⭐ ቴሌግራም ፕሪሚየም እንዲሁም ስታር መሸጥ ጀምረናል
✅ STAR PRICE ⬆️
✅50 ⬆️ /
✅75 ⬆️ /
✅100 ⬆️ /
✅150 ⬆️ /
✅250⬆️ /
✅500 ⬆️ /
✉️✉️INBOX ✉️✉️
⚙️Telegram Premium ለማስደረግ ለምትፈልጉ በሙሉ✅
⭐3 ወር - 1800 ብር
⭐6 ወር - 2500 ብር
⭐1 አመት - 4100 ብር
መግዛት ለምትፈልጉ inbox ማውራት ትችላላቹ 👤
"…ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ራሳቸውን ለሚያሰማሩ ለእስራኤል እረኞች ወዮላቸው! እረኞች በጎችን ያሰማሩ ዘንድ አይገባቸውምን? ጮማውን ትበላላችሁ ጠጕሩንም ትለብሳላችሁ፥ የወፈሩትን ታርዳላችሁ፤ በጎቹን ግን አታሰማሩም። የደከመውን አላጸናችሁትም የታመመውንም አላከማችሁትም የተሰበረውንም አልጠገናችሁትም የባዘነውንም አልመለሳችሁትም የጠፋውንም አልፈለጋችሁትም በኃይልና በጭቈናም ገዛችኋቸው። እረኛንም በማጣት ተበተኑ፥ ለምድርም አራዊት ሁሉ መብል ሆኑ፥ ተበተኑም። በጎቼ በተራሮች ሁሉና በረዘሙ ኮረብቶች ሁሉ ላይ ተቅበዝብዘዋል፥ በጎቼም በምድር ፊት ሁሉ ላይ ተበትነዋል፤ የሚሻም የሚፈልግም አልነበረም።
ሕዝ 34፥ 2-6
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
ሁለተኛው የ12ኛ ክፍል የሰንበት ት/ቤቶች የቅድመ ትግበራ ሲተገብሩ የነበሩ እና ምዘና የወሰዱ ተማሪዎች የምርቃት መርሐ ግብር ተከናወነ።
02/02/2017 ዓ.ም
በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በተዘጋጀው ሥርዓተ ትምህርት መሠረት በሙከራ የቅድመ ትግበራ ሲተገብሩ የነበሩ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት 7 እና ከጉራጌ ሀገረ ስብከት ደግሞ 1 በጠቅላላ 8 አጥቢያ ሰ/ት/ቤቶች የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የምረቃ መርሐ ግብራቸው በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ በዛሬው ዕለት ተከናውኗል።
በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሐላፊ ፣ የአንድነቱ የሥራ አመራር አባላት፣ ተመራቂ ተማሪዎች እና ወላጆች ተገኝተዋል። መርሐ ግብሩን ብፁዕ አቡነ በርናባስ የዋግህምራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጸሎት የከፈቱት ሲሆን ብፁዕ አቡነ አብርሃምም ባስተላለፉት አባታዊ መልእክት "ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው ጥበብንም ያበዛል። ጽድቅንም አስተምረው ዕውቀትንም ያበዛል። ጥበብን ፈላጊዎችና ራሳችሁን ለጥበብ ያዘጋጃችሁ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ዕውቀት ጥበብ ሥጋዊና ጥበብ መንፈሳዊን በነጻ ሰጥታችኋለችና የተማራችሁትን ወደ ተግባር ለውጡ። ቤተ ክርስቲያናችሁ ከናንተ ብዙ ትጠብቃለች" ብለዋል።
በመጨረሻም ለስምንቱም አጥቢያ ሰ/ት/ቤቶች ፣ ለተመራቂ ተማሪዎች የዕውቅና ምስክር ወረቀት ከብፁዕ አቡነ አብርሃምና ከብፁዕ አቡነ ሰላማ የም/ጎንደር ሊቀ ጳጳስ እጅ ተቀብለዋል። ከስምንቱ አጥቢያ ሰ/ት/ቤቶችም ጠቅላላ ውጤት አንደኛ በመውጣት ሳሪስ ምዕራፈ ቅዱሳን ፈለገ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስና አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።
(የሰ/ት/ቤቶች አንድነት)
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
#ማኅሌተ_ጽጌ፤ ምንጩ ትርጉሙና መልእክቱ (ክፍል ሁለት)
በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
የቀጠለ…
2, #ታሪክ
በብሉይና በሐዲስ ኪዳን በተለያዩ ጊዜያት የተፈጸሙትን ድርጊቶች እያነሣ የሚሔድና በዚያውም ከታሪኩ ጋር አብሮ ጸሎትና ምሥጢር የያዘ ነው፡፡ ታሪክን ከሚያነሡት መካከል የሚከተሉትን ለአብነት መመልከት ይቻላል፡፡
2.1. «እስከ መነነቶ ሜልኮል ቅድመ ታቦተ ሕግ ከመ ዘፈነ፣
ንጉሠ እስራኤል ኪያኪ ዘጸገየ ስነ፣
ቅድመ ገጸ ሥዕልኪ ድንግል እዘፍን አነ
ዘይሜንን ተአምረኪ ወስብሐተኪ ቁርባነ፣
በአፈ መላእክት ወሰብእ ለይኩን ምኑነ፡፡
ዳዊት ታቦተ ጽዮንን ከአቢዳራ ቤት ወደ ከተማው ባስመጣ ጊዜ በሙሉ ኃይሉ በ #እግዚአብሔር ታቦት ፊት ሲዘምር ሜልኮል ተመልክታ በልብዋ ናቀችው፡፡ በዚህም ምክንያት #እግዚአብሔር ስላዘነባት ልጅ ሳትወልድ ሞታለች፡፡ ሳሙ.6፡12-23፡፡ ደራሲውም ይህንን ታሪክ ካስታወሰ በኋላ «ቅድመ ገጸ ሥዕልኪ ድንግል እዘፍን አነ - ዳዊት ለ #እመቤታችን ምሳሌ በሆነች በታቦተ ጽዮን ፊት እንደዘመረ እኔም በሥዕልሽ ፊት ላንቺ እዘምራለሁ»፤ «ዘይሜንን ተአምረኪ ወስብሐትኪ ቁርባነ በአፈ መላእክት ወሰብእ ለይኩን ምኑነ ሜልኮል፡- በዳዊት ይቀርብ የነበረውን የታቦተ ጽዮንን ምስጋና በመናቋ እንደተረገመች ያንቺንም ተአምርሽንና ምስጋናሽን የሚንቅ ሁሉ በሰውና በመላእክት አፍ የተረገመ ይሁን» የሚል ነው፡፡ ሜልኮል የምሳሌዋን የታቦተ ጽዮንን ምሥጋና በመናቋ ከተረገመች ዛሬ የአማናዊቷን ታቦተ ጽዮን የ #እመቤታችንን ምሥጋና የሚንቁና ምሥጋና የሚያቀርቡትን የሚነቅፉ ሰዎች ምን ያኽል የተረገሙ ይሆኑ? እነዚህም «በድፍረትና በመናቅም በጻድቅ ላይ የሚናገሩ የሽንገላ ከንፈሮች ድዳ ይሁኑ» /መዝ.3ዐ÷18/ ባለው ርግማን የተረገሙ ናቸው፡፡
2.2. እንበይነ አውሎጊስ ለዳንኤል አመ አርአዮ ስቅለተ፣
ከመ እገሪሁ ሰዓምኪ ወሰአልኪዮ ምሕረተ፣
ለተአምረ ሣህል ወልድኪ በእንተ ፍቅረ ሰብእ ዘሞተ፣
እንዘ ታዘክሪዮ ድንግል ይምሐረኒ ሊተ፣
ከናፍሪሁ ጽጌ አንኂ ስዕመተ፡፡
አውሎጊስ የሚባል የወፍጮ ድንጋይ እየጠረበ በመሸጥ ከዚያ በሚያገኘው ትንሽ ገቢ የሚተዳደር ደኃ ሰው ነበር፡፡ የሚያገኘውንም ገንዘብ ለራሱ ትንሽ ለዕለት ኑሮው ካስቀረበ በኋላ ከርሱ የባሰባቸው ችግረኞችን እየረዳ ይኖር ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን በዚህ ግብር ሳለ አባ ዳንኤል የሚባል ባሕታዊ ያየዋል፡፡ ይህም ባሕታዊ አውሎጊስ በዚህ በድህነት ኑሮው እንደዚህ ድሆችን የሚረዳ ከሆነ ብዙ ገንዘብማ ቢያገኝ ምን ያክል ብዙ ሰው በረዳና መልካም ሥራ በሠራ ነበር» ብሎ #እግዚአብሔር ለዚህ ሰው ብዙ ሀብት እንዲሰጠው ሱባኤ ያዘ፡፡ #እግዚአብሔርም ሀብት ለዚህ ሰው /ለአውሎጊስ/ እንደማይጠቅመው ቢነግረውም አባ ዳንኤል በራሱ ሀሳብ ብቻ በመጓዝ ሀብቱን እንዲሰጠው አጥብቆ ስለተማፀነ እንደለመነው ሊያደርግለት ጸሎቱን ተቀበለ፡፡ ከዚህ በኋላ አውሎጊስ እንደልማዱ ድንጋይ ሲቆፍር በማሰሮ የተቀበረ ወርቅ አገኘ፡፡ ወርቁን ወስዶ ለንጉሡ ሰጠ፡፡ ንጉሡ ወርቅ ሲያገኝ ለራሱ ሳያደርግ ለንጉሥ የሚያመጣ ሰው ምን ያክል ታማኝ ቢሆን ነው ብሎ በዚያው በቤተ መንግሥቱ እንደራሴ አድርጎ ሾመው፡፡ አውሎጊስ ከተሾመ በኋላ አጃቢው ክብሩና ሀብቱ ሲበዛ ትሩፋት መጨመሩ ቀርቶ የቀደመ ሥራውንም ተወ፡፡ ለተበደለ የማይፈርድ ባለጉዳይ የሚያጉላላ ሆነ፡፡ በዚህ ጊዜ አባ ዳንኤል በሕልም #እግዚአብሔር ሲቆጣውና ሲፈርድበት አየ፡፡ የማይገባ ልመና ለምኖ አውሎጊስን የቀደመ ትሩፋቱን እንዲተውና አሁን እንዲበድል ምክንያት ሆኗልና፡፡ አባ ዳንኤል በደሉ ገብቶት ከ #ሥዕለ_ማርያም ሥር ወድቆ ተማፅኖ #እመቤታችን ልጇን ተማጽና ይቅር አስባለችው፡፡
አባ ዳንኤል በሕልም ያየው ነገር ስለከበደው ምናልባት አውሎጊስ ድሀ በድሎ ፍርድ አጓድሎ እንደሆነ ብሎ ሊያየው ቢሄድ እርሱንም የማያናግረው ሆነ፡፡ «ስለ ሰው ፍቅር የሞተ ልጅሽን ስለ አባ ዳንኤል ለምነሽ እንዳስማርሽው እኔንም ይቅር እንዲለኝ የጽጌ ልጅሽን ምሕረት ለምኝልኝ» በማለት እኛንም ባላወቅነው እየገባንና እየፈረድን ለሚመጣብን ቅጣት እንድታስምረን የሚያመለክት ነው፡፡
2.3. ኦ ረዳኢተ ድኩማን ዘይረድአኪ ኢትኃሥሢ፣
እምንበረ ላዕክኪ በምዕር ከመ ገፍታዕኪዮ ለወራሲ፣
ለገፍትዖ ፀርየ ድንግል ኃይለ ጽጌኪ ልበሲ፣
እንዘ ይሣለቅ ተአምረኪ ወሐሰተ ይሬሲ፣
መፍትውኑ ከመ ይህየው ከይሲ፡፡
የ #እመቤታችንን ተአምር አሰባስቦ የጻፈው ቅዱስ ደቅስዮስ ነው፡፡ #እመቤታችንም ለዚህ ውለታው ሌላ ሰው የማይቀመጥበት ሰማያዊ ወንበር እና ሌላ ሰው የማይለብሰው አጽፍ ሰጥታዋለች፡፡ ከደቅስዮስ ዕረፍት በኋላ በእርሱ ቦታ የተሾመው ኤጲስ ቆጶስ በዚህ መንበር ለመቀመጥና አጽፉን ለመልበስ ሲል «ተው ይህ ለደቅስዮስ ብቻ የተሰጠ ነው» ቢሉት «እኔም እንደርሱ ኤጲስ ቆጶስ ነኝ ከእርሱ በምን አንሳለሁ?» በማለት ከወንበሩ ሲቀመጥ ወዲያው ሞቷል፡፡ ከላይ የተጻፈው ድርሰትም የሚያስረዳው ይህንን ነው፡፡ «ድኩማንን፣ ችግረኞችን የምትረጅ አንቺ ግን ረዳት የማትሽ ሆይ ከወዳጅሽ ከደቅስዮስ ወንበር ላይ በትዕቢትና በድፍረት የተቀመጠውን እንደተቀበልሽው የእኔንም ጠላቶች አጋንንትን እኩያት ኃጣውእን ለማስወገድ የጽጌሽን ማለት የልጅሽን ኃይል ይዘሽ ተነሽ» በማለት ለወዳጆቿ የምትቆም #እመቤታችን ከጠላታችን እንድትታደገን ከታሪኩ አንጻር የቀረበ ጸሎት ነው፡፡
2.4. «በጌጋየ አዳም ወሔዋን ሱራፌል ዘአጸዋ፣
እንበለ ጽጌኪ መኑ ለአንቀጸ ገነት ዘአርኃዋ፣
ተፈሥሒ ድንግል መያጢተ አዳም እምጼዋ፣
በተአምርኪ ውስተ ምድረ ጽጌ አቲዋ
ከመ ጣዕዋ አንፈርዓፀት ጼዋ፡፡
አዳምና ሔዋን ባጠፉት ጥፋት ከገነት ተባረው ወደ ምድረ ፋይድ እንዲወርዱ ተፈርዶባቸው ገነትን ሱራፌል መልአክ በምትገለባበጥ የእሳት ሰይፍ ይጠብቅ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ የተዘጋጀት ገነትን «እንበለ ጽጌከ መኑ ለአንቀጸ ገነት ዘአርኃዋ፤ ያለ አንቺ ጽጌ ያለ #ክርስቶስ በሱራፌል ስትጠበቅ የነበረችውን ገነት ሊከፍታት የቻለ ማንም ፍጥረት የለም» ዘፍ.3፡24፡፡ ካንቺ በተገኘ በ #ክርስቶስ ወደ ቀደመ ክብሯና ቦታዋ የተመለሰች ሔዋን የእናቱን ጡት ጠብቶ ደስ እንደሚሰኝ እንደሚዘል እንቦሳ ደስ ተሰኘች፡፡ በአጠቃላይ ይህ የሚያስረዳው ያለ #ክርስቶስ ሰው መሆንና በ #መስቀል ተሰቅሎ ቤዛ መሆን ማንም የገነትን በር ሊከፍት እንደማይችል ሲሆን የተዘጋውን የገነት በር የከፈተና የሰው ልጅ ያጣውን የልጅነት ጸጋ የመለሰ #ክርስቶስ ደግሞ ከ #እመቤታችን የተገኘ መሆኑን ነው፡፡ #እግዚአብሔር በኢሳይያስ አንደበት «መድኃኒቴም አይዘገይም፤ ከጽዮን ለክብር እንዲሆን መድኃኒትን ለእስራኤል ሰጥቻለሁ» ኢሳ.46÷13፡፡ እንዳለ የተዋረደው የሰው ልጅ የከበረበትና የዳነበት መድኃኒት #ኢየሱስ_ክርስቶስ የተገኘው ጽዮን ከተባለች ከእመቤታችን ከቅድስት #ድንግል_ማርያም ነው፡፡ ይህንን መድኃኒት ለዓለሙ ያበረከተች እርሷ ናት፡፡
3. #ተግሣጽ
አባ ጽጌ ድንግል ይህንን ማኅሌተ ጽጌ ሲደርስ ለ #መስቀልና ለ #እመቤታችን ክብርና ስግደት አይገባም የሚሉ ደቂቀ እስጢፋ የሚባሉ መናፍቃን ተነሥተው ነበር፡፡ በዘመኑ የነበሩት ንጉሥ አፄ ዘርዐ ያዕቆብ ጉባኤ አሠርተው አከራክረው መናፍቃኑ ተረትተዋል፡፡ አባ ጽጌ ድንግልም በማኅሌተ ጽጌ ውስጥ እነዚህን የ #እመቤታችንን ተአምርና ክብር በመግለጽ መናፍቃንን በመገሰጽ በዚህ የተግሣጽ ድርሰታቸው አስተምረዋል፡፡ ለምሳሌ የተወሰኑትን እንመልከት፦
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
አዲስ ለሚመዘገቡ አባላት
👉30$ Deposit ላደረገ
👉10$ Bonus ይሰጣችኋል
👉50$ Deposit ላደረገ
👉15$ Bonus ይሰጣችኋል
👉100$ Deposit ላደረገ
👉50$ Bonus ይሰጣችኋል
ማሳሰቢያ 👇👇👇
ይህ ዕድል የምቆየው
ከጥቅምት 1,_ጥቅምት 10 ለ9 ቀናት ብቻ ነው ለበለጠ መረጃ በውስጥ አናግሩኝ
የጢሊቲ ገርቢ መካነ ህይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የሚገለኘው በሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር ካሉት አብያተ ክርስቲያናት አንዱ ሲሆን ።በዚህ ቦታ ላይ ያለ ጸበል ብዙዎችን በመፈወስ የሚታወቅ መሆኑን ብዞዎች ህያው ምስክሮች አሉ።በጸበሉ ተጠምቆ ያልዳነ ያልተፈወሰ የለም ።እርሶም ጸበሉን ከፈለጉ እዚህ ቦታ በመሄድ መጠመቅ ይችላሉ።ይህ ቦታ የሚገኘው ከሞጆ ወደ አረርቲ ወይም ወደምንጃር ስንጓዝ የጀሬ ሳንደርስ መሃል መንገድ ላይ የሚገኝ ነው። ስለዚህ ጥቅምት 5/02/2017 ዓ/ም ታላቅና ልዩ መንሳዊ ክብረ በአል ስላለ በዚህ ቦታ ተገኝተው መንፈሳዊ ገበያ ይገብዩ። ካነበቡ በኋላ ሼር በማድረግ ይተባበሩን።
ቀን 02/02/2017 ዓ/ም
መምህር ይላቅ ፈለቅ
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete site link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
በቤተ መቅደስ የተተከለች ሎሚ ፤ የጴጥሮስ መክፈቻ ቁልፍ ፤ አንቺ የጳውሎስ ምሥክር ድንኳን በእውነትም የጊዮርጊስ አክሊሉ ነሽ።
ሰቆቃወ ድንግል
በቤተ መቅደስ ዘልሕቀት ወለተ ካህናት እንዘ ትሴሰይ ሥሩዓ፣ ኅብስተ ኅቡዓ ወጽዋዓ ወይን ምሉዓ፤እፎ ከመ ነዳይ ሲሳየ ዕለት ዘኃጥአ፤ተአገሠት በብሔረ ግብጽ ረኃበ ወጽምዓ፤አልቦ ከማሃ ዘረከበ ግፍዓ።
ተሠርቶ የተዘጋጀ ሥውር ኅብስትን ምሉዕ የወይን ጽዋን እየተመገበች በቤተ መቅደስ ያደገች የካህናት ልጅ ፤ እንዴት የዕለት ምግቡን እንደ አጣ ደሃ በግብጽ ሃገር ረኃብና ጥምን ታገሰች፤ እንደርሷ ግፍስ ያገኘው ማንም የለም።
🌷ወረብ
እፎ ከመ ነዳይ ዘኃጥአ ሲሳየ ዕለት/፪/
በቤተ መቅደስ ዘልሕቀት ወለተ ካህናት እንዘ ትሴሰይ ኅብስተ መና ኅቡዓ/፪/
ዚቅ
እሴብሕ ጸጋኪ ኦ ዑጽፍተ ልብሰ ወርቅ እግዝዕትየ ወለተ ዳዊት ንጉሥ ዘተሐፀንኪ በቤተ መቅደስ ወተዓንገድኪ በፈሊስ እምሀገር ለሀገር እንዘ ተዓውዲ በተፅናስ።
በቤተመቅደስ ያደግሽ የንጉሥ ዳዊት ልጅ ከሃገር ለሃገር በመሰደድም ዕንግዳ በመሆን በችግር ዙሪያ የዞርሽ፤ የወርቅ ልብስን የተጎናጸፍሽ እመቤቴ ሆይ ጸጋሽን አመሰግናለሁ።
መዝሙር
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ
ኪነ ጥበቡ መንክር ወእፁብ፤ኪነ ጥበቡ መንክር ወእፁብ ለዘሀሎ መልእልተ አርያም።አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ።ዘከለሎ ለሰማይ በከዋክብት ብሩህ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ ወለምድርኒ አሠርገዋ በጽጌያት ንፁህ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ ወሠርዓ ሰንበተ ለነባረ ያዕርፉ ባቲ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌ:ማ- መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ፅጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት። ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ።
ኪነ ጥበቡ ድንቅና ዕጹብ በአርያም ከፍታ ያለው ኪነ ጥበቡ ድንቅና ዕጹብ ነው። ምሕረቱን በእኛ ላይ አሳየ፤ ብሩህ በሆኑ ከዋክብት ሰማይን የጋረደው ምሕረቱን በእኛ ላይ አሳየ፤ ምድርንም በንፁሕ አበቦች ያስዋበ ምሕረቱን በእኛ ላይ አሳየ፤ሰንበትንም ያርፉባት ዘንድ የሠራ ምሕረቱን በእኛ ላይ አሳየ፤ (በኅብረት)፡ በዱር ውስጥ እንዳሉ የቆላ አበቦች የቅዱሳን መአዛቸው ቀንሞስና ናርዶስ የተባሉ ሽቱዎችን አፈሩልን።
አመላለስ
መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ፅጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት/፪/
ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ/፬/
እንኳን አደረሳችሁ! በአካባቢያችን ካለ አጥቢያ በመሄድ የዚህ ድንቅ ምስጢር ተሳታፊ እንሁን!
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
የቤተክርስቲናችንን ልህልና ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚፈታተኑ ጉዳዮች እየተፈጠሩ ነው ለዚህም በዋናነት አባቶች አቋም የለሽ መሆናቸው እና ሆዳቸውን ማስቀደማቸው ነው እናም ለእናንተ ወየውላችሁ…….እየመጣ ያለው አደጋ እናንተንም አይምርም ተመለሱ
Читать полностью…ከመ ይትፌሣሕ ጻድቅ ሶበ ይሬኢ በቀለ፣
በተበቅሎ ፀር ያርኢ ዘተአምርኪ ኃይለ፣
እፎ የሐዩ እመአምላክ እንተ ኪያከ ፀአለ፣
አኮኑ በፍትሐ ጽጌኪ ይሙት ተብህለ፣
ላዕለ አቡሁ ወእሙ ዘአሕስመ ቃለ፡፡
ጻድቅ #እግዚአብሔር ጠላቶቹን ሲበቀልለት ሲያይ ደስ ይለዋል፡፡ ይኸውም የአንቺን ተአምር ኃይል ያሳይ ዘንድ ነው፡፡ እንዲህ ከሆነ ያንቺን ተአምር የሚንቁና አንቺን የማያከብሩ ከሐድያን እንዴት በሕይወት ሊኖሩ ይገባቸዋል? ምክንያቱም «በልጅሽ በክርስቶስ ትእዛዝ «እናቱን ወይም አባቱን የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደል» /ዘጸ.21፡17/ ተብሎ ተፈርዷልና፡፡ እናት አባቱን የሰደበ ሞት የሚገባው ከሆነ #ክርስቶስ ሰማያዊውን አምላክ ወልዳ፣ ጡቷን አጥብታ፣ አዝላ፣ ተሰዳ ለዓለም ሕይወት ባበረከተችው በ #ድንግል_ማርያም ላይ ቃልን የተናገረማ እንዴት ያለ መከራ ይጠበቀው ይሆን?
ይቀጥላል…
🚩ትወድቃለህ ... ትንፏቀቃለህ ... እንደገና ትነሳለህ .. ደግሞ ትራመዳህ .. መሮጥ ትጀምራለህ ... ድጋሚ ትወድቃለህ ... እያለ ህይወት ዳግመኛ ይቀጥላል ...😃
ግን መቼም አትርሳ ስትወድቅ ለጥቅሙ ብሎ ታክል የገባብህን .. አምነኸው የጣለህን በፍፁም አትዘንጋ .. ስትነሳ እጅህን ጨብጦ ያነሳህን ወዳጅህን ደግሞ አትርሳ ..
ሁለቱም ባለውለታህ ናቸው ....😍
ትመጫለሽ አይደል?
ቤተመቅደስሽን ከበን አለን - መቅደስ ገላችን ቢረክስም
በሕንጻ መቅደስሽ ከትመናል - ሕንጻ ሥላሴን ብናፈርስም
በልማድና በእምነት መሐል – በተወጠረ መንፈሳችን
በጎጥ በጎሳ በታጠረ - በተፍረከረከ አንድነታችን
ስቀለው ስቀለው እንጂ – ምን በድሎ? በማይል ልሳናችን
ለክፋት ባደገደገ - በጎ ግብር በራቀው
ኃጢአት ባጠራቀመ – የጽድቅ መንገድ በናፈቀው
ነውርን መግለጥ እንጂ - ከባቴ አበሳነት በማያውቀው
በረከሰ ማንነት ነው – ንዒ ማርያም የምንልሽ
ከልዑሉ ሚካኤል ጋ ከደስተኛው ገብርኤል ጋ
ጽጌ ጸዐዳ ልጅሽን ይዘሽ
ነይ ርግባችን የምንልሽ
በሚገባ ንጽህና – ሆነን አይደለም ድንግል
ግን ነይ ስንልሽ አትቀሪም.... ትመጫለሽ አይደል?
ልባችን ቂምን ቋጥሮ በአፍ ዜማ ብቻ - ብንጠራሽም ንዒ ብንልም ድንግል
ርሕርሕተ ሕሊና እመ ትሕትና.....
ትመጫለሽ አይደል?
ስለተጠራው ስምሽ
ድንግል ትመጫለሽ አይደል?
ስለኪዳንሽ
ድንግል ትመጫለሽ አይደል?
አልቦ ምግባር ብንሆንም - እንደ ቃና ማድጋ
ማርያም አትቅሪ እኛ ጋ
ንዒ ስንል
አዛኝቱ ድንግል
ትመጫለሽ አይደል?
[ገጣሚ - ሀገሬ ኑሪ]
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete site link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ:
ሥርዓተ ማኅሌት ዘካልዓይ ጽጌ ወበዓለ በዓታ ለማርያም (የኹለተኛ ሳምንት ጽጌና የበዓታ ለማርያም ማኅሌት)
ግእዝና አማርኛ
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
አቤቱ ጽሎቴን ስማኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ጩኸቴም ከፊትህ ይድረስ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ፊትህንም ከእኔ ላይ አታዙርብኝ በጭንቀቴ ዕለት ጆሮዎችህ ያድምጡኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ በጠራሁህ ዕለት ፈጥነህ ስማኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለዘላለሙ ሃሌ ሉያ
ይህም ማለት፡ በልዕልናው ያለውን እግዚአብሔርን እናመስነው ፣ ዓለምን በአንዲት ቃል የመሠረተ እርሱ ፈጽሞ ምስጉን ነው።
📖መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ በህላዌ አካል ትክክል ለሚሆኑ ኩልያቶቻችሁ ሰላምታ ይገባል። ሥሉስ ቅዱስ ሆይ፤ ከእናንተ ከሦስቱ
አካላት አንዱ አካል እግዚአብሔር ቃል ይቅርታ ለማድረግ ዓለምን በጎበኘ ጊዜ የአባቶች ተስፋ በድንግል ማርያም ተፈጸመ። የነፃነት ዓርማ መስቀልም በቀራንዮ አደባባይ ተተከለ።
ዚቅ፦
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሐረገ ወይን፤እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕፁቂሃ ሐረገ ወይን፤እንተ በሥሉስ ትትገመድ ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከተ፤ሐረገ ወይን፤ሲሳዮሙ ለቅዱሳን፤ሐረገ ወይን፤ሠርዓ ሰንበተ በቃሉ ወጸገወ ሰላመ ለኩሉ።
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ የወይን ሐረግ፤ ሥሮቿ በምድር ጫፎቿ በሰማይ የወይን ሐረግ ፤ በሥሉስ ተቆርጣ የበረከት ዘለላ የምታፈራ የወይን ሐረግ ፤ የቅዱሳን ምግባቸው የወይን ሐረግ ፤ በቃሉ ሰንበትን ሠራ ሰላምንም ለኹሉ ሰጠ።
🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹
በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን፤ለዕረፍት ዘኮንኪ ትእምርተ(ጽላተ) ኪዳን፤ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ዕለተ ብርሃን፤ብኪ ይትፌስሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን፤ወብኪ ይወጽኡ ኃጥአን እምደይን፡፡
" መጽሐፍ በፈጣሪና በፍጡራን መካከል ለዕረፍት የተሾምሽ የቃል ኪዳን ምልክት ነሽ ብሎ እንደተናገረ፣ የሰንበታት ሰንበት የብርሃን ቀን ማርያም ሆይ፤ አበባ ያላት የገነት ጻድቃን በአንቺ ይደሰታሉ፤ ኃጥአንም በአንቺ ከኩነኔ ይወጣሉ"
🌷ወረብ
በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን ለዕረፍት ዘኮንኪ ትእምርተ ኪዳን/፪/
ብኪ ይትፌስሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን ብርሃን ዕለተ ብርሃን/፪/
ዚቅ
ሰንበቶሙ ይእቲ ለጻድቃን ትፍሥሕት፤ሰንበቶሙ ይእቲ ለኃጥአን ዕረፍት፤ኅቡረ ንትፈሳሕ ዮም በዛቲ ዕለት፡፡
" ለጻድቃን የደስታቸው ሰንበት ለኃጥአንም የዕረፍታቸው ሰንበት ይህቺ ናት በዚህች ዕለት በኅብረት እንደሰት"
🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹
ከመ ታቦት ሥርጉት በወርቀ ዓረብ ወተርሴስ፤በድንግልና ማርያም ሥርጉተ ሥጋ ወነፍስ፤ ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ፤ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ፤ እምዘ ጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ።
ማርያም ሆይ በአረብና በተርሴስ ወርቅ እንደ ተለበጠች ታቦት፣ በነፍስና በሥጋ በድንግልና የተለበጥሽ ነሽ፤ ኢያቄምና ሐና ቀንሞስና ቀናንሞስ የተባሉ ሽቱዎች ፤ መለኮት የጠበቀሽን አንቺን በሦስት ዓመት ካስገኙ በኋላ በቤተመቅደስ መኖር ተአምርን አሳየሽ።
🌷 ወረብ
እምዘ ጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ/፪/
ተአምረ ነቢር አርአይኪ ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ/፪/
ዚቅ
አንቲ ውእቱ ንጽሕት እምንጹሐን ድንግል ኅሪት ዘነበረኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ከመ ታቦት ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ ሥርግው በወርቅ ንጡፍ ወልቡጥ በዕንቍ ባሕርይ ዘየኃቱ ዘብዙኅ ሤጡ ከመዝ ነበርኪ በቤተ መቅደስ ወመላእክት ያመጽሑ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ ነበርኪ አሠርተ ወክልኤተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኀበ መላእክት ስቴኪኒ ስቴ ሕይወት ውእቱ ወመብልዕኪኒ ኅብስት ሰማያዊ።
ከንጹሓን ይልቅ ንጽሕት የሆንሽ አንቺ ነሽ ከማይነቅዝ ዕንጨት እንደ ተሠራ በወርቅ እንደ ተጌጠና ዋጋው ብዙ በሆነ በሚያበራ ዕንቁ እነደተለበጠ ታቦት በቤተ መቅደስ ውስጥ የኖርሽ የተመረጥሽ ድንግል ነሽ። እንዲህ ሆነሽ በቤተ መቅደስ ውስጥ ኖርሽ መላእክትም ዘወትር ምግብሽን ያመጡ ነበር በመላእክት እየተጽናናሽ እንዲህ ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖርሽ። መጠጥሽም የሕይወት መጠጥ ነበር ምግብሽም የሰማይ ኅብስት ነበር።
🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።
" በመንጻት ወራት፣ በተአምርም ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ስትገቢ፤ ነጭ እና ቀይ አበባ የሚባል ልጅሽን ታቅፈሽ፤ ከኀዘኔ ታረጋጊኝ ዘንድ ርግቤ ሆይ ነይ፤ መልካም እናቴ ሆይ ደስ የሚል ዜና ከያዘ ከገብርኤልና፤ እንደ አንቺ ርኅሩኅ ከሆነ ከሚካኤልም ጋራ ነይ።"
🌷ወረብ
ንዒ ርግብየ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል/፪/
ወንዒ ሰናይትየ ወንዒ ሰናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ/፪/
ዚቅ
ንዒ ርግብየ አግዓዚት ከመ ጎሕ ሠናይት ታቦተ መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን ዕፀ ጳጣስ ደብተራ ፍጽምት ማኅደረ መለኮት።
እንደ ማለዳ ብርሃን መልካም የሆንሽ ፤ ቅድስተ ቅዱሳን የተባልሽ የመቅደስ ታቦት ፤ የማትቃጠለዋ ቁጥቋጦ ተክል፤ የመለኮት ማደርያ ፍጽምት ድንኳን ነጻ አውጪዋ ርግቤ ሆይ ነይ።
ዓዲ ዚቅ
ንዒ ርግብየ ኲለንታኪ ሠናይት ፀምር ፀዓዳ እንተ አልባቲ ርስሐት መሶበ ወርቅ እንተ መና በትረ አሮን እንተ ሠረፀት።
ኹለመናሽ መልካም ፤ እድፍ የሌለብሽ ነጭ ፀምር ፣ መና ያለብሽ መሶበ ወርቅ፤ የበቀለች የአሮች በትር የተባልሽ ርግቤ ሆይ ነይ።
ወቦ ዘይቤ ዚቅ
ይዌድስዋ ትጉሃን፤ይቄድስዋ ቅዱሳን፤ሰሎሞን ይቤላ ርግብየ ሠናይት፤ጳውሎስኒ ይቤላ ደብተራ ፍጽምት፤ዳዊትኒ ይቤላ ስምዒ ወለትየ ወርይዪ ወአጽምዒ ዕዝንኪ
ትጉሃን ያወድሷታል ፤ ቅዱሳን ይቀድሷታል(ያመሰግኗታል) ፤ ሰሎሞን መልካሟ ርግቤ ይላታል ፤ ጳውሎስ ፍጽምት ድንኳን ይላታል፤ ዳዊት ልጄ ሆይ ስሚ እዪ ጆሮዎችሽንም አዘንብዪ ይላታል።
🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቄ ባሕርይ ዘይኀቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኩሎ ታሰግዲ ሎቱ ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።
"እመቤቴ! የሞቱ መታሰቢያ፤ የስሙ ምልክት የተጻፈብሽ፤ ከሚያበራ የባሕርይ እንቊ የጠራሽ የራስ ወርቅ ክበብ ነሽ፤
የአበባ ጉንጉን የተሣለብሽ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ ዘውድ ማርያም ሆይ!! አንቺ ሁሉን ታሰግጂለታለሽ እሱ ግን ለአንቺ ይሰግዳል።"
🌷ወረብ
ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየሐቱ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/
ማርያም አክሊለ ጽጌ ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ/፪/
ዚቅ
ከርካዕ ዘተተክለት በቤተ መቅደስ፤መራኁቱ ለጴጥሮስ፤አንቲ ውእቱ ደብተራ ስምዕ ዘጳውሎስ፤አማን አክሊሉ ለጊዮርጊስ
#ቅናት
ቅናት እና ምቀኝነት እንደ አረም በውስጣችን የምያድጉ ክፉ የሓጥያት መንሰሄዎች ናቸው!!
#በቅናትና በምቀኝነት የተለከፈ ልብ ሁል ጊዜ የሚያስበው ክፉ የሆኑ ነገሮችን መፈፀም ብቻ በመሆኑ መፃሓፍ ቅዱሳችን እንደሚለው” ሞት ወደ አለም የገባው በስይጣን ቅናት ነው” እንደሚለው ቅናት የሁሉም ክፉ ነገሮች መሰረት በመሆኑ ከዝህ ክፉ ስሜት ልንጠነቀቅ ያስፈልጋል
#ቅናት እጅግ_በጣም_አሳሳቢ በሕይወታችን እየተመላለሰ የምቀኝነትን ስሜት የሚፈጥር “አደገኛ በሽታ ነው”
++++ ምቀኝነት ደግሞ ክፉ ነገሮችን እንድንፈፅም ስለ ምያነሳሳን ትልቅ እና አደገኛ ሓጥያት ነው
+++++++ቅናት እና ምቀኝነት በልባችን ውስጥ እንደ አረም በማደግ መልካም ፍሬን እንድያፈራ በእግዚአብሔር ቃል በልባችን ውስጥ የተተከለውን እፅዋት እንዳያድግ ሰለምከለክለውና ተፅኖ ስለሚፈጥርበት የልባችንን ሰላም በመንሳት የታመመና የተሸበረ ልብ እንዲኖረን ያደርጋል ።
#የካህናት አለቆች በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የሞት ፍርድ ያስፈረዱበት በቅናት መንፈስ ተነሳስተው ነው ።
#ቅናት የሁሉም ሓጥያት ምንጭ መሆኑን በመረዳት ይህንን ክፉ ሓትያት ለማስወገድ እግዚአብሔር ፀጋውን እንዲሰጠን ልባችንን ክፉ ነገር እንድናደርግ ለሚገፋፋን ቅናትና ምቀኝነት ዘግተን በምትኩ ደግሞ እግዚአብሔር በፀጋ እንድሞላው መጸልይ እና ልባችንን ለርሱ ብቻ መክፈት ይጠበውብናል።
ለመቀላቀል 👉