ለትርፍ ጊዜ ስራ ፈላጊዎችና ስራ ለሌላቸው የወጣ የስራ ማስታወቂያ
ካምፓኒያችን በተለያዩ ትላልቅ የክልል ከተሞችና በተለያዩ በአዲስ አበባ ቅርጫፎች ከፍቷል ከተሰማራንበት የስራ ዘርፍ በተጨማሪም ሆነ እንደ ዋና ስራ አድርገን ሰርተን ገቢ የምናገኝበትና በእውነትም ለውጥ ማምጣት ለሚፈልጉ የስራ እድል አቅርቧል በመሆኑም፦
1. በግልም ሆነ በመንግስት ተቋማት ተቀጥራችሁ የምትሰሩ፣
2. የግላችሁን ስራ የምትሰሩ
3. ከዩኒቨርስቲ ተመርቃችሁ ስራ ያላገኛችሁ
4. 12 ተፈትናችሁ ነጥብ የመጣላችሁም ሆናችሁ ያልመጣላችሁ
ሰርታችሁ ተጨማሪ ዳጎስ ያለ ገቢ የምታገኙበት የስራ ዘርፍ ስለሆነ ማንኛውም ሰው መስራት የሚፈልግ ሙሉ ስም፣ የመኖሪያ አድራሻና ስልክ ቁጥር በውስጥ መስመር ያስቀምጥልኝ።.
ለዚህ ሁሉ መልስ እኛጋ ያገኛሉ።
"" ዘ እንበለ ሥጋ ኢትቀውም ነፍስ ""
ከፈለጉ በትርፍ ሰዓት ከፈለጉ በሙሉ ሰዓት የእጅዎን ስልክ እና ፈጣሪ የሰጥዎትን ጭንቅላት ተጠቅመው የሚሰሩት ሥራ ነው
ለበለጠ መረጃ ለማግኘት በውስጥ ያናግሩኝ
🧑💻 0777235250
0969263876
" እኛ ጋ መጥተው ያለ ሥራ አይመለሱም
“የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለኹና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችኹ፤ እላችኋለኹ፥ እንዲኹ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይኾናል፤ ... እንዲኹ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ #በእግዚአብሔር_መላእክት_ፊት ደስታ ይኾናል።” (ሉቃ. 15፥6-10)
በዘማሪ ሐዋዝና በሌሎቹም 70 ነፍሳት መመለስ በጣም ደስ ብሎኛል፤ ገና ብዙ ነፍሳት ወደቤተክርስቲያን ይፈልሳሉ።🤩🥰 አንድ ወንድማችን የጻፈው ነው፤ ስለማረከኝ እንደወረደ አቅርቤዋለኹ። ‛አንድ ሰው ንስሐ ገባ ወደ አባቱ ቤት ተመለሰ ሲባል የክርስቲያኑን ሕዝብ ደስታ ግን አስተውላችኋል? እኛ በኃጢአት ያለነው ክርስቲያኖች እንደዚኽ ከተደሰትን በሰማይ ድል አድርገው በፍጹም ቅድስና ያሉት እንዴት ይደሰቱ ይኾን?’
“ይኽ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ኾኗል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቷልም። #ደስም_ይላቸው_ጀመር።” (ሉቃ. 15፥24)
በአእምሮአችን ለመረዳት እንዲኾነን ስንነጣጥለው ነፍስ በሥጋ ኃጢአትን ትሠራለች። የእኛ የማስተዋል፣ የመናገር፣ የሕይወት፣ የአእምሮ ዐቅሙ ያለን በሥጋችን ሳይኾን በነፍሳችን ነው። ኹለቱ ባሕርያት ወደ አንድ ባሕርይ በመዋሐዳቸው የምታስተውል የምትናገር ነፍስ በሥጋ መሣሪያነት ኃጢአትን ታደርጋለች።
ሲቀጥል በአእምሮአችን ውስጥ ለመረዳት እንዲመች ነፍስና ሥጋ እያልን እንለያቸዋለን እንጂ በእውነታው ዓለም ተዋሕደው ሳሉ ሥራቸው አንድ ውሑድ ሥራ ነው። ስለዚህ ሥራውን የሠራችው ነፍስ ብቻዋን አይደለችም ፥ ሥጋም ብቻውን አይደለም እኒህ ኹለት ባሕርያት ተዋሕደው በእኛ ውስጥ ያሉን እኛ በአንዱ በውሑዱ ባሕርያችን ያንን ነገር እናደርጋለን እንጂ።
አልተመለሰም የተመለሰው ኦርቶዶክስን ሊበታትን ነው እሲ ወደት ነው የተመለሰው ከተመለሰስ በኋላ ምን መዝሙር ዘመረ የዘመረዉንስ እስኪ በደብ አዳምጡት የያሮዳዊ ዜማ ነው ?
Читать полностью…ኪዳነ ምህረት እንወድሻለን
ለግዚአብሔር ታቦቱ መቅደሱ
ቀርበናል ባንቺ ወደ ንጉሱ
የክብራችን ጌጥ ሽልማት
እንወድሻለን ኪዳነምህት
በጨለማው ላለ ብርሃንን አየ
ለርስቱ ተካፋይ እንዲሆን ተለየ
ወደ ቀድሞ ክብሩ ሊመለስ ዳግመኛ
አንቺ ነበርሽ ተስፍው ለአዳም መዳኛ
አዝ===========
ያንን ሁሉ ዘመናት የፈሰሰው ደም
አለምን ከእስራት ሊፈታ አልቻለም
ወደ ሚሻል ኪዳን በደም ሊያሻግረን
ደምሽን ተዋህዶ መዳኃኒ አለም ዋጀን
አዝ===========
አለን ብዙ ምክንያት አንቺን ምንወድበት
ዓለም ያልተረዳው ያላወቀው እውነት
ያወቀ የተረዳ የመዳኑን ሚስጢር
አያፍርም ክብርሽን ቆሞ ለመናገር
አዝ===========
አውቃለሁ እግዚአብሔር የሰጠሽን ክብር
ላመስግንሽ እኔም ሳልጨምር ሳልቀንስ
ሚባርክሽ ብሩክ ነውና እናቴ
ኪዳነ ምህረት ንገሽ እመቤቴ
አዝ===========
ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖
• ለእናት ቤተክርስቲያን ደግሞም ለኦርቶዶክስ የአዕምሮ ፍሬያቸውን፣ የላብ ድካማቸውን እንዲያው በነጻ ለመዋቅሯ ማደግ በስስት የማይሰጡ ሁሉ በእኔ እይታ የብብት ውስጥ ላቦች፣ የጭቃ ውስጥ እሾሆች፣ የቆዳ ላይ መዥገሮች ናቸው። ውሎ ይደር እንጂ መዳረሻቸው ሁሉ ጥቅማቸው ብቻ ነው። ‘ወንድሞች ሆይ፥ ሕግን ለሚያውቁ እናገራለሁና ሰው ባለበት ዘመን ሁሉ ሕግ እንዲገዛው አታውቁምን?’ ሮሜ 7-1
Читать полностью…“የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለኹና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችኹ፤ እላችኋለኹ፥ እንዲኹ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይኾናል፤ ... እንዲኹ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ #በእግዚአብሔር_መላእክት_ፊት ደስታ ይኾናል።” (ሉቃ. 15፥6-10)
በዘማሪ ሐዋዝና በሌሎቹም 70 ነፍሳት መመለስ በጣም ደስ ብሎኛል፤ ገና ብዙ ነፍሳት ወደቤተክርስቲያን ይፈልሳሉ።🤩🥰 አንድ ወንድማችን የጻፈው ነው፤ ስለማረከኝ እንደወረደ አቅርቤዋለኹ። ‛አንድ ሰው ንስሐ ገባ ወደ አባቱ ቤት ተመለሰ ሲባል የክርስቲያኑን ሕዝብ ደስታ ግን አስተውላችኋል? እኛ በኃጢአት ያለነው ክርስቲያኖች እንደዚኽ ከተደሰትን በሰማይ ድል አድርገው በፍጹም ቅድስና ያሉት እንዴት ይደሰቱ ይኾን?’
“ይኽ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ኾኗል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቷልም። #ደስም_ይላቸው_ጀመር።” (ሉቃ. 15፥24)
የቀድሞው ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ ወደ ቀደመው የአባቱ ቤት ወደሆነችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት መቅደስ ተመልሷል
***
በተ*ዶሶ እንቅስቃሴ ላይ የነበረው የቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዘማሪ የነበረው ሐዋዝ ተገኝ
ቀድሞ ያገለግልባት ወደነበረችው ቅድስት እና ንጽሕት ወደሆነችው ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ መቅደስ በንሰኃ ጥምቀት ተመልሷል።
እግዚአብሔር ይመስገን !!!
ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖
Getachin ke ilete arb iske ihud bemeqabir yeqoyew gize Indet sost qen ina sost lelit molaw
Читать полностью…ይነበብ
"የኔ ፍቅር እስቲ ዛሬ ስጋ ጋብዘኝ"የሚል ድምጿ ነበር ከሀሳቤ ብንን ያደረገኝ፡፡ገና ከተዋወቅን'ኳ ሁለት ሳምንታችን እኮ ነው፡፡ሳያት.. ወጪ አታስወጣም፤ መጠጥ አጠጣም፤ ጨዋ ናት ብዬ ነበር የቀረብኳት፡፡ምክንያቱም እኔ ቁርስ ዘልዬ ምሳ አማካኝ ሰአት በልቼ እራቴን በማሰብ ብቻ የማሳልፍ መናጢ ደሀ ነኝ፡፡እሷን ቁርጥ ጋበዝኩ ማለት የወር ደሞዜን ለአንድ ወፍራም የስጋ ቤት ባለቤት በነፃ ገበርኩ ማለት ነው....
በዛላይ ወይን መጠጣት እንዴት እንዳማረኝ .....(ስትል ጭራሽ በተቀመጥኩበት ፌንት ልበላ!!!ሰይጣን ጎኔ የተቀመጠ ያህል አማትቤ እሷ መሆኗን ለማረጋገጥም ቃጣኝ፡፡ "እቺማ እሷ አደለችም'' እያለም ልቤ ይሞግተኝ ገባ።እሷ ግን እራሷ ፍሬዬ ናት...
እ....እሺ ችግር የለውም፡፡ማለቴ ትንሽ መሸት ቢል አይሻልም??(አልኳት ተበድሬ ያልመለስኩላቸውን ሰወች ቆጥሬ ስጨርስ ሌላ ምበደረውን ሰው እያሰላሰልኩ
እን..ዴ ፍቅር ቀን ነው እንጂ ሚጀመረው፡፡ ማታማ ታውቅ የለ....(ተሸኮረመመች፡፡ለካ የአልጋም አለብኝ!!!ነገሩ ይበለኝ....በዚ ኑሮ ውድነት እኔን የመሠለ መናጢ ሴት ጋ ምን ይሰራል?!ምንም፡፡እኮ ይበለኛ!!!
ፍሬ ከወትሮዋ ለየት ብላ ስትቅበጠበጥ ነገሯ አላማረኝም፡፡ከኑሮዬ ጋ ትመጥናለች ታረጋጋኛለች ለትዳር ትሆናለች ብዬ ብቀርባት ገና በቀናት ውስጥ ኑሮዬ ልትገለባብጠው የመጣች መቅሰፍ ሆና ታየቺኝ፡፡ምናልባት ደሞ የምትመርጠው ቤት ትልቅ ከሆነስ??.....(እንባ እንባ እያለኝ ተከተልኳት
የኔ ፍቅር እዚ ይሻለናል አደል...?(መስቀያው ላይ ነጭ ነገር ያንጠለጠለ ስጋ ቤት እያሳየቺኝ...ደነገጥኩ፡፡ስጋ ቀይ አልነበር እንዴ???መልኩን ቀይሮ ነው?
አይ እዚህማ ግርግሩ ጫጫታው እያልኩ ዘላብጄ ረከስ ያለውን ቤት ፍለጋ አይኔን ሳማትር ፍሬ እጄን እንደያዘች ከፊታችን ወዳለ ቤተክርስትያን አመራች....
የት ነው ምትሄጂው ፍቅር??(አልኳት መተንፈሻ ጊዜ ስላገኘሁ ልቤ ጮቤ እየረገጠ
ስጋ ቤት(አለች ፈገግ ብላ እያየቺኝ
እሱማ አዎ.. ታድያ እዚህ..
እኮ ስጋ ቤቱኮ እዚህ ነው፡፡(ነጠላዋን ከቦርሳዋ አውጥታ አንዱን ሰጥታኝ አንዱን እራሷ እያጣፋች
አልገባኝም!!
የኔ ፍቅር ለዘመናት እያየን ባላየን እየሰማን ባልሰማ ያለፍነው ምርጡ ስጋ ቤት ይኼ ነው!!
አየህ ፆም መያዣ ሲባል ሁሉም የሚመጣለት የበሬው ስጋ እና የሚጠጣው አለማዊ ወይን ነው፡፡እዚህ ቤት ግን እለት እለት ያለማቋረጥ የክርስቶስ ስጋው ይቆረሳል፡፡ደሙ ይፈሳል፡፡ያውም ደሞ በነፃ...ግን ሁላችንም የበሬው ስጋ ሰልፍ ላይ ሆነን አንድም ቀን አስተውለነው አናውቅም፡፡
አሹዬ..ቅድም ስጋ ጋብዘኝ ስልህ ምን ያህል እንደተጨነቅክ እያየውህ ነበር... ምናልባት አንድ ትልቅ ሚባል ቤት ብንገባ አድሮ ቢውል የሚበላሸውን ስጋ ብዙ ሺወች እናወጣበት ይሆናል፡፡እዚህ ደሞ ማንም የማይጋፋበት፤አንዴ ቢበሉት የማያስርብ፤አንዴ ቢጠጡት የማያስጠማ የክርስቶስ ስጋ እና ደም በነፃ እየታደለ ማንም ሰው በልቶት አያቅም፡፡እንዲያውም የማያስርበውን ምግብ ትተን የሚያስርበው ጊዜያዊውን ምግብ መቃረም ልማድ አድርገነዋል፤ስራችንም ሁሉ የፈሪ ፉከራ ሆኗል....አስተውለካል??ፈሪ ሁሌ ከሚጣላው ሰው ጋ ሳይገጥም በፊት እንዲሁ በፉከራ ይደክማል ልክ ግጥሚያ ሲጀመር ግን እሱ ሮጦ ከጠፋ ቀይቷል..
እኛም ልክ እንደዛው ነን፡፡ፆሙ ሳይገባ ክራችንን አስረን በየሆቴሉ ስንጎፈላ፤ ስንፎክር፤ እዩኝ እዩኝ ስንል አምሽተን ልክ ፆሙ ላይ ግን የለንበትም፡፡ፆሙ ሲያዝም ሲፈታም እኛ ልክ ፆሙ ላይ ግን የለንበትም፡፡ፆሙ ሲያዝም ሲፈታም እኛ እዛው ስጋ ቤት ነን!!
ታድያ አይበቃም??እስከመቼ ፈርተን??እስከመቼ ለስጋ ወደሙ ራሳችንን ሰስተን?የኔ ፍቅር ስጋ ቤቱ ይኸውና ወይኑም (ደሙም)በነፃ እዚህ አለ፡፡ክርስትያን ፆም የሚይዘው ጭፈራ ቤት ሳይሆን እዚህ ነው!!ና አሁን ወደ ተከበረው ሥጋ ቤት እንግባ....
#እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የምህረት ቃል ኪዳን የተቀበለችበት ወርሃዊ መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ
#እንጦጦ ሀመረ ኖህ ኪዳነ ምህረት ገዳም
በአዲስ አበባ ከተማ በስተሰሜን ምሥራቅ በጉለሌ ክፍለ ከተማ የምትገኝ ስመጥርና ታሪካዊ ገዳም ስትሆን በተራራ፣በሸለቆና በወንዞች የተከበበች በመሆኑዋ በተፈጥሮ አቀማመጧ አረንጓዴ የተላበሰች ናት፡፡ ይህም ለቤተክርስቲያኗ ውበትና ግርማ ሞገስ ከመስጠት አልፎ በሚያስደስት ፀጥታ የአዕዋፍ ዝማሬ ተሞልታ ጸጋን እንድትላበስ አድርጓታል፡፡
ይህች ቦታ የተቆረቆረችው በ484 ዓ/ም ሲሆን በ500 ዓ.ም በአባ ሊባኖስ የአንድነት ገዳም ሆና ተቋቋመች፡፡ አባ ሊባኖስ ወደ ሌላ መንፈሳዊ ተልእኮ ለመሄድ መነኮሳቱን ሲሰናበቱ እንዲህ የሚል ትንቢት ተናግረው ነበር ‹‹ልጆቼ ሆይ በሉ ይህችን ቅድስት ቦታ አደራ ሰጥቻችኋለሁ በኋላ ዘመን ታላቅ ቦታ ትሆናለች' አጋንንት ይወገዱባታል' የብዙ ቅዱሳን አፅም ያርፍባታል' ነገስታት ጳጳሳት ይሰግዱባታል' ብዙ መናንያን መጠጊያ ያደርጋታል ቤተ መቅደሷም በወርቅ በብር ተጊጣ ትታነጻለች የአንድነቱም ገዳም ተሻሽሎ ይቋቋምባታል››፡፡ በ9ኛ መቶ ክ/ዘመን ዮዲት ጉዲት የአክሱም ጽዮንን ቤተ መቅደስ ለማቃጠል ስትነሳ ንጉሡ አንበሣ ውድም ታቦተጽዮንን በምሥጢር በማስያዝ ወደ ሸዋ መጥተው በእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነምሕረት ገዳም ታቦተ ጽዮንን አሳድረው ወደ ዝዋይ ደሴት ሲሄዱ ለገዳሟ ንዋየ ቅድሰት ስጦታ አበርክተዋል ጸበሏን ተጠምቀው ቦታውን መርቀው ሄደዋል፡፡
በ12ኛው መቶ ክ/ዘመን ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከንጉሥ ላሊበላ ጋር ወደ ዝቋላ አምባ ሲመጡ በዚህች ገዳም በእንግድነት አድረው በጸበሏ ተጠምቀው ቦታውን ባርከዋል፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ለመነኮሳቱ እንዲህ ብለው ነበር ‹‹ይህች ገዳም ታላቅ ስመጥር ገዳም ትሆናለች ከእርሷ በታች የሚታየው ጫካና ዱር መናገሻ ከተማ ይሆናል፡፡››
አፄ ዘርዓ ያዕቆብም ወደዚህች ገዳም መጥተው አቀማመጧንና የጸበሏን ፈዋሽነት ተመልክተዋል ‹‹ዳሯ እሳት መሐሏ ገነት ይሁን›› ብለው ብዙ ስጦታ አበርክተዋል፡፡ አፄ ልብነ ድንግልም ወደ ገዳሟ መጥተው ተማህጽኖ አድርገው በጸበሏ ተጠምቀው ታቦተ ልደታንና ብዙ ንዋየቅድሳት ሰጥተው ሄደዋል፡፡ በንግስት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት ይህች ገዳም ሐመረ ኖኅ ኪዳነምህረት ገዳም ተብላ ተሰይማለች፡፡
ይህች ቦታ እንደተነገረላት ትንቢት ብዙ ቅዱሳንና ነገሥታት መጥተው የሰገዱባት የባረኳት' ጸበሏ የአጋንንት ድል መንሻ' የብዙ መነኮሳት መጠጊያ 'የህሙማን መፈወሻ' የእመቤታችንን ቃል ኪዳን ለማግኘት ብዙን ጊዜ ለሱባኤ ከሚመረጡ ቦታዎች አንዷ ናት፡፡ ይህች ደብር በ1957 ዓ/ም የተመሠረተ ሰንበት ት/ቤት ሲኖራት በ1984 ዓ/ም በብፁዓን ጳጳሳት ‹‹መርሶ ሕይወት›› /የሕይወት ወደብ/ የሚለውን ስያሜ አግኝቷል፡፡ የገዳሟ ስያሜ ሐመረ ኖኅ ( የኖኅ መርከብ ) እንደሆነ ሁሉ መርሶ ሕይወት ( የሕይወት ወደብ ) በመባሉ ሁለቱ ተዛማችነት አላቸው ፡፡ ይህ ሰንበት ት/ቤት ለየት የሚያደርገው በግል መኖሪያ ቤት በጋሞኛ ቋንቋ ይሰጥ የነበረውን ትምህርት ከ1986 ጀምሮ በሰ/ት/ቤቱ ስር በማቀፍ የወንጌል ትምህርቱን ከመማር ባሻገር ለጋሞ ሕዝብ መንፈሳዊ እንቅስቃሴን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
አዘጋጅ፡- እህተ ማርያም
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘለአለም ትኑር!!!
ሰው ሁሉ ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን !
(ያዕቆብ 1፥19)
< ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@ortodoxtewahedo
እናት አለኝ
እናት አለኝ የምታብስ እንባ
አያታለው ስወጣ ስገባ
ኪዳነ ምህረት /3/ አንባ መጠጊያ ናት
ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ
እራቆቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደ እኔ ቀርበሻል
ደጓ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል
ኪዳነ ምህረት /3/ አንባ መጠጊያ ናት/
አዝ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ለዘላለም ንጽህይት በመሆኗ
ከኔ ጋር ነው ህያው ቃልኪዳኗ
ደስተኛ ነኝ ሀዘኔን አልፌ
አጽናኝ ሆናኝ የመስቀል ስር ትርፌ
ኪዳነ ምህረት /3/ አንባ መጠጊያ ናት/
አዝ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ከጥፋቱ ውሀ ማረፊያዬ
መርከቤ ነሽ ከሞት ማምለጫዬ
የአምላክ እናት ምልጃሽ ሆኖኝ ክብሬ በህይወት አለው ጥልቁን ተሻግሬ
ኪዳነ ምህረት /3/ አንባ መጠጊያ ናት/
አዝ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
በእናትነት ህይወቴን ጎብኝታ
ልቤ አረፈ ተነቅሎ በሽታ
ሰንሰለቴ ከእጄ ተቆረጠ
መራራዬ በልጅሽ ጣፈጠ
ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖
ኪዳነ ምህረት | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖