ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ። ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ›› ት.ኢሳ 58÷3 https://youtu.be/csxxAMGtC4I ለመቀላቀል http://t.me/ortodoxtewahedo
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete Username(ID) ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete The text contains the robot command ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
✝ መርጌታ ሊባኖስ የባህል ህክምና ሰጭ
✝ 👉👉☎️ 09 89 51 01 77 ☎️
09 89 51 01 77
1 ለገበያ መሣቢያ
2 ለቁማር (ለእድል)
3 ለወሲብ ሥንፈት ቶሎ ለሚያበቃ(ለውፍረት:ለቁመት
4 ለመስተፋቅር
5 ጥይት ለማያስመታ (ለጠላት አፍዝ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር)
8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
12 ሰላቢ የማያስጠጋ
13 ለመፍትሔ ሀብት
14 ለመስተፋቅር
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለገብያ
17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 ለመድፍነ ፀር
19 ሌባ የማያስነካ
20 ለበረከት
21 ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ)
22 አፍዝዝ አደንግዝ
23 ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
24 ለግርማ ሞገስ
25 መርበቡተ ሰለሞን
26 ለዓይነ ጥላ
27 ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
28 ለሁሉ መስተፋቅር
29 ጸሎተ ዕለታት
30 ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
31 ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
32 ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
33 ለድምፅ
34 ለብልት
አገልግሎት(ምናልባት ያለ ኮከባቸው
የተጋቡ ካሉ
አስማምቶ የሚያኖር መድሀኒት
ማሳሰቢያ፦🌿የሰውን ልጅ ለመጣል ለማሳበድ በ አጠቃላይ ከህይወት መስመር ለማውጣት አንሰራም🌿
ለጥያቄዎ ☎️☎️ 09 89 51 01 77ይደውሉሉ
✝✝✝✝✝✝✝✝✝
በወንጌሉ ያመናቹ እንኳን
ለብርሃነ መስቀሉ
አደረሳችሁ።
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ÷ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።"
1ቆሮ• 1 ÷ 18
#መልካም እለተ ይሁንልን
ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
✝✝✝✝✝✝✝✝✝
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ÷ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።"
1ቆሮ• 1 ÷ 18
#መልካም እለተ ይሁንልን
ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼.
#አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ 40 በላይ ድርሰቶቹ መካከል በአብዛኞቻችን ዘንድ የሚታወቁት 34ቶቹ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፤
1. ✼ ኆኀተ ብርሃን
2. ✼ መዝሙረ ኢየሱስ (ሰላመ ማርያም)
3. ✼ መዝሙረ ድንግል
4. ✼ የማርያም የምስጋና ሰላምታ
5. ✼ ውዳሴ መላእክት
6. ✼ ውዳሴ ነቢያት
7. ✼ ውዳሴ ሐዋርያት
8. ✼ ውዳሴ ሰማዕታት
9. ✼ ውዳሴ ጻድቃን
10. ✼ መጽሐፈ ብርሃን
11. ✼ መጽሐፈ ምሥጢር
12. ✼ መጽሐፈ ሰዐታት ዘመዓልት ወዘሌሊት
13. ✼ መጽሐፈ አርጋኖን
14. ✼ አርጋኖነ ውዳሴ
15. ✼ መሰንቆ መዝሙር
16. ✼ እንዚራ ስብሐት
17. ✼ ውዳሴ መስቀል
18. ✼ ፍካሬ ሃይማኖት
19. ✼ ፍካሬ ሐዋርያት
20. ✼ መጻሕፍተ ቅዳሴያት
21. ✼ ቅዳሴ እግዚእ ካልዕ
22. ✼ መዐዛ ቅዳሴ
23. ✼ ሕይወታ ለማርያም (ሕይወተ ማርያም)
24. ✼ ውዳሴ ስብሐት
25. ✼ ውዳሴ ማርያም ካልዕ
26. ✼ ውዳሴ ስብሐት ወሰላምታ
27. ✼ ማኅሌት ዘነቢያት ወዘሐዋርያት
28. ✼ የሰባቱ ጊዜያት ጸሎት (መልክአ ሕማማት)
29. ✼ ጸሎተ ፈትቶ (ጸሎተ ማዕድ)
30. ✼ ጸሎት ዘ(ቤት)ውስተ ቤት
31. ✼ መልክአ ቊርባን
32. ✼ ተአምኆ ቅዱሳን
33. ✼ ተአምኆታ ለእግዝእትነ ማርያም
34. ✼ ክብረ ቅዱሳን
< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >
#መልካም ቀን
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
በመንገዳችን ላይ ውብ የጋሞ እናት እና ወጣቶች መስቀልን ለማክበር ጉዞ ወደ መስቀል አደባባይ።
Читать полностью…††† እንኳን ለጻድቃን ቅዱሳን አባ አጋቶን ወአቡነ ያሳይ ዘመንዳባ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† አባ አጋቶን ዘዓምድ †††
††† ታላቁ ጻድቅ በትውልድ ግብጻዊ ሲሆኑ የነበሩበት ዘመንም ከ4ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ እስከ 5ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ አካባቢ ነው:: በእርግጥ 'አጋቶን ' በሚባል ስም የሚጠሩ ብዙ አበው አሉ:: ቅድሚያውን 2ቱ ይወስዳሉ::
አንደኛው አባ አጋቶን ለ30 ዓመታት ድንጋይ ጐርሰው የኖሩት አባት ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ ዛሬ የምናከብራቸው ናቸው:: እኒህኛው 'ዘዓምድ ' ይባላሉ:: ምክንያቱም ለ50 ዓመታት አንድ ምሰሶ ላይ ያለ ዕረፍት ጸልየዋልና ነው::
አባ አጋቶን ገና ከልጅነታቸው መጻሕፍትን የተማሩ ሲሆኑ ምናኔን አጥብቀው ይፈልጓት ነበር:: በዚህም ራሳቸውን በትሕርምት እየገዙ: በዲቁና ማዕርጋቸውም እያገለገሉ እስከ 35ዓመታቸው ቆዩ:: በዚህ ጊዜ ደግሞ 'ይገባሃል' ብለው ቅስናን ሾሟቸው::
የማታ ማታ የለመኑትን የማይነሳ ጌታ ተምኔተ ልባቸውን ፈጽሞላቸው ወደ በርሃ ሔዱ:: ወቅቱ የግብጽ ገዳማት በቅዱሳን ሕይወት የበሩበት ነውና እዚህም እዚያም አበውና እናቶች ይገኙ ነበር::
አባ አጋቶንም የከዋክብቱ አበው አባ ገዐርጊና አባ አብርሃም ደቀ መዝሙር ሆነው ገቡ:: አስፈላጊውን የምንኩስና ፈተና ካለፉ በኋላም ምንኩስናን ከእነዚህ አባቶች ተቀበሉ:: በዚያው በገዳመ አስቄጥስ በጽኑ ገድል ተጠምደው ለ15 ዓመታት አገለገሉ::
ጻድቁ ከእርሳቸው በፊት የነበሩ ቅዱሳንን ተጋድሎ ጠዋት ማታእያነበቡ መንፈሳዊ ቅናትን ይቀኑ ነበር:: በተለይ የታላቁን ስምዖን ዘዓምድን ገድል ሲያነቡ ሕሊናቸውን ደስ ይለው: ይህንኑ ገድል ይመኙ ነበር:: እድሜአቸው 50 ዓመት በሞላ ጊዜ በልቡናቸው እንደ አባ ስምዖን ዘዓምድ ለመጋደል ወሰኑ:: ይህን ለገዳሙ አባቶች ቢያማክሯቸው አበው:- "ይበል! ሸጋ ምክር ነው:: እግዚአብሔር ያስፈጽምህ!" ብለው መርቀው አሰናበቷቸው:: አባ አጋቶን የዳዊትን መዝሙር እየዘመሩ ከገዳሙ ወጡ:: በጣምም ወደ ዓለም ሳይገቡ: ከዓለም (ከከተማም) በጣም ሳይርቁ አንድ ረዥም ምሰሶ አገኙና ከላዩ ላይ ወጡ::
ከዚህች ዕለት ጀምረው ጻድቁ ለ50 ዓመታት ከዚያች ዓምድ (ምሰሶ) ወርደው: ለሥጋቸውም ዕረፍትን ሰጥተውት አያውቁም:: ማዕከለ ገዳም ወዓለም ናቸውና ለምዕመናንም ሆነ ለመነኮሳት አጽናኝ አባት ሆኑ:: ለአካባቢውም የብርሃን ምሰሶ ሆኑ:: የታመመ ቢኖር ይፈውሱታል:: የበደለውን በንስሃ ይመልሱታል:: ሰይጣን የቋጠረውን ይፈቱታል:: ለራሳቸው ግን ከጸሎት: ከጾምና ከትሕርምት በቀር ምንም አልነበራቸውም:: በተለይ እነዚህ ስራዎቻቸው ይዘከሩላቸዋል::
1.አጥማቂ ነን እያሉ ሕዝቡን ያስቱ የነበሩ ሰዎችን እየጠሩ እንዲህ የሚያስደርጋቸውን ጋኔን ከእነሱ አስወጥተዋል::
2.እርሳቸውን ያልሰሙት ግን መጨረሻቸው ጥፋት ሆኗል::
3.ፍጹም ወንጌልን በሕይወትና በአንደበት መስክረዋል::
4.ሕዝቡን በንስሃ አስጊጠዋል::
5.ተግሳጽ የሚገባውን ገስጸዋል::
ጻድቁ አባ አጋቶን ዘዓምድ ከእነዚህ የቅድስና ዘመናት በኋላበተወለዱ በ100 ዓመታቸው በዚህች ቀን ዐርፈው በክብርና በዝማሬ ተቀብረዋል::
††† አቡነ ያሳይ ዘመንዳባ †††
††† እኒህ ኢትዮዽያዊ ጻድቅ በ14ኛው መቶ ክ/ዘ በጣና ገዳማትውስጥ ያበሩ ኮከብ ናቸው:: ከ7ቱ ከዋክብት (አባ ዮሐንስ፣ አባ ታዴዎስ፣ አባ ያፍቅረነ እግዚእ፣ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አባ ሳሙኤል ዘቆየጻና አባ ሳሙኤል ዘጣሬጣ ) እርሳቸው አንዱ ናቸው:: እነዚህ አበው ከገዳማዊ ሕይወታቸው ባሻገር በምስጉን የወንጌል አገልግሎታቸው የሚታወቁ ናቸው::
ገድላቸው እንደሚለው አቡነ ያሳይ የዐፄ ዐምደ ጽዮን ቀዳማዊ ልጅ ሲሆኑ የተወለዱትም በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ሽዋ: ተጉለት ውስጥ ነው:: ገና በልጅነታቸው ወደ አባታቸው ቤተ መንግስት የሚመጡ መነኮሳትን እግር እያጠቡ ሥርዓተ ምንኩስናን በድብቅ ያጠኑ ነበር::
ብሉይ ከሐዲስ የጠነቀቁ ናቸውና የአባታቸውን ዙፋን (ልዑልነት) ስለ ፍቅረ ክርስቶስ ንቀውት እየዘመሩ ጠፍተው ወደ ትግራይ ተጓዙ:: በዚህም ምክንያት 'መናኔ መንግስት' ይባላሉ:: በዚያም ወደ ደብረ በንኮል ገዳም ውስጥ ገብተው የታላቁ አባት የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደቀ መዝሙር ሆኑ::
ቀደም ሲል የጠቀስናቸው 7ቱ አበው በዚያ ነበሩና 7ቱም በአንድ ቀን ሲመነኩሱ ገዳሙ የተቃጠለ እስኪመስል ድረስ ብርሃን ወርዶ ነበር:: አቡነ ያሳይ በረድእነት በቆዩበት ዘመን ዛፎችን መትከል ይወዱ ነበር:: ከትሩፋት መልስም በልብሳቸው ውሃ እየቀዱ ያጠጡ ነበር:: በተለይ "ምዕራገ ጸሎት" የሚባለው ተአምረኛ ዛፍ ዛሬ ድረስ አለ ይባላል::
አቡነ ያሳይ ጊዜው በደረሰ ሰዓት ከአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ተባርከው: ከ2ቱ ባልንጀሮቻቸው (አቡነ ሳሙኤል ዘዋሊና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ) ጋር ወደ ጣና ሐይቅ መጡ:: በዚያም አካባቢ ተአምራትን እየሠሩ ሕዝቡንም እያስተማሩ ከቆዩ በኋላ ጌታ ወደየፈቀደላቸው ቦታ ተለያዩ::
አቡነ ሳሙኤል ወደ ዋልድባ: አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ወደ ገሊላ: ከዚያ ወደ ጉጉቤ ሲሔዱ አቡነ ያሳይ መንዳባ ውስጥ ገቡ:: ጻድቁ ወደ አርባ ምንጭ ሒደው ታቦተ መድኃኔ ዓለምን ይዘው ሲመጡ ጣናን የሚሻገሩበት አጡ:: ጌታን ቢማጸኑት:- "ምነው እሷን ድንጋይ ባርከህ አትቀመጥባትም?" አላቸው:: እሳቸውም በእምነት: ድንጋይ ላይ ተቀምጠው ጣናን ተሻገሩት:: ይህንን ከርቀት ያዩ የዘመኑ ሰዎች "ብዙ ተአምር አይተናል: ነገር ግን ማን እንደ አባ! ጣናን በድንጋይ የተሻገረ" ሲሉ አድንቀዋቸዋል::
ጻድቁ ጣናን ተሻግረው: ገዳም መሥርተው: ብዙ አርድእትን አፍርተው: በተጋድሎ ሕይወታቸው ቀጥለዋል:: በተለይ ዛሬ ድረስ የሚተረከው የ'አትማረኝ' ታሪክም የሚገኘው እዚሁ ገዳም ውስጥ ነው:: ታሪኩም በየዋህነት "አትማረኝ" ብለው ጸልየው ጣናን ያለ ታንኳ በእግራቸው የረገጡ አባትን የሚመለከት ሲሆን ከአቡነ ያሳይ ጋርም ወዳጅ ነበሩ::
አባታችን አቡነ ያሳይ ለዘመናት በቅድስና ኑረው: ቅዱሳንንም ወልደው መስከረም 14 ቀን ታመሙ:: "ጌታ ሆይ!" ብለው ቢጠሩት መድኃኔ ዓለም መጣላቸው:: ጣና በብርሃን ተከበበች:: ጌታም "ወዳጄ! ስለ ድካምህ: ደጅህን የረገጠውን: መታሰቢያህን ያደረገውን: በስምህ የተማጸነውን ሁሉ ከነትውልዱ እምርልሃለሁ" ብሏቸው ነፍሳቸውን አሳረገ:: አበውም ሥጋቸውን ገንዘው እዚያው መንዳባ መድኃኔ ዓለም ውስጥ ቀበሩት:: ዐጽማቸው ዛሬም ድረስ ይገኛል::
††† አምላከ ጻድቃን በምልጃቸው የበዛች ኃጢአታችንን ይቅር ይበለን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::
††† መስከረም 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ አጋቶን ዘዓምድ
2.አቡነ ያሳይ ዘመንዳባ
3.አባ ጴጥሮስ መምሕረ ጻና (ጣና)
4.ቅዱስ ዴግና ቀሲስ
††† ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)
2.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
3.ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው)
5.አባ ስምዖን ገዳማዊ
6.አባ ዮሐንስ ጻድቅ
7.እናታችን ቅድስት ነሣሒት
††† "ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል:: ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም::" †††
(ማቴ. ፲፥፵፩)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
#እንደ_ሞተ_ሰው_ሁን
ከወንድሞች አንዱ ወደ አባ መቃርዬስ መጥቶ " አባክህ ለህይወቴ የሚሆን መመርያ ስጠኝ" አለው ፡፡ አባ መቃርዬስም ያንን ወንድም ወደ መቃብር ሂድና በሙታን ላይ ክፋ ነገር አድርግባቸው፡፡ ብሎ ላከው ሰውየውም በሙታኑ ላይ ድንጋይ በመወርወርና በመሳደብ የተላከውን ፈፅሞ መጣ ፡፡ " አባ መቃርዮስም ምን አሉህ ? ሲል ጠየቀው " ያም ወንድም "ምንም አላሉኝም " ብሎ መለሰ ፡፡ በነጋታውም ተመልሰህ ናና አመስግናቸው አለው፡፡ በነጋታውም ያ ወንድም ወደ መቃብሩ ስፋራ ተጉዞ ሙታኑን " ሐዋርያ ፣ ቅዱሳን ፣ጻድቃን ፣ እያለ አመሠገናቸውና ተመለሰ ፡፡ መቃርዮስም " ምን መለሱልህ አለው" ምንም አለ ፡፡" መቃርዮስም " ስትሰድባቸው ፣በድንጋይ ስትመታቸው ፣ ስታመሰግናቸውም ፣ ስታወድሳቸው ፣ ምንም አልመለሱልህም ፡፡ አንተም ለነፋስህ ድህነት ከፈለግክ እንደ "ሞተ ሰው ሆነህ ኑር" ፡፡ ሰዎች ክፋ ቢያደርጉብህም ቢያመሰግኑህም ምንም አይሰማህ አለው ፡፡፡
ወዳጄ ሆይ የታላቁን አባት ምክር ልብ አልክን ? የሚሰድብህንና ድንጋይ የሚወረውርብህን እንዴት ማለፋ እንዳለብህ ተማርክ ? የሚያመሰግኑህንና የሚያወድሱህን እንዴት መቀበል እንዳለብህ አስተዋልክ ?
ቀልብህን የሚቀሙህ ብዙ ሰዳቢዎች አሉብህ፡፡ የሚያስጎነብሱህ ብዙ ድንጋይ ወርዋርዎች አሉብህ ፡፡ አንዱ ድህነትህን እያነሳ ያሸማቅቅሀል ፤ሀብት የሌለህና ገንዘብ መቁጠር ያልቻልከው የማትረባ ስለሆንክ ብቻ እንሆነ በማሰብ ያሳንስሀል።
በምግባርህ የሞትህ እንደሆንክ እየጮኸ ይነግርሀል ሃይማኖትህና ኢትዮጲያዊነትህ ለድህነት አስተዋፅኦ እንዳደረገና ማንነትህ ራሱ የተዋረደ እንደሆነ በመንገር ተፈጥሮህን " ንቀህ "አርቴፋሻል እንድትሆን ኦርጅናልነትህን አርክሰህ ፌክ እንድትሆን ይሰብክሃል፡፡ በዘር ገመድ ተብትበው ከወንድምህ ጋር የሚያናቁሩህ ሃይማኖትህንና ሰብአዊነትህ ሳይቀር በዘረኝነት ሰፌድ የሚያበጥሩ ድንጋይ ወርዋርዎችን እንዴት ይሆን ያለፋካቸው፡፡
ጾምህን የሚያንቋሽሹ ፣ ሱባኤህን የሚረብሹ ፣ ጸበል መጠጣትህን ፤እምነት መቀባትህን የሚያንሻፋፉ ፤እግዚአብሔር በሞተ ነገር ላይ ታሪክ እንደሚሰራ ስትነግራቸው የሚስቁ ፤ በሰማይ ህይወት አለ ስትላቸው በሙት አምራቸው የሚሳለቁ ፤ይልቅ ዓለምህን ቅጭ ጊዜህን ተጠቀምበት የሚሉ አለማውያንና ማንነትህን ለማርከስ ማንነታቸውን ለማንገስ የሚወረውሩት ጥቁር ድንጋይ አቁስሎህ ይሆን ?
ወዳጄ ሆይ ታላቁ አባት እንዲህ ይልሃል ለስጋውያን ለስሌታውያን እንደ ሞተ ሰው ሁን ! ደግሞስ ገና ልትሰራ የምትችለውን ገና በልዑልነትህ ንጉስ ብለውህ ገና በወጣትነትህ ጻዲቅ አድርገውህ ገና በተማሪነትህ ረብኒ ብለውህ ዳዴህን ሳትጨርስ የአትሌትነት ማዕረግን ሰጥተውህ በዲያብሎስ መዝሙር ከፋ ከፋ በጣሙን ከፋ ከፋ ሗላ ስትወድቅ አጥንትህ እንዳይተርፋ ሰቅለው በአፋጢምህ የሚደፋህን አድር ባዮችና ህሊና ቢሶች እንዴት አልፈሀቸው ይሆን ? ለእነርሱም ወሬ መንኩሰህ እንደ ሞተ ሰው ሆንክን ??
- እንደ ሞተ ሰው ሆነህ የምታድነው ትዳር አለህ ፡፡
- እንደ ሞተ ሰው ሆነህ የምታድነው ህይወት አለህ።
- እንደ ሞተ ሰው ሆነህ የምታጠነክረው ወዳጅነት አለህ።
- እንደ ሞተ ሰው ሆነህ የምትሰራው እልፋ ስራ አለህ ፡፡
ደግሜ ደግሜ እልሃለሁ የታላቁን አባት ቃል ተውሼ ለእነዚህ እንደሞተ ሰው ሁን! እንደ ሞተ ሰው ሁን እንጂ ሙት ሁን አልተባልክም ፤ እንደ ሞተ ሰው ሆነህ በግብርህ ሕያው ሁን እንጂ ሙት አትሁን፡፡
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma
✍️Comment @Chan
"አባቱ አየውና አዘነለት፤"
(ሉቃ. 15፥20)
***
ይህ ልጅ አባቱ በቁሙ ሳይሞት ገና ንብረት ያወርሰው ዘንድ ጠይቆ የድርሻውን ወስዶ ያባከነ ከንቱ ልጅ ነበር። አባት ሳይሞት ከንብረትህ የድርሻዬን አካፍለኝ ማለት አባት እስኪሞት እንደመቸኮል ያለ ጽኑ በደል ነው፤ የአባቱን ውርስ ወስዶ ማባከን ደግሞ ሌላ በደል!
ግን አንድ ነገር ሕይወቱን መለሰችለት፦ የአባቱን መልካምነት አልዘነጋም፤ በአባቱ መታመኑን አልተወም። ወደ ልቡ ተመልሶ ያደረገው ነገር ጽኑ በደል መሆኑን አምኖ ተጸጸተ፤ ልጅ ሊባል እንደማይገባውም ተናዘዘ። ልጅ ሊባል እንደማይገባው ቢያምንም የአባቱን ቸርነት አልረሳም። ምሕረትን የምትሻ፣ ከሞት ጋር የተካከለች የጎሰቆለች ሕይወቱን ይዞ ወደ አባቱ ቤት ተመለሰ።
አባቱ ከቤቱ በር ሆኖ የልጁን መምጣት እየተጠባበቀ ሩቅ ይመለከታል። የተጎሳቆለ ልጁን ከሩቅ ሲያየው አዘነለት። ልብ ይነካል!
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአባቱን ቸርነት በዚህ መንገድ ገለጠልን። ከእርሱ ጋር አንድ ፈቃድ ያለውን የአባቱን ልብ ገልጦ አሳየን። ሐዋርያው ጳውሎስ “ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን፤” በማለት ከዘላለም በአብ ልብ ውስጥ ለእኛ ታስባ የነበረች ቸርነቱን ነገረን። (ኤፌ. 1፥4) ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዲ "አባታዊት ርኅራኄ የምትገለጥበት ጊዜ ሲደርስ" ሰው ሆኖ አዳነን ብሎ የገለጣት ይህችን ቸርነት ነው።
ጌታችን ስለ አባቱ ሲነግረን በጽኑ በደል የተለየውን ክፉ ልጁን ከሩቅ አይቶ በሚያዝን እና በመመለሱ ደስታን በሚያደርግ ቸር አባት ምሳሌ ነው። በደለኛ ስለሆነ ዓይኔን እንዳያይ በሚል መራር አባት ምሳሌ አይደለም። ይህን የእግዚአብሔር ቸርነት እና ፍቅር በምልዓት ሊረዳው የሚችል ፍጡር የለም፤ ከእውቀት በላይ ነው።
ኃጢአታችን እጅግ የበዛ የምድር ጎስቋሎች ብንሆን ይህች አባታዊት ቸርነት ትጠብቀናለች፤ ከሩቅ ትመለከተናለች። በአባታቸው ቸርነት አምነው በእውነተኛ ንስሐ የሚመለሱትን ልታቅፍ ዘወትር የተዘጋጀች ናት። ቀድሞ በልጁ ሞት የተደረገች መዳናችን በዚህች ቸርነት ላይ የተመሠረተች ነች። የምንታደስባት ንስሐችንም በዚህች ቸርነት ላይ የተመሠረተች ናት።
መንፈስ ቅዱስ በልባችን የሚያፈሰው አባ አባት ብለን እንድንጮህ የሚያነሣሣ የልጅነት መንፈስ ይህን የእግዚአብሔር አባትነት ከልብ ማመን ነው፤ በዚህች ቸርነት ላይ መደገፍ ነው። (ገላ. 4፥6)
***
ሰማያዊ አባታችን ሆይ፥ ስምህ ይመስገን!
Bereket Azmeraw
በኢትዮጵያ ብር የምሰራ ከ300ብር ተነስታቹ መስራት የምትችሉ ስራ ነው ይበልጥ እንድትረዱ በውስጥ አናግሩኝ
👇👇👇👇
@Diriba12
ከVGM 10 እጥፍ የምበልጥ ስራ አገኘው👍
👇👇👇👇👇👇
1, VGM ላይ 30$ Invest ካረጋቹ በየቀኑ 0.6$ ነው የሚታገኙት
2 አዲሱ ስራላይ ግን 49$ ብቻ invest አድርጋቹ በየቀኑ 5$ እያገኘው ነው👍
ለመስራት ፍላጎት ካላቹ ቶሎ ጀምሩ
ሊንኩን ከፈለጋቹ አናግሩኝ👇👇
@Steven2716
በሞጆ ዋርካ ደብረ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በአመት ስንት ጊዜ ጉባኤ እንደሚዘጋጅ በዝርዝር ተቀምጦሎታል።ውድ የኦርቶዶስ ተዋህዶ ልጆች ይህን መንፈሳዊ ጉባኤ ሼር :ላይክ ማድረግ አሉባልተኝነት አይደለምና ሼር አድርጉ ለሁሉም አስተዋውቁ።ከመስከረም 17-19 /2017 ዓ/ም ድረስ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ልዩ መንፈሳዊ ጉባኤ በዚሁ ደብር ስለተዘጋጀ እንዳይቀሩ ።የቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች ሼር አድርጉ
መምህር ይላቅ ፈለቅ
ቀን 14/01/2017 ዓ/ም
Hello Besufkad, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
የምሥራች :- የሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተክህነት የሰባክያን ጥምረት ከዛሬ መስከረም 14 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የቴሌግራም ፣ የፌስ ቡክ እና የቲክቶክ ፔጅ የተከፈተ ስለሆነ ሁላችሁም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ልጆች የሆናችሁ ከፔጆቹ የሚተላለፉ መንፈሳዊ መልዕክቶችንና ስብከቶችን ለመከታተል የምትችሉ መሆኑን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው። ቻናሎቹን ለመከታተል ላይክ፣ ሼር ፣ ፎሎው እና ሰብስክራይብ በማድረግ ይቀላቀሉን። በፍቅሩ ያስጀመረን አምላካችን ፍፃሜያችንንም ያሳምርልን።
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete Username(ID) ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
✝✝✝✝✝✝✝✝✝
በወንጌሉ ያመናቹ እንኳን
ለብርሃነ መስቀሉ
አደረሳችሁ።
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ÷ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።"
1ቆሮ• 1 ÷ 18
#መልካም እለተ ይሁንልን
ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
✝✝✝✝✝✝✝✝✝
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ÷ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።"
1ቆሮ• 1 ÷ 18
#መልካም እለተ ይሁንልን
ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼.
" ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:13፤)
"+ የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ! በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተስሎ ነበር:: ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው? +
+ (ገላ. 3:1)
#መልካም ቀን
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
ኦ አባይ ሀገር በሀኪ ኢትዮጵያ
ሀገረ ነጎድጓድ ሀገረ እግዚአብሔር
ተንስኢ ወልበሲ ሀይለ እግዚአብሔር እስመ ተንስኡ ፀላእትኪ ወአብቀዋ ኦሙ ላይለ ህዝብኪ
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
#መልካም እለተ ይሁንልን
ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼.
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖ መስከረም ፲፮ (16) ❖
✞✞✞ እንኩዋን ለቅድስት ሃገር #ኢየሩሳሌም: ለቅዱስ #ጦቢት እና ለአባ #አጋቶን_ባሕታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+"+ #ሕንጸታ_ለኢየሩሳሌም +"+
=>ኢየሩሳሌም በብሉይም: በሐዲስም ቅድስት ሃገረ
እግዚአብሔር ናት:: '#ኢየሩ' ማለት 'ሃገር' ማለት ሲሆን
'#ሳሌም' ደግሞ 'ሰላም' ማለት ነው:: ስለዚህ በቁሙ
'ሃገረ ሰላም': '#ሃገረ_ክርስቶስ' ማለት ነው::
+ኢየሩሳሌም የሚለው ቃል በቁሙ ቅድስት ሃገርን
ሲመለከት በምሥጢሩ ግን የቤተ ክርስቲያን: የመንግስተ
ሰማያት እና የአማናዊት ሃገረ ሰላም #ድንግል_ማርያም
መጠሪያ ነው:: ኢየሩሳሌምን በከተማ ደረጃ የመሠረታት
ታላቁ ካህን #መልከ_ጼዴቅ ሲሆን 'ንጉሠ ሳሌም'
ተብሎም ኑሮባታል::
+ይህች ቅድስት ሃገር በብሉይ ዘመን እግዚአብሔር
በረድኤት ቢገለጥባት: ጻድቃነ ብሊት ቢኖሩባት
ተቀድሳለች:: በሐዲስ ኪዳን ግን አምላካችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ከሰማያት ወርዶ 33 ዓመት ከ3 ወር ያህል
የድኅነ ትሥራውን ቢፈጽምባት: ለድንግል ማርያምና
ለብዙ ቅዱሳን ቤት ብትሆን የበለጠ ተቀድሳለች::
+ዛሬም ድረስ ከተለያዩ ክፍላተ ዓለማት በብዙ ድካምና
ወጪ ሊያዩዎት ይጉዋዛሉ:: የቀደመው ዘመን
አባቶቻችንም ይህችን ቅድስት ከተማ ለመሳለም እስከ
ደም ጠብታ ከፍለዋል::
+ወደ ዋናው ጉዳያችን እንለፍና የኢየሩሳሌምን መታነጽ
እንይ:: ኢየሩሳሌም በአሕዛብ እጅ ብዙ ጊዜ ፈርሳ
ታንጻለች:: እኛ ግን ዛሬ የምናከብረው የከተማዋን
መታነጽ ሳይሆን በከተማዋ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ
መንገድ በአንድ ጊዜ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት
መታነጻቸውን ነው:: ይሕስ እንደምን ነው ቢሉ:-
+ከክርስቶስ ዕርገት 300 ዓመታት በሁዋላ ለቤተ
ክርስቲያን የተነሳችው #ቅድስት_ዕሌኒ በጐ ሃሳብ
በሕሊናዋ ተመላልሷልና ተነሳች::
#ጉባኤ_ኒቅያ ከተጠናቀቀ በሁዋላ ልጇ ቆስጠንጢኖስ
በነገሠ በ20 ዓመቱ በ227 ዓ/ም አካባቢ ቅዱስ ዕጸ
መስቀሉን ትፈልግ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ጉዞ አደረገች::
+መስቀሉን ፈልጋ ያገኘችበት ታሪክ ለነገ ይቆየንና
መስቀሉን ካገኘችው በሁዋላ በሙሉ ከተማዋ ላይ
አብያተ ክርስቲያናትን ለማነጽ ከልጇ ጋር ተስማማች::
+ለሕንጻው የሚሆን ብዙ ወርቅ: ብርና እንቁ ጭና
ማምጣቷን የተመለከቱት #አባ_መቃርስ (የኢየሩሳሌም
ሊቀ ዻዻስ ናቸው) "ልምከርሽ! ቤተ ክርስቲያኑን
በጠንካራ አለት ላይ ሥሪ:: ወርቅና ብሩን ግን ለነዳያን
በትኚ" ስላሏት በአካባቢው ላሉ ነዳያን ታላቅ ፌሽታ
ሆነ:: እጅግ ብዙ ሠራዊት: ብዙ ሺህ ሠራተኞች
ታጥቀው 80 አብያተ ክርስቲያናትን ያንጹ ጀመሩ::
+ሥራው ረቂቅና ብዙ ሥለ ነበረ እጅግ አድካሚ ነበር::
ቅድስት ዕሌኒ ሃገሪቷን በቤተ መቅደሶች መሸፈን ስለ
ፈለገች እንዲታነጽ ያዘዘችው የቤተ ክርስቲያን ቁጥር 80
ደረሰ:: እነዚህም ጌታ ከጽንሰቱ እስከ ዕርገቱ
የረገጣቸውና #እመ_ብርሃን የረገጠቻቸው ቦታዎች
ናቸው::
+#ቤተ_ልሔም: #ዮርዳኖስ: #ደብረ_ሊባኖስ:
#ደብረ_ታቦር: #ደብረ_ዘይት: #ጐልጐታ: #ጌቴ_ሴማኒ:
#ቤተ_ሳይዳ: #ጽርሃ_ጽዮን ደግሞ ዋና ዋናዎቹ ናቸው::
በአካባቢው ያሉ ነዳያን ሳይርባቸው: ሠራተኞችም ደሞዝ
ሳይቸግራቸው: 80ው አብያተ ክርስቲያናት በፈጣሪ
ረዳትነት: በ10 ዓመታት ታነጹ::
+ቀጥሎም ንጉሡ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ በዓለም ያሉ
ታላላቅ ቅዱሳን ሊቃነ ዻዻሳትን ጠርቶ: ሁሉም እስከ
መስከረም 15 ቀን ወደ ኢየሩሳሌም በተሰበሰቡበት
የሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ቅዳሴ ቤት በአንድ ላይ
ሲከበር ከዝማሬው ብዛት: ከአምላክ ጸጋ የተነሳ
በከተማዋ ታይቶ የማይታወቅ ሐሴት ተደረገ::
*ኢየሩሳሌም ፍጹም አጊጣ እስከ መከራ ቀን (አሕዛብ እስከ ተነሱበት) ቆይታለች::
+"+ #ቅዱስ_ጦቢት (ጻድቅ ነቢይ) "+
=>ከክርስቶስ ልደት በፊት እሥራኤላውያን ክፋትን
ሲያበዙ ጠላት መጥቶ ይማርካቸው: ንስሃ ሲገቡ ደግሞ
በድንቅ ተአምር ይወጡ ነበር:: ሕዝቡ ሲማረክ ነቢያት
እረኞች ናቸውና ያለ ጥፋታቸው አብረው ይማረኩ ነበር::
በዚያም ሕዝቡን ያስተምራሉ: ያጽናናሉ::
+በተመሳሳይ እሥራኤላውያን ተማርከው ወደ #ነነዌ
በወረዱበት ወራት ጦቢት የሚሉት ደግ ሰው
በመካከላቸው ነበር:: ይህ ደግ ሰው ከምርኮ በፊት
መልካም አምልኮት የነበረው: አሥራቱን በኩራቱን
የሚያወጣ: ለነዳያን የሚራራ ነበር::
+ከተማረኩ በሁዋላም ሕዝቡ ከአሕዛብ ጋራ ሲቀላቀሉ
እርሱ ንጽሕናውን ጠብቆ እግዚአብሔርን ያመልክ ነበር::
ቅዱስ ጦቢት በተለይ የሞተ ሰው ሲያገኝ ሳይቀብር
እህል አይቀምስም ነበር:: በዚህም ምክንያት የዘወትር
ጦመኛ ነበር::
+ይሕ ቅዱስ እድሜው 58 በሆነ ጊዜ ዓይኑ ጠፋ:: ብዙ
በመሰቃየቱም ሞቱን ለመነ:: በሌላ አቅጣጫ ደግሞ
#ሣራ 'አስማንድዮስ' የሚባል ጋኔን 7 ባሎቿን እየገደለ
አሳቅቁዋት ነበርና እርሷም ሞቷን ተመኘች::
+እግዚአብሔር ግን መልአኩን ልኮ: #ቅዱስ_ሩፋኤል
አዛርያን መስሎ የጦብያና የሣራን ጋብቻ ባርኩዋል::
ጋኔኑንም በጥልቁ አስጥሞታል:: በዓሣ ሐሞትም
የጦቢት ዓይኑ በርቶለት በእድሜው ላይ 100 ዓመታት
ተጨምረውለታል:: ቅዱስ ጦቢት ብዙ ሕብረ ትንቢቶችን
ተናግሮ በ158 ዓመቱ በዚህች ቀን ዐርፏል::
+"+ #አባ_አጋቶን_ባሕታዊ +"+
=>ይህንን ቅዱስ የማያውቅ የቤተ ክርስቲያን ሰው
ይኖራል ብየ አልገምትም:: እርሱ ታላቅ ጻድቅ: ገዳማዊና
የእግዚአብሔር ሰው ሲሆን አንደበቱን ከክፋት ይከለክል
ዘንድ ለ30 ዓመታት ድንጋይ ጐርሶ ኖሯል::
+ይህንን ቅዱስ #ሊቃውንት ሲገልጹት "ክምረ ክምር
ጽድቁ እስከ አስተርአየ" ይሉታል:: ትእግስቱ: ደግነቱ:
አርምሞው: ትሩፋቱ ከመነገር በላይ ነው:: በነበረበት
በ4ኛው መቶ ክ/ዘመንም እንደ ኮከብ ያበራ ታላቅ አባት
ነው::
=>አምላከ ቅዱሳን የኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያንን
ሰላምና ደስታ ያሳየን:: ከበዓላቱ ከሚገኘውም ጸጋ
በረከት አይለየን::
=>መስከረም 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት=
1.ሕንጸታ ለኢየሩሳሌም
2.ቅድስት እሌኒ ንግሥት
3.ቅዱስ ጦቢት ነቢይ
4.ቅዱሳን ጦብያና ሣራ
5.አባ አጋቶን ባሕታዊ
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም)
2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት)
3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ (የቅ/
ላሊበላ ወንድም)
4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ
6.አባ ዳንኤል ጻድቅ
7.ቅዱስ አባ ዮሐንስ ጻድቅ (ወንጌሉ ዘወርቅ)
=>+"+ ወደ #እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ:: #ኢየሩሳሌም ሆይ እግሮቻችን በአደባባይሽ ቆሙ:: ኢየሩሳሌምስ እርስ በርሷ እንደ ተገለጠች ከተማ ተሠርታለች . . . ስለ ወንድሞቼ ስለ ባልንጀሮቼም በውስጥሽ ሰላም ይሁን አልሁ:: ስለ አምላካችን ስለ እግዚአብሔር ቤት ላንቺ መልካምነትሽን ፈለግሁ:: +"+ (መዝ. 121:1-9)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
ሰው ሁሉ ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን !
(ያዕቆብ 1፥19)
< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >
#መልካም ቀን
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete Username(ID) ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete Username(ID) ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
1⃣7⃣ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል
የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!
በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ