ortodoxtewahedoo | Unsorted

Telegram-канал ortodoxtewahedoo - ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

3754

ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ። ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ›› ት.ኢሳ 58÷3 https://youtu.be/csxxAMGtC4I ለመቀላቀል http://t.me/ortodoxtewahedo

Subscribe to a channel

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ደብረ ቁስቋም

ኅዳር ፮ ቀን የአርያም ንግሥት፣ የፍጥረታት ሁሉ እመቤት፣ የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ አረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍንና ቅድስት ሰሎሜን አስከትላ ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት የስደት እና የመከራ ዓመታት በኋላ በስተደቡብ የምትገኘው ደብረ ቁስቋም ላይ ያረፉችበት ዕለት ይከበራል፡፡

ደብረ ቁስቋም በደቡብ ግብጽ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ይህ ተራራ የተቀደሰ ተራራ ስለመሆኑ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ታኦፊሎጎስ በድርሳነ ማርያም ‹‹ይህም ከሀገሮቹ ሁሉ ተራሮች የሚበልጥ (የተለየ) ከፍ ያለ ተራራ ነው፡፡ በውስጡ ቅዱስ አግዚአብሔር ያድራል፡፡ ይህንን ተራራ የእግዚአብሔር ልጅ ወዶታል፤ አክብሮታልምና፤ ከዓለም ሀገሮች ሁሉ ከተቀደሰች እናቱ ጋር አድሮባታልና፡፡ ከመላእክት ቤት ያድር ዘንድ አልወደደም፤ ቢታንያንም አልመረጠም፡፡ ከተራራው ላይ ባለች ገዳም ቤት ውስጥ አደረ እንጂ፤ ነቢዩ ዳዊት የጽዮንን ተራራ ወደደ፤ በአርያምም መቅደሱን ሠራ እንዳለ፡፡››

በቅዱስ ወንጌል እንደ ተጻፈ ሄሮድስ ክርስቶስን ለመግደል በፈለገ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለአረጋዊው ዮሴፍ በሕልሙ ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ›› ባለው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ (ማቴ. ፪፥፲፫-፲፭)

በስደቱም ጣዖታተ ግብጽ እየተሰባበሩ ሲወድቁ፤ በእነርሱም አድረው ሰውን ሲያስቱ የነበሩ አጋንንትም ሲሸሹ ታይተዋል፤ ደግሞም ጌታችን ዳግማዊ አዳም ነውና በምክረ ከይሲ (ዲያብሎስ) ምክንያት ተሰዶ የነበረው ቀዳማዊ አዳምን ለመካስ ተሰደደ፤ በዚህም አጋንንትን ከሰው ልቡና አውጥቶ አሳደደ፡፡

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Berhanu, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

የእወነት ኦርቶዶክሥ መሪ ካጣች ሠንብታለች ገዳማት እየወደሙ ተከታዮቿ በግፍ እየተረሸኑ ግን ጥቅማቸውን የሚጎዳ ነገር ሲመጣ ፐአባቶች ተብዬዎቹ የሥብሰባ ጥሪ ያውጃሉ በበራሣቸው ሙድ እንጂ ህዝበ ክርስትያኑን ካገለሉት ቆይቷል እርሥ በርሥም እንዳይተማመን አድርገውታል😢

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

የጴጥሮስ ጥላ የጳውሎስ ሰበኑ እመቤቴ ሆይ ቀራጩ ማቴዎስ ወንጌላዊ ተብሎ የተጠራው፣ ዐሣ አጥማጆቹ ወንድማማቾች ሰውን ወደ ማጥመድ የተለወጡት፣ ገበሬው ታዴዎስ፣ አትክልተኛው በርተሎሜዎስ ለዚህ መዐርግ የበቁት ባንች ነው። ሿሚውን ወለድሽላቸው፤ ታሪካቸውን የሚለውጠውን ወደ ዓለም አመጣሽላቸው። በእኛ ዘንድ ግን ነገሮች ሁሉ ተገለባብጠውብናል። ዓሣ አስጋሪ የነበሩት እነዚያ ወንድማማቾችም እንደገና መረብና መርከባቸውን ይዘው ወደ ገሊላ ባሕር ገብተዋል። ማቴዎስም ወደ ቀራጭነቱ ተመልሷል፤ ታዴዎስም ወንጌልን በገበሬ ዘር መስሎ ያስተምረናል ብለን ስንጠብቅ ዘር ወደ መዝራት ተመልሶ ዘሩን እየዘራ ነው።

በርተሎሜዎሶቻችንም ሰውን ተክለው ያጸድቁታል ብለን ተስፋ ስናደርግ ሰፊ እርሻ ከመንግሥት ተቀብለው አትክልት እየተከሉ እንደሆነ ሰማን እንግዲህ በዚህ ሰዓት የቀረን ብቸኛ ተስፋ ያንች መመለስ ነውና ርግቢቱ ሆይ! እባክሽ ተመየጢ?

ከመጣሽማ እንኳን ሰዎች መላእክት ይወርዳሉ። “ወሰላም በምድር” የሚለው ቅዳሴአችንም እውነት ይሆንልናል። ከመጣሽማ አባ ሕርያቆስም ለከንቱ ውዳሴ ሳይሆን በማብዛት ያይደለ በማሳነስ፤ በማስረዘም ያይደለ በማሳጠር ምስጋናሽን ያቀርባል። አድማጭ ሲኖር ዜማ የሚያስረዝሙ አድማጭ እንደሌለ ካወቁ ምስጋናሽን አስታጉለው የሚወጡ እነዚህን አናገኛቸውም ነበር።

ከመጣሽልንማ እንዚራ ስብሐቱን፣ አርጋኖኑን፣ ሰዓታቱን፣ ኆኅተ ብርሃኑን፣ ማኅሌተ ጽጌውን፣ አንቀጸ ብርሃኑን በስምሽ የሚደርሱልሽ አዲሶቹ አባ ጊዮርጊሶች፣ ቅዱስ ያሬዶች ይነሡልን ነበር። ይሄው አዲስ ድርሰት አዲስ ምስጋና የሚያሰማን አጥተን ስንት ጊዜ ሆነን። የዳዊት የሰሎሞን ርግብ ድንግል ማርያም ሆይ ተመየጢ ተመየጢ? እናይሽ ዘንድ ተመለሺ::

ማስታወሻ:- ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello ታነች ልደታ, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ማኅሌተ ጽጌን የደረሱት አባት ማን ናቸው?

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

እንጦጦ መንበረ ንግስት ቁስቋም ማርያም አዲስ አበባ ።

እንኳን ለእናታችን ለደብረ ቁስቋም ዓመታዊ በዓል በሰላም በጤና አደረሰን!

ዮም ጸለሉ መላእክት ላዕለ ማርያም ወላዕለ ወልዳ
ክርስቶስ በደብረ ቁስቋም(2)
እንዘይብሉ ስብሐት ስብሐት በአርያም ስብሐት በአርያም(2)

#ትርጉም

ዛሬ መላእክት በማርያምና በልጇ በክርስቶስ ላይ በደብረ
ቁስቋም ጸለሉ እንደዚህ አሉ ምስጋና በሰማይ ።

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ከዐራቱ ወንጌላውያን በስዕሉ ላይ አንበሳ ከጎኑ ሆኖ የሚሳለው ማን ነው❓

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Ѕαмяαωιт, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

በሴቶች አውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ...

ባርሴሎና 7-0 ፖልተን
ጁቬንቱስ 0-4 አርሰናል

@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ቃ ል (በወንድም Enoch Ignatius)

ትውልድ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ተመልከቱ።” (ኤር. 2፥31)

ቃል ከልብ የሚመነጭ፥ በአፍ የሚወጣ፥ የፈቃድ መፈጸሚያ፥ ትርጉም ያለው፥ ለሰዎች የሚታወቅ የድምጽ ፍሬ ነው። ሰው በቃሉ (በንግግሩ) ማንነቱ ይታወቃል። ከቃሉም የተነሣ ይፈረድበታል ወይም ይጸድቃል። ወንጌላዊው ማቴዎስ ይህንን ሀሳብ ሲያፀናልን እንዲህ ይላል፤ “ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ።” (ማቴ. 12፥37) ሰው በእግዚአብሔር አምሳል እንደ መፈጠሩ መጠን ቃልን ከእግዚአብሔር አግኝቷል። እግዚአብሔር ቃል አለውና። ይኸውም ዓለምን የፈጠረው በቃሉ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። “ይሁን” ሲል ሁሉ ይሆናል፥ ሆኗልም።

በዓለማችን ላይ እጅግ ብዙ ድምጾች አሉ - ከመብረቅ ነጎድጓድ አንስቶ እስከ ትንሿ ሹክሹክታ ድረስ። ከእነዚህ ሁሉ ድምጾች የሚበልጥ ግን አንድ ታላቅ የሆነ ድምጽ አለ። ይህም የአምላካችን የእግዚአብሔር የቃሉ ድምፅ ነው። ይህ ቃል ሕይወት ነው፥ ይህ ቃል ወተት ነው፥ ይህ ቃል እሳት ነው፥ ይህ ቃል ዳግም ምንወለድበት ነው።

የሰው ልጅ ምግበ ሥጋ ካላገኘ መኖር እንደማይችል ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ካልሰማም ደግሞ በመንፈሱ ይሞታል። ስለዚህ እኛ የሰው ልጆች የእግዚአብሔርን ቃል ልንሰማ፥ ልንመገብ ይገባናል።

በሌላ በኩል የእግዚአብሔር ቃል በውስጡ የሌለ ሰው የዲያቢሎስ ወዳጅ፥ የዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መጨረሻው የዘላለም ሞት ነው የሚሆነው። ስለዚህ ለእለት እንጀራችን ጠዋት ወጥተን ማታ እንደምንገባ ለነፍሳችን ምግብ ለሆነው ለእግዚአብሔር ቃልም ጊዜ ልንሰጠውና ልንሰማ ያስፈልጋል። “ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።” (ማቴ. 6፥33)

የእግዚአብሔር ቃል ሕግም ትዕዛዝም ነው። መፅሐፍ ቅዱስ ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል የያዘ የሕይወታችን ካርታ ነው። መርከበኛ በባሕር ላይ ሲጓዝ ካርታውን እያየ ወዴት እንደሚሄድ ይመራበታል፤ በፊቱ የሚያጋጥመውን መሰናክል ሁሉ አስቀድሞ ስለሚያሳየው አቅጣጫውን ያስተካክልበታል። እንደዚሁ ሁሉ ቅዱስ መፅሐፍም ሕይወታችንን የምንመራበት በኑሮአችን የሚገጥመንን ፈተና በብቃት የምንወጣበት፥ መድረሻችንም ተስፋይቱ ኢየሩስአሌም ሰማያዊት እንደሆነች የምናይበት የእግዚአብሔር ቃል ያለበት መጽሐፍ ነው።

የመናፍቃንን ምላስ፥ የአሕዛብን ሰይፍ የምንመክተው በእግዚአብሔር ቃል ነው። አንድም ነፍሳችንን ከክህደት፥ ሥጋችንን ከጉዳት የምንቀብቀው በእግዚአብሔር ቃል ነው። “... በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው” እንዲል (ኤፌ. 6፥16-17)

መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ቃል አለማወቅ ስህተት ላይ ይጥላል። አለማወቅ ጌታን ያሰቅላል፤ እምነት ያስታል፤ ወደ ሞት ያደርሳል። አይሁድ በትልቁ የተሳሳቱት ባለማወቃቸው ነው።“አውቀውስ ቢሆኑ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉትም ነበር።” (1ኛ ቆሮ. 2፥8) እንደዚሁ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመልዕልተ መስቀል ሳለ አለማወቃቸውን ሲገልፅ “አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” ብሎ ተናግሯል። (ሉቃ. 23፥34)

በእግዚአብሔር ቃል አብርሐም ጣኦትን ትቶ፥ ያዕቆብ የጣዖት አማልዕክትን ቀብሮ፥ ማቴዎስ የቀረጥ ስራውን ትቶ፥ ጴጥሮስ መረቡን ጥሎ በተሰበረና በአዲስ ልብ እግዚአብሔርን ፈልገውታል እርሱም በቃሉ አስተማራቸው፥ በቃሉም አናገራቸው። እነርሱም የእግዚአብሔር ቃል በማዳመጣቸው ለዘላለማዊ ክብር በቅተዋል።

🛑በመጨረሻም ወዳጆች ሆይ እያወቅን በሔድን ቁጥር አለማወቅ ምን እንደሆነ እናውቃለንና የእግዚአብሔርን ቃል ለማወቅ እለት እለት የተጋን እንሁን!!!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello šęb §ë ĵ, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello ኢትዮ, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Tebareku abo yefetari fekad yhunlin ledeje selamu yabkan 🙏🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ለትርፍ ጊዜ ስራ ፈላጊዎችና ስራ ለሌላቸው የወጣ የስራ ማስታወቂያ
ካምፓኒያችን በተለያዩ ትላልቅ የክልል ከተሞችና በተለያዩ በአዲስ አበባ ቅርጫፎች ከፍቷል ከተሰማራንበት የስራ ዘርፍ በተጨማሪም ሆነ እንደ ዋና ስራ አድርገን ሰርተን ገቢ የምናገኝበትና በእውነትም ለውጥ ማምጣት ለሚፈልጉ የስራ እድል አቅርቧል በመሆኑም፦
1. በግልም ሆነ በመንግስት ተቋማት ተቀጥራችሁ የምትሰሩ፣
2. የግላችሁን ስራ የምትሰሩ
3.  ከዩኒቨርስቲ ተመርቃችሁ ስራ ያላገኛችሁ
4. 12 ተፈትናችሁ ነጥብ የመጣላችሁም ሆናችሁ ያልመጣላችሁ
ሰርታችሁ ተጨማሪ ዳጎስ ያለ ገቢ የምታገኙበት የስራ ዘርፍ ስለሆነ ማንኛውም ሰው መስራት የሚፈልግ ሙሉ ስም፣ የመኖሪያ አድራሻና ስልክ ቁጥር በውስጥ መስመር ያስቀምጥልኝ።.

ለዚህ ሁሉ መልስ እኛጋ ያገኛሉ።
"" ዘ እንበለ ሥጋ ኢትቀውም ነፍስ ""
ከፈለጉ በትርፍ ሰዓት ከፈለጉ በሙሉ ሰዓት የእጅዎን ስልክ እና ፈጣሪ የሰጥዎትን ጭንቅላት ተጠቅመው የሚሰሩት ሥራ ነው
ለበለጠ መረጃ ለማግኘት በውስጥ ያናግሩኝ
 
 
     🧑‍💻 0777235250
0969263876
" እኛ ጋ መጥተው ያለ ሥራ አይመለሱም

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Ymaryam @the slasa, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

👉 🖐🖐🖐ስለ_በዓታ_ለማርያም🖐🖐🖐
የጎፎሬ በዓታ ተአምረኛዋ ድንበሯዋ በመብረቅ የተከለለበት ተመልከች አጥታ በምስጥ ተበልታ ለመውደቅ የተቀረበች
የተዋህዶ ልጆች አለች ከለችሁ ይችን የእመቤቴ ቤተመቅደስ አብረን እንስራ ሼር ሼር እናድረግ

👉 በገጠር ያለችው እናታችን በዓታ ለማርያም ትጣራለች ልጆቼ ድረሱልኝ ቤቴንም ሥሩልኝ ትላለች።

👉 #በከምባታ_ጠምባሮና_ሀላባ_ሀገረ_ስብከት_በጠምባሮ_ልዩ_ወረዳ_ለምትገኘው_የጎፎሬ_ደብረ_መንክራት_በዓታ_ለማርያም_ቤተክርስቲያን።

🤲 #ከ100 ብር ጀምሮ 🤲 🤲 5,000 ሰዎች የቅማችንን ለበዓታ እናታችን ብንረዳ 500,000 ይሆናል መሠረት ሥራው ለማስጀመር ይበቃና
ቦታው ላይ ጥቂት ምዕመናንና አንድ ካህን ብቻ የሚገኙበት በመብረቅ የተካለለችው ተአምራዊቷ የጎፎሬ ደብረ መንክራት በኣታ ለማርያም ቤተ-ክርስቲያን አዲስ ለሚሠራው ህንፃ ቤተክርስቲያን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገረ የምትገኙ ውድ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች ምዕመናንና ምዕመናት እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ የመሠረትና የፖድ ቁፋሮ ተጠናቋል እስከ ታኅሣሥ በኣታ ድረስ የእመቤታችን ቤተ መቅደስ የመሠረት ሥራ ለመጀመር ጥረት እያደረግን እንገኛለን እናንተም የበኣታ ለማርያም ህንፃ ቤተ ክርስቲያን የመሠረት ግንባታ ለማከናወን የበኩላችሁን ድጋፍ እንድታደርግልን በእመቤታችን በድንግል ማርያም ስም እንጠይቃለን።

👉 የየህፃ ሥራው መሠረቱ አስፈላጊ ግብአቶች፦

ፌሮ ብረት    ብዛት   የአንዱ ዋጋ    ድምር
ባለ 8           50        800        40,000
   12            50       1,200        60,000
   14            70         1,600      112,000
   16            50           1,700     119,000
ሲሚንቶ      40 ኩንታል   2,000   80,000
አሸዋ          2 ቢያጆ      30,000   60,000
ጠጠር ባለ 02   2 ቢያጆ     35,000   70,000

ስሆን ጠቅላላ ድምር= 541,000።

👉 ተስፈኞች የቤተ ክርስቲያን አካውንት ቁጥር፦

      1000624326281  ንግድ ባንክ።
      3621111079916110 ዓባይ ባንክ።

👉 ለበለጠ መረጃ ስልክ፦  0933055802   0911414852።

👉 ከበረከቱ የሚትሳተፋ ደረሰኙቹንና ስለ ቤተ ክርስቲያን ሥራ በማኅበረም ሆነ በግለሰብ ለማውራት የምትፈልጉ በሀገር ውስጥና በባሕር ማዶ ያላቹ ምዕመናንና ምዕመናት ከላይ ባሉት ቁጥሮች  በቴሌግራም፣ በኢሞና ዋትሳፕ ላኩልንና አውሩን።

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ተመየጢ ተመየጢ

  ✍ ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ

“አንቺ ሱላማጢስ ሆይ ተመለሽ ተመለሽ፤ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ ተመለሽ” መኃ 7፥1  በኖኅ መርከብ ውስጥ ሆኖ ዐይኖቹ አሻግሮ ማየት የማይፈልግ ማን አለ? ከዚያ ሁሉ ጥፋት በኋላ ምድርን መልሶ ማየት ያጓጓል። ለዐርባ ቀናት ከሰማይ የወረደውና ከምድር የገነፈለው ትኩስ ውኃ የተራሮችን ራስ ሳይቀር የሚገሽር ትኩሳት የነበረው ውኃ ነው።

ማንም ቢሆን ለአንድ መቶ ሃምሳ ቀናት ምድርን ይዟት የቆየውን ውኃ መጉደል አለመጉደሉን በልቡ ማውጣት ማውረዱ አይቀርም። በዚህ መካከል የምድሪቱን ዕጣ ፋንታ ሊያሳውቅ የሚችል ታማኝ መልዕክተኛ ማግኘት እንዴት መታደል ነው? መዓቱ ቆሟል፤ በመርከቧ ውስጥ የሚኖሩት ሁሉ የምድሩን ፊት ማየት ይፈልጋሉ። በዚህ ጊዜ ነው ኖኅ ርግብን ምድሩን አይታ እንድትመለስ የላካት። መጀመሪያ ሄደች ለእግሯ ማረፊያ ስላላገኘች ተመልሳ መጣች፤ ምድሩ በውኃ ተሞልቶ ነበርና። ዳግመኛ ላካት የውኃውን መድረቅ ለማመልከት የወይራ ዝንጣፊ ይዛ ተመለሰች ከሰባት ቀን በኋላ መልሶ ላካት አልተመለሰችም። ኖኅም ምድር ከጥፋት ውኃ ማረፏን በዚህ አወቀና ከመርከቡ ወጣ።

ርግቢቱን ወደ ዓለም ልኮ ኖኀ ከመርከብ ወጣ። ለጥፋት ውኃ መምጣት ምክንያት የሆነው ኃጢአት መጉደሉን የምትናገረዋ ርግብ እመቤታችን እስከትመጣ ድረስ የዚህችኛዋ ርግብ አገልግሎት እስከዚህ ድረስ ስለነበረ ነው − መመለሷን ሳይጠብቅ ከመርከብ የወጣው። የኖኅ ርግብ ሳትመለስ በዚያው መቅረቷ እንደ ቁራ የምድሩ ነገር ስቧት አይደለም፤ እውነተኛው ሰላም የሚሰበክበት፣ የጥፋት ውኃ በሚጎድልበት ሳይሆን የሰው ልጅ ከኃጢአት የሚያርፍበት ዘመን እስኪመጣ ድረስ ርግቢቱ አትመለስም።

ከዚያ በኋላ የተነሡ ነቢያት ይህንን ስለሚያውቁ ነው እንደ ኖኅ ዘመን ከሚበሩት አእዋፍ መካከል የሆነችውን ርግብ ሳይሆን ከሰዎች መካከል አንዷ የሆነችውን ርግብ ተመየጢ ተመየጢ ሲሉ የኖሩት። ከጥፋት ውኃ ሳይሆን ከኃጢአት መውጫ ጊዜው መድረሱን የምታበሥራቸውን ርግብ በሕይወተ ሥጋ መቆየት እስከቻሉበት ዘመን ድረስ ተመየጢ ተመየጢ እያሉ ደጅ ይጠኗታል። ርግቧ ካልተመለሰች ሰላም በምድር ላይ መታወጁን ማን ይናገራል? ቁራም አልተመለሰም። ሌላ መልዕክተኛም አልተገኘም።

መጥቀው ከሚበሩ ንስሮች ይልቅ ለሰላም አብሣሪነት የተመረጠች ይህች ርግብ እንዴት ያለች የተመረጠች ናት? ይህች ርግብ የእመቤታችን ምሳሌ ናት ብለው ሊቃውንት ተርጉመዋል። በሰሎሞን መኃልይ ላይ “ርግቤ መደምደሚያዬ” መኃ 5፥2 ተብላ የተጠራች እመቤታችንን ቅዱስ ኤፍሬም “ተፈሥሒ ኦ ማርያም ርግብ ሠናይት፤ በጎ ርግብ እመቤታችን ደስ ይበልሽ” ብሎ አመስግኗታል። ከዚህ አያይዞ የመልክአ ውዳሴ ደራሲ ደግሞ “ርግበ ገነት ጽባሓዊ፤ በምሥራቅ በኩል የተተከለችው የገነት ርግብ” ብሏታል። ከእመቤታችን ቀድመው ለእናትነት ቀድመው የተመረጡ ብዙ ቢሆኑም የሰላም አለቃ ክርስቶስን ለመውለድ ግን አልተቻላቸውም። በቅድስና የተመረጡ የታወቁ ሴቶችም ነበሩ የእመቤታችንን ያኽል በሰውና በእግዚአብሔር ዘንድ የታመነ የሰላም መልዕክተኛ ግን አልተገኘም።

በምድር ላይ የሚኖር ፍጥረት ሁሉ መምጣቷን እያሰበ ሲናፍቅ ነው የኖረው። በርግጥም በመጣች ጊዜ ክርስቶስን ይዛ በመገኘቷ መላእክት በምድር ላይ ለሚኖሩ ሁሉ “ለግዚአብሔር ምስጋና በሰማይ ይሁን በምድርም ሰላም” ሉቃ 2፥14 እያሉ አዋጅ ነገሩ። ስትጠበቅ የነበረችው የኖኅ ርግብ መጣችና ሰላምን ወለደችልን። ሰላም ከማንም ዘንድ የሆነችለን አይደለም፤ ሰላምን ተወልዳ ነው ያገኘናት ያውም ከሌላ አይደለም − ከእመቤታችን ነው።

ዛሬም የኖኅ ርግብ ሆይ! ተመየጢ ተመየጢ እንላለን።

ምድር እንደዚያን ጊዜው ሁሉ ሰላም የላትም። የሰላም ወሬ ሊያወራን የሚችል ማንም የለም። በያንዳንዱ ቀን ማለዳ መስኮታችንን ከፍተን የጥፋት ውኃ መጉደሉን የሚነግረን ሰው እንፈልጋለን ነገር ግን እስካሁን የነገረን የለምና ርግቢቱ እመቤታችን ሆይ እባክሽ ተመየጢ?

ይሆናል ብለን የላክነው ቁራ የምድርን በሬሳ መሞላት እንደ መልካም ነገር ሆኖለት ፊቱን ወደ እኛ አልመለሰም። ከኛ ጋር በነበረ ጊዜ በፊታችን ላይ ያየውን ጭንቀት ከኛ ተለይቶ ከወጣ በኋላ ረስቶት ሰላሙን ሊያበሥረን ወደኛ መመለስ አልፈለገም። ዛሬም የኛን ተሰብስቦ በአንድ ስፍራ መቀመጥ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ዓለምን እንደፈለገ ብቻውን ከወዲያ ወዲህ ይመላልስባታል። ነገሮችን ሁሉ ለብቻው ሊጠቀምባቸው ወደደ። የመርከቧ ነዋሪዎች ተጨንቀዋልና ርግቢቱ ድንግል ማርያም ሆይ እባክሽ ተመየጢ?

ወይናችን እንዲያፈራ፤ አበባም በምድራችን ላይ እንዲታይ በመርከቧ ውስጥ ያለን እኛ ልጆችሽ ምድርን እንድንወርሳት ሱላማጢስ ሆይ ተመለሽ።

ሔሮድስ ሞቷል፣ አርኬላዎስ ነግሷል አልልሽም፤ እንዳልሞተ ታውቂአለሽ። አርኬላዎስ ብለን የሾምናቸው ሁሉ ሔሮድስ እየሆኑብን ተቸገርን። በኛ ዘመን በዳዊት ዙፋን የሚቀመጥልን፤ በልቡ እግዚአብሔርን መፈለግ ደስ የሚያሰኘው ንጉሥ እንኳን ባናገኝ በሔሮድስ ፋንታ ለይሁዳ የምንሾመው አርኬላዎስ ብንፈልግ አላገኘንም። የሕጻኑን ነፍስ የሚሿት ዛሬም አሉ አልሞቱም ግን ቢሆንም ተመየጢ!

ምድር የሞላት በግፍ የፈሰሰው የገሊላ አውራጃ ሕጻናት ደም ስለቆመ አይደለም ተመየጢ የምንልሽ ግፋችንን እንድታይልን ነው እንጅ። በኛ ዘንድ ስለልጆቿ የምታለቅስ ራሔል አሁንም እያለቀሰች ነው። ለቅሶም በራማ እየተሰማ ነው። ዋይታ በየደጁ አለ። ከሔሮድስ ቃል ተገብቶላቸው በገደሉት ሰው ልክ ሽልማት ሊቀበሉ የወጡት ገና አልተመለሱም። ግን ምን እናድርግ? ሰለ አባታሽ ስለ ኢያቄም፣ ስለ እናትሽ ስለ ሐና ብለሽ እመቤቴ ሆይ ተመየጢ?

ካልተመለስሽማ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ ደራሲ፤ “ወእቀውም ዮም በትሕትና ወበፍቅር” ብሎ የሚቀድስ፤ እንደ ዘካርያስ የሚያጥን፤ እንደ ሙሴ ቅብዐ ክህነት የሚቀባን ካህን ከወዴት እናገኛለን? ስለዚህ ነው ተመየጢ የምንልሽ። እመቤቴ ሆይ! አባቶቻችንን እንደ ጥንቱ የልብሳቸውን ዘርፍ ዳስሰን መፈወስ አምሮናል፤ ጥላውን ሲጥልብን የሚፈውስ ካህን ያስፈልገናል፤ ጋኔን ማውጣትም በገንዘብ ሆነ፥ እኛን ድሆችሽን ከአጋንንት እስራት ማን ነጻ ያውጣን? ተአምራት ማድረግም ትንቢት መናገርም ለግያዝ ሆነ።

ገንዘብ ሳይቀበሉ ከለምጻችን የሚያነጹን እነ ኤልሳዕ ቢፈለጉ አይገኙም። ስለሌሉ ሳይሆን ቅብዝብዝነታችንና ምልክት ፈላጊነታችን ካጠገባችን አርቋቸው ይኸው ባጠገባችን የሉም። ግሩም በሆነው በቊርባኑ ፊት በቆመ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ “ጎሥዐ” ብሎ የሚያመሰግን ካህን ዐይናችን ፈለገ፤ ልባችን ተመኘ፤ ነገር ግን በምስጋና እና በውዳሴ “ጎሥዐ” ማለትን ትተው በልሳነ ሥጋ “ጎሳ” የሚሉት በዝተውብን እየተጨነቅን ነውና ተመየጢ?


#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello ..., welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Jerry, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ህዳር 6

#ቁስቋም ማርያም

"አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ፤እናይሽ ዘንድ ተመለሽ" መኋ 7፥1

ጠቢብ ሶሎሞን እመቤታችንን ከጠራበት ከገለፀበት ቃላት አንዱ ሱላማጢስ የሚል ነው ጠቢብ እንደ ነብይነቱ ስለ ንጽሕናዋ፣ስለ ድንግልናዋ፣ስለ ትህትናዋ..... እንደተናገረ ሁሉ ድንግል ማርያም ፍቅር ያላት ፍቅር በቃል ኪዳኗ አማልዳ የምታሰጥ ሰላማዊት መሆኗን ሲገልፅ ሱላማጢስ ብሏታል።

እመቤታችን ብዙ መከራ ካየችበት ብዙ መከራንም ከተቀበለችበት ከዚያ የግብጽ በረሃ የመመለሷን ነገር ሶሎሞን በትንቢት መነፅርነት ተመልክቶ ተመለሽ ሲላት እንመለከታለን የእመቤታችን የመከራዋ ጊዜ ሲፈፀም የህፃኑን ነፍስ የሚሻው ሄሮርስ በሞተ ግዜ (ማቴ 2፥19)እመቤታችን ከስደት ተመልሳለች።

የእመቤታችን የስደት ወቅት ሊቃውንቱ እንደሚነግሩን 3 አመት ከ6ወር ነው ይህ ግዜ ሲፈፀም ህዳር 6 ድንግል ማርያም ስደቷን ጨርሳ ተመልሳለች የነብዪ ሆሴዕ ቃልም ተፈጽሟል (ሆሴ 11፥1)::

አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሙሉ ሰላም ላጣ ለአዳም ሰላም የሆነች "ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር" ተብሎ እንዲመሰገን ምክንያት የሆነች የሰላም እናት የሰላም እመቤት ድንግል ማርያም (ሱላማጢስ) ከስደት ተመልሳለች።

ዛሬ በኋጥያት ስደት ያለን ብዙዎች ነን የሰራነው ኋጢአት ከእግዚአብሔር ፊት ከቤተክርስቲያን ደጅ ያሰደደን ብዙዎች ነን።

ዛሬ በትዕቢት ልብ ተይዘን ትላንት ካስቀደስንባት፣ከቆረብንባት፣ከቀደስንባት፣ከተማርንባት፣ካስተማርንት ደጅ የተሰደድን ብዙዎች ነን ሚጠታችን መቼ ይሆን።

ከስጋወደሙ የተሰደድን ከልጅነት ግዜያችን በኋላ፣ከትዳራችን በኋላ ከአገልግሎታችን በኋላ ሥጋ ወደሙን መቀበል ያቆምን ከሕይወት ምግብ የተሠደድን ሥጋችን እየደለበ ነፍሳችን ከህይወት ምግብ እጥረት የቀጨጨችብን ሚጠታችን መቼ ይሆን???

ከአገልግሎቱ የተሰደድን ትላንት እንዘምር፣ትላንት እንማር ትላንት እናስተባብር የነበርን አገልጋዮች ዛሬ የት ነን??መመለሳችን መቼ ይሆን??

ወዳጄ በቤተክርስቲያን አለሁ እንጂ ነበርኩ አያድንምና ያለነው የነበርንበት ካልሆነ ወደ ነበርንበት እንመለስ በደልን እንጂ በደለኛን ወደ ማይጠላ አምላክ እንሰደድ የት ነህ ስንባል እዚህ ነኝ ለማለት ከምናፍርበት ቦታ እንዳንገኝ ወደ ደገኛይቱ ቤት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንመለስ።

ፍቅር አንድነት ያላት ፍቅር አንድነት የምታሰጥ ሱላማጢስ ድንግል ማርያም ከኋጥያት ስደት ትመልሰን።

👉ዮም ጸለሉ መላእክት ላዕለ ማርያም ወላዕለ ወልዳ

ክርስቶስ በደብረ ቁስቋም(2)
እንዘይብሉ ስብሐት ስብሐት በአርያም ስብሐት በአርያም(2)

#ትርጉም
ዛሬ መላእክት በማርያምና በልጇ በክርስቶስ ላይ በደብረ
ቁስቋም ጸለሉ እንደዚህ አሉ ምስጋና በሰማይ ።

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Tadesse, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Relationship ወይም ትዳር ውስጥ ላላችሁ ወንዶች መፅሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

1 ሌላ ሴት አትውደድ
  ምሳሌ 5:20
2 ተንከባከባት
   ኤፌሶን 5 : 30
3 አመስግናት
   ምሳሌ 31 : 28
4 ከሷ ሌላ አትይ ይፈረድብሃል
    ዕብራዉያን 13 : 4
5 መራራ አትሁንባት
    ቆላይስያስ 3 : 19
6 እንደገዛ ሰውነትህ ውደዳት
   ኤፌሶን 5 : 28
7 ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን እንደወደዳት ውደዳት
    ኤፌሶን 5 : 25

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Abu❤❤❤, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Time መጽሔት በልዩ እትሙ "የአእላፋት ዝማሬ"ን ምስል አወጣ

| ጃንደረባው ሚድያ | ኅዳር 2017 ዓ.ም. |

በአሜሪካን ሀገር ኒውዮርክ የሚታተመውና ከ1923 ዓ.ም. ጀምሮ ኅትመቱ ያልቆመው 105 ሚልዮን አንባቢያን ባሉት ቁጥር አንዱ "Time” መጽሔት የኢትዮጵያን የገና በዓል በማስመልከት በጻፈበት አንቀጽ የአእላፋት ዝማሬን ከፊል ገጽታ በውስጥ ገጹ ላይ አካትቶአል:: "Jesus” በሚል ዐቢይ ርእስ የታተመው የ2024 ዓ.ም. የመጽሔቱ ልዩ ዕትም ላይ "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በታኅሣሥ 27 (January 6, 2024) በገና ቅዳሴ ላይ ሲካፈሉ በማለት የአእላፋት ዝማሬ ላይ ጧፍ ይዘው እየዘመሩ የነበሩ ምእመናንን ይዞ ወጥቶአል::

"መጽሔቱ የአእላፋት ዝማሬን ገጽታ ይዞ መውጣቱ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የቀረበ የሚታይ ማስታወቂያ መሆኑ ደስ ይለናል" ያሉት የአእላፋት ዝማሬ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ወ/ሮ ቤርሳቤሕ ደረጄ "ሆኖም መጽሔቱ ዝማሬውን "ቅዳሴ ሲያስቀድሱ" ብሎ መግለጹ በቅዳሴ ላይ ምእመናን መብራት ይዘው የሚሳተፉበት ሥርዓት የሌለ ከመሆኑ አንጻር ዘግባውን ያጎድለዋል ብለዋል::

በዘገባው ላይ ታይም መጽሔት "የኢትዮጵያ ስድሳ በመቶ የሚሆን ሕዝብ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ነው" ሲል የገለጸ ሲሆን "ከራሽያ ቀጥሎ የዓለም ትልቁ ኦርቶዶክስ ሕዝብ ቁጥር ያለባት ሀገር ናት" ብሎአል:: በ2024 ጃንዋሪ 6 የተካሔደውን የአእላፋት ዝማሬ በመስቀል አደባባይ እንደተካሔደ አድርጎ ቢገልጸውም በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም የተካሔደ መሆኑ ይታወሳል:: የዘንድሮው የአእላፋት ዝማሬ በመሐረነ አብ ዑደት እና በመዝሙር ጥናት ከጾመ ነቢያት ጋር አብሮ እንደሚጀመር የኢጃት ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ኢየሩሳሌም ዳግማዊት ገልጸዋል::

#የሚከለክለኝ_ምንድር_ነው
#በፍጹም_ልብህ_ብታምን_ተፈቅዶአል

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ቃላት ነው ያጣሁት ሲያልቅ ፎቶውን እፈልገዋለው😍😍😍😍😍😍😍😍

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello ◡̈ great, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello መርጌታ, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Tebarekuln esu medhn alem ybarkachu abo 🙏🙏🙏🙏

Читать полностью…
Subscribe to a channel