ortodoxtewahedoo | Unsorted

Telegram-канал ortodoxtewahedoo - ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

3754

ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ። ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ›› ት.ኢሳ 58÷3 https://youtu.be/csxxAMGtC4I ለመቀላቀል http://t.me/ortodoxtewahedo

Subscribe to a channel

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ጾመ ነቢያት (Nativity Fast) - ኪዳን ዘኢየሱስ እንደከተበው

ቤተ ክርስቲያናችን ከጌታ ልደት በፊት ያሉትን 40 ቀናት በጾም እንድናሳልፍ ታዘናለች። ይኽም ሙሴ አሠርቱ ቃላትን ለመቀበል በሲና ተራራ የጾመውን 40 ቀናት ይወክልልናል። ሙሴ አሠርቱ ቃላትን ለመቀበል 40 ቀናት እንደ ጾመ እኛም ደግሞ የአካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋዌ (Incarnation of the Logos) ለመቀበል እንዲሁ #40_ቀናትን እንጾማለን።

የአዳም መድኃኒት፥ የነቢያት ትንቢታቸው "እጅኽን ከአርያም ላክ ናና አድነን" እያሉ የለመኑት፥ የ5500 ዓመት ተስፋቸው፥ ለሙሴ የመጀመርያ ስሙን በየውጣ የነገረው (የውጣ ማለት Iota ከሚለው የግሪክ እና ኮፕቲች ፊደል የመጣ ነው በኮፕቲክ አሥር የሚለው ቃል በIota ፊደል ይጀምራል፥ ኢየሱስ የሚለው ስምም በግሪክም በኮፕቲክ በIota ፊደል ይጀምራል። ስለዚህ Iota , the name of salvation of our Lord የጌታ የማዳኑ ስም ተብሏል። (ውዳሴ ማርያም ዘእሑድ) ሙሴ አሠርቱ ቃላትን እንደተቀበለ አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና)፥ የኢያሱ ስሙ ኃይል (ኢያሱ እና ኢየሱስ ማለት ትርጉሙ አንድ ሲኾን ያህዌ ያድን ማለት ነው፥ መድኃኒት ተብሎም ይተረጎማል)፥ የኤልያስ መሶበ ወርቅ ውስጥ ያለ መናበዳዊት ዙፋን ለዘላለም የሚነግሥ የንግሥናው ፈጻሚ፥ የሰሎሞን ጥበብ "ጥበብሰ መድኃኒነ ውእቱ - ጥበብስ መድኃኒታችን ነው" (ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ) የተባለለት፥ የነቢያት ትንቢት ኹሉ ፈጻሚ፥ አዳኙ፥ አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ሊወለድ ነውና የተስፋውን ቀን በመጠባበቅ እኛም ከነቢያት ጋር እንጾማለን።

"የበዓል ቀን ሊመጣ ነው። እርሱም ከኹሉም በዓላት በላይ እጅግ የተቀደሰ እና ያማረ ነው፥ የተቀደሱ ቀናት ኹሉ አለቃ እና እናት ብለን ብንጠራው ስህተት አይኾንም። ይሄም በዓል #የክርስቶስ_ልደት ቀን ነው።" — ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

እሑድ ኅዳር 15 ይገባልና ለነቢያት ጾም እንኳን አደረሳችኹ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Biruk, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ነቢያት ጌታ "ይወርዳል ይወለዳል" ብለው የተናገሩት ትንቢት እንዲፈጸም ተመኝተው ጾሙ ጸለዩ:: እኛ ስለምን እንጾማለን? ክርስቶስ ተወልዶ ፣ ተጠምቆ ፣ አስተምሮ ፣ ተሰቅሎ ፣ ሞቶ ፣ ተነሥቶ ፣ ዐርጎ ፣ በአባቱ ቀኝ አይደለምን? አሁን ለምን እንጾማለን? ብለን እናስባለን::

ጌታ በእኔና አንተ ልብ ውስጥ እውነት ተወልዶአልን? እውነት የእኛ ልብ እንደ ቤተልሔም ግርግም ለክርስቶስ ማደሪያ ሆኖአል? ማደሪያ አሳጥተን ከእናቱ ጋር አልመለስነውም?

የጥምቀቱ ትሕትና በእኛ ልብ መቼ ደረሰ? የስቅለቱ ሕማም መች በእኛ ሕሊና ተጻፈ? የትንሣኤው ተስፋ የዕርገቱ ልዕልና በእኛ ልቡና መቼ ዐረፈ?

ስለዚህ ነቢያት "ውረድ ተወለድ" ብለው የጾሙትን ጾም እንጾማለን:: ጌታ ሆይ በእኔ ሕይወትም ውስጥ ውረድ ተወለድ የእኔን ሰውነት ማደሪያህ አድርገው:: ሕዋሳቶቼ ከኃጢአት አርፈው እንደ ቤተልሔም ግርግም ማደሪያህ ይሁኑ:: 

የቤተልሔም እንስሳት ትንፋሽ ገበሩልህ ፣ የቢታንያ ድንጋዮች ዘማሪ ቢጠፋ ሊዘምሩ ዝግጁ ነበሩ ፣ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ለክብርህ ተቀደደ ፣ ጨረቃ ላንተ ደም ለበሰች ፣ ፀሐይ ስላንተ ጨለመች ፣ ከዋክብት ለስምህ ረገፉ ፣ ዓለቶች ለፍቅርህ ተሰነጠቁ::

ከቤተልሔም እንስሳት ፣ ከቢታንያ ድንጋዮች ፣ ከቤተ መቅደስ መጋረጃ እኔ እንዴት አንሼ ልገኝ? የቢታንያ ድንጋይ ያወቀህን ያህል ሳላውቅህ ፣ የቤተ መቅደስ መጋረጃ የተረዳህን ያህል ሳልረዳህ እንዴት ልኑር? 

ዓለት ላንተ ሲሰነጠቅ የኔ ልብ ለምን ከዓለት ደነደነ? ጨረቃ ደም ስታለቅስ እኔ መከራህ ለምን አልተሰማኝም?
ሙታን በሞትህ ሲነሡ እኔ ምነው ከኃጢአት ሞት መነሣት ተሳነኝ?

ለዚህ ነው በእኔ ሕይወት ገና አልተወለድክም የምለው::

ስለዚህ ጌታ ሆይ የነቢያትህን ጾም ጸሎት ሰምተህ የወረድህ የተወለድህ ጌታ ሆይ በእኔም ሕይወት ውረድ ተወለድና እኔም ከመላእክት ጋር አብሬ ልዘምር ፣ ከሰብአ ሰገል ጋር ሥጦታህን ልቁጠር ፣ ከእረኞች ጋራ ልደነቅ:: ልደትህ ሳይገባኝ ምጽዓትህ እንዳይደርስብኝ እርዳኝ::

(ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)

@ortodoxtewahedo

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

"እግዚአብሔር አምላክ ለአገልጋዮቹ የሚልቅ ጸጋን ከሰጠ፣ የሚነኩት ኹሉ ሰው ከበሽታው ከተፈወሰ፤ ጥላቸው ያረፈበት ተዓምር ከተፈጸመለት፤ ጴጥሮስ በጥላው ካደነ፤ የጳውሎስ የልብሱ ጨርቅ ዕራፊ መናፍስትን ካወጣ ከሁሉ ለምትልቅ እናቱማ ምን ዓይነት ሥልጣንና ኃይል ተሰጥቷት ይሆን?"

#ቅዱስ_ባስልዮስ

"If the Lord God gives great grace to His servants, if everyone they touch is healed of the disease, if a miracle is done for them to rest in their shadow, if Peter is hunted by the shadow, if the fabric of Paul's clothes casts out evil spirits, what kind of authority and power has been given to the greatest mother?"

#Saint_Basilios

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

+++መንገድ መሪው ሰማእት+++
[ሚናስን የሚወደው ሚናስ]

በአንድ ወቅት የካይሮ ዴር ኤል ማላክ ኤልባህሪ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሊቀ ካህናት የሆኑት ቄስ ሚካኤል አብድ ኤል ሜሳህ ፤ ከ18 ካህናት ጋር በሰማእቱ ቅዱስ ሚናስ ገዳም የነበሩትን ፤ አቡነ ቄርሎስ 6ኛን(መነኩሴው ሚናስን) ለማነጋገር ጉዞ አድርገው ነበር። በወቅቱ ባሂግ ከተባለችው መንደር እስከ ገዳሙ ያለው መንገድ ያልተሠራ በመሆኑ ፤ መንገደኞች የሰው የእግር ምልክት እና የመንገድ ጥርጊያ እየተከተሉ ነበር ወደ ገዳሙ የሚጓዙት። ካህናቱ በመኪና ብዙ ከተጓዙ በኋላ መንገድ ስተው ኖሮ ፤ ራሳቸውን የበረኃው መካከል ላይ አገኙት። ለመ'መለስ እንኳን ቢሞክሩ መንገዱን መለየት የማይችሉበት አጣብቂኝ ኹኔታ ውስጥ ገቡ።

ከቦታው በረኃማነት የተነሣ ሊመራቸው የሚችል ሰው እንኳን ሊገኝ የሚችልበት ዕድል አልነበረም። ድንገት አንድ በረኽኛ ወጣት ወደ እነርሱ ቀርቦ "ወደ ቅዱስ ሚናስ ገዳም መሔድ ፈልጋችሁ ነው?" አላቸው። አስደንጋጭ ክስተት ነበር ፤ ሊቀ ካህኑም በደስታ "አዎ ወደዚያ መሔድ እንፈልጋለን" አሉት። እርሱም በሾፌሩ በኩል ሆኖ ገዳሙ ጋር እስኪደርሱ ድረስ መንገዱን መራቸው። ካህናቱም ከበረኃማው ስፋት የተነሣ እንዳይጠፉ የረዳቸውን ጌታችን መድኃኒትችን ኢየሱስ ክርስቶስን በፍጹም ልባቸው አመሰገኑ።

ካህናቱ መነኩሴው ሚናስ (አቡነ ቄርሎስ 6ኛ) ከገዳሙ በር ላይ እየጠበቋቸው ሲመለከቱ የበለጠ ተደነቁ። አቡነ ቄርሎስም በፍጹም አባታዊ ፍቅር እና አቀባበል ፤ ሊቀ ካህኑን "ልጄ ምን ሆናችሁ ነው? መንገድ ጠፋባችሁ እንዴ?" አሉት። ሊቀ ካህኑ ሚካኤልም "አዎ መንገድ ጠፍቶብን ነበር ፤ እግዚአብሔር ግን አንድ በረኽኛ ወጣት ልኮልን እስከ ገዳሙ እየመራ አደረሰን" በማለት መለሱ። አቡነ ቄርሎስም ፈገግ ብለው "የታለ ታዲያ ያ በረኽኛ ወጣት?" ብለው ጠየቁ። ሊቀ ካህኑም ሊፈልጉት ዞር ዞር አሉ ፤ ግን አላገኙትም ፤ ወደ መነኩሴው ሚናስ ተመልሰው "አሁን የት እንደሄደ እንጃ አላገኘሁትም የለም" አሉ።

አቡነ ቄርሎስም በልዩ ደስታ እና ፈገግታ ውስጥ ሆነው ፤ "ልጄ መንገድ እንደጠፋባችሁ አውቄ ፤ ሰማእቱ ሚናስን የላኩላችሁ እኔ ነኝ" አሉት። ካህናቱ ሁሉ በሰማእቱ ሚናስና በአቡነ ቄርሎስ 6ኛ(መነኩሴው ሚናስ) መካከል ያለው መንፈሳዊ ግንኙነት እያስደነቃቸው ፤ እግዚአብሔርን አመሰገኑ!!!

+++

+ የሰማእቱ የቅዱስ ሚናስ ፤ የአባታችን የአቡነ ቄርሎስ በረከት ረድኤት ልመናና ጸሎት አይለየን!!!

Source: The Great Egyptian and Coptic Martyr, The Miraculous Saint Mina, Published by Saint Mina Coptic Orthodox Monastery

ስብሐት ለእግዚአብሔር
ዲያቆን ደረጀ ድንቁ
ኅዳር 14 2016 ዓ.ም

@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ነገ የፍስክ ምግብ ይበላል?

ጾሙ የሚገባው በ15 ስለኾነ አይበላም፤ በሰዓትም አይጾምም።

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Ĵøķ€ŕ, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Seni, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello ..., welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello @HAILEMARYAM HABTAMU, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Medi Love, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Esuma awo GN yaw kefetari gar yetebeke genegnunet kelele fetena yetelal eko

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ልጅን #የመስጠት #ቃልኪዳን #ያለው #የሾላው #እምነት #ፍሬ
#ሾላዋ #ማርያም #ለደጅሽ አብቂኝ በሏት #ከካንሰር፣#ከማይግሪን፣#ከአስም ሁሉ #የሚፈውሰው #የድንግል #ማርያም #የሾላ #ፍሬ እምነት

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስና ኢትዮጵያን በቅንነት ያገለገሉ ባለውለታዎች በግፍ የተገደሉበት ሃምሳኛ ዓመት የጸሎት ሥነ ሥርዓት ተካሄደ፡፡

የጸሎት ሥነ ሥርዓቱ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ኅዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን ሃምሳኛ ዓመታቸው የተዘከረላቸው ሰማዕታት ኅዳር 14 ቀን 1967 ዓ.ም በደርግ የተገደሉ አባቶች እና ሐምሌ 7 ቀን 1971 ዓ.ም ከእስር ቤት በሰንሰለት እየታሰሩ ተወስደው የተገደሉ ናቸው፡፡

ከሰብአዊነት ውጭ በሆነ በግፍና በሚያሰቅቅ ሁኔታ በገመድ ታንቀው የተገደሉት ሁለተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስም በወቅት ከተገደሉት ሰማዕታት ውስጥ ናቸው፡፡

ኅዳር 14 ቀን 1967 ዓ.ም የተገደሉት ኢትዮጵያውያን ሲቪል ባለሥልጣናት፣ ወታደራዊ መኮንኖችና ከዐምስት ዓመት በኋላ በ1971 ዓ.ም በሰንሰለት እየታሠሩ በግፍና በስቃይ በደርግ የተገደሉት አባቶች የመታሰቢያ ሐውልትና ዐጽማቸው ያረፈበት ቦታ በዘመናዊ አሠራር ለጉብኝት በሚያመች ሁኔታ በመንበረ ጸባዖት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተሠርቶላቸዋል፡፡

በ1971 ዓ.ም የተሰውት የሰማዕቱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ዐጽም ሐምሌ 4 ቀን 1984 ዓ.ም አሟሟታቸውንና የት እንደተቀበሩ በዐይኑ ባየ በወቅቱ የደርግ ደኅንነት ክፍል ወታደር ጥቆማ ወጥቶ ሐምሌ 4 ቀን 1984 ዓ.ም በጎፋ ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በክብር አርፏል፡፡

በጸሎት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የእንግሊዝና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ፣ የምሥራቅ ጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ እና የቀድሞ የኢፌድሪ ፕሪዚዳንት ክብርት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ተገኝተዋል፡፡

ዘገባው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት ነው ።

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Demoze, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ጾመ ነቢያት !

ይህ ፆም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን አበው ነብያት የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መውረድ መወለድ በትንቢት መነፅር እየተመለከቱ የፆሙት ታላቅ ፆም ነው።

ዛሬም እኛ ክርስቲያኖች የአባቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በፆምና በፀሎት ወቅቱን በማሳለፍ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ዝቅ አድርጎ ወደ አለም መምጣቱንና የዓለም ቤዛ መሆኑን የምናስብበት ነው።

ይህንን ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ብዙ ቅዱሳን ጾመውታል፤ በዚህም ምክንያት የሚከተሉት ስያሜዎች አሉት፡፡ እነርሱም፤

፩.  ጾመ አዳም:- አዳም ዕፀ በለስን በልቶ ከገት ከተባረረ በኋላ; በፈጸመው በደል አዝኖ ፥ ተክዞ፤ አለቀሰ (እንባ ቢያልቅበት እዥ እስከሚያፈስ፤ እዥ ቢያልቅበት ደም በዓይኑ እስከሚፈስና ዓይኑ ይቡስ ወይም ደረቅ እስከሚሆን ድረስ አለቀሰ) ፥ ጾመ፣ ጸለየ፡፡ ከልብ የሆነ ጸጸቱን፣ ዕንባውን፣ በራሱ መፍረዱንም እግዚአብሔር አይቶ ተስፋ ድኅነት ሰጠው፡፡ ‹‹ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ፣ በደጅህ ድኼ፣ በዕፀ መስቀል ተሰቅዬ፣ ሞቼ አድንሃለሁ፡፡›› የሚል ነው፡፡ /ገላ. ፬፥፬፣ መጽ.ቀሌምንጦስ/ ስለዚህ ጾሙ የተሰጠው ተስፋ ፥ የተቆጠረው ሱባኤ ስለተፈጸመበት ‹‹ጾመ አዳም›› ይባላል፡፡

፪. ጾመ ነቢያት:- ነቢያትም የምሥጢረ ሥጋዌ ነገር ተገለጦ ስለታያቸው፣ ክርስቶስ ለሰው ልጅ የሚከፍለውን የፍቅር ዋጋ በትንቢት ተመልክተው ጾመውታልና ጾመ ነቢያት ይባላል፡፡ ይህ ጾም ከአባታችን አዳም እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ የተነሱ አበውና እናቶች: ድኅነትንና ረድኤትን ሲሹ የጾሙት ጾም ነው:: በተለይ አባታችን አዳም: ቅዱስ ሙሴ: ቅዱስ ኤልያስ፣ ቅዱስ ዳንኤል ና ቅዱስ ዳዊት በጾማቸው የተመሰከረላቸው ቅዱሳን ናቸው:: (ዘዳ 9:19, ነገ. 19:8, ዳን. 9:3፣ መዝ. 68:10, 108:24) ቅዱሳን ነቢያት በጭንቅ በመከራ ሆነው የጾሙት ጾም ወደ መንበረ ጸባኦት ደርሶ: ወልድን ከዙፋኑ ስቦታል:: ለሞትም አብቅቶታል::

፫. ጾመ ሐዋርያት:- ሐዋርያት ‹‹ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብራለን፣ ልደትን ምን ሥራ ሠርተን እናከብረዋለን?›› ብለው ከልደተ ክርስቶስ በፊት ያሉትን ፵፫ ዕለታት ጾመዋልና፡፡

፬. ጾመ ማርያም:-  እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር አምላክ ቅድስናዋን አይቶ በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ወልደ አምላክን ያለ ሰስሎተ ድንግልና በግብረ መንፈስ ቅዱስ ጸንሳ እንደምትወልደው ቢነግራትም የትሕትና እናት ናትና ‹‹ምን ሠርቼ የሰማይና ምድርን ፈጣሪ እችለዋለሁ?›› ብላ ጌታን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማለችና ‹‹ጾመ ማርያም›› ይባላል፡፡

፭. ጾመ ፊልጶስ:- ሐዋርያው ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ እያስተማረ ሳለ በሰማዕትነት ሲሞት፤ አስክሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ፤ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስክሬን እንዲገለጽላቸው ከኅዳር ፲፮ ጀምረው ጾመው በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስክሬን ተመልሶላቸዋል፤ ነገር ግን አስከሬኑ ቢመለስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል፡፡

፮. ጾመ ስብከት:- የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት፥ የሰው ልጆች ተስፋ የተመሰከረበት፥ የምስራች የተነገረበት ስለሆነ ጾመ ስብከትም ይባላል፡፡

፯. ጾመ ልደት:- የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት ስለሆነ ‹‹ጾመ ልደት›› ይባላል፡፡

ጾምን ትእዛዝ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን የፍቅርና የበረከት ምንጭ በመሆኑ ጭምር ደስ እያለን ብንጾመው የቅዱሳኑ በረከት ያድርብናል፡፡ ፆመ ነብያት ወይም የገና ፆም ሐሙስ ህዳር 15 ይጀምራል ታህሳስ 29 ይፈታል።

ሀገራችንም ሃገረ ሰላም እንድትሆን እና ለእኛ ለህዝቦቻ መተሳስብ ፍቅር አንድነቱን እንዲያድለን ወደ ፈጣሪያችን አብዝተን እንፀልይ !!!

መሰረቷ ጉልላቷ እሱ ነው ሙሽራዋም መስቀል ላይ የሞተው ዛሬም ነገም ያውነው ለዘላለም አትንገሩን አዲስ ጌታ የለም

#ሊቀ መዘምራን ቴድሮስ ዮሴፍ

ለመቀላቀል
👉 @ortodoxtewahedo

is the foundation, the dome, and the bridegroom died on the cross. Don't tell us today, tomorrow, forever. There is no new Lord.

#Choir Tedros Yosef

to join
👉 @ortodoxtewahedo

📔📒📕📗📘📙📙📚📔

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ሰንበተ ክርስትያን

እሑድ ማለት"አሐደ" ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲኾን ትርጉሙ የመጀመሪያ እንደማለት ነው። ይኽች ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ "ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን " በመባል ትታወቃለች።

ዮሐንስም በራዕዩ "የጌታ ቀን" ያላት ናት
(ራዕይ 1፥10)

ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ "ዕለተ እግዚአብሔር" የሚላት ዕለተ እሑድ ናት።

መልካም ዕለተ ሰንበት ይኹንልን

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ይህ አይነት ሀሳብ አልፎበታል ወዳጄ

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello JJ, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

በውጭው ካሉት ይልቅ በአንተ ውስጥ የሚገኙት ፍትወታት ጠንካራ ጠላቶችህ ናቸው። ልክ ያልተሠራለት ምኞት ከባቢሎን እሳት ይልቅ ያቃጥላል። አልጠግብ ባይነትም ከጥፋት ውኃ ይልቅ ያሰጥማል። ያልተገራ ፍላጎት ማንነትን አስጥሎ የሰይጣን ባሪያ ያደርጋል። ራስን መግዛት የሰው ልጆች ጌጥ ነው። ዮሴፍ ግብጽን ከፈርዖን ሁለተኛ ሆኖ ከገዛበት ታላቅ ሥልጣን ይልቅ፥ በጌታው ሚስት ፊት ያሳየው ራስን መግዛት ይበልጥ ይደነቃል። ጠቢቡ "በመንፈሱ ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስዱ (ከሚገዙ) ይበልጣል" እንዳለ። (ምሳ 16፥32)

ራስህን ነጻ ማውጣት ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ ከውስጥህ ጀምር። ሁል ጊዜ ካልበላሁ የሚለው ሆድህ ስስት አስለምዶ በወንድምህ ላይ ጨካኝ እንዳያደርግህ #ለሰውነትህ_ጾም_አስተምረው "ነገ እሞታለሁና ልብላ ልጠጣ" የሚለውን የዐሣማ ፍልስፍናህን (Pig philosophy) ተውና አንተ በፈቃድህ እየተራብህ (እየጾምህ) ያለ ፈቃዱ የተራበው ወንድምህን በምጽዋት አጥግበው።

ጌታ ወደ ገሊላ የተመለሰው ሄሮድስ ከሞተ በኋላ ነበር። (ማቴ 2፥20) አንተ ውስጥ ያለውን ሄሮድስ የተባለ ክፉ ምኞት እንዲሞት ካላደረግኸው በቀር የተሰደደው ክርስቶስ ወደ አንተ ሊመለስ አይችልም። ይህ ክርስቶስን ከልብህ የሚያሳድድብህን ሄሮድስ እንዴት ልትገድለው ትችላለህ? እርሱንስ ወግተህ የምትጥልበት የብረት ካስማ ምን ይሆን? ለዚህስ ከጾም እና ከጸሎት የሚበረታ ምንም ዓይነት የጦር ዕቃ አታገኝም። በል እነዚህን ይዘህ ዝመትበት።

መልካም የነቢያት ጾም ይሁንልን!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello ጎዶልያስ, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Hello ብራዘር, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Ere egzabher yalew yihonal wendme fetena lebego nw

Читать полностью…
Subscribe to a channel