3. የተቋቋመው ኮሚቴ ከቤተ ክርስቲያኒቱ የሕግ ድንጋጌ ውጭ የተቋቋመ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን የአስተዳደር ሥርዓት ውጭ ላሉ አካላት አሳልፎ ለመስጠትና ርካሽ ተወዳጅነትን ከመፈለግ አንጻር የተቋቋመ ኮሚቴ ነው ተብሎ የተገለጸውን በተመለከተ፡- በመጀምሪያ ደረጃ እናት ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ደም የተመሠረተችው በማህበረ ሐዋርያትና በማህበረ ምዕመናን ላይ እንደመሆኑ መጠን አንዱ የውስጥ አንዱ የውጭ በማለት የሚገለጽ አስተምህሮ ሳይኖራት የውስጥና የውጭ ተብሎ የተገለጸው ከፋፋይ ሐሳብ
ተቀባይነት የሌለው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ከ7ቱ አጣሪ ኮሚቴዎች ውስጥ 3ቱ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነጽ ጽ/ቤቱ የመምሪያ ኃላፊዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ደግሞ በቤተ ክርስቲያን ልጅነታቸው በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፍ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሲያገለግሉ የቆዩና እራሳቸው የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እና ዋና ሥራ አስኪያጅም የቤተ ክርስቲያን ልጅነታቸውን እና ሙያዊ እውቀታቸውን በማረጋገጥ ካሁን ቀደም በሀገረ ስብከቱ ሥር ያሉትን የአሠራር ችግር አጣርተው እንዲያቀርቡ መድበዋቸው የነበሩ በመሆናቸው የአሠራር ችግሩን ስለሚያውቁት ያላቸውን ልምድ ለመጠቀም ታስቦ ባላቸው ሙያዊ እውቀት በአጣሪነት የተመደቡ ሲሆን ሀገረ ስብከቱ እራሱ በአጣሪነት ሲመድባቸው የውስጥ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በአጣሪነት ሲመድባቸው ደግሞ የውጭ የሚሆኑበት ምንም አይነት የሕግ አግባብ የሌለ ከመሆኑም በተጨማሪ እንኳንስ ውሉደ ክህነት /ሀብተ ክህነት/ ያላቸውን አጣሪዎች ይቅርና የቤተ ክርስቲያናችንን የቅርብ ጊዜ የችግር አፈታት መለስ ብለን ብንመለከት ለረጅም አመታት ከሁለት ተከፍሎ የቆየውን ሲኖዶሳዊ አስተዳደር እንኳን ገምግመውና አወያይተው ወደ አንድት ከመለሱት ብፁዓን አባቶች ጋር ትልቁን ሚና የተወጡት ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደራዊ መዋቅር ውጪ የሆኑት ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋይ ምዕመናን መሆናቸውን ለተመለከተና ለሚያውቅ ሰው የሀገረ ስብከቱን የመልካም አስተዳደር ችግር አጥንተው እንዲያቀርቡ ከተመደቡት የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋይ ልጆች ጋር ሲነጻጸር ቢያስመሠግን እንጅ የሚያስነቅፍ አለመሆኑን የታወቀ ሲሆን ሀገረ ስብከቱ የተመደቡት አጣሪ ኮሚቴዎች ሥራቸውን እንዳያከናውኑ እያቀረበው ያለው በመላምት የተሞላ ምላሽ ሲታይ ዝርዝር ጉዳዩ ቢጣራ በርካታ ችግሮችና የአሠራር ግድፈቶች መኖራቸው ገሀድ ይወጡብኛል በሕግም ያስጠይቁኛል ከሚል ስጋት የመነጨ መሆኑን ከመያረጋግጥ በስተቀር የበላይ መ/ቤት የሆነው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አስተዳደር ጉባኤ የመደበውን አጣሪ ኮሚቴ ሀገረ ስብከቱ አልቀበልም የማለት ስልጣን የሌለው መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
4. የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱም ሆነ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚመሩት ተጣሪነታቸው ለቅዱስ ሲኖዶስ በሆኑት ሊቃነ ጳጳሳት እንደመሆኑ መጠን ሊቀ ጳጳስ ያልመራው ኮሚቴ ሊያጣራን አይችልም የተባለውን በተመለከተ፡- በመጀመሪያ መታየት ያለበት የሕጎች ሁሉ የበላይ ሕግ በሆነው በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አንቀጽ 52 ንዑስ ቁጥር 8 እና አንቀጽ 57 ንዑስ ቁጥር 3 የሕግ ድንጋጌ መሠረት የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት ተጠሪነቱ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እንደመሆኑ መጠን የሁሉም አህጉረ ስብከት የአሠራር ግድፈቶች የሚጣሩት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በሚመድባቸው አጣሪዎች መሆኑ አጠያያቂ ካለመሆኑም በላይ እራሳችሁ አሁን አንጣራም ባዮቹም ጭምር በኃላፊነት የተመደባችሁት ሊቀ ጳጳስ በመራው አጣሪ ኮሚቴ ሳይሆን የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በመደበው አጣሪ ኮሚቴ ተጣርቶ በቀረበው ሪፖርት መነሻነት በተሰጠ ውሳኔ መሆኑ ሊሠመርበት ይገባል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሀገረ ስብከቱ ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱን እንደሽፋን አቀረባቸው እንጂ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አጣሪ የመደበው አጠቃላይ የጽ/ቤቱ አሠራር ለመገምገም እንጂ በተለየ ሁኔታ የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ ለማጣራት የመደበው አጣሪ የሌለ መሆኑን እየገለጽን በማጣራት ሂደቱ ብፁዕ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የሚመለከቱ ጉዳዮች ካጋጠሙ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ መሠረት የብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ ጉዳይ የሚታየው እስካሁንም ሲደረግ እንደቆየው ሁሉ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የሚታይ መሆኑን እየገለጽን ለማጣራት ሥራው ትልቁና ዋናው ጉዳይ በአብዛኛው ቅጥር፣ ዝውውርና እድገትን በጀትና ሌሎች የሥ አፈጻጸሞች አስመልክቶ በተፈጸሙ የአሠራር ግድፈቶች ዙሪያ እንደመሆኑ መጠን እነዚህ ሥራዎች ደግሞ ከሥራ አስኪያጅ ጀምሮ በተዋረድ ባሉት የሥራ ክፍሎች እንጂ በሊቀ ጳጳሱ የሚፈጸሙ ባለመሆኑ ሀገረ ስብከቱ የሊቀ ጳጳሱን ተጠሪነት እንደሽፋን በመጠቀም ለማጣራት ሥራው መሠናክል ከመሆን ሊቆጠብ ይገባል ለማለት እንወዳልን፡፡
5. አዲስ አበባ ሀ/ስብከት ከሌሎች አህጉረ ስብከቶች የሚለይበት ምንም አይነት የሕግ አግባብ የለም የተባለውን በተመለከተ፡- በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አንቀጽ 57 ንዑስ ቁጥር 3 ላይ ከሌሎች አህጉረ ስብከቶች የተለየ በመሆኑ በቅዱስ ሲኖደስ ጸድቆ በሚመጣ ልዩ ደንብ እንደሚተዳደር በግልጽ ተደንግጎ እያለ እና ይህንም ተከትሎ በ2015 ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ ጽድቆ ሥራ ላይ የዋለው የሀገረ ስብከቱ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 10 ላይ በግልጽ እንደተደነገገው ሀገረ ስብከቱን የመቆጣጠርና በበላይነት የመምራት ስልጣኑ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ እንደመሆኑ መጠን ለችግሮቹ መፍትሔ ለመስጠት አጣሪ ኮሚቴ መመደቡ በሕግ የተጣለበትን ኃላፊነቱን ተወጣ ከሚያስብል በስተቀር ሕግን እንደጣሰ ተደርጎ የተሰጠው የሀገረ ስብከቱ ምላሽ ተቀባይነት የሌለውና ሕገ ቤተ ክርስቲያኑንና መተዳደሪያ ደንቡን ካለመረዳት የተሰጠ ምላሽ መሆኑን ሊሠመርበት ይገባል፡፡
6. በሌሎች አህጉረ ስብከቶች ብዙ ችግር እያለ እነዚያን ችግሮች አጣርቶ ከማረም ይልቅ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን ብቻ የሚጣራ ኮሚቴ መሠየሙ ምክንያታዊ አይደለም የተባለውን በተመለከተ፡- ሀገረ ስብከቱ በመረጃ እጥረት ይህን ይበል እንጅ እንኳንስ በመቶዎች የሚቆጠሩ አገልጋዮች በእንባ የታጀበ አቤቱታ የሚቀርብበትን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን ይቅርና በይግባኝ ቅሬታ ለሚቀርቡ የአንድ ግለሰብ ወይም አጥቢያን ጉዳይ ሳይቀር ትክክለኛ ውሳኔ ለመሥጠት ይቻል ዘንድ ጠረፍ ያሉ አህጉረ ስብከት ድረስ ሳይቀር አጣሪ ኮሚቴ በመላክ ችግር ፈቺ የሆኑ ውሳኔዎችን ስንሰጥ የቆየን መሆኑን ሀገረ ስብከቱ በአካል ተገኝቶ በርካታ ማህደሮችን አይቶ እውነታውን ማረጋገጥ የሚችል መሆኑን እያሳወቅን አብነት ት/ቤት ተበትኗል በሚል ከተለያዩ የሶሻል ሚዲያ ተወስዶ የተጠቀሰውን ሐሳብ በተመለከተ ሀገረ ስብከቱ ተበተነ ለማለት የፈለገው አብነት ት/ቤት መ/ር ለሥራ ጉዳይ መጥተው አዲስ አበባ ስለሚገኙ በአካል አግኝቶ እውነታውን ማረጋገጥ የሚችል መሆኑን እየገለጽን፤ ከዚህም በላይ የተለየ መረጃ አለኝ የሚልም ከሆነ ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች በአካል ተገኝተው አጣርተው ሪፖርት እንዲያቀርቡ ከታላቅ አክብሮት ጋር በመጋበዝ በሩ ክፍት መሆኑን እያረጋገጥን የዓመት እረፍታቸውን አስፈቅደው በእረፍት ላይ ያሉ የሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ለምን አዲስ አበባ መጡ የሚለው እሳቤ ግን ሀገረ ስብከቱ ሌሎችን ለመተቸት ምን ያህል ብዙ እንደደከመ የሚያረጋጥ በመሆኑ ከዚህ በላይ ምላሽ መስጠት
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ጥቅምት_2_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2ኛ ቆሮ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ ነገር ግን የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን፤
⁸ በሁሉ እንገፋለን እንጂ አንጨነቅም፤ እናመነታለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም፤
⁹ እንሰደዳለን እንጂ አንጣልም፤ እንወድቃለን እንጂ አንጠፋም፤
¹⁰ የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን ይገለጥ ዘንድ ሁልጊዜ የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን።
¹¹ የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሚሞት ሥጋችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋን የሆንን ከኢየሱስ የተነሣ ዘወትር ለሞት አልፈን እንሰጣለንና።
¹² ስለዚህ ሞቱ በእኛ ሕይወቱም በእናንተ ይሠራል።
¹³ ነገር ግን፦ አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን፥ እኛ ደግሞ እናምናለን ስለዚህም እንናገራለን፤
¹⁴ ጌታን ኢየሱስን ያስነሣው እኛን ደግሞ ከኢየሱስ ጋር እንዲያስነሣን ከእናንተም ጋር እንዲያቀርበን እናውቃለንና።
¹⁵ በብዙዎች በኩል የተትረፈረፈው ጸጋ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋናን ያበዛ ዘንድ፥ ሁሉ ስለ እናንተ ነውና።
¹⁶ ስለዚህም አንታክትም፥ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል።
¹⁷-¹⁸ የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።
⁶ እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤
⁷ እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።
⁸ በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤
⁹ በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።
¹⁰ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁማል ያበረታችሁማል።
¹¹ ለእርሱ ክብርና ኃይል እስከዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 20
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ሁከቱም ከቀረ በኋላ ጳውሎስ ደቀ መዛሙርቱን አስመጥቶ መከራቸው፥ ተሰናብቶአቸውም ወደ መቄዶንያ ይሄድ ዘንድ ወጣ።
² ያንም አገር እያለፈ በብዙ ቃል ከመከራቸው በኋላ ወደ ግሪክ አገር መጣ።
³ በዚያም ሦስት ወር ተቀምጦ ወደ ሶርያ በመርከብ ሊሄድ ባሰበ ጊዜ፥ አይሁድ ሴራ ስላደረጉበት በመቄዶንያ አልፎ ይመለስ ዘንድ ቆረጠ።
⁴ የሸኙትም የቤርያው ሱሲጳጥሮስ ከተሰሎንቄ ሰዎችም አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ የደርቤኑም ጋይዮስና ጢሞቴዎስ የእስያ ሰዎችም ቲኪቆስ ጥሮፊሞስም ነበሩ፤
⁵ እነዚህም ወደ ፊታችን አልፈው በጢሮአዳ ቆዩን።
⁶ እኛ ግን ከቂጣ በዓል ቀን በኋላ ከፊልጵስዩስ በመርከብ ተነሥተን በአምስት ቀን ወደ ጢሮአዳ ወደ እነርሱ ደረስንና በዚያ ሰባት ቀን ተቀመጥን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ጥቅምት_2_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"በእግዚአብሔር ተወከልኩ እፎ ትብልዋ ለነፍስየ። አዐይል ውስተ አድባር ከመ ዖፍ። እስመ ናሁ ኀጥአን ወሰቁ ቀስቶሙ"። መዝ 10፥1-2።
"በእግዚአብሔር ታመንሁ፤ ነፍሴን፦ እንደ ወፍ ወደ ተራሮች ተቅበዝበዢ እንዴት ትሉአታላችሁ? ኃጢአተኞች እነሆ ቀስታቸውን ገትረዋልና፥ ፍላጻቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋልና፥ ልበ ቅኖችን በስውር ይነድፉ ዘንድ"። መዝ 10፥1-2።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ጥቅምት_2_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።
¹¹ ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።
¹² ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።
¹³ እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም።
¹⁴ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።
¹⁵ መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል።
¹⁶ መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።
¹⁷ እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም።🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🌹የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #እመቤታችን_የማርያም_ቅዳሴ ነው። መልካም የአባ ሕርያቆስና የአቡነ ማትያስ የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete The text contains the robot command ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete site link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
መልስ፡ ሮሜ 9 ቅድመ-ውሳኔን ያረጋግጣልን? /ክፍል ኹለት/
/ሮሜ 9 ፥ 10 - 19/
“10 ይህ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ርብቃ ደግሞ ከአንዱ ከአባታችን ከይስሐቅ በፀነሰች ጊዜ፥
11 ልጆቹ ገና ሳይወለዱ፥ በጎ ወይም ክፉ ምንም ሳያደርጉ፥ ከጠሪው እንጂ ከሥራ ሳይሆን በምርጫ የሚሆን የእግዚአብሔር አሳብ ይጸና ዘንድ፥
12 ለእርስዋ፦ ታላቁ ለታናሹ ይገዛል ተባለላት።
13 ያዕቆብን ወደድሁ ኤሳውን ግን ጠላሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።
14 እንግዲህ ምን እንላለን? በእግዚአብሔር ዘንድ ዓመፃ አለ ወይ? አይደለም።
15 ለሙሴ፦ የምምረውን ሁሉ እምረዋለሁ ለምራራለትም ሁሉ እራራለታለሁ ይላልና።
16 እንግዲህ ምሕረት ለወደደ ወይም ለሮጠ አይደለም፥ ከሚምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ።
17 መጽሐፍ ፈርዖንን፦ ኃይሌን በአንተ አሳይ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ይነገር ዘንድ ለዚህ አስነሣሁህ ይላልና።
18 እንግዲህ የሚወደውን ይምረዋል፥ የሚወደውንም እልከኛ ያደርገዋል።
19 እንግዲህ ስለ ምን እስከ አሁን ድረስ ይነቅፋል? ፈቃዱንስ የሚቃወም ማን ነው? ትለኝ ይሆናል።”
/2ኛ ጴጥ 3 ፥ 15-17/
“15 የጌታችንም ትዕግሥት መዳናችሁ እንደ ሆነ ቍጠሩ። እንዲህም የተወደደው ወንድማችን ጳውሎስ ደግሞ እንደ ተሰጠው ጥበብ መጠን ጻፈላችሁ፥ በመልእክቱም ሁሉ ደግሞ እንደ ነገረ ስለዚህ ነገር ተናገረ።
16 በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ፥ ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ።
17 እንግዲህ እናንተ፥ ወዳጆች ሆይ፥ ይህን አስቀድማችሁ ስለምታውቁ፥ በዓመፀኞቹ ስሕተት ተስባችሁ ከራሳችሁ ጽናት እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ።”
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ጥቅምት_1_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ቆሮንቶስ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³² ነገር ግን ያለ አሳብ ልትኖሩ እወዳለሁ። ያላገባው ጌታን እንዴት ደስ እንዲያሰኘው የጌታን ነገር ያስባል፤
³³ ያገባው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ እንዲያሰኛት የዓለምን ነገር ያስባል፥ ልቡም ተከፍሎአል።
³⁴ ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፤ የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንድታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።
³⁵ ይህንም ለራሳችሁ ጥቅም እላለሁ፤ በአገባብ እንድትኖሩ ሳትባክኑም በጌታ እንድትጸኑ ነው እንጂ ላጠምዳችሁ ብዬ አይደለም።
³⁶ ዳሩ ግን ማግባት ወደሚገባው ዕድሜ በደረሰ ጊዜ ስለ ድንግልናው ያፈረ ሰው ቢኖር፥ የወደደውን ያድርግ፤ ኃጢአት የለበትም፤ ይጋቡ።
³⁷ ሳይናወጥ በልቡ የጸና ግን ግድ የለበትም፥ የወደደውን እንዲያደርግ ተፈቅዶለታል፤ ድንግልናውንም በልቡ ይጠብቅ ዘንድ ቢጸና፥ መልካም አደረገ።
³⁸ እንዲሁም ድንግልን ያገባ መልካም አደረገ ያላገባም የተሻለ አደረገ።
³⁹ ሴት ባልዋ በሕይወት ሳለ የታሰረች ናት፤ ባልዋ ቢሞት ግን በጌታ ይሁን እንጂ የወደደችውን ልታገባ ነጻነት አላት።
⁴⁰ እንደ ምክሬ ግን እንዳለች ብትኖር ደስተኛ ናት፤ እኔም ደግሞ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ያለ ይመስለኛል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹-² እንዲሁም፥ እናንተ ሚስቶች ሆይ፥ ከባሎቻችሁ አንዳንዱ ለትምህርት የማይታዘዙ ቢኖሩ፥ በፍርሃት ያለውን ንጹሑን ኑሮአችሁን እየተመለከቱ ያለ ትምህርት በሚስቶቻቸው ኑሮ እንዲገኙ ተገዙላቸው።
³ ለእናንተም ጠጕርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ፥
⁴ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 17
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ ወዲያውም ወንድሞች ጳውሎስንና ሲላስን በሌሊት ወደ ቤርያ ሰደዱአቸው፥ በደረሱም ጊዜ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገቡ፤
¹¹ እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና፦ ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።
¹² ስለዚህም ከእነርሱ ብዙ፥ ከግሪኮችም የከበሩት ሴቶችና ወንዶች ጥቂት ያይደሉ፥ አመኑ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ጥቅምት_1_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ተዘከር እግዚኦ ከመ መሬት ንሕነ። ሰብእሰ ከመ ሣዕር መዋዕሊሁ። ወከመ ጽጌ ገዳም ከማሁ ይፈሪ"። መዝ 102፥14-15።
"ፍጥረታችንን እርሱ ያውቃልና፤ አቤቱ፥ እኛ አፈር እንደ ሆንን አስብ። ሰውስ ዘመኑ እንደ ሣር ነው፤ እንደ ዱር አበባ እንዲሁ ያብባል"፤ መዝ 102፥14-15።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ጥቅምት_1_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁵ ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?
²⁶ ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፥ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?
²⁷ ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው?
²⁸ ስለ ልብስስ ስለ ምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፤
²⁹ አይደክሙም አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም።
³⁰ እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት?
³¹ እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤
³² ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና።
³³ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።
³⁴ ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🌹የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጎድጓድ_ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
የሥራ አስኪያጆቹ ፣የሥልጣን ትንቅንቅ፣።
ቤተክርስቲያን በምን አይነት አጣብቂኝ ውስጥ እንዳለች በቂ አመላክች ነው።
የበላይና የበታች የሌለው መ/ቤት ከሆነ ቆይቷል። የት ይደርሳሉ ያልናቸው እንዲህ ሁነው ስናያቸው እጅግ ያሳዝናል።
ወደፊትስ ማንን እንመን። ከማን ምን እጠብቅ። ከጳጳሳት ውስጥ ከአቡነ አብርሃም በላይ አቅም የነበረው ነበር ወይ?
#ከወጣቶችስ ከየማነ የተሻለ ልምድና የትምህርት ዝግጅት ነበር ወይ? ቤቱ የላይኛው መዋቅር ሰው አልባ ስለሆነ፣ ሲኖዶሱም ሰብሳቢና ወሳኝ በማጣቱ ፣የአቅም መለካካት እየታየበት ቀጥሏል። ሌቦች በአደባባይ ሲፎክሩ ፣ነጹሓን ከቤታቸው ሁነው ሲያዝኑ አየን ሰማን። ወደየት እየሄድን ነው። የመንገዱ መጨረሻስ የት ይሆን?
ሀገረ ስብከቱ ሌብነት የለኝም ብሎ ደፍሮ ሲናገር. ፣ ሌብነትን ሥራ ብሎ ወደ ማመን ደረጃ አድጎ ከሆነ እንጅ ያለ ጉቦ ቅጥር እንደሌለ ከበቂ በላይ መረጃዎች አሉ፣።
እኔ እራሴ አንድ የድጓ መምህር ለመርዳት የማውቀውን ወዳጄን ስደውልለት ወዳጄ ቃል በቃል ያለኝ የእኔ ድርሻ. ይቀር እንደሆነ እንጅ ያለ ገንዘብ አይሆንም ነው ያለኝ።
በጣም የማከብረው ወዳጄ ቢችል እኔን ለመታዘዝ ፈቃደኛ ነበር። እኔም ስለአመንኩበት ነበር የደወልኩት ። የቤቱ ሕግ ግን ያለ ጉቦ ስለማይሆን ነው።
#ደግሞ እኮ ጉቦው ተቀጥሮ ሲሰራ ለሰባት ዓመታት በነጻ የሚያስገለግል ነው። የሰባት ዓመት ደመወዝን ጉቦ ከፍሎ ነው የሚቀጠረው ፣ ይህን የለም ብሎ ማስተባበል አይቻልም ብቻ ሳይሆን ለእነዚህ ሰዎች ጉቦ ሌላ መልክ ኑሮት እንዳይሆን ያስብላል። ሥራህ ከሆነ ነውር መሆኑ ይቀራል ። ሲፈክሩ የነበሩ አለቆች በሙሉ በመቶ ሺህዎች ከፍለው የተሾሙ ናቸው።
ሀገረ ስብከቱ ላይ ደጅ ጸንተው የሚሾሙት ለመስረቅ እንጅ ለመሥራት እንዳልሆነም ግልጽ ነው።
ችግሩ ታውቆ ያደረ ነው። በሌላ ጉዳይ ተጋጭተው፣ ወደ አደባባይ ሲወጡ ግን ሕዝቡ የሚሰማውን አጀንዳ የግጭት መንስኤ አድገውታል።
በዚህ ጊዜ ለጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ፣ ትይዩ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ሆነ።
እውነት ለመናገር፣ ሰውዬው የማነ ሁኖ ቅዱስነታቸውም የኔ ሰዎች አይሳሳቱም የሚል አቋም ስላላቸው እንጅ ሌላ ቢሆን ኑሮ ከሥራም ከደመወዝ ለመታገድ ያዋቀረው ኮሚቴ በቂ ነው።
አቡነ አብርሃም ወቅቱንና ከላይና ከታች ያለውን ትስስር አለመረዳታቸውና ከዚህ ውጥቅጥ ውስጥ መግባታቸው ገርሞኛል።
ቤተክህነቱ የሚጠራው ከመዋቅሩ አስፈጻሚ ሲኖር ነው። ለቤተክርስቲያኗ ወሳኙ ፓትርያሪኩ ናቸው ።
የጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አጋዥ ባለመኖሩ ብዙ መሥራት እየቻሉ የሥራ ዘመናቸው በውዝግብ አለፈ።
ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሙስና ባህል ነው። ሙስና ባለበት መልካም አስተዳደር አይታሰብም።
የቤተክህነት መልካም አስተዳደር ምንጩ ርእሰ መንበሩ ፓትርያርኩ ናቸው።
እሳቸው የዳኝነት አቅም ፈጥረው እስካልሰሩ ድርስ ምንም መፍትሄ አይኖርም።
ከዚህም ከዚያም የጳጳሳት ሹመት ምንጩ ፣ርዕሰ መንበሩ ናቸው። ቤተክርስቲያን ያለችው በተአምር ነው ። እንደሰዎቹ አያያዝ ፣የለችም ነበር።
በዚህም በዚያም ብንሸፋፍነው እውነቱ ይህ ነው። የጠቅላይ ቤተክህነቱ ሥራ ሥራ አስኪያጅ የስልጣን ልዕልና እየተሸረሸረ ያለው ከላይ የሚያባላ ዳኛ ስላለ ነው።
ሀገረ ስብከቱ ላይ በነበረው ስብሰባ የተናገሩት ሰዎች አየኋቸው። እነሱ እየሰማሁ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ይቅር ባይነት ወይም ታገሽነትና የፍርድ መዘግየት አስብ ነበር።
ኃጢአት በበዛበት የእግዚአብሔር ቸርነት ይበዛል ያለውን ቅዱስ ኤፍሬምን ለምን ያህል ጊዜ ብዬ እንደሚበዛ እጠይቀውና እኔ በብስጭት መሞነጫጨሬን እተወው ነበር። አለማወቅ ደጉ ግን በምሰማው ሐሰት በጠፋው እውነት እንድተክዝና ታዛቢ አድርጎኛል ። ኤፍሬም ሆይ ያየኸውን ጸጋ ለእኔም ግለጽልኝ።
ለማኛውም ሀገሪቱም ቤተክርስቲያኗ ብዙ ችግሮች አሉባት ፣እውነተኛ ችግሮቿ፣ ለሀገሪቱ ፖለቲከኞች፣ ለቤተክርስቲያኗ ጳጳሳትና አለቆች ናቸው። ህዝቡ ሆነ ምእመኑ እውነተኛ ባለ መሆን ያግዛቸዋል። በመንደር ቲፎዞ በመሆን ያጅባቸዋል።
ለማኛውም ለሁሉም ልቦና ይስጥልን ።
@ Fresew Demis
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
አስፈላጊ ነው ብለን አናምንም፡፡
7. ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በየጊዜው የሀገረ ስብከቱን የፋይናንስ ሂደት ኦዲት እያደረገ ያገኘው የአሠራር ጉድለት የሌለና የወሰደውም የመስተካከያ እርማት ሳይኖር አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውጥ ሁለተኛ አጣሪ መመደቡ አሳማኝ አይደለም የተባለውን በተመለከተ፡- ሀገረ ስብከቱ በምላሹ ተራ ቁጥር 2 ላይ እንደገለጸው በ2015 ዓ.ም በተደረገው ማጣራትና ኦዲት ሀገረ ስብከቱ ከ500 ሚሊዬን ብር በላይ ወጭ የሚያስወጣ ሕንፃ ለመገንባት ያለ ውድድር በተጋነነ ዋጋ አማካሪ ድርጅት በመቅጠርና
ክፍያ በመፈጸም እንዲሁም የኮንትራክተር ውደድሩን ከጨረታ ሕገ ደንብ መርህ ውጭ በመምራት የሚመለከተው የበላይ አካል ሳያጸድቀው እና ሳይፈቅድ ቅድመ ክፍያ 170,000,000.00 (አንድ መቶ ሰባ ሚሊዮን ብር) በመክፈል እና በሌሎችም በርካታ የአሠራር ግድፈቶች በወቅቱ የነበሩት የሥራ ኃላፊዎች በሙሉ እንዲነሱ በማድረግ ዛሬ አንጣራም ባዮቹ የተመደቡ መሆናቸው እየታወቀ እስካሁን የተገኘ ጉድለት የለም ተብሎ የተሰጠው ምላሽ ተገቢነት የሌለው ከመሆኑም በላይ ከአሁን ቀደም የተላኩት የሀገረ ስብከቱን የሥራ አፈጻጸም የሚያጣሩ ሳይሆን ሀገረ ስብከቱ አላግባብ ከሥራ አፈናቅሎናል በማለት አቤቱታ ያቀረቡትን 439 አገልጋይ ሠራተኞች ጉዳይ ብቻ ከሀገረ ስብከቱ ጋር በመነጋር ወደ ሥራ እንዲመለሱ ለማድረግ ሲሆን አሁን የተመደበው አጣሪ ኮሚቴ ደግሞ ከሦስቱም ሚዲያዎች በዜና የተዘገበውን የሙስናና ብልሹ አሠራር እንዲሁም ሌሎች አጠቃላይ የሀገረ ስብከቱን የአሠራር ጉድለቶች በሙሉ አጣርቶ ከመፍትሔ ሐሣብ ጋር የሚያቀርብ የሕግና የሒሣብ ባለሙያዎችን ያካተተ ልዩ አጣሪ ኮሚቴ መሆኑ እየታወቀ ጉዳዩን በመሸፋፈንና በማድበስበስ ላለመጠራት የሚደረገው ጥረት ተቀባይነት የለውም፡፡
8. ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የመደበው አጣሪ ልክ እንደ ኦሮሚያ እና ትግራይ የተከሠተውን የመከፋፈል ችግር በአዲስ አበባ ለማስፋፋት እና ሁከት ለማንገስ ነው የተባለውን በተመለከተ፡- በመጀመሪያ ደረጃ ችግሮች ተጣርተው መፍትሔ እንዳይሰጥ አልጣራም በማለትና ስህተት መኖሩን በሚያረጋገጥ ሁኔታ ልዩ ልዩ ድብቅ ስብሰባዎችን ለአድማ በመጥራት ሁከት ለመፍጠር አበክሮ እየሠራ ያለው ሀገረ ስብከቱ ሆኖ እያለ ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል እንዲሉ አበው ሀገረ ስብከቱ የራሱን ችግር ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ለመቀጸል የሄደበት መንገድ አግባብነት የሌለውና ጉዳዩ የሚመለከታቸው መንግስታዊ አካላትም ልዩ ትኩረት ሰጥተው ሊከታተሉት የሚገባ አድራጎት መሆኑን እያሳሰብን እንደ ኦሮሚያ እና ትግራይ እንከፋፈላለን የሚለው የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕጎች በሙሉ የሚጻረር ያልተገባ እሳቤ ግን የአንዳንድ የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች የግል የሕልም ፍላጎት እንጂ ከሀገረ ስብከት እስከ አጥቢያ ለቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነትና ሐዋርያዊ ተልዕኮ ሌት ከቀን የሚደክሙትን አገልጋዮች እና ተገልጋይ ምዕመናንን የማይወክል እሳቤ መሆኑን ስለምንረዳ የተለየ ምላሽ አይኖረንም፡፡
በአጠቃላይ ሀገረ ስብከቱ ያሉበትን የአሠራር ክፍተቶችና የመልካም አስተዳደር ችግርች ተጣርተው በሚሠጠው ውሳኔ መሠረት ችግሮቹ እንዲፈቱ የበኩሉን ድጋፍና ትብብር ማድረግ ሲገባው እለት እለት በእንባ የታጀበ አቤቱታቸውን በማቅረብ ላይ ያሉትን ተበዳይ አገልጋዮችና የጽ/ቤቱን ብልሹ አሠራሮች አይጣሩም በማለት የጻፈው ምላሽ ጥፋተኛነትን እንደማረጋገጥ የሚያስቆጥር ከመሆኑም በላይ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሊታሰብ የማይቻል አድራጎት መሆኑ ታውቆ ሀገረ ስብከቱ ለአጣሪ ኮሚቴው በሩን ክፍት በማድረግ ለማጣራት ሥራው የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ በድጋሜ እየገለጽን በግልባጭ የተመዘገበላችሁ መንግስታዊ አካላትም ይህን በመረዳት ለአጣሪው ኮሚቴው የሥራ መቃናት የበኩላችሁን የሥራ ትብብር ታደርጉ ዘንድ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ስም እንጠይቃለን፡፡
አምላካችን እግዚአብሔር
ለአገራችን ኢትዮጵያና ለዓለም ሁሉ ሰላምን ይስጥ
ግልባጭ
• ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
• ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
• ለአስተዳደር መምሪያ
• ለሕግ አገልግሎት መምሪያ
• ለቁጥጥር አገልግሎት መምሪያ
• ለበጀትና ሒሳብ መምሪያ
• ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት
• ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ ቢሮ
• ለአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን
• ለ7ቱም የክ/ከተማ ቤተ ከህነት ጽ/ቤቶች
• ለአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ
• ለአጣሪ ኮሚቴ አባላት
አዲስ አበባ
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለጻፈው ደብዳቤ የሰጠው ምላሽ የመንበረ ፓትርያርክ ሕዝብ ግንኙነት ግንኙነት መምሪያ ልኮልናል።
ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት
አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡- በቁጥር 4730/546/2017 በቀን 22/01/2017 ዓ.ም ለጻፋችሁት ደብዳቤ ምላሽ መስጠትን ይመለከታል፤
በመጀመሪያ ደረጃ የሀገረ ስብከቱ የመልካም አስተዳደር ችግር ከቤተ ክርስቲያኒቱ ተቋማዊ መዋቅርም አልፎ በዋዜማ ራዲዮ፣ በሸገር ኤፍ ኤም እና በአባይ ቴሌቪዥን የዜና ርእስ መሆኑን ተከትሎ በሦስቱም ሚዲያዎች የተሠራጨውን ዘገባ አስመልክቶ ተገቢውን አስተዳደራዊ እርምት ለመስጠት ይቻል ዘንድ ቅድሚያ እድሉን ለሀገረ ስብከቱ በመስጠት ዝርዝር ጉዳዩ ተጣርቶ ሪፖርት እንዲቀርብልን በቁጥር 443/357/2016 በ10/12/2016 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ የሥራ መመሪያ ብንሰጥም በመመሪያው መሠረት ችግሩን አጣርቶና የችግሩን ባለቤት ለይቶ ሪፖርት ማቅረብ ሲገባ አገር ያወቀውንና ፀሐይ የሞቀውን የሀገረ ስብከቱን የመልካም አስተዳደር ችግር ወደ ጎን በመተው መግለጫ ለመስጠት ስልጣን በሌላቸው ጥቂት የሀገረ ስብከቱ የክፍል ኃላፊዎች አማካኝነት ሀገረ ስብከቱ እንከን የለሽ እና ቅጥርና ዝውውርን አስመልክቶ ምንም አይነት ችግር እንደሌለበት መግለጫ ከመስጠቱም በላይ ቅጥርና ዝውውር የሚፈጸመው በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አመራር ሰጭነት እንደሆነ በማስመሠል ባሠራጨው ከእውነት የራቀ መግለጫ መነሻነት በጉዳዩ ላይ የተወያየው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት አስተዳደር ጉባኤ የሀገረ ስብከቱ አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸምና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን አጣርተው የሚያቀርቡ አጣሪ ኮሚቴ የተሠየመ ቢሆንም ሀገረ ስብከቱ በአስተዳደር ጉባኤው ውሳኔ መሠረት ለማጣራት ሥራው ተባባሪ መሆን ሲገባው ያሉበት የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዳይገለጡና ሀገረ ስብከቱ አደረሰብን በሚሉት አስተዳደራዊ በደል ዘወትር በጽ/ቤታችን በር ላይ ቆመው ፍትሕ የሚጠይቁትን አገልጋይ ሠራተኞች ችግር ተፈትቶ እንባቸው እንዳይታበስ እዚህ ግባ የማይባሉ ምክንያቶችን በመዘርዘር በቁጥር 4730/546/2017 በቀን 22/01/2017 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ አጣሪ ልዑካኑን አንቀበልም በማለት የላካችሁትን ምላሽ ደርሶን ተመልክተነዋል፡፡
ምንም እንኳን ሀገረ ስብከቱ በጻፈው ደብዳቤ የተዘረዘሩት ምክንያቶች ከእውነታው የራቁ እና አንጣራም ለማለት ባልተገባ መንገድ የተገለጹ መሆናቸውን እንኳንስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቱ በየደረጃው ያሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት የሚያውቁት ጥሬ ሐቅ ቢሆንም በግልባጭ የተመዘገበላቸው መንግስታዊ ተቋማት እውነታውን ያውቁት ዘንድ ለጻፋችሁት ደብዳቤ በየተራ ቁጥሩ አንድ በአንድ ተከታዩን ምላሽ ልከናል፡፡ በዚሁ መሠረት፡-
1. ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አጣሪ ኮሚቴ የመደበው አጣሪ ለመመደብ የሚያበቃ ቅሬታ አቅራቢ ሳይኖር ነው ተብሎ የተገለጸውን በተመለከተ፡- የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት አስተዳዳራዊ በደል ደርሶበት ቅሬታ ያቀረበብኝ ሳይኖር አጣሪ ተመደበብኝ ማለቱ እንኳንስ እኛ ዘወትር ሀገረ ስብከቱ በፈጸመባቸው አስተዳደራዊ በደል ከሥራ ገበታቸው ተፈናቅለው ያለምንም ሥራና ደመወዝ በርሐብ አለንጋ እየተገረፉ እንባቸውን እያፈሰሱ አቤቱታ የሚያቀርቡ ባለጉዳዮች መውጫና መግቢያ በማሳጣት ለሚያለቅሱብን ይቅርና በጽ/ቤቱ በር አልፎ ለሚሄድ ተመልካችም ቢሆን ዘወትር በር ተዘግቶባቸው የሚጮሁትን ባለጉዳዮች ለተመለከተ የሀገረ ስብከቱ ምላሽ ከእውነት የራቀ እና እንባ በሚያፈሱት አቤቱታ አቅራቢዎች ላይ የተፈጸመ የግፍ ስላቅ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡
ምንም እንኳን እውነትን መናገር እንደ ሰማይ የሚከብደው ሀገረ ስብከቱ ተበድሎ ቅሬታ ያቀረበ ሳይኖር አጣሪ ተመደበብኝ ይላል እንጅ አሁን በቅርብ የቀረበውን እንኳን እንግለጽ ብንል 439 አገልጋይ ሠራተኞች አስተዳደራዊ በደል ደረሠብንና ከሥራ ገበታችን ተፈናቀልን ብለው እንባቸውን እያፈሰሱ አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን 152 ደግሞ ያለምንም ሥራና ደመወዝ በርሃብ አለንጋ እየተገረፉ ያሉ መሆናቸውን ተረጋግጦ እያለ እነዚህ በችግር ላይ ያሉ ከሥራ የተፈናቀሉትን የቤተ ክርስቲያኒቱን አገልጋዮች ወደ ሥራ ከመመለስ ይልቅ ሀገረ ስብከቱ በሌለ ሥራና በጀት አዲስ ሠራተኛ ለመቅጠር ከብር 300 ሺህ እስከ ብር 1 ሚሊዮን ጉቦ እየተቀበለ ቅጥርና ዝውውር እንደሚፈጽም ከላይ በገለጽናቸው ሦስቱም ሚዲያዎች ዋና የዜና ርእስ ሆኖ የተዘገበ መሆኑን መላው ኢትዮጵያዊያን የሚያውቁት ጥሬ ሀቅ መሆኑንና ይህም ድርጊት ታላቋን ቤተ ክርስቲያን ክብሯን ዝቅ በማድረግ አንገት እንድትደፋ ያደረጋት ታሪክ ይቅር የማይለው አድራጎት መሆኑ እየታወቀ እና ከእኛ አልፎ መንግስታዊ መደበኛ ፍ/ቤቶችን አጨናንቀው የሚውሉት በሀገረ ስብከቱ አስተዳደራዊ በደል የደረሰባቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች መሆናቸው እና በፍርድ ቤቶቹም ውሳኔ በየጊዜው ከሀገረ ስብከቱ ካዝና ለፍርድ ባለመብቶች የሚከፈለው በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠረው ገንዘብ እንደ ጽድቅ ሥራ ተቆጥሮ አጣሪ ለመመደብ የሚያስችል ቅሬታ ሳይኖር ነው አጣሪ የተመደበው የሚለው የሀገረ ስብከቱ ምላሽ ከእውነታው የራቀና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን፤
2. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ችግር የተፈጠረው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በ2015 ዓ.ም ጣልቃ በመግባት አስተዳደር ጉባኤውን በትኖ ከሕግ ውጪ አዲስ ሠራተኛ በመመደቡ ነው በማለት የተገለጸውን በተመለከተ፡- ሠራተኛን ከሥራ ማፈናቀልና ያለምንም ደመወዝ በርሃብ አለንጋ እንዲገረፉ ማድረግ የማይሰለቸው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በወቅቱ በክልል ትግራይ ተከስቶ የነበረውን ጦርነት ተከትሎ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ 577 አገልጋይ ሠራተኞችን ወቅቱን ተገን አድርጎ ከሥራና ከደመወዝ በማፈናቀል ለርሃብ እንዲዳረጉ በማድረግ በእነርሱ ሥራና በጀት ሌላ ሰው በመቅጠር የተፈጸመው ሕገ ወጥ አድራጎት አጀንዳው እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ ደርሶ ዝርዝር ችግሩ ተጣርቶ ተገቢው አስተዳደራዊ እርምት ይሰጥበት ተብሎ በተሰጠው አመራር መሠረት እንዳሁኑ ሁሉ አጣሪ ኮሚቴ በመመደብ ተጣርቶ በቀረበው ሪፖርት መሠረት በወቀቱ በኃላፊነት ይሠሩ የነበሩትን የሀገረ ስከቱን ሠራተኞች ከኃላፊነት በማንሳት የሀገረ ስብከትን ችግር ይቀርፋሉ ተብለው የታመነባቸውን የሥራ ኃላፊዎች በአዲስ መልክ የተመደበ መሆኑን እና ይህም ተግባር እስከ ቋሚ ሲኖዶስ ደርሶ በተሰጠው ውሳኔ መሠረት የተፈጸመ መሆኑ እየታወቀ እና አሁን በሀገረ ስብከቱ በኃላፊነት ተመድበው እየሠሩ ያሉት በሙሉ በዚሁ አግባብ የተመደቡ መሆናቸውን እራሳቸው እያወቁና ይሻላሉ ተብለው ቢመደቡ የቀደመውን ብልሹ አሠራር በማስቀጠላቸው አጣሪ የተመደበ መሆኑን ሁሉም አካላት እንዲያውቁት እየገለጽን ሀገረ ስብከቱ የራሱን የአሠራር ችግር ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ለመግፋት የሄደበት ርቀት ሲታይ በርግጥም ሀገረ ስብከቱ በከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግር ውስጥ መሆኑን የሚያረጋግጥ ብቁ ማስረጃ ነው፡፡
አዲስ መፅሐፍ ምረቃ
ርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረኪዳን ግርማ አሐቲ ድንግል የተሰኘውን መጽሐፍት ሊያስመርቁ ነው
ጥቅምት 2/2017 ዓ.ም በቦሌ መድኃኔዓለም አዳራሽ ከቀኑ 7:30 ጀምሮ
መጽሓፉ
ርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ:
1•የእመቤታችንን ሕይወት የያዘ ሙሉ የነገረ ማርያም አስትምህሮ
2•በነገረ ድኅነት ያላት ድርሻ
3•ዕርገቷን የሚመለከቱ
4•እመቤታችንን የሚመለከቱ ጥያቄዎች
5•በእመቤታችን ፍቅር እንዴት መጽናትና ማደግ ይቻላል?
የሚሉትን ዓበይት ጉዳዮች የሚተነትን ነው
628 ገጾች
12 ምእራፎች አሉት
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
፩ ልደታ ለማርያም
ድንግል ሆይ!አንቺ ከፍጥረት ሁሉ ትበልጫለሽ አንቺ የአምላክ እናት ተብለሻል አንቺ መለኮትን በማህፀንሽ ተሸክመሻል አንቺ የመልካሞች ሁሉ መልካም ነሽ አንቺ ከምርጦች ሁሉ የተመረጥሽ እንቁ ነሽ ማርያም ሆይ በዕውነት ላንቺ ከፍ ያለ ክብር ይገባሻል ።
ልደታ ማርያም በምልጃዋ ትጠብቀን አሜን ፫
ልደታ ማርያም ሀገራችንን ሰላም አድርጊልን ከኃጢዓት በቀር የልባችንን መሻት ፈፅሚልን በያለንበት አንቺ ጠብቂን አሜን
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete site link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
Yikrta tiyakeye endaygermachu gizt ena ezit yalonu bealat mileyayubrt miknyatu mindnew??? amesegnalehu🙏🙏🙏
Читать полностью…