ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ። ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ›› ት.ኢሳ 58÷3 https://youtu.be/csxxAMGtC4I ለመቀላቀል http://t.me/ortodoxtewahedo
አይቶ መለፍ እጅግ በጠም ይከብደል፡፡
እባካቹ እናንተ ደጋጎች ሼር ሼር አድርጉላቸው
ወዳጆቼ በዚ ከበድ ወቅት የበረከት ስራ እንስራ መርዳት ቢያቅተን ሼር ማድረግ እራሱ ትልቅ እርዳታ ነው:: ይህ የምትመለከቱወት ህፃን የሁለት አመት ከሶስት ወር ህፃን ነት የካንሰር ታማሚ ነት ካንሰር በሽታ የያዘውት ከተወለደች ከሶስ ወር ጀመሮ የካንሰር ታማሚ ነት ይሄው እሷም እናቱወም አባቱወም ሁለት አመት ሙሉ አሚን አጠቀለይ ሆስፒተል ንብረታቸውን ሸጠው እሷን በማስታመም ላይ ይገኛሉ ህፃኑወን ካንሰሩ አይንወን አሳውሮታል አንደኛው አይንወ በቀዶ ጥገና ወጥቶለት አንደኛውንም አይኑወ ከሰሞኑ እንደሚወጣ ከዶክቶሮቹ ሰምቻለው በዚያ ላይ አንድ አፍንጫወን ደፍኖታል እናትና አባትወ ለሁለት አመት ከልጃቸው ጋ ስቃይ ውስጥ ይገኛሉ አሁን ላይ ከስቃዩም በላይ የህክምና እና የመድሀኒቱ ወጪ ሌላ ስቃይ ነው የሆነባቸው ለመድሀኒቱና ህክምና ለአስራ አምስት ቀን ሰባ ሺ ብር ይፈልጋሉ አሁን ላይ ውጪ ሄደ የመታከም እድልም አለት ለህክምናወ ወጪ ከአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር በላይ ይፈልጋልጋሉ እና ልጅቷም በስቃይ ውስጥ እናትና አባትም በስቃይና ጭንቀት ውስጥ ናቸው እንድረስላቸው ለወገን ደራሽ ወገን ነው የቻልነውን አነሰም በዛ ሳንል እጃችንን እንዘርጋላቸው ስል በፈጠሪ ስም እንማፀናለን መርዳት ለምትፈልጉ
ንግድ ባንክ 1000603332346 እስማኢል ሀሠን አብደላ (Ismail Hassen)
ስልክ ቁጥር 0960067157
የማትችሉ በፀሎትና ሼር ሼር ሼር በማድረግ እንርዳቸው
ሼር ሼር ሼር በማድረግ አይከፈልበትም
☞ ሁለችንም 5 ብር ብንረደት ልነሰክመት እንችለለን፡፡
☞ ሁለቹም ለፈጠሪ ብለቹ ሲትረዱ የረደቹበትን መረጀ በዚ profile አስቀምጡልን፡፡
“ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሃብተ ማርያም "
እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም ወርሃዊ ክብረ በዓል በሰላም በጤና አደረሰን አደሰችሁ ።
ጽሩይ እምወርቅ ወእምብሩር ንጡፍ ወኅሩይ እምአእላፍ ሀብተ ማርያም መልአክ ዘውገ ኪሩብ ቀሊለ ክንፍ አማን ስሙዐ ዜና እስከ አጽናፍ ፡፡
ሰላም ለፅንሰትከ እማህፀነ ቅድስት ዮስቴና በብሥራተ ጻድቅ ባሕታዊ ሠናየ ዜና ሐብተ ማርያም ጴጥሮስ ሐዋርያ ወልደ ዮና መሐረኒ ምግባረ ጽድቅ ወጸግወኒ ልቦና አፍቅሮ ቢጽ እኃሥሥ ዘምስለ ፍጽምት ትሕትና::
(መልክአ አቡነ ሀብተ ማርያም)
" እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና ::
ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና ::
ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . . ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ :: የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል ::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል ::
የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው :: በእርምጃውም አይሰናከልም:: "
(መዝ 36፥28-31 )
ቅዱስ አባታችን ፅንሰታቸው ነሐሴ 26
ልደታቸው ግንቦት 26
ዕረፍታቸው ኅዳር 26 ነው ፡፡
ኦ አምላከ አቡነ ሀብተ ማርያም ዕቀቦ ወአድኅኖ ወባልሆ እመከራ ሥጋ ወነፍስ ወእምኩሉ ተቃራኒ ወእምኩልነ ክቡር ሀብተ ማርያም ለዓለም ዓለም አሜን ለይኩን ለይኩን ::
ወስብሐት ለእግዚአብሔር !
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖
150cmx80cm
Price 3500 birr
With free delivery 🚚
የገጠማ አይጨምርም ❗️‼️
👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
@GraceWallArt
(0943448637)
@hani_nata
(0936239392)
🕊 † የናግራን ሰማዕታት † 🕊
በ፮ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ናግራን [የአሁኗ የመን] የክርስቲያኖች ሃገር ነበረች:: የሳባ ግዛትን የእኛ ነገሥታት ሲተዋት የተተካው ፊንሐስ ደግሞ ጨካኝ አይሁዳዊ ነበርና ናግራንን ሊያጠፋት ተመኘ:: ቀጥሎም "ሃገራችሁን ልጐብኝ" ብሎ በማታለል ገባ::
ወዲያውም ሕዝቡንና ካህናትን ሰብስቦ "ክርስቶስን ካዱ" አላቸው:: ጽኑ ክርስቲያኖች ግን "አይደረግም" አሉት:: እርሱም ሊያስፈራራቸው አስቦ ፬ ሺህ ያህል ካህናት: ዲያቆናትና ምሑራንን ጨፈጨፋቸው::
ይሕንን አድርጐ "አሁንሳ?" አላቸው:: ሕዝቡ ግን አሁንም "ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን የለም" አሉት:: [ሮሜ.፰፥፭] ጨካኙ ፊንሐስም እንደ ገና ከሕዝቡ መካከል ከ፬ ሺህ ፩ መቶ በላይ የሚሆኑትን ጨፈጨፈ::
ታላቁን ቅዱስ ሒሩትንም [የሕዝቡ መሪ ነው] ብዙ አሰቃይቶ ሰየፈው:: ሚስቱን ቅድስት ድማሕንም ፪ ሴት ልጆቿን ሰይፈው የልጆቿን ደም አጠጧት:: ከዚያም ሰየፏት:: ይሕንን የተመለከቱ የናግራን ክርስቲያኖች ግን ስለ መፍራት ፈንታ በፈቃዳቸው እየተሯሯጡ ወደ እሳትና ሰይፍ ተሽቀዳደሙ::
ከተማዋም እየነደደችና ደም እየፈሰሰባት ለ፵ ቀናት ቆየች:: ይሕንን የሰማው ቅዱሱ አፄ ካሌብም ደርሶ የተረፉትን ሲታደግ ፊንሐስን ከነ ወታደሮቹ አጥፍቶታል::
አምላከ አበው ወሰማዕት ጣዕመ ፍቅራቸውን: ክብራቸውን: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን::
🕊
[ † ኅዳር ፳፮ [ 26 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
፪. አቡነ ሃብተ ማርያም ንጹሕ
፫. ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
፬. ቅዱስ ሒሩት አረጋዊ
፭. ቅዱሳን ቢላርያኖስ: ኪልቅያና ታቱስብያ [ሰማዕታት]
፮. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘደሴተ ሰንሲላ
፯. ቅድስት ዮስቴና ቡርክት
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
፪. ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
" እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና:: ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና:: ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . . ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ:: የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል:: የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም::" [መዝ.፴፮፥፳፰-፴፩]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
Hello Alan, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…🎨" የድርጅቶን ዋጋ በኒየን አንድ ደረጃ ከፍ ያድርጉ"
👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
@GraceWallArt
(0943448637)
@hani_nata
(0936239392)
🛵 ያሉበት ድረስ በነፆ
👌 ምርጫዎ ስለሆንን እናመሠግናለን
†
[ 🕊 ፍኖተ ቅዱሳን 🕊 ]
[ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ሁል ጊዜ በትጋትና በጥንቃቄ መሆን እንደሚገባ ! ]
🕊
❝ አይ አይደለም ፣ ዛሬ ንስሐ እገባለሁ ! ❞
........
- አንድ አረጋዊ እንዲህ አለ ፦ " ወደ ንጉሥ የቀረበን ሰው ጠላቱ ሊያገኘውና ሊጎዳው እንደማይችለው ሁሉ ወደ እግዚአብሔር የቀረበን ሰውም ዲያብሎስ ምንም ሊያደርገው አይችልም። ነገር ግን ብዙ ጊዜ ራሳችንን ከፍ ስለምናደርግና ድካማችንን ስለማናውቅ ጠላት እኛን ወደ ታች ለመጣልና ወደ አሳፋሪ ነውሮችም ለማውረድ አይቸገርም።
- አንድ አባት ክፉ ሃሳቦች በኅሊናው ፦ " ዛሬ ተዝናና ፣ ደስም ይበልህ ፣ ነገ ንስሐ ትገባለህ" ሲሉት እርሱ ግን መልሶ ፦ " አይ አይደለም ፣ ዛሬ ንስሐ እገባለሁ ፣ ነገ ደግሞ የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን" አለ።
የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
Hello Entsar, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…✅OLD 👨👨👧👧👨👨👧👧 ላላችሁ መልካም ዜና የምገዛበት ዋጋ ላይ ጭማሪ አርግያለው ❗️❗️❗️
የዋጋ ጭማሪ 🆕🆕🆕
✅በ2022 - 650ብር
✅በ2021 - 650ብር
☑️በ2020 - 650ብር
✅በ2019 - 650ብር
✅በ2018 - 700ብር
✈️✈️በእነዚህ ዓ.ም ውስጥ የተከፈተ ማንኛውም group ካላችሁ አናግሩኝ 🆕🆕🆕
እኔ የምፈልገው የተከፈተበት ቀን እንጂ የግሩፑን አባል ብዛት አይደለም ‼️❕
➡️ቅድሚያ ክፍያ ምናምን የምትሉ ሰዎች እንዳትመጡ ምክንያቱም ልፋት ብቻ ነው የሚሆንባችሁ ❌❌❌
✉️✉️✉️✉️ግሩፕ ካላችሁ
በውስጥ መስመር
☑ 100% trusted
አዳም ❤ለሄዋን
@ortopiyaaa
@ortopiyaaa
@ortopiyaaa
የሌሊት ወፍ
"የሌት ወፍ እንደ ዓይጥ ጥርስ አላት፤ እንደ ወፍም ከንፍ አላት፡፡ አንድ ጊዜ የሰማይ ወፎችና የዱር አራዊቶች ተጣልተው አራት ቀን ሙሉ ጦርነት አደረጉ፡፡
የሌት ወፍ ግን በዳር ሁና ትመለከትና የዱር አራዊቶች ሲበረቱ ያየች እንደ ሆነ ወደነዚያ ትሔድና እኔ እኮቁጥሬ ወደናንተ ነው እዩት ጥርሴን! እዩት ጡቴን እስቲ ከሰማይ ወፎች እንደኔ ጥርስና ጡት ያለው ማነው ትላቸዋለች፡፡
ደግሞ የሰማይ ወፎች ሲበረቱ ያየች እንደ ሆነ ወደነዚያ
ትሔድና እኔ እኮ ቁጥሬ ወደናንተ ነው! እዩት ክንፌን እስቲ ከዱር አራዊት ወገን እንደኔ በከንፍ እየበረረ በአየር ላይ የሚሔድ ማነው ትላቸዋለች፡፡
ወደ ጦርነቱ ግን ምንም ቢሆን አትገባም፡፡
ከጥቂት ቀን በኋላ ዕርቅ ተደረገና ጦርነቱ ቆመ፡፡ ስለዚሁም የሰማይ ወፎችና አራዊቶች ትልቅ በዓል አደረጉ፡፡
የሌት ወፍም ወደ ወፎች ድግስ ብትሔድ እኛ እንደ አውሬ ጥርስ የለን ወደኛ ለምን መጣሽ ብለው አባረርዋት፡፡ ወደ ዱር አራዊትም ብትሔድ እኛ እንደወፍ ክንፍ የለን ወደኛ ለምን መጣሽ ብለው አባረርዋት፡፡
ከዚህ በኋላ አፈረችና ወፎችም አራዊትም እንዳያይዋት ቀን ቀን እየተደበቀኝ እየዋለች፤ ማታ ማታ ምግብዋን ለመፈለግ ጀመረች። ቀን ወፎችም ቢያገኝዋት! አራዊትም ቢያገኝዋት አይተዋትም ይገድልዋታል እንጂ
የሌት ወፍ የተባለችውም ከዚያ ወዲህ ነው ይባላል፡፡" (ብላቴን ጌታ ኅሩይ)
አንዳንዶች እንዲህ ናቸው፤ያጠቃ ያሸነፈ ከመሰላቸው ጋር ቦርጫቸውን ያስተካክላሉ፤ላጠቃው መወድስ ለተጠቃው ተረት አያጡም። ጥርሳቸውንና ክንፋቸውን እያቀያየሩ እያሳዩ "እኔ ያንተ አሽከር ያንተ ቡችላ" ይላሉ።
እንደ ንሥርም እንደ አንበሳም ኮራ ብሎ መብረር ወይም መንጎማለል የሚቻለው ወይ ወፍነትን ወይ አውሬነትን መምረጥ ሲቻል ነው!
ጦርነትም ሆነ ጠብ በእርቅ አልያም በመሸናነፍ ይጠናቀቃል። ያኔ እንደ ሌት ወፍ ሌት መጓዝ ይመጣል።
ያድኅነነ እመዓቱ ይሰውረነ
#መርቆሬዎስ ፳፭
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖
Hello Heni, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ ህዳር 25 እና ሐምሌ 25 አመታዊ ክብረ በአሉ ነው
Читать полностью…🎨" የድርጅቶን ዋጋ በኒየን አንድ ደረጃ ከፍ ያድርጉ"
👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
@GraceWallArt
(0943448637)
@hani_nata
(0936239392)
🛵 ያሉበት ድረስ በነፆ
👌 ምርጫዎ ስለሆንን እናመሠግናለን
150cmx80cm
Price 3500 birr
With free delivery 🚚
የገጠማ አይጨምርም ❗️‼️
👉 በይበልጥ ለመረዳት👇
@GraceWallArt
(0943448637)
@hani_nata
(0936239392)
Hello 12, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…✝️ ፃድቁ ሀብተማርያም ✝️
ዝማሬ:- ዘማሪ ምትኩ ስዩም
▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾
▸ @hayle_Tube_Official ◂
▸▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴
#ሀብተማርያም #ፃድቁ_ሀብተማርያም #ሀይሌ_ቲዩብ #Haile_Tube
🕊
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞
† ኅዳር ፳፮ [ 26 ] †
🕊 † አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ † 🕊
እግዚአብሔር በ፲፫ኛው መቶ ክ/ዘ እነ አቡነ ኢየሱስ ሞዐን ባያስነሳ ኑሮ ምናልባትም ዛሬ የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያንን በምናያት መንገድ ላናገኛት እንችል ነበር:: እውነተኛ አባቶቻችን ፈጽሞ ከሚቆረቁራቸው ነገር አንዱ የጻድቅና ሐዋርያዊ አባት አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መዘንጋት ነው::
እርሳቸው ፍሬ ሃይማኖት ሆነው ከጽድቅ ፍሬአቸው አዕላፍ ቅዱሳንን ወልደው ሃገራችን በወንጌል ትምሕርትና በገዳማዊ ሕይወት እንድታሸበርቅ አድርገዋል:: እስኪ በዕለተ ዕረፍታቸው ስለ ጻድቁ ጥቂት ነገሮችን እናንሳ::
አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ የተወለዱት ጐንደር: የድሮው ስማዳ [ዳኅና] አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ዘክርስቶስና እግዚእ ክብራ ይባላሉ:: የተወለዱት በ1210 ዓ/ም ነው:: ነገር ግን አንዳንድ ምንጮች በ1196 ዓ/ም ያደርጉታል::
ጻድቁ ከክርስቲያን ወላጆቻቸው ጋር እንደሚገባ አድገዋል:: በልጅነታቸው በብዛት ወላጆቻቸውን ያግዙ ነበር:: በትርፍ ጊዜአቸው ደግሞ ትምሕርተ ሃይማኖትንና ሥርዓቱን ያጠኑ ነበር:: በ1240 ዓ/ም ግን [ማለትም ፴ ዓመት ሲሞላቸው] ይሕቺን ዓለም ይተዋት ዘንድ አሰቡ::
አስበውም አልቀሩ ፈጣሪን እየለመኑ ደብረ ዳሕሞ ገቡ:: በወቅቱ ዳሞ የትምሕርት: የምናኔ ማዕከል ከመሆኑ ባሻገር የአቡነ አረጋዊ ፭ኛ የቆብ ልጅ ካልዕ ዮሐኒ ነበሩና የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ሆኑ::
አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በደብረ ዳሞ በነበራቸው ቆይታ ቀን ቀን ሲታዘዙ: ሲፈጩ: ውሃ ሲቀዱ ውለው ሌሊት እኩሉን በጸሎት በስግደትና የቀረውን ሰዓት ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመገልበጥ አሳለፉ::
በመጨረሻም ልብሰ ምንኩስናን ለበሱ:: ይህን ጊዜ ፴፯ ዓመታቸው ሲሆን ዘመኑም 1247 ዓ/ም ነው:: ወዲያውም በዳሞ ሳሉ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ "ወደ ወሎ ሐይቅ ሒድ: ብዙ የምትሠራው አለና" አላቸው::
በአንዴም ከዳሞ [ትግራይ] ነጥቆ ሐይቅ እስጢፋኖስ [ወሎ] አደረሳቸው:: በዚያም ለ፯ ዓመታት በዼጥሮስ ወዻውሎስ ቤተ መቅደስ በተጋድሎ: በስብከተ ወንጌል: በማዕጠንትና ሐይቁ ውስጥ ሰጥሞ በመጸለይ ኖሩ::
ቅድስናቸውን የተመለከቱ አበውም በግድ አበ ምኔት አድርገው ሾሟቸው:: ይህ ነው እንግዲህ በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ትልቁ መሠረት የተጣለበት አጋጣሚ:: ነገሩ እንዲህ ነው :-
ስም አጠራሯ የከፋ ዮዲት ጉዲት ለ፵ ዓመታት ሃገሪቱን እንዳልነበረች ብታደርጋት ክርስትና ተዳከመ:: ባዕድ አምልኮም ነገሠ:: አቡነ ኢየሱስ ሞዐ [ትርጉሙ ኢየሱስ ክርስቶስ አሸነፈ ማለት ነው] ደግሞ ሃይማኖታቸው የቀና ከ፰ መቶ በላይ ክርስቲያኖችን ሰበሰቡ::
በሃገሪቱ ትልቅና የመጀመሪያው ሊባል የሚችል ቤተ መጻሕፍት አደራጁ:: እነዚያን አርድእት በቅድስናና በትምሕርት አብስለው አመነኮሱና "ሒዱ! ሃገሪቱን ታበሩ ዘንድ ተጋደሉ" ብለው አሰናበቷቸው::
ክእነዚህ መካከልም ታላላቁን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን: አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እና የሁዋላውን ፍሬ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን መጥቀስ እንችላለን:: በዚህም ምክንያት ጻድቁ "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን - አእላፍ ቅዱሳንን የወለደ" ሲባሉ ይኖራሉ::
ጻድቁ ከዚህ በተጨማሪ የወቅቱን ንጉሥ አፄ ይኩኖ አምላክን በማስተማር ለሃገርና ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ሰው አድርገዋል:: በግላቸው ሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ የብርሃን ምሰሶ ይወርድላቸው ነበር:: ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምንም ከጠፋ ከ፫ መቶ ዓመታት በሁዋላ አቅንተዋል::
እንዲህ ለቤተ ክርስቲያን ሲተጉ: በተለይ በአበ ምኔትነት በቆዩባቸው ፵፭ ዓመታት ለዓይናቸው እንቅልፍን አላስመኙትም:: ጐድናቸውም ከምኝታ ጋር ተገናኝቶ አያውቅም::
"እንዘ የኀሊ ዘበሰማያት ዐስቦ::
መጠነ ዓመታት ሃምሳ ኢሰከበ በገቦ::" እንዲል::
ከዚህ በሁዋላ የሚያርፉበት ዕለት ቢደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: በተወለዱ በ፹፪ [82] ዓመታቸው [በ፹፮ [86] ዓመታቸው የሚልም አለ] በ1282 ዓ/ም በዕለተ ሰንበት ዐርፈው ተቀብረዋል:: "ጻድቁ ስም አጠራራቸው እጅግ የከበረ ነው!!"
🕊 † አቡነ ሃብተ ማርያም ጻድቅ † 🕊
እኒህ ጻድቅ ደግሞ የሃገራችን ኮከበ ገዳም ናቸው:: "ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሃብተ ማርያም" እንዲሉ አበው:: ባሕር ከሆነ ጣዕመ ሕይወታቸው ጥቂቱን ለበረከት እንካፈል::
ጻድቁ መካነ ሙላዳቸው ሽዋ [የራውዕይ] ውስጥ ሲሆን አባታቸው ፍሬ ቡሩክ: እናታቸው ደግሞ ቅድስት ዮስቴና ትባላለች:: በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ: ምጽዋትን ወዳጅ: ቡርክት ሴት ነበረች:: እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር::
ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት "ከማሕጸንሽ ደግ የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ" ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች:: ጻድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ ፯ አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች::
ወደ ጻድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ አቡነ ሃብተ ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ:: ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን?" እያሉ ይሰግዱ ነበር::
የ፭ ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል:: ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ:: ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል:: የፈጣሪውን ስም ያቃለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል::
ከዚያ ግን ለአካለ መጠን ሲደርሱ ወደ ት/ቤት ገብተው: መጻሕፍትንም አጥንተው መንነዋል:: በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ ከመነኮሱ በሁዋላ የሠሩትን ትሩፋትና የነበራቸውን ተጋድሎ ግን የኔ ብጤ ደካማ ሰው ሊዘረዝረው አይችልም::
- ባሕር ውስጥ ሰጥመው ፭ መቶ ጊዜ ይሰግዳሉ::
- በየቀኑ ፬ቱን ወንጌልና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ:: [መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ታላቅ ጸሎት ነው]
- በ፵ ቀናት: ቀጥሎም በ፹ ቀን አንዴ ብቻ ይመገባሉ::
- ምግባቸው ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው::
- በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋሉ:: [ካህን ናቸውና]
- ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላሉ: ክቡር ደሙን ይጠጣሉ::
- በፍጹም በልባቸው ውስጥ ቂምን: መከፋትን አላሳደሩም::
በእነዚህና በሌሎች ትሩፋቶቻቸው ደስ የተሰኘ ጌታም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቷቸው በዚያ እየበረሩ ኢየሩሳሌም ይሔዱ ነበር:: ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በሁዋላም የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አዕላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ አላቸው::
"ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ : ስለ ምናኔሕ : ስለ ተባረከ ምንኩስናህ : ስለ ንጹሕ ድንግልናህ : ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ : ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ : ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ ፯ አክሊላትን እሰጥሃለሁ::"
"በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን: ፭ መቶ የእንቁ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ:: በስምህ የሚለምኑ: በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ! በርእስየ!' ብዬሃለሁ" አላቸው::
ቅዱሳን መላእክትም "ሃብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው:: ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው:: ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች:: በዝማሬም ወሰዷት::"
የመዳን ትምህርት
(ነገረ ድኅነት) ክፍል ~ 1
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ነገረ ድኅነት ትምህርት እንዲህ ይላል ...
♦️ "የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቷልና »፡፡ ሉቃ. 19፡10
♦️" . . . ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤ እርሱም የሰጠን ተስፋ ይህ የዘላለም ሕይወት ነው።" 1 ዮሐ. 1፡1-2 ፤ 2፡25
♦️"በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።" 1 ዮሐ. 4፡9
♦️“ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” ዮሐ. 3፡16
♦️“ለእናንተም ስለሚሰጠው ጸጋ ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ተግተው እየፈለጉ መረመሩት፤ በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ፥ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ እየመሰከረ፥ በምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር።”1 ጴጥ. 1፡10-11
♦️"ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤ ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፏል።" ዮሐ. 20፡30-31
♦️"ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉ ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል፡፡ » 1 ጢሞ. 3፡15
♦️“ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፣ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።” ማር. 16፡15-16
♦️« . . . ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ » 1 ጴጥ. 1፡2-3
♦️"አንተ ግን ሕይወት ለሚገኝበት ትምህርት የሚገባውን ተናገር" ብሎታል። ቲቶ 2፡21
♦️“ጌታ ሆይ፣ ማን ነህ? አለው። እርሱም፦ አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ . . . አለው። እየተንቀጠቀጠና እየተደነቀ ጌታ ሆይ፥ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ? አለው። ጌታም፦ ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባና ታደርገው ዘንድ የሚያስፈልግህን ይነግሩሃል አለው።” የሐዋ. 9፡5-“አሁንም ወደ ኢዮጴ ሰዎችን ልከህ ጴጥሮስ የሚባለውን ስምዖንን አስመጣ። … ልታደርገው የሚገባህን እርሱ ይነግርሃል።” የሐዋ. 10፡5
ክፍል 2 ላይ እንመለስበታለን...
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
Hello Teddy, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…Hello Bemnet, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…አይቶ መለፍ እጅግ በጠም ይከብደል፡፡
እባካቹ እናንተ ደጋጎች ሼር ሼር አድርጉላቸው
ወዳጆቼ በዚ ከበድ ወቅት የበረከት ስራ እንስራ መርዳት ቢያቅተን ሼር ማድረግ እራሱ ትልቅ እርዳታ ነው:: ይህ የምትመለከቱወት ህፃን የሁለት አመት ከሶስት ወር ህፃን ነት የካንሰር ታማሚ ነት ካንሰር በሽታ የያዘውት ከተወለደች ከሶስ ወር ጀመሮ የካንሰር ታማሚ ነት ይሄው እሷም እናቱወም አባቱወም ሁለት አመት ሙሉ አሚን አጠቀለይ ሆስፒተል ንብረታቸውን ሸጠው እሷን በማስታመም ላይ ይገኛሉ ህፃኑወን ካንሰሩ አይንወን አሳውሮታል አንደኛው አይንወ በቀዶ ጥገና ወጥቶለት አንደኛውንም አይኑወ ከሰሞኑ እንደሚወጣ ከዶክቶሮቹ ሰምቻለው በዚያ ላይ አንድ አፍንጫወን ደፍኖታል እናትና አባትወ ለሁለት አመት ከልጃቸው ጋ ስቃይ ውስጥ ይገኛሉ አሁን ላይ ከስቃዩም በላይ የህክምና እና የመድሀኒቱ ወጪ ሌላ ስቃይ ነው የሆነባቸው ለመድሀኒቱና ህክምና ለአስራ አምስት ቀን ሰባ ሺ ብር ይፈልጋሉ አሁን ላይ ውጪ ሄደ የመታከም እድልም አለት ለህክምናወ ወጪ ከአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር በላይ ይፈልጋልጋሉ እና ልጅቷም በስቃይ ውስጥ እናትና አባትም በስቃይና ጭንቀት ውስጥ ናቸው እንድረስላቸው ለወገን ደራሽ ወገን ነው የቻልነውን አነሰም በዛ ሳንል እጃችንን እንዘርጋላቸው ስል በፈጠሪ ስም እንማፀናለን መርዳት ለምትፈልጉ
ንግድ ባንክ 1000603332346 እስማኢል ሀሠን አብደላ (Ismail Hassen)
ስልክ ቁጥር 0960067157
የማትችሉ በፀሎትና ሼር ሼር ሼር በማድረግ እንርዳቸው
ሼር ሼር ሼር በማድረግ አይከፈልበትም
☞ ሁለችንም 5 ብር ብንረደት ልነሰክመት እንችለለን፡፡
☞ ሁለቹም ለፈጠሪ ብለቹ ሲትረዱ የረደቹበትን መረጀ በዚ profile አስቀምጡልን፡፡
Hello bu, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…ሄዋን❤ለአዳም
@ortopiyaaa
@ortopiyaaa
@ortopiyaaa
#የሚፈውስ_እንባ
ሰውን የምታድን #ክርስቶስ ሆይ! ከአንተ በቀር ማን ያድነኛል? የድኅነት ምንጭ ከኾንከው ከአንተ በቀር የታመመችውን ነፍሴን ማን ይፈውሳታል? አቤቱ ሆይ! እንኪያስ የታመመችውን ችግረኛ ሴት እንደፈወስካት እኔንም ከጥፋት ከመረረ ገሃነም አድነኝ፡፡ ምሕረት ቸርነትኅ በእኔ ላይ ትኹን፡፡ ጠላቴን ድል አደርገው ዘንድ እርዳኝ፡፡ ብርቱ በምትኾን ክንድኅ ደካማ የምኾን እኔን አበርታኝ፡፡ አበርታኝና ለተጋድሎ የተዘጋጀኹ እንደኾንኩ ዐይቶ ጠላቴ ይራድ፤ ይንቀጥቀጥ፤ ይፈርም፡፡ አበርታኝና ጠላቴ የተዋረደ ይኹን፡፡ አበርታኝና ጠላቴ (ዲያብሎስ) በሐፍረት ከፊቴ ይመለስ፡፡ አበርታኝና እኔም ስምኽን ከፍ ከፍ ላድርገው፡፡
አቤቱ ሆይ! ጐስቋላ የምኾን #እንባዬን ተቀበልልኝ፤ ዕዳዬንም ፋቅልኝ፡፡ ፍቅርኅ የእኔን የበደለኛውን የክፉ ምግባሬ ፍሬ ይደምስስልኝ፤ ምረረ ገሃነምም አያግኘኝ፡፡ ቸርና ሰው ወዳጅ ሆይ! ዕዳዬን ደምስስልኝና ጠላቴ ይፈር፡፡ ፈተናውን ድል አደርግ ዘንድ፥ ድል አድርጌም ዘወትር ከአንተ ጋር እኖር ዘንድ ምሕረት ቸርነትኅ ከእኔ ጋር ትኹን፡፡
አቤቱ ሆይ! #አልቅሳ ሰምታኻታልና፥ #በሚፈውስ_እንባ አጥባኻታልና፥ ፍጥረትን ኹሉ ለፈጠርከው ለአንተም ቤተ መቅደስህ አድርጋኻታልና በደለኛ የምትኾን ሰውነቴ፥ ከባሕርይ አባትኅ ከአብ ከባሕርይ ሕይወትኅ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ታከብርኻለች፡፡ አሜን!!!
#ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ
#ገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖
#መርቆሬዎስ ፳፭
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖
Hello Mestawot, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…Hello TaYseno, welcome to ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ!
Читать полностью…