ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ። ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ›› ት.ኢሳ 58÷3 https://youtu.be/csxxAMGtC4I ለመቀላቀል http://t.me/ortodoxtewahedo
Hello Emu, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…Geta becherinetu yibarkih memihirachin
Читать полностью…✞✞ጥያቄ✞✞
➥ ቤተክርስቲያን የማትቀበለው ጉባኤ ከተዘረዘሩት ውስጥ የቱ ነው?
ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖
ኪዳነ ምህረት እንወድሻለን
ለግዚአብሔር ታቦቱ መቅደሱ
ቀርበናል ባንቺ ወደ ንጉሱ
የክብራችን ጌጥ ሽልማት
እንወድሻለን ኪዳነምህት
በጨለማው ላለ ብርሃንን አየ
ለርስቱ ተካፋይ እንዲሆን ተለየ
ወደ ቀድሞ ክብሩ ሊመለስ ዳግመኛ
አንቺ ነበርሽ ተስፍው ለአዳም መዳኛ
አዝ===========
ያንን ሁሉ ዘመናት የፈሰሰው ደም
አለምን ከእስራት ሊፈታ አልቻለም
ወደ ሚሻል ኪዳን በደም ሊያሻግረን
ደምሽን ተዋህዶ መዳኃኒ አለም ዋጀን
አዝ===========
አለን ብዙ ምክንያት አንቺን ምንወድበት
ዓለም ያልተረዳው ያላወቀው እውነት
ያወቀ የተረዳ የመዳኑን ሚስጢር
አያፍርም ክብርሽን ቆሞ ለመናገር
አዝ===========
አውቃለሁ እግዚአብሔር የሰጠሽን ክብር
ላመስግንሽ እኔም ሳልጨምር ሳልቀንስ
ሚባርክሽ ብሩክ ነውና እናቴ
ኪዳነ ምህረት ንገሽ እመቤቴ
አዝ===========
ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖
#ኪዳነ_ምህረት_ልዩ_ነሽ_ለኔ
ኪዳነ ምህረት ልዩ ነሽ ለኔ
ሳዝን ስጨነቅ አትራቂኝ ከጎኔ
የችግሬ ደራሽ እመ እግዚአብሔር
ቃል ኪዳንሽ ይርዳኝ ካንቺ ጋር ልኑር(፪)
#አዝ
የአዳም ተስፋው ነሽ የሴት ቸርነቱ
ኪዳነምህረት ነሽ የኖህ ምልክቱ
አዳም ደጅ የጠናሽ ሲገባ ንስሀ
ኖህም ድኖብሻል ከጥፋቱ ውሃ
#አዝ
የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ
ማርያም አንቺ ነሽ የፈጣሪ እናቱ
የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ
እመብርሃን ስሚኝ ልመናየን ሁሉ
#አዝ
የሰሎሞን አክሊል የዳዊት ዝማሬ
ድንግል መሆንሽን ትመስክር ከንፈሬ
ለተጠማው ውሻ የሚራራው ልብሽ
ለኔም እራርቶልኝ አስታርቂኝ ከልጅሽ
#አዝ
የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ
ማርያም አንች ነሽ የፈጣሪ እናቱ
የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ
እመብርሃን ስሚኝ ልመናዬን ሁሉ
ዘማሪት ሲስተር ፋሲካ መኮንን
ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖
ኪዳነ ምህረት | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖
❤አልረሳውም ያንን ዕለት❤
አልረሳውም ያንን ዕለት
አልዘነጋው ያን ደግነት
እናቴ ሆይ ምልሽ ኪዳነ ምሕረት
እምዬ ሆይ ምልሽ ኪዳነ ምሕረት
ስላለኝ ነው ምክንያት/፪/
ለሠው ተናግሬ ያልተረዳኝ ሰው
ዕንባዬ በምሬት ከዓይኔ የሚፈሰው
የቤቴን ገመና ሁሉን ስነግርሽ
አዛኝ እህት ነሽና እራራልኝ ልብሽ
አረሳው መቼም የአንቺን ደግነት/፪/
ውለታ አለብኝ ኪዳነ ምሕረት
አዝ__
ልቤ በሐዘን ጠቁሮ ውስጤ እየደማ
በቅረዜ ሲጨልም ስጓዝ በጨለማ
በራፌን ዘግቼ ዝምብዬ አለቅሳለሁ
አይኔን አቀርቅሬ እናቴ እልሻለሁ
ዘንበል አልሽልኝ ሠምተሽ ፆሎቴን/፪/
አልተጸየፍሽም ብቸኝነቴን
አዝ__
እናት የለኝ ብዬ ከቶም አልከፋ
እኔስ አይቻለሁ ስትሞይኝ በተስፋ
ምድራዋዊ እናቴ ለጊዜው ነው ፍቅሯ
ያንቺስ ግን ልዩ ነው እረ ስንቱን ላውራ
ማርያም ማርያም ብል አልሠለችሽ/፪/
በልቤ ጽላት ስለ ታተምሽ
አዝ___
ሲረበኝ መጥተሻል ሲጠመኝ ደርሰሻል
ለጎደለው ቤቴ በረከት ሆነሻል
ጭንቄም ቀለለልኝ ሐዘኔም ራቀ
ያስጨነቀኝ ጠላት ራሱ ተጨነቀ
መዳኒት ወልደሽ ዳኩኝ ከመሜ/፪/
ይኸው ዘመርኩኝ በምልጃሽ ቆሜ
ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖
Hello Golden, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…ጾመ ነበያት ከህዳር 15-18 ድረስ ባለው ቀናት ውስጥ ይጾማል የሚል ጽሁፍ አምብቤ ነበር እንደትነው ሚሆነው ለነ ግልጽ አይደለም
Читать полностью…Hello Wagaye, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…Hello Heavi_ii, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью… †
🕊 [ እንኳን አደረሰን ! ] 🕊
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 [ ጾም ] 🕊
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ምዕመናን እንዲጾሟቸው የሠራቻቸው ፯ [ 7 ] አጽዋማት አሏት:: " ጾም " ማለት "መከልከል" ነው::
የምንከለከለው ደግሞ ከኃጢአትና ከክፋት ሲሆን አንድም ሰውነትን ወደዚያ ከሚወስዱ መባልዕት መከልከልን ይመለከታል::
ጾም ለክፉ ሥራ ከሚያነሣሱ የምግብ ዓይነቶች መከልከል ወይም ለተወሰነ ጊዜና ሰዓት ሰውነት ከሚፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ መወሰን [ መታቀብ ] ማለት ነው፡፡ ለሰውነት የሚያምረውንና የሚያስጎመዠውን ነገር ሁሉ ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ብሎ መተው ነው፡፡
ጾም ከመንፈሳዊ ተጋድሎዎች አንዱ ነው፡፡ ለሥጋም መንፈሳዊ ልጓም ነው፡፡ ጸዋሚ ሰው ፈቃደ ሥጋውን እየገታ ነፍሱን የሚያለማምድበት ስንቅ ነው፡፡ "ጾም ቁስለ ነፍስን የምትፈውስ ፤ ኃይለ ፍትወትን የምታደክም ፤ የበጎ ምግባራት ሁሉ መጀመሪያ ፤ ከእግዚአብሔር ጸጋን የምታሰጥ ፤ የወንጌል ሥራ መጀመሪያ ፤ የጽሙዳን ክብራቸው ፤ የድንግልና የንጽሕና ጌጣቸው ፤ የንጽሕና መገለጫ ፤ የጸሎት ምክንያት እናት ፤ የዕንባ መገኛ መፍለቂያዋ ፤ አርምሞን የምታስተምር ፤ ለበጎ ሥራ ሁሉ የምታነቃቃ ፣ ሰውነትን በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትሕትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ መድኃኒተ ነፍስ ናት፡፡" [ማር ይስሐቅ አንቀጽ ፬፥፮]
ጾም ተድላ ሥጋን የምታጠፋ ፥ የሥጋን ጾር የምታደክም ፥ ቁስለ ነፍስን የምታደርቅ ፥ ለጎልማሶች ጸጥታንና ዕርጋታን የምታስተምር ፥ ከግብረ እንስሳዊ የምትከለክል ፥ ሰው መላእክትን መስሎ የሚኖርባትና ኃይል መንፈሳዊን የሚጎናጸፍባት ደገኛ መሣሪያ ናት፡፡ ከኃጢአት ፆር ከፍትወት አንዱንም አንዱን ድል ለመንሳት ለማጥፋት ፥ የዲያብሎስን ረቂቅ ፍላጻ ለመመከት በጾም መድከም የሥራ ሁሉ መጀመሪያ እንደሆነች የታወቀ ነው፡፡ ጾም ምህረት መለመኛ ፥ የንስሐ መገለጫ ፥ ከመከራ የሚሠወሩባት ፥ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር አስታርቃ ርስት መንግሥተ ሰማያት የምታስገባ "ኆኅተ ጽድቅ - የጽድቅ በር" ሆና የተሰጠች ቀዳማዊት ሕግ ናት፡፡
[ እንኳን ለጾመ ነቢያት [ የገና ጾም ] በሰላም አደረሳችሁ ! ]
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
Hello 😁, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…በእውንት ትልቅ ትምህርት ነው ቃለህውት ያሰማልን በእድሜ በፀጋ ይጠብቅልን
Читать полностью…Getachin ke ilete arb iske ihud bemeqabir yeqoyew gize Indet sost qen ina sost lelit molaw
Читать полностью…ይነበብ
"የኔ ፍቅር እስቲ ዛሬ ስጋ ጋብዘኝ"የሚል ድምጿ ነበር ከሀሳቤ ብንን ያደረገኝ፡፡ገና ከተዋወቅን'ኳ ሁለት ሳምንታችን እኮ ነው፡፡ሳያት.. ወጪ አታስወጣም፤ መጠጥ አጠጣም፤ ጨዋ ናት ብዬ ነበር የቀረብኳት፡፡ምክንያቱም እኔ ቁርስ ዘልዬ ምሳ አማካኝ ሰአት በልቼ እራቴን በማሰብ ብቻ የማሳልፍ መናጢ ደሀ ነኝ፡፡እሷን ቁርጥ ጋበዝኩ ማለት የወር ደሞዜን ለአንድ ወፍራም የስጋ ቤት ባለቤት በነፃ ገበርኩ ማለት ነው....
በዛላይ ወይን መጠጣት እንዴት እንዳማረኝ .....(ስትል ጭራሽ በተቀመጥኩበት ፌንት ልበላ!!!ሰይጣን ጎኔ የተቀመጠ ያህል አማትቤ እሷ መሆኗን ለማረጋገጥም ቃጣኝ፡፡ "እቺማ እሷ አደለችም'' እያለም ልቤ ይሞግተኝ ገባ።እሷ ግን እራሷ ፍሬዬ ናት...
እ....እሺ ችግር የለውም፡፡ማለቴ ትንሽ መሸት ቢል አይሻልም??(አልኳት ተበድሬ ያልመለስኩላቸውን ሰወች ቆጥሬ ስጨርስ ሌላ ምበደረውን ሰው እያሰላሰልኩ
እን..ዴ ፍቅር ቀን ነው እንጂ ሚጀመረው፡፡ ማታማ ታውቅ የለ....(ተሸኮረመመች፡፡ለካ የአልጋም አለብኝ!!!ነገሩ ይበለኝ....በዚ ኑሮ ውድነት እኔን የመሠለ መናጢ ሴት ጋ ምን ይሰራል?!ምንም፡፡እኮ ይበለኛ!!!
ፍሬ ከወትሮዋ ለየት ብላ ስትቅበጠበጥ ነገሯ አላማረኝም፡፡ከኑሮዬ ጋ ትመጥናለች ታረጋጋኛለች ለትዳር ትሆናለች ብዬ ብቀርባት ገና በቀናት ውስጥ ኑሮዬ ልትገለባብጠው የመጣች መቅሰፍ ሆና ታየቺኝ፡፡ምናልባት ደሞ የምትመርጠው ቤት ትልቅ ከሆነስ??.....(እንባ እንባ እያለኝ ተከተልኳት
የኔ ፍቅር እዚ ይሻለናል አደል...?(መስቀያው ላይ ነጭ ነገር ያንጠለጠለ ስጋ ቤት እያሳየቺኝ...ደነገጥኩ፡፡ስጋ ቀይ አልነበር እንዴ???መልኩን ቀይሮ ነው?
አይ እዚህማ ግርግሩ ጫጫታው እያልኩ ዘላብጄ ረከስ ያለውን ቤት ፍለጋ አይኔን ሳማትር ፍሬ እጄን እንደያዘች ከፊታችን ወዳለ ቤተክርስትያን አመራች....
የት ነው ምትሄጂው ፍቅር??(አልኳት መተንፈሻ ጊዜ ስላገኘሁ ልቤ ጮቤ እየረገጠ
ስጋ ቤት(አለች ፈገግ ብላ እያየቺኝ
እሱማ አዎ.. ታድያ እዚህ..
እኮ ስጋ ቤቱኮ እዚህ ነው፡፡(ነጠላዋን ከቦርሳዋ አውጥታ አንዱን ሰጥታኝ አንዱን እራሷ እያጣፋች
አልገባኝም!!
የኔ ፍቅር ለዘመናት እያየን ባላየን እየሰማን ባልሰማ ያለፍነው ምርጡ ስጋ ቤት ይኼ ነው!!
አየህ ፆም መያዣ ሲባል ሁሉም የሚመጣለት የበሬው ስጋ እና የሚጠጣው አለማዊ ወይን ነው፡፡እዚህ ቤት ግን እለት እለት ያለማቋረጥ የክርስቶስ ስጋው ይቆረሳል፡፡ደሙ ይፈሳል፡፡ያውም ደሞ በነፃ...ግን ሁላችንም የበሬው ስጋ ሰልፍ ላይ ሆነን አንድም ቀን አስተውለነው አናውቅም፡፡
አሹዬ..ቅድም ስጋ ጋብዘኝ ስልህ ምን ያህል እንደተጨነቅክ እያየውህ ነበር... ምናልባት አንድ ትልቅ ሚባል ቤት ብንገባ አድሮ ቢውል የሚበላሸውን ስጋ ብዙ ሺወች እናወጣበት ይሆናል፡፡እዚህ ደሞ ማንም የማይጋፋበት፤አንዴ ቢበሉት የማያስርብ፤አንዴ ቢጠጡት የማያስጠማ የክርስቶስ ስጋ እና ደም በነፃ እየታደለ ማንም ሰው በልቶት አያቅም፡፡እንዲያውም የማያስርበውን ምግብ ትተን የሚያስርበው ጊዜያዊውን ምግብ መቃረም ልማድ አድርገነዋል፤ስራችንም ሁሉ የፈሪ ፉከራ ሆኗል....አስተውለካል??ፈሪ ሁሌ ከሚጣላው ሰው ጋ ሳይገጥም በፊት እንዲሁ በፉከራ ይደክማል ልክ ግጥሚያ ሲጀመር ግን እሱ ሮጦ ከጠፋ ቀይቷል..
እኛም ልክ እንደዛው ነን፡፡ፆሙ ሳይገባ ክራችንን አስረን በየሆቴሉ ስንጎፈላ፤ ስንፎክር፤ እዩኝ እዩኝ ስንል አምሽተን ልክ ፆሙ ላይ ግን የለንበትም፡፡ፆሙ ሲያዝም ሲፈታም እኛ ልክ ፆሙ ላይ ግን የለንበትም፡፡ፆሙ ሲያዝም ሲፈታም እኛ እዛው ስጋ ቤት ነን!!
ታድያ አይበቃም??እስከመቼ ፈርተን??እስከመቼ ለስጋ ወደሙ ራሳችንን ሰስተን?የኔ ፍቅር ስጋ ቤቱ ይኸውና ወይኑም (ደሙም)በነፃ እዚህ አለ፡፡ክርስትያን ፆም የሚይዘው ጭፈራ ቤት ሳይሆን እዚህ ነው!!ና አሁን ወደ ተከበረው ሥጋ ቤት እንግባ....
#እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የምህረት ቃል ኪዳን የተቀበለችበት ወርሃዊ መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ
#እንጦጦ ሀመረ ኖህ ኪዳነ ምህረት ገዳም
በአዲስ አበባ ከተማ በስተሰሜን ምሥራቅ በጉለሌ ክፍለ ከተማ የምትገኝ ስመጥርና ታሪካዊ ገዳም ስትሆን በተራራ፣በሸለቆና በወንዞች የተከበበች በመሆኑዋ በተፈጥሮ አቀማመጧ አረንጓዴ የተላበሰች ናት፡፡ ይህም ለቤተክርስቲያኗ ውበትና ግርማ ሞገስ ከመስጠት አልፎ በሚያስደስት ፀጥታ የአዕዋፍ ዝማሬ ተሞልታ ጸጋን እንድትላበስ አድርጓታል፡፡
ይህች ቦታ የተቆረቆረችው በ484 ዓ/ም ሲሆን በ500 ዓ.ም በአባ ሊባኖስ የአንድነት ገዳም ሆና ተቋቋመች፡፡ አባ ሊባኖስ ወደ ሌላ መንፈሳዊ ተልእኮ ለመሄድ መነኮሳቱን ሲሰናበቱ እንዲህ የሚል ትንቢት ተናግረው ነበር ‹‹ልጆቼ ሆይ በሉ ይህችን ቅድስት ቦታ አደራ ሰጥቻችኋለሁ በኋላ ዘመን ታላቅ ቦታ ትሆናለች' አጋንንት ይወገዱባታል' የብዙ ቅዱሳን አፅም ያርፍባታል' ነገስታት ጳጳሳት ይሰግዱባታል' ብዙ መናንያን መጠጊያ ያደርጋታል ቤተ መቅደሷም በወርቅ በብር ተጊጣ ትታነጻለች የአንድነቱም ገዳም ተሻሽሎ ይቋቋምባታል››፡፡ በ9ኛ መቶ ክ/ዘመን ዮዲት ጉዲት የአክሱም ጽዮንን ቤተ መቅደስ ለማቃጠል ስትነሳ ንጉሡ አንበሣ ውድም ታቦተጽዮንን በምሥጢር በማስያዝ ወደ ሸዋ መጥተው በእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነምሕረት ገዳም ታቦተ ጽዮንን አሳድረው ወደ ዝዋይ ደሴት ሲሄዱ ለገዳሟ ንዋየ ቅድሰት ስጦታ አበርክተዋል ጸበሏን ተጠምቀው ቦታውን መርቀው ሄደዋል፡፡
በ12ኛው መቶ ክ/ዘመን ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከንጉሥ ላሊበላ ጋር ወደ ዝቋላ አምባ ሲመጡ በዚህች ገዳም በእንግድነት አድረው በጸበሏ ተጠምቀው ቦታውን ባርከዋል፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ለመነኮሳቱ እንዲህ ብለው ነበር ‹‹ይህች ገዳም ታላቅ ስመጥር ገዳም ትሆናለች ከእርሷ በታች የሚታየው ጫካና ዱር መናገሻ ከተማ ይሆናል፡፡››
አፄ ዘርዓ ያዕቆብም ወደዚህች ገዳም መጥተው አቀማመጧንና የጸበሏን ፈዋሽነት ተመልክተዋል ‹‹ዳሯ እሳት መሐሏ ገነት ይሁን›› ብለው ብዙ ስጦታ አበርክተዋል፡፡ አፄ ልብነ ድንግልም ወደ ገዳሟ መጥተው ተማህጽኖ አድርገው በጸበሏ ተጠምቀው ታቦተ ልደታንና ብዙ ንዋየቅድሳት ሰጥተው ሄደዋል፡፡ በንግስት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት ይህች ገዳም ሐመረ ኖኅ ኪዳነምህረት ገዳም ተብላ ተሰይማለች፡፡
ይህች ቦታ እንደተነገረላት ትንቢት ብዙ ቅዱሳንና ነገሥታት መጥተው የሰገዱባት የባረኳት' ጸበሏ የአጋንንት ድል መንሻ' የብዙ መነኮሳት መጠጊያ 'የህሙማን መፈወሻ' የእመቤታችንን ቃል ኪዳን ለማግኘት ብዙን ጊዜ ለሱባኤ ከሚመረጡ ቦታዎች አንዷ ናት፡፡ ይህች ደብር በ1957 ዓ/ም የተመሠረተ ሰንበት ት/ቤት ሲኖራት በ1984 ዓ/ም በብፁዓን ጳጳሳት ‹‹መርሶ ሕይወት›› /የሕይወት ወደብ/ የሚለውን ስያሜ አግኝቷል፡፡ የገዳሟ ስያሜ ሐመረ ኖኅ ( የኖኅ መርከብ ) እንደሆነ ሁሉ መርሶ ሕይወት ( የሕይወት ወደብ ) በመባሉ ሁለቱ ተዛማችነት አላቸው ፡፡ ይህ ሰንበት ት/ቤት ለየት የሚያደርገው በግል መኖሪያ ቤት በጋሞኛ ቋንቋ ይሰጥ የነበረውን ትምህርት ከ1986 ጀምሮ በሰ/ት/ቤቱ ስር በማቀፍ የወንጌል ትምህርቱን ከመማር ባሻገር ለጋሞ ሕዝብ መንፈሳዊ እንቅስቃሴን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
አዘጋጅ፡- እህተ ማርያም
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘለአለም ትኑር!!!
ሰው ሁሉ ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን !
(ያዕቆብ 1፥19)
< ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@ortodoxtewahedo
እናት አለኝ
እናት አለኝ የምታብስ እንባ
አያታለው ስወጣ ስገባ
ኪዳነ ምህረት /3/ አንባ መጠጊያ ናት
ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ
እራቆቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደ እኔ ቀርበሻል
ደጓ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል
ኪዳነ ምህረት /3/ አንባ መጠጊያ ናት/
አዝ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ለዘላለም ንጽህይት በመሆኗ
ከኔ ጋር ነው ህያው ቃልኪዳኗ
ደስተኛ ነኝ ሀዘኔን አልፌ
አጽናኝ ሆናኝ የመስቀል ስር ትርፌ
ኪዳነ ምህረት /3/ አንባ መጠጊያ ናት/
አዝ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ከጥፋቱ ውሀ ማረፊያዬ
መርከቤ ነሽ ከሞት ማምለጫዬ
የአምላክ እናት ምልጃሽ ሆኖኝ ክብሬ በህይወት አለው ጥልቁን ተሻግሬ
ኪዳነ ምህረት /3/ አንባ መጠጊያ ናት/
አዝ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
በእናትነት ህይወቴን ጎብኝታ
ልቤ አረፈ ተነቅሎ በሽታ
ሰንሰለቴ ከእጄ ተቆረጠ
መራራዬ በልጅሽ ጣፈጠ
ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖
ኪዳነ ምህረት | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖
✤ ኪዳነ ምህረት
ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖
ደጅ_ጠናሁ
ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምህረትን
ተፅናናሁኝ ረሳሁ ሀዘኔን
የአምላክ እናት እመቤታችንን
ሞገስ ሁኚኝ ቀሪው ዘመኔን
የመከራው ዘመን አለፈ እንደዋዛ
አንቺን ተጠግቼ የአለሟን ቤዛ
የልጅሽ ቸርነት የአንቺ ደግነት
ባርያሽን ሰውሪኝ ከአስጨናቂው ሞት
እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያሁሉ መከራ
እምባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ በአንቺ እየታበሰ ሰላም ለኪ
#አዝ
ልቤ ባንቺ ፀና ከፍ ከፍም አለ
በጠላቶቼ ላይ አፌ ተናገረ
በማዳንሽ ስራ ባሪያሽ ደስ ብሎኛል
የኃያላኑን ቀስት ልጅሽ ሰብሮልኛል
እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያሁሉ መከራ
እምባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ ባንቺ የታበሰ ሰላም ለኪ
#አዝ
እጄ ባዶ ሲሆን ወዳጆቼም ሸሹኝ
በመርገም ምክራቸው ሊለያዩን ሲሹ
እርሱ የሰጠኝን እሱ ወሰደ አልኳቸው
እመቤቴ አለችኝ ብዬ አሳፈርኳቸው
እናቴ ስምሽን ሰጠራ አለፈ ያሁሉ መከራ
እምባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ በአንቺ እየታበሰ ሰላም ለኪ
#አዝ
በአውደ ምሕረቱ ሆኜ ስጠራት
ዘንበል ብላ አየችን ኪዳነ ምህረት
ሀሳብሽን ምንም የለም የሚመስለው
እረፍት ያገኘሁት እናቴ ባንቺ ነው
እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያሁሉ መከራ
እምባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ ባንቺ እየታበሰ ሰላም ለኪ
ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖
Hello Weyeneyshet, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…Hello Girma, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…Hello Emito, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…Hello Nafi, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…Hello kasech, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…ጾመ ነቢያት (Nativity Fast) - ኪዳን ዘኢየሱስ እንደከተበው
ቤተ ክርስቲያናችን ከጌታ ልደት በፊት ያሉትን 40 ቀናት በጾም እንድናሳልፍ ታዘናለች። ይኽም ሙሴ አሠርቱ ቃላትን ለመቀበል በሲና ተራራ የጾመውን 40 ቀናት ይወክልልናል። ሙሴ አሠርቱ ቃላትን ለመቀበል 40 ቀናት እንደ ጾመ እኛም ደግሞ የአካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋዌ (Incarnation of the Logos) ለመቀበል እንዲሁ #40_ቀናትን እንጾማለን።
የአዳም መድኃኒት፥ የነቢያት ትንቢታቸው "እጅኽን ከአርያም ላክ ናና አድነን" እያሉ የለመኑት፥ የ5500 ዓመት ተስፋቸው፥ ለሙሴ የመጀመርያ ስሙን በየውጣ የነገረው (የውጣ ማለት Iota ከሚለው የግሪክ እና ኮፕቲች ፊደል የመጣ ነው በኮፕቲክ አሥር የሚለው ቃል በIota ፊደል ይጀምራል፥ ኢየሱስ የሚለው ስምም በግሪክም በኮፕቲክ በIota ፊደል ይጀምራል። ስለዚህ Iota , the name of salvation of our Lord የጌታ የማዳኑ ስም ተብሏል። (ውዳሴ ማርያም ዘእሑድ) ሙሴ አሠርቱ ቃላትን እንደተቀበለ አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና)፥ የኢያሱ ስሙ ኃይል (ኢያሱ እና ኢየሱስ ማለት ትርጉሙ አንድ ሲኾን ያህዌ ያድን ማለት ነው፥ መድኃኒት ተብሎም ይተረጎማል)፥ የኤልያስ መሶበ ወርቅ ውስጥ ያለ መና፥ በዳዊት ዙፋን ለዘላለም የሚነግሥ የንግሥናው ፈጻሚ፥ የሰሎሞን ጥበብ "ጥበብሰ መድኃኒነ ውእቱ - ጥበብስ መድኃኒታችን ነው" (ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ) የተባለለት፥ የነቢያት ትንቢት ኹሉ ፈጻሚ፥ አዳኙ፥ አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ሊወለድ ነውና የተስፋውን ቀን በመጠባበቅ እኛም ከነቢያት ጋር እንጾማለን።
"የበዓል ቀን ሊመጣ ነው። እርሱም ከኹሉም በዓላት በላይ እጅግ የተቀደሰ እና ያማረ ነው፥ የተቀደሱ ቀናት ኹሉ አለቃ እና እናት ብለን ብንጠራው ስህተት አይኾንም። ይሄም በዓል #የክርስቶስ_ልደት ቀን ነው።" — ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
እሑድ ኅዳር 15 ይገባልና ለነቢያት ጾም እንኳን አደረሳችኹ!