ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ አስተምህር ለነ ሰአልናከ በ፲ ወ፬ ትንብልናከ፤ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ዓይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ ሐመልማለ ወርቅ፤ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ይሰግድ በብረኪሁ እስከ ይመጽእ ሥርየት ለኃጥአን፤ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ መኑ ከማከ ክቡር
እንኳን አደረሳችሁ
Family picture
በተለያዩ ምክንያቶች ተለያይተው ፎቶ አንደላይ መነሳት ያልቻሉ ቤተሰብዎን ፎቶዎች እኛ ዘንድ ያሰባስቡ!
Price 60x120 cm 4200 birr
60x90 cm : 3800 birr
50x80 cm : 2500 birr
40x60cm : 1900 birr
30x45 cm : 1300 birr
Delivery fee: 200
👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
@GraceWallArt
@hani_nata
Join more our work
@grace_wallart
“የምንባርከው የበረከት ጽዋ #ከክርስቶስ_ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ #ከክርስቶስ_ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? አንድ እንጀራ ስለ ኾነ፥ እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን፤ ኹላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና።” (1ኛ ቆሮ. 10፥16-17)
Читать полностью…150cmx80cm
Price 3500 birr
With free delivery 🚚
የገጠማ አይጨምርም ❗️‼️
👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
@GraceWallArt
(0943448637)
@hani_nata
(0936239392)
ስድብ ኃጢአት ባይሆን ኖሮ መሰደብ የሚገባው ዲያቢሎስ ነው:: ፍጥረት ሁሉ ስድብ ቢያዋጣ ለዲያቢሎስ የሚመጥን አይሆንም:: የክፋት ምንጭ ለሆነ ለእርሱ ሁሉም ክፉ ቃል መገለጫው ነው::
ይሁንና ቅዱስ ሚካኤል ይህንን ክፉ ጠላት ደፍሮ አልሰደበውም:: "እግዚአሔር ይገሥጽህ!" አለው::
(ይሁ 1:9)
እንደ ሚካኤል ንጹሕ በእኛ ዘን ማን አለ? እንደ ዲያቢሎስስ ክፉ በእኛ ዘንድ ማን አለ?
መልእክቱ ግልጽ ነው:: አንሆንም እንጂ እንደ ሚካኤል ንጹሕ ብንሆን እንኳን እንደ ሰይጣን የከፋን ሰው እንኳን መሳደብ አንችልም::
የመላእክት አለቃ ሚካኤል ከሥልጣኑ የወረደውን የቀድሞውን የመላእክት አለቃ ዲያቢሎስን አንድም ክፉ ቃል አልተናገረውም:: አንዱ ከሥልጣኑ ወድቆ ሌላው ሲሾም አዲሱ ተሿሚ ስለወደቀው ምን እንደሚል እናውቃለን:: አንደበቱ ስድብ በመናገር ያልረከሰው ቅዱስ ሚካኤል ግን ወድቆ በማያርፈው ዲያቢሎስ ላይ የስድብን ቃል አልተናገረም::
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
@semetnbegtm
ኦ ሚካኤል...
ፍፁም ትሁት ቢሆን ተሠጠው ልዕልና
ተርበው ለጠሩት የሚመግብ መና
ሞግዚት ነው በዓለም ለሌላቸው ወላጅ፣
ለታመኑት አባት ጠላትን አሳዳጅ
..
ነገድ ብሔር አይለይ ሲቀበል አደራ
ልጆች አሳዳጊ ከፊት እየመራ
ቦታ አይወስነው ጊዜ አይወስነው
ልጆቹን ሲጠብቅ፣
ስሙ ግርማ ያለው ጠላት የሚያስጨንቅ
የማይሰለች አባት ፍቅሩ የሚጨምር
የሞትን ደብዳቤ በህይወት የሚቀይር
..
ልዑል እምልዑላን ስልጣኑ ከፍ ያለ
ሠልፉን እየመራ ዘንዶውን የጣለ
እሱ ያልረዳው ሠው አይገኝ በዓለሙ
ለአህዛብ አደለም ክርስቲያኖች ስሙ
..
ዓለም ጥበበኛ ያውቅበታል ሴራ
ቆላ ደጋ ብሎ ቢደግስ መከራ
ስጋችሁ አይራድ ፍፁም አትደንግጡ
ሠልፋችሁን ይምራ ልክ እንደ አፎምያ
ለሚካኤል ስጡ፣
የዓለምን ሴራ የገንዘብን ድግስ
በእምነት ብለጡ፣
የሚካኤል ልጆች አትፍሩ ቀኑ
ቢጨልምም
እንኳን የአዳም ዘር ዘንዶው አልቻለውም!!
✍ኤርሚ ግርማ
@semetnbegtm
@semetnbegtm
በእንተ ቅዱስ ዳዊት - ፮
‛እኔ ግን #ትል ነኝ ሰውም አይደለሁም፤ የሰው ማላገጫ በሕዝብም ዘንድ #የተናቅኹ ነኝ።’ እዚኽ ላይም የዲያቆን አቤል ካሳሁንን ጽሑፍ ላስነብባችኹና እንቀጥል። “ብዙ ጊዜ በእኛ ዘንድ የተናቀ ልብስ መልበስ፥ አንገት መስበር፥ ዝግ ብሎ ማውራት እና ‹እኔ በደለኛ የማይገባ ሰው ነኝ› እያሉ ደጋግሞ መናገር እንደ ትሑት ያስቆጥር ይኾናል፡፡ ነገር ግን የትሕትና ትርጉም ከዚህም በላይ ነው፡፡ [...]
ትሕትና በእኛ እና በእግዚአብሔር መካከል ያለ #እውነተኛ_ኑሮ ነው፡፡ አንድ ክርስቲያን ስለ ትሕትና ሲያስብ እነዚኽን ኹለት ነገሮች አብሮ በትኩረት ሊያሰላስል ይገባዋል፡፡ እነርሱም አንደኛ ተፈጥሮውን (መሬታዊ፥ ትቢያ መኾኑን) አለመዘንጋት ሲኾን፥ ኹለተኛው ደግሞ ተቀባይነቱን ለዘወትር ማስታወስ ነው፡፡ ሰው በጫማው እየረገጠ የሚራመደው አፈር እንደኾነ ሲያስብ ደካማነቱን ይረዳል፡፡ ስለዚኽም በነገሮች ሁሉ ‹አቤቱ እኛ አፈር እንደ ኾንን አስብ› እያለ ረድዔተ እግዚአብሔርን የሚማጸን ትሑት ይኾናል፡፡ (መዝ. 103፥14)
ተቀባይነቱንም ኹል ጊዜ የሚያስታውስ ከኾነ ለሌሎች በሚያደርጋቸው በጎ ሥራዎች አይኩራራም፡፡ ብልጫም አይሰማውም፡፡ ምክንያቱም የራሱን ሳይኾን ከአምላኩ ከተሰጠው ላይ ቀንሶ የሚያካፍል ምስኪን ምጽዋተኛ ስለኾነ፡፡ ሐዋርያውስ ቢሆን በቆሮንቶስ መልእክቱ በታላቅ ቃል ‹አንተ እንድትበልጥ ማን አድርጎኻል? ያልተቀበልኸውስ ምን አለኽ? የተቀበልኽ ከሆንኽ ግን እንዳልተቀበልኽ የምትመካ ስለምንድር ነው?› ሲል የሚገስጸው ስለዚሁ አይደለምን? (1ኛ ቆሮ. 4፥7)
ሶርያዊው አባት ማር ይስሐቅ ስለ ትሕትና ትርጉም አንድ ቁም ነገር ያካፍለናል፡፡ ምን አለ? ‹ውድቀትና ኃጢአቱን እያነሣ #ራሱን_የሚወቅስና የሚያዋርድ ጥሩ ቢያደርግም ትሑት ተብሎ ግን አይጠራም፡፡ ትሑት ሰው ራሱን ማሳመንና ኅሊናውም ይህን ሐሳብ እንዲይዝ መጫን አይጠበቅበትም፡፡ እንዲኹ ራሱን ምንም አድርጎ ይቆጥራል እንጂ› ሲል አስተማረ፡፡ እንደ ማር ይስሐቅ ትምህርት ከሆነ ትሑት ለመሆን ሲባል ራስን ማስጨነቅ ወደ ትሕትና ጫፍ ለመድረስ ሯጭ (ተጋዳይ) መኾንን የሚያሳይ እንጂ ‹ትሑት› አያሰኝም፡፡
እውነተኞቹ ትሑታን ሌላ የሚጋፋ እና ትግል የሚጠይቅ አንዳች የበላይነት (የእኔነት) ስሜት ሳይሰማቸው እንዲኹ ራሳቸውን የሰው ሁሉ መጨረሻ አድርገው የሚቆጥሩ ናቸው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ባሕታዊም ‹ትሑት ሰው የሚባለው ራሱን የሚሰድብና የሚያዋርድ ሳይሆን፥ ከሌሎች ሰዎች በሚደርስበት ስድብና ትችት ፊት #ፍቅሩ_ሳይቀንስበት መቆም የሚችል ሰው ነው› በማለት ያስተማረው ይኽን የፍጹማኑን ትሕትና ለማሳየት ነው፡፡” [..] *
* [‛ትሕትና ምንድር ነው?’ በሚል ርዕስ ከጻፈው ላይ ያገኘኹት ነው፤ ጨርሳችኹ አንብቡት።]
#ይቀጥላል...
እግዚአብሔር ትኁት ልቡናን ያድለኝ ዘንድ ታናሽ ወንድማችኹ ገብረ ማርያምን በጸሎታችኹ አስቡኝ።
በበረሀው በሀሩሩ በሚያስፈራው በባህሩ
እስራኤልን የታደገው በክንፎቹ የጋረደው ሚካኤል ነው
ሚካኤል ነው አፅናኝ ደጋፊየ
ሚካኤል ነው በዱር በበረሀ
ሚካኤል ነው ነፍሴን ያረካልኝ
ሚካኤል ነው በአለቱ ውሀ
የፊቴ ፈገግታ የውስጤ ፍስሐ
ከአምላክ የተሰጠኝ በረከት አምሀ
አዝ
ሚካኤል ነው መብረቅ ያወረደው
ሚካኤል ነው ጠላት ድል የነሳ
ሚካኤል ነው የባህራን ወዳጅ
ሚካኤል ነው ሀዘኑን ያስረሳ
ፊቱን ያበራለት በእግሮቹ ያቆመው
እንደ እናት እንደአባት ደግሶ የዳረው
አዝ
ሚካኤል ነው ያሳደገኝ መላክ
ሚካኤል ነው በጽድቅ የመራኝ
ሚካኤል ነው ስደክም ያገዘኝ
ሚካኤል ነው ስወድቅ ያነሳኝ
በሀዘኔ ሁሉ የቀደመልኝ
ሚካኤል እርሱ ነው ከጥልቅ ያወጣኝ
አዝ
ሚካኤል ነው ክሴን ያስቀደደ
ሚካኤል ነው የበደሌን እዳ
ሚካኤል ነው በአማላጅነቱ
ሚካኤል ነው ያዳነኝ ከፍዳ
በመንገዴ ሁሉ እኔን እየረዳ
ፍቅሩን ፅፎት አልፏል በልቤ ሰሌዳ
በበረሀው በሀሩሩ በሚያስፈራው በባህሩ
እስራኤልን የታደገው በክንፎቹ የጋረደው ሚካኤል ነው #ውድ-የተዋህዶ- ልጆች - የቅዱስ- ሚካኤል ምልጃ እና- በረከት- አይለየን አሜን፫ #ሀገራችንና ህዝቦቿን ይጠብቅልን አሜን፫
መልካም ቀን
💗🌷💗
🅢🅗🅐🅡🅔
† † †
💖 🕊 💖
👉ቻናላችንን ለመቀላቀል የምትፈልጉ☚ ከላይ☝️☝️ forwarded
Ⓜ️essageየሚለውን ይጫኑት🎯🙏💓💒💒💒
በቅንነት ቴሌግራም ይቀላቀሉ
Or "";Saerching👇
Tewahdotisfafa
150cmx80cm
Price 3500 birr
With free delivery 🚚
የገጠማ አይጨምርም ❗️‼️
👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
@GraceWallArt
(0943448637)
@hani_nata
(0936239392)
ትንሽዬ ምክር ለወንድሞቼ (በተለይ ለወጣቶች)
አንድን ነገር ዓለማዊ ኾኖ ካገኛችኹት ‛ራስኽን አድን፤ #ወደኋላህ_አትይ፥ በዚኽም ዙሪያ ኹሉ አትቁም፤ እንዳትጠፋም ወደ ተራራው #ሸሽተኽ_አምልጥ’ እንደተባለው ከዚያ ነገር ሽ ሽ! በቃ መቋቋም የማትችለው ነገር ከኾነ ሽ ሽ! ‛ራሴን አውቀዋለኹ፤ እቋቋመዋለኹ!’ ብለኽ ኃይልኽን አትጨርስ!
ያንን ነገር በማየትኽ፥ በማሰብኽ ወይም በማድረግኽ ከእግዚአብሔር የምትለይ ከኾነ ያንን ነገር ደግመኽ አትመልከተው! በተረፈ ነገ በዓለ ሲመቱን የምናከብረውን ቅዱስ ሚካኤልን በጸሎታችኹ ጥሩት፤ ‛ሩኅሩኁ መልአክ ምልጃኽ ጥበቃኽ አይለየን’ በሉት።
ታዲያ ታናሻችኹን በጸሎታችኹ መሐል አትዘንጉኝ! ጸሎታችኹ ያስፈልገኛል።
በእንተ ቅዱስ ዳዊት - ፮
‛እኔ ግን #ትል ነኝ ሰውም አይደለሁም፤ የሰው ማላገጫ በሕዝብም ዘንድ #የተናቅኹ ነኝ።’ እዚኽ ላይም የዲያቆን አቤል ካሳሁንን ጽሑፍ ላስነብባችኹና እንቀጥል። “ብዙ ጊዜ በእኛ ዘንድ የተናቀ ልብስ መልበስ፥ አንገት መስበር፥ ዝግ ብሎ ማውራት እና ‹እኔ በደለኛ የማይገባ ሰው ነኝ› እያሉ ደጋግሞ መናገር እንደ ትሑት ያስቆጥር ይኾናል፡፡ ነገር ግን የትሕትና ትርጉም ከዚህም በላይ ነው፡፡ [...]
ትሕትና በእኛ እና በእግዚአብሔር መካከል ያለ #እውነተኛ_ኑሮ ነው፡፡ አንድ ክርስቲያን ስለ ትሕትና ሲያስብ እነዚኽን ኹለት ነገሮች አብሮ በትኩረት ሊያሰላስል ይገባዋል፡፡ እነርሱም አንደኛ ተፈጥሮውን (መሬታዊ፥ ትቢያ መኾኑን) አለመዘንጋት ሲኾን፥ ኹለተኛው ደግሞ ተቀባይነቱን ለዘወትር ማስታወስ ነው፡፡ ሰው በጫማው እየረገጠ የሚራመደው አፈር እንደኾነ ሲያስብ ደካማነቱን ይረዳል፡፡ ስለዚኽም በነገሮች ሁሉ ‹አቤቱ እኛ አፈር እንደ ኾንን አስብ› እያለ ረድዔተ እግዚአብሔርን የሚማጸን ትሑት ይኾናል፡፡ (መዝ. 103፥14)
ተቀባይነቱንም ኹል ጊዜ የሚያስታውስ ከኾነ ለሌሎች በሚያደርጋቸው በጎ ሥራዎች አይኩራራም፡፡ ብልጫም አይሰማውም፡፡ ምክንያቱም የራሱን ሳይኾን ከአምላኩ ከተሰጠው ላይ ቀንሶ የሚያካፍል ምስኪን ምጽዋተኛ ስለኾነ፡፡ ሐዋርያውስ ቢሆን በቆሮንቶስ መልእክቱ በታላቅ ቃል ‹አንተ እንድትበልጥ ማን አድርጎኻል? ያልተቀበልኸውስ ምን አለኽ? የተቀበልኽ ከሆንኽ ግን እንዳልተቀበልኽ የምትመካ ስለምንድር ነው?› ሲል የሚገስጸው ስለዚሁ አይደለምን? (1ኛ ቆሮ. 4፥7)
ሶርያዊው አባት ማር ይስሐቅ ስለ ትሕትና ትርጉም አንድ ቁም ነገር ያካፍለናል፡፡ ምን አለ? ‹ውድቀትና ኃጢአቱን እያነሣ #ራሱን_የሚወቅስና የሚያዋርድ ጥሩ ቢያደርግም ትሑት ተብሎ ግን አይጠራም፡፡ ትሑት ሰው ራሱን ማሳመንና ኅሊናውም ይህን ሐሳብ እንዲይዝ መጫን አይጠበቅበትም፡፡ እንዲኹ ራሱን ምንም አድርጎ ይቆጥራል እንጂ› ሲል አስተማረ፡፡ እንደ ማር ይስሐቅ ትምህርት ከሆነ ትሑት ለመሆን ሲባል ራስን ማስጨነቅ ወደ ትሕትና ጫፍ ለመድረስ ሯጭ (ተጋዳይ) መኾንን የሚያሳይ እንጂ ‹ትሑት› አያሰኝም፡፡
እውነተኞቹ ትሑታን ሌላ የሚጋፋ እና ትግል የሚጠይቅ አንዳች የበላይነት (የእኔነት) ስሜት ሳይሰማቸው እንዲኹ ራሳቸውን የሰው ሁሉ መጨረሻ አድርገው የሚቆጥሩ ናቸው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ባሕታዊም ‹ትሑት ሰው የሚባለው ራሱን የሚሰድብና የሚያዋርድ ሳይሆን፥ ከሌሎች ሰዎች በሚደርስበት ስድብና ትችት ፊት #ፍቅሩ_ሳይቀንስበት መቆም የሚችል ሰው ነው› በማለት ያስተማረው ይኽን የፍጹማኑን ትሕትና ለማሳየት ነው፡፡” [..] *
* [‛ትሕትና ምንድር ነው?’ በሚል ርዕስ ከጻፈው ላይ ያገኘኹት ነው፤ ጨርሳችኹ አንብቡት።]
#ይቀጥላል...
እግዚአብሔር የዳዊትን ታጋሽ ልብ ያድለኝ ዘንድ ታናሽ ወንድማችኹ ገብረ ማርያምን በጸሎታችኹ አስቡኝ።
#የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓላት በዓመት 14 ናቸው
📖1ኛ ህዳር 12 የተሾመበት ዲያብሎስን ድል የነሳበት ህዝበ እስራኤል የመራበት እለት ነው።
📖2ኛ ህዳር 13 በዓለመ መላእክት ያሉ አእላፍ መላእክት በዓለ ሲመቱን ተሰብስበው ያከበሩበት ቀን ነው። ዕለቱ ምነአእላፍ መላእክት ይባላል።
📖3ኛ ታኅሣስ 12 ዱራታወስና ሚስቱ ቲወብስታን የረዳበት ዕለት ነው።
📖4ኛ ጥር 12 የደሃዋን ልጅ ተላፊኖስን የረዳበት ያዕቆብን ከወንድሙ ከኤሳው እጅ የጠበቀበት ዕለት ነው።
📖5ኛ የካቲት 12 የሚበላው የሚጠጣው የሚለብሰው ላጣ አንድ ሰው በሰው አምሳል ተገልጦ ከሀብታም ሲበደር ዋስ የሆነበት ሶምሶንን ረድቶ አህዛብን ያጠፋበት ዕለት ነው።
📖6ኛ መጋቢት 12 ማቴዎስ የተባለውን ሰው እና ሚስቱን ልጆቹን የረዳበት የበለአምን አህያ ያናገረበት ዕለት ነው
📖7ኛ ሚያዝያ 12 አዳምን ወደ ገነት ያስገባበት ኤርሚያስን ከእስር ቤት ያወጣበት ዕለት ነው።
📖8ኛ ግንቦት 12 ዳንኤል በአንበሳ ጉድጓድ ውስጥ ሳለ እንባቆምን ምግብ አስይዞ በአንዲት የእራስ ጠጉሩ አንጠልጥሎ ከኢየሩሳሌም ዳንኤል ወዳለበት ወደ ባቢሎን ወስዶ ዳንኤልን በጉድጓዱ ውስጥ የመገበበት ዕለት ነው።
📖9ኛ ሰኔ 12 ባህራንን ከባህር ያወጣበት አፎምያን ከሰይጣን ያዳነበት ዕለት ነው
📖10ኛ ሐምሌ 12 የደኀይቱን ልጅ ተለሀሶንን ከባህር አውጥቶ የጠበቀበት ንጉሥ ሰናክሬምን ከነሰራዊቱ ደምስሶ ጻድቁ ሕዝቅያስን ያዳነበት ዕለት ነው።
📖11ኛ ነሐሴ 12 ሶስናን ከእደ ረበናት ያዳነበት ንጉሥ ቆስጠንጢኖስን ረድቶ መክስምያኖስን ድል ያደረገበት ዕለት ነው።
📖12ኛ ጳጉሜን 3 ቅዱስ ሩፋኤል ያሳረገው የዕመቱን ጸሎት ዕጣን ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርብበት ዕለት ነው።
📖13ኛ መስከረም 12 ሰማዕቱ ፋሲለደስን የረዳበት ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ነቢዩ ሕዝቅያስ ሂዶ እንዲመክረው ያደረገበት ዕለት ነው።
📖14ኛ ጥቅምት 12 ነቢዩ ሳሙኤል ዳዊትን ቀብቶ እንዲያነግሰው የላከበትና ዳዊትን የረዳበት ዕለት ነው። በዚህ በዓላት ወደ ፈጣሪው 14 ልመናዎችን ያቀርባል።
📖ቅዱስ ያሬድን የቅዱስ ሚካኤል ልመናዎች 14 እንደሆኑ ገልጿል።
📖ወአሰርቱ ወአርባዕቱ ትንብልናከ በማለት ዘምሯል
14ቱ ልመናዎቹ በ 14ቱ በዓላቶቹ በጉልበቱ እየሰገደ ፈጣሪውን ለሰው ምህረት ይቅርታ እንዲደረግላቸው የሚለምናቸው ልመናዎች ናቸው።
እንግዲህ የቅዱስ ሚካኤል በዓላት በየወሩ የዓመት መሆኑን መርሳት የለብንም።
-------------------------
#ሰላም ለአዕዛኒከ
ሚካኤል ሆይ የችግረኛውን ጸሎት ፈጥነው ለሚሰሙ አዕዛኖችህ ሰላምታ ይገባል።የይቅርታ መልአክ ሆይ ችግሬን አቃልልኝ፤ጭንቀቴንም አስወግድልኝ። ምክርን ትለግሰኝ፣ጥበብንም ታስተምረኝ ዘንድ አባት እንዳደረኩህ አንተም ልጅህ አድርገኝ!
❤መልክአ ሚካኤል
📖ወስበሐት ለእግዚአብሔር ይቆየን
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo