#ከአሐቲ ድንግል
ድንግል ማርያም እግዚአብሔር ስለመረጣት ነው ንጽሕት የሆነችው ወይስ ንጽሕት ስለሆነች ነው እግዚአብሔር የመረጣት?
አንዳንዶች ስለ ድንግል መመረጥ ሲነገር ሲሰሙ ሲመርጣት ላትመረጥ ነውን? እርሱ ጠበቃት እንጂ እርስዋ ምን አደረገች ሲሉ ይሰማሉ። እግዚአብሔር ሰለመረጣት ነው ንጽሕት የሆነችው የሚለው አደገኛ ክህደት ነው። ለምን ቢሉ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠውን ነፃ ፈቃድ የሚንድ ነውና። ዳግመኛ እርሷ እግዚአብሔር ስለመረጣት ብቻ ከሆነ ንጽሕት የሆነችው እያንዳንዱ ሰው ንጹሕ የማይሆነው እግዚአብሔር ስላልመረጠው ነው ወደሚል የቅድመ ውሳኔ ክህደት የሚያመራ ጠማማ መንገድ ነው።
እንዲህ ከሆነ ደግሞ በዓለም ላይ ለሚሠሩ የርኩሰትና የአመፅ የበደል ውድቀቶች ሁሉ ተጠያቂው እግዚአብሔር እንጂ ሰው አይደለም ብሎ እግዚአብሔርን መሳደብ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር የመረጠው ብቻ ንጹሕ ከሆነ ሁሉም የመንጻት ሥልጣን ካልተሰጠው በበደለኛነት ዘመናቸውን የፈፀሙ ሰዎች ተጠያቂ መሆን የለባቸውም፤ ከኃጢአት ለመንጻት ቢፈልጉ እንኳን አልተመረጡምና አይችሉም ማለት ነዋ! እንዲህ ከሆነ ሰዎች ሁሉ ሊድኑ እና እውነቱን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ የሚወድ እግዚአብሔር (ጢሞ. ፪፥፫) ፈቃዱ ወዴት አለ? እርሱ የመረጣቸው ብቻ የሚነጹ ከሆነ ባልመረጣቸው ላይ ለምን ይፈርድባቸዋል? ፈታሒ በጽድቅነቱስ ወዴት አለ?
ነገር ግን ርቱዕ የሆነው የሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የቀና የጸና አስተምህሮዋ እንዲህ አይደለም። እግዚአብሔር ሰዎችን ፍጻሜያቸውን አስቀድሞ አይቶ ይመርጣል እንጂ ወስኖ መርጦ የፈጠረው ሰው የለም። በወንጌል የእግዚአብሔር መንግስት በመካከላችሁ ናት ማለቱም ሰው ለመዳን የሚያስችለው ለመምረጥ የሚያበቃው ኃይል በእጁ እንዳለ ሲያጠይቅ ነው። በስሙ ለሚያምኑ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው የተባለውም ለዚህ ነው። በስሙ ለሚያምኑ የተሰጣቸው ስልጣን የተባለው ለመዳንም ላለመዳንም የሰው ነፃ ፈቃድና ልጅነት እንደተሰጠ ሲያስረዳ ነው። እግዚአብሔር ወደ አቤልና ወደ መስዕዋቱ ተመለከተ የተባለውም አቤል የልቡን ቅንነት የመስዕዋቱን መበጀት ስሙርነት አይቶ ተመልክቶ አቤልን ተቀበለው እንጂ አቤል እንዲያ እንዲሆን አድርጎ ወሰኖ መርጦ አልፈጠረውም። በአንፃሩ ወደ ቃየልና መስዕዋቱ አልተመለከተም ማለት የቃየልን የልቡን ጥመት አየና የመስዕዋቱን አለመበጀት አይቶ አልተቀበለውም ነገር ግን እግዚአብሔር ለክፋት ወስኖ አልፈጠረውም። እግዚአብሔር ሲኦል የሚገቡ ሰዎች እንዳሉ አውቆ ሲኦልን አዘጋጀ እንጂ ሲኦል በሚገቡ ሰዎች ላይ አስቀድሞ እንዲገቡ አድርጎ ወስኖ አልፈጠረም።
እናቱ ድንግል ማርያምን ከእናቷ ማሕፀን መርገም እንዳይኖርባት የጠበቃት እርሱ ነው ቅድመ ዓለም የአምላክ እናት እንድትሆን የመረጣትም እርሱ ነው። ነገር ግን ፍፃሜዋን በነፍስ በስጋ በአፍኣ ንጽሕት እንድትሆን አውቆ መረጣት እንጂ እርሱ ሰለወሰነ የጠበቃት የመረጣት አይደለችም። በዘመኗ ሁሉ በቅድስናዋ ተሸልማ እንደምትኖር አውቆ ከመርገም አነጻት፥ ኖሮባት አይደለም እንዳይኖርባት ጠበቃት እንጂ!
መንፈስ ቅዱስ ጠበቃት አነፃት መባሉም ፍፃሜዋን አይቶ መርገም እንዳይኖርባት ጠበቃት ማለት ነው እንጂ በዓለም ኃጢአት እንዳትሰራ ከለከላት ማለት አይደለም። ንጹህ ሆኖ መፈጠርማ አዳምም ተፈጥሮ ነበር በተፈጥሮ የተሰጠውን ንጹህ ጠባይ በቅድስና መጠቀም አልተቻለውም እንጂ እርሷ ግን ንጽሕናን ቅድስናን ደራርባ ይዛ ተገኝታለችና በዛው ድንግልናዋ ለአምላክ እናትነት በቃች። የሕይወት ፍሬን አፈራችበት እንዲመርጣት እግዚአብሔርን የሳበ በአምላክ ዘንድ ሞገስን የያዘ ንጽሕና ይዛ ተገኝታለችና እንድትመረጥ ሆና ተገኝታለች። ንጹሃንን ለክብር መምረጥማ ለፈጣሪ ድንቅ አይደለም ከእርስዋ ይልቅ ጠላቶቹን እኛን በደሙ ፈሳሽነት ይቅር ማለቱ አይደንቅምን?.......(ቀጣዩን መጽሐፉን ገዝተው ያንብቡ)
(ከርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ አሐቲ ድንግል ገፅ 272-277 ላይ የተቀነጨበ)
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
የሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት የአገልግሎት ውጤት አንዱ ይህ ነው።ኅዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በተደረገው 43ኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተክህነት በአመራር ብቃት ፣ ሰብከተ ወንጌልን በማስፋፋት ፣ ሰበካ ጉባኤንና የሰንበት ት/ቤትን በማጠናከር ብሎም የአብነት ት/ቤት ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት በሀገረ ስብከቱ ካሉት ወረዳዎች ሁሉ አንደኛ በመውጣት ላሳየው ከፍተኛ ውጤት የዋንጫ እና የሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆኖአል። እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን የሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተክህነት ሰባክያን ጥምረት በልዩ ሁኔታ አድናቆቱን እየገለጸ በቀጣዩ ከክቡር አባታችን መ/ሰ/ቆሞስ አባ ሠይፈ ገብርኤል ገረመው የሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተክህነት ዋና ሥራ አሥኪያጅ ጎን በመቆም የተሰጠንን የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ኃላፊነት በገጠሪቱ ቤተክርስቲያን በማስፋፋት ሰብከተ ወንጌልን ተደራሽ ለማድረግ ተግተን እንሠራለን አባታችን እንኳን ደስ አልዎት እድሜ እና ጤና አብዝቶ ይስጥልን ።
Читать полностью…#ኅዳር_7
#ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሊቀ_ሰማዕት
ኅዳር ሰባት በዚህችም ቀን የልዳ ሀገር የሆነ የሰማዕታት አለቃ የታላቁ መስተጋድል የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው ዳግመኛም ጌታችን በውስጧ ላደረገው ድንቅ ተአምር መታሰቢያ ሆነ።
ይህም እንዲህ ነው በውስጧ ድንቆች ተአምራት እንደሚሠሩ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ ሊአፈርሳት አሰበ ስሙ አውህዮስ የሚባለውንም መኰንን ከብዙ ሠራዊት ጋር ላከው፤ ያም መኰንን በደረሰ ጊዜ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥዕል ወዳለበት አዳራሽ በትዕቢት ሆኖ ገባ። በሥዕሉም ፊት በብርጭቆ መቅረዝ መብራት ነበረ በቤተ ክርስቲያኒቱና በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ እየዘበተ በእጁ በያዘው በትር የመብራቱን መቅረዝ መትቶ ሰበረው የመቅረዙም ስባሪ ወደ ከሀዱው ራስ ደርሶ መታው ራሱንም ታመመ ፍርሃትና እንቅጥቅጥም መጣበት ወድቆም ተዘረረ ባልንጀሮቹም ወደ አገሩ ሊወስዱት ተሸከሙት በክፉ አሟሟትም ተጐሳቊሎ ሞተ ወስደውም ከባሕር ጣሉት ወገኖቹም ወደ ሀገራቸው አፍረው ተመለሱ።
ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ በልዳ ሀገር ያለች የቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን ያፈርሳት ዘንድ ራሱ ተነሥቶ ሔደ በዚያንም ጊዜ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ መታው ሰባት ዓመት ያህልም ዐይኖቹ ታውረው አእምሮውንም አጥቶ ቁራሽ እንጀራም እየለመነ ኑሮ ሞተ።
ክብር ይግባውና ጌታችንም የቤተ መንግሥቱን ሰዎች አስነሣበት እርሱን አስወግደው ጻድቅ ሰው ቁስጠንጢኖስን በእግዚአብሔር ፈቃድ አነገሡት እርሱም በአዋጅ የጣዖታትን ቤቶች ዘግቶ አብያተ ክርስቲያናትን ከፈተ ለክርስቲያን ወገኖችም በሁሉ ዓለም ተድላ ደስታ ሆነ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘኅዳር)
@ortodoxtewahedo
ሰላም ቤተሰቦቼ እንደምናችው እስኪ የመቤቴን ምስለ አድን ፎቶ በቁምዋ ሆኗ ደም ያለ ያላችው ላኩልኝ ለቤተክርስትያን ለማሳተም ተፈልጎ ነው
Читать полностью…😢😢😢#ልጅ #ቢኒን አንገት #አስደፍተን #ከአገልግሎት #እንድንለየው የፈቀደልን #ማነው? #እኛንስ ምሮን እንጂ መርምሮን ቢሆንስ ንጉሱ ፊት እሚያቆም ስራ ሰርተናል?
ልጅ ቢኒ የት ነው አጠይቁም??
“ሄሮድስም ከሞተ በኋላ፥ እነኾ፥ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ፦ የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘኽ ወደ እስራኤል አገር ሂድ አለ። እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ያዘና ወደ እስራኤል አገር ገባ። በአባቱም በሄሮድስ ፈንታ አርኬላዎስ በይሁዳ እንደ ነገሠ በሰማ ጊዜ፥ ወደዚያ መሄድን ፈራ፤ በሕልምም ተረድቶ ወደ ገሊላ አገር ሄደ።” (ማቴ. 2፥19-22)
“እስከ መቼ ድረስ እመቤቴ በሰው ሀገር ትኖሪያለሽ? ሀገርሽ ገሊላ ግቢ። እናቴ ኾይ ወደ ልቤ ግቢ፤ የእኔም ልብ ወደ ልጅሽ ወደ ወዳጅሽ ሚጠት መመለስን ይፈልጋልና።” - ሰቆቃወ ድንግል
“እስከ መቼ ድረስ እመቤቴ በሰው ሀገር ትኖሪያለሽ? ሀገርሽ ገሊላ ግቢ። እናቴ ኾይ ወደ ልቤ ግቢ፤ የእኔም ልብ ወደ ልጅሽ ወደ ወዳጅሽ ሚጠት መመለስን ይፈልጋልና።”
Читать полностью…በእንተ ቅዱስ ዳዊት - ፪
ኹሉም ፈርተው ባሉበት ሰዓት ዳዊት ለሳኦል ‛እኔ ባሪያኽ ሔጄ ያንን ፍልስጥኤማዊ እወጋዋለኹ አለው።’ ሊከለክለው ሲሞክርም በጎቹን ሲጠብቅ ያጋጥመው የነበረውን ነግሮት ‛ከአንበሳና ከድብ እጅ #ያስጣለኝ_እግዚአብሔር ከዚህ ፍልስጥኤማዊ እጅ ያስጥለኛል አለ። ሳኦልም ዳዊትን፦ ሂድ፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይኾናል አለው።’ ዳዊትም በትር፥ ድንጋይና ወንጭፍ ይዞ ወደጎልያድ ቀረበ። ጎልያድም ‛ዳዊትን፦ ወደ እኔ ና፥ ሥጋኽንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት እሰጣለኹ አለው።’ ዳዊት በትሩንና፥ አምስት ድንጋዮችን አንስቶ ወንጭፉን ታጥቆ ሔደ፤ በአንዲቷ ድንጋይ ግንባሩን ሲለው ያ ግዙፉ ጎልያድ ወደቀ። ዳዊትም በራሱ ሰይፍ አንገቱን ቀላው።
ግን እኛስ እንደዳዊት ያለ እምነት አለን? እስካኹኗ ቅጽበት ድረስ ለኛ 'በጣም አስቸጋሪ ናቸው፥ አናልፋቸውም' ብለን ያሰብናቸውን ፈተናዎች ያሳለፈንን አምላክ አኹን በገጠመን ፈተና እንደረሳን ኾኖ ለምን ይሰማናል? አብረን ከዳዊት ጋር እንዲኽ እንበል፤ “ከአንበሳና ከድብ እጅ ያስጣለኝ እግዚአብሔር ከዚህ ፍልስጥኤማዊ እጅ #ያስጥለኛል!”
‛እንዲኽም ኾነ፤ ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ገድሎ በተመለሰ ጊዜ፥ እየዘመሩና እየዘፈኑ እልልም እያሉ ከበሮና አታሞ ይዘው ንጉሡን ሳኦልን ሊቀበሉ ሴቶች ከእስራኤል ከተሞች ሁሉ ወጡ። ሴቶችም፦ ሳኦል ሺህ፥ ዳዊትም እልፍ ገደለ እያሉ እየተቀባበሉ ይዘፍኑ ነበር።’ ሳኦልም ተቈጣ፤ ‛በነጋውም ሳኦልን ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያዘው፥ በቤቱም ውስጥ ትንቢት ተናገረ። ዳዊትም በየቀኑ ያደርግ እንደ ነበረ በእጁ በገና ይመታ ነበር። ሳኦልም ጦሩን በእጁ ይዞ ነበር። ሳኦልም፦ ዳዊትን ከግንቡ ጋር አጣብቄ እመታዋለኹ ብሎ ጦሩን ወረወረ። ዳዊትም ኹለት ጊዜ ከፊቱ ዘወር አለ። እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ ከሳኦልም #ስለተለየ ሳኦል ዳዊትን #ፈራው።’
‛ሳኦልም፦ ወጥመድ ትሆነው ዘንድ፥ የፍልስጥኤማውያንም እጅ በእርሱ ላይ ትሆን ዘንድ እርስዋን (ሜልኮልን) እድርለታለኹ አለ፤ ሳኦልም ዳዊትን፦ ዛሬ ኹለተኛ አማች ትኾነኛለኽ አለው። … ዳዊትም [ለሳኦል ባሮች]፦ እኔ ድሀ የተጠቃኹም ሰው ስኾን ለንጉሥ አማች እኾን ዘንድ ትንሽ ነገር ይመስላችኋልን? አለ።’ ሳኦልም በፍልስጤማውያን እጅ ሊጥለው አስቦ ማጫ እንዲኾንለት የ100 ፍልስጤማውያንን ሸለፈት እንዲመጣ ነገረው፤ ተዋግቶ አቀረበለት፤ ሜልኮልንም ዳረለት። ‛ሳኦልም እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር እንደኾነ አየ፤ እስራኤልም ኹሉ ወደዱ። ሳኦልም ዳዊትን አጥብቆ ፈራው፤ ሳኦልም ዕድሜውን ኹሉ ለዳዊት ጠላት ኾነ።’
አያችኹ? ቅድም ‛እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ ከሳኦልም ስለ ተለየ ሳኦል ዳዊትን ፈራው’ አለን፤ አኹንም ያንኑ ሐሳብ ደገመው። ወደሕይወታችን እናምጣው። እኛ ከእግዚአብሔር ጋር ከኾንን ጌታችን “ጠላት” ያለው ዲያብሎስ እኛን ከእግዚአብሔር ለመለየት የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም፤ ጸጋው እየረዳን እኛም ከበረታን፥ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ቁርኝት ካጠበቅን ግን ሊያሸንፈን ከቶም አይችልም። እኛ ከእግዚአብሔር ጋር ከኾንን፥ ፈቃዱን ለመፈጸም ከታመን'ለት እርሱም በነገር ኹሉ ሊረዳን ከኛ ጋር ሊኾን የታመነ ነው።
#ይቀጥላል...
የቃል ሳይኾን የተግባር ክርስቲያን ያደርገኝ ዘንድ ታናሽ ወንድማችኹ ገብረ ማርያምን በጸሎታችኹ አስቡኝ።
በእንተ ቅዱስ ዳዊት - ፪

በእንተ ቅዱስ ዳዊት - ፩
በባለፈው ጽሑፍ ስለነቢዩ ሙሴ በጥቂቱም ቢኾን ለማየት ሞክረናል፤ ለዛሬ ደግሞ ስለ ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት እና እኛ ከዳዊት ምን እንደምንማር እንመለከታለን።
ወደንግሥና ከመጠራቱ ጀምረን እንመልከት። ሳኦል እግዚአብሔርን በደለ፤ መጽሐፍ ‛ተጸጸተ’ እስኪል ድረስም አዘነበት። ሳሙኤልም ለሳኦል አለቀሰ፤ ‛እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፦ በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? በቀንድህ ዘይቱን ሞልተኽ ሒድ፤ በልጆቹ መካከል ንጉሥ አዘጋጅቻለኹና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እልክኻለሁ አለው።’
ከእሴይ የተወለዱ ብዙ ልጆች ነበሩ፤ ነገር ግን ልብንና ኩላሊትን በሚመረምረው ፊት ለንግሥና ብቁ አልነበሩምና ‛ሳሙኤል እሴይን፦ እግዚአብሔር እነዚኽን አልመረጠም አለው።’ ሳሙኤልም የቀረ ልጅ እንዳለው ጠየቀው፤ ‛እርሱም፦ ታናሹ ገና ቀርቷል፤ እነሆም፥ በጎችን ይጠብቃል አለ።’ ልኮም አስመጣው። ‛ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ መካከል ቀባው። የእግዚአብሔርም መንፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳዊት ላይ #በኃይል_መጣ።’
እኛ ደግሞ የእግዚአብሔር ኃይል የምንታጠቀው በጥምቀት ካገኘነው የእግዚአብሔር ልጅነት በተጨማሪ ምስጢራትን በመፈጸም ነው - በተለይም ደግሞ #ንስሐ ስንገባና #ቊርባንን ስንቀበል። እኛ ግን መዳኑን እየፈለገ ግን የመዳኑን ቀን እንደሚያራዝም ታማሚ ማድረግ እየፈለግን ለነገ ቀጠሮ እየሰጠን ይበልጥ ኃይላችንን እናሟጥጣለን።
‛የእግዚአብሔርም መንፈስ ከሳኦል ራቀ፥ ክፉም መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ አሠቃየው። ሳኦልም ባሪያዎቹን፦ መልካም አድርጎ በገና መምታት የሚችል ሰው ፈልጋችኹ አምጡልኝ አላቸው።’ ዳዊትን አግኝተው አመጡለት፤ በገናውን ሲደረድርለትም የያዘው ርኵስ መንፈስም ይርቅ ነበር። ሳኦል በነገሠበት ዘመን እስራኤል ከፍልስጤም ጋር ለመዋጋት ተሰልፈው ነበር፤ ፍልስጤማውያኑም አንድ ግዙፍ ሰው መርጠው ይዋጋ ዘንድ ላኩት። እስራኤል ግን ግዝፈቱንና በተናገራቸውን ቃላት ፍርሐት ያዛቸው። *
* [የተቀረውን ታሪክ 1ኛ ሳሙ. 17፥12-36 ላይ አንብቡት።]
#ይቀጥላል...
የጻፍኩትን በሕይወቴ እገልጸው ዘንድ ታናሽ ወንድማችኹ ገብረ ማርያምን በጸሎታችኹ አስቡኝ።

ሀሳብህ ልክ ነው ነገር ግን አባቶች ቢያጠፉ የኛ አፍ በእነሱ ላይ ባይከፈት ጥሩ ነው ብየ አምናለሁ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለሁሉም ሰው መጥፎ ሲሰራ የመገሰፅ ስልጣን የሱ ነውና እና እንደ ኦርቶዶክሳዊ እንጂ ስሜታዊ ሆነን ባንናገር።
Читать полностью…እመቤታችን ቅድስት ማርያም ከጌታችን ኢየሱስ ጋር ከመሰደዷ አስቀድሞ ነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹ወይወርድ እግዚእነ ውስተ ምድረ ግብጽ እንዘ ይጼዐን ዲበ ደመና ቀሊል፤ ጌታችን በፈጣን ደመና (በእመቤታችን ጀርባ) ተጭኖ ወደ ግብጽ ይወርዳል›› ተብሎም በተናገረው መሠረት ትንቢቱ ተፈጽሟል፡፡ (ኢሳ. ፲፱፥፩)
ጌታችን ኢየሱስ በደብረ ቁስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቱን ሰበሰባቸው፤ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንንም አክብሮ የቁርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ሰጥቷቸዋል፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከጌታችን ኢየሱስ ጋር በቁስቋም ተራራ ስድስት ወራትን ያረፈች ሲሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኅዳር ፮ የእነርሱን ስደትና ወደ ሀገራቸው እስራኤል መመለሳቸውን በማስታወስ ታከብራለች፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!!!
ምንጭ፤ ድርሳነ ማርያም (ትርጉም ፳፻፫ ዓ.ም)
ስንክሳር ዘወርኃ ኅዳር
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo