አይቶ መለፍ እጅግ በጠም ይከብደል፡፡
እባካቹ እናንተ ደጋጎች ሼር ሼር አድርጉላቸው
ወዳጆቼ በዚ ከበድ ወቅት የበረከት ስራ እንስራ መርዳት ቢያቅተን ሼር ማድረግ እራሱ ትልቅ እርዳታ ነው:: ይህ የምትመለከቱወት ህፃን የሁለት አመት ከሶስት ወር ህፃን ነት የካንሰር ታማሚ ነት ካንሰር በሽታ የያዘውት ከተወለደች ከሶስ ወር ጀመሮ የካንሰር ታማሚ ነት ይሄው እሷም እናቱወም አባቱወም ሁለት አመት ሙሉ አሚን አጠቀለይ ሆስፒተል ንብረታቸውን ሸጠው እሷን በማስታመም ላይ ይገኛሉ ህፃኑወን ካንሰሩ አይንወን አሳውሮታል አንደኛው አይንወ በቀዶ ጥገና ወጥቶለት አንደኛውንም አይኑወ ከሰሞኑ እንደሚወጣ ከዶክቶሮቹ ሰምቻለው በዚያ ላይ አንድ አፍንጫወን ደፍኖታል እናትና አባትወ ለሁለት አመት ከልጃቸው ጋ ስቃይ ውስጥ ይገኛሉ አሁን ላይ ከስቃዩም በላይ የህክምና እና የመድሀኒቱ ወጪ ሌላ ስቃይ ነው የሆነባቸው ለመድሀኒቱና ህክምና ለአስራ አምስት ቀን ሰባ ሺ ብር ይፈልጋሉ አሁን ላይ ውጪ ሄደ የመታከም እድልም አለት ለህክምናወ ወጪ ከአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር በላይ ይፈልጋልጋሉ እና ልጅቷም በስቃይ ውስጥ እናትና አባትም በስቃይና ጭንቀት ውስጥ ናቸው እንድረስላቸው ለወገን ደራሽ ወገን ነው የቻልነውን አነሰም በዛ ሳንል እጃችንን እንዘርጋላቸው ስል በፈጠሪ ስም እንማፀናለን መርዳት ለምትፈልጉ
ንግድ ባንክ 1000603332346 እስማኢል ሀሠን አብደላ (Ismail Hassen)
ስልክ ቁጥር 0960067157
የማትችሉ በፀሎትና ሼር ሼር ሼር በማድረግ እንርዳቸው
ሼር ሼር ሼር በማድረግ አይከፈልበትም
☞ ሁለችንም 5 ብር ብንረደት ልነሰክመት እንችለለን፡፡
☞ ሁለቹም ለፈጠሪ ብለቹ ሲትረዱ የረደቹበትን መረጀ በዚ profile አስቀምጡልን፡፡
#የሚፈውስ_እንባ
ሰውን የምታድን #ክርስቶስ ሆይ! ከአንተ በቀር ማን ያድነኛል? የድኅነት ምንጭ ከኾንከው ከአንተ በቀር የታመመችውን ነፍሴን ማን ይፈውሳታል? አቤቱ ሆይ! እንኪያስ የታመመችውን ችግረኛ ሴት እንደፈወስካት እኔንም ከጥፋት ከመረረ ገሃነም አድነኝ፡፡ ምሕረት ቸርነትኅ በእኔ ላይ ትኹን፡፡ ጠላቴን ድል አደርገው ዘንድ እርዳኝ፡፡ ብርቱ በምትኾን ክንድኅ ደካማ የምኾን እኔን አበርታኝ፡፡ አበርታኝና ለተጋድሎ የተዘጋጀኹ እንደኾንኩ ዐይቶ ጠላቴ ይራድ፤ ይንቀጥቀጥ፤ ይፈርም፡፡ አበርታኝና ጠላቴ የተዋረደ ይኹን፡፡ አበርታኝና ጠላቴ (ዲያብሎስ) በሐፍረት ከፊቴ ይመለስ፡፡ አበርታኝና እኔም ስምኽን ከፍ ከፍ ላድርገው፡፡
አቤቱ ሆይ! ጐስቋላ የምኾን #እንባዬን ተቀበልልኝ፤ ዕዳዬንም ፋቅልኝ፡፡ ፍቅርኅ የእኔን የበደለኛውን የክፉ ምግባሬ ፍሬ ይደምስስልኝ፤ ምረረ ገሃነምም አያግኘኝ፡፡ ቸርና ሰው ወዳጅ ሆይ! ዕዳዬን ደምስስልኝና ጠላቴ ይፈር፡፡ ፈተናውን ድል አደርግ ዘንድ፥ ድል አድርጌም ዘወትር ከአንተ ጋር እኖር ዘንድ ምሕረት ቸርነትኅ ከእኔ ጋር ትኹን፡፡
አቤቱ ሆይ! #አልቅሳ ሰምታኻታልና፥ #በሚፈውስ_እንባ አጥባኻታልና፥ ፍጥረትን ኹሉ ለፈጠርከው ለአንተም ቤተ መቅደስህ አድርጋኻታልና በደለኛ የምትኾን ሰውነቴ፥ ከባሕርይ አባትኅ ከአብ ከባሕርይ ሕይወትኅ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ታከብርኻለች፡፡ አሜን!!!
#ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ
#ገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖
ኢትዮጵያዊነት ምንድነው❕?
. ▬▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬▬
ኢትዮጵያዊነት እንቁነት ነው። ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከሌሎች የሚለየው ልዩ ነገር አለው። ኢትዮጲያዊነት ባህል ነው ያደግንበት ስርአት ቆንጣጭ መካሪ ኮርኮሚ ፈርተን። ኢትዮጲያዊነት ነብስ ነው ካገር የወጣ ህይወቱ የሚናፍቃት ነብሱ ሚንሰፈሰፍላት። ኢትዮጲያዊነት ንግስና ነው በሄድንበት የምንከበርባት። ምንም እንኳ መከበሪያችን ተደርጎ የተሳለው ነጭ ማሸነፋችን ቢመስልም ነገር ግን በማናውቀው ጥበባችን እና ዕውቀታችንም ጭምር እንደ ነገስታት በአለም የነገስን ነገር ግን የራሳችንን የጣልን የሌሎችን ያገዘፍን ነን። ያው ትርጉሙን ስላልተረዳን ነው በሚል እንለፈው። በሃገራችን እንኩራ ሃገርን እንውደድ ጊዜው አልረፈደም ካልቃን ግን አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ብዙ ጊዜያት ይረፍዳሉ።
▬▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬▬
🍀 ኢትዮጲያዊነት ይለምልም 🇪🇹
እንዴት አረፈዳችሁ
መልካም ውሎ
መልካም ዕለተ ማክሰኞ
ይቺ ገዳም በሰ/ውሎ መቄት ወረዳ የምትገኝ ገዳመ ሲሃት ቅ/ፍቅርተ ክርስቶስ ገዳም ትባላለች።ይቺ ገዳም ላዘኑ ለታመሙ ሁሉ መፍትሄ ሁኖ የኖረች ገዳም ናት ዛሬ ላይ ግን ከኛ ከልጆቿ መፍትሄ የምትሻበት ደረጃ ላይ ደርሳለች ከላይ በፎቶ ላይ እንደምታዩት ገዳሟ ከገደል ጫፍ ላይ የተሰራች በመሆኗና ይህ ገደልም በጎርፍና መሰል አደጋ እየተሸረሸረ ቤተ ክርስቲያኗ ከገደሉ ያላት እርቀት ከ1ሜትር ያልበለጠ ሁኗል ስለሆነም ሁላቹሁም ይቺን ከ400 ዓመት በላይ የቆየች ገዳም እንድትታደጉልን ትልቅ የበረከት ገባኤ በአዲስ አበባ ሜኪሲኮ ማህደረ ስብሀት ቅ/ልደታ ለማርያም እና ደ/መድሃኒዓለም ቤ/ክ እሁድ/29/03/2017 በሚዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ላይ በመገኘት ለገዳሟ የሚቻላቹሁን እንድታደርጉልን በፃድቋ ስም እለምናለሁ።
በ ባንክ መርዳት ለምትፈልጉም በኢ/ን/ባ1000076665285 አቢሲንያ 8089205 ስለምታደርጉት ድጋፍ ሁሉ ፃድቋ በበረከት ትጎብኛቹህ።
✝✞✝ እንኩዋን አደረሳችሁ ✝✞✝
"" ቅዱስ አባታችን #ተክለ_ሃይማኖት ከ24ቱ #ካህናተ_ሰማይ ጋር መንበረ ጸባኦትን ያጠኑበት ቀን ኅዳር 24 ይታሰባል:: ""
ስለዚህም አበው "ተክለ ሃይማኖት #ሱራፊ እለ ስድስቱ ክነፊሁ (6 ክንፍ ያለው አባታችን መልአኩ ሱራፊን ሆነ)" ሲሉ ያመሰግኗቸዋል::
" የቅዱሱ አባታችንና የቅድስት ገዳሙ (#ደብረ #ሊባኖስ) በረከት ይደርብን:: "
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ):
††† ❇️እንኳን ለ24ቱ ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ እና ቅዱስ አዝቂር ሰማዕት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
†††✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††✝
††† ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ †††
††† እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ መቶ (100): በክፍለ ነገድ አሥር (10) አድርጓቸዋል:: አቀማመጣቸውንም በሦስት ሰማያትና በ10 ከተሞች (ዓለማት) አድርጓል::
††† መላእክት ያሉባቸው ከተሞች ከታች ወደ ላይ "ኤረር: ራማና ኢዮር" ይባላሉ:: አሥሩ ክፍለ ነገድ ደግሞ ከነ አለቆቻቸው ይህንን ይመስላሉ:-
1."አጋእዝት" (የቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል: አሁን የተረፉት በቅዱስ ሚካኤል ሥር ናቸው)
2."ኪሩቤል" (አለቃቸው ኪሩብ)
3."ሱራፌል" (አለቃቸው ሱራፊ)
4."ኃይላት" (አለቃቸው ሚካኤል)
5."አርባብ" (አለቃቸው ገብርኤል)
6."መናብርት" (አለቃቸው ሩፋኤል)
7."ስልጣናት" (አለቃቸው ሱርያል)
8."መኳንንት" (አለቃቸው ሰዳካኤል)
9."ሊቃናት" (አለቃቸው ሰላታኤል)
10."መላእክት" (አለቃቸው አናንኤል) ናቸው::
††† ከእነዚህም:-
*አጋእዝት: *ኪሩቤል *ሱራፌልና *ኃይላት መኖሪያቸው በኢዮር (በ3ኛው ሰማይ) ነው::
*አርባብ: *መናብርትና *ስልጣናት ቤታቸው ራማ (2ኛው ሰማይ) ነው::
*መኳንንት: *ሊቃናትና *መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር (በ1ኛው) ሰማይ ነው::
መላእክት ተፈጥሯቸው እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ ነው:: አይራቡም: አይጠሙም: አይዋለዱም: አይሞቱም:: ተፈጥሯቸውም ረቂቅ ነው:: ተግባራቸውም ዘወትር "ቅዱስ: ቅዱስ: ቅዱስ" እያሉ ፈጣሪያቸውን ማመስገን ነው:: ምግባቸውም ይሔው ነው::
ዕረፍት ብሎ ነገርን አያውቁም:: "አኮቴቶሙ ዕረፍቶሙ: ወዕረፍቶሙ አኮቴቶሙ" እንዲል:: በተጨማሪም መልአክ ማለት ተላላኪ (አገልጋይ) ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም: ለመዓትም ይላካሉ::
ምሕረትን ያወርዳሉ:: ልመናን ያሳርጋሉ:: ቅጡ ሲባሉም ይቀጣሉ:: ስነ ፍጥረት (አራቱ ወቅቶች) እንዳይዛቡ ይጠብቃሉ::
*ዘወትርም ስለ ሰው ልጆች ያማልዳሉ:: (ዘካ. 1:12)
*ምሥጢርን ይገልጣሉ:: (ዳን. 9:21)
*ይረዳሉ:: (ኢያ. 5:13)
*እንዳንሰናከል ይጠብቃሉ:: (መዝ. 90:11)
*ያድናሉ:: (መዝ. 33:7)
*ስግደት ይገባቸዋል:: (መሳ. 13:20, ኢያ. 5:13, ራዕ. 22:8)
*በፍርድ ቀንም ኃጥአንን ከጻድቃን ይለያሉ:: (ማቴ. 25:31)
*በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ሕይወትና ድኅነት ሲባል ከፈጣሪያቸው የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ሲጠብቁና ፈቃዱን ሲፈጽሙ ይኖራሉ::
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህች ዕለት የሃያ አራቱን ቅዱሳን ካህናተ ሰማይን መታሰቢያ ታደርጋለች:: እኒህ ቅዱሳን መላእክት በነገድ 10 ሲሆኑ መጠሪያቸው "ሱራፌል" : መኖሪያቸውም በኢዮር ነው:: ነገር ግን ሃያ አራቱ አለቆቻቸው ተመርጠው በመሪያቸው በቅዱስ ሱራፊ አለቅነት በጽርሐ አርያም ያገለግላሉ::
በቀናች ሃይማኖት ትምሕርት ሁሉም ቅዱሳን መላእክት ለእግዚአብሔር ቅርብ ቢሆኑም: በነጠላ የቅዱስ ሚካኤልን ያህል: በነገድ ደግሞ የኪሩቤል (አራቱ እንስሳ) እና የሱራፌልን (ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ) ያህል ቅርብ የለም::
††† ሃያ አራቱ ቅዱሳን ካህናት ሥራቸው:-
1.እንደ ሞገድ ከአንደበታቸው ምስጋና እየወጣ: ጧት ማታ ፈጣሪያቸውን ይቀድሱታል:: (ኢሳ. 6:1, ራዕይ 4:11, 5:11)
2.የሥላሴን መንበር ያለ ማቋረጥ ያጥናሉ:: (ራዕይ 5:8)
3.የሰው ልጆችን: በተለይም የቅዱሳንን ጸሎት በማዕጠንታቸው ያሳርጋሉ:: (ራዕይ 8:3)
4.የረከሱትን ይቀድሳሉ:: (ኢሳ. 6:6)
5.ዘወትርም ለሰው ልጆች ምሕረትን ሲለምኑ ይኖራሉ:: (ዘካ. 1:12)
ስለ እነዚህ ቅዱሳን ካህናት (ሱራፌል) ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ብዙ ይላል:: ለምሳሌ:- ዐቢይ ነቢይ ወልዑለ ቃል ኢሳይያስ ፈጣሪው ተቀይሞት በነበረበትና ዖዝያን በሞተበት ወራት: ግሩማን ሆነው ሥላሴን "ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ" እያሉ ዙሪያውን ከበው ሲያመሰግኑ ሰምቷል::
ከእነርሱም አንዱ (ሱራፊ) መጥቶ በጉጠት እሳት ከንፈሩን ዳስሶ ከለምጹ አንጽቶታል:: (ኢሳ. 6:1) አቡቀለምሲስ የተባለ ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ በግርማ: በአምሳለ አረጋዊ ተመልክቷቸዋል:: (ራዕይ 4:4)
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን የመሰሉ ቅዱሳን ሊቃውንት ደግሞ በጣዕመ ምስጋናቸው ሲገልጿቸው:-
"ካህናተ ሰማይ ቅውማን በዐውዱ::
አክሊላቲሆሙ ያወርዱ::
ቅድመ መንበሩ እንዘ ይሰግዱ::
ይርዕዱ::
ከመ ኢይዝብጦሙ ሶበ ይበርቅ ነዱ::" ብለዋል:: (መጽሐፈ ሰዓታት)
ትርጉሙም "በፈጣሪ መንበር ዙሪያ የሚቆሙ የሰማይ ካህናት አክሊለ ክብራቸውን አውርደው በመንበሩ ፊት ይሰግዳሉ:: መብረቀ መለኮቱ በተገለጠ ጊዜም በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ::" ነው:: ግሩም ባሕርየ ሥላሴን ሊቋቋመው የሚችል ፍጡር የለምና::
ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ በምስጋናቸው: በማዕጠንታቸውና በምልጃቸው ክቡራን ናቸውና ዘወትር ልናከብራቸው ይገባናል:: የረከሰ ማንነታችንን ይቀድሱ ዘንድ: በምልጃቸውም ዘንድ እንድንታሰብ: ጸሎታችንንም ያሳርጉልን ዘንድ እንለምናቸው::
††† ኅዳር 24 ቀን ዓመታዊ በዓላቸው ነው ማለት በየወሩ በ24 ወርኀዊ በዓላቸው መሆኑን ያሳያልና ዘወትር ልናስባቸው ይገባል::
በተለይ ያዘነን ልብ ደስ ያሰኛሉና እንደ ሊቃውንት እንዲህ ብለን እንጠራቸዋለን::
"ሰላም ለክሙ ካህናተ ሕጉ ወትዕዛዙ::
ለእግዚአብሔር ቃል ዘጶዴሬ ሥጋ አራዙ::
እምነቅዐ አፉክሙ ሐሴት ዘኢይነጽፍ ዉሒዙ::
ኪያየ ኅዙነ ወትኩዘ ልብ ናዝዙ::
ወበክንፍክሙ ብርሃናዊ ዐውድየ ሐውዙ::" (አርኬ ዘኅዳር 24)
††† ቅዱስ አዝቂር ካህን †††
††† ከዜና ካህናት ወደ ዜና ካህናት እንለፍ:: ቅዱስ አዝቂርን የመሰሉ ካህናት ምንም ሥጋ ለባሽ ቢሆኑም ሥልጣናቸውና ግብራቸው ሰማያዊ ነውና መላእክትን ይመስላሉ:: አንድም በስልጣናቸው ከመላእክት ይበልጣሉ::
"ካህናትየ ይቤሎሙ::
ወእምኩሉ ፈድፋደ አክበሮሙ::
ዘኢተገብረ ለመላእክት ተገብረ ለካህናት::"
ትርጉም "አገልጋዮቼ አላቸው::
ከሁሉ በላይ አከበራቸው::
ለመላእክት ያልተደረገ ለካህናት ተደረገ::" እንዳለ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ:: (መጽሐፈ ቅዳሴ)
ቅዱስ አዝቂርም የናግራን (አሁን የመን) ክርስቲያን ሲሆን በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በንጹሕ የክህነት አገልግሎቱ ሰውንም: ክርስቶስንም ደስ ያሰኘ አባት ነው:: አሕዛብን: አረማውያንን ሁሉ ድል ነስቶ መንጋውን ጠብቋል:: በቁጥርም አብዝቷል::
ገርፈው ቢያስሩት በቃሉ ስልጣን የብረት በሮችን ከፍቶ አሕዛብን ሲያጠምቅ ተገኝቷል:: ሊገድሉት ሲወስዱት በየመንገዱ ይሰብክ ነበር:: ገዳዮቹ በርሃ ላይ ውኃ ጥም እንዳይገድላቸውም በአንዲት ገበታ ላይ ዝናም አዝንሞ 700 ወታደሮች ከነ ፈረሶቻቸው አጥግቧል::
በመጨረሻም አይሁድ በድንጋይ ሲወግሩት ድንጋዮቹ እየተመለሱ አናት አናታቸውን ብሏቸዋል:: ያን ጊዜ በብስጭት አንገቱን ቆርጠውታል:: አብረውም ቅዱስ ኪርያቅ ወዳጁንና 48 ተከታዮቹን ሰይፈዋል::
††† አምላከ ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ ከምስጋናቸው ሐሴትን: ከማዕጠንታቸው በጐ መዓዛን ያውርድልን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::
†
[ 🕊 ፍኖተ ቅዱሳን 🕊 ]
[ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ሁል ጊዜ በትጋትና በጥንቃቄ መሆን እንደሚገባ ! ]
🕊
❝ አይ አይደለም ፣ ዛሬ ንስሐ እገባለሁ ! ❞
........
- አንድ አረጋዊ እንዲህ አለ ፦ " ወደ ንጉሥ የቀረበን ሰው ጠላቱ ሊያገኘውና ሊጎዳው እንደማይችለው ሁሉ ወደ እግዚአብሔር የቀረበን ሰውም ዲያብሎስ ምንም ሊያደርገው አይችልም። ነገር ግን ብዙ ጊዜ ራሳችንን ከፍ ስለምናደርግና ድካማችንን ስለማናውቅ ጠላት እኛን ወደ ታች ለመጣልና ወደ አሳፋሪ ነውሮችም ለማውረድ አይቸገርም።
- አንድ አባት ክፉ ሃሳቦች በኅሊናው ፦ " ዛሬ ተዝናና ፣ ደስም ይበልህ ፣ ነገ ንስሐ ትገባለህ" ሲሉት እርሱ ግን መልሶ ፦ " አይ አይደለም ፣ ዛሬ ንስሐ እገባለሁ ፣ ነገ ደግሞ የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን" አለ።
የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
✅OLD 👨👨👧👧👨👨👧👧 ላላችሁ መልካም ዜና የምገዛበት ዋጋ ላይ ጭማሪ አርግያለው ❗️❗️❗️
የዋጋ ጭማሪ 🆕🆕🆕
✅በ2022 - 650ብር
✅በ2021 - 650ብር
☑️በ2020 - 650ብር
✅በ2019 - 650ብር
✅በ2018 - 700ብር
✈️✈️በእነዚህ ዓ.ም ውስጥ የተከፈተ ማንኛውም group ካላችሁ አናግሩኝ 🆕🆕🆕
እኔ የምፈልገው የተከፈተበት ቀን እንጂ የግሩፑን አባል ብዛት አይደለም ‼️❕
➡️ቅድሚያ ክፍያ ምናምን የምትሉ ሰዎች እንዳትመጡ ምክንያቱም ልፋት ብቻ ነው የሚሆንባችሁ ❌❌❌
✉️✉️✉️✉️ግሩፕ ካላችሁ
በውስጥ መስመር
☑ 100% trusted
የሌሊት ወፍ
"የሌት ወፍ እንደ ዓይጥ ጥርስ አላት፤ እንደ ወፍም ከንፍ አላት፡፡ አንድ ጊዜ የሰማይ ወፎችና የዱር አራዊቶች ተጣልተው አራት ቀን ሙሉ ጦርነት አደረጉ፡፡
የሌት ወፍ ግን በዳር ሁና ትመለከትና የዱር አራዊቶች ሲበረቱ ያየች እንደ ሆነ ወደነዚያ ትሔድና እኔ እኮቁጥሬ ወደናንተ ነው እዩት ጥርሴን! እዩት ጡቴን እስቲ ከሰማይ ወፎች እንደኔ ጥርስና ጡት ያለው ማነው ትላቸዋለች፡፡
ደግሞ የሰማይ ወፎች ሲበረቱ ያየች እንደ ሆነ ወደነዚያ
ትሔድና እኔ እኮ ቁጥሬ ወደናንተ ነው! እዩት ክንፌን እስቲ ከዱር አራዊት ወገን እንደኔ በከንፍ እየበረረ በአየር ላይ የሚሔድ ማነው ትላቸዋለች፡፡
ወደ ጦርነቱ ግን ምንም ቢሆን አትገባም፡፡
ከጥቂት ቀን በኋላ ዕርቅ ተደረገና ጦርነቱ ቆመ፡፡ ስለዚሁም የሰማይ ወፎችና አራዊቶች ትልቅ በዓል አደረጉ፡፡
የሌት ወፍም ወደ ወፎች ድግስ ብትሔድ እኛ እንደ አውሬ ጥርስ የለን ወደኛ ለምን መጣሽ ብለው አባረርዋት፡፡ ወደ ዱር አራዊትም ብትሔድ እኛ እንደወፍ ክንፍ የለን ወደኛ ለምን መጣሽ ብለው አባረርዋት፡፡
ከዚህ በኋላ አፈረችና ወፎችም አራዊትም እንዳያይዋት ቀን ቀን እየተደበቀኝ እየዋለች፤ ማታ ማታ ምግብዋን ለመፈለግ ጀመረች። ቀን ወፎችም ቢያገኝዋት! አራዊትም ቢያገኝዋት አይተዋትም ይገድልዋታል እንጂ
የሌት ወፍ የተባለችውም ከዚያ ወዲህ ነው ይባላል፡፡" (ብላቴን ጌታ ኅሩይ)
አንዳንዶች እንዲህ ናቸው፤ያጠቃ ያሸነፈ ከመሰላቸው ጋር ቦርጫቸውን ያስተካክላሉ፤ላጠቃው መወድስ ለተጠቃው ተረት አያጡም። ጥርሳቸውንና ክንፋቸውን እያቀያየሩ እያሳዩ "እኔ ያንተ አሽከር ያንተ ቡችላ" ይላሉ።
እንደ ንሥርም እንደ አንበሳም ኮራ ብሎ መብረር ወይም መንጎማለል የሚቻለው ወይ ወፍነትን ወይ አውሬነትን መምረጥ ሲቻል ነው!
ጦርነትም ሆነ ጠብ በእርቅ አልያም በመሸናነፍ ይጠናቀቃል። ያኔ እንደ ሌት ወፍ ሌት መጓዝ ይመጣል።
ያድኅነነ እመዓቱ ይሰውረነ
#መርቆሬዎስ ፳፭
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖
🎨" የድርጅቶን ዋጋ በኒየን አንድ ደረጃ ከፍ ያድርጉ"
👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
@GraceWallArt
(0943448637)
@hani_nata
(0936239392)
🛵 ያሉበት ድረስ በነፆ
👌 ምርጫዎ ስለሆንን እናመሠግናለን
በሰ/ወሎ ዞን በመቄት ወረዳ የምትገኘው ገዳመ ሲሀት ቅ/ፍቅርተ ክርስቶስ አንድነት ገዳም
_ይቺ ገዳም ለታመሙና ለተጨነቁ መፍትሄ በመሆን የምትታወቅ ገዳም ስትሆን ዛሬ ላይ ግን ከኛ ከልጆቿ መፍትሄ የምትሻበት ደረጃ ላይ ደርሳለች።ይቺ ገዳም ከገደል ዳር ላይ የተሰራች በመሆኗና ይህ ገደልም በጎርፍና መሰል አደጋ እነተሸረሸረ ከቤተ-ክርስቲያኑ እስከ ገደሉ ያለው እርቀት ከ1ሜትር ያልበለጠ ሁኗል።ስለሆነም ይቺን ከ400ዓመት በላይ የቆየችውን ይህቺን ድንቅ ገዳም ከተጋረጠባት ከባድ አደጋ እንታደጋት።
ስለዚህ እሁድ 29/03/2017 ዓ/ም በአዲስ አበባ ሜኪሲኮ ማህደረ ስብሐት ቅ/ልደታ ለማርያምና ደ/መድሀኒዓለም ቤ/ክ አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣መምህራን፣ዘማርያን እና ታዋቂ እንግዶች በተገኙበት በሚዘጋጀው ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ላይ በመገኘት የድርሻችሁን እንድታደርጉልን በፃድቋ ስም እንለምናለን።
በባንክ መደገፍ ለምትፈልጉ
የኢ/ን/ባ
1000076665285
አቢሲንያ
8089205
ስለምታደርጉት ሁሉ ፃድቋ በበረከት ትጎብኛቹሁ።
🙏🙏🙏🙏
✝✞✝ እንኩዋን አደረሳችሁ ✝✞✝
"" ቅዱስ አባታችን #ተክለ_ሃይማኖት ከ24ቱ #ካህናተ_ሰማይ ጋር መንበረ ጸባኦትን ያጠኑበት ቀን ኅዳር 24 ይታሰባል:: ""
ስለዚህም አበው "ተክለ ሃይማኖት #ሱራፊ እለ ስድስቱ ክነፊሁ (6 ክንፍ ያለው አባታችን መልአኩ ሱራፊን ሆነ)" ሲሉ ያመሰግኗቸዋል::
" የቅዱሱ አባታችንና የቅድስት ገዳሙ (#ደብረ #ሊባኖስ) በረከት ይደርብን:: "
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖
✝አቡነ ዜና ማርቆስ✝
ባርከኒ አባ እንሣእ በረከተከ በእንተ ሰላማ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዜናማርቆስ አባ ባርከኒ እንሣእ በረከተከ።
✝የጻድቁ ልደታቸው ኅዳር 24 ነው።
✝ከበዓለ ልደታቸው በረከት ያድለን።
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖
🎨" የድርጅቶን ዋጋ በኒየን አንድ ደረጃ ከፍ ያድርጉ"
👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
@GraceWallArt
(0943448637)
@hani_nata
(0936239392)
🛵 ያሉበት ድረስ በነፆ
👌 ምርጫዎ ስለሆንን እናመሠግናለን