ortodoxtewahedoo | Unsorted

Telegram-канал ortodoxtewahedoo - ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

3754

ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ። ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ›› ት.ኢሳ 58÷3 https://youtu.be/csxxAMGtC4I ለመቀላቀል http://t.me/ortodoxtewahedo

Subscribe to a channel

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

=>+"+ እንኩዋን ለጽዮን "ማርያም ማሕደረ አምላክ" እና ለቅዱሳኑ "ጐርጐርዮስ ወዮሐንስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+

+*"+ ጽዮን ማርያም +"*+

=>"ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው:: አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም: ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል::

+እግዚአብሔር ከዘመነ አበው በሁዋላ በጊዜው ለእሥራኤላውያን ክብር: ሞገስ: አምባ የምትሆናቸውን ታቦተ ጽዮንን በቅዱስ ሙሴ አማካኝነት ሰጥቷቸዋል:: (ዘጸ. 31:18) ከዚያም ለ500 ዓመታት ከእነሱ ጋር በመሆኗ በፈጣሪና በእነሱ መካከል ድልድይ ሆና ኖራለች::

+ከዚያም ባለቤቱ ሲፈቅድ በዘመነ ሳባ: በቀዳማዊ ምኒልክ (እብነ መለክ-እብነ ሐኪም) አማካኝነት ወደ ኢትዮዽያ መጥታለች:: እነሆ በሃገራችን የ3ሺ ዓመት ቆይታዋን ልትደፍን የቀራት ጥቂት ዓመታት ብቻ ናቸው:: ጌታ እንደ ፈቀደ ቅዱስ መስቀሉንና ታቦተ ጽዮንን ይዘን ይሔው በቸርነቱ እንኖራለን::

+ያም ሆኖ ታቦተ ጽዮንን መስረቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀሳጢዎች እንዳሉ እናውቃለን:: ግን አንጨነቅም:: ምክንያቱም የመጣችውም: የምትጠበቀውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነውና እንጸልያለን እንጂ አንጨነቅም:: በተለያየ ወሬም ራሳችንን አናማጥንም:: ባለቤቱ እንድትሔድ ከፈቀደ ደግሞ ማንም ጉልበተኛ አያስቀራትም::

+ታቦተ ጽዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን: ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች:: "ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው:: "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል - ስምምነት" ነው::

+"ታቦት" ማለት "ማሕደር - ማደሪያ"
እንደ ማለት ነው:: ሕጉ የተጻፈባቸውን ሰላድው "ጽላት" ስንላቸው የጽላቱ ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል:: ጽላት (ታቦትን) ያመጣ ፈጣሪ ነው:: በሐዲስ ኪዳንም ምሥጢርና ሐተታ ቢኖረውም 2 ቦታ ላይ ስለ ታቦት ተጠቅሶ እናገኛለን:: (2ቆሮ. 6:16, ራዕይ. 11:19)

+በመጨረሻም ኅዳር 21 ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች እንመለከታለን:: በዚህች ቀን:-

1.ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን:: ይሕ ሲሆንም ቅዱስ ሙሴ 40 መዓልት: 40 ሌሊት ጾሞ እንደ ተቀበለ ሳንዘነጋ ማለት ነው:: (ዘጸ. 31:18, ዘዳ. 9:19)

2.በዘመነ ኤሊ ሊቀ ካህናት ታቦተ ጽዮን በታሪኩዋ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ (ኢሎፍላውያን) እጅ ተማርካለች:: ግን ደግሞ ዳጐንን ቀጥቅጣዋለች:: (1ሳሙ. 5:1)

3.በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና: ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ: አገለገለ:: ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ ተቀኘላት:: በዚህም ሜልኮል ንቃው ማሕጸኗ ተዘግቷል:: (1ዜና. 15:25) ሊቃውንትም "ድንግል እመቤታችን ማርያም በትንቢት መነጽር ተመልክቷል" ብለውናል::

"ሰላም ለኪ ማርያም እምነ::
ዘሰመይናኪ ጸወነ::
ሶበ እምርሑቅ ርእየ ዘጽላሎትኪ ስነ::
ለቢሶ ዳዊት ልብሰ ክብር ዘየኀይድ ዓይነ::
ቅድመ ታቦተ ሕግ ኀለየ ወዓዲ ዘፈነ::" እንዲል:: (አርኬ ዘኅዳር 21)

4.በዘመነ ንጉሥ ሰሎሞን (መፍቀሬ ጥበብ) ግሩም የሆነ ቤተ መቅደስ ተሰርቶላት ስትገባ ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: እግዚአብሔርም በደመና ወርዶ ንጉሡን አነጋግሯል:: (2ዜና. 5:1, 1ነገ. 8:1)

5.በዚያው ዘመንም በፈጣሪ ፈቃድ ንጉሥ ምኒልክ ቀዳማዊ (ዕብነ ሐኪም)
ታቦተ ጽዮንን ይዞ ወደ ኢትዮዽያ ገብቷል::

6.በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች:: በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታል::

7.በ4ኛው መቶ ክ/ዘመንም ነገሥት ጻድቃን አብርሐ ወአጽብሐ 12 መቅደሶች ያሏትን ግሩም ቤተ ክርስቲያን ለእመ ብርሃን ሠርተው በዚሁ ቀን በጌታችን ተቀድሷል::

8.በተጨማሪም በየጊዜው: ማለትም በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አማካኝነት ስትፈርስ ወደ ዝዋይ ትሰደድ ነበር:: ተመልሳ ስትታነጽም ቅዳሴ ቤቷ የሚከበረው ኅዳር 21 ቀን ነው:: በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ይህ በዓል ልዩ ነው::

+*" አማናዊት ጽዮን እመ ብርሃን ድንግል ማርያምን እንዲህ እንላታለን "*+

=>"ቅድስት" የሚለው ቃል ለሁሉም ቅዱሳት እናቶች ቢሰጥም ቅሉ ለድንግል ማርያም ሲሰጥ ግን ትርጉሙ ይለያል:: እርሷ "ቅድስተ ቅዱሳን: ንጽሕተ ንጹሐን: ቡርክት እምቡሩካን: ኅሪት እምኅሩያን" ናትና::

+ከሰው ልጆችም ሁሉ ትበልጣለች:: ይቅርና የሰው ልጅን ንጹሐን መላእክትንም በንጽሕናና በቅድስና ትበልጣቸዋለች:: እርሷ እመ ብርሃን: የአምላክ እናቱ: የሰውነታችን መመኪያ ናትና::

+እመቤታችንን "ቅድስት" ስንል "ጽንዕት: ንጽሕት: ክብርት: ልዩ" ማለታችን ነው::

1."ንጽሕት" ትባላለች:: ሌሎች ቅዱሳን ቢነጹ ከገቢር: ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም:: እርሷ ግን ከነቢብ: ከገቢር: ከኃልዮ ንጽሕት ናት::

"ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና: ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ-ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች ለማን ተሰጠው: ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል:: (ተአምረ ማርያም)

2."ጽንዕት" እንላታለን:: ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው
እንጂ በሁዋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን ቅድመ ጸኒስ: ጊዜ ጸኒስ: ድኅረ ጸኒስ: ቅድመ ወሊድ: ጊዜ ወሊድ: ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና::

¤"ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት:: (ቅዱስ ያሬድ)
¤ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስም "ወትረ ድንግል ማርያም-ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ:: (መጽሐፈ ቅዳሴ)

3.ድንግልን "ክብርት" እንላታለን:: ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን: ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው:: እመቤታችንን ግን የምናከብራት "ወላዲተ አምላክ-የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና::

4.እመቤታችንን "ልዩ" እንላታለን:: ከእርሷ በቀር እናት ሁና ድንግል: እመቤት ሁና አገልጋይ የሆነች: በድንግልና ወልዳ ወተትን (ሐሊበ ድንግልናዌን) ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና::

+"+ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘሮም +"+

=>በቤተ ክርስቲያን እጅግ ስመ ጥር ከሆኑት ሊቃውንት አንዱ ሲሆን ብዙ ጊዜ የሚታወቀው "ገባሬ መንክራት" በሚለው ስሙ ነው:: ገባሬ መንክራት የተባለውም እጅግ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን በመሥራቱ ነው::

+በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም ግዛት ሥር ተወልዶ ያደገው ቅዱስ ጐርጐርዮስ ከመመነኑ በፊት ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምሯል:: እርሱ በበርሃ እያለም ከሮም ዻዻሳት የአንዱ በማረፉ ተሿሚ ፍለጋ አበው ሱባኤ ገቡ:: እግዚአብሔርም "የበረሃውን ጐርጐርዮስን ፈልጉት" አላቸው::

+"እሺ!" ብለው ፍለጋ በርሃ ቢሔዱ ውዳሴ ከንቱን ይጠላልና ተሰወረባቸው:: እነርሱም እያዘኑ ተመልሰው በመንበረ ዽዽስናው ላይ ወንጌልን አኖሩና ተለያዩ:: በዚህ ጊዜ ቅዱስ መልአክ ወርዶ "ጐርጐርዮስ ሆይ! ልትሔድ ይገባሃል" አለው::

+እርሱም ወደ ከተማ ወርዶ ታላቁ ሊቅ ነባቤ መለኮት ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘእንዚናዙ ባለበት በዓለ ሲመቱ ተከብሯል::
ቅዱስ ጐርጐርዮስ በዘመኑ ብዙ መጻሕፍትን ደርሶ: የክርስቶስን መንጋም ጠብቆ: ድንቅ ድንቅ ተአምራትንም ፈጽሞ በዚህች ቀን ዐርፏል:: ከተአምራቱም:-

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

በቤትኽ እኖር ዘንድ እኔን ከጥፋት ጠብቀኝ!

“ጌታ ሆይ ይቅርታ በዚያ አለና ከደጅኽ አልራቅ። ፍቅርኽና ቸርነትኽም የሚገኝበት #መጠጊያ_የሚኾነኝን ቤትኽን አልተው። ከቆሰልኩበት የኃጢአት ቁስል ድኅነትን ሳላገኝ የስንፍና በሽታ ድምጹን አጥፍቶ እንዳያጠቃኝ፥ ኤሳው ብኩርናውን እንዳጣ በፍላጎቴ #ቤትኽን_እንዳልተው የቸልተኝነት ፍሬ የሚያፈራ ሥራ በውስጤ አይግባ።

[ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ]

ሰናይ ዕለተ ዓርብ!❤

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ዝምተኛው አባት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብጹዕ ወ ቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አራተኛ ፓትርያርክ የመታሰቢያ ሐውልት ሊቆምላቸው ነው ።

በሰዓሊና ቀራጺ ቡዝዬ ካሰሽ በስሜን አሜሪካን የተሰራው መታሰቢያ በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል አቡነ መርቆርዮስ አጽማቸው ባረፈበት ስፍራ እንዲቆም ይደረጋል።

ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

🎨" የድርጅቶን ዋጋ በኒየን አንድ ደረጃ ከፍ  ያድርጉ"

👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
    @GraceWallArt
(0943448637)
   
@hani_nata
(0936239392)
   
🛵 ያሉበት ድረስ በነፆ

👌 ምርጫዎ ስለሆንን እናመሠግናለን

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello kalkidan kefyalew, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Yealaf zemare group add argegne kaleh

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ሰሜናውያን ጉዞ ወደ አክሱም ጽዮን!
#ጽዮን አደየ

እግዚአብሔር ማስተዋሉን ሰቶን ወደ ቀድሞ ሰላማችን ይመልሰን ወንድም እህቶቼ የእውነት አምላክ ሲነሳ ሁሉም ነገር ይስተካከላል ኢትዮጵያ በራሷ እውነት ትድናለች እውነት እግዚአብሔር ነው ።

የአክሱም ጽዮኗ ማርያም የአስራት ሀገርሽን ወደቀደመ ክብራ ይመልስልን ዘንድ ለምኝልን ። 💚💛❤

ፅዮን አናታችን አምባ መጠጊያችን ❤❤❤

ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ጥያቄዎ
1. ስራ የለኝም እና ምን ሠርቼ የተሻለ ገቢ ላግኝ? ከሆነ
2. ስራ አለኝ ግን በማገኘው ደሞዝ ብቻ ኑሮ ውድነቱን መቋቋም አልቻልኩም እና እንዴት ተጨማሪ ገቢ ላግኝ? ከሆነ
3. ተማሪ ነኝ ግን ከትምህርቴ ጎን ለጎን ቢዝነስ በመስራት ለነገዬ ህይወት የሚሆን ገቢ እንዴት ማግኘት እችላለው? ከሆነ ለዚህ ሁሉ መልስ እኛጋ ያገኛሉ።

🥰 ፍላጎትዎ ከሆነ
👉 1. ስም
👉 2. ስልክ ቁጥር
👉 3. አድራሻ (ከተማ) በቴሌግራም ይላኩልን ወይም ይደውሉልን!

✍️  ምንም አይነት የስራ ልምድ አይጠይቅም።

ስ.ቁ 👉 ☎️   +251953034169
0918117333
ይደውሉልን
ዛሬውኑ  ይመዝገቡ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ቅዱሳኑን ያዳነ ቅዱስ መልአክ እኛንም ያድነን ዘንድ እንደ አባቶቻችን "አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ በአክናፊከ ምንትው:: አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ሠለስቱ እደው::" እያልን እንለምነው::

(መልክዐ ገብርኤል)

"በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን: ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ:: በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ:: አስተማረኝም ." †

(ዳን. ፱፥፳)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †

#አቤቱ የሆነብንን አስብ

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው ከፍ ከፍ አድርጋቸው።

@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ገብርኤል ሆይ፤ ከሰው ወገን ጠዋትና ማታ ከቶ እንደ እኔ ኀዘንና ትካዜ የሚበዛበት የለም፣
ከመላእክትም ወገን እንደ አንተ ያዘኑትን የሚያረጋጋ የለም፣
ገብርኤል ሆይ፤ ስለዚህ እኔም አውቄና አንተን አምኜ ያቀረብኩትን ይህን ጸሎት እንደ ትልቅ ዋጋ ቆጥረህ የሚያረጋጋ ቃልህን አሰማኝ።

መልክአ ገብርኤል

እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በዓል በሰላም አደረሰን።

@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

🎨" የድርጅቶን ዋጋ በኒየን አንድ ደረጃ ከፍ  ያድርጉ"

👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
    @GraceWallArt
(0943448637)
   
@hani_nata
(0936239392)
   
🛵 ያሉበት ድረስ በነፆ

👌 ምርጫዎ ስለሆንን እናመሠግናለን

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

እናቴ🥰

እመ ብርሃን አዛኚቷ እመቤት
ልነግርሽ ባነባ የሀዘኔን ብርታት
እንባዬ ቢጎረፍ ፊትሽ ተንበርክኬ
ምስጢሬን ነገርኩሽ የነውር ታሪኬ
ደጅሽ ማረፍያዬ ቢሆን ማልቀሻዬ
የውድቀቴ ሸፋኝ ሆንሽኝ ከለላዬ
ኪዳንሽ ሆነልኝ ለኔስ መዳኛዬ
የደስታዬ ምንጯ ቤዛዊተ ዓለም
አማልጅኝ ከልጅሽ ከመድኃኒዓለም
ዕፀ ህይወት ማርያም ድንግል አዛኚቱ
አንቺ አይደለሽ ወይ ለወልድ እናቱ
ከመጣብኝ ሀዘን ሆንኩ እንድፅናና
በረከት አሰታኝ ማርያም ሙዳየ መና

✍️የተክልዬዋ
@ortopiyaaa
@ortopiyaaa
@ortopiyaaa

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Family picture
በተለያዩ ምክንያቶች ተለያይተው ፎቶ አንደላይ መነሳት ያልቻሉ ቤተሰብዎን ፎቶዎች እኛ ዘንድ ያሰባስቡ!

Price 60x120 cm 4200 birr
           60x90 cm : 3800 birr
           50x80 cm : 2500 birr
          40x60cm : 1900 birr
          30x45 cm  : 1300 birr
Delivery fee: 200

👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
    @GraceWallArt   
@hani_nata
Join more our work
@grace_wallart

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Yonatan, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

እናስታውስዎ፦

✝ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ኢቲሳ ደብረ ጽላልሽ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም
ማኅበራችን ቤተ-ደራ መንፈሳዊ ማኅበር እሁድ ታህሳስ 13/04/17 ዓ.ም ጉዞ አዘጋጅቷል። ዕፁብና ድንቅ የሆነውን አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት የተወለዱበትን ቅዱስ ቦታ ያዩ ዘንድና በረከትን ያተርፉ ዘንድ ማኅበራችን ይህን ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ አዘጋጅቶሎታል። ስለዚህ ቀድመን ትኬቱን እንግዛ። ከመንፈሳዊ ጉዞ ፍቅርን፣ አንድነትን በረከትን ያተርፋሉና ስለዚህ ሁላችንም ተሳታፊዎች እንሁን።
ለበለጠ መረጃ: 0924517114/0919553753 ይደውሉ። ትኬቱን ባሉበት እናደርሳለን

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello 00000, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

@ortopiyaaa
@ortopiyaaa
@ortopiyaaa

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ሠላም ሠላም ዉድ የሀገሬ ልጆች
#ስራ አተዉ ተቸግረዋል ፣ወይም በአሉበት ሁነው ገቢዎን ማሳድ መለወጥ ይፈልጋሉ ?
#ተቀጥረዉ ሆነ ተማሬ ሆነ ስራ አጥ እንዲሁም "12"ክፍለ ያልመጣለችሁ ምን ልስራ ብለው ተቸግረዋል መፍተሔ እኛ ጋ አለ.
#ራዕይና አላማ አዉቀዉ አለቃ የሌለበት በነፃነት የሚሰሩት ደስተኛ ሁነው እራሶን ቤተስቦን ብሎም አገራችን የምነለዉጥብት ትልቅ መፍትሔ አለ !
ለችግሩ መፍትሔ ከፈለጉ 0918117333ወይም  በ251953034169 ይደውሉ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር አስቀምጡልን ጊዜዎን ሳይፈጁ በአሉበት ሁነዉ በያዝት ስልክ ይጠቀሙ አብረን እንዘምን!!!!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

💁‍♂⛪️እርሶ በቴሌግራም የቱን ቢያገኙ ደስ ይሎታል⁉️

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ሰላም የሃገሬ እንዴት ናችሁ። እንኳን ለ 2017 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ በአዲሱ አመት ምን አቅዳችኋል?
1ኛ የተሻለ ሥራ ?
2ኛ) ተጨማሪ ስራ?
3ኛ) የትርፍ ጊዜ ሥራ?
4)የ online ስራ?
4)የጊዜ እና የገንዘብ ነጻነት ያለው ሥራ? ባሉበት ቦታ ሆነው የሚሰሩት ምርጦ ሥራ
ሁሉም እኛ ጋር  ይህንን ሁሉ የምትፈልጉ ከሆነ ደውሉልኝ ወይም በውስጥ መስመር አናግሩኝ
👇👇👇👇👇
ሙሉ ስም
ስልክ ቁጥር
የመኖሪያ አድራሻ በውስጥ መስመር አስቀምጡልኝ
ለበለጠ መረጃ 09 53034169 ደውሉልኝ

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ጽዮን ማርያም

" ውስተ አፍላገ ባቢሎን ህየ ነበርነ ወበከይነ።
ሶበ ተዘከርነ ተዘከርናሃ ለጽዮን።
ውስተ ኩሐቲሃ ሰቀልነ ዕንዚራቲነ።
እስመ በህየ ተስእሉነ እለ ፄወዉነ ነገረ ማኅሌት።
ወእለሂ ይወስዱነ ይቤሉነ ኅለዩ ለነ እመ ኃልይሃ ለጽዮን።
እፎ ነኀሊ ማኅሌተ እግዚአብሔር በምድረ ነኪር።
እመሰ ረሳዕኩኪ ኢየሩሳሌም ለትርስዐኒ የማንየ።
ወይጥጋእ ልሳንየ በጉርዔየ ለእመ ኢተዘከርኩኪ።
ወለእመ ኢበፃዕኩ ለኢየሩሳሌም በቀዳሜ ትፍሥሕት። "

#ትርጉም

በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀምጠን ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስ ።
በአሓያ ዛፎቿ ላይ እንዚራችንን ሰቀልን።
የማረኩን በዚያ ዝማሬን ፈለጉብን የወሰዱንም የጽዮንን ዝማሬ ዘምሩልን አሉን።
የእግዚአብሔርን ዝማሬ በባዕድ ምድር እንዴት እንዘምራለን?
ኢየሩሳሌም ሆይ ብረሳሽ ቀኘ ትርሳኝ
ባላስብሽም ምላሴ በጉረሮዬ ይጣበቅ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድ።
መዝ 36:1-7

አዎ ጽዮንን በሌለችበት ሁሉም ባዶ ነው ምስጋናም ከእርሷ ዘንድ ነው ለቅሶም በእርሷ ፊት ነው የደስታ ምንጭ ከእርሷ ነው እንዴት እንርሳት እርሷን የረሳ ሕይወቱም የረሳ የሕይወት እንጀራ ከእርሷ ነውና
እንኳን አደረሳችሁ!

ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Beti, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

የንጉስ ጭካኔ ፥ ክንዱ ቢበረታ፤
ለጣዖት ሳንሰግድ፥ እኛ ሳንረታ፡፡
የምናምነው አምላክ፥ ሊያድነን ወደደ፤
ገብርኤል መጣና፥ እሳቱ በረደ፡፡

ፍላፃና ሠይፉን፥ አጠፈው መላኩ፤
ሰላም ይዞ መጣ፥ ባለም ለታወኩ፡፡
አትጠራጠሩ፥ ምልጃው ያስምረናል፤
የሚነደው እሳት፥ ሳይነካን ወተናል፡፡

የሰልስቱ ደቂቅ፥ የእጠሉጣ ብርታት፤
የድንግል አብሳሪ፥ የቂርቆስ ረዳት፡፡
በሚመጣው አለም፥ እንዳይበላኝ እሳት፤
አማልደኝ ከጌታ፥ ነፍሴን እንዲምራት፡፡

የነገርኩህ ሁሉ፥ በቀኑ ደረሰ ፤
በዘብር ገብርኤል፥ እንባዬ ታበሰ፡፡
ና ልጄ ስትለኝ፥ አልልህም እንቢ፤
ስለቴን ተቀበል፥ አባቴ ቁልቢ፡፡

የልቤን ነግሬህ፥ የቁልቢው ገብርኤል፤
ሳትረሳ ፈፀምከው፥ ስለቴን ተቀበል፡፡
ለንግስ እንመጣለን፥ አንተ አትረሳምና፤
ደሞ የዛሬ አመት፥ አድርሰን በደህና፡፡
+++++++
©ታዜና
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች

#ሼር
💚 @ortopiyaaa 💚
💛 @ortopiyaaa 💛
❤️ @ortopiyaaa ❤️

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

# መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል

❖ ከ7ቱ ሊቀነ መላእክት አንዱ ነው።

❖ ገብርኤል ማለት የስሙ ትርጉም የእግዚአብሔር ልጅ የሚመስል የእግዚአብሔር ሰው ማለት ሲሆን
ት.ዳን 3+25ሕዝ 9፥2 በተጨማሪም መጋቤ ሐዲስ( የሐዲስ ኪዳን አስተማሪ) እግዚእ ወገብረ (እግዚአብሔር አደረገ ) ማለት ነው።

❖ ብስራታዊ (አብሳሪው) መልአክ ነው። እመቤታችንንና ዘመዷ ኤልሳቤትና አብስሮአልና።

❖ ቅዱስ ገብርኤል አርባብ የተበለው ነገደ መላእክት አለቃ ነው።

❖ በመጀመሪያው የመላእክት ጦርነት ጊዜ አምላካችንን እስክናውቅ ባለንበት ፀንተን እንቁም በማለት መላእክት ያፀናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው።
❖ ተራዳዩ መልአክ ነው።

ዳን ፫፥፲፱-፳፯፣ዳን ፰፥፲፭ ዳን፱፥፳፩-፳፯
❖ ቅዱስ ገብርኤል ከ፯ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ነው።

❖ በጎ በጎውን የምንሰማበት መልካም መልካሙን የምናደርግበት መልካም ቀን ይሁንልን።

ቅዱሳኑን ያዳነ ቅዱስ መልአክ እኛንም ያድነን ዘንድ እንደ አባቶቻችን "አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ በአክናፊከ ምንትው:: አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ሠለስቱ እደው::" እያልን እንለምነው::

(መልክዐ ገብርኤል)

"በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን: ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ:: በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ:: አስተማረኝም ." †

(ዳን. ፱፥፳)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †

ለመቀላቀል👉@weludebirhane

#አቤቱ የሆነብንን አስብ

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

💁‍♂⛪️እርሶ በቴሌግራም የቱን ቢያገኙ ደስ ይሎታል⁉️

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

🎨" የድርጅቶን ዋጋ በኒየን አንድ ደረጃ ከፍ  ያድርጉ"

👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
    @GraceWallArt
(0943448637)
   
@hani_nata
(0936239392)
   
🛵 ያሉበት ድረስ በነፆ

👌 ምርጫዎ ስለሆንን እናመሠግናለን

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

🎨" የድርጅቶን ዋጋ በኒየን አንድ ደረጃ ከፍ  ያድርጉ"

👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
    @GraceWallArt
(0943448637)
   
@hani_nata
(0936239392)
   
🛵 ያሉበት ድረስ በነፆ

👌 ምርጫዎ ስለሆንን እናመሠግናለን

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

በጣም እኔ ሁሌም ነው የማለቅስለት ያሳዝነኛል በእውነት ሀጤያተኛ ብሆንም ግን ለፀሎት በቆምኩኝ ሰዓት በሀይምሮየ ይመጣል አምላኬ እባክን ቅዱስ መንፈስህን ላክለት እባክን ወደቤቱ መልሰው ብየ አለቅሳለሁ ያ ሁሉ ማንነቱ ጸጋው ተራቁቶ ሳየው በጣም ያሰለቅሰኛል ብቻ ለፈጣሪ የሚሳነው የለም አንድ ቀን ወደ ልቡ መልሶት እናያለን እርሱ ካለ የሚገደው የለም እሰከ ሚጠራ 😭😭እሰከዚያው ድርስ ግን በሰውነቱ እየወደድነው በሰራው በተግባሩ እያለቀስንለት በተሰፋ እንጠብቀው በእውነት

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

የክርስቶስ ሰላም ይብዛልን!

ከዚኽ በፊት “ነቢያት ስለራሳቸው ምን አሉ?” ብለን ከተናገሯቸው ቃላት በጣም በጥቂቱ አይተናል፤ በዚኽኛው [እና ምናልባት ከረዘመ በቀጣዩም] ጽሑፍ የምንዳስሰው ደግሞ እግዚአብሔር ለነቢያቱ የሰጣቸውን ምላሽ፥ በትኅትናቸውና እግዚአብሔርን ‛እሺ’ በማለታቸው ያደረገላቸውን ነገር በጥቂቱ እንመለከታለን።

ከነቢዩ ሙሴ እንጀምር፤ በፈርዖን ቤት ኹሉ ተመቻችቶለት ሲኖር ቆይቶ ‛ጎበዝ በኾነ ጊዜ’ ወንድሞቹ (ዕብራውያን) የሚሠሩትን ተመለከተ። ግብጻዊ የኾነውም ዕብራውያንን ሲመታ ተመለከተው፤ ማንም እንደሌለ አይቶ ‛ገደለው፤ በአሸዋም ውስጥ ሸሸገው።’ በቀጣዩም ቀን ኹለት ዕብራውያን ሲጣሉ አይቶ ‛በዳዩን፦ ለምን ባልንጀራኽን ትመታዋለኽ? አለው። ያም፦ በእኛ ላይ አንተን #አለቃ ወይስ #ዳኛ ማን አደረገኽ? ወይስ ግብፃዊውን እንደ ገደልኸው ልትገድለኝ ትሻለህን? አለው። ሙሴም፦ በእውነት ይህ ነገር ታውቋል ብሎ ፈራ። ፈርዖንም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ሙሴን ሊገድለው ፈለገ። ሙሴ ግን ከፈርዖን ፊት ኰበለለ፥ በምድያምም ምድር ተቀመጠ።’ ሙሉ ታሪኩን ኦሪት ዘጸአት 2፥11-15 ላይ ታገኙታላችኹ። አኹን እኛ የምንፈልገው ክፍል ላይ እናተኩር። ዕብራዊው ወንድሙን የሚደበድበው ሙሴ ለጠየቀው ጥያቄ ሲመልስ ‛በእኛ ላይ አንተን አለቃ ወይስ ዳኛ ማን አደረገኽ?’ ብሎት ነበር።

እንድናስተውል የፈለግኹት ነገር ምንድን ነው? እኛ ከእግዚአብሔር ጋር ከኾንን [እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሊኾን የታመነ ነውና] ማንም ሊያሸንፈን አይችልም። ከዚኽ ቀጥሎ የማስቀምጠው ጥቅስ ይኽን ሐሳብ ግልጽ የሚያደርግላችኹ ይመስለኛል፤ “ሙሴ በሕዝቡ #ሊፈርድ ተቀመጠ።” (ዘጸ. 18፥13) ‛ማን ፈራጅ አደረገኽ?’ የተባለው ሙሴ ‛በሕዝቡ ሊፈርድ ተቀመጠ።’

ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር በመኾኑ በሕዝቡ ላይ የመፍረድን ሥልጣን አግኝቷል። ከእግዚአብሔር ጋር ከኾንን ምንም እንኳን ከርሱ ጋር ባልነበርንበት ወራት የሚገዙን የነበሩ ከእግዚአብሔር የሚለዩን ሥራዎች የሚሰለጥኑብን ብንኾንም በሥጋችን ላይ ጨክነን ወደእግዚአብሔር ከቀረብን ግን ምንም አይነት ሥጋዊ ምኞት የማያሸንፈን እንደምንኾን ከሙሴ ታሪክ እንማራለን። ቅዱስ እስጢፋኖስም “ሹምና ፈራጅ እንድትሆን የሾመህ ማን ነው? ብለው የካዱትን፥ ይህን ሙሴን በቍጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።” (ሐዋ. 7፥35) በማለት ይናገራል።

“እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ እይ፥ እኔ ለፈርዖን አምላክ #አድርጌኻለሁ።” (ዘጸ. 7፥1) እኛ ከእግዚአብሔር ጋር ስንኾን ሥጋዊ ምኞታችንን መግታት ቀላል ይኾናል፤ ከዚኽም አልፈን ርኩሳን መናፍስትንም ማዘዝ መቆጣጠር እንችላለን።

ሙሴ በፈርዖን ቤት አድጎ ኋላ በሱ ላይ የተሾመው (የጸጋ አምላክነትን/ገዥነትን የተቀበለው) እግዚአብሔር ከርሱ ጋር በመኾኑ ነው። እኛም በቀደመ ሕይወታችን የርኩሳን አጋንንትን ምክር ሰምተን ለፈቃደ ሥጋችን አድልተን ከእግዚአብሔር ብንለይም እግዚአብሔር ከዚኽ ሕይወት እንደሚያወጣን አምነን፥ ለፍቅረ እግዚአብሔር ቀንተን፥ የተከፈለልንን ዋጋ አስበን ከኃጢአት ብንርቅ ነፍሳችንን ከማትረፋችንም በተጨማሪ በርኩሳን አጋንንት ላይም ሥልጣን ይኖረናል። ጌታችን በወንጌል “በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚኽም #የሚበልጥ ያደርጋል” (ዮሐ. 14፥12) እንዳለው።

አላብዛባችኹ፤ ሐሳቤን ልጠቅልል። እግዚአብሔር ኹላችንንም ወደርሱ እንድንመለስ ጠርቶናል። ወደርሱ እስከሚጠራን ቀን ድረስም በትዕግሥት የንስሐ ዕድሜን እየጨመረ ይጠብቀናል። ጥሪውን ተቀብለን ከመጣን የሠራነውን ከርሱ ያራቀንን ኃጢአት ምንም #ያልሠራን እስክመስል ድረስ በንስሐ ያጥበናል።

“ሁላችን በብዙ ነገር #እንሰናከላለንና በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው።” (ያዕ. 3፥2) እንዳለ ሐዋርያው ኹለመናችንን ለርሱ አስገዝተን ወደርሱ ተመልሰን ከርሱ ጋር እንድንኖር እግዚአብሔር ይርዳን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Yekidus gebrel photo lakulgn

Читать полностью…
Subscribe to a channel