:
Eneko yo yo gifata, chembela , ashenda mnamn zm blachu irrecha lay mtchohut .......😁😁😁
Ante lemsale be kiduas tamnalek bilkk tkkil aydel like u gave them wt they deserve , but Protestant says that we believe in them as a God....it's big fallacy
Ahunm eyanesachu yalachut yhen fallacy nw 1 sew irrecha sihed wstu mn eyasebe endemihed esu bcha nw yemiyakew .....zm bleh generalize atarg ...
Atnchachu ke kenachu makber nw be fkr enkebelalen ..... be chfn tilacha mtaweru yalachubetn group eweku
We all produ to be Orthodox❤️
ጣኦትን መሸሽ አስፈላግ ነው ፖለትካው የፈበረከውን የጥንት አባቶች ጣኦት ወደኋላ መመልከት እንዴሎጥ ምስት የጨው ሃውልት መሆን ነውና ፖለትከኞቹም ሆኔ ለሁለት ጌታ የምገዙ የቤ/ክርስትያን አባቶች ቆም ብሎ ብያስቡ ጥሩ ነው ባይ ነኝ።
Читать полностью…✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_24_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ቆሮንቶስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም።
¹³ መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን መንፈስ በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን እንጂ የሰው ጥበብ በሚያስተምረን ቃል አይደለም።
¹⁴ ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም።
¹⁵ መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል ራሱ ግን በማንም አይመረመርም።
¹⁶ እንዲያስተምረው የጌታን ልብ ማን አውቆት ነው? እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ዮሐንስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ።
²¹ እውነትን የምታውቁ ስለ ሆናችሁ፥ ውሸትም ሁሉ ከእውነት እንዳልሆነ ስለምታውቁ እንጂ እውነትን ስለማታውቁ አልጽፍላችሁም።
²² ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ውሸተኛው ማን ነው? አብንና ወልድን የሚክድ ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።
²³ ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ እንኳ የለውም፤ በወልድ የሚታመን አብ ደግሞ አለው።
²⁴ እናንተስ ከመጀመሪያ የሰማችሁት በእናንተ ጸንቶ ይኑር። ከመጀመሪያ የሰማችሁት በእናንተ ቢኖር፥ እናንተ ደግሞ በወልድና በአብ ትኖራላችሁ።
²⁵ እርሱም የሰጠን ተስፋ ይህ የዘላለም ሕይወት ነው።
²⁶ ስለሚያስቱአችሁ ሰዎች ይህን ጽፌላችኋለሁ።
²⁷ እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ።
²⁸ አሁንም፥ ልጆች ሆይ፥ በሚገለጥበት ጊዜ እምነት እንዲሆንልን በመምጣቱም በእርሱ ፊት እንዳናፍር በእርሱ ኑሩ።
²⁹ ጻድቅ እንደ ሆነ ካወቃችሁ ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ከእርሱ እንደ ተወለደ እወቁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁹ እኛም በአይሁድ አገርና በኢየሩሳሌም ባደረገው ነገር ሁሉ ምስክሮች ነን፤ እርሱንም በእንጨት ላይ ሰቅለው ገደሉት።
⁴⁰ እርሱን እግዚአብሔር በሦስተኛው ቀን አስነሣው ይገለጥም ዘንድ ሰጠው፤
⁴¹ ይኸውም ለሕዝብ ሁሉ አይደለም ነገር ግን በእግዚአብሔር አስቀድሞ የተመረጡ ምስክሮች ለሆንን ለእኛ ነው እንጂ፤ ከሙታንም ከተነሣ በኋላ ከእርሱ ጋር የበላን የጠጣንም እኛ ነን።
⁴² ለሕዝብም እንድንሰብክና በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ በእግዚአብሔር የተወሰነ እርሱ እንደ ሆነ እንመሰክር ዘንድ አዘዘን።
⁴³ በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት እንዲቀበል ነቢያት ሁሉ ይመሰክሩለታል።
⁴⁴ ጴጥሮስ ይህን ነገር ገና ሲናገር ቃሉን በሰሙት ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደ።
⁴⁵ ከጴጥሮስም ጋር የመጡት ሁሉ ከተገረዙት ወገን የሆኑ ምዕመናን በአሕዛብ ላይ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ስለ ፈሰሰ ተገረሙ፤
⁴⁶ በልሳኖች ሲናገሩ እግዚአብሔርንም ሲያከብሩ ሰምተዋቸዋልና።
⁴⁷ በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ፦ እነዚህ እንደ እኛ ደግሞ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ እንዳይጠመቁ ውኃን ይከለክላቸው ዘንድ የሚችል ማን ነው? አለ።
⁴⁸ በኢየሱስ ክርስቶስ ስምም ይጠመቁ ዘንድ አዘዛቸው። ከዚህ በኋላ ጥቂት ቀን እንዲቀመጥ ለመኑት።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_24_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አፅናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ። ወውስተ ፀሓይ ሤመ ጽላሎቶ"። መዝ.18፥4-5።
"ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፥ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ። በእነርሱም ውስጥ የፀሐይን ድንኳን አደረገ፥ እርሱም እንደ ሙሽራ ከእልፍኙ ይወጣል፤ እንደ አርበኛ በመንገዱ ለመሮጥ ደስ ይለዋል"። መዝ.18፥4-5።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_24_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሉቃስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ከዚህም በኋላ ጌታ ሌሎቹን ሰብዓ ሾመ፥ ሁለት ሁለትም አድርጎ እርሱ ሊሄድበት ወዳለው ከተማና ስፍራ ሁሉ በፊቱ ላካቸው።
² አላቸውም፦ መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ለመከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት።
³ ሂዱ፤ እነሆ፥ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ።
⁴ ኮረጆም ከረጢትም ጫማም አትያዙ፤ በመንገድም ለማንም እጅ አትንሡ።
⁵ ወደምትገቡበት ቤት ሁሉ አስቀድማችሁ፦ ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን በሉ።
⁶ በዚያም የሰላም ልጅ ቢኖር፥ ሰላማችሁ ያድርበታል፤ አለዚያም ይመለስላችኋል።
⁷ በዚያም ቤት ከእነርሱ ዘንድ ካለው እየበላችሁና እየጠጣችሁ ተቀመጡ፤ ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋልና። ከቤት ወደ ቤት አትተላለፉ።
⁸ ወደምትገቡባትም ከተማ ሁሉ ቢቀበሉአችሁ፥ ያቀረቡላችሁን ብሉ፤
⁹ በእርስዋም ያሉትን ድውዮችን ፈውሱና፦ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ቀረበች በሉአቸው። (ከኦሪትና ከነብያት አንዲቱ ቃል ከምትወድቅ የሰማይና የምድር ማለፍ ይቀላል)
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጎድጓድ_ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው ቅዱስ አድሊጦስ እና የአቡነ ጎርጎርዮስ የዕረፍታቸው በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
ቅዱስ ፓትርያርኩ ለአጣሪ ኮሚቴው የሥራ መመሪያ ሰጡ።
*****
"ምዕመናን ገንዘባቸውን የሚሰጡት ለሃይማኖት ማስፋፊያ እንጂ ለዘረፋ አይደለም።"
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ
መስከረም ፳፫ ቀን፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም.
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
=============
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚስተዋለውን የሙስናና ብልሹ
አሰራር በዝርዝር በማጥናት የመፍትሔ ሐሳብ እንዲያቀርብ በጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት የተቋቋመው አጥኚ ኮሚቴ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖትና ከብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጋር ከተቋቋመ ጀምሮ እስካሁን የሠራቸውን ሥራዎች ሪፓርት በማቅረብ በቀጣይ በሚያከናውናቸው ተግባራት ዙሪያ በመወያየት የሥራ መመሪያ ተቀብሏል።
ኮሚቴው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚስተዋለው የመልካም አስተዳደር ችግር ከውስጥ አልፎ በአደባባይ መነጋገርያ በመሆኑ በጥናት ላይ በተመሠረተ አግባብ ተቋማዊ ለውጥ ማምጣት የሚያስችልና የቤተ ክርስቲያናችንን ክብር በሚመጥን መልኩ እንዲደራጅ የሚያደርግ የመፍትሔ ሐሳብ ለማቅረብ የሚያስችለውን ዕቅድ በማውጣት ወደ ተግባር መግባቱን የኮሚቴው ሰብሳቢ መ/ሰ ቆሞስ አባ ቃለጽድቅ ሙሉጌታ (ዶር)
እና ዲ/ን ስንታየሁ ምስጋናው ባቀረቡት ሪፖርት ገልጸዋል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርኩ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሰጡት አባታዊ የሥራ መመሪያ "ምዕመናን ገንዘባቸውን የሚሰጡት ለሃይማኖት ማስፋፊያ እንጂ ለዘረፋ አይደለም። ያሉ ሲሆን ስለሆነም ሕግና ሥርዓትን አክብራችሁ፣ በእውነተኝነት ለቤተክርስቲያን፣ለእግዚአብሔርና ለራሳችሁ ብላችሁ ሳታፍሩና ሳትፈሩ ሥራችሁን ሥሩ። ሥራው ታማኝነት"ጥብዓት" ያስፈልጋል ብለዋል።
ከብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ጋር ሆናችሁ በጋራ ሥሩ ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ ጠንከር ያለ መድኅኒት ሊሆን የሚችል ጥናት ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር እንደምታቀርቡ እምነቴ የጸና ነው ያሉ ሲሆን አያይዘውም የተላካችሁበት ሥራ ያለ ውጤት የሚቀር መሆን የለበትም። ቤተክርስቲያን የተዋረደችበት ጊዜ ማብቃት አለበት ያሉት ቅዱስነታቸው ቤተክርስቲያናችን ራሷን አንጽታ ለሌሎች መልካም አብነት መሆን አለባት ካሉ በኋላ ዓለማዊያን የሚሰሩት ሥህተት እንዳይኖር በተግባር የምታስተምር ተቋም እንጂ በሙስና የምትታማ መሆን የለበትም ብለዋል።
ልጆቼ እውነቱን ለማውጣት ታጥቃችሁ ሥሩ በሙስና ህመም ለምትሰቃየው ቤተክርስቲያን መድኃኒት ፈልጉላት በማለት አባታዊ መልዕክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው አንመረመርም ማለት ራሱን ችሎ ወንጀል ነው ካሉ በኋላ ይህ ሥራ ለእናንተም ታሪክ ነው። እውነትን መሰረት አድርጋችሁ በመሥራት ታሪክ አስመዝግቡ ብለዋል።
በመልዕክታቸው ማጠቃለያ ላይም ወደ እዚህ ተቋም የሚገቡ ሁሉ ይህን ያህል ጊዜ ቆይተን ይህን ያህል ይዘን እንውጣ የሚሉ እንጂ ለቤተክርስቲያን የሚቆረቆሩና የሚያስቡ እንዳልሆኑ ይታወቃል ካሉ በኋላ የተሰጣችሁን ኋላፊነት በትጋት ፈጽሙ ብለዋል።
በመጨረሻም ሥራችሁ ሁሉ የተሳካና ውጤታማ እንዲሆን እንጸልያለን እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን በማለት አባታዊ መልዕክታቸውን አጠናቀዋል።
ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete site link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
#23 💚💛❤️
ሰማዕተ ኢየሱስ የእውነት ምስክር
ህያው ነው በሰማይ ብፁዕ ነው በምድር ።
የኢትዮጵያ ገበዝ
የአራዳው ንጉስ
የልዳው ኮከብ
ሊቀ ሰማዕት
ፍጡነ ረድኤት
ፈረሰኛው ቅዱስ ጊዮርጊስ አባቶቻችንን የረዳ ዛሬም ከኛ ጋር ነው ።
ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
አሁንም እንዲሁ ልብህን አትታመን፤
/ምሳ 28 ፤ 26/
"በገዛ ልቡ የሚታመን ሰው ሰነፍ ነው፤ በጥበብ የሚሄድ ግን ይድናል።"
/ኤር 17 ፤ 9/
"የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው፤ ማንስ ያውቀዋል?"
ቤተ ክርስቲያኒቱ ሐኪም ቤት ናት ፤ እንዳንተ ሕመም ያለው በጣም ብዙ ሰው የሚሄድባት ቤት ናት። አይደለም በመንፈሳዊው በዓለማዊው እንኳን የመጀመሪያዎቹ ሐኪም ቤቶች የተመሠረቱት በእነቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ነው። ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለውን ማኅበር ዐይተህ ፤ የቤተ ክርስቲያኒቱን ኅብረት ዐይተኸው ታውቃለህ? እስኪ ሂድ የቤተ ክርስቲያኒቱን ማኅበር ጎብኘው ፤ ሕመምና መጥፎ ነገሮች አሉ። ነገር ግን ዐይተኸው የማታውቀው ፍቅር አለ ፤ እኔ አሁን ለአንተ ጉዳይ መጨነቅ የለብኝም። አሁን በዚህ ሰዓት እንቅልፌን ባጣጥም ደስ ይለኝ ነበር ፤ ለጌታዬ ግን አንተ የሚወድህ ልጁ ነህ። ስለዚህ ጌታዬን የምወደው ከኾነ አንተንም እወድሃለሁኝ ፤ የአንተ ጉዳይ የእኔ ጉዳይ ነው። እንዲህ ዐይነት ሰማያዊ አምላክ ሰማያዊ አባት ነው ያለን። በክርስቶስ ወንድሜ ነህ ፤ የምወድህ ሰው ነህ። ያንን እስኪ በቤተ ክርስቲያኒቱ የማኅበርና የኅብረት ሕይወት ውስጥ ገብተህ ዕየው።
ከዚያ በላይ ደግሞ እንዲህ የሚል አፍቃሪ አለህ፤
"ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።" /ማቴ 11 ፤ 30/
ቀንበር በአንድ ብቻ በሬ አይነዳም ፤ በሁለት እንጂ። እርሱም እያለን ያለው እንደዚያ ነው ፤ እኛ በአንዱ በኩል ስንይዘው ፤ በሌላ በኩል ደግሞ እኒ እሸከመዋለሁኝ። አይዟችሁ ፤ እኔን አምናችሁ አይከብዳችሁም እያለ ነው። ማን ነው እንዲህ እያለ የሚያጽናናህ? ደግሞስ "ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።" /ዮሐ 14 ፤ 16/ እንዲህ ያለ አባት ነው ያለን።
አሁን ጥያቄው ያለው አንተ ልብ ውስጥ ነው ፤ 'እውነት ከልብህ ይህንን ቃል ማመን ትፈልጋለህ? ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ እንደተመላለሰ፣ ተሰቅሎ እንደሞተ፣ ተቀብሮ ከሙታን እንደተነሣም ከልብህ ገብቶ ታምናለህ? ክርስቶስ ከሙታን በመነሣት እውነተኛ አምላክ እንደኾነ በማሳየቱ ለእኔ ድኅነትና ለእኔ ኑሮ የሚታመን እንደኾነ ርግጠኛ መኾን እችላለሁኝ በብለህ ታምናለህ?' እኒህን አጥና፣ መርምርና ዕወቃቸው ፤ ከልብህም በእውነት እመናቸው።
እስከአሁን ድረስ ያልተወህ አምላክህ ያን ጊዜ የበለጠ የተገለጠ ይመጣል። አሁን ራሱ እኔ ድንገት ባላሰብኩበት ሰዓት እዚህ እንድገባ አድርጎ ፤ አንተ ደግሞ ልብህ እንዲያስብበት አድርጎ ከሁሉ ቦታ መርጦ እንድንገናኝ ያደረገን መንፈስ ቅዱስ ነው። አሁንም ወንድሞችህና እኅቶችህ እዚህ አለን ፤ እኛም ሕመምተኞች ስለኾንን ነው ቤተ ክርስቲያን እየሄድን ከወንድሞችና ከእኅቶች ጋር የኅብረት ኑሮን የምንኖረው። ጌታችንም ይህንን ዐውቆ ነው በምድር ላይ ቤተ ክርስቲያን የሰጠን ፤ የኅብረት እንጂ የግል ኑሮ ለባሕርያችን የተስማማ አይደለም። ያጠፋናል እንጂ አይገነባንም።
ለዚያም ነው አሁን ወደ ካህን ሂድ የምልህ ፤ እስኪ እስከአሁን ድረስ በራስህ መንገድ ሞከርከው። መልካም እንዳልኾነም ዐየህ ፤ አሁን ደግሞ እንደጌታችን መንገድ ሞክረው። እስኪ እስከአሁን እንዳልነበረ ቆጠርከው አሁን ጌታችን ማን እንደኾነ ከወንጌላቱ ዕወቀው ፤ እስከአሁን እንደራስህ ኖርክ አሁን ደግሞ እንደጌታችን ሞክረው። እስኪ እስከአሁን ብቻህን ኖርክ ፤ አሁን ደግሞ በቤተ ከርስቲያኒቱ እቅፍ ውስጥ ገብተህ ከቤተ ክርስቲያን ሰዎች ጋር ኑር።
ዳዊት ዝሙት አለፈጸመም? ኀጢአተኛ አልነበረም? እንደዚያ ብለህ ከቅድስናው ታወርደዋልህ?
መጽሐፍ ቅዱስ የተሞላው ኀጢአተኛ በኾኑ ሰዎች አይደሉም? ጌታችን እንኳን በሕይወት እያለ ኀጢአተኛ ሰዎች አልነበሩም? ታዲያ ኀጢአተኛ ናቸው ብሎ "ለካህናት አትናገሩ" ብሎ ትቷል? ይልቁንም በወዳጁ በያዕቆብ በኩል "እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ።" /ያዕ 5 ፤ 16/ አይደል ብሎ የተናገረን?
እነርሱ ኀጢአት ስላለባቸው የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት አይፈጽሙም ማለት አይደለም። ሐዋርያት፣ ነቢያት በሙሉ በደል የነበረባቸው አይደሉም? ታዲያ ወደእነርሱ አልሄድም ልትል ነው? ጌታችን የበደለውን ጴጥሮስን አይደል ለዓለም ብርሃን አድርጎ የቤተ ክርስቲያኒቱ መሠረት አድርጎ የላከው?
እሬቻ_ላይ_የሚከብረው_እግዚአብሔር_አይደለም_ዲያብሎስ_ነዉ።
🔵 እሬቻ ከክርስትና እምነት ጋር ፈጽሞ ተጻራሪና ጸረ ነፍስ ነው። የእሬቻ የዛር መንፈስ እንጂ ከመንፈስ ቅዱስ አይደለም። ለእግዚአብሔር እንጂ ለዛፍ አትንበርከክ። ለሚያልፍ ፖለቲካ የማያልፍ እግዚአብሔርን አናስቀይም።
"በወደዳችኋት የአድባር ዛፍ ታፍራላችሁና፥ " ኢሳይያስ 1፥29
🔵 እሬቻ ደብረ ዘይት [ቢሾፍቱ] ሆራ አርሰዲ ሓይቅ ዙርያ አርሰዲ የሚባለው መንፈስ እየተወደሰ አንዲት የአድባር ዛፍ ስር ይከበራል። ኢሬቻ የራሱ ካህናት አሉት።
🔵 ተከታዮቹም የሚገብሩት ራሱን የቻለ ግብር አለ። የአድባር ዛፏ ቅቤ ትቀባለች። ሐይቁ ውስጥ አለ ተብሎ ለሚገመተው ቆሪጥም የስለት አረቄ ይጣልለታል። ደስ እንዲለውም ከብት እየታረደለት ደም ይጠጣል። ሞራ ገላጮች "ትንቢት" ይናገራሉ። አማኞችም ተንበርክከው ተረፈ መስዋዕትን ይበላሉ።
🔵 ቪድዮውንና ፎቶውን ይመልከቱ። ቪድዮው ላይ ቁልጭ ብሎ እንደምትመለከቱት ኢሬቻ ሲደርስ አርሰዲ ለሚባለው መንፈስ የደም ግብር ይቀርብለታል። ደም ይጠጣል። የተረፈውን መስዋት ደግሞ ተከታዮቹ ይበሉታል። አርሰዲ የተባለው የኢሬቻ መንፈስ ደም ከጠጣ በኋላ - የኢሬቻ ካህን የሆኑት ወገኖች ላይ አድሮ ያስጓራቸዋል። መንፈሱ አርሰዲም "እኔ ሰው አይደለሁም። መንፈስ ነኝ። አልሞትም ወዘተ" እያለ ይፎክራል። የዛር ፈረስ በመባል የሚታወቁት ካህናቱም ለታመመ "ፈውስ" ይሰጣሉ።
🔵 እነዚህ የኢሬቻ ካህናት ኢሬቻ ሲከበር ሆራ አርሰዲ ያለችው የአድባር ዛፍ ስር እየተገናኙ ድቤ ይመታላቸዋል። ሆራ ቀውጢ ትሆናለች። ያቺ የአድባር ዛፍም ቅቤ ትቀባለች። በግምጃ ታጌጣለች። የሽቶ አይነት ይርከፈከፍላታል። ወዘተ . . . ማንም ሰው የፈለገውን ማምለክ ይችላል። መብቱ ነው። እጁን ወደሚያቃጥለው ወይም ወደ ቀዘቀዘው ውሃ የመክተት ነጻ ሕሊና አለው። መዘዙ ግን በኋላ ነው- የዛሬ ሳቅ የነገ ለቅሶ ስትሆን! ግን ኢሬቻ በሃይማኖት በተለይም በክርስትና አይን ሲታይ ምንድነው? ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ኢሬቻን ማክበር ይገባዋልን? መልሱን መፅሐፍ ቅዱስ በማያሻማ ሁኔታ እንዲህ ሲል ይነግረናል።
🔵 "በወደዳችኋት የአድባር ዛፍ ታፍራላችሁና፥ " ኢሳይያስ 1፥29፤ እርግጥ ነው ኢሬቻ የምስጋና ቀን [thanksgiving] ነው። ግን የሚመሰገነውና የሚክብረው ማነው? አርሰዲ የሚባል ደም የሚጠጣ ክርስቲያናዊ አምላክ ወይም ቅዱስ መንፈስ የለም። የኢሬቻን ካህናት የሚያስጓራው ዛር ከክፉው እንጂ ከቅዱስ መንፈስ አይደለም። የክርስቶስም መገኛ ዛፍ ስር ወይም ሐይቅ ውስጥ አይደለም። የራሱ መመለኪያ ቦታ አለው።
🔵 ሳር የሚበተንለት፣ ስለት የሚገባለት፣ ከብት ታርዶ ደም የሚረጭለት፣ የሆራው ቆሪጥ ርኩስ መንፈስ እንጂ ቅዱስ መንፈስ አይደለም። ዛፍ ምን ስለሆነ ነው ቅቤ የሚቀባው? እንዴት ክርስቲያን ራሱ ተክሎ ላበቀላት ዛፍ ይሰግዳል? እንዴትስ እንደ አምላክ እየታየ ቅቤ ይቀባል። ለምን ህዝብ ይንበረከካል ? ለምንስ ዛፍ ግምጃ ያለብሳል? እኛ ክርስቲያኖች በአምልኮ ልንሰግድለት፣ ልንበረከክለት የሚገባን አንድ አምላክ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንጂ ዛፍ አይደለም።
🔵 እዚህ በዓል ላይ መገኘትም ሆነ መታደም በክርስትና ዓይን ፈጽሞ የነፍስ ስብራትን የሚያመጣ አምልኮ ባዕድ ነው። ጮክ ብዬ እደግመዋለሁ:- እሬቻን ያከበረ ክርስቲያን በእግዚአብሔር ፊት መጠየቁ አይቀርም። እሬቻ ላይ እግዚአብሔር አይከብርም። እርግጥ ነው:- ዛሬ ፖለቲካው ሃይማኖት ሆኗል። ብዙዎቹንም ፖለቲካ ከሃይማኖት በልጦባቸው "እሬቻ" አይነኬና አይደፈሬ ፖለቲካዊ ሃይማኖት ሆኗል። ትሰሙ እንደሆነ ለራሳችሁ ስትሉ ስሙ መቼም ቢሆን የጅብ ራስ ከመሆን ያንበሳ ጭራ እንሁን! ፖለቲከኞች ተደስተውብን እግዚአብሔር ከሚያዝንብን - መንጋው ጠልቶን እግዚአብሔር አይፈርብን። በነጻነት ስም በአምልኮ ባዕድ አተላ አንጠመድ። ወፍጮ ቤት ገብቶ ብናኝ ዱቄት ሳያገኘው የማይወጣ ሰው የለም። እንዲህ ዓይነት በዓላትም ላይ ተሳትፎ በመንፈሱ የማይወጋ አይኖርም። ወደሽ ከተደፋሽ - ቢረግጡሽ አይክፋሽ ነው ነገሩ። ዛሬ በዓል ያከበርን መስሎን ያደመቅነው የመንፈስ በዓል ነገ spiritual parasite ሆኖ እድሜ ዘመናችን ዋጋ የሚያስከፍለን እንዳንሆን!
🔵 ሞቀ ደመቀ በሚል በይሉኝታ ወይም በአድባርይነት የአምልኮ ባዕድ ሰባኪዎች የሆናችሁም - ነገ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋ ትከፍሉበታላችሁ። የማይረባ የዘር ፖለቲካ ሰማይ ቤት ተክትሎህ አይሄድም። ዛሬ የሰበካት ውሸት ነገ ሰማይ ቤት እሳት ሆና ትበላሃለች። ዛሬ ለዛፍ እንዲሰግድ፣ ዛፍ ቅቤ እንዲቀባ ባደረከው ሕዝብ ነፍስ ነገ ለፍርድ ትቀርባለህ።
🔵 የመጨረሻው ዘመን ስለሆነ ሚሊዮኖች ይተማሉ። ርኩሰትም በተቀደሰችው ሀገር ይበዛል። ሌላው ቀርቶ መስቀል ይዞ የክርስቶስን ቀሚስ ለብሶ "እሬቻ ክርስቲያናዊ ነው" ብለው የሚሰብኩ ተረፈ ይሁዳዎች በየሚድያው ይበዛሉ። የመጨረሻው ዘመን ላይ ነን። ትንቢቱ ይደርስ ዘንድ ግድ ነው። ግን አንተ እግዚብሔርን እንጂ ዛፍን አታምልክ። ለቅዱስ መንፈስ እንጂ ለዛር አትገብር። ለክርስቶስ እንጂ ለአርሰዲ አትሸበር። "እሬቻ ኦርቶዶክሳዊ ወይን ኦሪታዊ ነው" የሚሉ በለአሞችን አትስማ። ስለበዙና መንጋ ስለሆኑ የቁጥራቸው ብዛት ያንተን እግዚአብሔርን አያስፈራውም። አንተንም በቁጥር አነስክ ብሎ አይንቅህም። ብቻህን ብትቀር እንኳን ከእውነት ጋር ብቻህን ኑር። አሸናፊው አንተ ነህ። ግን ሁሌም እውነትን እውነት በል።
🔵 እንኳን ለእሬቻ አደረሳችሁ ወይም መልካም እሬቻ ከማለታችን በፊት ደጋግመን ቃሉን እናስበው። ለማን አምልኮ በዓል አደረሳችሁ እያልን እንደሆነ እያስተዋልን።
🔵 እግዚአብሔርንም አመልካለዉ እያላችሁ ነገር ግን [ከእሬቻ፣ ከጨንበላላ፣ ከጊፋታ፣ በመስቀል ስም በሌሎች ባህላዊ አምልኮ ስም] ሰጥታችሁ ከምታመልኩት ጣዖት አምልኮ ባስትመለሱ መጨረሻችሁ ገሃነም እሳት ነው።
“ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”
— ራእይ 21፥8
“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።”
— 2ኛ ቆሮ 13፥14
👉 እሬቻን በተመለከተ ጥያቄ ለምታነሱ ከስር አንብቡ ቅዱሱ መፅሀፍ የሚለውን
2ኛ ቆሮ 6 :14-18
" ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና?
ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?
ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው?
ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው? እኛ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነንና እንዲሁም እግዚአብሔር ተናገረ እንዲህ ሲል፦ በእነርሱ እኖራለሁ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፥ አምላካቸውም እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።
ስለዚህም ጌታ፦ ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኵስንም አትንኩ ይላል፤ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ፦ እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ለእናንተም አባት እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ ይላል። "
ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo
የ Barok መልእክት ለ ውድ የVGM አባላት፣
በጥልቅ ፍቅር እና በVGM በመተማመን ዛሬ ወደ እናንተ ይሄን መልእክት እፅፋለሁ።
ከቪጂኤም ጋር መስራት ከጀመርኩ አንድ አመት ሆኖኛል።
የእኔን ህይወት ብቻ ሳይሆን የቤተሰቦቼን፣ የዘመዶቼን፣ የጓደኞቼን እና ስፍር ቁጥር የሌላቸውን የሌሎችን ህይወት በሚያስደንቅ ሁኔታ እንደለወጠው በልበ ሙሉነት መናገር እችላለሁ።
ቪጂኤም በሺዎች የሚቆጠሩ ህይወትን በተሻለ ሁኔታ ቀይሯል።
ስለ VGM አሉታዊ አስተያየቶችን መስማት በጣም ያማል። ዝም ብዬ ቆሜ ማየትም አልችልም።
ለዚህም ነው ሁሉም የቪጂኤም አባላት አንድ እንዲሆኑ እና የኩባንያችንን ስም እንዲጠብቁ ጥሪ የማቀርበው።
VGMን ለመጠበቅ በማህበራዊ መድረኮች ላይ ስለ VGM ማንኛውንም አሉታዊ አስተያየቶችን ሪፖርት ማድረግ አስፈላጊ ነው።
ለVGM በማይናወጥ አጋርነት የምንነሳበት እና የምንቆምበት ጊዜ አሁን ነው።
እንደ መሪ በቡድኖቻችን ላይ በተለይም በአስቸጋሪ ጊዜያት እምነትን ማጠንከር የእኛ ኃላፊነት ነው።
ወሬዎች የገነባነውን ይሄን ትልቅ መሰረት እንዲያበላሹ መፍቀድ የለብንም።
በተሳሳተ መረጃ ምክንያት የሄዱት ወደ ስራቸው መመለስ አለባቸው፤ ይሄን እድል ማበላሸት የለባቸውም።
እዚህ ደረጃ ላይ ለመድረስ ጠንክረን ሰርተናል፤ ብዙ ዋጋም ከፍለናል ፣ እንዲመለሱ፣ እንዲቆዩ እና ከእኛ ጋር መገንባታቸውን እንዲቀጥሉ እናበረታታ፣ ምክንያቱም እውነት ሁል ጊዜ ያሸንፋል።
VGM ደሞ 100% እውነት ነው።
ይህንን ቡድን በእምነት እና በጋራ ስኬት ላይ በአመት ልፋት ገንብተናል። ብዙዎቻችሁ በተለይም ከፍተኛ አባሎቻችን አስደናቂ ክንዋኔዎችን አሳክተናል።
አሁን፣ አዲሱን የVGM's ጥንካሬ እና ደህንነት አባሎቻችንን ለማረጋጋት እርምጃ እንድትወስዱ እጠይቃለሁ።
ከ30 USDT ወይም ከዚያ በላይ ጋር ከተቀላቀሉን ኢንቨስትመንታቸው ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ያሳውቁ፣ ምንም አይነት ኪሳራ እንደማይደርስባቸው በግሌ ዋስትና እሰጣለሁ። እኛ እዚህ የመጣነው እርስ በርሳችን ኢንቨስትመንቶቻችንን እየጠበቅን ፣ 100% በማረጋገጥ ነው።
በተጨማሪም ኩባንያችን ከ20,000 USDT (2,600,000 ETB) በላይ ኢንቨስት በማድረግ የተገኘውን የVGM Head Quarter Operation Centerን በኩራት አጠናቋል።
ታላቁ መክፈቻም ጥቅምት 7 የሚካሄድ ሲሆን የሀገር ውስጥ እና የሌሎች አፍሪካ ሀገራት መሪዎች ይገኛሉ፤ ይህንንም መጥታችሁ በአይናቹ ማየት ትችላላችሁ።
ይህ ለቀጣይ ቁርጠኝነታችን እና እድገታችን ቀጣይነት አስተማማኝ ዋስትና ነው።
ሁላችሁም ዋና መሥሪያ ቤቱን እንድትጎበኙ እና ይህን ስኬት ለራሳችሁ እንድትመሰክሩ ተጋብዛችኋል።
በደህንነት፣ በመተማመን እና ሁላችንም የምናምንበትን የወደፊት የVGM ኩባንያ እውነተኛ ጥንካሬ ለሁሉም በማሳየት እንደ አንድ ወደፊት እንሂድ።
አንድ ላይ ሆነን በራስ መተማመንን ማነሳሳት እና ወደፊት መግፋታችንን እንቀጥል።
ከVGM ጋር ቁሙ እና የሄዱም ካሉ በሙሉ እምነት መልሷቸው።
ፍቅራችንን እና እምነትን በVGM እናሳይ❗
ቪጂኤም በጭራሽ አያሳፍረንም❗
ቪጂኤም ህይወታችንን መቀየሩን ይቀጥላል❗
✍️diro Oromo
በፍጥነት መረጃዎችን ከፈለጋቹ ቻናሌን ተቀላቀሉ
በተጨማሪ በ youtube ልዩ በሆነ መልኩ ለመምጣት አስበናል አብራችሁን መስራት የምትፈልጉ ባለሙያዎች
👉 ካሜራ
👉 ኤዲተር
👉 መምህራን
በውስጥ መስመር አናግሩን ።
👉 @ZOSKALESSS
አባቶቻችን ስለ ኃጢአተኛ እንዲህ አሉ: –
"በጽድቁ ከሚመካ ጻድቅ ሰው ይልቅ ስለ ኃጢአቱ የሚያለቅስ ዘማዊን እግዚአብሔር ይወድደዋል"
ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
"የትናንት ታሪክ የሌለው ጻድቅ የነገ ተስፋ የሌለው ኃጢአተኛ የለም"
ቅዱስ አውግስጢኖስ
"አቤቱ እንደ እኔ ያለ ኃጢአተኛ እንደ አንተ ያለ መሐሪ የለምና ይቅር በለኝ"
ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
"ቤተ ክርስቲያን ሐኪም ቤት ናት እንጂ በነፍሳት ላይ የምትፈርድ ፍርድ ቤት አይደለችም። ስለ ኃጢአትም ስርየትን ትሠጣለች እንጂ ፍርድ አትሠጥም"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"ኃጢአትን ለማዋጋት ስትሞክሩ ኃጢአተኛውን እንዳትወጉ ተጠንቀቁ"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo
እንኩዋን ለቅዱስ "ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት በዓል በሰላም አደረሳቹ።
+ ቅዱስ ጊዮርጊስ ልዳዊ +
=>መጽሐፈ ገድሉ እንደሚለው የሰማዕታት አለቃቸው: አንድም ሞገሳቸው ታላቅና ክቡር ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ7 ዓመታት ስቃይ በሁዋላ ተሰይፏል:: ይሕስ ጥንተ ነገሩ እንደምን ነው ቢሉ:-
+ቅዱሱ የተወለደው ከአባቱ ዘረንቶስ (አንስጣስዮስ) እና ከእናቱ ቴዎብስታ የድሮው ፋርስ ግዛት ፍልስጥኤም (ልዳ) ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቹ ክርስትናን ጠንቅቀው አስተምረውት አባቱ ይሞታል::
+ቅዱስ ጊዮርጊስ 20 ዓመት ሲሞላው የአባቱን ስልጣን እጅ ለማድረግ ሲሔድ የቢሩት (የአሁኗ ቤይሩት - ሊባኖስ) ሰዎች ዘንዶ (ደራጎን) ሲያመልኩ አገኛቸው:: እርሱ ግን የከተማውን ሕዝብ አስተምሮ: አሳምኖ: ደራጎኑንም በፈጣሪው ኃይል ገድሎ መንገዱን ቀጥሏል::
+ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ዱድያኖስና 70 ነገሥታት ዘንድ ሲደርስ ክርስቶስ ተክዶ ለጣዖት ይሠገድ ነበር:: በዚያች ሰዓት ድንግል እመቤታችን ወደ ሰማዕቱ መጥታ መከራውንና ክብሩን ነገረችው:: እርሱም በክርስቶስ ስም መሞት ምርጫው ነበርና ከእመቤታችን ተባርኮ ወደ ምስክርነት አደባባይ (ዐውደ ስምዕ) ደረሰ::
+ከዚያም ለተከታታይ 7 ዓመታት ብዙ ጸዋትወ መከራዎችን ተቀበለ:: 3 ጊዜ ሙቶ ተነሳ:: ከሰው ልጅ የተፈጥሮ ትዕግስት በላይ የሆነ ስቃይን ስለ ቀናች ሃይማኖት ሲል በመቀበሉ "የሰማዕታት አለቃቸው" : "ፀሐይና የንጋት ኮከብ" በሚል ይጠራል::
"ተውላጠ ጻማሁ ወሕማሙ::
ዘተለዐለ ሞገሰ ስሙ::" እንዲል መጽሐፍ::
+ከ7 ዓመታት መከራ በሁዋላም ከብዙ ተዓምራት ጋር ተሰይፎ ደም: ውሃና ወተት ከአንገቱ ፈሷል:: 7 አክሊላትም ወርደውለታል::
=>ይህቺ ዕለት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ኃያል ቅዳሴ ቤቱ ናት:: እርሱ በ390ዎቹ አካባቢ ሰማዕት ከሆነ ከጥቂጥ ዓመታት በሁዋላ በዚያው በሃገሩ ደብር አንጸው: አጽሙን አፍልሠው በዚህች ቀን ቀድሰዋታል::
+ቅዱሱ ሰማዕት ከሰማዕትነቱ በፊትም ሆነ በሁዋላ ተአምረኛ ነውና አንዷን እንመልከት:: በዘመኑ የክርስቲያኖችን ደም ሲያፈሱ ከነበሩ አራዊት (ነገሥታት) መካከል አንዱ የሆነው ዲዮቅልጢያኖስ ርጉም የ47 ሚሊየን ክርስቲያኖችን ደም አፍስሶ ነበርና ፈጣሪ ደመ ሰማዕታትን የሚበቀልበት ጊዜ ደረሰ::
+በ305 ዓ/ም አካባቢ አረመኔው ንጉሥ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተአምረኛነት ሰምቶ እንዲያፈርሱት ሠራዊት ላከ:: የሠራዊቱ አለቃም ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ገብቶ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስዕል ላይ ተሳለቀ::
+ከፊቱ የነበረውን ቀንዲል በሰይፍ እመታለሁ ሲል ግን ቀንዲሉ ተገልብጦ መሐል አናቱን መታው:: እንደ እብድ ሆኖ ሞተ:: ሠራዊቱም ሰምቶ ወደ ንጉሡ ሸሸ:: ይሕን ሰምቶ የተበሳጨው ዲዮቅልጢያኖስ ግን ራሱ ሊያፈርሰው ሔደ:: ከቤተ ክርስቲያኑ በር ላይ ሲደርስ ሚካኤልና ገብርኤል ዐይኑን አጠፉት::
+እገባለሁ ሲል ቅዱስ ጊዮርጊስ ከላይ መረዋውን (ደወሉን) ለቀቀበት:: ራሱን ቢመታው ደነዘዘ:: የብዙ ቅዱሳንን ደም የጠጣው ርጉሙ ንጉሥም አብዶ ለ7 ዓመታት ፍርፋሪ ሲለምን ኑሮሰ ይጣን ከገደል ጫፍ ወርውሮ ገድሎታል::
=>አምላካችን እግዚአብሔር ከኃያሉ ሰማዕት ጽናትና ትእግስት: ከበረከቱም ይክፈለን::
ለመቀላቀላ 👉 @ortodoxtewahedo
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete site link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
ለምኑም ሰላም እደር ፤ እንወድሃለን። ልናጽናናህና ልናፈቅርህ እንጂ ልናወግዝህ አይደለም ቤተሰቦችህ የኾነው። ጌታችን ለአንተ ካለው ፍቅር የተነሣ፣ አንተን ከመውደዱ የተነሣ እኛን 'በሰፈራችሁበት መስፈሪያ ትሰፈራላችሁ' ብሎ አስጠንቅቆ አገልጋይህ አድርጎ ከያለንበት አስቀምጦናልና። አሁንም በጌታ ደስ ይበለን ፤ ፊት ለፊቱ ብንበድለው እንኳን ተስፋ ያልቆረጠብን አባት አለን።
"ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም። ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል።" /1ኛ ዮሐ 4 ፤ 10 - 11/