ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ። ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ›› ት.ኢሳ 58÷3 https://youtu.be/csxxAMGtC4I ለመቀላቀል http://t.me/ortodoxtewahedo
Hello Sitanaa, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…Hello 057289, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
እመቤቴ ሆይ....
"የሕይወት ዘመኔ በስንፍናና በእንዝላልነት ሊያልቅ ቢቃረብ፥ንስሐ የምገባበት ፥ጽድቅ የምሰራበት ዕድሜ ጨምሪልኝ።" መልክአ.ማርያም
🌻🌼🌼
ስንቶች ሲያልፉ፣ሲጠፉ፣ሲደናቀፉ፣ሲከፉ፣ሲገፉ
በህይወት ጠብቆ፥ዘመንን ጨምሮ ለዚህ ያደረሰን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላካችን ስሙ ምስጉን ይሁን !!በዚህ ሰአት እኛ ያገኘነውን ላጡ በረሀብና ጥም፣ በጦርነትና ስደት ያሉ ወገኖቻችንን በቸርነቱ ይታደግልን።!!! ዘመነ ማቴዎስ ( ለሀገራችን ህመም መዳኛዋ ይሁንልን!!
"...ዕለታት ክፉዎች ወይም ጥሩዎች የሚኾኑት በተፈጥሮአቸው እንደዚያ ኾነው አይደለም፡፡ ዕለቱን ክፉ ወይም ደግ እንዲኾን የምናደርገው እኛው ነን፡፡ የአምናው እሁድ ከዘንድሮ እሁድ የተለየ አይደለም፡፡ የተለየ የሚያደርገው የእኛ ብርታት ወይም ስንፍና ብቻ ነው፡፡"ቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ
🌼 አዲሱ ዓመት እምነታችን የሚያፀናልን ልብ ሰላምን ጤና እድገትን መከባበር መተሳሰብ አንድነትን የሚጠነክርበት አዲስ አመት ይሁንልን🌻
🌷መልካም በዓል ይሁንላችሁ🤲☦
✝ክርስትናና ሚዲያ እንዴት?✝
Size:- 102.2MB
Length:-1:50:26
በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
Hello Ras, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete The text contains the robot command ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
Hello Besufekad, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
መልእክት ለወንድሞቼና እኅቶቼ /መልእክት ዐሥር/
እንኳን ለዐዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ። ፀሐይ ወደ ተፈጠረችበት ዕለት [ዕለተ ረቡዕ] ፈቷን ታዞራለች ፤ በተወለደችበትም በዚያኑ ዕለት ልደቷን ታከብራለች። ክርስቲያኖች ሆይ ፤ እኅቶቼ ሆይ ፤ ወንድሞቼ ሆይ እስከአሁን በሌላ በሌላ መንገድ ኖርን። አሁን ወደ ማሕፀናችን እንመለስ ፤ ወደ አባታችን ዕቅፍ፣ ወደ ጌታችን ወደ ክብር ባለቤት ፊታችንን እናዙር። እውነት እላችኋለሁኝ ፤ በዘመናችን ሁሉ ደጉን ሁሉ ጌታችን አሳይቶናል። ደግ ሁሉ ከጌታችን ከአምላካችን ነውና።
እስከአሁን ስሜታችን ደስ ካላለው ጌታችን የተናገረውን እንደባዶ ቃል እንወረውረዋለን ፤ አሁን ደግሞ እስኪ የጌታችንን ቃል ለማድረግ እንጣጣር። እስከአሁን ድረስ በራሳችን መንገድ ሞከርነው [ያተረፍነውንም እናውቀዋለን] እስኪ ይህንን ዓመት ደግሞ በእግዚአብሔር መንገድ እንሞክረው። ዮሐንስ ተሻረ ማቴዎስ ተሾመ ፤ በሕይወታችንም ውስጥ ስሜት ይሻር መጽሐፍ ቅዱስም ይሾም። 2016 አለፈ 2017 ደረሰ ፤ እኛም በኀጢአት ላይ ተረማምደን አልፈን ወደ ጽድቅ እንድረስ። ምንስ ብናደርግለት በእውነት እስከመሞት ለወደደን አምላክ ይበዛበት ይኾን?
እስከአሁን ክቡር የሆነ አብ ይክበር፣ ፍጹም አምላክ የኾነ ወልድ ይመስገን፣ መጽኛ መጽናኛ ለኾነ ለመንፈስ ቅዱስ ክብርና ሞገስ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሁን። ቅዱሳን ጻድቃን በዐዲሱ ዓመት አምላካችንን እናስደስተው ዘንድ ጸልዩልን። አባታችን የእምነት ጀግና አግናጥዮስ ሆይ ጸልይልን ፤ ምርጥ ዕቃ ጳውሎስ ሆይ ለምንልን። ከሁሉ ቅዱሳን የምትበልጪ የምድር እመቤት የሰማይም ንግሥት ሆይ ጸሎትሽ ለድኅነታችን እንዲሆን ከልጅሽ ዘንድ ለምኚ።
እንኳን ለ2017 ዓ.ም. ዐዲስ ዓመት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። አብን አፍቅረን ወልደ አብን አክብረን መንፈስ ቅዱስን ተከትለን የምንድንበት የድኅነት ዘመን ፤ እረኛችን እንዲሸከመን የተረጋጋን በግ የምንሆንበት፣ የዓለም ድካም አሰልቺ እንደሆነ እንድናውቅ ዐይናችን ተከፍቶ የዓለምን ከባድ ሸክም ጥለን የአምላካችንን ልዝብ ሸክም የምንሸከምበት ፤ ከጠፋንበት ወደ አባታችን የሞቀ ቤት የምንመለስበት፣ በሚያበረታቱ ቅዱሳን ምስክሮች ተከበን ሩጫውን እያበረታቱን የምንፈጽምበት ዘመን ይሁንልን። /ሉቃ 15/ዕብ 12/
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete site link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደዘመነ ማቴዎስ በሰላም፥ በፍቅር አሸጋገራችኹ! [ምንም እንኳን በሰላም ያላለፈላቸው ቢኖሩም ለእነርሱም ሰላምን ይሰጥልን ዘንድ በጸሎታችን እናስባቸው! በሕይወት መኖራችን ራሱ ትልቅ ስጦታ ነውና እናመስገነው!] ዘመኑን ሰላምን በሩቁ ከመስማት አልፈን እንደልባችን የምንጠግብበት የፍቅር ዘመን ያድርግልን። ቅዱስ እስጢፋኖስ በምልጃው አይለየን!
🤲 [አሜን እያላችኹ የወንድም አቡን ምርቃት ተቀበሉ!] በአዲሱ ዓመት የጌታን ስጋና ደም ለመቀበል ያብቃችኹም። ጌታ በአዲሱ ዓመት ኃጢያትን ለመስራት የደነደነ ልብ ጽድቅን ለመስራት የበረታ የጠነከረ ልብ ያድለን። በአዲሱ ዓመት ጌታ ጸሎት ወዳድነትን፥ ጥበብን፥ ማስተዋልን፥ ትዕግስትን ያድላችኹ፤ እንዲሁም ሰዉን ኹሉ የሚወድ ልብ ይስጣችኹ። አዲሱን ዓመት በማንበብ በክርስቲያናዊ ስራ እንድታሳልፉ ጌታ ይርዳችኹ።
❤️ ከኹሉም በላይ አባ ገብረ ኪዳን እንዳሉን በክርስቶስ የምንደሰትበት [ክርስቶስም በኛ የሚደሰትበት] ዓመት ያድርግልን!
Hello Calm, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…#ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ
መስከረም 2
መስከረም ሁለት በዚህች ቀን የካህኑ የዘካርያስ ልጅ የከበረ አጥማቂው ዮሐንስ ሕግን አፍራሽ በሆነ በንጉሥ ሄሮድስ እጅ ሰማዕት ሆነ።
ይህም እንዲህ ነው በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ነቢዩ ዮሐንስ በገሠጸው ጊዜ ፊልጶስ ወንድሙ ስለሆነ ቅዱስ ዮሐንስም የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም ይለው ነበርና።
ቅዱስ ዮሐንስም ሄሮድስን የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን ስለማግባቱና ሌላም ያደርገው ስለነበረ ክፉ ሥራ ሁሉ ይገሥጸው ነበር። ደግሞም በተግሣጽ ላይ ተግሣጽን ጨመረ። ስለዚህም ዮሐንስን ተቀየመውና በግዞት ቤት አኖረው።
ሄሮድስም ዮሐንስን ይፈራው ነበር ጻድቅ ቅዱስ ሰው እንደሆነ ያውቅ ነበርና ብዙ ይጠባበቀውም ነበር። ሄሮድስ የተወለደባትን ቀን በዓል የሚያከብርባት ዕለት ነበረች መኳንንቱን አለቆቹን መሣፍንቱን ሹሞቹን በገሊላ አገር ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ግብር አገባ።
የሄሮድያዳ ልጅም ወደ አዳራሹ ገብታ ዘፈነች ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው ከእርሱ ጋር በማዕድ የነበሩትንም ንጉሡም ያቺን ብላቴና የምትሺውን ለምኚኝ እሰጥሻለሁ አላት። እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ሊሰጣት ማለላት።
ወጥታም እናቷን ምን ልለምነው አለቻት እናቷም የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ አለቻት። ያን ጊዜም እየሮጠች ወደ ንጉሡ ገብታ የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በወጭት አሁን እንድትሰጠኝ እሻለሁ ብላ ለመነችው። ንጉሡም ስለ መሐላው አብረውት ስለ ነበሩትም ሰዎች አዘነ እምቢ ሊላት ግን አልወደደም።
ያን ጊዜም ባለወጎችን ላከ በእሥር ቤትም ሳለ የዮሐንስን ራስ ቆረጡ ራሱንም በወጭት አምጥተው ለዚያች ብላቴና ሰጡአት እርሷም ወስዳ ለእናቷ ሰጠች። በዚያችም ቀን የቅዱስ ዮሐንስ ራስ ከሄሮድያዳ ከእጆቿ ላይ ወደ አየር ስለ በረረች ታላቅ ድንጋፄ ሆነ።
ደግሞም ሄሮድስ ሆይ የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም እያለች በመጮኽ ዘልፋዋለችና። ደቀ መዛሙርቱም በሰሙ ጊዜ መጥተው በድኑን ወስደው ቀበሩት።
#ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ!
❤ከ #መጥምቀ_መለኮት_ቅዱስ_ዮሐንስ ❤ ታሪክ ምን ያስተምረናል.....
#አስቀድሞ መሐላ መማል ፈጽሞ ተገቢ እንደልሆነ፡- "የሄሮድያዳ ልጅ ንጉሥ ሄሮድስን በዘፈኗ በጣም አድርጋ ስላስደሰተችው
እርሱም በተራው ሊያስደስታት ፈለገ፡፡ ‹እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን
የለመነችውን ይሰጣት ዘንድ በሕዝቦቹና በመኳንንቱ ሁሉ ፊት እንዳይከዳት በፅኑ ቃልኪዳን ማለላት፡፡› እንዲህም እያለ
‹የፈለግሽውን ጠይቂኝ፣ የመንግሥቴንም እኩሌታ ቢሆን እሰጥሻለሁ ምን ላድርግልሽ?›
እያለ በመሐላ ባላት ጊዜ በእናቷ ምክር የዮሐንስን አንገት ቆርጦ ይሰጣት ዘንድ ለመነችው፡፡ ንጉሥ ሄሮድስም ይህን ልመና
ከአፏ በሰማ ጊዜ ‹የፈለግሽውን እሰጥሻለሁ› ብሎ በሕዝቡ ፊት ስለማለ ለሰው ይምሰል አዘነ፣ ተከዘ፡፡ ኃዘኑም ስለ ዮሐንስ መሞት
አይደለም፣ ዮሐንስን ሕዝቡ ይወደው ስለነበር እነርሱን ስለ መፍራቱና መሐላ ምሎ ከዳ
እንዳይባል ነው እንጂ፡፡ ስለ ዮሐንስ አዝኖ ቢሆን ኖሮ ቀድሞውንም በግፍ እንዲታሰር ባላደረገው ነበር፡፡
#ወንድሞቼ እኅቶቼ ሆይ! ከመሐላ የተነሣ መፍራት ይገባችኋል፡፡ ‹የለመንሽውን ሁሉ
እሰጥሻለሁ› ብሎ ስለማለ ሄሮድስ የዮሐንስን አንገት እንድትቆረጥ አደረገ፡፡
📌ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በቅዱስ ወንጌል ‹ፈጽማችሁ አትማሉ› ብሏል፡፡ ከዚህ በኋላ ወታደሮች ሠይፍ ይዘው የዮሐንስን አንገት ይቆርጡ ዘንድ ወደ መኅኒ ቤት ሄዱ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም የሄሮድስ ጭፍሮች ሊገድሉት
እንደመጡ በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ስላወቀ ከጨለማው ቤት ውስጥ አንገቱን በመስኮት አውጥቶ እንደሚመቻቸው አድርጎ ጠበቃቸው፡፡ የሄሮድስን ቃል እንዳያቃልሉ ጭፍሮቹም የ"መጥምቀ መለኮት ዮሐንስን"
አንገት ስለ መሐላው ቆረጡት፡፡ በመሐላ ምክንያት ባይሆን ኖሮ ሄሮድስ መጥምቀ መለኮት ዮሐንስን ባላስገደለው ነበር፡፡ ስለዚህ
ወንድሞቸ እኅቶች ሆይ! እናንተም ከመሐላ የተነሣ መፍራት ይገባችኋል፣ ፈጽማችሁም መማል የለባችሁም፡፡››
📌ስካርና ዘፈን ከሚገኙበት ቦታ አጋንንትና ኃጢአት ከዚያ አሉ፡-
‹‹ወንድሞችና እኅቶች ሆይ! አለልክ መብላትና መጠጣት ካለበት ቦታ #እግዚአብሔርን መበደል፣ ማስቀየምና ማስቆጣት ይገኝበታል፡፡ ስካር ከሚገኝበት ቦታ አጋንንትና ኃጢአት ከዚያ አሉ፡፡ ስካርና ዘፈን ከሚገኝበት
ቦታ የ #እግዚአብሔር መቅሰፍት የፈጣሪያችን ቁጣና በቀል ይፈጸምበታልና፡፡ እናንተ ሕዝበ ክርስቲያኖች ሆይ! ከስካር፣ ከዘፈንና
ከዝሙት መራቅ ይገባችኋል፡፡
📌መጥምቀ መለኮት ዮሐንስን ያስገደለው
ዘፈን፣ ስካርና የዜማ ፍቅር መሆኑን ልብ በማለት መገንዘብ አለባችሁ፡፡››
✝ሥር ሰዳችሁ እደጉ✝
Size:- 68.3MB
Length:-1:13:47
በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
አመታዊ ክብረ በአል አደረሳቹ
Invite me to your chatgroup, give me admin rights and I will delete any gif that someone will send.
Feedback? -> https://goo.gl/forms/IfRolehbn3n3SQbV2
Welcomes everyone that enters a group chat that this bot is a part of. By default, only the person who invited the bot into the group is able to change settings.
Commands:
/welcome - Set welcome message
/goodbye - Set goodbye message
/disable_goodbye - Disable the goodbye message
/lock - Only the person who invited the bot can change messages
/unlock - Everyone can change messages
/quiet - Disable "Sorry, only the person who..." & help messages
/unquiet - Enable "Sorry, only the person who..." & help messages
You can use $username and $title as placeholders when setting messages. HTML formatting is also supported.
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
🌼"ሌቦች ባዶ ቤትን ለመበርበር አይመጡም፤ ወርቅና ብር ወዳለበት ቤት እንጂ፡፡ ዲያብሎስም ልክ እንደዚህ ነው፤ ሊፈትናቸው የሚመጣው መንፈሳዊ ሀብታትን ወዳከማቹት ነው፡፡"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
Hello Amanuel, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
online job መስራት ምትፈልጉ በውስጥ አሁኑኑ አዋሩኝ ታመሰግኑኛላቹ
Читать полностью…🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_1_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2ኛ ቆሮ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አብረንም እየሠራን የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ እንዳትቀበሉ ደግሞ እንለምናለን፤
² በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።
³ አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ በአንዳች ነገር ማሰናከያ ከቶ አንሰጥም።
⁴ ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤
⁵ በብዙ መጽናት፥ በመከራ፥ በችግር፥ በጭንቀት፥ በመገረፍ፥ በወኅኒ፥ በሁከት፥ በድካም፥ እንቅልፍ በማጣት፥
⁶ በመጦም፥ በንጽህና፥ በእውቀት፥ በትዕግሥት፥ በቸርነት፥ በመንፈስ ቅዱስ፥ ግብዝነት በሌለው ፍቅር፥ በእውነት ቃል፥
⁷ በእግዚአብሔር ኃይል፥ ለቀኝና ለግራ በሚሆን በጽድቅ የጦር ዕቃ፥ በክብርና በውርደት፥
⁸ በክፉ ወሬና በመልካም ወሬ ራሳችንን እናማጥናለን፤ አሳቾች ስንባል እውነተኞች ነን፤
⁹ ያልታወቁ ስንባል የታወቅን ነን፤ የምንሞት ስንመስል እነሆ ሕያዋን ነን፤ የተቀጣን ስንሆን አንገደልም፤
¹⁰ ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ያዕቆብ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁸ እናንተ ደግሞ ታገሡ፥ ልባችሁንም አጽኑ፤ የጌታ መምጣት ቀርቦአልና።
⁹ ወንድሞች ሆይ፥ እንዳይፈረድባችሁ እርስ በርሳችሁ አታጉረምርሙ፤ እነሆ፥ ፈራጅ በደጅ ፊት ቆሞአል።
¹⁰ ወንድሞች ሆይ፥ የመከራና የትዕግሥት ምሳሌ የሆኑትን በጌታ ስም የተናገሩትን ነቢያትን ተመልከቱ።
¹¹ እነሆ፥ በትዕግሥት የጸኑትን ብፁዓን እንላቸዋለን፤ ኢዮብ እንደ ታገሠ ሰምታችኋል፥ ጌታም እንደ ፈጸመለት አይታችኋል፤ ጌታ እጅግ የሚምር የሚራራም ነውና።
¹² ከሁሉም በፊት፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ በሰማይ ቢሆን በምድርም ቢሆን በሌላ መሐላም ቢሆን በምንም አትማሉ፤ ነገር ግን ከፍርድ በታች እንዳትወድቁ ነገራችሁ አዎን ቢሆን አዎን ይሁን፥ አይደለምም ቢሆን አይደለም ይሁን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² በሐዋርያትም እጅ ብዙ ምልክትና ድንቅ በሕዝብ መካከል ይደረግ ነበር፤ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው በሰሎሞን ደጅ መመላለሻ ነበሩ።
¹³ ከሌሎችም አንድ ስንኳ ሊተባበራቸው የሚደፍር አልነበረም፥
¹⁴ ሕዝቡ ግን ያከብሩአቸው ነበር፤ የሚያምኑትም ከፊት ይልቅ ለጌታ ይጨመሩለት ነበር፤ ወንዶችና ሴቶችም ብዙ ነበሩ።
¹⁵ ስለዚህም ጴጥሮስ ሲያልፍ ጥላውም ቢሆን ከእነርሱ አንዱን ይጋርድ ዘንድ ድውያንን ወደ አደባባይ አውጥተው በአልጋና በወሰካ ያኖሩአቸው ነበር።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_1_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"አድኅንኒ እምእለ ሮዱኒ እስመ ይኄይሉኒ። ወአውጽነ እሞሕቅ ለነፍስየ። ከመ እግነይ ለስምከ እግዚኦ"። መዝ 141፥6-7።
"እጅግ ተቸግሬአለሁና ወደ ልመናዬ አድምጥ፤ በርትተውብኛልና ከሚያሳድዱኝ አድነኝ። አቤቱ፥ ስምህን አመሰግን ዘንድ ነፍሴን ከወህኒ አውጣት፤ ዋጋዬን እስክትሰጠኝ ድረስ ጻድቃን እኔን ይጠብቃሉ"።
መዝ 141፥6-7።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_1_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ኢየሱስም አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ማዘዝ በፈጸመ ጊዜ በከተሞቻቸው ሊያስተምርና ሊሰብክ ከዚያ አለፈ።
² ዮሐንስም በወህኒ ሳለ የክርስቶስን ሥራ ሰምቶ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከና፦
³ የሚመጣው አንተ ነህን? ወይስ ሌላ እንጠብቅ? አለው።
⁴ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ሄዳችሁ ያያችሁትን የሰማችሁትንም ለዮሐንስ አውሩለት፤
⁵ ዕውሮች ያያሉ አንካሶችም ይሄዳሉ፥ ለምጻሞችም ይነጻሉ ደንቆሮችም ይሰማሉ፥ ሙታንም ይነሣሉ
⁶ ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤ በእኔም የማይሰናከለው ሁሉ ብፁዕ ነው።
⁷ እነዚያም ሲሄዱ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ እንዲህም አለ፦ ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣችሁ?
⁸ ነፋስ የሚወዘውዘውን ሸምበቆን? ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ቀጭን ልብስ የለበሰ ሰውን? እነሆ፥ ቀጭን ልብስ የለበሱ በነገሥታት ቤት አሉ።
⁹ ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ፥ ከነቢይም የሚበልጠውን።
¹⁰ እነሆ፥ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነውና።
¹¹ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤ በመንግሥተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።
¹² ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፥ ግፈኞችም ይናጠቋታል።
¹³ ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ፤
¹⁴ ልትቀበሉትስ ብትወዱ፥ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይህ ነው።
¹⁵ የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።
¹⁶ ነገር ግን ይህን ትውልድ በምን እመስለዋለሁ? በገበያ የሚቀመጡትን ልጆች ይመስላሉ፥ እነርሱም ባልንጀሮቻቸውን እየጠሩ።
¹⁷ እንቢልታ ነፋንላችሁ ዘፈንም አልዘፈናችሁም ሙሾ አወጣንላችሁ ዋይ ዋይም አላላችሁም ይሉአቸዋል።
¹⁸ ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፥ እነርሱም፦ ጋኔን አለበት አሉት።
¹⁹ የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፥ እነርሱም፦ እነሆ፥ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ ይሉታል። ጥበብም በልጆችዋ ጸደቀች።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱሳን_ሐዋርያት ወይም የ #ቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ ነጎድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም የመልአኩ የቅዱስ ራጉኤል በዓለ ሲመቱ፣ የሐዋርያው የቅዱስ በርተሎሜዎስም የዕረፍት በዓልና የታላቁ አባት የአባ ሚልኪ የዕረፍት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🌻አዲሱን ዓመት ንስሐ ገብተን #ቅዱስ_ሥጋውንና #ክቡር_ደሙን የምንቀበልበት ዓመት ያድርግልን🌻