ortodoxtewahedo | Unsorted

Telegram-канал ortodoxtewahedo - ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

64069

ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ። ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ›› ት.ኢሳ 58÷3 https://youtu.be/csxxAMGtC4I ለመቀላቀል http://t.me/ortodoxtewahedo

Subscribe to a channel

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

#ቅድስት ሥላሴ

ሥላሴ በአብ ልብነት ያስባሉ፣ በወልድ ቃልነት ይናገራሉ፣ በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት ህልው ሆነው ይኖራሉ።
ተግባራቸውም የውሕደታቸው ውጤት ነው።
የሰው ልጅም በሥላሴ መልክ ስለተፈጠረ ልብ፣ ቃል፣ እስትስፋስ አለው። በልቡ ያስባል፣ ያሰበውን በአንደበቱ ይናገራል፣ የተናገርውን ደግሞ በሕይወቱ ይኖረዋል።

በመልካም ሥነ ምግባር የሚኖር ሰው ማለት
የሚያስበውን የሚናገር፣ የሚናገረው ከሚኖረው ወይም ከሚሠራው ጋር የተስማማለት ማለት ነው።

ሀሳባችን አንደበታችንና ሕይወታችን እንዲስማማልን ማድረግ በሥላሴ መልክ የመፈጠራችንን ማሳያ ነው። ስለዚህም "ሥላሴን እናስባለን፣ ሥላሴን እንናገራለን፣ ሥላሴን እንተነፍሳለን"

እንዲ እናምናለን አንታመናለን አብ ወልድ መንፋስ ቅዱስ አንድ እግዚአብሔር ብለን

#እንኲን ለየአብርሀሙ ሥላሴ በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

የአብርሐምን ቤት የባረኩ ሥላሴ እኛንም በህይወታችን በኑሮዋጭን በአገልግሎታችን በትዳርአችን በትምርታችን በሥራችን ይባርኩን ።

ሥሉስ ቅዱስ ለሚታምን ሁሉ እምነትን በረከትን ሀገራችን ኢትዮጽያን ሰላም ያድርጉልን አሜን ::

#መልካም እለተ ይሁንልን

◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >
             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

#ጌቶቼ_ከቤት_ገብታችሁ_እረፉ

ቅዱስ እግዚአብሔር "ብየ አርክ በዲበ ምድር አብርሃም ፍቁር በዲበ ምድር" በምድር እንደ አብርሃም ያለ ወዳጅ የለኝም ብሎ የተናገረለት አሥረ አንድ የቃልኪዳን ተስፋዎች የተገባለት አበ ብዙኃን አብርሃም በመጸሐፍ ቅዱስ ውስጥ ታሪካቸው ከሰፈረላቸው አበውበላይ እጅግ የከበረ ያደረገውን ክስተት አስተናግዷል። ይህም በቤቱ በዓለምና ከዓለም ውጪ ያለውን የፈጠሩ ፈጥረውም የሚገዙ ቅድስት ሥላሴን ማስተናገዱ ነው። ኅቡዕ ሽሽግ በነበረበት ፍዳና መርገም ባየለበት ዘመን የሥላሴ ምሥጢር የተገለጠበት ታሪክ በአብርሃም ሕይወት ውስጥ ጎልቶ የሚጠቀስ ነው።

ነገሩ እንዲህ ነው። ጻድቅ አብርሃም በነፋስ አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የሚመግብ እግዚአብሔር አይደለምን? ብሎ ከመስቀለኝ ቦታ ድንኳን ተክሎ ያለፈ ያገደመውን የሚያቀው የማያቀውን ሁሉ እየተቀበለ ያሳርፋቸው ይመግባቸው ነበር። ዛሬ ደግ የሆነ ሰው ቤተ የገባን እንደሆነ "ይህ ቤት ቤተ አብርሃም" ብለን ምናወድሰው። መልካም ሥራ ለምሥራት የደከመ ለክፋት የፈጠን ጥንት ጠላት ሰይጣን የአብርሃም ደግነት ቢያውከው ፍቁረ እግዚአብሔር መባሉ ቢጨንቀው። እርሱም መስቀለኛ ቦታ ላይ ተሰይሞ የተደበደበ መከራ ያገኝው መስሎ ወደ አብርሃም የሚያቀኑ እንግድችን "ወዴት ትሄዳላችሁ ይላቸዋል" እነርሱም ከአብርሃም ዘንድ እየሄዱ እንደሆነ ሲነግሩት። የተገመሰ ራሱን የፈሰሰ ደሙን እያሳየ አብርሃም እንደ ቀድሞ አይመሰላችሁ አብዱ እንዲህ አደረገኝ እናንተንም እንዳይጎዳችሁ እያለ ይመልሳቸዋል። እንዲህ እያለ ለ3 ቀን ያክልክ እንግዳ ከለከለበት።

የእግዚአብሔር ወዳጅ አብርሃምም የለምድኩትን አጣሁኝ እንግዳ ቀረብኝ ብሎ ሁለት ቀን ከእህል ተከልክሎ ቆየ በሦስተኛው ቀን አዝኖ ተክዞ ሳለ ቅድስት ሥላሴ በጎነቱን የእምነቱን ፍጹምነት ተመልክተው ከዛፍ ሥር በሰው ገጽ ተገለጡለት። ኦሪት ዘፍጥረት ከዛፍ ሥር ተገለጡለት ሲል ገድለ አብርሃም በቤቱ ተገለጡለት ይላል ገድለ አብርሃም መግባታቸውን ባያይ ከቤት አለ። በሐዘን የቆየው ታላቁ ሰው አብርሃም በተመለከታቸው ጊዜ ሐዘኑ ተወግዶለት በደስታ ተቀበላቸው። "ገሐሡ አጋእዝትየ ቤተ ገብርክሙ" ጌቶቼ ከቤት ገብታችሁ እረፉም አላቸው። መጸሐፍ እንደሚነግረን እነርሱም ደክሞናል ያላዘልከን እንደሆነ ቤተ አንገባም አሉት አብርሃም የጌታውን ቃል ሰምቶ አንዱን ቢያዝለው ሁለቱም ቤት ገብተው አገኛቸው። መተርጉማን ከሦስቱ አንዱን አዝሎት ገባ የተባለው ወልድን ነው ይሉናል። ከእርሱ ባሕርይ ሰው የሆነው ከሦስቱ አካል አንዱ አካል ወልድ መሆኑን ለማስረዳት ነው።

አርከ እግዚአብሔር አብርሃም የአንድነትና የሦስትነት ምሥጢር ቢገለጥለት ሦስት መሥፈርያ ዱቄት በአንድ አድርጋ ጋግራ እንድታመጣ ሚስቱ ሣራን አዘዛት። ሦስት መሥፈርያ ማድረጉ የሦስትነት በአንድ ማድረጉ አንድነትን ያሳያል። በብሉይ በጉልህና በተረዳ አንድነትና ሦስትነት የተገለጠው በአብርሃም ቤት ነው። በዚህ ክፍል አብርሃም አንድ ጊዜ አንተ አንድ ጊዜ እናንት በሚል አገላለጽ ይጠቀም ነበር። "አቤቱ፥ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ፥ እግራችሁን ታጠቡ፥ ከዚህችም ዛፍ በታች ዕረፉ፤ቍራሽ እንጀራም ላምጣላችሁ፥ ልባችሁንም ደግፋ ከዚያም በኋላ ትሄዳላችሁ፤ ስለዚህ ወደ ባሪያችሁ መጥታችኋልና። እነርሱም፦ እንዳልህ አድርግ አሉት።" ዘፍ 18:3

አብርሃምም ያዘጋጀላቸውን እነርሱም በሉ። ቅድሥት ሥላሴ መብላት መጠጣት ለባሕርያቸው አይሰማማም ታድያ ብሎ መባሉ እንዴት ነው። ቅድሥት ሥላሴ በሉ ማለት እሳት ቅቤን በላ እንደማለት ያለ ነው ይሉናል።አብርሃምም ያዘጋጀላቸውን እነርሱም በሉ። ቅድሥት ሥላሴ መብላት መጠጣት ለባሕርያቸው አይሰማማም ታድያ ብሎ መባሉ እንዴት ነው። ቅድሥት ሥላሴ በሉ ማለት እሳት ቅቤን በላ እንደማለት ያለ ነው ይሉናል። እሳት ቅቤን ያቀልጠዋል እንጂ እንደ እንጨት አቃጥሎ አመድ አድርጎ አይተወውም። ቅድስት ሥላሴም ለአብርሃም የበሉ መስለው ታዩት እንጂ መብልዕ አያሻቸውም። በስተመጨረሻም እግዚአብሔር "አመ ከመ ዮም እገብእ ኀቤክ" እንዲህ እንደ ዛሬ ወደ አንተ እመለሳለሁ ብሎት ሔዷል። ለጊዜው የዛሬ ዓመት ይስሐቅን ትወሌዳለህ ፍጻሜው ግን ከአንተ ባሕርይ ከተወለደች ከዴንግል እወለዳለው ሲል ነው።

ጭብጥ ሐሳብ

✍️በመንገድ መሰናክል የሚያኖር በድግነትህ እንቅፋት ሚያመጣ በመልካም ሥራህ የሚቀና በጽድቅ ሩጫህ ላይ የሚያውክ ጠላት ሲነሳብህ ታገስ። እግዚአብሔር እራሱን እስኪገልጥ ድረስ ለሌሎች የተሰወረውን ምስጢር እስኪያሳይህ ድረስ ይክሰሀል።

✍️አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ለወደዷቸው ምሥጢር የሚገልጡ ናቸው። ላከበሯቸው በጠላት ፊት ያከብራሉ። ለታመነባቸው በገንዘቦቻቸው ላይ ሁሉ ይሾሙታል።

{ኦሪት ዘፍጥረት ትርጓሜ ገድለ አብርሐም )

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

✤✤✤ #ሐምሌ_ቅድስት_ሥላሴ
ቅድስት ቀደሰ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣና ትርጕሙም ልዩ ማለት ሲኾን የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ልዩ (የሥላሴን አንድነትና ሦስትነትን የሚመስል ስለሌለ፤ ቢመስልም ምሳሌ ዘየኀጽጽ) ስለኾነ ሥላሴን ቅድስት በሚል ቅጽል እንጠራለን፡፡

#ሐምሌ_7_ቀን_ቅድስት_ሥላሴ_ለአብርሃም_የተገለጹበት_ነው፡፡ ይኸውም ስለ ፫ት ምክንያቶች ነው፤
#፩ኛ) ለመልካም ነገር /በአብርሃም አንግዳ መቀበል ፀር የኾነ ሰይጣንን ለማሳፈር/ (ሰይጣን በምቀኝነት አብርሃም እንግዳ እንዳይቀበል የውሸቱን ወደ አብርሃም ቤት በሚወስድ መንገድ ላይ ግንባሩን ገምሶ፥ ደሙን አፍስሶ ሰዎች አብርሃም እንዲህ መጥፎ ነውን እንዲሉና እንግዶች ወደ ቤቱ ሂደው እንዳይስተናገዱ አድርጓል፤ አብርሃምም ለ3 ቀናት እንግዳ እየጠበቀ ጾሙን ውሎ ነበር፡፡ ይህን የሰይጣን ክፋት የአብርሃምን እምነትና እንግዳ መቀበል የተመለከቱ ፥ ምግብን የማይመገቡ ሥላሴ በአብርሃም ቤት ገብተው እሳት ቅቤን እንደሚበላ ተስተናግደዋልና ነው፡፡ መስተናገዳቸውንም መምህረ ጋሥጫ የኾነው ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በመልክአ ሕማማት ድርሰቱ እንዲህ በግጥም አስቀምጦታል፤
ለንግሥክሙ ሰገደ አብርሃም በርእሱ፡፡
ቤተ ገብርክሙ እንዘ ይብል ገሐሡ፤
አጋዕዝትየ ዘትሤለሱ ግናይ ለክሙ፡፡
እዚህ ላይ ልናስተውለው የሚገባው አምላካችንም ኾነ ቅዱሳን መላእክት ለአብርሃምና ለሌሎችም ቅዱሳን በተለያየ አምሳል መገለጻቸውን ልብ ይሏል፡፡ ለአብነትም፤
፠ ለአብርሃም በአምሳለ አረጋዊ፤
፠ ለሕዝቅኤል በዘባነ ኪሩብ፤
፠ ለዳንኤል በአረጋዊ፣
፠ ለዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ በተለያየ አምሳል፤
፠ ለደብረ መጕናው (ሞጊና) ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን አቡነ አብሳዲ ደግሞ ራሱ መድኀኔዓለም ተገልጾላቸውና ተቀብለውት እንደ አብርሃም እግሩን ያጠቡት መኾኑን ልብ ይሏል፡፡

#፪ኛ) ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ፥ እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛልሃለሁ ያሉት ሥላሴ ቃሉ የማይታበይ መኾኑን ለማሳየት (ሰማይና ምድር ያልፋል ፥ ቃሌ ግን አያልፍም ብሎ በኋለኛው ዘመን ጌታችንም እንዳረጋገጠው)፤ ለአብርሃምና ለሣራ ልጅ ሊሰጧቸው፡፡ አባታችን አብርሃም 99 ዓመት ፥ እናታችን ሣራ 89 ዓመት መልቷቸውና የመውለጃ ጊዜያቸው ባለፈበት ሰዐት እንደሚወልዱ ለማብሰር፡፡

#፫ኛ) ምግብ ተመግበን ካበቃን በኋላ አምላካችንን ማመሰገን እንደሚገባን ለማስተማር፡፡ (የታረደው ወይፈንም በተዓምራት ተነሥቶ ስብሐት ብሎ አመሰግኗል፤ ይህንንም መምህረ ጋሥጫ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በመልክአ ሕማማት ድርሰቱ በግጥም እንዲህ አስቀምጦታል፤
ድኅረ በላዕክሙ ላሕመ እንበይነ ፍቅረ ሰብእ ፍጹም ፤
ዘበኀይልሙ ሐይወ ላሕም፤
ሥላሴ ክቡራነ ስም፡፡ ግናይ ለክሙ፡፡
            
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

...ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ሲሆን ከሰማይ ታላቅ ነጎድጓድ ድምጽ ተሰማ ጌታችን መላአክትን አስከትሎ ወደ አባታችን ወረደ፤ ከሰማይ ወደ ምድር ህብሩ አምሳያው ልዩ ልዩ የሆነ እንደ ጸሐይና እንደ ጨረቃ የሚያበራ እንደ ወንጪፍ ድንጋይ ይወረወር ነበር ከዚያ የነበሩ ሁሉ ፈሩ ወደ ኃላም ሸሹ ምድር ራደች ተራሮች ኮረብቶች ተናወጡ ብርቱ ጩህት ንውጽውጽታም ሆነ።

« ወዳጄ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሰላም ላንተ ይሁን እነሆ የማይታበል ቃል ኪዳን እገባልኃለው ስምህን የጠራ መታሰቢያህን ያደረገውን፤ እጣን ቋጥሮ ግብር ሰፍሮ መባ ይዞ ቤትህ የመጣውን እምርልኃለው አንተ ከገባህበት ገነት መንግስተ ሰማያት አገባዋለሁ አለው ። »

#የአባታችን_በረከታቸው_ረድኤታቸው_አማላጅነታቸው_አይለየን_አሜን

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አባቶቻችን ሐዋርያትን ሰማዕትነት በተቀበሉበት ቀናት በዓላት ሰይማ ታከብራቸዋለች፡፡ እንዲሁም በስማቸው የተሰየመውን ጾም በመጾም አሠረ ፍኖታቸውን ይከተሉ ዘንድ ምእመናንን ታሳስባለች፡፡ በሐምሌ ፭ ቀን ደግሞ የደጋጎቹን ሐዋርያት የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስን በዓል ታደርጋለች፡፡ የእነዚህ ቅዱሳን አባቶቻችን በዓል መደረጉ በአንድ ቀን ሰማዕትነት በመቀበላቸው ነው፡፡

ሁለቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አመራረጣቸው በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ የጥሪው መንገድ ግን ይለያይ ነበር፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለሐዋርያነት የተመረጠው ጌታችን በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስ ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ሆኖ ዓሣ ለማጥመድ መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፤ ወደ እነርሱም ቀርቦ “በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ” አላቸው፡፡ ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት፡፡ (ማቴ.፬፥፲፰‐፳)

በአንጻሩ የቅዱስ ጳውሎስ አመራረጥ ደግሞ በተአምር ነው፤ ይኸውም እንዲህ ነው፡፡ በቀደመ ስሙ ሳውል ተብሎ የሚታወቀው ይህ ሐዋርያ የቤተ ክርስቲያን አሳዳጅ ነበር፡፡ ቀዳሜ ሰማዕት እስጢፋኖስ በአይሁድ እጅ ሲወገር የተስማማ የገዳዮቹንም ልብስ ጠባቂ ነበር፡፡ (የሐዋ. ፯፥፶፰-፷)

ቅዱስ መጽሐፍ “ሳውል ግን ቤተ ክርስቲያንን ያፈርስ ነበር ወደ ሁሉም ቤት እየገባ ወንዶችንም ሴቶችንም እየጐተተ ወደ ወህኒ አሳልፎ ይሰጥ ነበር፡፡ . . . ሳውል ግን የጌታን ደቀ መዛሙርት እንዲገድላቸው እየዛተ . . .” እንዲል፡፡ (የሐዋ.፰፥፫፤፱፥፩) በክርስቶስ አምነው የተጠመቁ ክርስቲያኖችን ለማሳደድ ከሊቁ ካህናቱ ዘንድ የፈቃድ ደብዳቤ ጠየቀ፡፡ ይህን ዓላማውን ለማስፈጸም ወደ ደማስቆ ሲጓዝ በርሱ ዙሪያ ከሰማይ መብረቅ ወረደ፤ ዐይኖቹም ታወሩ፤ ወደ ምድርም ወደቀ፡፡

በዚያም ሳለ “ሳውል ሳውል፥ ስለምን ታሳድደኛለህ” የሚለውን ድምፅ ሰማ፡፡ ያነጋገረው ሳውል የሚያሳድደው ጌታ ነበር፡፡ “አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብኻል” አለው፡፡ ከዚያም በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ተነሥቶ ወደ ከተማው ገባ፡፡ ሦስት ቀንም ሳይበላ ሳይጠጣ ተቀመጠ፡፡ ሐናንያ የተባለው ከደቀ መዛሙርት ወገን የሆነ ወደ እርሱ ዘንድ ቀርቦ ጸለየለት፤ ዐይኖቹም ተፈወሱ፤ ተነሥቶም ተጠመቀ፡፡ (የሐዋ.፱፥፩‐፲፰)

ቅዱስ ጳውሎስ በወቅቱ ስለሆነው ነገር ለቆሮንቶስ ምእመናን ሲተረክላቸው “ ከሁሉም በኋላ እንደ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ፡፡ እኔ ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ ነኝና፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ስላሳደድሁ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ” እንዲል፡፡ (፩ኛቆሮ.፰፥፱)

የቤተ ሰብ ሕይወታቸው
ቅዱስ ጴጥሮስ የተወለደው በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ቤተ ሰቦቹ ደግሞ በቅፍርናሆም ይኖሩ ነበር፡፡ የኦሪት መጻሕፍትን ያልተማረ ከዝቅተኛው የማኅበረሰብ ክፍል የተገኘ ሰው ነበር፡፡ (የሐዋ. ፬፥፲፫) ጳውሎስ ደግሞ በኪልቅያ በምትገኘው በጠርሴስ ተወለደ፡፡ ከአይሁድ ወገን ከብንያም ወገን ነበር፡፡ (ፊል.፫፥፭) በጠርሴስም ሳለ በገማልያል እግር ሥር የኦሪት ትምህርቱን ተማረ፤ በትምህርቱም የተመሰከረለት ነበር፤ (የሐዋ.፳፪፥፫፤፳፮፥፳፬) ይህ የሚያሳየው የእግዚአብሔር መንግሥት ለተማሩትም ላልተማሩትም፣ ለባለጸጎችም ለድሆችም የተዘጋጀ መሆኑን ነው፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ ባለ ትዳር ነበር፡፡ አማቱም ታማ በነበር ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤቷ ገብቶ እንደፈወሳት በወንጌል ተጽፏል፡፡ (ማቴ.፰፥፲፬‐፲፭) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ድንግል ነበር፡፡ “ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሊሆን እወዳለሁና ነገር ግን፥ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ለራሱ የጸጋ ስጦታ አለው፥ አንዱ እንደዚህ ሁለተኛውም እንደዚያ፡፡ ላላገቡና ለመበለቶች ግን እላለሁ፡- እንደ እኔ ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው፤ ነገር ግን፥ በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና፥ ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ” በማለት ለቆሮንቶስ ምእመናን ጽፏል፡፡ (፩ኛቆሮ. ፯፥፯‐፱) ቤተ ክርስቲያን እንደ ጴጥሮስ ያገቡ እንደ ጳውሎስ ያሉ ደናግላንን ይዛ የምትገኘው ጌታችን ሁሉንም ወደ እርሱ ስለጠራ ነው፡፡

የስማቸው መለወጥ
ቅዱስ ጴጥሮስ የዮና ልጅ ስምዖን ተብሎ ይጠራ ነበር፡፡ (ዮሐ.፳፩፥፲፭) ነገር ግን ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን “እናንተስ ማን ትሉታላችሁ” ብሎ ሲጠይቃቸው ሐዋርያው ተነሣና፡- “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብሎ መለሰለት፡፡ ያን ጊዜም ጌታችን “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ፡፡ እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም አለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሏትም” በማለት ጴጥሮስ ብሎ ሰየመው፡፡ (ማቴ.፲፮፥፲፯—፲፰)

ጳውሎስን ደግሞ ጌታችን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጠራው በመጀመሪያ ስሙ ሳውል ብሎ ጠራው፤ በምስክርነቱ ጊዜ ደግሞ “ጳውሎስ ሆይ፥ በኢየሩሳሌም ስለ እኔ እንደ መሰከርህ እንዲሁ በሮሜም ትመሰክርልኝ ዘንድ ይገባሃልና፥ አይዞህ አለው፡፡” (የሐዋ.፳፫፥፲፩)

አገልግሎታቸው
የቅዱስ ጴጥሮስ አገልግሎቱ በአብዛኛው ሕግ ለተጻፈላቸው፣ ነቢያት ለተላኩላቸው፣ መሥዋዕት ለሚያቀርቡ፣ ግርዛት ለተሰጣቸው ለአይሁድ ነበር፡፡ በአንጻሩ ደግሞ የቅዱስ ጳውሎስ አገልግሎት የነበረው በአሕዛብ መካከል ነበር፡፡ ይህንንም ሲመሰክር “ለተገረዙት ሐዋርያ እንዲሆን ለጴጥሮስ የሠራለት፥ ለእኔ ደግሞ ለአሕዛብ ሐዋርያ እንድሆን ሠርቷልና፡፡” ብሏል፡፡ (ገላ.፪፥፯‐፰) እንዲያውም በአንድ ወቅት ጳውሎስና በርናባስን አይሁድ ትምህርታቸውን በተቃወሟቸው ጊዜ “እነሆ ወደ አሕዛብ ዘወር እንላለን እንዲሁ ጌታ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለማዳን ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ ብሎ አዞናልና” ብለው ነበር፡፡ (የሐዋ. ፲፫፥፵፮—፵፯)

በበዓለ ኀምሳ ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ከተቀበሉ በኋላ ጴጥሮስና ዮሐንስ በትምህርታቸው በኢየሩሳሌም ለነበሩ ነፍሳት ደረሱ፡፡ በአንድ ቀን ብቻ ሦስት ሺህ ነፍሳት ወደ ቤተ ክርስቲያን ተጨመሩ፡፡ (የሐዋ.፪) ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ “ከሁላችሁ ይልቅ በልሳኖች እናገራለሁና እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” በማለት ስለተሰጠው የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ መስክሯል፡፡ (፩ኛቆሮ. ፲፬፥፲፰) ሁለቱም ሐዋርያት በምእመናን ላይ እጃቸውን በመጫን ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ያሳድሩ ነበር፡፡ (የሐዋ.፰፥፲፬፤፲፱፥፭‐፮)

በአገልግሎታቸው ድንቅ ተአምራትን ፈጽመዋል፡፡ ለምሳሌ ስለ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፡፡ “እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር፤ ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር፥ ደዌያቸውም ይለቃቸው ነበር ክፉዎች መናፍስትም ይወጡ ነበር፡፡” (የሐዋ.፲፱፥፲፩—፲፪) በኢዮጴም ጣቢታ የምትባል አገልጋይን ከሞተች፤ አጥበውም በሰገነት ከአኖሯት በኋላ ቅዱስ ጴጥሮስ ካለበት ተጠርቶ ከጸለየ በኋላ ጣቢታ ሆይ ተነሽ ሲላት ዐይኖቿን እንደከፈተች ተጽፏል፡፡ (የሐዋ.፱፥፴፮—፵፪) በተመሳሳይ ቅዱስ ጳውሎስ አውጤኪስ የሚባል ከሦስተኛ ደርብ ወደ ታች ወድቆ የሞተን ጎልማሳ እንዲነሣ አድርጓል፡፡ (የሐዋ.፳፥፯—፲፪)

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

ኦፈ ጳልቃን :- ድንቅ ወፍ ስትሆን የፍቅር ትክክለኛዋ ገለጫ እላታለሁ
ይህች ወፍ ልጅ ትወልድና ልጆቿን የሚትመግበውን ስታጣ በወፍ የመግባቢያ ቋንቋቸው ሲያለቅሱባት የራሷን ሥጋ በአፏ ( በማንቁሯ ) እየቆረሰች ትመግባቸዋለች ( ምን አይነት ሀያል ፍቅር እንደሆነ ለመገመት ይከብዳል ! )
በዚያው ሥጋው የተቆረሰ የተገመሰ ፍጥረት ይቆስላልና ያኝ ተዳክመው እናታቸውን በመስለምለም, በመሞት ጻሕር ላይ የነበሩት የእናታቸውን ሥጋ በልተው ጠንክረው በጣም ስለሚወዷት የፍቅር መግለጫ ( እንደሚወዷት ለመናገር ፈልገው ) ቁስሏን ይነካኳታል ይወጉታል
በዚህ ጊዜ ምንም እናት ብትሆን ቁስል ሲነካ የሚያደርጉትን አያሳውቅምና ልክ ሲነኳት በአክናፏ ትመታቸዋለች እነርሱም ያልጠነከሩ ናቸውና ይሞታሉ
መሞታቸውን ስታውቅ አምርራ ታለቅሳለች  እናም እራሳንን እንደገና ታደማዉና በልጆቿ ላይ ደሟን ታፈስባቸዋለች ሞተው የነበሩት እንደገና ነፍስ ይዘራሉ
እናቲቱ ግን ከደሟ  ፍሰት የተነሳ ለዘልዓለም ታሸልባለች
ይህም ምሳሌ አለው
ዲያብሎስ ለ 5500 ቀጥቅጦ ሲገዛው ክርስቶስ እራሱን የዘልዓለም እንጀራ እኔ ነኝ ብሎ እራሱን ሰጠን ተወለደልን በአይን አይተው ጠገቡ ነገር ግን ፍቅሩ ያልገባን ሰቀልነው ደሙን አፍሶ የሞትን እኛ ላይ አፈሰሰ እርሱ ሞቶ እኛን አዳነን

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ምስለ ኖኅ
ኪዳነ ዘአቀምከ፤ ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ፤
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ ወሥነ
ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ወከመ
ወሬዛ ኃየል መላትሒሁ ጉርዔሁ መዓርዒር አምሳሉ
ዘወይጠል፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ሰማየ ወምድረ ዘአንተ
ፈጠርከ፤ ፀሐየ ወወርኀ ዘአስተዋደድከ፤ ወመኑ መሐሪ
ዘከማከ፤ በከዋክብት ሰማየ ዘከለልከ፤ ወመኑ መሐሪ
ዘከማከ፤ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ ወመኑ መሐሪ
ዘከማከ፤ ቀደሳ ወአክበራ አዕበያ ለሰንበት፤ ወአልዓላ
እምኵሉ ዕለት፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ወኵሉ ይሴፎ ኪያከ፤

#ትርጉም
ከኖኅ ጋር ቃል ኪዳን የገባህ እንዳንተ ይቅር ባይ ማነው
ለእስራኤል ልጆች መናን ያወረድክ፤ ምድርን በአበቦች
ያስጌጥክ፤ እንዳንተ ይቅር ባይ ማነው ? የምድረ በዳውን
አራዊት ከወዳጆችህ ጋር ያስማማህ እንዳንተ ያለ ይቅር ባይ
ማነው፤ ጉንጮቹ እንደ ዋልያ እንቦሳ ፈጣኖች ናቸው፤
አንደበቱ ጣፋጭ ነው፤ ተወዳጅነቱ እንደ ፌቆ ግልገል ነው፤
ሰማይና ምድርን የፈጠርክ፤ ፀሐይና ጨረቃን ያስማማህ፤
ሰማይን በከዋክብት የሸፈንክ፤ ምድርን በአበቦች ያሸበረቅህ፤
ሰንበትን ያከበርካት ከዕለታትም ለይተህ ከፍከፍያደረግኻት፤
አቤት!! እንዳንተ ይቅር ባይ ማንም የለምና ኹሉም አንተን
ተስፋ ያደርጋሉ።
#እንኳን_ለዓለም_ጌታ_ለፍጥረታት_አምላክ_ለነገስታት_ንጉስ_ልዑለ_ባህሪ_ለሆነው_ለአምላካችን_ለመድሐኒታችን_መድኃኒዓለም_ወርሀዊ_በዓል_አደረሰን !

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

#በከንቱ_አምተናታል

ዮሴፍ በጽኑ መረበሽ የተያዘበት ወቅት ነበር። የእመቤታችን መፀነስ ከሚያወቀው ተፈጥሯዊ አካሔድ ውጪ ስለሆነበት ልቡ ክፉኛ ተሸብሮ ነበር። በእርግጥ ዮሴፍ በእመቤታችን መፀነስ መደናገጡ ብዙም ላያስደንቅ ይችላል። መካን ሆነው ሳለ በልመናቸው ብርታት የወለዱ አሉ÷ እንደነ ሣራ በስተርጅናቸው የፀነሱም አሉ። የእርሷ ግን የተለየ ነው በድንግልና የወለደ ከእርሷ በፊትም ይሁን ከእርሷም በኋላ አልተገኘም።

መጻሕፍት እንደሚነግሩን ዮሴፍ ግን ከመደነቅ ይልቅ ከንግድ ሲመለስ ያገኘው ፈላስፋው ዮሐንስ "ይህቺ ሴት ካንተ ነው የፀነሰችው" ብሎ የተናገረው ቃል ከድንጋጤ አድርሶታል። በዚህም ምክንያት ነበር "መኑ ቀረጸ አክናፈ ድንግልናኪ" ብሎ የመፀነሷን ነገር የጠየቃት። ንጽሕት የሆነች እርሷ ግን "መልአኩ አክብሮ ከነገረኝ ውጪ ሌላ ምንም የማውቀው የለም አለችው" የእመቤታችን ትሕትና መግለጽ የሚቻለው አንደበት የለም ቃሏና ምላሿ ሁሉ በትሕትና የታሹ ናቸው።

ዮሴፍ አሁንም ቢሆን ከጥርጣሬው መዳን አልቻልም አንድ አንድ ጊዜ ፍርሐት እና የሰዎችን ወቀሳ ማስታወስ ወደ ጥርጣሬ አሮንቃ ውስጥ ይከተናል አረጋዊው ዮሴፍም የሆነው እንዲሁ ነው። ይህንን ጥርጣሬውን ልታስወግድለት የወደደች እመቤታችን ግን አአዕዋፍ እንዲራቡ የሚያደርግ አአዕዋም እንዲያፈሩ የሚያደርግ ማን ምስሎሃል? ብላ ከግሰጸችው በኋላ ከደጃቸው የቆመ ደረቅ ግንድ ነበር እርሱን አለምልማ አሳየችው። መልአኩ ትፀንሺያለሽ ብሎ ባበሠራት ወቅት ይህ እንዴት ይሆንልኛል ብትለው "ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም" ብሎ የመለሰላትና እርሷ በተግባር አሳየችው። በተረቱበት መርታት ልማድ ነው።

እመቤታን ያለውንድ ዘር በድንግልና የመጸነሷ ነገር ምትሐት ሳይሆን የእግዚአብሔር ሥራ መሆኑን ብትገልጥለትም። ለቆጠራ ወቅት ግን ይዟት ይወጣ ዘንድ ፈራ። ከእግዚአብሔር ሥራ ይልቅ ፍርሐታችንን እናምነዋለን በዚህም በተሳሳተ እምነታችን የእግዚአብሔር ዓላማ አደናቃፊዎች ሆነን እንገኛለን። ዮሴፍም ያለ ወንድ ዘር እንድትጸንስ ያደረገውን የእግዚአብሔርን ሐይል ሳያስተውል ይዟት ሲወጣ ግን አይሁዶች ሊፈጥሩት የሚችሉት ትንኮሳ አስፈራው።

ይዟት ቢወጣ ሕጋቸውን ቢያስቀራት ደግሞ ያደረገውን ዓውቆ ጥሏት ወጣ እንዳይሉ ወሪያቸውን ፈርቶ ሳለ መልአኩ ከያዘው ፍርሐት አርቆ ይዟት ይወጣ ዘንድ አዘዘው። ዮሴፍ በመልአኩ ትዕዛዝ ይዟት ቢወጣም የዲያቢሎስ የግብር ልጆች የሚሆኑ በትጠጣው ለሞት የሚያደርሳትን ማየ ዘለፋን ትጠጣልን አሉ። የአምላክ እናት እርሷ ግን ማየ ዘለፋን ከጠጣችው በኋላ እነርሱ እንዳሰቡት ሳይሆን ከወትሮው አበራች ጽድልት ሆና ታየች ከፀሐይ ይልቅ አብርታ ተገኘች በጊዜ የተቀሩት አይሁድም ይህን ቢመለከቱ "ይህችን ብላቴና በከንቱ አምተናታል" አሉ።

የእመቤታችንን ክብር ከመናገር እርቀው በከንቱ የሚያሙ ሰዎች የበቀሉት ገና በማኅጸን ሳለች ነው። መወለዷን የጠሉ ዳግመኛ የመውለዷን ነገር አለወደድዱምና በጊዜው ነውር እንደተገኘባቸው ሴቶች እርሷን በከንቱ አሟት። እውነት ደቆ ሐስት ረቆ ባየለበት በእኛ ዘመንም ዓይነ ልቦናቸው የታወረባቸው በከንቱ ያማሉ። የእግዚአብሔርን ሳይሆን የግብር አባታቸውን የዲያቢሎስን ድምፅ እየሰሙ በቅዱሳኑ ላይ በከንቱ ይናገራሉ። ከሁሉ ልቆ የታየው ግን የአይሁድ ከንቱ የሆነው ሐሜታቸው ሳይሆን ስለ ክፉ ፈንታ ክፉ ያለመለሰች የእመቤታችን ትሕትና ነበር።

ዲ/ን ሞገስ አብርሃም
          
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

የዘመኑ ምንኩስና ሕይወት ከቀደሙት ጋር ሲነጻጸር✝
  
           
Size:-76.8MB
Length:-1:22:58

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

ዋናው መሠረታዊ እውነት ይህ ነው፡- እውነተኛ ለውጥና ትንሳኤ የሚመጣው ቤተክርስቲያንን በመክስና በግላዊ የክለሳ አካሄድ ሳይሆን፣ በታማኝ አገልግሎትና የጋራ ሸክምን በመሸከም ነው።

፮. ሸክሙን መሸከም ወይስ ጣትን መቀሰር?
ቤተ ክርስቲያን ዛሬ የምትፈልገው ተጨማሪ ከሳሾችንና በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚተቹትን አይደለም፤ የምትፈልገው የሃቢብ ጊዮርጊስን ዓይነት መንፈስ የተላበሱ ልጆችን ነው። ችግሩን ከማራገብ ይልቅ የመፍትሔው አካል የሚሆኑትን፤ የቤተ ክርስቲያንን ሸክም በትከሻቸው ተሸክመው የክርስቶስን ሕግ የሚፈጽሙትን።

ስለዚህ፣ እያንዳንዱ የበሰለ ኦርቶዶክሳዊ አማኝ ራሱን ሊጠይቅ ይገባል፡- እኔ የቤተ ክርስቲያንን ሸክም አግዤ እየተሸከምኩ ነው? ወይስ በቁስሏ ላይ ጣቴን እየቀሰርኩ፣ የውግዘት ድንጋይ እየወረወርኩ ነው?

የዛሬው ጥሪ፣ ልክ እንደ ሃቢብ ጊዮርጊስ፣ ኃላፊነትን መውሰድ ነው። ይህ ደግሞ በፍቅር፣ በዲሲፕሊን፣ በትሕትናና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና እርሱ አካሉ በሆነችው ቤተ ክርስቲያኑ ላይ ባለ ጽኑ እምነት የሚከናወን የተቀደሰ ተግባር ነው።

©አቦርሃም ሲሳይ
        
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

#ሰኔ_21_እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ለሕንጸተ ቤተ ክርስቲያን ዘእግዝእትነ ማርያም እና ሰኔ ጐልጐታ እንኳን አደረሰን! የእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነቷ ረድኤቷ በረከቷ ጥበቃዋ አይለየን እመ ብዙኃን የብዙኃን እናት ድንግል ማርያም ሆይ ሳይነግሩሽ የሰውን ችግር ጭንቀት የምታውቂ እሩህሩህ እናት ነሽና የጎደለንን ሙይልን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለው አማላጅነትሽ ፍፁም ረድኤትሽ አይለየን፤ የቃል ኪዳን ሀገርሽን ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያን በምልጃሽ አስቢያት! አሜን፡፡

''በዕንቊ ሰንፔር ትትሐነጽ ወበመረግድ
ሃሌ ሉያ ለአብ ሐጹር የዓውዳ ትበርህ እምከዋክብት
ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ
ጽዮን ቅድስት ቤተ ክርስትያን ደብተራ ፍጽምት''
ዚቅ ዘቅዱስ ያሬድ

እንኳን ለእናታችን ለቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

እግዚአብሔር በሚያደርገው በጎ ነገር ሚካኤል ይታዘዛል✝
                         
Size 51.2MB
Length 55:18

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

 "+ እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ:- 'በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ:: እያበዛሁም አበዛሃለሁ' ብሎ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ በራሱ ማለ:: እንዲሁም እርሱ ከታገሠ በሁዋላ ተስፋውን አገኘ:: +"+

(ዕብ.6:13)

            
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

ሥርዓተ ማህሌት ዘ ሀምሌ ሥላሴ

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

ሀምሌ ➎ ጴጥሮስ ወ ጳውሎስ እንኳን አደረሳችሁ

➖ ሐምሌ ➎ ብርሃናተዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወ ቅዱስ ጳውሎስ የእረፍታቸው መታሰቢያ እለት ነው።

➖ ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌል በማሰፋፋቱ ምክንያት ታስሮ ከዚያም አንገቱን በስለት ተሰይፎ ሰማዕትነትን ተቀብሏል

➖ ቅዱስ ጴጥሮስ‹‹እንደ ክብር ንጉሥ እንደ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አቁማችሁ ሳይኾን፣ ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ›ብሎ በመስቀል ተዘቅዝቆ በመሰቀል በሮም አደባባይ ሰማዕትነትን ተቀብሏል።

በረከታቸው ይደርብን አሜን 🙏

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

እኔንም ያውቀኛል ማለት ነው🤔
...

ሁለት ጓደኛሞች ነበሩ፤ ገጽታቸው የሚለያዩ ጓደኞች፤ አንደኛው በመንፈሳዊ ሕይወቱ የበረታ የጠነከረ ፤ ዘወትር ቃለ እግዚአብሔርን የሚሰማ ቅዱሳት መጻሕፍትንም የሚያነብ ነበር፥ ጓደኛው ግን ኃጢአት ጀርባውን ያጎበጠችው ፤ ለእግዚአብሔር ጊዜ መስጠትን መለማመድ ያቃተው ሰው ነበር፤

በአንድ ወቅት በአቅራቢያቸው ባለች ቤተ ክርስቲያን አንድ ትልቅ ጉባኤ ተዘጋጀ፤ በጉባኤውም ትልቅ መምህር እንዲያስተምሩ ተጋብዘው ነበር፤ በመንፈሳዊ ሕይወቱ የበረታው ልጅ ይህን ሲመለከት ጓደኛውን እንደምንም ወትውቶና ይህ መምህር ይመጣል ተብሏል፤ ና እንሂድ እስኪ ጉባኤ እንሳተፍ ብሎ አሳምኖ ይዞት ይሄዳል፤

ጉባኤውን ይመራ የነበረው መርሐግብር መሪ ግን ለጉባኤው መክፈቻ መዝሙር ካዘመረ በኋላ፤ "ለዛሬ የጋበዝናቸው መምህር ሊገኙልን አልቻሉም፤" ብሎ ተነገረ፤ "ያው ግን በእግዚአብሔር ቤት በጉባኤ የተሰባሰብነው የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ስለሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ክፍል አውጥቼ ላንብብላችሁና ጉባኤያችንን እንፈጽማለን" አለ፤

በዚህ ጊዜ ሁሉም የሚነበበውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ለማዳመጥ ተዘጋጀ፤ መርሐግብር መሪውም ከማቴዎስ ወንጌል ይህን ክፍል አነበበ፤

"...
የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።
² አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤
³ ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስም ኤስሮምን ወለደ፤
⁴ ኤስሮምም አራምን ወለደ፤ አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤


¹⁵ ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛርም ማታንን ወለደ፤ ማታንም ያዕቆብን ወለደ፤
¹⁶ ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ።
... "


ይህን ካነበበ በኋላ ስለ ቃሉ የአምላካችን ስም የተመሰገነ ይሁን ብሎ በጸሎት አሳርገ፤

ይህ በሕይወቱ ብርቱ የሆነው ልጅ በመርሐ ግብር መሪው ደስተኛ አልሆነም፤ ይመጣሉ ብሎ ያሰባቸው መምህር መቅረት ሳያንስ ስንትና ስንት የሚነበብ የመጽሐፍ ቅዱስ ተግሳጽ ትምህርት እያለ እንዴት ይህን መርጦ ያነባል ብሎ ተናዷል፤ ሁሉንም አስቦ... ና እንማር ብሎ ጎትጉቶ ለምኖ ያመጣውን ጓደኛውን ፊት ማየት ከበደው፤ ጓደኛው ግን አንገቱን ደፍቶ ስቅስቅ ብሎ እያለቀሰ ነበር፤ ለምን ታለቅሳለህ ሲለው መልሱ ይህ ነበር፤

"... እነዚህ ሁሉ ሰዎች በእግዚአብሔር የታወቁና የታሰቡ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ያሉ ናቸው፤ በዚህ ቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሱት፤ እነዚህን ሁሉ እግዚአብሔር የሚያስታውስና የሚያውቅ ከሆነማ እኔንም ይስባል ያውቀኝማል ማለት ነው..."

የጓደኛው መልስ ከሁሉም ነገር በላይ አስደነቀው፤ ብርቱ ነኝ ብሎ የሚያስብ የራሱን ሕይወት እንዲመለከትም አደረገው፤

ወንድም እህቶቼ እመኑኝ እግዚአብሔር እያንዳንዳችንን ያውቀናል ፤ ያስበንማል፤ ዝም ያለ ቢመስለን እንኳ ለጊዜው ነው የምንከብርበት ጊዜ እስኪደርስ ድረስ ነው፤ በስኬት ላይ ስኬት ቢሰጠንም ሁሌም አብሮን እንዳለ ሲነግረን ነው፤

ጌታም ይላል...

ማቴዎስ 10
...
²⁹ ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም።
³⁰ የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቈጥሮአል።
³¹ እንግዲህ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች እናንተ ትበልጣላችሁ።



ሐምሌ ፪ - ፳፻፲፯ ዓ.ም
መነሻ ሐሳብ - በአንድ ወቅት ከተሰጠ ስብከት

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

ክሮስ ኘሮሞሽን መስራት እምትፈልጉ ከ 40k በላይ ፎሎወር ያላቹ ቻናሎል አድሚኖች በውስጥ አዋሩን ።

👉 @ZOSKALESSS

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

መጥምቁ ዮሐንስ እንዴት ተጠራጠረ?

ቅዱስ ማቴዎስ የዓሥራ ሁለቱን ደቀመዛሙርት ስም ዝርዝር እና ለማስተማር ወደ ዓለም እንደተላኩ ከገለጸ በኋላ ነበር የመጥምቁ ዮሐንስን ጥያቄ የሚያመጣው። ቅዱስ ሉቃስ ደግሞ ጌታ የአንዲት መበለት ልጅ ከሞት እንዳስነሣ ከተረከ በኋላ ከመጥምቁ ዮሐንስ ወደ ጌታችን ስለተላኩ መልእክተኞች ያወራል። በሉቃስ ወንጌል የአተራረክ ሒደት የጥያቄውን ቅድመ ነገር እንመልከት።

ጌታች ናይን ወደምትባል ሐገር ሄዶ ሳለ ብዙ ሰዎች ተከትለውት ሄዱ ከከተማው በር ሊገባ በቀረበ ጊዜ ያንዲት ድኃ ልጅ በቃሬዛ ተሸክመውት ሰዎች አገኘ። ጌታም እናትየዋን ባያት ጊዜ አዘነላት አታልቅሺ ብሎ ካረጋጋት በኋላ አንተ ጎበዝ ተነሥ እልሀለው አለው። ያም በድን ተነሥቶ ተቀመጠ አቃንቶም መናገር ቻለ። በቦታው የነበሩ ይህን የተመለከቱ ሁሉ ፈሩ ። አንድ አንዶቹም ታላቅ ነቢይ ተነሣልን እያሉ አመሰገኑ። ይህ ነገር ከተፈጸመበት ቦታ አልፎ በይሁዳ አውራጃ ሁሉ ተሰማ። የዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱም በጌታ የተደረገው እና በይሁዳ አውራጃ የተሰማውን ሁሉ ለመምህራቸው ነገሩት።

ቅዱስ ዮሐንስ በዚህ ወቅት በግዞት ቤት ታሥሮ ነበር። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገውን ተዓምራት ያስተማረውን ትምህርት የሠራውን ድንቅ ሥራ የሰማው በዚህ በግዞት ቤት ሳለ ነው። ይህን ድንቅ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ በኩል እንደሰማ ከደቀመዛሙርቱ ሁለቱን ላከ እነዚህም አካውህ እና እስጢፋኖስ ይባላሉ። እነርሱም ወደ ጌታችን ሔደው ትመጣለህ ብለን ተስፋ የምናደርግህ አንተ ነህ? ወይም ይመጣል ብለን ተስፋ የምናደርገው ሌላ አለን? ብለው ጠየቁት።

እናስተውል ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል ብሎ የመሰከረው ቅዱስ ዮሐንስ እንዴት ሊጠራጠር ቻለ? በእሳትና በመንፈስ ያጠምቃቹሀል ብሎ ተናግሮ ሳለ ይህን የጥርጣሬ ቃል እንዴት ሊያነሳ ቻል?

መተርጉማን ለዚህ ምላሽ ይሰጣሉ። ራሱም የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው፥ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሀ ማር ነበረ ተብሎ የተነገረለት ቅዱስ ዮሐንስ ይሄንን ጥያቄ መጠየቁ እርሱ ተጠራጥሩ አይደለም ይልቁንም ደቀ መዛሙርቱ ተጠራጥረው ነበርና አይተው አምላክነቱን ይረዱት ዘንድ ብሎ እርሱ ስለደቀዛሙርቱ ጥርጣሬ ጠየቀ።

በርግጥ በጌታችን እጅግ በሚያስገርሙ ቃላቶች
ምስክርነት የተሰጠው መጥምቁ ዮሐንስ መናኒ እንደመሆኑ በጾም በጸሎት ይህ ምሥጢር
ሊገለጥለት የሚችል ጻድቅ ነው። ለዚህም ነው ስለ እነርሱ ጥርጣሬ እርሱ ጠየቀ የሚለውን ትርጉም እንድንቀበል ይበልጥ የሚገፋፋን። ስለ ተማሪዎቹ የልብ ጥርጣሪ የተረዳውን የሚጠይቅ መምህር።

ዲ/ን ሞገስ አብርሃም

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

#ወንድማችንን ፍቱት

ሊቀ ትጉኅን ደረጀ ነጋሽ (ዘወይንዬ) ዛሬ ከግል ቢሮአቸዉ ወጥተዉ ወደ ተሽከርካሪያቸዉ ሲያመሩ ለጥያቄ እንፈልግዎታለን ተብለዉ ደህንነት ነን ባሉ አካላት መወሰዳቸዉን ከቤተሰቦቻቸዉና ከሥራ ባልደረቦቻቸው ከሰማን ቀናት አለፊ ።

ይሁን እንጂ መምህር ደረጀ ነጋሽ እስከ አሁን ያሉበትን ፖሊስ ጣቢያ ለማወቅ አልታቻለም።
             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

ሃቢብ ጊዮርጊስ ግን ቤተ ክርስቲያንን አልከሰሰም፤ ሸክሟን ተሸከመ እንጂ።

፩. የዘመኑ ታሪካዊ ቀውስና የቤተ ክርስቲያን ፈተና

በዐሥራ ዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃና በሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን መባቻ ላይ፣ የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ እጅግ ውስብስብ ከሆኑት ፈተናዎች እያስተናገደች ነበር። ቀውሱ የውጭ ጫና ብቻ ሳይሆን፣ ከውስጥ የመነጨና የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕልውና የሚፈታተን ነበር። ይህ ድክመት በአስተዳደር መላሸቅ፣ በመልካም አስተዳደር እጦት፣ በሙስናና በአንዳንድ አገልጋዮች የሥነ ምግባር ውድቀት ተገልጧል። ከዚህም በላይ፣ የትምህርተ ሃይማኖት ዕውቀት በእጅጉ ተዳክሞ፣ የመንፈሳዊ አገልግሎት ጥራትና ስፋት በእጅጉ ቀንሶ ነበር።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ፣ የዚያን ዘመን አሳሳቢ ገጽታ ሲመሰክሩ እንዲህ በማለት ሁኔታውን ያጠቃልሉታል፡-

“በሃያኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ፣ ስብከቶች ደረቅና ሕይወት አልባ ነበሩ፤ መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች ከሞላ ጎደል አልነበሩም፤ ድንቁርና በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ፣ እንዲያውም በቀሳውስቱ መካከል እንኳ ሰፍኖ ነበር።”

ይህ ምስክርነት እንደሚያሳየው፣ ችግሩ የገጸ-ድካም ጉዳይ አልነበረም። ይልቁንም፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሐዋርያዊ ተልዕኮና የአደረጃጀት መሠረት ያናጋ፣ ብዙዎችን ተስፋ ሊያስቆርጥና ለዓመፅ ወይም ለመለያየት ሊዳርግ የሚችል ጥልቅ መንፈሳዊና መዋቅራዊ ቀውስ ነበር። እንዲህ ባለ ከባድ ወቅት፣ የአንድ አማኝ ቤተ ክርስቲያናዊ ንቃተ ህሊና (ecclesiological consciousness) እና ታማኝነት በእጅጉ ይፈተናል።

፪. የዲያቆን ሃቢብ ጊዮርጊስ መነሣትና የመስዋዕትነት መንገድ
በዚህ መንፈሳዊ ጨለማ ውስጥ ነበር ሃቢብ ጊዮርጊስ የተባለው የብርሃን ሰው የተነሳው። እርሱ በቤተ ክርስቲያን ያደገና ዲያቆን እንደመሆኑ፣ የችግሮቹን ስፋትና ጥልቀት ከውስጥ ሆኖ ተመልክቷል። የቤተ ክርስቲያኒቱን የአስተዳደር ድክመት፣ የአገልጋዮቿን የዕውቀት ማነስና የሕዝቡን መንፈሳዊ ጥማት ተገንዝቧል። ነገር ግን፣ እንደ ብዙዎቹ፣ ጣቱን ለመቀሰር፣ ለማሳጣትና ለማጣጣል፣ የውግዘት ድምፅን ለማሰማት ወይንም በራሱ አካሄድ የቤተክርስቲያኒቷን አካሄድ ልከልስ ማለትን አልመረጠም። ይልቁንም፣ በታማኝ አገልግሎትና ሸክምን በመሸከም ለችግሩ ተግባራዊ ምላሽ ሰጠ። መንገዱ የክስ ሳይሆን የመስዋዕትነት ነበር፤ ይህም በገላትያ 6፡2 ላይ ያለውን “የአንዱን ሸክም አንዱ ይሸከም፣ እንዲሁም የክርስቶስን ሕግ ፈጽሙ” የሚለውን ሐዋርያዊ ትዕዛዝ ሕያው ምስክርነት ነው።

ገና ከወጣትነቱ ጀምሮ ለትምህርት በነበረው ጥልቅ ፍቅር፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀጣይ ትውልድ የማነጽ ኃላፊነት በራሱ ላይ ጫነ። የሰንበት ትምህርት ቤቶችን ንቅናቄ በመላ ሀገሪቱ በማደራጀት፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕፃናትና ወጣቶች የኦርቶዶክሳዊት እምነታቸውን እንዲያውቁና እንዲኖሩባት መሠረት ጣለ። በካይሮ ሥነ-መለኮታዊ ኮሌጅ ውስጥ በአካዳሚክ ዲንነትና በመምህርነት ሲያገለግል፣ ዕውቀትና መንፈሳዊነት የተዋሐደላቸውን አገልጋዮች አፈራ። ድርጊቱ ሁሉ ይመነጭ የነበረው፣ ቤተ ክርስቲያንን በአስተዳደራዊ ድክመቶቿ ውስጥ እያየ እንኳ፣ የማይነቀንቅ የክርስቶስ አካልና የድኅነት ታቦት መሆኗን ካመነበት ጥልቅ ሥነ-መለኮታዊ እምነት ነበር።

ለዚህም ነው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ፣ የአንድን ሰው ታማኝ አገልግሎት ፍሬያማነት ሲመሰክሩ፣ እንዲህ ያሉት፡-

“የሰንበት ትምህርት ቤት ንቅናቄ ከሃቢብ ጊዮርጊስ በቀር ሌላ ፍሬ ባያፈራ ኖሮ እንኳ፣ እርሱ ብቻ በቂ ነበር።”

፫. የመዋቅር ድክመትን ከሃይማኖት ስህተት መለየት
የሃቢብ ጊዮርጊስ ጥበብና ሥነ-መለኮታዊ ልሕቀት ከሁሉ በላይ የሚገለጠው፣ በዘመኑ የነበረውን የመዋቅር ድክመት ከቤተ ክርስቲያን ንጽሕተ ሃይማኖት ጋር ባለማደባለቁ ነው። ቤተ ክርስቲያን በትምህርተ መለኮቷ ኑፋቄን ታስተምራለች ብሎ አንድም ቀን አልከሰሰም። ሥርዓቷን አላጣጣለም፤ ቀኖናዎቿንና ይትባሕሎቿን "ካልከለስኩ" አላለም። ችግሩ ያለው በሐዋርያት በኩል በተሰጠችው የቀናች እምነት ላይ ሳይሆን፣ ያችን እምነት በሚያገለግሉና በሚያስተዳድሩ ሰዎች ላይ በሚታየው ድካም እንደሆነ በሚገባ ተረድቶ ነበር።
ይህ መረዳት፣ ቤተ ክርስቲያን መለኮታዊ-ሰብዓዊ (Theanthropic) ተቋም መሆኗን ከመቀበል ይመነጫል።

እርሷ፣ እንደ ክርስቶስ አካል፣ በመለኮታዊ ተፈጥሮዋ ቅድስት፣ ፍጽምትና ከስህተት የጸዳች ናት፤ ነገር ግን በውስጧ የሚያገለግሉት ሰዎች የሰብዓዊ ድካም ተገዢዎች ናቸው። ቅዱሳን አባቶች ይህንን ልዩነት በሚገባ አስተምረዋል። ለምሳሌ፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የክህነትን ቅድስናና የአገልጋዩን ግላዊ ድካም ሲለይ፣ የክህነቱ ኃይል የሚመነጨው ከሰውየው ማንነት ሳይሆን ከክርስቶስ ሹመት መሆኑን ያስረዳል። ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያም ንስጥሮስን የታገለው፣ የአንጾኪያን ቤተ ክርስቲያን መዋቅር ለመናድ ሳይሆን የተሳሳተውን የሃይማኖት ትምህርት ለማረም ነበር።

ስለሆነም፣ የሃቢብ ጊዮርጊስ መፍትሔ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ አዲስ ሥርዓት መመሥረት ሳይሆን፣ በውስጧ በመሆን፣ በትሕትናና በመታዘዝ፣ ያንን ሰብዓዊ ድካም መፈወስና ማነጽ ነበር። ሥራው ሁሉ የሚያሳየው ይህንን ነው፡- በገዛ አረዳዱ "የተበላሸውን" ብሎ የገመተውን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ለማረም አልሞከረም፤ ይልቁንም ያንን ያልተበረዘ ትምህርት ለተራበው ሕዝብ ለማድረስ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።

፬. ትምህርቱ ለዛሬው ትውልድ፡- የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ተዛምዶ

ይህ የታሪክ ትምህርት በዘመናችን ላለችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥልቅና አስቸኳይ መልእክት አለው። ዛሬ በርካታ ምእመናን በአስተዳደራዊ ብልሽቶች፣ በመንፈሳዊ አመራር ድክመትና በአንዳንድ አገልጋዮች ሥነ ምግባር ጉድለት የተነሣ በብስጭትና በቅሬታ ተሞልተዋል። ይህ ስሜት መነሻው ቅን ሊሆን ይችላል።

ችግሩ ያለው ለዚህ ስሜት በሚሰጠው ምላሽ ላይ ነው። ብዙዎች፣ ልክ በሃቢብ ጊዮርጊስ ዘመን እንደነበሩት ተቺዎች፣ መላዋን ቤተ ክርስቲያንን ይወቅሳሉ፤ ሐዋርያዊ ትውፊቷን ይጠራጠራሉ፤ አልፎ ተርፎም በግል አስተያየታቸውና ፍልስፍናቸው ያንን ትውፊት ለመተካት ይዳዳሉ። ከዚህም የከፋው፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ትይዩ መዋቅሮችንና ርዕዮተ ዓለሞችን ለመገንባት መሞከር ነው፤ ይህም አንድነቷንና ሐዋርያዊ ሥርዓቷን በእጅጉ ይጎዳል። ይህ አካሄድ፣ የቅዱስ ኢግናጥዮስ ዘአንጾኪያ "ከኤጲስ ቆጶሱ ውጭ ምንም ነገር አታድርጉ" የሚለውን ሐዋርያዊ መመሪያ የሚጻረር ነው።

፭. ኦርቶዶክሳዊው የማነጽ መንገድ፡-
ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ቤተ ክርስቲያንን የምትረዳበትና የማነጽ አካሄዷ ግልጽ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን 4፡11–13 ላይ፣ ክርስቶስ ራሱ ለቤተ ክርስቲያኑ "ሐዋርያትንና ነቢያትን፣ ወንጌላውያንንም፣ እረኞችንና አስተማሪዎችንም" የሰጠው፣ "ቅዱሳን … ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ፣ ለክርስቶስም አካል ሕንጻ" እንደሆነ ያስረዳል። መዋቅርና ሥርዓት የተሰጠው ለማነጽ እንጂ ለመበታተን አይደለም።

የማረምና የማነጽ ሥራ እንዴት መከናወን እንዳለበትም መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስቀምጣል። በይሁዳ መልእክት 1፡22 ላይ "አንዳንዶችንም በምትለዩበት ጊዜ፣ ምሕረት አድርጉላቸው፤ ሌሎችን ግን ከእሳት እየነጠቃችሁ በፍርሃት አድኗቸው" ይላል። ይህ ቃል፣ ችግሮችን የምንቀርብበት መንገድ በጥበብና በልዩነት መሆን እንዳለበት ያስተምራል እንጂ ሁሉን በአንድ ላይ የመውቀስ አካሄድን አይደግፍም።

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

++ሐራሩኤል ጭርዋቅ++

ጥበብን የለበሳት ጠቢብ ሰሎሞን ለራሱ ሐራሩኤል ጭርዋቅ የሚል ስመ አምላክ የሰፈረበት ቀለበት ነበረው። ትእምርተ መንግሥቱ ግርማ ሞገሱ እሱ ነው ከሴት ሲደርስ አንበሳ መደብ ሲወጣ ቀለበቱን አውልቆ ከዙፋኑ ላይ ያኖረው ነበር። በአንድ ወቅት አንበሳ መደብ ደርሱ ሲመጣ ሰይጣን ለምቀኝነት አያርፍምና ቀለበቱን ከዙፋኑ ማንሳት ባይቻለው ከነዙፋኑ ጠቅሎ ባሕር ላይ ጣለው ሰሎሞን ሲመለስ ዙፋን ቤቱ ከለከለው የንግሥናውን ምልክት ግርማ ሞገሱን አጥቷልና ጎስቋላ ሆነ። ከዚህ በኋላ በገዛ ከተማው ሁለት ሳምንት ለምኗል ሰይጣን የሰው ልቡና አጽንቶበት የሚሰጠው አጥቶ ከመሠግራነ ዓሳ ሄዶ ስመ እግዚአብሔር ጠራባቸው ከመሀከላቸው አንዱም ይህ ዘብዛባ ብሎ የሞተ አሳ ጣለለት ሆድ እቃውን አውጥቶ ለመመገብ ቢቀደው ቀለበቱን አገኘ ቀለበቱን እንዳገኘ ግርማ ሞገሱ ከነክብሩ ተመለሰለት። በሰይጣን የተነጠቀው መንግሥቱ ተመለሰ ብዙዎቹም ሰሎሞን መሆነን ሲያውቁ ንጉሥን ከዚህ ምን አመጣው ብለው ከበቡት ቡሀላም መርበበተ ሰሎሞን የሚባል ስመ አምላክ አትሞ ቀብሮታል።ሰሎሞንን እዚህ ያደረሰው ምንድነው ቢሉ ከዕለታት በአንዳቸው የተራበ ሰው ስመ እግዚአብሔር እየጠራ ሲለምነው ይህ ሰው ምን ሆኗል አለ ተርቦ ነው ቢሉት ረኀብ ምንድነው ብሎ ነበርና የረኀብን ጽናት ሊያሳየው ይህ ተፈጸመበት።>>{ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ}

👇👇👇👇👇

የሰሎሞን መንግሥት እና ንግሥና በቀለበት ምክንያት እንደተመለስ በአዳም የሄድ አንድም ያጣነው ልጅነት እንደ ቃልህ ይደረግልኝ በሚለው የእምነት ቃሏ በእርሷ ተመልሱልናልና መርበብት ሰሎሞን ተብሎ የታተመበት ሐሩራኤል ጭርዋቅ የሚል ስመ አምላክ የተጻፈባት የሰሎሞን ቀለበት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት እንላለን።

የሰው ልጅ በጥንት መርገም ተይዞ በነበረበት ዘመን በንጽህናና በቅድስና አጊጣ በምክረ ከይሲ በአዳም ስህተት ያጣነውን ልጅነት ያገኘንባት ለእርሷ ለሰው እንዲረዳ መሰልንላት አንጂ ከሰሎሞን ቀለበት በብዙ ትልቃለች።

በረከቷ ምልጃዋና ጸሎቷ አይለየን

ዲ/ን ሞገስ አብረሃም

ሰኔ 23 የንጉሥ ዳዊት ልጅ ጠቢቡ ሰለሞን ያረፈበት ቀን ነው ::
             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

ደስታ ምንድንው?✝
  
           
Size:-66.5MB
Length:-1:11:51

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

"ኦ ሚካኤል ኦ መተንብል፣ ካህነ አርያም ትሰመይ ቢጸ ሱራፌል፣ ዘእምርዑሳን ርዑስ ወዘእምልዑላን ልዑል፣ ጊዜ ጸዋዕኩከ ቅረበኒ በምሕረት ወሣህል፡፡"

"አማላጃችን ሚካኤል ሆይ ፈጥኖ ደራሻችን ሚካኤል ሆይ የጌታን ዙፋን ከሚያጥኑ ሱራፌል ካህናት አንዱ ሰማያዊ ካህን አንተ ነህ እኮን። የሰማያውያን ሊቃነ መላእክት ሁሉ አንተ አለቃቸው ነህ እኮን። ይልቁንም የልዑላንም ልዑል አንተ ነህና በጠራሁህ ጊዜ ሁሉ በይቅርታና በቸርነት ድረስልኝ አትራቀኝ።"

(መልክአ ሚካኤል)

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

በዓለ ቅዱስ ሚካኤል

እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል በዓል አደረሳችሁ!

ሚካኤል ማለት ‹‹መኑ ከመ አምላክ (እግዚአብሔር)፤ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው›› ማለት ነው፡፡ ይህም የእግዚአብሔርን ገናንነትና እርሱን የሚመስል አምላክ እንደሌለ፣ እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ፣ ርኀሩኅ፣ ኃያልና ረቂቅ ማንም እንደሌለ የሚያመለክት ነው፡፡

ቅዱስ ሚካኤል ሌሎች መጠሪያዎች አሉት፤ እነዚህም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠውን የባለሟልነት ክብር የሚገልጹ ናቸው፡፡ እነርሱም ‹‹መልአከ ኃይል፣ መጋቤ ብሉይ፣ መልአከ ምክሩ፣…›› ናቸው፡፡ መልአከ ኃይል የተባለው እግዚአብሔር በእርሱ አማካይነት ታላላቅ ሥራዎችን በመሥራት ኃይሉን ስለገለጸና ዲያብሎስን ከነሠራዊቱ ስላሸነፈ ነው፡፡

መጋቤ ብሉይ የተባለበት ምክንያት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከእግዚአብሔር እየተላከ ብዙ ታላላቅ ሥራዎችን የሠራ በመሆኑ ነው፡፡ መልአከ ምክር ወይም የእግዚአብሔር የምክሩ አበጋዝ የተባለበት ምክንያት እግዚአብሔርን በምክሩ ይረዳዋል ለማለት ሳይሆን እግዚአብሔር የሚሠራውን ሥራ ለወዳጁ ለቅዱስ ሚካኤል ይገልጽለታልና በእርሱ አማካኝነት ይሠራል ለማለት ነው፡፡

ቅዱስ ሚካኤል በዚህ ሁሉ ልዕልና ላይ ትሕትናን ደርቦ የያዘ፣ በጸሎቱ ተማጽኖና በተራዳኢነት አምኖ ለሚለምነው ሁሉ ፈጥኖ በመድረስ ከሠራዊተ አጋንንት ተንኰል የሚያድን መልአክ እንደሆነ በቅዱስ መጽሐፍ ተጠቅሶ እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ ሙሴንና እስራኤልን በሲና በረሃ (ዘፀ.፳፫÷፳-፳፪)፤ (ዘፀ.፲፬÷፲፭-፳) ኢያሱን በኢያሪኮ (ኢያ.፭÷፲፫-፲፭)፤ ከአሞራውያንም እጅ ሕዝቅያስን እንደረዳቸው ተጽፏል፡፡ (ኢሳ.፴፯÷፴፮) በትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ፲ ቁጥር ፲፫ ላይ ‹‹የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሃያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ እነሆም ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ›› በማለት የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት ተገልጿል፡፡ በዚሁ የመጽሐፍ ክፍል ምዕራፍ ፲፪ ቁጥር ፩ ላይ ‹‹በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል›› በማለት ታላቅነቱን፣ ለሰው ልጆች ሁሉ በአማላጅነቱና በተራዳኢነት የሚቆም እንደሆነ በማያሻማ ቃል ተገልጿል፡፡

በአጠቃላይ በኦሪት የእግዚአብሔር መልአክ እየተባለ የሚጠራው አብዛኛውን ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ያስተምራሉ፤ በድርሳነ ሚካኤልም ተጽፎ ይገኛል፡፡ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ያልረዳው ቅዱስ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ በዘመነ ሰመዕታትም ሰማዕታትን በተጋድሎ ያጸናቸው ይህ ሩኅሩኅ መላክ እንደሆነ በእነ ቅዱስ ፋሲለደስ እንዲሁም በእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገድላት ላይ በሰፊው ተገልጿል፡፡
የቤተ ክርስቲያን አባቶች በየወሩ በ፲፪ ቀን መታሰቢያውን እንድናደርግ አዘውናል፡፡ ይህንንም ያልቻለ በዓመት አራት ዓበይት በዓላትን ከቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ጀምሮ እንደተቻለ ማዝከር ይገባል፡፡ እነዚህም ኅዳር ፲፪ ቀን ቀጥሎ ሰኔ ፲፪ ቀን ከዚያም ነሐሴ ፲፪ ቀንና ታኅሣሥ ፲፪ ቀን ናቸው፡፡

ሰኔ ፲፪፡- በቅዳሴያችን ‹‹ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል፤ ለሚካኤል ምሕረት (ይቅርታ ርኀራኄ) ተሰጠው እንላለን፤ ነቢዩ ሄኖክም ምሕረት ለሚካኤል መሰጠቱን ገልጿል፤ ትሕትናውን ታዛዥነቱን አስረድቷል፡፡ (ሄኖ.፮÷፭፣፲÷፲፪)

የሰማያውያን ሠራዊት አለቃ፣ ለሰው ሁሉ የሚራራና ስለ ሰው ልጆች ሳያቋርጥ ወደ ፈጣሪው የሚለምን፣ ርኀሩኀና ትሑት የሆነው ኃያሉ ቅዱስ ሚካኤል ባሕራንን ከሞት ያዳነበት፣ የሞቱን ደብዳቤ ወደ ሕይወት የቀየረበት የመታሰቢያው ዕለት ነው፡፡


             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…
Subscribe to a channel