ortodoxtewahedoo | Unsorted

Telegram-канал ortodoxtewahedoo - ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

3754

ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ። ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ›› ት.ኢሳ 58÷3 https://youtu.be/csxxAMGtC4I ለመቀላቀል http://t.me/ortodoxtewahedo

Subscribe to a channel

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

በእንተ ቅዱስ ዳዊት - ፪

ኹሉም ፈርተው ባሉበት ሰዓት ዳዊት ለሳኦል ‛እኔ ባሪያኽ ሔጄ ያንን ፍልስጥኤማዊ እወጋዋለኹ አለው።’ ሊከለክለው ሲሞክርም በጎቹን ሲጠብቅ ያጋጥመው የነበረውን ነግሮት ‛ከአንበሳና ከድብ እጅ #ያስጣለኝ_እግዚአብሔር ከዚህ ፍልስጥኤማዊ እጅ ያስጥለኛል አለ። ሳኦልም ዳዊትን፦ ሂድ፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይኾናል አለው።’ ዳዊትም በትር፥ ድንጋይና ወንጭፍ ይዞ ወደጎልያድ ቀረበ። ጎልያድም ‛ዳዊትን፦ ወደ እኔ ና፥ ሥጋኽንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት እሰጣለኹ አለው።’ ዳዊት በትሩንና፥ አምስት ድንጋዮችን አንስቶ ወንጭፉን ታጥቆ ሔደ፤ በአንዲቷ ድንጋይ ግንባሩን ሲለው ያ ግዙፉ ጎልያድ ወደቀ። ዳዊትም በራሱ ሰይፍ አንገቱን ቀላው።

ግን እኛስ እንደዳዊት ያለ እምነት አለን? እስካኹኗ ቅጽበት ድረስ ለኛ 'በጣም አስቸጋሪ ናቸው፥ አናልፋቸውም' ብለን ያሰብናቸውን ፈተናዎች ያሳለፈንን አምላክ አኹን በገጠመን ፈተና እንደረሳን ኾኖ ለምን ይሰማናል? አብረን ከዳዊት ጋር እንዲኽ እንበል፤ “ከአንበሳና ከድብ እጅ ያስጣለኝ እግዚአብሔር ከዚህ ፍልስጥኤማዊ እጅ #ያስጥለኛል!

‛እንዲኽም ኾነ፤ ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ገድሎ በተመለሰ ጊዜ፥ እየዘመሩና እየዘፈኑ እልልም እያሉ ከበሮና አታሞ ይዘው ንጉሡን ሳኦልን ሊቀበሉ ሴቶች ከእስራኤል ከተሞች ሁሉ ወጡ። ሴቶችም፦ ሳኦል ሺህ፥ ዳዊትም እልፍ ገደለ እያሉ እየተቀባበሉ ይዘፍኑ ነበር።’ ሳኦልም ተቈጣ፤ ‛በነጋውም ሳኦልን ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያዘው፥ በቤቱም ውስጥ ትንቢት ተናገረ። ዳዊትም በየቀኑ ያደርግ እንደ ነበረ በእጁ በገና ይመታ ነበር። ሳኦልም ጦሩን በእጁ ይዞ ነበር። ሳኦልም፦ ዳዊትን ከግንቡ ጋር አጣብቄ እመታዋለኹ ብሎ ጦሩን ወረወረ። ዳዊትም ኹለት ጊዜ ከፊቱ ዘወር አለ። እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ ከሳኦልም #ስለተለየ ሳኦል ዳዊትን #ፈራው

‛ሳኦልም፦ ወጥመድ ትሆነው ዘንድ፥ የፍልስጥኤማውያንም እጅ በእርሱ ላይ ትሆን ዘንድ እርስዋን (ሜልኮልን) እድርለታለኹ አለ፤ ሳኦልም ዳዊትን፦ ዛሬ ኹለተኛ አማች ትኾነኛለኽ አለው። … ዳዊትም [ለሳኦል ባሮች]፦ እኔ ድሀ የተጠቃኹም ሰው ስኾን ለንጉሥ አማች እኾን ዘንድ ትንሽ ነገር ይመስላችኋልን? አለ።’ ሳኦልም በፍልስጤማውያን እጅ ሊጥለው አስቦ ማጫ እንዲኾንለት የ100 ፍልስጤማውያንን ሸለፈት እንዲመጣ ነገረው፤ ተዋግቶ አቀረበለት፤ ሜልኮልንም ዳረለት። ‛ሳኦልም እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር እንደኾነ አየ፤ እስራኤልም ኹሉ ወደዱ። ሳኦልም ዳዊትን አጥብቆ ፈራው፤ ሳኦልም ዕድሜውን ኹሉ ለዳዊት ጠላት ኾነ።

አያችኹ? ቅድም ‛እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ ከሳኦልም ስለ ተለየ ሳኦል ዳዊትን ፈራው’ አለን፤ አኹንም ያንኑ ሐሳብ ደገመው። ወደሕይወታችን እናምጣው። እኛ ከእግዚአብሔር ጋር ከኾንን ጌታችን “ጠላት” ያለው ዲያብሎስ እኛን ከእግዚአብሔር ለመለየት የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም፤ ጸጋው እየረዳን እኛም ከበረታን፥ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ቁርኝት ካጠበቅን ግን ሊያሸንፈን ከቶም አይችልም። እኛ ከእግዚአብሔር ጋር ከኾንን፥ ፈቃዱን ለመፈጸም ከታመን'ለት እርሱም በነገር ኹሉ ሊረዳን ከኛ ጋር ሊኾን የታመነ ነው።

#ይቀጥላል...

የቃል ሳይኾን የተግባር ክርስቲያን ያደርገኝ ዘንድ ታናሽ ወንድማችኹ ገብረ ማርያምን በጸሎታችኹ አስቡኝ።

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ያበሰራት ቅዱስ መላዕክ ማን ይባላል?

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Ayalew, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Hello Ë𝑙𝑜ℎ𝑒☦️, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

በእንተ ቅዱስ ዳዊት - ፩

በባለፈው ጽሑፍ ስለነቢዩ ሙሴ በጥቂቱም ቢኾን ለማየት ሞክረናል፤ ለዛሬ ደግሞ ስለ ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት እና እኛ ከዳዊት ምን እንደምንማር እንመለከታለን።

ወደንግሥና ከመጠራቱ ጀምረን እንመልከት። ሳኦል እግዚአብሔርን በደለ፤ መጽሐፍ ‛ተጸጸተ’ እስኪል ድረስም አዘነበት። ሳሙኤልም ለሳኦል አለቀሰ፤ ‛እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፦ በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? በቀንድህ ዘይቱን ሞልተኽ ሒድ፤ በልጆቹ መካከል ንጉሥ አዘጋጅቻለኹና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እልክኻለሁ አለው።’

ከእሴይ የተወለዱ ብዙ ልጆች ነበሩ፤ ነገር ግን ልብንና ኩላሊትን በሚመረምረው ፊት ለንግሥና ብቁ አልነበሩምና ‛ሳሙኤል እሴይን፦ እግዚአብሔር እነዚኽን አልመረጠም አለው።’ ሳሙኤልም የቀረ ልጅ እንዳለው ጠየቀው፤ ‛እርሱም፦ ታናሹ ገና ቀርቷል፤ እነሆም፥ በጎችን ይጠብቃል አለ።’ ልኮም አስመጣው። ‛ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ መካከል ቀባው። የእግዚአብሔርም መንፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳዊት ላይ #በኃይል_መጣ

እኛ ደግሞ የእግዚአብሔር ኃይል የምንታጠቀው በጥምቀት ካገኘነው የእግዚአብሔር ልጅነት በተጨማሪ ምስጢራትን በመፈጸም ነው - በተለይም ደግሞ #ንስሐ ስንገባና #ቊርባንን ስንቀበል። እኛ ግን መዳኑን እየፈለገ ግን የመዳኑን ቀን እንደሚያራዝም ታማሚ ማድረግ እየፈለግን ለነገ ቀጠሮ እየሰጠን ይበልጥ ኃይላችንን እናሟጥጣለን።

‛የእግዚአብሔርም መንፈስ ከሳኦል ራቀ፥ ክፉም መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ አሠቃየው። ሳኦልም ባሪያዎቹን፦ መልካም አድርጎ በገና መምታት የሚችል ሰው ፈልጋችኹ አምጡልኝ አላቸው።’ ዳዊትን አግኝተው አመጡለት፤ በገናውን ሲደረድርለትም የያዘው ርኵስ መንፈስም ይርቅ ነበር። ሳኦል በነገሠበት ዘመን እስራኤል ከፍልስጤም ጋር ለመዋጋት ተሰልፈው ነበር፤ ፍልስጤማውያኑም አንድ ግዙፍ ሰው መርጠው ይዋጋ ዘንድ ላኩት። እስራኤል ግን ግዝፈቱንና በተናገራቸውን ቃላት ፍርሐት ያዛቸው። *

* [የተቀረውን ታሪክ 1ኛ ሳሙ. 17፥12-36 ላይ አንብቡት።]

#ይቀጥላል...

የጻፍኩትን በሕይወቴ እገልጸው ዘንድ ታናሽ ወንድማችኹ ገብረ ማርያምን በጸሎታችኹ አስቡኝ።

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ልክ እንደዚህ በቁምዋ እግሯ ድረስ የሚታይ ሆኖ ደሞቅ ያላችው

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

💁‍♂እቤቶ ቁጭ ብለው ገንዘብ ማግኘት ይፈልጋሉ ?

ሀሳብህ ልክ ነው ነገር ግን አባቶች ቢያጠፉ የኛ አፍ በእነሱ ላይ ባይከፈት ጥሩ ነው ብየ አምናለሁ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለሁሉም ሰው መጥፎ ሲሰራ የመገሰፅ ስልጣን የሱ ነውና እና እንደ ኦርቶዶክሳዊ እንጂ ስሜታዊ ሆነን ባንናገር።

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Abebech, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

@semetnbegtm
@semetnbegtm
@semetnbegtm

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ከአሐቲ ድንግል

ድንግል ማርያም እግዚአብሔር ስለመረጣት ነው ንጽሕት የሆነችው ወይስ ንጽሕት ስለሆነች ነው እግዚአብሔር የመረጣት?

አንዳንዶች ስለ ድንግል መመረጥ ሲነገር ሲሰሙ ሲመርጣት ላትመረጥ ነውን? እርሱ ጠበቃት እንጂ እርስዋ ምን አደረገች ሲሉ ይሰማሉ። እግዚአብሔር ሰለመረጣት ነው ንጽሕት የሆነችው የሚለው አደገኛ ክህደት ነው። ለምን ቢሉ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠውን ነፃ ፈቃድ የሚንድ ነውና። ዳግመኛ እርሷ እግዚአብሔር ስለመረጣት ብቻ ከሆነ ንጽሕት የሆነችው እያንዳንዱ ሰው ንጹሕ የማይሆነው እግዚአብሔር ስላልመረጠው ነው ወደሚል የቅድመ ውሳኔ ክህደት የሚያመራ ጠማማ መንገድ ነው።

እንዲህ ከሆነ ደግሞ በዓለም ላይ ለሚሠሩ የርኩሰትና የአመፅ የበደል ውድቀቶች ሁሉ ተጠያቂው እግዚአብሔር እንጂ ሰው አይደለም ብሎ እግዚአብሔርን መሳደብ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር የመረጠው ብቻ ንጹሕ ከሆነ ሁሉም የመንጻት ሥልጣን ካልተሰጠው በበደለኛነት ዘመናቸውን የፈፀሙ ሰዎች ተጠያቂ መሆን የለባቸውም፤ ከኃጢአት ለመንጻት ቢፈልጉ እንኳን አልተመረጡምና አይችሉም ማለት ነዋ! እንዲህ ከሆነ ሰዎች ሁሉ ሊድኑ እና እውነቱን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ የሚወድ እግዚአብሔር (ጢሞ. ፪፥፫) ፈቃዱ ወዴት አለ? እርሱ የመረጣቸው ብቻ የሚነጹ ከሆነ ባልመረጣቸው ላይ ለምን ይፈርድባቸዋል? ፈታሒ በጽድቅነቱስ ወዴት አለ?

ነገር ግን ርቱዕ የሆነው የሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የቀና የጸና አስተምህሮዋ እንዲህ አይደለም። እግዚአብሔር ሰዎችን ፍጻሜያቸውን አስቀድሞ አይቶ ይመርጣል እንጂ ወስኖ መርጦ የፈጠረው ሰው የለም። በወንጌል የእግዚአብሔር መንግስት በመካከላችሁ ናት ማለቱም ሰው ለመዳን የሚያስችለው ለመምረጥ የሚያበቃው ኃይል በእጁ እንዳለ ሲያጠይቅ ነው። በስሙ ለሚያምኑ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው የተባለውም ለዚህ ነው። በስሙ ለሚያምኑ የተሰጣቸው ስልጣን የተባለው ለመዳንም ላለመዳንም የሰው ነፃ ፈቃድና ልጅነት እንደተሰጠ ሲያስረዳ ነው። እግዚአብሔር ወደ አቤልና ወደ መስዕዋቱ ተመለከተ የተባለውም አቤል የልቡን ቅንነት የመስዕዋቱን መበጀት ስሙርነት አይቶ ተመልክቶ አቤልን ተቀበለው እንጂ አቤል እንዲያ እንዲሆን አድርጎ ወሰኖ መርጦ አልፈጠረውም። በአንፃሩ ወደ ቃየልና መስዕዋቱ አልተመለከተም ማለት የቃየልን የልቡን ጥመት አየና የመስዕዋቱን አለመበጀት አይቶ አልተቀበለውም ነገር ግን እግዚአብሔር ለክፋት ወስኖ አልፈጠረውም። እግዚአብሔር ሲኦል የሚገቡ ሰዎች እንዳሉ አውቆ ሲኦልን አዘጋጀ እንጂ ሲኦል በሚገቡ ሰዎች ላይ አስቀድሞ እንዲገቡ አድርጎ ወስኖ አልፈጠረም።

እናቱ ድንግል ማርያምን ከእናቷ ማሕፀን መርገም እንዳይኖርባት የጠበቃት እርሱ ነው ቅድመ ዓለም የአምላክ እናት እንድትሆን የመረጣትም እርሱ ነው። ነገር ግን ፍፃሜዋን በነፍስ በስጋ በአፍኣ ንጽሕት እንድትሆን አውቆ መረጣት እንጂ እርሱ ሰለወሰነ የጠበቃት የመረጣት አይደለችም። በዘመኗ ሁሉ በቅድስናዋ ተሸልማ እንደምትኖር አውቆ ከመርገም አነጻት፥ ኖሮባት አይደለም እንዳይኖርባት ጠበቃት እንጂ!

መንፈስ ቅዱስ ጠበቃት አነፃት መባሉም ፍፃሜዋን አይቶ መርገም እንዳይኖርባት ጠበቃት ማለት ነው እንጂ በዓለም ኃጢአት እንዳትሰራ ከለከላት ማለት አይደለም። ንጹህ ሆኖ መፈጠርማ አዳምም ተፈጥሮ ነበር በተፈጥሮ የተሰጠውን ንጹህ ጠባይ በቅድስና መጠቀም አልተቻለውም እንጂ እርሷ ግን ንጽሕናን ቅድስናን ደራርባ ይዛ ተገኝታለችና በዛው ድንግልናዋ ለአምላክ እናትነት በቃች። የሕይወት ፍሬን አፈራችበት እንዲመርጣት እግዚአብሔርን የሳበ በአምላክ ዘንድ ሞገስን የያዘ ንጽሕና ይዛ ተገኝታለችና እንድትመረጥ ሆና ተገኝታለች። ንጹሃንን ለክብር መምረጥማ ለፈጣሪ ድንቅ አይደለም ከእርስዋ ይልቅ ጠላቶቹን እኛን በደሙ ፈሳሽነት ይቅር ማለቱ አይደንቅምን?.......(ቀጣዩን መጽሐፉን ገዝተው ያንብቡ)

(ከርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ አሐቲ ድንግል ገፅ 272-277 ላይ የተቀነጨበ)

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Diribe, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

የሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት የአገልግሎት ውጤት አንዱ ይህ ነው።ኅዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በተደረገው 43ኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተክህነት በአመራር ብቃት ፣ ሰብከተ ወንጌልን በማስፋፋት ፣ ሰበካ ጉባኤንና የሰንበት ት/ቤትን በማጠናከር ብሎም የአብነት ት/ቤት ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት በሀገረ ስብከቱ ካሉት ወረዳዎች ሁሉ አንደኛ በመውጣት ላሳየው ከፍተኛ ውጤት የዋንጫ እና የሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆኖአል። እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን የሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተክህነት ሰባክያን ጥምረት በልዩ ሁኔታ አድናቆቱን እየገለጸ በቀጣዩ ከክቡር አባታችን መ/ሰ/ቆሞስ አባ ሠይፈ ገብርኤል ገረመው የሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተክህነት ዋና ሥራ አሥኪያጅ ጎን በመቆም የተሰጠንን የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ኃላፊነት በገጠሪቱ ቤተክርስቲያን በማስፋፋት ሰብከተ ወንጌልን ተደራሽ ለማድረግ ተግተን እንሠራለን አባታችን እንኳን ደስ አልዎት እድሜ እና ጤና አብዝቶ ይስጥልን ።

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Ăbrham, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ሠላም እንደምን ዋላቸሁ የእግዚአብሔር ቤተሠቦች አን መጠየቅ እምፈልገዉ ጥያቄ ነበር በማርያም 🙏

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ኅዳር_7

#ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሊቀ_ሰማዕት

ኅዳር ሰባት በዚህችም ቀን የልዳ ሀገር የሆነ የሰማዕታት አለቃ የታላቁ መስተጋድል የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው ዳግመኛም ጌታችን በውስጧ ላደረገው ድንቅ ተአምር መታሰቢያ ሆነ።

ይህም እንዲህ ነው በውስጧ ድንቆች ተአምራት እንደሚሠሩ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ ሊአፈርሳት አሰበ ስሙ አውህዮስ የሚባለውንም መኰንን ከብዙ ሠራዊት ጋር ላከው፤ ያም መኰንን በደረሰ ጊዜ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥዕል ወዳለበት አዳራሽ በትዕቢት ሆኖ ገባ። በሥዕሉም ፊት በብርጭቆ መቅረዝ መብራት ነበረ በቤተ ክርስቲያኒቱና በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ እየዘበተ በእጁ በያዘው በትር የመብራቱን መቅረዝ መትቶ ሰበረው የመቅረዙም ስባሪ ወደ ከሀዱው ራስ ደርሶ መታው ራሱንም ታመመ ፍርሃትና እንቅጥቅጥም መጣበት ወድቆም ተዘረረ ባልንጀሮቹም ወደ አገሩ ሊወስዱት ተሸከሙት በክፉ አሟሟትም ተጐሳቊሎ ሞተ ወስደውም ከባሕር ጣሉት ወገኖቹም ወደ ሀገራቸው አፍረው ተመለሱ።

ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ በልዳ ሀገር ያለች የቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን ያፈርሳት ዘንድ ራሱ ተነሥቶ ሔደ በዚያንም ጊዜ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ መታው ሰባት ዓመት ያህልም ዐይኖቹ ታውረው አእምሮውንም አጥቶ ቁራሽ እንጀራም እየለመነ ኑሮ ሞተ።

ክብር ይግባውና ጌታችንም የቤተ መንግሥቱን ሰዎች አስነሣበት እርሱን አስወግደው ጻድቅ ሰው ቁስጠንጢኖስን በእግዚአብሔር ፈቃድ አነገሡት እርሱም በአዋጅ የጣዖታትን ቤቶች ዘግቶ አብያተ ክርስቲያናትን ከፈተ ለክርስቲያን ወገኖችም በሁሉ ዓለም ተድላ ደስታ ሆነ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘኅዳር)

@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Dawit, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ሰላም ቤተሰቦቼ እንደምናችው እስኪ የመቤቴን ምስለ አድን ፎቶ በቁምዋ ሆኗ ደም ያለ ያላችው ላኩልኝ ለቤተክርስትያን ለማሳተም ተፈልጎ ነው

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Meazi, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

😢😢😢#ልጅ #ቢኒን አንገት #አስደፍተን #ከአገልግሎት #እንድንለየው የፈቀደልን #ማነው? #እኛንስ ምሮን እንጂ መርምሮን ቢሆንስ ንጉሱ ፊት እሚያቆም ስራ ሰርተናል?
ልጅ ቢኒ የት ነው አጠይቁም??

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello sami, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

በስርሃተ ቁርባን ለሚፈጸም ጋብቻ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አድርሱን

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

“ሄሮድስም ከሞተ በኋላ፥ እነኾ፥ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ፦ የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘኽ ወደ እስራኤል አገር ሂድ አለ። እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ያዘና ወደ እስራኤል አገር ገባ። በአባቱም በሄሮድስ ፈንታ አርኬላዎስ በይሁዳ እንደ ነገሠ በሰማ ጊዜ፥ ወደዚያ መሄድን ፈራ፤ በሕልምም ተረድቶ ወደ ገሊላ አገር ሄደ።” (ማቴ. 2፥19-22)

“እስከ መቼ ድረስ እመቤቴ በሰው ሀገር ትኖሪያለሽ? ሀገርሽ ገሊላ ግቢ። እናቴ ኾይ ወደ ልቤ ግቢ፤ የእኔም ልብ ወደ ልጅሽ ወደ ወዳጅሽ ሚጠት መመለስን ይፈልጋልና።” - ሰቆቃወ ድንግል

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

“እስከ መቼ ድረስ እመቤቴ በሰው ሀገር ትኖሪያለሽ? ሀገርሽ ገሊላ ግቢ። እናቴ ኾይ ወደ ልቤ ግቢ፤ የእኔም ልብ ወደ ልጅሽ ወደ ወዳጅሽ ሚጠት መመለስን ይፈልጋልና።”

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ሰላም እንዴት ናችሁ አንድ ጉዳይ ላማክራችሁ ነበር

Читать полностью…
Subscribe to a channel