵጵስና ማዕረጉም ተሻረ። የሱን አስተምህሮ የሚከተሉ ሁሉም ተወገዙ።

በዚህም ንስጥሮስና ተከታዮቹ ጠፉ። ነገር ግን አስተምህሮው አልጠፋም ነበር። በ451 በተካሄደ ጉባኤ የግሪክና የላቲን ቤተ ክርስቲያናት የሱን አስተምህሮ በተዘዋዋሪ ተቀበሉ። በአፋቸው ንስጥሮስ የተወገዘ ነው ቢሉም ግን የተቀበሉትን በተዘዋዋሪ የንስጥሮስን ሁለት ባህርይ አስተምህሮ ነው። ይህን የተቃወሙትም የኦሪየንታል ቤተክርስቲያናት ከነሱ ተለዩ።


ሌሎችም የንስጥሮስ ተከታዮች ነበሩ። ይህም በምዕራብ ሶርያና ምስራቅ ኢራቅ አከባቢ የምትገኘው የ"ምስራቅ" ቤተክርስቲያን ተከታዮች ነበሩ። ይህ ቤተክርስቲያን ከዛን ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬም የቆየ ሲሆን የንስጥሮስን አስተምህሮ በቀጥታ የሚቀበሉ እና ንስጥሮስንም እንደ ቅዱስ የሚቆጥሩ ናቸው።


ታዲያ ይህ ከላይ ያየነው አባት የዚህ ቤተክርስቲያን አባል ነው። ከልደቱም ጀምሮ በዚህች ንስጥሮሳዊት ቤተክርስቲያን ውስጥ የነበረ ሲሆን በዚያም ዲቁና እና ክህነት ያገኘ ነበር። በኋላ ላይ ግን ከዚያም በመለየት የራሱን ቸርች የከፈተ ሰው ነው።

እንደ ቻናሌ የዚህን ሰው የኋላ ታሪክ ሳልመረምር መልክቱን በመልቀቄ ይቅርታ እጠይቃለሁ።
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

"እንደቀድሞ ጊዜ ቢሆን ቤተ ክርስቲያን እያለች ሰላም ከሀገር አይርቅም ነበር፤ ዛሬ በእኛ በአገልጋዮቿ ምክንያት ያን ሚናዋን አጥታለች"

ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

በማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤ ተገኝተው ቡራኬና ቃለ ምእዳን የሰጡት ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በወቅታዊ የሀገራችን የሰላም ሁኔታ ላይ ለተሳታፊዎቹ መልእክት አስተላልፈዋል።

"ቤተ ክርስቲያን አንድ ሁኑ ብላ ታስተምራለች፤ ጥላቻን መገዳደልን ታወግዛለች፤በንግግር በውይይት ፍቱ ትላለች" ያሉት ብፁዕነታቸው "ይህንን አቋሟን በበጎ የማይመለከቱ ግን ይኖራሉ" ብለዋል።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም በመልእክታቸውም "እንደቀድሞ ጊዜ ቢሆን ቤተ ክርስቲያን እያለች ሰላም ከሀገር አይርቅም ነበር፤ ዛሬ በእኛ በአገልጋዮቿ ምክንያት ያን ሚናዋን አጥታለች" በማለት "ወላዋይና አድርባዮች ስለሆንን፣ ምን አገባኝ ብለን መስለን ስላለን ሀገሪቱን ዋጋ እያስከፈልን ነው፤ የወገን ደምም ሲፈስ ማየት ተለምዷል ሲሉ ገልጸዋል።

በመጨረሻም " ያለፈው ዘመን ይበቃ ዘንድ ስለሰላም ልንጸልይ ይገባል" ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

🟢 🟡 🔴
መስከረም 2 | የካህኑ የዘካርያስ ልጅ የከበረ #አጥማቂው_ዮሐንስ ሕግን አፍራሽ በሆነ በንጉሥ ሄሮድስ እጅ ሰማዕት ሆነ።

ይህም እንዲህ ነው፦

ቅዱስ ዮሐንስ ሄሮድስን የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን ስለማግባቱና ሌላም ያደርገው ስለነበረ ክፉ ሥራ ሁሉ ይገሥጸው ነበር። ደግሞም በተግሣጽ ላይ ተግሣጽን ጨመረ። ስለዚህም ዮሐንስን ተቀየመውና በግዞት ቤት አኖረው።

ሄሮድስም ዮሐንስን ይፈራው ነበር። ጻድቅ ቅዱስ ሰው እንደሆነ ያውቅ ነበርና ብዙ ይጠባበቀውም ነበር። ሄሮድስ የተወለደባትን ቀን በዓል የሚያከብርባት ዕለት ነበረች። መኳንንቱን አለቆቹን መሣፍንቱን ሹሞቹን በገሊላ አገር ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ግብር አገባ።

የሄሮድያዳ ልጅም ወደ አዳራሹ ገብታ ዘፈነች። ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው ከእርሱ ጋር በማዕድ የነበሩትንም ንጉሡም ያቺን ብላቴና የምትሺውን ለምኚኝ እሰጥሻለሁ አላት። እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ሊሰጣት ማለላት።

ወጥታም እናቷን ምን ልለምነው አለቻት። እናቷም የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ አለቻት። ያን ጊዜም እየሮጠች ወደ ንጉሡ ገብታ የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በወጭት አሁን እንድትሰጠኝ እሻለሁ ብላ ለመነችው። ንጉሡም ስለ መሐላው አብረውት ስለ ነበሩትም ሰዎች አዘነ፤ እምቢ ሊላት ግን አልወደደም።

ያን ጊዜም ባለወጎችን ላከ በእሥር ቤትም ሳለ የዮሐንስን ራስ ቆረጡ። ራሱንም በወጭት አምጥተው ለዚያች ብላቴና ሰጧት። እርሷም ወስዳ ለእናቷ ሰጠች። በዚያችም ቀን የቅዱስ ዮሐንስ ራስ ከሄሮድያዳ ከእጆቿ ላይ ወደ አየር ስለ በረረች ታላቅ ድንጋፄ ሆነ።

ደግሞም ሄሮድስ ሆይ የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም አለች። ደቀ መዛሙርቱም በሰሙ ጊዜ መጥተው በድኑን ወስደው ቀበሩት።

              #እንኳን_አደረሳችሁ
                  ◦🌿◦🌿◦🌿◦

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

ርእሰ ዐውደ ዓመት

ዐውደ ዓመት መነሻው ዖደ ከሚለው የግእዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ዖደ ዞረ፤ዐውድ ዙርያ፣ ማለት ነው፤ ዐውደ ዓመት የፀሐይ ዐውደ ዓመት ፫፻፷፭ ዕለት ከሩብ ይላል፡፡ (ምንጭ፡ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ሰዋሰወ ወግስ ወመዘግበ ቃላት ገጽ ፮፻፹፯)፡፡ ወበዐውዱ ለወእቱ መንበር፡፡ ይቀውሙ ዐውዶ፡፡ ዐውደ ጸሓይ፣ ዐውደ ወርኅ፣ ዐውደ ዓመት (ራእ.፬፡፬፤ አቡሻህር ፳፫)

ዐውደ ዓመት በግእዝ ሲሆን በአማርኛ የዘመን መለወጫ ይባላል፡፡ ርእሰ ዐውደ ዓመት ቅዱስ ዮሐንስ መፅምቅን ያወሳናል፤ የቅዱስ ዮሐንስ ዕረፍት (ምትረተ ርእሱ) የሚታሰበው መስከረም ሁለት ቀን ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስን በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ መካከል የነበረ መሸጋገሪያ ነው፡፡ መታሰቢያ በዓሉም የብሉይ ኪዳን ምሳሌ ከሆነው ካለፈው ዓመት የሐዲስ ኪዳን ምሳሌ ወደሚሆነው አዲሱ ዓመት መሸጋገሪያ በሆነው በመስከረም አንድ ቀን ይከበራል፡፡ቅዱስ ዮሐንስ በነቢያት መጨረሻ በሐዋርያት መጀመሪያ ተገኝቶ ዘመነ ሐዲስን እንደሰበከና ከዘመነ ብሉይ ወደ ዘመነ ሐዲስ መሸጋገሪያ ጊዜ ላይ ስለነበረ ያለፈውን ዘመን የምንሸጋገርበት የዘመን መለወጫ ቀን የቅዱስ ዮሐንስ መታሰቢያ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ (ማር.፩፥፪-፭)

የዘመን ቆጠራ ከጌታችን ልደት በፊት የነበረው አገልግሎት  የሰው ልጆች ሁሉ በተለይ አበው ነቢያት/ በተስፋ ይጠብቁት የነበረውን የጌታችንን መምጣት የቀረውን ጊዜ እንዲሁም በብሉይ ኪዳን አጽዋማትና በዓላት ለማወቅ ነበር፡፡ ተስፋው ከተፈፀመ በኋላ ደግሞ የዘመን ቆጠራ ዋና አገልግሎቱ በዓላትና አጽዋማት በዓመቱ የሚወሉበትን ዕለት ለማወቅ ነው፡፡ እነዚህ በዓላት እግዚአብሔር በተለያዩ ዘመናት ለሰው ልጆች ያደረጋቸው ድንቅ ነገሮችና ውለታዎች የፈጸመባቸው ስቅለት፣ ትንሣኤ እና ሌሎችም በዓላት የሚታሰቡባቸው ናቸው፡፡

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

ዕንቁጣጣሽ!
 
እንኳን ለዘመነ ዮሐንስ አደረሰን!
 
የዕንቁጣጣሽ ስያሜ እና መሠረታዊ አመጣጥ
 
በየዓመቱ በመጀመሪያ መስከረም አንድ ቀን የዘመን መለወጫን ዕንቁ ጣጣሽ በማለት ቅድስት እናከብራለን። ዕንቁጣጣሽ መሠረታዊ መነሻውና አመጣጥ “ዕንቁ ዕፅ አወጣሽ” (ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ) ከሚለው ቃል ነው፡፡ አዲስ ዓመት በአንዳንድ ቦታ ዕንቁጣጣሽ እየተባለ ሲጠራ በሌላ በኩል ደግሞ “ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዓውደ ዓመት፣ አዲስ ዓመት፣ ዕንቁጣጣሽ” እየተባለ ይጠራል፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚያስረዱት ዕንቁ ጣጣሽ የሚለው ስያሜ የተለያየ ትርጉም ቢሰጠውም እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሚሰጠው ትርጉም እንደሚከተለው ነው፡፡
 
አንደኛ “ዕንቁ - ዕፅ አወጣሽ” ብሎ የአበባውን መፈንዳት የሚያመለክት ነው፤ ሁለተኛ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በዕጣ ሲያካፍላቸው አፍሪካ ለካም ሲደርሰው በአፍሪካ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በወርኃ መስከረም በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃና ደምቃ ነበር፡፡ በመሆኑም ደስ ብሎት ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ በማለት ይህችን ወቅት ዕንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡
 
ሦስተኛው ኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ሳባ (ንግሥተ አዜብ) የንጉሡን ጥበብ ከመስማት ማየትን መርጣ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን ከብዙ ሠራዊቶቿ ጋር የእጅ መንሻ በመያዝ ሄደች፤ (፩ነገ.፲፥፩-፲)፡፡ ንጉሡም በደስታ ተቀብሎ እርሱም “ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንሽ” በማለት አራት ዓይነት ቀለም የሚታይበት በቀንና በሌሊት የምታበራ ቀለበት በወርኃ መስከረም ሰጥቷታት ነበር፡፡ እነዚህን ምክንያቶች መነሻ በማድረግ አዲስ ዓመት ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
 @ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

ጳጉሜ ፯  እንዴት ነው የምትሆነው  ?



"…የራሷ የሆነ የዘመን አቆጣጠርና የራሷ ፊደል ያላት ኢትዮጵያችን ይሄን ቀመር ሠርታ አስቀምጣልናለች። ዓመት 365 ¼ ቀናት ሲኖሩ በ4 ዓመት አንዴ 366 ይሆናል። 30 ሠላሳ ቀናትን የያዙ 12 ወሮችና 5 ወይም 6 የሚሆኑ የጷግሜ ቀናትን 1 ዓመት ይዟል። የአዲስ ዓመት መጀመሪያም መስከረም 1 ነው።

"…እነዚህ የጳጉሜን ቀናት ከየት መጡ?ለሚለው ስለ ዘመን መቁጠሪያ ባህረ ሀሳብ ወይም አቡሻህር የተጸፉ በርካታ መጻሕፍት ስላሉ እነርሱን በማንበብ መልስ ማግኘት ይቻላል።

1 ዓመት
•በፀሐይ 365 ዕለት ከ6 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ነው። በጨረቃ ደግሞ 354 ዕለት ከ8 ሰዓት ከ48 ደቂቃ ከ39 ሴኮንድ ነው።

•በፀሐይ 365 ዕለት ከ6 ሰዓት ከ2 ቂቂቃ ነው የሚለውን ይዘን የትመጣውን ለማስረዳት አንሞክራለን።

"…በቀደምት ኢትዮጵያውያን ጥልቅ ትንተና መሰረት አንድ ዕለት የምንለው 24 ሰዓት ከ21 ደቂቃ ከ0.4 ሰከንድ ነው። ይህ የሚያሳየውም ከ1 ዕለት ትርፍ 21 ደቂቃ ከ 0.4 ሴኮንድ እንዳለ ነው። ስለዚህ 21 ደቂቃ x 30 ቀን = 630 ቂቂቃ ማለትም 10 ሰዓት ከ 30 ደቂቃ ማለት ነው።

•በ3 ወር 30 ሰዓት ከ 90 ደቂቃ ማለትም 1 ዕለት ከ7 ሰዓት ከ30 ደቂቃ
•በ 12 ወር 4 ዕለት ከ28 ሰዓት ከ120 ደቂቃ ማለትም 5 ዕለት ከ6 ሰዓት
•በ4 ዓመት 6 ሰዓት x 4 = 24 ሰዓት ስድስተኛዋ ጳጉሜን የቀረችዋ 0.4 ሰከንድ ደግሞ…
• 0.4 ሰኮንድ X በ 30 ዕለት = 12 ሰከንድ፣
• በ 12 ወር 12 ሰከንድ x 12 = 144 ሰከንድ ማለትም 2.4 ደቂቃ
• በ10 ዓመት 24 ደቂቃ
• በ100 ዓመት 240 ደቂቃ ማለትም 4 ሰዓት
• በ200 ዓመት 8 ሰዓት
• በ400 ዓመት 16 ሰዓት
• በ600 ዓመት 24 ሰዓት ይሆናል። ስለዚህ በ 600 ዓመት አንድ ጊዜ ጳጉሜን 7 ትሆናለች።

ምንጭ :-አቡሻኽር መጽሐፍ
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

🥀በአጠቃላይ ዓይነ ልቦናችን ተዐውሮ ዛሬም እንደ ቀድሞው በኃጢአት ተተብትበን፣ ከንጽሕና ከቅድስና ርቀን ያለነውን በአማላጅነቱ ውሳጣዊ ዓይኖቻችንን አብርቶ መንፈሳዊውን ዓይን አድሎን መልክአ ክርስቶስን እያየን ለክብር እንድንበቃ ታላቁን መልአክ ና አካሄዴን አሳምርልኝ እንበለው "መራሔ ፍኖት" ነውና። በነፍስ በሽታ ማለትም በፍቅር አልባነት፣ በአልቦ ትሕትና፣ በአልቦ የዋሐት፣ በአልቦ ፍቅረ ቢጽ ወፍቅረ እግዚአብሔር፣ በአልቦ ጾም ወጸሎት ድርቅ ታመን ያለነውን እኛን ፈዋሽ በኾነው ስምኽ ፈውስን እንበለው።

🥀የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሩፋኤል በረከት ከኹላችን ጋር ይኹን አሜን!!
    #ሼር    ቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

Читать полностью…
Subscribe to a channel