ortodoxtewahedoo | Unsorted

Telegram-канал ortodoxtewahedoo - ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

3754

ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ። ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ›› ት.ኢሳ 58÷3 https://youtu.be/csxxAMGtC4I ለመቀላቀል http://t.me/ortodoxtewahedo

Subscribe to a channel

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Yet new maetebu😂😂😂

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ኑ በብርሃኑ ተመላለሱ🥰🥰🥰


ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። ኢሳይያስ 9፥6
እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።


@ortopiyaaa
@ortopiyaaa
@ortopiyaaa

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

🗓⚪️#አንድ_ጥያቄ

●✥ ከመንፈስ ፍሬዎች መካከል ቀዳሚነትን የሚይዘው የትኛው ነው❓ ●✥

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል ስናከብር ምን ምን ልንገነዘብ ይገባል


በመ/ር ናሆም ታጠቅ የቀረበ

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

አይቶ መለፍ እጅግ በጠም ይከብደል፡፡
እባካቹ እናንተ ደጋጎች ሼር ሼር አድርጉላቸው

ወዳጆቼ በዚ ከበድ ወቅት የበረከት ስራ እንስራ መርዳት ቢያቅተን ሼር ማድረግ እራሱ ትልቅ እርዳታ ነው:: ይህ የምትመለከቱወት ህፃን የሁለት አመት ከሶስት ወር ህፃን ነት የካንሰር ታማሚ ነት ካንሰር በሽታ የያዘውት ከተወለደች ከሶስ ወር  ጀመሮ የካንሰር ታማሚ ነት ይሄው እሷም እናቱወም አባቱወም ሁለት አመት ሙሉ አሚን አጠቀለይ ሆስፒተል ንብረታቸውን ሸጠው እሷን በማስታመም ላይ ይገኛሉ ህፃኑወን ካንሰሩ አይንወን አሳውሮታል አንደኛው አይንወ በቀዶ ጥገና ወጥቶለት አንደኛውንም አይኑወ ከሰሞኑ እንደሚወጣ ከዶክቶሮቹ ሰምቻለው በዚያ ላይ አንድ አፍንጫወን ደፍኖታል እናትና አባትወ  ለሁለት አመት ከልጃቸው ጋ ስቃይ ውስጥ ይገኛሉ አሁን ላይ ከስቃዩም በላይ የህክምና እና የመድሀኒቱ ወጪ ሌላ ስቃይ ነው የሆነባቸው  ለመድሀኒቱና ህክምና ለአስራ አምስት ቀን ሰባ ሺ ብር ይፈልጋሉ አሁን ላይ ውጪ ሄደ የመታከም እድልም አለት ለህክምናወ ወጪ ከአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር በላይ ይፈልጋልጋሉ እና ልጅቷም በስቃይ ውስጥ እናትና አባትም በስቃይና ጭንቀት ውስጥ ናቸው እንድረስላቸው ለወገን ደራሽ ወገን ነው የቻልነውን  አነሰም በዛ ሳንል እጃችንን እንዘርጋላቸው ስል በፈጠሪ   ስም እንማፀናለን መርዳት ለምትፈልጉ
ንግድ ባንክ 1000603332346 እስማኢል ሀሠን አብደላ (Ismail Hassen)
ስልክ ቁጥር 0960067157

የማትችሉ በፀሎትና ሼር ሼር ሼር በማድረግ እንርዳቸው
ሼር ሼር ሼር በማድረግ አይከፈልበትም

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

🙋‍♂አንድጥያቄ

✞በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ሰውን መግደል የጀመረው በማን ነበር ⁉️✟

         

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ቤዛ ኩሉ አለም ዮም ተወልደ

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በቅዱስ ላሊበላ በከፍተኛ ድምቀት ይከበራል ፡፡

መላእክት ከእኛ ጋር በእዚህ አሉ....
***

የአማናዊው ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በሚነሳበት በእዛ .... ቅዱሳን መላእክት ይነጠፋሉ።

ቤተክርስቲያን በምትዘረጋዊ ሚስጢሯ ውስጥ ሰማያውያን ተሰልፈው ከተመረጡ የአብ ተክል አመስጋኞች ተርታ በአንድነት ይቆማሉ።

የሚታዩት ከማይታዩት ፣ ሰማያውያን ከምድራውያን ጋር ለአንድ ርስት እና ለአንድ ጌታ የሚደክሙበት ንጽሁ እና ቅዱስ በዓት .....ቤተክርስቲያን ::

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ነገ እሑድ ታኅሣሥ 20 ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት በደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ምንም እንኳን እንደ ሰብአ ሰገል የከበሩ ማዕድናትን እጅ መንሻ አድርገን ማቅረብ ባንችል እርሱ በሰጠን አንደበት በበረት የተወለደውን ንጉሥ በዝማሬ በውዳሴ ልናመሰግነው ተዘጋጅተናል። ነገ ማርፈድ ያስቆጫል! መቅረትማ አይታሰብም!

‛የጌታን ልደት የት ታከብራለኽ?’

✍ ዲያቆን ሔኖክ ኃይሌ ከጻፈው

ሰብአ ሰገል (የጥበብ ሰዎች) እየመራቸው የነበረውን ኮከብ ሲያጡት ወደ ሔሮድስ መጡና “የተወለደው #ንጉሥ ወዴት ነው?” አሉ። እውነትም ጠቢባን ናቸው። መንገድ ከጠፋብን፥ መሪ ኮከብ ካጣን ልደቱን የፈለግንበት እናክብር አላሉም። ‛የተወለደው ወዴት ነው?’ ብለው ቤተ መንግሥት ሔደው ጠየቁ። ጥሩ በዓል ለማክበር ከቤተ መንግሥት የተሻለ ሥፍራ የለም። በቤተ መንግሥት ራት እየበሉ፥ ጮማ እየቆረጡ፥ በዘፈን ታጅበው በዓሉን ማክበር ይችላሉ። እነርሱ ግን የትም ቢኾን ንጉሡን ሳናገኝ አንቆይም። እሱ የሌለበት ቦታ ቤተ መንግሥትም ቢኾን ልደቱን አናከብርም። አይ ሰብአ ሰገል! ይኽንን ዘመን መጥተው ቢያዩ ምን ይላሉ?

ወዳጄ አንተስ የጌታን ልደት #የት_ታከብራለኽ? መቼም ልደት የሚከበረው ባለ ልደቱ ባለበት ሥፍራ ነው። በእውነት የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? በጭፈራ ቤት ነውን? በመጠጥ ቤት ነውን? የት ነው ያለው ብለህ ጠይቀኻል?

የሚመራኝ ኮከብ የለም” ትል ይኾናል። ምንም ቢኾን ግን ሕፃኑ በሌለበት ልደቱን ለማክበር መወሰን የለብኽም። ምንም ያሸበረቁ ሥፍራዎች ቢኖሩም እንዳትታለል። የሔሮድስ ቤተመንግሥት ውበት የግብዣው ስፋት አታልሎኽ #የተወለደውን_ንጉሥ እንዳያስረሳኽ ተጠንቀቅ። እሱ ከሌለበት ያማረ ሥፍራ ይልቅ እሱ ያለበት በረት ይሻልኻል። እሱ ያልመረጠውን ሥፍራ መርጠኽ ከመንገድ አትቅር። “የተወለደው የአይሁድ ወዴት ነው?” ብለኽ ጠይቅ።

እሱ ደሃ ሆኖ ባለጠጋ የሚያደርግኽን ንጉሥ በሚያልፍ ደስታ አትጣው። በስካር በዝሙት በጭፈራ በሔሮድስ ቤተ መንግሥት ቀልጠኽ ቀርተኽ የተወለደውን #ሕፃን ሳታየው አትቅር። እሱ በተወለደባት ሌሊት አንተ ስትሞት አትደር። እመነኝ የተወለደው ይሻልኻል፤ ከሞቱት ጋር ጊዜኽን አታጥፋ።

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

‛የጌታን ልደት የት ታከብራለኽ?’

✍ ዲያቆን ሔኖክ ኃይሌ ከጻፈው

ሰብአ ሰገል (የጥበብ ሰዎች) እየመራቸው የነበረውን ኮከብ ሲያጡት ወደ ሔሮድስ መጡና “የተወለደው #ንጉሥ ወዴት ነው?” አሉ። እውነትም ጠቢባን ናቸው። መንገድ ከጠፋብን፥ መሪ ኮከብ ካጣን ልደቱን የፈለግንበት እናክብር አላሉም። ‛የተወለደው ወዴት ነው?’ ብለው ቤተ መንግሥት ሔደው ጠየቁ። ጥሩ በዓል ለማክበር ከቤተ መንግሥት የተሻለ ሥፍራ የለም። በቤተ መንግሥት ራት እየበሉ፥ ጮማ እየቆረጡ፥ በዘፈን ታጅበው በዓሉን ማክበር ይችላሉ። እነርሱ ግን የትም ቢኾን ንጉሡን ሳናገኝ አንቆይም። እሱ የሌለበት ቦታ ቤተ መንግሥትም ቢኾን ልደቱን አናከብርም። አይ ሰብአ ሰገል! ይኽንን ዘመን መጥተው ቢያዩ ምን ይላሉ?

ወዳጄ አንተስ የጌታን ልደት #የት_ታከብራለኽ? መቼም ልደት የሚከበረው ባለ ልደቱ ባለበት ሥፍራ ነው። በእውነት የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? በጭፈራ ቤት ነውን? በመጠጥ ቤት ነውን? የት ነው ያለው ብለህ ጠይቀኻል?

የሚመራኝ ኮከብ የለም” ትል ይኾናል። ምንም ቢኾን ግን ሕፃኑ በሌለበት ልደቱን ለማክበር መወሰን የለብኽም። ምንም ያሸበረቁ ሥፍራዎች ቢኖሩም እንዳትታለል። የሔሮድስ ቤተመንግሥት ውበት የግብዣው ስፋት አታልሎኽ #የተወለደውን_ንጉሥ እንዳያስረሳኽ ተጠንቀቅ። እሱ ከሌለበት ያማረ ሥፍራ ይልቅ እሱ ያለበት በረት ይሻልኻል። እሱ ያልመረጠውን ሥፍራ መርጠኽ ከመንገድ አትቅር። “የተወለደው የአይሁድ ወዴት ነው?” ብለኽ ጠይቅ።

እሱ ደሃ ሆኖ ባለጠጋ የሚያደርግኽን ንጉሥ በሚያልፍ ደስታ አትጣው። በስካር በዝሙት በጭፈራ በሔሮድስ ቤተ መንግሥት ቀልጠኽ ቀርተኽ የተወለደውን #ሕፃን ሳታየው አትቅር። እሱ በተወለደባት ሌሊት አንተ ስትሞት አትደር። እመነኝ የተወለደው ይሻልኻል፤ ከሞቱት ጋር ጊዜኽን አታጥፋ።

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Respect your boss and follow your goals, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello A.B, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

<<ሕፃን ተወልዶልናልና÷ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል ÷አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል÷ስሙም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ÷የዘላለም አባት÷የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።>>

ት.ኢሳ.9÷6

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሰላም አደረሳችሁ!!!😍
የሰላም አለቃ የተባለ መድኃኒታችን ክርስቶስ የዘላለም አባት የተባለ ክርስቶስ ካለንበት የኃጢት መንደር በአባትነቱ ጎትቶ ያውጣን.!!!🙏🙏🙏

በድጋሚ ለመላው ክርስቶሳዊያን መልካም የዝማሬ የአምልኮና የመልካም አገልግሎት በአል ይሁን እላለሁ.!🙏😍🥰

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

“አነ ውእቱ ኖላዊ ኄር ወኖላዊሰ ኄር ይሜጡ ነፍሶ ቤዛ አባግዒሁ ፤ መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።”
— ዮሐንስ ፲፥፲፩

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአምሳለ ኖላዊ ለሚታሰብበት እና ከጌታችን ንዑሳት በዓላት መካከል አንዱ ለሆነው ለበዓለ "ኖላዊ" እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ !

እንደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት በዚህች ዕለተ ሰንበት ስለ መድኃኒታችን ቸር እና እውነተኛ ጠባቂነት በነቢያት የተነገረው ትንቢት በሐዋርያት የተሰበከውን ሁሉ እንናገራለን ፣ እናስተምራለን።

በብዙ ምሳሌ በቀደሙ ነቢያት ትንቢት የተነገረለት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እውነተኛ ጠባቂያችን ስለበጎቹ ራሱን ቤዛ አድርጎ የሚሰጥ መሆኑን ቀምሰን አይተነዋል።

ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት “እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋምም።” (መዝሙር ፻፳፩፥፬) እንዳለ በእውነት ትናንት ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ያዳነን ጠባቂያችን ቅዱስ እግዚአብሔር ዛሬም ጥበቃው እንደማይለየን እናምናለን።

እግዚአብሔር አምላካችን ሀገራችን ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ይባርክ ፣ ይጠብቅ !

አሜን !

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Wellahi yemeleselen😂😂

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ዛሬ እንጊዲ የኢየሱስ ልደት ነው ስለዚህ ለመላው ክርስቲያን በሙሉ
.
.
.
.
ይሄን ንኩት👇
አረ ልደት ያለውን ሰው ከማምለክ አምልጡ😂

አስባቹታል ግን ነገ በጠዋት ኢየሱስ ከተኛበት ቦታ መልአክቶች ሰርፕራይዝ ሊያደርጉት በለሊት ኬክ ይዘው ሀፒ ፐርስደይ ኢየሱስ መልካም ልደት ለኢየሱስ ሲሉ ኢየሱስ እንኳን ተወለድክልን ሲሉት አበስኩ ገበርኩ አለች እትዬ ብርቄ አረ ወገን ነቃ በሉ


✍ከወንድም NEJA 𝑺𝒕𝒖𝒅𝒆𝒏𝒕 🇵🇸
@eslmnan_teqebelu
ወሠላሙ ዐለይኩም

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ልደተ እግዚእ

<< ሦስት ነገሮች ያስደንቁኛል!!!
-"አባቱ የማይቀድመዉ ልጅ
-እናቱን የፈጠረ ልጅ
-የፈጠራትን የወለደች እናት"   ምንስ እንላለን ልደቱ  ድንቅ ነው!!! >>

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ።

መልካም በዓል!

ለቻናሉ አዲስ የሆናችሁ ክርስቲያኖች  𝕛𝕠𝕚𝕟 እያላችሁ ቤተሰብ ሁኑ
👇👇👇👇👇👇👇

@Lisanetewahido
@Lisanetewahido
@Lisanetewahido

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

+ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ! ከእርስዋ የተጸነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ:: ልጅም ትወልዳለች:: እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ:: በነቢይ ከጌታ ዘንድ:-'እነሆ ድንግል ትጸንሳለች:: ልጅም ትወልዳለች:: ስሙንም አማኑኤል ይሉታል:: የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኗል:: ትርጉዋሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው::

(ማቴ. 1:20)

+" እነሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራቹሃለሁና አትፍሩ:: ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት: እርሱም ክርስቶስ: ጌታ የሆነ ተወልዶላቹሃልና::

(ሉቃ. 2:10)

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello ⚔️Pen killer ⚔️🗡️, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ፤
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤
ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያት በሙሉ፤

በምሉእ ፍቅሩ ሰውን ከባርነት ወደ ነጻነት ለመመለስ በሥጋ ሰብእ የተወለደው ጌታችን  አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ሰባት ዓመተ ምሕረት የልደት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡

“ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ለዘሠምሮ ለሰብእ፤ ክብር በሰማያት ለእግዚአብሔር ይሁን›› በምድርም እጅግ ለወደደው የሰው ልጅ ሰላም ይሁን” (ሉቃ ፪÷፲፬)
ይህ ቃለ ሰላም በጌታችን ዕለተ ልደት የተነገረ ነው፣ ቃሉ የተነገረው እንዲሁ እንደ ተራ ነገር ሳይሆን በቃለ መዝሙር እየተደጋገመ ነው፡፡ የተዘመረውም በምድራውያን ደራሲዎች ሳይሆን በሰማያውያን መላእክተ እግዚአብሔር ነው፣ የያዘው መልእክትም ሰማያውያንና ምድራውያንን ሁሉ ያካለለ ነው፡፡ የመልእክቱ ገዢ ሓሳብም አምላክ ከሰውነታችን ጋር ባለመለያየት፣ባለመጠፋፋት፣ባለመቀላቀል፣ባለመዋዋጥ፣ ባለመለዋወጥና ያለባዕድና አንድ አካል፣አንድ ክዋኔ፣አንድ ጠባይ ሆኖ በተዋሕዶ ተገልጾኣልና እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን፡፡ የተዋሕዶውም ምስጢር ሰላምን ያሰፍናልና እግዚአብሔር ሰውን በእጅጉ መውደዱ ከዚህ ተዋሕዶ ዓውቀናል የሚል ነው፡፡

በእርግጥም እግዚአብሔር ሰውን ለመውደዱ ከዚህ የበለጠ ማሳያ ወይም ማስረጃ የለም፤ እንከን የለሽ ንጹህ አምላክ የእኛን ኃጢአተኛ ሰውነት አካሉ አድርጎ ተወለደ ሲባል ላስተዋለው ሰው ምንኛ ቢወደን ነው የሚለው ጥልቅ አድናቆትን ያጭራልና ነው፡፡ይህ ብቻም አይደለም በዚህ ነገረ ተዋሕዶ ምክንያት ሰውነታችን አምላክ ሆኖ በመንበረ ጸባኦት እንዲቀመጥ መብቃቱ የድኅነታችንና የክብራችን ከፍታ ምን ያህል አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንደደረሰ መንፈሳችን በአንክሮ ይረዳዋል፡፡ ድምር ውጤቱም በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ፍጹምና አስተማማኝ ሰላም መፈጠሩን ያስረዳናል፤ ሰማያውያኑ መላእክተ እግዚአብሔር በመዝሙራቸው ያበሰሩን ይህንን የምስራች ነው፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

እኛ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ እግዚአብሔር በእጅጉ ይወደናል ስንል እንዲሁ ከሜዳ ተነሥተን ኣይደለም፡፡ በበደላችንና በኃጢአታችን ሳይጸየፈን ሰውነታችንን በረድኤት ወይም በኅድረት ያይደለ በኩነት ተዋሕዶ ወደ አምላክነት ደረጃ ከፍ ስላደረገው  ነው እንጂ፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ፍጹምና ምሉእ ፍቅሩ ሰውነታችንን በመበረ ጸባኦት ኣስቀምጦ መላእክት ሳይቀሩ ፍጥረታትን በሙሉ እንድንገዛ አድርጎናል፤ ምክንያቱም መላእክት በዕለተ ልደት የዘመሩለት በተዋሕዶ አምላክም ሰውም ለሆነ ለቤተ ልሔሙ ሕፃን እንጂ ለመለኮት ብቻ ኣይደለምና ነው፡፡ የዕለተ ልደት መዝሙር ዛሬም በሰማያትም ሆነ በምድር በተዋሕዶ ሰውም አምላክም የሆነ አንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመለክበታል፣ ይመሰገንበታል፡፡ የሰማዩና የምድሩ ዕርቅ ወደ ኋላ ላይመለስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በዚህ ተከናውኗል፣ የእግዚአብሔር ፈቃድ የሰውም አዋጭ ምርጫ ይህ ዕርቅ ተጠብቆ እንዲኖር ነው፣ ያለ ዕርቅ ሰላም ሕይወት የለውምና፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

የእግዚአብሔር ክብርና ሰላም በእጅጉ የተሳሰሩና የተቆራኙ ናቸው፤ እኛ እግዚአብሔርን ካከበርነው፣ ካዳመጥነው፣ ከታዘዝነውና ከተከተልነው ሰላም አለ ማለት ነው፡፡ ለሱ ካልታዘዝንና እሱን ካላከበርን ግን ዘላቂ ሰላምን ማግኘት ፈጽሞ የማይታሰብ ነው፤ ምክንያቱም ሰላምን ጨምሮ መልካም ነገር ሁሉ ያለው በእግዚአብሔር እጅ ነውና፡፡ ዛሬ በሁሉም የዓለማችን ማዕዘን የሚታየው የሰላም መደፍረስ እግዚአብሔርን ካለማክበራችንና ለእርሱ ካለመታዘዛችን የተነሣ እንደሆነ መዘንጋት የለብንም፡፡ ዓለም ከእግዚአብሔር ቃል ርቃ ለመሄድ በእጅጉ እየኳተነች ነው፤ በዚህ እኩይ ተግባርዋ ደግሞ እግዚአብሔር ለስጋትና ለጉስቁልና አሳልፎ እየሰጣት ነው፡፡ እግዚአብሔር በምስጢረ ሥጋዌው ቢታረቃትም ዕርቁን ማክበር አቅቷታል፤ ይህንን የእግዚአብሔር ጸጋ ቸል ብላ የምታደርገው ሩጫ የትም ሊያደርሳት እንደማይችል ብታውቅና በንስሓ ብትመለስ እግጅ ተጠቃሚ ትሆናለች፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

የእግዚአብሔር ቃል “እናንተስ ከማይጠፋ ዘር ተወለዳችሁ” ብሎ ተስፋውን እንደነገረን ምድባችን ከማይጠፋ ዘር እንዲሆን ክርስቲያኖች የሆን ሁላችን በአእምሮ ጎልብተን፣ በሥነ-ምግባር አምረን፣ ጤናማ ሕይወትን ልንመራ ይገባናል፡፡

የአምላካችንን በዓለ ልደት ስናከብር ነገረ እግዚአብሔርን፣ነገረ ፍቅርን፣ነገረ ዕርቅንና ነገረ ሰላምን በማኅበረሰባችን የማሥረጽ አጀንዳ ይዘን ልናከብር ይገባል፡፡
ጠቡ፣ጥላቻው፣መለያየቱ፣መጠፋፋቱ፣ ለወንድሜ  ከማለት ይልቅ ለኔ ለኔ ማለቱ ሲጎዳን እንጂ ሲጠቅመን አላየንም፡፡ አሁንም ወደ ልባችን እንመለስና በፍቅር፣ በዕርቅና በእኩልነት፣ በስምምነትና በወንድምነት ወደሚገኝ አንድነት እንምጣ፤የልደቱ መዝሙር ያስተማረን ይህና ይህ ብቻ ነውና፡፡ በሌሎቹ ክፍለ ዓለማት እንደሆነው ሁሉ በሀገራችን የተከሠተው አላስፈላጊ ግጭት ብዙዎችን አሳጥቶናል፤ ብዙዎችንም ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሎ ሜዳ ላይ ፈሰው የሰቆቃ ኑሮ እንዲገፉ አድርጎብናል፡፡ የሀገር ሀብት እንዲወድም ሆኗል፤ ልጆቻችን ምናለ ከእንግዲህ ወዲህ ቢበቃንና ምድሪቱን የሰላም አየር እንድትተነፍስ ብንፈቅድላት፤ ይህ የወቅቱ የቤተክርስቲያናችን ዋነኛ መልእክትና ጥሪ ነው፡፡    

በመጨረሻም፡-

በዓለ ልደት የእግዚአብሔር በዓል ነውና፣ እግዚአብሔር በምድራችን ሰላምን ያወርድ ዘንድ ካለን ከፍለን ለተፈናቃዮች፣ለነዳያን እና ለአካል ጉዳተኞች በመለገስ በዓሉን በመንፈሳዊ ደስታና በሰላም እንድናከብር አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤

መልካም በዓለ ልደት ያድርግልን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር  አሜን!

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ሁለተኛው የአእላፋት ዝማሬ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ በተገኙበት እየተከናወ ነው።

ከቅዱስነታቸው ጋር ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ሌሎች ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንበረ ፓትርያርክና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና እጅግ በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናንና ምእመናት ተገኝተዋል።

መርሐ ግብሩን በቀጥታ ሥርጭት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቴሌቪዥን(EOTC TV)፣ ሀገሬ ቲቪ እና አርትስ ቲቪ እያስተላላፉት ይገኛሉ።

እንኳን ለበዓለ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ።

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

+ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ! ከእርስዋ የተጸነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ:: ልጅም ትወልዳለች:: እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ:: በነቢይ ከጌታ ዘንድ:-'እነሆ ድንግል ትጸንሳለች:: ልጅም ትወልዳለች:: ስሙንም አማኑኤል ይሉታል:: የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኗል:: ትርጉዋሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው::

(ማቴ. 1:20)

+" እነሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራቹሃለሁና አትፍሩ:: ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት: እርሱም ክርስቶስ: ጌታ የሆነ ተወልዶላቹሃልና::

(ሉቃ. 2:10)

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

የአእላፋት ዝማሬ ጀምሯል !!!


እሰይ ተወለደ በሚለው መዝሙር

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Henok, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Wubanch, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ስለገና በዓልና ጾም አንዳንድ ጥያቄዎች

የገና እና የጥምቀት በዓላት ሲደርሱ በምእመናኑ ዘወትር የሚጠየቁ ጥያቄዎች አሉ፡፡ እነዚኽን እና መሰል የሕዝቡን የዘወትር ጥያቄዎች መልስ የያዘ የማያዳግም ጥራዝ ማውጣት ከሊቃውንት ጉባኤ የሚጠበቅ ነው - አብዛኛዎቹ ጉዳዮች አበው ቀድመው ሥርዓት የሠሩባቸው እና ማብራርያ ብቻ የሚያስፈልጋቸው ናቸውና፡፡ ለዛሬ ሦስቱን ብቻ እንመልስ፡፡

ገና እና ጥምቀት ዓርብ እና ረቡዕ ቢውሉ ይበላባቸዋል ወይስ ይጾማሉ?

የቤተ ክርስትያናችን መመሪያ የሆነው ፍትሐ ነገሥት እንዲህ ይላል፤ “ዳግመኛ በየሳምንቱ ዓርብ እና ረቡዕን መጾም ነው፡፡ በዓለ ሃምሳ፥ የልደት እና የጥምቀት በዓል የተባበሩባቸው ጊዜ ካልኾነ በቀር .. የዓርብን እና የረቡዕን ጾም ግን ከልደት፥ ከጥምቀት እና ከበዓለ ኃምሳ በቀር ዘወትር ይጹሙ።” (ዐንቀጽ 15፥ ቁ. 566፤ ዐንቀጽ 15፥ ቁ. 603) ስለዚኽ ገና "ረቡዕ/ዓርብ" ከዋለ አይጾምም፤ ይበላል ማለት ነው!

የገና እና የጥምቀት ቅዳሴ ስንት ሰዓት ነው?

“ስለ ልደት እና ጥምቀት ግን በዚያ ዘመን በኒቂያ የተሰበሰቡ ሊቃውንት ቅዳሴው በሌሊት ይኾን ዘንድ አዘዙ።” (ፍትሐ ነገሥት ዐንቀጽ 15፥ ቁ. 595)

ልደት (ገና) ጋድ አለው?

“የልደት እና የጥምቀት በዓላት ጋድ አላቸው።” (ፍትሐ ነገሥት ዐንቀጽ 15፥ ቁ. 566) ትንታኔ፦ የገና ጾም 44 ቀናትን ይይዛል። 40 ቀን - ጾመ ነቢያት፥ 3 ቀን - ጾመ አብርሃም ሶርያዊ፥ 1 ቀን - ጋድ፤ ድምር 44 ቀን። የገና ጋድ ከጾሙ ተያይዞ የተቀመጠ እንጂ ለብቻው የተቀመጠ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ሰሙነ ሕማማት ለብቻው የሚቆጠር ጾም ነው፡፡ (ፍትሐ ነገሥት ዐንቀጽ 15፥ ቁ. 565) ነገር ግን አንድ ሰው ዐቢይ ጾምን ሳይጾም ከርሞ ሕማማትን ለብቻው መጾም አይችልም፡፡ የገናም ጋድ እንዲኹ ነው፡፡

ይኽንን ጋድ የልደትን ጾም የማይጾሙ ሰዎች እንዲጾሙት የተሠራ ነውን?

በቤተ ክርስቲያን ላልተጠመቁ፥ ለማይቆርቡ፥ ንስሐ ለማይገቡ፥ ለማያስቀድሱ፥ ለማይጾሙ ሰዎች ተብሎ የተሠራ ልዩ ሥርዓት የለም፡፡ በፍትሐ ነገሥት ዐንቀጽ 15፥ ቁ. 565 እንደተገለጠው ሰባቱ አጽዋማት ‛ለክርስቲያን ኹሉ’ የታዘዙ ናቸው፡፡ ስለዚኽም የገናን ጾም ክርስቲያን ኹሉ ጾመው በበዓለ ልደት ሊገድፉ ይገባቸዋል፡፡

ስለዚኽ ገና (ልደት) እና ጥምቀት ረቡዕ ወይም አርብ ከዋሉ ማክሰኞ እና ኃሙስ ጋድ ኾነው የበዓሉ ቀን አይጾምም ማለት ነው!

✍ ዲያቆን ታምራት

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Bogale, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

መልሱን ከነ ማብራረያው ቢነገረን

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ከይቅርታ ጋር ይሔ መረጃ ስህትት ነው
ብፁነታቸው ካረፉ በጣም ቆይቶል የተሳሳተ መረጃ ነው።

Читать полностью…
Subscribe to a channel