#ደጉ እና ሩሩህ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል አመታዊ በዓል እንኳን አደረሳቹ።
" የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።"
#መዝሙረ ዳዊት 34:7፤)
"በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፤ ሕዝብም ከሆነ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል፤ በዚያም ዘመን በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ እያንዳንዱ ይድናል። "
#ትንቢተ ዳንኤል 12:1
" የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሀያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ እነሆም፥ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፤ እኔም ከፋርስ ነገሥታት ጋር በዚያ ተውሁት። "
#ትንቢተ ዳንኤል 10:13
" ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም።
"
#ትንቢተ ዳንኤል 10:21፤)ዐ
"የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር። ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።"
#የይሁዳ መልእክት 1:9፤
"ቅዱስ ሚካኤል ኾይ
እንደ ፀሐይ ሥነ ጸዳል የሚያንጸባርቁ በሰማይ ላይ ለሚንበለበሉ አክናፎችኽ ሰላም እላለኹ
የእግዚአብሔር ልዩ መልእክተኛ ሚካኤል ኾይ ከላይ ከሰማይ ተመልክተኽ በምትመጣበት ጊዜ ኹሉ በሲዖል የሚኖሩ ግዞተኞች ሚካኤል ኾይ መጣኽልን ደረስክልን እያሉ ደስታቸውን ይገልጻሉ።"
#መልክአ ቅዱስ ሚካኤል.
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
በእንተ ቅዱስ ዳዊት - ፭
የዳዊትን ትዕግሥት የምናደንቅበት ታሪክ ደግሞ በቤተክርስቲያናችን በተራጋሚነቱ የሚታወቀው ‛ሳሚ’ የሰደበውን ስድብ ተቀብሎ ወታደሩ ሊበቀልለት ሲነሳም ከልክሎ እግዚአብሔር በበደሉ ምክንያት እንዲሰድበው እንዳዘዘው መናገሩ ነው።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የዳዊትን ትዕግሥት እንዲኽ ሲል ያደንቃል፤ “በጸጸት የተሞላች ነፍስ ወዳለችው ወደ ዳዊት ተመልከቱ! እነዚያን ኹሉ መልካም ነገሮች ካደረገ በኋላ ከሀገሩ ከቤቱ ሌላው ቀርቶ ከሕይወቱ እንኳን ስደተኛ ኾኖ እያለ በመከራው ጊዜ የአንድን ተራ ሰው ስድብ ታገሠ፤ መልሶ አለመሳደብ ብቻ ሳይሆን ከወታደሮቹ አንዱ ሊበቀልለት ሲነሣ ከልክሎ ‛እግዚአብሔር አዝዞታልና ይርገመኝ’ አለ፡፡”
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ጽሑፍ በዚኹ ዙርያ ከጻፈው ላስነብባችኹ። “ቅዱስ ጴጥሮስ ‛ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ፥ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና’ በማለት እንደተናገረ ሲሰድቡት መልሶ መሳደብ #የክርስቲያን ተግባር አይደለም፡፡ ምክንያቱም ክርስቲያን ያሰኘን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‛ሲሰድቡት መልሶ #አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ’ እንጂ። (1ኛ ጴጥ. 2፥23፤ 3፥9)
በእውነቱ ክርስቲያኖች እንሰኝ እንጂ ተሰድቦ መታገስ ግን ለብዙዎቻችን የሚዋጥ አይደለም፡፡ ተሰድቦ ዝም ማለት በብዙዎቻችን ትርጓሜ ራስን ማስናቅ፥ ፊት መስጠት፥ ፈሪነት እንጂ ትዕግሥት ተብሎ አይጠራም፡፡ አንዳንድ ዝም ያልንባቸው አጋጣሚዎች ቢኖሩም እንኳን በትሕትና ታግሠን አለመሆኑና የዝምታችን ምክንያት ሌላ መሆኑ የመታገሣችንን ደረጃ ዝቅ ያደርገዋል፡፡ ተሰድበን ዝም የምንልባቸው ብዙ ምክንያቶችም አሉ። [ለተሳዳቢው ቦታ ካለመስጠት፥ ተሳዳቢው የበላያችን ከኾነ፥ ሌላ የመበቀያ መንገድ በመፈለግ፥... ብሎ ምክንያቶቹን ይዘረዝርና] ይህ ግን ትዕግሥት ኾኖ ዋጋን የሚያሰጥ አይደለም።
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ብዙ ጊዜ ታግሠን ከቆየን በኋላ በአንድ አጋጣሚ ስንጋጭ ታግሠን ያሳለፍናቸውን ስድቦች ሁሉ ካጠራቀምንበት ልባችን አውጥተን ‛ታግሼ ነው እንጂ፤ ለእግዚአብሔር ሰጥቼ ነው እንጂ እንዲህ እንዲህ ብለኸኝ/ ብለሽኝ ነበር’ ብለን እናስታውሳቸዋለን፡፡ ቅዱስ ዳዊት ግን በተግባር ያስተማረን ስድብን መታገስ ብቻ ሳይሆን #ይገባኛል ብሎ ማመንንና ከእግዚአብሔር እንደተላከ ተግሣጽ መቀበልን ነው፡፡” [...] *
እዚኽ ላይ የምጨምረው ዳዊት የሳሚን ስድብ በትዕግሥት መቀበሉ የደነደነውን የሳሚን ልብ ዳዊት እግር ሥር ተደፍቶ ይቅርታ እስከመጠየቅ አድርሶታል። ‛የጌራ ልጅ ሳሚም በፊቱ ተደፋ። ንጉሡንም፦ ጌታዬ ሆይ፥ ኃጢአቴን አትቍጠርብኝ፤ ጌታዬ ንጉሡ፥ ከኢየሩሳሌም በወጣህ ቀን ባሪያህ የበደልሁህን አታስብብኝ፥ ንጉሡም በልቡ አያኑረው። ባሪያህ በደለኛ እንደ ሆንሁ አውቄአለሁና እነሆ፥ ከዮሴፍ ቤት ሁሉ አስቀድሜ ዛሬ መጣሁ።’ ዳዊትም በመሰደቡ ቂም ሳዪ'ዝ [ከወዳጅነታቸው የተነሣ] እንደገና ሊበቀሉለት ሲነሱ ‛ሳሚን፦ አትሞትም አለው። ንጉሡም ማለለት።’ የዳዊትን ስብእና ተመለከታችኹ? ለርሱ የማይገባውን ስድብ ለዚያውም ክፉ ቀን በገጠመው፥ የገዛ ልጁ ዐምፆበት በሚንከራተትበትና ሆድ በባሰው ሰዓት ታግሦ ተቀብሎ እንደገና ይቅር ማለቱ አያስደንቅም? እኛ ብንኾን እንደዚኽ ለማድረግ ሞራሉ ይኖረን ይኾን?
* [የተቀረውን ‛በተሰደብክ ጊዜ’ - በሚል ርዕስ የጻፈው ነው፤ ፈልጋችኹ አንብቡት።]
#ይቀጥላል...
እግዚአብሔር የዳዊትን ታጋሽ ልብ ያድለኝ ዘንድ ታናሽ ወንድማችኹ ገብረ ማርያምን በጸሎታችኹ አስቡኝ።
150cmx80cm
Price 3500 birr
With free delivery 🚚
የገጠማ አይጨምርም ❗️‼️
👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
@GraceWallArt
(0943448637)
@hani_nata
(0936239392)
safari
0717841917
0703958003
TEle
0936239392
0943448637
Join more our work
@grace_wallart
👌 ምርጫዎ ስለሆንን እናመሠግናለን
🕊
[ † እንኩዋን "ለቅድስት ወብጽዕት ሐና" [ እመ ማርያም ] ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]
🕊 † ብጽዕት ሐና † 🕊
"ሐና" ማለት በእብራይስጥኛው "የእግዚአብሔር ስጦታ" እንደ ማለት ነው:: "ሐና: ዮሐና: ሐናንያ" የሚሉ የዕብራይስጥ ስሞች ትርጉማቸው ተወራራሽ ነው:: የዚህችን ቅድስት እናት ክብሯን መናገር የሚችል የለም:: እርሷ ሰማይና ምድርን ለፈጠረ ለእግዚአብሔር ወልድ በሥጋ አያቱ ተብላለችና::
† አንድም ለሰማይና ለምድር ንግስት ለድንግል ማርያም ወላጅ እናቷ ናትና:: ከዓለም ሴቶች ሁሉ የቅድስት ሐና ማሕጸን እንደ ምን ይከብር! በፍጥረት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥንተ አብሶ [ የአዳም በደል ] መተላለፍ የቀረው በማሕጸነ ሐና ውስጥ ነውና:: [ ለዚህ አንክሮ ይገባል!!! ]
† ይስሐቅን የተሸከመ የሣራ ማሕጸን ቡሩክ ከተባለ የቅድስት ሐናማ እንደምን አይባል! ከፍጥረታት ሁሉ እግዚአብሔር ድንግል ማርያምን እንደ መረጠ ሁሉ ቅድስት ሐናንም ለአያትነት መርጧታል::
- ለመሆኑ ቅድስት ሐና ማን ናት? ለዚህ ክብርስ ያበቃት ምሥጢረ ቅድስናዋ ምንድን ነው?
† ቅድስት ሐና ትውልዷ: ነገዷ ከላይ ከቅዱስ አብርሃም: ከታች ደግሞ ከነገደ ካህናት ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
- አብርሃም ይስሐቅን: ይስሐቅ ያዕቆብን: ያያዕቆብ ደግሞ ሌዊንና ፲፩ ወንድሞቹን ይወልዳል::
- ሌዊ ቀዓትን: ቀዓት እንበረምን: እንበረም አሮን ካህኑን ይወልዳሉ::
- ቅዱስ አሮን አልዓዛርን: አልዓዛር ፊንሐስን እያለ ትውልዱ እስከ ቴክታና በጥሪቃ ይወርዳል:: ቴክታና በጥሪቃም ልጅ በማጣት ኖረው: የእንቦሳዎች: የፀሐይና: የጨረቃን ምሥጢር ተመልክተው ሄኤሜንን ይወልዳሉ::
- ሄኤሜን ዴርዴን: ዴርዴ ቶናሕን: ቶናሕ ሲካርን: ሲካርም ሔርሜላን ይወልዳሉ::
- ሔርሜላም ከክርስቶስ ልደት ፺ ዓመታት በፊት ማጣት ["ጣ" ጠብቆ ይነበብ] የሚባል ደግ ሰው ከካህናት ወገን አግብታ በስርዓተ ኦሪት ትኖር ነበር:: እግዚአብሔር ለዚህች ደግ ሴት የተባረኩ ፫ ሴቶች ልጆችን ሰጣት::
† የመጀመሪያዋን "ማርያም" አለቻት:: ይህቺውም የአረጋዊው ዮሴፍ ሚስትና የቅድስት ሰሎሜ ቡርክት እናት ናት:: ሁለተኛዋን "ሶፍያ" አለቻት:: እርሷም ቅድስት ኤልሳቤጥን [የመጥምቁን እናት] ወልዳለች::
† በመጨረሻ የወለዷትን ግን "ሐና" አሏት:: ይህቺውም የፈጣሪ የሥጋ አያቱ: የድንግል ማርያምም እናቷ ትሆን ዘንድ የተመረጠችውና ስም አጠራሯ የከበረው: ዛሬ የምናከብራት እናት ናት::
† መጽሐፈ ስንክሳርን ስመለከት እንዲህ የሚል ዓረፍተ ነገር አየሁ:: "ለዛቲ ቅድስት ኢያዕመርነ ገድላቲሃ ዘትገብሮን በኅቡዕ ከመ ንዝክሮን" ይላል:: ትርጉሙም "የዚህቺን ቅድስት ገድሏንና ትሩፋቷን እንዳንዘረዝር አላወቅነውም" እንደ ማለት ነው::
† የሚገርመው አበው እንዲህ ያሉት ክብሯን መግለጹን አልጠግብ ብለው ነው:: እኛም በመጠናችን የብጽዕት ሐናን ሕይወት በአጭሩ ቀጥለን እንመልከት::
† ብጽዕት ሐና ወላጆቿ [ ማጣትና ሔርሜላ ] ከካህናት ወገን በመሆናቸው ልጆቻቸውን በጥንቃቄ: በሥርዓተ ኦሪት እንዳሳደጉ ይታመናል:: ቅድስት ሐናንም ለአቅመ ሔዋን እስክትደርስ ድረስ በሕጉ: በሥርዓቱ አሳድገዋታል::
† በወቅቱ በፈቃደ እግዚአብሔር ትውልዱ ከነገደ ይሁዳ የሚሆን አንድ ደግ ሰው አጩላት:: ይህ ሰው "ኢያቄም" ይባላል:: አንዳንዴም "ሳዶቅ" ወይም "ዮናኪር" እየተባለ ይጠራል:: ቅዱስ ኢያቄም ማለት ክፉ ከአንደበቱ የማይወጣው: ምጽዋትን የሚወድ: አምላከ እሥራኤልን በንጹሕ ልቡ የሚያመልክ ሰው ነበረ::
† እንደ ኦሪቱ ሥርዓት ፪ቱ [ኢያቄም ወሐና] ከተጋቡ በሁዋላ ቶሎ መውለድ አልቻሉም:: ይሕ ደግሞ የወቅቱ ከባድ ፈተና ነው:: በዘመድ የከበሩ: በጠባያቸው የተመሰገኑ: መልካምንም የሚሠሩ ሰዎች ልጅ ስለሌላቸው ብቻ "ኅጡአነ በረከት" እየተባሉ ከቤተ እግዚአብሔር ይገፉ: በአደባባይም ይነቀፉ ነበር::
† ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን ልጅ አለመውለድ እንደ ኃጢአተኛ ያስቆጥር ነበር:: ደግነቱ የወቅቱ ሊቀ ካህናት ቅዱስ ዘካርያስ [ የመጥምቁ አባት ] እንደ እነሱ ልጅ ያጣ በመሆኑ አብረው ይጽናኑ ነበር::
† የሆነው ሆኖ እኒህ ቡሩካን ሰዎች አምላከ እሥራኤልን ከመለመንና ከማመስገን በቀር ሌላ ትርፍ አልተገኘባቸውም:: ምንም የሞላቸውና የደላቸው ባይሆኑም ደሃን ሳያጐርሱ አይበሉም ነበር::
† ቅድስት ሐናን ግን "ቢወልዷት እንጂ አትወልድ: ድንጋይ: በቅሎ" እያሉ ጐረቤቶቿ ይሳለቁባት ነበር:: ከማልቀስ በቀር ደግሞ መልስ አልነበራትም::
† አንድ ቀን ግን ርግቦች ከልጆቻቸው ጋር ሲጫወቱ ተመልክታ "ፈጣሪ ሆይ! የእንስሳትን ማሕጸን የምትከፍት: ዕፀዋትንም ከባሕርያቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ:: እውነትም ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ስትል አለቀሰች::
† ቅዱስ ኢያቄምም ወደ ተራራ ወጥቶ ለ፵ ቀናት አለቀሰ: ተማለለ:: ይህ ሲሆን ፪ቱም አርጅተው ነበር:: ሐምሌ ፴ ቀን ግን ነጭ ርግብ ፯ቱን ሰማያት ሰንጥቃ በማሕጸነ ሐና ስታድር አዩ:: ደስ ብሏቸው ለ፯ ቀናት ሱባኤ ይዘው ቅድስት ሐና እመቤታችንን ነሐሴ ፯ ቀን ጸነሰቻት::
† ይሕም ለእነርሱም: ለወገኖቻቸውም ታላቅ ተድላ ሆነ:: ብጽዕት ሐና ግን ፈጣሪዋን ታከብረው ዘንድ በጐነትንና ንጽሕናን አበዛች:: ጸንሳ ሳለም ዕውራንን አበራች: ድውያንን ፈወሰች::
† የጦሊቅ ልጅ በሞተ ጊዜም እያለቀሰች ስትዞረው ጥላዋ ቢያርፍበት አፈፍ ብሎ ተነስቶ :- "ሰላም ለኪ እሙ ለፀሐየ ጽድቅ" ብሎ ድንግል ማርያምን::
"ወሰላም ለኪ እምሔውቱ ለዘገብረ ሰማየ ወምድረ" ብሎ ቅድስት ሐናን አመስግኗል:: ትርጉሙም ድንግልን "የፀሐየ ጽድቅ እናቱ": ሐናን "ሰማይና ምድርን ለፈጠረ አያቱ" ማለት ነው::
† ይህንን ያዩ አይሁድ ቅድስት ሐናን ሊገድሉ ብዙ ጊዜ ሞክረዋል:: ግን መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል አልፈቀደላቸውም:: ግንቦት ፩ ቀንም የሰማይና የምድር ንግስትን ሊባኖስ ተራራ ላይ ወልዳ ሽሙጥን ከሁላችንም አራቀች::
† ስሟን "ማርያም-የአምላክ ስጦታ" ብለው ሰይመው ለ፫ ዓመታት አሳድገዋታል:: የሚገርመው በ፫ቱ ዓመታት ውስጥ ቅድስት ሐና ድንግል ማርያምን ከክንዷ አውርዳት አታውቅም ነበር:: አንድ ጊዜም መላእክት ወስደውባት ፍጹም አልቅሳለች:: ሁዋላ ግን መልሰውላታል::
† ሌላኛው የሚደንቀው እግዚአብሔር የዓለም ውዱን ስጦታ እመ ብርሃንን ሰጣቸው:: እነርሱም ይሕችን ውድ ስጦታ ሳይሰስቱ ለፈጣሪ መለሱለት::
"እምቅድሜክሙ አልቦ::
ወእምድኅሬክሙ አልቦ::
ከመዝ መስዋዕት ለእግዚአብሔር ዘወሃቦ::" እንዲል::
† ቅድስት ሐና ድንግል ወደ ቤተ መቅደስ ከገባች በሁዋላ የእናትነት ፍቅሯ እያገበራት ለ፭ ዓመታት እየተመላለሰች ትጐበኛት: ትስማት ነበር:: እመቤታችን ፰ ዓመት በሞላት ጊዜ ግን የእግዚአብሔር ጥሪ ወደ ቅድስት ሐና ደረሰ::
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሃይማኖታዊ ነጻነታችንን የሚጋፋ መመሪያ አውጥቷል ሲሉ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ገለጹ፡፡
ተማሪዎቹ ይህንን ያሉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም ያወጣውን የሥነ መግባርና ዲሲፕሊን መመሪያ ተከትሎ ነው፡፡
በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ወደ መመገቢያ አዳራሽ ሲሄዱ ነጠላ እንዳይለብሱና ምግብ እንዳያወጡ ሃይማኖታዊ መብታቸውን የሚጋፋ የሥነ ምግባርና ዲሲፕሊን መመሪያ መውጣቱን የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ ኀላፊ አቶ አበበ በዳዳ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገልጸዋል።
አቶ አበበ በዳዳ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ኦርቶዶክሳውያን የከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎች ሃይማኖታዊ የመብት ጥሰት እንዳይፈጸምባቸው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መወያየት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
ዩንቨርሲቲው በ2017 ዓ.ም ባወጣው የሥነ ምግባር ዲስፕሊን መመሪያ የተለያዩ እምነት ተከታይ ተማሪዎች በግቢው ስለሚያስተናገዱ ከሃይማኖትና ከበዓላት ጋር የተያያዙ የአለባበስ ሥርዓቶች የማንነትና የእምነት መገለጫዎች በመሆናቸው ሊከበሩ ይገባቸዋል ይላል፡፡
በሌላ በኩል የኒቨርሲቲው ሃይማኖታዊ ነጻነታችንን የሚጋፋ መመሪያ አውጥቷል ሲሉ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም በምግብ ሰዓት የህሊና ጸሎት ካልሆነ በቀር ጸሎት እንዳናደርግና ከዳቦ ውጭ ምግብ እንዳናወ እንዲሁም በመመግቢያ አዳራሽ ውስጥ ነጠላ እንዳንለብስ መመሪያ ወጥቷል ብለዋል፡፡
ተማሪዎች አክለውም የወጣውን መመሪያ ምክንያት በማድረግ በአንዳንድ የጥበቃ አካላትና ግለሰቦች ጫና እየተደረገብን ነው ሲሉም ጠቁመዋል፡፡
ምግባችንን አውጥተን ለነዳያን መስጠትና መንፈሳዊ ጉዞ በምናከናውንበት ወቅት አውጥተን መጠቀም እንዳንችል ተደርጓልም ብለዋል፡፡
የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ ኀላፊ አቶ አበበ በዳዳ ዩንቨርሲቲው በመጀመሪያው ረቂቅ መመሪያ ያወጣቸው ሕጎች ለኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች በጣም አስቸጋሪ ነበሩም ብለዋል፡፡
ነገር ግን በተማሪዎች በተቋቋመ ኮሚቴ በመመሪያው አንዳንድ አንቀጾች ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ በቀረበው አስተያየት መሠረት ከበፊቱ የተሻለ ቢሆንም አሁንም ግን የተማሪዎችን ሃይማኖታዊ መብት የሚጋፋ መመሪያ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የማስተባበሪያው ኀላፊ አክለውም በተለይም ነጠላን አላስፈላጊ ልብስ በማለት የተገለጸው መመሪያ አግባብነት የሌለው ነውም ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ይህ አካሄድ ሀገርን የማይጠቅም በመሆኑ ሊታሰብበት እንደሚገባ አሳስበው ዩንቨርሲቲው አሳማኝ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሰዎች በልዩ ሁኔታ ሃይማኖቱ የሚፈቅደውን አለባበስ መልበስ ይችላሉ የሚል መመሪያ ስላለው የሚመለከታቸው አካላት ውይይትና ምክክር እንዲያደርጉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
150cmx80cm
Price 3500 birr
With free delivery 🚚
የገጠማ አይጨምርም ❗️‼️
👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
@GraceWallArt
(0943448637)
@hani_nata
(0936239392)
safari
0717841917
0703958003
TEle
0936239392
0943448637
Join more our work
@grace_wallart
👌 ምርጫዎ ስለሆንን እናመሠግናለን
Family picture
Price 60x120 cm 4200 birr
60x90 cm : 3800 birr
50x80 cm : 2500 birr
40x60cm : 1900 birr
30x45 cm : 1300 birr
Delivery fee: 200
👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
@GraceWallArt
@hani_nata
👌 ምርጫዎ ስለሆንን እናመሠግናለን
L
Size. 60x90 cm , 30x30 cm
Price 5000 birr
With free delivery 🚚
👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
@GraceWallArt
(0943448637)
@hani_nata
(0936239392)
safari
0717841917
0703958003
TEle
0936239392
0943448637
Join more our work
@grace_wallart
👌 ምርጫዎ ስለሆንን እናመሠግናለን
L
Size. 60x90 cm , 30x30 cm
Price 5000 birr
With free delivery 🚚
👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
@GraceWallArt
(0943448637)
@hani_nata
(0936239392)
safari
0717841917
0703958003
TEle
0936239392
0943448637
Join more our work
@grace_wallart
👌 ምርጫዎ ስለሆንን እናመሠግናለን
150cmx80cm
Price 3500 birr
With free delivery 🚚
የገጠማ አይጨምርም ❗️‼️
👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
@GraceWallArt
(0943448637)
@hani_nata
(0936239392)
† ከክርስቶስ ልደት ፰ ዓመታት አስቀድማ ብጽዕት እናት ሐና በዚህች ቀን ዐረፈች:: ትንሽ ቆይቶም ባለቤቷ ቅዱስ ኢያቄም ተከተላት እኛም ልጆቿ "ብጽዕት ሐና ብጽዓን ይገባሻል!" እያልን እናመስግናት::
† ሊቃውንቱ ለእርሷ እንዲህ ብለዋልና :-
"ሰላም ለኪ ለጸሎተ ኩሉ ምዕራጋ::
ከመ አስካለ ወይን ዲበ ሐረጋ::
ሐና ብጽዕት ተፈስሒ እንበለ ንትጋ::
እስመ ረከብኪ ሞገሰ ወአድማዕኪ ጸጋ::
እምሔውተ አምላክ ትኩኒ በሥጋ::" [አርኬ]
አምላከ ብጽዕት ሐና በምልጃዋ ከዘለዓለም እሳት ያድነን:: ጸጋ በረከቷንም ይክፈለን::
🕊
[ † ኅዳር ፲፩ [ 11 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅድስት ሐና ቡርክት
፪. ቅዱስ አርኬላዎስ ሰማዕት
፫. አባ ኤልሳዕ አበ ምኔት
፬. አባ ዻኩሚስ መነኮስ
፭. ቅዱስ ሚናስ ሰማዕት
፮. ቅድስት አውራንያ [የሰማዕቱ እናት]
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ያሬድ ካህን
፪. ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት
፫. ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
፬. አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
" መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው::
ከያዕቆብ ድንኩዋኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል:: የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ በአንቺ የተደረገው ነገር ድንቅ ነው . . . ሰው እናታችን ጽዮን ይላል:: በውስጥዋም ሰው ተወለደ:: እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት::" [መዝ.፹፮፥፩]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
#እንኳን አደረሳችሁ ቅዱስ እያቄም ወ ቅድስት ሀና ዓመታዊ በዓል በወጭም በሀገር ውስጥ ላላችሁ እህቶች ወንድሞች
ሀና ማለት ፀጋ ማለት ነው።አምላክን የወለደች የእመቤታችን
ቅድስት ድንግል ማርያም እናት ናት ።እርሷም ከኢየሩስአሌም አገር ከሌዊ ወገን ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ
ለሆነው ለማጣት ልጁ ናት ። የቅድስት ሀና ማጣትና እናቷ ሔርሜላ ከ እርሷ በተጨማሪ ሶፊያና ማርያም የሚባሉ ሌሎች ሁለት ሴቶች ልጆች ወልደዋል።
ቅድስት ሀና ከ ይሁዳ ነገድ የሆነውን ጻድቅ ኢያቄምን አግብታ ቅድስት ድንግል ማርያም ወልዳለች። ድንግል ማርያምም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወልዳለች።ሶፍያ ኤሌሳቤጥን ወለደች,ኤልሳቤጥም መጥምቁ ዮሐንስን ወለደች,ከሶስቱም ታናሽ የሆነችው ማርያም የተባለችው የማጣትና የሔርሜላ ልጅ ደግሞ ሰሎሜን ወለደች ።
ይህችም ታላቅ እናት ቅድስት ሀና አምላክን በድንግልና ለወለደች ቅድስት ድንግል ማርያም ወላጅ እናት ትሆን ዘንድ
የተገባት ሆናለችና። ከሴቶች ሁሉ እንደምትበልጥና እንደምትከበር እንረዳ ።
ለዓለም ሁሉ ድህነት የተደረገባትን ልዩ ስጦታ የሆነችውን ድንግል ማርያምን እርሷ አስገኘቻት ። ከሴቶች ሁሉ የሚበለጥና የሚበዛ ትሩፋትና ተጋድሎ ባይኖራት ይህን
ታላቅ ፀጋ ባልተሰጣት ነበር ።የዚህች ድንቅ የሆነች ቅድስት
እናታችን ሀና ዛሬ ህዳር 11 ቀን እረፍቷ ነው።
የእናታችን ቅድስት ሀና እረድኤት በረከቷ አይለየን
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
#ኅዳር_11
#ቅድስት_ሐና
ኅዳር ዐሥራ አንድ በዚች ዕለት አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናቷ የሆነች የተመሰገነች የቅድስት ሐና የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው።
ይችም ቅድስት ከኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ ለሆነ ለማጣት ልጁ ናት። ለማጣትም ሦስት ሴቶች ልጆች አሉት የታላቂቱም ስሟ ማርያም ናት ሁለተኛዋም ስሟ ሶፍያ ሦስተኛዪቱም ስሟ ሐና ናት ታላቂቱ ማርያምም ለባል ተድራ አዋላጅ የሆነች ሰሎሜን ወለደቻት እርሷም መድኃኒታችንን ከወለደችበት ጊዜ ጀምሮ በስደቷም ወራት ከአረጋዊ ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ድንግል ማርያምን ያገለገለቻት ናት።
ሶፍያም ለባል ተድራ ለመጥመቁ ዮሐንስ እናቱ የሆነች ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደቻት። ይችንም ቅድስት ሐናን ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ጻድቅ ስሙ ኢያቄም ለሚባል አጋቧትና እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለደቻት እሊህም ሰሎሜና ኤልሳቤጥ ለቅድስት ሐና የእኅትማማች ልጆች ናቸው።
የዚችንም የቅድስት ሐናን በሥውር የምትሠራውን ገድሏንና ትሩፋቷን እንዳናስታውሰው አናውቀውም ግን ከሴቶች ሁሉ እንደምትበልጥና እንደምትከብር እናውቃለን እንረዳለን እርሷ አምላክን በሥጋ ለወለደችው ወላጅዋ ትሆን ዘንድ የተገባት ሁናለችና ከሴቶች ሁሉ የሚበልጥና የሚበዛ ትሩፋትና ተጋድሎ ባይኖራት ይህ ታላቅ ጸጋ ባልተገባት ነበር።
ይህችም ጻድቅት ሐና መካን በመሆንዋ ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር በጸሎት ትማልድ ነበር እግዚአብሔርም በእርሷ ለዓለም ሁሉ ድኅነት የተደረገባትን ይቺን የተባረከችና የከበረች ልጅን ሰጣት እርሷም አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት።
ስለዚህም ይህን ታላቅ ጸጋ ስለሰጣት የበዓሏን መታሰቢያ በደስታ ልናከብር ይገባናል።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷም ከእኛ ጋር ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
150cmx80cm
Price 3500 birr
With free delivery 🚚
የገጠማ አይጨምርም ❗️‼️
👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
@GraceWallArt
(0943448637)
@hani_nata
(0936239392)
safari
0717841917
0703958003
TEle
0936239392
0943448637
Join more our work
@grace_wallart
👌 ምርጫዎ ስለሆንን እናመሠግናለን
በእንተ ቅዱስ ዳዊት - ፭
የዳዊትን ትዕግሥት የምናደንቅበት ታሪክ ደግሞ በቤተክርስቲያናችን በተራጋሚነቱ የሚታወቀው ‛ሳሚ’ የሰደበውን ስድብ ተቀብሎ ወታደሩ ሊበቀልለት ሲነሳም ከልክሎ እግዚአብሔር በበደሉ ምክንያት እንዲሰድበው እንዳዘዘው መናገሩ ነው።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የዳዊትን ትዕግሥት እንዲኽ ሲል ያደንቃል፤ “በጸጸት የተሞላች ነፍስ ወዳለችው ወደ ዳዊት ተመልከቱ! እነዚያን ኹሉ መልካም ነገሮች ካደረገ በኋላ ከሀገሩ ከቤቱ ሌላው ቀርቶ ከሕይወቱ እንኳን ስደተኛ ኾኖ እያለ በመከራው ጊዜ የአንድን ተራ ሰው ስድብ ታገሠ፤ መልሶ አለመሳደብ ብቻ ሳይሆን ከወታደሮቹ አንዱ ሊበቀልለት ሲነሣ ከልክሎ ‛እግዚአብሔር አዝዞታልና ይርገመኝ’ አለ፡፡”
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ጽሑፍ በዚኹ ዙርያ ከጻፈው ላስነብባችኹ። “ቅዱስ ጴጥሮስ ‛ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ፥ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና’ በማለት እንደተናገረ ሲሰድቡት መልሶ መሳደብ #የክርስቲያን ተግባር አይደለም፡፡ ምክንያቱም ክርስቲያን ያሰኘን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‛ሲሰድቡት መልሶ #አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ’ እንጂ። (1ኛ ጴጥ. 2፥23፤ 3፥9)
በእውነቱ ክርስቲያኖች እንሰኝ እንጂ ተሰድቦ መታገስ ግን ለብዙዎቻችን የሚዋጥ አይደለም፡፡ ተሰድቦ ዝም ማለት በብዙዎቻችን ትርጓሜ ራስን ማስናቅ፥ ፊት መስጠት፥ ፈሪነት እንጂ ትዕግሥት ተብሎ አይጠራም፡፡ አንዳንድ ዝም ያልንባቸው አጋጣሚዎች ቢኖሩም እንኳን በትሕትና ታግሠን አለመሆኑና የዝምታችን ምክንያት ሌላ መሆኑ የመታገሣችንን ደረጃ ዝቅ ያደርገዋል፡፡ ተሰድበን ዝም የምንልባቸው ብዙ ምክንያቶችም አሉ። [ለተሳዳቢው ቦታ ካለመስጠት፥ ተሳዳቢው የበላያችን ከኾነ፥ ሌላ የመበቀያ መንገድ በመፈለግ፥... ብሎ ምክንያቶቹን ይዘረዝርና] ይህ ግን ትዕግሥት ኾኖ ዋጋን የሚያሰጥ አይደለም።
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ብዙ ጊዜ ታግሠን ከቆየን በኋላ በአንድ አጋጣሚ ስንጋጭ ታግሠን ያሳለፍናቸውን ስድቦች ሁሉ ካጠራቀምንበት ልባችን አውጥተን ‛ታግሼ ነው እንጂ፤ ለእግዚአብሔር ሰጥቼ ነው እንጂ እንዲህ እንዲህ ብለኸኝ/ ብለሽኝ ነበር’ ብለን እናስታውሳቸዋለን፡፡ ቅዱስ ዳዊት ግን በተግባር ያስተማረን ስድብን መታገስ ብቻ ሳይሆን #ይገባኛል ብሎ ማመንንና ከእግዚአብሔር እንደተላከ ተግሣጽ መቀበልን ነው፡፡” [...] *
እዚኽ ላይ የምጨምረው ዳዊት የሳሚን ስድብ በትዕግሥት መቀበሉ የደነደነውን የሳሚን ልብ ዳዊት እግር ሥር ተደፍቶ ይቅርታ እስከመጠየቅ አድርሶታል። ‛የጌራ ልጅ ሳሚም በፊቱ ተደፋ። ንጉሡንም፦ ጌታዬ ሆይ፥ ኃጢአቴን አትቍጠርብኝ፤ ጌታዬ ንጉሡ፥ ከኢየሩሳሌም በወጣህ ቀን ባሪያህ የበደልሁህን አታስብብኝ፥ ንጉሡም በልቡ አያኑረው። ባሪያህ በደለኛ እንደ ሆንሁ አውቄአለሁና እነሆ፥ ከዮሴፍ ቤት ሁሉ አስቀድሜ ዛሬ መጣሁ።’ ዳዊትም በመሰደቡ ቂም ሳዪ'ዝ [ከወዳጅነታቸው የተነሣ] እንደገና ሊበቀሉለት ሲነሱ ‛ሳሚን፦ አትሞትም አለው። ንጉሡም ማለለት።’ የዳዊትን ስብእና ተመለከታችኹ? ለርሱ የማይገባውን ስድብ ለዚያውም ክፉ ቀን በገጠመው፥ የገዛ ልጁ ዐምፆበት በሚንከራተትበትና ሆድ በባሰው ሰዓት ታግሦ ተቀብሎ እንደገና ይቅር ማለቱ አያስደንቅም? እኛ ብንኾን እንደዚኽ ለማድረግ ሞራሉ ይኖረን ይኾን?
* [የተቀረውን ‛በተሰደብክ ጊዜ’ - በሚል ርዕስ የጻፈው ነው፤ ፈልጋችኹ አንብቡት።]
#ይቀጥላል...
እግዚአብሔር የዳዊትን ታጋሽ ልብ ያድለኝ ዘንድ ታናሽ ወንድማችኹ ገብረ ማርያምን በጸሎታችኹ አስቡኝ።
Hexagon
Price 6900 birr
free delivery 🚚
👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
@GraceWallArt
(0943448637)
@hani_nata
(0936239392)
150cmx80cm
Price 3500 birr
With free delivery 🚚
የገጠማ አይጨምርም ❗️‼️
👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
@GraceWallArt
(0943448637)
@hani_nata
(0936239392)
safari
0717841917
0703958003
TEle
0936239392
0943448637
Join more our work
@grace_wallart
👌 ምርጫዎ ስለሆንን እናመሠግናለን