ortodoxtewahedoo | Unsorted

Telegram-канал ortodoxtewahedoo - ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

3754

ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ። ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ›› ት.ኢሳ 58÷3 https://youtu.be/csxxAMGtC4I ለመቀላቀል http://t.me/ortodoxtewahedo

Subscribe to a channel

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

እናት አለኝ

እናት አለኝ የምታብስ እንባ
አያታለው ስወጣ ስገባ
ኪዳነ ምህረት /3/ አንባ መጠጊያ ናት

ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ
እራቆቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደ እኔ ቀርበሻል
ደጓ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል

ኪዳነ ምህረት /3/ አንባ መጠጊያ ናት/

አዝ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

ለዘላለም ንጽህይት በመሆኗ
ከኔ ጋር ነው ህያው ቃልኪዳኗ
ደስተኛ ነኝ ሀዘኔን አልፌ
አጽናኝ ሆናኝ የመስቀል ስር ትርፌ

ኪዳነ ምህረት /3/ አንባ መጠጊያ ናት/

አዝ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

ከጥፋቱ ውሀ ማረፊያዬ
መርከቤ ነሽ ከሞት ማምለጫዬ
የአምላክ እናት ምልጃሽ ሆኖኝ ክብሬ በህይወት አለው ጥልቁን ተሻግሬ

ኪዳነ ምህረት /3/ አንባ መጠጊያ ናት/

አዝ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

በእናትነት ህይወቴን ጎብኝታ
ልቤ አረፈ ተነቅሎ በሽታ
ሰንሰለቴ ከእጄ ተቆረጠ
መራራዬ በልጅሽ ጣፈጠ



ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ኪዳነ ምህረት | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ



ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

✤ ኪዳነ ምህረት

ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ደጅ_ጠናሁ

ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምህረትን
ተፅናናሁኝ ረሳሁ ሀዘኔን
የአምላክ እናት እመቤታችንን
ሞገስ ሁኚኝ ቀሪው ዘመኔን

የመከራው ዘመን አለፈ እንደዋዛ
አንቺን ተጠግቼ የአለሟን ቤዛ
የልጅሽ ቸርነት የአንቺ ደግነት
ባርያሽን ሰውሪኝ ከአስጨናቂው ሞት
እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያሁሉ መከራ
እምባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ በአንቺ እየታበሰ ሰላም ለኪ

#አዝ

ልቤ ባንቺ ፀና ከፍ ከፍም አለ
በጠላቶቼ ላይ አፌ ተናገረ
በማዳንሽ ስራ ባሪያሽ ደስ ብሎኛል
የኃያላኑን ቀስት ልጅሽ ሰብሮልኛል
እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያሁሉ መከራ
እምባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ ባንቺ የታበሰ ሰላም ለኪ

#አዝ

እጄ ባዶ ሲሆን ወዳጆቼም ሸሹኝ
በመርገም ምክራቸው ሊለያዩን ሲሹ
እርሱ የሰጠኝን እሱ ወሰደ አልኳቸው
እመቤቴ አለችኝ ብዬ አሳፈርኳቸው
እናቴ ስምሽን ሰጠራ አለፈ ያሁሉ መከራ
እምባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ በአንቺ እየታበሰ ሰላም ለኪ

#አዝ

በአውደ ምሕረቱ ሆኜ ስጠራት
ዘንበል ብላ አየችን ኪዳነ ምህረት
ሀሳብሽን ምንም የለም የሚመስለው
እረፍት ያገኘሁት እናቴ ባንቺ ነው
እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያሁሉ መከራ
እምባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ ባንቺ እየታበሰ ሰላም ለኪ



ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Weyeneyshet, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Girma, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Emito, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Nafi, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello kasech, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ጾመ ነቢያት (Nativity Fast) - ኪዳን ዘኢየሱስ እንደከተበው

ቤተ ክርስቲያናችን ከጌታ ልደት በፊት ያሉትን 40 ቀናት በጾም እንድናሳልፍ ታዘናለች። ይኽም ሙሴ አሠርቱ ቃላትን ለመቀበል በሲና ተራራ የጾመውን 40 ቀናት ይወክልልናል። ሙሴ አሠርቱ ቃላትን ለመቀበል 40 ቀናት እንደ ጾመ እኛም ደግሞ የአካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋዌ (Incarnation of the Logos) ለመቀበል እንዲሁ #40_ቀናትን እንጾማለን።

የአዳም መድኃኒት፥ የነቢያት ትንቢታቸው "እጅኽን ከአርያም ላክ ናና አድነን" እያሉ የለመኑት፥ የ5500 ዓመት ተስፋቸው፥ ለሙሴ የመጀመርያ ስሙን በየውጣ የነገረው (የውጣ ማለት Iota ከሚለው የግሪክ እና ኮፕቲች ፊደል የመጣ ነው በኮፕቲክ አሥር የሚለው ቃል በIota ፊደል ይጀምራል፥ ኢየሱስ የሚለው ስምም በግሪክም በኮፕቲክ በIota ፊደል ይጀምራል። ስለዚህ Iota , the name of salvation of our Lord የጌታ የማዳኑ ስም ተብሏል። (ውዳሴ ማርያም ዘእሑድ) ሙሴ አሠርቱ ቃላትን እንደተቀበለ አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና)፥ የኢያሱ ስሙ ኃይል (ኢያሱ እና ኢየሱስ ማለት ትርጉሙ አንድ ሲኾን ያህዌ ያድን ማለት ነው፥ መድኃኒት ተብሎም ይተረጎማል)፥ የኤልያስ መሶበ ወርቅ ውስጥ ያለ መናበዳዊት ዙፋን ለዘላለም የሚነግሥ የንግሥናው ፈጻሚ፥ የሰሎሞን ጥበብ "ጥበብሰ መድኃኒነ ውእቱ - ጥበብስ መድኃኒታችን ነው" (ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ) የተባለለት፥ የነቢያት ትንቢት ኹሉ ፈጻሚ፥ አዳኙ፥ አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ሊወለድ ነውና የተስፋውን ቀን በመጠባበቅ እኛም ከነቢያት ጋር እንጾማለን።

"የበዓል ቀን ሊመጣ ነው። እርሱም ከኹሉም በዓላት በላይ እጅግ የተቀደሰ እና ያማረ ነው፥ የተቀደሱ ቀናት ኹሉ አለቃ እና እናት ብለን ብንጠራው ስህተት አይኾንም። ይሄም በዓል #የክርስቶስ_ልደት ቀን ነው።" — ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

እሑድ ኅዳር 15 ይገባልና ለነቢያት ጾም እንኳን አደረሳችኹ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

የገና ጾም(ጾመ ነብያት)
ህዳር 15 /2017 ዓ.ም ይገባል

~ ጾመ ነቢያት እስከ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ የሚጾም እና ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንደኛው ጾም ነው። እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ፤ ወደ ግብፅ መሰደዱ፤ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ እና ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለመቀበሉ በየዘመናቱ የተነሱ ነቢያት በመንፈስቅዱስ ተቀኝተው ትንቢት ተናግረዋል።
~ ትንቢቱም ደርሶ ተፈጽሞ ለመመልከት "አንሥእ ኃይልከ ፈኑ እዴከ" ኃይልህን አንሣ እጅህን ላክ እያሉ በጾም በፀሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚሆንበትን ጊዜ በቀናት፤ በሳምንት፤ በወራትና በአመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል። ይህ ጾም የእግዚአብሔርን ሰው መሆን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመሆኑ "ጾመ ነብያት" እየተባለ ይጠራል።

የበረከት ጾም ያድርግልን።

ጾመ ነቢያት (የገና ጾም)
ነገ ኅዳር 15/2017 ዓ.ም
(Nov 24/2024 G.C) ይገባል፡፡
#kidanmedia ኪዳን ሚዲያ

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Amen enkewan abro adersen

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Price 60x120 cm 3500 birr
           60x90 cm : 2500 birr
           50x80 cm : 1900 birr
          40x60cm : 1500 birr
          30x45 cm  : 950 birr
Delivery fee: 200

👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
    @GraceWallArt   
@hani_nata

0703958003
0715328414
0936239392
0943448637
Join more our work
@grace_wallart

👌 ምርጫዎ ስለሆንን እናመሠግናለን

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ማርያምን የሚወድ ካለ ባዮ ላይ ያለውን chanal join በሉልኝ ፈልጌው ነው

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Haymi, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ኪዳነ ምህረት እንወድሻለን

ለግዚአብሔር ታቦቱ መቅደሱ
ቀርበናል ባንቺ ወደ ንጉሱ
የክብራችን ጌጥ ሽልማት
እንወድሻለን ኪዳነምህት

በጨለማው ላለ ብርሃንን አየ
ለርስቱ ተካፋይ እንዲሆን ተለየ
ወደ ቀድሞ ክብሩ ሊመለስ ዳግመኛ
አንቺ ነበርሽ ተስፍው ለአዳም መዳኛ

አዝ===========
ያንን ሁሉ ዘመናት የፈሰሰው ደም
አለምን ከእስራት ሊፈታ አልቻለም
ወደ ሚሻል ኪዳን በደም ሊያሻግረን
ደምሽን ተዋህዶ መዳኃኒ አለም ዋጀን

አዝ===========
አለን ብዙ ምክንያት አንቺን ምንወድበት
ዓለም ያልተረዳው ያላወቀው እውነት
ያወቀ የተረዳ የመዳኑን ሚስጢር
አያፍርም ክብርሽን ቆሞ ለመናገር

አዝ===========
አውቃለሁ እግዚአብሔር የሰጠሽን ክብር
ላመስግንሽ እኔም ሳልጨምር ሳልቀንስ
ሚባርክሽ ብሩክ ነውና እናቴ
ኪዳነ ምህረት ንገሽ እመቤቴ
አዝ===========         



ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ኪዳነ_ምህረት_ልዩ_ነሽ_ለኔ

ኪዳነ ምህረት ልዩ ነሽ ለኔ
ሳዝን ስጨነቅ አትራቂኝ ከጎኔ
የችግሬ ደራሽ እመ እግዚአብሔር
ቃል ኪዳንሽ ይርዳኝ ካንቺ ጋር ልኑር(፪)
#አዝ
የአዳም ተስፋው ነሽ የሴት ቸርነቱ
ኪዳነምህረት ነሽ የኖህ ምልክቱ
አዳም ደጅ የጠናሽ ሲገባ ንስሀ
ኖህም ድኖብሻል ከጥፋቱ ውሃ
#አዝ
የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ
ማርያም አንቺ ነሽ የፈጣሪ እናቱ
የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ
እመብርሃን ስሚኝ ልመናየን ሁሉ
#አዝ
የሰሎሞን አክሊል የዳዊት ዝማሬ
ድንግል መሆንሽን ትመስክር ከንፈሬ
ለተጠማው ውሻ የሚራራው ልብሽ
ለኔም እራርቶልኝ አስታርቂኝ ከልጅሽ
#አዝ
የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ
ማርያም አንች ነሽ የፈጣሪ እናቱ
የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ
እመብርሃን ስሚኝ ልመናዬን ሁሉ

ዘማሪት ሲስተር ፋሲካ መኮንን
    



ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ኪዳነ ምህረት | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ



ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

❤አልረሳውም ያንን ዕለት

አልረሳውም ያንን ዕለት
አልዘነጋው ያን ደግነት
እናቴ ሆይ ምልሽ ኪዳነ ምሕረት
እምዬ ሆይ ምልሽ ኪዳነ ምሕረት
ስላለኝ ነው ምክንያት/፪/


ለሠው ተናግሬ ያልተረዳኝ ሰው
ዕንባዬ በምሬት ከዓይኔ የሚፈሰው
የቤቴን ገመና ሁሉን ስነግርሽ
አዛኝ እህት ነሽና እራራልኝ ልብሽ
አረሳው መቼም የአንቺን ደግነት/፪/
ውለታ አለብኝ ኪዳነ ምሕረት

አዝ__

ልቤ በሐዘን ጠቁሮ ውስጤ እየደማ
በቅረዜ ሲጨልም ስጓዝ በጨለማ
በራፌን ዘግቼ ዝምብዬ አለቅሳለሁ
አይኔን አቀርቅሬ እናቴ እልሻለሁ
ዘንበል አልሽልኝ ሠምተሽ ፆሎቴን/፪/
አልተጸየፍሽም ብቸኝነቴን

አዝ__

እናት የለኝ ብዬ ከቶም አልከፋ
እኔስ አይቻለሁ ስትሞይኝ በተስፋ
ምድራዋዊ እናቴ ለጊዜው ነው ፍቅሯ
ያንቺስ ግን ልዩ ነው እረ ስንቱን ላውራ
ማርያም ማርያም ብል አልሠለችሽ/፪/
በልቤ ጽላት ስለ ታተምሽ

አዝ___

ሲረበኝ መጥተሻል ሲጠመኝ ደርሰሻል
ለጎደለው ቤቴ በረከት ሆነሻል
ጭንቄም ቀለለልኝ ሐዘኔም ራቀ
ያስጨነቀኝ ጠላት ራሱ ተጨነቀ
መዳኒት ወልደሽ ዳኩኝ ከመሜ/፪/
ይኸው ዘመርኩኝ በምልጃሽ ቆሜ



ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Golden, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ጾመ ነበያት ከህዳር 15-18 ድረስ ባለው ቀናት ውስጥ ይጾማል የሚል ጽሁፍ አምብቤ ነበር እንደትነው ሚሆነው ለነ ግልጽ አይደለም

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Wagaye, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Heavi_ii, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

                          †                          

🕊     [     እንኳን አደረሰን !    ]     🕊

   ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

           🕊   [    ጾም   ]    🕊

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ምዕመናን እንዲጾሟቸው የሠራቻቸው ፯ [ 7 ] አጽዋማት አሏት:: " ጾም " ማለት "መከልከል" ነው::

የምንከለከለው ደግሞ ከኃጢአትና ከክፋት ሲሆን አንድም ሰውነትን ወደዚያ ከሚወስዱ መባልዕት መከልከልን ይመለከታል::

ጾም ለክፉ ሥራ ከሚያነሣሱ የምግብ ዓይነቶች መከልከል ወይም ለተወሰነ ጊዜና ሰዓት ሰውነት ከሚፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ መወሰን [ መታቀብ ] ማለት ነው፡፡ ለሰውነት የሚያምረውንና የሚያስጎመዠውን ነገር ሁሉ ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ብሎ መተው ነው፡፡

ጾም ከመንፈሳዊ ተጋድሎዎች አንዱ ነው፡፡ ለሥጋም መንፈሳዊ ልጓም ነው፡፡ ጸዋሚ ሰው ፈቃደ ሥጋውን እየገታ ነፍሱን የሚያለማምድበት ስንቅ ነው፡፡ "ጾም ቁስለ ነፍስን የምትፈውስ ፤ ኃይለ ፍትወትን የምታደክም ፤ የበጎ ምግባራት ሁሉ መጀመሪያ ፤ ከእግዚአብሔር ጸጋን የምታሰጥ ፤ የወንጌል ሥራ መጀመሪያ ፤ የጽሙዳን ክብራቸው ፤ የድንግልና የንጽሕና ጌጣቸው ፤ የንጽሕና መገለጫ ፤ የጸሎት ምክንያት እናት ፤ የዕንባ መገኛ መፍለቂያዋ ፤ አርምሞን የምታስተምር ፤ ለበጎ ሥራ ሁሉ የምታነቃቃ ፣ ሰውነትን በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትሕትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ መድኃኒተ ነፍስ ናት፡፡" [ማር ይስሐቅ አንቀጽ ፬፥፮]

ጾም ተድላ ሥጋን የምታጠፋ ፥ የሥጋን ጾር የምታደክም ፥ ቁስለ ነፍስን የምታደርቅ ፥ ለጎልማሶች ጸጥታንና ዕርጋታን የምታስተምር ፥ ከግብረ እንስሳዊ የምትከለክል ፥ ሰው መላእክትን መስሎ የሚኖርባትና ኃይል መንፈሳዊን የሚጎናጸፍባት ደገኛ መሣሪያ ናት፡፡ ከኃጢአት ፆር ከፍትወት አንዱንም አንዱን ድል ለመንሳት ለማጥፋት ፥ የዲያብሎስን ረቂቅ ፍላጻ ለመመከት በጾም መድከም የሥራ ሁሉ መጀመሪያ እንደሆነች የታወቀ ነው፡፡ ጾም ምህረት መለመኛ ፥ የንስሐ መገለጫ ፥ ከመከራ የሚሠወሩባት ፥ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር አስታርቃ ርስት መንግሥተ ሰማያት የምታስገባ "ኆኅተ ጽድቅ - የጽድቅ በር" ሆና የተሰጠች ቀዳማዊት ሕግ ናት፡፡

[  እንኳን ለጾመ ነቢያት [ የገና ጾም ] በሰላም አደረሳችሁ ! ]


#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Beeeeeee, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Fikiru, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Enkuan letsome nebyat bselam aderesachehu

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች፤ ሙሽሪትን በሠርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል፤ ይሸልሙታል፡፡ ወደ ሠርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሠርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል፡፡ እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ልቡናችንን በማንጻት፣ ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ፣ የክፋት እርሾን በማስወገድ፣ ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት የምግባር እናት፣ የማስተዋል እንዲኹሉም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡

በሌላ አገላለጽ ብነግራችኹ ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፣ መርዘኛ ፈሳሽን ማስገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቈጠብ ነው፡፡ ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሓኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም፡፡

እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል፡፡ እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello 𝔟𝔢𝔩𝔦𝔫𝔤𝔥𝔞𝔪, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ጾመ ነቢያት (Nativity Fast) - ኪዳን ዘኢየሱስ እንደከተበው

ቤተ ክርስቲያናችን ከጌታ ልደት በፊት ያሉትን 40 ቀናት በጾም እንድናሳልፍ ታዘናለች። ይኽም ሙሴ አሠርቱ ቃላትን ለመቀበል በሲና ተራራ የጾመውን 40 ቀናት ይወክልልናል። ሙሴ አሠርቱ ቃላትን ለመቀበል 40 ቀናት እንደ ጾመ እኛም ደግሞ የአካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋዌ (Incarnation of the Logos) ለመቀበል እንዲሁ #40_ቀናትን እንጾማለን።

የአዳም መድኃኒት፥ የነቢያት ትንቢታቸው "እጅኽን ከአርያም ላክ ናና አድነን" እያሉ የለመኑት፥ የ5500 ዓመት ተስፋቸው፥ ለሙሴ የመጀመርያ ስሙን በየውጣ የነገረው (የውጣ ማለት Iota ከሚለው የግሪክ እና ኮፕቲች ፊደል የመጣ ነው በኮፕቲክ አሥር የሚለው ቃል በIota ፊደል ይጀምራል፥ ኢየሱስ የሚለው ስምም በግሪክም በኮፕቲክ በIota ፊደል ይጀምራል። ስለዚህ Iota , the name of salvation of our Lord የጌታ የማዳኑ ስም ተብሏል። (ውዳሴ ማርያም ዘእሑድ) ሙሴ አሠርቱ ቃላትን እንደተቀበለ አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና)፥ የኢያሱ ስሙ ኃይል (ኢያሱ እና ኢየሱስ ማለት ትርጉሙ አንድ ሲኾን ያህዌ ያድን ማለት ነው፥ መድኃኒት ተብሎም ይተረጎማል)፥ የኤልያስ መሶበ ወርቅ ውስጥ ያለ መናበዳዊት ዙፋን ለዘላለም የሚነግሥ የንግሥናው ፈጻሚ፥ የሰሎሞን ጥበብ "ጥበብሰ መድኃኒነ ውእቱ - ጥበብስ መድኃኒታችን ነው" (ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ) የተባለለት፥ የነቢያት ትንቢት ኹሉ ፈጻሚ፥ አዳኙ፥ አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ሊወለድ ነውና የተስፋውን ቀን በመጠባበቅ እኛም ከነቢያት ጋር እንጾማለን።

"የበዓል ቀን ሊመጣ ነው። እርሱም ከኹሉም በዓላት በላይ እጅግ የተቀደሰ እና ያማረ ነው፥ የተቀደሱ ቀናት ኹሉ አለቃ እና እናት ብለን ብንጠራው ስህተት አይኾንም። ይሄም በዓል #የክርስቶስ_ልደት ቀን ነው።" — ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

እሑድ ኅዳር 15 ይገባልና ለነቢያት ጾም እንኳን አደረሳችኹ!

Читать полностью…
Subscribe to a channel