ortodoxtewahedoo | Unsorted

Telegram-канал ortodoxtewahedoo - ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

3673

ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ። ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ›› ት.ኢሳ 58÷3 https://youtu.be/csxxAMGtC4I ለመቀላቀል http://t.me/ortodoxtewahedo

Subscribe to a channel

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ምን አይነት መዝሙሮችን ይፈልጋሉ?👇👇👇

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

✞ጥያቄ✞✞

➥ ቤተክርስቲያን የማትቀበለው ጉባኤ ከተዘረዘሩት ውስጥ የቱ ነው?

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

በሰ/ወሎ ዞን በመቄት ወረዳ የምትገኘው ገዳመ ሲሀት ቅ/ፍቅርተ ክርስቶስ አንድነት ገዳም
_ይቺ ገዳም ለታመሙና ለተጨነቁ መፍትሄ በመሆን የምትታወቅ ገዳም ስትሆን ዛሬ ላይ ግን ከኛ ከልጆቿ መፍትሄ የምትሻበት ደረጃ ላይ ደርሳለች።ይቺ ገዳም ከገደል ዳር ላይ የተሰራች በመሆኗና ይህ ገደልም በጎርፍና መሰል አደጋ እነተሸረሸረ ከቤተ-ክርስቲያኑ እስከ ገደሉ ያለው እርቀት ከ1ሜትር ያልበለጠ ሁኗል።ስለሆነም ይቺን ከ400ዓመት በላይ የቆየችውን ይህቺን ድንቅ  ገዳም ከተጋረጠባት ከባድ አደጋ እንታደጋት።
ስለዚህ እሁድ 29/03/2017  ዓ/ም በአዲስ አበባ ሜኪሲኮ ማህደረ ስብሐት ቅ/ልደታ ለማርያምና ደ/መድሀኒዓለም ቤ/ክ አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣መምህራን፣ዘማርያን እና ታዋቂ እንግዶች በተገኙበት በሚዘጋጀው ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ላይ በመገኘት የድርሻችሁን እንድታደርጉልን በፃድቋ ስም እንለምናለን።
በባንክ መደገፍ ለምትፈልጉ
የኢ/ን/ባ
1000076665285
አቢሲንያ
8089205
ስለምታደርጉት ሁሉ ፃድቋ በበረከት ትጎብኛቹሁ።
🙏🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

እንኳን አደረሳችሁ🙏፳፬🥰🥰🥰

@ortopiyaaa
@ortopiyaaa
@ortopiyaaa

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

✝✞✝ እንኩዋን አደረሳችሁ ✝✞✝

"" ቅዱስ አባታችን #ተክለ_ሃይማኖት ከ24ቱ #ካህናተ_ሰማይ ጋር መንበረ ጸባኦትን ያጠኑበት ቀን ኅዳር 24 ይታሰባል:: ""
ስለዚህም አበው "ተክለ ሃይማኖት #ሱራፊ እለ ስድስቱ ክነፊሁ (6 ክንፍ ያለው አባታችን መልአኩ ሱራፊን ሆነ)" ሲሉ ያመሰግኗቸዋል::

" የቅዱሱ አባታችንና የቅድስት ገዳሙ (#ደብረ #ሊባኖስ) በረከት ይደርብን:: " 


" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

✝አቡነ ዜና ማርቆስ✝

ባርከኒ አባ እንሣእ በረከተከ በእንተ ሰላማ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዜናማርቆስ አባ ባርከኒ እንሣእ በረከተከ።

✝የጻድቁ ልደታቸው ኅዳር 24 ነው።

✝ከበዓለ ልደታቸው በረከት ያድለን።

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

🎨" የድርጅቶን ዋጋ በኒየን አንድ ደረጃ ከፍ  ያድርጉ"

👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
    @GraceWallArt
(0943448637)
   
@hani_nata
(0936239392)
   
🛵 ያሉበት ድረስ በነፆ

👌 ምርጫዎ ስለሆንን እናመሠግናለን

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

🎨" የድርጅቶን ዋጋ በኒየን አንድ ደረጃ ከፍ  ያድርጉ"

👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
    @GraceWallArt
(0943448637)
   
@hani_nata
(0936239392)
   
🛵 ያሉበት ድረስ በነፆ

👌 ምርጫዎ ስለሆንን እናመሠግናለን

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Muluken, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ሊቀ_ሰማዕታት1ቅዱስ_ጊዮርጊስ

እንኳን ለሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል አደረሰን !!!

ፀሐይና የአጥቢያ ኮከብ የተባለ፣ ታላቅ እና ክቡር ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ የክርስቶስ ወታደር ሆኖ ክርስትናን እያጸና ጣኦትን የተቃወመ ሰማዕት።

መገረፍና እስራት፣ ሞት ወደኋላ ያልጎተተው ጻድቅ አባት ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ ጻድቅ፣ ቅዱስ፣ ሰባኪ፣ ሰማዕት የሆነው የልዳው ኮከብ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬም በቤተ ክርስቲያናችን ይታሰባል።

የሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በረከትና የእምነት ጽናት በእኛም ላይ ይሁን 🙏

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

«አንተ ታማኝ ሆነኽ #በፈቃድኽ ከምትሠራቸው ኃጢአቶች ከታቀብክ እግዚአብሔር ደግሞ ያለፍቃድኽ እንድትሠራቸው ከሚመጡብኽ ኃጢአቶች ኹሉ #ይጠብቅኻል» - አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello ደንነት, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Firaol, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

You need to send a message, too! For example:
/welcome Hello $username, welcome to $title!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

You need to send a message, too! For example:
/goodbye Goodbye, $username!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Yodit, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ኢትዮጵያዊነት ምንድነው❕?

. ▬▬▬▬▬▬  ▬▬▬▬▬▬

ኢትዮጵያዊነት እንቁነት ነው። ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከሌሎች የሚለየው ልዩ ነገር አለው። ኢትዮጲያዊነት ባህል ነው ያደግንበት ስርአት ቆንጣጭ መካሪ ኮርኮሚ ፈርተን። ኢትዮጲያዊነት ነብስ ነው ካገር የወጣ ህይወቱ የሚናፍቃት ነብሱ ሚንሰፈሰፍላት። ኢትዮጲያዊነት ንግስና ነው በሄድንበት የምንከበርባት። ምንም እንኳ መከበሪያችን ተደርጎ የተሳለው ነጭ ማሸነፋችን ቢመስልም ነገር ግን በማናውቀው ጥበባችን እና ዕውቀታችንም ጭምር እንደ ነገስታት በአለም የነገስን ነገር ግን የራሳችንን የጣልን የሌሎችን ያገዘፍን ነን። ያው ትርጉሙን ስላልተረዳን ነው በሚል እንለፈው። በሃገራችን እንኩራ ሃገርን እንውደድ ጊዜው አልረፈደም ካልቃን ግን አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ብዙ ጊዜያት ይረፍዳሉ።



▬▬▬▬▬▬  ▬▬▬▬▬▬


🍀 ኢትዮጲያዊነት ይለምልም 🇪🇹
እንዴት አረፈዳችሁ
መልካም ውሎ
መልካም ዕለተ ማክሰኞ

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ይቺ ገዳም በሰ/ውሎ መቄት ወረዳ የምትገኝ ገዳመ ሲሃት ቅ/ፍቅርተ ክርስቶስ ገዳም ትባላለች።ይቺ ገዳም ላዘኑ ለታመሙ ሁሉ መፍትሄ ሁኖ የኖረች ገዳም ናት ዛሬ ላይ ግን ከኛ ከልጆቿ መፍትሄ የምትሻበት ደረጃ ላይ ደርሳለች ከላይ በፎቶ ላይ እንደምታዩት ገዳሟ ከገደል ጫፍ ላይ የተሰራች በመሆኗና ይህ ገደልም በጎርፍና መሰል አደጋ እየተሸረሸረ ቤተ ክርስቲያኗ ከገደሉ ያላት እርቀት ከ1ሜትር ያልበለጠ ሁኗል ስለሆነም ሁላቹሁም ይቺን ከ400 ዓመት በላይ የቆየች ገዳም እንድትታደጉልን ትልቅ የበረከት ገባኤ በአዲስ አበባ ሜኪሲኮ ማህደረ ስብሀት ቅ/ልደታ ለማርያም እና ደ/መድሃኒዓለም ቤ/ክ እሁድ/29/03/2017 በሚዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ላይ በመገኘት ለገዳሟ የሚቻላቹሁን እንድታደርጉልን በፃድቋ ስም እለምናለሁ።
በ ባንክ መርዳት ለምትፈልጉም በኢ/ን/ባ1000076665285 አቢሲንያ 8089205 ስለምታደርጉት ድጋፍ ሁሉ ፃድቋ በበረከት ትጎብኛቹህ።

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Ayu, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

✝✞✝ እንኩዋን አደረሳችሁ ✝✞✝

"" ቅዱስ አባታችን #ተክለ_ሃይማኖት ከ24ቱ #ካህናተ_ሰማይ ጋር መንበረ ጸባኦትን ያጠኑበት ቀን ኅዳር 24 ይታሰባል:: ""
ስለዚህም አበው "ተክለ ሃይማኖት #ሱራፊ እለ ስድስቱ ክነፊሁ (6 ክንፍ ያለው አባታችን መልአኩ ሱራፊን ሆነ)" ሲሉ ያመሰግኗቸዋል::

" የቅዱሱ አባታችንና የቅድስት ገዳሙ (#ደብረ #ሊባኖስ) በረከት ይደርብን:: " 


" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ):
††† ❇️እንኳን ለ24ቱ ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ እና ቅዱስ አዝቂር ሰማዕት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

†††✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††✝

††† ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ †††

††† እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ መቶ (100): በክፍለ ነገድ አሥር (10) አድርጓቸዋል:: አቀማመጣቸውንም በሦስት ሰማያትና በ10 ከተሞች (ዓለማት) አድርጓል::

††† መላእክት ያሉባቸው ከተሞች ከታች ወደ ላይ "ኤረር: ራማና ኢዮር" ይባላሉ:: አሥሩ ክፍለ ነገድ ደግሞ ከነ አለቆቻቸው ይህንን ይመስላሉ:-
1."አጋእዝት" (የቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል: አሁን የተረፉት በቅዱስ ሚካኤል ሥር ናቸው)
2."ኪሩቤል" (አለቃቸው ኪሩብ)
3."ሱራፌል" (አለቃቸው ሱራፊ)
4."ኃይላት" (አለቃቸው ሚካኤል)
5."አርባብ" (አለቃቸው ገብርኤል)
6."መናብርት" (አለቃቸው ሩፋኤል)
7."ስልጣናት" (አለቃቸው ሱርያል)
8."መኳንንት" (አለቃቸው ሰዳካኤል)
9."ሊቃናት" (አለቃቸው ሰላታኤል)
10."መላእክት" (አለቃቸው አናንኤል) ናቸው::

††† ከእነዚህም:-
*አጋእዝት: *ኪሩቤል *ሱራፌልና *ኃይላት መኖሪያቸው በኢዮር (በ3ኛው ሰማይ) ነው::
*አርባብ: *መናብርትና *ስልጣናት ቤታቸው ራማ (2ኛው ሰማይ) ነው::
*መኳንንት: *ሊቃናትና *መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር (በ1ኛው) ሰማይ ነው::

መላእክት ተፈጥሯቸው እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ ነው:: አይራቡም: አይጠሙም: አይዋለዱም: አይሞቱም:: ተፈጥሯቸውም ረቂቅ ነው:: ተግባራቸውም ዘወትር "ቅዱስ: ቅዱስ: ቅዱስ" እያሉ ፈጣሪያቸውን ማመስገን ነው:: ምግባቸውም ይሔው ነው::

ዕረፍት ብሎ ነገርን አያውቁም:: "አኮቴቶሙ ዕረፍቶሙ: ወዕረፍቶሙ አኮቴቶሙ" እንዲል:: በተጨማሪም መልአክ ማለት ተላላኪ (አገልጋይ) ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም: ለመዓትም ይላካሉ::

ምሕረትን ያወርዳሉ:: ልመናን ያሳርጋሉ:: ቅጡ ሲባሉም ይቀጣሉ:: ስነ ፍጥረት (አራቱ ወቅቶች) እንዳይዛቡ ይጠብቃሉ::
*ዘወትርም ስለ ሰው ልጆች ያማልዳሉ:: (ዘካ. 1:12)
*ምሥጢርን ይገልጣሉ:: (ዳን. 9:21)
*ይረዳሉ:: (ኢያ. 5:13)
*እንዳንሰናከል ይጠብቃሉ:: (መዝ. 90:11)
*ያድናሉ:: (መዝ. 33:7)
*ስግደት ይገባቸዋል:: (መሳ. 13:20, ኢያ. 5:13, ራዕ. 22:8)
*በፍርድ ቀንም ኃጥአንን ከጻድቃን ይለያሉ:: (ማቴ. 25:31)
*በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ሕይወትና ድኅነት ሲባል ከፈጣሪያቸው የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ሲጠብቁና ፈቃዱን ሲፈጽሙ ይኖራሉ::

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህች ዕለት የሃያ አራቱን ቅዱሳን ካህናተ ሰማይን መታሰቢያ ታደርጋለች:: እኒህ ቅዱሳን መላእክት በነገድ 10 ሲሆኑ መጠሪያቸው "ሱራፌል" : መኖሪያቸውም በኢዮር ነው:: ነገር ግን ሃያ አራቱ አለቆቻቸው ተመርጠው በመሪያቸው በቅዱስ ሱራፊ አለቅነት በጽርሐ አርያም ያገለግላሉ::

በቀናች ሃይማኖት ትምሕርት ሁሉም ቅዱሳን መላእክት ለእግዚአብሔር ቅርብ ቢሆኑም: በነጠላ የቅዱስ ሚካኤልን ያህል: በነገድ ደግሞ የኪሩቤል (አራቱ እንስሳ) እና የሱራፌልን (ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ) ያህል ቅርብ የለም::

††† ሃያ አራቱ ቅዱሳን ካህናት ሥራቸው:-
1.እንደ ሞገድ ከአንደበታቸው ምስጋና እየወጣ: ጧት ማታ ፈጣሪያቸውን ይቀድሱታል:: (ኢሳ. 6:1, ራዕይ 4:11, 5:11)

2.የሥላሴን መንበር ያለ ማቋረጥ ያጥናሉ:: (ራዕይ 5:8)

3.የሰው ልጆችን: በተለይም የቅዱሳንን ጸሎት በማዕጠንታቸው ያሳርጋሉ:: (ራዕይ 8:3)

4.የረከሱትን ይቀድሳሉ:: (ኢሳ. 6:6)

5.ዘወትርም ለሰው ልጆች ምሕረትን ሲለምኑ ይኖራሉ:: (ዘካ. 1:12)

ስለ እነዚህ ቅዱሳን ካህናት (ሱራፌል) ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ብዙ ይላል:: ለምሳሌ:- ዐቢይ ነቢይ ወልዑለ ቃል ኢሳይያስ ፈጣሪው ተቀይሞት በነበረበትና ዖዝያን በሞተበት ወራት: ግሩማን ሆነው ሥላሴን "ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ" እያሉ ዙሪያውን ከበው ሲያመሰግኑ ሰምቷል::

ከእነርሱም አንዱ (ሱራፊ) መጥቶ በጉጠት እሳት ከንፈሩን ዳስሶ ከለምጹ አንጽቶታል:: (ኢሳ. 6:1) አቡቀለምሲስ የተባለ ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ በግርማ: በአምሳለ አረጋዊ ተመልክቷቸዋል:: (ራዕይ 4:4)

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን የመሰሉ ቅዱሳን ሊቃውንት ደግሞ በጣዕመ ምስጋናቸው ሲገልጿቸው:-
"ካህናተ ሰማይ ቅውማን በዐውዱ::
አክሊላቲሆሙ ያወርዱ::
ቅድመ መንበሩ እንዘ ይሰግዱ::
ይርዕዱ::
ከመ ኢይዝብጦሙ ሶበ ይበርቅ ነዱ::" ብለዋል:: (መጽሐፈ ሰዓታት)
ትርጉሙም "በፈጣሪ መንበር ዙሪያ የሚቆሙ የሰማይ ካህናት አክሊለ ክብራቸውን አውርደው በመንበሩ ፊት ይሰግዳሉ:: መብረቀ መለኮቱ በተገለጠ ጊዜም በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ::" ነው:: ግሩም ባሕርየ ሥላሴን ሊቋቋመው የሚችል ፍጡር የለምና::

ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ በምስጋናቸው: በማዕጠንታቸውና በምልጃቸው ክቡራን ናቸውና ዘወትር ልናከብራቸው ይገባናል:: የረከሰ ማንነታችንን ይቀድሱ ዘንድ: በምልጃቸውም ዘንድ እንድንታሰብ: ጸሎታችንንም ያሳርጉልን ዘንድ እንለምናቸው::

††† ኅዳር 24 ቀን ዓመታዊ በዓላቸው ነው ማለት በየወሩ በ24 ወርኀዊ በዓላቸው መሆኑን ያሳያልና ዘወትር ልናስባቸው ይገባል::

በተለይ ያዘነን ልብ ደስ ያሰኛሉና እንደ ሊቃውንት እንዲህ ብለን እንጠራቸዋለን::
"ሰላም ለክሙ ካህናተ ሕጉ ወትዕዛዙ::
ለእግዚአብሔር ቃል ዘጶዴሬ ሥጋ አራዙ::
እምነቅዐ አፉክሙ ሐሴት ዘኢይነጽፍ ዉሒዙ::
ኪያየ ኅዙነ ወትኩዘ ልብ ናዝዙ::
ወበክንፍክሙ ብርሃናዊ ዐውድየ ሐውዙ::" (አርኬ ዘኅዳር 24)

††† ቅዱስ አዝቂር ካህን †††

††† ከዜና ካህናት ወደ ዜና ካህናት እንለፍ:: ቅዱስ አዝቂርን የመሰሉ ካህናት ምንም ሥጋ ለባሽ ቢሆኑም ሥልጣናቸውና ግብራቸው ሰማያዊ ነውና መላእክትን ይመስላሉ:: አንድም በስልጣናቸው ከመላእክት ይበልጣሉ::

"ካህናትየ ይቤሎሙ::
ወእምኩሉ ፈድፋደ አክበሮሙ::
ዘኢተገብረ ለመላእክት ተገብረ ለካህናት::"

ትርጉም "አገልጋዮቼ አላቸው::
ከሁሉ በላይ አከበራቸው::
ለመላእክት ያልተደረገ ለካህናት ተደረገ::" እንዳለ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ:: (መጽሐፈ ቅዳሴ)

ቅዱስ አዝቂርም የናግራን (አሁን የመን) ክርስቲያን ሲሆን በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በንጹሕ የክህነት አገልግሎቱ ሰውንም: ክርስቶስንም ደስ ያሰኘ አባት ነው:: አሕዛብን: አረማውያንን ሁሉ ድል ነስቶ መንጋውን ጠብቋል:: በቁጥርም አብዝቷል::

ገርፈው ቢያስሩት በቃሉ ስልጣን የብረት በሮችን ከፍቶ አሕዛብን ሲያጠምቅ ተገኝቷል:: ሊገድሉት ሲወስዱት በየመንገዱ ይሰብክ ነበር:: ገዳዮቹ በርሃ ላይ ውኃ ጥም እንዳይገድላቸውም በአንዲት ገበታ ላይ ዝናም አዝንሞ 700 ወታደሮች ከነ ፈረሶቻቸው አጥግቧል::

በመጨረሻም አይሁድ በድንጋይ ሲወግሩት ድንጋዮቹ እየተመለሱ አናት አናታቸውን ብሏቸዋል:: ያን ጊዜ በብስጭት አንገቱን ቆርጠውታል:: አብረውም ቅዱስ ኪርያቅ ወዳጁንና 48 ተከታዮቹን ሰይፈዋል::

††† አምላከ ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ ከምስጋናቸው ሐሴትን: ከማዕጠንታቸው በጐ መዓዛን ያውርድልን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello Alayee, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ወየው ወገኔ ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያሳርፍላቸው አሜን

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello SEIFU, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

✞ጥያቄ✞✞

➥ ቤተክርስቲያን የማትቀበለው ጉባኤ ከተዘረዘሩት ውስጥ የቱ ነው?

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

🤑 TON
⭐️ TELEGRAM PREMIUM
⭐️ TELEGRAM STAR
   
መግዛት የምትፈልጉ በውስጥ አናግሩኝ

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Please የ ጊዮርጊስ ፎቶ 🙏🙏🙏

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ሰንበተ ክርስትያን

እሑድ ማለት"አሐደ" ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲኾን ትርጉሙ የመጀመሪያ እንደማለት ነው። ይኽች ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ "ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን " በመባል ትታወቃለች።

ዮሐንስም በራዕዩ "የጌታ ቀን" ያላት ናት
(ራዕይ 1፥10)

ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ "ዕለተ እግዚአብሔር" የሚላት ዕለተ እሑድ ናት።

መልካም ዕለተ ሰንበት ይኹንልን

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Hello ቀሲስ ወልደ ጊዮርጊስ, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

/goodbye@jh0ker_welcomebot

Читать полностью…
Subscribe to a channel