ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ። ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ›› ት.ኢሳ 58÷3 https://youtu.be/csxxAMGtC4I ለመቀላቀል http://t.me/ortodoxtewahedo
AntGPT Automatic Quantitative Trading Platform
🔥 Project Launched on October 28!
Join this stable platform for a rare opportunity to earn 100% profits! Invite friends to boost your income and enjoy high returns.
✅Registration Gift: 8 USDT
✅Minimum Deposit: 10USDT
✅Minimum Withdrawal: 1USDT
✅Withdrawal Time: Withdraw daily, with funds credited in 2 minutes.
Fees and Commissions (Automatic)
VIP1: 5% (Minimum: $10 or invite 2 VIP1 members)
VIP2: 5.5% (Minimum: $500 or invite 10 VIP1 members)
VIP3: 6% (Minimum: $4,000 or invite 20 VIP1 members)
Team Commissions (Automatic)
Level 1: 10%
Level 2: 5%
Level 3: 4%
Level 4: 3%
Join now and seize this earning opportunity!
If you are interested, feel free to contact me
If you are interested, feel free to contact me
If you are interested, feel free to contact me
Hello Yodit, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡
እመቤቴ! የሞቱ መታሰቢያ፤ የስሙ ምልክት የተጻፈብሽ፤ ከሚያበራ የባሕርይ እንቊ የጠራሽ የራስ ወርቅ ክበብ ነሽ፤
የአበባ ጉንጉን የተሣለብሽየጊዮርጊስ የመንግሥቱ ዘውድ ማርያም ሆይ!! አንቺ ሁሉን ታሰግጂለታለሽ እሱ ግን ለአንቺ ይሰግዳል።
💐ወረብ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘየኃቱ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/
አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ መንግሥቱ ለመፍቀሬ አምላክ/፪/
ዚቅ
አክሊል ዘእምጳዝዮን ተደለወ :ጌራ ባሕርይ ወቀጸላ ወርቅ ጽሩይ በቤተልሔም ተወልደ እምድንግል በብሥራትክሙ መሐይምናን እምአፈ ዮሐንስ ሥርግው ተቀሰመ አፈው ሰባኬ ወንጌል ነዋ በማዕከለ አኃው
ጳዝዮን ከተባለ ዕንቁ አክሊል ተዘጋጀ፤ ባሕርይ ከተባለ ዕንቁ የራስ ቁር ፣ የጠራ የወርቅ ዘውድም ከድንግል በአማኞች ብሥራት በቤተልሔም ተወለደ፤ ካጌጠ ዮሐንስ አፍ ሽቱ ተቀሰመ በወንድሞች መሃል የወንጌል ሰባኪ እነሆ።
🌹ማኅሌተ ጽጌ፦🌹
ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር፤ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር፤ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር፤አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር፤ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር፡፡
ንጹሕ ተአምርሽ እንደ ብር ገንቦ ጌጥ ፣ የነጭና የቀይ ኅብረት መልክ ባለው ወርቅ አምሳል የተዘጋጀ ነው እነሆ ማኅሌተ ጽጌ የተባለ ያማረና የተወደደ ምስጋና ተፈጸመ፤ የሰማይና የምድር ንግሥት ሆይ ተወዳጅ ልጅሽ በእቅፍሽ እንዳለ ይህንን ምስጋና አሳርጊ።
💐ወረብ
ናሁ ተፈጸመ ተፈጸመ ናሁ ማኀሌተ ጽጌ ሥሙር ተፈጸመ ናሁ/፪/
አስምኪ ቦቱ አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት/፪/
ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ጥቀ አዳም መላትሕኪ ከመ ማዕነቅ ይግበሩ ለኪ
ኰሰኰሰ ወርቅ፡፡
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ጉንጭሽ እንደ ከበረ ሉል በጣም ያማረ ነው የወርቅ ገንቦን ያሠሩልሻል
🍂ሰቆቃወ ድንግል🍂
ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፤ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፤በላዕሌኪ አልቦ እንተ ያመጽእ ሁከተ፤ለወልድኪ ዘየኃሥሦ ይእዜሰ ሞተ፤በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ፡፡
እመቤቴ ማርያም ሆይ ቤት እንደ ሌለሽ በግብጽ አትዘግዪ ወደ ሃገርሽ ናዝሬት ተመለሽ ፤ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራትን እንደ ነገረው በአንቺ ላይ ሁከትን የሚያመጣው የለም ልጅሽንም የሚፈልገው እነሆ ሞቷል።
💐ወረብ
ተመየጢ ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ/፪/
ወኢትጎንድዪ በግብፅ በግብፅ ከመ ዘአልብኪ ቤተ/፪/
ዚቅ
ተመየጢ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት ወንርአይ ብኪ ሰላመ፤ምንተኑ ትኔጽሩ በእንተ ሰላመ ሰጣዊት፤እንተ ትሔውጽ እምርኁቅ ከመ መድበለ ማኅበር፤ሑረታቲሃ ዘበሥን ለወለተ አሚናዳብ።
ሱላማጢስ (ሰላምን ሰጪዋ) ሆይ ተመለሽ ተመልሽ ፤ በአንቺም ሰላምን እናይ ዘንድ ተመለሽ በሱላማጢስ ምን ታያላችሁ እርሷ እንደ መሃናይም መዝሙር ከእሩቅ ትጎበኛለች ፤ የአሚናዳብ ልጅ ጉዞዋ ያማረ ነው።
መዝሙር ፦
በ፮ ሃሌታ-
ክርስቶስ ሠርዓ ሰንበት፤ክርስቶስ ሠርዓ ሰንበት ወጸገወነ ዕረፍት ከመ ንትፌሳሕ ኅቡረ።አዕፃዳተ ወይን ጸገዩ ቀንሞስ ፈረየ፤ማ- ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ፤ከመ አሐዱ እምእሉ
ክርስቶስ ሰንበትን ሠራ፤ ክርስቶስ ሰንበትን ሠራ በኅብረት እንደሰት ዘንድም ዕረፍትን ሰጠን። የወይን ፈርጆች አበቡ ቀንሞስ ሽቱም አፈራ፡ (በኅብረት)፦ ከእነዚህ እንደ አንዱ ሰሎሞን እንኳን አለበሰም።
አመላለስ፦
ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ/፪/
ከመ አሐዱ እምእሉ/፬/
🌹🌹🌹ናሁ ተፈጸመ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር🌹🌹🌹
የመጨረሻ ማኅሌት ነው፤ ኹላችንም ተገኝተን እናመስግን።
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
Hello Fetsume, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…🕊
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ †
† ጥቅምት ፴ [ 30 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት †
🕊 † ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ † 🕊
በዚሕች ዕለት ከ፸፪ ቱ አርድእት አንዱ የሆነ: ወንጌላዊ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ዘአንበሳና ርዕሰ ሊቃነ ዻዻሳት የተባለ ቅዱስ ማርቆስ ተወልዷል ::
ቅዱስ ማርቆስ እናቱ ማርያም: አባቱ አርስጥቦሎስ ይባላሉ:: በልጅነቱ ኦሪትንና የዘመኑን ጥበብ ሥጋዊ በሚገባ ተምሮ ክርስቶስን ከቤተሰቦቹ ጋር ተከትሏል:: የመጀመሪያ ስሙ ዮሐንስ ሲሆን ከ፻፳ው ቤተሰብ በእድሜ በጣም ትንሹ /፳ ዓመት/ እርሱ ነበር::
ለ፫ ዓመታት ከጌታ እግር ሥር ተምሮ: በበዓለ ሃምሳ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ብዙ ደክሟል:: በተለይ የግብፅና የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን አባት ነው:: ክህነትን ያገኘን ከርሱ ነውና::
ቅዱስ ማርቆስ ፲፮ ምዕራፍ ያለውን ወንጌሉን ሲጽፍ ኪሩብ ገጸ አንበሳ በቀኙ: ሊቀ ሐዋርያት በግራው ሆነው ይራዱት ነበር:: ቅዱሱ ክቅዱስ ዻውሎስ: ከበርናባስና ዼጥሮስ ጋር ተጉዟል:: ከብዙ ስቃይና መከራ በኋላ ሰሜን አፍሪካ አካባቢ አረማውያን ገድለውታል:: ይህቺ ዕለት የልደቱ መታሠቢያ ናት::
ዳግመኛ በዚህ ቀን የቅዱስ ማርቆስን ወላጆችን እናስባቸው ዘንድ ይገባል:: ቅዱስ አርስጥቦሎስ [አባቱ] የጌታ ቅን አገልጋይ የነበረ: ቅድስት ማርያም [እናቱ] ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ: ጌታችንን ያገለገለች ቤቷን ለሐዋርያትና ለጌታ በስጦታ ያበረከተች ቅድስት ናት::
ቤቷም [ጽርሐ ጽዮን] የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ስትሆን ይህች ቤት መንፈስ ቅዱስ ወርዶባታል:: የእመቤታችን ግንዘትም ተከናውኖባታል::
እግዚአብሔር ከሐዋርያዊው ቅዱስ ቤተሰብ በረከትን ያድለን::
🕊 † ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ † 🕊
ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: [ሉቃ.፩፥፮]
የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ [አድናቆት] ይገባል!
እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ ፺ የዘካርያስ ፻ ደግሞ ደርሶ ነበር::
ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት [ኢሳ.፵፥፫, ሚል.፫፥፩] ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::
ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም ፳፮ ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ፮ ወራት ራሷን ሠወረች:: በ፮ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::
የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ [ሰገደ]:: ከዚህ በኋላ በዚህች ቀን [ሰኔ ፴] ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::
ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ ፪ ዓመት ከ፮ ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ::
እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ፫ [፭] ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ ፭ [፯] ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው ቀበሯት::
ሕጻኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ ድንግል ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ::
ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በኋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ፳፭ [፳፫] ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም::
ከዚህ በኋላ ፴ ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጀን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: [ኢሳ.፵፥፫, ሚል.፫፥፩] አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" [ሉቃ.፩፥፸፮] ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና::
ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና::
ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሃ ሰበከ: ለንስሃም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ፮ ወራት ቆይቶ ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነልብሱ የያዘ ፈጣሪ 'አጥምቀኝ' ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው::
"እንቢ ጌታየ! አንተ አጥምቀኝ" አለው:: ጌታ ግን "ፈቅጄልሃለሁ" አለው: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ ዛሬም "መጥምቀ መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ ለ፯ ቀናት አሠረው::
በዚህች ቀንም ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: [ማቴ.፫፥፩, ማር.፮፥፲፬, ሉቃ.፫፥፩, ዮሐ.፩፥፮]
ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በኋላ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት ጌታችን ወዳለበት ደብረ ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች:: ቅዱሳን ሐዋርያት በአዩት ነገር ተገርመው ራሱን እጅ ነሷት::
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
🗣 ልሣነ ተዋሕዶ 🗣
✍ አሥርቱ_ትዕዛዛት
👉 ወዳጆቼ እስቲ ዛሬ ከአሥርቱ ትዕዛዛት ውስጥ የሚገርመኝን አንድ እውነታ ልንገራችሁ። አስተውላችሁ ከሆነ ሁሉም ትዕዛዛት የተነገሩት በነጠላ (ለአንድ ሰው) ብቻ ነው። 'አድርግ ወይም አታድርግ!" ተብለው።
👉 ሙሴ ከተራራው ላይ አሥርቱን ትዕዛዛት ይዞ የወረደው በመቶ ሺ ለሚቆጠሩት እስራኤላውያን ቢሆንም ትእዛዙ ግን እንደብዛታቸው አታምልኩ ፣ አትስረቁ ፣ በሐሰት አትማሉ እያለ የሚናገር አልነበረም፡፡ አሥሩም አድርግና አታድርግ በሚሉ በነጠላ ትዕዛዝና ሕግ የተሞሉ ናቸው፡፡
👉 ስለዚህ ልክ መስረቅ ሲያምርህ 'ሀገሩ ሁሉ እየሰረቀ ነው እኔ ብቻዬን ምን ለውጥ አመጣለሁ? ጊዜው የሌብነት ነው!' ብለህ አትጽናና እግዚአብሔር 'አትስረቅ' እንጂ አትስረቁ አላለም፡፡ ሀገሩ ሁሉ ይስረቅ አንተ ግን 'አትስረቅ' ተብለህ የታዘዝከው ለብቻህ ነው ፤ የሚጠይቅህም ለብቻህ ነው፡፡ ማመንዘር በእኔ አልተጀመረ የማያመነዝር ማን አለ? ብለህ ለኃጢአትህ መጽናኛዎችን አታፈላልግ፡፡ 'አታመንዝር' ያለው ለአንተ ለብቻህ ነው፡፡ በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር ያለውም ላንተ ነው፡፡ 'የሥራዬ ጸባይ ነው ሥራዬ መዋሸት ይጠይቃል' ብለህ ሐሰትህን የኑሮ መግፊያ ስልት አታድርገው ብዙዎች በሐሰት ቢመሰክሩም አንተ ግን አትመስክር፡፡ ሁሉም መስክሮ እኔ ብቀር ምን ለውጥ ያመጣል? ብለህ ተስፋ አትቁረጥ፡፡ 'ብዙ ናቸው ብለህ ከክፉዎች ጋር አትተባበር' ፈጣሪህ ያዘዘህ ለብቻህ ነው ምክንያቱም የጋራ ኩነኔና የጋራ ጽድቅ የለም፡፡
👉 ጌታችን እንዲህ ይላል ፦ 'እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ' /ራእ. 22÷12/
ለቻናሉ አዲስ የሆናችሁ ክርስቲያኖች 𝕛𝕠𝕚𝕟 እያላችሁ ቤተሰብ ሁኑ
👇👇👇👇👇👇👇
@Lisanetewahido
@Lisanetewahido
@Lisanetewahido
Hello Marye asmamaw, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…bezih samint le 3 ken biye subaye gebau....keza be 2gna kenu jemiro ye kegn ayine eyetergebegeb aschegeregn ...mn ladirg bilachiu beteseboche????
Читать полностью…Hello Ëphãä, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…አህያና ግርዛት
አሁን ሐዲስ ኪዳን ነው:: መገረዝ ግዴታ አይደለም:: ዋናው ጥምቀት ነው:: ባንገረዝ ምንም አይጎድልብንም:: በዚህ ጉዳይ በመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ውዝግብ ተነሣ:: አሕዛብ ሳይገረዙ ኖረዋልና ጸረ ግዝረት ሆኑ:: አይሁድ ደግሞ እንዴት ግዝረት እንተዋለን አሉ::
ወደ ክርስትና የተጠሩት እነዚህ ሁለት ወገኖች ሁለቱም ከራሳቸው አመጣጥ አንጻር እውነት አላቸው:: አሕዛብ የማያውቁትን ነገር መቀበል ሊገደዱ አይችሉም:: ክርስትናም አላስገደዳቸውም:: አይሁድ ደግሞ የኖሩበትን መተው አይችሉም:: ክርስትናም ግዝረትን ባይጠይቅም አልከለከለም::
በመጨረሻ በብዙ ምክር የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን አሕዛብንም ያላገለለ እስራኤልንም ያላቃለለ ውሳኔ ወሰነች:: ውሳኔውን በጥሩ ቃል በመልእክቱ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ሲል ገልጾታል::
“ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ፡፡ ... እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት እንደዚሁ ይኑር" 1 ቆሮንቶስ 7:18፣ 20
በዚህ መሠረት ኦሪትን ተቀብለው ተገርዘው ወደ ክርስትና የተጠሩት እስራኤል በመገረዛቸው ይቀጥሉ እንጂ ወደ አለመገረዝ አይመለሱ ተባለላቸው:: ሳይገረዙ የተጠሩት አሕዛብ ግን መገረዝ የእነርሱ ልማድ አልነበረምና አይገረዙ ተባለ:: ይህ ለእስራኤል የተወሰነ ውሳኔም እንደ ኢትዮጵያ ኦሪትን ተቀብላ ለኖረችና ተገርዛ ሳለ የተጠራች (ሐውልቶችዋ ሳይቀር የተገረዘ ወንድን የሚያሳዩባት) ሀገርም ላይ ይጸናል::
ይህ ውሳኔ ለሁሉም እንደ ግዝረት ያሉ ሕግጋት ይሠራል::
“ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ”
"ማንም አህያ እየበላ ተጠርቶ እንደ ሆነ አህያ ወዳለመብላት አይመለስ ፤ ማንም አህያ ሳይበላ ተጠርቶ እንደሆነም አህያ አይብላ"
እስራኤል በግዝረት ቀጥሉ ሲባሉ ደስ አላቸው አሕዛብም አትገረዙ ሲባል ደስ አላቸው:: ለእስራኤል ሔደህ የአሕዛብን ዜና ብትነግራቸው ምንም እንኩዋን ግዝረት ግድ ባይሆንም ቅር ይላቸዋል:: የአህያ መበላት ዜናም የሚያስደስተው አህያን እንዴት ልንተው እንችላለን ብለው ለተጨነቁ አሕዛብ ብቻ እንጂ ለእኛ ሆድ የሚበጠብጥ ዜና ነው::
ከዚያ ውጪ እንደ ክርስቲያን ብሉ ብለን ልንሰብከው የሚገባን የሕይወት እንጀራ ሥጋ ወደሙ ብቻ ነው::
እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት ይኑር!
ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ቄራ(የበሬ)
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
Hello 😎ONE LO❤️ES, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…Hello ፌብሮንያ, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…Hello Gentle man, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…ለችግረኛ እና ለምስኪን የሚያስብ እሱ ምስጉን ነው
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
Hello Samrawit, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…በሰላም ንዒ
========
በሰላም ንዒ
ንዒ ማርያም/2/
አ.ዝ----------------//
ትናዝዘኒ/2/ ኃዘነ ልብየ
አ.ዝ------------------------//
ምስለ ሚካኤል/2/ ወገብርኤል
አ.ዝ-----------------------//
ምስለ ሱራፌል /2/ ወኪሩቤል
አ.ዝ--------------//
ምስለ ዑራኤል/2/ ወሩፋኤል
አ.ዝ-----------------------//
ምስለ ኩሎሙ/2/ ቅዱሳን
አ.ዝ-------------------------//
ምስለ ወልድኪ/2/ አማኑኤል
ዘሳድሳይ ሣምንት ጽጌ(ተፈጸመ) ወበዓለ ልደታ ወራጉኤል ሊቀ መላእክት ሥርዓተ ማኅሌት (የስድስተኛ ሳምንት ጽጌ ፣ የልደታና የሊቀ መላእክት ራጉኤል በዓል ማኅሌት)
ነግሥ
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
አቤቱ ጽሎቴን ስማኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ጩኸቴም ከፊትህ ይድረስ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ፊትህንም ከእኔ ላይ አታዙርብኝ በጭንቀቴ ዕለት ጆሮዎችህ ያድምጡኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ በጠራሁህ ዕለት ፈጥነህ ስማኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለዘላለሙ ሃሌ ሉያ
ይህም ማለት፡ በልዕልናው ያለውን እግዚአብሔርን እናመስነው ፣ ዓለምን በአንዲት ቃል የመሠረተ እርሱ ፈጽሞ ምስጉን ነው።
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለአፉክሙ ዘማዕፆሁ ሰላም፤ጽጌያቲሁ ሥላሴ ለተዋሕዶ ገዳም፤መንገለ አሐዱ አምላክ ንዋየ መጻኢ ዓለም፤ወልጡ አምልኮትየ በጸጋክሙ ፍጹም፤እምአምልኮ ጣዖት ግሉፍ አሐዱ ድርህም።
" አብ ወልድ መንፈስቅዱስ ሆይ የሰላም መድረክ ለኾነ መለኮታዊ አፋችሁ ሰላምታ ይባል ለተዋሕዶ ሃይማኖት ዱር አበባው ጌጡ ናቸው ሥሉስ ቅዱስ ሆይ በአንድ ከተቀረጸ የጣዖት አምልኮት በፍጹም ቸርነታችሁ በሚመጣው ዓለም ገንዘብ ወደ እውነተኛው አምላክ አምልኮቴን ለውጡልኝ"
ዚቅ፦
አሠርገወ ገዳማት ሥን በመንክር ኪን አርአያሁ ዘገብረ ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ በኩሉ ክብሩ ከመ እሎን ጽጌያት ኢቀደምት ወኢደኃርት :ዓራዛተ ሰርጎ ነሢኦሙ ኢክህሉ ከመ ክርስቶስ መዊአ።
ምድረ በዳውን በድንቅ ጥበቡ ውበትን አስጌጠ፤ በእርሱ የተመሰለው ሰሎሞን እንኳን እንደነዚህ አበቦች አለበሰም ከርሱ በፊትም የለበሰ የለም ወደፊትም አይለበስም፤ ልብሶቹን እንኳን ወስደው ክርስቶስ እንዳሸነፈው ማሸነፍ አይችሉም።
መልክአ ሥላሴ (ሌላ)፤
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ በህላዌ አካል ትክክል ለሚሆኑ ኩልያቶቻችሁ ሰላምታ ይገባል። ሥሉስ ቅዱስ ሆይ፤ ከእናንተ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል እግዚአብሔር ቃል ይቅርታ ለማድረግ ዓለምን በጎበኘ ጊዜ የአባቶች ተስፋ በድንግል ማርያም፣ ተፈጸመ። የነፃነት ዓርማ መስቀልም በቀራንዮ አደባባይ ተተከለ።
ዚቅ፦
እምሥርወ ዕሤይ ሠሪፃ ዘእምዘርዓ ዳዊት ተወሊዳ ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ድንግል ሳይዳ ከመ ፍሥሖ ቀይሕ ከናፍሪሃ ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ድንግል ሳይዳ ወከመ ሮማን መላትሒሃ ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ድንግል ሳይዳ ኅብስተ ሕይወት በየማና ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ድንግል ሳይዳ ወጽዋዓ ወይን በጸጋማ ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ድንግል ሳይዳ ጸሎታ ወበረከታ ይኩነነ ወልታ።
ከእሴይ ሥር ሠርፃ ከዳዊት ዘርም ተወልዳ ድንግል በምሕረት ነፍሴ እግዚአብሔርን ታላቅ ታደርገዋለች ትላለች፤ ከንፈሮቿ እንደ ሚያስደስት ቀይ ነው፤ ድንግል በምሕረት ነፍሴ እግዚአብሔርን ታላቅ ታደርገዋለች ትላለች ጉንጮቿ እንደ ሮማን ናቸው ድንግል በምሕረት ነፍሴ እግዚአብሔርን ታላቅ ታደርገዋለች ትላለች፤ የሕይወት እንጀራ በቀኟ ነው ድንግል በምሕረት ነፍሴ እግዚአብሔርን ታላቅ ታደርገዋለች ትላለች፤ የወይን ጽዋም በግራዋ ነው ድንግል በምሕረት ነፍሴ እግዚአብሔርን ታላቅ ታደርገዋለች ትላለች፤ ጸሎቷና በረከቷ ጋሻ ይኹነን።
🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹
ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ሥዕልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ፤ዘኢየኃልቅ ስብሐተኪ እንዘ እሴብሐኪ ጥቀ፤ተአምርኪ ማርያም ከመ አጠየቀ፤ጸውዖ ስምኪ ያነሥእ ዘወድቀ፤ኃጥአኒ ይሬሲ ጻድቀ፡፡
በማያልቅ ምስጋናሽ አብዝቼ ሳመሰግንሽ፤ ዘመነ ጽጌ ቢያልቅም በሥዕልሽ ፊት መቆምን አላፍርም፤ ማርያም ሆይ ተአምርሽ እንደሚያስረዳው፤ ስም አጠራርሽ የወደቀውን ያስነሣል፤ ኃጢአተኛውንም ጻድቅ ያደርጋል።
💐ወረብ
ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ሥዕልኪ ወርኃ ጽጌ ረዳ አመ ኃለቀ/፪/
ዘኢየኃልቅ ስብሐተ ስብሐተ እንዘ እሴብሐኪ/፪/
ዚቅ
እለትነብሩ ተንሥኡ ወእለ ታረምሙ አውሥኡ፤ማርያምሃ በቃለ ስብሐት ጸውዑ፤ቁሙ ወአጽምዑ ተአምረ ድንግል ከመ ትስምዑ፤ጸልዩ ቅድመ ሥዕላ ለቅድስት ድንግል ፤መርዓተ አብ ወእመ በግዑ፡፡
የተቀመጣችሁ ተነሡ ዝም ያላችሁም ተናገሩ ፤ ማርያምን በምስጋና ቃል ጥሯት ፤ የድንግልን ተአምር ትሰሙ ዘንድ ቆማችሁም አድምጡ ፤ የቅድስት ድንግል ሥዕል ፊት ጸልዩ ፤ የአብ ሙሽራ የበጉ እናት ናትና።
💐ወረብ
እለ ትነብሩ ተንሥኡ ወእለ ተረምሙ አውስዑ ማርያምሃ በቃለ ስብሐት ጸውኡ/፪/
ጸልዩ ቅድመ ሥዕላ ለቅድስት ድንግል እመ በግዕ ወመርዓተ አብ/፪/
🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹
ለንጉሠ ነገሥት ሰሎሞን ከመ ተፈሥሐ ልቡ፤በዕለተ ወፃእኪ መርዓት ለአንበሳ ትንቢት እምግቡ፤ማዕከለ ማኅበር ፍሡሓን ተአምረኪ ዘይነቡ፤እዜምር ለኪ ጽጌ ሐና ወፍኖተ ነፈርዓፅ እሌቡ፤ከመ ጣዕዋ ሐሊበ ዘይጠቡ።
ሙሽሪት ሆይ ከትንቢት አንበሳ ጉድጓድ በወጣሽ ቀን፤ የነገሥታት ንጉሥ የሰሎሞን ልብ እንደተደሰተ፤
የሐና አበባ ሆይ በደስተኞች ማኅበር መካከል፤ ተአምርሽን እየተናገርኩ አመሰግንሻለሁ፤
እንደሚጠባ እንቦሳም በማስተዋል ጐዳና እዘላለሁ።
💐ወረብ
እዜምር ለኪ ጽጌ ሐና ወፍኖተ ነፈርዓፅ እሌቡ ፍኖተ ነፈርዓፅ/፪/
ማዕከለ ማኅበር እዜምር ማዕከለ ማኅበር/፪/
ዚቅ
ሰሎሞን ይቤላ ለማርያም፤ወለተ ሐና ወኢያቄም፤ ጽጌ ደመና ዘብርሃን።
ሰሎሞን ማርያምን የሐናና የኢያቄም ልጅ ሆይ ብርሃናማ የደመና አበባ ነሽ ይላታል።
ዓዲ ዚቅ፦
ወትወፅእ እምግበበ አናብስት ፤ እምታዕካ ዘነገሥት እምቅድመ ሃይማኖት ፤ንዒ ርግብ ሠናይት፤ኵለንታኪ ሠናይት አልብኪ ነውር ፤ወኢምንትኒ ላዕሌኪ፤ንዒ ርግብ ሠናይት፤ንዒ ርግብየ።
ከአንበሶች ጉድጓድ፣ ከነገሥታት አዳራሽ ከሃይማኖት ፊት ይወጣለች፤ መልካሟ ርግብ ሆይ ነይ ኹለንተናሽ መልካም ነው ባንቺ ላይ አንድም እንኳን ነውር የለብሽም ፤ መልካሟ ርግቤ ሆይ ነይ ፤ ርግቤ ሆይ ነይ።
🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፣ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ ፡፡
በመንጻት ወራት፣ በተአምርም ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ስትገቢ፤ ነጭ እና ቀይ አበባ የሚባል ልጅሽን ታቅፈሽ፤ ከኀዘኔ ታረጋጊኝ ዘንድ ርግቤ ሆይ ነይ፤ መልካም እናቴ ሆይ ደስ የሚል ዜና ከያዘ ከገብርኤልና፤ እንደ አንቺ ርኅሩኅ ከሆነ ከሚካኤልም ጋራ ነይ።
💐ወረብ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/
ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ሚካኤል/፪/
ዚቅ
ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ወልድኪ ፍቁርኪ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትባርኪ ላዕሌነ
ድንግል ሆይ ከተወዳጁ ልጅሽ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ትባርኪን ዘንድ ወደ እኔ ነይ።
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
ከዚሕ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት:: በመላው ዓለም ለ፲፭ ዓመታት ስትሰብክ ኑራ ዓረቢያ ውስጥ ዓርፋለች::
ይህች ዕለት ለቅዱሱ 'አስተርዕዮተ ርዕሱ' ወይም ቅድስት ራሱ ከተወረችበት የተገለጠችበት ነው::
🕊
ጥቅምት ፴ [ 30 ]ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩. ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ
፪. ቅዱስ አርስጥቦሎስ [አባቱ]
፫. ቅድስት ማርያም [እናቱ]
፬. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
፭. አባ አብርሃም ገዳማዊ
፮. ቅዱስ ይስሐቅ ንጉሥ
ወርኃዊ በዓላት
፩. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
፪. ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
፫. አባ ሣሉሲ ጻድቅ
" ... እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ:: ዼጥሮስም የደጁን መዝጊያ ባንኳኳ ጊዜ ሮዴ የሚሏት አንዲት አገልጋይ ትሰማ ዘንድ ቀረበች:: የዼጥሮስ ድምጽ መሆኑንም ባወቀች ጊዜ ከደስታዋ የተነሳ ደጁን አልከፈተችም:: ነገር ግን ወደ ውስጥ ሮጣ ዼጥሮስ በደጅ ፊት ቆሞ እንዳለ አወራች::" [ሐዋ.፲፪፥፲፪-፲፭]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
፠ተፈፀመ ማህሌተ ጽጌ
(የማህሌተ ፅጌ ፍፃሜ)
"የህፃኑን ነፍስ የሚሹ ሙተዋልና ተነስተህ ህፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል ሀገር ሂድ!"ማቴ ፪፥፳
፨ምነው የሞተ አንድ ሄሮድስ ሁኖ ሳለ "ሙተዋልና"ብሎ አበዛ ?ቢሉ
፩)እረኛው ከተመታ መንጋው እንደሚበተን ሁሉ አድራጊ ፈጣሪና የምክር ጋን የሆነው ሄሮድስ ከሞተ መንጋው ሀይል የለውምና "ሙተዋልና"ብሎ አብዝቶ ተናገረ።
፪)በ3 ዓመት ከመንፈቅ የስደት ወቅት ብዙ አላውያን(የሄሮድስ ተከታዪች)ሞተው ነበርና አብዝቶ ተናገረ።
፨እናም የተዋህዶ ልጆችና የድንግል ወዳጆች "ሊምረው የወደደውን የእናቱን ፍቅር ያሳድርበታል" ነውና ከእናትም እናት የአምላክ እናት ድንግል ማርያምን የስደቷ ጊዜ ማለቁንና መፈፀሙን እያሰብን"ምስለ ሚካኤል ወገብርኤል ንዒ ሰናይትየ ማርያም፤ንዒ ንዒ ንዒ(2) እመአምላክ ነዒ ማርያም"እያልን በዝማሬና በይባቤ እናታችንን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተሰባስበን እንድንቀበላት ይሁን!
፨ወዲህም እናት የሌለው ነውና ዘለአለም የሚያለቅሰው ከለቅሶና ከዋይታ እናርፍ ዘንድ ድንግልን እንቀበላት ወዳጄ!!
፠ድንግል...........
ስለ አማላጅነትሽ......እናቴ
ስለ ንግስትነትሽ......እመቤቴ እልሻለሁ!
(አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
ጥቅምት 30 ልደቱ ለወንጌላዊ ሐዋርያ #ቅዱስ_ማርቆስ ዘአንበሳ
“ሰላም ለማርቆስ ለማርያም ዕጓላ ዘሰሐብዎ በአሕባል ውስተ ዐጸደ ላሕም ከመ ዳቤላ አመ አውዕዮቶ ፈቀዱ ለእሳት በነበልባላ ዝናም ወአስሐትያ አጥፍዑ ማዕበላ መብረቅኒ ለሥጋሁ ከለላ”
(በላም በረት ውስጥ እንደ ወይፈን በገመድ የሳቡት ለኾነ ለማርያም ልጅ ለማርቆስ ሰላምታ ይገባል፤ ርሱን በእሳቲቱ ላንቃ (ወላፈን) ለማቃጠል በወደዱ ጊዜ ውርጭ እና ዝናብ ማዕበሏን አጠፉ፤ መብረቅም ሥጋውን ጋረዳት)
[ሊቁ አርከ ሥሉስ]
“ሰላም ለማርቆስ ዜናዊ ወንጌለ ጽድቅ ሰባኪ ለእለ በግብጽ ኖላዊ”፡፡
(በግብጽ ላሉ ምእመናን ጠባቂን ለኾነ የጽድቅ ወንጌልን የሚያስተምር ለኾነው ለባለምሥራቹ ለማርቆስ ሰላምታ ይገባል) [ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን]
የቅዱስ ማርቆስ በረከት በኹላችን ዐድሮ ይኑር፨
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
ሱባኤሽን ሳትጨርሺ እንድትወጪ ሰይጣን ያመጣው ፈተና ነው፤ ሳትጨርሺ እንዳትወጪ!
Читать полностью…Hello Wubishet, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…🗣 ልሣነ ተዋሕዶ 🗣
⛪️ አህያና ግርዛት
✍ ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ እንደጻፈው
✍ አሁን ሐዲስ ኪዳን ነው:: መገረዝ ግዴታ አይደለም:: ዋናው ጥምቀት ነው:: ባንገረዝ ምንም አይጎድልብንም:: በዚህ ጉዳይ በመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ውዝግብ ተነሣ:: አሕዛብ ሳይገረዙ ኖረዋልና ጸረ ግዝረት ሆኑ:: አይሁድ ደግሞ እንዴት ግዝረት እንተዋለን አሉ::
✍ ወደ ክርስትና የተጠሩት እነዚህ ሁለት ወገኖች ሁለቱም ከራሳቸው አመጣጥ አንጻር እውነት አላቸው:: አሕዛብ የማያውቁትን ነገር መቀበል ሊገደዱ አይችሉም:: ክርስትናም አላስገደዳቸውም:: አይሁድ ደግሞ የኖሩበትን መተው አይችሉም:: ክርስትናም ግዝረትን ባይጠይቅም አልከለከለም::
✍ በመጨረሻ በብዙ ምክር የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን አሕዛብንም ያላገለለ እስራኤልንም ያላቃለለ ውሳኔ ወሰነች:: ውሳኔውን በጥሩ ቃል በመልእክቱ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ሲል ገልጾታል::
👉 “ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ፡፡ ... እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት እንደዚሁ ይኑር" 1 ቆሮንቶስ 7:18፣ 20
✍ በዚህ መሠረት ኦሪትን ተቀብለው ተገርዘው ወደ ክርስትና የተጠሩት እስራኤል በመገረዛቸው ይቀጥሉ እንጂ ወደ አለመገረዝ አይመለሱ ተባለላቸው:: ሳይገረዙ የተጠሩት አሕዛብ ግን መገረዝ የእነርሱ ልማድ አልነበረምና አይገረዙ ተባለ:: ይህ ለእስራኤል የተወሰነ ውሳኔም እንደ ኢትዮጵያ ኦሪትን ተቀብላ ለኖረችና ተገርዛ ሳለ የተጠራች (ሐውልቶችዋ ሳይቀር የተገረዘ ወንድን የሚያሳዩባት) ሀገርም ላይ ይጸናል::
✍ ይህ ውሳኔ ለሁሉም እንደ ግዝረት ያሉ ሕግጋት ይሠራል::
👉 “ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ”
👉 "ማንም አህያ እየበላ ተጠርቶ እንደ ሆነ አህያ ወዳለመብላት አይመለስ ፤ ማንም አህያ ሳይበላ ተጠርቶ እንደሆነም አህያ አይብላ"
✍ እስራኤል በግዝረት ቀጥሉ ሲባሉ ደስ አላቸው አሕዛብም አትገረዙ ሲባል ደስ አላቸው:: ለእስራኤል ሔደህ የአሕዛብን ዜና ብትነግራቸው ምንም እንኩዋን ግዝረት ግድ ባይሆንም ቅር ይላቸዋል:: የአህያ መበላት ዜናም የሚያስደስተው አህያን እንዴት ልንተው እንችላለን ብለው ለተጨነቁ አሕዛብ ብቻ እንጂ ለእኛ ሆድ የሚበጠብጥ ዜና ነው::
✍ ከዚያ ውጪ እንደ ክርስቲያን ብሉ ብለን ልንሰብከው የሚገባን የሕይወት እንጀራ ሥጋ ወደሙ ብቻ ነው::
🙏 እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት ይኑር!
ለቻናሉ አዲስ የሆናችሁ ክርስቲያኖች 𝕛𝕠𝕚𝕟 እያላችሁ ቤተሰብ ሁኑ
@Lisanetewahido
@Lisanetewahido
@Lisanetewahido
እዚህ Group ላይ add አድርጉ
እስከ ነገ በዚህ ሰዓት Add ያደረገው ተመርጦ ይሸለማል አሁን ጀምሩ❗
Link in bio
ቀልድ አድለም ገብታችሁ ተመልከቱ ❗
OLD GROUP እየገዛው ነው።
2018
2019
2020
2021
2022
በተመጣጣኝ ዋጋ እንገዛሌን
አናግሩኝ👉@Diroro12
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥቅምት ፳፱ (29) ቀን።
✝ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_ኤርትራ_አገር የሚገኘውን #ገዳመ_ደብረ_ኣንገብ ለመሰረቱት እንደ ሙሽራው #ቅዱስ_ገብረ_ክርስቶስ መናኔ መንግሥት ወብእሲት ለሆኑት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ዕንቈ_ብርሃን ለዕረፍታቸው እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ #የአቡነ_ዕንቈ_ብርሃንን፦ ገድላቸውን በሰፊው ማግኘት ባንችልም ከኤርትራ አባቶች ያገኘነው ማስታወሻ እንደሚናገረው ጻድቁ የንጉሥ ልጅ ናቸው። የአባታቸውን ንግሥና ንቀው ዓለምን ከነግሳንግሷ እንደትቢያ ቆጥረው በመተው በረኀብ በጥም በጾም በጸሎት በታላቅ ተጋድሎ መኖርን ስለመረጡ እንደሙሽራው ገብረ ክርስቶስ መናኔ መንግሥት ወብእሲት ናቸው።
አቡነ ዕንቈ ብርሃን በምንኩስና #እግዚአብሔርን ለማገልገል ከአባታቸው ቤተ መንሥት ወጥተው ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ሔደው ገዳም ገብተው ትምህርተ ሃይማኖትን ተማሩ። በገዳም ውስጥ አባቶችን በጉልበት ሥራ እያገለገሉ በትምህርታቸውም ብሉይንና ሐዲስን እንዲሁም የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢር ሁሉ አጠናቀው ተማሩ። ከዚኸም በኋላ የገዳሙ አበ ምኔት አባታችንን "ስምህ ማን ይባላል? ሲሏቸው አባታችንም ስማቸው ዕንቈ ብርሃን እንደሚባል ነገሯቸው። አበ ምኔቱም "በእኛ ዘንድ እንደ ደማቅ ብርሃን ደምቀህ አብርተሃልና ከዚኽም በኋላ እንደ ድሮው ስምህ ዕንቈ ብርሃን ይባል፣ አማን በአማን ዕንቈ ብርሃን ነህ" አሏቸው። አቡነ ዕንቈ ብርሃን ከመነኰሱ በኋላ በገድል ላይ ገድል በመጨመር በታላቅ ተጋድሎ ኖሩ። እርሳቸውም በነበሩበት አካባቢ በጣዖት አምልኮ ውስጥ የነበሩትን ብዙ ሰዎች የከበረች ወንጌልን አስተምረው #ክርስቶስን ወደማመን መለሷቸው።
ከዚኽም በኋላ አቡነ ዕንቈ ብርሃን በ16ኛው መ.ክ.ዘ ወደ ኤርትራ በመምጣት ልዩ ስሙ "ደብረ ኣንገብ ደቂ ሻሓይ" በሚባል ቦታ ተቀመጡ፣ ይኸም ቦታ ከአስመራ 30 ኪሜ ርቀት ላይ በምዕራብ ዞን ጋሽ ባርካ በንዑስ ዞን ሎጎ ዓንሰባ ላይ ይገኛል። አቡነ ዕንቈ ብርሃን በዚኸ ቦታ ላይ ብዙዎች ቅዱሳንን አስተምረው ከብቃት ደረጃ ያደረሱና በምንኲስና በርካታ ቅዱሳን የወለዱ አንጋፋ አባት ናቸው። ከልጆቻቸውም ውስጥ የፀዓዳ ዓምባው ታላቁ ጻድቅ አቡነ ሰይፈ ሚካኤል አንዱ ናቸው።
ጻድቁ በገዳማቸው በደብረ ኣንገብ ውስጥ በርካታ ተኣምራትን በማድረግ የሚታወቁ ሲሆን ምድርን ባርከው ያፈለቁት ፈዋሽ ጠበል በርካታ ሕሙማንን እየፈወሰ ይገኛል። ዳግመኛም ለሰውም ለእንስሳትም የሚሆን ውኃን አፈለቁ።
የአቡነ ዕንቈ ብርሃን የዕረፍታቸው ጊዜ ሲደርስ #ጌታችን_መድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከእልፍ አእላፍ ቅዱሳን መላእክቱ ጋር ተገለጠላቸውና "ስምህን የጠሩትን፣ ዝክርህን የዘከሩትን ደብርህን ያነጹትን፣ ገድልህን የጻፉትንና ያነበቡትን የሰሙትን ሁሉንም እምርልሃለሁ" የሚል ታላቅ የምሕረት ቃልኪዳን ገባላቸው። ከዚኽም በኋላ የጸሎት በኣታቸው ተከፈተችና አባታችንም እዚያው ሲያርፉ ከሰማይ ብርሃን ወረደላቸው፤ ወዲያውም በኣታቸው እንደቀድሞው ተዘጋች።
ከአቡነ ዕንቈ ብርሃን ዕረፍት በኋላም ገዳማቸው ለብዙ ባሕታውያን መኖሪያ ሆነ። እንዲሁም በግራኝ አህመድ የ15 ዓመት የመከራ ዘመን ወቅትም ለ79 ታቦታትና ለበርካታ ቅዱሳት መጻሕፍት መሠወሪያ (መሽሽጊያ) ቦታ ሆኖ አገልግሏል። የመከራውም ዘመን ካለፈ በኋላ ታቦታቱ ወጥተው ለተለያዩ ገዳማትና አድባራት ተሰጡ። አሁን ላይ ግን በዚህ ታሪካዊ ገዳም ውስጥ የሚኖሩት መነኰሳት ጥቂት ከመሆናቸውም በላይ ገዳሙ እየተዳከመ ስለሆነ መነኰሳቱ የገዳሙን ክብር ለመጠበቅ ብዙ እየደከሙ ይገኛሉ። የአቡነ ዕንቈ ብርሃን የዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል ጥቅምት 29 ቀን በገዳማቸው ደብረ ኣንገብ በታላቅ ድምቀት ይከበራል። #ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን ለዘላለሙ አሜን!!!
ምንጭ፦ በእንተ ኅሩይ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ።
Hello Akrem, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete Username(ID) ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️