የኢየሱስ አምላክነት በይሁዳ መልዕክት
የይሁዳ መጽሐፍ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ካሉት እጅግ አጫጭር መጻሕፍት መካከል አንዱ ሲሆን አንድ አጭር ምዕራፍ ብቻ የያዘ አነስተኛ መጽሐፍ ነው፤ ሆኖም በእነዚህ ጥቂት መስመሮች ውስጥ ይሁዳ ስለ ክርስቶስ መለኮትነት በአጽንዖት ሲገልጽ እናነባለን።
ቍጥር ዐራት፦
“ረጅም ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንድ ሰዎች ሾልከው ወደ እናንተ ገብተዋልና፤ እነርሱ ፈሪሀ እግዚአብሔር የሌላቸው፣ የአምላካችንን ጸጋ በርኵሰት የሚለውጡና እርሱ ብቻ ልዑል ገዣችንና ጌታችን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚክዱ ናቸው።” (አ.መ.ት)
παρεισεδύησαν γάρ τινες ἄνθρωποι, οἱ πάλαι προγεγραμμένοι εἰς τοῦτο τὸ κρίμα, ἀσεβεῖς τὴν τοῦ θεοῦ ἡμῶν χάριτα μετατιθέντες εἰς ἀσέλγειαν καὶ τὸν μόνον δεσπότην καὶ κύριον ἡμῶν Ἰησοῦν Χριστὸν ἀρνούμενοι.
ግራንቪል ሻርፕ የተሰኘ የግሪክ ቋንቋ ሊቅ ለይቶ ካስቀመጣቸው የግሪክ ሰዋስው ሕግጋት መካከል አንዱ በሆነው ሕግ 1 መሠረት ይሁዳ ከላይ ባነበብነው ጥቅስ፣ “ገዣችንና ጌታችን” ብሎ የሚገልጸው አንዱን አካል ይኸውም ኢየሱስን መሆኑን እንረዳለን። ሕጉ እንደሚለው “በዋናው የግሪክ አወቃቀር (ትርጉም ባልሆነ ግሪክ) “ካይ” በሚል መስተጻምር የተያያዙ ሁለት ስሞች አንድ መስተኣምር ከፊታቸው ከገባ እና ሁለቱም ባሕርይ ገላጮች (1) በሰዋሰውም ሆነ በቃል ደረጃ ነጠላ ከሆኑ (2) ማንነታዊ ከሆኑ (ህልውና ያላቸውን አካላት አመልካች ከሆኑ) እና (3) የወል ስሞች ከሆኑ (የተጸውዖ ስሞች ወይንም ቅደም ተከተላዊ ካልሆኑ) አንድን አካል ያመለክታሉ፡፡” በዚህ መሠረት τὸν μόνον δεσπότην καὶ κύριον ἡμῶν Ἰησοῦν Χριστὸν (ቶን ሞኖን ዴስፖቴን ካይ ኩሪዮን ሄሞን ኢዬሱን ክሪስቶን) በሚለው ውስጥ “ዴስፖቴን” (ገዣችን) እና “ኩሪዮን” (ጌታችን) የሚሉት ባሕርይ ገላጮች “ቶን” በሚል አንድ መስተአምር የተቀደሙና “ካይ” በሚል መስተጻምር የተያያዙ በመሆናቸው ሕጉን ያሟላሉ፤ እናም በዚህ ቦታ “ገዣችን እና ጌታችን” የተባለው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በተጨማሪም፣ በዐውደ-ምንባቡ ውስጥ ብቸኛ አምላክ የተባለው አብ፣ በብቸኛው ጌታ በክርስቶስ በኩል አኮቴት እንደሚቀርብለት ይናገራል (ቍጥር 25)፤ ይኽውም ይሁዳ ብቸኛ አምላክ የሚለውን ቅጽል ለአብ፣ “ብቸኛ ጌታ” የሚለውን ደግሞ ለወልድ ይጠቀማል ማለት ነው። ታዲያ በዚህ ጥቅስ ውስጥ “ገዣችንና ጌታችን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚክዱ ናቸው” የሚለውን የመጨረሻ ሐረግ አሁንም በጥንቃቄ ማስተዋል አስፈላጊ ነው። “ገዣችን” ተብሎ የተተረጎመው የጽርእ ቃል δεσπότην “ዴስፖቴን” የሚል ሲሆን፣ δεσπότης “ዴስፖቴስ” ከሚል የጽርእ ቅጽል የመጣ ነው። በዚኽ ቅጽል የሚጠራ ግለሰብ፣ በአንድ ማሕበረሰብ ወይም ቤተሰብ የበላይ መሪ ወይም ከሁሉም የላቀ ሥልጣን ያለው አካልን ለማመልከት የሚገባ ቃል ነው[1]። በይበልጥ ደግሞ ይኼ ቅጽል በሮማውያን ባሕል ውስጥ ያለው ሥልጣን እጅግ የላቀ ነው፤ ይኸውም የአንድ ቤተሰብ ራስና ባለ ሙሉ ሥልጣን ከመሆኑ የተነሳ፣ የአብራክ ልጆቹ ምን ትልቅ እና ራሳቸውን የቻሉ ቢሆኑ እንኳ ሥነ ምግባራቸው ደስ ካላሰኘው እስከ መግደል የደረሰ ሕጋዊ መብት አለው[2]። ይሁዳ ይኽንን ቃል የተጠቀመው በብሉይ ኪዳን ስመ-ያህዌን ወክሎ ለእልፍ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለውን “ጌታ” በጽርእ κύριος “ኩሪዮስ” ከሚል ቃል ጋር በማጣመር ነው። እነኚህ ኹለት ቅጽሎች ማለትም፣ δεσπότην “ዴስፖቴን” እና κύριον “ኩሪዮን” በአንድ ላይ ተያይዘው የቀረቡት እውነተኛውን አምላክ ያህዌን ለመግለጽ መሆኑን የብሉይ ኪዳን የሰብዓ ሊቃናት ትርጉምን (LXX) ስንመለከት እንገነዘባለን። ለምሳሌ፦
“አብራምም፣ “ገዢ ጌታ ሆይ (Δέσποτα Κύριε)፤ ይህችን ምድር እንደምወርሳት በምን ዐውቃለሁ?” አለ።”
— ዘፍጥረት 15፥8 LXX
“እኔም፣ “ጌታ ገዢ ሆይ (δέσποτα Κύριε) ፤ ሰይፍ አንገታቸው ላይ ተቃጥቶ ሳለ፣ ‘ሰላም ይሆንላችኋል’ ብለህ ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን ለምን እጅግ አታለልህ?” አልሁ።”
— ኤርምያስ 4፥10 LXX
“ስለዚህ የሠራዊት ገዢ (δεσπότης) ጌታ (Κύριος) እንዲህ ይላል፦ ለእስራኤል ኃያላን ወዮላቸው። ቍጣዬ በጠላቶቼ ላይ አይወገድምና፥ በጠላቶቼም ላይ ፍርድን አደርጋለሁ” ኢሳይያስ 1፥24 LXX
ኢየሱስ የኛ ብቸኛ ገዢ እና ጌታ ሊሆን የሚችልበት ብቸኛው መንገድ እርሱ ያህዌ አምላክ ከሆነ ብቻ ነው።
ቍጥር አምስት፦
“ምንም እንኳ አስቀድማችሁ ይህን ሁሉ የምታውቁ ቢሆንም፣ ኢየሱስ ሕዝቡን ከግብፅ ምድር እንዴት እንዳወጣ፣ በኋላ ግን ያላመኑትን እንዳጠፋ ላስታውሳችሁ እወዳለሁ።”
— ይሁዳ 1፥5 (ESV)
Ὑπομνῆσαι δὲ ὑμᾶς βούλομαι, εἰδότας ἅπαξ πάντα ὅτι Ἰησοῦς λαὸν ἐκ γῆς Αἰγύπτου σώσας τὸ δεύτερον τοὺς μὴ πιστεύσαντας ἀπώλεσεν,
አንዳንድ የግሪክ የእጅ ጽሑፎች “ኢየሱስ” የሚለውን “ጌታ ሕዝቡን ከግብፅ ምድር እንዴት እንዳወጣ” ይላሉ፤ ነገር ግን በቍጥር 5 ላይ ጌታ ብለው የጠቀሱት ክርስቶስ መሆኑን በመካድ አይደለም፤ ምክንያቱም፣ በቍጥር 4 ላይ፣ ብቸኛ ጌትነቱ የተነገረለት ኢየሱስ ነው፤ ሆኖም ግን በቊጥር 5 “ጌታ” የሚለው ቀዳማይ የግሪክ ዕደክታብ ኮዴክስ ሳይናቲከስ ሲሆን፣ ከእርሱ በዕድሜም ሆነ በጥራት ቀዳማይና ተመራጭ የሆነው ኮዴክስ ቫቲካነስ “ኢየሱስ” ይላል። ከዚህ በፊት በሌላ ጽሑፍ ላይ እንደገለጥነው በአዲስ ኪዳን የምንባባዌ ሕያሴ ሊቃውንት (New testament textual critics ) ዘንድ ከሳይናቲከስ ይልቅ ቫቲካነስ ይበልጥ ተቀባይነት አለው[3]፤ እንዲሁም፣ እንደ አርጌንስ፣ ቆጵርያኖስ፣ ጀሮሜ፣ ወዘተ. ያሉ ቀደምት የቤተክርስቲያን አበው ይሁዳ 1፥5ን በሚጠቅሱበት ጊዜ “ጌታ” ከሚለው ቃል ይልቅ “ኢየሱስ” የሚለውን በጽሑፋቸው ውስጥ ተጠቅመዋል። ይበልጡኑ ደግሞ ፓፒረስ 72 በመባል የሚታው የይሁዳ መልዕክት የመጀመሪያው የእጅ ጽሑፍ፣ “አምላክ ክርስቶስ” (θς χρς) በማለት “ኢየሱስ” ለሚሉት ዕደክታባት ጥሩ ግብአት ሆኗቸዋል።

ፓፒረስ 72
ክርስቶስ ሕዝቡን ከግብፅ ማውጣቱን በተመለከተ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ተመሳሳይ ሐሳብ አንጸባርቋል፦
“ወንድሞች ሆይ፥ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ። አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ ሁሉም በባሕር መካከል ተሻገሩ፤ ሁሉም ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ በደመናና በባሕር ተጠመቁ፤ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መብል በሉ፥ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዓለት ጠጥተዋልና፥ ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ።” (1ቆሮ. 10፥1-4)
መስከረም 29
ቅድስት አርሴማ በሰማዕትነት አረፈች።
የቅድስት አርሴማ እናት አትናስያ ትባላለች ልጅ በማጣት ለረጅም ዘመን ታዝን ታለቅስ ነበር በኃላም እግዚያብሔር ልመናዋን ሰማት ይህችን ክብርት ቅድስት ልጅንም ሰጣት፤ቅድስት አርሴማ ጥር 6 ነው የተወለደችው፤15 ዓመት ሲሆናት ሊያጋቧት አሰቡ እርሷ ግን ይህን አልወደደችም፤ በደናግል ገዳም ገብታ በተጋድሎ መኖር ጀመረች። ከዚህ በኋላ እንዲህ ሆነ ከሃዲው ንጉስ ዲዮቅልጥያኖስ ሊያገባት ወደደ ቅድስት አርሴማ ግን ከደናግሉ ጋር ሸሽታ ወደ አርማንያ ሄደች በዚያም በበርሃ ለጥቂት ቀናት ተቀመጠች በኋላ ላይ ድርጣድስ የሚባል አገር ገዢ በበርሃ እንደሚኖሩ ሰማ ወታደሮችንም ልኮ አስመጣቸው፤ የቅድስት አርሴማን መልክ በተመለከተ ጊዜ ፈዞ ደንዝዞ ቀረ የፊቷ ውበት እጹብ ድንቅ፤ ግርማዋ የሚያስደነግጥ ልብ የሚያርድ ነበርና፤ስለዚህም ሊያሰቃያት አልደፈረም በእንክብካቤ በሰገነት ላይ አኖራት፤ ሌሎቹን ግን ለጣአት እንዲሰግዱ ገረፋቸው፤ ቅድስት አርሴማ እኔንም አሰቃዩኝ እያለች አምርራ ታለቅስ ነበር። ድርጣድስ ብዙ ጊዜ ሊሸነግላት ሞከረ እርሷ ግን ትዘልፈው ጣኦታቱንም ትረግም ነበር፤ እርሷ ጸንታ ደናግሉን ታጸና እና ታረጋጋቸው ነበር፤ ድርጣድስ ሽንገላው እንደማያዋጠው በአወቀ ጊዜ ማሰቃየት ጀመረ፤ በመጨረሻም ከብዙ ስቃይ በኃላ መስከረም 29 ቀን አንገቷን ቆረጣት ከእርሷ ጋር 27 ሰማዕታት አብረው ተሰይፈዋል።ታህሳስ 6 ፍልሰተ አጽሟ ነው።
የእናታችን የቅድስት አርሴማ በረከት በሁላችን ይደር።
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete Username(ID) ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete Username(ID) ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
✝️ቅድስት አርሴማ ሰማዕት
እንኳን ለሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!✝️
✝️ ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ጣኦታ አምላኪ ነገሥታት እና አሕዛብ ባየሉበት ዘመን ተወልዳ በክርስትና ያበበች ከቅዱሳን አንስት አንዷ ናት
✝️ ከቤተሰቦቿ እና ከቅዱሳት መጻሕፍት የተማረችውን እውነት በተግባር የተረጎመች እናት ናት
✝️ በውበቷ ተማርከው ዓለማዊ ቁስን እንደ መደለያ ያቀረቡላት ነገሥታትን ንቃ ለሰማያዊው መንግሥት ሕይወቷን መስዋዕት ያደረገች ቅድስት እናት አርሴማ
✝️ ቅድስት አርሴማ እስከ ሕይወቷ ፍጻሜ በጾም፣ በጸሎትና ጌታዋን በማምለክ ጸንታለች
✝️ በገዳማዊ ሕይወት በድንግልና የኖረችው ቅድስት አርሴማ በብዙ መከራና ስቃይ ብትፈተንም በእምነቷ ከመጽናት ምንም አላገዳትም
✝️ በመጨረሻም በመስከረም ፳፱ ቀን እምነቷን ጠብቃ ሰማዕትነትን ተቀበለች
የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ምልጃና በረከት ይደርብን። በጸሎቷ ታስበን።
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ባለፉት ሁለት ዓመታት የገጠሙትን ተግዳሮቶች በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት እና ምክርር አደረገ !
መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ባለፉት ሁለት ዓመታት የገጠሙትን ተግዳሮቶች እና ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ አካላት እየቀረበበት ያለውን አቤቱታ እና ክስ በተመለከተ በሀገረስብከቱ ከሚገኙ አድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፣ ጸሐፊዎች እና ሒሳብ ሹሞች ጋር ውይይት እና ምክክር በዛሬው ዕለት አድርጓል።
በውይይቱ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር " መስቀል ማለት ሁሉን አፋቅሮ የሚሰበስብ እንጂ የሚለያይ አይደለምና በመስቀሉ ፍቅር ተሰብስበን እግዚአብሔር ከፊታችን ያለውን ፈተና ሁሉ እንዲያሻግረን እየጠየቅን ፣ ሀገረስብከታችን ባሳለፍነው ሁለት ዓመታት ውስጥ በርካታ ችግሮች እንደገጠመው ይታወቃል ፣ እና በትዕግስት እና በዝምታ ለመፍታት ስንታገል ቆይተናል፣ አሁን ግን ችግሮቻችንን ለመፍታት ተነጋግረን እና ወስነን ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ ለማቅረብ ፣ ለምእመናንም ሆነ ለራሳችን ተገቢውን አገልግሎት እንድንሰጥ ይህንን ውይይት ማድረግ አስፈልጓል" ብለዋል።
የሀገረስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስቅዱስ " ከሰሞኑ በሀገረስብከታችን ላይ እንዲደረግ የተባለው የማጣራት ሂደት ምንም ችግር የለውም። ነገር ግን አሁን ያለው ችግር እኛ ከመምጣታችን በፊት የተከሰተ ቢሆንም እኛ ችግሮቹን ለመፍታት ጥረት አድርገናል ፣ ምርመራ መደረጉ ችግር የለውም ፣በየጊዜው በምስል እና ድምፅ ይጣራል እኛም ምንም መረጃ ከልክለን አናውቅም። ነገር ግን ሪፖርት ቀርቦልንም በማያውቅበት ሁኔታ ከማይመለከተው አካል የይጣራ ሀሳብ ሲመጣ አልተቀበልንም። ስለሆነ የዛሬው ውይይታችን መፍትሔ የምንፈልግበት እና ከቤተክርስቲያን ጎን የምንቆምበት ጊዜ ነው" በማለት በ 5 ዋና መወያያ ጉዳዮች በመዘርዘር ውይይቱን አስጀምረዋል።
ከውይይቱ ተሳታፊ አባቶች እጅግ በርካታ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን በዋነኛነት :- በመጀመሪያ እስከዛሬ ሲጣራ የቆየበት ሪፖርት ይቅረብ ፣ የማጣራት ሂደቱን ሁላችንም እንደግፋለን ነገር ግን የሚያጣራው አካል ደረጃ እና ክብሩን የጠበቀ መሆን ስለሚገባው አጣሪ ኮሚቴ ተብሎ የተዋቀረው አካል መዋቅሩን ጠብቆ መጥቶ ማጣራት ይገባዋል ብለዋል።ባለድርሻ አካላት ሳይመክሩበት ጸድቆ የመጣው የሀገረ ስብከቱ ደንብ እንዲሻሻል የጉባኤው ተሳታፊዎች ጠይቀዋል።ሀገረስብከቱ ከሌሎች አህጉረ ስብከት ተለይቶ የሚደርስበት ጫና እንዲቆምና አገልግሎቱን በነጻነት እንዲሰጥ ጭምር የጉባኤው ተሳታፊዎች ጠይቀዋል።በየጊዜው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባን ተከትሎ የሚነሱ አሉባልታዎች መቅረት እንደሚገባቸው ፣ ጠቅላይ ቤተክህነቱ ከሕግ ውጭ ወደ ሀገረስብከቱ አድባራት እና ገዳማት ጫና ማሳረፉ አግባብ አለመሆኑ እና ፣ በሚዲያ ለምእመናንን የሚተላለፈው የተሳሳተ መልእክት እንዲቆም ፣ የሚሉ እና ሌሎች በርካታ ጥያቄና ሀሳቦች ተሰጥዋል።
በውይይቱ ማጠናቀቂያ ብፁዕነታቸው የቀረቡትን ጥያቄዎች ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ እንደሚያቀርቡ እና እስከመጨረሻው መፍትሔ እንዲገኝለት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። በመጨረሻም ባለ 12 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማስፈር እና ጉዳዩን የሚከታተል ኮሚቴ በማዋቀር በብፁዕነታቸው ቡራኬና ጸሎት ውይይቱ ተጠናቋል።
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
አንተ ብቻ ነክ የኔ
አንተ ብቻ የልቤ
አንተ ብቻ የቆምክ ጎኔ
አንተ ብቻ ማልቀሻዬ
አንተ ብቻ አዳማጬ
አንተ ብቻ መጠጊያዬ
አንተ ብቻ ጓደኛዬ
አንተ ብቻ ተስፋዬ
አንተ ብቻ ነህ ደስታዬ
የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ መዳኛዬ
@mkreab
@mkreab
አበው ስለ እመቤታችን እንዲህ አሉ
"አምላክ ከንጉሥ ሔሮድስ ሴት ልጅ ቢወለድ ኖሮ አልጋ ወራሽ በሆነና ባልተሰደደ ነበር። እርሱ ግን የድሆች ልጅ የሆነችውን ድንግል መረጠ"
#አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ
"ታላቁ ተራራ ሆይ ታናሽዋ ብላቴና የተሸከመችህ ራስህን በሚቻላት መጠን አድርገህላት ነው ፣ ታላቁ እሳት ሆይ ታናሽዋ ብላቴና ተሸክማህ ያልተቃጠለችው ኃይልን ትችል ዘንድ አጽንተሃት ነው "
#ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ
"ይህ ዓለም የእግዚአብሔርን ልጅ በቀጥታ ከእግዚአብሔር አብ እጅ ለመቀበል የተገባ ሆኖ ስላልተገኘ ፣ ዓለም ከእርስዋ ይቀበል ዘንድ አንድያ ልጁን ለድንግል ማርያም እናት ትሆነው ዘንድ ሠጣት"
#ቅዱስ_አውግስጢኖስ
"ጌታ ሆይ እናትህን ማን ብለን እንጥራት? እናት ብቻ እንዳንላት ድንግል ሆና አገኘናት ፣ ድንግል እንዳንላት ልጅ ታቅፋ አየናት። ጌታ ሆይ እናትህን ለመጥራት እንዲህ የሚያስቸግር ከሆነ አንተን ከቶ ምን ብለን እንጠራሃለን??"
#ቅዱስ_ኤፍሬም
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
ጌታችን ኢየሱስ ሥልጣንን ከአብ መቀበሉ አምላክ አለመሆኑን ያሳያልን?
ጥያቄ፡-
“ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።” (ማቴዎስ 28፡18-20)፡፡
ሥልጣን የራሱ ቢሆን ኖሮ ግን “ሥልጣን ተሰጠኝ” ሳይኾን “ሥልጣን አለኝ ” ነበር የሚለው ስለዚህ ለኢየሱስ ሥልጣን የሰጠው አምላክ መኾኑን እንረዳለን፡፡
መልስ፡-
ይህንን ጥያቄ የሚጠይቁ ሰዎች እግዚአብሔር አንድ አካል ብቻ እንዳለው ቅድመ ግንዛቤ የያዙ ናቸው፡፡ የሥሉስ ቅዱስ አካላት አንዳቸው ከሌላቸው የመቀበላቸውና አንዳቸው ለሌላቸው የመታዘዛቸው እውነታ መታየት ያለበት አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ የአንዱ ግፃዌ መለኮት አካላት መሆናቸውን በሚናገረው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምሕሮ መሠረት እንጂ በነጠላ አሓዳዊነት መሠረት መኾን የለበትም፡፡ ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል ግን ከሞላ ጎደል በእያንዳንዱ ጥያቄያቸው ውስጥ ይህንን መሠረታዊ ሃቅ በመዘንጋት የራሳቸውን ቁርአናዊ እምነት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለመጫን ሲሞክሩ ይስተዋላሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ከአብ እንደሚቀበል ብቻ ሳይኾን ለአብ እንደሚሰጥም ጭምር ይናገራል፡- “በኋላም፥ መንግሥቱን ለእግዚአብሔር ለአባቱ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ አለቅነትንም ኹሉና ሥልጣንን ኹሉ ኃይልንም በሻረ ጊዜ፥ ፍጻሜ ይሆናል” (1ቆሮ. 15፡24)፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር በመለኮት አንድ ቢሆንም በአካል ግን ሦስት በመኾኑ አንዱ የሥላሴ አካል ከሌላው መቀበሉ ከአንዱ ግፃዌ መለኮት ውጪ ከሚገኝ ሌላ አካል እስካልተቀበለ ድረስ አምላክነቱን ሊያጠራጥር አይችልም፡፡ ሌላው መረሳት የሌለበት ነጥብ በባሕርዩ ፍጹም አምላክ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክብሩን ጥሎ የባርያን መልክ በመያዝ ወደ ምድር መምጣቱ ነው (ዮሐ. 6፡38፣ ማቴዎስ 20፡24-28፣ ፊልጵሲዩስ 2፡5-8)፡፡ ስለዚህ ተልዕኮውን ከፈፀመ በኋላ አብ አክብሮታል፡-
“በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ኹሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ኹሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ መላስም ኹሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው” (ፊልጵሲዩስ 2፡9-11)፡፡
በማቴዎስ 28፡18 ላይ የሚገኘውን ቃል በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ከተመለከትን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ለማዳን ለአባቱ ታዝዞ በገዛ ፈቃዱ ትቶት የመጣውንና መለኮታዊ መብቱ የሆነውን ሥልጣን መልሶ ተቀበለ እንጂ የእርሱ ያልሆነውን ስላልተቀበለ ይህ አባባል አምላክነቱን አጠራጣሪ ለማድረግ ምክንያት አይኾንም፡፡
ሌላው መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር ከተሠግዎ በፊት ጌታችን ፍጹም አምላክ እንደነበረና ከተሠግዎ በኋላ ግን አምላካዊ ባሕርዩ ሳይለወጥ ፍጹም ሰው መኾኑ ነው፡፡ ስለዚህ ወደ ክብሩ የተመለሰው ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ኾኖ ነው፡፡ የአባቱን ፈቃድ ያለ ምንም እንከን ከዳር በማድረሱ ምክንያት መለኮታዊ ባሕርዩ ብቻ ሳይኾን ሰብዓዊ ባሕርዩም ጭምር ክብርን ተቀዳጅቷል፡፡ ይህ ደግሞ በስሙ የሚያምኑት ቅዱሳን የርስቱ ወራሽና የግዛቱ ተካፋይ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ነው (ሉቃ 22፡29-30፣ ዮሐ 17፡24፣ ሮሜ 8፡17፣ ራዕ 2፡26-27፣ ራዕ 3፡21)፡፡
ጠያቂው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥልጣንን ከአብ መቀበሉን የሚናገረውን ቃል ብቻ ነጥለው ጠቀሱ እንጂ ሙሉ አውዱን ቢያነቡት ኖሮ የኢየሱስን አምላክነት አሻሚ ባልሆነ ኹኔታ በተመለከቱ ነበር፡፡ እስኪ በክፍሉ አውድ ውስጥ የሚገኙትን ደምቀው የተጸፉትን ቃላት ልብ ብለን እንመልከት፡-
“አሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት ግን ኢየሱስ ወዳዘዛቸው ተራራ ወደ ገሊላ ሄዱ፥ ባዩትም ጊዜ ሰገዱለት፤ የተጠራጠሩ ግን ነበሩ፡፡ ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ኹሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ፡፡ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ኹሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ኹሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ” (ማቴ 28፡16-20)፡፡
በዚህ ቦታ ላይ ሐዋርያት ለኢየሱስ ሰግደዋል፡፡ የጠያቂው ሃይማኖት አጥብቆ እንደሚያስተምረው ኢየሱስ ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ ሌሎች ቅዱሳን ሰዎችና መላዕክት እንዳደረጉት ሐዋርያቱ እንዳይሰግዱለት በነገራቸው ነበር (ሐዋ. 10፡25-26፣ ራዕ 22፡8-9)፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ አንድም ጊዜ ያንን አድርጎ አያውቅም፡፡ ኢየሱስ በሰማይና በምድር ሥልጣን ኹሉ እንደተሰጠው ተናግሯል፡፡ የእግዚአብሔር አንድያ ልጅና ወራሽ ባይኾን ኖሮ አብ እንዴት በሰማይና በምድር ሥልጣንን ኹሉ ይሰጠው ነበር? የጥምቀቱ ደግሞ ከኹሉም በላቀ ኹኔታ አምላክነቱን ይገልጣል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የእግዚአብሔር ስም ባሕርዩን ይወክላል (ዘጸ 33፡17-23፣ 34፡5-7)፡፡ የእግዚአብሔርን ስም ማመስገን ማለት እግዚአብሔርን ማመስገን ማለት ነው (መዝ 7፡17)፡፡ የእግዚአብሔር ስም ረዳታችን እንደሆነ መናገር እግዚአብሔር ረዳታችን እንደሆነ መናገር ነው (መዝ. 124፡8፣ 121፡2)፡፡ በእግዚአብሔር ስም መምጣት ማለት በእግዚአብሔር ኃይል መምጣት ማለት ነው (1ሳሙኤል 17፡45፣ ዮሐንስ 5፡43)፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔርና ስሙ አይነጣጠሉም፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀት የገዛ ስሙ ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ እኩል እንዲጠቀስ በማዘዝ አንድ ስም እንዳላቸው ግልፅ አድርጓል፡፡ ይህም ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በባሕርይም ሆነ በአገዛዝ አንድ መኾኑን ያሳያል፡፡ ማንም ፍጡር እንዲህ ዓይነት ነገር ቢናገር በእውነተኛው አምላክ ላይ ክህደትን መፈፀም በመኾኑ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ አሁንም በዚሁ ስፍራ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ ሁል ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር እንደሚሆን በመናገር በኹሉም ቦታ መገኘቱን አስታውቋል፡፡ በእርግጥ በኹሉ ቦታ መገኘት መቻሉን ሲናገር ይህ ለመጀመርያ ጊዜ አይደለም (ማቴ 18፡20 ይመልከቱ)፡፡ ማንም ሰው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ሥልጣን ከአብ መቀበል በዚህ አውድ ውስጥ በማንበብ መረዳት ያስፈልገዋል እንጂ ከአውዱ ገንጥሎ በማውጣት የተለየ ትርጉም መስጠት የለበትም፡፡
ድንግል ሆይ የሚወዱሽ የተወደዱ ናቸው፡፡
ንግስት ሆይ የሚያከብሩሽ የከበሩ ናቸው፡፡ ንጽሕት ሆይ የሚቀድሱሽ ሁሉ የተቀደሱ ናቸው፡፡
ፍሥሕት ሆይ የሚመርቁሽ የተመረቁ ናቸው፡፡
ልዕልት ሆይ የሚያደንቁሽ የተደነቁ ናቸው፡፡ ውድስት ሆይ ለንግሥትነትሽ የሚገዙ ሁሉ የተባረኩ ናቸው፡፡
አሁንም ከስንፍና እንቅልፍ እንንቃ፡፡ የልጅሽ የወዳጅሽን ምሥጋና በሚያስቀር በክቡድ እንቅልፍ እንደ በድን አንሁን፡፡
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
አርጋኖን ዘሠሉስ