በ2016 ዓ.ም በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት 271 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸው ተገለጸ !
በየዓመቱ በሚካሄደው በ፵፫ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ዓመታዊ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በሀገረ ስብከቱ በሚገኙ ከተሞችና ወረዳዎች የሚገኙ መንፈሳዊ የአብነት ትምህርት ቤቶች የመምህራንና የተማሪዎች መሠረታዊ ፍላጎት ማሟላት መቻሉ ተገልጿል፡፡
በአሰላ ማኅደረ ስብሐት በዓታ ለማርያም ቅ/ፋኑኤል ወቅ/ዮሐንስ ወ/ነጎድጓድ ገዳም በማኅበረ ቅዱሳን ከተገነባው ሕንጻ በተጨማሪ በመንፈሳዊ ትምህርት ቤቱ የመማርያ ክፍሎች አንዲሁም የመምህራንና የደቀ መዛሙርት ማረፊያ ቤቶች መሥራት ተችሏል ተብሏል፡፡
በሀገረ ስብከቱ በሽርካ ወረዳ ከ10 ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ 91 ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ ምእመናን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ሲል ሀገረ ስብከቱ በሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡
በተጨማሪም በደጁ ወረዳ ቡርቃ ጉራቻ ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የሚኖሩ 150 ምእመናን በጉሬ ደቢኖ ቅ/እግዚአብሔር አብና አርጆ ቅ/ጊዮርጊስ ከ30 በላይ ምእመናን መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን 499 አባወራና እማወራ ለስደት መዳረጋቸው ተነግሯል፡፡
ዘገባው የተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል ነው
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete Username(ID) ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
1⃣7⃣ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል
የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!
በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete site link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete site link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
" ሰዎች ማን ይሉኛል? "
" ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን። ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ። እነርሱም። አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት።"
ማቴ. ፲፮፥፲፫-፲፬ /16፥13-14/
⛪️ የኢየሱስ ክርስቶስን ማንነት ያልተረዱ ሰዎች በአይሁድ ዘንድ እንዳየነው ክርስቶስን "ፍጡር ነው" ብለው መጥራታቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ አይተናል።
⛪️ ዛሬም ወንጌል ተስፋፍቶ፣ የክርስቶስ ማንነት ፍንትው ብሎ ለዓለሙ በተገለጠበት ጊዜ ክርስቶስን "ፍጡር ነው" (ሎቱ ስብሐት) እያሉ የሚናገሩ ሰዎችን አየን፣ የአይሁድ አ*ተያየት፣ እምነትንም ተመለከትንባቸው
⛪️ ሰሞኑን እንዳልካቸው በተባለው የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ላይም ይህንን አየን
⛪️ በእርግጥ በጨ*ላነቱ ብዙም ላንደነቅ እንችላለን፤ ግን የአንድን እምነት ተከታዮች እንዲህ ነው የምታምኑት ብሎ መናገር በራሱ ወንጀል ነው
⛪️ ይህንን እየሰሙ ዝም ማለት ነገም ለሌላው በር መክፈት ነውና የሚመለከትው የቤተክርስቲያኒቱ የሕግ ክፍል አስፈላጊው እርምጃ ይወሰድ ዘንድ ጉዳዩን ወደ ሕግ ማቅረብ አለበት እንላለን
⛪️ እሳትና ውሃን በፊታችን አቀረበ፣ እኛም ወደ ወደድነው እጃችንን የመስደድን መብት ሰጠን።
⛪️ የሰማይ የምድሩ ፈጣሪ ሰው የፈለገውን ይከተል ዘንድ መብት ሰጠ፤ ስለዚህም ማንም በወደደው ቢያምን በእምነቱ ሊሰደብ፣ ሊብጠለጠል፣ ሊነቀፍ አይገባም
⛪️ ስርዓት መያዝ፣ የራስን እምነት ተከትሎ መጓዝ የግድ አስፈላጊ ነገር ነውና
ኦርቶዶክሳውያንም አስፈላጊውን ትብብር እናድርግ፣ አንድ ሆነን ጠላትን በእግዚአብሔር ስም እንከላከል
የአምላካችን ጥበቃና ቸርነት ከእኛ አይለይ። አሜን።
የቤተክርስቲያኔ ጉዳይ ይመለከተኛል
#አንዲት_ሐይማኖት_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ
#አንዲት_ቤተክርስቲያን
#አንዲት_ጥምቀት
#ተዋህዶ
#orthodoxchurch
#ኢትዮጵያ
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
በ2016 ዓ.ም በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት 271 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸው ተገለጸ !
በሀገረ ስብከቱ በሽርካ ወረዳ ከ10 ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ 91 ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ ምእመናን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ሲል ሀገረ ስብከቱ በሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡
በተጨማሪም በደጁ ወረዳ ቡርቃ ጉራቻ ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የሚኖሩ 150 ምእመናን በጉሬ ደቢኖ ቅ/እግዚአብሔር አብና አርጆ ቅ/ጊዮርጊስ ከ30 በላይ ምእመናን መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን 499 አባወራና እማወራ ለስደት መዳረጋቸው ተነግሯል፡፡ @TewahidoMediaCenter
“ቤተ ክርስቲያን የሙሰኞች ዋሻ ሆናለች የሚለው ዘርፈ ብዙ ፍርጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ እንጂ ሲቀንስ አይታይም”
ብፁዕ አቡነ አብርሃም
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፤የሰሜን ጎጃምና የባሕርዳር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በ43ተኛው የመንበረ ፓትርያርክ ዓለም አቀፍ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፈተና የሆነው “ሙስና ሊወገዝ” እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ብፁዕነታቸው “በሚዲያ ሳይቀር ቤተ ክርስቲያን የሙሰኞች ዋሻ ሆናለች የሚለው ዘርፈ ብዙ ፍርጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ እንጂ ሲቀንስ አይታይም” ሲሉም ተደምጠዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ አብርሃም በጉባኤው መክፈቻ ላይ ሪፖርታቸውን ሲያቀርቡ “ይህ ለምን ሆነ ብለን ራሳችንን ብንጠይቅ እውነታውን በመጋፈጥ ችግሩን ለማስቆም ከመትጋት ይቅል ቸልተኝነት እየመረጥን በብዙዎቹ መሥዋዕትነት የሚሰበሰበው ሀብት እንዲመዘበር የተስማማን በሚመስል ሰምተን እንዳልሰማን መሆናችን እንደሆነ” ጠቁመዋል፡፡
ብፁዕነታቸው “ይህንን አስነዋሪ ድርጊት እያወገዝን እውነትን ተላብሰን ከሙሰኞች የጸዳችና የከበረች ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለተተኪው ትውልድ ልናስተላልፍ ይገባል” ነው ያሉት በንግግራቸው ፡፡
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፤የሰሜን ጎጃምና የባሕርዳር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መልዕክታቸውን ሲቋጩም “ርትዕ የሰፈነባት ቤተ ክርስቲያንን ለተተኪ ትውልድ ለማስረከብ እንትጋ” እያሉም አባታዊ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
@EoTC TV
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
እንኳን አደረሳቹ
ጥቅምት 5-ኑሮአቸው እንደሰው ያይደለ በምድረ በዳ እንደመላእክት የኖሩትና በዝቋላ ተራራ ባለው ባሕር ውስጥ 100 ዓመት ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ሰዎች ምሕረትን የለመኑት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታላቅ ቃልኪዳን የተቀበሉበት ዕለት ነው፡፡
አባታችን አራት ሺህ እልፍ እየሰገዱ፣ 300 ጊዜ የቀኝ 300 ጊዜ ደግሞ የግራ ፊታቸውን በድንጋይ እየመቱ፣ መዝሙረ ዳዊትን እየደገሙ፣ 15ቱን መኅልየ ነቢያት፣ መኅልየ ሰለምንንና ውዳሴ ማርያም እየጸለዩ ለኃጥአን ምሕረትን ሲለምኑ ዕንባቸው እንደ ውኃ ይፈስ ነበር፡፡ ጌታችንም ‹‹በተወለድሁባት፣ በተጠመቅሁባትና ከሞት በተነሣሁባት ዕለት እልፍ እልፍ ነፍሳትን እምርልሃለሁ›› የሚል ቃል ኪዳን ሰጣቸዉ
አምላካችን በቃል ኪዳናቸው ይማረን
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
ማኅበረ ቅዱሳን ከአርባ ሺህ በላይ አዳዲስ አማንያን የሥላሴ ልጅነት እንዲያገኙ ማድረጉ ተገለጸ !
በየዓመቱ በሚካሄደው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ዋና ምክትል ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ በማኅበረ ቅዱሳን የተሠሩ ሥራዎች ሪፖርት አቀረቡ።
በቀረበው ሪፖርትም ማኅበሩ ለ310 ተማሪዎች ክህነት እንዲሰጡ ማድረጉ፣ ለዐይነ ስውራን የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ማስተማሪያ ዐምስት የኮርስ መጻሕፍት የድምጽ ትረካ አዘጋጅቶ ማሰራጨቱ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም በሀገር ቤት ዐርባ ሺሕ ፣በውጭ ሀገር ደግሞ አንድ መቶ ዐስራ ሁለት አዳዲስ አማንያን የሥላሴ ልጅነት እንዲያገኙ ማድረጉ ተጠቅሷል፡፡
በከንባታ ጠንባሮ ሀላባ፣ በደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች፣ በወላይታ ሶዶ፣ በካፋ፣ በጋሞና አካባቢው ዞኖች፣ በቤንች ሸኮ፣ ሸካና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች እንዲሆም በዳውሮ አህጉረ ስብከት በካህናት እጥረት ተዘግተው የነበሩ 34 አብያተ ክርስቲያናት ካህናት ተቀጥሮላቸው አገልግሎት እንዲጀምሩ ተደርጓል ተብሏል፡፡
በደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች፣በወላይታ ሶዶ፣ በቤንች ሸኮ፣ ሸካና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች አህጉረ ስብከት ለአዳዲስ አማንያን መገልገያ የሚውሉ ዐምስት ሕንጻ አብያተ ክርስቲያናትና ዐራት መካነ ስብከት አዳራሾችን አሠርቶ ለአገልግሎት ማዋሉ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡
በ169 የአብነት ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ 224 መምህራንና 2018 ደቀ መዛሙርት የገንዘብ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን 73 ተማሪዎችን የአባ ጊዮርጊስ ነጻ የትምህርት እድል ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ተብሏል፡፡
በትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት በተለያዩ ቋንቋዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ለ1226 አገልጋዮች፣ ለ3650 የደረጃ 1 እና 2 ተተኪ አመራሮች ሥልጠና መስጠቱና ለ213 አገልጋዮች ወርሐዊ ደሞዝ በመክፈል ድጋፍና ክትትል ማድረጉ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡
ስብከተ ወንጌልን ተደራሽ ለማድረግ በአማርኛና ኦሮምኛ ቋንቋዎች በርቀት ትምህርት 111 በሞጁልና 68 በኢለርኒንግ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መሠረተ እምነት ማስተማር መቻሉና ለዐይነ ሥውራን ወገኖች የውዳሴ ማርምና ሰኔ ጎለጎታ የጸሎት መጽሐፍ በብሬል ተዘጋጅቶ ተሰራጭቷል፡፡
ማኅበሩ በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም፣ በቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት የበደሌ ሁለገብ የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክት ግንባታ ማከናወኑ ተገልጿል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን በተጨማሪም በምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት የምስካበ ቅዱሳን ቅዱስ ዑራኤል ወሳሙኤል ዘዋልድባ ገዳም አብነት ትምህርት ቤት ግንባታ አከናውኗል፡፡
በሦስት አህጉረ ስብከት በድርቅ ለተጎዱና በሃይማኖት ተኮር ጥቃት ከስልጤ ዞን ቅበት ከተማ ተሰደው ለነበሩ ኦርቶዶክሳውያን የምግብና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉም በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡
በተለያዩ 7 ቋንቋዎች የተዘጋጁ 261 መዙሙራትንና በ10 ቋንቋዎች 328 የመዝሙር ጥራዞችን ለምእመናን ተደራሽ ማድረጉ በሪፖርቱ የተገለጸ ሲሆን በማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን የተለያዩ ይዘቶችን በመጨመር የተመልካቾችን ፍላጎት ለማሳደግ የሚየስችሉ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡
ዘገባው የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ነው።
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
1⃣7⃣ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል
የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!
በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ
ገብረ : መንፈስ : ቅዱስ : ለኢትዮጰያን : ህዝብ : ምሕረትን : የለመነ
#ጥቅምት_5 ቀን በምድረ በዳ እንደመላእክት የኖሩትና በዝቋላ ተራራ ባለው ባሕር ውስጥ 100 ዓመት ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ሰዎች ምሕረትን የለመኑት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቃል ኪዳን የተቀበሉበት ዕለት በሀገራችን ኢትዮጵያ በድምቀት ይከበራል፡፡
የማይሰለች ተጋዳይ የክብር ኮከብ የገዳም መብራት ስም አጠራሩ እርግናው የተመሰገነ ብጹእ ቅዱስ ደግ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከግብጽ ደቡብ ከቆላው አገር ከንሂሳ የተገኘ ገዳማዊ አባት ።
በግብጽ በርሃ 300 ዓመት የኖረ ከዚያም ወደ ኢትዮጵያ ወጥቶ በዝቋላ ገዳም እህል ሳይበላ ውሃ ሳይጠጣ ልብስ ሳይለብስ 262 አመት የኖረ ኑሮውም እንድ ሰው ያልነበረ በምድር ላይ እንደ መላእክት ሆኖ የኖረ
የሃይማኖር አርበኛ ገድሉ ትሩፋቱ ከሰማይ ከዋክብት ከምድር አሸዋ የበዛ ኢትዮጰያን አብዝቶ የሚወዳት « አቤቱ ጌታ ሆይ የኢትዮጰያን ህዝብ ማርልኝ» ብሎ ፈጣሪውን የለመነ ፤ ምድራዊ ምግብ ያልተመገበ ።
የእናቱን ጡት እንኳን ያልጠባ ልብስ መጠለያ እንኳን ያልፈለገ የክረምት ቁር የበጋ ሐሩር እየተፈራረቀበት በተጋድሎ 562 ዓመት ኖረ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ።
የ አ ቡ ነ : ገ ብ ረ : መ ን ፈ ስ : ቅ ዱ ስ : ረ ድ ኤ ት : በ ረ ከ ታ ቸ ው
ይ ደ ር ብ ን : በ ጸ ሎ ታ ቸ ው : ይ ማ ረ ን !
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo