#ጥቅምት_1
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የተባረከ የጥቅምት ወር የቀኑ ሰዓት ዐሥራ አንድ ነውከዚህ በኃላ ይቀንሳል
ጥቅምት አንድ በዚህችም ቀን #ቅድስት_አንስጣስያ በሰማዕትነት አረፈች፤ ዳግመኛም የማርታና የአልዓዛር እህት #የቅድስት_ማርያም_እንተ_ዕፍረት የእረፍቷ መታሰቢያ ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_አንስጣስያ_ሰማዕት
በዚህችም ቀን በጥቅምት አንድ ቅድስት አንስጣስያ በሰማዕትነት አረፈች። ይችም ቅድስት መስተጋድልት ከሮሜ አገር ናት ወላጆቿም ክርስቲያኖች ናቸው ጠቃሚ የሆነ ትምህርትን በማስተማር ክብር ባለው በመልካም ሥርዓት አሳደጓት።
በአደገችም ጊዜ ወላጆቿ ሊያጋቧት ፈለጉ እርሷ ግን ይህን ሥራ አልፈለገችም የምንኲስናን ልብስ መልበስ ፈለገች እንጂ፤ ከታናሽነቷም መንፈሳዊ ገድልን መረጠች።
ስለዚህም በሥውር ሒዳ በሮሜ ካሉ ገዳማት ወደ አንዱ ገዳም ገባች ታናሽ ስትሆንም የምንኲስና ልብስን በመልበስ በጾም በጸሎት በረኃብ በጽምዕ በመጠመድ የዚህን ዓለም ሐሳብ ሁሉ ከልቡናዋ ቆርጣ በመተው በመጋደል ሥጋዋን አደከመች።
በቀኑ ርዝመትም ሁሉ የምትጾም ሆነች በየሁለት ቀኖችም ታከፍላለች በ #ጌታችን ጾም ግን ያለ ሰንበታት ቀን የምትመገበው የለም። በሰንበታትም የምትመገበው ከቀትር ጸሎት በኋላ ነው። በነዚያም በምንኲስናዋ ወራት በእሳት ያበሰሉትን ወጥ አልቀመሰችም።
በገዳሟ አቅራቢያም ሌላ የደናግል ገደም አለ የዚያ ደብር በዓልም በደረሰ ጊዜ እመ ምኔቷ በዓሉን ለማክበር ይቺን ቅድስት አንስጣስያን ከእኅቶቿ ደናግል ጋር አስክትላት በአንድነት ተጓዙ። ሲጓዙም የንጉሥ ዳኬዎስን ወታደሮች አየቻቸው። ከእርሳቸውም ጋር የታሠሩ ክርስቲያኖች አሉ ወታደሮቹም አሥረው በቁጣ ይጎትቷቸው ነበር። ልቧም በሃይማኖቷ ፍቅር ነደደና ያን ጊዜ እንዲህ ብላ ዘለፈቻቸው የእውነት ፈጣሪን የካዳችሁ ልባችሁ የደነዘዘ #እግዚአብሔር በመልኩና በአምሳሉ በፈጠራቸውና ስለእነርሱም ነፍሱን ለሞት አሳልፎ በሰጠላቸው ላይ ለምን እንዲህ ትሠራላችሁ።
ይህንንም በአለቻቸው ጊዜ ወታደሮች ተቆጡ ይዘውም ወደ መኰንኑ አቀረቧት እርሱም እንዲህ ብሎ ጠየቃት በእውነት አንቺ የተሰቀለውን የምታመልኪው ክርስቲያን ነሽን? እርሷም ስለእኛ የተሰቀለውን ክብር ይግባውና እርሱን አመልከዋለሁ ብላ መለሰችለት።
በዚያን ጊዜም ጽኑ ሥቃይን አሠቃያት በሥጋዋም እሳትን ጨመረ ከዚህም በኋላ ዘቅዝቆ ሰቀላት ከበታቿም አጤሱባት ከሃይማኖቷም ባልተናወጸች ጊዜ ራሷን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። በዚህ በታላቅ ሥቃይም ውስጥ ሳለች ራሷን በሰይፍ ቆረጧት። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለች።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስቷ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_ማርያም_እንተ_ዕፍረት
ዳግመኛም በዚህች ዕለት የማርታና የአልዓዛር እህት ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት የእረፍቷ መታሰቢያ ነው።
በዘመነ ሐዋርያት በተመሳሳይ 'እንተ ዕፍረት' (ባለ ሽቱ) ተብለው የሚጠሩ 2 እናቶች ነበሩ:: ሁለቱም ስማቸው ማርያም ስለ ነበር ለመለየት እንዲያመች አንደኛዋን 'ማርያም ኃጥዕት (ከኃጢአት የተመለሰች) ሁለተኛዋን ደግሞ 'ማርያም እኅተ አልዓዛር በቢታንያ የነበረችው ብለው አበው ይጠሯቸዋል።
በሉቃስ ወንጌል ላይ የምትገኘው ከኃጢአት ሕይወት የተመለሰችው ስትሆን በዮሐ. 12:1 ላይ ያለችው የአልዓዛር እህት (ድንግሊቱ) ናት። ዛሬም የምናስባት ይህቺውን እናታችን ነው።
ቅድስት ማርያም #መድኃኒታችን_ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ በሚያስተመርበት ዘመን በቢታንያ አካባቢ ትኖር የነበረች ድንግል ወጣት ናት። ወላጆች ባልነበረበት ቤት ውስጥ ታላቆቿ አልዓዛርና ማርታ አሳድገዋታል።
በቤተሰብ ደረጃ እንግዳን ይቀበሉ ነበርና #ጌታችን ወደዳቸው። አልዓዛርን ከ72ቱ አርድእት: ማርያምና ማርታን ደግሞ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል። ወንድማቸው አልዓዛር በታመመ ጊዜ ወደ #ጌታ ልከው ነበር።
ያለ ጊዜው የማይሠራ #ጌታ ባይመጣ አልዓዛር ሞተ። በ4ኛው ቀን አምላክ ሲመጣ ቅድስት ማርያም በጌታ ፊት ሰግዳ "እግዚእየ ሶበሰ ኀሎከ ዝየ እምኢሞተ እኁየ" "አንተ በዚህ በኖርክስ ወንድሜ ባልሞተ ነበር" ብላ አለቀሰች። (ዮሐ.11)
#ጌታም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አምላክነቱ አራርቶት አለቀሰ። ወዲያውም በስልጣነ ቃሉ አዞ አልዓዛርን አስነሳው። ከፋሲካ (ጌታ ከመሰቀሉ 6 ቀናት) በፊትም ቅዱሳኑ ለ #ጌታ ግብር አገቡ። እርሱም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ታደመላቸው። (ዮሐ.12፥1)
በዚያም አልዓዛር ከ #ጌታ ጐን ሲቀመጥ ቅድስት ማርያም ከጌታ ሥር ተንበርክካ ናርዶስ የሚሉትን የ300 ዲናር ሽቱ በ #ጌታ ላይ አፈሰሰች። መዓዛ መለኮቱና ሽቱው ሲገናኝ "መልዐ መዓዛሁ" እንዲል የሚመስጥ ሽታ ቤቱን ሞላው።
በወቅቱ ይሁዳ ቢቃወምም #ጌታ ምላሹን ሰጥቶታል። ቅድስት ማርያምንም "ማርያምሰ ኃርየት መክፈልተ ሠናየ ዘኢየኃይድዋ" ብሎ አመስግኗታል። ያስመሰገናት ቁጭ ብላ በተመስጦ መማሯ ብቻ እንዳልሆነ አባ ሕርያቆስ መስከሯል።
ሲመክረንም "አርምሞንና ትዕግስትን እንደ ማርያም ገንዘብ እናድርግ" ብሎናል። (ቅዳሴ ማርያም) ቅድስት ማርያም በ #ጌታችን_ክርስቶስ በኅማሙ ጊዜ ሲቀብሩት ነበረች። ትንሳኤውንም ዐይታለች።
ከ #ጌታ እርገት በኋላም መንፈስ ቅዱስን ተከትላ ለወንጌል አገልግሎት ተግታለች። ቅድስት እናታችን ማርያም እንተ ዕፍረት ዛሬ እንዳረፈች እናዘክራለን።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት_1 ና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
አንዳንዶች እንደ ፅሃፍት ፈሪሳውያን ዝም በሉ ይህ ቃሉ አይነገር ቢሉ አሁንም ድንጋዮች ይህንን ቃል ያስከብራሉ ቃሉ የመንፈስ ቅዱስ ቃል ነውና ድንግል ማርያምን ስናመሰግን የአምላካችንን ምስጋና ለርሷ ሰተን ለሚመስላቸው ኢ-አማኒያን ቅዱሳንን ማመስገን እግዚአብሔርን ማመስገን እንደሆነ ቃሉ እንደዚህ ያስተምረናል :-/1ኛ ሳሙ 8:7/ << እግዚአብሔርም ሳሙኤልን አለው:-በእነርሱ ላይ እንዳልንግስ እኔን እንጂ አንተን አልናቁምና በሚሉህ ነገር ሁሉ ህዝቡን ስማ>>::
/ማቴ 10:40/<<እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል እኔንም የሚቀበል የላከኝንይቀበላል::ነቢይን በነብይ ስም የሚቀበል የነብዩን ዋጋ ይወስዳል ፃድቅንም በፃድቅ ስም የሚቀበል የፃድቁን ዋጋ ያገኛል::እንግዲህ ይህ ሁሉ ለፍጡር የተሰጠክብር ነው ያከበራቸው ድግሞ ሁሉ በርሱ የሆነው የጌቶች ጌታ የነገሥታትም ንጉሥ ከአብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንድነት የምናመልከው ጥንት ዓለም ሳይፈጠር በአምላክነት የነበረ ህያው የህያውያን አምላክ የሆነው አልፋና ኦሜጋ እርሱ እየሱስ ክርስቶስ ነው:
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ቅዳሴ #ማርያምን እየደገሙ ውኃው በተአምራት ኅብስት ይሆንላቸው ነበር፡፡ ይህን ተአምር ከአደነቀ በኋላ « #ማርያም ሆይ ሁሉን ማድረግ ትችያለሽና ኃጢአቴን አስተስርይልኝ» ይላል፡፡ #ጌታችን «እውነት እላችኋለሁ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ ይህን ተራራ ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም» /ማቴ.17፡20/ በማለት ላመነ የሚሣነው ነገር እንደሌለ ተናግሯል፡፡ እመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያም መልአኩ «ትጸንሻለሽ፣ ትወልጃለሽ ...» ብሎ ባበሠራት ጊዜ ይህ እንደምን ይሆንልኛል? ብላ ስትጠይቅ «ለ #እግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም» ሲላት በፍጹም እምነት ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ እንደቃልህ ይሁልኝ» በማለት የተቀበለች ናት፡፡ ይህንንም ቅድስት ኤልሳቤጥ መንፈስ ቅዱስን ተመልታ «ከ #ጌታ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና የታመነች ብፅዕት ናት» /ሉቃ.1፡45/ ብላ መስክራለች፡፡ ላመኑ ሁሉ የሚቻል ከሆነ #እመቤታችን ግን ቅዱሳን ሁሉ የሚማጸኑትን አምላክ በሥጋ ወልዳ ያስገኘች ስለሆነች ለእርሷ የሚሳናት ነገር የለም፡፡ ስለዚህም ነው ላንቺ የሚሳንሽ ነገር የለምና ኃጢአቴን አስተስርዪልኝ፣ የከበደኝን ሁሉ አቅልይልኝ በማለት የለመነው፡፡
1.2. «ተአምርኪ #ማርያም ተሰብከ በኦሪት፣
አመ ተሰነዓውኪ ጳጦስ ምስለ መለኮት፣
ዘርእየኪ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
ጸልልኒ በአዕፁቅኪ ሐመልማላዊት ዕፀት
ሦከ ኃጢአትየ ያውዒ ጽጌኪ እሳት፡፡
«#ማርያም ሆይ ነበልባል ከሐመልማል ተዋሕዶ ሙሴ በደብረ ኮሬብ ባየ ጊዜ ተአምርሽ በኦሪት ተሰበከ ተነገረ፡፡ ምሳሌሽ በሐመልማልና በእሳት አምሳል የታየ #ማርያም ሆይ ጽጌ ልጅሽ ኃጢአቴን ያጠፋልኝ ዘንድ በጥላሽ ሥር አስጠጊኝ፡፡”
ሙሴ በምድያም በስደት ሆኖ የአማቱን የዮቶርን በጎች እየጠበቀ ሳለ በኮሬብ ተራራ ድንቅ ራእይ ታየው፡፡ ቁጥቋጦው በእሳት ሲነድ፡፡ ቁጥቋጦውም ሳይቃጠል አየ፡፡ ዘጸ.3÷3፡፡ ይህ የምሥጢር ተዋሕዶ ተምሳሌታዊ ራእይ ነበር፡፡ ሐመልማል የ #እመቤታችን ምሳሌ ሲሆን እሳቱ ደግሞ የ #መለኮት ምሳሌ ነው፡፡ የሐመልማሉ ርጥበት እሳቱን አለማጥፋቱ #አምላክ ሰው ሲሆን ከ #መለኮቱ ክብር ዝቅ ያለማለቱ ምሳሌ ነው፡፡ እሳቱ ደግሞ ሐመልማሉን አለማቃጠሉ #መለኮት ከ #እመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ በተዋሐደ ጊዜ እንዳጸናትና እንዳደረገችው የሚያስረዳ ነው፡፡
ደራሲው የ #እመቤታችን_ክርስቶስን የማስገኘት ተአምርና የእርሷ የ #አምላክ እናት መሆን ከጥንት ጀምሮ ሲነገር የኖረ መሆኑን ካስታወሰ በኋላ ጸሎቱን «ጸልልኒ በአዕፁቅኪ ሐመልማላዊት ዕፀትኮ ሦከ ኃጢአትየ ያውኢ ጽጌኪ እሳት» በማለት ያቀርባል፡፡ ይኸም ማለት «ያ ከሐመልማል ጋር ተዋሕዶ የታየው እሳት ጽጌሽ/ ልጅሽ #ክርስቶስ/ ኃጢአቴን ይቅር ይለኝ ዘንድ በአንቺ ሐመልማልነት አስጠጊኝ” ማለት ነው፡፡
ዳዊት «በአንቺ የሚኖሩ ሁሉ ደስ ይላቸዋል» /መዝ.86፡7/ ብሎ እንደተናገረ በ #እመቤታችን እናትነትና አማላጅነት ጥላ ሥር የሚኖሩ ከልጇ ከ #ክርስቶስ ሥርየተ ኃጢአትን አግኝተው፣ በ #መንፈስ_ቅዱስ ጸጋ ተጐብኝተው ደስተኞች እንደሚሆኑ የተናገረው ትንቢት መፈጸሙን የሚያስረዳ ነው፡፡
ይቀጥላል…
በዐይነ ሥጋ የማይታይና የማይመረመር፣ ሁሉን ማድረግ የሚችል፣ የሰው ህሊና አስሶ የማይደርስበት፣ ሁሉን የፈጠረ፣ መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው፣ ለዘላለም የሚኖር አምላክ መኖሩን እናምናለን፡፡ እርሱም በአካል፣ በስም፣ በግብር ሦስት፤ በባሕርይ፣ በመለኮት፣ በሕልውና፣ በፈቃድ አንድ ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር በመስጠት በመንሳት፣ በመፍጠር በማሳለፍ፣ በመግዛትና በአኗኗር አንድ ነው፡፡
“ሥላሴ” የሚለው ቃል “ሠለሰ” ሦስት አደረገ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሦስትነት ማለት ነው፡፡ ቅድስት ሥላሴ ስንል ለሥላሴ ቅድስት ብለን እንቀጽላለን፡፡ ቅድስት ሥላሴ ማለት ልዩ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ ይህም ሦስት ሲሆኑ አንድ፣ አንድ ሲሆን ሦስት ስለሚሆኑ ልዩ ሦስትነት ተብሏል፡፡ ሥላሴ የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ያለና የሚኖረውን አምላክ ለመግለጽ የተጠቀመው የአንጾኪያው ቴዎፍሎስ በ169ዓ.ም ነው፡፡ኋላም በኒቅያ ጉባዔ 318ቱ ሊቃውንት አጽንተውታል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በቅዱሳት መጻሕፍት የተመሰከረውን የእግዚአብሔርን ፍጹም አንድነትና ልዩ ሦስትነት ለእኛ በሚረዳ ቋንቋ ገለጡት እንጂ አዲስ ትምህርት አላመጡም፡፡ ይልቁንም ነገረ ሥላሴን ሳይረዱ በሥላሴ መካከል የክብርና የተቀድሞ ልዩነት ያለ አስመስለው በክህደት ትምህርት የተነሱ መናፍቃንን ክህደት ለማስረዳት፣ የሐዋርያዊት ቤተክርስቲያንን የቀናች ሃይማኖት ለመግለጥ ምሥጢረ ሥላሴን አብራርተው አስተምረዋል፡፡
ምስጢረ ሥላሴ (Mystery of the Trinity) ማለት የአንድነት የሦስትነት ምስጢር ማለት ነው፡፡ ምሥጢር መባሉም በእምነት የተገለጠ፣ ያለ እምነትም የማይመረመር ስለሆነ ነው፡፡ ይኸውም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት ሲሆኑ በባሕርይ በሕልውና፣ በመለኮት ደግሞ አንድ ናቸው፡፡ እንደዚህ ባለ ድንቅ ነገር አንድ ሲሆኑ ሦስት፣ ሦስት ሲሆኑ አንድ ይባላሉና፣ ይህም ልዩ ሦስትነት ረቂቅ እና በሰው አእምሮ የማይመረመር ስለሆነ ምስጢር ይባላል፡፡ ስለዚህም በአንድ አምላክ፣ በሦስቱ አካላት እናምናለን፡፡
የክርስትና ዶግማ (መሠረተ እምነት) በምስጢረ ሥላሴ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ምስጢረ ሥላሴ የእምነታችን ዋነኛው ምሰሶ ነው፡፡ በመዳን ትምህርት ውስጥ የመጀመሪያውን ደረጃ የሚይዘው ምስጢረ ሥላሴ ነው፡፡ ለመዳናችንም መሠረት ነው፡፡ ክርስቲያኖች ሁላችን የተጠመቅነው በሥላሴ (በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ) ስም ነው (ማቴ 28፡19)፡፡ የሥራችን ሁሉ መጀመሪያም አድርገን በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ስንልም በሥላሴ ማመናችንን እየመሰከርን ነው፡፡ በሥራችን መጨረሻም “ምስጋና ይሁን አንድ አምላክ ለሚሆን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን” ብለን ሥራችንን በሥላሴ ስም ጀምረን በሥላሴ ስም እንፈጽማለን፡፡ሆኖም ግን ምስጢረ ሥላሴ ለሰው አእምሮ እጅግ የረቀቀ ስለሆነ የሰው አእምሮ ሊያውቅ የሚችለው እግዚአብሔር በገለጠለት መጠን ብቻ ነው፡፡
አበው ሥለ ሥላሴ እንዲህ አሉ
“እግዚአብሔር አንድ ነው፤ የማትከፈል የማትፋለስ መንግስትም አንዲት ናት፤ ከሥላሴ ምንም ምን ፍጡር ደኃራዊ የለም፤ በእነርሱ ዘንድ አንዱ ለአንዱ መገዛት የለም፡፡ አብ ከወልድ ተለይቶ የኖረበት ዘመን የለም፣ ወልድም ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ የኖረበት ዘመን የለም፤ መንፈስ ቅዱስም ከአብ ከወልድ ተለይቶ የኖረበት ዘመን የለም፤ ሥሉስ ቅዱስ በዘመኑ በቀኑ ሁሉ በግብርም በስምም ሳይለወጥ ሳይፋለስ ጸንቶ ያለ ነው እንጂ፡፡” (ሃይማኖተ አበው ዘሠለስቱ ምዕት ምዕራፍ 19፡5-6)
“ወንድሞቻችን እኛስ እንዲህ እናምናለን፤ ያልተወለደ እግዚአብሔር አብ በተለየ አካሉ አንድ ነው፤ የተወለደ እግዚአብሔር ወልድ ዋሕድ ኢየሱስ ክርስቶስም በተለየ አካሉ አንድ ነው፤ በወደደው የሚያድር የአብ የወልድ እስትንፋስ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም በተለየ አካሉ አንድ ነው እንላለን፡፡…አብ አምላክ ነው፤ ወልድም አምላክ ነው፤ መንፈስ ቅዱስም አምላክ ነው፡፡ ግን ሦስት አማልክት አይባሉም አንድ አምላክ እንጂ፡፡” (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ምዕራፍ 25፡2-4)
“ከሦስቱ ፍጡር የለም ፍጡራን አይደሉምና፡፡ ከዕውቀት ከሃይማኖት የተለዩ መናፍቃን ከቅድስት ሥላሴ መለኮት መከፈልን በአካላት መጠቅለልን ሊያመጡ አይድፈሩ ሦስት አማልክት ብለን አንሰግድም አንድ አምላክ ብለን እንሰግዳለን እንጂ፡፡ በስም ሦስት ናቸው እንላለን፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ ባህርይ አንድ ሥልጣን ናቸው፤ በአንድ መለኮት በባህርይ አንድነት የጸኑ ሦስት አካላት ሲሆኑ ከሦስቱ አንዱ የሚበልጥ አንዱ የሚያንስ አይደለም፤ በማይመረመር በአንድ ክብር የተካከሉ ናቸው እንጂ፡፡” (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ምዕራፍ 60፡6-7)
“ወልድ ሳይኖር አብ ከአዝማን በዘመን ፈጽሞ አልነበረም፤ ወልድም ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ በዘመን አልነበረም፤ ሳይለወጡ ሳይለዋወጡ በገጽ በመልክ ፍጹማን በሚሆኑ በሦስት አካላት ጥንት ሳይኖራቸው በዘመን ሁሉ የነበሩ፤ ፍጻሜ ሳይኖራቸው የሚኖሩ ናቸው እንጂ፡፡” (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ቴዎፍሎስ ምዕራፍ 68፡5)
“አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በአካል ሦስት በባህርይ አንድ ነው ብሎ ማመን ይህ ነው፤ የማይመረመር በቅድምና የነበረ አብ በገጹ በአካሉ ፍጹም ነው፤…የማይመረመር በቅድምና ነበረ ወልድም በገጹ በአካሉ ፍጹም ነው፤….የማይመረመር በቅድምና የነበረ መንፈስ ቅዱስም በገጹ በአካሉ ፍጹም ነው፤ ሐዋርያት ያስተማሩዋት ቅድስት ቤተክርስቲያን የተቀበለቻቸው ቅዱሳት መጻሕፍት እንደተናገሩ፡፡” (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ቄርሎስ ምዕራፍ 70፡14-17)
“እኛ ግን በሥላሴ ዘንድ በማዕረግ ማነሥና መብለጥ የለም በመለኮት አንድ ወገን ናቸው እንላለን” (አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ተግሳጽ ዘሰባልዮስ)
አቡነ አብሳዲ ገዳማትንና ምንኵስናን ለማስፋፋት ብዙ የደከሙ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ቀንና ሌሊት ሳያርፉ ምእመናን በማስተማር አባታቸው ኤዎስጣቴዎስ እንዳስተማሯቸው
ገዳማትንና ምንኵስናን በኤርትራና በኢትዮጵያ በማስፋፋት ለገዳማዊ ምናኔ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረጉ ሐዋርያ ናችው፡፡ በመንፈስ የወለዷቸው በርካታ መነኵሳት ልጆቻቸው አማካኝነት በኢትዮጵያና በኤርትራ የተገደሙት ገዳማት ከ120 በላይ ናቸው፡፡
በልጆቻቸው አማካኝነት በኤርትራ ከተገደሙት ገዳማት ውስጥ፦ ደብረ ኮል አቡነ ብሩክ (መራጉዝ)፣ የአቡነ ዮናስ ገዳማት (ደብረ ድኹኻን ቆሓይን፣ ደብረ ጽጌ ትምዛእ፣ ደብረ ሣህል ዛይዶኮሎም)፣ ደብረ አቡነ ሙሴ (ማይ ጎርዞ)፣ ደብረ ሲና አቡነ ድምያኖስ፣ ምድሪ ወዲ ሰበራ፣ ደብረ ሐዋርያት አቡነ ሴት (ዓዲ ቂታ)፣ ደብረ ማርያም (ዓይላ) እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ እነኚህን እንደ ምሳሌ ጠቀስን እንጂ በኢትዮጵያም የአቡነ አብሳዲ ልጆች የመሠረቷቸው በርካታ ገዳማት አሉ፡፡
አባታችን የረጅም ዘመን ተጋድሏቸውን በፈጸሙ ጊዜ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ለኹለተኛ ጊዜ ተገልጦላቸው ‹‹በሰሜን ያለች ይኽችን ገዳም ባርኬልሃለውና ከልጆችህ ጋር በእርሷ ኑር›› ካላቸው በኋላ ቃልኪዳን ገብቶላቸው ተሰወረ፡፡ ቀደም ብለን እንደጠቀስነው ይኽችም ለአባታችን የተሰጠቻቸው ገዳም ደበረማርያም (ደብረ ክሳሄ) ናት፡፡
ከዚኸም በኋለ ቅዱስ አባታችን አብሳዲ ደከመኝ ልረፍ ሳይሉ መላ ዘመናቸውን ሐዋርያዊ ተልዕኳቸውን ፈጽመው ከ #እግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ተቀብለው በ101 ዓመታቸው መስከረም 30 ቀን 1383 ዓ.ም ዐርፈው ቆሓይን በምትገኘው ገዳማቸው ደብረ ክሳሄ ደብረ ማርያም ገዳም ተቀበሩ፡፡
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አብሳዲ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ገሪማ_ዘመደራ (#አባ_ይስሐቅ)
አቡነ ገሪማ የተወለዱት በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሮም ውስጥ ነው። ወላጆቻቸው መስፍንያኖስ እና ሰፍንግያ #እግዚአብሔርን የሚወዱ የሮም ከተማ ንጉሥና ንግሥት ነበሩ። ልጅ በማጣታቸው #እመቤታችንን ለመኑ።
እመ ብርሃንም ደግ ፍሬ ሰጠቻቸው። ስሙን ይስሐቅ ብለው አሳደጉት። ገና በልጅነቱ አባቱ ድንገት በመሞቱ ይስሐቅ በዙፋኑ ተተክቶ ነገሠ። ለሰባት ዓመታት ሕዝቡን በፍትሕ እያስተዳደረ መጻሕፍትንም እያጠና ኑሯል።
አንድ ቀን ግን ከግብጽ በርሃ የተላከ ደብዳቤ ደረሰው። ላኪው አባ ጰንጠሌዎን ሲሆኑ መልዕክቱ "ምድራዊ ንግሥና ምን ያደርግልሃል? ይልቁኑስ በሰማይ ለዘላለም እንድትነግሥ ወደ በርሃ ና!" የሚል ነበር።
ንጉሥ ይስሐቅ አላመነታም ሌሊት ተነስቶ ወደ ፈጣሪው ጸልዮ በለበሳት ልብስ ብቻ ዙፋኑን ጥሎ መነነ። ድንገት ግን ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ በቀኝ ክንፉ ነጥቆ ግብጽ አባ ጰንጠሌዎን በዓት ላይ አኖረው።
እርሳቸውም ተቀብለው ፍኖተ አበውን አስተምረው አመነኮሱትና ዘጠኝ ሁነው ወደ ኢትዮጵያ መጡ። ተስዓቱ ቅዱሳን በሃገራችን ብዙ ሲሰሩ አንዱና ታላቁ አባ ይስሐቅ (ገሪማ) ናቸው። ሰውነታቸውን በገድል ቀጥቅጠውት ቆዳና አጥንታቸው ተጣብቆ ነበር።
አንድ ቀን አባ ይስሐቅ በልቶ ቀደሰ ብለው ነግረዋቸው አባ ጰንጠሌዎን አዘኑ። ልምከር ብለው "ልጄ ይስሐቅ የሰማውብህ ነገር አለና ሰዎችን አርቅልኝ።" አሉ። አባ ይስሐቅ ግን "ሰዎች ብቻ አይደሉም፤ ዛፉም እንጨቱም ገለል ይበል።" ቢሉ የቤተ ክርስቲያኑ አጸድ አንድ ምዕራፍ (ሁለት መቶ ሜትር) ተጠራርጎ ሸሸ።
ይህንን የተመለከቱት አባ ጰንጠሌዎን "ወልድየ ይስሐቅ ገረምከኒ (ልጄ ይስሐቅ ገረምከኝ)።" አሏቸው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮም "አቡነ ገሪማ" ተብለው ቀሩ።
አቡነ ገሪማ ወደ መደራ ሲሔዱ እነዚያ የሸሹ ዛፍና ድንጋዮች "ገሪማ ለእኛም ግሩም ነህ።" እያሉ በዝማሬ ተከትለዋቸዋል። ይህም የተደረገው በዚህች ዕለት መስከረም ፴ ቀን ነው።
ጻድቁ ወንጌልንና ገዳማትን ከማስፋፋት ባለፈ ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል፦
፩. ስንዴ ጧት ዘርተውት በዘጠኝ ሰዓት ያፈራ ነበር። "በጽባሕ ይዘርዕ ወበሠርክ የአርር" እንዲል።
፪. ጧት የተከሉት ወይን በዘጠኝ ሰዓት ያፈራ ነበር።
፫. አንድ ቀን ምራቃቸው ቢወድቅ ጠበል ሆኖ ዛሬም አለ።
፬. ብዕራቸው ወድቃ አብባ አፍርታለች።
፭. አንድ ቀን ድርሳን እየደረሱ ሊመሽ በመሆኑ ፀሐይን አቁመዋታል።
ከእነዚህ ሁሉ ዘመናት በኋላ #ጌታችን ተገልጦ በማይዋሽ ንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ሰጣቸው። "ስምህን የጠራ መታሰቢያህን ያደረገ እስከ አሥራ ሁለት ትውልድ እምርልሃለሁ። አንተ ግን ሞትን አትቀምስም።" ብሏቸው ተሰወረ። ያን ጊዜ መላእክቱ በሠረገላ ጭነው እየዘመሩ ብሔረ ሕያዋን አድርሰዋቸዋል።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረም_30)
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete Username(ID) ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
"የቅድስት አርሴማ ትርፏ ምንድነው?...
ካላችሁኝ እኛ ነን እኛን የክርስቶስ አድርጋ ማስረከቧ ነው፤ ክርስቶስ እኛን ነው ለሰማዕታት የሸለማቸው ፤ ምዕመናን በነሱ ስም ተሰብስበው እንዲድኑ ለማድረግ ነው፤"
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ
የቅድስት እናታችን በረከት ለሁላችን ይድረሰን🥰
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
የቫን ጎግ ፊልምን ( VGM )ይቀላቀሉ እና ማለቂያ የሌለውን ሀብት አብረው ያስሱ
ታላቅ የምስራች ስራ ፈታችሁ ወይም አጥታችሁ ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ ላላችሁ፣ ለተማሪዎች፣ ለደሞዝተኞች እና ኑሮ ለከበዳችሁ እና ተጨማሪ ገቢ ማግኘት ለምትፈልጉ ሰዎች በሙሉ! የቫን ጎግ ካምፓኒን በመቀላቀል እና አብሮ በመስራት ከትንሽ እስከ ትልቅ የራሶን የሆነ የገቢ ምንጭ በመፍጠር ህይወቶን መለወጥ፣ ገቢዎን ማሳደግ ይችላሉ።
ይህን ቢዝነስ ለመስራት መድከም አያስፈልጋችሁም። ቤታችሁ ቁጭ ብላችሁ በሞባይል ስልካችሁ ነው።
⁉️በኛ link የተመዘገባችሁ የግል ቦነስ በ ቴሌ ብር ልከን ጨርሰናል ሌሎቻቹሁም ተመዝገቡ ለተጨማሪ ቦነስ በኛ በግሩፕ ሊንክ
📈 ይግቡ👇👇👇👇👇👇👇
******
መልካም ጊዜ ከ VGM ጋር💪💰
📜 አንዳንድ ጊዜ ሃይማኖትን (ሃይማኖት ውስጥ ያሉ ነገሮችን] ከlogic ወይም ከአእምሯችን በላይ ስለሚኾኑ ዝም ብለን መቀበል እንጂ እንዴት ሊኾን ይችላል እያልን አጉል መፈላሰፍ አይገባንም!
Читать полностью…³⁷ ዕለት ዕለትም በመቅደስ ያስተምር ነበር፥ ሌሊት ግን ደብረ ዘይት ወደምትባል ተራራ ወጥቶ ያድር ነበር።
³⁸ ሕዝቡም ሁሉ ይሰሙት ዘንድ ማልደው በመቅደስ ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
የሚቀደሰው ቅዳሴ #ቅዳሴ_እግዚእነ ነው። መልካም የ #ጌታችን_የመድኃኒታችን_የኢየሱስ_ክርስቶስ የልደት በዓል፣ የቅድስት አርሴማ የዕረፍት በዓል፣ የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ መታሰቢያ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
አንድ ሀብታም በመስኮት ሲመለከት አንዱ ደሀ ከቆሻሻ ውስጥ ምግብ ሲፈልግ ይመለከተውና አምላኩን ደሀ አድርጎ ስላልፈጠረው ያመሰግናል ደሀው ሰው ደሞ ዞር ሲል አንድ ብስጩ ሰው ይመለከትና አምላከን ብስጩ አድርጎ ስላልፈጠረው ያመሰግናል ብስጩ ሰው ደዋ ዞር ሲል አንድ የታመመ ሰው በ አምፑላንስ ውስጥ ገብቶ ወደ ሀኪም ቤት ሲሄድ ተመልክቶ እርሱ ጤኔኛ ስለሆነ አምላኩን ያመሰግናል በሽተኛው ሰውዬ ደሞ ሀኪም ቤቱስጥ የሞተ ሰው ተጠቅልሎ ሲመለከት እረስሱ በህይወት ስላለ አምላኩን ያመሰግናል የሞተ ሰው ግን ማመስገን አይችልም
ስለተሰጠን ጤና
ስሱተሰጠን ፍቅር
ስለተሰጠን ነገር ሁሉ አምላካችንን እናመስግን
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete site link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
ይኽን ያውቁ ኖሯል ! በመስከረም 30ቀን መታሠቢያቸው የሆኑ ቅዱሳኖች እናስተዋውቆት:: መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ:ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊው:ቅዱስ አትናቴዎስ ሙት ያስነሳበት ዕለት:የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስ አንዳችንን በቀኙ አንዳችንን በግራው እንዲደረጉ የጠየቁበት ዕለትና ወርሀዊ መታሠቢያ በዓላቸው ሲሆን:አሮን ዘገሊላ የተባለው ጻድቅ ያረፈበት:ዮሐንስ ዘጽጌ እረፍት አመታዊ በዓላቸው ነው:ምንጭ ሊቀ ብርሃናት መርቆሬዎስ አረጋ 36ቱ ቅዱሳት አንስት ከሚለው መጽሐፍት ቸር ያቆየን::በምን በምን እንመስላት ድንግል ማርያምን
ምሳሌ የላትም ክብሯን የሚመጥን
የሙሴ ጽላት ነሽ የምህረት ቃል ኪዳን
የያእቆብ መሰላል የአብርሀም ድንኳን
የብርሃን መውጫ የኖህ ድንቅ መርከብ
የመላእክት እህት የሩህሩሃን እርግብ
የሰሎሞን አክሊል የአሮን በትር
የእዝራ መሰንቆ የጌድዮን ፀምር
ድንግል እመቤት ናት የፃድቃኖች በር
ሆና የተገኘች የአምላክ ማህደር
የቅዱሳን እናት የአለም ንግስት
ችላ የተሸከመች መለኮተ እሳት
ብርሃን ትሁነን ጨለማን ገላልጣ
አማልዳ ታስምረን ከዚህ አለም ጣጣ
ከማር ይጣፍጣል የድንግል መአዛ
አምላክን አቅፋለች በሁለት እጇ ይዛ
አለም ሁሉ የዳነው በልጅሽ ነውና
እናታችን ፅዮን ይድረስሽ ምስጋየፍቅር እናት
ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል::/ሉቃ 1:48/
ይህ ቃል ድንግል ማርያም ምስጋና እንደሚገባት በግልፅ ቃል ይነግረናል::
እመቤታችን የከበረች ፍጡር ናት::አንዳንዶች ማርያም ፍጡር ናትና ለፍጡር ድግሞ ምስጋና አንሰጥም ይላሉ::
መፅሐፍ ቅዱስ ግን ይህን ሃሳባቸውን ከንቱያደረግባቸዋል::
በመዝሙር 32:1 ላይ እንዲህ ብሎ ቃሉ ይንግረናል :- <<ፃድቃን ሆይ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ ለቅኖች ምስጋና ይገባል>>:: ብሎ በደማቁ ፅፎታል ያው መናፍቃን መፅሐፍ ቅዱስን በአንዱ የእግዚአብሔር ቃል ላይ ከመፅናት ይህ የብሉይ ኪዳን ነው ይህ የአዲስ ኪዳን ነው እያሉ በፊት የነበረው እግዚአብሔር ሌላ ቃል ያለው አሁን ያለው እግዚአብሔር ሌላ
ያለው አድረገው ስለሚያሰቡ ሐዋርያው ቅዱስጳውሎስ ወደ ሮሜ ሰወች መልክቱ እንዲህ ብሎ ፅፎ እናነባለን :- <<ነገር ግን በጎሥራ ለሚያደረጉ ሁሉ ምስጋና ክብር ሰላምምይሆንላቸዋል>>ብሎ ዘርዝሮ ይነግረናል አሁን ድንግል ማርያም ማን ናት??ስንል በመጀመሪያ እግዚአብሔር አዳም የሞት ሞትንበቀመሰ ጊዜ እርሱን ሊያድን ቃል መግባቱንበነብያቱም ትንቢት መነገሩን እነሆ ድንግልበድንግልና ትወልዳለች የሚለውን ቃል ስናይልዑል ማደሪያ አድርጎ የመረጣት ትሁት እናት ድንቅ እናት ከሴቶች የተለየች በሰውም በመላክትም የተመሰገነች ጌታ ክብሯን ያበዛላት በዶኪማስ ጎጆ ምን እንዳለቀ ቀድማ ያወቀች ወደ ጌታም ሄዳ የለመነች እርሱ ጌታ ሁሉ በርሱ እንደሆነ አምላክነቱንም የተናገረች እናቱ ናት:: እርስዋን መፅሐፍ ቅዱስ በቅድስት ኤልሳቤጥላይ ያደረው መንፈስ ቅዱስ የጌታዬ እናት ወደኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆናል?የሚለውን ቃል ሲያናግር ስናይ ቅዱስ ገብርኤልም ከእግዚአብሔር ተልኮ አንቺ ከሴቶ
ች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ ብሎ ሲያመሰግናት ስናይ በራስዋም ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል ብላ በመንፈስ ቅዱስ ስትናገርእኛም ለርሷ ምስጋና መስጠታችን መፅሐፍ ቅዱሳዊ እውነታ ነው::
ከእግዚአብሔር የሆነ ይህንን ምስጋና ያመሰግናል ከእግዚአብሔር ያልሆነ ግን ከቶም ሊያመሰግን አይቻለውም ድንግል ማርያምንኮ ትውልድ ሁሉ አያመሰግናትም እኛብቻ ነን የምናመሰግነው ለሚል የሰው ሰውኛአስተሳሰብ እርስዋን ብፅዕት ሁሉ ባይሉዋትቃሉ ቃል ነውና ጌታችን በአህያ ውርንጭላ ላይ ሆኖ ወደ ደብረዘይት በመጣ ጊዜ አንዳንዶች ደቀመዙርቱንና ሕፃናቱን ዝም እንዲያስብላቸው ጠየቁት እርሱም አለ:- እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮሀሉ ቃሉ ይህ ነው እመቤታችን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እነሆ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛልብላ አንዳንዶች እንደ ፅሃፍት ፈሪሳውያን ዝም በሉ ይህ ቃሉ አይነገር ቢሉ አሁንም ድንጋዮች ይህንን ቃል ያስከብራሉ ቃሉ የመንፈስ ቅዱስ ቃል ነውና ድንግል ማርያምን ስናመሰግን የአምላካችንን ምስጋና ለርሷ ሰተን ለሚመስላቸው ኢ-አማኒያን ቅዱሳንን ማመስገን እግዚአብሔርን ማመስገን እንደሆነ ቃሉ እንደዚህ ያስተምረናል :-/1ኛ ሳሙ 8:7/ << እግዚአብሔርም ሳሙኤልን አለው:-በእነርሱ ላይ እንዳልንግስ እኔን እንጂ አንተን አልናቁምና በሚሉህ ነገር ሁሉ ህዝቡን ስማ>>::
/ማቴ 10:40/<<እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል እኔንም የሚቀበል የላከኝንይቀበላል::ነቢይን በነብይ ስም የሚቀበል የነብዩን ዋጋ ይወስዳል ፃድቅንም በፃድቅ ስም የሚቀበል የፃድቁን ዋጋ ያገኛል::እንግዲህ ይህ ሁሉ ለፍጡር የተሰጠክብር ነው ያከበራቸው ድግሞ ሁሉ በርሱ የሆነው የጌቶች ጌታ የነገሥታትም ንጉሥ ከአብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንድነት የምናመልከው ጥንት ዓለም ሳይፈጠር በአምላክነት የነበረ ህያው የህያውያን አምላክ የሆነው አልፋና ኦሜጋ እርሱ እየሱስ ክርስቶስ ነው:የፍቅር እናት
ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል::/ሉቃ 1:48/
ይህ ቃል ድንግል ማርያም ምስጋና እንደሚገባት በግልፅ ቃል ይነግረናል::
እመቤታችን የከበረች ፍጡር ናት::አንዳንዶች ማርያም ፍጡር ናትና ለፍጡር ድግሞ ምስጋና አንሰጥም ይላሉ::
መፅሐፍ ቅዱስ ግን ይህን ሃሳባቸውን ከንቱያደረግባቸዋል::
በመዝሙር 32:1 ላይ እንዲህ ብሎ ቃሉ ይንግረናል :- <<ፃድቃን ሆይ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ ለቅኖች ምስጋና ይገባል>>:: ብሎ በደማቁ ፅፎታል ያው መናፍቃን መፅሐፍ ቅዱስን በአንዱ የእግዚአብሔር ቃል ላይ ከመፅናት ይህ የብሉይ ኪዳን ነው ይህ የአዲስ ኪዳን ነው እያሉ በፊት የነበረው እግዚአብሔር ሌላ ቃል ያለው አሁን ያለው እግዚአብሔር ሌላ
ያለው አድረገው ስለሚያሰቡ ሐዋርያው ቅዱስጳውሎስ ወደ ሮሜ ሰወች መልክቱ እንዲህ ብሎ ፅፎ እናነባለን :- <<ነገር ግን በጎሥራ ለሚያደረጉ ሁሉ ምስጋና ክብር ሰላምምይሆንላቸዋል>>ብሎ ዘርዝሮ ይነግረናል አሁን ድንግል ማርያም ማን ናት??ስንል በመጀመሪያ እግዚአብሔር አዳም የሞት ሞትንበቀመሰ ጊዜ እርሱን ሊያድን ቃል መግባቱንበነብያቱም ትንቢት መነገሩን እነሆ ድንግልበድንግልና ትወልዳለች የሚለውን ቃል ስናይልዑል ማደሪያ አድርጎ የመረጣት ትሁት እናት ድንቅ እናት ከሴቶች የተለየች በሰውም በመላክትም የተመሰገነች ጌታ ክብሯን ያበዛላት በዶኪማስ ጎጆ ምን እንዳለቀ ቀድማ ያወቀች ወደ ጌታም ሄዳ የለመነች እርሱ ጌታ ሁሉ በርሱ እንደሆነ አምላክነቱንም የተናገረች እናቱ ናት:: እርስዋን መፅሐፍ ቅዱስ በቅድስት ኤልሳቤጥላይ ያደረው መንፈስ ቅዱስ የጌታዬ እናት ወደኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆናል?የሚለውን ቃል ሲያናግር ስናይ ቅዱስ ገብርኤልም ከእግዚአብሔር ተልኮ አንቺ ከሴቶ
ች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ ብሎ ሲያመሰግናት ስናይ በራስዋም ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል ብላ በመንፈስ ቅዱስ ስትናገርእኛም ለርሷ ምስጋና መስጠታችን መፅሐፍ ቅዱሳዊ እውነታ ነው::
ከእግዚአብሔር የሆነ ይህንን ምስጋና ያመሰግናል ከእግዚአብሔር ያልሆነ ግን ከቶም ሊያመሰግን አይቻለውም ድንግል ማርያምንኮ ትውልድ ሁሉ አያመሰግናትም እኛብቻ ነን የምናመሰግነው ለሚል የሰው ሰውኛአስተሳሰብ እርስዋን ብፅዕት ሁሉ ባይሉዋትቃሉ ቃል ነውና ጌታችን በአህያ ውርንጭላ ላይ ሆኖ ወደ ደብረዘይት በመጣ ጊዜ አንዳንዶች ደቀመዙርቱንና ሕፃናቱን ዝም እንዲያስብላቸው ጠየቁት እርሱም አለ:- እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮሀሉ ቃሉ ይህ ነው እመቤታችን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እነሆ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛልብላ
#ማኅሌተ_ጽጌ ፤ ምንጩ ትርጉሙና መልእክቱ (ክፍል አንድ)
በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ኃይለ ቃልን ከትርጓሜ፣ ትርጓሜን ከምሥጢር እንዲሁም ደግሞ ምሥጢርን ከዜማ ጋር አስተባብረውና አስማምተው የሚደርሱ ሊቃውንት ባለቤት ናት፡፡ በ5ኛው መ.ክ.ዘመን የተነሣው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ አምስቱን ጸዋትወ ዜማ ሲደርስ በ14ኛው መ.ክ.ዘመን የተነሣው አባ ጊዮርጊስ ደግሞ ሰዓታትን ደርሷል፡፡ በዚሁ ዘመን አባ ጊዮርጊስ ጋር ጥልቅ መንፈሳዊ ፍቅር የነበረው አባ ጽጌ ድንግል “ማኅሌተ ጽጌ” የተባለውን ድርሰት ደርሷል፡፡ ማኅሌተ ጽጌ ግጥማዊ አካሔድ ያለው ድንቅ ኢትዮጵያዊ ድርሰት ነው፡፡ ይህ ድርሰት በማንኛውም ጊዜ የሚጸለይ ቢሆንም በተለየ ሁኔታ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውለው ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ቀን ድረስ ባለው የእመቤታችን የቅድስት #ድንግል_ማርያም የስደት ዘመን ነው፡፡ በዚህ ወቅት በየሳምንቱ እሑድ ሌሊት በሙሉ የእመቤታችንን ከልጇ ጋር ወደ ግብፅ መሰደድና መንከራተት እያሰቡ የሚደረስ ምሥጋናና ጸሎት ነው፡፡
በሀገራችን የመስከረምና የጥቅምት ወራት የአበባ ወራት /ዘመነ ጽጌ/ ናቸው፡፡ ይህም ወቅት ተራሮች በአበባ የሚያጌጡበትና ለዓይን ማራኪ የሚሆኑበት ጊዜ ነው፡፡ በዚህም ዘመን #ጌታችንና_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ “ስለ ልብስስ ስለምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፡፡ አይደክሙም፣ አይፈትሉም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም፡፡ እግዚአብሔርን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ እናንተ እምነት የጐደላችሁ እናንተንማ ይልቁን እንዴት እንግዲህ ምን እንበላለን ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ ...» /ማቴ.5፡28-33/ በማለት የተናገረውን ቃል በማሰብ መጨነቅ የሚገባን መንግሥተ ሰማያት ለመግባት እንጂ በዚህ ዓለም ስላለው ነገር እንዳልሆነ ተራሮችን በአበባ ያለበሰ አምላክ በአርአያውና በአምሳሉ የፈጠረንን እኛን ለኑሮ የሚያስፈልገንን ምግብና ልብስ እንደማይነሳን እያሰብን የምንዘክርበት ወቅት ነው፡፡ እንዲሁም ክቡር ዳዊት «ተዘከር እግዚኦ ከመ መሬት ንሕነ ሰብእሰ ከመ ሳዕር መዋዕሊሁ ወከመ ጽጌ ገዳም ከማሁ ይፈሪ፤ አቤቱ እኛ አፈር እንደሆን አስብ ሰውስ ዘመኑ እንደሣር ነው እንደ ዱር አበባ እንዲሁ ያብባል ነፋስ በነፈሰበት ጊዜ ያልፋልና» /መዝ.1ዐ2፤14-16/ በማለት እንደ ተናገረው የሰው ሕይወት በሣር ይመሰላል፡፡ ሣር አድጐ አብቦ ከዚያ በኋላ ይደርቅና በነፋስ አማካኝነት ያ የረገፈው ሣር እየተነሣ የነበረበት ቦታ ስንኳ እስከማይታወቅ ድረስ ይሆናል፡፡ ሰውም ከአደገ በኋላ በሕማም ፀሐይነት ይደርቅና በሞተ ነፋስነት ይወሰዳል፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ መቃብር ሲወርድ የነበረበት ቦታ ይዘነጋል፡፡ ስለዚህ ዘመነ ጽጌ ሰው ዘመኑ እንደ አበባ በቶሎ የሚረግፍ መሆኑን በማሰብ ይህ ዘመን ሳያልፍ መልካም ሥራ ለመሥራት ትንሣኤ ኅሊና የሚነሣበት ጊዜ ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ለዘመነ ጽጌ የሠራው ድጓም ይህንኑ የሰውን ዘመን አጭርነት የሕይወቱን ኢምንትነት በዚህ ሕላዌ የተፈጠረ ሰው በዚህ ዓለም ክፉ ሥራ መሥራት እንደሌለበት ሁልጊዜ በተዘክሮተ ሞት እንዲኖር የሚያስረዳ ነው፡፡
በዘመነ ጽጌ ቅዱስ ያሬድ ከደረሰው ድጓ በተጨማሪ ከላይ እንደተጠቀሰው በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሣ አባ ጽጌ ድንግል ከዚሁ ዘመን ጋር የተያያዘ ድርሰት ደርሷል፡፡ ይህ ድርሰት በግጥም መልክ የተደረሰ በአብዛኛው አምስት ስንኞች ያሉት ሲሆን ብዛቱም 15ዐ ያክል ነው፡፡ ይህም ድርሰት «ማኅሌተ ጽጌ» በመባል የሚታወቀው ነው፡፡ ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኘው ሁሉ ማኅሌተ ጽጌም እመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያምንና ልጇን #መድኃኒታችንና_አምላካችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን በአበባና በፍሬ እየመሰለ የሚያስረዳ ድርሰት ነው፡፡ እርሷን በአበባ ሲመስል ልጇን በፍሬ እርሷን በፍሬ ሲመስል ደግሞ ልጇን በአበባ እየመሰለ ይናገራል፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ «ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ ወየዓርግ ጽጌ እምጉንዱ፤ ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፤ ከሥሩም ቁጥቋጦ ያፈራል» /ኢሳ.11፡1/ ብሎ ከእሴይ ዘር የምትገኘውን #እመቤታችንን በበትር ከርሷ የሚገኘውን #ክርስቶስን ደግሞ በጽጌ መስሎ ትንቢቱን ተናግሯል፡፡ አባ ጽጌ ድንግልም ድርሰቱን በዚሁ አንጻር በመቀመር እያንዳንዱን መልክዕ #እመቤታችንንና ልጇን አስተባብሮ በጽጌና በፍሬ በመመሰል የ #እግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ በምሥጢር በታሪክ፣ በጸሎትና በመሳሰለው መልክ ድንቅ በሆነና በተዋበ ሁኔታ አዋሕዶ ደርሶታል፡፡
#እመቤታችን ጣዕሟንና ፍቅሯን እንዲሁም ምስጋናዋን ሲናፍቁ የነበሩትን ቅዱስ ኤፍሬምንና አባ ሕርያቆስን ውዳሴዋንና ቅዳሴዋን እንደገለጸችላቸው ለፍቅሯ ሲሳሳ ለነበረው ለአባ ጽጌ ድንግል ደግሞ ይህንን ማኅሌተ ጽጌን እንዲደርስ አድርጋዋለች፡፡ ከላይ እንደተገለጸው ማኅሌተ ጽጌ በመልክዕ አደራረስ ሥርዓት የተደረሰ ሲሆን ይህንንም ለመመልከት እንዲያመች በሚከተሉት ክፍሎች ከፋፍሎ ማቅረብ ይቻላል፡፡
1, #ጸሎት
በዚህ አገባብ ጸሎት ስንል በተለየ ሁኔታ ጸሎትነቱ የጐላውን ለማየት እንጂ ድርሰቱ በሙሉ ጸሎት ነው፡፡ ሌሎቹንም እንዲሁ ታሪክ፣ ተግሳጽ፣ ምሥጢር ተብለው መከፈላቸው በበዛውና በጐላው ለመግለጽ ነው እንጂ ሁሉም በሁሉ አለ፡፡ በጸሎትነታቸው ጐልተው ከሚታዩት ውስጥ የተወሰኑትን እንመለከታለን፡፡
1.1. አንብርኒ #ማርያም ውስተ ልብኪ ከመ ሕልቀት፣
ወከመ ማዕተብ ፁርኒ በመዝራዕትኪ ልዕልት፣
በእንተ ርስሐትየሰ ኢትመንንኒ ንግሥት፣
እስመ ወሀብኩ ንብረትየ ለፍቅርኪ ሞት፣
ዘአሰገርዎሙ ለሰማዕት በጽጌሁ ሕይወት፡፡
ጠቢቡ ሰሎሞን «የምእመናንንና የ #ክርስቶስን ነገር በምሥጢር በተናገረበት በመኃልይ መጽሐፉ «እንደ ማኅተም በልብህ እንደ ማኅተም በክንድህ አኑረኝ» /መኃ.9፤6/ ይላል፡፡ ይኸውም የምእመናንንና የ #ክርስቶስን አንድነት የሚገልጽ ነው፡፡ «አንብርኒ #ማርያም ውስተ ልብኪ ከመ ሕልቀት፤ ወከመ ማዕተብ ፁርኒ በመዝራዕትኪ ልዕልት» ማለቱ #እመቤታችንን እንደ ማኅተም በልብሽ አኑሪኝ በማለት በእናትነትሽ፣ በአማላጅነትሽ አትርሽኝ ካለ በኋላ «በእንተ ርስሐትየሰ አትመንኒ ንግሥት» ይላል፡፡ ይኸም ማለት አትርሽኝ በልብሽ አኑሪኝ ብዬ የምለምንሽ አንቺ እንዳትረሽኝ የሚያደርግ መልካም ሥራ ኖሮኝ አይደለም፡፡ ስለዚህ በሰውነቴ ክፋት ምክንያት በኃጢአቴና በወራዳነቴ ምክንያት እኔን ከማሰብ ከልቡናሽ አታውጪኝ በማለት #እመቤታችን በርኅሩኅ ልቧ «መሐር ወልድየ ወተዘከር ኪዳንየ» እያለች እንድታዘክረን የሚያሳስብ ጸሎት ነው፡፡
ሶበ አተቦ ለማይ በቅዳሴኪ እንዘ ይጼሊ፣
ረሰዮ ኅብስተ ጽጌ ሃይማኖት ሳሙኤል ዘሐቅለ ዋሊ፣
ምሕረተ ወፍትሐ ለተአምርኪ አኀሊ፣
ሥረዪ ኃጢአትየ ወእጸብየ አቅልሊ፣
እስመ ኩሉ ገቢረ ማርያም ትክሊ፡፡
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_30_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ቆሮንቶስ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ አይሁድንም እጠቅም ዘንድ ከአይሁድ ጋር እንደ አይሁዳዊ ሆንሁ፤ ከሕግ በታች ያሉትን እጠቅም ዘንድ፥ እኔ ራሴ ከሕግ በታች ሳልሆን፥ ከሕግ በታች ላሉት ከሕግ በታች እንዳለሁ ሆንሁ፤
²¹ ሕግ የሌላቸውን እጠቅም ዘንድ፥ ያለ እግዚአብሔር ሕግ ሳልኖር ነገር ግን በክርስቶስ ሕግ በታች ሳለሁ፥ ሕግ ለሌላቸው ሕግ እንደ ሌለኝ ሆንሁ፤
²² ደካሞችን እጠቅም ዘንድ ለደካሞች እንደ ደካማ ሆንሁ፤ በሁሉ መንገድ አንዳንዶችን አድን ዘንድ፥ ከሁሉ ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነርሱ ሆንሁ።
²³ በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።
²⁴ በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ።
²⁵ የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፥ እኛ ግን የማይጠፋውን።
²⁶ ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፥ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም፤
²⁷ ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁸ ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
⁹ በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።
¹⁰ ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 20
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁸ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
²⁹-³⁰ ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_30_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ናሁ ሠናይ ወናሁ አዳም። ሶበ ይሔልው አኃው ኅቡረ። ከመ ዕረፍት ዘይውኅዝ እምርእሱ እስከ ጽሕሙ"። መዝ 132፥1-2።
"ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው። ከራስ እስከ ጢም እንደሚፈስስ፥ እስከ አሮን ጢም፥ በልብሱ መደረቢያ እንደሚወርድ ሽቱ ነው"።
መዝ 132፥1-2።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_30_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማርቆስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ በገሊላ ባሕርም አጠገብ ሲያልፍ ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፥ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና።
¹⁷ ኢየሱስም፦ በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው።
¹⁸ ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት።
¹⁹ ከዚያም ጥቂት እልፍ ብሎ የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ደግሞ በታንኳ ላይ መረባቸውን ሲያበጁ አየ።
²⁰ ወዲያውም ጠራቸው አባታቸውንም ዘብዴዎስን ከሞያተኞቹ ጋር በታንኳ ላይ ትተው ተከትለውት ሄዱ።
²¹ ወደ ቅፍርናሆምም ገቡ፤ ወዲያውም በሰንበት ወደ ምኵራብ ገብቶ አስተማረ።
²² እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበር እንጂ እንደ ጻፎች አይደለምና በትምህርቱ ተገረሙ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የ #ማርያም_ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ አቡሳዲ የዕረፍትና የአባ ሣሉሲ የዕረፍት በዓል፣ የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_30
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መስከረም ሠላሳ በዚህች ቀን #በአባ_አትናቴዎስ ላይ ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ላደረገው ተአምር መታሰቢያ ነው፣ #የቅዱስ_አባ_ሣሉሲ እና #የደብረ_ክሳሄው_አቡነ_አብሳዲ ዕረፍታቸው ነው። ዳግመኛም #አባ_ገሪማ (ይስሐቅ) ዘመደራ መታሰቢያ ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አትናቴዎስ
መስከረም ሠላሳ በዚህች ቀን የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት በሆነ በከበረና በተመሰገነ በአባ አትናቴዎስ ላይ ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ላደረገው ተአምር መታሰቢያ ሆነ።
ይህም ሁለተኛም ቁስጠንጢኖስ ወደ ረከሰች የአርዮስ ሃይማኖት በገባ ጊዜ የእስክንድርያውን ሊቀ ጳጳሳት አባ አትናቴዎስን አሳድዶ ከሀዲውን ጊዮርጊስን በእስክንድርያ መንበር ላይ ሾመው። የአርዮስንም ሃይማኖት እንዲአጠናክር የረከሰ የአርዮስን ሃይማኖት የማይቀበሉትን ግን ሁሉንም ይገድላቸው ዘንድ አዘዘው ብዙዎች ፈረሰኞች ጦረኞችን ለእርሱ ሰጥቶታልና። ስለዚህም ከእስክንድርያ ሰዎች ቁጥር የሌላቸውን ብዙዎች ምእመናንን ገደላቸው።
ቅዱስ አትናቴዎስም በተሰደደበት ስድስት ዓመት ኖረ። ከዚህም በኋላ የ #እግዚአብሔርን ልጅ የካደው ታናሹ ቁስጠንጢኖስ ወደአለበት ወደ ቁስጥንጥንያ ተነሥቶ ሔደ ንጉሡንም እንዲህ አለው ወደ ተሾምሁበት መንበሬ ትመልሰኝ እንደሆነ መልሰኝ ይህ ካልሆነ የምስክርነት አክሊልን እንድቀበል ግደለኝ።
ንጉሡም ይህን ነገር ከእርሱ በሰማ ጊዜ በታናሸ መርከብ አድርገው ያለ ቀዛፊና ያለ መብልና መጠጥ በባሕር ውስጥ እንዲተዉት አዘዘ ንጉሡም በስጥመት ወይም በረኃብና በጥም እንደሚሞትለት አስቦ ነበርና የቀናች ሃይማኖትንም ስለመለወጡ እንዳይዘልፈው ከእርሱ ያርፍ ዘንድ እንዲሁም ንጉሡ እንዳዘዘ በቅዱስ አትናቴዎስ ላይ አደረጉበት። ንጉሡም እንጀራና ውኃ ባይሰጠው ከሰማይ ለእርሱ የወረደ እንጀራ ስለርሱ የፈለቀ ውኃም አለው። የመርከብም ቀዛፊ ቢከለክለው እነሆ ዓለሙን ሁሉ በቃሉ የሚጠብቅ የሚመራ ከእርሱ ጋር ነበር። ስለዚህም ቅዱስ አትናቴዎስ በውስጧ የተቀመጠባት ያቺ መርከብ መላእክት እየቀዘፏት በጸጥታና በሰላም ተጓዘች በሦስተኛውም ቀን ከእስክንድርያ ወደብ ደረሰ።
የምእመናን ወገኖችም ደግ ጠባቂያቸው እንደ ደረሰ በሰሙ ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው መብራቶችንም በመያዝ በምስጋና እየዘመሩ ሊቀበሉት ወጡ። #እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን አስገቡት። ከሀዲው ጊዮርጊስም ከወገኖቹ ጋር ወጥቶ ሔደ።
በዚያችም ቀን ቅዱስ አትናቴዎስ ለ #እግዚአብሔር ታላቅ በዓልን አከበረ የእስክንድርያም ሰዎች እስከ ዛሬ ድረስ ያከብሩ አታል።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የቅዱስ አትናቴዎስም በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ሣሉሲ
በዚችም ቀን ቅዱስ አባ ሣሉሲ አረፈ። ይህም ቅዱስ መስተጋድል ሲሆን ራሱን እንደ እብድ አደረገ እርሱም በሥውር ይጸልያል ይጾማልም በሰው ፊት ግን ምንም ምን አይጸልይም አይጾምም በየጥዋቱ ሁሉ የሚመገበውን የሣር ፍሬ አድርጎ በሰው ፊት ያላምጣል በምሽት ጊዜ ግን ከውንድሞች መነኰሳት ጋር ምንም ምን አይቀምስም።
አበ ምኔቱ አባ ይስሕቅና መነኰሳቱ ሁሉ ከሥራው የተነሣ ያደንቃሉ ይህንንም ልማዱን ሊአስጥሉት ይሻሉ ነገር ግን ልቡን እንዳያሳዝኑት ያስባሉ።
በአንዲትም ዕለት የገዳማቸው በዓል ሆነ አበ ምኔቱ አባ ይስሐቅም መነኰሳቱን እንዲህ አላቸው #ቅዱስ_ቁርባንን ከመቀበሉ በፊት እህልን እንዳይቀምስ አባ ሣሉሲን ጠብቁት። እነርሱም ጠበቁት የሚበላበትም ጊዜ ሲደርስ ከእነርሱ ሊለይ ወደደ መነኰሳቱም ከለከሉት እርሱም በረኃብ እንዳልሞትና በእናንተ ላይ በደል እንዳይሆንባችሁ ልቀቁኝ ብሎ ጮኸባቸው።
ባልተውትም ጊዜ በዚያን ወቅት ቆቡን ከራሱ ላይ አውልቆ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ ከእሊህ መነኰሳት እጅ አድኝኝ ብሎ የቤተ ክርስቲያኑን ግድግዳ በቆቡ መታበት ሕንፃውም ተሠንጥቆለት በዚያ ወጥቶ ሔደ የግድግዳውም ግምብ ተመልሶ እንደቀድሞው ሆነ።
የተሰበሰቡትም ይህን ድንቅ ተአምር በአዩ ጊዜ ሦስት መቶ ጊዜ ኪርያላይሶን እያሉ ጮኹ በዚያንም ጊዜ ያቺን ቆብ ወድቃ አገኙአት በታላቅም ክብር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖሩዋት ድውያንንም በመፈወስ ከእርሷ ብዙ ተአምራት ተደረገ።
ሊቀ ጳጳሳቱም በሰማ ጊዜ ከእርሷ ሊባረክ ወዶ ያቺን ቆብ ሊወስዳት ፈለገ በየጊዜውም ሲወስዳት ወደቦታዋ ወደዚያ ገዳም ትመለሳለች እንዲህም ሦስት ጊዜ ሆነ ከዚህም በኋላ መውሰዱን ተወ።
ከብዙ ወራትም በኋላ እንደ ዛሬው ሁሉ በዚች ቀን አባ ሣሉሲ በዚሁ ገዳም በአረፈበት ቦታ ተገልጾ ተገኘ በክብርም ገንዘው ቀበሩት።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ በአባ ሣሉሲ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_አብሳዲ_ዘደብረ_ማርያም (ክሳሄ)
አቡነ አብሳዲ አጽፋቸውን እንደጀልባ ተጠቅመው የኢያሪኮን ባሕር የተሻገሩት የታላቁ ጻድቅ የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ከፋሌ ባሕር ደቀ መዝሙር ናቸው፡፡ የደብረ ክሳሄው አቡነ አብሳዲ ገድላቸውን የፈጸሙት ኤርትራ ውስጥ ነው፡፡
አቡነ ኤዎስጣቴዎስን #ጌታችን በቃሉ ጠርቶ ‹‹በላይህ ላይ ያለውን ቅዱስ መንፈስ በወዳጅህ በልጅህ አብሳዲ ላይ አሳድር፣ ሙሴ የራሱን መንፈስ በነዌ ልጅ በኢያሱ ላይ እንዳሳደረ፣ ኤልያስም በረድኡ በኤልሳዕ ላይ እንዳሳደረ›› አላቸው፡፡ ምክንያቱም ልጆቻቸውን ትተው ወደ ኢየሩሳሌም ከዚያም ወደ አርማንያ እንዲሔዱ ነግሯቸዋልና ነው፡፡ አባታችንም ልጃቸውን አቡነ አብሳዲን ሦስት ጊዜ ‹‹አብሳዲ አብሳዲ አብሳዲ›› ብለው ጠሩት፡፡ እርሱም አባቱን ‹‹አቤት ጌታዬ እነሆ ጠርተኸኛልና›› አለው፡፡ አባታችን ኤዎስጣቴዎስም ‹‹እነሆ በረከት ከሰማይ ለአንተ ተሰጠች፣ ይህችንም በረከት ብርንና ወርቅን የማይወዱ ራሳቸውንም ወደ ጠባብ በር ያስገቡ እንደ አንተ ካለ ጻድቃንና ከተመረጡት በቀር መቀበል የሚችል የለም፤ እነርሱም ሥጋቸውን አሳልፈው ለጻዕር ለጭንቅ የሰጡ ናቸው፤ ከተወለዱም ጀምሮ ጣፋጭ የሆኑ የምድር ምግቦችን ያልወደዱ ናቸው፣ ራሳቸውንም እንደምታልፍ ነፋስ ያደረጉ ናቸው፡፡›› አባታችን ኤዎስጣቴዎስም ይህንን ተናግረው በአብሳዲ ራስ ላይ እጃቸውን ጫኑ፡፡ ሙሴ በኢያሱ እንደጫነ፣ ያዕቆብም በይሁዳና በሌዊ ላይ እጁን ጭኖ ለመንግሥትና ለክህነት እንደባረካቸው ዮሴፍም ልጆቹን ኤፍሬምና ምናሴን ይባርካቸው ዘንድ ወደ አባቱ እስራኤል አምጥቷቸው እርሱም የተባረከና ቅዱስ ሕዝብ ያድርጋችሁ ብሎ እንደባረካቸው እንደዚሁም ሁሉ አባታችን ኤዎስጣቴዎስ ልጃቸውን አብሳዲን እንዲህ እያሉ ባረኩት፡- ‹‹የቀደሙ አባቶች በረከት፣ የነቢያትና የሐዋርያት በረከት፣ ድል የሚነሡ የሰማዕታት በረከትና በተጋድሎ የጸኑ የጻድቃን በረከት፣ የቅዱሳን መላእክት በረከት፣ ማኅበረ በኩር የተባሉ የሁሉም ቅዱሳን በረከት፣ አምላክን የወለደች የቅድስት #ድንግል_ማርያም በረከት፣ የ #አብ የ #ወልድ የ #መንፈስ_ቅዱስ በረከት በአንተ ላይና በልጆችህ ላይ ይደር፤ መታሰቢያዬንና መታሰቢያህንም በሚያደርጉ ላይ ይደር ለዘለዓለሙ አሜን›› ብለው መባረክን ከባረኩት በኋላ አብሳዲን ግንባሩን ቀብተው አተሙት፡፡
🌺🌺ለልጆችህ ማድረግ የምትችለው ትልቁ ነገር ቢኖር እናታቸውን መውደድ ነው።🌺🌺
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
እባካችኹ 🙏
ስትመዘገቡ የመጀመሪያችኹ እንደመኾኑ ፣ የሌላ ሰው እገዛ ያስፈልጋችዃል።
ስለዚኽ ብትጠይቁ መልካም ነው ፣ ሥራው በመተጋገዝ ቢሰራ የበለጠ አዋጭ ነው።
ምክንያቱም 👇
ቦነስ እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞችን ታጣላችኹ❗
👉 አንዳንድ መረጃዎችንም ለራሳችኹ ስትሉ ብትከታተሉ ታተርፋላችኹ።
👉 ይኽ ቴሌግራም ቻናል አላማው ይኽው ነው።
👉 እስከቻልን ድረስ የ Team አባሎቻችንን ለማገዝ ዝግጁ ነን ።
እባካችኹ 🙏
በስራችኹ ሰዎች ስትመዘግቡ ኃላፊነት ተሰምቷችኹ ስለ ሥራው አሳውቋቸው ።
በተጨማሪም
አንዳንድ የ VGM አሰራሮች እዚኽ Yoytube ላይ አለላችኹ 👇
Dave info Youtube Channel
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_29_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ገላትያ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ነገር ግን እላለሁ፥ ወራሹ ሕፃን ሆኖ ባለበት ዘመን ሁሉ፥ ምንም የሁሉ ጌታ ቢሆን ከቶ ከባሪያ አይለይም፥
² ነገር ግን አባቱ እስከ ቀጠረለት ቀን ድረስ ከጠባቂዎችና ከመጋቢዎች በታች ነው።
³ እንዲሁ እኛ ደግሞ ሕፃናት ሆነን ሳለን ከዓለም መጀመሪያ ትምህርት በታች ተገዝተን ባሪያዎች ነበርን፤
⁴ ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤
⁵ እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ።
⁶ ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ።
⁷ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅም ከሆንህ ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ።
⁸ ነገር ግን በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን ሳታውቁ በባሕርያቸው አማልክት ለማይሆኑ ባሪያዎች ሆናችሁ ተገዛችሁ፤
⁹ አሁን ግን እግዚአብሔርን ስታውቁ ይልቅስ በእግዚአብሔር ስትታወቁ እንደ ገና ወደ ደካማ ወደሚናቅም ወደ መጀመሪያ ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ? እንደ ገና ባሪያዎች ሆናችሁ ዳግመኛ ለዚያ ልትገዙ ትወዳላችሁን?
¹⁰ ቀንንና ወርን ዘመንንም ዓመትንም በጥንቃቄ ትጠብቃላችሁ።
¹¹ ምናልባት በከንቱ ለእናንተ ደክሜአለሁ ብዬ እፈራችኋለሁ።
¹² ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ደግሞ እንደ እናንተ ሆኜአለሁና፦ እንደ እኔ ሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ። አንዳችም አልበደላችሁኝም።
¹³ በመጀመሪያ ወንጌልን በሰበክሁላችሁ ጊዜ ከሥጋ ድካም የተነሣ እንደ ነበረ ታውቃላችሁ፥
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤
² ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤
³ እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።
⁴ ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን።
⁵ ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፦ እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።
⁶ ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፤
⁷ ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።
⁸ ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
⁹ በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።
¹⁰ ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ጴጥሮስና ዮሐንስም በጸሎት ጊዜ በዘጠኝ ሰዓት ወደ መቅደስ ይወጡ ነበር።
² ወደ መቅደስም ከሚገቡት ምጽዋት ይለምን ዘንድ፥ ሰዎች ተሸክመው መልካም በሚሉአት በመቅደስ ደጅ በየቀኑ ያስቀምጡት የነበሩ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ አንድ ሰው ነበረ።
³ እርሱም ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ መቅደስ ሊገቡ እንዳላቸው ባየ ጊዜ፥ ምጽዋትን ለመናቸው።
⁴ ጴጥሮስም ከዮሐንስ ጋር ትኵር ብሎ ወደ እርሱ ተመልክቶ፦ ወደ እኛ ተመልከት አለው።
⁵ እርሱም አንድ ነገር ከእነርሱ እንዲቀበል ሲጠብቅ ወደ እነርሱ ተመለከተ።
⁶ ጴጥሮስ ግን፦ ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ አለው።
⁷ በቀኝ እጁም ይዞ አስነሣው፤ በዚያን ጊዜም እግሩና ቍርጭምጭምቱ ጸና፥
⁸ ወደ ላይ ዘሎም ቆመ፥ ይመላለስም ጀመር፤ እየተመላለሰም እየዘለለም እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ከእነርሱ ጋር ወደ መቅደስ ገባ።
⁹ ሕዝቡም ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ሲመላለስ አዩት፤
¹⁰ መልካምም በሚሉአት በመቅደስ ደጅ ስለ ምጽዋት ተቀምጦ የነበረው እርሱ እንደ ሆነ አወቁት፤ በእርሱም ከሆነው የተነሣ መደነቅና መገረም ሞላባቸው።
¹¹ እርሱም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ይዞ ሳለ፥ ሕዝቡ ሁሉ እየተደነቁ የሰሎሞን ደጅ መመላለሻ በሚባለው አብረው ወደ እነርሱ ሮጡ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_29_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"እግዚአብሔር ይቤለኒ ወልድየ አንተ። ወአነ ዮም ወለድኩከ። ሰአል እምኔየ እሁበከ አሕዛበ ለርስትከ። መዝ. 2፥7-8።
"ትእዛዙን እናገራለሁ፤ እግዚአብሔር አለኝ፦ አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለድሁህ። ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ"። መዝ. 2፥7-8።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_29_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሉቃስ 21
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²¹ የዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራራዎች ይሽሹ፥ በመካከልዋም ያሉ ከእርስዋ ፈቀቅ ይበሉ፥ በገጠር ያሉም ወደ እርስዋ አይግቡ፤
²² የተጻፈው ሁሉ እንዲፈጸም ይህ የበቀል ጊዜ ነውና።
²³ በዚያን ወራት ለእርጕዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው፤ ታላቅ ችግር በምድር ላይ፥ በዚህም ሕዝብ ላይ ቍጣ ይሆናልና፤
²⁴ በሰይፍ ስለትም ይወድቃሉ፤ ወደ አሕዛብ ሁሉም ይማረካሉ፤ የአሕዛብም ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።
²⁵ በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ከባሕሩና ከሞገዱም ድምፅ የተነሣ እያመነቱ ይጨነቃሉ፤
²⁶ ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም የሚመጣበትን ከመጠበቅ የተነሣ ይደክማሉ፤ የሰማያት ኃይላት ይናወጣሉና።
²⁷ በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በኃይልና በብዙ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።
²⁸ ይህም ሊሆን ሲጀምር ቤዛችሁ ቀርቦአልና አሻቅባችሁ ራሳችሁን አንሡ።
²⁹ ምሳሌንም ነገራቸው እንዲህ ሲል፦ በለስንና ዛፎችን ሁሉ እዩ፤
³⁰ ሲያቈጠቍጡ ተመልክታችሁ በጋ አሁን እንደ ቀረበ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።
³¹ እንዲሁ ደግሞ እናንተ ይህ ሁሉ መሆኑን ስታዩ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ቀረበች እወቁ።
³² እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም።
³³ ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም።
³⁴ ነገር ግን ልባችሁ በመጠጥ ብዛትና በስካር ስለ ትዳርም በማሰብ እንዳይከብድ፥ ያ ቀንም በድንገት እንዳይመጣባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤
³⁵ በምድር ሁሉ ላይ በሚቀመጡ ሁሉ እንደ ወጥመድ ይደርስባቸዋልና።
³⁶ እንግዲህ ሊመጣ ካለው ከዚህ ሁሉ ለማምለጥ፥ በሰው ልጅም ፊት ለመቆም እንድትችሉ ስትጸልዩ ሁል ጊዜ ትጉ።